am_ulb/63-1JN.usfm

209 lines
20 KiB
Plaintext

\id 1JN
\ide UTF-8
\h 1ኛ ዬሐንስ
\toc1 1ኛ ዬሐንስ
\toc2 1ኛ ዬሐንስ
\toc3 1jn
\mt 1ኛ ዬሐንስ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 ከመጀመሪያው ስለ ነበረው፣ ስለ ሰማነው፣ በዓይኖቻች ስላየነው፣ ስለ ተመለከትነው ፣በእጆቻችንም ስለ ዳሰስነው ስለ ህይወት ቃል
\v 2 ህይወትም ተገልጦ ነበር ፤እኛም አይተናል፣ምስክሮችም ነን፤ በአብ ዘንድ ስለ ነበረው ለእኛም ስለ ተገለጠው፣ የዘላለም ሕይወት እንናገራለን፤
\s5
\v 3 ከእኛም ጋር ህብረት እንዲኖራቸሁ፣ ያየነውንና የሰማነውን እንነግራችኋለን፤ ህብረታችንም ከአብና፣ ከልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው፡፡
\v 4 ደስታችሁም ሙሉ እንዲሆን ፣እነዚህን ነገሮች እንጽፍላችኋለን።
\s5
\v 5 ከእርሱ የሰማነው፣ለናንተም የምንነግራችሁ መልዕክት፣ እግዚአብሔር ብርሃን ነው፤ በእርሱም ምንም ጨለማ የለም፤ የሚል ነው፡፡
\v 6 ከእርሱ ጋር ህብረት አለን እያልን፣ ነገር ግን በጨለማ ውስጥ ብንመላለስ፣እንዋሻለን ፣እውነትንም አናደርግም፡፡
\v 7 እርሱ ብርሃን እንደሆነ ፣ በብርሃን ብንመለላለስ እርስ በርሳችን ህብረት ይኖረናል፡፡የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስም ደም ከሃጢአት ሁሉ ያነጻናል።
\s5
\v 8 ሃጢያት የለብንም ብንል፣ ራሳችንን እናስታለን፣ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።
\v 9 ነገር ግን ሃጢያታችንን ብንናዘዝ፣ሃጢያታችንን ይቅር ሊለንና ከዓመጽ ሁሉ ሊያነጻን፣ የታመነና ፃድቅ ነው፡፡
\v 10 ሃጢአት አላደረግንም ብንል፣ ሃሰተኛ እናደርገዋለን፣ ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም፡፡
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 የተወደዳችሁ ልጆቼ ፣ሃጢያት እንዳታደርጉ ይህን እፅፍላችኋላሁ። ግን ማንም ሃጢያት ቢያደርግ ፣ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን ፤እርሱም ፃድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፡፡
\v 2 እርሱ የእኛ ብቻ ሳይሆን፣ የዓለሙም ሁሉ ሃጢዓት ማስተስረያ ነው፣፡፡
\v 3 ትዕእዛዙን የምንጠብቅ ከሆነ ፣በዚህ እርሱን እንዳወቅነው እናውቃለን።
\s5
\v 4 "እግዚአብሔርን አውቀዋለሁ" የሚል ፣ግን ትዕዛዛቱን የማይጠብቅ፣ ውሸታም ነው ፣እውነትም በውስጡ የለም፡፡
\v 5 ሆኖም ማንም ቃሉን ቢጠብቅ፣ በርግርጥ በዚያ ሰው ለእግዚአብሔር ያለው ፍቅር ተገልጧል፤ በዚህም በእርሱ እንደሆንን እናውቃለን።
\v 6 በእግዚአብሔር እኖራለሁ የሚል ፣ኢየሱስ ክርስቶስ እንደኖረ መኖር አለበት።
\s5
\v 7 የተወደዳችሁ፣የምጽፍላችሁ በመጀመሪያ የነበረውን አሮጌ ትዕዛዝ እንጂ አዲስ ትዕዛዝ አይደለም።አሮጌውም ትእዛዝ የሰማችሁት ቃል ነው፡፡
\v 8 ሆኖ በክርስቶስና በናንተ እውነት የሆነውን አዲሱን ትእዛዝ እጽፍላችኋለሁ።ምክንያቱም ጨለማው አልፎ እውነተኛው ብርሃን እያበራ ነው።
