14ሴቶችን፣ ልጆችን፣ የቀንድ ከብቶችን እና በከተማዋ ውስጥ የሚገኘውን ማናቸውንም መውሰድ የምትፈልጉትን ነገር ሁሉ መውሰድ ተፈቅዶላችኋል፡፡ የጠላቶቻችሁ በነበሩና ያህዌ አምላካችን ለእናንተ አሳልፎ በሰጣችሁ ነገሮች ሁሉ ደስ መሰኘት ተፈቅዶላችኋል፡፡ 15ከምትሰፍሩበት ምድር ርቀው በሚገኙ ከተሞች ላይ ሁሉ ይህንን ማድረግ አለባችሁ፡፡