am_ulb/02-EXO.usfm

2243 lines
244 KiB
Plaintext
Raw Blame History

This file contains ambiguous Unicode characters

This file contains Unicode characters that might be confused with other characters. If you think that this is intentional, you can safely ignore this warning. Use the Escape button to reveal them.

\id EXO
\ide UTF-8
\h ዘጸአት
\toc1 ዘጸአት
\toc2 ዘጸአት
\toc3 exo
\mt ዘጸአት
\s5
\c 1
\p
\v 1 እያንዳንዳቸው ቤተ ሰባቸውን በመያዝ፣ ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት የእስራኤል ልጆች ስሞች እነዚህ ናቸው፦
\v 2 ሮሜል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣
\v 3 ይሳኮር፣ ዛብሎን፣ ብንያም፣
\v 4 ዳን፣ ንፍታሌም፣ ጋድና አሴር።
\v 5 ከያዕቆብ ዘር የተገኙት ሰዎች ሰባ ነበር። ዮሴፍ ቀድሞውኑ በግብፅ ውስጥ ነበረ።
\s5
\v 6 ከጊዜ በኋላ ዮሴፍ፣ ወንድሞቹ ሁሉና ያ ትውልድ በሙሉ ሞቱ።
\v 7 ነገር ግን እስራኤላውያን እየተዋለዱ ሄዱ፤ ቊጥራቸውም እጅግ ጨምሮ በጣም ብርቱዎች ሆኑ፤ ምድሪቱንም ሞሏት።
\s5
\v 8 በግብፅ ስለ ዮሴፍ የማያውቅ ዐዲስ ንጉሥ ተነሣ።
\v 9 ለሕዝቡም እንደዚህ አለ፤ “እስራኤላውያንን ተመልከቷቸው፤ ከእኛ ይልቅ በቍጥር በዝተዋል፤ እጅግም በርትተዋል።
\v 10 በቍጥር እየበዙ እንዳይሄዱ፣ ጦርነት ቢነሣም ከጠላቶቻችን ጋር ዐብረው እንዳይወጉንና ምድሪቱ ጥለው እንዳይሄዱ ኑ በዘዴ እርምጃ እንውሰድባቸው።”
\s5
\v 11 በከባድ ሥራ የሚያስጨንቋቸው አሠሪ አለቆችን በላያቸው ሾሙ። እስራኤላውያን ለፈርዖን ፊቶምና ራምሴ የተባሉ የንብረት ማከማቻ ከተሞችን ሠሩ።
\v 12 ግን ግብፃውያን እስራኤላውያንን ባስጨነቋቸው ቊጥር፣ እስራኤላውያን በቊጥር እየበዙና በምድሪቱ እየተስፋፉ ሄዱ። ስለዚህ ግብፃውያን እስራኤላውያን መፍራት ጀመሩ።
\s5
\v 13 ግብፃውያን እስራኤላውያንን በጥብቅ እንዲሠሩ አደረጓቸው።
\v 14 በሸክላ ሥራና ጭቃ በማስቦካት፣ በዕርሻ ውስጥም ሁሉን ዐይነት ከባድ ሥራ በማሠራት አስመረሯቸው (ሕይወታቸውን መራራ አደረጉባቸው) ። የሚጠበቅባቸው ሥራ ሁሉ ከባድ ነበር።
\s5
\v 15 ከዚያም በኋላ የግብፅ ንጉሥ ሲፓራና ፉሐ የሚባሉ ዕብራውያት አዋላጆችን እንዲህ አላቸው፤
\v 16 “ዕብራውያት ሴቶችን በማማጫው ላይ ስታዋልዱ፣ በሚወልዱበት ጊዜ ተመልከቱ። ወንድ ከተወለደ ግደሉት፤ ሴት ከሆነች ግን በሕይወት ትኑር።”
\v 17 ነገር ግን አዋላጆቹ እግዚአብሔርን ፈሩ፣ ንጉሡ ያዘዛቸውንም አልፈጸኩም፤ ትእዛዙን በመፈጸም ፈንታ ሕፃናት ወንዶችን በሕይወት እንዲኖሩ አደረጉ።
\s5
\v 18 የግብፅ ንጉሥ አዋላጆቹን ጠርቶ፣ “ለምን ይህን አደረጋችሁ፣ ሕፃናት ወንዶችንስ ለምን አልገደላችኋቸውም?” አላቸው።
\v 19 አዋላጆቹም ለፈርዖን፣ “ዕብራውያት ሴቶች እንደ ግብፃውያት ሴቶች አይደሉም። እነርሱ ብርቱዎች ናቸው፣ የሚወልዱትም አዋላጅ ወደ እነርሱ ከመምጣቱ በፊት ነው” በማለት መለሱለት፥
\s5
\v 20 እግዚአብሔር እነዚህን አዋላጆች ጠበቃቸው። ሕዝቡ በቍጥር በዙ፣ እጅግ ብርቱዎችም ሆኑ።
\v 21 አዋላጆቹ እግዚአብሔርን ስለ ፈሩ፣ እግዚአብሔር ቤተ ሰቦችን ሰጣቸው።
\v 22 ፈርዖን፣ “የተወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ ወንዝ ውስጥ ጣሉ፣ ሴትን ልጅ ግን በሕይወት እንድትኖር ታደርጋላችሁ” በማለት ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ።
\s5
\c 2
\p
\v 1 ከሌዊ ወገን የሆነ አንድ ሰው ሌዋዊት ሴት አገባ፡፡
\v 2 ሴትዮዋ ፀነሰች ወንድ ልጅም ወለደች፡፡ ሕፃኑ መልከ መልካም መሆኑን ስታይ፣ ሦስት ወር ሸሸገችው፡፡
\s5
\v 3 ከዚያ በላይ ልትሸሽገው ባልቻለች ጊዜ፣ የደንገል ቅርጫት ወስዳ በዝፍትና በቅጥራን ለቀለቀችው፡፡ ከዚያም ልጁን በውስጡ አስተኝታ ውሃው ውስጥ በቄጠማው መካከል በወንዙ ዳርቻ አስቀመጠችው፡፡
\v 4 የሚያጋጥመውን ለማየት የሕፃኑ እኅት በርቀት ቆማ ነበር፡፡
\s5
\v 5 ጠባቂዎቿ በወንዙ ዳር እየሄዱ ሳለ፣ የፈርዖን ልጅ በወንዙ ለመታጠብ ወረደች፡፡ ልዕቲቱ ቅርጫቱን በቄጠማዎች መካከል አየችው፡፡ ቅርጫቱን እንዲያመጣላት ጠባቂዋን ላከች፡፡
\v 6 ቅርጫቱን ስትከፍተው፣ ሕፃኑን አየች፡፡ እነሆ፣ ሕፃኑ ያለቅስ ነበር፡፡ ራራችለትና፣ «ይህ በእርግጥ ከዕብራውያን ልጆች አንዱ ነው» አለች፡፡
\s5
\v 7 ከዚያም በኋላ የሕፃኑን እኅት የፈርዖንን ልጅ፣ «ልሂድና ሕፃኑን የምታሳድግልሽ ዕብራዊት ሴት ልፈልግልሽ?» አለቻት፡፡
\v 8 የፈርዖንም ልጅ «ሂጂ» አለቻት፡፡ ወጣቷም ልጅ ሄዳ የሕፃኑን እናት አመጣች፡፡
\s5
\v 9 የፈርዖን ልጅ የሕፃኑን እናት፣ «ይህ ሕፃን ውሰጅና አሳድጊልኝ፤ ደሞዝ እከፍልሻለሁ» አለቻት፡፡ ሴትዮዋም ሕፃኑን ወስዳ አሳደገችው፡፡
\v 10 ሕፃኑ ባደገ ጊዜም ወደ ፈርዖን ልጅ አመጣችው፤ የልዕልቲቱም ልጅ ሆነ፡፡ «ከውሃ አውጥቼዋለሁና» ብላም ስሙን ሙሴ አለችው፡፡
\s5
\v 11 ሙሴ ባደገ ጊዜ ወደ ወገኖቹ ሄዶ የሚሠሩትን ከባድ ሥራ ተመለከተ፡፡ ከገዛ ወገኖቹ መካከል አንዱን ዕብራዊ አንድ ግብፃዊ ሲደበድበው አየ፡፡
\v 12 ግራና ቀኙን ተመልክቶ ማንም አለመኖሩን ሲያረጋግጥ፣ ግብፃዊውን ገድሎ በአሸዋ ውስጥ ደበቀው፡፡
\s5
\v 13 ቀን ሙሴ ወደ ውጭ ወጣ፤ እነሆም ሁለት ዕብራውያን ወንዶች እየተጣሉ ነበር፡፡በደለኛ የነበረውን ሰውየ፣ «ባልንጀራህ ለምን ትደበድበዋለህ?» አለው፡፡
\v 14 ሰውየው ግን፣ «አንተን በእኛ ላይ አለቃና ዳኛ ማን አደረገህ? ያን ግብፃዊ እንድ ገደልኸው እኔንም ልትገድለኝ ታስባለህ?» አለ፡፡ ሙሴም ፈራና፣ «ያደረግሁት በሌሎች ሰዎች ዘንድ በእርግጥ ታውቋል» አለ፡፡
\s5
\v 15 ስለ ጉዳዩ ሲሰማ ሙሴን ሊገድለው ፈለገ፡፡ ነገር ግን ከፈርዖን ሸሽቶ በምድያም አገር ኖረ፡፡ እዚያም በአንድ የውሀ ጉድጓድ አጠገብ ተቀመጠ፡፡
\v 16 ካህን ሰባት ሴት ልጆች ነበሩት፡፡ እነርሱም ወደ ጉድጓዱ መጥተው ውሀ ቀዱ፣ የአባታቸውን መንጋ ለማጠጣትም ገንዳውን ሞሉት፡፡
\v 17 መጥተው ሊያባርሯቸው ሞከሩ፣ ነገር ግን ሙሴ ሄዶ ዐገዛቸው፡፡ መንጋቸውንም አጠጣላቸው፤
\s5
\v 18 ወደ አባታቸው ወደ ራጉኤል ሲሄዱም፣ አባታቸው፣ «ዛሬ እንዴት ቶሎ ወደ ቤት መጣችሁ?» አለ፡፡
\v 19 «አንድ ግብፃዊ ከእረኞች አዳነን፤ ውሀም ቀድቶ መንጋውን አጠጣልን» አሉ፡፡
\v 20 ልጆቹን፣ «ታዲያ የት አለ?» ሰውየውን ለምን ተዋችሁት? ምግብ ከእኛ ጋር እንዲበላ ጥሩት» አላቸው፡፡
\s5
\v 21 ሲፓራን እንዲያገባትም እንኳ ከሰጠው ሰውየ ጋር ለመኖር ሙሴ ተስማማ፡፡
\v 22 ወንድ ልጅ ወለደች፤ ሙሴም፣ «የባዕድ ምድር ኗሪ ነኝ» ሲልም ስሙን ጌርሳም አለው፡፡
\s5
\v 23 ከረጅም ጊዜ በኋላ፣ የግብፅ ንጉሥ ሞተ፡፡ እስራኤላውያን ከባርነት ሥራ የተነሣ አለቀሱ፣ ለርዳትም ጮኹ፤ ከባርነት ቀበራቸው የተነሣም ያሰሙት ጩኸት ወደ እግዚአብሔር ወጣ፡፡
\v 24 እግዚአብሔር ልቅሶአቸውን ሲሰማ ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር የገባውን ቃል ኪዳኑን ዐሰበ፡፡
\v 25 እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አየ፤ ሁኔታቸውንም ተረዳ፡፡
\s5
\c 3
\p
\v 1 ሙሴ የምድያምን ካህን፣ የዐማቱን የየቶርን በጎች ጠብቅ ነበር፡፡ በጎቹን ወደ ምድረ በዳው ዳርቻ ነድቶ ወደ እግዚአብሔር ተራራ ወደ ኮሬብ ደረሰ፡፡
\v 2 በዚያም የእግዚአብሔር መልአክ በቊጥቋጦ ውስጥ በእሳት ነበልባል ተገለጠለት፡፡ ሙሴ ተመለከተ፣ እነሆም ቊጥቋጦው እየተቀጣጠለ ነበር፤ ነገር ግን ቊጥቋጦው አልተቃጠለም፡፡
\v 3 ሙሴም፣ «ልቅረብና ቊጥቋጦው ለምን እንዳልተቃጠለ ይህን አስደናቂ ነገር ልይ» አለ፡፡
\s5
\v 4 ሊመለከት እንደ ቀረበ እግዚአብሔር ሲያየው፣ ከቊጥቋጦው ውስጥ ጠራው፤ «ሙሴ፣ ሙሴ» አለውመ፡፡ ሙሴም፣ «እነሆኝ» አለ፡፡
\v 5 እግዚአብሔር፣ «አትቅረብ! የቆምህበት ምድር ለእኔ ተቀድሶአልና ጫማህን አውልቅ» አለው፡፡
\v 6 ደግሞም፣ «እኔ የአባትህ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ ነኝ» አለው፡፡ ከዚያም በኋላ ሙሴ እግዚአብሔርን ማየት ስለ ፈራ ፊቱን ሸፈነ፡፡
\s5
\v 7 እንዲህ አለ፤ «በግብፅ የሚኖሩትን የሕዝቤን ሥቃይ በእርግጥ አይቻለሁ፡፡ አሠሪ አለቆቻቸው ከሚያደርሱባቸው ጭቈና የተነሣ ጩኸታቸውን ሰምቻለሁ፤ ስለ ሥቃያቸው ዐውቃለሁና፡፡
\v 8 ከግብፃውያን አገዛዝ ነጻ ላወጣቸውና ከዚያም ጋር አውጥቼ ማርና ወተት ወደምታፈሰው መልካምና ለም ወደሆነችው፤ ወደ ከነዓናውያን፣ ኬጢያውያን፣ አሞራውያንን፣ ፌርዛውያን፣ ኤውያውያንና ኢያቡሳውያን ምድር ላሰገባቸው ወርጃለሁ አለ፡፡
\s5
\v 9 የእስራል ሕዝብ ጩኸት ወደ እኔ ደርሶአል፡፡ ይልቁንም ግብፃውያን ያደረሱባቸውን ጭቈና አይቻለሁ፡፡
\v 10 ስለዚህ ሕዝቤን፣ እስራኤላውያንን ከግብፅ እንድታወጣ ወደ ፈርዖን እልክልሃለሁ፡፡»
\s5
\v 11 ግን፣ እግዚአብሔርን «ወደ ፈርዖን የምሄድና እስራኤላውያንን ከግብፅ የማወጣቸው እኔ ማን ነኝ?» አለው፡፡
\v 12 ሙሴን መልሶ፣ «እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፡፡ ይህ እኔ እንደ ላክሁህ ምልክት ይሆናል፡፡ ሕዝቡን ከግብፅ ስታወጣቸው፣ በዚህ ተራራ ላይ ታመልኩኛላችሁ» አለው፡፡
\s5
\v 13 ሙሴም እግዚአብሔርን፣ «ወደ እስራኤላውያን ስሄድና ‹የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ልኮኛል› ብዬ ስነግራቸው፣ እነርሱም፣ «ስሙ ማን ነው? ሲሉኝ ምን እነግራቸዋሉ? አለው፡፡
\v 14 እግዚአብሔርም ሙሴን፣ «እኔ ያለሁ የምኖርም ነኝ፡፡ ያለና የሚኖር ወደ እናንተ ልኮኛል ብለህ ለእስራኤላውያን ንገራቸው» አለው፡፡
\v 15 ደግሞም እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ አለ፤ እግዚአብሔር የአባቶቻችሁ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ ወደ እናንተ ልኮኛል፡፡ ስሜ ለዘለዓለም ይህ ነው፤ ለትውልዶች ሁሉ የታስበውም በዚህ ነው ብለህ ለእስራኤላውያን ንገራቸው፡፡»
\s5
\v 16 ሂድና የእስራኤልን ሽማግሌዎች ሰብስብ፤ እንዲህም ብለህ ንገራቸው፤ የአባቶቻችሁ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ለእኔ ተገለጠልኝ፤ እንዲህም አለኝ፣ «ጐብኝቻችኋለሁ፤ በግብፅ ውስጥ የደረሰባችሁንም አይቻለሁ፡፡
\v 17 በግብፅ ከደረሰባችሁ ጭቈና ነጻ ላወጣችሁና ማርና ወተት ወደምታፈሰው ወደ ከነዓናውያን፣ ወደ ኬጢያውያን፣ ወደ አሞራውያን፣ ወደ ፌርዛውያን፣ ወደኤዊያውያንና ወደ ኢያቡሳውያን ምድር ላገባችሁ ቃል ገብቻለሁ፡፡»
\v 18 ሽማግሌዎቹም ይሰሙሃል፡፡ አንተና የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ግብፅ ንጉሥ ሂዱና፣ የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ተገለጠልን፡፡ ስለዚህም ለአምላካችን ለእግዚአብሔር መሠዋት እንድንችል በምድረ በዳው ውስጥ የሦስት ቀን ጕዞ እንሂድ በሉት፡፡
\s5
\v 19 ነገር ግን የግብፅ ንጉሥ እጁ ካልተገደደ በቀር ለመሄድ እንደማይፈቅድላችሁ ዐውቃለሁ፡፡
\v 20 በመካከላቸው በማድረጋቸው ተአምራት ሁሉ ግብፃውያንን እመታቸዋለሁ፡፡ ከዚያ በኋላ፣ እንድትሄዱ ይፈቅድላችኋል፡፡
\v 21 ሕዝብ ከግብፃውያን ዘንድ መወደድን እንዲያገኝ አደርጋለሁ፣ ስለዚህ ስትወጡ፣ ባዶ እጃችሁን አትወጡም፡፡
\v 22 ሴት ከግብፃውያት ጎረቤቶቿና በጎረቤቶቿ ቤቶች ውስጥ ከምትኖር ማንኛውም ሴት የብርና የወርቅ ጌጣጌጦች፣ ልብስም እንዲሰጣት ትጠይቃለች፡፡ እነርሱንም በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁ ላይ ታደርጓቸዋላችሁ፡፡ ግብፃውያንን በዚህ መንገድ ትበዘብዟቸዋላችሁ፡፡
\s5
\c 4
\p
\v 1 ሙሴም መልሶ፣ «ባያምኑኝስ ወይም ባይሰሙኝ ነገር ግን በምትኩ፣ እግዚአብሔር አልተገለጠልህም» ቢሉኝስ?
\v 2 እግዚአብሔር ሙሴን፣ «በእጅህ ያለው ምንድን ነው?» አለው፡፡ ሙሴም «በትር» አለ፡፡
\v 3 እግዚአብሔር፣ «መሬት ላይ ጣለው» አለው፡፡ ሙሴም በትሩን መሬት ላይ ጣለው፤ በትሩም እባብ ሆነ፡፡ ሙሴ ከእባቡ ሸሸ፡፡
\s5
\v 4 እግዚአብሔር ሙሴን፣ «እጅህን ዘርግተህ የእባቡን ጅራት ያዝ» አለው፡፡ ሙሴም እጁን ዘረገና እባቡን ያዘው፡፡ እባቡ በእጁ ላይ እንደ ገና በትር ሆነ፡፡
\v 5 «ይህ የሆነው የአባቶቻቸው አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር የተገለጠልህ መሆኑን እነዲያምኑ ነው፡፡»
\s5
\v 6 ደግሞም እግዚአብሔር ሙሴን፣ «እጅህን በብትህ ውስጥ አግባ» አለው፡፡ እጁን ሲያወጣው እነሆ፣ እንደ በረዶ ነጽቶ ለምጽ ሆኖአል፡፡
\v 7 እግዚአብሔር፣ «እጅህን እንደ ገና በብብትህ ውስጥ አግባ» አለው፡፡ ሙሴም እጁን በብብቱ ውስጥ አገባ፣ ከብብቱ ሲወጣውም እንደ ሌላው ሰውነቱ ጤናማ ሆኖ አየው፡፡
\s5
\v 8 እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ «ባያምኑህ፣ የመጀመሪያውን የተአምር ምልክት ባይቀበሉ ወይም ባያምኑበት፣ ሁለተኛውን ያምናሉ፡፡
\v 9 እነዚህን ሁለት የተአምር ምልክቶች ባያምኑም እንኳ፣ ወይም ባይሰሙህ፣ ከወንዙ ጥቂት ውሀ ወስደህ በደረቁ መሬት ላይ አፍስሰው፡፡ ያፈሰስኸውም ውሀ በደረቁ መሬት ላይ ደም ይሆናል፡፡»
\s5
\v 10 እግዚአብሔርን፣ «ጌታ ሆይ፣ በፊትም፣ አንተ ለባሪያህ ከተናገርህ ወዲህም ርቱዕ አንደበት ያለኝ አይደለሁም፡፡ ኮልታፋና ንግግር የማልችል ሰው ነኝ» አለው፡፡
\v 11 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ «የሰውን አንደበት የፈጠረ ማን ነው? ሰውን ዲዳ ወይም ደንቈሮ ወይም እንዲያይ ወይም እንዲታወር የሚያደርግስ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር አይደለምን?
\v 12 አሁን ሂድ፤ እኔም ከአፍህ ጋር እሆናለሁ፤ ምን እንደምትናገርም አስተምርሃለሁ፡፡»
\v 13 ሙሴ ግን፣ «ጌታ ሆይ፣ እባክህ ልትልከው የምትፈልገውን ሌላ ሰው ላክ» አለ፡፡
\s5
\v 14 በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን ተቈጣው፡፡ እንዲህም አለው፤ «ሌዋዊው ወንድምህ አሮንስ? እርሱ በሚገባ መናገር እንደሚችል ዐውቃለሁ፡፡ እንዲያውም ከአንተ ጋር ለመገናኘት እየመጣ ነውና ሲያይህ በልቡ ደስ ይሰኛል፡፡
\v 15 አንተ ለእርሱ ትናገራለህ፤ የሚናገራቸውንም ቃላት በአፉ ውስጥ ታስቀምጣለህ፡፡ እኔ በአፍህና በአፉ እሆናለሁ፣ ምን እነደምታደርጉም አሳያችኋለሁ፡፡
\v 16 ለሕዝቡ ይናገርልሃል፡፡ እርሱ የአንተ አፍ ይሆናል፤ አንተም ለእርሱ እንደ እኔ፣ አምላክ ትሆነዋህ፡፡
\v 17 ይህን በትር በእጅህ ትይዛለህ፣ በእርሱም ተአምራትን ታደርጋለህ፡፡»
\s5
\v 18 ሙሴም ወደ ዐማቱ ወደ የቶር ተመልሶ ሄደ፤ «ግብፅ ውስጥ ወዳሉት ዘመዶቼ ተመልሼ እንድሄድና አሁንም ድረስ በሕይወት መኖራቸውን እንዳይ ፍቀድልኝ» አለው፡፡ ዮቶርም ሙሴን፣ «በሰላም ሂድ» አለው፡፡
\v 19 ምድያም ውስጥ እያለ እግዚአብሔር «ሂድ፣ ወደ ግብፅ ተመለሰ፤ ሊገድሉህ የሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ ሞተዋል» አለው፡፡
\v 20 መሴም ሚስቱንና ልጆቹን ይዞ፣ በአህያ ላይም አስቀምጦ ወደ ግብፅ ተመለሰ፤ የእግዚአብሔርን በትርም በእጁ ይዞ ነበር፡፡
\s5
\v 21 ሙሴን እንዲህ አለው፤ «ወደ ግብፅ ተመልሰህ ስትሄድ፣ በእጅህ ያስቀመጥኋቸውን ተአምራት ሁሉ በፈርዖን ፊት እንደምታደርግ ዐስብ፡፡ ነገር ግን እኔ ልቡን አደነድነዋለሁ፤ ሕዝቡ እንዲሄዱም አይፈቅድም፡፡
\v 22 እንዲህ ብለህ ንገረው፤ «እግዚአብሔር እየተናገረ ያለው ይህን ነው፤ እስራኤል ልጄ፣ በኵሬ ነው፤
\v 23 «እንዲያመልከኝ ልጄን ልቀቅ ብዬ እነግርሃለሁ፡፡» ነገር ግን ለመልቀቅ እምቢ ስላለህ፣ በኵር ልጅህን እገድላለሁ፡፡»
\s5
\v 24 ላይ ለምሽቱ ዐርፈው ሳለ፣ እግዚአብሔር ሙሴን አግንኝቶ ሊገድለው ነበር፡፡
\v 25 ግን ስለታም ቢላዋ ይዛ የልጇን ሸለፈት ገረዘች፤ እግሩንም አስነካችው፡፡ ከዚያም በኋላ «አንተ ለእኔ በእውነት የደም ሙሽራዬ ነህ» አለች፡፡
\v 26 እግዚአብሔር ሙሴን ተወው፡፡ «አንተ የደም ሙሽራ ነህ» ብላ የተናገረችው በግርዘቱ ምክንያት ነው፡፡
\s5
\v 27 አሮንን፣ «ወደ ምድረ በዳ ሂድና ከሙሴ ጋር ተገናኝ» አለው፡፡ አሮን ሄደ፣ ሙሴንም በእግዚአብሔር ተራራ ላይ አግኝቶ ሳመው፡፡
\v 28 እንዲናገር የላከለትን የእግዚአብሔር ቃሎች ሁሉና እንዲፈጽማቸው ያዘዘውን ተአምራት በሙሉ ለአሮን ነገረው፡፡
\s5
\v 29 በኋላ ሙሴና አሮን ሄደው የእስራኤልን ሽማግሌዎች ሁሉ በአንድነት ሰበሰቡ፡፡
\v 30 እግዚአብሔር ተአምራትም በሕዝቡ ፊት አሳየ፡፡
\v 31 አመኑ፡፡ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን የጐበኛቸውና የደረሰባቸውን ጭቈና የተመለከተ መሆኑን ሲሰሙም ሰገዱ፣ አመለኩትም፡፡
\s5
\c 5
\p
\v 1 እነዚህ ነገሮች ከሆኑ በኋላ፣ ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ሄደው፣ እንደዚህ አሉ፤ «የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፡- ‹በምድረ በዳው ለእኔ በዓል እንዲያደርጉ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡»›
\v 2 ፈርዖንም፣ «እግዚአብሔር ማን ነው? ቃሉን የምሰማው፣ እስራኤልንስ የምለቅ ለምንድን ነው? እግዚአብሔርን አላውቀውም፤ እስራኤልንም አልለቅም» አለ፡፡
\s5
\v 3 ሙሴና አሮንም፣ «የዕብራውያን አምላክ ከእኛ ጋር ተገናኝቶአል፡፡ በመቅሠፍትና በሰይፍ እንዳይመታን፣ ወደ ምድረ በዳው የሦስት ቀን ጕዞ እንድናደርግና ለእግዚአብሔር እንድንሠዋ ፍቀድልን» አሉት፡፡
\v 4 የግብፅ ንጉሥ ግን፣ «አንተ ሙሴ አንተም አሮን! ሕዝቡን ሥራቸውን አስፈትታችሁ የምትወስዷቸው ለምንድን ነው? ወደ ሥራችሁ ሂዱ» አላቸው፡፡
\v 5 እንዲህ አላቸው፤ «በምድራችን አሁን ብዙ ዕብራውያን አሉ፤ እናንተም ሥራ ታስፈቷቸዋላችሁ፡፡»
\s5
\v 6 በዚያው ቀን ፈርዖን ለሕዝቡ አሠሪዎችና ተቈጣጣሪዎች ትእዛዝ ሰጠ፡፡ እንዲህም አለ፤
\v 7 «እንደ ቀድሞው፣ ከእንግዲህ ወዲያ ለሸክላ ሥራ ጭድ አታቅርቡ፡፡ እነርሱ ራሳቸው ይሂዱና ጭድ ይሰብስቡ፡፡
\v 8 ሆኖም በፊት የሚሠሩትን አንድ ዐይነት የሸክላ ቊጥር አሁንም ሠርተው እንዲያቀርቡ ማድረግ አለባችሁ፡፡ ከዚያ ያነሰ አትቀበሉ፤ ምክንያቱም ሰነፎች ናቸው፡፡ ‹እንሂድ ፍቀድልንና ለአምላካችን እንሠዋ› እያሉ የሚጮኹትም ለዚህ ነው፡፡
\v 9 እንዲተጉና ለማይረባ ንግግር ትኵረት እንዳይሰጡ ሥራውን ጨምራችሁ አክብዱባቸው፡፡»
\s5
\v 10 ስለዚህ የሕዝቡ አሠሪ አለቆችና ተቈጣጣሪዎች ወጥተው ሄዱ፤ ለሕዝቡም ነገሯቸው፡፡ እንዲህም አሉ፤ «ፈርዖን የሚለው ይህ ነው፡- ‹ከእንግዲህ ወዲያ ምንም ጭድ አልሰጣችሁም፡፡
\v 11 ሂዱና ማግኘት ከምትችሉበት ፈልጋችሁ አምጡ፤ የሥራችሁ መጠንም አይቀላለም፡፡»
\s5
\v 12 ሕዝቡ በጭድ ፈንታ ገለባ ለመሰብሰብ በግብፅ ምድር ሁሉ ተሠራጩ፡፡
\v 13 አለቆቹ፣ «ጭድ በሚቀርብላችሁ ጊዜ የምትሠሩትን ሥራችሁን ጨርሱ» ይሏቸውና ያስጠነቅቋቸው ነበር፡፡»
\v 14 ፈርዖን የመደባቸው አሠሪ አለቆች የሠራተኞች ተቈጣጣሪ ያደረጓቸውን እስራኤላውያን ኀላፊዎች ገረፏቸው፡፡ አሠሪ አለቆቹ፣ «በፊት ታደርጉት እንደ ነበረው፣ ትናንትናም ዛሬም የሚጠበቅባችሁን ሸክላ በሙሉ ሠርታችሁ ያላቀረባችሁ ለምንድን ነው?» እያሉ ይጠይቋቸው ነበር፡፡
\s5
\v 15 እስራኤላውያን ተቈጣጣሪዎቹም ወደ ፈርዖን መጥተው አቤቱታ አቀረቡ፡፡ እንደዚህም አሉት፤ «ባሪያዎችህን በዚህ መንገድ ለምን እንድንኖር ታደርጋለህ?
\v 16 ጭድ አይሰጡንም፤ ነገር ግን አሁንም ‹ሸክላ ሥሩ! ይሉናል፡፡ እኛ ባሪያዎችህ ተገርፈናልም፤ ስሕተቱ ግን የገዛ ሕዝብህ ነው፡፡»
\v 17 ግን እንዲህ አለ፤ «እናንተ ሰነፎች! እናንተ ሰነፎች! ‹ለእግዚአብሔር እንድንሠዋ ፍቀድልን› ትላላችሁ፡፡
\v 18 ወደ ሥራ ተመለሱ፡፡ አንዳችም ጭድ አይሰጣችሁም፤ ነገር ግን አሁንም ያንኑ የሸክላ ቊጥር መሥራት አለባችሁ፡፡»
\s5
\v 19 «የየቀኑን የሸክላ ቊጥር መቀነስ የለባችሁም» የሚለው ሲነገራቸው፣ እስራኤላውያን ተቈጣጣሪዎች ችግር ውስጥ እንደ ነበሩ አስተዋሉ፡፡
\v 20 ከፈርዖን ዘንድ ሲወጡ፣ ከቤተ መንግሥቱ ውጭ ቆመው ከነበሩት ከሙሴና ከአሮን ጋር ተገናኙ፡፡
\v 21 ለሙሴና ለአሮንም እንዲህ አሏቸው፣ «እግዚአብሔር ይይላችሁ፣ ይፍረድባችሁም፤ ምክንያቱም በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ፊት አስጸያፊዎች እንድንሆን አድርጋችሁናል፡፡»
\s5
\v 22 ወደ እግዚአብሔር ተመልሶ፣ «ጌታ ሆይ፣ በዚህ ሕዝብ ላይ መከራ እንዲደርስበት ያደረግህ ለምንድን ነው? እኔንስ ቀድሞውኑ ለምን ላክኸኝ?
\v 23 ስም ልነግረው ወደ ፈርዖን ከመጣሁበት ጊዜ ጀምሮ፣ በዚህ ሕዝብ ላይ መከራ አምጥቶአል፤ አንተም ሕዝብህን ከቶ ነጻ አላወጣኸውም» አለው፡፡
\s5
\c 6
\p
\v 1 ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን፣ «በፈርዖን ላይ የማደርገውን አሁን ታያለህ፡፡ ከጽኑዕ እጄ የተነሣ ሕዝቡን ይለቃቸዋልና፣ ይህን ታያለህ፡፡ ከጽኑዕ እጄ የተነሣ ሕዝቡን ከምድሩ ያስወጣቸዋል» አለው፡፡
\s5
\v 2 ለሙሴ እንዲህ አለው፤ «እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡
\v 3 እኔ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ ሁሉን እንደሚችል አምላክ ተገለጥሁላቸው፤ ነገር ግን በስሜ፣ በእግዚአብሔር ለእነርሱ አልታወቅሁላቸውም ነበር፡፡
\v 4 የተሰደዱባትን፣ በእንግድነት የኖሩባትን የከነዓንን ምድር ልሰጣቸው፣ ከእነርሱ ጋር ኪዳን አጽንቻለሁ፡፡
\v 5 ደግሞም ግብፃውያን ባሪያ ያደረጓቸውን የአስራኤላውያንን ጩኸት ሰምቻለሁ፤ ኪዳኔንም አስታውሻለሁ፡፡
\s5
\v 6 ስለዚህ ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፤ ‹እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡ በግብፃውያን ሥር ከምትኖሩባት ባርነት እታደጋችኋለሁ፤ ከአገዛዛቸውም ነፃ አወጣችኋለሁ፡፡ በታላቅ ፍርድና ኀይሌን በማሳየት እታደጋችኋለሁ፡፡
\v 7 አድርጌ ወደ ራሴ እወስዳችኋለሁ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ፡፡ ግብፃውያን ከጫኑባችሁ ባርነት ነፃ ያወጣኋችሁ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፡፡
\s5
\v 8 ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ልሰጥ ቃል ወደገባሁባት ምድር አስገባችኋለሁ፡፡ ምድሪቱን ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ፡፡ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡»
\v 9 ይህን ለእስራኤላውያን በነገራቸው ጊዜ፣ በአስከፊው ባርነታቸው ተስፋ ከመቊረጣቸው የተነሣ አላደመጡትም፡፡
\s5
\v 10 ሙሴን እንዲህ አለው፤
\v 11 ሂድና ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን የእስራኤልን ሕዝብ ከምድሩ እንዲለቅ ንገረው፡፡
\v 12 ሙሴም እግዚአብሔርን፣ «ተብታባ በመሆኔ እስራኤላውያን ካልሰሙኝ፣ ፈርዖን እንዴት ይሰማኛል?
