am_ulb/67-REV.usfm

861 lines
93 KiB
Plaintext

\id REV
\ide UTF-8
\h የዮሐንስ ራእይ
\toc1 የዮሐንስ ራእይ
\toc2 የዮሐንስ ራእይ
\toc3 rev
\mt የዮሐንስ ራእይ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 ይህ ፈጥኖ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለአገልጋዮቹ እንዲያሳይ እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው ራእይ ነው። እርሱም ይህን ራእይ መልአኩን ወደ አገልጋዩ ወደ ዮሐንስ በመላክ እንዲታወቅ አድርጓል።
\v 2 ዮሐንስም የእግዚአብሔርን ቃል በሚመለከት ስላየው ማንኛውንም ነገር እና ክርስቶስን በሚመለከት ስለተሰጠው ምስክርነት ተናግሯል።
\v 3 ዘመኑ ስለ ቀረበ ፥ የዚህን የትንቢት ቃል የሚያነብ የተባረከ ነው፤እንዲሁም የሚሰሙት ሁሉ በውስጡም የተጻፈው ን ነገር የሚፈጽሙ የተባረኩ ናቸው።
\s5
\v 4 ከዮሐንስ፥በእስያ ላሉት ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት፤ካለው፥ከነበረው፥ወደፊትም ከሚመጣውና በዙፋኑ ፊት ካሉት ከሰባቱ መንፈሶች
\v 5 እንዲሁም ታማኝ ምስክር፥ከሙታን በኩርና የምድር ነገሥታት ገዥ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለሚወደንና ከኀጢአታችንም በደሙ ነጻ ላወጣን፥
\v 6 አባቱ ለሆነው እግዚአብሔር መንግሥትና ካህናት እንሆን ዘንድ ላደረገን ለእርሱ ክብርና ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን፤አሜን።
\s5
\v 7 እነሆ፤እርሱ በደመና ይመጣል፤የወጉትን ጨምሮ ዐይን ሁሉ ያየዋል። የምድርም ነገዶች ሁሉ በእርሱ ምክንያት ያለቅሳሉ፤እንደዚያም ይሆናል፤አሜን።
\v 8 ጌታ እግዚአብሔር፥«አልፋና ኦሜጋ፥ ያለሁና የነበርሁ፥ወደፊትም የምመጣው ሁሉን ቻይ እኔ ነኝ» ይላል።
\s5
\v 9 እኔ ከእናንተ ጋር በመከራው፥በመንግሥቱና በኢየሱስ በሚገኘው ትዕግሥት ተካፋይ የሆንሁ ወንድማችሁ ዮሐንስ፥ በእግዚአብሔር ቃልና በኢየሱስ ምስክርነት ምክንያት ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ።
\v 10 በጌታም ቀን በመንፈስ ነበርሁ፤በኋላዬም የመለከትን ድምጽ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ።
\v 11 ድምፁም እንዲህ የሚል ነበር፤«የምታየውን በመጽሓፍ ጻፈው፤ ከዚያም በኤፌሶን፥ በሰምርኔስ፥ በጴርጋሞን፥ በትያጥሮን፥ በሰርዴስ፥ በፊለደልፍያና በሎዶቅያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላከው።
\s5
\v 12 ይናገረኝ የነበረው የማን ድምፅ እንደ ሆነ ለማየት ዘወር አልሁ፤ ዘወር በምልበትም ጊዜ ሰባት የወርቅ መቅረዞችን አየሁ።
\v 13 በመቅረዞቹም መካከል እስከ እግሩ ድረስ የሚደርስ ረጅም ልብስ የለበሰና ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ የሰው ልጅ የሚመስለው ነበር።
\s5
\v 14 ራሱና ጸጉሩ እንደ ነጭ የበግ ጸጉር ማለትም እንደ በረዶ ነጭ ነበሩ፤ዐይኖቹ የእሳት ነበልባል፥
\v 15 እግሮቹም በእቶን እሳት እንደ ነጠረ የጋለ ናስ፥ ድምፁም እንደ ብዙ ወራጅ ውኃ ድምፅ ነበር።
\v 16 በቀኝ እጁ ሰባት ከዋክብት ይዞ ነበር፤ከአፉም በሁለት በኩል የተሳለ ስለታም ሰይፍ ይወጣ ነበር፤ፊቱም ጸሐይ በሙሉ ኀይልዋ ስታበራ የምታበራውን ያህል ያበራ ነበር።
\s5
\v 17 ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ በእግሩ ሥር ወደቅሁ፤ እርሱም ቀኝ እጁን በእኔ ላይ በመጫን እንዲህ አለኝ፤ «አትፍራ፤እኔ የመጀመሪያውና የመጨረሻው
\v 18 ሕያውም ሆኜ የምኖር ነኝ። ሞቼ ነበር፤እነሆም ለዘላለም ሕያው ነኝ፤የሞትና የሲዖል መክፈቻም አለኝ።
\s5
\v 19 ስለዚህ ያየኽውን፥አሁን ያለውን ሁኔታና ከዚህ በኋላ የሚሆነውን ነገር ጻፍ።
\v 20 በቀኝ እጄ ያሉት አንተም ያየሃቸውን የሰባቱን ከዋክብትና የሰባቱን የወርቅ መቅረዞች ምስጢር በተመለከተ ትርጉሙ ይህ ነው፤ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ሲሆኑ፥ ሰባቱ መቅረዞች ደግሞ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 “በኤፌሶን ወዳለው መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ ‘ሰባቱን ከዋክብት በቀኝ እጁ የያዘውና በሰባቱ የወርቅመቅረዞች መካከል የሚመላለሰው እንዲህ ይላል፤
\v 2 ‘ሥራህን፣ ትዕግሥትህንና ጽናትህን አውቃለሁ። ክፉ ሰዎችን መታገሥ አለመቻልህንም አውቃለሁ። ሐዋሪያት ሳይሆኑ “ሐዋሪያት ነን” የሚሉትን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸውም አውቃለሁ።”
\s5
\v 3 በትዕግሥት እንደ ጸናህ፥ስለ ስሜ ብዙ መከራ ቢደርስብህም እንዳልደከመህ አውቃለሁ።
\v 4 ነገር ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤ይኽውም የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃል።
\v 5 እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ ለይተህ እወቅ፤ንስሓ ግባ፤ቀደም ሲል ታደርገው የነበረውንም ነገር አድርግ። ንስሓ ካልገባህ እመጣብሃለሁ፤መቅረዝህንም ከስፍራው አስወግዳለሁ።
\s5
\v 6 ነገር ግን ይህ መልካም ነገር አለህ፤ እኔ የምጠላውን የኒቆላውያንን ሥራ ጠልተሃል።
\v 7 ጆሮያለው መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን ይስማ። ድል ለሚነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው የሕይወት ዛፍ የመብላትን መብት እሰጠዋለሁ።”
\s5
\v 8 «በሰምርኔስ ላለችው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ "እነዚህ መጀመሪያም መጨረሻም የሆነው የእርሱ ቃሎች ናቸው፤ሞቶ የነበረው፥እንደ ገና ሕያው የሆነው እንዲህ ይላል፤
\v 9 '"መከራህንና ድኽነትህንም አውቃለሁ፤ነገር ግን ባለጠጋ ነህ፤የሰይጣን ማኅበር ሆነው እያለ፥አይሁድ ሳይሆኑ አይሁድ ነን ብለው የሚናገሩ ሰዎች የሚሳደቡትን ስድብ አውቃለሁ።
\s5
\v 10 ወደ ፊት የሚደርስብህን መከራ አትፍራ። ተመልከት ከእናንተ አንዳንዶቹን እንድትፈተኑ ዲያብሎስ እስር ቤት ያስገባችኋል፤ ለአሥር ቀን መከራ ትቀበላላችሁ። እስከ ሞት ድረስ ታማኝ ሁን፤ እኔም የሕይወትን አክሊል እሰጥሃለሁ።
\v 11 ጆሮ ያለው መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለው ይስማ። ድል የሚነሻ በሁለተኛው ሞት አይጎዳም።
\s5
\v 12 «በጴርጋሞን ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ "እነዚህ በሁለት በኩል የተሳለ ስለታም ሰይፍ ካለው የተነገሩ ቃሎች ናቸው፤እርሱም እንዲህ ይላል፤
\v 13 '"የሰይጣን ዙፋን ባለበት በዚያ እንደምትኖር አውቃለሁ፤ነገር ግን ስሜን አጥብቀህ ይዘሃል። ሰይጣን በሚኖርበት በእናንተ መካከል በተገደለው በታማኙ ምስክሬ በአንቲጳስ ዘመን እንኳ በእኔ ያለህን እምነት አልካድህም።
\s5
\v 14 ነገር ግን የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ፤የእስራኤል ልጆች ለጣዖት የተሰዋ ምግብ እንዲበሉና እንዲሴስኑ በፊታቸው ማሰናከያ ያስቀምጥ ዘንድ ባላቅን የመከረው የበለዓምን ትምህርት አጥብቀው የሚከተሉ አንዳንድ ሰዎች በመካከልህ አሉ።
\v 15 እንደዚሁም የኒቆላውያንን ትምህርት አጥብቀው የያዙ ሰዎች እንኳ በአንተ ዘንድ አሉ።
\s5
\v 16 ስለዚህ ንስሓ ግባ፤አለበለዚያ ፈጥኜ እመጣብሃለሁ፤ከአፌም በሚወጣው ሰይፍ አዋጋቸዋለሁ።
\v 17 ጆሮ ካለህ፥መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ስማ። ድል ለሚነሳ ከተሰወረው መና እሰጠዋለሁ፤እንደዚሁም ከሚቀበለው ሰው በስተቀር ማንም የማያውቀውን አዲስ ስም የተጻፈብትን ነጭ ድንጋይ እሰጠዋለሁ።>
\s5
\v 18 በቲያጥሮን ወዳለው መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ “የእሰት ነበልባል የመሰሉ ዐይኖችና በእሳት ፍም የነጠረ ናስ የሚመስሉ እግሮች ያሉት የእግዚአብሔር ልጅ እንዲህ ይላል።
\v 19 ሥራህን፣ ፍቅርህንና እምነትህን፣ አገልግሎትህንና በትዕግሥት መጽናትህን አውቃለሁ። አሁን በቅርቡ ያደረግኸው ቀድሞ ካደረግኸው የበለጠ መሆኑን አውቃለሁ።”
\s5
\v 20 ነገር ግን የምነቅፍብህ አንድ ነገር አለኝ፤ራሷን ነቢይት ብላ የምትጠራውን ሴት ኤልዛቤልን ችላ ብለሃታል። ይህች ሴት በትምህርትዋ አገልጋዮቼ ሴሰኛ እንዲሆኑና ለጣዖት የተሰዋ ምግብ እንዲበሉ ታስታቸዋለች።
\v 21 ንስሓ እንድትገባ ጊዜ ሰጥቻት ነበር ፤ይሁን እንጂ ከርኩሰትዋ ንስሓ ለመግባት ፈቃደኛ አልሆነችም።
\s5
\v 22 እነሆ በሥቃይ አልጋ ላይ እጥላታለሁ፤ከእርስዋም ጋር የሚያመነዝሩት እርስዋ ከፈጸመችው ነገር ንስሓ ካልገቡ በስተቀር በከባድ ሥቃይ እንዲወድቁ አደርጋለሁ።
\v 23 በሞት እቀጣለሁ፤በመሆኑም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የሰውን ሐሳብና ፍላጎትን የምመረምር እኔ እንደሆንሁ ያውቃሉ። ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እከፍላለሁ።
\s5
\v 24 ዳሩ ግን ይህን ትምህርት ለማትከተሉ ሁሉ እንዲሁም አንዳንዶች የሰይጣን ጥልቅ ምስጢር ነው የሚሉትን ነገር ለማታውቁ በትያጥሮን ለምትኖሩ ለቀራችሁት ሌላ ሸክም አልጭንባችሁም።>
\v 25 ሆኖም እስክመጣ ድርስ ያላችሁን ነገር አጸንታችሁ ጠብቁ።
\s5
\v 26 ለሚነሣውና እስከ መጨረሻው እኔ የደረግሁትን ለሚያደርግ በሕዝቦች ላይ ሥልጣን እሰጠዋለሁ።
\v 27 በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እንደ ሸክላም ዕቃ የደቃቸዋል።
\v 28 እኔ ከአባቴ እንደ ተቀበልሁ የንጋትን ኮከብ እሰጠዋለሁ።
\v 29 ጆሮ ያለው መንፈስ መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን ይስማ።”
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 «በሰርዴስ ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ "ሰባቱን የእግዚአብሔር መንፈሶችና ሰባቱን ከዋክብት የያዘው እንዲህ በማለት ይናገራል፤«ሥራህን ዐውቃለሁ፤ሕያው እንደሆንህ የሚገልጽ ዝነኛ ስም አለህ፤ነገር ግን ሞተሃል።
\v 2 ሥራህን በእግዚአብሔር ፊት ፍጹም ሆኖ ስላላገኘሁት ንቃ፤ሊሞቱ የተቃረቡትን የቀሩትን ነገሮች አጽና።
\s5
\v 3 እንግዲህ ምን እንደተቀበልህና ምን እንደሰማህ አስታውስ፤ጠብቀው፤ንስሓም ግባ። ነገር ግን ባትነቃ ፥እንደ ሌባ እመጣለሁ፤በምን ሰዓት እንደምመጣብህም አታውቅም።
\v 4 ነገር ግን በሰርዴስ ልብሳቸውን ያላቆሸሹ ጥቂት ሰዎች አሉ። የተገባቸውም ስለ ሆነ፥ ነጭ ልብሳቸውን ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ።
\s5
\v 5 ድል የሚነሳ ነጭ ልብስ ይለብሳል፤ስሙን ከሕይወት መጽሐፍ ፈጽሞ አልደመስሰውም፤ይልቁን በአባቴና በመላእክቱ ፊት ለስሙ እመሰክራለሁ።
\v 6 ጆሮ ካለህም መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት ይሚናገረውን ስማ።»
\s5
\v 7 «በፊላደልፍያ ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ የዳዊት መክፈቻ ያለው፥የሚከፍት እርሱ የከፈተውን ማንም የማይዘጋ፥የሚዘጋ እርሱ የዘጋውን ማንም ሊከፍት የማይችል ቅዱስና እውነተኛ የሆነው እርሱ እንዲህ ይላል፤
