am_ulb/62-2PE.usfm

126 lines
14 KiB
Plaintext

\id 2PE
\ide UTF-8
\h 2ኛ ጴጥሮስ
\toc1 2ኛ ጴጥሮስ
\toc2 2ኛ ጴጥሮስ
\toc3 2pe
\mt 2ኛ ጴጥሮስ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 ክርስቶስ አገልጋይና ሐዋርያ ከሆነው ስምዖን ጴጥሮስ፤ በአምላካችንና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ አማካይነት የተቀበልነውን ዐይነት ክቡር እምነት ለተቀበሉት፤
\v 2 እግዚአብሔርንና ጌታችንን ኢየሱስን በማወቅ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።
\s5
\v 3 በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን እግዚአብሔርን በማወቅ እንድንኖር ለሕይወትና ለእውነተኛ መንፈሳዊነት የሚያስፈልገን ሁሉ በመለኮቱ ኀይል ተሰጥቶናል።
\v 4 በእነዚህ ነገሮች አማካይነት እጅግ የከበረና ታላቅ ተስፋ ሰጠን፤ ይህንም ያደረገው በክፉ ምኞቶች ሰበብ በዓለም ካለው ምግባረ ብልሹ ሕይወት አምልጣችሁ ከመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋዮች እንድትሆኑ ነው።
\s5
\v 5 በዚህም ምክንያት፣ የሚከተሉትን ነገሮች ለመጨመር ትጉ፣ በእምነታችሁ ላይ ደግነትን፣ በደግነት ላይ ዕውቀትን፣
\v 6 በዕውቀት ላይ ራስን መግዛት፣ ራስን በመግዛት ላይ መጽናትን፣ በመጽናት ላይ እግዚአብሔርን መምሰልን፤
\v 7 እግዚአብሔርን በመምሰል ላይ ላይ ወንድማዊ መዋደድን፣ በወንድማዊ መዋደድ ላይ ፍቅርን ጨምሩ።
\s5
\v 8 እነዚህ ነገሮች በውስጣችሁ ቢኖሩና በውስጣችሁ ቢያድጉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በማወቅ ዳተኞችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋል።
\v 9 እነዚህ ነገሮች የሌሉት ግን ዕውር ነው፤ በቅርብ ያለውን ብቻ ያያል፤ ከቀድሞው ኀጢአቱ መንጻቱንም ረስቶአል።
\s5
\v 10 ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፤ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ለማጽናት ትጉ፤ ይህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉም፤
\v 11 በዚህም ወደ ጌታችንና አዳኛችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘላለማዊ መንግሥት መግባት በሙላት ይሰጣችኋል።
\s5
\v 12 ስለዚህ ምንም እንኳ እነዚህን ነገሮች ብታውቋቸውና በያዛችሁት እውነት ብትጸኑም፣ ስለ እነዚህ ነገሮች ዘወትር እናንተን ከማሳሰብ ቸል አልልም።
\v 13 በዚህ ምድራዊ ድንኳን ውስጥ እስካለሁ ድረስ ስለ እነዚህ ነገሮች እናንተን ማሳሰብ ትክክል ነው ብዬ አስባለሁ፤
\v 14 ምክንያቱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ገለጠልኝ ይህን ምድራዊ ድንኳን ቶሎ ለቅቄ እንደምሄድ ዐውቃለሁ፤