\v 13 እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን አናገራቸው፡፡ እስራኤላውያን ከግብፅ ምድር እንዲያስወጡ ስለ ግብፅ ንጉሥ ስለ ፈርዖንና ስለ እስራኤላውያንም ትእዛዝ ሰጣቸው፡፡
\s5
\v 14 የአባቶቻቸውም ቤት አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ የእስራኤል በኵር ልጅ የሮቤል ልጆች ሄኖኅ፣ ፈሉስ፣ አስሮንና ከርሚ ነበሩ፡፡ እነዚህ የሮቤል ነገድ ናቸው፡፡
\v 15 የስምዖን ልጆች ይሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ ዱሐርና የከነዓናዊቷ ሴት ልጅ ሳኡል ነበሩ፡፡ እነዚህ የስምዖን ነገድ አባቶች ናቸው፡፡
\s5
\v 16 የሌዊ ልጆች ስሞች ከትውልዶቻቸው ጋር እነዚህ ናቸው፤ ጌድሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ነበሩ፡፡ ሌዊ መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፡፡
\v 17 የጌድሶን ልጆች ሉቤኒና ሰሜኢ ነበሩ፡፡
\v 18 የቀዓት ልጆች እንበረም፣ ይሰዓር፣ ኬብሮንና ዑዝኤል ነበሩ፡፡ ቀዓት መቶ ሠላሳ ሦስት ዓመት ኖረ፡፡
\v 19 የሜራሪ ልጆች ሞሖሊና ሙሲ ነበሩ፡፡ እነዚህ በትውልዶቻቸው መሠረት፣ የሌዋውያን የነገድ አባቶች ሆኑ፡፡
\s5
\v 20 የአባቱን እኅት ዮካብድን አገባ፤ እርሷምአሮንንና ሙሴን ወለደችለት፡፡ እንበረም መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ኖሮ ሞተ፡፡
\v 21 የይስዓር ልጆች ቆሬ፣ ናፌግና ዝክሪ ነበሩ፡፡
\v 22 ልጆች ሚሳኤል፣ ኤልዳፋንና ሥትሪ ነበሩ፡፡
\s5
\v 23 የአሚካዳብን ልጅ፣ የነኦሶንን እኅት ኤልሳቤጥን አገባ፡፡ እርሷም ናዳብንና አብዩድን፣ አልዓዛርንና ኢተምርን ወለደችለት፡፡
\v 24 የቆሬ ልጆች አሴር፣ ሕልቃናና አብያሳፍ ነበሩ፡፡ እነዚህ የቆሬ ነገድ አባቶች ናቸው፡፡
\v 25 ልጅ አልዓር ከፏትኤል ልጆች አንዲቱን አገባ፡፡ እርሷም ፊንሐስን ወለደችለት፡፡ እነዚህ በየትውልዶቻቸው የሌዋውያን አባቶች ቤቶች አለቆች ናቸው፡፡
\s5
\v 26 ሁለት ሰዎች፣ «እስራኤላውያንን በየተዋጊ ሰራዊታቸው ከግብፅ ምድር አውጡ» ብሎ እግዚአብሔር ያዘዛቸው አሮንና ሙሴ ነበሩ፡፡
\v 27 ሙሴ እስራኤላውያንን ከግብፅ ለማውጣት እንዲፈቅድላቸው ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን ተናገሩ፡፡ እነዚህ ሙሴና አሮን እነዚያው ራሳቸው ነበሩ፡፡
\s5
\v 28 እግዚአብሔር በግብፅ ውስጥ ሙሴን ባናገረው ጊዜ፣
\v 29 «እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡ የምነግርህን ሁሉ ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን ንገረው» አለው፡፡
\v 30 ግን እግዚአብሔርን፣ «እኔ ተብታባ ነኝ፤ ፈርዖን ታዲያ እንዴት ይሰማኛል? አለው፡፡
\s5
\c 7
\p
\v 1 ሙሴን እንዲህ አለው፤ «ልብ በል፤ አንተን ለፈርዖን እንደ አምላክ አድርጌሃለሁ፡፡ ወንድምህ አሮን ነቢይህ ይሆናል፡፡
\v 2 እንድትናገር ያዘዝሁህን ሁሉ ትናራለህ፡፡ የእስራኤል ሕዝብ ከምድሩ እንዲለቀ፣ ወንድምህ አሮን ለፈርዖን ይናገራል፡፡
\s5
\v 3 ነገር ግን እኔ የፈርዖንን ለብ አደነድነዋሁ፤ የተአምራቴን ብዙ ምልክቶች፣ ብዙ ድንቆችም በግብፅ ምድር አሳያለሁ፡፡
\v 4 ነገር ግን ፈርዖን አይሰማችሁም፤ ስለዚህ እጄን በግብፅ ላይ አደርጋሁ፤ ሰራዊቱን፣ ሕዝቤን፣ የእስራኤልን ልጆች በታላቅ ፍርድ ከግብፅ ምድር አወጣለሁ፡፡
\v 5 በግብፅ ላይ ስዘረጋና እስራኤላውያንን ከመካከላቸው ሳወጣ፣ ግብፃውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፡፡»
\s5
\v 6 አሮን እንዲሁ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ያዘዛቸውን ፈጸሙ፡፡
\v 7 ባጋገሩት ጊዜ፣ የሙሴ ዕድሜ ሰማንያ፣ የአሮን ደግሞ ሰማንያ ሦስት ነበር፡፡
\s5
\v 8 ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤
\v 9 ‹ተአምር አሳዩ› ሲላችሁ፣ አሮንን እንዲህ በለው፤ ‹በትርህን ውሰድና በፈርዖን ፊት ጣለው፤ እባብም ይሀናል፡፡»›
\v 10 ሙሴ አሮን ወደ ፈርዖን ሄደው፣ እግዚአብሔር አዝዞአቸው የነበረውን አደረጉ፡፡ አሮን በትሩን በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ፊት ጣለው፤ እባብም ሆነ፡፡
\s5
\v 11 ደግሞ ለጥበበኛ ሰዎቹና ለጠንቋዮቹ ጥሪ አደረገ፡፡ እነርሱም በምትሀታቸው ያንኑ አደረጉ፡፡
\v 12 እያንዳንዱ ሰው በትሩን ጣለ፤ በትሮቹም እባብ ሆኑ፣ ነገር ግን የአሮን በትር የእነርሱን እባቦች ዋጣቸው፡፡
\v 13 አስቀድሞ እንደ ተናገረው፣ የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ አልሰማምም፡፡
\s5
\v 14 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ «የፈርዖን ልብ ደንድኖአል፤ ሕዘቡም እንዲሄዱ አይፈቅድም፡፡
\v 15 ወደ ውሃው በሚሄድበት ጊዜ፣ በጠዋት ወደ ፈርዖን ሂድ፡፡ እንዳገኘውም በወንዙ ዳር ቁም፤ ወደ እባብነት ተለውጦ የነበረውን በትርህን ውሰድ፡፡
\s5
\v 16 እንዲህ በለው፤ ‹የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ይህን እንድናገር ወደ አንተ ላከኝ፤ «በምድረ በዳ እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፤ እስካሁን ድረስ አልሰማህም፡፡»
\v 17 የሚናገረው ይህ ነው፤ «እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ በዚህ ታውቃለህ፡፡ የአባይን ወንዝ ውሀ በእጄ በያዝሁት በትር እመታዋለሁ፣ ወንዙም ወደ ደምነት ይለወጣል፡፡
\v 18 ውስጥ የሚገኙት ዓሦች ይሞታሉ፤ ወንዙ ይከረፋል፡፡ግብፃውያኑም ከወንዙ ውሀ መጠጣት አይችሉም፡፡»
\s5
\v 19 ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ አለ፤ አሮንን፣ ‹በትርህን ውሰድና ውሀቸው ደም እንዲሆን፣ በግብፅ ውሀዎች ላይ፣ በወንዞቻቸውም፣ በምንጮቻቸውም፣ በውሀ ማጠራቀሚያዎቻቸውና በኩሬዎቻቸው ሁሉ ላይ እጅህን ዘርጋ ብለህ ንገረው፡፡ በመላው የግብፅ ምድር፣ ከዕንጨትና ከድንጋይ በተሠሩ ውሀ መያዣዎች ያለው ውሀም እንኳ ደም እንዲሆን ይህን አድርግ፡፡»›
\s5
\v 20 ሙሴና አሮን እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው አደረጉ፡፡ አሮን በትሩን አንሥቶ በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ፊት የወንዙን ውሀ መታው፡፡ የወንዙ ውሀ በሙሉ ወደ ደምነት ተለወጠ፡፡
\v 21 ውስጥ ያለው ዓሣ ሞተ ወንዙም መከርፋት ጀመረ፡፡ ግብፃውያኑ ከወንዙ ውሀ መጠጣት አልቻም፤ ደሙም በግብፅ ምድር በየትኛውም ስፍራ ነበረ፡፡
\v 22 የግብፅ ጠንቋዮችም በምትሀታቸው ያንኑ ዐይነት ነገር አደረጉ፡፡ ስለዚህ የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ እግዚአብሔር ይሆናለ ብሎ ተናግሮት እንደ ተናገረውም ሙሴንና አሮንን ለመስማት እምቢ አለ፡፡
\s5
\v 23 ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ ለዚህ ጉዳይ ትኵረትም እንኳ አልሰጠም፡፡
\v 24 ግብፃውያኑ ሁሉ በወንዙ ዙሪያ የሚጠጣ ውሀ ለማግኘት ቈፈሩ፤ ነገ ርግን የወንዙን ውሀ መጠጣት አልቻሉም፡፡
\v 25 እግዚአብሔር ወንዙን ከመታው በኋላ ሰባት ቀን ዐለፈ፡፡
\s5
\c 8
\p
\v 1 ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ «ወደ ፈርዖን ሂድና እንዲህ በለው፤ ‹እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ «እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡
\v 2 ካልህ፣ አገርህን በሙሉ በጓጕንቸው መቅሠፍት እመታዋለሁ፡፡
\v 3 ጓጕንቸር ይርመሰመሳል፡፡ ጓጕንቸሮቹ ከወንዙ ይወጡና ወደ ቤትህ፣ ወደ መኝታ ክፍልህና ወደ ዐልጋህ ውስጥ ይገባሉ፡፡ ወደ አገልጋዮችህም ቤቶች ውስጥ ይገባሉ፡፡ ወደ ሕዝብህ፣ ወደ ምድጆችህና ወደ ቡሃቆችም ይዛመታሉ፡፡
\v 4 ጓጕንቸሮቹ አንተን፣ ሕዝብህንና አገልጋዮችህን ሁሉ ይመታሉ፡፡»
\s5
\v 5 ለሙሴ እንዲህ አለ፤ «አሮንን፣ እጅህንና በትርህን በወንዞች፣ በምንጮችና በቦዮች ላይ ዘርጋና በግብፅ ምድር ላይ ጓጕንቸሮች እንዲወጡ አድርግ» በለው፡፡
\v 6 በግብፅ ውሆች ላይ እጁን ዘረጋ፤ ጓጕንቸዎቹም ወጥተው የግብፅን ምድር ሸፈኑት፡፡
\v 7 ጠንቋዮቹም በምትሃቸው ያንኑ አደረጉ፤ ጓጕንቸሮቹ በግብፅ ምድር ላይ እንዲወጡ አደረጉ፡፡
\s5
\v 8 ሙሴንና አሮንን አስጠርቶ፣ «ጓጕንቸሮቹን ከእኔና ከሕዝቤ ላይ አንዲያስወግድ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ፡፡ ከዚያም ለእግዚአብሔር እንዲሠዉ ሕዝቡን እለቃቸዋለሁ» አላቸው፡፡
\v 9 ፈርዖንን እንዲህ አለው፤ «ጓጕንቸሮቹ ከአንተና ከቤቶችህ እንዲወገዱ፣ በወንዙ ውስጥ ብቻ ግን እንዲቈዩ፣ ለአንተ፣ ለአገልጋዮችህና ለሕዝብህ የምጸልይበትን ጊዜ ለእኔ መንገሩ የአንተ ድርሻ ነው፡፡»
\s5
\v 10 «ነገ» አለው፡፡ ሙሴም ፈርዖንን መልሶ፣ «እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም እንደሌለ እንድታውቅ አንተ እንደምትለው ይሁን፡፡
\v 11 ጓጕንቸሮቹ ከአንተ፣ ከቤቶችህ ከአገልጋዮችህና ከሕዝብህ ይወገዳሉ፡፡ በወንዙ ውስጥ ብቻ ግን ይቈያሉ» አለው፡፡
\v 12 አሮን ከፈርዖን ወጥተው ሄዱ፡፡ ሙሴም እግዚአብሔር በፈርዖን ላይ ስላመጣቸው ጓጕንቸሮች ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፡፡
\s5
\v 13 ሙሴ እንደ ለመነው አደረገ፡- ጓጕንቸሮቹ በየቤቱ፣ በየግቢውና በየሜዳው ሞቱ፡፡
\v 14 ሕዝቡ የሞቱትን ሰብስበው ከመሯቸው፤ ምድሩም ከረፋ፡፡
\v 15 ነገር ግን ፈርዖን ፋታ መገኘቱን ሲያይ፣ ልቡን አደነደነ፤ እንደዚህ ያደርጋል ብሎ እግዚአብሔር ተናግሮ እንድ ነበረ፣ ሙሴንና አሮንንም አልሰማቸውም፡፡
\s5
\v 16 ለሙሴ እንዲህ አለ፤ «አሮንን እንዲህ በለው ‹በመላው የግብፅ ምድር ተባይ እንዲሆን የምድሩን ትቢያ በበትርህ ምታ፡፡»
\v 17 እነርሱም እንዲሁ አደረጉ፡- አሮን እጁን ዘርግቶ በበትሩ የምድሩን ትቢያ መታው፡፡ በሰውና በእንስሳ ላይ ተባይ መጣ፡፡ የምድሩ ትቢያ ሁሉ በመላው የግብፅ ምድር ተባይ ሆነ፡፡
\s5
\v 18 በምትሃቸው ተባይ እንዲመጣ ሙከራ አደረጉ፤ ነገር ግን አልቻም፡፡ በሰውና በእንስሳ ላይ ተባዮች ነበሩ፡፡
\v 19 ጠንቋዮቹ ታዲያ ፈርዖንን፣ «ይህ የእግዚአብሔር ጣት ነው» አሉት፡፡ ነገር ግን የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ እነርሱንም ለማድመጥ እምቢ አለ፡፡ ይህም የሆነው ፈርዖን እንዲህ እንደሚያደርግ እግዚአብሔር ተናግሮት በነበረው መሠረት ነው፡፡
\s5
\v 20 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ «በማለዳ ተነሣና ፈርዖን ወደ ወንዙ ሲወጣ በፊት ለፊቱ ቁም፡፡ እንደዚህም ብለህ ንገረው፤ ‹እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፡- «እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡
\v 21 የማትለቅ ከሆነ ግን፣ በአንተ፣ በአገልጋዮችህና በሕዝብህ ላይ፣ ወደ ቤቶችህም ውስጥ የዝንብ መንጋ እልካለሁ፡፡ የግብፃውያን ቤቶች በዝንብ መንጋ ይሞላሉ፤ የሚቆሙበት ምድርም እንኳ ዝንብ ብቻ ይሆናል፡፡
\s5
\v 22 ግን በዚያ ቀን የዝንብ መንጋ እንዳይገኝባ፣ ሕዝቤ የሚኖርባትን የጌሤምን ምድር በተለየ ሁኔታ እይዛታለሁ፡፡ እኔ እግዚአብሔር በዚህ ምድር እንዳለሁ እንድታውቅ ይህ ይሆናል፡፡
\v 23 በሕዝቤና በሕዝብህ መካከል ልዩነት እንዲኖር አደርጋለሁ፡፡ ይህ ተአምራዊ ምልክት ነገ ነው የሚሆነው፡፡»
\v 24 እግዚአብሔር እንዲሁ አደረገ፤ ጥቅጥቅ ያለ የዝንብ መንጋም ወደ ፈርዖን ቤትና ወደ አገልጋዮቹ ቤቶች መጣ፡፡ በመላው የግብፅ ውስጥ ምድሩ ከዝንቡ መንጋ የተነሣ ተበላሽቶ ነበር፡፡
\s5
\v 25 ሙሴንና አሮንን አስጠርቶ፣ «ሂዱና በምድራችሁ ለአምላካችሁ ሠዉ» አላቸው፡፡
\v 26 እንዲህ ለማድረግ ለእኛ ትክክል አይደለም፤ ለአምላካችን በእግዚአብሔር የምንሠዋቸው መሥዋዕቶች ለግብፃውያን አስጸያፊዎች ናቸውና፡፡ ለግብፃውያን አስጸያፊ የሆኑትን መሥዋዕቶች እያን በፊታቸው ብንሠዋ፣ በድንጋይ አይወግሩንም?
\v 27 ባዘዘን መሠረት፣ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር መሠዋት ያለብን ወደ ምድረ በዳወ የሦስት ቀን ጕዞ ሄደን ነው» አለ፡፡
\s5
\v 28 «እንድትሄዱና በምድረ በዳው ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር እንድትሠዉ እፈቅድላችኋለሁ፡፡ ርቃችሁ መሄድ ግን የለባችሁም፡፡ ለእኔም ጸልዩልኝ» አለ፡፡
\v 29 «ከአንተ ወጥቼ እንደ ሄድሁ፣ የዝንቦቹ መንጋ አንተን ፈርዖንን፣ አገልጋዮችህንና ሕዝብህን ነገ ለቀው እንዲሄዱ ወደ እግዚአብሔር እጸልይልሃለሁ፡፡ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ለመሠዋት ሕዝባችን እንዲሄድ ባለመፍቀድ ከእንግዲህ ወዲያ ልታታልለን አይገባም» አለ፡፡
\s5
\v 30 ከፈርዖን ወጥቶ ሄደና ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፡፡
\v 31 እግዚአብሔር ሙሴ እንደ ለመነው አደረገ፡- የዝንቡን መንጋ ከፈርዖን፣ ከአገልጋዮቹና ከሕዝቡ ላይ አስወገደ፡፡ አንድም አልቀረም፡፡
\v 32 ነገር ግን ፈርዖን በዚህም ጊዜ ልቡ አደነደነ፤ ሕዝቡም እንዲሄድ አልፈቀደም፡፡
\s5
\c 9
\p
\v 1 ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ አለ፤ «ወደ ፈርዖን ሂድና እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‹የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ይህን ይናገራል፡፡ «እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡»
\v 2 ብትልና አሁንም ከልክለህ ብታስቀራቸው፣
\v 3 የእግዚአብሔር እጅ መስክ ላይ ባለው ከብትህ፣ በፈረሶችህ፣ በአህዮችህ፣ በግመሎችህ፣ በፍየሎችህና በበጎችህ ላይ ይሆናል፤ አስከፊ በሽታም ያመጣል፡፡
\v 4 እግዚአብሔር በእስራኤል ከብትና በግብፅ ከብት መካከል ልዩነት አድርጓል፡- የእስራኤል ከብት አይሞትም፡፡
\s5
\v 5 ጊዜ ወስኖአል፤ «በምድሪቱ ላይ ይህን የማደርገው ነገ ነው» ብሎአል፡፡
\v 6 ይህን በሚቀጥለው ቀን አደረገው፡- የግብፅ ከብት ሁሉ ሞተ፡፡ ከእስራኤል ከብት ግን አንድም አልሞተም፡፡
\v 7 ተከታትሎ አጣራ፣ ከእስራኤል ከብት አንድም እንኳ አለመሞቱን ተረዳ፡፡ ነገር ግን ልቡ ደንድኖ ነበር፤ ስለዚህ ሕዝቡ እንዲሄድ አልፈቀደም፡፡
\s5
\v 8 እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን አላቸው፤ «ከምድጃ ላይ እፍኝ ዐመድ ውሰዱና አንተ ሙሴ ወደ ሰማይ ፈርዖን እያየ ዐመዱን በትነው፡፡
\v 9 በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ትቢያ ይሆናል፡፡ ይህም በመላው የግብፅ ምድር በሰውና በእንስሳት ላይ ዕባጭና ቊስል ያመጣል፡፡»
\v 10 ስለዚህ ሙሴና አሮን ከምድጃ ዐመድ ወስደው ከፈርዖን ፊት ለፊት ቆሙ፡፡ ከዚያም ሙሴ ዐመዱን ወደ ሰማይ በተነው፡፡ ዐመዱ በሰውና በእንስሳ ላይ የሚወጣ ዕባጭና ቊስልን አመጣ፡፡
\s5
\v 11 በእነርሱና በሌች ግብፃውያን ሁሉ ላይ ወጥቶ በነበረው ዕባጭ ምክንያት ጠንቋዮቹ በሙሴ ፊት መቆም አልቻሉም፡፡
\v 12 እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ ስለ አደነደነው፣ ፈርዖን ሙሴንና አሮንን አልሰማቸውም፡፡ ይህም የሆነው ፈርዖን እንደዚህ እንደሚደርግ እግዚአብሔር ለሙሴ ነግሮት እንድ ነበረው ነው፡፡
\s5
\v 13 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ «በጠዋት ተነሣና ከፈርዖን ፊት ለፊት ቁም፤ እንደዚህ ብለህም ንገረው፤ ‹የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ይህን ተናገሯል፡- «እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡
\v 14 ጊዜ በአንተ በራስህ፣ በአገልጋዮችህና በሕዝብህ ላይ መቅሠፍቴን ሁሉ እልካለሁ፡፡ ይህን የማየደርገውም በድምር ሁሉ እንደ እኔ ያለ እንደሌለ እንድታውቅ ነው፡፡
\s5
\v 15 ጊዜ እጄን ዘርግቼ አንተንና ሕዝብህን በበሽታ በመምታት ከምድር ባጠፋኋችሁ ነበር፡፡
\v 16 ግን በሕይወት እንድትቈይ ያደረግሁህ፣ ኀይሌን እንድገልጥብህና ስሜም በምድር ሁሉ እንዲታወቅ ነው፡፡
\v 17 ሕዝቤን እንዳይሄድ በማድረግ በሕዝቤ ላይ ራስህን እያሳበይህ ነው፡፡
\s5
\v 18 ነገ በዚህ ጊዜ ከተመሠረተችበት ቀን ጀምሮ እስካሁን ድረስ በግብፅ ታይቶ የማይታወቅ ከባድ የበረዶ ማዕበል አመጣለሁ፡፡
\v 19 አሁን ሰው ላክና ከብትህን፣ በመስክ ላይ ያለህን ማንኛውንም ነገር ወደ ጠለያ ስፍራ ሰብስብ፡፡ መስክ ላይ የቀረና ወደ ቤት ያልመጣ ማንኛውም ከብትና ሰው ሁሉ በረዶው ይወርድባቸውና ይሞታሉ፡፡»
\s5
\v 20 አገልጋዮች የእግዚአብሔር ቃል የተቀበሉት ባሮቻቸውንና ከብቶቻቸውን ወደ ቤት ለማምጣት ተጣደፉ፡፡
\v 21 የእግዚአብሔርን ቃል ከምር ያልተቀበሉት ግን ባሮቻቸውንና ከብታቸውን መስክ ላይ ተዉ፡፡
\s5
\v 22 ሙሴን እንዲህ አለው፤ «በሁሉም የግብፅ ምድር፣ በሕዝብ፣ በእንስሳትና በመላው የግብፅ ምድር መስክ ላይ ባሉ ተክሎች ሁሉ ላይ በረዶ እንዲወርድ እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ፡፡»
\v 23 በትሩን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ነጐድጓድ፣ በረዶና መብረቅ ወደ ምድር ላከ፡፡በግብፅም ምድር ላይ በረዶ አዘነበ፡፡
\v 24 ግብፅ አገር ከሆነችበት ጊዜ ጀምሮ በምድሪቱ ሁሉ ያልታየ እጅግ ከባድ የበረዶና የመብረቅ ቅልቅል ነበር የዘነበው፡፡
\s5
\v 25 የግብፅ ምድር፣ በረዶው መስክ ላይ ያለውን ማንኛውንም ነገር፣ ሰውንም እንስሳቱንም መታ፡፡ በመስክ ያለውን ተክል ሁሉ መታው፣ ዛፉንም ሁሉ ሰባበረው፡፡
\v 26 እስራኤላውያን በሚኖሩበት በጌሤም ምድር ብቻ በረዶ አልነበረም፡፡
\s5
\v 27 በኋላ ፈርዖን ሙሴንና አሮንን እንዲጠሩ ሰዎችን ላከ፡፡ እንዲህም አላቸው፤ «በዚህ ጊዜ ኀጢአት ፈጽሜአለሁ፡፡ እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ እኔና ሕዝቤ ግን ኀጢአተኞች ነን፡፡
\v 28 እግዚአብሔር ጸልዩ፤ ምክንያቱም ከባዱ ነጐድጓድና በረዶ እጅግ በዝቶብናል፡፡ እለቅቃችኋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ እዚህ አትቆዩም፡፡
\s5
\v 29 ፈርዖንን እንዲህ አለው፤ «ከከተማዪቱ እንደ ወጣሁ፣ እጆቼን ወደ እግዚአብሔር እዘረጋለሁ፡፡ ነጐድጓዱ ያቆማል፣ በረዶም አይኖርም፡፡ በዚህ መንገድ አንተ ምድር የእግዚአብሔር መሆኗን ታውቃለህ፡፡
\v 30 ግን አንተንና አገልጋዮችህን በሚመለከት እግዚአብሔር አምላክን ገና በእውነት እንደማታከብሩ ዐውቃለሁ፡፡»
\s5
\v 31 ጊዜ ተልባው አብቦ፣ ገብሱም ፍሬ በመያዝ ላይ ነበረ፣ ተልባውና ገብሱ ከጥቅም ውጭ ሆነዋል፡፡
\v 32 አጃው ግን ቈይተው የሚደርሱ ሰብሎች በመሆናቸው አልተጐዱም፡፡
\v 33 ሙሴ ከፈርዖንና ከከተማዪቱ ሲወጣ፣ እጆቹን ወደ እግዚአብሔር ዘረጋ፤ ነጐድጓዱና በረዶው ቆሙ፤ ዝናብም አልዘነበም፡፡
\s5
\v 34 ፈርዖን ዝናቡ፣ በረዶውና ነጐድጓዱ መቆሙን ሲያይ፣ እንደ ገና ኀጢአት አደረገ፤ ከአገልጋዮቹ ጋርም በአንድነት ልቡን አደነደነ፡፡
\v 35 የፈርዖን ልብ ስለ ደነደነ፣ የእስራኤል ሕዝብ እንዲሄዱ አልፈቀደም፡፡ ይህም የሆነው ፈርዖን ልቡን እንድሚያደነድን እግዚአብሔር ለሙሴ ነግሮት የነበረው መንገድ ነው፡፡
\s5
\c 10
\p
\v 1
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ «የፈርዖንና የአገልጋዮቹን ልብ አደነድናለሁና ወደ ፈርዖን ሂድ፡፡ እነዚህን የተአምራቴን ምልክቶች ለማሳየት ይህን አድርጌአለሁ፡፡
\v 2 ይህን ያደረግሁት ግብፃውያንን እንዴት በከባድ አያያዝ እንደያዝኋቸውና በመካከላቸውም የተአምራትን ልዩ ልዩ ምልክቶች እንዳሳየሁ ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ እንድትነግሯቸው ነው፡፡ በዚህ መንገድ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፡፡
\s5
\v 3 አሮንም ወደ ፈርዖን ሄደው እንዲህ አሉት፤ «የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፡- ‹ራስህን በፊቴ ለማዋረድ እምቢ የምትለው እስከ መቼ ነው? እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡
\v 4 ግን ሕዝቤን አልለቅም ብትል፣ እነሆ፣ በነገው ቀን በአገርህ ላይ አንበጣዎችን አመጣለሁ፡፡
\s5
\v 5 ማንም ሰው መድሩን ማየት እስከማይችል ድረስ የምድሩን ገጽ ይሸፍኑታል፡፡ ከበረዶው አምልጦ የቀረውን ሁሉ ይበሉታል፡፡ መስክ ላይ የሚያድግላችሁንም ዛፍ ሁሉ ይበሉታል፡፡
\v 6 አንበጣዎቹ የአንተን፣ የአገልጋዮችህን ቤቶች ሁሉ ይሞሏቸዋል፤ ይህም፣ አባትህም አያትህም በዚህ ምድር ላይ መኖር ከጀመሩበት ቀን አነሥቶ እስከዚህ ጊዜ ድረስ ታይቶ የማይታወቅ ነው፡፡» ሙሴም ከፈርዖን ዘንድ ወጥቶ ሄደ፡፡
\s5
\v 7 ፈርዖንን፣ «ይህ ሰው ወጥመድ የሚሆንብን እስከ መቼ ነው? አምላካቸውን እግዚአብሔርን እንዲያመልኩት እስራኤላውያን ይሂዱ፡፡ ግብፅ መጥፋቷን ገና አልተገነዘብህምን?» አሉት፡፡
\v 8 ሙሴና አሮን፣ «ሂዱ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አምልኩ፡፡ ነገር ግን የሚሄዱት የትኞቹ ናቸው?» ወዳላቸው ወደ ፈርዖን እንደገና እንዲመጡ ተደረገ፡፡
\s5
\v 9 የምንሄደው ከወጣቶቻችንና ከሽማግሌዎቻችን፣ ከወንድና ከሴት ልጆችን ጋር ነው፡፡ ለእግዚአብሔር በዓል ማክበር ስለሚገባን፣ የበግና የፍየል መንጎቻችንን፣ የቀንድ ከብቶቻችንንም ይዘን እንሄዳለን» አለ፡፡
\v 10 ፈርዖንም እንዲህ አላቸው፤ «እናንተንና ታናናሽ ልጆቻችሁን ስለችሁ፣ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፡፡ ነገር ግን ተመልከቱ፣ ክፉ ነገር ዐስባችኋል፡፡
\v 11 ከመካከላችሁ ወንዶች ብቻ ይሂዱና እግዚአብሔርን ያምልኩ፤ የምትፈልጉት ያንን ነውና፡፡» ከዚያም በኋላ ሙሴና አሮን ከፈርዖን ዘንድ እንዲወጡ ተደረገ፡፡
\s5
\v 12 እግዚአብሔርም ሙሴን፣ «አንበጣዎች የግብፅን ምድር እንዲወርሩትና ከበረዶው ተርፎ የቀረውን፣ በምድሩ ያለውን ተክል ሁሉ እንዲበሉት እጅህን በግብፅ ምድር ላይ ዘርጋ» አለው፡፡
\v 13 ሙሴም በትሩን በግብፅ ምድር ላይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም በዚያ ቀንና ሌሊት ሁሉ የምሥራቅ ነፋስ በምድሩ ላይ እንዲነፍስ አደረገ። ማለዳ ላይ የምሥራቁ ነፋስ አንበጣዎቹን አምጥቶ ነበር።
\s5
\v 14 በግብፅ ምድር ሁሉ ተሠራጩ፤ አገሩንም ሁሉ ወረሩት። እንደዚህ እጅግ የበዙ አንበጣዎች በምድሩ ውስጥ ከዚህ በፊት አልነበሩም፤ ወደፊትም አይኖሩም።
\v 15 ጨለማ እስኪሆን ድረስ የምድሩን ሁሉ ገጽ ሸፈኑት። በምድሩ ላይ ያለውን ማንኛውንም ተክልና ከበረዶው ተርፎ የቀረውን የዛፍ ፍሬ ሁሉ በሉት። በግብፅ ምድር ሁሉ ለምለም ቅጠል ያለው ተክል አልቀረም፤ በመስክም ላይ ምንም ዛፍ አልነበረም።
\s5
\v 16 ሙሴንና አሮንን በፍጥነት አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “በአምላካችሁ በእግዚአብሔርና በእናንተ ላይ ኀጢአት ሠርቻለሁ።
\v 17 እንግዲህ አሁን ኀጢአቴን ይቅር በሉኝና ይህን ሞት ከእኔ እንዲያስወግድልኝ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ።”
\v 18 ስለዚህ ሙሴ ከፈርዖን ዘንድ ወጥቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።
\s5
\v 19 አንበጣዎቹን ለቃቅሞ ወደ ቀይ ባሕር የሚከትታቸውን ብርቱ የምዕራብ ነፋስ አመጣ፤ በግብፅ ግዛት ሁሉ የቀረ አንድም አንበጣ አልነበረም።
\v 20 ነገር ግን እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ ስላደነደነው፣ ፈርዖን እስራኤላውያንን አልለቀቃቸውም።
\s5
\v 21 ሙሴን፣ “በግብፅ ምድር ላይ የሚዳስስ ከባድ ጨለማ እንዲሆን እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ” አለው።
\v 22 እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ በግብፅም ምድር ሁሉ ለሦስት ቀን ድቅድቅ ጨለማ ሆነ።
\v 23 ቀኖች አንዱ ሌላውን ማየት አልቻለም፤ ከቤቱም የወጣ ማንም የለም። ለእስራኤላውያን ግን በሚኖሩበት ስፍራ ብርሃን ነበራቸው።
\s5
\v 24 ፈርዖን ሙሴን አስጠርቶ፣ “ሂዱ እግዚአብሔርን አምልኩ። ቤተ ሰቦቻችሁም እንኳ ዐብረዋችሁ መሄድ ይችላሉ፤ በጎቻችሁና ከብቶቻችሁ ግን እዚህ መቅረት አለባቸው” አለው።
\v 25 እንዲህ አለው፤ “ለአምላካችን ለእግዚአብሔር እንድንሠዋቸው ለመሥዋዕትና ለሚቃጠል መሥዋዕት እንስሳቱንም ልትሰጠን ይገባል።
\v 26 ከብቶቻችንም ከእኛ ጋር መሄድ አለባቸው፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን ለማምለክ ልንወስዳቸው ይገባልና ከእነርሱ ሰኮናም እንኳ እዚህ አይቀርም። ምክንያቱም እግዚአብሔርን በምን እንደምናመልከው እዚያ እስክንደርስ ድረስ አናውቅም።”
\s5
