am_deu_text_udb/05/12.txt

1 line
937 B
Plaintext

12የእያንዳንዱን ሳምንት ሰባተኛ ቀን እኔ ያህዌ አምላክህ እንደማዝህ እኔን በተለየ የምታከብርበት መሆኑን አትርሳ፣ 13በእያንዳንዱ ሳምንት ስራዎችህን ሁሉ የምትሰራባቸው ስድስት ቀናት አሉ፣ 14ሰባተኛው ቀን ግን የዕረፍት ቀን ነው፣ ለእኔ ለአምላክህ ለያህዌ የተለየ ቀን ነው፡፡ በዚያ ቀን አንዳች ሥራ መሥራት የለብህም፡፡ አንተ፣ ወንድና ሴት ልጆችህ፣ ወንድና ሴት ባሮችህ በዚህ ቀን መስራት የለባችሁም፡፡ እንስሳህን እንኳን አትጠምድም፣ ወይም አትጭንም፣ በአገርህ የሚኖረውን መጻተኛ እንዲሰራ አታዘውም በዚያ ቀን ባሮችህ እንደ አንተው እንዲያርፉ ልትፈቅድላቸው ይገባል፡፡