am_deu_text_udb/03/19.txt

1 line
711 B
Plaintext

19ነገር ግን ሚስቶቻችሁና ልጆቻችሁ እንዲሁም እጅግ የበዙት ከብቶቻችሁ ለእናንተ በሰጠኋችሁ ከተሞች ውስጥ ይቆዩ፡፡ 20ያህዌ አምላካችን እናንተን እዚህ በምስራቅ የባህሩ ዳርቻ እንዳሳረፋችሁ እነርሱንም በምዕራብ ዮርዳኖስን ዳርቻ በሚገቡባት ምድር አሳርፏቸው በሰላም መኖር እስከሚጀምሩ ድረስ የእናንተ ወንዶች፣ ወንድሞቻችሁን እስራኤላውያንን ሊረዷቸው ይገባል፡፡ ከዚያ በኋላ፣ ሁላችሁም ወደሰጠኋችሁ ወደዚህ ምድር ትመለሳላችሁ፡፡›