743 lines
88 KiB
Plaintext
743 lines
88 KiB
Plaintext
\id DAN
|
|
\ide UTF-8
|
|
\h ዳንኤል
|
|
\toc1 ዳንኤል
|
|
\toc2 ዳንኤል
|
|
\toc3 dan
|
|
\mt ዳንኤል
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 1
|
|
\p
|
|
\v 1 በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት በሦሥተኛው ዓመት፥አቅርቦቶቿን ሁሉ ለማስቆም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፥ ከበባትም።
|
|
\v 2 ጌታም ለናቡከደነፆር በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአቄም ላይ ድል ሰጠው፥እርሱም ከእግዚአብሔር ቤት የተቀድሱ ዕቃዎች ጥቂቱን ሰጠው። እርሱም ወደ ባቢሎን ምድር፥ ወደ አምላኩ ቤት አመጣቸው፥የተቀደሱትንም ዕቃዎች በአምላኩ ግምጃ ቤት ውስጥ አኖራቸው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 ንጉሡም ዋና አለቃውን አስፋኔዝን፥ ከነገሥታቱና ከመሳፍንቱ ቤተስብ የሆኑትን፥ ከእስራኤል ሰዎች አንዳንዶችን፦
|
|
\v 4 ነውር የሌለባቸውን ወጣት ወንድች፥ መልከ መልካሞችን፥ ጥበበኞችን፥ በዕውቀትና በማስተዋል የተሞሉትንና በንጉሡ ቤት ለማገልገል ብቁዎች የሆኑትን እን ዲያመጣ ተናገረው። የባቢሎናውያንን ሥነ ጽሑፍና ቋንቋ እንዲያስተምራቸው ተናገረው።
|
|
\v 5 ንጉሡ ከምግቡና ከሚጠጣው ወይን በየዕለቱ ድርሻ መደበላቸው። እነዚህ ወጣት ወንዶች ለሦሥት ዓመት መሠልጠንና ከዚያ በኋላ ንጉሡን ማገልገል ይጠበቅባቸዋል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 6 ከእነዚህም መካከል አንዳንድ የይሁዳ ሰዎች፥ ዳንኤል፥ አናንያ፥ ሚሳኤልና አዛሪያ ነበሩ።
|
|
\v 7 ዋና አለቃውም ስም አወጣላቸው፦ ዳንኤልን ብልጣሶር፥ አናንያን ሲድራቅ፥ ሚሳኤልን ሚሳቅ፥ አዛሪያንም አብድናጎ ብሎ ጠራቸው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 8 ነገር ግን ዳንኤል በንጉሡ ምግብና በሚጠጣውም ወይን ራሱን እንዳያረክስ በውስጡ አሰበ። ራሱን እንዳያረክስ ከዋናው አለቃ ፈቃድ ጠየቀ።
|
|
\v 9 ዋና አለቃው ለእርሱ ባለው አክብሮት አማካይነት እግዚአብሔር ለዳንኤል ሞገስንና ጸጋን ሰጠው።
|
|
\v 10 ዋና አለቃውም ዳንኤልን አለው፥ «እኔ ጌታዬን ንጉሥን እፈራለሁ። ምን ዓይነት ምግብና መጥጥ ማግኘት እንዳለባችሁ አዞኛል። በእናንተ እድሜ ካሉ ወጣቶች ይልቅ ከስታችሁ ስለ ምን ይመለከታል? ንጉሡ ከእናንተ የተነሳ በሞት ይቀጣኝ ይሆናል።»
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 11 ዳንኤልም ዋናው አለቃ በዳንኤል፥በአናንያ፥በሚሳኤልና በአዛሪያ ላይ ለሾመው መጋቢ ተናገረ።
|
|
\v 12 እርሱም አለ፥«እባክህ፥እኛን አገልጋዮችህን ለአሥር ቀናት ፈትነን። የምንመገብው ጥቂት አትክልትና የምንጠጣው ውኃ ብቻ ስጠን።
|
|
\v 13 ከዚያም የእኛን ፊት የንጉሡን ምግብ ከሚመገቡ ወጣቶች ጋር አስተያይ፥ባየኽውም መሠረት በአገልጋዮችህ ላይ አድርግ።»
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 14 መጋቢውም ይህን ለማድረግ ከእርሱ ጋር ተስማማ፥ለአሥር ቀናትም ፈተናቸው።
|
|
\v 15 ከአሥርም ቀን በኋላ የንጉሡን መብል ከተመገቡ ወጣቶች ይልቅ ጤነኞችና የተሻለ የተመገቡ ሆነው ታዩ።
|
|
\v 16 ስለዚህ መጋቢው የተመደበላቸውን የተመረጠ ምግብና ወይን አስቀርቶ አትክልት ብቻ ሰጣቸው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 17 ለእነዚህ አራት ወጣቶች፥ እግዚአብሔር በሁሉም ሥነ ጽሑፍና በጥበብ ዕውቀትና ማስተዋል ሰጣቸው፥ ዳንኤልም ሁሉንም ዐይነት ራዕይና ሕልም መረዳት ይችል ነበር።
|
|
\v 18 እንዲያስገቡአቸው ንጉሡ የመደበው ጊዜ እንዳበቃ፥ዋናው አለቃ በናቡከደነፆር ፊት አቀረባቸው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 19 ንጉሡም ከእነርሱ ጋር ተነጋገረ፥አብረዋቸው ከነበሩት ሁሉ መካከል ከዳንኤል፥ሐናንያ፥ ሚሳኤልና አዛርያ ጋር የሚወዳድር ማንም አልነበረም። በንጉሡ ፊት ቆሙ፥ ሊያገለግሉት ዝግጁዎች ነበሩ።
|
|
\v 20 ንጉሡ በጠየቃቸው የጥበብና የማስተዋል ጥያቄዎች ሁሉ፥በግዛቱ ሁሉ ከሚገኙ አስማተኞችና ሙታን ሳቢዎች አሥር እጥፍ በልጠው ተገኙ።
|
|
\v 21 ዳንኤልም እስከ ንጉሥ ቂሮስ የመጀመሪያ ዓመት ድረስ እዚያው ነበረ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 2
|
|
\p
|
|
\v 1 ናቡከደነፆር በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ሕልም አለመ፤ አእምሮው ታወከ፥ ሊተኛም አልቻለም።
|
|
\v 2 ከዚያም አስማተኞችና ሙታን ሳቢዎች እንዲመጡ አዘዘ፤ ጠንቋዮችንና ጠቢባንን ደግሞ ጠራ፤ ስለ ሕልሙ እንዲነግሩት ፈለጋቸው፤ ስለዚህ ገቡና በንጉሡ ፊት ቆሙ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 ንጉሡ አላቸው፥«ሕልም አልሜአልሁ፥ሕልሙም ምን ማለት እንደሆነ ለማወቅ አእምሮዬ ተጨንቋል።»
|
|
\v 4 ከዚያም ጠቢባኑ በአረማይክ፥ «ንጉሥ ሆይ ለዘላለም ንገሥ! ሕልሙን ለእኛ ለባሪያዎችህ ተናገር፥ እኛም ፍቺውን እናስታውቅሃለን» ብለው ለንጉሡ ተናገሩ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 5 ንጉሡም ለጠቢባኑ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፥«ሕልሙን ካልገለጣችሁልኝና ካልተረጎማችሁት፥ ሰውነታችሁ እንዲቆራረጥና ቤታችሁም የቆሻሻ ክምር እንዲሆን ወስኜአለሁ።
|
|
\v 6 ነገር ግን ሕልሙንና ትርጉሙን ከነገራችሁኝ፥ ከእኔ ዘንድ ሥጦታ፥ ሽልማትና ታላቅ ክብር ትቀበላላችሁ። ስለዚህ ሕልሙንና ትርጉሙን ንገሩኝ።»
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 እነርሱም እንደገና እንዲህ ሲሉ መለሱ፥ «ንጉሡ ሕልሙን ለአገልጋዮቹ ይንገር፥ እኛም ትርጉሙን እንነግርሃለን።»
|
|
\v 8 ንጉሡም መለሰላቸው፥ «ይህን ጉዳይ በተመለከተ ውሳኔዬ ምን ያህል ጽኑ እንደሆነ ስላወቃችሁ ተጨማሪ ጊዜ ማግኘት እንደምትፈልጉ በእርግጥ አውቃለሁ።
|
|
\v 9 ነገር ግን ሕልሙን ባትነግሩኝ፥ ሁላችሁን አንድ ቅጣት ይጠብቃችኋል። ሐሰት የሆኑ አሳች አሳቦችን ለማዘጋጅት ወስናችኋል፥ አሳቤንም እስክለውጥ ድረስ ልትነግሩኝ በአንድነት ተስማምታችኋል። ስለዚህ ሕልሙን ንገሩኝ፥ ያን ጊዜም ልትተረጉሙልኝ እንደምትችሉ አውቃለሁ።»
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 10 ጠቢባኑም ለንጉሡ እንዲህ ሲሉ መለሱ፥«የንጉሡን ጥያቄ ሊመልስ የሚችል ሰው በምድር አይገኝም። አስማተኞችን፥ ሙታን ሳቢዎችን ወይም ጠቢባንን እንዲህ ዓይነት ጥያቄ የጠየቀ ታላቅና ኃያል ንጉሥ የለም።
|
|
\v 11 ንጉሡ የሚጠይቀው ነገር አስቸጋሪ ነው፥ በሰዎች መካከል ከማይኖሩት አማልክት በስተቀር ይህንን ለንጉሡ መንገር የሚችል ማንም የለም።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 12 ይህም ንጉሡን አስቆጣው እጅግም አበሳጨው፥ በባቢሎንም በጥበባቸው የሚታወቁትን ሁሉ እንዲያጠፉአቸው አዘዘ።
|
|
\v 13 ስለዚህም አዋጁ ወጣ፤ በጥበባቸው የሚታወቁት ሁሉ ሊገድሉ ሆነ፥ ዳንኤልንና ጓደኞቹንም ሊገድሉአቸው ፈለጉአቸው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 14 በዚያን ጊዜ ዳንኤል በባቢሎን በጥበባቸው የሚታወቁትን ሁሉ ሊገድል ለመጣው ለንጉሡ የዘበኞች አዛዥ ለአርዮክ በጥንቃቄና በማስተዋል መለሰለት።
|
|
\v 15 ዳንኤልም «የንጉሡ አዋጅ ለምን አስቸኳይ ሆነ?» ሲል የንጉሡን አዛዥ ጠየቀው፤ አርዮክም የሆነውን ለዳንኤል ነገረው።
|
|
\v 16 በዚያን ጊዜ ዳንኤል ገባና ትርጉሙን ለንጉሡ የሚያስታውቅበት ቀጠሮ ከንጉሥ እንዲሰጠው ጠየቀ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 17 በዚያን ጊዜ ዳንኤል ወደ ቤቱ ሄደና የሆነውን ለአናንያ፥ ለሚሳኤልና ለአዛርያ ነገራቸው።
|
|
\v 18 እርሱም እነርሱም በጥበባቸው ከሚታወቁት ከተቀሩት የባቢሎን ሰዎች ጋር አብረው እንዳይገደሉ፥ ስለዚህ ምሥጢር ከሰማይ አምላክ ምሕረት እንዲለምኑ አጥብቆ ነገራቸው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 19 በዚያች ሌሊት ምሥጢሩ ለዳንኤል በራዕይ ተገለጠለት። በዚያን ጊዜ ዳንኤል የሰማይን አምላክ አመሰገነ፥ አለም፦
|
|
\v 20 «ጥበብና ኃይል የእርሱ ነውና የእግዚአብሔር ስም ከዘላለም እስከ ዘላለም የተባረከ ይሁን።»
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 21 ጊዜዎችንና ወቅቶችን ይለውጣል፤ነገሥታትን ይሽራል በዙፋናቸውም ነገሥታትን ያስቀምጣል። ጥበብን ለጠቢባን እውቀትንም ለአስተዋዮች ይሰጣል።
|
|
\v 22 እርሱ በጨለማ ያለውን ያውቃልና ብርሃንም ከእርሱ ጋር ነውና የጠለቁትንና የተሰወሩትን ነገሮች ይገልጣል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 23 የአባቶቼ አምላክ ስለ ሰጠኽኝ ጥበብና ኃይል አመሰግንሃለሁ፥እባርክሃለሁም። የለመንህን ነገር አስታውቀኽኛል፥ንጉሡን ያሳሰበውን ነገር አስታውቀኽናል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 24 ከዚህም በኋላ ዳንኤል የባቢሎንን ጠቢባን ሁሉ እንዲገድል ንጉሡ ኃላፊነት ወደ ሰጠው ወደ አርዮክ ሄደ። ሄዶም አለው፦«በባቢሎን የሚገኙትን ጠቢባን አትግድል። ወደ ንጉሡ ይዘኽኝ ግባ እኔም የሕልሙን ትርጉም ለንጉሥ እናገራለሁ።»
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 25 ከዚያም አርዮክ በፍጥነት ዳንኤልን ወደ ንጉሡ አስገባና አለ፦«የንጉሡን ሕልም ትርጉም የሚገልጥ ሰው ከይሁዳ ምርኮኞች መካከል አግኝቼአለሁ።
|
|
\v 26 ንጉሡም (ብልጣሶር ተብሎ የሚጠራውን) ዳንኤልን አለው፦«ያየሁትን ሕልምና ትርጉሙን ልትነግረኝ ትችላለህን?»
