am_deu_text_udb/29/22.txt

1 line
880 B
Plaintext

22በመጪዎቹ አመታት፣ የአንተ ልጆችና ህዝብ ከሌሎች አገሮች ያህዌ በአንተ ላይ ያደረሰውን ጥፋትና በሽታዎች ይመለከታሉ፡፡ 23ምድርህ በሙሉ በሚነድ ዲንና ጨው እንደጠፋች ይመለከታሉ፡፡አንዳች ነገር አይዘራባትም፡፤ አረም እንኳን አይገኝባትም፡፡ ምድርህ እንደ ሶዶምና ጎሞራ፣ እዲሁም እነዚያን ህዝቦች እጅግ በተቆጣ ጊዜ እንዳጠፋቸው እንደ አዳማና ሲባዩ ከተሞች ትመስላለች፡፡ 24እናም ከሌላ ሀገር የመጡ ህዝቦች ‘ያህዌ በዚህች ምድር ላይ ለምን ይህን አደረገ? በዚህ ይኖሩ በነበሩ ህዝቦች ላይ እርሱ ስለምን እንደዚህ ተቆጣ?' ብለው ይጠይቃሉ፡፡