\v 27 ግን የፈርዖንን ልብ ስላደነደነው ፈርዖን ሕዝቡን አልለቀቃቸውም።
\v 28 ሙሴን፣ “ሂድ ከእኔ ዘንድ! ፊቴን እንዳታይ ተጠንቀቅ፤ ፊቴን ባየህበት ቀን ትሞታለህና” አለው።
\v 29 ሙሴም፣ “አንተ ራስህ ተናግረሃል። ፊትህን እንደ ገና አላየውም” አለው።
\s5
\c 11
\p
\v 1 ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ አለ፤ “በፈርዖንና በግብፅ ላይ የማመጣው ገና አንድ መቅሠፍት አለ። ከዚያ በኋላ ከዚህ እንድትሄዱ ይፈቅድላችኋል። በመጨረሻ እንድሄድ ሲያደርግም፣ ሙሉ በሙሉ ያባርራችኋል።
\v 2 ወንድና እያንዳንዱ ሴት ከጎረቤቱ ወይም ከጎረቤቱ የብርና የወርቅ ዕቃዎችን ስጡን ብለው እንዲጠይቁ ለሕዝቡ ተናገር።”
\v 3 እስራኤላውያንን ደስ ለማሰኘት ግብፃውያን እንዲነሣሡ አደረገ። ሙሴም በፈርዖን አገልጋዮችና በግብፅ ሕዝብ ዘንድ እጅግ የሚደነቅ ሰው ሆነ።
\s5
\v 4 እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር ይህን ተናግሯል፦ ‘እኩለ ሌሊት ላይ በመላው ግብፅ ዐልፋለሁ።
\v 5 ላይ ከሚቀመጠው ከፈርዖን በኵር ልጅ ጀምሮ፣ ወፍጮ ላይ እስከምትፈጨዋ እስከ ባሪያዪቱ በኵር ልጅና እስከ እንስሳቱ በኵር ሁሉ ድረስ በግብፅ ምድር ያሉ በኵር በሙሉ ይሞታል።
\s5
\v 6 በቀድሞው ጊዜ ያልነበረ እንደገናም የማይደገም ታላቅ ዋይታ በግብፅ ምድር ሁሉ ይሆናል።
\v 7 ሕዝብ ላይ ግን፣ በሰውም ሆነ በእንስሳ ላይ ውሻ እንኳ አይጮኽም። በዚህም ግብፃውያንንና እስራኤላውያንን የማስተናግድበት መንገድ የተለያየ እንደ ሆነ ታውቃላችሁ።’
\v 8 እነዚህ አገልጋዮችህ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣሉ፤ ለእኔም ይሰግዳሉ። ‘አንተና ተከታዮችህ ሁሉ ሂዱ! ብለውም ይናገራሉ። ከዚያ በኋላ እወጣለሁ።” ከዚያም ሙሉ ከፈርዖን ዘንድ በትልቅ ቊጣ ወጥቶ ሄደ።
\s5
\v 9 ሙሴን፣ “ፈርዖን እናንተን አይሰማችሁም። ይህም የሆነው ብዙ አስደናቂ ነገሮችን በግብፅ ምድር ላይ እንዳደርግ ነው” አለው።
\v 10 አሮን እነዚህን ድንቆች ሁሉ በፈርዖን ፊት አደረጉ። ነገር ግን እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ ስላደነደነው፣ ፈርዖን የእስራኤል ሕዝብ ከምድሩ እንዲወጡ አልፈቀደም።
\s5
\c 12
\p
\v 1 በግብፅ ምድር ለሙሴና ለአሮን እንዲህ ብሎ ነገራቸው፤
\v 2 ወር ለእናንተ የወሮች መጀመሪያ፣ የዓመቱም የመጀመሪያ ወር ይሁናችሁ።
\s5
\v 3 ጉባኤ ይህን ንገሩ፤ ‘በዚህ ወር ዐሥረኛ ቀን ላይ እያንዳንዳቸው ለራሳቸው አንድ ጠቦት የሚያንስ ከሆነ፣
\v 4 የቅርብ ጎረቤቱ ከቊጥራቸው ጋር የሚመጣጠን ጠቦት ያዘጋጁ። የሚመገቡትን በቂ ሥጋ መውሰድ እንዲችሉ፣ ጠቦቱ ለሁሉም የሚበቃ መሆን አለበት።
\s5
\v 5 ወይም የፍየል ጠቦታችሁ እንከን የሌለበት የአንድ ዓመት ተባት ጠቦት ሊሆን ይገባል። ከበጎቹ ወይም ከፍየሎቹ አንዱን ልትወስዱ ትችላላችሁ።
\v 6 እስከ ወሩ ዐሥራ አራተኛ ወር ድረስ አቆዩአቸው። ከዚያም መላው የእስራኤል ጉባኤ እነዚህን እንስሳት ፀሐይ ስትጠልቅ ይረዷቸው።
\v 7 ከዚያም ከደሙ ጥቂት ውሰዱና ሥጋውን በምትበሉበት ቤት በር መቃንና ጉበን ላይ አድርጉት።
\v 8 በእሳት ከጠበሳችሁት በኋላ፣ በዚያው ሌሊት ከቂጣና ከመራራ ቅጠል ጋር ብሉት።
\s5
\v 9 ወይም ቅቅሉን አትብሉት። ይልቁን ከጭንቅላቱ፣ ከእግሮቹና ከሆድ ዕቃው ጋር በእሳት ጠብሳችሁ ብሉት።
\v 10 ድረስ ከሥጋው አንዳችም አታስቀሩ። የተራረፈ ነገር ቢኖር፣ በእሳት ይቃጠል።
\v 11 ወገባችሁን ታጥቃችሁ፣ ጫማችሁን አጥልቃችሁና በትራችሁን በእጃችሁ ይዛችሁ ነው። ተጣድፋችሁ ልትበሉት ይገባል። የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው።
\s5
\v 12 በዚያ ሌሊት በግብፅ ምድር ሁሉ ዐልፋለሁ፤ በግብፅ ምድርም የሰውንና የእንስሳትን በኵር በሙሉ እመታለሁ። በግብፅ አማልክት ሁሉ ላይ እፈርድባቸዋለሁ። እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
\v 13 ደሙ እኔ ወደ እናንተ በቤቶቻችሁ ላይ ምልክት ይሆናል። ደሙንም በማይበት ጊዜ የግብፅን ምድር ስመታ እናንተን ዐልፌአችሁ እሄዳለሁ። ይህ መቅሠፍት በእናንተ ላይ አይመጣም፤ አያጠፋችሁምም።
\v 14 ቀን የእግዚአብሔር በዓል ቀን አድርጋችሁ የምታከብሩት የመታሰቢያ ቀን ይሆንላችኋል። ቀኑን እንድታከብሩት ለእናንተ፣ ለትውልዶቻችሁም ሁሉ ቋሚ ሥርዐት ይሆናችኋል።
\s5
\v 15 ቀን ቂጣ ትበላላችሁ። በመጀመሪያው ቀን እርሾውን ከቤታችሁ ታስወግዳላችሁ። ከመጀመሪያው ቀን እስከ ሰባተኛው ቀን እርሾ ያለበትን እንጀራ የበላ ሰው ሁሉ ከእስራኤል ይወገድ።
\v 16 በመጀመሪያው ቀን ለእኔ የተቀደሰ ጉባኤ ይደረጋል፤ በሰባተኛውም ቀን እንደዚሁ ያለ ሌላ ጉባኤ ይሆናል። ሁሉም የሚበላውን ከመቀቀል በቀር፣ በእነዚህ ቀኖች ሥራ አይሠራም። የምትሠሩት የምግብ ዝግጅቱን ሥራ ብቻ ነው።
\s5
\v 17 በዓልን አክብሩት ምክንያቱም ሕዝባችሁን ሰራዊት በሰራዊት አድርጌ ከግብፅ ምድር ያወጣሁት በዚህ ቀን ነው። ስለዚህ ይህን ቀን በትውልዶቻችሁ ሁሉ አክብሩት፤ ለእናንተ ቋሚ ሥርዓት ይሆናችኋል።
\v 18 የመጀመሪያ ወር ዐሥራ አራተኛ ቀን ፀሐይ መጥለቅ አንሥቶ፣ እስከ ወሩ ሃያ አንደኛ ቀን ፀሐይ መጥለቅ ድረስ ቂጣ ትበላላችሁ።
\s5
\v 19 በሰባቱ ቀኖች በቤታችሁ ውስጥ እርሾ መገኘት የለበትም። እርሾ ያለበት እንጀራ የሚበላ እንግዳም ሆነ በምድራችሁ የተወለደ ሰው ከእስራኤል ማኅበረ ሰ ይወገዳል።
\v 20 የተጋገረ አንዳችም መብላት የለባችሁም። የትም ብትኖሩ፣ መብላት የሚገባችሁ እርሾ የሌለበትን ነው።”
\s5
\v 21 በኋላ ሙሴ የእስራኤልን ሽማግሌዎች ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ሂዱና ቤተ ሰቦቻችሁን ለመመገብ የሚበቁ ጠቦቶችን ወይም ግልገሎችን መርጣችሁ የፋሲካን በግ ዕረዱ።
\v 22 ጭብጥ የሂሶጵ ቅጠል ያዙና በሳሕን ውስጥ በሚቀመጠው ደም ውስጥ በመንከር፣ የቤታችሁን ጉበን ዐናትና ሁለቱን መቃኖች እርጩ። እስኪነጋ ድረስ ከእናንተ አንድም ከቤቱ አይወጣ።
\s5
\v 23 ለመቅሠፍት እግዚአብሔር ስለሚያልፍ፣ ደሙን በጉበኑ ዐናትና በሁለቱ መቃኖች ላይ ሲያይ፣ በበራፋችሁ ላይ ያልፋል፣ ቀሣፊውም ወደ ቤታችሁ እንዲገባና እናንተን እንዲቀሥፋችሁ አይፈቅድም።
\s5
\v 24 ይህ ሥርዐት ለእናንተም ለልጆቻችሁም የሁልጊዜ ሥርዐት ስለ ሆነ ልታከብሩት ይገባል።
\v 25 ቃል በገባላችሁ መሠረት፣ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ስትገቡ፣ ይህን የአምልኮ ሥርዐት ጠብቁት።
\s5
\v 26 ‘ይህ የአምልኮ ሥርዐት ምን ትርጕም አለው? ብለው በሚጠይቋችሁ ጊዜ፣
\v 27 እንደዚህ ብላችሁ ልትነግሯቸው ይገባል፤ ‘ይህ የእግዚአብሔር ፋሲካ መሥዋዕት ነው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ግብፃውያንን ሲቀሥፍ፣ በግብፅ ውስጥ በእስራኤላውያን ቤቶች ዐልፎ ሄዶአል። ቤተ ሰቦቻችንን ነጻ አውጥቷቸዋል።” ከዚያም ሕዝቡ ሰገዱ፣ እግዚአብሔርንም አመለኩት።
\v 28 ሄደው እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዳዝዛቸው አደረጉ።
\s5
\v 29
እኩለ ሌሊት ላይ በዙፋኑ ላይ ከሚቀመጠው ከፈርዖን በኵር ልጅ ጀምሮ፣ በእስር ቤት ውስጥ እስካለው ሰው በኵር ልጅና እስከ እንስሳት በኵር ሁሉ ድረስ፣ እግዚአብሔር በግብፅ ምድር የሚገኝን በኵር በሙሉ ቀሠፈ።
\v 30 አገልጋዮቹ ሁሉና ግብፃውያን በሙሉ ሌሊት ላይ ተነሡ። በግብፅ ውስጥ ጕልሕ የልቅሶ ጩኸት ነበረ፤ ሰው ያልሞተበት እንደም ቤት አልነበረምና።
\s5
\v 31 ሙሴንና አሮንን በሌሊት አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ተነሡ፤ እናንተና እስራኤላውያን ከሕዝቤ መካከል ውጡ። ማድረግ የምትፈልጉትን እንደ ተናገራችሁ ሂዱ፣ እግዚአብሔርን አምልኩ።
\v 32 እንደ ተናገራችሁት፣ የበግና የፍየል መንጎቻችሁን፣ የቀንድና የጋማ ከብቶቻችሁንም ይዛችሁ ሂዱ፤ እኔንም ባርኩኝ።”
\v 33 እስራኤላውያንን ከአገራቸው ለማባረር በትልቅ ጥድፊያ ላይ ነበሩ፤ “ሁላችንም ማለቃችን ነው” ብለው ነበርና።
\s5
\v 34 ሕዝቡ እርሾ ያልተጨመረበትን ሊጣቸውን ያዙ። የቡሆ እቃዎቻቸውን ቀድሞውኑ በጨርቃቸው አስረው በትከሾቻቸው ተሸክመዋቸዋል።
\v 35 ሕዝብ ሙሴ እንደ ነገራቸው አደረጉ። የወርቅና የብር ዕቃዎችን፣ ልብስም እንዲሰጧቸው ግብፃውያንን ጠየቁ።
\v 36 ደስ ለማሰኘት እግዚአብሔር ግብፃውያንን አነሣሣ። ስለዚህ እስራኤላውያን የጠየቋቸውን ሁሉ ግብፃውያን ሰጧቸው። በዚህ መንገድ፣ እስራኤላውያን ግብፃውያንን በዘበዟቸው።
\s5
\v 37 ከራምሴ በመነሣት ወደ ሱኮት ተጓዙ። ቊጥራቸው ከሕፃናቱና ከሴቶቹ ሌላ ስድስት መቶ ሺሕ ያህል እግረኛ ነበር።
\v 38 እስራኤላዊ ያልሆነ ድብልቅ ሕዝቤም፣ ከበግና ከፍየል፣ እጅግ ብዙ ከሆነ የከብት መንጋ ጋር ዐብሯቸው ሄደ።
\v 39 ከግብፅ ያመጡትን እርሾ ተባርረው ስለ ወጡና ምግብ ማዘጋጀት ስላልቻሉ ነው።
\v 40 እስራኤላውያን በግብፅ ውስጥ የኖሩት አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ነበር።
\s5
\v 41 መቶ ሠላሳው ዓመት ፍጻሜ፣ በዚያው ቀን፣ ሁሉም የእግዚአብሔር ሰራዊት ከግብፅ ምድር ወጣ።
\v 42 ሌሊት እግዚአብሔር ከግብፅ ምድር እንዲያወጣቸው ለእስራኤላውያን ነቅቶ የመቆያ ሌሊት ነበር። ይህ ሌሊት እስራኤላውያን ሁሉ፣ መላ ትውልዶቻቸው ሊያከብሩት የሚገባ ሌሊት ነው።
\s5
\v 43 እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ “የፋሲካ ሕግ እነሆ፦ ባዕድ ሰው ፋሲካን አይበላውም።
\v 44 የተገዛ እያንዳንዱ የእስራኤል ባሪያ ግን ከገረዛችሁት በኋላ መብላት ይችላል።
\s5
\v 45 ቅጥር አገልጋዮች መብላት አይገባቸውም።
\v 46 ምግቡ በአንድ ቤት ውስጥ መበላት አለበት። ሥጋ ከቤት ማውጣት፣ ዐጥንትም መስበር የለባችሁም።
\s5
\v 47 የእስራኤል ማኅበረ ሰብ በዓሉን ሊያከብር ይገባል።
\v 48 ባዕድ ሰው ከእናንተ ጋር ቢኖርና ፋሲካን ለእግዚአብሔር ለማክበር ቢፈልግ፣ ወንድ ዘመዶቹ ሁሉ መገረዝ አለባቸው። ከዚያም በኋላ፣ ሰውየው መምጣትና በዓሉን ማክበር ይችላል። በምድሩ እንደ ተወለዱት ሰዎች ይሆናል። ይሁን እንጂ፣ ያልተገረዘ ሰው የፋሲካን ምግብ አይበላም።
\s5
\v 49 አንድ ዐይነት ሕግ ተግባራዊ የሚሆነው በሁለቱም ማለት በአገሬው ተወላጅና በመካከላችሁ በሚኖረው ባዕድ ሰውም ላይ ነው።”
\v 50 እስራኤላውያን ሁሉ እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዳዘዛቸው አደረጉ።
\v 51 በዚያው ቀን እግዚአብሔር እስራኤላውያንን በየሰራዊታቸው ከግብፅ ምድር አወጣቸው።
\s5
\c 13
\p
\v 1 ሙሴን እንዲህ አለው፤
\v 2 ‘በእስራኤላውያን ዘንድ ከሰውም ሆነ ከእንስሳት በመጀመሪያ የተወለደውን ወንድ ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ። በኵር የእኔ ነው።”
\s5
\v 3 ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “ከባርነት ቤት ከግብፅ የወጣችሁበትን ይህን ቀን አስታውሱት፤ በዚህ ቀን እግዚአብሔር በብርቱ እጁ ከዚህ ስፍራ አውጥቶአችኋልና። እርሾ ያለበት ምግብ አይበላም።
\v 4 በዚህ ቀን፣ በአቢብ ወር ከግብፅ ወጥቷችኋል።
\v 5 ለእናንተ ለመስጠት ለአባቶቻችሁ ወደ ማለላቸው፣ ማርና ወተት ወደምታፈስሰው፣ ወደ ከነዓናውያን፣ ኬጢያውያን፣ አሞራውያን፣ ኤውያውያን፣ ኢያቡሳውያን ምድር እግዚአብሔር ሲያስገባችሁ፣ ይህን አምልኮ በዚህ ወር ትፈጽማላችሁ።
\s5
\v 6 ቀን ቂጣ ትበላላችሁ፤ በሰባተኛውም ቀን እግዚአብሔርን የምታከብሩበት በዓል ይሆናል።
\v 7 ቀን ሁሉ መበላት ያለበት ቂጣ ነው፤ እርሾ ያለበት እንጀራ በእናንተ ዘንድ መታየት የለበትም። በአዋሳኞቻችሁም ዘንድ እርሾ አይኑር።
\s5
\v 8 ቀን፣ ‘ይህ እንዲህ የሚሆነው ከግብፅ ስወጣ እግዚአብሔር ለእኔ ካደረገው የተነሣ ነው’ ብላችሁ ለልጆቻችሁ ትነግሯቸዋላችሁ።’
\v 9 ይህም በእጃችሁና በግንባራችሁ ላይ መታሰቢያ ይሆናል። ይኸውም እግዚአብሔር በብርቱ እጁ ከግብፅ ስላወጣችሁ፣ የእግዚአብሔር ሕግ በአፋችሁ እንዲሆን ነው።
\v 10 ይህን ሕግ በየዓመቱ በተወሰነለት ጊዜ ልትጠብቁት ይገባል።
\s5
\v 11 ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በማለው መሠረት፣ እግዚአብሔር ወደ ከነዓናውያን ምድር ሲያስገባችሁ፣
\v 12 በመጀመሪያ የተወሰደውን፣ የእንስሶቻችሁንም በኵር ሁሉ ለእግዚአብሔር ቀድሱ። ወንዶች የእግዚአብሔር ናቸው።
\v 13 ከአህያ በመጀመሪያ የተወለደውን ሁሉ በጠቦት ትዋጁታላችሁ። ካልዋጃችሁት፣ ዐንገቱን ስበሩት። ከወንድ ልጆቻችሁ መካከል በኵር የሆኑትን ሁሉ ዋጇቸው።
\s5
\v 14 ልጅህ፣ ‘ይህ ምን ማለት ነው? ብሎ ወደፊት ቢጠይቅህ፣ እንደዚህ ትነግረዋለህ ‘ከባርነት ቤት፣ ከግብፅ እግዚአብሔር ያወጣን በብርቱ እጅ ነበር።
\v 15 እኛን ለመልቀቅ በግትርነት እንቢ ባለ ጊዜ፣ እግዚአብሔር በግብፅ ምድር ያለውን በኵር ሁሉ፣ የሰውንም ሆነ የእንስሳትን በኵር በሙሉ ገደለ። ከእንስሳት ሁሉ በመጀመሪያ የተወለደውን ለእግዚአብሔር የምሠዋውና ከወንድ ልጆችም በኵር የሆነውን የምዋጀውን በዚህ ምክንያት ነው።’
\v 16 ከግብፅ ያወጣን በብርቱ እጅ ነውና፣ ይህ በእጅህና በግንባር ላይ ማስታወሻ ይሆናል።”
\s5
\v 17 ሕዝቡን ሲለቅቃቸው፣ እግዚአብሔር ምንም እንኳ ቅርብ ቢሆንም፣ በፍልስጥኤማውያን ምድር ባለው መንገድ አልመራቸውም። እግዚአብሔር፣ “ሕዝብ ጦርነት ቢያጋጥማቸው፥ ምናልባት ሐሳባቸውን ይለውጣሉ፣ ወደ ግብፅም ይመለሳሉ” ብሎ ነበርና።
\v 18 እግዚአብሔር ሕዝቡን በምድረ በዳው ዙሪያ ውደ ቀይ ባሕር መራቸው። እስራኤላውያን ለውጊያ ተዘጋጅተው ከግብፅ ምድር ወጥተው ሄዱ፣
\s5
\v 19 ሙሴ የዮሴፍን ዐፅም ይዞ ሄደ፤ ምክንያቱም ዮሴፍ፣ “እግዚአብሔር በእርግጥ ይታደጋችኋልና ዐፅሜን ይዛችሁ እንድትሄዱ” በማለት እስራኤላውያንን አስምሎአቸው ነበር።
\v 20 ከሱኮት በመጓዝ ምድረ በዳው ዳር ላይ በሚገኘው በአታም ሰፈሩ።
\v 21 እግዚአብሔር ሕዝቡን በመንገድ ላይ ሊመራቸው ቀን ቀን በደመና ዐምድ በፊታቸው ሄደ። ሌሊት ሌሊት ደግሞ ብርሃን ሊሰጣቸው በእሳት ዐምድ ሄደ። በዚህ ዐይነት ሕዝቡ በቀንም በሌሊትም መጓዝ ቻሉ።
\v 22 እግዚአብሔር የቀኑን የደመና ዐምድ ወይም የሌሊቱን የብርሃን ዐምድ ከሕዝቡ ፊት አላነሣም።
\s5
\c 14
\p
\v 1 ለሙሴ እንዲህ ብሎ ተናገር፤
\v 2 በሚግዶልና በባሕሩ መካከል ባለው በፊሀሒሮት ፊት፣ በበኣልዛፎንም አንጻር እንዲሰፍሩ ለእስራኤላውያን ንገር። በፊሀሒሮት ትይዩ በባሕሩ አጠገብ ትሰፍራላችሁ።
\v 3 ፈርዖን ስለ እስራኤላውያን፣ ‘በምድሪቱ እየተንከራተቱ ነው፤ ምድረ በዳውም ዘግቶባቸዋል’ ይላል።
\s5
\v 4 የፈርዖንን ልብ እኔ አደነድነዋለሁ፤ እርሱም እስራኤላውያንን ይከታተላቸዋል። በፈርዖንና በመላው ሰራዊቱ ምክንያት እኔ እከብራለሁ። ግብፃውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።” ስለዚህ እስራኤላውያን በተነገራቸው መሠረት ሰፈሩ።
\v 5 ንጉሥ እስራኤላውያን እንደ ሄዱ ሲነገረው፣ ፈርዖንና አገልጋዮቹ ሐሳባቸውን በመለወጥ፣ እስራኤላውያን ለእኛ ከመሥራት ነጻ ሆነው እንዲሄዱ መፍቀዳችን ምን ማድረጋችን ነው? አሉ።
\s5
\v 6 ሠረገላዎቹ እንዲዘጋጁለት አደረገ፤ ሰራዊቱንም ከእርሱ ጋር ይዞ ሄደ።
\v 7 መቶ ምርጥ ሠረገሎችንና የግብፅን ሌሎች ሠረገሎች በሙሉ፣ በያንዳንዳቸው ላይ መኮንኖች ያሉባቸውን ይዞ ተንቀሳቀሰ።
\v 8 እግዚአብሔር የግብፅን ንጉሥ፣ የፈርዖንን ልብ ስላደነደነው፣ ንጉሡ እስራኤላውያንን ተከታተላቸው። አሁን እስራኤላውያን በድል ወጥተው ሄደዋል።
\v 9 ነገር ግን ግብፃውያን፣ ሁሉም የፈርዖን ፈረሶችና ሠረገሎች፣ የፈርዖን ፈረሰኞችና ሰራዊቱ እስራኤላውያንን አሳደዷቸው። በበኣልዛፎን አንጻር በባሕሩ አጠገብ ፊሀሒሮት ጥግ ሰፍረው እንዳሉ ደረሱባቸው።
\s5
\v 10 ፈርዖን በቀረ ጊዜ፣ እስራኤላውያን ወደ ላይ ተመለከቱ፣ ተደነቁም። ግብፃውያን ከኋላ እየተከተሏቸው ነበርና ፈሩ። እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።
\v 11 እንዲህ አሉት፤ “እዚህ ያመጣኸንና በምድረ በዳ እንድንሞት ያደረግኸው በግብፅ መቃብር ታጥቶ ይህን ነግረንህ አልነበረምን?
\v 12 ሠራተኞች እንድንሆን ተወን’ ብለንህ ነበር። በምድረ በዳ ከምንሞት፣ ለእነርሱ ሠራተኞች ሆነን ብንቀር ይሻል ነበር።’”
\s5
\v 13 እንዲህ አላቸው፤ “አትፍሩ። ጸንታችሁ ቁሙና ዛሬ እግዚአብሔር ለእናንተ የሚያደርግላችሁን ትድግና ታያላችሁ። ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ዳግም አታዩአቸውም።
\v 14 እግዚአብሔር ለእናንተ ይዋጋል፤ እናንተ መታገሥ ብቻ ነው ያለባችሁ።”
\s5
\v 15 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “አንተ ሙሴ ለምን ትጮኽብኛለህ? እስራኤላውያን ወደ ፊት እንዲሄዱ ንገራቸው።
\v 16 የእስራኤል ስዎች በባሕሩ ውስጥ በደረቅ መሬት እንዲሻገሩ በትርህን አንሣና እጅህን በባሕሩ ላይ ዘርግተህ ለሁለት ክፈለው።
\v 17 ተከትለዋቸው እንዲገቡ እኔ የግብፃውያንን ልብ የማደነድን መሆኔን ዕወቅ። ከፈርዖንና ከሰራዊቱ ሁሉ፣ ከሠረገሎቹና ከፈረሰኞቹ የተነሣ እኔ እከብራለሁ።
\v 18 በፈርዖን፣ ሠረገሎቹና በፈረሰኞቹ ምክንያት ክብርን ሳገኝ፣ ግብፃውያኑ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”
\s5
\v 19 ፊት ይሄድ የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ በስተ ኋላቸው ሄደ። የደመናውም ዐምድ ከፊታቸው ተንቀሳቅሶ በስተኋላቸው ሄዶ ቆመ።
\v 20 በግብፅ ሰራዊትና በእስራኤል መካከል መጣ። ለግብፃውያን የጨለማ ደመና ሲሆን፣ ለእስራኤላውያን ግን ሌሊቱን ብሩህ ያደረገ ደመና ነበር፤ ይህም ሌሊቱን ሙሉ አንደኛው ወገን ወደ ሌላው እንዳይጠጋ አደረገ።
\s5
\v 21 እጁን በባሕሩ ላይ ዘረጋ። እግዚአብሔርም በዚያ ሌሊት ባሕሩን በብርቱ የምሥራቅ ነፋስ ወደ ኋላ እንዲሄድ በማድረግ ባሕሩን ደረቅ መሬት አደረገው። በዚህ መንገድ ውሃው ተከፈለ።
\v 22 እስራኤላውያን በባሕሩ መካከል ገብተው በደረቅ መሬት ዐለፉ። ውሃው በቀኛቸውና በግራቸውና በኩል ግድግዳ ሆነላቸው።
\s5
\v 23 ተከታትለዋቸው መጡ። እነርሱ፣ የፈርዖን ፈረሶች ሠረገሎችና ፈረሰኞች ሁሉ እስራኤላውያኑ ተከትለው በባሕሩ መካከል ገቡ።
\v 24 ላይ እግዚአብሔር በእሳቱና በደመናው ዐምድ ውስጥ የግብፃውያንን ሰራዊት ወደ ታች ተመለከተ። በግብፃውያን መካከልም ሽብር እንዲፈጠር አደረገ።
\v 25 የሠረገሎቻቸው መንኯራኵሮች ተቆላለፉ፤ ፈረሰኞችም ለመንቀሳቀስ እጅግ ተቸገሩ። ስለዚህ ግብፃውያኑ፣ እግዚአብሔር እኛን እየወጋላቸው ነውና፣ ከእስራኤል እንሽሽ” አሉ።
\s5
\v 26 ሙሴን፣ “ውሃው በግብፃውያኑ፣ በሠረገሎቻቸውና በፈረሰኞቻቸው ላይ ተመልሶ እንዲመጣባቸው እጅህን በባሕሩ ላይ ዘርጋ” አለው።
\v 27 እጁን በባሕሩ ላይ ዘረጋ፤ ንጋት ላይም ባሕሩ ወደ ተለመደ ስፍራው ተመለሰ። ግብፃውያኑ ከባሕሩ ሸሹ፤ እግዚአብሔር ግን ወደ ባሕሩ መካከል አስገባቸው።
\v 28 ውሃው ተመስሎ በመምጣት የፈረዖንን ሠረገሎች፣ ፈረሰኞችን ሠረገሎቹን ተከትለው ወደ ባሕሩ የገቡትን ጠቅላላ ሰራዊቱን ሸፈናቸው። አንድም ሳይሰምጥ የቀረ አልነበረም።
\s5
\v 29 ግን በባሕሩ መካከል በደረቅ መሬት ላይ ተራምደው ሄዱ። ውሃው በቀኛቸውም በግራቸውም በኩል ለእነርሱ ግድግዳ ሆናላቸዋል።
\v 30 እግዚአብሔር በዚያ ቀን እስራኤላውያንን ከግብፃውያን እጅ ታደጋቸው፤ እስራኤላውያኑም የግብፃውያኑን ሬሳ በባሕሩ ዳር አዩ።
\v 31 እግዚአብሔር በግብፃውያኑ ላይ የገለጠውን ታላቅ ኀይል ሲያዩ፣ ሕዝቡ እግዚአብሔርን አከበሩ፣ በእግዚአብሔርና በአገልጋዩ በሙሴም ታመኑ።
\s5
\c 15
\p
\v 1 ጊዜ ሙሴና የእስራኤል ሕዝብ ይህን መዝሙር ለእግዚአብሔር እንዲህ እያሉ ዘመሩ፦ “በክብር ከፍ ከፍ ብሎአልና ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ውስጥ ጥሎአል።
\s5
\v 2 ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም ሆኖልኛል። እርሱ አምላኬ ነው፣ አመሰግነዋለሁ፤ የአባቴ አምላክ ነው፣ ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።
\v 3 ተዋጊ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው።
\s5
\v 4 ሠረገሎችና ሠራዊት በባሕር ውስጥ ጥሎአል። የፈርዖን ምርጥ መኮንኖች በቀይ ባሕር ውስጥ ሰመጡ።
\v 5 ማዕበሎቹ ሽፈናቸው፤ እንደ ድንጋይ ወደ ጥልቆቹ ወረዱ።
\s5
\v 6 እግዚአብሔር ሆይ፣ ቀኝ እጅህ ጠላትን ሰባበረ።
\v 7 ላይ የተነሡትን በታላቅ ግርማ ገለበጥሃቸው። ቊጣህን ላክህ፤ እንደ ገለባም አርጎ በላቸው።
\v 8 በአፍንጫህ እስትንፋስ ውሆች ተከመሩ፤ ፈሳሾች እንደ ክምር ቆሙ፤ የጥልቁ ውሃ በባሕሩ ውስጥ ረጋ።
\s5
\v 9 ጠላት፣ ‘አሳድዳቸዋለሁ፣ እይዛቸዋለሁ፣ ምርኮም እካፈላለሁ፤ ፍላጎቴ በእነርሱ ርዳታ ያገኛል፤ ሰይፌን እመዝዛለሁ፤ እጄም ታጠፋቸዋለች’ አለ።
\v 10 ግን በነፋስህ እፍ አልህ፣ ባሕሩም ሸፈናቸው፤ በኀይለኛ ውሆች ውስጥ እንደ ብረት ሰመጡ።
\v 11 ሆይ፣ ክአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በቅድስና የከበረ፣ ተአምራትን በማድረግ በምስጋና ከፍ ያለ፣ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?
\s5
\v 12 እጅህን ዘረጋህ፤ ምድርም ዋጠቻቸው።
\v 13 ፍቅርህ የታደግሃቸውን ሕዝብህን መራህ። በብርታትህ ወደ ቅዱስ ማደሪያህ መራሃቸው።
\s5
\v 14 ይሰማሉ፣ ይንቀጠቀጣሉም፤ የፍልስጥኤምን ኗሪዎች ሽብር ይይዛቸዋል።
\v 15 ጊዜ የኤዶም እለቆች ይደነግጣሉ፤ የሞዓብ መሪዎች ይርበደበዳሉ፤ የከነዓን ኗሪዎች ሁሉ ይቀልጣሉ።
\s5
\v 16 ሆይ፣ ሕዝብህ እስከሚያልፉ፣ የታደግሃቸው ሕዝብህ ዐልፈው እስከሚሄዱ ድረስ፣ ሽብርና ድንጋቴ ይወድቅባቸዋል፤ ከክንድህ ብርታት የተነሣ፣ እንደ ድንጋይ የማይንቀሳቀሱ ይሆናሉ።
\s5
\v 17 ሆይ፣ ማደሪያህ ባደረግኸው ስፍራ፣ ጌታችን ሆይ፣ እጆችህ በሠሩት መቅደስ፣ በርስትህ ተራራ ላይ ሕዝብህን ታመጣቸዋለህ፣ ትተክላቸዋለህም።
\v 18 ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል።”
\s5
\v 19 ፈረሶች ከሠረገሎቹና ከፈረሰኞቹ ጋር ወደ ባሕሩ ውስጥ ሲገቡ፣ እግዚአብሔር የባሕሩን ውሀ መልሶ በላያቸው አመጣባቸው። እስራኤላውያን ግን በባሕሩ መካከል በደረቅ መሬት ሄዱ።
\v 20 ይአሮን እኅት፣ ነቢይቱ ማርያም ከበሮ አነሣች፤ ሌሎቹ ሴቶችም በሙሉ ከበሮ ይዘው ከእርሷ ጋር እያሸበሸቡ ወጡ።
\v 21 “ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ውስጥ ጥሎአል፤ በክብር ከፍ ከፍ ብሎአልና፣ ለእግዚአብሔር ዘመሩ” እያለች ዘመረችላቸው።
\s5
\v 22 ሙሴ እስራኤላውያንን ከቀይ ባሕር እየመራቸው ወደ ሱር ምድረ በዳ ሄዱ። በምድረ በዳው ውስጥ ሦስት ቀን ሲጓዙ ውሀ አላገኙም።
\v 23 ማራም ደረሱ፤ ነገር ግን እዚያ የሚገኘው ውሀ መራራ ስለ ነበረ ሊጠጡት አልቻሉም። ቦታውን ማራ ያሉት ከዚህ የተነሣ ነው።
\s5
\v 24 ሕዝቡ፣ “ምን እንጠጣ?” ብለው በሙሴ ላይ አጕረመረሙ።
\v 25 ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፣ እግዚአብሔርም አንድ ዛፍ አሳየው። ሙሴም የዛፉን ዕንጨት ወደ ውሀው ውስጥ ጣለው፣ ውሀውም ጣፋጭ ሆነ። እግዚአብሔር ለሕዝቡ ሕግና ሥርዐት የሰጣቸውና የፈተናቸው በዚያ ስፍራ ነበር።
\v 26 እንዲህ አለ፤ “የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ድምፅ በጥንቃቄ ብትሰሙ፥ ትክክለኛ የሆነውንም በፊቱ ብታደርጉ፣ ትእዛዛቱንም ብታስተውሉና ሕግጋቱን ሁሉ ብትጠብቁ፣ ግብፃውያን ላይ ካመጣኋቸው በሽታዎች አንዱንም በእናንተ ላይ አላመጣም፤ እኔ ፈዋሻችሁ እግዚአብሔር ነኝና።”
\s5
\v 27 በኋላ ሕዝቡ ዐሥራ ሁለት ምንጮችና ሰባ የዘንባባ ዛፎች ወደ ነበሩበት ወደ ኤሊም መጡ። በዚያም በውሀው አጠገብ ሰፈሩ።
\s5
\c 16
\p
\v 1 የእስራኤል ማኅበር አባላት ከኤሊም ተንሥተው፣ ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው ወር ዐሥራ አምስተኛ ቀን በኤሊምና በሲና መካከል ወዳለው ወደ ሲን ምድረ በዳ መጡ።
\v 2 በዳው ውስጥም ጠቅላላ የማኅበሩ አባላት በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ።
\v 3 ሙሴንና አሮንንም፣ “በሥጋ ምንቸቶች ዙሪያ ተቀምጠን እስክንጠግብ ምግብ በምንበላበት በግብፅ ምድር በእግዚአብሔር እጅ ምነው በሞትን ኖሮ፤ ከዚያ አውጥታችሁ ወደዚህ ምድረ በዳ ያመጣችሁን መላውን ማኅበራችንን በረኃብ ልትጨርሱ ነውና” አሏቸው።
\s5
\v 4 ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እንጀራ ከሰማይ አዘንብላችኋለሁ። በሕጌ የሚመሩ ወይም የማይመሩ መሆናቸውን እንድፈትናቸው፣ ሕዝቡ ይውጡና በየቀኑ ለአንድ ቀን የሚሆነውን ይሰብስቡ።
\v 5 ቀን በየቀኑ ከሚሰበስቡት ዕጥፍ ይሰብስቡ፤ ያመጡትንም ያዘጋጁ።”
\s5
\v 6 ከዚያም ሙሴና አሮን ለእስራኤል ሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አሉ፤ “ከግብፅም ምድር ያወጣችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ማታ ታውቃላችሁ።
\v 7 በእርሱ ላይ ያጕረመረማችሁትን ሰምቶአልና፣ የእግዚአብሔርንም ክብር ጠዋት ታያላችሁ። በእኛ ላይ ልታጕረመርሙ እኛ ለእናንተ ምንድን ነን?”