\v 8 ሥራህን ዐውቃለሁ፤እነሆ፤ማንም ሊዘጋው የማይችል የተከፈተ በር በፊትህ አድርጌአለሁ። ዐቅምህ ትንሽ እንደሆነ አውቃለሁ፤ይሁን እንጂ ቃሌን ጠብቀሃል፤ስሜንም አልካድህም።
\s5
\v 9 እነሆ፤አይሁድ ሳይሆኑ አይሁድ ነን የሚሉት እነዚያ ከሰይጣን ማኅበር የሆኑት ውሸተኞች ናቸው። እነርሱንም እኔ እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ መጥተው በእግርህ እንዲወድቁ አደርጋለሁ።
\v 10 በትዕግሥ እንድትጸና የሰጠሁህን ትእዛዜን ስለ ጠበቅህ ፥በምድር የሚኖሩትን ይፈትን ዘንድ በዓለም ላይ ሁሉ ሊመጣ ካለው የፈተና ሰዓት እጠብቅሃለሁ።
\v 11 በቶሎ እመጣለሁ፤አክሊልህን ማንም እዳይወስድብህ፥ያለህን አጥብቀህ ያዝ።
\s5
\v 12 ድል የሚነሻውን በአባቴ ቤተ መቅደስ ዐምድ አደርገዋለሁ፤ ከዚያ በፍጹም አይወጣም። እርሱ ላይ የአምላኬን ከተማ ስም፣ ማለት ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ የምትወጣውን የአዲሲቱ ኢዩሳሌምን ስም ደግሞ አዲሱ ስሜን እጽፋለሁ።
\v 13 ጆሮ ያለው መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን የስማ።”
\s5
\v 14 «በሎዶቅያ ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ "ይህም በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ ገዥ እንዲሁም እውነተኛና ታማኝ ምስክር ከሆነው ቃሉም አሜን ከሆነው የተነገረ ነው፤
\v 15 ሥራህን አውቃለሁ፤በራድ ወይም ትኩስ አይደለህም። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆን ኖሮ መልካም ይሆን ነበር።
\v 16 እንግዲህ ትኩስ ወይም በራድ ሳትሆን በመካከል ለብ ስላልህ ከአፌ ልተፋህ ነው።
\s5
\v 17 «እኔ ሀብታም ነኝ፤ብዙ ገንዘብ አለኝ፤የጎደለኝ ምንም ነገር የለም» ትላለህ፤ነገር ግን እጅግ ጎስቋላ፥ምስኪን፥ድኻ፥ዕውርና የተራቆትህ እንደሆንህ አታውቅም።
\v 18 ሀብታም ትሆን ዘንድ በእሳት የተፈተነውን ወርቅ ከእኔ እንድትገዛ፥የራቁትነትህን ሐፍረት ለመሽፈን ነጭ ልብስ እንድትለብስ፥አጥርተህ ለማየትም ዐይንህን እንድትኳል እመክርሃለሁ።
\s5
\v 19 እኔ የምወዳቸውን እንዴት መኖር እንደሚገባቸው ያውቁ ዘንድ እቀጣቸዋለሁ፤ አስተምራቸዋለሁም። ስለዚህ ትጋ፤ንስሓም ግባ።
\v 20 እነሆ፤በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ። ማንም ድምጼን ሰምቶ ቢከፍትልኝ ወደ ቤቱ እገባለሁ፤ከእርሱ ጋር እበላለሁ፤እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።
\s5
\v 21 እኔ ድል እንደነሳሁና በዙፋኑ ላይ ከአባቴ ጋር እንደተቀመጥሁ፥ድል ለሚነሳም በዙፋኔ ላይ ከእኔ ጋር የመቀመጥን መብት እሰጠዋለሁ።
\v 22 መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ።»
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 ከእነዚህ ነገሮች በኋላ እነሆ የተከፈተ በር በሰማይ አየሁ። እንደ መለከት ድምፅ ሆኖ ሲናገረኝ የነበረው የመጀመሪያው ድምፅ፥«ወደዚህ ና! ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ በኋላ የሚሆነውን አሳይሃለሁ።» አለ።
\v 2 ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤በሰማይ ዙፋን ተዘርግቶ አየሁ፤በዙፋኑም ላይ አንድ የተቀመጠ አካል ነበር።
\v 3 በዙፋኑም ላይ ተቀምጦ የነበረው መልኩ የኢያስጲድንና የሰርዲኖን ዕንቁ ይመስል ነበር። በዙፋኑም ዙሪያ የመረግድ ዕንቁ የመሰለ ቀስተ ደመና ነበር።
\s5
\v 4 በዙፋኑም ዙሪያ ሃያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፤በእነዚህም ዙፋኖች ላይ ነጭ ልብስ የለበሱና በራሳቸውም ላይ የወርቅ አክሊል የደፉ ሃያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር።
\v 5 ከዙፋኑም የመብረቅ ብልጭታና የነጎድጓድ ድምፅ ወጣ። በዙፋኑም ፊት ሰባት መብራቶች ይበሩ ነበር፤እነዚህም ሰባቱ የእግዚአብሔር መንፈሶች ናቸው።
\s5
\v 6 እንደዚሁም በዙፋኑ ፊት እንደ መስተዋት እጅግ የጠራ ባሕር ነበር። በዙፋኑም ዙሪያ ሁሉ ከፊትና ከኋላ በዐይን የተሞሉ አራት ሕያዋን ፍጡራን ነበሩ።
\s5
\v 7 የመጀመሪያው ሕያው ፍጡር አንበሳ ሲመስል፥ሁለተኛው ሕያው ፍጡር ጥጃ ይመስል ነበር፤ሦስተኛው ሕያው ፍጡር የሰውን ፊት የሚመስል ፊት ነበረው፤አራተኛው ሕያው ፍጡር ደግሞ የሚበር ንስር ይመስል ነበር።
\v 8 አራቱም ሕያዋን ፍጡራን እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፍ ነበራቸው፤ከላይና ከሥርም በዐይኖች የተሞሉ ነበሩ። እነርሱም ቀንና ሌሊት፥ «ቅዱስ፥ቅዱስ፥ቅዱስ፥ በሁሉም ላይ የሚገዛ፥የነበረና ያለ፥ወደፊትም የሚመጣው ጌታ አምላክ» ማለትን አያቋርጡም ነበር።
\s5
\v 9 ሕያዋን ፍጡራኑም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠውና ከዘላለም እስከ ዘላለም ለሚኖረው ክብር፥ ሞገስና ምስጋና በሚሰጡበት ጊዜ፥
\v 10 ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው ፊት በግምባራቸው ተደፍተው ከዘላለም እስከ ዘላለም ለሚኖረው ሰገዱ፤አክሊላቸውንም በዙፋኑ ፊት አስቀምጠው፥
\v 11 «ጌታችንና አምላካችን ሆይ፤አንተ ሁሉንም ነገር ስለፈጠርህ፥በፈቃድህ ስለፈጠርሃቸውና እንደዚያም ሆነው ስለተገኙ ክብር፥ሞገስ፥ኅይልም ልትቀበል ይገባሃል።» ይሉ ነበር።
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 በዙፋኑም ላይ በተቀመጠው ቀኝ እጅ ከፊትና ከጀርባ የተጻፈበት በሰባትም ማኅተም የታሸገ ጥቅልል መጽሓፍ አየሁ።
\v 2 አንድ ብርቱ መልአክ፥«መጽሓፉን ሊከፍት፥ ማኅተሙን ሊፈታ የተገባው ማን ነው?» ብሎ በታላቅ ድምፅ ሲያውጅ አየሁ።
\s5
\v 3 በሰማይ ቢሆን በምድር ወይም ከምድር በታች መጽሓፉን ሊከፍት ወይም ሊያነብ ማንም አልቻለም።
\v 4 መጽሓፉን ሊከፍት ወይም ሊያነብ የተገባው ማንም ስላልተገኘ፥አምርሬ አለቀስሁ።
\v 5 ነገር ግን ከሽማግሌዎች አንዱ፥«አታልቅስ፤እነሆ! ከዳዊት ሥር፥ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ መጽሓፉን ይከፍትና ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነስቷል» አለኝ።
\s5
\v 6 በዙፋኑና በአራቱ ሕያዋን ፍጡራን መካከል እንዲሁም በሽማግሌዎች መካከል አንድ ታርዶ የነበረ የሚመስል በግ ቆሞ አየሁ። እርሱም ሰባት ቀንዶችና ሰባት ዐይኖች ነበሩት፤እነዚህም በምድር ሁሉ ላይ የተላኩ ሰባቱ የእግዚአብሔር መንፈሶች ናቸው።
\v 7 ሄዶም በዙፋን ላይ ከተቀመጠው ቀኝ እጅ ጥቅልል መጽሓፉን ወሰደ።
\s5
\v 8 ጥቅልል መጽሓፉንም በሚወስድበት ጊዜ አራቱ ሕያዋን ፍጡራን እና ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት በግምባራቸው ተደፉ፤ እያንዳንዳቸውም በገና እና የቅዱሳን ጸሎት የሆነው ዕጣን የሞላበት የወርቅ ዕቃ ይዘው ነበር።
\s5
\v 9 እነርሱም እንዲህ የሚል አዲስ ቅኔ ዘመሩ፤«መጽሓፉን ትወስድ እና ማኅተሞቹን ተፈታ ዘንድ ይገባሃል፤ ታርደሃልና በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ፥ከቋንቋ ሁሉ፥ ከሕዝብና ከአገር ሁሉ ሰዎችን ዋጅተሃል።
\v 10 አምላካችንን ያገለግሉ ዘንድ መንግሥትና ካህናት አደረግሃቸው፤እነርሱም በምድር ላይ ይገዛሉ።»
\s5
\v 11 ከዚያም በኋላ ስመለከት፥በዙፋኑ፥በሕያዋኑ ፍጡራን እና በሽማግሌዎች ዙሪያ የብዙ መላእክት ድምፅ ሰማሁ፤ቁጥራቸውም ሁለት መቶ ሚሊዮን ነበር።
\v 12 እነርሱም በታላቅ ድምፅ፥«የታረደው በግ ኀይልና ባለጠግነት፥ጥበብና ብርታት፥ምስጋና እና ክብር ሊቀበል ይገባዋል።» አሉ።
\s5
\v 13 በሰማይና በምድር፥ከምድር በታች እንዲሁም በባሕር ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ ፥«ምስጋና፥ክብር፥ውዳሴ፥የመግዛትም ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው እና ለበጉ ይሁን።» ሲሉ ሰማሁ፤
\v 14 አራቱ ሕያዋን ፍጡራን፥«አሜን» አሉ፤ሽምግሌዎችም በግምባራቸው ተደፍተው ሰገዱ።
\s5
\c 6
\cl ምዕራፍ 6
\p
\v 1 ከዚህም በኋላ በጉ ከሰባቱ ማኅተሞች አንዱን ሲከፍት አየሁ፤ከአራቱ ሕያዋን ፍጡራን አንዱ እንደ ነጎድጓድ ባለ ድምፅ «ና!» ሲል ሰማሁ።
\v 2 አየሁም ፤እነሆም አንድ ነጭ ፈረስ አየሁ፤ባላዩ ላይ የተቀመጠውም ቀስት ይዞ ነበር፤አክሊልም ተሰጠው። እንደ ድል አድራጊ ሆኖ ድል ይነሳ ዘንድ ወጣ።
\s5
\v 3 በጉ ሁለተኛውን ማኅተም በሚከፍትበት ጊዜ፥ሁለተኛው ሕያው ፍጡር«ና!» ሲል ሰማሁ።
\v 4 ከዚያም ደማቅ ቀይ ፈረስ ወጣ፤በፈረሱም ላይ ለተቀመጠው ሰዎች እርስ በርስ ይተራረዱ ዘንድ ሰላምን ከምድር እንዲያስወግድ ሥልጣን ተሰጠው፤ትልቅ ሰይፍም ተሰጠው።
\s5
\v 5 በጉ ሦስተኛውን ማኅተም በሚከፍትበት ጊዜ፥ ሦስተኛው ሕያው ፍጡር «ና!» ሲል ሰማሁ፤ ጥቁር ፈረስ አየሁ፤በፈረሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ይዞ ነበር።
\v 6 ከአራቱ ሕያዋን ፍጡራን የመጣ የሚመስል ድምፅ፥«አንድ እርቦ ስንዴ በዲናር፥ሦስት እርቦ ገብስም በዲናር፤ ነገር ግን ዘይቱንና ወይኑን አትጉዳ» ሲል ሰማሁ።
\s5
\v 7 በጉ አራተኛውን ማኅተም በሚከፍትበት ጊዜ የአራተኛው ሕያው ፍጡር ድምፅ «ና!» ሲል ሰማሁ።
\v 8 ከዚያም በኋላ ግራጫ ፈረስ አየሁ፤በላዩም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ተብሎ ይጠራ ነበር፤ሲኦልም ይከተለው ነበር። ሞትና ሲኦልም የምድርን አንድ አራተኛ በሰይፍ፥በረሃብ፥ በበሽታ፥በዱር አራዊት እንዲገድሉ ሥልጣን ተሰጣቸው።
\s5
\v 9 በጉ አምስተኛውን ማኅተም በሚከፍትበት ጊዜ ስለ እግዚአብሔር ቃልና በጽናት ስለ ጠበቁት ምስክርነት የተገደሉትን ሰዎች ነፍሶች ከመሠዊያው በታች አየሁ።
\v 10 እነርሱም በታላቅ ድምፅ፥«በሁሉም ላይ የምትገዛ ቅዱስና እውነተኛ የሆንህ ጌታ አምላክ ሆይ፤በምድር በሚኖሩት ላይ የማትፈርደው፥ ደማችንስ የማትበቀለው እስከ መቼ ድረስ ነው?» በማለት ይጮኹ ነበር።
\v 11 ከዚያም በኋላ ለእያንዳንዳቸው ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፤እነርሱ እንደ ተገደሉ፥ ገና የሚገደሉ አገልጋይ ጓደኞቻቸው፥ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ቁጥር እስኪሞላ ድረስ ለጥቂት ጊዜ እንዲታገሱ ተነገራቸው።
\s5
\v 12 በጉ ስድስተኛውን ማኅተም በሚከፍትበት ጊዜ አየሁ፤ እነሆ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ። ፀሐይም እንደ ጥቁር ጨርቅ ጠቆረች፤ ጨረቃም ሙሉ በሙሉ እንደ ደም ቀላች።
\v 13 የበለስ ዛፍ ኀይለኛ ነፋስ በሚወዘውዛት ጊዜ በላይዋ ያለ ያልበሰለ ፍሬ እንደሚረግፍ ሁሉ የሰማይ ከዋክብት ወደ ምድር ረገፉ።
\v 14 ሰማይም እንደ ብራና እየተጠቀለለ ተወገደ፤ እያንዳንዱ ተራራና ደሴት ከስፍራው ተነቀለ።
\s5
\v 15 ከዚያም በኋላ የምድር ነገሥታት፥ታላላቅ ሰዎች፥ የጦር መኮንኖች፥ ሀብታሞች፥ብርቱዎች፥ ባሮችና ጌቶች ሁሉ በዋሻዎችና በተራሮች ዐለት ውስጥ ተሸሸጉ።
\v 16 ለተራሮችና ለዐለቶችም እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፤«በላያችን ላይ ውደቁ፤ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ፊት፥ከበጉም ቁጣ ሰውሩን
\v 17 ታላቁ የቁጣቸው ቀን ስለ መጣ ማን መቆም ይችላል?»