\v 15 ከተለየኋችሁም በኋላ እነዚህን ነገሮች ዘወትር እንድታስቡ የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ።
\s5
\v 16 ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኀይልና ስለ ዳግም መምጣቱም በነገርናችሁ ጊዜ ግርማውን በዐይናችን አይተን መሰከርን እንጂ በብልሃት የተፈጠረውን ተረት ተከትለን አይደለም።
\v 17 «በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው» የሚል ድምፅ ከግርማዊው ክብር በመጣለት ጊዜ፣ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ሞገስን ተቀብሎአል።
\v 18 ከእርሱ ጋር በተቀደሰው ተራራ ላይ በነበርንበት ጊዜ ይህን ከሰማይ የመጣውን ድምፅ ሰምተነዋል።
\s5
\v 19 ትንቢታዊው ቃል ይበልጥ ተረጋግጦልናል፤ ሌሊቱ እስኪነጋ ድረስ በጨለማ ስፍራ ለሚያበራ መብራት እንደምትጠንቀቁ፣ የንጋቱ ኮከብ በልባችሁ እስኪበራ ድረስ ለዚህ ቃል ብትጠነቀቁ መልካም ታደርጋላችሁ።
\v 20 ይህን በመጀመሪያ ዕወቁ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት የሚገኘውን የትንቢት ቃል ማንም ሰው በራሱ መንገድ የሚተረጒመው አይደለም፤
\v 21 ምክንያቱም ትንቢት ከእግዚአብሔር የተላኩ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው ተናገሩት እንጂ ከቶ በሰው ፈቃድ የመጣ አይደለም።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 ሐሰተኞች ነቢያት በእስራኤላውያን መካከል ነበሩ፤ በእናንተ መካከል ደግሞ ሐሰተኞች መምህራን ይኖራሉ፤ እነርሱ ጥፋትን የሚያስከትል ሐሰተኛ ትምህርት በስውር ያስገባሉ፤ የዋጃቸውንም ጌታ ክደው ፈጣን ጥፋትን በራሳቸው ላይ ያመጣሉ። ብዙዎች የእነርሱን መዳራት ይከተላሉ።
\v 2 ከእነርሱም አድራጎት የተነሣ የእውነት መንገድ ይሰደባል።
\v 3 እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን ለገንዘብ ከመስገብገባቸው የተነሣ የሚያታልሉ ቃላትን በመጠቀም ይበዘብዙአችኋል። በእነርሱ ላይ ያለው ፍርድ አይዘገይም፤ መጥፊያቸውም የራቀ አይደለም።
\s5
\v 4 እግዚአብሔር ኀጢአት የሠሩትን መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሐነም ከጣላቸውና በሰንሰለት አስሮ እስከ ፍርድ ጊዜ ድረስ በጨለማ ውስጥ ካስቀመጣቸው፣
\v 5 የጽድቅ ሰባኪ የነበረውን ኖኅን ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር አድኖ ለጥንቱ ዓለም ሳይራራ በኀጢአተኞች ላይ የጥፋት ውሃ ካመጣ፣
\v 6 ደግሞም ኀጢአት በሚያደርጉ ሁሉ ላይ የሚመጣው ጥፋት ምሳሌ እንዲሆኑ የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ዐመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎ ከፈረደባቸው፣
\s5