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 27 ዳንኤልም ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰ፦«ንጉሡ የጠየቀው ምሥጢር ጥበብ ባላቸው፥ በሙታን ሳቢዎች፥ በአስማተኞችና በኮከብ ቆጣሪዎችም ሊገለጥ አይችልም።
|
|
\v 28 ነገር ግን ምሥጢር የሚገልጥ አምላክ በሰማያት ውስጥ አለ፤ ንጉሥ ናቡከደነፆር ሆይ! እርሱም በሚመጡት ዘመናት ሊሆን ያለውን አስታውቆሃል። በአልጋህ ላይ ተኝተህ ሳለህ ያየኽው ሕልምህና የአእምሮህ ራዕዮች እነዚህ ናቸው፦
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 29 ንጉሥ ሆይ! በአልጋህ ላይ ሆነህ ሊሆኑ ስላሉ ነገሮች ታስብ ነበር፤ ምሥጢርንም የሚገልጠው ሊሆን ያለውን አስታውቆሃል።
|
|
\v 30 እኔ ከሌሎች ሰዎች የሚበልጥ ጥበብ ስላለኝ ይህ ምሥጢር አልተገለጠልኝም። ንጉሥ ሆይ! ይህ ምሥጢር ለእኔ የተገለጠው አንተ ትርጉሙን ትረዳ ዘንድና የውስጥ አሳብህንም ታውቅ ዘንድ ነው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 31 ንጉሥ ሆይ! ትልቅ ምስል አየህ ተመለከትህም። ምስሉም እጅግ ታላቅና አንጸባራቂ ነበር፥ በፊትህም ቆሞ ነበር። ማንጸባረቁም አስፈሪ ነበር።
|
|
\v 32 የምስሉ ራስ ከወርቅ የተሠራ ነበር። ደረቱና ክንዶቹ ከብር የተሠሩ ነበሩ። ወገቡና ጭኖቹ ከናስ፥
|
|
\v 33 እግሮቹም ከብረት የተሠሩ ነበሩ። መርገጫ እግሮቹ ከፊሉ ከብረት ከፊሉ ከሸክላ የተሠሩ ነበሩ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 34 የሰው እጆች ሳይነኩት ድንጋይ ሲፈነቀል፥ ከብረትና ከሸክላ የተሠሩትንም የምስሉን መርገጫ እግሮች ሲመታቸውና ሲያደቃቸው ተመለከትህ።
|
|
\v 35 ከዚያም ብረቱ፥ሸክላው፥ ናሱ፥ ብሩና ወርቁ ወዲያው እንክትክታቸው ወጣ፤ በመከርም ወቅት በአውድማ ላይ እንዳል እብቅ ሆኑ። ነፋሱም ጠርጎ ወሰዳችው ምልክታቸውም አልቀረም። ነገር ግን ምስሉን የመታው ድንጋይ ታላቅ ተራራ ሆነ ምድርንም ሞላ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 36 ሕልምህ ይህ ነበር። አሁን ትርጉሙን ለንጉሥ እንናግራለን።
|
|
\v 37 አንተ ንጉሥ ሆይ! የሰማይ አምላክ መንግስትን፥ ኃይልን፥ብርታትንና ክብርን የሰጠህ የነገሥታት ንጉሥ ነህ።
|
|
\v 38 የሰው ልጆች የሚኖሩበትን ስፍራ ሁሉ በእጅህ ሰጠህ። የምድር እንሰሳትንና የሰማያት ወፎችን በእጅህ ሰጠህ፤ በእነርሱ ሁሉ ላይም ግዢ አደረገህ። አንተ የምስሉ የወርቅ ራስ ነህ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 39 ከአንተም በኋላ ከአንተ የሚያንስ ሌላ መንግሥት ይነሳል፤ከዚያም በኋላ በምድር ሁሉ ላይ የሚገዛ ሦሥተኛ የናስ መንግሥት ይነሳል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 40 ብረት ሌሎች ነገሮችን እንደሚሰባብርና ሁሉን ነገር እንደሚያደቅቅ፥እንዲሁ እንደ ብረት ብርቱ የሆነ አራተኛ መንግሥት ይነሳል። እነዚህን ነገሮች ሁሉ ያደቅቃቸዋል ይፈጫቸዋልም።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 41 እግሮቹና ጣቶቹ በከፊል ከሸክላ በከፊል ከብረት ተሠርተው እንዳየህ እንዲሁ የተከፋፈለ መንግሥት ይሆናል፤ ለስላሳ ሸክላ ከብረት ጋር ተደባልቆ እንዳየህ እንዲሁ የተወሰነ የብረት ብርታት ይኖረዋል።
|
|
\v 42 የእግሮቹ ጣቶች በከፊል ከብረት በከፊል ከሸክላ ተሠርተው እንዳየህ መንግሥቱ በከፊል ብርቱ በከፊል ደካማ ይሆናል።
|
|
\v 43 ብረትና ለስላሳ ሸክላ ተደባልቀው እንዳየህ እንዲሁ ሕዝቡም ድብልቅ ይሆናል፤ብረትና ሸክላ እ ንደማይዋሓድ እነርሱም አብረው አይዘልቁም።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 44 በእነዚያ ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ፈጽሞ የማይጠፋና በሌላ ሕዝብ የማይሸንፍ መንግሥት ያቆማል። ሌሎቹን መንግሥታት ይፈጫቸዋል ፈጽሞም ያጠፋቸዋል፤ እርሱ ግን ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
|
|
\v 45 የሰው እጆች ሳይነኩት ድንጋይ ከተራራ ሲፈነቀል እንዳየህ እንዲሁ ነው። እርሱም ብረቱን፥ ናሱን፥ ሸክላውን፥ ብሩንና ወርቁን አደቀቃቸው። ንጉሥ ሆይ! ከዚህ በኋላ ሊሆን ያለውን ታላቁ አምላክ አስታውቆሃል። ሕልሙ እውነተኛ ፍቺውም የታመነ ነው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 46 ንጉሥ ናቡከደነፆርም በዳንኤል ፊት በግንባሩ ተደፋ አከበረውም፤ መሥዋዕትና ዕጣን እንዲይቀርቡለት አዘዘ።
|
|
\v 47 ንጉሡ ዳንኤልን እንዲህ አለው፦«ይህን ምሥጢር መግለጥ ችለሃልና፥ ምሥጢርን ሁሉ የሚገልጠው አምላክህ በእውነት የአማልክት አምላክ፥ የነገሥታት ጌታ ነው።»
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 48 ከዚያም በኋላ ንጉሡ ዳንኤልን እጅግ አከበረው፥ብዙ አስደናቂ ሥጦታዎችንም ሰጠው። በባቢሎን ክፍለ አገር ሁሉ ላይ ገዢ አደረገው። በባቢሎን ጠቢባን ሁሉ ላይ ዋነኛ አስተዳዳሪ ሆነ።
|
|
\v 49 ዳንኤልም ለንጉሡ ጥያቄ አቀረበ፥ ንጉሡም ሲድራቅን፥ሚሳቅንና አብድናጎን በባቢሎን ክፍለ አገር ላይ አስተዳዳሪዎች አድርጎ ሾማቸው። ዳንኤል ግን በንጉሡ ቤተ መንግሥት ተቀመጠ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 3
|
|
\p
|
|
\v 1 ንጉሡ ናቡከደነፆር ርዝመቱ ስድሳ ክንድ ስፋቱ ስድስት ክንድ የሆነ የወርቅ ምስል አሠራ። በባቢሎንም ክፍለ አገር በዱራ ሜዳ አቆመው።
|
|
\v 2 ከዚያም ናቡከደነፆር አማካሪዎችን፥ የግምጃ ቤት ኃላፊዎችን፥ ዳኞችን፥ የአጥቢያ ፈራጆችንና የክፍላተ አገር ከፍተኛ ባለ ሥልጣናትን ሁሉ ጨምሮ የክፍለ አገር አስተዳዳሪዎች፥ የክልል አስተዳዳሪዎችና የአካባቢ አስተዳዳሪዎች ላቆመው ምስል ምረቃ እንዲመጡ፥ በአንድ ላይ እንዲሰበሰቡ መልእክት ላከ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 በዚያን ጊዜም አማካሪዎችን፥ የግምጃ ቤት ኋላፊዎችን፥ ዳኞችን፥ የአጥቢያ ፈራጆችንና የክፍላተ አገር ከፍተኛ ባለ ሥልጣናትን ጨምሮ የክፍለ አገር አስተዳዳሪዎች፥ የክልል አስተዳዳሪዎችና የአካባቢ አስተዳዳሪዎች ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ በአንድነት ተሰበሰቡ። በፊቱም ቆሙ።
|
|
\v 4 ከዚያም አዋጅ ነጋሪ እየጮኽ እንዲህ አለ፡- «አሕዛብ፥ መንግሥታትና ልዩ ልዩ ቋንቋ የምትናገሩ ሁሉ፥
|
|
\v 5 የመለከትና የእንቢልታ፥ የመስንቆና የክራር፥ የበገናና የዋሽንት፥ የዘፈንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ንጉሥ ናቡከደነፆር ላቆመው የወርቅ ምስል ወድቃችሁ እንድትሰግዱ ታዝዛችኋል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 6 ማንም የማይወድቅና የማይሰግድ፥ በዚያው ጊዜ በሚንቦገቦገው የእሳት እቶን ውስጥ ይጣላል።»
|
|
\v 7 ስለዚህም አሕዛብ ሁሉ የመለከቱንና የእንቢልታውን፥ የመስንቆውንና የክራሩን፥ የበገናውንና የዋሽንቱን፥ የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰሙ ጊዜ አሕዛብ ሁሉ፥ መንግሥታትና ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ሁሉ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው የወርቅ ምስል ወድቀው ሰገዱ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 8 በዚህ ጊዜም አንዳንድ ከለዳውያን መጥተው አይሁድን ከሰሱ።
|
|
\v 9 ለንጉሡ ናቡከደነፆርም እንዲህ አሉ፦ «ንጉሥ ሆይ ለዘላለም ኑር!
|
|
\v 10 ንጉሥ ሆይ፥አንተ የመለከቱንና የእንቢልታውን፥ የመስንቆውንና የክራሩን፥ የበገናውንና የዋሽንቱን፥ የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ የሰማ ማንኛውም ሰው ለወርቁ ምስል እንዲውድቅና እንዲሰግድ ትዕዛዝ አውጥተህ ነበር።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 11 ማንም ያልወደቀና ያላመለከ በሚንቦገቦገው የእሳት እቶን ውስጥ ሊጣል ይገባዋል።
|
|
\v 12 አሁን ግን በባቢሎን ክፍለ አገር ጉዳይ ላይ የሾምካቸው፥ ሲድራቅ፥ ሚሳቅና አብድናጎ የሚባሉ አንዳንድ አይሁድ አሉ። ንጉሥ ሆይ፥ እነዚህ ሰዎች አንተን ከምንም አይቆጥሩም። አማልክትህን አያመልኩም፥ አያገለግሉምም ወይም ላቆምከው የወርቁ ምስል አይሰግዱም።»
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 13 በዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር በቁጣና በብስጭት ተሞላ፤ ሲድራቅን፥ ሚሳቅንና አብድናጎን ወደ እርሱ እንዲያመጡአቸው አዘዘ። ስለዚም እነዚህን ሰዎች ወደ ንጉሡ ፊት አመጡአቸው።
|
|
\v 14 ናቡከደነፆርም አላቸው፦«ሲድራቅ፥ ሚሳቅና አብድናጎ አማልክቴን አለማምለካችሁ ወይም ላቆምኩት የወርቅ ምስል አለመስገዳችሁ እውነት ነውን?
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 15 አሁንም የመለከቱንና የእንቢልታውን፥የመስንቆውንና የክራሩን፥ የበገናውንና የዋሽንቱን፥ የዘፈኑንም ድምፅ ሁሉ በሰማችሁ ጊዜ ለመውደቅ እና ላሠራሁት ምስል ለመስግድ ዝግጅዎች ከሆናችሁ ሁሉም መልካም ይሆናል። ካላመለካችሁ ግን ወዲያው ወደ ሚንቦገቦገው የእሳት እቶን ትጣላላችሁ። ከእጄስ ሊያድናችሁ የሚችል አምላክ ማነው?»