\s5
\c 7
\cl ምዕራፍ 7
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ አራት መላእክት በአራቱም የምድር ማዕዘን ቆመው አየሁ፤ እነርሱም በምድር ቢሆን በባሕር ላይ ወይም በማንኛውም ዛፍ ላይ ፈጽሞ ነፋስ እንዳይነፍስ አራቱን የምድር ነፋሳትን አጥብቀው ይከለክሉ ነበር።
\v 2 የሕያው አምላክ ማኅተም የያዘ ሌላ መልአክ ከምስራቅ ሲመጣ አየሁ። እርሱም ምድርንና ባሕርን ይጎዱ ዘንድ ሥልጣን ወደ ተሰጣቸው ወደ አራቱ መላእክት በታላቅ ድምፅ እየጮኽ፥
\v 3 «በአምላካችን አገልጋዮች ግምባር ላይ ማኅተም እስክናደርግ ድረስ ምድርንም ሆነ ባሕርን ወይም ዛፎችን እንዳትጎዱ» አለ።
\s5
\v 4 ከእስራኤል ሕዝብ ነገድ ሁሉ የታተሙት ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ አርባ አራት ሺህ እንደ ሆነ ሰማሁ።
\v 5 ከይሁዳ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ ፥ከሮቤል ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ ፥ከጋድ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥
\v 6 ከአሴር ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ ከንፍታሌም ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ ፥ከምናሴ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ
\s5
\v 7 ከስምዖን ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ ፥ከሌዊ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ከይሳኮር ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥
\v 8 ከዛብሎን ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ከዮሴፍ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ከብንያም ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ ታተሙ።
\s5
\v 9 ከዚህ በኋላ ከሕዝብ፥ከነገድ፥ከወገንና ከቋንቋ ሁሉ የመጡ ቁጥራቸው ማንም ሊቆጥረው የማይችል አጅግ ብዙ ሕዝብ ነጭ ልብስ ለብሰው፥ በእጃቸውም የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆመው አየሁ።
\v 10 በታላቅ ድምፅም «ማዳን፥ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው የአምላካችንና የበጉ ነው!» እያሉ ይጮኹ ነበር።
\s5
\v 11 መላእክቱም ሁሉ በዙፋኑ እና በሽማግሌዎች ዙሪያ እንዲሁም በአራቱ ሕያዋን ፍጡራን ዙሪያ ቆመው ነበር፤እነርሱም በመሬት ላይ ወድቀው በዙፋኑም ፊት በግምባራቸው ተደፍተው ለእግዚአብሔር እየሰገዱ፥
\v 12 «አሜን! ውዳሴ፥ ክብር፥ጥበብ፥ምስጋና፥ኀይልና ብርታትም ከዘላለም እስከ ዘላለም ለአምላካችን ይሁን፤አሜን» ይሉ ነበር።
\s5
\v 13 ከዚያም በኋላ ከሽማግሌዎች አንዱ፥«እነዚህ ነጭ ልብስ የለበሱ እነማናቸው ከየትስ የመጡ ናቸው?» በማለት ጠየቀኝ፤
\v 14 እኔም «ጌታ ሆይ፥አንተ ታውቃለህ» አልሁት። እርሱም እንዲህ አለኝ፤«እነዚህ በታላቁ መከራ ውስጥ አልፈው የመጡ ናቸው፤ልብሳቸውንም በበጉ ደም አጥበው በማንጻት ነጭ አድርገዋል።
\s5
\v 15 ክዚህም የተነሳ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት መሆን ችለዋል፤ እርሱንም በመቅደሱ ውስጥ ቀንና ሌሊት ያመልኩታል። በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው ድንኳኑን በእነርሱ ላይ ይዘረጋል።
\v 16 እነርሱም ከእንግዲህ አይራቡም፤አይጠሙምም። ፀሐይ አያቃጥላቸውም፤ ሙቀትም አያሰቃያቸውም።
\v 17 ምክንያቱም በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናል፤ወደ ሕይወት ውኃ ምንጭ ይመራቸዋል፤እግዚአብሔር እንባንም ሁሉ ከዐይኖቻቸው ያብሳል።»
\s5
\c 8
\cl ምዕራፍ 8
\p
\v 1 በጉ ሰባተኛውን ማህተም በፈታ ጊዜ በሰማይ ለግማሽ ሰዓት ያህል ጸጥታ ሆነ፤
\v 2 ከዚያም በእግዚአብሄር ፊት የቆሙ ስባት መላዕክትን አየሁ፡፤ሰባት መለከቶችም ተሰጣቸው።
\s5
\v 3 ሌላም መልኣክ መጣ፤በእጁም ከወርቅ የተሰራ ጥና ይዞ ነበር።እርሱም በመሰዊያው አጠገብ ቆሞ ነበር።በዙፋኑ ፊት ባለው በወርቅ በተሰራ መሰዊያ ላይ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር የሚያቀርበው ብዙ ዕጣን ተሰጠው።
\v 4 የእጣኑ ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ ወደ እግዚአብሄር ወጣ፤
\v 5 መልአኩም ጥናውን ወስዶ ከመሰዊያው በወስድው እሳት ሞላው ከዚያም በኃላ ወደ ምድር ወረወረው፤የነጎድጛድ ድምጽ፤መብረቅ፤የምድር መናወጥም ሆነ።
\s5
\v 6 ሰባት መለከቶችን የያዙ ስባት መላዕክት መለከቶቻቸውን ለመንፋት ተዘጋጁ።
\v 7 የመጀመሪያውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ደም የተቀላቀለበት እሳትና በረዶ ሆነ። ይህም ወደ ምድር ተጣለ፤ ከዚህም የተነሣ የምድርም አንድ ሦስተኛ ተቃጠለ፤ የዛፎችም አንድ ሦስተኛ ተቃጠለ፤ የለመለመ ሣር ሁሉ ተቃጠለ።
\s5
\v 8 ሁለተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በእሳት የሚቃጠል ትልቅ ተራራ የሚመስል ነገር ወደ ባህር ተጣለ፤ የባህር አንድ ሦስተኛ ወደ ደም ተለወጠ።
\v 9 በባህር ውስጥ ካሉ ህያዋን ፍጥረታት አንድ ሦስተኛ ሞቱ፤ የመርከቦችም አንድ ሦስተኛ ተደመሰሱ።
\s5
\v 10 ሦስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ እንደ ችቦ የሚቃጠል ታላቅ ኮከብ ከሰማይ ወደቀ፤ የወደቀውም በወንዞች አንድ ሦስተኛ በውሃ ምንጮች ላይ ነው።
\v 11 የኮከቡም ስም እሬቶ ይባላል። የውኆችም አንድ ሦስተኛ መራራ ሆነ። ከውሃው መራራነት የተነሳ ብዙ ሰዎች ሞቱ።
\s5
\v 12 አራተኛውም መልአክ መልከቱን ነፋ፤የፀሐይ አንድ ሦስተኛ፣ የጨረቃ አንድ ሦስተኛ የኮከቦች አንድ ሦስተኛ ተመታ። ስለዚህ የእነርሱ አንድ ሦስተኛ ጨለመ፤ በዚህም ምክንያት የቀን አንድ ሦስተኛና የሌሊት አንድ ሦስተኛው ያለ ብርሃን ሆነ።
\s5
\v 13 እነሆ በሰማይ መካከል ሲበርር የነበር አንድ ንስር በታላቅ ድምጽ፤ ሦስቱ መላእክት የቀሩትን መለከቶች ስለሚነፉ «በምድር ላይ ለሚኖሩ ወዮላቸው! ወዮላቸው! ወዮላቸው!» ሲል ሰማሁ።
\s5
\c 9
\cl ምዕራፍ 9
\p
\v 1 አምስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ አንድን ኮከብ ከሰማይ ወደ ምድር ሲወድቅ አየሁ። ኮከቡም የጥልቁ ጕድጓድ መክፈቻ ተሰጠው፤
\v 2 እርሱም ጥልቅ የሆነውን ጕድጓድ ከፈተው፤ ጢስም ከታላቅ ምድጃ እንደሚወጣ ጢስ ሆኖ ከጕድጓዱ ወጣ፤ ከጕድጓዱ በሚወጣው ጢስ ምክንያት ፀሐይና አየር ወደ ጨለማነት ተለወጡ፤
\s5
\v 3 ከጢሱም ውስጥ አንበጣዎች በምድር ላይ ወጡ፤የምድር ጊንጦችን ኅይል የመሰለ ኅይል ተሰጣቸው፤
\v 4 የምድርንም ሣር ሆነ ማናቸውንም የለመለመ ተክል ወይም ማናቸውንም ዛፍ እንዳይጎዱ ተነገራቸው። መጉዳት የነበረባቸው ግን በግንባራቸው ላይ የእግዚአብሔር ማህተም የሌለባቸውን ሰዎች ብቻ ነው።
\s5
\v 5 እነርሱንም ቢሆን ለአምስት ወር ለማሰቃየት ብቻ እንጂ የመግደል ሥልጣን አልተሰጣቸውም። የእነርሱም ስቃይ ጊንጥ ሰውን ነድፎ እንደሚሰማው ስቃይ ዐይነት ነበር።
\v 6 በእነዚያ ቀናት ሰዎች ሞትን ይፈልጋሉ፤ነገር ግን አያገኙትም። ለመሞት በብርቱ ይሻሉ፤ ነገር ግን ሞት ከእነርሱ ይሸሻል።
\s5
\v 7 አንበጦቹ ለጦርነት እንደ ተዘጋጁ ፈረሶች ነበሩ። በራሳቸውም ላይ የወርቅ አክሊል የመሰለ ነገር ነበር፤ ፊታቸውም የሰው ፊት ይመስል ነበር።
\v 8 የሴቶች ጠጕር የሚመስል ጠጕር ነበራቸው። ጥርሳቸው የአንበሳ ጥርስ ይመስል ነበር።
\v 9 የብረት ጥሩር የሚመስልጥሩር ነበራቸው፤ የክንፎቻቸውም ድምፅ ወደ ጦርነት የሚጋልቡ ብዙ ፈረሶችና ሰረገሎች የሚያሰሙትን ድምፅ ይመስል ነበር።
\s5
\v 10 እንደ ጊንጥ መንደፊያ ያለው ጅራት ነበራቸው። ሰዎችንም በጅራታቸው ባለ መንደፊያ ለአምስት ወር ለመጉዳት ስልጣን ነበራቸው።
\v 11 በእነርሱም ላይ የጥልቁ ጕድጓድ መልአክ የሆነ ንጉሥ ነበራቸው። ስሙም በዕብራይስጥ አብዶን ሲሆን በግሪክ ደግሞ አጶሊዮን ይባላል፥
\v 12 የመጀመሪያው ወዮ አልፎአል፥ልብ በል! ከዚህ በኋላ ሌላ ሁለት ጥፋቶች ይመጣሉ።
\s5
\v 13 ስድስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፥ በእግዚአብሔር ፊት ካለው በወርቅ ከተሰራው መሰዊያ ከቀንዶቹ ድምጽ ሲወጣ ሰማሁ።
\v 14 ድምፁም መለከት የያዘውን ስድስተኛውን መልአክ፣ «በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ የታሰሩትን አራቱን መላእክት ፍታቸው» አለው።
\v 15 ለዚያ ሰዓትና ለዚያ ቀን ለዚያ ወርና ለዚያ ዓመት ተዘጋጅተው የነበሩት አራት መላእክት የሰዎችን አንድ ሦስተኛ እንዲገድሉ ተፈቱ።
\s5
\v 16 የፈረሰኛው ሰራዊት ብዛት ሁለት መቶ ሚሊዮን ነበር።ቍጥራቸውንም ሰማሁ።
\v 17 ፈረሶቹና በፈረሶቹ ላይ የሚጋልቡ በራእይ ያየኋቸው በዚህ ዐይነት ነበር፥ በደረታቸው ላይ የነበረው ጥሩር እንደ እሳት ቀይ፣ እንደ ያክንት (ጥቁር ሰማያዊ)፣ እንደ ዲንም ቢጫ ነበር፥ የፈረሶቹ ራስ የአንበሳ ራስ ይመስል ነበር። ከአፋቸው እሳትና ጢስ ዲንም ይወጣ ነበር።
\s5
\v 18 በእነዚህ ሦስት መቅሰፍቶች ማለትም ከአፋቸው በወጣው እሳት፤ ጢስና ዲን የሰዎች አንድ ሦስተኛ ተገደለ።