\v 8 ደግሞ እንዲህ አለ፤ በእርሱ ላይ ያጕረመረማችሁትን ሰምቶታልና፣ እግዚአብሔር ማታ ሥጋ፣ ጠዋትም ምግብ እስክትጠግቡ ሲሰጣችሁ፣ ይህን ታውቁታላችሁ። አሮንና እኔ ምንድን ነን? የምታጕረመርሙት በእኛ ላይ ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር ላይ ነው።”
\s5
\v 9 ሙሴ አሮንን፣ “‘ጕርምርምታችሁን ሰምቶታልና ወደ እግዚአብሔር ፊት ቅረቡ’ በልህ ለእስራኤል ሕዝብ ማኅበር ሁሉ ተናገር’” አለው።
\v 10 አሮን ለእስራኤል ሕዝብ ማኅበር ሁሉ እንደ ተናገረ፣ ወደ ምድረ በዳው ተመለከቱ፤ እነሆም፣ የእግዚአብሔር ክብር በደመናው ውስጥ ታየ።
\v 11 እግዚአብሔርም ለሙሴ እንዲህ ብሎ ነገረው፤
\v 12 “የእስራኤልን ሕዝብ ጕርምርምታ ሰምቻለሁ። እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘ማታ ሥጋ ትበላላችሁ፤ ጠዋት ደግሞ እንጀራ ትበሉና ትጠግባላችሁ። ከዚያም በኋላ እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።
\s5
\v 13 ላይ ድርጭቶች መጡና ሰፈሩን ሸፈኑት። በጠዋቱም የሰፈሩን ዙሪያ ጤዛ ተኝቶበታል።
\v 14 ሲጠፋ፣ እንደ ዐመዳይ ያለ ስስ ቅርፊት በምድረ በዳው ላይ ታየ።
\v 15 ሰዎች ሲያዩት፣ አንዳቸው ለአንዳቸው፣ “ምንድን ነው?” ተባባሉ። ምን እንደ ነበረ አላወቁም። ሙሴም እንዲህ አላቸው፤ “ይህ እንድትበሉት እግዚአብሔር የሰጣችሁ እንጀራ ነው።
\s5
\v 16 እግዚአብሔር ይህን ትእዛዝ ሰጥቶአል፦ ‘ለመብላት የምትፈልጉትን መጠን በሕዝባችሁ ቊጥር ለያንዳንዱ ሰው አንድ ጎሞር ሰብስቡ። የምትሰበስቡት እንደዚህ ነው፦ በድንኳናችሁ ውስጥ ለሚኖር ለእያንዳንዱ ሰው ለመብላት የሚበቃውን ሰብስቡ።”
\v 17 የተነገራቸውን አደረጉ። አንዳንዶች የበለጠ፣ አንዳንዶችም ያነሰ ሰበሰቡ።
\v 18 በጎሞር መጠን ሲለኩት፣ ብዙ የሰበሰቡት የተረፈ አላገኙም፤ ትንሽ የሰበሰቡትም ያጡትናየጎደለባቸው አልነበረም። እያንዳንዱ ሰው የሰበሰበው ለፍላጎቱ የሚበቃውን ያህል ነበር።
\s5
\v 19 “ማንም ሰው ለነገ ከእርሱ ምንም ማስተረፍ የለበትም” አላቸው።
\v 20 ግን ሕዝቡ ሙሴን አልሰሙትም። አንዳንዶቻቸው ከሰበሰቡት እስከሚቀጥለው ጠዋት የተወሰነ አስቀሩ፤ ያስቀሩት ምግብ ግን ተላ፣ ሸተተም። ሙሴ ተቆጣቸው።
\v 21 የሰበሰቡት ጠዋት ጠዋት ነበር። እያንዳንዱ ሰው ለቀኑ የሚበቃውን ሰበሰበ። ፀሐይ ስትሞቅ ቀለጠ።
\s5
\v 22 ቀን ለያንዳንዱ ሰው ሁለት ሁለት ጎሞር እንጀራ አድርገው ዕጥፍ ሰበሰቡ። የማኅበረ ሰቡ አለቆችም በሙሉ መጥተው ለሙሴ ነገሩት።
\v 23 “እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል፦ ‘ነገ ፍጹም ዕረፍት፣ ለእግዚአብሔር ክብር የተቀደሰ ሰንበት ነው። መጋገር የምትፈልጉትን ጋግሩ፤ መቀቀል የምትፈልጉትንም ቀቅሉ። ተርፎ የሚቀረውን ሁሉ እስከ ጠዋት ለራሳችሁ አስቀምጡት’” አላቸው።
\s5
\v 24 የተረፈውን ሙሴ በነገራቸው መሠረት እስከ ጠዋት አቆዩት። አልሸተተም፤ ትልም አልነበረበትም።
\v 25 እንዲህ አለ፤ “ዛሬ እግዚአብሔርን ለማክበር የተቀደሰ ሰንበት ነውና፣ ያስተረፋችሁትን ያን ምግብ ዛሬ ብሉት። ዛሬ ሜላ ላይ አታገኙትም።
\s5
\v 26 ቀኖች ትሰበስቡታላችሁ፤ ሰባተኛው ቀን ግን የሰንበት ቀን ነው። በሰንበት ቀን መና የለም።”
\v 27 ቀን አንዳንዶች መና ሊሰበስቡ ወጡ፣ ነገር ግን ምንም አላገኙም።
\s5
\v 28 ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ትእዛዛቴንና ሕገጋቴን ለመጠበቅ እንቢ የምትሉት እስከ መቼ ነው?
\v 29 በሉ፤ እግዚአብሔር ሰንበትን ሰጥቶአችኋል። ስለዚህ በስድስተኛው ቀን የሰጣችሁ ለሁለት ቀን የሚሆን እንጀራ ነው። ከእናንተ እያንዳንዱ በገዛ ስፍራው ይቆይ፤ በሰባተኛው ቀን ማንም ሰው ከስፍራው መውጣት የለበትም።”
\v 30 በሰባተኛው ቀን ዐረፉ።
\s5
\v 31 ምግቡን “መና” ብለው ጠሩት። ምግቡም እንደ ድንብላል ዘር ነጭ፣ ጣዕሙም በማር በስሱ እንደ ተጋገረ ቂጣ ነበረ።
\v 32 ሙሴም፣ “እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው፦ ‘ከግብፅ ምድር ካወጣኋችሁ በኋላ በምድረ በዳ ያበላኋችሁን እንጀራ ልጆቻችሁ ማየት እንዲችሉ፣ አንድ ጎመር መና ለትውልዶቻችሁ ሁሉ ይቀመጥ” አለ።
\s5
\v 33 አሮንን፣ “አንድ ማሰሮ ውሰድና አንድ ጎሞር መና አስቀምጥበት፤ ለትውልዶች ሁሉ ተጠብቆ እንዲቆይም በእግዚአብሔር ፊት አስቀምጠው” አለው።
\v 34 ሙሴን ባዘዘው መሠረት፣ አሮን መናውን በምስክሩ ፊት አስቀመጠው።
\v 35 ወደሚኖሩበት ምድር እስከሚመጡ ድረስ አርባ ዓመት መና በሉ። ወደ ከነዓን ምድር ድንበር እስከሚመጡ ድረስ የተመገቡት እርሱን ነው።
\v 36 አንድ ጎመር የኢፍ አንድ ዐሥረኛ ነው።
\s5
\c 17
\p
\v 1 የእስራኤል ማኅበር የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመከተል ከሲን ምድረ በዳ ተነሡ፤ በራፊዲምም ሰፈሩ፤ ነገር ግን ሕዝቡ የሚጠጡት ውሀ አልነበረም።
\v 2 ሕዝቡ ሙሴን ወቀሡት፤ “የምንጠጣው ውሀ ስጠን” ብለውም ተናገሩት። ሙሴም፣ “ለምን እኔን ትጣሉኛላችሁ? እግዚአብሔርንስ ለምን ትፈታተኑታላችሁ?” አላቸው።
\v 3 ያ ሕዝቡ ውሀ በጣም ጠምቷቸው ስለ ነበር በሙሴ ላይ አጕረመረሙ። እንዲህም አሉት፤ “እኛንና ልጆቻችንን፣ ከብቶቻችንንም በውሀ ጥም ለመፍጀት ከግብፅ ለምን አወጣኸን?”
\s5
\v 4 እነዚህን ሰዎች ምንድን ነው ማድረግ ያለብኝ? በድንጋይ ሊወግሩኝ ተዘጋጅተዋል” በማለት ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።
\v 5 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ከእስራኤል ሽማግሌዎች አንዳንዶችን፣ ወንዙን የመታህበትንም በትር ያዝና ከሕዝቡ ፊት ቀድመህ ሂድ።
\v 6 ኮሬብ ባለው ዐለት ላይ እኔ ከፊትህ እቆማለሁ፤ ዐለቱንም ትመታዋለህ። ከእርሱም ሕዝቡ የሚጠቱት ውሀ ይወጣል።” ሙሴም በእስራኤል ሽማግሌዎች ፊት የታዘዘውን አደረገ።
\v 7 ስላጕረመረሙና “እግዚአብሔር በመካከላችን አለ ወይስ የለም?” በማለት እግዚአብሔርን ስለ ተፈታተኑት ያን ስፍራ ማሳህና መሪባ ብሎ ጠራው።
\s5
\v 8 መጥተው እስራኤልን ራፊዲም ላይ ወጉ።
\v 9 ስለዚህም ሙሴ ኢያሱን፣ “ጥቂት ሰዎችን ምረጥና ውጣ፤ ከአማሌቃውያን ጋርም ተዋጋ። ነገ እኔ የእግዚአብሔን በትር ይዤ በኮረብታው ዐናት ላይ እቆማለሁ” አለው።
\v 10 ሙሴ ባዘዘው መሠረት አማሌቃውያን ተዋጋቸው፤ ሙሴ፣ አሮንና ሖርም ወደ ኮረብታው ዐናት ወጡ።
\s5
\v 11 እጁን ወደ ላይ ሲያነሣ፣ እስራኤላውያን ድል ያደርጉ ነበር፤ እጁን ሲያወርድ ግን አማሌቃውያን ለማሸነፍ ይጀምሩ ነበር።
\v 12 የሙሴ እጆች እየደከሙ ሲሄዱ፣ አሮንና ሖር ድንጋይ ወስደው እንዲቀመጥበት ከእርሱ ሥር አስቀመጡለት። በዚያውም ጊዜ አሮንና ሖር አንዳቸው በአንድ ጎኑ፣ የቀረውም በሌላው ጎኑ በኩል በመሆን የሙሴን እጆች ወደ ላይ ደግፈው ያዙ። የሙሴ እጆችም ፀሐይ እስክትገባ ድረስ ጠንክረው ቆዩ።
\v 13 ስለዚህም ኢያሱ አማሌቃውያንን በሰይፍ ድል አደረጋቸው።
\s5
\v 14 እግዚአብሔር ሙሴን፣ “የአማሌቃውያንን መታሰቢያ ከሰማይ በታች ሙሉ በሙሉ ስለምደመስስ፣ ይህን በመጽሐፍ ጽፈህ ኢያሱ እየሰማ አንብበው” አለው።
\v 15 ሙሴም መሠዊያ ሠርቶ፣ “እግዚአብሔር አርማዬ ነው” ብሎ ሰየመው።
\v 16 “እጅ ወደ እግዚአብሔር ዙፋን ተነሥቶአልና፣ እግዚአብሔር በአማሌቃውያን ላይ ከትውልድ እስከ ትውልድ ጦርነት ያደርጋል” አለ።
\s5
\c 18
\p
\v 1 ካህን፣ የሙሴ ዐማት ዮቶር ለሙሴና ለሕዝቡ ለእስራኤላውያን እግዚአብሔር ያደረገውን ሁሉ ሰማ። እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከግብፅ ያወጣቸው መሆኑን ዮቶር ሰምቶ ነበር።
\v 2 ሙሴ ወደ ቤት ከመለሳት በኋላ፣ የሙሴ ዐማት ዮቶር የሙሴን ሚስት ሲፓራን፣
\v 3 ምድር ባዕድ ነበርሁ” ሲል ጌርሳም ብሎ የጠራውንና ሌላውንም ልጅ ተቀብሏቸው ነበር።
\v 4 “የአባቶቼ አምላክ ረድቶኛል፤ ከፈርዖንም ሰይፍ አድኖኛል” ብሎ ነበርና፣ የሌላው ልጁ ስም አልዓዛር ነው።
\s5
\v 5 ዐማት ዮቶር ከሙሴ ልጆችና ከሚስቱ ጋር በምድረ በዳው ውስጥ በእግዚአብሔር ተራራ አጠገብ ሰፍሮ ወደ ነበረው ወደ ሙሴ መጣ።
\v 6 ሙሴን፣ “እኔ ዐማትህ፣ ዮቶር ከሚስትህና ከልጆችህ ጋር ወደ አንተ እየመጣሁ ነው” አለው።
\s5
\v 7 ዐማቱን ሊቀበለው ወጣ፤ ሰገደ፤ ሳመውም። ስለ እያንዳንዳቸው ደኅንነት ተጠያይቀው ወደ ድንኳኑ ውስጥ ገቡ።
\v 8 ሙሴም እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ሲል በፈርዖንና በግብፃውያን ላይ ያደረገውን በሙሉ፣ በመንገድም በእነርሱ ላይ የደረሰባቸውን ችግር ሁሉና እግዚአብሔር እንዴት እንደታደጋቸው ለዐማቱ ነገረው።
\s5
\v 9 ዮቶር እስራኤላውያንን ከግብፃውያን እጅ በመታደግ እግዚአብሔር ባደረገው መልካም ነገር ሁሉ ተደሰተ።
\v 10 እንዲህ አለ፤ “ከግብፃውያን እጅና ከፈርዖን እጅ አድኖአችኋል፤ ሕዝቡንም ከግብፃውያን እጅ ታድጎአቸዋልና እግዚአብሔር ይመስገን።
\v 11 እግዚአብሔር ከአማልክት ሁሉ ታላቅ እንደ ሆነ አሁን ዐውቃለሁ፤ ምክንያቱም ግብፃውያን እስራኤላውያንን በትዕቢት ይዘዋቸው በነበረ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሕዝቡን ታድጎአል።”
\s5
\v 12 ዐማት ዮቶር የሚቃጠል መሥዋዕቶችን ለእግዚአብሔር አቀረበ። አሮንና የእስራኤል አለቆች ሁሉ ከሙሴ ዐማት ጋር በእግዚአብሔር ለመብላት መጡ።
\s5
\v 13 በሚቀጥለው ቀን ሙሉ ሕዝቡን ሊዳኝ ተቀመጠ። ሕዝቡ ከጠዋት እስከ ማታ ድረስ በእርሱ ዙሪያ ቆሙ።
\v 14 የሙሴ ዐማት ሙሴ ለሕዝቡ ያደረገውን ሁሉ ተመልክቶ፣ “ምን እያደረግህ ነው? ብቻህን ለምን ትቀመጣለህ? ሰዎችስ ሁሉ ከጧት እስከ ማታ ድረስ ለምን በአንተ ዙሪያ ይቆማሉ?” አለው።
\s5
\v 15 ዐማቱን እንዲህ አለው፤ “ሰዎቹ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመጠየቅ ወደ እኔ ይመጣሉ።
\v 16 ሲኖራቸው፣ ወደ እኔ ይመጡና በመካከላቸው ላለው ችግር ውሳኔ እሰጣለሁ፤ የእግዚአብሔርን ሕገጋትና ሥርዐትም አስተምራቸዋለሁ።”
\s5
\v 17 ዐማቱም ሙሴን መልሶ እንዲህ አለው፤ “የምታደርገው ተገቢ አይደለም።
\v 18 ዐብረውህ ያሉ ሰዎች በእውነት ራሳችሁን ታደክማላችሁ። ይህ ለአንተ ከባድ ሸክም ነው። ይህን ተግባር ብቻህን ማከናወን አትችልም።
\v 19 ስማኝ። ምክር እሰጥሃለሁ፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሆናል፤ ምክንያቱም አንተ በእግዚአብሔር ፊት የሕዝቡ ወኪል ነህ፤ አቤቱታቸውንም ወደ እግዚአብሔር ታቀርባለህ።
\v 20 ሥርዐታትና ሕገጋት ልታስተምራቸው፣ የሚሄዱበትን መንገድና የሚሠሩትን ሥራም ልታሳያቸው ይገባል።
\s5
\v 21 እግዚአብሔርን የሚፈሩ ችሎታቸውን፣ ኢፍትሓዊ ጥቅምን የሚጠሉ የእውነት ሰዎችንከሕዝቡ ሁሉ ምረጥ። ዕነርሱን መሪዎች እንዲሆኑ በሕዝቡ ላይ ሸለቆች፣ መቶ አለቆች፣ ዐምሳ አለቆችና ዐሥር አለቆች አድርገህ ሹማቸው።
\v 22 ጉዳዮችን ሁሉ በሚመለከት ሕዝቡን የሚዳኙት እነርሱ ይሆናሉ፤ ከባድ ከባድ ጉዳዮችን ግን ወደ አንተ ያቀርባሉ። አነስተኛ ጉዳዮችን ሁሉ በሚመለከት፣ እነርሱ ራሳቸው ውሳኔ ሊሰጡባቸው ይችላሉ። በዚህ መንገድ ሥራው ለአንተ ይቀልልሃል፤ እነርሱም ሸክሙን ከአንተ ጋር ይሸከማሉ።
\v 23 ይህን ብታደርግና እግዚአብሔርም እንደዚሁ እንድታደርግ ቢያዝዝህ፣ በርትተህ መሥራት ትችላለህ፤ መላው ሕዝብም ረክቶ ወደ ቤት መሄድ ይችላል።”
\s5
\v 24 የዐማቱን ምክር በመስማት የነገረውን ሁሉ አደረገ።
\v 25 ሙሴ ከእስራኤል ሁሉ ችሎታ ያላቸውን ሰዎች መረጠ፤ ሸለቆች፣ መቶ አለቆች፣ ዐምሳ አለቆችና ዐሥር አለቆች አድርጎም የሕዝቡ መሪዎች እንዲሆኑ ሾማቸው።
\v 26 በቀላላል ጉዳዮች ሕዝቡን ይዳኙ ነበር። ከበባድ ጉዳዮችን ለሙሴ አቀረቡ፤ ትንንሽ ጉዳዮችን ሁሉ ግን እነርሱ ለራሳቸው ብያኔ ሰጡባቸው።
\v 27 በኋላ ሙሴ ዐማቱን አሰናበተው፤ ዮቶርም ወደ ገዛ ምድሩ ተመልሶ ሄደ።
\s5
\c 19
\p
\v 1 ወር፣ እስራኤላውያን ከግብፅ ምድር በወጡበት በዚያው ቀን ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ።
\v 2 ከራፊዲም ከተነሡ በኋላ፣ ወደ ሲና ምድረ በዳ መጥተው በምድረ በዳው ውስጥ ከተራራው ፊት ለፊት ሰፈሩ።
\s5
\v 3 ወደ እግዚአብሔር ወጣ። እግዚአብሔርም ከተራራው ጠርቶት እንዲህ አለው፤
\v 4 “ለያዕቆብ ቤት፣ ለእስራኤል ሕዝብ እንደዚህ ብለህ ተናገር፦ በግብፃውያን ላይ ምን እንዳደረግሁ ፣ እናንተንም በርግም ክንፎች እንዴት እንደ ተከከምኋችሁና ወደ ራሴ እንዴት እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል።
\v 5 ቃሌን በታዛዥነት ብትሰሙና ኪዳኔንም ብትጠብቁ፣ ከሕዝብ ሁሉ መካከል የእኔ ርስት ትሆናላችሁ፤ ምድር ሁሉ የእኔ ነውና።
\v 6 እናንተ ለእኔ የካህናት መንግሕትና ቅዱስ ሕዝብ ትሆናላችሁ። ለእስራኤላውያን የምትነግራቸው ቃሎች እነዚህ ናቸው።
\s5
\v 7 መጣ፤ የሕዝቡንም ሽማግሌዎች ጠርቶ እግዚአብሔር ያዘዘውን እነዚህን ቃሎች ሁሉ በፊታቸው ተናገረ።
\v 8 ሁሉ በአንድነት፣ “እግዚአብሔር የተናገረውን ሁሉ እናደርጋለን” በማለት መልስ ሰጡ። ሙሴ ሕዝቡ የተናገሩትን ወደ እግዚአብሔር ለማቅረብ መጣ።
\v 9 ሙሴን፤ “እኔ ከአንተ ጋር ስነጋገር፣ መስማት እንዲችሉና አንተንም ሁልጊዜ እንዲያምኑህ፣ ወደ አንተ በከባድ ደመና እመጣለሁ” አለው። ሙሴም ሕዝቡ የተናገሯቸውን ቃሎች ለእግዚአብሔር ነገረው።
\s5
\v 10 ሙሴን፣ “ወደ ሕዝቡ ሂድ። ዛሬና ነገ ለእኔ ቀድሳቸው፤ ልብሳቸውንም እንዲያጥቡ አድርግ።
\v 11 ቀንም ይዘጋጁ፤ በሦስተኛው ቀን እኔ እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ እወርዳለሁና።
\s5
\v 12 ዙሪያ ሁሉ ለሕዝቡ ወሰን አብጅና ለሕዝቡ እንዲህ በላቸው፤ ‘ወደ ተራራው እንዳትወጡ ወይም የተራራውን ግርጌ ጫፍ እንዳትነኩ ተጠንቀቁ። ተራራውን የነካ ይሞታል።’
\v 13 ዐይነቱን ሰው ማንም አይንካው። እንዲያውም የነካው በድንጋይ ይወገራል ወይም በቀስታ ይወጋል። ሰውም ሆነ እንስሳ ይሞታል። መለከቱ የማያቋርጥ ድምፅ ሲያሰማ፣ ሕዝቡ ወደ ተራራው መውጣት ይችላሉ” አለው።
\s5
\v 14 ሙሴም ከተራራው ወደ ሕዝቡ ወረደ። ሕዝቡን ለእግዚአብሔር ቀደሳቸው፤ ልብሳቸውንም አጠቡ።
\v 15 “በሦስተኛው ቀን ተዘጋጁ፤ ወደ ሚስቶቻችሁም አትጠጉ” አላቸው።
\s5
\v 16 ቀን ጠዋት ላይ ነጏድጓድና የመብረቅ ብልጭታ፣ ከባድ ደመና እና ጉሉሕ የመለከት ድምፅ በተራራው ላይ ነበሩ። በሰፈሩ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ተንቀጠቀጡ።
\v 17 ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲገናኙ ሕዝቡን ከሰፈር አወጣቸው፤ በተራራው ግርጌም ቆሙ።
\v 18 እግዚአብሔር በእሳትና በጢስ ወርዶበት ስለ ነበረ፣ የሲና ተራራ ሙሉ በሙሉ በጢስ ተሸፈነ። ጢሱ እንደ ምድጃ ጢስ ይወጣ ነበር፤ ጠቅላላ ተራራውም በኀይል ተናወጠ።
\s5
\v 19 ድምፅ እየጨመረና እየጎላ ሲሄድ፣ ሙሴ ተናገረ፤ እግዚአብሔርም በድምፅ መለሰለት።
\v 20 እግዚአብሔር በሲና ተራራ ጫፍ ላይ ወርዶ፣ ሙሴን ወደ ተራራው ጫፍ እንዲወጣ ጠራው። ሙሴም ወጣ።
\v 21 ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለማየት ዐልፈው ወደ እኔ እንድይመጡ፣ ሂድና ሕዝቡን አስጠንቅቃቸው፤ አለዚያ ብዙዎች ይሞታሉ።
\v 22 ወደ እኔ የሚቀርቡ ካህናትም ራሳቸውን ይቀድሱ፤ እንዳላጠፋቸውም ለእኔ መምጣት ራሳቸውን ያዘጋጁ።”
\s5
\v 23 እግዚአብሔርን፣ “ሕዝቡ ወደ ተራራው መውጣት አይችሉም፤ ምክንያቱም ‘በተራራው ዙሪያ ወሰን አብጅና ለእግዚአብሔር ቀድሰው’ ብለህ አዝዘኸናል” አለው።
\v 24 ሙሴን፣ “ከተራራው ወርደህ ሂድና አሮንን ክአንተ ጋር ይዘኸው ና፤ ካህናቱና ሕዝቡ ግን ወሰን ዐልፈው ወደ እኔ እንዲመጡ አትፍቀድላቸው፤ አለዚያ አጠፋቸዋለሁ” አለው።
\v 25 ስለዚህ ሙሴ ወደ ሕዝቡ ሄዶ ይህንኑ ነገራቸው።
\s5
\c 20
\p
\v 1 እነዚህን ቃሎች እንዲህ በማለት ተናገረ፦
\v 2 ከግብፅ ምድር፣ ከባርነት ምድር ያወጣሁህ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ።
\v 3 ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ።
\s5
\v 4 በላይ በሰማይ ያለውን፣ ወይም በታች በምድር ያለውን፣ ከምድርም በታች በውሀ ውስጥ ያለውን የማንኛውንም ነገር የተቀረጸ ምስልና ሥዕል ለራስህ ጣዖት አታብጅ።
\v 5 አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። የሚጠሉኝን ሦስትና አራት ትውልድ በልጆች ላይ ቅጣት በማምጣት የአባቶችን ኀጢአት እቀጣለሁ።
\v 6 በሚወዱኝና ትእዛዛቴን በሚጠብቁት በሺዎች ላይ ግን የኪዳን ታማኝነት አሳያለሁ።
\s5
\v 7 የአምላክህን የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ አታንሣ፤ ስሜን በከንቱ የሚያነሣውን በደል ዐልባ አላደርገውምና።
\s5
\v 8 እንድትቀድሰው፣ የሰንበትን ቀን ዐስብ።
\v 9 ቀን ሥራ፤ ተግባርህንም ሁሉ አከናውን።
\v 10 ቀን ለእኔ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ሰንበት ነው። በሰንበት ቀን አንተም ወንድ ልጅህም፣ ሴት ልጅህም፣ ወንድ አገልጋይህም፣ ሴት አገልጋይህም፣ እንስሳትህም፣ በግቢህ ያለ እንግዳም ሥራ አትሠሩም።
\v 11 እግዚአብሔር ሰማያትን፣ ምድርንና ባሕርን፣ በእነርሱ ውስጥ ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀን ፈጥሬ በሰባተኛው ቀን ዐርፌአለሁና። ስለዚህ እኔ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባረክሁት፤ ለራሴም ቀደስሁት።
\s5
\v 12 እኔ እግዚአብሔር አምላክህ በምሰጥህ ምድር ብዙ ጊዜ እንድትቆይ፣ አባትህንና እናትህን አክብር።
\v 13 አትግደል።
\v 14 አታመንዝር።
\s5
\v 15 አትስረቅ።
\v 16 በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።
\v 17 የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ የባልንጀራህን ሚስት፣ ወንድ አገልጋዩን፣ ሴት አገልጋዩን፣ በሬውን፣ አህያውን፣ ወይም የባልንጀራህ የሆነውን ማንኛውንም ነገር አትመኝ።”
\s5
\v 18 ሰዎች ሁሉ ነጎድጓዱንና መብረቁን አዩ፤ የመለከቱን ድምፅም ሰሙ፤ የሚጨሰውንም ተራራ ተመለከቱ። ሕዝቡ ይህን ሲያዩ፣ ተንቀጠቀጡ፤ ርቀውም ቆሙ።
\v 19 ሙሴን፣ “አንተ ተናገረን፤ እኛም እንሰማሃለን፤ ነገር ግን እግዚአብሔር እንዲናገረን አታድርግ፤ አለዚያ እንሞታለን” አሉት።
\v 20 ሙሴም ሕዝቡን፣ “አትፍሩ፤ ፈሪሀ እግዚአብሔር በእናንተ ዘንድ እንዲገኝና ኀጢአት እንዳትሠሩ ሊፈትናችሁ እግዚአብሔር መጥቶአልና” አላቸው።
\v 21 ስለዚህ ሕዝቡ ርቀው ቆሙ፤ ሙሴም እግዚአብሔር ወዳለበት ወደ ጨለማው ተጠጋ።
\s5
\v 22 ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለእስራኤላውያን የምትነግራቸው ይህ ነው፦ ‘እኔ ከሰማይ ከእናንተ ጋር እንደ ተነጋገርሁ እናንተ ራሳችሁ አይታችኋል።
\v 23 በቀር ሌሎች አማልክትን፣ የብር ወይም የወርቅ አማልክትን ለራሳችሁ አታብጁ።
\s5
\v 24 የጭቃ መሠዊያ ሥራልኝ፣ በእርሱም ላይ የሚቃጠሉትን መሥዋዕቶችህን፣ የኅብረት መሥዋዕቶችህን፣ በጎችህንና በሬዎችህን ሠዋበት። ስሜ እንዲከበር በማደርግበት ስፍራ ሁሉ፣ ወዳንተ እመጣለሁ፤ እባርክሃለሁም።
\v 25 መሠዊያ የምትሠራልኝ ከሆነ፣ በተጠረበ በድንጋይ አትሥራው፤ ለመጥረብ ስትል መሣሪያህን በላዩ ካሳረፍህበት ታረክሰዋለህና።
\v 26 ሆነህ እንዳትጋለጥ፣ በመሠዊያዬ ላይ በደረጃ አትውጣ።”
\s5
\c 21
\p
\v 1 የምትመሠርታቸው ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፦
\s5
\v 2 አገልጋይ ብትገዛ፣ ስድስት ዓመት ያገልግልህና በሰባተኛው ዓመት ያለ ክፍያ ነጻ ይውጣ።
\v 3 ከመጣ፣ ብቻውን ነጻ ይውጣ፤ ሚስት ያገባ ከሆነ፣ ሚስቱም ዐብራው ነጻ ትውጣ።
\v 4 ጌታው ሚስት አጋብቶት ከሆነና እርሷም ወንዶች ወይም ሴቶች ልጆችን ከወለደችለት፣ ሚስቲቱና ልጆቿ የጌታዋ ይሆናሉ፤ ባልዮው ግን ብቻውን በነጻ ይሂድ።
\s5
\v 5 ግን አገልጋይ፣ “ጌታዬን፣ ሚስቴንና ልጆቼን እወድዳለሁ፤ ነጻ ወጥቼ አልሄድም” ቢል፣
\v 6 ውደ ዳኞች ይውስደው፥ ወደ በሩ ወይም ወደ መቃኑ ወስዶም ጆሮውን በወስፌ ይብሳው፤ ከዚያም አገልጋይ ጌታውን ለዘለዓለም ያገለግለዋል።
\s5
\v 7 ሰው ሴቶ ልጁን በአገልጋይነት ቢሸጣት፣ እንደ ወንዶቹ አገልጋዮች በነጻ መሄድ የለባትም።
\v 8 ለራሱ የመረጣትን ጌታዋን ደስ ባታሰኝ፣ በዎጆ ይልቀቃት። ለባዕዳን እንዲሸጣት መብት የለውም፤ ምክንያቱም አታልሎአታል።
\s5
\v 9 ለልጁ አያያዝ ያድርግለት።
\v 10 ሌላ ሚስት ቢያጋባውም፣ የመጀመሪያዋን ሚስቱን ምግብ፥ ልብስ፣ ወይም ቊሳዊ መብት ማጕደል የለበትም።
\v 11 ነገር ግን እነዚህን ሦስት ነገሮች የማይሰጣት ቢሆን፣ ያለ ምንም የገንዘብ ክፍያ በነጻ መሄድ ትችላለች።
\s5
\v 12 ሰው ሰውን ቢደበድብና ቢገድል፣ ሊሞት ይገባዋል።
\v 13 ሰውየው ዐስቦ ሳይሆን ድንገት አድርጎት ከሆነ፣ የሚሸሽበት ስፍራ አዘጋጃለሁ።
\v 14 አንድ ሰው ባልንጀራውን ሆነ ብሎ በተንኮል ቢያጠቃውና ቢገድለው፣ ከእግዚአብሔር መሠዊያም እንኳ ተወስዶ ይገደል።
\s5
\v 15 ወይም እናቱን የሚመጣ ይገደል።
\v 16 የሚጠልፍና የሚሸጥ፣ ወይም የተጠለፈው ሰው በእጁየሚገኝበት ይገደል።
\v 17 ወይም እናቱን የሚሳደብ ይገደል።
\s5
\v 18 ቢጣሉና እንደኛው ሌላውን በድንጋይ ወይም በቡጢ ቢመታው፣ የተመታው ሰውም ባይሞትና ዐልጋው ላይ ቢቀር፤
\v 19 በኋላም ቢያገግምና በትሩን ተደግፎ በአካባቢው መንቀሳቀስ ቢችል፣ ለባከነበት ጊዜ የመታው ሰውን ይክፈል፤ ያገገመበትንም በሙሉ ይክፈል። ነገር ግን ያ ሰው የነፍስ ተጠያቂ አይደለም።
\s5
\v 20 አንድ ሰው ወንድ ወይም የሴት አገልጋዩን በበትር ሲመታና አገልጋዩም ከድብደባው የተነሣ ቢሞት፥ ያ ሰው መቀጣት አለበት።
\v 21 ነገር ግን አገልጋዩ አንድ ወይም ሁለት ቀን በሕይወት ቢቆይ፣ ጌታው መቀጣት የለበትም፤ አገልጋዩ የግል ንብረቱ ነውና።
\s5
\v 22 ሰዎች ቢጣሉና ነፍሰ ጡር ሴት ቢጎዱ፣ እርሷም ብትጨነግፍ፣ ሆኖም ሌላ ጉዳት ባይደርስባት፣ በደለኛው ሰውዬ የሴትዮዋ ባል የሚጠብቅበትንና ዳኞቹ የሚወስኑትን መክፈል አለበት።
\v 23 ጉዳት ካደረሰ ግን፣ ሕይወትን ለሕይወት፣
\v 24 ዐይንን ለዐይን፣ ጥርስን ለጥርስ፣ እጅን ለእጅ፣ እግርን ለእግር፣
\v 25 ቃጠሎን ለቃተሎ፣ ቊስልን ለቊስል፣ ወይም ግርፋትን ለግርፋት በቅጣት ታስከፍላለህ።
\s5
\v 26 አንድ ሰው የወንድ ወይም የሴት አገልጋዩን ዐይን ቢመታና ቢያጠፋው፣ አገልጋዩን ስለ ዐይኑ ካሣ ነጻ ሊያደርገው ይገባል።
\v 27 የወንድ ወይም የሴት አገልጋዩን ጥርስ ቢያወልቅ፣ አገልጋዩን ለጥርሱ ካሣ ነጻ ሆኖ እንዲሄድ ማድረግ አለበት።
\s5
\v 28 በሬ አንድን ሰው ወይም ሴት ቢወጋና የሞት አደጋ ቢያደርስ፣ በሬው በድንጋይ ይወገር፣ ሥጋውም አይበላ፤ የበሬው ባለቤት ግን ከተጠያቂነት ነጻ ይሁን።
\v 29 ግን በሬው የመዋጋት ልማድ ከቀድሞ ጀምሮ ካለበትና ባለቤቱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት በሬውን ሳይጠብቀው ቀርቶ፣ በሬው አንድ ወንድ ወይም ሴት ወግቶ ቢገድል፣ ያ በሬ በድንጋይ ይወገር፤ ባለቤቱም በሞት ይቀጣ።
\v 30 ለሕይወቱ ካሣ እንዲከፍል ካስፈለገ፣ የተጠየቀውን ይክፈል።
\s5
\v 31 በሬው የአንድን ሰው ወንድ ወይም ሴት ልጅ ቢወጋ፣ የበሬው ባለቤት ይህ ሕግ የሚጠብቅበትን ያድርግ።
\v 32 ወንድ ወይም ሴት አገልጋይን ቢወጋ፣ የበሬው ባለቤት ሠላሳ የብር ሰቅል ለአገልጋዩ ጌታ መክፈልና በሬውም በድንጋይ መወገር አለበት።
\s5
\v 33 ሰው ጕድጓድ ቢከፍት ወይም ቢቆፍርና ሳይደፍነው ቀርቶ በሬ ወይም አህያ ቢገባበት፣
\v 34 ባለቤት ለጠፋው መክፈል ይኖርበታል። ለሞተው እንስሳ ባለቤት ገንዘብ መክፈል አለበት፤ የሞተው እንስሳም የእርሱ ይሆናል።
\s5
\v 35 የአንድ ሰው በሬ የሌላ ሰውን በሬ ቢወጋና ቢሞት፣ የበሬዎቹ ባለቤቶች በሕይወት ያለውን በሬ ሽጠው የተሸጠበትንና የሞተውንም በሬ ይካፈሉ።
\v 36 ነገር ግን በሬው ከቀድሞ ጀምሮ የመውጋት ልማድ ያለበት መሆኑ ከታወቀና ባለቤቱም ያልጠበቀው ከሆነ፣ በበሬው ፈንታ በሬውን መክፈል አለበት፤ የሞተው እንስሳም የእርሱ ይሆናል።
\s5
\c 22
\p
\v 1 ሰው በሬ ወይም በግ ቢሰርቅና ቢያርደው ወይም ቢሸጠው፣ ለአንድ በሬ ዐምስት በሬ፣ ለአንድ በግም ዐምስት በግ መክፈል አለበት፥
\v 2 ሌባ በር ሰብሮ ሲገባ ቢገኝና ተደብድቦ ቢሞት፣ በማንም ሰው ላይ የደም ዕዳ አይኖርም።
\v 3 ነገር ግን ሰብሮ ከመግባቱ በፊት ፀሐይ ከወጣ፣ በገደለው ሰው ላይ የደም ተጠያቂነት ይኖራል። ሌባ የሰረቀውን መመለስ አለበት። ምንም ነገር ከሌለው፣ የሰረቀውን እንዲከፍል እርሱ ራሱ መሸጥ ይኖርበታል።
\v 4 ሆነ አህያ ወይም በግ ቢሆን የተሰረቀው እንስሳ በሕይወት እርሱ ዘንድ ከተገኘ፣ ዕጥፉን መልሶ መክፈል አለበት።
\s5
\v 5 ሰው ከብቱን መስክ ላይ ወይም የወይን ዕርሻ ውስጥ አሰማርቶ ቢለቅቀውና በሌላ ሰው ዕርሻ ውስጥ ገብቶ ቢግጥ፣ ምርጥ ከሆነው ከራሱ መስክና የወይን ዕርሻ መካስ ይኖርበታል።
\s5
\v 6 እሳት ቢነሣና በእሾኾችም ውስጥ ቢዛመት፣ ክምሩም፣ ያልታጨደውም እህል ወይም ዕርሻው ቢቃጠል፣ እሳቱን ያቀጣጠለው ሰው ካሣ ይካሥ።
\s5
\v 7 ሰው እንዲጠበቅለት ገንዘቡን ወይም ዕቃውን ለጎረቤቱ ቢሰጥ፣ በዐደራ ያስቀመጠውንም ከሰውዬው ቤት ሌባ ቢሰርቀውና ሌባውም ቢገኝ፣ ያ ሌባ ዕጥፍ መክፈል አለበት፤
\v 8 ባይገኝ ግን፣ የቤቱ ባለቤት እጁን በጎረቤቱ ንብረት ላይ መዘርጋቱንና አለመዘርጋቱን ለማየት፣ በዳኞች ፊት ሊቀርብ ይገባል።
