\c 33 1የእግዚአብሔር ነብይ ሙሴ ከመሞቱ አስቀድሞ፣ የእስራኤልን ህዝብ እንዲባርክ እግዚአብሔርን ጠየቀ፡፡ 2የተናገረውም ይህንን ነው፡
“ያህዌ በሲና ተራራ ላይ ለእኛ ተናገረን፤
በኤዶም ግዛት እንደምትወጣ ፀሐይ መጣ
እንዲሁም ሲና ተራራን ትተን በፋራን ተራራ አጠገብ በበረሃ በነበርንበት ጊዜ በእኛ ላይ አበራ፡፡
ከአስር ሺ መላዕክት ጋር መጣ፣
በቀኙ የሚነድ እሳት ነበር፡፡