am_deu_text_udb/12/05.txt

1 line
808 B
Plaintext

ይልቁንም ያህዌ ወደሚመርጠው ስፍራ ሂዱ፡፡ ይህም ከነገዶቻችሁ አንዱ የሚኖሩበት አካባቢ ይሆናል፡፡ ወደ ያህዌ ማንነት የምትገቡበትና የምታመልኩት ስፍራ ያ ነው፡፡ 6ካህናቱ በመሰዊያ ላይ የሚሰዉበት እናንተም መስዋዕቶቻችሁን የምታቀርቡት ስፍራ ይህ መሆን አለበት፤ እንዲሁም ሌሎች እናንተ ራሳችሁ የምታቀርቡልኝ መስዋዕቶች፣ አስራቶቻችሁ፣ ለእኔ ለማቅረብ ቃል የገባችኋቸው ሌሎች ስጦታዎች፣ ከከብቶቻችሁና በጎቻችሁ በኩራት ወይም ሌላ ማናቸውም አይነት ስጦታዎች በዚህ ስፍራ መቅረብ አለበት፡፡