This file contains Unicode characters that might be confused with other characters. If you think that this is intentional, you can safely ignore this warning. Use the Escape button to reveal them.
4ያህዌ በእሳት መሃል፣ በዚያ ተራራ ከእኛ ጋር ፊት ለፊት ተናገረ፡፡ 5በዚያ ቀን እርሱ የተናገረውን እነግራቸው ዘንድ እኔ በአባቶቻችሁና በያህዌ መሀል ቆምኩ፣ ምክንያቱም እነርሱ እሳቱን ፈርተው ነበር፣ ደግሞም እነርሱ ወደ ተራራው ለመውጣት አልፈለጉም፡፡ ያህዌ የተናገረው ይህን ነው፣ 6‹እኔ የምታመልኩኝ አምላካችሁ ያህዌ ነኝ፤ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ነኝ፤ በዚያ በባርነት ከምትኖሩበት ነጻ ያወጣኋችሁ እኔ ነኝ፡፡