\v 19 የፈረሶቹ ኃይል በአፋቸውና በጅራታቸው ነበር፥ ምክንያቱም ጅራታቸው እባብ ይመስላል፥ ራስ አላቸው፥ ሰውን የሚጎዱትም በእርሱ ነበር።
\s5
\v 20 በእነዚያ መቅሰፍቶች ከመሞት የተረፉት ሰዎች ከክፉ ሥራቸው ንስሓ አልገቡም፤ አጋንንትንና ከወር፣ ከብር፣ ከናስ፣ ከድንጋይና ከእንጨት የተሠሩ፣ ማየት ወይም መሄድ የማይችሉትን ጣዖታት ማምለክንም አልተዉም።
\v 21 እንዲሁም ከነፍሰ ገዳይነት ወይም ከሟርት፥ ከሴስኛነትና፥ ከሌብነት ንስሓ አልገቡም።
\s5
\c 10
\cl ምዕራፍ 10
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ ሌላ ብርቱ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ። እርሱም ደመናን የለበሰ ነበር። በራሱም ዙሪያ ቀስተ ደመና ነበር። ፊቱ እንደ ፀሐይ እግሮቹ እንደ እሳት ዐምድ ነበሩ፤
\v 2 የተከፈተ ትንሽ ጥቅል መጽሐፍ በእጁ ይዞ ነበር፤ ቀኝ እግሩን በባህር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አደረገ።
\s5
\v 3 ከዚያም እንደሚያገሳ አንበሳ በመሰለ ታላቅ ድምጽ ጮኸ፤ በጮኸ ጊዜ፣ ሰባቱም ነጎድጓዶች ድምፃቸውን አሰሙ ፤
\v 4 ሰባቱ ነድጓዶች በተናገሩ ድምፃቸውን ባሰሙ ጊዜ፣ እኔ ልጽፍ አሰብሁ። ነገር ግን «ሰባቱ ነጎድጓዶች የተናገሩትን በምስጢር ያዘው እንጂ አትጻፈው» የሚል ድምጽ ከሰማይ ሰማሁ።
\s5
\v 5 ከዚያም በባህርና በምድር ላይ ቆሞ ያየሁት መልአክ ቀኝ እጁን ወደ ሰማይ አነሣና
\v 6 ዘላለም በሚኖረው ሰማይንና በእርሱ ያሉትን፣ ምድርንና በእርስዋ ያሉትን፣ ባህርንና በርስዋ ያሉትን በፈጠረው አምላክ ስም ማለ። እንዲህም አለ፤«ከእንግዲህ ወዲህ አይዘገይም
\v 7 ነገር ግን ሰባተኛው መልአክ መለከቱን በሚነፋበት ቀን ለአገልጋዮቹ ለነቢያት በገለጠላቸው መሰረት የእግዚአብሔር ምስጢር ይፈጸማል።»
\s5
\v 8 ከሰማይ የሰማሁት ድምጽ፣«በባህርና በምድር ላይ የቆመው መልአክ በእጁ የያዘውንና የተፈታውን ጥቅል መጽሐፍ ሂድና ውሰድ» ብሎ እንደገና ሲናገረኝ ሰማሁት»።
\v 9 ወደ መልእኩም ሄጄ «ትንሹን ጥቅል መጽሐፍ ስጠኝ?» አልሁት። እርሱም «ውሰድና ብላ በሆድህም ውስጥ መራራ ይሆናል፤ በአፍህ ግን እንደ ማር ይጣፍጣል»አለኝ።
\s5
\v 10 እኔም ትንሹን ጥቅል መጽሐፍ ከመልአኩ እጅ ወስጄ በላሁት፤ በአፌ እንደ ማር ጣፈጠ፤ ከበላሁት በኋላ ግን ሆዴ መራራ ሆነ።
\v 11 ከዚህም በኋላ «ስለብዙ ሕዝቦች፤ አገራት፤ ልዩ ልዩ ቋንቋ ስለሚናገሩ ሰዎችና ሰለ ነገሥታት እንደ ገና ትንቢት መናገር አለብህ» ተብሎ ተነገረኝ።
\s5
\c 11
\cl ምዕራፍ 11
\p
\v 1 ከዚያም ለመለኪያ የሚያገለግል አንድ ረዥም ዘንግ ተሰጠኝ፤እንዲህም ተባልሁ፣«ተነሥተህ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ፥ መሰዊያውንና በዚያ የሚያመለኩትንም ቍጠር።
\v 2 ከቤተመቅደሱ ውጭ ያለውን አደባባይ ግን ተወው፤ እርሱ ለአሕዛብ የተሰጠ ስለ ሆነ አትለካው፥አሕዛብ ቅድስቲቱን ከተማ አርባ ሁለት ወራት ይረግጧታል።
\s5
\v 3 ሁለቱ ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ለ1260 ቀን ትንቢት እንዲናገሩ ሥልጣን እሰጣቸዋለሁ።»
\v 4 እነዚህም በምድር ጌታ ፊት የቆሙ ሁለቱ የወይራ ዛፎችና ሁለቱ መቅረዞች ናቸው፤
\v 5 ማንም እነርሱን ሊጎዳ ቢፈልግ እሳት ከአፋቸው ወጥቶ ጠላቶቻቸውን ይበላል፤ እነርሱን ሊጎዳ የሚፈልግ ሁሉ የሚሞተው በዚህ ዐይነት ነው፥
\s5
\v 6 እነዚህ ምስክሮች ትንቢት በሚናገሩባቸው ቀናት ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን ለመዝጋት ሥልጣን አላቸው፥ እንዲሁም ውሆችን ወደ ደም ለመለወጥና በሚፈልጉበትም ጊዜ ሁሉ በማንኛውም ዓይነት መቅሰፍት ምድርን ለመምታት ሥልጣን አላቸው፡
\v 7 ምስክርነታቸውን በጨረሱ ጊዜ ከጥልቁ ጉድጛድ የሚወጣው አውሬ ከእነርሱ ጋር ይዋጋል፤ ያሸንፋቸዋል ይገድላቸውማል።
\s5
\v 8 ሬሳቸውም በምሳሌያዊ አጠራር ሰዶም ወይም ግብጽ ተብላ በምትጠራው በታላቂቱ ከተማ አደባባይ ይጋደማል፤ ከተማይቱም የእነርሱ ጌታ የተሰቀለባት ናት፤
\v 9 ከልዩ ልዩ ወገን፥ ነገድ፥ ከልዩ ልዩ ቋንቋና ሕዝብ የሆኑ ሰዎች ሶስት ቀን ተኩል ሬሳቸውን ይመለከታሉ፥ ሬሳቸውም እንዳይቀበር ይከለክላሉ።
\s5
\v 10 ሁለቱ ነቢያት የምድርን ሰዎች ሁሉ አስጨንቀው ስለ ነበር፣ በእነርሱ ሞት በምድር የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ደስ ይላቸዋል፤ በደስታም በዓል ያደርጋሉ፤ ስጦታም ይለዋወጣሉ።
\v 11 ነገር ግን ሦስት ቀን ተኩል ካለፈ በኋላ፣ የሕይወት እስትንፋስ ከእግዚአብሔር መጥቶ ወደ ሬሳዎቹ ይገባል፤ በእግራቸውም ይቆማሉ፤ የሚመለከቷቸውም ሰዎች ታላቅ ፍርሃት ይወድቅባቸዋል።
\v 12 ከዚህ በኋላ ሁለቱ ነቢያት፣ «ወደዚህ ውጡ» የሚል ታላቅ ድምጽ ከሰማይ ሰሙ፤ ጠላቶቻቸውም እየተመለከቷቸው በደመና ወደ ሰማይ ወጡ።
\s5
\v 13 በዚያኑ ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ የከተማይቱም አንድ ዐሥረኛ ወደመ። በምድር መናወጥም ምክንያት ሰባት ሺህ ሰዎች ሞቱ፤ ከሞት የተረፉትም እጅግ ፈሩ፤ለሰማይም አምላክ ክብርን ሰጡ።
\v 14 ሁለተኛው ወዮ አልፎአል፤ልብ በል! ሦስተኛው ወዮ ፈጥኖ ይመጣል።
\s5
\v 15 ሰባተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤በሰማይም«የዓለም መንግሥት የጌታ አምላካችንና የእርሱ ክርስቶስ ሆናለች፤ እርሱም ለዘላለም ይነግሣል» የሚል ታላቅ ድምጽ ሰማሁ።
\s5
\v 16 በእግዚአብሔርም ፊት በዙፋኖቻቸው ላይ የተቀመጡት ሃያ አራቱም ሽማግሌዎች በግምባራቸው ተደፍተው ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤
\v 17 እነርሱም እንዲህ አሉ፣«ያለህና የነበርህ፣ ሁሉን የምትችል፣ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ትልቁን ሥልጣንህን በእጅህ አድርገህ ስለ ነገሥህ እናመሰግንሃለን።
\s5
\v 18 አሕዛብ ተቆጡ፤ ነገር ግን የአንተም ቁጣ መጣ ።በሙታን ላይ የምትፈርድበት ዘመንም መጣ፤ለአገልጋዮችህ፣ ለነቢያት፣ ለቅዱሳን፣ ስምህንም ለሚያከብሩት ለታናናሾችና ለታላላቆች ሽልማታቸውን የምትሰጥበት ጊዜ እንዲሁም ምድርን ያጠፏትን የምታጠፋበት ጊዜ ደረሰ።»
\s5
\v 19 በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተከፈተ፤የእርሱም የቃል ኪዳን ታቦት በቤተ መቅደሱ ውስጥ ታየ። መብረቅ የመብረቅ ድምጽ፣ነጎድጓድም፣የምድር መናወጥና ታላቅም ማዕበል ሆነ።
\s5
\c 12
\cl ምዕራፍ 12
\p
\v 1 በሰማይም ታላቅ ምልክት ታየ ፤ ፀሐይን የለበሰችና ጨረቃን ከእግሯ በታች ያደረገች፣ ዐሥራ ሁለት ከዋክብት ያሉት አክሊልም በራስዋ ላይ የደፋች አንዲት ሴት ታየች።
\v 2 እርስዋም ነፍሰ ጡር ነበረች፤ ምጥ ይዟትም ተጨንቃ ትጮህ ነበር፥
\s5
\v 3 እንዲሁም ሌላ ምልክት በሰማይ ታየ፤እነሆ፤ሰባት ራሶችና ዐሥር ቀንዶች የነበሩት፤በራሶቹም ላይ ሰባት አክሊል የደፋ ትልቅ ቀይ ዘንዶ ታየ።
\v 4 በጅራቱ የኮከቦችን አንድ ሦስተኛ ከሰማይ ስቦ ወደ ምድር ጣለ፤ዘንዶውም ሴቲቱ በምትወልድበት ጊዜ ልጅዋን ለመዋጥ አስቦ ልትወልድ ወደ ተቃረበችው ሴት ፊት ቆመ።
\s5
\v 5 ሴቲቱም ሕዝቦችን ሁሉ በብረት በትር የሚገዛ ወንድ ልጅ ወለደች። ልጅዋ ግን ወደ እግዚአብሔርና ወደ እግዚአብሔር ዙፋን ተወሰደ፤
\v 6 ሴቲቱም ወደ ምድረበዳ ሸሽታ ሄደች፤ በዚያም እግዚአብሔር ለ1260 ቀን በክብካቤ ተይዛ እንድትጠበቅ አደረጋት።
\s5
\v 7 በሰማይም ጦርነት ሆነ። ሚካኤልና መላእክቱ ከዘንዶው ጋር ተዋጉ፤ዘንዶውና መላእክቱ መልሰው ተዋጓቸው።
\v 8 ነገር ግን ዘንዶው የማሸነፍ ዐቅም አልነበረውም፤ከዚያም ወዲያ እርሱና መላእክቱ በሰማይ የነበራቸውን ስፍራ አጡ።
\v 9 ታላቁም ዘንዶ ወደ ምድር ተጣለ፤ እርሱም ሰዎችን ሁሉ የሚያስተው ዲያቢሎስ ወይም ሰይጣን ተብሎ የሚጠራው የቀደመው እባብ ነው።እርሱ ወደ ምድር ተጣለ፤ የእርሱም መላእክት ከእርሱ ጋር አብረው ተጣሉ።
\s5
\v 10 ከዚህ በኋላ ታላቅ ድምፅ ከሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤«አሁን ማዳንና ኃይል መንግሥትም የአምላካችን ሆኖአል፤ሥልጣንም የእርሱ ክርስቶስ ሆኖአል።ምክንያቱም ወንድሞቻችንን በአምላካችን ፊት ቀንና ለሊት ሲከሳቸው የነበረ የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአል።
\s5
\v 11 እነርሱም በበጉ ደምና በተናገሩት የምስክርነት ቃል ድል ነሡት፤ ለሕይወታቸው ሳይሳሱ ራሳቸውን ለሞት አሳልፈው ሰጥተዋልና።
\v 12 ስለዚህ ሰማይና በውስጣቸው የምትኖሩ ሁሉ ደስ ይበላችሁ፤ ምድርና ባህር ግን ወዮላችሁ፤ ምክንያቱም ጥቂት ጊዜ እንደ ቀረው ዐውቆ ዲያቢሎስ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዷል።
\s5
\v 13 ዘንዶው ወደ ምድር እንደተጣለ ባስተዋለ ጊዜ፤ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት፤
\v 14 ሴቲቱ ከእባቡ ፊት ርቃ ለዘመን፣ ለዘመናትና ለዘመንም እኩሌታ በክብካቤ ተጠብቃ ወደ ምትኖርበት በምድረ በዳ ወደ ተዘጋጀላት ስፍራ በርራ እንድትሄድ ሁለት የታላቅ ንስር ክንፎች ተሰጧት።
\s5
\v 15 እባቡ የወንዝ ውሃ የሚያህል ውሃ ከአፉ ተፍቶ ሴቲቱ በጎርፍ እንድትወሰድ ብሎ በስተ ኋላዋ አፈሰሰ።
\v 16 ነገር ግን ምድር አፍዋን ከፍታ ዘንዶው በአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ በመዋጥ ረዳቻት።