\v 9 ስለ በሬ፣ ስለ አህያ፣ ስለ በግ፣ ስለ ልብስ ወይም አንድ ሰው፣ “ይህ የእኔ ነው” ስለሚለው ስለ ማንኛውም የጠፋ ነገር የሚነሣ ክርክር ሁሉ፣ የሁለቱም ወገን አቤቱታ በዳኞች ፊት መቅረብ አለበት። ዳኞች በደለኛ ሆኖ ያገኙት ሰው ለጎረቤቱ ዕጥፍ መክፈል ይኖርበታል።
\s5
\v 10 አንድ ሰው አህያ፣ በሬ፣ በግ፣ ወይም ማንኛውም እንስሳ እንዲጠበቅለት ለጎረቤቱ በዐደራ ቢሰጥና እንስሳው ቢሞት፣ ወይም ጕዳይ ቢደርስበት፣ ወይም ማንም ሳያይ ቢወሰድ፣
\v 11 ሰው በጎረቤቱ ንብረት ላይ እጁን መዘርጋቱን ወይም አለመዘርጋቱን ለመለየት፣ ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት መማል አለባቸው። ባለቤቱ ይህን ሊቀበል ይገባል፤ ሌላውም ሰው ካሣ አይክሥም።
\v 12 ነገር ግን እንስሳው ከእርፍሱ ተሰርቆ ከሆነ፣ ሌላው ሰው ለባለቤቱ ካሣ መካሥ አለበት።
\v 13 አንድን እንስሳ አውሬ ቢዘነጥለው፣ ሌላው ሰውዬ እንስሳውን ማስረጃ አድርጎ ያቅርብ። ለተዘነጣጠለው እንስሳ ካሣ መክፈል የለበትም።
\s5
\v 14 አንድ ሰው ከጎረቤቱ እንስሳ ቢዋስና እንስሳው ባለቤቱ በሌለበት ቢጎዳ ወይም ቢሞት፣ ሌላው ሰውዬ ካሣ መካሥ አለበት።
\v 15 ባለቤቱ ካለበት ከሆነ ግን፣ ሌላው ሰውዬ ካሣ መክፈል የለበትም፤ እንስሳ ተከራይቶ የነበረ ከሆነ፣ በተከራየበት ዋጋ ይከፈላል።
\s5
\v 16 አንድ ሰው ያልታጨች ልጃገረድን ቢያታልልና ዐብሯት ቢተኛ፣ ለዚህ ተገቢ የሆነውን ማጫ ከፍሎ ሚስቱ ሊያደርጋት ይገባል።
\v 17 አባቷ በሚስትነት አልሰጥህም ካለው፣ ልጃገረዶች ማጫ ከሚከፈለው ጋር እኩል የሆነ ገንዘብ መክፈል አለበት።
\s5
\v 18 መተተኛ ሴት በሕይወት እንድትኖር አትፍቀድ።
\v 19 ከእንስሳት ጋር የወሲብ ግንኙነት የሚያደርግ መምት አለበት።
\s5
\v 20 ከእግዚአብሔር በቀር ለማንኛውም ባዕድ አምላክ መሥዋዕት የሚሠዋ ፈጽሞ መጥፋት ይኖርበታል።
\v 21 መጻተኛውን አትበድሉት ወይም አታስጨንቁት፤ እናንተም በግብፅ ምድር መጻተኞች ነበራችሁና።
\s5
\v 22 ማንኛዋንም መበለት ወይም አባትና እናት የሌለውን ልጁ ማስጨነቅ የለባችሁም።
\v 23 የምታስጨንቋቸው ከሆነና እነርሱም ወደ እኔ ከጮኹ፤ እኔ እግዚአብሔር ጩኸታቸውን እሰማለሁ።
\v 24 ቊጣዬ ይቀጣጠላል፤ በሰይፍም እገድላችኋለሁ፤ ሚስቶቻችሁ መበለታት፣ ልጆቻችሁም አባት ዐልባዎች ይሆናሉ።
\s5
\v 25 ከሕዝቤ መካከል ድኻ ከሆኑት ለአንዱ ገንዘብ ብታበድሩ፣ እንደ አራጣ አበዳሪ አትሁኑበት ወይም ወለድ አታስከፍሉት።
\v 26 የጎረቤትህን ልብስ በመያዣነት ብትወስድ፣ ፀሐይ ከመግባቷ በፊት ልትመልስለት ይገባል።
\v 27 ሰውነቱን የሚሸፍንበት ልብሱ እርሱ ብቻ ነውና። ምን ሌላ ልብስ ለብሶ መተኛት ይችላል? ወደ እኔ ሲጮኽ፣ ርኅሩኅ ነኝና እሰማዋለሁ።
\s5
\v 28 ፈራጆችንም አትስደብ፤ የሕዝብህን አለቃም አትርገም።
\s5
\v 29 ወይም ከወይን ጭማቂዎችህ የምታቀርባቸውን ስጦታዎች ማዘግየት የለብህም። የወንድ ልጆችህንም በኵር ለእኔ መስጠት አለብህ።
\v 30 በበጎችህ ላይም ይህንኑ ማድረግ ይኖርብሃል። ልጆቹ ሰባት ቀን ክአእናቶቻቸው ጋር መቆየት ይችላሉ፤ በስምንተኛው ቀን ግን ለእኔ መስጠት አለብህ።
\v 31 ለእኔ ቅዱስ ሕዝብ ትሆናላችሁ። ስለዚህ መስክ ላይ አውሬ የዘነጣጠለውን ሥጋ ለውሾች ጣሉት፣ ልትበሉት አይገባም።
\s5
\c 23
\p
\v 1 ማንም ሰው የሐሰት ወሬ እትናገር። ሐሰተኛ ምስክር ለመሆን ከክፉ ሰው ጋር አትተባበር።
\v 2 ክፋት ለመፈጸም ሕዝብን አትከተል፤ ወይም ፍትሕን ለማጣመም ከሰዎች ጋር ተባብረህ ምስክርነት አትስጥ።
\v 3 ድኻውን በሙግቱ አታድላለት።
\s5
\v 4 በሬ ወይም አህያ ጠፍቶ ብታገኘው መልስለት።
\v 5 የሚጠላህን ሰው አህያ እንደ ተጫነ ከጭነቱ ሥር ወድቆ ብታየው፣ ያን ሰው ትተኸው አትሂድ። አህያውን ለማንሣት ልታግዘው ይገባል።
\s5
\v 6 ጊዜ ለድኻው ወገንህ የሚሰጠውን ፍትሕ አታጣምም።
\v 7 በሐሰት ክስ ከሌሎች ጋር አትተ ባበር፤ ንጹሑንም ወይም ጻድቁንም አትግደል፤ እኔ ኀጢአተኛውን ንጹሕ አላደርግምና።
\v 8 አትቀበል፤ ጕቦ የሚያዩ ሰዎችን ያሳውራል፤ የታማኝ ሰዎችን ቃልም ያጣምማልና።
\v 9 የመጻተኛነትን ስለምታውቁት፣ መጻተኛን አታስጨንቁ፤ እናንተም በግብፅ ምድር መጻተኞች ነበራችሁና።
\s5
\v 10 ስድስት ዓመት በመሬትህ ላይ ዘር ዝራ፤ መከሩንም ሰብስብ።
\v 11 በሰባተኛው ዓመት ግን በሕዝብህ መካከል ያሉ ድኾች መብላት እንዲችሉ ሳታርሰው ዕዳሪውን ተወው። ከድኾች የሚተርፈውንም የዱር እንስሳት ይበሉታል። በወይን ቦታዎችህና በወይራ ዛፎችህም ይህንኑ ታደርጋለህ።
\s5
\v 12 ቀን ሥራህን ትሠራለህ፤ በሰባተኛው ቀን ግን ታርፋለህ። ይህን የምታደርገውም፦ በሬህ፣ አህያህ፣ የሴት አገልጋይህ ወንድ ልጅና መጻተኛው ሁሉ ዕረፍት እንዲያገኙና እንዲዝናኑ ነው።
\v 13 የነገርኋችሁን ሁሉ ጠብቁ። የሌሎች አማልክትን ስም አትጥሩ፤ ወይም ስማቸው ከአፋችሁ አይሰማ።
\s5
\v 14 በየዓመቱ ሦስት ጊዜ ልአእኔ በዓል ታከብራላችሁ።
\v 15 በዓልን አክብር። ባዘዝሁህ መሠረት ሰባት ቀን ቂጣ ትበላለህ። በዚያ ጊዜ፣ ለዚህ በተወሰነው በአቢብ ወር በፊቴ ትቀርባለህ። ከግብፅ የወጣኸው በዚህ ወር ነበር። ነገር ግን በፊቴ ባዶ እጅህን መቅረብ የለብህም።
\s5
\v 16 ላይ የዘራኸውን የእህልህን በኵራት፣ የመከርን በዓል አክብር። በዓመቱ መጨረሻ ምርትህን ከማሳ ስትሰበስብ፣ የመክተቻውን በዓል አክብር።
\v 17 ዘንድ ያለ ወንድ ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ በእኔ በእግዚአብሔር ፊት ይቅረብ።
\s5
\v 18 የመሥዋዕቱን ደም እርሾ ካለበት ዳቦ ጋር ለእኔ አታቅርብ። በበዓሎቼ የሚቀርበው የመሥዋዕቴ ሥብ እስከ ንጋት ድረስ መቆየት የለበትም።
\v 19 የመሬትህን ምርጥ ፍሬ በኵራት ወደ እኔ፣ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጣ። የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።
\s5
\v 20 በመንገድ የሚጠብቅህንና ወዳዘጋጀሁልህ ስፍራ መርቶ የሚያስገባህን መልአክ በፊትህ እልካለሁ።
\v 21 ተከተለው፤ ታዘዝለትም። ኀጢአትህን ይቅር አይልህምና አታስቆጣው። ስሜ በእርሱ ላይ ነው።
\v 22 ድምፁን በእውነት ብትሰማና የምነግርህን ሁሉ ብታደርግ፣ ለጠላቶችህ ጠላት እሆናለሁ፤ የሚቃወሙህንም እቃወማለሁ።
\s5
\v 23 መልአክ በፊትህ ይሄዳል፤ አንተንም ወደ አሞራውያንና ወደ ኢያቡሳውያን ምድር ያስገባሃል። እኔ እነርሱን አጠፋቸዋለሁ።
\v 24 ለአማልክታቸው አትስገድ፤ አታምልካቸውም፤ ወይም ሕዝቡ እንደሚያደርጉት አታድርግ፤ ይልቁን ፈጽመህ ልታፈራርሳቸው፣ የድንጋይ ዐምዶቻቸውንም ልትሰባብራቸው ይገባል።
\v 25 እኔን አምላክህን እግዚአብሔርን አምልክ። ይህን ካደረግህ፣ የምትባውንና የምትጠጣውን እባርካለሁ። በሽታንም ከመካከልህ አጠፋለሁ።
\s5
\v 26 የምትጨነግፍ ወይም የምትመክን ሴት አትምርም። ለአንተ ረጅም ዕድሜ እሰጥሃለሁ።
\v 27 ምድር ሕዝብ ላይ ማስፈራቴን እልካለሁ። የሚያጋጥሙህን ሰዎች ሁሉ እገድላለሁ። ጠላቶችህን ሁሉ ከፍርሀት የተነሣ ጀርባቸውን ወደ አንተ እንዲያዞሩ አደርጋለሁ።
\v 28 ከነዓናውያንና ኬጤያውያንን ከፊትህ እንዲያበሯቸው ተርቦችን በፊትህ እሰድዳለሁ።
\v 29 ወና እንዳትሆንና የዱር አራዊትም እጅግ እንዳበዙብህ፣ የምድሪቱን ኗሪዎች በአንድ ዓመት ውስጥ ከፊትህ አላባርራቸውም።
\s5
\v 30 ነገር ግን አንተ እስክትበዛና ምድሪቱን እስክትወርሳት ድረስ በትንሽ በትንሹ አስወጣቸዋለሁ።
\v 31 ከቀይ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፣ ከምድር በዳውም እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ አደርገዋለሁ። በምድሪቱ ኗሪዎች ላይ ድል እንድትጎናጸፍ አደርጋለሁ፤ ከፊትህም ታባርራቸዋለህ።
\v 32 ወይም ከአማልክታቸው ጋር ኪዳን አታድርግ።
\v 33 እነርሱ በምድርህ ውስጥ መኖር አይገባቸውም፤ አልዚያ በእኔ ላይ ኀጢአት እንድትሠራ ያደርጉሃል። አማልክታቸውን ብታመልክ፣ ይህ በእውነት ወጥመድ ይሆንብሃል።”
\s5
\c 24
\p
\v 1 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “አንተ፣ ናዳብ፣ አብድዩና ሰባው የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ እኔ ኑ፤ በርቀት ሆናችሁም ስገዱልኝ።
\v 2 ሙሴ ብቻ ወደ እኔ መቅረብ ይችላል። ሌሎች መቅረብ የለባቸውም፤ ወይም ሕዝቡ ከሙሴ ጋር መምጣት አይችሉም።”
\s5
\v 3 ሙሴ ወደ ሕዝቡ ሄዶ እግዚአብሔር የተናገራቸውን ቃሎችና ሕጎቹን ሁሉ ነገራቸው። ሕዝቡም ሁሉ በአንድ ድምፅ፣ “እግዚአብሔር የተናገራቸውን ቃሎች ሁሉ እናደርጋለን” ብለው መለሱ።
\v 4 ሙሴም የእግዚአብሔርን ቃሎች ሁሉ ጻፈ። ማለዳ ላይም በተራራው ግርጌ መሠዊያ ሠራ፤ ዐሥራ ሁለቱን የእስራኤል ነገዶች እንዲወክሉም፣ ዐሥራ ሁለት የድንጋይ ዐምዶችን አቆመ።
\s5
\v 5 የሚቃጠልና የኅብረት መሥዋዕቶችን ከበሬዎች ለእግዚአብሔር እንዲያቀርቡም፣ ጥቂት የእስራኤል ወጣት ወንዶችን ላከ።
\v 6 ሙሴ የደሙን እኩሌታ በሣህን አደረገው፣ የቀረውንም እኩሌታ በመሠዊያው ላይ ረጨው።
\s5
\v 7 መጽሐፍ ወስዶ ለሕዝቡ ጮኽ ብሎ አነበበላቸው። ሕዝቡም፣ “እግዚአብሔር የተናገረውን ሁሉእናደርጋለን፤ እንታዘዛለንም” ብለው ተናገር።
\v 8 ሙሴ ደሙን ወስዶ በሕዝቡ ላይ ረጨው። “ይህ፣ ይህን የተስፋ ቃል ከእነዚህ ቃሎች ጋር ለእናንተ በመስጠት፣ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የገባው የኪዳኑ ደም ነው” በማለትም ተናገረ።
\s5
\v 9 ከዚያም በኋላ ሙሴ፣ አሮን፣ ናዳብ፣ አብድዩና ሰባው የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ተራራው ወጡ።
\v 10 የእስራኤልን አምላክ አዩት። ከእግሮቹ ሥርም እንደ ንጹሕ ሰማይ ከጠራ የሰንፒር ድንጋይ የተሠራ ወለል ነበረ።
\v 11 በእስራኤላውያን ሽማግሌዎች ላይ ተቆጥሮ እጅ አላሳረፈባቸውም። እነርሱ እግዚአብሔርን አዩ፤ በሉ፣ ጠጡም።
\s5
\v 12 እግዚአብሔር ሙሴን፣ “ተራራው ላይ ወደ እኔ ና፤ በዚያም ቆይ። የድንጋይ ጽላቱን ሕዝቡን እንድታስተምራቸውም የፋጽሏቸውን ሕጉንና ትእዛዛቱን እሰጥሃለሁ” አለው።
\v 13 ስለዚህ ሙሴ ከረዳቱ ከኢያሱ ጋር ወደ እግዚአብሔር ተራራ ሄደ።
\s5
\v 14 ሙሴ ሽማግሌዎቹን፣ “ተመልሰን ወደ እናንተ እስክንመጣ ድረስ እዚህ ቆዩን። አሮንና ሖር ከእናንተ ጋር ናቸው። ክርክር የሚኖርበት ሰው ካለ፣ ወደ እነርሱ ይቅረብ” አላቸው።
\v 15 ወደ ተራራው ወጣ፤ ደመናውም ተራራውን ሸፈነው።
\s5
\v 16 የእግዚአብሔር ክብር በሲና ተራራ ላይ ወረደ፤ ደመናውም ተራራውን ስድስት ቀን ሸፈነው። በሰባተኛው ቀን እግዚአብሔር ከደመናው ውስጥ ሙሴን ጠራው።
\v 17 የእግዚአብሔርን ክብር እስራኤላውያን ሲያዩት እንደሚያጋይ እሳት ነበር።
\v 18 ሙሴ ደመናው ውስጥ ገብቶ ወደ ተራራው ወጣ። በተራራውም ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ቆየ።
\s5
\c 25
\p
\v 1 ሙሴን እንዲህ አለው፤
\v 2 “እያንዳንዱ ሰው ልቡ በፈቀደለት መሠረት ስጦታ ለእኔ እንዲያመጣ ለእስራኤላውያን ንገር። እነዚህን ስጦታዎች ተቀበልልኝ።
\s5
\v 3 ከእነርሱ የምትቀበላቸውም ስጦታዎች እነዚህ ናቸው፦ ወርቅ፣ ብርና ነሐስ፤
\v 4 ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና የበፍታ ድር ልብስ፣ የፍየል ጠጕር፣
\v 5 ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳና የአቆስጣ ቁርበት፣ የግራር ዕንጨት፤
\v 6 ለመቅደሱ መብራቶች ዘይት፣ ለመቅቢያው ዘይት ቅመሞችና ጣፋጭ መዐዛ ያለው ዕጣን፤
\v 7 ለኤፉድና ለደረት ኪሱ የሚሆኑ መረግዶችና ሌሎች ዕንቆች።
\s5
\v 8 እንዳድር ሕዝቡ መቅደስ ይሥሩልኝ።
\v 9 ለመገናኛው ድንኳንና ለዕቃዎቹ ሁሉ እኔ ባሳየሁህ ምሳሌ መሠረት ሥሩት።
\s5
\v 10 ሁለት ክንድ ተኩል፣ ስፋቱ አንድ ክንድ ተኩል፣ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ታቦት ከግራር ዕንጨት ይሠሩ።
\v 11 ውስጡንም ውጭውንም በንጹሕ ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አድርግለት።
\s5
\v 12 የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተህለት በታቦቱ አራት እግሮች ላይ፣ ሁለቱን በአንድ ጎኑ፣ ሁለቱን ደግሞ በሌላው ጎኑ አስቀምጣቸው።
\v 13 መሎጎያዎችን ከግራር ዕንጨት ሥራና አወርቅ ለብጣቸው።
\v 14 ታቦቱን ለመሸከም መሎጊያዎቹን በታቦቱ ጎን ባሉ ቀለበቶች ውስጥ አስገባ።
\s5
\v 15 መሎጊያዎቹ ምንጊዜም በታቦቱ ቀለበቶች ውስጥ ይቀመጣሉ እንጂ ከዚያ አይወጡም።
\v 16 የኪዳኑን ምስክሮች በታቦቱ ውስጥ ታስቀምጣለህ።
\v 17 ሁለት ክንድ ተኩል፣ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ የስርየት መክደኛ ከንጹሕ ወርቅ ሥራ።
\v 18 ለሁለቱ የስርየት መክደኛ ጫፎች ሁለት ኪሩቤልን ከተቀጠቀጠ ወርቅ ትሠራለህ።
\s5
\v 19 ኪሩብ ለስርየት መክደኛው አንድ ጫፍ፣ ሌላውን ኪሩብ ደግሞ ለሌላው ጫፍ በማድረግ ከስርየት መክደኛው ጋር ወጥ ሆነው መሠራት አለባቸው።
\v 20 ክንፎቻቸውን ወደ ላይ መዘርጋትና የስርየት መክደኛውን በክንፎቻቸው መጋረድ ይኖርባቸዋል። እርስ በርሳቸው መተያየትና ወደ ስርየት መክደኛውም መመልከት አለባቸው።
\v 21 መክደኛውን በታቦቱ ላይ ታደርገዋለህ፤ በታቦቱ ውስጥም የምሰጥህን የኪዳኑን ምስክሮች ታስቀምጣለህ።
\s5
\v 22 እኔ ከአንተ ጋር የምገናኘው በታቦቱ ነው። በስርየት መክደኛው ላይ ሆኜ ከአንተ በተናገርሁበት በምስክሩ ታቦት ላይ ባሉት በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ነው።
\s5
\v 23 እርዝመቱ ሁለት ክንድ፣ ወርዱ አንድ ክንድ፣ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ጠረጴዛ ከግራር ዕንጨት ሥራ።
\v 24 ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አድርግለት።
\s5
\v 25 አንድ ስንዝር ስፋት ያለው ጠርዝ ለጠርዙ በዙሪያው ከሚኖረው የወርቅ ክፈፍ ጋር አብጅለት።
\v 26 አራት የወርቅ ቀለበቶችን ሥራለትና ቀለበቶችን አራቱ እግሮቹ ባሉበት ከሚገኙት አራት ማዕዘኖች ጋር አያይዛቸው።
\v 27 ለማስቀመጥና ጠረጴዛውን መሸከም እንዲቻል፣ ቀለበቶቹ ከክፈፉ ጋር መያያዝ አለባቸው።
\s5
\v 28 የጠረጴዛው መሸከሚያ እንዲሆኑም መሎጊያዎችን ከግራር ዕንጨት ሥራና በወርቅ ለብጣቸው።
\v 29 ቊርባኑን ለማፍሰስ ጥቅም እንዲሰጡ ወጭቶችን፣ ጭልፋዎችን፣ ማንቆርቆሪያዎችንና ጎድጓዳ ሣህኖችን ከንጹህ ወርቅ ሥራ።
\v 30 በጠረጴዛውም ላይ የገጽ ኅብስት ሁልጊዜ በፊቴ ታደርጋለህ።
\s5
\v 31 መቆሚያና ዘንግ አበጅተህበት ከተቀጠቀጠ ንጹሕ ወርቅ መቅረዝ። ጽዋዎቹ፣ ቀንበጦቹና አበባዎቹ ሁሉ ወጥ ሆነው ከመቅረዙ ጋር ይሠራሉ።
\v 32 ሦስት ቅርንጫፎች በአንድ ጎን፣ ሦስት ቅርንጫፍ ደግሞ በሌላው ጎን፣ ስድስት ቅርንጫፎች ለመቅረዙ ይውጡለት።
\s5
\v 33 የመጀመሪያው ቅርንጫፍ የለውዝ አበቦችን መስለው የተሠሩ ሦስት ጽዋዎች ከቀንበጥና ክአበባ ጋር፣ በሌላው ቅርንጫፍም እንደዚሁ የለውዝ አበቦችን የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች የተቀረጹበት ከቀንበጥና ከአበባ ጋር ሊኖሩት ይገባል። ከመቅረዙ በሚወጡት በስድስት ቅርንጫፎች ሁሉ ላይ የሚሆነውም እንደዚሁ አንድ ዐይነት ነው።
\v 34 ላይ የለውዝ አበባ መስለው የተቀረጹ አራት ጽዋዎች ከቀንበጦቹና ከአበባዎቹ ጋር ሊኖሩበት ይገባል።
\s5
\v 35 በመጀመሪያዎቹ ቅርንጫፎች ጥንድ ሥር ወጥ ሆኖ ዐብሮ የተሠራ ቀንበጥ፣ በሁለተኛው የቅርንጫፎች ጥንድ ሥርም እንደዚሁ ወጥ ሆኖ ዐብሮ የተሠራ ቀንበጥ ይኖረዋል። በሦስተኛው የቅርንጫፎቹ ጥንድ ሥርም ወጥ ሆኖ ዐብሮ የተሠራ ቀንበጥ ይበጅለታል። ከመቅረዙ በሚወጡ በስድስቱ ቅርንጫፎች ሁሉ የሚሆነውም ይኸው አንድ ዐይነት ነው።
\v 36 ቀንበጦቻቸውና ቅርንጫፎቻቸው ሁሉ አንድ ወጥና ከተቀጠቀጠ ንጹሕ ወርቅ የተሠሩ መሆን አለባቸው።
\s5
\v 37 መቅረዙንና ሰባት መብራቶችን ሠርተህ ፊት ለፊት ላለው ስፍራ ብርሃን እንዲሰጥ አድርግ።
\v 38 የኵስታሪ መሰብሰቢያ ሣህኖቻቸው ከንጹሕ ወርቅ መሠራት አለባቸው።
\v 39 መቅረዙንና የመቅረዙን ዕቃ ሁሉ ለመሥራት አንድ መክሊት ንጹሕ ወርቅ ተጠቀም።
\v 40 ላይ ባሳየሁህ ምሳሌ መሠረት የሠራሃቸው ስለ መሆንህ እርግጠኛ ሁን።
\s5
\c 26
\p
\v 1 ከተፈተለ በፍታ ድር፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ ከተሠሩና ኪሩቤል ከተጠለፉባቸው ዐሥር መጋረጃዎች ጋር ማደሪያ ድንኳኑን ሥራ። ይህም ብልኅ ሠራተኛ የሚሠራው ሥራ ነው።
\v 2 የያንዳንዱ መጋረሣ እርዝመት ሃያ ስምንት ክንድ፣ ወርዱ አራት ክንድ ይሁን። መጋረጃዎቹ ሁሉ እኩል መጠን ይኑራቸው።
\v 3 ዐምስቱ መጋረጃዎች እርስ በርስ መያያዝ አለባቸው፤ ሌሎቹ ዐምስት መጋረጃዎችም እንደዚሁ እርስ በርሳቸው መገጣጠም ይኖርባቸዋል።
\s5
\v 4 በአንደኛው ወገን የመጨረሻ መጋረጃ የውጭ ጠርዝ ላይ የሰማያዊ ግምጃ ቀለበቶችን አድርግ። ለሁለተኛው ወገን የመጨረሻ መጋረጃ የውጭ ጠርዝም ይህንኑ አበጅለት።
\v 5 ዐምሳ ቀለበቶችን በአንደኛው የመጋረጃ ወገን፣ ዐምሳ ቀለበቶችን በሌላው የመጨረሻ መጋረጃ ላይ አድርግ። ይህን የምትሠራውም ቀለበቶቹ እርስ በርስ እንዲተያዩ በማድረግ ነው።
\v 6 ዐምሳ የወርቅ ማያያዣዊችብ ሠርተህ ማደሪያ ድንኳኑ አንድ እንዲሆን፣ መጋረጃዎቹን በእነርሱ አያይዛቸው።
\s5
\v 7 ከማደሪያው በላይ ለድንኳን የሚሆኑ ዐሥራ አንድ የፍየል ጠጕር መጋረጃዎችን ሥራ።
\v 8 መጋረጃ እርዝመት ሠላሳ ክንድ፣ ወርዱ አራት ክንድ ይሁን። ዐሥራ አንዱም መጋረጃዎች እኩል መጠን ይኑራቸው።
\v 9 ዐምስት መጋረጃዎችን በአንድነት፣ ስድስት መጋረጃውችንም እንዲሁ እርስ በርስ አያይዛቸው። ስድስተኛውን መጋረጃ በድንኳኑ ፊት ዕጠፈው።
\s5
\v 10 በመጀመሪያ ተገጣጣሚ የመጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይ ዐምሳ ቀለበቶችን፣ ሁለተኛውን የመጋረጃ አካል በሚያገጣጥመው የመጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይም እንደዚሁ ዐምሳ ቀለበቶችን አድርግ።
\v 11 ዐምሳ የነሐስ ማያያዣዎችን ሥራና በቀለበቶቹ ውስጥ አስገ ባቸው። ከዚያም አንድ ወጥ እንዲሆን ድንኳኑን አገጣጥመው።
\s5
\v 12 መጋረጃዎች ተንጠልጥሎ ያለው ቀሪ ግማሽ መጋረጃ ከማደሪያ ድንኳኑ ጀርባ ይንጠልጠል።
\v 13 ከመጋረጃዎቹ እርዝመት የተረፈው በአንድ በኩል አንድ ክንድ ምጋረጃ፣
\v 14 በሌላው ጎንም አንድ ክንድ መጋረጃ ማደሪያው ድንኳን መሸፈኛ በቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳና ከዚያም በላይ የሚሆን የአስቆጣ ቁርበት አዘጋጅ።
\s5
\v 15 ለማደሪያው ድንኳን የሚሆኑ ወጋግራዎችን ከግራር ዕንጨት አብጅ።
\v 16 ወጋግራ እርዝመት ዐሥር ክንድ፣ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን።
\v 17 በርስ የሚያገናኗቸው ሁለት ጕጣጕጦች በያንዳንዱ ወጋግራ ላይ ይኑር። የመገናኛ ድንኳኑን ወጋግራዎች ሁሉ በዚህ መንገድ ሥራ።
\v 18 ድንኳን ወጋግራዎችን ስታበጅ፣ በደቡብ መኩል ላለው ሃያ ወጋግራዎችን አብጅ።
\s5
\v 19 ወጋግራዎች የሚሆኑ አርባ የብር መቆሚያዎችን አብጅ። ከመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መጋጠሚያዎች እንዲሆኑ ሁለት መቆሚያዎች ይኑሩ። በሌሎች ወጋግራዎች በያንዳንዳቸው ሥርም ለሁለት መጋጠሚያዎቻቸው ሁለት መቆሚያዎች ይዘጋጁ።
\v 20 በሰሜን በኩል ላለው ለሁለተኛው የመገናኛው ድንኳን ጎን ሃያ ወጋግራዎችንና አርባ የብር መቆሚያዎቻቸውን ሥራ።
\v 21 በመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች፣ በሚቀጥለው ወጋግራ ሥርም እንደዚሁ ሁለት መቆሚያዎች. በእያንዳንዱ ሥር ይሁኑ።
\s5
\v 22 በምዕራብ በኩል ላለው ለመገናኛው ድንኳኑ የኋላ ጎን ስድስት ወጋግራዎችን አብጅ።
\v 23 ለኋላ ማእዘኖቹም ሁለት ወጋግራዎችን አብጅ።
\v 24 እነዚህ ወጋግራዎች ከታች ጥንድ፣ ከላይ ደግሞ በአንድ ቀለበት የተያያዙ መሆን አለባቸው። ለሁለቱም የኋላ ማእዘኖች የሚሆነው በዚህ መንገድ ነው።
\v 25 ወጋግራዎች ከብር መቆሚያዎቻቸው ጋር ሊኖሩ ይገባል። በሁሉም ዐሥራ ስድስት መቆሚያዎች ናቸው ያሉት፤ በመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች፣ በሚቀጥለው ወጋራ ሥርም ሁለት መቆሚያዎችና በእያንዳንዱም ሥር እንዲሁ።
\s5
\v 26 ድንኳኑ አንደኛ ጎን ወጋግራዎች ዐምስት አግዳሚዎችን ከግራር ዕንጨት አዘጋጅ፤
\v 27 ለማደሪያ ድንኳኑ ሌላ ጎንም ወጋግራዎች ዐምስት አግዳሚዎችን፣ በምዕራብ በኩል ላለው ለመገናኛ ድንኳኑ የኋላ ጎን ወጋግራዎችም ዐምስት አግዳሚዎችን እንዲሁ አብጅ።
\v 28 በወጋግራዎቹ መካከል ላይ ያለው አግዳሚ ከዳር እስከ ዳር መድረስ አለበት።
\s5
\v 29 ወጋግራዎቹን በወርቅ ለብጣቸው። አግዳምዎችን ደግፍ በመያዝ እንዲያገለግሉም የወርቅ ቀለበቶቻቸውን ሥራላቸው፤ አግዳሚዎችንም በወርቅ ለብጣቸው።
\v 30 ድንኳኑን መትከል ያለብህ በተራራው ላይ ያየኸውን ምሳሌ በመተከትል ነው።
\s5
\v 31 ብልኅ ሠራተኛ ኪሩቤልን የጠለፈበት፣ የሰማያዊ፣ የሐምራዊ፣ የቀይ ግምጃና አምሮ የተፈተለ በፍታ መጋረጃ አብጅ።
\v 32 በወርቅ በተለበጡ የግራር ዕንጨት አራት ዐምዶች ላይ ልትሰቅለው ይገባል። እነዚህ ዐምዶች በአራት የብር መቆሚያዎች ላይ የተቀመጡ የወርቅ ኵላቦች ይኖሯቸዋል።
\v 33 መጋረጃውን በማያያዣዎቹ አንጠልጥለው፤ የምስክሩንም ታቦት አግባው። መጋረጃው ቅድስቱን ከቅድስተ ቅዱሳን ይለየዋል።
\s5
\v 34 በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ባለ ውበምስክሩ ታቦት ላይ የስርየት መክደኛውን አስቀምጥ።
\v 35 ከመጋረጃው ውጭ፣ መቅረዙንም ከመገናኛው ድንኳን ደቡባዊ ጎን ከጠረጴዛው ትይዩ አስቀምጥ። ጠረጴዛው በሰሜናዊ ጎኑ በኩል መቀመጥ ይኖርበታል።
\s5
\v 36 መግቢያ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ በጥልፍ ብሚያስጌጥ ሠራተኛ የተሠራ መጋረጃ አብጅለት።
\v 37 ዐምስት ምሰሶዎችን ከግራር ዕንጨት አብጅና በወርቅ ለብጣቸው። ኵላቦቻቸውም የውርቅ መሆን እላቸው፤ ዐምስት የነሐስ መቆሚያዎችንም ሥራላቸው።
\s5
\c 27
\p
\v 1 ዐምስት ክንድ ወርዱም ዐምስት ክንድ የሆነ መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሥራ። መሠዊያው አራት ማእዘንና ሦስት ክንድ ከፍታ ይኑረው።
\v 2 ማእዘኖች የበሬ ቀንድ ቅርጽ እንዲኖራቸው ታደርጋለህ። ቀንዶቹ ከመሠዊያው ጋር አንድ ወጥና በነሐስ የተለበጡ ይሆናሉ።
\s5
\v 3 የመሠዊያውን ዕቃዎች፦ የዐምድ ማስወገጃ ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችን፣ ጎድጓዳ ሳሕኖችን፣ የሥጋ ሜንጦዎችንና የፍም መያዣዎችን ሁሉ ከነሐስ አብጃቸው።
\v 4 ለመሠዊያው ከነሐስ እንደ መረብ የተሠራ ፍርግርግ አብጅለት። በፍርግርጉ አራት ማእዘኖች በያንዳንዳቸው ላይም የነሐስ ቀለበት አድርግ።
\s5
\v 5 አጋማሽ ወገብ እስከ ታች እንዲደርስ ፍርግርጉን ከመሠዊያው እርከን ሥር አድርገው።
\v 6 ለመሠዊያው መሎጊያዎችን ከግራር ዕንጨት አበጅተህ በነሐስ ለብጣቸው።
\s5
\v 7 በቀለበቶቹ ውስጥ መግባትና መሠዊያውን ለመሸከም በሁለቱ ጎኖቹ ላይ መቀመጥ አለባቸው።
\v 8 ባዶ እንዲሆን ከሳንቃዎች አብጀው። በተራራው ላይ ባየኸው መሠረት ልትሠራው ይገባል።
\s5
\v 9 ድንኳን አደባባይ ሥራለት። በአደባባዩ ደቡብ ጎንም አንድ መቶ ክንድ እርዝመት ያላቸው የአማረ በፍታ መጋረጃዎች ይደረጉ።
\v 10 መጋረጃዎቹ ከሃያ የነሐስ መቆሚያዎች ጋር ሃያ ምሰሶዎች ይኑሯቸው። ከምስሶዎቹ ጋር የተያያዙ የብር ኵላቦችና ዘንጎችም መኖር አለባቸው።
\s5
\v 11 በሰሜን በኩልም እንደዚሁ አንድ መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ከሃያ ምሰሶዎች፣ ከሃያ የነሐስ መቆሚያዎችም ጋር ከምሰሶውቹ ጋር የተያያዙ የብር ኵላቦችና ዘንጎች ሊኖሩ ይገባል።
\v 12 በአደባባዩ ምዕራብ ጎንም ዐምሳ ክንድ ርዝመት ያለው መጋረጃ ይደረግ። ዐሥር ምሰሶዎችና ዐሥር መቆሚያዎችም ይኑሩት።
\v 13 በምሥራቅም በኩል አደባባዩ ዐምሳ ክንድ እርዝመት ይኑረው።
\s5
\v 14 የመግቢያው አንድ ጎን መጋረጃዎች ዐሥራ ዐምስት ክንድ እርዝመት ሊኖራቸው ይገባል። ሦስት ምሰዎችም ከሦስት መቆሚያዎች ጋር ይኖሯቸዋል።
\v 15 ሌላው ጎንም ዐሥራ ዐምስት ክንድ እርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ይኖሩታል። የራሳቸው ሦስት ምሰሶዎችና ሦስት መቆሚያዎች ይኖሯቸዋል።
\v 16 መግቢያ መጋረጃ ሃያ ክንድ እርዝመት ያለው፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ ጠላፊ ጠልፎበት የተሠራ ይሁን። አራት ምሰሶዎች ከአራት መቆሚያዎች ጋር ሊኖሩት ይገባል።
\s5
\v 17 የአደባዩ ምሰሶዎች ሁሉ የብር ዘንጎችና ኵላቦች፣ የነሐስ መቆሚያዎችም ይኑሯቸው።
\v 18 የአደባባዩ እርዝመት አንድ መቶ ክንድ፣ ወርዱ ዐምሳ ክንድ፣ ቁመቱ ዐምስት ክንድ ይሁን፤ የበፍታ መጋረጃዎችና የነሐስ መቆሚያዎችም ይኑሩት።
\v 19 በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አገልግሎት የሚሰጥ ዕቃ ሁሉ፣ የድንኳኑ ካስማዎችም በሙሉ፣ አደባባዩም ከነሐስ መሠራት አለባቸው።
\s5
\v 20 ሁልጊዜ እንዲበሩ ለመብራቶቹ የወይራ ጭማቂ ንጹሕ ዘይት እንዲያመጡ እስራኤላውያንን እዘዛቸው።
\v 21 በመገናኛው ድንኳን ውስጥ፣ ከመጋረጃው ውጭ በምስክሩ ታቦት ፊት፣ አሮንና ልጆቹ መብራቶቹን ከማታ እስከ ንጋት ድረስ በእግዚአብሔር ፊት እንዲበሩ ያድርጉ። ይህም ለእስራኤል ትውልድ ሁሉ የዘለዓለም ሥርዐት ይሆናል።
\s5
\c 28
\p
\v 1 ሆነው እንዲያገለግሉኝ ወንድምህን ዘሮንንና ልጆቹን ናዳብን፣ አብድዩን፣ አልዓዛርንና ኢታምርን ከእስራኤል መካከል ወደ አንተ ጥራ።