\s5
\v 9 በብርሃን አለሁ እያለ ፣ወንድሙን ግን የሚጠላ ፣አሁንም እንኳ በጨለማ ውስጥ ነው፡፡
\v 10 ወንድሙን የሚወድ በብርሃን ይኖራል። የሚያሰናክል ሁኔታም የለም፡፡
\v 11 ወንድሙን የሚጠላ በጨለማ ውስጥ ነው፣ በጨለማም ይኖራል፤ ወዴት እንደሚሄድም አያውቅም ፣ምክንያቱም ጨለማው ዓይኖች አሳውሮታል፡፡
\s5
\v 12 ልጆች ሆይ! ኃጢያታችሁ በክርስቶስ ስም ይቅር ስለተባለ እፅፍላችኋለሁ፡፡
\v 13 አባቶች ሆይ! ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃኋልና እጽፍላችኋለሁ። ወጣቶች ሆይ! ክፉውን ስላሸነፋችሁ እጽፍላችኋለሁ፡፡ ታናናሽ ልጆች ሆይ! አብን ስላወቃችሁ እጽፍላችኋለሁ፡፡
\v 14 አባቶችሆይ! ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ወጣቶች ሆይ! ብርቱዎች ስለሆናቹ ፣የእግዚአብሔርም ቃል በእናንተ ስለሚኖር፣ ክፉውንም አሸንፋችኋልና እጽፍላችኋለሁ፡፡
\s5
\v 15 ዓለምን ወይም በዓለም ያሉት ነገሮች አትውደዱ። ማንም ዓለምን ቢወድ የአብ ፍቅር በርሱ ውስጥ የለም፡፡
\v 16 በዓለም ያለው ሁሉ፣ የሥጋ ምኞት፣ የዓይን አምሮትና ትምክህት ከዓለም እንጂ ከአብ አይደሉም፡፡
\v 17 ዓለሙና ምኞቱም ያልፋሉ፣የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል፡፡
\s5
\v 18 ታናናሾች ልጆች ሆይ! የክርስቶስ ተቀዋሚ ስለመምጣቱ እንደሰማችሁት ፣ይህ የመጨረሻው ሰዓት ነው፡፡ አሁንም እንኳ፣ ብዙ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች መጥተዋል፡፡
\v 19 ከእኛው መካከል ወጥተዋል ፣ከእኛ ወገን ግን አልነበሩም። ከእኛ ወገን ቢሆኑ ኖሮ፣ ከእኛ ጋር ፀንተው ይኖሩ ነበር። ሆኖም ከእኛ ወገን እንዳልነበሩ እንዲገለጥ ወጡ።
\s5
\v 20 እናንት ግን፣ከቅዱሱ የተቀበላችሁት ቅባት ስላላችሁ፣ሁላችሁም እውነትን ታውቃላችሁ።
\v 21 የምጽፍላችሁ እውነትን ስለማታውቁ አይደለም፤ነገር ግን ስለምታውቁትና፣ በእውነትም ምንም ሃሰት ስለሌለ ነው።
\s5
\v 22 ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ከሚክድ በስተቀር ሃሰተኛ ማነው ነው? አብና ወልድን ስለሚክድ፣እንዲህ ዓይነት ሰው የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።
\v 23 ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ የለውም፤ ወልድንን የሚያውቅ አብም ደግሞ አለው።
\s5
\v 24 እናንተ ግን ፣ከመጀመሪያው የሰማችሁት በውስጣችሁ ይኑር። ከመጀመሪያ የሰማችሁት፣በእናንተ ቢኖር፣እናንተም በወልድና በአብ ትኖራላችሁ።
\v 25 እርሱ የሰጠን ተስፋ ይህ ነው፤ እርሱም የዘላለም ሕይወት ነው።
\v 26 የሚያስቷችሁን በተመለከተ ፣ ይህን ፅፌላችኋለሁ፡፡
\s5
\v 27 እናንተ ግን የተቀበለች ቅባት በእናንተ ስለሚኖር ፣ማንም እንዲያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም። የርሱም ቅባት ስለ ሁሉም ነገሮች እውነት እንጂ ሃሰት ስለማያስተምራችሁ ፣ እንደተማራችሁት በርሱ ኑሩ፡፡
