|
12ዛሬ እናንተ ሁላችሁ የያህዌን ኪዳን ተቀብላችሁ ለመስማማትና ከኪዳኑ ጋር ራሳችሁን ለማጣበቅ በዚህ ተሰብስባችኋል፡፡ 13እርሱ ይህንን ስምምነት ከእናንተ ጋር የሚያደርገው እናንተ የእርሱ ህዝብ መሆናችሁንና እርሱ የእናንተ አምላክ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው፡፡ እርሱ ለእናንተ ሊያደርግላች ቃል የገባው ይህንን ነው፣ ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፣ ለይስሃቅ እና ለያዕቆብ ሊፈጽምላቸው ቃል የገባው ይህንን ነው፡፡ |