\v 2 ለወንድምህ ለአሮን ለእኔ የተቀደሱ ልብሶችን አዘጋጅ። እነዚህ ልብሶች ለአሮን ክብርና ማዕርግ የሚሆኑ ናቸው።
\v 3 ካህኔ ሆኖ እንዲያገለግለኝ የአሮንን ልብሶች የሚሠሩለትን፣ በልባቸው ጥበበኛ የሆኑትን፣ የጥበብን መንፈስም የሞላሁባቸውን ሰዎች ሁሉ አነጋግር።
\s5
\v 4 የሚሠሯቸው ልብሶችም የደረት ኪስ፣ ኤፉድ፣ ቀሚስ፣ ጥልፍ የተጠለፈበት ሸሚዝ፣ መጠምጠሚያና መታጠቂያ ናቸው። ለእኔ የተቀደሱትን እነዚህን ልብሶች መሥራት አለባቸው። ልብሶቹ ካህናት ሆነው እንዲያግለግሉኝ ለወንድምህ ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናሉ።
\v 5 ወርቅ፣ ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና የአማረ በፍታ ይጠቀሙ።
\s5
\v 6 ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግን ኣአምሮ ከተፈተለ በፍታ ይሥሩት። ሥራው የብልኀተኛ ሙያተኝ ሥራ ሊሆን ይገባል።
\v 7 ኤፉዱ ከሁለቱ ጠርዞቹ ጋር የሚያያዙ ሁለት የትከሻ ንጣዮች ይኑሩት።
\v 8 በብልኀት የተጠለፈው የወገብ መታጠቂያም እንደ ኤፉድ መሆን አለበት፦ ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ ወጥ ሆኖ የተሠራ ይሁን።
\v 9 ሁለት የመረግድ ድንጋዮችን ወስደህ የዐሥራ ሁለቱን የእስራኤል ልጆች ስሞች ቅረጽባቸው።
\s5
\v 10 ስድስቱ ስሞቻቸው በአንድ ድንጋይ፣ ስድስቱ ሌሎች ደግሞ በሌላው ድንጋይ ላይ እንደየልጁ ልደት ቀደም ተከተል ይቀረጹ።
\v 11 ሠራተኛ ማኅተም እንደሚቀርጽ የእስራኤልን ዐሥራ ሁለት ልጆች ስሞች በሁለቱ ድንጋዮች ላይ ቅረጽ። ድንጋዮቹንም በወርቅ ክፈፋቸው።
\v 12 ሁለቱን ድንጋዮች የእስራኤልን ልጆች አምላክ የሚያስታውሱ ድንጋዮች እንዲሆኑ በኤፉዱ የትከሻ ንጣዮች ላይ አስቀምጥ። መታሰቢያ እንዲሆኑ አሮን ስሞቻቸውን በሁለቱ ትከሻዎቹ ላይ በእግዚአብሔር ፊት ይሸከማል።
\s5
\v 13 ፈርጦችንና
\v 14 እንደ ገመድ የተጎነጎኑ የንጹሕ ወርቅ ድሪዎችን አበጅተህ ከፈርጦቹ ጋር አያይዛቸው።
\s5
\v 15 ብልኅ ሠራተኛ እንደሚሠራው፣ ኤፉዱ በተሠራበት መንገድ ፍርድ የሚሰጥበትን የደረት ኪስ አብጅ። ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ ሥራው።
\v 16 አራት ማእዘን ያለ ውይሁን። የደረት ኪሱን ዐጥፈህ ድርብ አድርገው። አንድ ስንዝር እርዝመት፣ አንድ ስንዝር ስፋትም ይኑረው።
\s5
\v 17 ዕንቆችን በአራት ረድፍ አስቀምጥ። የመጀመሪያው ረድፍ ሰርድዮን፣ ቶነዝዮንና አብረቅራቂ ዕንቊ ሊኖሩት ይገባል።
\v 18 ሁለተኛው ረድፍ በሉር፣ ሰንፔርና አልማዝ ይኑሩት።
\v 19 ሦስተኛው ረድፍ ያክንት፣ ኬልቄዶንና አማቴስጢኖስ ይገኙበታል።
\v 20 አራተኛው ረድፍ ቢረሌ፣ መረግድና ኢያስጲድ ይኑሩት። በወርቅ ፈርጥ ክፈፍ ሊደረግላቸው ይገባል።
\s5
\v 21 ድንጋዮቹ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ልጆች ስሞች ቅደም ተከተል መሠረት መቀመጥ፣ ከእስራኤል ነገዶች አንዱን በመወከልም በቀለበት ማተሚያ እንደሚቀረጽ እያንዳንዱ ስም የተቀረጸባቸው መሆን አለባቸው።
\v 22 ኪሱ ከንጹሕ ወርቅ እንደ ገመድ የተጎነጎኑ ድሪዎችን አብጅለት።
\v 23 ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሥራና ከደረት ኪሱ ሁለት ጎኖች ጋር አያይዛቸው።
\v 24 የወርቅ ድሪዎች ከደረት ኪሱ ሁለት ማእዘኖች ጋር አያይዛቸው።
\s5
\v 25 ጕንጕን ድሪዎች ሌሎች ጎኖች ከሁለቱ የወርቅ ፈርጦች ጋር አገናኛቸው። ከኤፉፉ የትከሻ ንጣዮች ጋርም በፊቱ በኩል አያይዛቸው።
\v 26 የወርቅ ቀለበቶችን ሥራና ከውስጠኛው የኤፉዱ ጎን ቀጥሎ ባለው ጠርዝ ላይ፣ በደረት ኪሱ ሌሎች ሁለት ጎኖች ላይ አድርጋቸው።
\s5
\v 27 ሁለት ተጨማሪ የወርቅ ቀለበቶችን አብጅና በብልኀት ከተጠለፈው ከሴፉዱ መታጠቂያ በላይ፣ መጋጠሚያው አጠገብ ከኤፉዱ ፊት ሁለት የትከሻ ንጣዮች ግርጌ ጋር አያይዛቸው።
\v 28 ከኤፉዱ መታጠቂያ በላይ መያያዝ እንዲችሉ፣ የደረት ኪሱን ቀለበቶቹ ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋር በሰማያዊ ገመድ ማሰር አለባቸው። ይህም የሚሆነው የደረት ኪሱ ከኤፉዱ ጋር ሳይያያዝ እንዳይቀር ነው።
\s5
\v 29 አሮን ወደ መቅደሱ በገባ ጊዜ፣ የዐሥራ ሁለቱን የእስራኤል ልጆች ስሞች በደረት ኪሱ ላይ ለፍርድ በልቡ ላይ ይሸከም። ይህም በእግዚአብሔር ፊት የዘለዓለም መታሰቢያ ሆኖ ያገለግላል።
\v 30 በፍርድ መስጫው የደረት ኪስ ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን አስቀምጥ። አሮን ወደ እግዚአብሔር ፊት ሲቀርብ፣ ኡሪምና ቱሚም በደረቱ ላይ መኖር አለባቸው፤ አሮንም ለእስራኤል ፍርድ መስጫውን በእግዚአብሔር ፊት ሲቀርብ ሁልጊዜ መሸከም ይኖርበታል።
\s5
\v 31 ቀሚስ ሙሉ በሙሉ ሰማያዊ ይሁን።
\v 32 ለራስ ማስገቢያ ክፍተት ይኑረው፤ ክፍተቱም እንዳይቀደድ ዙሪያውን የተዘመዘመ ጠርዝ ይኑረው። ይህ ሥራ የሸማኔ ሥራ መሆን አለበት።
\s5
\v 33 የግርጌ ጠርዝ ላይ የሰማያዊ፣ የሐምራዊና የቀይ ማግ ሮማኖችን በዙሪያው አድርግ። በመካከላቸውም ዙሪያውን የወርቅ ሻኵራዎችን አብጅ።
\v 34 የወርቅ ሻኵራዎቹና ሮማኖቹ በቀሚሱ ጠርዝ ዙሪያ እየተፈራረቁ መቀመጥ አለባቸው።
\v 35 ወደ መቅደሱ ሲገባና በእግዚአብሔር ፊት ሲሆን፣ ከመቅደስ ሲወጣም፣ ድምፁ እንዲሰማ ቀሚሱን አሮን ሲያገለግል ይልበሰው። ይህም የሚደረገው አሮን እንዳይሞት ነው።
\s5
\v 36 ከንጹሕ ወርቅ ሳሕን አብጅና በቀለበት ላይ ማኅተም እንደሚቀረጽ፣ “ቅዱስ ለእግዚአብሔር” ብለህ በላዩ ቅርጽበት።
\v 37 ሳሕን ከመጠምጠሚያው ፊት ጋር በሰማያዊ ገመድ አያይዘው።
\v 38 ሁልጊዜም በአሮን ግንባር ላይ ይሁን፤ አሮን እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር ለይተው ከሚያቀርቧቸው የተቀደሱ ስጦታዎች ጋር የሚያያዝ ማንኛውንም በደል ይሸከማል። እግዚአብሔር ስጦታዎቻቸውን እንዲቀበል፣ መጠምጠሚያ ሁልጊዜ በአሮን ግንባር ላይ መሆን አለበት።
\s5
\v 39 ሸሚዙንም፣ መጠምጠሚያውንም ከአማረ በፍታ ትሠራለህ። መታጠቂያውም በጥልፍ ጠላፊ እንዲሠራ ታደርጋለህ።
\s5
\v 40 ለአሮን ልጆችም ሸሚዞቹን፣ መታጠቂያዎችንና የራስ ማሰሪያዎችን ለክብራቸውና ለማዕረጋቸው ታደርጋለህ።
\v 41 ለወንድምህ ለአሮንና ለልጆቹ አልብሳቸው። ቅባቸው፣ ሹማቸውም፤ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝም ለእኔ ቀድሳቸው።
\s5
\v 42 እስከ ጭን የውስጥ ሰውነታቸውን የሚሸፍን የውስጥ ልብሶችን ከበፍታ ሥራ።
\v 43 ልጆቹ ውደ መገናኛው ድንኳን ሲገቡ፣ ወይም መቅደሱ ውስጥ ለማገልገል ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ እነዚህን የውስጥ ልብሶች መልበስ አልባቸው። በደል እንዳይገኝባቸውና እንዳይሞቱ ይህን ማድረግ ይገባቸዋል። ይህ ለአሮንና ከእርሱም በኋላ ለሚመጡት ዘሮቹ የዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል።
\s5
\c 29
\p
\v 1 ሆነው እንዲያገለግሉኝ እነርሱን ለእኔ ለመቀደስ አሁን የምታደርገው ይህ ነው። ነውር የሌለባቸውን አንድ ወይፈንና ሁለት አውራ በጎች፣
\v 2 የሌለበትን እንጀራና ዘይት የተቀላቀለበትን እንጎቻ ውሰድ፤ ዘይት የተቀባ ስስ ቂጣም አድርግ።
\s5
\v 3 በአንድ ሌማት አድርጋቸውና ከወይፈኑና ከአውራ በጎቹ ጋር አቅርባቸው።
\v 4 አሮንንና ልጆቹንም ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ አቅርባቸው። በውሀም እጠባቸው።
\s5
\v 5 ውሰድና፦ ሸሚዙን፣ የኤፉዱን ቀሚስ፣ ኤፉዱን፣ የደረት ኪሱን፣ በብልኀት የተጠለፈውን የኤፉዱን መታጠቂያ በወገቡ ዙሪያ በማስታጠቅ አሮን አልብሰው።
\v 6 ቅዱሱን አክሊል በላዩ አስቀምጠህ መጠምጠሚያውን በአሮን ራስ አድርግ።
\v 7 ዘይቱንም ወስደህ በራሱ ላይ በማፍሰስ ቅባው።
\s5
\v 8 አምጥተህ ሸሚዞችን አልብሳቸው።
\v 9 መታጠቂያዎችን ለአሮንና ለልጆቹ ታስታጥቃቸዋለህ፤ የራስ ማሰሪያዎችንም ታደርግላቸዋለህ። የክህነቱ ሥራ በዘለዓለማዊ ሕግ የእነርሱ ይሆናል። እኔን እንዲያገለግሉኝ አሮንና ልጆቹን ትክናቸዋለህ።
\s5
\v 10 በመገናኛው ድንኳን ፊት አቅርብ፤ አሮንና ልጆቹም በወይፈኑ ራስ ላይ እጆቻቸውን ይጫኑ።
\v 11 በእኔ በእግዚአብሔር ፊት በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ዕረደው።
\s5
\v 12 ከወይፈኑ ደም ጥቂት በጣትህ ወስደህ በመሠዊያው ቀንዶች ላይ ታደርጋለህ፤
\v 13 የሆድ እቃዎችን የሚሸፍነውን ስብ ሁሉ ጉበቱን የሚሸፍነውንና ሁለቱን ኩላሊቶች በላያቸው ካለው ስብ ጋር ወስደህ ሁሉንም በመሰዊያው ላይ ታቃጥላቸዋለህ።
\v 14 ነገር ግን የወይፈኑን ሥጋ ግን ቁርበቱንና ፈርሱን ጭምር ከሰፈር ውጭ አውጥተህ ታቃጥላለህ። ያ የኀጢአት መሥዋዕት ይሆናል።
\s5
\v 15 የአውራ በግም ውሰድና አሮንና ልጆቹ እጆቻቸውን ይጫኑበት።
\v 16 በጉን ዕረደው፤ ደሙንም ወስደህ በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን እርጨው።
\v 17 በጉን ለሁለት ክፈልና የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን እጠብ፤ የሆድ ዕቃውንም ከተቆራተጡ ብልቶችና ከራሱ ጋር
\v 18 ላይ አስቀምጥ። ከዚያም እውራ በጉን ሙሉ በሙሉ አቃጥለው። ለእኔ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆናል። ይህም ለእኔ ጣፋጭ መዐዛ ያለው፣ በእሳት የቀረበልኝ መሥዋዕት ይሆናል።
\s5
\v 19 ሌላውንም አውራ በግ ወስደህ አሮንና ልጆቹ እጆቻቸውን በራሱ ላይ ይጫኑበት።
\v 20 በኋላ አውራ በጉን ዕረደው፤ ከደሙም ጥቂት ውሰድና በአሮን ቀኝ ጆሮ ጫፍና በልጆቹ ቀኝ ጆሮዎች ጫፍ ላይ፣ በቀኝ እጆቻቸውና በቀኝ እግሮቻቸው አውራ ጣቶች ላይ አድርግ። ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን እርጨው።
\s5
\v 21 ካለው ደም፣ ከመቅቢያው ዘይትም ጥቂት ውሰድና በአሮንና በልብሶቹ፣ በልጆቹና በልብሶቻቸውም ላይ እርጨው። አሮንና ልብሶቹ፣ ልጆቹና ልብሶቻቸው ከእርሱ ጋር ይቀደሱልኛል።
\s5
\v 22 በጉን ሥብ፣ ላቱን፣ ሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሥብ፣ የጉበቱን መሸፈኛ፣ ሁለቱን ኵላሊቶችና በላያቸው የሚገኘውን ሥብ፣ የቀኙን ወርችም ውሰድ፤ ይህ አውራ በግ ካህኑ ለእኔ የሚቀደስበት ነውና።
\v 23 እንጀራ፣ አንድ በዘይት የተጋገረ እንጎቻና አንድ ስስ ቂጣ በእኔ በእግዚአብሔር ፊት ከሚሆነው ያለ እርሾ ከተጋገረው ኅብስት ሌማት ትወስዳለህ።
\s5
\v 24 እነዚህን በአሮን እጆችና በልጆቹ እጆች ታስቀምጣለህ። እነርሱ በእኔ በእግዚአብሔር ፊት ይወዝውዟቸው፤ መሥዋዕት አድርገውም ለእኔ ያቅርቧቸው።
\v 25 ከእጆቻቸው ወስደህ ከሚቃጠለው መሥዋዕት ጋር በመሠዊያው ላይ አቃጥለው። ለእኔ ጣፋጭ መዐዛ ያለው፣ በእሳት የቀረበልኝ መሥዋዕት ይሆናል።
\s5
\v 26 የአሮንን የክህነት አውራ በግ ፍርምባ ወስደህ ወዝውዘውና መሥዋዕት አድርገህ ለእኔ ለእግዚአብሔር አቅርበው። ይህም አንተ የምትበላው የአንተ ድርሻ ይሆናል።
\v 27 የመሥዋዕቱን ፍርምባና የቀረበውን የመሥዋዕቱን ወርች ለእኔ ቀድስልኝ፤ ሁለቱም አሮንና ልጆቹ ለእኔ ካህናት መሆናቸውን ለማረጋገጥ ከአውራ በጉ የሚገኙ ናቸው።
\v 28 የሚሰጧቸው እነዚህ የሥጋ ክፍሎች ምንጊዜም የአሮንና የልጆቹ ናቸው። በኅብረቱ መሥዋዕቶች ሥርዐት፣ ከእስራኤላውያን ለካህናቱ፣ ለእኔ ለእግዚአብሔር የሚቀርቡ መሥዋዕቶች ይሆናሉ።
\s5
\v 29 የአሮን የተቀደሱ ልብሶች ከእርሱ በኋላ ለልጆቹም ይሆናሉ። በልብሶቹ የአሮን ልጆች ለእኔ መቀባትና መካን አለባቸው።
\v 30 በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ እኔን ለማገልገል ወደ መገናኛው ድንኳን የሚገባ፣ አሮንን ከልጆቹ መካከል የሚተካ እነዚያን ልብሶች ሰባት ቀን ይልበስ።
\s5
\v 31 የክህነቱን አውራ በግ ውሰድና ሥጋውን በተቀደሰ ስፍራ ቀቅለው።
\v 32 ልጆቹ የአውራ በጉን ሥጋና በመገናኛው ድንኳን መግቢያ በር ባለው ሌማት የተቀመጠውን ኅብስት ይብሉት።
\v 33 ለማስተስረይና ለእኔ እንዲቀደሱ የቀረቡትን ሥጋውንና ኅብስቱን መብላት አለባቸው። ሌላ ሰው መብላት አይችልም፤ ምክንያቱም ምግቡን ለእኔ የተቀደሰ አድርገው ሊይዙት ይገባል።
\v 34 መሥዋዕቱ ሥጋ፣ ወይም ከኅብስቱ እስከሚቀጥለው ጠዋት ድረስ አንዳች የሚተርፍ ከሆነ፣ አቃጥለው። ለእኔ የተቀደሰ ስለ ሆነ መበላት የለበትም።
\s5
\v 35 በዚህ መንገድ እንድታደርገው ያዘዝሁህን ሁሉ በመከተል ለአሮንና ለልጆቹ ትፈጽምላቸዋለህ። እነርሱን ሰባት ፍቀን ቀድስልኝ።
\v 36 ለስርየት የሚሆን የኀጢአት መሥዋዕት በየቀኑ አንድ ወይፈን አቅርብ። ማስተሰረያውን በማድረግም መሠዊያውን አንጻ፤ ለእኔ ለመቀደስም ቅባው።
\v 37 ሰባት ቀን ማስተሰረያ አድርግለትና ለእግዚአብሔር ቀድሰው። ከዚያ በኋላ መሠዊያው ሙሉ በሙሉ የተቀደሰ ይሆናል፤ መሠዊያውን የሚነካውም ሁሉ ይቀደሳል።
\s5
\v 38 የአንድ ዓመት ጠቦቶችን ዘወትር በየቀኑ በመሠዊያው ላይ አቅርብ።
\v 39 ጠቦት ማለዳ፣ ሌላውን ደግሞ ምሽት ላይ ታቀርበዋህ።
\s5
\v 40 ከመጀመሪያው ጠቦታ ጋር የኢፍ አንድ ዐሥረኛን ያማረ ዱቄት ተወቅጦ ከተጠለለ ሩብ ኢፍ ዘይት ጋር በመለወስ፣ ሩብ ወይንንም የመጠጥ ቍርባን በማድረግ አቅርብ።
\s5
\v 41 ሁለተኛውን ጠቦት በምሽት ሠዋው። በማለዳ እንደ ተሠዋው ጠቦት ተመሳሳይ የእህልና የመጠት ቍርባን ማቅረብ አለብህ። እነዚህ መሥዋዕቶች ለእኔ ጣፋጭ መዐዛ ያላቸው በእሳት የቀረቡልኝ መሥዋዕቶች ናቸው።
\v 42 ትውልዶች ሁሉ ዘወትር የሚቀርቡ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ናቸው። ላናግራችሁ ከእናንተ ጋር በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን መግቢያ በር በእኔ በእግዚአብሔር ፊት መሥዋዕቶቹን አቅርቧቸው።
\s5
\v 43 ከእስራኤላውያን ጋር የምገናኝበት ቦታ ያ ነው፤ ድንኳኑ በክብሬ ይቀደስልኛል።
\v 44 የመገናኛውን ድንኳንና መሠዊያውን የእኔ ብቻ እንዲሆኑ እቀድሳቸዋለሁ። ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝ አሮንንና ልጆቹን እለያቸዋለሁ።
\s5
\v 45 በእስራኤላውያን መካከል እኖራለሁ፤ አምላካችውም እሆናለሁ።
\v 46 በመካከላቸው እንድኖር፣ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው እኔ እግዚአብሔር አምላካችው እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
\s5
\c 30
\p
\v 1 ዕጣን የሚጤስበት መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሥራ።
\v 2 እርዝመቱ አንድ ክንድ፣ ወርዱም አንድ ክንድ ይሁን። አራት ማእዘንና ሁለት ክንድ ከፍታ ይኑረው። ቀንዶቹ ከመሠዊያው ጋር ወጥ ይሁኑ።
\s5
\v 3 የዕጣን መሠዊያውን ላይኛ ክፍል፣ ጎኖቹንና ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ለብጣቸው። የመሠዊያውን ዙሪያ በወርቅ ክፈፈው።
\v 4 ከክፈፉ በታች በሁለቱ ትይዩ ጎኖቹ ላይ እንዲያያዙ ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን አብጅ። ቀለበቶቹ መሠዊያውን ለመሸከም መሎጊያዎችን ደግፈው የሚይዙ ናቸው።
\s5
\v 5 ከግራር ዕንጨት ሥራና በወርቅ ለብጣቸው።
\v 6 የዕጣን መሠዊያውን ከመጋረጃው ፊት በምስክሩ ታቦታ አጠገብ አስቀምጠው። ይህም እኔ ከአንተ ጋር በምገናኝበት፣ በምስክሩ ታቦታ ላይ ካለው ከስርየት መክደኛው ፊት ይሆናል።
\s5
\v 7 ደስ የሚያሰኝ መዐዛ ያለውን ዕጣን ሁልጊዜ ጧት ቷት ያጢስ። ማጤስ ያለበትም መብራቶቹን በሚያዘጋጅበት ጊዜ ነው።
\v 8 መብራቶቹን በምሽት ሲያበራም፣ በዕጣን መሠዊያው ላይ ዕጣን ማጤስ አለበት። ይህ በእኔ በእግዚአብሔር ፊት ዘወትር በትውልዶች ሁሉ የሚጤስ ዕጣን ይሆናል።
\v 9 ነገር ግን ሌላ ዕጣን፣ አንዳችም የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም የእህል ቍርባን በዕጣን መሠዊያው ላይ አታቅርብ፤ ምንም ዐይነት የመጠጥ ቍርባንም አታፍስስበት።
\s5
\v 10 መሠዊያው ቀንዶች ላይ አሮን በዓመት አንድ ጊዜ ማስተስረያ ያድርግ ይህንም የሚያደርገው የኀጢአት ስርየት ደሙን በመጠቀም ነው። ሊቀ ካህናቱ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ይህን ያድርገው። ይህ መሥዋዕት ሙሉ በሙሉ ለእኔ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል።”
\s5
\v 11 ሙሴን እንዲህ አለው፤
\v 12 ስትቆጥራቸው፣ እያንዳንዱ ሰው ለራሱ ሕይወት ቤዛ ለእግዚአብሔር መክፈል አለበት። ስትቆጥራቸውና ከቆጠርሃቸውም በኋላ በመካከላቸው መቅሠፍት እንዳይኖር ይህን አድርግ።
\v 13 የተመዘገበ እያንዳንዱ ሰው በመቅደሱ ሰቅል ክብደት መሠረት የብር ግማሽ ሰቅል ይክፈል። ይህ ግማሽ ሰቅልም ለእኔ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት ይሆናል።
\v 14 ከሃያ እና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያለው የተቆጠረ ሁሉ ይህን መሥዋዕት ለእኔ ማቅረብ አለበት።
\s5
\v 15 ለሕይወታቸው ማስተስረያ ለማድረግ ይህን መሥዋዕት ለእኔ ሲያቀርቡ፣ ባለጠጋው ከግማሽ ሰቅል የበለጠ፣ ድኻውም ከዚያ ያነሰ መስጠት የለባቸውም።
\v 16 የማስተስረያ ገንዘብ ከእስራኤላውያን ተቀበልና ለመገናኛ ድንኳኑ ሥራ አውለው። ለሕይወታችሁ ማስተስረያ ማድረግ በፊቴ ለእስራኤላውያን መታሰቢያ ይሁን።”
\s5
\v 17 ሙሴን እንዲህ አለው፤
\v 18 ትልቅ የናስ ሳሕን ከናስ መቆሚያ ጋር አብጅ። በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል አስቀምጠውና ውሀ አድርግበት።
\s5
\v 19 ልጆቹ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ውስጡ ባለው ውሀ ይታጠቡ።
\v 20 መገናኛው ድንኳን ሲገቡ ወይም የሚቃጠል መሥዋዕት በማቅረብ እኔን ለማገልገል ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ፣ እንዳይሞቱ በውሀ መታጠብ አለባቸው።
\v 21 እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ሊታጠቡ ይገባል። ይህ ለአሮንና ለዘሮቹ በትውልዶቻቸው ሁሉ የሁልጊዜ ሕግ ይሁን።”
\s5
\v 22 ሙሴን እንዲህ አለው፤
\v 23 ምርጥ ቅመሞች፦ ዐምስት መቶ ሰቅል ፈሳሽ ከርቤ፣ ሁለት መቶ ዐምሳ ሰቅል ጣፋጭ ሽታ ያለው ቀረፋ፣ ሁለት መቶ ዐምሳ ሰቅል ጠጅ ሣር፣
\v 24 ዐምስት መቶ ሰቅል ብርጕድ በመቅደሱ ሰቅል ክብደት ተለክቶ፣ አንድ የኢን መስፈሪያ ወይራ ዘይትም ውሰድ።
\v 25 ቅመሞች በሽቶ ቀማሚ ሥራ የተቀደሰ መቅቢያ ዘይት አዘጋጅ። ይህ ለእኔ የተቀደሰ መቅቢያ ዘይት ይሆናል።
\s5
\v 26 ዘይት የመገናኛውን ድንኳን፣ የምስክሩን ታቦትም፣
\v 27 ጠረጴዛውንና ዕቃውንም ሁሉ፣ መቅረዙንና ዕቃውን፣ የዕጣን መሠዊያውንም፣
\v 28 የሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረቢያ መሠዊያውን ከዕቃው ሁሉ ጋር፣ መታጠቢያ ሳሕኑንም ከመቆፕሚያው ጋር ቅባ።
\s5
\v 29 ለእኔ የተቀደሱ እንዲሆኑ እነርሱን ለይልኝ። እነርሱን የሚነካ ማንኛውም ነገርም የተቀደሰ ይሆናል።
\v 30 ሆነው እንዲያገለግሉኝ አሮንንና ልጆቹን ቅባቸው፣ ለእኔም ለያቸው።
\v 31 እንዲህ በላቸው፤ ‘ይህ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ መቅቢያ ዘይት መሆን አለበት።
\s5
\v 32 የሰው ቆዳ ሊቀባበት አይገባም፤ እንደዚህ ያለ አንዳችም ዘይት በአንድ ዐይነት ቀመር መሥራት የለባችሁም ምክንያቱም ይህ ዘይት ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ዘይት ነው። እናንተም ቅዱስ መሆኑን ዐስቡ።
\v 33 እንደዚህ የሚሠራ ሁሉ፣ ወይም ከዚህ ዘይት ጥቂት በሰው ላይ የሚያፈስስ ሁሉ፣ ከወገኑ ይወገድ።’”
\s5
\v 34 ሙሴን እንዲህ አለው፤ “የጣፋጭ ሽቶ ቅመሞችን፦ የሚንጠባጠብ ሙጫ፣ በዛጎል ውስጥ ያለ ሽቶ፣ የሚሸት ሙጫ ከንጹሕ ዕጣን ጋር፣ እያንዳንዱን በእኩል መጠን ውሰድ፥
\v 35 በሽቶ ቀማሚ እንደ ተሠራ፣ በጨው የተቀመመ፣ ንጹሕና ለእኔ የተቀደሰ ዕጣን አድርገው።
\v 36 አድቅቀህ ትወቅጠዋለህ። ከፊሉን ከአንተ ጋር በምገናኝበት፣ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ባለው በምስክሩ ታቦት ፊት ለፊት አስቀምጥ። ለእኔ የተቄደሰ መሆኑንም ዐስብ።
\s5
\v 37 እንደምትዘጋጀው ዕጣን በአንድ ዐይነት ቀመር ለራስህ ምንም አታድርግ። ለአንተ እጅግ ቅዱስ ይሁን።
\v 38 እንደ ሽቶ ለመጠቀም እንደዚህ አድርጎ የሚሠራ ሁሉ ከገዛ ወገኑ ይወገድ።”
\s5
\c 31
\p
\v 1 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤
\v 2 “የሖር የልጅ ልጅ የሆነውን የኡሪን ልጅ ባስልኤልን ከይሁዳ ነገድ በስሙ ጠርቼዋለሁ።
\s5
\v 3 ለሁሉም ዐይነት የእጅ ሞያ ጥበብን፣ ማስተዋልንንና ዕውቀትን እንዲሰጠው፣ ባስልኤልን በመንፈስ ሞልቼዋለሁ፤
\v 4 ይኸውም ጥበባዊ ሥራዎችን በወርቅ፣ በብርና በነሐስ እንዲሠራ፣
\v 5 ዐይነት የእጅ ሞያ ለማከናወንም ድንጋይ እንዲጠርብና ዕንጨትም እንዲቀርጽ ነው።
\s5
\v 6 ከእርሱም በተጨማሪ የአሂሳሚክን ልጅ ኤልያብን ከዳን ነገድ መርጬዋለሁ። ያዘዝሁህንም ሁሉ እንዲሠሩ የእጅ ሞያ ዐዋቂዎች በሆኑት ልብ ውስጥ ብልኀትን አስቀምጫለሁ።
\v 7 የመገናኛውን ድንኳን፣ የምስክሩን ታቦት፣ በታቦቱ ላይ ያለውን የስርየት መክደኛና የድንኳኑን ዕቃ ሁሉ፦
\v 8 ጠረጴዛውንና ዕቃውን፣ ንጹሑን መቅረዝ ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋር፣ የዕጣኑን መሠዊያ:
\v 9 የሚቃጠለውን መሥዋዕት መሠዊያ ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋርና ትልቁን ሰን ከነመቆሚያው የሚያካትት ይሆናል።
\s5
\v 10 የተሠሩትን ልብሶች፦ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝ ለእኔ የተለዩትን የካህኑን የአሮንንና የልጆቹን የተቀደሱ ልብሶችም ይጨምራል።
\v 11 ዘይቱንና የመቅደሱን ጣፋጭ ዕጣንም ያካትታል። እነዚህ የእሥ ሞያ ዐዋቂዎች እነዚህን ሁሉ እኔ ባዘዝሁህ መሠረት ይሥሯችው።”
\s5
\v 12 ሙሴን እንዲህ አለው፤
\v 13 “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘የእግዚአብሔርን የሰንበት ቀኖች ጠብቁ፤ እናንተን ለራሱ የለያችሁ እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን እንድታውቁ፣ ይህ በእርሱና በእናንተ መካከል በትውልዶቻችሁ ሁሉ ምልክት ነውና።
\v 14 ስለዚህ ለእናንተ የተቀደሰ የእግዚአብሔር ሰንበት ነውና አክብሩት። ሰንበትን የሚያረክስ ሁሉ ይሞታል። በሰንበት የሚሠራም ከወገኑ ተነጥሎ ይጥፋ።
\v 15 ስድስት ቀን ይሠራል፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ክብር የተጠበቀና የተቀደሰ የፍጹም ዕረፍት ሰንበትን ያክብሩ።
\s5
\v 16 በትውልዶቻቸው ሁሉ ቋሚ ሕግ አድረገው ሰንበትን ሊያከብሩት ይገባል።
\v 17 እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐርፎአልና፣ ሰንበት በእግዚአብሔርና በእስራኤላውያን መካከል ሁልጊዜ ምልክት ይሆናል።”
\s5
\v 18 እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ከሙሴ ጋር የሚያደርገውን ንግግር ከጨረሰ በኋላ፣ በገዛ እጁ የጻፈባቸውን የምስክሩን ሁለት የድጋይ ጽላት ለሙሴ ሰጠው።
\s5
\c 32
\p
\v 1 ከተራራው ሳይወርድ እንደ ዘገየ ሕዝቡ ሲመለከቱ፣ በአሮን ዙሪያ ተሰብስበው እንዲህ አሉት፤ “በፊታችን የሚሄድ ጣዖት ሥራልን። ከግብፅ ያወጣን ሙሴ ምን እንዳጋጠምው አናውቅም።”
\v 2 እንዲህ አላቸው፤ “በሚስቶቻችሁ ጆሮዎች፣ በወንድና በሴት ልጆቻችሁ ጆሮዎችም ላይ ያሉ የወርቅ ቀለበቶችን አውልቁና ወደ እኔ እምጧቸው።”
\s5
\v 3 ሁሉም በጆሮዎቻቸው ላይ ያሉ የወርቅ ቀለበቶችን አውልቀው ወደ አሮን አመጧቸው።
\v 4 ወርቁን ከእነርሱ ተቀብሎ በማቅለጥ ቅርጽ ሰጠው፤ የጥጃ ምስልም አደረገው። ሕዝቡም፣ “እስራኤል፣ ይህ ከግብፅ ምድር ያወጣህ አምላክህ ነው” አሉ።
\s5
\v 5 ይህን ባየው ጊዜ፣ በጥጃው ምስል ፊት መሠዊያ ሠራ፤ “ነገ ለእግዚአብሔር ክብር በዐል ይሆናል” ብሎም ዐወጀ።
\v 6 ሕዝቡ በማግስቱ ማልደው በመነሣት የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችንና የኅብረት መሥዋዕቶችን አቀረቡ። ሊበሉና ሊጠጡም ተቀመጡ፤ ለመዝፈንም ተነሡ።
\s5
\v 7 ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ከግብፅ ያወጣሃቸው ሕዝብህ ራሳቸውን በክለዋልና ቶሎ ሂድ።
\v 8 መንገድ ፈጥነው ወጥተዋል። ለራሳቸው የጥጃ ምስል ሠርተው ሰግደውለታል፤ መሥዋዕትም አቅርበውለታል። ‘እስራኤል፣ ከግብፅ ያወጣህ አምላክህ ይህ ነው ብለውም ተናግረዋል።’”
\s5
\v 9 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ይህን ሕዝብ አይቼዋለሁ። ተመልከት፣ ዐንገተ ደንዳናዎች ናቸው።
\v 10 በእነርሱ ላይ እንዲቀጣጠልና እንዳጠፋቸው ተወኝ። ከአንተም ታላቅ ሕዝብ አደርጋለሁ (አንተንም ለታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ) ።”
\v 11 ግን አምላኩ እግዚአብሔር ዝም እንዲልለት ፈለገ፤ እንዲህም አለ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፣ በታላቁ ኀይልና በኀያል እጅ ከግብፅ ባወጣሃው ሕዝብህ ላይ ቊጣህ ለምን ይቀጣጠላል?
