19እስራኤላዊ ለሆነ ወገንህ ገንዘብ ወይም እህል ወይም ሌላ ማናቸውም ነገር ስታበድር ወለድ አታስከፍላቸው፡፡ 20ወለድ ማስከፈል የሚፈቀድልህ በመካከልህ ለሚኖር ባእድ ገነዘብ ስታበድር እንጂ ለእስራኤላዊው ገንዘብ ስታበድር አይደለም፡፡ በምትገባበትና በምትወርሳት ምድር ያህዌ አምላካችን በምትሰራው ሁሉ እንዲባርክህ ይህን አድርግ፡፡