am_deu_text_udb/12/01.txt

1 line
759 B
Plaintext

\c 12 ትወርሷት ዘንድ የአባቶቻችን አምላክ ያህዌ በሚሰጣችሁ ምድር ስትኖሩ በታማኝነት ልትጠብቋቸው የሚገባችሁን ህግጋትና ድንጋጌዎች አሁን እነግራችኋለሁ፡፡ እነዚህን ህጎች በዘመናችሁ ሁሉ ልትጠብቋቸው ይገባል፡፡ 2ምድራቸውን የምታስለቅቋቸውን እነዚያን ህዝቦች ስታባርሩ፣ አማልክቶቻቸውን የሚያመልኩባቸውን በተራሮች አናት ላይ የሚገኙ ስፍራዎችን እና ኮረብቶች፣ እንዲሁም ከትልልቅ ዛፎች በታች የሚገኙ የማምለኪያ ስፍራዎቻቸውን ሁሉ ማስወገድ ይኖርባችኋል፡፡