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 16 ሲድራቅ፥ሚሳቅና አብድናጎም ለንጉሡ እንዲህ ሲሉ መለሱ፦«ናቡከደነፆር ሆይ በዚህ ጉዳይ መልስ ልንሰጥህ አያስፈልገንም።
|
|
\v 17 መልስ መስጠት የሚገባን ከሆነ፥ የምናገለግለው አምላካችን ከሚንቦገቦገው የእሳት እቶን ሊያድነን ይችላል፥ ንጉሥ ሆይ፥ ከእጅህም ያድነናል።
|
|
\v 18 ነገር ግን ንጉሥ ሆይ ባያድነን እንኳን፥አማልክትህን እንደማናመልክና ላቆምከውም የወርቅ ምስል እንደማንሰግድ በአንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 19 በዚያን ጊዜ ናቡከደነፆር በቁጣ ተሞላ፤ በሲድራቅ፥ በሚሳቅና በአብድናጎ ላይ ፊቱ ተለወጠባቸው። የእቶኑ እሳት ብዙውን ጊዜ ይነድድ ከነበረው ይልቅ ሰባት እጥፍ እንዲነድድ አዘዘ።
|
|
\v 20 ከዚያም ከሠራዊቱ ጥቂት በጣም ብርቱ ሰዎችን፥ ሲድራቅን፥ሚሳቅንና አብድናጎን አሥረው ወደ ሚንቦገቦገው የእቶኑ እሳት እንዲጥሉአችው አዘዘ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 21 እነርሱም መጎናጸፊያቸውን፥ ቀሚሳቸውን፥ ጥምጥማቸውንና ሌሎች ልብሶቻቸውን እንደ ለበሱ ታስረው ወደ ሚንቦገቦገው የእቶን እሳት ተጣሉ።
|
|
\v 22 የንጉሡ ትእዛዝ ጥብቅ ስለነበረና የእቶኑ እሳት እጅግ ነዶ ስለነበረ፥ ሲድራቅን፥ ሚሳቅንና አብድናጎን የወሰዱአቸውን ሰዎች ነበልባሉ ገደላቸው።
|
|
\v 23 እነዚህ ሦሥት ሰዎች እንደ ታሰሩ በሚንቦገቦገው የእቶን እሳት ውስጥ ወደቁ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 24 ከዚያም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ፥ ፈጥኖም ተነሣ። አማካሪዎቹንም፦ «ሦሥት ሰዎችን አስረን እሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን?» ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም ለንጉሡ፦ «ንጉሥ ሆይ እርግጥ ነው» ብለው መለሱ።
|
|
\v 25 እርሱም፦ «እኔ ግን ያልታሰሩ አራት ሰዎች በእሳት ውስጥ ሲመላለሱ አያልሁ፥ጉዳትም አላገኛቸውም። የአራተኛው ማንጸባረቅ የአማልክትን ልጅ ይመስላል።» አለ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 26 ከዚያም ናቡከደነፆር ወደ እሳቱ እቶን በር ቀረቦ፦ «የልዑል አምላክ ባሪያዎች ሲድራቅ፥ ሚሳቅና አብድናጎ ኑ ውጡ! ወደዚህ ኑ!» ብሎ ተጣራ። በዚያን ጊዜም ሲድራቅ፥ ሚሳቅና አብድናጎ ከእሳቱ ውስጥ ወጡ።
|
|
\v 27 በአንድነት የተሰበሰቡት የክፍላተ አገር አስተዳዳሪዎች፥ የክልል አስተዳዳሪዎች፥ ሌሎች አስተዳዳሪዎችና የንጉሡ አማካሪዎች እነዚህን ሰዎች ተመለከቱ። እሳቱ ሰውነታቸውን አልጎዳውም፥ የራሳችው ጸጉር አልተቃጠለም፥ መጎናጸፊያቸው አልተጎዳም፥ የእሳቱም ሽታ በላያቸው አልነበረም።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 28 ናቡከደነፆርም እንዲህ አለ፦«መልአኩን የላከውንና ለአገልጋዮቹ መልእክቱን የሰጠውን የሲድራቅን፥የሚሳቅንና የአብድናጎን አምላክ እናመስግን። በእርሱ በመታመን ትእዛዜን ችላ ብለዋል፥ ከአምላካቸውም ሌላ ማንኛውንም ሌላ አምላክ ከማምለክ ወይም ለእርሱ ከመስገድ ይልቅ ሰውነ ታቸውን አሳልፈው መስጠትን መርጠዋል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 29 ስለዚህ እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና፥በሲድራቅ፥ሚሳቅና አብድናጎ አምላክ ላይ ክፉ የሚናገር ማንኛውም ሕዝብ፥አገር ወይም ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ይቆራረጣሉ፥ቤቶቻቸውም የቆሻሻ ክምር ይሆናሉ ብዬ አዝዤአለሁ።
|
|
\v 30 ከዚያም ንጉሡ ሲድራቅን፣ ሚሳቅንና አብድናጎን በባቢሎን አውራጃ ሾማቸው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 4
|
|
\p
|
|
\v 1 ከንጉሥ ናቡከደነፆር፥በምድር ሁሉ ለሚኖሩ አሕዛብ፥ መንግሥታትና ልዩ ልዩ ቋንቋ ለሚናገሩ ሁሉ፦ «ሰላማችሁ ይብዛ።
|
|
\v 2 ልዑል አምላክ ስላደረገልኝ ምልክቶችና ድንቆች እነግራችሁ ዘንድ መልካም ሆኖ ታየኝ።
|
|
\v 3 ምልክቶቹ እንዴት ታላላቅ ናቸው! ድንቆቹም እንዴት ብርቱዎች ናቸው! መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፥ ግዛቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 4 እኔ ናቡከደነፆር በቤቴ ደስ ብሎኝ፥ በቤተ መንግሥቴም በብልጽግና ፍሥሐ እያደረግሁ እኖር ነበር።
|
|
\v 5 ነገር ግን የአስፈራኝን ሕልም አለምሁ፤ ተኝቼም ሳለሁ ያየኋቸው ምስሎችና የአእምሮዬ ራዕዮች አወኩኝ።
|
|
\v 6 ስለዚህ ሕልሙን ይተረጉሙልኝ ዘንድ የባቢሎንን ጠቢባን ሁሉ በፊቴ እንዲያቀርቧቸው ትእዛዝ አወጣሁ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 በዚያን ጊዜ አስማተኞች፥ሙታን ሳቢዎች፥ጠቢባንና ኮከብ ቆጣሪዎች መጡ፤ ሕልሙንም ነገርኳችው፥ ነገር ግን ሊተረጉሙልኝ አልቻሉም።
|
|
\v 8 በመጨረሻም፥ እንደ አምላኬ ስም ብልጣሶር ተብሎ የተጠራውና የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያለበት ዳንኤል ገባ። ሕልሙን ነገርኩት።
|
|
\v 9 «የአስማተኞች አለቃ ብልጣሶር ሆይ፦የቅዱሳን አማልክት መንፈስ እንዳለብህና የሚያስችግርህ ምሥጢር እንደሌለ አውቄአልሁና፤ በሕልሜ ምን እንዳየሁና ትርጉሙ ምን እንደሆነ ንገረኝ አልኩት።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 10 በአልጋዬ ላይ ትኝቼ ሳልሁ በአእምሮዬ ያየኋቸው ራዕዮች እነዚህ ነበሩ፦ ተመለከትኩ፥ በምድርም መካከል ዛፍ ነበረ፥ቁመቱም እጅግ ታላቅ ነበረ።
|
|
\v 11 ዛፉ አደገ፥በረታም። ጫፉ ሰማይ ደረሰ፥ እስከ መላው ዓለም ዳርቻ ድርስም ይታይ ነበረ።
|
|
\v 12 ቅጠሎቹ ያማሩ፥ ፍሬዎቹም የተት ረፈረፉ ነበሩ፤ ለሁሉ የሚሆን ምግብም በላዩ ነበረበት። የዱር አራዊት ከበታቹ ጥላ አግኝተው ነበር፥ የሰማያት አእዋፍም በቅርንጫፎቹ ይኖሩ ነበር። ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ከእርሱ ይመገቡ ነበር።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 13 በአልጋዬ ላይ ተኝቼ ሳለሁ በአእምሮዬ አየሁ፥ አንድ ቅዱስ መልእክተኛም ከሰማያት ወረደ።
|
|
\v 14 እርሱም ጮኽ፥ እንዲህም አለ፦ ዛፉንና ቅርንጫፎቹን ቁረጡ፥ ቅጠሎቹን አራግፉ፥ ፍሬውንም በትኑ። አራዊቱ ከሥሩ፥ አእዋፍም ከቅርንጫፎቹ ይሽሹ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 15 የሥሮቹን ጉቶ፥ በሜዳው ለምለም ሳር መካከል በብረትና በናስ ማሰሪያ እንደታሰረ በመሬት ውስጥ ተውት። በሰማያት ጠል ይረስርስ፥ በምድር ዛፎች መካከል ከአራዊት ጋር ይኑር።
|
|
\v 16 አእምሮው ከሰው አእምሮ ይለወጥ፥ ሰባት ዓመታትም እስኪያልፉ ድረስ የአውሬ አእምሮ ይሰጠው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 17 በመልእክተኛው በተነገረው አዋጅ ይህ ውሳኔ ሆነ። ልዑሉ በሰዎች መንግሥታት ላይ እንደሚገዛና እነዚህንም መንግሥታት ለተናቁ እጅግ ትሑታን ለሆኑ ሰዎች እንኳን ሳይቀር፥ ሊያነግሠው ለወደደው ለማንም እንደሚስጥ ሕያዋን ሁሉ ያውቁ ዘንድ ይህ የቅዱሱ ውሳኔ ነው።
|
|
\v 18 እኔ ንጉሡ ናቡከደነፆር ይህን ሕልም አልሜአለሁ። አሁንም አንተ ብልጣሶር፥ በመንግሥቴ ካሉ ጠቢባን ሰዎች አንዳቸውም ሊተረጉሙልኝ አልቻሉምና ትርጉሙን ንገረኝ። አንተ የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በውስጥህ ስላለ ልትተረጉም ትችላለህ።»
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 19 በዚያን ጊዜ ብልጣሶር የተባለው ዳንኤል፥ ለትንሽ ጊዜ እጅግ ታወከ፥ ሐሳቡም አስደነገጠው። ንጉሡም አለው፦ «ብልጣሶር ሆይ ሕልሙ ወይም ትርጉሙ አያስደንግጥህ።» ብልጣሶርም እንዲህ ሲል መለስ፥ «ጌታዬ ሆይ፥ ሕልሙ ለሚጠልህ፥ ትርጉሙም ለጠላቶችህ ይሁን።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 20 ያየኽው ዛፍ፥ ያድግ የነበረውና የበረታው፥ ጫፉም ወደ ሰማያት የደረሰው፥ እስከ መላው ዓለም ዳርቻ ድረስ የታየው፥
|
|
\v 21 ቅጠሎቹያምሩ የነበሩት፥ ፍሬዎቹም የተትረፈረፉት፥ ስለዚህም ለሁሉ የሚሆን መብል የነበረበት፥ ከበታቹም የምድር አራዊት ጥላ ያገኙበት፥ የሰማያት አእዋፍም ይኖሩበት የነበረ፥
|
|
\v 22 ያ ዛፍ፥ እጅግ ኃያል የሆንከው ንጉሥ አንተ ነህ። ታላቅነትህ እስከ ሰማያት፥ ሥልጣንህም እስከ ምድር ዳርቻ ደረሰ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 23 አንተ ንጉሥ ሆይ፥ አንድ ቅዱስ መልእክተኛ ከሰማይ ሲወርድና እንዲህ ሲል አየህ፦«ዛፉን ቁረጡና አጥፉት፥ ነገር ግን የሥሮቹን ጉቶ በሜዳው ለምለም ሣር መካከል በብረትና በናስ ማሰሪያ እንደታሰረ በመሬት ውስጥ ተውት። በሰማያት ጠል ይረስርስ። ሰባት ዓመታት እስኪያልፉ ድረስ ከአራዊት ጋር በሜዳ ይኑር።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 24 ንጉሥ ሆይ ትርጉሙ ይህ ነው። ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ይህ በአንተ ላይ የወጣ የልዑሉ አዋጅ ነው።
|
|
\v 25 ከሰዎች መካከል ተለይተህ ትባረራለህ፥ በሜዳም ከአራዊት ጋር ትኖራለህ። እንደ በሬ ሣር እንድትበላ ትደረጋለህ፥ በሰማያትም ጠል ትረሰርሳለህ፥ ልዑሉ በአሕዛብ መንግሥታት ላይ እንደሚገዛና እንዚህንም መንግሥታት እርሱ ለወደደው ለማንም ሊሰጣቸው እንደሚችል እስክታውቅ ድረስ ሰባት ዓመታት ያልፉብሃል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 26 የዛፉን የሥሩን ጉቶ ይተዉት ዘንድ እንደታዘዘው፥ እንዲሁ ሰማይ እንደሚገዛ ከተማርህ በኋላ መንግሥትህ ይመለስልሃል።
|
|
\v 27 ስለዚህ ንጉሥ ሆይ ምክሬ በፊትህ ተቀባይነት ያግኝ። ኃጢአት ማድረግህን አቁምና ትክክል የሆንውን ሥራ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 28 እነዚህ ነገሮች ሁሉ በናቡከደነፆር ላይ ደረሱ።
|
|
\v 29 ከዐሥራ ሁለት ወሮች በኋላ በባቢሎን ቤተ መንግሥት ሰገነት ላይ ሲመላለስ፣
|
|