\s5
\v 12 ‘እግዚአብሔር በተራሮች ላይ ሊገድላቸውና ከገጸ ምድር ሊያጠፋቸው ዐስቦ ነው ያወጣቸው’ ለምን ይበሉ? ከሚነድደው ቊጣህ ተመለስ፤ በሕዝብህ ላይ ይህን ቊጣ ከማምጣትም ታገሥ።
\v 13 ‘ዘራችሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛዋለሁ፣ የተናገርሁትን ይህንም ምድር ሁሉ ለዘራችሁ እሰጠዋለሁ፤ የዘለዓለም ርስታቸው ይሆናል’ ያልሃቸውንና በራስህ የማልህላቸውን ባሪያዎችህ አብርሃምን፣ ይስሐቅንና እስራኤልን ዐስብ።”
\v 14 ከዚያም እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ አመጣባቸዋለሁ ካለው ቊጣ ታገሠ።
\s5
\v 15 ተመለሰ፤ የምስክሩን ሁለት ጽላት በእጁ ይዞ ከተራራው ወረደ። ጽላቱ በሁለቱም ጎኖቻቸው፣ በፊትም በኋላም ተጽፎባቸው ነበር።
\v 16 የእግዚአብሔር ሥራ ነበር፤ በጽላቱ ላይ የተቀረጸው ጽሕፈትም የእግዚአብሔር ጽሕፈት ነበር።
\s5
\v 17 ላይ የተቀረጸው ጽሕፈትም የእግዚአብሔር ጽሕፈት ነበር። 17 ኢያሱ የሕዝቡን ጫጫታ ሲሰማ፣ ሙሴን፣ “በሰፈር ውስጥ የጦርነት ድምፅ አለ” አለው።
\v 18 ሙሴም “የድል አድራጊ ድምፅ አይደለም፤ ድል የተደረገ ሕዝብ ድምፅም አይደለም፤ የምሰማው የዘፈን ድምፅ ነው” ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 19 ወደ ሰፈሩ ሲቀርብ፣ ጥጃውንና የሚጨፍረውን ሕዝብ አይቶ በጣም ተናደደ። ጽላቱን ከእጁ ወርውሮ በተራራው ግርጌ ሰበራቸው።
\v 20 ሠርተውት የነበረውን ጥጃም ወስዶ አቃጠለው፤ ዱቄት እስከሚሆን ድረስ በመፍጨትም በውሀ ውስጥ በተነው። ከዚያም የእስራኤል ሕዝብ እንዲጠጣው አደረገ።
\s5
\v 21 “እንደዚህ ያለ ታላቅ ኀጢአት ያመጣህበት ይህ ሕዝብ ምን አድርጎህ ነው?” አለው።
\v 22 እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ “ጌታዬ ሆይ ቊጣህ አይንደድ። እነዚህ ሰዎች ለክፋት የተዘጋጁ እንደ ሆኑ ታውቃለህ።
\v 23 እንደዚህ ብለውኛል፤ ‘በፊታችን የሚሄድ አምላክ አብጅልን። ከግብፅ ያወጣን ሰውየ ይህ ሙሴ ምን እንዳጋጠመው አናውቅም።’
\v 24 እኔም፣ ‘ወርቅ ያለው ሰው ሁሉ ያውልቀው’ አልኋቸው። እነርሱም ወርቁን ሰጡኝ። በእሳት ውስጥም ጣልሁትና ይህ ጥጃ ወጣ።”
\s5
\v 25 መዘባበቻ እንዲሆኑ አሮን መረን ስለ ለቀቃቸው፣ ሕዝቡ ከቊጥጥር ውጭ መሆናቸውን ሙሴ አስተዋለ።
\v 26 በሰፈሩ መግቢያ ቆሞ፣ “የእግዚአብሔር የሆነ ሁሉ ወደ እኔ ይምጣ” አለ። ሌዋውያን ሁሉ በሙሴ ዙሪያ ተሰበሰቡ።
\v 27 ሌዋውያኑን እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል፦ ‘እያንዳንዱ ሰይፉን በወገቡ ይታጠቅና በሰፈሩ ሁሉ ከበር እስከ በር ወደ ኋላና ወደ ፊት እየተመላለሰ ወንድሙን፣ ጓደኛውንና ጎረቤቱን ይግደል።’”
\s5
\v 28 ሌዋውያኑ ሙሴ ያዘዘውን ፈጸሙ። በዚያ ቀን ከሕዝቡ ሦስት ሺሕ ያህል ሰዎች ሞቱ።
\v 29 ሌዋውያኑን፣ “ዛሬ ከእናንተ እያንዳንዱ በልጁና በወንድሙ ላይ እርምጃ ስለ ወሰደ፣ ለእግዚአብሔር አገልግሎት ተቀድሳችኋል። ስለዚህም እግዚአብሔር ዛሬ ባርኳችኋል” አላቸው።
\s5
\v 30 በማግስቱም ሙሴ ሕዝቡን፣ “ታላቅ ኀጢአት ሠርታችኋል። አሁን ወደ እግዚአብሔር እወጣለሁ። ምናልባት ለኀጢአታችሁ ማስተሰረያ ማድረግ እችል ይህናል” አላቸው።
\v 31 ሙሴ ወደ እግዚአብሔር ተመልሶ ሄደ፤ እንዲህም አለ፤ “ወዮ! እነዚህ ስዎች ታላቅ ኀጢአት ሠርተዋል፤ ለራሳቸውም ከወርቅ ጣዖት አበጅተዋል።
\v 32 ግን እባክህ ኀጢአታቸውን ይቅር በል፤ ይቅር የማትላቸው ከሆነ ግን ከጻፍኸው መጽሐፍ እኔን ደምስስልኝ።”
\s5
\v 33 ሙሴን እንዲህ አለው፤ እኔን የበደለኝን ሁሉ ከመጽሐፌ እደመስሰዋለሁ።
\v 34 ሂድ፤ ሕዝቡን ወደ ነገርኋችሁ ስፍራ ምራው። እነሆ፣ የእኔ መልአክ በፊትህ ይሄዳል። ሕዝቡን በምቀጣበት ቀን ግን ስለ ኀጢአታቸው እቀጣቸዋለሁ።”
\v 35 አሮን በሠራው ጥጃ ስላደረጉት፣ እግዚአብሔር በሕቡ ላይ መቅሠፍት ላከባቸው።
\s5
\c 33
\p
\v 1 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “አንተና ከግብፅ ያወጣሃው ሕዝብ ከዚህ ሂድ። ‘ለዘርህ እሰጠዋለሁ’ ባልሁ ጊዜ፣ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደማልሁበት ምድር ሂድ።
\v 2 በፊትህ መልአክ እሰድዳለሁ፤ ከነዓናውያንን፣ አሞራውያንን፣ ኬጤያውያንን፣ ፌርዛውያንን፣ ኤዊያውያንና ኢያቡሳውያንንም አስወጣቸዋለሁ።
\v 3 ማርና ወተት ወደምታፈስሰዋ ምድር ሂዱ፤ ነግር ግን እናንተ ግትሮች ስለ ሆናችሁ፣ እኔ ከእናንተ ጋር አልወጣም። በመንገድ ላይ ላጠፋችሁ እችላለሁ።”
\s5
\v 4 እነዚህን አስጨናቂ ቃሎች ሲሰሙ፣ አለቀሱ፤ ምንም ዐይነት ጌጥ ያደረገ ሰውም አልነበረም።
\v 5 ሙሴን እንዲህ ብሎት ነበር፤ “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘እናንተ ግትር ሰዎች ናችሁ። ለአፍታ እንኳ ዐብሬአችሁ ብሄድ፣ አጠፋችኋለሁ። ስለዚህ ምን እንደማደርግባችሁ ለመወሰን ጌጣጌጦቻችሁን አውልቁ።”
\v 6 እስራኤላውያንም ከኮሬብ ተራራ ጀምረው ጌጦቻቸውን አወለቁ።
\s5
\v 7 አንድ ድንኳን ወሰደና በተወሰነ ርቀት ላይ ከሰፈር ውጭ ተከለው። የመገናኛ ድንኳን ብሎ ጠራው። ስለ ማንኛውም ጕዳይ እግዚአብሔርን የሚጠይቅ ሰው ሁሉ ከሰፈሩ ውጭ ወደሚገኘው የመገናኛ ድንኳን ይሄድ ነበር።
\v 8 ወደ ድንኳኑ ሲሄድ፣ ሕዝቡ ሁሉ በየድንኳኑ መግቢያ ላይ ቆሞ ወደ ድንኳኑ ሲገባ ሙሴን ይመለከት ነበር።
\v 9 ወደ ድንኳኑ በሚገባበት ጊዜ ሁሉ፣ የደመና ዐምድ ይወርድና በድንኳኑ መግቢያ ላይ ይቆማል። እግዚአብሔርም ከሙሴ ጋር ይነጋገራል።
\s5
\v 10 ሕዝቡ በድንኳኑ መግቢያ ላይ የደመናውን ዐምድ ቆሞ ሲያዩት፣ እያንዳንዱ ሰው በራሱ ድንኳን መግቢያ ላይ ይነሣና ይሰግዳል።
\v 11 እግዚአብሔር አንድ ሰው ጓደኛውን እንደሚያነጋግር፣ ሙሴን ፊት ለፊት ያነጋግረዋል። ከዚያም በኋላ ሙሴ ወደ ሰፈሩ ይመለሳል፤ አገልጋዩና ወጣት የነበረው የነዌ ልጅ ኢያሱ ግን ከድንኳኑ አይለይም ነበር።
\s5
\v 12 ሙሴ እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “ይህን ሕዝብ ምራው ብለኸኝ ነበር፤ ከእኔ ጋር ማንን እንደምትልክ ግን አላሳወቅኸኝም። ‘በስም ዐውቅሃለሁ፤ በፊቴም ሞገስ አግኝተሃል’ ብለሃል።
\v 13 በፊትህ ሞገስ ካገኘሁ፣ እንዳውቅህና በፊትህ ሞገስን በማግኘት እንድቀጥል መንገዶችህን አሳየኝ። ይህ ሕዝብ የአንተ ሕዝብ እንደ ሆነም አስታውስ።”
\s5
\v 14 እግዚአብሔርም መልሶ፣ “የእኔ ሀልዎት ከአንተ ጋር ዐብቶ ይሄዳል፤ ዕረፍትም እሰጥሃለሁ” አለው።
\v 15 እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “የአንተ ሀልዎት ዐብሮን የማይሄድ ከሆነ፣ ከዚህ አታውጣን።
\v 16 ከእኛ ጋር ካልሄድህ፣ እኔና ሕዝብህ በፊትህ ሞገስ ያገኘን መሆናችን እንዴት ሊታወቅ ይችላል? እኔና ሕዝብህ በምድር ገጽ ካለው ሕዝብ ሁሉ የተለየን የምንሆነው አንተ ከእኛ ጋር ብትሄድ ብቻ አይደለምን?”
\s5
\v 17 ሙሴን፣ “በፊቴ ሞገስን ስላገኘህና በስምም ስለማውቅህ፣ የጠየቅኸውን አድረጋለሁ” አለው።
\v 18 “እባክህ ክብርህን አሳየኝ” አለ።
\s5
\v 19 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ “መልካምነቴ ሁሉ በፊትህ እንዲያልፍ አደርጋለሁ፤ ስሜን እግዚአብሔርንም በፊትህ ዐውጃለሁ። የምምረውን እምረዋለሁ፤ የምራራለትንም እራራለታለሁ።”
\v 20 ነገር ግን እግዚአብሔር፣ ፊቴን ማየትና በሕይወት መኖር የሚችል ሰው ስለሌለ፣ አንተ የእኔን ፊት ማየት አትችልም” ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 21 እንዲህ አለ፤ “እነሆ፣ በእኔ ዘንድ ስፍራ አለ፤ አንተ በዚህ ዐለት ላይ ትቆማለህ።
\v 22 ክብሬ በዚያ ሲያልፍ፣ እኔ እስከማልፍ ድረስ አንተን በዐለቱ ስንጥቅ ውስጥ በእጄ እሸፍንያለሁ።
\v 23 ከዚያም እጁን አነሣውና ጀርባዬን ታያለህ፤ ፊቴ ግን አይታይም።”
\s5
\c 34
\p
\v 1 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ሁለት የድንጋይ ጽላትን እንደ መጀመሪያዎቹ ጽላት አድርገህ ጥረብ። በሰበርሃቸው በመጀመሪያዎቹ ጽላት ላይ ተጽፈው የነበሩ ቃሎችን በእነዚህ ጽላት ላይ እጽፍባቸዋለሁ።
\v 2 ማለዳ ላይ ተዘጋጅተህ ወደ ሲና ተራራ ውጣና በዚያ በተራራው ዐናት ላይ በፊቴ ቁም።
\s5
\v 3 ከአንተ ጋር ማንም ሰው አይምጣ። በተራራው ላይ በየትኛውም ስፍራ ማንም እንዲታይ አታድርግ። የበግና የፍየል መንጋዎች፣ የቀንድ ከብቶችም እንኳ በተራራው ፊት ለፊት ሣር መጋጥ የለባቸውም።”
\v 4 ሁለት የድንጋይ ጽላትን እንድ መጀመሪያዎቹ አድርጎ ጠረበ፤ እግዚአብሔር እንዳዘዘውም በማለዳ ተነሥቶ ወደ ሲና ተራራ ወጣ። ሙሴ ሁለቱን የድንጋይ ጽላት በእጁ ይዞ ነበር።
\s5
\v 5 እግዚአብሔር በደመና ወርዶ ከሙሴ ጋር በእዚያ ቆመ፤ ስሙን እግዚአብሔርንም ዐወጀ።
\v 6 በሙሴ ፊትም እንዲህ እያለ በማወጅ ዐለፈ፤ “እግዚአብሔር፣ ርኅሩኅም ቸርም አምላክ እግዚአብሔር፣ ለቊጣ የዘገየ፣ በጽኑዕ ፍቅርና በታማኝነት ባለ ጸጋ፣
\v 7 ጽኑዕ ፍቅሩን ለሺሕ ትውልድ የሚጠብቅ፣ ክፋትን፣ ዐመፅንና ኀጢአትን ይቅር የሚል፤ በደለኛውን ግን ከቶ ንጹሕ አያደርገውም። ለአባቶች ኀጢአት ልጆቻቸውንና የልጅ ልጆቻቸውን እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ ይቀጣል።”
\s5
\v 8 ሙሴ ወዲያውኑ ወደ መሬት ዝቅ ብሎ ሰገደ።
\v 9 አለ፤ “ጌታዬ ሆይ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ፣ እባክህ ዐብረኸን ሂድ፤ ይህ ሕዝብ ግትር ሕዝብ ቢሆንም፣ ክፋታችንና ኀጢአታችንን ይቅር በለን፤ ርስትህም አድርገህ ውሰደን።”
\s5
\v 10 እንዲህ አለ፤ “እነሆ፣ ኪዳን እገባለሁ። በምድር ሁሉ አየትኛውም ሕዝብ ዘንድ ተደርገው የማያውቁ ድንቆችን በሕዝብህ ሁሉ ፊት አደርጋለሁ። በአንተ ዘንድ የማደርገው የሚያስፈራ ነውና፣ ዐብሮህ ያለው ሕዝብ ሁሉ ሥራዬን ያያል።
\v 11 የማዝዝህን ፈጽም። አሞራውያንን፣ ከነዓናውያንን፣ ኬጤያውያንን፣ ፌርዛውያንን፣ ኢዊያውያንንና ኢያቡሳውያንን በፊትህ አስወጣቸዋለሁ።
\s5
\v 12 አገር ኗሪዎች ጋር ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤ አለዚያ በመካከልህ ወጥመድ ይሆኑብሃል።
\v 13 ሰባብሩ፤ የማምለኪያ ዐምዶቻቸውን አድቅቋቸው፤ የአሼራ ዐፀዶቻቸውንም ቍረጡ።
\v 14 ስሜ ‘ቀናተኛ’ የሆነ እኔ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነኝና ሌላ አምላክ አታምልክ።
\s5
\v 15 ስለዚህም ከምድሪቱ ኗሪዎች ጋር ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤ ምክንያቱም አማልክታቸውን በመከተልያመነዝራሉና፣ መሥዋዕትም ያቀርቡላቸዋልና አንተንም አንዱ ስለሚጋብዝህና ከመሥዋዕቱም ጥቂት ስለምትበላ፣
\v 16 ከዚያም ከሴቶች ልጆቹ የተወሰኑትን ለወንዶች ልጆችህ ትወስዳለህ፤ ሴት ልጆቹም አማልክታቸውን በመከተል ያመነዝራሉ፤ ወንዶች ልጆችህንም ለአማልክታቸው እንዲያመነዝሩ ያደርጓቸዋል።
\v 17 የተሠሩ አማልክትን ለራስህ አታብጅ።
\s5
\v 18 የቂጣ በዓልን አክብር። ባዘዝሁህ መሠረት እርሾ ያልገባበትን ዳቦ በተወሰነው ጊዜ በአቢብ ወር ሰባት ቀን ብላ፤ ከግብፅ የወጣሃው በአቢብ ወር ነበርና።
\s5
\v 19 በኵር ሁሉ፣ የከብትህም እንኳ ተባዕት በኵር በሙሉ፣ የበሬዎችህም የበጎችም በኵር የእኔ ነው።
\v 20 የአህያውን በኵር በጠቦት ዋጀው፤ ካልዋጀኸው ግን ዐንገቱን ስበረው። በኵር ወንድ ልጆችህን ሁሉ ዋጃቸው። ባዶ እጁን በፊቴ የሚቀርብ ማንም እይኑር።
\s5
\v 21 ቀን ሥራ፤ በሰባተኛው ቀን ግን ዕረፍ። በዕርሻና በመከር ጊዜም እንኳ ዕረፍ።
\v 22 ሱባዔ በዓል ከስንዴው በኵራት ጋር፣ የመክተቻውንም በዓል በዓመቱ መጨረሻ አክብር።
\s5
\v 23 በአንተ ዘንድ ያለ ወንድ ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ በእኔ በእስራኤል አምላክ ፊት ይቅረብ።
\v 24 በፊትህ አስወጣቸዋለሁ፤ ወሰንህንም አሰፋዋለሁ። በዓመት ሦስት ጊዜ በእኔ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ለመቅረብ ስትወጣ፣ ምድርህን ለመውረርና ለመቆጣጠር ማንም አይመኝም።
\s5
\v 25 ደም ከእርሾ ጋር አታቅርብ፤ ወይም በፋሲካ በዓል የቀረበው መሥዋዕት ሥጋ እስከ ማለዳ ተርፎ አይቆይ።
\v 26 የዕርሻህ ምርጥ በኵራት ወደ ቤቴ አምጣ። የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።”
\s5
\v 27 እግዚአብሔር ሙሴን፣ “እነዚህን ቃሎች ጻፋቸው፤ በተናገርሏቸው በእነዚህ ቃሎች ክአንተና ከእስራኤል ጋር ኪዳን አድርጌአለሁና አለው።
\v 28 አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከእግዚአብሔር ጋር እዚያው ነበረ። ምግብም አልበላም፤ ውሃም አልጠጣም።
\s5
\v 29 ሁለቱን የምስክሩን ጽላት በእጁ ይዞ ከሲና ተራራ ወረደ። ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገረ ሳለ፣ ፊቱ የሚያበራ ምሆኑን አላወቀም።
\v 30 እስራኤላውያን ሙሴን ሲያዩት፣ ፊቱ ይበራ ነበር፤ ስለዚህም ወደ እርሱ ለመጠጋት ፈሩ።
\v 31 ግን ጠራቸው፤ አሮንና የሕዝቡ መሪዎችም ወደ እርሱ መቱ፣ ሙሴም ከእነርሱ ጋር ተነጋገረ።
\s5
\v 32 ከዚያ በኋላም፣ የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ሙሴ መጡ፤ እርሱም በሲና ተራራ ላይ እግዚአብሔር ሰጥቶት የነበረውን ትእዛዝ ሁሉ ነገራቸው።
\v 33 ንግግሩን ከጨረሰ በኋላ፣ በፊቱ ላይ መሸፈኛ አደረገ።
\s5
\v 34 ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር በፊቱ በሚቀርብበት ጊዜ ሁሉ፣ እስከሚወጣበት ጊዜ ድረስ መሸፈኛውን ያወልቀው ነበር። ሲወጣ ምን እንዲል እንደታዘዘ ለእስራኤላይዋን ይነግራቸዋል።
\v 35 እስራኤላውያን የሚያበራውን ፊቱን ሲያዩ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር ተመልሶ እስኪሄድ ድረስ መሸፈኛውን እንደ ገና በፊቱ ላይ ያደርገዋል።
\s5
\c 35
\p
\v 1 የእስራኤልን ማኅበረ ሰብ ሁሉ ሰብስቦ እንዲህ አላቸው፤ “እንድትፈጽሟቸው እግዚአብሔር የሰጣችሁ ትእዛዝት እነዚህ ናቸው።
\v 2 ስድስት ቀን ሥራ ትሠራላችሁ፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የፍጹም ዕረፍት የሰንበት ቀን ይሁንላችሁ። በዚያ ቀን ሥራ የሚሥዐራ ሁሉ ይሞታል።
\v 3 በሰንበት ቀን በማንኛችሁም ቤት ውስጥ እሳት አይንደድ።”
\s5
\v 4 ሁሉን የእስራኤል ማኅበረ ሰብ እንዲህ አላቸው፤ “እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው።
\v 5 ከልብ ፈቃደኛ የሆናችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቅርቡ። ሁሉም ለእግዚአብሔር የወርቅ፣ የብር፣ የነሐስ መባያምጣ፤
\v 6 ሐምራዊና ቀይ ማግ፣ ቀጭን በፍታ፣ የፍየል ጠጒር፣
\v 7 በቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳና የአቆስጣ ቆዳ፣ የግራር ዕንጨት፣
\v 8 መብራቶች ዘይት፣ ለመቅቢያ ዘይቱ ቅመምና ጣፋጭ መዐዛ ያለው ዕጣን፣
\v 9 መረግዶችና ለኤፉዱና ለደረት ኪሱ የሚሆኑ ሌሎች ዕንጨቶችንም መባ አድርጎ ያቅርብ።
\s5
\v 10 በመካከላችሁ ያሉ ብልኀተኛ ሰዎች ሁሉ ይምጡና እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ይሥሩ፦
\v 11 ከድንኳኑ ጋር፣ መደሪያውን፣ ማያያዣዎቹን፣ ክፈፎቹን፣ አግዳሚዎቹን፣ ቋሚዎቹንና መሠረቶቹን፤
\v 12 ታቦቱንም ከነመሎጊያዎቹ፣ የስርየት መክደኛውንና የሚሸፍነውን መጋረጃ፤
\s5
\v 13 ከመሎጊያዎቹ ጋር፣ ዕቃዎቹንም ሁሉን ኣየገጽ ኅብስቱን፤
\v 14 የመብራቶቹን መቅረዝ ከዐባሪ ዕቃዎቹ ጋር፣ መብራቶቹንና የመብራቶቹን ዘይት፤
\v 15 የዕጣኑን መሠዊያ ከመሎጊያዎቹ ጋር፣ መቅቢያ ዘይቱንና ጣፋጭ መዓዛ ያለውን ዕጣን፣ የመገናኛ ድንኳኑን መግቢያ መጋረጃ፣
\v 16 የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን መሠዊያ ከነሐስ መጫሪያው፣ ከመሎጊያዎቹና ከዕቃዎቹ ጋር፤ ትልቁን የመታጠቢያ ሰን እስከ ማስቀመጫው፤
\s5
\v 17 የአድደባባዩን መጋረጃዎች ከምሰሶዎቹና ከመሠረቶቹ ጋር፣ የአደባባዩን መግቢይ ኣመጋረጃ፤
\v 18 የማደሪያውን ድንኳን ካስማዎች ከነገመዶቻቸው፤
\v 19 ውስጥ ለማገልገል በብልኀት የተሠሩ ልብሶችን፣ ካህናት ሆነው ለማገልገል ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹ የሚሆኑ የተቀደሱ ልብሶችን ያምጡ።”
\s5
\v 20 ከዚያም ሁሉም የእስራኤል ነገዶች ሁሉ ከሙሴ ፊት ወጥተው ሄዱ።
\v 21 ልቡ የተነሣሣና ፈቃደኛ የሆነ ሁሉ በመምጣት ለመገናኛው ድንኳን ሥራ፣ ለውስጡም ለሚደረገው አገልግሎትና ለተቀደሱ ልብሶች የሚሆን ስጦታን ሰጡ።
\v 22 ፈቃደኛ የነበሩ ወንዶችም ሴቶችም መጥተው የአፍንጫ ጌጦችን፣ የጆሮ ጌጦችን፣ ቀለበቶችን፣ ድሪዎችንና ሁሉንም ዓይነት የወርቅ ጌጣጌጦች አመጡ።
\s5
\v 23 ሐምራዊ፣ ቀይም ቀይ ማግ፣ ያማረ በፍታ፣ የፍየል ጠጕር፣ በቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፣ ወይም የአስቆጣ ቆዳ የነበራቸውም አመጡ።
\v 24 ለማንኛውም ተግባር የሚጠቅም የግራር ዕንጨት የነራቸው፣ የብርና የነሐስ ስጦታ ማድረግ የሚፈልጉ ሁሉ በስጦታነት ለእግዚአብሔር አቀረቡ።
\s5
\v 25 ብልኀተኛ ሴቶችም ሁሉ ማግ ፈትለው፣ የፈተሉትን ሰማያዊ፣ ሕዐምራዊ፣ ወይም ቀይ ማግ አመጡ።
\v 26 ያነሣሣቸውና ብልኀተኛ የሆኑ ሴቶች ሁሉ የፍየል ጠጕር ፈተሉ።
\s5
\v 27 ለአፉዱና ለደረት ኪሱ የሚሆኑ መረግዶችንና ሌሎች ዕንቆችን አመጡ፤
\v 28 ለመቅቢያው ዘይትና ጣፋጭ መዐዛ ላለው ዕጣን ዘይትና ቅመምም አመጡ።
\v 29 የነጻ ፈቃድ ስጦታ ለእግዚአብሔር በሙሴ በኩል እንዲፈጸም አዝዞት ለነበረው ሥራ ሁሉ ቍሳቍሶችን አመጡ።
\s5
\v 30 እስራኤላውያንን እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፣ እግዚአብሔር የሖር የልጅ ልጅ የሆነውን የኡሪን ልጅ ባስልኤልን ከይሁዳ ነገድ በስም ጠርቶታል።
\v 31 ለሁሉም ዐይነት የጥበብ ሥራ ጥበብን፣ ማስተዋልንና ዕውቀትን ሊሰጠው ባስልኤልን በመንፈሱ ሞልቶታል፤
\v 32 የወርቅ፣ የብርና የነሐስ ጥበባዊ ሥራዎችን ለመሥራት፣
\v 33 የጥበባዊ ሥራ ዐይነቶችን ሁሉ ለመሥራት ድንጋዮችን እንዲጠርብና ዕንጨትም እንዲቀርጽ ነው።
\s5
\v 34 እግዚአብሔር በባስልኤልና ከዳን ነገድ በሆነው በአሂሳሚክ ልጅ በኤልያብ ልብ ይህን ችሎታ አስቀመጠ።
\v 35 ጥበበኛ ሰዎች፣ እንደ ቀራጺዎች፣ በሰማያዊ፣ በሐምራዊና በቀይ ማግ፣ ባማረ በፍታም እንደ ጥልፍ ጠላፊዎችና እንደ ሸመና ሠራተኞች እንዲሠሩም ብልኀትን ሞላባቸው። እነርሱ በሥራ ዐይነቶች ሁሉ ጥበበኞች የሆኑ የጥበብ ባለሙያዎች ናቸው።
\s5
\c 36
\p
\v 1 ስለዚህ ባስልኤልና ኤልያብ፣ የልብ ጥበበኞች የነበሩና እንዲፈጽሙት እግዚአብሔር ያዘዘውን በመከተል መቅደሱ እንዴት እንደሚሠራ ለማወቅ ብልኀትንና ማስተዋልን ያስቀመጠባቸውም ሁሉ ይሠራሉ።
\s5
\v 2 ባስልኤልንና ኤልያብን፣ እግዚአብሔር በልቡ ብልኀትን አስቀምጦበት የነበረ ጥበበኛ ስውን ሁሉ፣ መጥቶ ሥራውን ለመሥራት ልቡ ያነሣሣውንም ጠራ።
\v 3 የጠራቸውም ለመቅደሱ ሥራ እስራኤላውያን አምጥተውት የነበረውን ስጦታ ሁሉ ከሙሴ ተቀበሉ። ሕዝቡ የነጻ ፈቃድ ስጦታዎችን ጠዋት ጠዋት ወደ ሙሴ ማምጣት አላቋረጡም ነበር።
\v 4 ስለዚህ በመቅደሱ ሥራ ላይ የተሰማሩ ብልኀተኛ ሰዎች ሁሉ ከሚሠሩት ሥራ ተነሥተው መጡ።
\s5
\v 5 ሙሴን፣ “እግዚአብሔር እንድንሠራው ላዘዘን ሥራ ከሚበቃው በጣም የሚበልጥ ሕዝቡ እያመጡ ነው” አሉት።
\v 6 ሙሴም በሰፈሩ ውስጥ ያለ ማንም ሰው ለመቅደሱ ሥራ ሌላ ስጦታ እንዳያመጣ ትእዛዝ ሰጠ። ከዚያም በኋላ ሕዝቡ ስጦታ ማምጣቱን አቆሙ።
\v 7 ለሥራው ሁሉ ከሚበቃው በላይ ቍሳቍሶች ነበሯቸው።
\s5
\v 8 ያሉ ጥበበኞችም ሁሉ ከአማረ በፍታና ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግም ከተሠሩትና ኪሩቤልም ከተጠለፉባቸው ዕሥር መጋረጃዎች ጋር የመገናኛውን ድንኳን ሠሩት። ይህም እጅግ ጥበበኛ የነበረው የባስልኤል ሥራ ነው።
\v 9 መጋረጃ እርዝመት ሃያ ስምንት ክንድ፣ ወርዱም አራት ክንድ ነበረ። ሁሉም መጋረጃዎች እኩል መጠን ነበራቸው።
\v 10 ባስልኤል ዐምስት ዐምስቱን መጋረጃዎች በአንድ ላይ አድርጎ እርስ በርስ አገጣጠማቸው።
\s5
\v 11 መጋረጃዎች የመጨረሻ የውጭ ጠርዝ ላይና በሁለተኛውም ተገጣጣሚ መጋረጃ የመጨረሻ የውጭ ጠርዝ ላይ ሰማያዊ ቀለበቶችን አደረገ።
\v 12 በሁለተኛው መጋረጃ ጠርዞች ዐምሳ ዐምሳ ቀለበቶችን አበጀ። ስለሆነም ቀለበቶቹ እርስ በርስ ትይዩ ሆነው የተደረጉ ነበር።
\v 13 ባስልኤል ዐምሳ የወርቅ ማያያዣዎችን ሠርቶ የመገናኛው ድንኳን ወጥ እንዲሆን መጋረጃዎቹን አያያዛቸው።
\s5
\v 14 ባስልኤል በማደሪያው ላይ ላለው ድንኳን ዐሥራ አንድ የፍየል ጠጕር መጋረጃዎችን ሠራ።
\v 15 የእያንዳንዱ መጋረጃ እርዝመት ሠላሳ ክንድ፣ ወርዱም አራት ክንድ ነበረ። ዐሥራ አንድ መጋረጃዎች እያንዳንዳቸው እኩል መጠን ነበራቸው።
\v 16 መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው፣ ስድስቱንም መጋረጃዎች እንደዚሁ እርስ በርሳቸው አያያዛቸው።
\v 17 ተገጣጣሚ መጋረጃዎች የመጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይ ዐምሳ ቀለበቶችን በሁለተኛዎቹ ተገጣጣሚ መጋረጃዎች የመጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይም እንደዚሁ ዐምሳ ቀለበቶችን አበጀ።
\s5
\v 18 ባስልኤል ወጥ እንዲሆን ድንኳኑን ለማገጣጠም ዐምሳ የነሐስ ማያያዣዎችን ሠራ።
\v 19 ለድንኳኑ መሸፈኛ በቀይ ቅለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፣ ከበላዩም የሚህን የአቆስጣ ቆዳ ሠራ።
\s5
\v 20 ባስልኤል ከግራር ዕንጨት ወጋግራዎችን ለመገናኛው ድንኳን ሠራ።
\v 21 ወጋግራ እርዝመት ዐሥር ክንድ፣ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ነበር።
\v 22 እርስ በርስ ለማያያዝ በያንዳንዱ ወጋግራ ሁለት ማያያዣዎች ነበር። የመገናኛውን ድንኳን ወጋግራዎች ሁሉ በዚህ መንገድ ሠራ።
\v 23 ባስልኤል በዚህ መንገድ ወጋግራዎችን ለመገናኛው ድንኳን ሠራ። ለደቡቡ ጎንም ሃያ ወጋግራዎችን አበጀ።
\s5
\v 24 ባስልኤል ከሃያዎቹ ወጋግራዎች ሥር የሚሆኑ አራ የብር መቆሚያዎችን አበጀ። ማያያዣዎች ለመሆን ከመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች ከያንዳንዱ ሌላ ወጋግራ በታችም እንደዚሁ ሁለት መቆሚያዎች ነበሩ።
\v 25 ጎን ላለው ለመገናኛው ድንኳን ሁለተኛ ጎን ሃያ ወጋግራዎችንና
\v 26 የብር መቆሚያዎቻቸውን አበጀ። በመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች፣ በሚቀጥለው ወጋግራ ሥርም እንዲሁ ሁለት ሁለት መቆሚያ አበጅቶአል።
\s5
\v 27 በስተ ምዕራብ ላለው ለመገናኛው ድንኳን ጀርባ ባስልኤል ስድስት ወጋግራዎችን ሠራ።
\v 28 ድንኳን የኋላ ማእዘኖች ሁለት ወጋግራዎችን አበጀ።
\s5
\v 29 እነዚህ ወጋግራዎች ከታች የተነጣጠሉ፣ ከላይ ደግሞ በአንድ ቀለበት የየያያዙ ነበር። ለሁለቱም የኋላ ማእዘኖች የተደረገው በዚህ መንገድ ነበር።
\v 30 ከብር መቆሚያዎቻቸው ጋር ስምንት ወጋግራዎች ነበሩ። በመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች፣ በሚቀጥለውም ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች ለያንዳንዱ ወጋግራ ሁለት ሁለት በመሆን ዐሥራ ስድስት መቆሚያዎች ነበሩ።
\s5
\v 31 ባስልኤል የግራር ዕንጨት አግዳሚዎችን አበጀ፦ ለመገናኛው ድንኳን አንድ ጎን ወጋግራዎች ዐምስት፣ አግዳሚዎችን፣
\v 32 የመገናኛው ድንኳን ጎን ወጋግራዎች አምስት አግዳሚዎችን፣ በምዕራብ በኩል ላለው ለመገናኛው ድንኳን የኋላ ጎን ወጋግራዎችም ዐምስት አግዳሚዎችን ሠራ።