\v 17 ከዚያም ዘንዶው በሴቲቱ ላይ ተቆጥቶ ከትሩፋን ዝርያዎችዋ ጋር ሊዋጋ ሄደ። እነርሱም የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁና ስለ ኢየሱስ በታማኝነት የሚመሰክሩት ናቸው።
\v 18 ዘንዶውም በባህር ዳር ባለው አሸዋ ላይ ቆመ።
\s5
\c 13
\cl ምዕራፍ 13
\p
\v 1 ከዚያም አንድ አውሬ ከባህር ሲወጣ አየሁ። እርሱም ዐስር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት። በቀንዶቹም ላይ አስር አክሊሎች ነበሩ፤ በራሶቹም ላይ እግዚአብሔርን የሚሰድብ ስሞች ነበሩት።
\v 2 ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፤ እግሮቹ የድብ እግሮች፤ አፉ የአንበሳ አፍ ይመስል ነበር። ይገዛም ዘንድ ዘንዶው የራሱን ኅይልና የራሱን ዙፋን ትልቅም ስልጣን ለአውሬው ሰጠው።
\s5
\v 3 ከአውሬው ራሶቹ አንዱ ለሞት የሚያበቃ ቁስል እንደነበረው ሆኖ አየሁት፤ ነገር ግን ለሞት የሚያደርስው ቁስል ዳነ፤በዚህም ምክንያት ዓለም በሙሉ በመደነቅ አውሬውን ተከተለ።
\v 4 አውሬውም ስልጣኑን በመስጠቱ ሁሉም ለዘንዶው ሰገዱለት «አውሬውን ማን ይመስለዋል? ከእርሱስ ጋር ማን ሊዋጋ ይችላል?» እያሉ ለአውሬው ሰገዱለት።
\s5
\v 5 አውሬውም የትዕቢትና የስድብ ቃል የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፤ ለአርባ ሁለት ወራትም ስልጣኑን እንዲያሳይ ተፈቀደለት።
\v 6 አውሬው አፉን ከፍቶ እግዚአብሔርን፤ የእግዚአብሔርን ስም፤ መኖሪያውንና በሰማይ የሚኖሩትን መሳደብ ጀምረ።
\s5
\v 7 አውሬው ቅዱሳንን እንዲዋጋ ና፤ ድል እንዲነሳቸውም ስልጣን ተሰጠው። በነገድና በወገን በቃንቃና በህዝብ ሁሉ ላይ ስልጣን ተስጠው።
\v 8 ዓለም ሲፈጠር ጀምሮ ስሞቻቸው በታረደው በግ የህይወት መጽሀፍ ያልተጻፈ በዓለም ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁ ሉ ለአውሬው ይሰግዳሉ።
\s5
\v 9 የሚሰማ ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ።
\v 10 «የሚማረክ ማንም ቢኖር ወደ ምርኮ ይሄዳል፤ በሰይፍ የሚገደል ማንም ቢኖር በሰይፍ ይገደላል» እንግዲህ የቅዱሳን ትዕግስትና እምነት የሚታየው በዚህ ጊዜ ነው።
\s5
\v 11 ከዚህም በኃላ ሌላ አውሬ ደግሞ ከምድር ሲውጣ አየሁ፤ የበግ ቀንዶች የሚመስሉ ሁለት ቀንዶች ነበሩት አነጋግሩም እንደ ዘንዶው ነበር።
\v 12 የመጀመሪያውን አውሬ ስልጣን ሁሉ በመጀመሪያው አውሬ ፊት ሆኖ ይሰራበት ነበር፤ ምድርና በእርስዋ ላይ የሚኖሩት ሁሉ ለአውሬው እንዲሰግዱለት ያደርጋል፤ ይህም አውሬ ያ ለሞት የሚያድርስ ቁስል የዳነለት የመጀመሪያው አውሬ ነው።
\s5
\v 13 እርሱም በሰዎች ፊት እሳትን ከሰማይ እስከማውረድ ድረስ ታላላቅ ምልክቶችን ያደርግ ነበር፤
\v 14 እንዲያደርግ በተፈቀደለት ተዓምራት በሰይፍ ቁስሎ የዳነውን የአውሬውን ምስል እንዲሰሩ በማዘዝ በምድር ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያስት ነበር።
\s5
\v 15 እርሱም ምስሉ መናገር እንካ እስከሚችል ድረስ እስትንፋስ ለመስጠትና ለአውሬው የማይስግዱትን መግደል ይችል ዘንድ ለማድረግ ስልጣን ተሰጠው።
\v 16 እርሱም ታናናሾችም ሆኑ ታላላቆች፤ ሀብታሞችም ሆኑ ድኾች ጌቶችም ሆኑ አገልጋዮች ሁሉም በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ላይ ምልክት እንዲያደርጉ አስገደዳቸው።
\v 17 የአውሬው ስም የሆነው ምልክት ወይም የስሙ ቁጥር የሌለው ማንም ሰው መግዛትም ሆን መሸጥ አይችልም ነበር።
\s5
\v 18 ይህ ጥበብን የሚጠይቅ ነው።የሚያስተውል የአውሬውን ቁጥር ያስላው፤ ቁጥሩም የሰው ቁጥር ነው፤ የውሬውም ቁጥር 666 ነው፤
\s5
\c 14
\cl ምዕራፍ 14
\p
\v 1 አየሁም እነሆ በጉ በጽዮን ተራራ በፊቴ ቆሞ ነበር። ከእርሱ ጋር የእርሱ ስምና የአባቱ ስም በግንባራቸው ላይ የተጻፈባቸው አንድ መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።
\v 2 በሰማይ እንደ ብዙ ውኃ ድምጽና ና እንደታላቅ ነጎድጋድ ድምጽ የመሰለ ድምጽ ሰማሁ፤ የሰማሁትም ድምጽ በገና ደርዳሪዎች በገና እየደረደሩ የሚያሰሙትን ድምጽ ይመስል ነበር።
\s5
\v 3 እነርሱም በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች በሽማግሌዎችም ፊት አዲስ መዝሙር ዘመሩ። ይህንም መዝሙር ከምድር ከተዋጁት ከአንድ መቶ አርባ አራት ሺህ በቀር ማንም ሊማረው አልቻለም።
\v 4 እነርሱም ራሳቸውን ከሴቶች ጋር ካላረከሱት ናቸው፤ ራሳቸውንም በግብረ ስጋ ግንኙነት ካለማርከስ ጠብቀዋል። እነርሱ ናቸው በጉ ወደሚሄድበት ሁሉ የሚከተሉት እነዚህ ናቸው፤ እነርሱ ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኩራት ለመሆን ከሰዎች መካከል የተዋጁ ናቸው።
\v 5 በአንደበታቸውም ሀሰት ተናግረው አያውቁም። ነቀፋም የሌለባቸው ናቸው።
\s5
\v 6 በምድር ላይ ለሚኖሩ ለህዝብ፤ ለነገድ፤ ለቃንቃና ለወገን ሁሉ ለማብሰር ዘላለማዊውን የምስራች ቃል የያዘ ሌላ መልዓክ በሰማይ መካከል ሲበር አየሁ
\v 7 እርሱም በታላቅ ድምጽ «እግዚአብሄርን ፍሩ፤ አክብሩትም። ምክንያቱም የእርሱ የፍርድ ሰዓት ደርሳል፤ ሰማይን፤ ምድርን፤ ባህርንና የውሃ ምንጮችን የፈጠረን አምላክ አምልኩ» አለ
\s5
\v 8 ሌላም ሁለተኛ መልአክ «የዝሙትዋ ፍትወት የሆነውን የሚያሰክር የወይን ጠጅ ለህዝቦች ሁሉ ያጠጣች ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፤ ወደቀች» እያለ የመጀመሪያውን መልዓክ ተከተለው
\s5
\v 9 ሌላ ሶስተኛ መለዓክ በታላቅ ድምጽ እንዲህ እያለ ተከተላቸው «ለአውሬውና ለምስሉ ቢሰግዱ ምልክቱን በግምባሩ ወይም በእጁ ቢያደርግ፤
\v 10 የእግዚአብሔርን የቁጣ የወይን ጠጅ ይጠጣል፤ ይህም የወይን ጠጅ ሳይበረዝ በቁጣው ጽዋ የተዘጋጀ ነው፤ ፅሚጠጣውም ሰው በቅዱሳን መላዕክት ፊትና በበጉ ፊት በእሳትና በዲን ይሰቃያል፤
\s5
\v 11 የስቃያቸውም ጢስ ከዘላለም እስከ ዘላለም ወደ ላይ ይወጣል፤ ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግዱ የስሙንም ምልክት ያደረጉ ሁሉ ቀንና ለሊት ዕረፍት የላቸውም።
\v 12 የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ የሚጠብቁና በኢየሱስ የሚያምኑማመኑ ቅዱሳን፤ ትዕግስታቸው የሚታየው እዚህ ላይ ነው።
\s5
\v 13 ከሰማይም እንዲህ የሚል ድምጽ ሰማሁ «ይህን ጻፍ ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ ሆነው የሚሞቱ የተባረኩ ናቸው» መንፈስም አዎ ስራቸው ስለሚከተላቸው ከድካማቸው ያርፋሉ» ይላል
\s5
\v 14 አየሁም እነሆ ነጭ ደመና ነበር በደመናውም ላይ የሰውን ልጅ የሚመስል ተቀምጦ ነበር። በራሱም ላይ የወርቅ አክሊል አድርጎአል፤ በእጁም ስለታም ማጭድ ይዞአል።
\v 15 ከዚህም በኃላ ሌላ መልአክ ከመቅደሱ ወጣ በደመና ላይ የተቀመጠውን በታላቅ ድምጽ «የምድር መከር ደርሶአል የአጨዳ ሰዓትም ቀርቦአል፤ ስለዚህ ማጭድህን ስደድ» አለው።
\v 16 በደመናው ላይ የተቀመጠውም ማጭዱን ወደ ምድር ሰደደው ምድርም ታጨደች።
\s5
\v 17 ሌላ መልዓክ ከሰማይ ባለው መቅደስ ወጣ፤ እርሱም ስለታም ማጭድ ይዞ ነበር።
\v 18 በእሳትም ላይ ስልጣን ያለው ሌላ መልዓክ ከመሰዊያው አጠገብ ወጣና ስለታም ማጭድ የያዘውን መልዓክ በታላቅ ድምጽ «የዘለላዎቹ ፍሬዎች ስለበሰሉ የወይን ዘለላዎችን ሁሉ ከምድር ወይን ቁረጥ» አለው።
\s5
\v 19 መልዓኩም ማጭዱን ወደ ምድር ሰደደው፤ የምድርንም ወይን ዘለላ ቆረጠ፤ ወደ ታላቁ ወደ እግዚአብሔር የቁጣ ወይን መጭመቂያ ውስጥ ጣለው።
\v 20 ከከተማው ውጭ ባለው በወይን መጥመቂያም ተጨመቀ ከመጭመቂያውም እስከ ፈረስ ልጋም ወደ ላይ ከፍ ያለና 300 ኪሎ ሜትር የሚደርስ ደም ወጥቶ ፈሰሰ።
\s5
\c 15
\cl ምዕራፍ 15
\p
\v 1 ከዚህም በኃላ ታላቅና ድንቅ ምልክት በሰማይ አየሁ፤ የእግዚአብሔር ቁጣ የሚፈጽምባቸው የመጨረሻዎቹን ሰባት መቅሰፍት የያዙትን ሰባት መላዕክት አየሁ
\s5
\v 2 እኔም እሳት የተቀላቀለበት የሚመስል የመስተዋት ባህር አየሁ፤ አውሬውንና የአውሬውን ምስል የስሙንም ቁጥር ድል የነሱትን በባህሩ አጥገብ ቆመው ነበር። እግዚአብሔር የሰጣቸውንም በገና ይዘው ነበር።
\s5
\v 3 እነርሱም የእግዚአብሔር አገልጋይ የሙሴን መዝሙርና የበጉን መዝሙር እንዲህ እያሉ ይዘምሩ ነበር «ሁሉን የምትችል ጌታ አምላክ ሆይ ስራህ ታላቅና አስደናቂ ነው። የእዝቦች ንጉስ ሆይ መንገድህ ትክክልና እውነት ነው።
\v 4 ጌታ ሆይ አንተን የማይፈራና ስምህንም የማያከብር ማን ነው? ምክንያቱም አንተ ብቻ ቅዱስ ነህ የጽድቅ ስራህ ስለተገለጠ ሕዝቦች ሁሉ መጥተው በፊትህ ይሰግዳሉ።»
\s5
\v 5 ከዚህም በኃላ አየሁ እነሆ የምስክር ድንካን የሆንው ቅድስተ ቅዱሳን በሰማይ ተከፈተ።
\v 6 ከቅድስተ ቅዱሳንም ሰባቱን መቅሰፍቶች የያዙት ሰባት መላዕክት ወጡ፤ የሚያንጸባርቅ ነጭ ልብስ ለብሰው ነበር። ደረታቸውንም በወርቅ መታጥቂያ ታጥቀው ነበር።
\s5
\v 7 ከአራቱ ህያዋን ፍጡራን አንዱ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሚኖረው አምላክ ቁጣ የተሞሉትን ሰባት የውርቅ ጽዋዎች ለሰባቱ መላዕክት ሰጣቸው።
\v 8 ቅድስተ ቅዱሳኑም ከእግዚአብሔር ክብርና ኃይል የተነሳ በጢስ ተሞላ፤ ሰባቱ መላዕክት የያዙእቸው ስባት መቅሰፍቶች እስኪፈጽሙ ድረስ ማንም ወደ ቅዱሰተ ቅዱሳኑ መገባት አልቻሉም።
\s5
\c 16
\cl ምዕራፍ 16
\p
\v 1 ሰባቱን መላእክት፣ “ሂዱና ሰባቱን የእግዚአብሔርን ቁጣ ጽዋዎች ምድር ላይ አፍስሱ” የሚል ታላቅ ድምፅ ከመቅደሱ ሲወጣ ሰማሁ።