\v 30 “ይህች ለንግሥናዬ መኖሪያ፣ ለክብሬም ግርማ እንድትሆን የመሠረትኋት ባቢሎን አይደለችምን?” አለ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 31 ንጉሡ ይህን ገና ተናግሮ ሳይጨርስ እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ መጣ፣ “መንግሥትህ ከአንተ እንደ ተወሰደ ተነግሮአል፤
|
|
\v 32 ከሰዎች ትገለላለህ፤ መኖሪያህ ዱር ውስጥ ከአራዊት ጋር ይሆናል። እንደ በሬ ሣር ትበላለህ። ልዑል በሰዎች መንግሥት ላይ እንደሚገዛና እርሱ ለፈለገው እንደሚሰጥ እስክትገነዘብ ድረስ ሰባት ዓመታት ያልፉብሃል።”
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 33 ይህ ቃል ናቡከደነፆር ላይ የተፈጸመው ወዲያውኑ ነበር፤ ከሰዎች ተገለለ፤ እንደ በሬ ሣር በላ፤ ሰውነቱ ከሰማይ በሚወርድ ጠል ረሰረሰ፤ ጠጉሩ እንደ ንስር ላባ፣ ጥፍሩም እንደ ወፍ ጥፍር ሆነ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 34 ጊዜው ከተፈጸመ በኋላ እኔ ናቡከደነፆር ዐይኖቼን ወደ ሰማይ አነሣሁ፤ አእምሮዬም ተመለሰልኝ። “ልዑልንም ባረክሁት ለዘላለም የሚኖረውን እርሱን አመሰገንሁት አከበርሁት። እርሱ ለዘላለም ይነግሣልና መንግሥቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ዘመን ነው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 35 የምድር ሕዝቦች ሁሉ እንደ ኢምንት ይቆጠራሉ፤ በሰማይ ሰራዊትና በምድር ሕዝቦች መካከል የወደደውን ያደርጋል። የሚያስቆመው ወይም የሚከራከረው የለም። “ለምን እንዲህ አደረግህ?” የሚለውም የለም።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 36 አእምሮዬ እንደ ተመለሰልኝ ወዲያውኑ ከመንግሥቴ ክብር ግርማዊነቴና ሞገስ ተመለሰልኝ። አማካሪዎቼና ሹማምንቴ ፈለጉኝ። ወደ ዙፋኔ ተመለስሁ፤ የበለጠ ታላቅነትም ተሰጠኝ።
|
|
\v 37 እኔ ናቡከደነፆር አሁን የሰማይን ንጉሥ እባርካለሁ፤ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ። ሥራዎቹ ትክክል መንገዶችም ጽድቅ ናቸው። በትዕቢታቸው የሚራመዱትን ያዋርዳል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 5
|
|
\p
|
|
\v 1 ንጉሥ ቤልሻዛር በሺህ ለሚቆጠሩ መኳንንቱ ታላቅ ግብዣ አደረገ፣ በሺሁም ፊት የወይን ጠጅ ይጠጣ ነበር።
|
|
\v 2 ቤልሻዘር የወይን ጠጅ እየጠጣ ሳለ፣ አባቱ ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ ያመጣቸውን የወርቅና የብር መጠጫዎችን እርሱና መኳንንቱ፣ ሚስቶቹና ቁባቶቹ ይጠጡባቸው ዘንድ እንዲያመጡለት አዘዘ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 አገልጋዮቹም እነዚያን ከኢየሩሳሌም ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የተወሰዱትን የወርቅ ዕቃዎች አመጡ፤ ንጉሡና መኳንንቱ፣ ሚስቶቹና ቁባቶቹም ጠጡባቸው።
|
|
\v 4 የወይን ጠጁንም እየጠጡ የወርቅና የብር፣ የናስ፣ የብረት፣ የዕንጨትና የድንጋይ አማልክቶቻቸውን አመሰገኑ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 5 በዚያን ቅጽበት የሰው እጅ ጣቶች ታዩ፤ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ በመቅረዙ ትይዩ ባለው በግድግዳው ልስን ላይ ጻፉ፤ ንጉሡም ይጽፍ የነበረውን እጅ አየ፤
|
|
\v 6 በዚያን ጊዜ የንጉሡ ፊት ተለዋወጠ በድንጋጤም ተሞላ፤ እጆቹና እግሮቹ ከዱት፤ ጉልበቶቹም ተብረከረኩ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 ንጉሡም ድምፁን ከፍ አድርጎ አስማተኞችን፣ ኮከብ ቆጣሪዎችንና መተተኞችን እንዲያስገቡለት አዘዘ፤ ለባቢሎናውያኑ ጠቢባን ንጉሡ እንዲህ አላቸው፤ “ይህን ጽሕፈት አንብቦ ትርጉሙን የሚነግረኝን ሐምራዊ መጎናጸፊያ አለብሰዋለሁ፤ የወርቅ ሐብልም በዐንገቱ አጠልቅለታለሁ፤ በመንግሥቴም ሥልጣን ሦስተኛውን ማዕረግ ይይዛል።”
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 8 ከዚያም የንጉሡ ጠቢባን ሁሉ ገቡ፤ ነገር ግን ጽሕፈቱን ሊያነብም ሆነ ትርጉሙ ምን እንደሆነ ለንጉሡ ሊነግር የሚችል ማንም አልነበረም።
|
|
\v 9 ንጉሥ ቤልሻዘር ፈራ ፊቱም እጅግ ተለወጠ፤ መኳንንቱም ግራ ግብቶአቸው ተደናገጡ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 10 ንግሥቲቱም የንጉሡንና የመኳንንቱን ድምፅ ሰምታ ወደ ግብዣው አዳራሽ ገባች፤ እንዲህም አለች፤ “ንጉሥ ሆይ፤ ለዘላለም ንገሥ፣ አትደንግጥ፣ ፊትህም አይለዋወጥ
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 11 በመንግሥትህ ውስጥ የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያለበት አንድ ሰው አለ፤ ይህ ሰው በአባትህ ዘመን እንደ አማልክት ጥበብና ማስተዋል ዕውቀትም የሞላበት ሆኖ ተገኝቶአል፤ አባትህ ንጉሥ ናቡከደነፆርም የጠንቋዮች፣ የአስማተኞች፣ የኮከብ ቆጣሪዎችና የመተተኞች አለቃ አደረገው።
|
|
\v 12 ንጉሡ ብልጣሶር ብሎ የጠራው ይህ ዳንኤል መልካም መንፈስ፥ ዕውቀትና ማስተዋል ያለው ሆኖ ተገኘ፤ ሕልምን የመተርጎም፣ እንቆቅልሽን የመፍታትና የተሰወረውን የመግለጥ ልዩ ችሎታም ነበረው። ስለዚህ ዳንኤልን አስጠራ፣ እርሱም የጽሕፈቱን ትርጉም ይነግርሃል።”
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 13 ዳንኤልንም ወደ ንጉሥ አቀረቡት፤ ንጉሡም እንዲህ አለው፤ “ንጉሡ አባቴ ከይሁዳ ማርኮ ካመጣቸው መካከል አንዱ የሆንኸው ዳንኤል አንተ ነህን?
|
|
\v 14 የአማልክት መንፈስ በውስጥህ እንዳለ፣ ዕውቀት፣ ማስተዋልና ልዩ ጥበብ እንዳለህ ሰምቻለሁ፤
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 15 ይህን ጽሕፈት አንብበው ትርጉሙ ምን እንደሆነ ይነግሩኝ ዘንድ ጠቢባንና አስማተኞች በፊቴ ቀርበው ነበር፣ ነገር ግን ሊገልጡት አልቻሉም።
|
|
\v 16 አንተ ግን መተርጎምና አስቸጋሪ የሆነውን ነገር መፍታት እንደምትችል ሰምቻለሁ። ይህን ጽሕፈት አንብበ ትርጉሙን ብትነግረኝ፣ ሐምራዊ መጎናጸፊያ ያለብሱሃል፣ የወርቅ ሐብል በዓንገትህ ያጠልቁልሃል፣ በመንግሥት ሥልጣንም ሦስተኛውን ማዕረግ እንድትይዝ ትደረጋለህ።”
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 17 ዳንኤልም ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ስጦታዎችህን ለራስህ አድርግ፤ ሽልማቶችህንም ለሌላ ሰው ስጥ፤ ይሁን እንጂ ጽሕፈቱን ለንጉሡ አነባለሁ፤ ትርጉሙ ምን እንደሆነም እነግረዋለሁ።”
|
|
\v 18 “ንጉሥ ሆይ፤ ልዑል አምላክ ለአባትህ ለናቡከደነፆር ገናናነትንና ታላቅነትን፣ ክብርንና ግርማን ሰጠው።
|
|
\v 19 ከሰጠው ታላቅ ሥልጣን የተነሣ ሕዝቦችና መንግሥታት፣ ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎችም ሁሉ ተንቀጠቀጡለት ፈሩትም። ንጉሡም ሊገድል የፈለገውን ይገድል፣ ሊያድን የፈለገውን ሊያድን፣ ሊሾም ይፈለገውን ይሾም፣ ሊያዋርድ የፈለገውንም ያዋርድ ነበር።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 20 ነገር ግን ልቡ በትዕቢት በጸናና በእብሪት በተሞላ ጊዜ ከዙፋኑ ተወገደ፤ ክብሩም ተገፈፈ።
|
|
\v 21 ከሰው መካከል ተሰደደ፤ የእንስሳም አእምሮ ተሰጠው፤ ከዱር አህዮች ጋር ኖረ፤ እንድች በሬም ሣር በላ፤ ልዑል አምላክ በሰዎች መንግሥት ላይ እንደሚገዛና እነርሱምን ለወደደው እንደሚሰጥ እስኪያውቅ ድረስ ሰውነቱ በሰማይ ጠል ረሰረሰ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 22 “ቤልሻዘር ሆይ፤ አንተ ልጁ ሆነህ ይሁ ሁሉ ብታውቅም፣ ራስህን ዝቅ አላደረግህም፤
|
|
\v 23 ይልቁንም በሰማይ አምላክ ላይ በመታበይ ራስህን ከፍ ከፍ አደረግህ፤ የመቅደሱን መጠጫዎች አስመጣህ፤ አንተና መኳንንትህ፣ ሚስቶችህና ቁባቶችህም የወይን ጠጅ ጠጣችሁባቸው፣ ማየት፣ መስማት፣ ማስተዋልም የማይችሉትን የብርና የወርቅ የናስና የብረት፣ የእንጨትና የድንጋይ አማልክትን አመሰገንህ። ሕይወትህንና መንገድህን ሁሉ በእጁ የያዘውን አምላክ ግን አላከበርህም።
|
|
\v 24 ስለዚህ እርሱ ጽሕፈቱን ይጻፈውን እጅ ላከ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 25 የተጻፈውም ጽሕፈት፣ ‘ማኔ፣ ቴቄል፣ ፋሬስ’ ይላል
|
|
\v 26 የቃሉም ትርጉም ይህ ነው፤ ‘ማኔ’ ማለት እግዚአብሔር የመንግሥትህን ዘመን ቆጠረው፣ ወደ ፍጻሜም አደረሰው ማለት ነው።
|
|
\v 27 ‘ቴቄል’ ማለት በሚዛን ተመዝነህ ቀለህም ተገኘህ ማለት ነው።
|
|
\v 28 ‘ፋሬስ’ ማለት መንግሥትህ ተከፈለ፣ ለሜዶናውያንና ለፋርስ ሰዎች ተሰጠ ማለት ነው።”
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 29 ከዚህ በኋላ በቤልሻዘር ትእዛዝ ዳንኤልን ሐምራዊ መጎናጸፊያ አለበሱት፣ የወርቅ ሐብል በዐንገቱ ኣይ አጠለቁለት፣ በመንግሥቱም ሥልጣን ሦስተኛውን ማዕረግ እንዲይዝ እንዲያደርጉት በዐዋጅ አዘዘ።
|
|
\v 30 በዚያኑ ሌሊት የባቢሎናውያን ንጉሥ ቤልሻዘር ተገደለ፤
|
|
\v 31 የሥልሳ ሁለት ዓመት ዕድሜ የነበረው ሜዶናዊው ዳርዮስም መንግሥቱን ወሰደ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 6
|
|
\p
|
|
\v 1 ዳርዮስ በመንግሥቱ ሁሉ ላይ እንዲገዙ አንድ መቶ ሃያ መሳፍንትን መሾም ፈለገ፤
|
|
\v 2 በእነዚህም ላይ ሦስት የበላይ አስተዳዳሪዎችን አደረገ፣ ከእነርሱም አንዱ ዳንኤል ነበረ። ንጉሡ ጉዳት እንዳይደርስበት መሳፍንቱ ተጠሪነታቸው ለሦስቱ የበላይ አስተዳዳሪዎች እንዲሆን ተደረገ።
|
|
\v 3 ከመሳፍንቱና ከበላይ አስተዳዳሪዎቹ ሁሉ ይልቅ ዳንኤል ልዩ የጥበብ መንፈስ የሞላበት ሆኖ በመገኘቱ፣ ንጉሡ በመላው ግዛቱ ላይ ሊሾመው አሰበ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 4 በዚህ ምክንያት የበላይ አስተዳዳሪዎቹና መሳፍንቱ ዳንኤል በሚያከናውነው የመንግሥት ሥራ እንከን ለማግኘት ፈለጉ፤ ነገር ግን ዳንኤል ታማኝ ጠንቃቃና በሥራው እንከን የሌለበት ስለነበር በእርሱ ላይ ስህተት ሊያገኙ አልቻሉም።
|
|
\v 5 እነዚህም ሰዎች፣ “ከአምላኩ ሕግ ጋር የተያያዘ ጉዳይ ካልሆነ በቀር፣ ይህን ሰው የምንከስበት ምንም ሰበብ አናገኝበትም” አሉ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 6 ከዚያም የበላይ አስተዳዳሪዎቹና አሳፍንቱ ዕቅድ ካወጡ በኋላ በአንድነት ወደ ንጉሡ ሄደው እንዲህ አሉ፤ “ንጉሥ ዳርዮስ ሆይ፤ ለዘላለም ንገሥ!