\v 28 አሁንም የተወዳዳችሁ ልጆች፣ በሚገለጥበለት ጊዜ ድፍረት እንዲኖረንና ፣በመምጣቱም እንዳናፍር በእርሱ ኑሩ፡፡
\v 29 እርሱ ፃድቅ እንደሆነ ካወቃችሁ ፣ፅድቅን የሚያደርግ ሁሉ ከርሱ እንደተወለደ ታውቃላችሁ፡፡
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ፣አብ የሰጠን ፍቅር ፣ምን ዓይነት እንደሆነ አስተውሉ ፤ እኛም ልክ እንደዛው ነን! በዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን እንደማያውቀው እኛንም አያውቀንም።
\v 2 የተወደዳችሁ፣አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን፤ምክንያቱም ትክክለኛ ማንንነቱን እናየዋለን።
\v 3 በእርሱም ላይ ይህ ጽኑ እምነት ያለው ሁሉ፣ እርሱ ንፁህ እንደሆነ ራሱን ያነፃል፡፡
\s5
\v 4 ኃጢያትን የሚሠራ ሁሉ ዐመጽን ያደርጋል፣ ኃጢአትም ዐመጽ ነው፡፡
\v 5 ኃጢያትን ለማስወገድ ክርስቶስ እንደተገለፀ ታውቃላችሁ፣ በእርሱም ኃጢያት የለም፡፡
\v 6 በእርሱ የሚኖር ኃጢያት አያደርግም፡፡ ኃጢያት የሚያደርግ እርሱን አላየውም ወይም አላወቀውም፡፡
\s5
\v 7 የተወደዳችሁ ልጆች፣ ማንም አያስታችሁ፡፡ ክርስቶስ ፃድቅ እንደሆነ ሁሉ፣ ፅድቅን የሚያደርግ ፃድቅ ነው።
\v 8 ኃጢያት የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፤ምክንያቱም ዲያብሎስ ከመጀመሪያው ኃጢያት አድርጓል፡፡ በዚህም ምንክያት የዲያብሎስን ሥራ ለማፍረስ ፣የእግዚአብሔር ልጅ ተገልጧል፡፡
\s5
\v 9 የእግዚአብሔር ዘር በርሱ ስለሚኖር ፣ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢያትን አያደርግም፤ ከእግዚአብሔር ተወልዷልና ኃጢያትን ሊያደርግም አይችልም።
\v 10 በዚህም የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች ይታወቃሉ፡፡ ፅድቅን የማያደርግ ወይም ወንድሙን የማይወድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፡፡
\s5
\v 11 ከመጀመሪያው የሰማችኋት መልእክት፣ይህ እርስ በርሳችን እንድንዋደድ የሚለው ነው።
\v 12 ክፉ እንደሆነውና ወንድሙን እንደ ገደለው እንደ ቃየል አይደለም። የገደለው ለምንድን ነው? ምክንያቱ የራሱ ሥራ ክፉ፣ የወንድሙ ጽድቅ ስለነበረ ነው፡፡
\s5
\v 13 ወንድሞች፣ ዓለም ቢጠላችሁ፣አትደነቁ።
\v 14 ወንድሞችን ስለምንወድ ፣ከሞት ወደ ህይወት እንደተሻገርን እናውቃለን። ፍቅር የሌለው በሞት ውስጥ ይኖራል፡፡
\v 15 ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው፡፡ ነፍሰ ገዳይ የሆነ ሁሉ፣ በውስጡ የዘላለም ህይወት እንደሌለው ታውቃላችሁ፡፡
\s5
\v 16 ክርስቶስ ለእኛ ህይወቱን ሰጥቷልና፣በዚህ ፍቅርን እናውቃለን።እኛም ለወንድሞቻችን ህይወታችንን አሳልፈን መስጠት ይገባናል።
\v 17 ነገር ግን ማንም የዚህ ዓለም ንብረት ያለውና፣ወንድሙም የሚያስፈልገውን አውቆ፣ባይራራለት፣ እንዴት የእግዚአብሔር ፍቅር በርሱ ይኖራል?