\s5
\v 2 የመጀመሪያው መልአክ ጽዋውን ምድር ላይ አፈሰሰ፤ የአውሬው ምልክት ባላቸውና ለምስሉ በሰገዱት አስከፊና የሚያሠቃይ ቁስል ወጣባቸው።
\s5
\v 3 ሁለተኛው መልአክ ጽዋውን ባሕር ላይ አፈሰሰ፤ ባሕሩ እንደ ሞተ ሰው ደም ሆነ፤ ባሕር ውስጥ የነበረ ሕያው ፍጡር ሁሉ ሞተ።
\s5
\v 4 ሦስተኛው መልአክ ጽዋውን ወንዞችና የውሃ ምንጮች ላይ አፈሰሰ እነርሱም ደም ሆኑ።
\v 5 የውሃውም መልአክ፣ “ያለህና የነበርህ ቅዱስ ጌታ እንዲህ ስለ ፈረድህ ትክክል ነህ፣
\v 6 ምክንያቱም የቅዱሳንህና የነበያትን ደም ስላፈሰሱ፣ ደም አጠጣሃቸው፤ ይህም የሚገባቸው ነው” ሲል ሰማሁ።
\v 7 ከመሠዊያውም፣ “አዎን፣ ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ፍርድህ እውነትና ትክክል ነው” የሚል ድምፅ ወጣ።
\s5
\v 8 አራተኛው መልአክ ጽዋውን ፀሐይ ላይ አፈሰሰ፤ ለእርሷም ሰዎችን በግለትዋ የማቃጠል ሥልጣን ተሰጣት።
\v 9 ሰዎች በከባድ ሙቀቷ ተቃጠሉ፤ በእነዚህ መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔር ስም ሰደቡ። ንሰሐ አልገቡም፤ ክብርም አልሰጡትም።
\s5
\v 10 አምስተኛው መልአክ ጽዋውን በአውሬው ዙፋን ላይ አፈሰሰ፤ የአውሬውም መንግሥት በጨለማ ተዋጠ። ከሥቃያቸውም የተነሣ ምላሳቸውን ያኝኩ ነበር።
\v 11 ከሥቃያቸውና ከደረሰባቸው ቁስል የተነሣ የሰማይን አምላክ ተሳደቡ፤ ያም ሆኖ ግን ስላደረጉት ክፉ ሥራ ንስሐ ለመግባት ፈቃደኞች አልሆኑም።
\s5
\v 12 ስድስተኛው መልአክ ጽዋውን ታላቁ ወንዝ ኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከምሥራቅ ለመጡ ነገሥታት መንገድ ለማዘጋጀት የወንዙ ውሃ ደረቀ።
\v 13 ከዘንዶው አፍና ከአውሬው አፍ እንዲሁም ከሐስተኛው ነቢይ አፍ እንቁራሪት የሚመስሉ ሦስት ርኩሳን መናፍስት ስወጡ አየሁ።
\v 14 እነዚህ ተአምራዊ ምልክቶች የሚያደርጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸው። ሁሉን በሚገዛ አምላክ ታላቅ ቀን ለሚደረገው ጦርነት የዓለም መንግሥታችን ሁሉ ለመሰብሰብ ወደ ወጥተው ሄዱ።
\s5
\v 15 “ልብ በሉ! እኔ እንደ ሌባ እመጣለሁ! ራቁቱን እንዳይገኝና ሰዎችም ሐፍረቱን እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ የተባረከ ነው።”
\v 16 መናፍስቱ ነገሥታቱን ሰብስበው በዕብራይስጥ አርማጌደን ወደሚባል ቦታ አመጧቸው።
\s5
\v 17 ሰባተኛው መልአክ ጽዋውን አየር ላይ አፈሰሰ። በዚያን ጊዜ፣ “ተፈጸመ!” የሚል ታላቅ ድምፅ ከመቅደሱና ከዙፋኑ ወጣ።
\v 18 ከዚያም የመብረቅ ብልጥታ፣ ሁካታ ነጎድጓድና ከባድ የመሬት መናወጥ ሆነ፤ የዚያ ዓይነት የምድር ነውጥ የሰው ልጅ ምድር ላይ መኖር ከጀመረ አንሥቶ ሆኖ የማያውቅ እጅግ ከባድ ነበር።
\v 19 ታላቂቷ ከተማ ለሦስት ተከፈለች፤ የሕዝቦች ከተሞችም ተደመሰሱ። እግዚአብሔር ታላቂቱ ባቢሎንን አስታወሰ፤ ለዚያች ከተማም የብርቱ ቁጣው ወይን ጠጅ የሞላበት ጽዋ እንድትጠጣ ሰጣት።
\s5
\v 20 ደሴቶች ሁሉ ጠፋ፤ ተራሮችም በቦታቸው አልተገኙም።
\v 21 አንድ ታለንት የሚመዝን የበረዶ ድንጋይ ከሰማይ ወርዶ ሰዎች ላይ ወደቀ፤ መቅሠፍቱ እጅግ አሰቃቂ ከመሆኑ የተነሣ ሰዎች ስለ በረዶው ድንጋይ እግዚአብሔርን ተራገሙ።
\s5
\c 17
\cl ምዕራፍ 17
\p
\v 1 ሰባቱን ጽዋዎች ይዘው ከነበሩት ሰባት መላእክት አንዱ ወደ እኔ መጥቶ እንዲህ አለን፤ “በብዙ ውሆች ላይ የተቀመጠችውን ታላቂቱ አመንዝራ የፍርድ ቅጣት አሳይሃለሁ፤
\v 2 የምድር ነገሥታት ከእርሷ ጋር አመንዝረሃል፤ ከዝሙቷ ወይን ጠጅ የምድር ነዋሪዎች ሰክረዋል።”
\s5
\v 3 መልአኩ በመንፈስ ወደ በረሐ ወስዶኝ፣ የስድብ ስሞች በሞሉበት ቀይ አውሬ ላይ የተቀመጠች ሴት አየሁ። አወሬው ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶች ነበሩት።
\v 4 ሴትዬዋ ሐምራዊና ቀይ ልብስ ለብሳ፣ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች እንዲሁም በዕንቁዎች አጊጣ ነበር። በእዛም ጸያፍ ነገሮችና የዝሙቷ ርኩሰት የሞላበት የወርቅ ጽዋ ይዛ ነበር።
\v 5 ግንባሯም ላይ፣ “ታላቂቱ ባቢሎን፣ የአመንዝሮችና የምድር ጸያፍ ነገሮች እናት” የሚል ምስጢራዊ ትርጉም ያለው ስም ተጽፎ ነበር።
\s5
\v 6 ሴትዬዋ በቅዱሳንና በኢየሱስ ሰማዕታት ደም ሰክራ አየሁ። ባየኋት ጊዜ በጣም ተደነቅሁ።
\v 7 መልአኩ ግን፣ “ለምን ትደነቃለህ? የሴትዮዋንና የተሸከማትን አውሬ (ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶች ያሉትን አውሬ) ምንነት እነግርሃለሁ።
\s5
\v 8 ያየኸው አውሬ ቀድሞ ነበረ፤ አሁን የለም፤ ሆኖም በኃላ ከጥልቁ ጉድጓድ ይመጣል። ከዚያም ወደ ጥፋት ይሄዳል። ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ሰማቸው በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፈ በምድር የሚኖሩ ሰዎች ቀድሞ የነበረውን፣ አሁን የሌለውን በኃላ ግን የሚመጣውን አውሬ ሲያዩ ይደነቃሉ።
\s5
\v 9 ይህ አስተዋይ አእምሮን የሚጠይቅ ጉዳይ ነው። ሰባቱ ራሶች ሴትዬዋ የተቀመጠችባቸው ሰባት ኮረብቶች ናቸው።
\v 10 እነርሱም ሰባት ነገሥታት ናቸው። አምስቱ ወድቀዋል፤ አንድሱ አሁንም አለ፤ ሌለው ገና አልመጣም፤ በሚመጣበት ጊዜ ግን ለአጭር ጊዜ መቆየት ይገባዋል።
\s5
\v 11 ቀድሞ የነበረው አሁን ግን የሌለው አውሬ ራሱ ስምንተኛው ንጉሥ ነው ሆኖም፣ ከሰባቱ አንዱም ነው ወደ ጥፋትም ይሄዳል።
\s5
\v 12 ያዩኋቸው አሥር ቀንዶች ገና መንግሥት ያልተቀበሉ አሥር ነገሥታት ናቸው፤ ነገር ግን ለአንድ ሰዓት ያህል ከአውሬው ጋር እንዲነግሡ ሥልጣን ይቀበላሉ።
\v 13 እነዚህ ነገሥታት ተመሳሳይ ሐሳብ አላቸው፤ ኅይልና ሥልጣናቸውን ሁሉ ለአውሬው ያስረክባሉ።
\v 14 በጉን ይዋጋሉ። ይሁን እንጂ፣ በጉ የጌቶች ጌታ የነገሥታት ንጉሥ በመሆኑ እርሱ ያሸንፋቸዋል የተጠሩት፣ የተመረጡትና ታማኝ የሆኑት ከእርሱ ጋር ድል ይነሣሉ።”
\s5
\v 15 መልአኩም፣ “አመንዝራዋ ተቀመጣባቸው የነበሩት ያየሃቸው ውሆች ሕዝቦችና ሰዎች፣ ወገኖችና ቋንቋዎች ናቸው” አለኝ።
\s5
\v 16 ያየሃቸው አሥር ቀንዶች ከአውሬው ጋር አንድ ላይ ሆነው አመንዝራዋን ይጠላሉ። ያጠፏታል፤ ራቁትዋን ያስቀሯታል፤ ሥጋዋን ይበላሉ፤ ጨርሶ እስክትጠፋ በእሳት ያቃጥሏታል።
\v 17 ምክንያቱም፣ የእግዚአብሔር ቃል እስኪፈጸም ድረስ ሥልጣናቸውን ለአውሬው ለመስጠት በመስማማት ዕቅዱን እንዲፈጽሙ እግዚአብሔር ይህን ሐሳብ በልባቸው ውስጥ አኑሮአል።
\s5
\v 18 ያይየሃት ሴት በምድር ነገሥታት ላይ የምትገባ ታላቂቱ ከተማ ናት።”
\s5
\c 18
\cl ምዕራፍ 17
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ። ታላቅ ሥልጣንም ነበረው፤ ምድርም በክብሩ አበራች።
\v 2 በታላቅ ድምፅም ጮኾ እንደኢህ አለ፤ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፣ ወደቀች! የአጋንንት መኖሪያ፣ የርኩሳን መናፍስት ሁሉ ማደሪያ፣ የማንኛውም ርኩስና ጠያፍ ወፍ መጠጊያ ሆነች
\v 3 ሕዝቦች ሁሉ ቁጣ በሚያመጣበት የዝሙቷ ወይን ጠጅ ሰክረዋል። የምድር ነገሥታት ከእርሷ ጋር አመንዝረዋል። የምድር ነጋዴዎች በምቾት ኑሮዋ በልጽገዋል።”
\s5
\v 4 ሌላ ድምጽም ከሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሕዝቤ ሆይ፣ በኃጢአትዋ እንዳትካፈሉ የማመጣበትንም መቅሠፍት እንዳትቀበሉ ከእርሷ ውጡ።
\v 5 ኃጢአቷ እስከ ሰማይ ተከምሯል እግዚአብሔር ክፉ ሥራዋን አስታውሷል።
\v 6 በሰጠችው መጠን ስጧት፤ ባደረገችው መጠን ዕጥፍ አድርጉባት እርሷ በቀካቀከችው ጽዋ መጠን፣ ዕጥፍ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት።
\s5
\v 7 እርሷ ራስዋን እንዳከበረችውና በምቾት በኖረችው መጠን፣ የዚያኑ ያህል ስቃይና ሐዘን ስጧት እርሷ በልቧ ‘እንደ ንግሥት ተቀምጫለሁ መበለትም አይደለሁም ሀዘንም አይደርስብኝም’ ብላለች።
\v 8 ስለዚህ፣ መቅሠፍቶችዋ በእብንድ ቀን ይደርሱባታል፣ ሞት፣ ሐዘንና ረሐብ ይመጡባታል። በእሳት ትቃጠላለች፤ እርሷ ላይ የሚፈርድ ጌታ እግዚአብሔር ብርቱ ነው”
\s5
\v 9 ከእርሷ ጋር ያመነዘሩና ቅጥ ያጣ ሕይወት የኖሩ፣ የቃጠሎዋ ጭስ ሲወጣ ሲያዩ ስለ እርሷ እየጮኹ ያለቅሳሉ።
\v 10 ሥቃይዋንም በመፍራት በሩቅ ቆመው፣ “ታላቂቱ ከተማ፣ አንቺ ብርቱ ከተማ በአንድ ሰዓት ውስጥ ቅጣትሽ መጥቷልና ወዮልሽ ወዮልሽ” ይላሉ።
\s5
\v 11 ከእንግዲህ ሸቀጧን የሚገዛ ስለማይኖር የምድር ነጋዴዎች ለእርሷ ያለቅሳሉ፤ ያዝኑላታል፤
\v 12 ሸቀጦችዋ ወርቅ፣ ብር፣ የከበረ ድንጋይ፣ ዕንቁ፣ ቀጭን ልብስ፣ ሐምራዊ ጨርቅ፣ ሐር ጨርቅ፣ ቀይ ጨርቅ፣ ማንኛውም ዓይነት ጣፋጭ ሽታ ያለው እንጨት፣ ማንኛውም ከዝሆን ጥርስ የተሠራ ዕቃ፣ ማንኛውም ከከበረ ድንጋይ የተሠራ ዕቃ፣ ነሐስ፣ ብረት፣ እብነ በረድ
\v 13 ቀረፋ፣ ቅመም፣ የሚሸር እንጨት፣ ከርቤ፣ ዕጣን፣ ወይን ጠጅ፣ ዘይት፣ንጹሕ ዱቄት፣ ስንዴ፣ ከብቶች፣ በጎች፣ ፈረሶችና ሰረገሎች ባሪያዎችና የሰዎች ነፍሶች ናቸው።
\s5
\v 14 አጥብቀሽ የተመኘሻቸው ነገሮች ከአንቺ አምልጠዋል። ምቾትና ውበትሽ ጠፍተዋል ከእንግዲህም አይገኙም።
\s5
\v 15 በእርሷ የበለጸጉ እነዚህን ዕቃዎች የሚነግዱ ሰዎች ሥቃይዋን በመፍራት ከእርሷ ርቀው በመቆም በታላቅ ድምፅ ያለቅሳሉ
\v 16 እንዲህም ይላሉ “ቀጭን ልብስ፣ ሐምራዊና ቀይ ልብስ ትለብስ ለነበች፤ በመርቅ፣ በከበረ ድንጋይና በዕንቁ ታጌጥ ለነበረች ታላቂቱ ከተማ ወዮ ወዮ!”