|
|
\v 7 ንጉሥ ሆይ፤ እስከ ሠላሳ ቀን ድረስ ወደ አንተ ካልሆነ በቀር ማንም ሰው ወደ ሌላ አምላክ መጸለይ እንደሌለበት ንጉሡ ዐዋጅ እንዲያወጣ ትእዛዙም እንዲፈጸም፤ ይህንም የተላለፈ ወደ አንበሶች ጉድጓድ እንዲጣል፣ የመንግሥት የበላይ አስተዳዳሪዎች፣ መኳንንት፣ መሳፍንት፣ አማካሪዎችና አገረ-ገዦች ሁሉ በአንድነት ተስማምተዋል፤
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 8 ንጉሥ ሆይ፤ ይህን ዐዋጅ አውጣ፤ እንደማይሻረውና እንደማይለወጠው የሜዶንና የፋርስ ሕግ እንዲሆን ትእዛዙን በጽሑፍ አድርገው።”
|
|
\v 9 ስለዚህ ንጉሡ ዳርዮስ ዐዋጁ ተጽፎ እንዲወጣ አደረገ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 10 ዳንኤልም ዐዋጁ እንደወጣ ባወቀ ጊዜ ወደ ቤቱ ሄደ፤ መስኮቶቹን በኢየሩሳሌም አንፃር ተከፍተው ባሉበት በሰገነቱ ቀድሞ ያደርግ እንደነበረው በቀን ሦስት ጊዜ ተንበርክኮ ጸለየ አምላኩንም አመሰገነ።
|
|
\v 11 ሰዎቹም በአንድ ላይ ሄደው ዳንኤልን ሲጸልይና አምላኩን ሲማጸን አገኙት።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 12 ወደ ንጉሡም ሄደው፤ “ንጉሥ ሆይ፤ በሚቀጥሉት ሠላሳ ቀናት ማንም ሰው ወደ አንተ ካልሆነ በቀር ወደ ሰውም ሆነ ወደ ማንኛውም አምላክ ቢጸልይ በአንበሶች ጉድጓድ ውስጥ እንደሚጣል ዐዋጅ አውጥተህ አልነበረምን?” ሲሉ እርሱ ስላወጣው ዐዋጅ ጠየቁት። ንጉሡም፤ “ዐዋጁ እንደማይሻረው እንደ ሜዶንና እንደ ፋርስ ሕግ የጸና ነው” ሲል መለሰ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 13 እርሱም ንጉሡን፤ “ንጉሥ ሆይ፤ ከይሁዳ ምርኮኞች አንዱ የሆነው ዳንኤል፣ አንተም ሆነ በጽሑፍ ያወጣኸውን ዐዋጅ አያከብርም፤ አሁንም በቀን ሦስት ጊዜ ወደ አምላኩ ይጸልያል” አሉት።
|
|
\v 14 ንጉሡ ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ፤ ዳንኤልንም ከዚህ ትእዛዝ የሚያድንበትን መንገድ አሰላሰለ፤ ፀሐይ እስክትጠልቅም ድረስ የተቻለውን ሁሉ አደረገ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 15 ከዚያም ሰዎቹ በአንድ ላይ ወደ ንጉሡ ቀርበው፣ “ንጉሥ ሆይ፤ በሜዶንና በፋርስ ሕግ መሠረት፣ አንድ ንጉሥ የጣው ዐዋጅም ሆነ ትእዛዝ ሊለወጥ እንደማይችል ዕወቅ” አሉት።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 16
|
|
ስለዚህ ንጉሡ ትእዛዝ ሰጠ፤ እነርሱም ዳንኤልን አመጡት፤ ወደ አንበሶቹም ጉድጓድ ጣሉት። ንጉሡም ዳንኤልን፣ ሁልጊዜ የምታመልከው አምላክህ ያድንህ” አለው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 17 ድንጋይ አምጥተው በጉድጓዱ አፍ ላይ ገጠሙበት፤ ንጉሡም በዳንኤል ላይ የተፈጸመው እንዳይለወጥ በራሱ የቀለበት ማሕተምና በመሳፍንቱ ቀለበቶች አተመበት።
|
|
\v 18 ንጉሡም ወደ ቤተ መንግሥቱ ተመለሰ፤ በዚያም ሌሊት ምግብ ሳይበላ፣ የሚያዝናናውም ነገር ሳይቀርብለት ዐደረ፤ እንቅልፍም ከእርሱ ራቀ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 19 በማለዳም ገና ጎሕ ሲቀድ፣ ንጉሡ ተነሥቶ ወደ አንበሶቹ ጉድጓድ እየተጣደፈ ሄደ።
|
|
\v 20 ወደ ጉድጓዱም ቀርቦ በሐዘን ድምፅ ዳንኤልን፣ “የሕያው አምላክ አገልጋይ ዳንኤል ሆይ፤ ሁልጊዜ የምታመልከው አምላክህ ከአንበሶቹ ሊያድንህ ችሎአልን?” ብሎ ጠየቀው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 21 ዳንኤልም እንዲህ ብሎ መለሰ፤ “ንጉሥ ሆይ፤ ለዘላለም ንገሥ፤
|
|
\v 22 ንጉሥ ሆይ፤ በፊቱ ቅን ሆኜ ስለተገኘሁ፣ በአንተም ፊት በደል ስላልተገኘብኝ አምላኬ መልአኩን ልኮ የአንበሶቹን አፍ ዘጋ፤ እነርሱም አልጎዱኝም።”
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 23 ንጉሡ እጅግ ተደሰተ፤ ዳንኤልን ከጉድጓድ እንዲያወጡት አዘዘ። ዳንኤል በአምላኩ ታምኖ ነበርና ከጉድጓድ በመጣ ጊዜ፣ አንዳች ጉዳት አልተገኘበትም።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 24 በንጉሡ ትእዛእ ዳንኤልን የከሰሱት ሰዎች ተይዘው እንዲመጡ ተደረገ፤ እነርሱም ተይዘው ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር በአንበሶቹ ጉድጓድ ውስጥ ተጣሉ። ወደ ጉድጓዱም መጨረሻ ገና ሳይደርሱ አንበሶቹ ቦጫጩቋቸው፤ ዐጥንቶቻቸውንም ሁሉ ሰባበሩ።
|
|
\v 25 ከዚያ በኋላ ንጉሥ ዳርዮስ፣ በምድር ላይ ለሚኖሩ ሕዝቦች፣ መንግሥታትና ልዩ ልዩ ቋንቋ ለሚናገሩ ሰዎች ሁሉ እንዲህ የሚል መልእክት ጻፈ፤ “ሰላም ይብዛላችሁ!
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 26 በማንኛውም የመንግሥቴ ግዛት ሰው ሁሉ፣ የዳንኤልን አምላክ እንዲፈራና እንዲያከብር ይህን ዐዋጅ አውጥቻለሁ። “እርሱ ለዘላለም የሚኖር ሕያው አምላክ ነውና መንግሥቱም አይጠፋም፤ ለግዛቱም መጨረሻ የለውም
|
|
\v 27 እርሱ ይታደጋል፣ ያድናልም በሰማይና በምድር ምልክቶችንና ድንቆችን ያደርጋል ዳንኤልን ከአንበሶች አፍ አድኖታል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 28 ስለዚህ ዳንኤል በዳርዮስ መንግሥትና በፋርሳዊው በቂሮስ ዘመነ መንግሥት ሁሉ ኑሮው ተሳካለት።
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 7
|
|
\p
|
|
\v 1 የባቢሎን ንጉሥ ቤልሻዘር በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት ዳንኤል በአልጋው ላይ ተኝቶ ሳለ ሕልም አለመ፤ ራእይም አየ፤ የሕልሙንም ዋና ሃሳብ ጻፈው።
|
|
\v 2 ዳንኤል እንዲህ አለ፤ “ኣቱ የሰማይ ነፋሳት ታላቁን ባሕር ሲያናውጡት ሌሊት በራእይ አየሁ፤
|
|
\v 3 እርስ በርሳቸው የማይመሳሰሉ አራት ታላላቅ አራዊት ከባሕሩ ወጡ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 4 የመጀመሪያው አንበሳ ይመስል ነበር፤ የንስርም ክንፎች ነበሩት፤ ክንፎቹ እስኪነቃቀሉ ድረስ ትመለከትሁ፤ እንደ ሰው በሁለት እግር እንዲቆም ከመድር ከፍ ከፍ ተደረገ፤ ሰብዓዊ አእምሮ ተሰጠው።
|
|
\v 5 እነሆም ሁለተኛው አውሬ ድብ ይመስል ነበር፤ በአንድ ጎኑ ከፍ ብሎአል፤ በአፉ ውስጥ በጥርሶቹ መካከል ሦስት የጎድን አጥንቶች ነበርት። እርሱም፤ “ተነሥ እስክትጠግብ ድረስ ሥጋ ብላ” ተባለ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 6 ከዚህ በኋላ ተመለክትሁ፤ በፊቱ በኩል ነብር የሚመስል ሌላ አውሬ ነበር፤ በጀርባውም በኩል የወፍ ክንፍ የሚመስሉ አራት ክንፎች ነበርት፤ ይህ አውሬ አራት ራስ ነበረው፤ ለመግዛትም ሥልጣን ተሰጠው።
|
|
\v 7 ከዚህ በኋላ በሌሊት ራእይ አየሁ፤ በፊቴም የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ በጣም ኃይለኛ የሆነ አራተኛ አውሬ ነበር፤ ትልቅ የብረት ጥርሶች ነበሩት፤ ያደቅና ይበላ፣ የቀረውንም ሁሉ በእግሮቹ ይረጋግጥ ነበር። ከእርሱ በፊት ከነበሩት አራዊት ሁሉ የተለየ ሲሆን፤ አሥር ቀንዶች ነበሩት።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 8
|
|
ስለ ቀንዶቹ ሳስብ ሳለሁ፣ ከመካከላቸው አንድ ሌላ ትንሽ ዘንድ ብቅ ሲል አየሁ፤ ከመጀመሪያዎቹ ቀንዶች ሦስቱ ከፊቱ ተነቃቀሉ፤ ይህም ቀንድ የሰው ዐይኖችን የሚመስሉ ዐይኖች፣ በትዕቢትም የሚናገር አፍ ነበረው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 9 እኔም ስመለከት፣ ዙፋኖች ተዘረጉ፣ ጥንታዌ ጥንቱም ተቀመጠ፣ ልብሱ እንደ በረዶ ነጭ ነበረ፣ የሩስም ጠጉር እንደ ጥጥ ነጭ ነበረ፣ ዙፋኑ የእሳት ነበልባል፣ መንኩራኩሮቹም ሁሉ እንደሚነድ እሳት ነበር፥
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 10
|
|
የእሳት ወንዝ ከፊት ለፊት ፈልቆ ይፈስ ነበር ሺህ ጊዜ ሺዎች ያገለግሉት ነበር፤ እልፍ ጊዜ እልፍ በፊቱ ቆመዋል፤ የፍርድ ጉባዔ ተሰየመ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 11 ቀንዱም ከሚናገረው የትዕቢት ቃል የተነሣ፣ መመልከቴን ቀጠልሁ፣ አውሬው እስኪታረድና እካሉድቆ ወደሚንበለበለው እሳት እስኪጣል ድረስ ማየቴን አላቋርጥሁም።
|
|
\v 12 ሌሎቹም አራዊት ሥልጣናቸው ተገፎ ነበር፤ ነገር ግን ለተወሰነ ጊዜና ወቅት በሕይወት እንዲኖሩ ተፈቀደላቸው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 13 ሌሊት ባየሁት ራእይ የሰውን ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመና ጋር ሲመጣ አየሁ፤ ወደ ጥንታዌ ጥንቱ መጣ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት።
|
|
\v 14 ሥልጣን፣ ክብርና ታላቅ ኃይል ተሰጠው፤ በልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች፤ መንግሥታትና ሕዝቦች ሰገዱለት፤ ግዛቱም ለዘላለም የማያልፍ ነው፤ መንግሥቱም ፈጽሞ የማይጠፋ ነው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 15 እኔ ዳንኤል በመንፈሴ ታወክሁ፤ ያየሁትንም ራእይ እጅግ አስጨነቀኝ።
|
|
\v 16 በዚያ ከቆሙት ወደ አንዱ ቀርቤ የዚህ ሁሉ ትርጕም ምን እንደ ሆነ ጠየቅሁት።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 17 “አራቱ ታላላቅ አራዊት ከምድር የሚነሡ መንግሥታት ናቸው፤
|
|
\v 18 ነገር ግን የልዑሉ ቅዱሳን መንግሥቱን ይወስዳሉ፣ ለዘላለምም ይይዙታል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 19 ከዚያም የሚያደቅቀውንና የሚበላውን የቀረውንም ሁሉ በእግሮቹ የሚረጋግጠውን የብረት ጥርሶችና የናስ ጥፍሮች የነበሩትን ከሌሎች የተለየና እጅግ አስፈሪ የሆነውን የአራተኛውን አውሬ ምንነት የበለጠ ማወቅ ፈለግሁ።
|
|
\v 20 ደግሞም በራሱ ላይ ስላሉት አሥር ቀንዶች፣ ከመካከላቸው ብቅ ስላለው ቀንድና ከዚሁ ቀንድ ፊት ስለተነቃቀሉት ሦስት ቀንዶች፣ እንደዚሁም ከሌሎች ስለበለጠው የሰው ዓይኖች የሚመስሉ ዓይኖች በትዕቢትም የሚናገር አፍ ስለነበሩት ስለዚሁ ቀንድ ማወቅ ፈለግሁ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 21 እየተመለክትኩም ሳለሁ ይህ ቀንድ በቅዱሳን ላይ ጦርነት ዐውጆ አሸነፋቸው።
|
|