\v 7 በሕገ ወጦች ሴሰኝነት ነፍሱ እየተጨነቀ ይኖር የነበረውን ጻድቁን ሎጥን ግን አዳነው፤
\v 8 ያ ጻድቅ ሰው በመካከላቸው ሲኖር በየቀኑ ያየውና ይሰማው በነበረው ሕገ ወጥ ድርጊታቸው ጻድቅ ነፍሱ ትጨነቅ ነበር።
\v 9 ጌታ፣ እግዚአብሔርን የሚመስሉትን ሰዎች ከፈተና እንዴት እንደሚያድናቸውና ዐመፀኞችን እየቀጣ ለፍርድ ቀን እንዴት ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል።
\s5
\v 10 በተለይም ብልሹ የሥጋ ምኞታቸውን የሚከተሉትንና ሥልጣንን የሚንቁትን ለፍርድ ጠብቆ ያቈያቸዋል። እነዚህ ሰዎች ደፋሮችና እብሪተኞች ስለ ሆኑ የከበሩትን ሲሳደቡ አይፈሩም፤
\v 11 መላእክት ከሰዎች ሁሉ ይልቅ ብርታትና ችሎታ ያላቸው ሆነው ሳሉ፣ በጌታ ፊት በእነርሱ ላይ ዘለፋ ያዘለ የፍርድ ቃል አይሰነዝሩም።
\s5
\v 12 እነዚህ አእምሮ እንደ ጎደላቸው እንስሳት ለምርኮና ለጥፋት የተፈጠሩ ናቸው፤ የሚሳደቡትን ስለማያውቁ ይጠፋሉ።
\v 13 እነርሱ የዐመፃቸውን ዋጋ ይቀበላሉ፤ በቀን በመስከርና ያለ ልክ በመፈንጠዝ ይኖራሉ ፤ እነርሱ አሳፋሪዎችና ነውረኞች ናቸው። ከእናንተ ጋር ግብዣ ላይ ሲገኙ፣ በአታላይ ፈንጠዝያቸው ሐሴት ያደርጋሉ።
\v 14 ዐይናቸው ቅንዝር የተሞላ በመሆኑ ኀጢአትን ከመሥራት ከቶ አይቈጠቡም፤ ጽኑ ያልሆኑትን ሰዎች ያስታሉ፤ መመኘትን የለመደ ልብ አላቸው፤ የተረገሙ ልጆች ናቸው።
\s5
\v 15 ቀናውን መንገድ ትተው፣ በክፉ ሥራ የሚገኘውን ገንዘብ የወደደውን የቢዖርን ልጅ የበለዓምን መንገድ ተከትለው ስተዋል፤
\v 16 እርሱ ስለ መተላለፉ ተገሥጾአል፤ መናገር የማይችል አህያ በሰው ቋንቋ ተናግሮ የነቢዩን እብደት አስቍሟልና።
\s5
\v 17 እነዚህ ሰዎች እንደ ደረቁ ምንጮችና በዐውሎ ነፋስ እንደሚነዱ ደመናዎች ናቸው፤ የሚጠብቃቸውም ድቅድቅ ጨለማ ነው፤
\v 18 ፍሬ ቢስ የዕብሪት ቃል በመናገር፥ በሥጋዊ ፍትወታቸው ሰዎችን ያጠምዳሉ፤ ከተሳሳተና ከብልሹ የሕይወት ዘይቤ ለማምለጥ የሚሞክሩትን ሰዎች ያጠምዳሉ።
\v 19 እነርሱ ራሳቸው የጥፋት ባሪያዎች ሆነው ሳሉ፣ ሌሎችን ነጻ ትወጣላችሁ እያሉ ተስፋ ይሰጧቸዋል፤ ሰው ለሚሸነፍለት ለማንኛውም ነገር ባሪያ ነውና።
\s5
\v 20 ጌታችንንና አዳኛችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማወቅ ከዓለም ርኵሰት ካመለጡ በኋላ፣ እንደ ገና ወደ ቀደሞው የርኵሰት ሕይወት ቢመለሱ፣ ከመጀመሪያው ይልቅ የኋለኛው የከፋ ይሆንባቸዋል።
\v 21 የጽድቅን መንገድ ካወቁ በኋላ ከተሰጣቸው ቅዱስ ትእዛዝ ወደ ኋላ ከሚመለሱ፣ ቀድሞውኑ የጽድቅን መንገድ ባያውቋት ይሻላቸው ነበር።
\v 22 «ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል» እንዲሁም «ዐሣማ ቢታጠብም ተመልሶ በጭቃ ላይ ይንከባለላል» የሚለው ምሳሌ እውን ይሆንባቸዋል።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 ወዳጆች ሆይ! ይህን ሁለተኛ መልእክት የምጽፍላችሁ፣ ቅን ልቦናችሁን ለማነቃቃት ነው፤
\v 2 ደግሞም አስቀድሞ በቅዱሳን ነቢያት የተነገረውን ቃል እንዲሁም በሐዋርያቶቻችሁ አማካይነት በጌታችንና በአዳኛችን የተሰጠውን ትእዛዝ እንድታስታውሱ ነው።
