am_deu_text_udb/23/03.txt

1 line
616 B
Plaintext

3ከአሞን ወይም ሞአብ ወገን የሆነ እስከ አስር ትውልዱ ድረስ የያህዌ ህዝብ ተደርጎ አይቆጠርም፡፡ 4ለዚህም አንዱ ምክንያት፣ አባቶቻችሁ ከግብጽ ተነስተው ወደ ከነዓን ሲጓዙ መሪዎቻቸው ምግብና ውሃ ሊሰጧቸው አልወደዱም ነበርና ነው፡፡ ሌላው ምክንያት በመስጴጦምያ በፐቶር ውስጥ ይኖር ለነበረው ለቢያር ልጅ ለበልዓም እናንተን እስራኤላዊያንን እንድረግም ገንዘብ ከፍለው ነበር፡፡