ለማናቸውም ጣኦት ወድቃችሁ መስገድና እርሱንም ማመልክ የለባችም፣ ምክንያቱም እኔ ያህዌ አምላክ ነኝ፣ ያንን ማድረጋችሁን አልታገስም፡፡ ከእናንተ መሀል ያንን የሚያደርገውን እቀጣለሁ፣ ደሞም ልጆቻቸውን፣ የልጅ ልጆቻቸውን እና የልጅ ልጅ ልጆቻቸውን እቀጣለሁ፡፡ 10እኔን የሚወዱኝንና ትዕዛዛቴን የሚጠብቁትን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ በጽኑ እወዳቸዋለሁ፡፡