\v 17 በእብንድ ሰዓት ያ ሀብት ሁሉ ጠፍቷል። የመርከብ አዛዦች ሁሉ፣ በመርከብ የሚጓዙ ሰዎች ሁሉ፣ መርከበኞችና በባሕር ላይ የሚሠሩ ሁሉ ርቀው ቆሙ።
\s5
\v 18 ያቀጠሎዋን ጭስ ሲመለከቱ፣ “ ታላቂቱን ከተማ የሚመስላት ማነው?” እያሉ ጮኹ።
\v 19 በራሳቸውም ላይ ዐመጽ ነስንሰው እያለቀሱና እያዘኑ፣ መርከቦች ያሏቸውና በእርሷ ሀብት የበለጸጉ ሁሉ ታላቂቱ ከተማ በአንድ ሰዓት ስለ ወደመች ወዮላት ወዮላት” አሉ።
\v 20 “ ሰማይ ሆይ ደስ ይበልህ፤ እግዚአብሔር ስለ እናንተ እርሷ ላይ ፈርዷልና እናንት ቅዱሳን፣ ሐዋርያትና ነቢያት ደስ ይበላችሁ!”
\s5
\v 21 ከዚያም አንድ ብርቱ መልአክ ታላቅ የወፍጮ ድንጋይ የሚመስልን ድንጋይ እንዲህ በማለት ወደ ባሕር ወረወሬ፣ “ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን በዚህ ሁኔታ በኅይል ተገፍታ ወደ ባሕር ትጣላለች፤ ከእንግዲህ ወዲህ ጨርሶ አትታይም
\v 22 የበገና ደርዳሪዎች፣ የሙዚቀኞች፣ የዋሽንትና መለኮት ነፊዎች ድምፅ ከእንዲህ በአንቺ አይሰማም። ማንኛውንም ዓይነት የጥበብ ሥራ የሚሠራ በአንቺ አይገኝም። የወፍጮ ድምፅም በአንቺ አይሰማም።
\s5
\v 23 የመብራት ብርሃን፣ ከእንግዲህ በአንቺ አያበራም። የሙሽራውና የሙሽራይቱ ድምፅ ከእንግዲህ በአንቺ አይሰማም። ነጋዴዎችሽ የምድር ልዑላን ነበሩ ሕዝቦችን በመተትሽ አሳስተሻል።
\v 24 የነቢያትና የቅዱሳን ደም፣ በዚህ ምድር የተገደሉ ሰዎች ሁሉ ደም በእርሷ ተገኝቷል።
\s5
\c 19
\cl ምዕራፍ 19
\p
\v 1 ከእነዚህ ነገሮች በኋላ የበዙ ሰዎች ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ከሰማይ ሰማሁ “ሃሌ ሉያ ማዳን፣ ክብርና ኃይል የአምላካችን ነው።
\v 2 በዝሙቷ ምድርን ያረከሰችውን ታላቂቱን አመንዝራ ስለ ፈረደባት ፍርዱ እውነትና ትክክል ነው። እርሷ ያፈሰሰችውን የአገልጋዮቹን ደም ተበቅሎአል።
\s5
\v 3 በድጋሚ “ሃሌ ሉያ፤ ጢስዋ ከዘላለም እስከ ዘላለም ከእርሷ ይወጣል” በማለት ተናገሩ።
\v 4 ሃያ አራቱ ሽማግሌዎችና አራቱ ሕያዋን ፍጡራን በግንባራቸው ተደፍተው፣ “አሜን ሃሌ ሉያ!” በማለት ዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ሰገዱ።
\s5
\v 5 ከዚያ በኋላ፣ “ታናናሾችም ታላላቆችም እርሱን የምትፈሩ አገልጋዮቹ ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግኑ!” የሚል ድምፅ ከዙፋኑ ወጣ።
\s5
\v 6 ከዚያም እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ፣ እንደ ብዙ ውሆች ድምፅና የብርቱ ነጎድጓድ የሚመስል ድምፅ እንዲህ አለ፤
\s5
\v 7 ደስ ይበለን፤ ሐሤት እናድርግ፤ የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ ሙሽራዋም ራስዋን ስላዘጋጀች፤ ደስ ይበለን፤ ሐሤት እናድርግ ፤ ክብርንም እንስጠው።”
\v 8 ደማቅና ቀጭን ንጹሕ ልብስ እንድትለብስ ገሰጣት። ቀጭኑ ልብስ የቅዱሳኑ የጽድቅ ሥራ ነው።
\s5
\v 9 መልአኩም፣ “ወደ በጉ ሰርግ እንደመጡ የተጋበዙ ሰዎች የተባረኩ ናቸው ብለህ ጻፍ” አለኝ። በተጨማሪም፣ “እነዚህ እውነተኛ የእግዚአብሔር ቃሎች ናቸው” አለኝ።
\v 10 እኔም ልሰግድለት በእግሩ ሥር ተደፋሁ፤ እርሱ ግን፣ “እንዳታደርገው! እኔ ራሴ ከአንተና ስለ ኢየሱስ የተሰጠውን ምስክር ከያዙ ወንድሞችህ ጋር አገልጋይ ነኝ። ልችእግዚአብሔር ስገድ፤ ስለ ኢየሱስ የተሰጠው ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና” አልኝ።
\s5
\v 11 ከዚያም ሰማይ ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም አንድ ነጭ ፈረስ ተመለከትኩ ፈረሱ ላይ የተቀመጠው ታማኝና እውነተኛ ይባላል። በጽድቅ ይፈርዳል፤ ይዋጋል።
\v 12 ዐይኖቹ እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፤ ራሱም ላይ ብዙ አክሊሎች ነበሩ። ከእርሱ በቀር ማንም የማያውቀው ስም እርሱ ላይ ተጽፎ ነበር።
\v 13 ደም የተነከረ ልብስ ለብሶ ነበር፤ ስሙ የእግዚአብሔር ቃል ተብሎ ይጠራል።
\s5
\v 14 ቀጭን፣ ነጭና ንጹሕ ልብስ የለበሱ ሠራዊት በነጫጭ ፈረሶች ተቀምጠው ይከተሉት ነበር።
\v 15 ከአፉም ሕዝቦችን የሚመታበት የተሳለ ሰይፍ ይወጣ ነበር፤ በብረት በትር ይገዛቸዋል። ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን ቁጣ የወይን ጠጅ መጭመቂያ ይረግጣል።
\v 16 ልብሱና ጭኑ ላይ፣ የነገሥታት ንጉሥ፣ የጌቶችም ጌታ የሚል ስም ተጽፎበት ነበር።
\s5
\v 17 አንድ መልአክ ፀሐይ ላይ ቆሞ አየሁ። እርሱም በታላቅ ድምፅ፣ “ኑ፣ ወደ ታላቁ የእግዚአብሔር ግብዣ ተሰብሰቡ።
\v 18 መጥታችሁ የነገሥታትን፣ የጦር አዛዦችን፣ ሥጋ የኅያላንን ሥጋ፣ የፈረሰኞችንና በላያቸው የተቀመጡትን ሥጋ፣ የጌቶችን የባሮችን፣ የታናናሾችንና የታላላቆችን ሥጋ፣ የሰዎችን ሁሉ ሥጋ ብሉ።”
\s5
\v 19 አውሬውንና ከእርሱም ጋር የምድር ነገሥታትንና ሰራዊታቸውን አየሁ። ፈረሱ ላይ ተቀምጦ ከነበረውና ከሰራዊቱ ጋር ውጊያ ለመግጠም ተዘጋጅተው ነበር።
\v 20 እነሆ አውሬው ተያዘ፤ ከእነርሱም ጋር በእርሱ ፊት ምልክቶችን የሚያደርገው ሐሰተኛ ነቢይ ተያዘ። በእነዚህ ምልክቶች አማካይነት የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትንና ለምስሉ የሰገዱትን አሳሳተ። ሁለቱም በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባሕር በሕይወት እያሉ ተጣሉ።
\s5
\v 21 የተቀሩትም ፈረስ ላይ ከተቀመጠው አፍ በሚወጣው ሰይፍ ተገደሉ። ወፎችም ሁሉ ሥጋቸውን በልተው ጠገቡ።
\s5
\c 20
\cl ምዕራፍ 20
\p
\v 1 ከዚህ በኃላ የጥልቁ መክፈቻ ያለው አንድ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በእጁም ትልቅ ሰንሰለት ይዞ ነበር።
\v 2 ዘንዶውን ይዞ ሺህ ዓመት አሰረው፤ ይህ ዘንዶ ዶያብሎስ ሰይጣን የተባለው የቀድሞው እባብ ነው።
\v 3 ወደ ጥልቁ ጣለው፤ ዘግቶም በእርሱ ላይ ማኅተም አደረገበት። ይህን ያደረገው ሺህ ዓመቱ እስኮፈጸም ድረስ ከእንግዚህ ሕዝቦችን እንዳያሳስት ነው። ከዚያ በኋላ ለአጭር ጊዜ መፈታት ይኖርበታል።
\s5
\v 4 ከዚያም ዙፋኖች አየሁ። ዙፋኖቹም ላይ የመፍረድ ሥልጣን የተሰጣቸው ተቀምጠው ነበር። ለኢየሱስና ለእግዚአብሔር ቃል ምስክር የተሰየፉ ሰዎችን ነፍሶችንም አየሁ። ለአውሬው ወይም ለምስሉ አልሰገዱም፤ ምልክቱም ግንባራቸው ወይም እጃቸው ላይ እንዲያረግ አልፈቀዱም። ከሞት ተነሥተው፣ ለሺህ ዓመት ከክርስቶስ ጋር ነገሡ።
\s5
\v 5 የተቀሩት ሙታን ግን ሺሁ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ ከሞት አልተነሡም። ይህ የመጀመሪያው ትንሣኤ ነው።
\v 6 በመጀመሪያው ትንሣኤ ድርሻ የሚኖራቸው ሁሉ የተባረኩና የተቀደሱ ናቸው! እነዚህን በመሳሰሉት ላይ ሁለተኛው ሞት ኅይል አይኖረውም። የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ፤ ከእርሱም ጋር ሺህ ዓመት ይነግሣሉ።
\s5
\v 7 ሽው ዓመት ካበቃ በኃላ ሰይጣን ከእስራት ይፈታል።
\v 8 በአራቱ የምድር ማእዘን ያሉ ሕዝቦች ማለትም ጎግና ማጎግን ወደ ጦርነት ለማምጣት እያሳተ ወደ ጦርነት ለማምጣት ይወጣል ቁጥራቸውም እንደ ባሕር አሸዋ ያህል እጅግ ብዙ ነው።
\s5
\v 9 እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ ሄደው የቅዱሳንን ሰፈር፣ እንዲሁም የተወደደችውን ከተማን ከበቡ። ሆኖም፣ እሳት ከሰማይ ወርዶ በላቸው።
\v 10 እነርሱን ያሳሳተው ዲያብሎስ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወደ ተጣለበት በዲን ወደሚነደው የእሳት ባሕር ተጣሉ። ቀንና ሌሊት ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሰቃያሉ።
\s5
\v 11 ከዚያም አንድ ታላቅ ነጭ ዙፋንና በላዩ የተቀመጠውን አየሁ። ምድርና ሰማይ ከፊቱ ሸሹ፣ ሆኖም፣ መሄጃ ቦታ አልነበራቸውም።
\v 12 በዙፋኑ ፊት መታን፣ ታላላቆችና ታናናሾች ቆመው አየሁ፤ መጽሕፍትም ተከፈቱ። ከዚያም የሕይወት መጽሐፍ የተባለ ሌላም መጽሐፍ ተከፈተ። መታንም መጻሕፍቱም ውስጥ በተመዘገበው መሠረት እንደ ሥራቸው ተፈረደባቸው
\s5
\v 13 ባሕር ውስጡ ያሉ ሙታንን ሰጡ። ሞትና ሲኦል ውስጣቸው ያሉትን ሙታን ስጡ፤ ሙታንም እንደ ሥራቸው ተፈረደባቸው።
\v 14 ሞትና ሲኦል ወደ እሳቱ ባሕር ተጣሉ። የእሳቱም ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው።
\v 15 ስሙ በሕይወት መጽሐፍ ያልተገኘ ሁሉ ወደ እሳቱ ባሕር ተጣለ።
\s5
\c 21
\cl ምዕራፍ 21
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር አየሁ፤ ምክንያቱም የመጀመሪያው ሰማይና የመጀመሪያው ምድር አልፈው ነበር፤ ባሕርም ከእንግዲህ አልተገኘም።