\v 18 የተወደዳችሁ ልጆቼ ፣በሥራና በእውነት እንጂ ፣በቃል ወይም በአንደበት አንዋደድ።
\s5
\v 19 በዚህም ከእውነት እንደሆንንና፣ልባችንም በፊቱ ትክክል እንደሆነ እናረጋግጣለን።
\v 20 ልባችን ግን የሚፈርድብን ከሆነ፣ እግዚአብሔር ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነው፣ሁሉንም ያውቃል፡፡
\v 21 ወዳጆች ሆይ! ልባችን የማይፈርድብን ከሆነ፣በእግዚአብሔር ፊት ድፍረት አለን።
\v 22 ትዕዛዙን የምንጠብቅና፣በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን የምናደርግ ስለሆነ፣ የምንለምነውንና ሁሉ እንቀበላለን፡፡
\s5
\v 23 የርሱም ትዕዛዙ፣በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንድናምንና፣ ትእዛዙን እንደሰጠን እንደዚያው እርስ በርስ እንድንዋደድ ነው፡፡
\v 24 የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ የሚጠብቅ ፣በርሱ ይኖራል እግዚአብሔርም በርሱ ይኖራል፡፡በዚህም በሰጠን በመንፈሱ፣ በእኛ ውስጥ እንደሚኖር እናውቃለን።
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 ወዳጆች ሆይ! መንፈስን ሁሉ አትመኑ፣ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር መሆናቸውን መርምሩ፣ ምክንያቱም ብዙ ሃሰተኛ ነቢያት ወደ ዓለም ገብተዋል፡፡
\v 2 የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ እናውቃለን፣- ጌታ ኢየሱስ በሥጋ እንደመጣ የሚቀበል መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው።
\v 3 ኢየሱስን የማይቀበል መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም። ይህ እንደሚመጣ የሰማችሁት የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፣ አሁን እንኳ በዓለም ውስጥ አለ፡፡
\s5
\v 4 የተወደዳችሁ ልጆች! እናንተ ከእግዚአብሔር ስለሆናችሁ፣ እነዚህን መናፍስት አሸንፋችኋል፣ ምክንያቱም በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ይበልጣል፡፡
\v 5 እነዚህ መናፍስት ከዓለም ናቸው፣ስለሆነም የሚናገሩት ሁሉ የዓለምን ነው፣ዓለምም ይሰማቸዋል፡፡
\v 6 እኛ ከእግዚአብሔር ነን። እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል። ከእግዚአብሔር ያልሆነ ግን አይሰማንም። በዚህም የእውነት መንፈስንና ፣የስህተትን መንፈስን እናውቃለን፡፡
\s5
\v 7 ወዳጆች ሆይ! እርስ በርስ እንዋደድ፣ምክንያቱም ፍቅር ከእግዚአብሔር ነውና፣ ፍቅር ያለው ከእግዚአብሔር ተወልዷል፣ እግዚአብሔርንም ያውቃል፡፡
\v 8 ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፣እግዚአብሔር ፍቅር ነውና፡፡
\s5
\v 9 በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በመካከላችን ተገልጧል፣ እግዚአብሔር በርሱ እንድንኖር ፣አንድ ልጁን ወደ ዓለም ላከው፡፡
\v 10 ፍቅር እንደዚህ ነው፣እግዚአብሔርን ስለወደድነው ሳይሆን፣ እርሱ ስለወደደን ለኃጢያታችን ማስተሰረያ እንዲሆን ልጁን ላከ፡፡
\s5
\v 11 ወዳጆች ሆይ! እግዚአብሔር ይህን ያህል ከወደደን፣እኛም እርስ በርሳችን መዋደድ ይገባናል።
\v 12 ማንም እግዚአብሔርን አላየውም። እርስ በርሳችን ብንዋደድ፣ እግዚአብሔር በኛ ይኖራል፣ ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ይሆናል፡፡
\v 13 መንፈሱን ሰጥቶናልና፣ በዚህም እኛ በእርሱ እንደምንኖር፣ እርሱም በኛ እንደሚኖር እናውቃለን።
\v 14 እኛም አይተናል፣እግዚአብሔር ልጁን የዓለም አዳኝ አድርጐ እንደላከውም እንመሰክራለን፡፡
\s5
\v 15 ማንም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ቢቀበል፣ እግዚአብሔር በርሱ ይኖራል ፤እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል፡፡
\v 16 እኛም እግዚአብሔር ለኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል ደግሞም አምነናል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፣እግዚአብሔርም በርሱ ይኖራል፡፡
\s5
\v 17 በፍርድ ቀን ድፍረት እንዲኖረን፣ይህም ፍቅር በመካከላችን ተፈጸሟል፣ እኛም በዚህ ዓለም እንደ እርሱ ነን ፡፡
\v 18 በፍቅር ፍርሃት የለም። ነገር ግን ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል፣ ምክንያቱም ፍርሃት የሚያመለክተው ቅጣት መኖሩን ነው። የሚፈራ ግን ፍቅሩ ፍፁም አይደለም፡፡
\s5
\v 19 አስቀድሞእግዚአብሔር ወዶናልና፣እኛም እንወደዋለን።
\v 20 አንድ ሰው "እግዚአብሔርን እወዳለሁ" እያለ ወንድሙን ግን ቢጠላ ሃሰተኛ ነው፤የሚያየውን ወንድሙን የማይወድ፣ የማያየውን እግዚአብሔርን ሊወድ አይችልም።
\v 21 እግዚአብሔርን የሚወድ ወንድሙን መውደድ አለበት፣የሚል ትእዛዝ ከእግዚአብሔር ተቀብለናል።
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ሆነ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዷል።አባት የሆነውን የሚወድ ሁሉ፣ከርሱ የተወለደውን ደግሞ ይወዳል።
\v 2 እግዚአብሔርን ስንወድና ትዕዛዙን ስንፈጽም፣ የእግዚአብሔርን ልጆች እንደምንወድ በዚህ እናውቃለን።
\v 3 እግዚአብሔርን የምንወደው የርሱን ትእዛዙን በመጠበቃችን ነው። የርሱም ትእዛዛት ከባዶች አይደሉም።
\s5
\v 4 ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋል። ዓለምን የሚያሽንፈው እምነታችን ነው።
\v 5 ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ከሚያምን በቀር፣ ዓለምን የሚየሸንፍ ማነው?
