15የገለአድን አካባቢ ሰሜናዊ ክፍል የምናሴ ነገድ ትውልዶች ለሆኑት ለማኪር ጎሣ ሰጠሁ፡፡ 16ለሮቤልና ጋድ ነገዶች የገለዓድን ደቡባዊ ክፍል፣ በደቡብ እስከ አርን ወንዝ ድረስ ሰጠኋቸው፡፡ የወንዙ ዕኩሌታ ደቡባዊ ድንበር ነው፡፡ ሰሜናዊው ድንበር የያቦቅ ወንዝ ነው፣ ይህም የአሞን ግዛት ዳርቻ ክፍል ነው፡፡