am_deu_text_udb/06/10.txt

1 line
951 B
Plaintext

ያህዌ አምላካችን እናንተ ያልገነባችኋቸውንና በውስጣቸው ታላላቅና የበለጸጉ ከተሞች ያሉትን ምድር እንደሚሰጣችሁ ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም ለይስሃቅና ለያዕቆብ የከበረ ቃል ኪዳኑን ሰጥቷቸዋል፡፡ 11የእነዚያ ከተሞች ቤቶች በብዙ ነገር የበለጸጉ ስሆኑ አንዳች ነገር ይዛችሁ መግባት አያስፈልጋችሁም ብሏል፡፡ የተቆፈሩ ጉድጓዶች አላቸው፡፡ አስቀድሞ የወይንና የወይራ ዛፎች ተተክለውባቸዋል፡፡ ስለዚህ ያህዌ ወደዚየ ምድር ሲያስገባችሁ ለኑሮ ሚያስፈልጋችሁ ሁሉ ይኖራችኋል፣12እናንተ ግን ከግብጽ ባርነት ያወጣችሁንና እነዚህን ነገሮች ሁሉ የሰጣችሁን ያህዌን እንዳትረሱ ተጠንቀቁ፡፡