\s5
\v 6 በውሃና በደም የመጣው እርሱም ነው፣እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ፣ በውሃ ብቻ ሳይሆን፣ነገር ግን በውሃና በደም የመጣ ነው።
\v 7-8 የጥንቶችቹ የተሻሉት ቅጅዎች ይተውታል። ሦሶት ምስክሮች አሉ፤እነርሱም መንፈሱ ፣ውሃውና ደሙ ናቸው፤ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ።
\s5
\v 9 የሰዎችን ምስክርነት የምንቀበል ከሆነ፣ የእግዚአብሔር ምስክርነት ደግሞ የበለጠ ነው። እግዚአብሔር ስለ ጁል የሰጠው ምስክር ይህ ነው።
\v 10 በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በውስጡ ምስክር አለው። በእግዚአብሔር የማያምን ፣እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክር ስለማያምን ሐሰተኛ አድርጎታል።
\s5
\v 11 ምስክሩም ይህ ነው ፣እግዚአብሔር የዘላለምን ህይወት እንደሰጥንና፣ይህም ህይወት በልጁ መሆኑ ነው።
\v 12 ልጁ ያለው ሕይወት አለው፥ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።
\s5
\v 13 በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ፣የዘላለም ህይወት እንዳላችሁ እንድታውቁ ፣እነዚህን ነገሮች እጽፍላችኋለሁ።
\v 14 በእርሱ ፊት ያለን ድፍረት ይህ ነው፣እንደ ፈቃዱ ማንኛውንም ነገር ብንጠይቀው፣ይሰማናል።
\v 15 የምንጠይቀውን ሁሉ እንደሚሰማን ካወቅን፣ከርሱ የጠየቅነውን ሁሉ እንደተቀበልን እናውቃለን።
\s5
\v 16 ማንም ወንድሙ ለሞት የማያበቃ ሃጢዓት ሲያደርግ ቢያይ፣ መጸለይ ይገባዋል፣ሞት የማይገባውን ሃጢዓት ለሚያደርጉት እግዚአብሔር ህይወትን ይሰጣል። ለሞት የሚያበቃ ኃጢዓት አለ። ያንን የተመለከተ ልመና እንዲያደርግ አላልኩም።
\v 17 ዓመጽ ሁሉ ኃጢዓት ነው፣ ነገር ግን ለሞት የማያበቃ ኃጢዓት አለ።
\s5
\v 18 ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢዓት እንደማያደርግ እናውቃለን፣ከእግዚአብሔር የተወለደውን፣እግዚአብሔር ከክፉ ይጠብቀዋል ፣ክፉውም አይነካውም።
\v 19 እኛ ከእግዚአብሔር እንደሆንን፣ዓለም ሁሉ በክፉው ቁጥጥር ሥር እንደሆነ እናውቃለን።
\s5
\v 20 እኛ ግን የእግዚአብሔር ልጅ እንደመጣና እውነት የሆነውን እንድናውቅ ማስተዋል እንደሰጠን እናውቃለን፤ እኛም እውነት በሆነው በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ እንዳለን እናውቃለን። እርሱም እውነተኛ አምላክና የዘላለም ህይወት ነው።
\v 21 ልጆች ሆይ! ከጣዖታት ዓምልኮ ራሳችሁን ጠብቁ።