\v 22 ይህም የሆነው ጥንታዌ ጥንቱ እስኪመጣና ለልዑሉ ቅዱሳን እስኪፈርድላቸው ድረስ ነበር፤ ኪዝያም የልዑሉ ቅዱሳን መንግሥቱን የሚወርሱበት ዘመን መጣ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 23 እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “አራተኛው አውሬ በምድር ላይ የሚነሣ አራተኛው መንግት ነው። ከሌሎች መንግሥታት ሁሉ የተለየ ይሆናል፤ መላውንም ምድር እየረገጠና እያደቀቀ ይበላል።
|
|
\v 24 ዐሥሩ ቀንዶች ከዚህ መንግሥት የሚወጡ ዐሥር ነገሥታት ናቸው፤ ከዚያም በኋላ ከእነርሱ የተለየ ሌላ ንጉሥ ይነሣል፤ ሦስቱንም ነገሥታት ያንበረክካል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 25 በልዑል ላይ የዓመፅ ቃል ይናገራል፤ የልዑልንም ቅዱሳን ያስጨንቃል፤ ለበዓላት የተመደበውን ጊዜና ሕግን ለመለወጥ ይሞክራል፤ እነዚህም ነገሮች ለዘመን፣ ለዘመናት፣ ለዘመን እኩሌታም ለእርሱ ዐልፈው ይሰጣሉ።
|
|
\v 26 ነገር ግን የፍርድ ዙፋን ይዘረጋል፤ ሥልጣኑም ይወሰድበታል፤ ፈጽሞ ለዘላለም ይደመሰሳል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 27 ከዚያም ከሰማይ በታች ያሉ መንግሥታት ልዕልና፣ ሥልጣንና ታላቅነት ለልዑሉ ሕዝብ ለቅዱሳን ይሰጣል። መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ይሆናል፤ ገዦች ሁሉ ያመልኩታል ይታዘዙታልም።
|
|
\v 28 የነገሩ ፍጻሜ ይህ ነው፤ እኔም ዳንኤል በሃሳቤ እጅግ ተጨነቅሁ፤ መልኬም ተለወጠ፤ ይሁን እንጂ ነገሩን በልቤ ጠበቅሁት።
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 8
|
|
\p
|
|
\v 1 ንጉሥ ቤልሻዘር በነገሠ በሦስተኛው ዓመት አስቀድሞ ከተገለጠልን ራእይ በኋላ እኔ ዳንኤል ሌላ ራእይ አየሁ።
|
|
\v 2 በራእዩም በኤሳም አውራጃ በሱሳ ግንብ ራሴን አየሁት፤ በራእዩም በኡባል የውሃ መውረጃ አጠገብነበርሁ፤
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 ዓይኔን አንስቼ ስመለከት እነሆ፣ ሁለት ቀንዶች ያሉት አውራ በግ በወንቁ አጠገብ ቆሞ አየሁ፤ ቀንዶቹም ረጃጅሞች ነበር፤ ከቀንዶቹም አንዱ ከሌላው ይረዝማል፤ ረጅሙ ቀንድ የበቀለው ዘግይቶ ቢሆንም ከአጭሩ ይልቅ በርዝመቱ የላቀ ነበር።
|
|
\v 4 አውራ በጉም ወደ ምዕራብ፣ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ በቀንዱ ሲጎሽም አየሁ። ምንም ዐይነት እንስሳ ሊቋቋመው አልቻለም፤ ከእጁም ሊያድን የሚችል አልነበረም፤ የፈለገውን ሁሉ አደረገ፤ ታላቅም ሆነ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 5 ስለዚህ ነገር እያሰብሁ ሳለሁ፣ በዐይኖቹ መካከል ትልቅ ቀንድ ያለው አውራ ፍየል፣ መሬት ሳይነካ ምድርን ሁሉ እያቋረጠ በድንገት ከምዕራብ መጣ፤
|
|
\v 6 በወንዙ አጠገብ ቆሞ ወዳየሁት፣ ሁለት ቀንድ ወዳለው አውራ በግ ተንደርዶ መጣበት፤ በታላቅ ቁጣም መታው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 እየወጋውና ሁለቱን ቀንዶቹን እየሰበረ፣ በጭካኔ አውራውን በግ ሲጎዳው አየሁ፤ አውራ በጉም ለመቋቋም ጉልበት አልነበረውም። ፍየሉ በምድር ላይ ጥሎ ረገጠው፤ አውራ ብጉንም ከፍየሉ እጅ ለማዳን የሚችል አልነበረም።
|
|
\v 8 ፍየሉም ታላቅ ሆነ፤ ነገር ግን በኃይሉ በበረታ ጊዜ፣ ትልቁ ቀንዱ ተሰበረ፤ በቦታውም ወደ አራቱ የሰማይ ነፋሳት የሚያመለክቱ አራት ታላላቅ ቀንዶች በቀሉ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 9 ከእነዚህም ቀንዶች መካከል በአንዱ ላይ አንድ ትንሽ ቀንድ በቀለ፤ ወደ ደቡብ፣ ወደ ምሥራቅና ወደ ተከበረችው የእስራኤል ምድር በኃይል አደገ።
|
|
\v 10 ከሰማይ ሠራዊት ጋር ጦርነት እስኪገጥም ድረስ አደገ፤ ከሰማይና ከክዋክብት ሠራዊት የተወሰኑትን ወደ ምድር ጣለ፣ ረጋገጣቸውም።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 11 ከሰማይ ሠራዊት አለቃ ጋር እስኪተካከል ድረስ ራሱን ከፍ ከፍ አደረገ፤ የልዑሉንም የዘወትር መሥዋዕት ወሰደበት፤ የመቅደሱንም ስፍራ አረከሰ።
|
|
\v 12 ከዐመፅ የተነሳም የቅዱሳን ሠራዊት ለፍየሉ ቀንድ አልፎ ተሰጠ፤ የሚቃጠል መሥዋዕቱም እንዲቆም ተደረገ። እውነትን ወደ ምድር ይጥላል የሚያደርገውም ሁሉ ይከናወንለታል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 13 ከቅዱሳኑም አንዱ ሲናገር ሰማሁ፤ ሌላውም ቅዱስ እንዲህ አለው፤ “ስለ ዘወትሩ መሥዋዕት፣ ለጥፋት ምክንያት ስለሆነው ዐመፅ፣ ከእግር በታች እንዲረገጡ ዐልፈው ስለሚሰቱት መቅደስና ሠራዊት የታየው ራእይ የሚፈጸመው መቼ ነው?”
|
|
\v 14 እርሱም፣ “እስከ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ምሽቶችና ማለዳዎች ድረስ ይቆያል፤ ከዚያም መቅደሱ እንደገና ይነጻል” አለኝ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 15 እኔ ዳንኤል ራእዩን ስመለከትና ሳስተውል ሳለ፣ ሰውን የሚመስል ከፊት ለፊቴ ቆመ፤
|
|
\v 16 ከኡባልም፣ “ገብርኤል ሆይ፤ ለዚህ ሰው የራእዩን ትርጕም ንገረው” ብሎ የሚጮህ የሰው ድምፅ ሰማሁ።
|
|
\v 17 እኔ ወደቆምሁበት እየቀረበ ሲመጣ፣ ደንግጬ በግንባሬ ተደፋሁ፣ እርሱም፣ “የሰው ልጅ ሆይ፤ ራእዩ ስለ ዘመኑ ፍጻሜ እንደሆነ አስተውል” አለኝ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 18 እየተናገረኝ ሳለ፣ በምድር ላይ በግንባሬ ተደፋሁ፤ በከባድ እንቅልፍም ተዋጥሁ፣ እርሱ ግን ዳሰሰኝና በእግሮቼ አቆመኝ።
|
|
\v 19 እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ራእዩ በመጨረሻው ዘመን ሊሆን ያለውን የሚያመለክት ስለሆነ፣ በኋላ በቁጣው ዘመን ምን እንደሚሆን እነግርሃለሁ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 20 ያየኸው ሁለት ቀንዶች የነበሩት አውራ በግ፣ የሜዶንና የፋርስን መንግሥታት ያመለክታል።
|
|
\v 21 ተባዕቱ ፍየል የግሪክ ንጉሥ ሲሆን፣ በዐይኖቹም መካከል ያለው ትልቁ ቀንድ የመጀመሪያው ንጉሥ ነው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 22 የተሰበረውን ቀንድ የተኩት አራቱ ቀንዶቹ፣ ከመንግሥቱ የሚወጡትን አራት መንግሥታትን ያመለክታሉ፣ ነገር ግን ከእርሱ ጋር የሚተካከል ኃይል አይኖራቸውም።
|
|
\v 23 “በዘመነ መንግሥታቸው በስተ መጨረሻ፣ ዐመፀኞች ፍጹም እየከፉ በሚሄዱበት ጊዜ፣ አስፈሪ ፊት ያለው አታላይ ንጉሥ ይነሣል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 24 እጅግ ብርቱ ይሆናል፤ ነገር ግን በገዛ ኃይሉ አይደለም። አሠቃቂ ጥፋት ይፈጽማል፤ የሚያደርገው ሁሉ ይከናወንለታል፤ ኃያላን ሰዎችንና ቅዱሳኑን ሕዝብ ያጠፋል።
|
|
\v 25 እጅግም ተንኮለኛ ስለሆነ በማታለል ይበለጽጋል፤ በልዑላን ልዑልም ላይ ይነሣል፤ ይሁን እንጂ እርሱም ይጠፋል ነገር ግን በሰው ኃይል አይደለም።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 26 የተሰጠህ የምሽቱና የማለዳው ራእይ እውነት ነው፤ ነገር ግን ከብዙ ዘመን በኋላ የሚሆነውን ስለሚያመለክት ራእዩን ዘግተህ አትምበት።”
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 27 እኔ ዳንኤል ዐቅሜ ተሟጦ ነበር፤ ለብዙ ቀናት ታመምሁ፣ ተኛሁም። ከዚያም በኋላ ተነሥቼ ወደ ንጉሡ ሥራ ሄድሁ። ባየሁት ራእይ ተደናግጬ ነበር፤ ነገሩም የገባው ማንም አልነበረም።
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 9
|
|
\p
|
|
\v 1 የሜዶናዊው የአርጤክስስ ልጅ ዳርዮስ በባቢሎን በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት
|
|
\v 2 በዘመነ መንግሥቱ በመጀመሪያው ዓመት፣ እኔ ዳንኤል ለነቢዩ ኤርምያስ በተሰጠው የእግዚአብሔር ቃል መሠረት፣ የኢየሩሳሌም መፈራረስ ሰባ ዓመት እንደሚቆይ ከቅዱሳት መጻሕፍት አስተዋልሁ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 ስለዚህ ማቅ ለብሼ በራሴም ላይ ዐመድ ነስንሼ በጾምና በጸሎት፣ በምልጃም ፊቴን ውደ ጌታ አምላክ አቀናሁ።
|
|
\v 4 ወደ እምላኬ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ብዬ ጸለይሁ፣ ተናዘዝሁም፤ “ከሚወዱህና ትእዛዝህን ከሚፈጽሙ ሁሉ ጋር የፍቅር ቃል ኪዳንህን የምትጠብቅ፣ ታላቅና የተፈራህ አምላክ ጌታ ሆይ፤
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 5 እኛ ኃጢአት ሠርተናል፣ በድለናልም፣ ክፋትን አድርገናል፣ ዐምፀናልም፣ ከትእዛዝህና ከሕግህ ዘወር ብለናል።
|
|
\v 6 ለንጉሦቻችን፣ ለልዑሎቻችንና ለአባቶቻችን እንዲሁም ለምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ በአንተ ስም የተናገሩትን አገልጋዮችህን ነቢያትን አልሰማንም።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 “ጌታ ሆይ፤ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን በአንተ ላይ ስለ ሠራነው ታላቅ ክፋት እኛን በበተንህባቸው አገሮች ሁሉ የምንገኝ የይሁዳ ሰዎች፣ የኢየሩሳሌምና የመላው እስራኤል ሕዝብ፣ በሩቅም ሆነ በቅርብ ያለን በዚህ ቀን ኀፍረት ተከናንበናል።
|
|
\v 8 እግዚአብሔር ሆይ፤ እኛና ንጉሦቻችን፣ ልዑሎቻችንና አባቶቻችን በአንተ ላይ ኃጢአት ስለ ሠራን ኀፍረት ተከናንበናል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 9 ምንም እንኳ በእርሱ ላይ ያመፅን ብንሆን፣ ጌታ አምላካችን ይቅር ባይና መሐሪ ነው።
|
|
\v 10 እግዚአብሔር አምላካችንን አልታዘዝነውም፤ ደግሞም በአገልጋይቹ በነቢያት በኩል የሰጠንን ሕግ አልጠበቅንም፤
|
|
\v 11 መላው እስራኤል አንተን ባለመታዘዝ ሕግህን ተላልፎአል፤ ዘወርም ብሎአል።በአንተ ላይ ላይ ኃጢአትን ስለ ሠራን፣ በእግዚአብሔር አገልጋይ በሙሴ ሕግ የተጸው መሐላና ርግማን ፈሰሰብን።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 12 ታላቅ ጥፋት በእኛ ላይ በማምጣት፣ የተነገረውን ቃል ፈጸምህብን፤ በኢየሩሳሌም ላይ የተደረገውን የሚያህል ከሰማይ በታች ከቶ የለም።
|
|
\v 13 በሙሴም ሕግ እንደ ተጻፈው፤ ይህ ሁሉ ጥፋት በእኛ ላይ ደረሰ፤ ሆኖም ከኃጢአታችን በመመለስና እውነትህን በመከተል ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ምሕረትን አልፈለግንም።
|
|
\v 14 አምላካችን እግዚአብሔር በሚያደርገው ሁሉ ጻድቅ ነውና፣ በእኛ ላይ እግዚአብሔር ጥፋት ከማምጣት አልተመለሰም፣ እኛም አልታዘዝነውም።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 15 አሁንም ሕዝብህን ከግብፅ ምድር በብርቱ እጅ ያወጣህ፣ እስከዚህም ቀን ድረስ ስምህ እንዲታወቅ ያደረግህ፤ ጌታ አምላካችን ሆይ፤ ኃጢአት ሠርተና፣ አንተንም በድለናል።