\v 2 ቅድስቲቱ ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ለባልዋ እንዳጌጠች ሙሽራ ተዘጋጅታ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ።
\s5
\v 3 ከዙፋኑም እንዲህ የሚል ታላዝ ድምፅ ሰማሁ፣ “እነሆ የእግዚአብሔር መኖሪያ ከሰዎች ጋር ነው፤ ከእነርሱ ጋር ይኖራል። እነርሱ ሕዝቡ ይሆናሉ፤ እግዚአብሔር ራሱም ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል።
\v 4 እንባን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ሞት፣ ወይም ሐዘን፣ ወይም ለቅሶ ወይም ሕመም አይኖርም። ምክንያቱም የቀድሞ ነገሮች አልፈዋል።
\s5
\v 5 በዙፋኑ የተቀመጠው፣ “እነሆ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ” አለ። “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛ ስለሆኑ ጻፍ” አለ።
\v 6 ለእኔም እንዲህ አለኝ፤”እነዚህ ሁሉ ተፈጽመዋል እኔ አልፋና ዖሜጋ፣ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ነኝ። ለተጠማ ሰው ከሕይወት ውሃ ምንጭ እንዲጠጣ ያለ ዋጋ እሰጣለሁ።
\s5
\v 7 ድል የነሣ እነዚህን ነገሮች ይወርሳል፤ አምላኩ እሆናለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል።
\v 8 ነገር ግን የፈሪዎች፣ የእምነተ ቢሶች፣ የርኩሶች፣ የነፍስ ገዳዮች፣ የአመንዝራዎች፣ የሟርተኞች፣ የጦዖት አምላኪዎችና የሐሰተኞኦች ቦታቸው በዲን በሚቃጠለው እሳት ባሕር ውስጥ ይሆናል። ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።
\s5
\v 9 የመጨረሻዎቹ ሰባት መቅሠፍቶች የሞሉበትን ሰባት ድዋዎች ከያዙት ሰባት መላእክት አንዱ ወደ እኔ መጥቶ፣ “ወደዚህ ና፣ የበጉን ሚስት ሙሽራዋን አሳይሃለሁ” አለኝ።
\v 10 ከዚያም ወደ አንድ ታላቅና ከፍ ወዳለ ተራራ በመንፈስ ወሰደኝና ቅዱሳቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አሳየኝ።
\s5
\v 11 ኢየሩሳሌም የእግዚአብሔር ክብር ነበራት፤ የብርሃንዋ ፀዳል እጅግ እንደከበረ ድንጋይ፣ እንደ አያሰጲድ ድንጋይ ጥርት ያለ ነበር።
\v 12 አሥራ ሁለት በሮች ያሉት በጣም ታላቅ ረጅም ግምብ ነበራት በየበሮቹ አሥራ ሁለት መላእክት ነበሩ። በእነርሱም ላይ የአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ልጆች ስሞች ተጽፈው ነበር።
\v 13 በምሥራቅ ሦስት በሮች፣ በሰሜን ሦስት በሮች፣ በደቡብ ሦስት በሮች፣ በምዕራብ ሦስት በሮች ነበሩ።
\s5
\v 14 የከተማዋ ግምብ አሥራ ሁለት መሠረቶች ነበሩት፤ በእነርሱም ላይ የአሥራ ሁለቱ የበጉ ሐዋርያት ስሞች ተጽፈው ነበር።
\v 15 ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ከተማዋን፣ በሮቹንና ቅጥሮቹን የሚለካበት የወርቅ ዘንግ ነበረው።
\s5
\v 16 ከተማዋ አራት ማእዘን ነበረች፤ ርዝመትና ስፋቱ ዕኩል ነበር። በመለኪያ ዘንጉ ሲለካ ርዝመቱ 12,000 ምዕራፍ ሆነ (ርዝመቱ፣ ስፋቱና ከፍታዋ ዕኩል ነበር)።
\v 17 ቅጥሯን ስለካ ስፋቱ በሰው መለኪያ (ይህም የመላእክት መለኪያም ነው) 144 ክንድ ሆነ
\s5
\v 18 ቅጥሩ ከኢያሰጲድ፣ ከተማዋም እንደ መስተዋት በጠራ ንጹሕ ወርቅ የተሠራች ነበረች።
\v 19 የቅጥሩ መሠረቶች በከበሩ ድንጋዮች ያጌጡ ነበር። የመጀመሪያው ኢያሰጲድ፣ ሁለተኛው ሶንፔር፣ ሦስተኛው ኬልቄዶን፣ አራተኛው መረግድ
\v 20 አምስተኛው ሰርደንክስ፣ ስድስተኛው ሰርድዮን፣ ሰባተኛው ክርስቲሎቤ፣ ስምንተኛው ቢረሌ፣ ዘጠነኛው ወራውሬ፣ አሥረኛው ክርስጵራስስ፣ አሥራ አንደኛው ያክንት፣ አሥራ ሁለተኛው አሜቴስ ቲኖስ ነበረ።
\s5
\v 21 አሥራ ሁለቱም በሮች፣ አሥራ ሁለት ዕንቁዎች ነበሩ፤ እያንዳንዱ በር ከአንድ ዕንቁ የተሠራ ነበር። የየከተማዋ መንገዶች ጥርት እንዳለ መስተዋት ንጽሕ ወርቅ ነበሩ።
\v 22 በከተማዋ ምንም መቅደስ አላየሁም፤ ምክንያቱም ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላክና በጉ መቅደሷ ነበሩ።
\s5
\v 23 የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያበራለት ከተማዋ የፀሐይ ወይም የጨረቃ ብርሃን አልነበራትም፤ ምክንያቱም በጉ ራሱ ብርሃንዋ ነው።
\v 24 ሕዝቦችም በዚያች ከተማ ብርሃን ይመላለሳሉ። የምድር ነገሥታት ክብራቸውን ወደ እርሷ ያመጣሉ።
\v 25 በሮቿ በቀን አይዘጉም፤ በዚያ ሌሊት የለም።
\s5
\v 26 የመንግሥታትን ግርማና ክብር ወደ እርሷ ያመጣሉ
\v 27 ርኩስ ነገር በፍጹም አይገባባትም። ጸያፍ ወይም አታላይ ወደዚያ አይገባም፤ ወደዚያ የሚገቡት ስሞቻቸው በበጉ የሕይወት መጽሐፍ የተጻፈ ብቻ ናቸው።
\s5
\c 22
\cl ምዕራፍ 22
\p
\v 1 ከዚያም መልአኩ፣ እንደ መስተዋት የጠራውን የሆነውን የሕይወት ውሃ ወንዝ አሳየኝ። ወንዙም የሚወጣው ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን ነበር
\v 2 በከተማዋ ዋና መንገድ መካከል ያልፍ ነበር። በወንዙ ግራና ቀኝ አሥራ ሁለት ወር ሙሉ አሥራ ሁለት ዓይነት ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበር። የዛፉ ቅጠሎች ሕዝቦችን ሁሉ ይፈውሱ ነበር።
\s5
\v 3 ከእንግዲህ ምንም ዐይነት መርገም አይሆንም። የእግዚአብሔርና የበጉ ዚፋን ከተማው ውስጥ ይሆናሉ፤ አገልጋዮቹም ያገለግሉታል።
\v 4 ፊቱን ያያሉ፤ ስሙም ግንባሮቻቸው ላይ ይሆናል።
\v 5 ከእንግዲህ ሌሊት አይሆንም፤ ጌታ አምላክ ስለሚያበራላቸው የመብራት ወይም የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም። ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ።
\s5
\v 6 መልአኩም እንዲህ አለኝ፤ “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛ ናቸው። ጌታ፣ የነቢያት መናፍቅ አምላክ ቶሎ መሆን ያለበትን ለአገልጋዮቹ እንዲያሳያቸው መልአኩን ላከ።”
\v 7 “እነሆ፣ ቶሎ እመጣለሁ! ለዚህ መጽሐፍ የትንቢት ቃሎች የሚታአእ የተባረከ ነው።
\s5
\v 8 እነዚህን ነገሮች የሰማሁና ያየሁ እኔ ዮሐንስ ነኝ። እነዚህን በሰማሁና ባይብሁ ጊዜ እነዚህን ነገሮች ላሳየኝ መልአክ ለመስገድ በፊቱ ተደፋሁ።
\v 9 እርሱ ግን፣ “እንዳታደርገው! እኔ ራሴ ከወንድሞችህ ከነቢያት ጋር፣ ለዚህ መጽሐፍ ቃል ከሚታዘዙት ጋር አብሬ አገልጋይ ነኝ። ይልቅ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ!”
\s5
\v 10 እንዲህም አለኝ፤ ጊዜው በጣም ቅርብ ስለሆነ የዚህን መጽሐፍ የትንቢት ቃሎች በማኅተም አትዝጋው።
\v 11 ዐመፀኛው ማመፁን ይቀጥል። ርኩሱም ርኩሰት ማድረጉን ይቀጥል። ጻድቁም ጽድቅ የሆነውን ማድረጉን ይቀጥል። ቅዱስም ቅዱስ መሆን ይቀጥል።
\s5
\v 12 “እነሆ፣ ቶሎ እመጣለሁ። ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው የምከፍለው ዋጋ ከእኔ ዘንድ አለ።
\v 13 እኔ አልፋና ዖሜጋ፣ ፊተኛውና ኋለኛው፤ የመጀመሪያውና የመጨረሻው ነኝ።
\s5
\v 14 ከሕይወት ዛፍ ለመብላትና በበሮቿ ወደ ከተማዋ ለመግባት መብት እንዲኖራቸው ልብሳቸውን የሚያጥቡ የተባረኩ ናቸው።
\v 15 ውሾች፣ ጠንቋዮች፣ አመንዝራዎች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ ጣዖት አምላኪዎችና ሐሰትን የሚወዱና የሚያደርጉ ግን በውጭ አሉ።
\s5
\v 16 እኔ ኢየሱስ ለእናንተ እንዲመሰክር መልአኬን ወደ አብያተ ክርስቲያናት ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርጥ ዘር ነኝ፤ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።”
\s5
\v 17 መንፈሱና ሙሽራይቱ፣ “ና!” ይላሉ፤ የሚሰማ ሁሉ፣ “ና!” ይበል። ማንም የተጠማ ቢኖር ይምጣ፣ የሚፈልግ የሕይወትን ውሃ በነጻ ይውሰድ።
\s5
\v 18 የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ለሚሰሙ ሁሉ እኔ እመሰክራለሁ፣ ማንም ትንቢቱ ላይ ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል።
\v 19 ማንም ከዚህ መጽሐፍ ትንቢት ቢያጎድል እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ ከተጻፈው የሕይወት ዛፍና ቅድስት ከተማ ዕድሉን ያጎልበታል።
\s5
\v 20 ለእነዚህ ነገሮች የሚመሰክር እርሱ፣”አዎን! ቶሎ እመጣለሁ” አሜን! ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና! ይላል።
\v 21 የጌታ ኢየሱስ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን