|
በሞአብ ግዛት በኩል ካለፍን በኋላ፣ ያህዌ እንዲህ ሲል ተናገረን፣ ‹አሁን የአርኖንን ባህር ተሻገሩ፡፡ እኔ የሴዎንን ሠራዊት በሔስቦን ከተማ የሚኖረውን የአሞር ህዝብ ወገን ንጉስ እንድታሸንፉ እረዳችኋለሁ፡፡ ስለዚህ ሰራዊታቸውን አትናቁ ከእነርሱ ምድራቸውን መውሰድ ጀመሩ፡፡ 25ዛሬ በሁሉም ስፍራ የሚገኝ እያንዳንዱ ሰው እናንተን መፍራት እንዲጀምር አደርጋለሁ፡፡ ስለ እናንተ የሚሰማ ሁሉ ይንቀጠቀጣል ይሸበራልም፡፡ |