|
|
\v 16 ጌታ ሆይ እንዳደረግኸው የጽድቅ ሥራህ ሁሉ፣ ከከተማህ ከኢየሩሳሌም፣ ከቅዱሱም ተራራህ ቁጣህን መልስ፣ በእኛ ኃጢአትና በአባቶቻችን በደል ምክንያት ኢየሩሳሌምና ህዝብህ በዙሪያችን ባሉት ዘንድ መሣለቂያ ሆነዋል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 17 አሁንም አምላካችን ሆይ፣ የአገልጋይህን ጸሎትና ልመና ስማ። ጌታ ሆይ፤ ስለ ስምህ ስትል ፊትህን ወደፈረሰው መቅደስ መልስ።
|
|
\v 18 አምላክ ሆይ፤ ጆሮህን አዘንብለህ ስማ፣ ዐይንህን ገልጠህ መጥፋታችንንና ስምህ የተጠራበትን ከተማ ተመልከት። ልመናችንን የምናቀርበው ስለ ጽድቃችን ሳይሆን፣ ስለ ታላቅ ምሕረትህ ነው።
|
|
\v 19 ጌታ ሆይ፣ አድምጥ! ጌታ ሆይ፤ ይቅር በል! ጌታ ሆይ፤ ስማ! አድርግም፤ ስምህ በከተማንህና በሕዝብህ ላይ ተጠርቶአልና አምላኬ ሆይ፣ ስለ ስምህ ስትል አትዘግይ።”
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 20 እኔም እየተናገርሁና እየጸለይሁ፣ የራሴንና የሕዝቤን የእስራኤልን ኃጢአት እየተናዘዝሁ፣ ስለ ቅዱስ ተራራውም እግዚአብሔር አምላኬን እየለመንህ
|
|
\v 21 እየጸለይሁም ሳለሁ፣ በመጀመሪያው ራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል፣ በሠርክ መሥዋዕት ጊዜ በፍጥነት እየበረረ ወደ እኔ መጣ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 22 እርሱም እንዲህ ብሎ አስረዳኝ፤ “ዳንኤል ሆይ፣ አሁን ጥበብንና ማስተዋልን ልሰጥህ መጥቻለሁ
|
|
\v 23 አንተ እጅግ የተወደድህ ስለሆንህ፣ ገና መጸለይ ስትጀምር መልስ ተሰጥቶአል፣ አኔም ይህን ልነግርህ መጣሁ። ስለዚህ መልእክቱን ልብ በል፤ ራእዩንም አስተውል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 24 ዐመፃን ለማስቆም፣ ኃጢአትን ለማስወገድ፣ በደልን ለማስተሰረይ፣ ዘላለማዊ ጽድቅን ለማምጣት፣ ራእይንና ትንቢትን ለማተምና እጅግ ቅዱስ የሆነውን ለመቀባት ስለ ሕዝብህና ስለ ተቀደሰችው ከተማህ ሰባ ሱባዔ ታውጇል።
|
|
\v 25 ይህንን ዕወቅ አስተውለውም፤ ኢየሩሳሌምን ለማደስና ለመጠገን ዐዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ገዢው መሲሕ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስልሳ ሁለት ሱባዔ ይህናል። ኢየሩሳሌም ከጎዳናዎቿና ከቅጥሮቿ ጋር ትታደሳለች፤ ይህ የሚሆነው ግን በመከራ ጊዜ ነው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 26 ከሥልሳ ሁለት ሱባዔ በኋላ መሲሑ ይገደላል፤ ምንም አይቀረውም። የሚመጣው አለቃ ሰዎችም ኢየሩሳሌምንና ቤተ መቅደሱን ይመደስሳል። ፍጻሜውም እንደ ጎርፍ ይመጣል፤ ጦርነት እስከ መጨረሻው ይቀጥላል፤ ጥፋትም ታውጇል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 27 አለቃው ከብዙዎች ጋር ለአንድ ሱባዔ ቃል ኪዳኑን ያጸናል፤ በሱባዔውም እኩሌታ መሥዋዕትና ቁርባን ማቅረብን ያስቀራል። በርኵሰቱ ጫፍ ላይ ጥፋቱን የሚፈጽመው ይገለጣል። የታወጀው ፍርድ ጥፋትን በሚያመጣው ላይ የሚፈስ ይሆናል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 10
|
|
\p
|
|
\v 1
|
|
የፋርስ ንጉስ ቂሮስ በነገሰ በሦስተኛው ዓመት ብልጣሶር ለተባለው ዳንኤል ራዕይ ታየው መልዕክቱ እውነት ነው፤ ስለ ታላቅ ጦርነትም የሚገልፅ ነበር፡፡ መልእክቱንም ይገነዘብ ዘንድ በራዕዩ ማስተዋል ተሰጠው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 2 በዚያ ጊዜ እኔ ዳንኤል ለሦስት ሳምንት አለቀስኩ፤
|
|
\v 3 ሦስቱም ሳምንት እስኪፈፀም ድረስ ጥሩ ምግብ አልበላሁም፤ ስጋም ሆነ የወይን ጠጅ ወደ አፌ አልገባም፤ ቅባትም አልተቀባሁም፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 4 በመጀመሪያው ወር አያ አራተኛው ቀን፤ በታላቁ በጤግሮስ ወንዝ ዳር ቆሜ፤
|
|
\v 5 ቀና ብዬ ስመለከት፣ በፊቴ በፍታ የለበሰ እና በወገቡም ላይ ምርጥ የወርቅ ቀበቶ የታጠቀ አንድ ሰው አየሁ፡፡
|
|
\v 6 አካሉ እንደ እንቁ፣ ፊቱ እንደ መብረቅ፣ ዐይኖቹ እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹ እንደ ጋለ ናስ የሚያብረቀርቁ ድምፁም እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 ራዕዩን ያየሁት እኔ ዳንኤል ብቻ ነበርሁ፤ ከእኔ ጋር የነበሩት ሰዎች አላዩም፤ ነገር ግን ታላቅ ፍርሃት ስለ ወደቀባቸው ሸሽተው ተደበቁ፡፡
|
|
\v 8 ስለዚህ ይህን ታላቅ ራዕይ እያየሁ ብቻዬን ቀረሁ፤ ምንም ጉልበት አልነበረኝም፤ መልኬ እጅጉን ገረጣ፤ ኃይልም አጣሁ፡፡
|
|
\v 9 ከዚያም የቃሉን ድምፅ ሰማሁ፤ የቃሉንም ድምፅ በሰማሁ ጊዜ፣ በግንባሬ በምድር ላይ ተደፍቼ በከባዱ እንቅልፍ ተኛሁ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 10 እነሆም አንድ እጅ ዳሰሰኝ፤ እየተንቀጠቀጥሁም በእጄና በጉልበቴ አቆመኝ፤
|
|
\v 11 እርሱም፤ “ እጅግ የተወደድህ ዳንኤል ሁይ፣ አሁን ወደ አንተ ተልኬአለሁና የምነግርህን አስተውል፤ ቀጥ ብለህም ቁም አለኝ፡፡ ይህን ሲለኝም፤ እየተንቀጠቀጥሁ ተነስቼ ቆምሁ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 12 ደግሞም እንዲ አለኝ፤ “ዳንኤል ሁይ፣ አትፍራ ማስተዋልን ለማግኘትና በአምላክህም ፊት ራስህን ለማዋረድ ከወሰንክበት ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ ቃልህ ተሰምቷል፤ እኔም የቃልህን መልስ ይዤ መጥቻለሁ፡፡
|
|
\v 13 ነገር ግን የፋርስ መንግስት አለቃ ሃያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ የሆነው ሚካኤል ሊረዳኝ ወጣ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 14 ራዕዩ ሊፈፀም ገና ብዙ ዘመን ስለሚቀረው ወደፊት በህዝብህ ላይ የሚሆነውን ልገልፅልህ አሁን ወደአንተ መጥቻለሁ፡፡”
|
|
\v 15 ይህን እየተናገረኝ ሳለ፣ ፊቴን ወደ ምድር አቀረቀርሁ፣ የምናገረውንም አጣሁ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 16 ከዛም የሰው ልጅ የሚመስል ከንፈሮቼን ዳሰሰ፣ እኔም አፌን ከፈትኩ፣ መናገርም ጀመርኩ፤ በፊቴ የነበረውንም እንዲህ አልኩት፤ “ ጌታዬ ሆዬ ከራዕዩ የተነሳ ተሰቃይቻለሁ ሃይልም አጣሁ፤
|
|
\v 17 ጉልቤቴ ከዳኝ፤ መተንፈስም አቅቶኛል፣ እኔ አገልጋይህ ከአንተ ጋር መነጋገር እንዴት እችላለሁ?”
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 18 እንደገናም ሰው የሚመስለው ዳሰሰኝ አበረታኝም፡፡
|
|
\v 19 እርሱም፤ “እጅግ የተወደድህ ሰው ሆይ፤ አትፍራ፤ ሰላም ላንተ ይሁን፤ በርታ፤ ፅና” አለኝ፡፡ እየተናገረኝም ሳለ፣ በረታሁና፣ “ጌታዬ ሆይ፤ አበረትተኸኛልና ተናገር” አልሁት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 20 እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ለምን ወደ አንተ እንደ መጣሁ ታውቃለህ? የፋርስን መንግሥት ለመውጋት እመለሳለሁ፤ እኔም ስሄድ የግሪክ አለቃ ይመጣል።
|
|
\v 21 አስቀድሜ ግን በእውነት መጽሐፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ ከእነዚህ አለቆች ጋር ለመዋጋት ከአለቃችሁ ከሚካኤል በስተቀር የሚረዳኝ የለም።
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 11
|
|
\p
|
|
\v 1 እኔም፣ ሜዶናዊ ዳርዮስ በነገሠ በመጀመሪው ዓመት እርሱን ለማገዝና ለማበርታት በአጠገቡ ቆሜ ነበር፡፡
|
|
\v 2 አሁንም እውነቱን እነግርሃለሁ፤ እነሆ ሦስት ሌሎች ነገስታት በፋርስ ይነሳሉ፤ አልተኛውም ከሌሎቹ ሁሉ ይልቅ እጅግ ባለጠጋ ይሆናል፡፡ በባለጠግነቱም እጅግ በበረታ ጊዜ ሌላውን ሁሉ አሳድሞ በግሪክ መንግስት ላይ ያስነሣል፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 ከዚያም በታላቅ ኃይል የሚገዛና የወደደውንም ሁሉ የሚያደርግ ሃይል ንጉስ ይነሣል፡፡
|
|
\v 4 በኃይሉ እየገነነ ሳለም፣ መንግስቱ ይፈርሳል፤ ወደ አራቱ የሰማይ ነፍሳትም ይከፋፈላል፡፡ መንግስቱ ተወስዶ ለሌሎች ስለሚሰጥ ለዘሩ አይተላለፉም፤ ኃይሉም እንደ መጀመሪያው አይሆንም
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 5 የደቡብ ንጉስ ይበረታል፤ ነገር ግን ከጦር አዛዦቹ አንዱ ከእርሱ የበለጠ የበረታ ይሆናል፣ ግዛቱም ታላቅ ይሆናል፡፡
|
|
\v 6 ከጥቂት ዓመታት በኋላም አመቺ ጊዜ ሲያገኙ አንድነት ይፈጥራሉ፡፡ የደቡብ ንጉስ ሴት ልጅ ስምምነት ለማድረግ ወደ ሰሜኑ ንጉስ ትሄዳለች፤ ነገር ግን ኃይሏን ይዞ መቆየት አትችልም፤ በእነዚያ ቀናት እርሷ ከቤተ መንግስት አጃቢቿ፣ ከአባቷና ከደጋፊዎቿ ጋር አልፋ ትሰጣለች፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 ከዘመዶቿ አንዱ ስፍራዋን ሊይዝ ይነሳል፤ የሰሜኑን ንጉስ ሰራዊት ይወጋል፤ ምሽጎቹንም ጥሶ ይገባል፤ ከእነርሱም ጋር ተዋግቶ ድል ያደርጋል፡፡
|
|
\v 8 አማልክታቸውን፤ የብረት ምስሎቻቸውን፣ ከክብርና ከወርቅ የተሰሩ የክብሩ ዕቃዎቻቸውን ይማርካሉ፤ ወደ ግብፅም ይወስዳል፡፡ ለጥቂት ዓመታም ከሰሜኑ ንጉስ ጋር ከመዋጋት ይቆጠባል፡፡
|
|
\v 9 የሰሜኑም ንጉስ፣ የደቡቡን ንጉስ ግዛት ይወራል፤ ነገር ግን አፈግፍጎ ወደ ገዛ አገሩ ይመለሳል፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 10 ወንዶች ልጆቹም ለጦርነት ይዘጋጃሉ፤ እስከ ጠላት ምሽግ ደርሶ የሚዋጋና ሊቋቋሙት እንደማይቻል ጎርፍ የሚጠራርግ ታላቅ ሰራዊት ይሰበስባሉ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 11 ከዚያም የደቡቡ ንጉስ በቁጣ ወጥቶ የሰሜኑን ንጉስ ይወጋል፡፡ የሰሜኑ ንጉስ ታላቅ ሰራዊት ቢያሰባስብም ሰራዊቱ ለደቡብ ንጉስ አልፎ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
|
|
