9ያህዌ እንዲህ አለኝ፣ ‹የሞአብ ሰዎችን አታስቸግሩ፣ ደግሞም ከእነርሱ ጋር መዋጋት አትጀምሩ፣ ምክንያቱም ከእነርሱ ምድር አንዳችም አልሰጣችሁም፡፡ የአብርሃም የወንድም ልጅ የሎጥ ትውልዶች መሆናቸውን አትርሱ፣ እናም እኔ የኤርን ከተማ ሰጥቻቸዋለሁ፡፡›