\v 33 አግዳሚዎቹን የሥራቸውም በወጋግራዎች መካከል ላይ ከዳር እስከ ዳር እንዲደርሱ አድርጎ ነው።
\v 34 ወጋግራዎቹን በወርቅ ለበጣቸው። አግዳሚዎችን ለማያያዝ የወርቅ ቀለበቶችን ሠራ፣ አግዳሚዎችንም በወርቅ ለበጣቸው።
\s5
\v 35 በብልኀተኛ ሠራተኛ ሥራ ኪሩቤል የተጠለፉበትን መጋረጃ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ፣ ካማረ በፍታም ሠራው።
\v 36 አራት የግራር ዕንጨት ምሰሶዎችን አበጅቶ በውርቅ ለበጣቸው። ለምሰሶዎችም የወርቅ ኵላቦችን ሠርቶ አራት የብር መቆሚያዎችን አደረገላቸው።
\s5
\v 37 ለድንኳኑ መግቢያ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ፣ ካማረ በፍታም በጥልፍ ጠላፊ ሥራ የተዘጋጀ መጋረጃ አበጀለት።
\v 38 የመጋረጃውን ዐምስት ምሰሶዎች ከኵላቦች ጋር ሠራ። የምሰሶዎችን ዐናትና ዘንግ በወርቅ ለበጣቸው። ዐምስት መቆሚያዎቻቸውም ከነሐስ የተሰሩ ነበሩ።
\s5
\c 37
\p
\v 1 ባስልኤል እርዝመቱ ሁለት ተኩል ክንድ፣ ወርዱ አንድ ተኩል ክንድ፣ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ታቦታ ከግራር ዕንጨት ሠራ።
\v 2 ውስጡንና ውጩንም በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አበጀለት።
\v 3 ለአራት እግሮቹም አራት የወርቅ ቀለበቶችን፣ በአንዱ ጎኑ ላይ ሁለት ቀለበቶችን፣ በሌላውም ጎኑ ላይ ሁለት ቀለበቶችን ጨምሮ ሠራ።
\s5
\v 4 ዕንጨት መሎጊያዎችን ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው።
\v 5 ታቦቱን ለመሸከም በታቦቱ ጎኖች ላይ ባሉት ቀለበቶች ውስጥ መሎጊያዎቹን አስገባቸው።
\v 6 ሁለት ተኩል ክንድ፣ ወርዱም አንድ ተኩል ክንድ የሆነ የስርየት መክደኛ ከንጹሕ ወርቅ ሠራ።
\s5
\v 7 ባስልኤል ለስርየት መክደኛው ሁለት ጫፎች ሁለት ኪሩቤልን ከተቀጠቀጠ ወርቅ አበጀ።
\v 8 አንዱ ኪሩብ ለአንዱ የስርየት መክደኛ፣ ሌላውም ለሌላው የስርየት መክደኛ ጫፍ ነበረ። ኪሩቤል ከስርየት መክደኛው ጋር ወጥ ሆነው ተበጅተው ነበር።
\v 9 ኪሩቤል ክንፎቻቸውን ወደ ላይ በመዘርጋት የስርየት መክደኛውን በድንፎቻቸው ጋረዱት። እርስ በርስ ትይዩ ሆነውም ወደ ስርየት መክደኛው መካከል ይመለከቱ ነበር።
\s5
\v 10 ባስልኤል እርዝመቱ ሁለት ክንድ፣ ቁመቱም አንድ ተኩል ክንድ የሆነ ጠረጴዛ ከግራር ዕንጨት ሠራ።
\v 11 ወርቅ ለበጠው፤ ዙሪያውንም በንጹሕ ወርቅ ከፈፈው።
\v 12 አንድ ስንዝር ጠርዝ ከወርቅ ክፈፍ ጋር አበጀለት።
\v 13 የወርቅ ቀለበቶችንም ሠርቶ የጠረጴዛው እግሮች ካሉበት ማእዘኖች ጋር አያያዛቸው።
\s5
\v 14 ለመሸከም መሎጊያዎችን ማስገባት እንዲቻል ቀለበቶቹ ከጠርዙ ጋር ተያይዘው ነበር።
\v 15 ጠረጴዛውን መሸከም እንዲቻል መሎጊያዎቹን ከግራር ዕንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው።
\v 16 በጠረጴዛው ላይ የሚቀመጡ ዕቃዎችን፦ ድስቶችን፣ ዝርግና ጎድጓዳ ሳሕኖችን ጭልፋዎችን፣ ወጭቶችንና የመጠጥ መሥዋዕቱን ማፍሰሻ ማንቆርቆሪያዎች ከንጹሕ ወርቅ ሠራ።
\s5
\v 17 ከነማቆሚያውና ከነዘንጉ ከተቀጠቀጠ ንጹሕ ወርቅ ሠራ። ጽዋዎቹ፣ ቀንበጦቹና አበባዎቹ በሙሉ ከመቅረዙ ጋር ወጥ ሆነው ነበር የተሠሩት።
\v 18 ቅርንጫፎች በመቅረዙ አንድ ጎን፣ ሦስት ቅርንጫፎች ደግሞ በሌላው የመቅረዙ ጎን ተሠርተው ስድስት ቅርንጫፎች ነበር።
\v 19 ቅርንጫፍ ከቀንበጥና ክአበባ ጋር የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች ነበሩት፤ በሌላውም ቅርንጫፍ እንደዚሁ የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች ከቀንበጥና ከአበባ ጋር ነበር። ከመቅረዙ ለሚወጡ ስድስት ቅርንጫፎች ሁሉ የተደረገው አንድ ዐይነት ነበር።
\s5
\v 20 በመቅረዙ መካከል ላይ ባለው ዘንግ ላይ የለውዝ አበቦችን የሚመስሉ እራት ጽዋዎች ከቀንበጦቻቸውና ከአበቦቻቸው ጋር ተሠርተዋል።
\v 21 በመጀመሪያ የቅርንጫፎች ጥንድ ሥር ወጥ ሆኖ ዐብሮት የተሠሩ ቀንበጦች ነበር። ከመቅረዙ በሚወጡ ስድስት ቅርንጫፎች ሁሉ የተደረገው አንድ ዐይነት ነበር።
\v 22 ቅርንጫፎቻቸው ከመቅረዙ ጋር ወጥ ሆነው ከተቀጠቀጠ ንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበር።
\s5
\v 23 መቅረዙንና ሰባቱን መብራቶች፣ መኮስተሪያዎቹንና የኵስታሪ ማስቀመጫዎቻቸውን ከንጹሕ ወርቅ ሠራ።
\v 24 መቅረዙንና ዐባሪ ዕቃዎቹን ከአንድ መክሊት ንጹሕ ወርቅ ሠራቸው።
\s5
\v 25 እርዝመቱ አንድ ክንድ፣ ወርዱም አንድ ክንድ የሆነውን የዕጣኑን መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሠራ። አራት ማእዘንና ቁመቱም ሁለት ክንድ ነበር። ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበር።
\v 26 የዕጣኑን መሠዊያ፦ ዐናቱን፣ ጎኖቹንና ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ለበጣቸው። ለዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አበጀለት።
\s5
\v 27 በሁለቱ ተነጻጻሪ ጎኖቹ ላይ ከክፈፉ ሥር እንዲያያይዙት ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠራ። ቀለበቶቹ መሠዊያውን ለመሸከም መሎጊያዎችን ለመያዝ የሚያገለግሉ ናቸው።
\v 28 ከግራር ዕንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው።
\v 29 የተቀሰውን የመቅቢያ ዘይትና የሽቶ ቀማሚ ሥራ የሆነውን፣ ንጹሕና ጣፋጭ መዐዛ ያለውን ዕጣን ሠራ።
\s5
\c 38
\p
\v 1 የሚቃጠለውን መሥዋዕት መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሠራ። ዐምስት ክንድ እርዝመትና ዐምስት ክንድ ስፋት፣ አራት ማእዘንና ሦስት ክንድ ቁመት ነበረው።
\v 2 ማእዘኖችም የበሬ ቀንዶችን የሚመስሉ ቅርጾችን በመሥራት አስረዘማቸው። ቀንዶቹ ከመሠዊያው ጋር ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ፤ መሠዊያውንም በነሐስ ለበጠው።
\v 3 ለመሠዊያው የሚያስፈልገውን ዕቃ ሁሉ፦ ለዐመድ ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችን፣ ጎድጓዳ ሳሕኖችን፣ ሜንጦዎችንና ማንደጃዎችን በሙሉ ከነሐስ ሠራ።
\s5
\v 4 ከደረጃው ሥር ከመሠዊያው እኩሌታ እስከ ታች የሚደርስ እንደ መረብ የተሠራ የነሐስ ፍርግርግ ለመሠዊያው አበጀ።
\v 5 ፍርግርግ አራት ማእዘኖች ለመሎጊያዎቹ መያዣ አራት ቀለበቶችን ሠራላቸው።
\s5
\v 6 ዕንጨት መሎጊያዎችን ሠርቶ በነሐስ ለበጣቸው።
\v 7 መሎጊያዎቹን መሠዊያውን ለመሸከም በመሠዊያው ጎኖች ላይ ባሉት ቀለበቶች ውስጥ አስገባቸው። መሠዊያውን ክፍት አድርጎ በሳንቃዎች ሠራው።
\s5
\v 8 ባስልኤል ትልቁን የመታጠቢያ ሳሕን ከነሐስ መቆሚያ ጋር ሠራ። ሳሕኑን የሠራውም በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ የሚያገለግሉት ሴቶች ይጠቀሙባቸው ከነበሩ መስተዋቶች ነው።
\s5
\v 9 ሠራው። በአደባባዩ ደቡብ ጎን ላይ የነበሩት መጋረጃዎች ከአማረ በፍታ የተሠሩና አንድ መቶ ክንድ እርዝመት ያላቸው ነበሩ።
\v 10 መጋረጃዎቹ ሃያ ምሰሶዎችና ሃያ መቆሚያዎች ነበሯቸው። ከምሰሶዎቹና ከብር ዘንጎቹ ጋር የተያያዙ ኵላቦችም ነበሩ።
\s5
\v 11 ጎን በኩልም እንደዚሁ አንድ መቶ ክንድ እርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ከሃያ ምሰሶዎችና ከሃያ የነሐስ መቆሚያዎች፣ ከምሰሶዎቹ ጋር ከተያያዙ ኲላቦችና ከብር ዘንጎች ጋር ነበር።
\v 12 የምዕራቡ ጎን መጋረጃዎች ዐምሳ ክንድ የሚረዝሙ፣ ዐሥር ምሰስዎችና መቆሚያዎች ያሏቸው ነበሩ። የምሰሶዎቹ ኵላቦችና ዘንጎች ብር ነበሩ።
\s5
\v 13 አደባባዩም በምሥራቁ ጎን ላይ ዐምሳ ክንድ ይረዝም ነበር።
\v 14 የመግቢያው አንድ ጎን መጋረጃዎች እርዝመት ዐሥራ ዐምስት ክንድ ነበረ። ሦስት ምሰሶዎች ከሦስት መቆሚያዎች ጋር ነበሯቸው።
\v 15 በአደባባዩ መግቢያ ሌላ ጎን ላይም ዐሥራ ዐምስት ክንድ የሚረዝሙና ሦስት ምሰሶዎችና ሦስት መቆሚያዎች ያሏቸው መጋረጃዎች ነበሩ።
\v 16 በአደባባዩ ዙሪያ ያሉት መጋረጃዎች ሁሉ አምሮ ከተፈተለ በፍታ የተሠሩ ነበሩ።
\s5
\v 17 የምሰሶዎቹ መቆሚያዎች ከነሐስ፣ የምሰሶዎቹ ኵላቦችና ዘንጎቻቸው፣ የዐናታቸውም መሸፈኛ ከብር የተሠሩ ነበሩ። የአደባባዩ ምሰሶዎች ሁሉ በብር የተለበጡ ነበር።
\v 18 የአደባባዩ በር መጋረጃቅ እርዝመት ሃያ ክንድ ነበረ። ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ የተሠራ ነበረ። እንደ አደባባዩ መጋረጃዎች ሃያ ክንድ እርዝመትና ዐምስት ክንድ ቁመት ነበረው።
\v 19 የነሐስ መቆሚያዎችና የብር ኵላቦች ነበሩት። የዐናታቸው መሸፈኛና ዘንጎቹ ከብር የተሠሩ ነበሩ።
\v 20 የመገናኛው ድንኳን ካስማዎች ሁሉ የተሠሩት ከነሐስ ነበር።
\s5
\v 21 የሙሴን ትእዛዝ በመከተል በተመዘገበው መሠረት የመገናኛው ድንኳን፣ ይኸውም የምስክሩ ድንኳኝ ቆጠራ ይህ ነው። በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታማር መሪነት ይህ የሌዋውያኑ ሥራ ነበረ።
\v 22 ከይሁዳ ነገድ የሆነው፣ የሖር የልጅ ልጅ፣ የኡሪ ልጅ ባስልኤል እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ትእዛዝ ሁሉ ፈጸመ።
\v 23 ከባስልኤልም ጋር ከዳን ነገድ የሆነው የአሂሳሚክ ልጅ ኤልያብ ቅርጽ አውጪ ሠራተኛ፣ የእጅ ጥበብ ሙያተኛ፣ በሰማያዊ፣ በሐምራዊ፣ በቀይ ግምጃና በአማረ በፍታ ጥልፍ ጠላፊም ሆኖ ዐብሮት ሠራ።
\s5
\v 24 ከመቅደሱ ሥራ ጋር ለተያያዘው ተግባር ሁሉ ጥቅም ላይ የዋለው ወርቅ ማለትም፣ ከስጦታው የተገኘው ወርቅ ሁሉ በመቅደሱ ሰቅል መጠን መሠረት ሃያ ዘጠኝ መክሊትና ሰባት መቶ ሠላሳ ሰቅል ነበረ።
\v 25 ማኅበረ ሰቡ የሰጠው ብር በመቅደሱ ሰቅል መጠን ተመዝኖ አንድ መቶ መክሊትና አንድ ሺሕ ሰባት መቶ ሰባ ዐምስት ሰቅል፣
\v 26 በአንድ ሰው አንድ ቤካ ይኸውም በመቅደሱ ሰቅል መጠን ግማሽ ሰቅል ነበረ። ይህ ቍጥር የተደረሰበት በሕዝብ ቆጠራው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆናቸው ተቆጥረው በተገኘው ስድስት መቶ ሦስት ሺሕ ዐምስት መቶ ዐምሳ ወንዶች ቍጥር በያንዳንዱ ሰው ተሰልቶ ነው።
\s5
\v 27 የመቅደሱንና የመጋረጃዎችን መቆሚያዎች ለመሥራት አንድ መቶ የብር መክሊት ወጪ ሆኖአል፦ መቆሚያዎቹ በጠቅላላ አንድ መቶ ሆነው፣ ለያንዳንዱ መቆሚያ አንድ መክሊት ተከፍሎአል ማለት ነው።
\v 28 በቀሩት አንድ ሺሕ ሰባቶ መቶ ሰባ ዐምስት የብር ሰቅሎች ባስልኤል የምሰሶዎቹን ኵላቦች ሠርቶ ዐናታቸውን ሸፈነባቸው፤ ዘንጎችንም ለምሰሶዎቹ ሠራባቸው።
\v 29 ከስጦታ የተገኘው ነሐስ ተመዝኖ ሰባ ታለንትና ሁለት ሺሕ አራት መቶ ሰቅል ሆነ።
\s5
\v 30 በዚህም የመገናኛውን ድንኳን መግቢያ መቆሚያዎች፣ የነሐስ መሠዊያውን፣ የእርሱንም የነሐስ ፍርግርግ፣ የመሠዊያውን ዕቃ ሁሉ፣
\v 31 የአደባባዩን መቆሚያዎች፣ የአደባባዩን መግቢያ መቆሚያዎች፣ የመገናኛውን ድንኳንና የአደባባዩን ድንኳን ካስሞች ሁሉ ሠራበት።
\s5
\c 39
\p
\v 1 በመቅደሱ ውስጥ ለሚከናወነው አገልግሎት ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ የተሠሩ ልብሶችን አበጁ። እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለቤተ መቅደሱ የሚሆኑ የአሮንን ልብሶች ሠሩ።
\s5
\v 2 ኤፉዱን ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ ሠራ።
\v 3 ሠራተኛ እንደሚሠራው፣ በሰማያዊ፣ በሐምራዊ፣ በቀይ ማግና በአማረ በፍታ ለመ|ሥራት ወርቁን ቀጥቅጠው ወደ ሽቦነት ቆራረጡት።
\s5
\v 4 የትከሻ ንጣዮችን ሠርተው ከላይኛዎቹ ጠርዞቹ ጋር አያያዙት።
\v 5 በብልኀት የተጠለፈው የወገብ መታጠቂያም እንደ ኤፉዱ ሲሆን፣ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው፣ አምሮ ከተፈተለ በፍታ ይኸውም ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ ከኤፉድ ጋር ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበረ።
\s5
\v 6 የመረግድ ድንጋዮችን በወርቅ ፈርጥ ክፈፍ አበጁላቸው፤ እንደ ማኅተምም የዐሥራ ሁለቱን የእስራኤል ልጆች ስሞች ቀረጹባቸው።
\v 7 እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት፣ ባስልኤል በሴፉዱ የትከሻ ንጣዮች ላይ ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ልጆች የመታሰቢያ ድንጋዮች አድርጎ አስቀመጣቸው።
\s5
\v 8 ኪሱንም ብልኅ ሠራተኛ እንደሚሠራው፣ እንደ ኤፉዱ አበጀው። ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከአማረ በፍታ ሠራው።
\v 9 ኪሱ አራት ማእዘን ነበረ። ርዝመቱም ወርዱም አንድ ስንዝር ሆኖ የተደረበ ዕጥፍ ነበረ።
\s5
\v 10 በውስጡም አራት የዕንቍ ድንጋዮች ፈድፎች አበጅተዋል። በመጀመሪያው ረድፍ ሰርድዮን፣ ቶጳዝዮንና አብራቅራቂ ዕንቍ ነበሩት።
\v 11 ረድፍ በሉር፣ ሰንፔር፣ አልማዝ፤
\v 12 በሦስተኛው ረድፍ ያክንት፣ ኬልቄዶን፣ አሜቴስጢኖስ፤
\v 13 በአራተኛውም ረድፍ ቢረሌ፣ መረግድና ኢያስጲድ ነበሩ። ድንጋዮቹ በወርቅ ፈርጥ ዙሪያቸውን የተከፈፉ ነበር።
\s5
\v 14 እያንዳንዳቸው በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ልጆች ስሞች ቅደም ተከተል መሠረት የተቀመጡ ነበር። እያንዳንዱ ስም ከዐሥራ ሁለቱ ነገዶች አንዱን በመወከል በማተሚያ ቀለበት ላይ እንደሚቀረጽ የተቀረጸባቸው ነበሩ።
\v 15 ኪሱ ላይ ከንጹሕ ወርቅ እንደ ገመድ የተጎነጎኑ ድሪዎችን አበጁ።
\v 16 ሁለት የወርቅ ፈርጦችንና ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው ሁለቱን ቀለበቶች ከደረት ኪሱ ሁለት ጠርዞች ጋር አያያዟቸው።
\s5
\v 17 ሁለቱን የተጎነጎኑ የወርቅ ድሪዎች በደረት ኪሱ ጠርዞች ሁለት ቀለበቶች ውስጥ አስቀመጧቸው።
\v 18 ሌሎች ሁለት ጫፎች ከሁለት ፈርጦች ጋር አያያዟቸው። ከኤፉዱ የትከሻ ንጣዮች ጋር በኤፉዱ ፊት አገናኗቸው።
\s5
\v 19 የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው ከውስጠኛው ጠርዝ ቀጥሎ በሚገኘው ጎን በደረት ኪሱ ሌሎች ሁለት ጠርዞች ላይ አስቀመጧቸው።
\v 20 ተጨማሪ የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው፣ በመያዣው አጠገብ በብልኀት ከተሠራው የወገብ መታጠቂያ በላይ፣ ከአፉዱ ፊት ሁለት የትከሻ ንጣዮች ግርጌ ጋር አያያዟቸው።
\s5
\v 21 በብልኀት ከተሠራው ከኤፉዱ የወገብ መታጠቂያ በላይ መያያዝ እንዲችል፣ የደረት ኪሱን በራሱ ቀለበቶች ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋር በሰማያዊ ፈትል አሰሩት። ይህ የሆነው የደረት ኪሱ ከኤፉዱ የተነጠለ እንዳይሆን ነው። የተደረገውም እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት በነበረው መሠረት ነው።
\s5
\v 22 የኤፉዱን ቀሚስ ሙሉ በሙሉ የሸማኔ ሥራ ከሆነው ከሐምራዊ ጨርቅ ሠራው።
\v 23 መካከሉ ላይ ዐንገት ማስገቢያ ነበረው። እንዳይቀደድም ዙሪያውን የተዘመዘመ ጠርዝ ነበረው።
\v 24 በታችኛው የቀሚሱ ዘርፍ ላይም የሰማያዊ፣ የሐምራዊ፣ የቀይ ማግና የአማረ በፍታ ሮማኖችን አበጁ።
\s5
\v 25 ሻኵራዎችን ከንጹሕ ወርቅ ሠርተው በታችኛው የቀሚሱ ጠርዝ ዙሪያ ላይ በሮማኖቹም መካከል፣
\v 26 አገልግሎት በቀሚሱ ጠርዝ ላይ ሻኵራን ሮማን፣ ሻኵራና ሮማን እያደረጉ አስቀመጧቸው። ይህም የሆነው እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት በነበረው መሠረት ነው።
\s5
\v 27 ለአሮንና ለልጆቹ ሸሚዞችን ከአማረ በፍታ ሠሩ።
\v 28 የራስ መጠምጠሚያዎችን፣ ቆቦችንና ሱሪዎችን ከአማረ በፍታ፣
\v 29 መታጠቂያዎችንም ከአማረ በፍታ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ ጥልፍ ጠላፊ እንደሚሠራው አድርገው አበጇቸው። ይህም የሆነው እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት በነበረው መሠረት ነው።
\s5
\v 30 አክሊል ሠሌዳ ከንጹሕ ወርቅ ሠርተው በቀለበት ላይ ማኅተም እንደሚቀረጽ በላዩ ቅዱስ ለእግዚአብሔርን ቀረጹበት።
\v 31 እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት እንደ ነበረው፣ በመጠምጠሚያው ዐናት ላይ ለማንጠልጠል ሰማያዊ ፈትል አሰሩበት።
\s5
\v 32 ድንኳን፣ የማደሪያው ሥራ ተጠናቀቀ። የእስራኤል ሰዎች እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጣቸውን መመሪያዎች በመከተል ሁሉንም አደረጉ።
\v 33 ድንኳኑንና ዕቃዎቹን ሁሉ፣ ካስማዎቹን፣ ወጋግራዎቹን፣ አግዳሚዎቹን፣ ምሰሶዎቹንና መቆሚያዎቹን፣
\v 34 በቀይ ቀለም የተነከረውን የአውራ በግ ቆዳ መሸፈኛ፣ የአስቆጣ ቆዳዊን መሸፈኛና የሚሸፍነውን መጋረጃ፣
\v 35 የምስክሩን ታቦት፣ መሎጊያዎቹንና የስርየት መክደኛውን ወደ ሙሴ አመጡ።
\s5
\v 36 ጠረጴዛውን፣ የጠረጴዛውን ዕቃዎች ሁሉና የገጽ ኅብስቱን፤
\v 37 የንጹሑን ወርቅ መቅረዝና የረድፍ መብራቶችን ከዐባሪ ዕቃዎቹና ከመብራቶቹ ዘይት ጋር፤
\v 38 መሥዐዊያውን፣ መቅቢያ ዘይቱንና ጣፋጭ መዐዛ ያለን ዕጣን፣ የመገናኛውን ድንኳን መግቢያ መጋረጃ፤
\v 39 የነሐስ መሠዊያውን ከነሐስ ፍርግርጉና ከመሎጊያዎቹ፣ ከዕቃዎቹ፣ ከትልቁ የመታጠቢያ ሳሕንና ከመቆሚያው ጋር አመጡ።
\s5
\v 40 የአደባባዩን መጋረጃዎች ከምሰሶዎቹና ከመቆሚያዎቹ ጋር፣ የአደባባዩን መግቢያ መጋረጃም፣ ገመዶቹንና የድንኳን ካስማዎችን፣ ለመገናኛው ድንኳን አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውለውን ዕቃ ሁሉ አመጡ።
\v 41 አገልግሎት በጥበብ የተሠሩትን ልብሶች፣ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉ የካህኑን የአሮንንና የልጆቹን የተቀደሱ ልብሶችም አመጡ።
\s5
\v 42 ስለዚህም የእስራኤል ሰዎች እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሥራውን በሙሉ አከናወኑ።
\v 43 ሙሴ ሥራውን ሁሉ ሲፈትሽ፣ እነሆ ሁሉን አከናውነውታል። ያከናወኑትም እግዚአብሔር አዝዞት በነበረው በዚያው መንገድ ነው። ሙሴም ሕዝቡን ባረካቸው።
\s5
\c 40
\p
\v 1 ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤
\v 2 “በዐዲሱ ዓመት የመጀመሪያ ወር የመጀመሪያ ቀን ማደረያውን፣ የመገናኛውን ድንኳን ትከለው።
\s5
\v 3 ታቦት በውስጡ አስቀምጠው፤ ታቦቱንም በመጋረጃ ከልለው።
\v 4 ጠረጴዛውንም ወደ ውስጥ አምጣና በላዩ የሚቀመጡትን ዕቃዎች በሥርዐት አስቀምጥ። ከዚያም መቅረዙን አስገብተህ መብራቶቹን አስተካክል።
\s5
\v 5 የወርቅ የዕጣን መሠዊያውን በምስክሩ ታቦት ፊት አስቀምጥ፤ የመገናኛውን ድንኳን መግቢያ መጋረጃም አድርግ።
\v 6 የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን መሠዊያ በማደሪያው፣ በመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት አስቀምጥ።
\v 7 ትልቁን የመታጠቢያ ሳሕን በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል አስቀምጠው፤ ውሀም አድርግበት።
\s5
\v 8 በዙሪያውም አደባባይ ሥራለትን በአደባባዩ መግቢያ ላይ መጋረጃውን ስቀል።
\v 9 መቅቢያ ዘይቱን ውሰድና መገናኛውን ድንኳንና አውስጡ ያለውን ዕቃ ሁሉ ቅባ። እርሱንና በውስጡ ያለውን ዕቃ ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ፤ ከዚያም የተቀደሰ ይሆናል።
\v 10 የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን መሠዊያና የመሠዊያውን ዕቃዎች ሁሉ ቅባቸው።
\v 11 መሠዊያውን ለእኔ ቀድስልኝ፤ ከዚያም ለእኔ እጅግ የተቀደሰ ይሆንልኛል።
\s5
\v 12 ልጆቹን ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ አምጣና በውሀ እጠባቸው።
\v 13 ለእኔ የተቀደሱ ልብሶችን ለአሮን አልብሰው፤ ካህኔ ሆኖ እንዲያገለግልም ቅባው፤ ቀድሰውም።
\s5
\v 14 ልጆቹንም አምጣና ሸሚዞችን አልብሳቸው።
\v 15 ካህናቴ ሆነው እንዲያገለግሉኝ፣ አባታቸውን እንደ ቀባኸው እነርሱንም ቅጣቸው። የእነርሱ መቀባት በትውልዶች ሁሉ የዘለቄታ ካህንነትን ለእነርሱ ያስገኛል።”
\v 16 ሙሴ ያደረገው ይህ ነው፦ እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ተከተለ። እነዚህንም ሁሉ አደረገ።
\s5
\v 17 በሁለተኛው ዓመት የመጀመሪያ ወር አንደኛ ቀን ላይ የመገናኛው ድንኳን ተተከለ።
\v 18 ሙሴ መገናኛውን ድንኳን ተከለ፤ መቆሚያዎቹንም በስፍራቸው አስቀመጠ፤ ወጋግራዎቹን አቁሞ አግዳሚዎቹን አያያዘ፤ ምሰሶዎቹንም አቆመ።
\v 19 በማደሪያው ላይ መሸፈኛውን ዘረጋ፤ ድንኳኑንም እግዚአብሔር አዝዞት እንደ ነበረው ከበላዩ አስቀመጠው።
\v 20 ምስክሩን ወስዶ በታቦቱ ውስጥ አስቀመጠው።
\s5
\v 21 ወደ መገናኛው ድንኳን አመጣው። እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት እንደ ነበረው፣ የምስክሩን ታቦት ለመከለል መጋረጃውን አደረገ።
\v 22 ሰሜን ጎን ከመጋረጃው ውጭ ጠረጴዛውን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አስቀመጠ።
\v 23 እግዚአብሔር አዝዞት እንደ ነበረው፣ ኅብስቱን በጠረጴዛው ላይ በሥርዐት በእግዚአብሔር ፊት አስቀመጠው።
\s5
\v 24 መቅረዙን በመገናኛው ድንኳን ደቡብ ጎን ከጠረጴዛው ትይዩ በማደሪያው ድንኳን ውስጥ አስቀመጠው።
\v 25 መብራቶቹን እግዚአብሔር እንዳዘዘው በእግዚአብሔር ፊት አበራቸው።
\s5
\v 26 የተሠራውን የዕጣን መሠዊያም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከመጋረጃው ፊት ለፊት አደረገው።
\v 27 ላይም እግዚአብሔር አዝዞት እንደ ነበረው ጣፋጭ መዐዛ ያለውን ዕጣን አቀጣጠለ።
\s5
\v 28 መጋረጃውን በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ሰቀለ።
\v 29 የሚቃጠለውን መሥዋዕት መሠዊያም በማደሪያው፣ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ አስቀመጠ። በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን እግዚአብሔር እንዳዘዘው አቀረበ።
\v 30 የመታጠቢያ ሳሕኑን በመገናኛው ድንኳንና በመሠውያው መካከል አኖረው፤ የመታጠቢያ ውሀም በውስጡ አደረገ።
\s5
\v 31 ሙሴ፣ አሮንና ልጆቹ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በመታጠቢያው ውሀ ይታጠቡ ነበር፤
\v 32 መገናኛው ድንኳን ውስጥ በሚገቡትና መሠዊያው ወዳለበት ወደ ላይ በሚወጡበት ጊዜ ሁሉ፣ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ታጥበውታል።
\v 33 ሙሴ በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው ዙሪያ አደባባዩን አቆመ። መጋረጃውንም በአደባባዩ መግቢያ ዘረጋ። ሙሴ በዚህ መንገድ ሥራውን ፈጸመ።
\s5
\v 34 ደመናውም የመገናኛውን ድንኳን ሸፈነ፤ የእግዚአብሔር ክብርም ማደሪያውን ሞላው።
\v 35 ደመናው በላዩ ስላረፈና የእግዚአብሔር ክብርም ማደሪያውን ስለ ሞላው፣ ሙሴ መገናኛው ድንኳን ውስጥ መግባት አልቻለም ነበር።
\s5
\v 36 ከማደሪያው ድንኳን በተነሣ ጊዜ ሁሉ፣ የእስራኤል ሰዎች ይጓዛሉ።
\v 37 ግን ደመናው ከማደሪያው ላይ ካልተነሣ፣ ሕዝቡ አይጓዙም። ደመናው እስከሚነሣበት ቀን ድረስ ይቆያሉ።
\v 38 በሁሉም የእስራኤል ሕዝብ ፊት በጕዟቸው ሁሉ ቀን የእግዚአብሔር ደመና፣ ማታ ደግሞ እሳቱ በማደሪያው ላይ ነበረ።