15ሆኖም፣ እግዚአብሔር በምትኖሩበት ስፍራ እንስሳቶቻችሁን አርዳችሁ እንድትበሉ ይፈቅዳል፡፡ ያህዌ አምላካችን ለእናንተ ባርኮ ከሚሰጣችሁ እንስሳት የወደዳችሁትን ያህል ስጋቸውን ልትበሉ ትችላላችሁ፡፡ በዚያኑ ጊዜ ንጹህ የሆኑ ወይም ያልሆኑ ሁሉ የአጋዘን ወይም የድኩላ ስጋ እንደምትበሉ ሁሉ ከዚያ ስጋ ሊበሉ ይችላሉ፡፡
16ነገር ግን የማናቸውንም እንስሳ ደም አትብሉ፣ ስጋውን ለመብላት ከማብሰልህ አስቀድሞ ደሙን በምድር ላይ አፍስስ፡፡