\v 12 ሰራዊቱ በሚማረክበት ጊዜ ልቡ በትዕቢት ይሞላል፤ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችንም ይገድላል፤ ነገር ግን በድል አድራጊነቱ አይጸናም፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 13 የሰሜን ንጉስ ከመጀመሪው የሚበልጥ ታላቅ ሰራዊት ያሰባስባል፤ ከብዙ አመታ በኋላ በትጥቅ እጅግ ከተደራጀ ታላቅ ሰራዊት ጋር ተመልሶ ይመጣል፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 14 በዚያም ዘመን ብዙዎች በደቡብ ንጉስ ላይ ይነሣሉ፡፡ ራዕዩ ይፈጸም ዘንድ ከህዝብህ መካከል ዐመፀኛ የሆኑ ሰዎች ይከሣሉ፤ ነገር ግን ተሰነካክለው ይወድቃሉ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 15 የሰሜኑም ንጉስ መጥቶ የዐፈር ድልድል ይክባል፤ የተመሸገእውንም ከተማ ይይዛል፡፡ የደቡቡ ሰራዊትም ለመቋቋም ኋይል ያጣል፤ የተመረጡት ተዋጊዎቻቸው እንኳ ፀንተው መዋጋት አይችሉም፡፡
|
|
\v 16 ነገር ግን የሰሜኑ ንጉስ በደቡቡ ንጉስ ላይ ደስ ያሰኘውን ያደርጋል፤ ማንም ሊቋቋመው አይችልም፡፡ በመልካሚቱ ምድር ላይ ይገዛል እርሷን ለማይፋትም ኋይል ይኖረዋል፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 17 የሰሜኑ መንግስት ያለውን ሠራዊት ሁሉ ይዞ ለመምጣት ይወስናል፤ ከደቡቡም ንጉስ ጋር ይስማል፣ የደቡቡንም መንግስት ለመጣል ሴት ልጁን ይድርለታል፤ ይሁን እንጂ ዕቅዱ አይሳካለትም፤ ያሰበውም ነገር አይጠቅመውም፡፡
|
|
\v 18 ከዚህም በኋላ በባሕር ጠረፍ ወዳሉት አገሮች ፊቱን በመመለስ ብዙዎቹን ይይዛል፤ ነገር ግን አንድ አዛዥ ትዕቢቱን ያከሸፍበታል፤ በራሱም ላይ ይመልስበታል፡፡
|
|
\v 19 በገዛ አገሩ ወዳሉት ምሽጎችም ፊቱን ይመልሳል፤ ነገር ግን ተሰናክሎ ይወድቃል፤ ደግሞም አይታይም፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 20 በእርሱ ቦታ የሚተካውም የመንግስቱን ክብር ለማስጠበቅ የሚውል ግብር እንዲከፍል የሚያስገድድ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ በቁጣ ወይም በጦርነት ሳይሆን በጥቂት ዓመታ ውስጥ ይደመሰሳል፡፡
|
|
\v 21 በእርሱም ፋንታ የተናቀ ሰው የነግሣል፤ ለእርሱም ሕዝቡ ንጉሳዊ ክር አይሰጡትም፣ በቀስታ ይገባና በተንኮል መንግስቱን ይዛል፡፡
|
|
\v 22 ከፊቱ የሚቆመው ሰራዊት እንደ ጎርፍ ተጠራርጎ ይወሰዳል፡፡ ሰራዊቱና የቃል ኪዳኑም አለቃ ሳይቀር ይደመሰሳሉ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 23 ከእርሱ ጋር ስምምነት ከተደረገ በኋላ የማታለል ስራውን ይሰራል፤ ከጥቂት ሰዎችም ጋር በብርታት እየጨመረ ይሄዳል
|
|
\v 24 የበለጸጉትን ክፍለ አገሮች በሰላ ሳሉ በድንገት ይወሯቸዋል፤ አባቶቹም ሆኑ አያቶቹ ያላደረጉትን ነገር ያደርጋሉ፤ ብዝበዛውን ምርኮውንና የተገኘውን ሀብት ሁሉ ለተከታዮቹ ያካሏቸዋል፤ ምሽጎችን ለመጣል ያሤራል፤ ይህን የሚያደርገውም ለጥቂት ጊዜ ብቻ ነው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 25 “ታላቅ ሠራዊት አደራጅቶ ኀይሉንና ብርታቱን በደቡብ ንጉስ ላይ ይነሳሳል፤ የደቡብ ንጉሱም ብርቱ የሆነ ኃይል ሰራዊት ይዞ ጦርነትን ያውጃል፤ ከር ግን ከተዶለተበት ሴራ የተነሳ መቋቋም አይእል፣፡፡
|
|
\v 26 ከንጉስ ማዕድ አብረውት ሲበሉ የነበሩት፤ ብዙዎቹም በጦርነት ይገደላሉ፡፡
|
|
\v 27 አንዳቸው በሌላኛው ላይ ልባቸው ወደ ክፋት ያዘነበለው ሁለት ነገስታት፣ በአንድ ገበታ አብረው ይቀመጣሌ፤ እርስ በእርሳቸውም በከንቱ ውሸት ይነጋገራሉ፤ ምክንያቱም ፍፃሜ የሚሆነው በተወሰነው ጊዜ ነው
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 28 የሰሜን ንጉስ ብዙ ሃብት ይዞ ወደ ሀዛ አገሩ ይመለሳ፤ ነገር ግ ልቡ በተቀደሰው ኪዳን ላይ ይነሣሣል፤ የወደደውን ያደርጋል፣ ከዚያም ወደ ገዛ አገሩ ይመለሳል፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 29 በተወሰነው ጊዜ ይመለስና ደቡቡን እንደ ገና ይወርራል፡፡ በዚህ ጊዜ ግን ውጤቱ ከበፊቱ የተለየ ይሆናል፡፡
|
|
\v 30 የኪቲም መርከቦች ይቃወሙታል፤ ልቡም ይሸበራል፡፡ ወደ ኋላም ይመለሳል፤ ቁጣውን በተቀደሰው ኪዳን ላይ ይወርዳል፤ ተመልሶም የተቀደሰውን ኪዳ የተዉትን ይንከባከባል፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 31 የጦ ሠራዊቶቹም ቤተ መቅደሱንና ቅጥሩን ያረክሳሉ፤ የዘውትሩንም መስዋዕት ያስቀራሉ፤ በዚያም ፍፁም ጥፋትን የሚያመጣውን የጥፋት ርኩሰት ይተክላሉ፤
|
|
\v 32 ኪዳኑን የሚተላለፉትን በማታለል ይስታል ይረክስባቸዋልም፤ አምላካቸውን የሚያውቁ ሕዝብ ግን ደንተው ይቃወሙታል፤ ርምጃም ይወስዳሉ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 33 “ለጊዜው በሰይፍ ቢወድቁም፣ ቢቃጠሉም፣ ቢማረኩና ቢዘረፉም፣ ጥበበኛ የሆኑ ሰዎች ብዙዎችን ያስተምራሉ፡፡
|
|
\v 34 በሚወድቁበት ጊዜ መጠነኛ ርዳታ ይገኛሉ፤ እውነተኛ ያልሆኑ ብዙ ሰዎችም ይተባበሯቸዋል፡፡
|
|
\v 35 ጥበበኛ ከሆኑ ሰዎች አንዳንዶቹ ይሰናከላሉ፣ ይህም እስከ ፍፃሜ ዘመን ድረስ የጠሩ፣ የነጠሩና እንከን የሌለባቸው ይሆን ዘንድ ነው፤ የተወሰነው ጊዜ ገና አልደረሰምና፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 36 ንጉሱ እንዳለው ያደርጋል፤ ከአማልክት ሁሉ በላይ ራሱን እጅግ ከፍ በማድረግ በአማልክት አማላክ ላይ አስገራሚ ነገሮችን ይናገራል፤ የቁጣውም ዘመን እስኪፈጸም ይሳካለታል፤ የተወሰነ ነገር ሁሉ መሆን አለበትና።
|
|
\v 37 ሴቶች ለሚወዱትም ሆነ ለአባቶቹ አምላክ ትክብርን አይሰጥም፤ ማንኛውንም አምላክ አያከብርም፤ ነገር ግን ራሱን ከእነዚህ ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርጋል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 38 በእነርሱም ምትክ የምሽጎችን አምላክ ያደብራል፤ አባቶቹ የማያውቁትን አምላክ በወርቅ፣ በብር፣ በከበሩ ድንጋዮችና በውድ ስጦታዎች ያከብራል።
|
|
\v 39 በባዕድ አምላክ ርዳታ ጽኑ ምሽቶችን ይወጋል፤ ለእርሱ የሚገዙትን በእጅጉ ያከበራቸዋል፤ በብዙ ሕዝብ ልያ ገዦች ያደርጋቸዋል፤ ምድሩንም በዋጋ ያከፋፍላቸዋል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 40 “በመጨረሻው ዘመን የደቡብ ንጉሥም ጦርነት ያውጅበታል፤ የሰሜን ንጉሥም በፈረሰኞችና በሰርጎች በብዙ መርከቦችም እንደ ማዕበል ይመጣበታል፤ ብዙ አገሮችን ይወራል፤ እንደ ጎርም እየጠራረገ በመካከላቸው ያልፋል።
|
|
\v 41 የከበረችውንም ምድር ይወራል፤ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩእስራኤላውያንም ተሰነካክለው ይወድቃሉ፣ ነገር ግን ከኤዶም፣ ከሞዓብ ብዙ ሰዎች እንዲሁም ከአሞን የቀሩት ሕዝብ ከእጁ ያመልጣሉ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 42 ሥልጣኑን በብዙ አገሮች ላይ ያንሰራፋል ግብፅም አታመልጥ።
|
|
\v 43 የወርቅና የብር ክምችትን፣ እንዲሁም የግብፅን ሀብት ሁሉ በቁጥጥሩ ሥር ያደርጋል፤ የሊቢያና የኢትዮጵያ ሰዎችም ይገዙታል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 44 ነገር ግን ከምሥራቅና ከሰሜን የሚመጣ ወሬ ያስደነግጠዋል፤ ብዙዎችንም ለማጥፋትና ለመደምሰስ በታላቅ ቁጣ ይወጣል።
|
|
\v 45 ንጉሣው ድንኳኖቹን በባሕሮች መካከል ውብ በሆነው ቅዱስ ተራራ ላይ ይተክላል፤ ይሁን እንጂ ወደ ፍጻሜው ይመጣል፤ ማንም አይረዳውም።
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 12
|
|
\p
|
|
\v 1 በዚያን ዘመን ስለ ሕዝብህ የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል። መንግሥታት ከተመሠረቱበት ጊዜ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ ታይቶ የማይታወቅ ታላቅ የመከራ ጊዜ ይሆናል። ነገር ግን በዚያን ጊዜ ስማቸው በመጽሐፉ ተጾጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ ይድናሉ።
|
|
\v 2 በምድር አፈር ውስጥ ካንቀላፉት ብዙዎች ይነቃሉ፤ አንዳንዶቹ ለዘላለም ሕይወት፣ ሌሎቹም ለውርደትና ለዘላለም ጉስቁልና ይነሣሉ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 ጥበበኞች እንደ ሰማይ ጸዳል፣ ብዙዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ክዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ።
|
|
\v 4 ዳንኤል ሆይ፣ አንተ ግን፣ እስከ ፍጻሜው ዘመን ድረስ የመጽሐፉን ቃል ዝጋ አትመውም። ብዙዎች ወዲያ ወዲህ ይራወጣሉ ዕውቀትም ይበዛል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 5 እኔም ዳንኤል ተመለከትሁ፤ እነሆ ከፊት ለፊቴ ሌሎች ሁለት ቆመው ነበር፤ አንዱ ከወንዙ በዚህኛው ዳር፣ ሌላው ደግሞ ከወንዙ በዚያኛው ዳር።
|
|
\v 6 ከእነርሱም አንዱ፣ ከወንዙ በላይ የነበረውንና በፍታ የለበሰውን ሰው፣ እነዚህ አስደናቂ ነገሮች ሊፈጽሙ ምን ያህል ጊዜ ይቀራል?” አለው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 ከወንዙ ውሃ በላይ የነበረው በፍታ የለበሰው ሰው፣ ቀኝ እጁንና ግራ እጁን ወደ ሰማይ አንሥቶ፣ “ለዘመን፣ ለዘመናት፣ ለዘምንም እኩሌታ ማለትም ለሦስት ዓመት ተኩል ይሆናል፤ የተቀደሰው ሕዝብ ኃይል መስበር ሲያከትም፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ይፈጸማሉ” ብሎ ለዘላልም በሚኖረው በእርሱ ሲምል ሰማሁ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 8 እኔም ሰማሁ፤ ነገር ግን አላስተዋልሁትም፤ ስለዚህ፣ ጌታዬ፣ የዚህ ሁሉ ፍጻሜ ምንድን ነው?” ብዬ ጠየቅሁ።
|
|
\v 9 እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ቃሉ እስከ ፍጻሜው ዘመን ድረስ የተዘጋና የታተመ ስለሆነ ሂድ፤
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 10 ብዙዎቹ ይነጻሉ፤ ይጠራሉ እንከን አልባምይሆናሉ፤ ክፉዎች ግን በክፋታቸው ይድናሉ፤ ከክፉዎች አንዳቸውም አያስተውሉም፣ ጠቢባን ግን ያስተውላሉ።
|
|
\v 11 “የዘወትሩ መሥዋዕት ከተቋረጠበትና ፍጹም ጥፋት የሚያመጣው አስጸያፊ ርኵሰት ከተተከለበት ጊዜ ጀምሮ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ቀን ይሆናል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 12 የሚታገሥና እስከ አንድ ሺህ ሦስት መቶ ሰለሳ አምስት ቀን ፍጻሜ የሚደርስ የተባረከ ነው።
|
|
\v 13 “አንተ ግን እስከ ፍጻሜ ድረስ ሂድ፣ ታርፋለህ፤ በቀኖች መጨረሻም ተንሥተህ የተመደበልህን ርስት ትቀበላለህ።”
|