am_deu_text_udb/08/01.txt

1 line
933 B
Plaintext

\c 8 1 “እኔ ዛሬ የምሰጥህን ትእዛዛት በሙሉ በታማኝነት መጠበቅ አለብህ፡፡ ያንን ብታደርግ፣ ረጅም ዘመን ትኖራለህ፣ በጣም ብዙ ህዝብ ትሆናለህ፣ ህዝብህም ያህዌ ለአንተ እንደሚሰጥህ ለአባቶች በክብር ቃል የገባላቸውን ምድር ይወርሳሉ፡፡ 2ደግሞም በእነዚህ ባለፉት አርባ አመታት በበረሃው ውስጥ ስንጓዝ ያህዌ አምላካችን እንዴት እንደመራን አትርሳ፡፡ እርሱ ብዙ ችግሮች እንዲገጥሙህ ፈቅዷል፣ ይህን ያደረገው በእርሱ እንጂ በራስህ መታመን እንደሌለብህ እንድታውቅ ስለፈለገ፡፡ ደግም፣ ትዕዛዛቱን ትጠብቅ ወይም አትጠብቅ እንደሆነ የልብህን ሀሳብ ለማወቅ ሊፈትንህ ፈለገ፡፡