\s5
\v 3 በቅድሚያ ይህን ዕወቁ፤ በመጨረሻዎቹ ቀኖች የራሳቸውን ክፉ ምኞት የሚከተሉ ዘባቾች እየዘበቱባችሁ ይመጣሉ።
\v 4 እነርሱም፣ «የመምጣቱ ተስፋ ወዴት አለ? አባቶቻችን ሞተዋል፤ ከፍጥረት መጀመሪያም አንሥቶ እስካሁን ድረስ ሁሉም ነገር እንዳለ ይኖራል» ይላሉ።
\s5
\v 5 እነዚህ ሰዎች ሰማያትና ምድር ከብዙ ዘመን በፊት በእግዚአብሔር ቃል ከውሃና በውሃ አማካይነት መፈጠራቸውን ፣ ሆን ብለው ይክዳሉ፤
\v 6 በቃሉና በውሃ እማካይነት በዚያን ጊዜ የነበረው ዓለም በውሃ ተጥለቅልቆ ጠፋ።
\v 7 ደግሞም በዚያው ቃል አሁን ያሉት ሰማያትና ምድር ኀጢአተኞች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ለእሳት ተጠብቀዋል።
\s5
\v 8 ወዳጆች ሆይ፤ ፤በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፣ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን መሆኑን ይህን አትዘንጉ ።
\v 9 አንዳንድ ሰዎች የዘገየ እንደሚመስላቸው ጌታ የተስፋ ቃሉን ለመፈጸም አይዘገይም፤ ነገር ግን ከእናንተ መካከል አንዳችሁም እንድትጠፉ ስለማይፈልግና ሰው ሁሉ በቂ የንስሓ ጊዜ እንዲያገኝ ፈልጎ ስለ እናንተ ይታገሳል።
\s5
\v 10 ይሁን እንጂ የጌታ ቀን ግን እንደ ሌባ ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፤ የሰማይም ፍጥረት በእሳት ይቃጠላል፤ በምድርና በእርሷም ውስጥ በተሠራው ነገር ሁሉ ላይ ይፈረድበታል።
\s5
\v 11 እንግዲህ እነዚህ ሁሉ ነገሮች በዚህ ሁኔታ የሚጠፉ ከሆነ፣ ታዲያ እናንተ በቅድስናና እግዚአብሔርን በመምሰል ሕይወት ለመኖር እንዴት ዐይነት ሰዎች ልትሆኑ ይገባችኋል?
\v 12 ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት በናፍቆት የምትጠባበቁና የምታፋጥኑ ሁኑ፤ በዚያን ቀን ሰማያት በእሳት ተቃጥለው ይጠፋሉ፤ ፍጥረታትም በእሳት ግለት ይቀልጣሉ፤
\v 13 እኛ ግን እርሱ በሰጠን ተስፋ መሠረት፣ ጽድቅ የሰፈነበትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንጠባበቃለን።
\s5
\v 14 ስለዚህ ወዳጆች ሆይ፤ እነዚህን ነገሮች የምትጠባበቁ እንደ መሆናችሁ፣ ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ ሆናችሁ ከእርሱም ጋር በሰላም እንድትገኙ ትጉ።
\v 15 እንዲሁም ወንድማችን ጳውሎስ በተሰጠው ጥበብ መጠን እንደ ጻፈላችሁ፤ የጌታችን ትዕግሥት እናንተ እንድትድኑ እንደ ሆነ አስቡ፤ ምንም እንኳ በመልእክቶቹ ውስጥ በቀላሉ ለመረዳት የሚያስቸግሩ ነገሮች ቢኖሩም፣
\v 16 ጳውሎስ ስለ እነዚህ ነገሮች በመልእክቶቹ ሁሉ ጽፎአል፤ ዕውቀት የጐደላቸውና ጽናት የሌላቸው ሰዎች ሌሎችን የቅዱሳት መጻሕፍት ክፍሎች እንደሚያጣምሙ ሁሉ እነዚህም ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ።
\s5
\v 17 እንግዲህ ወዳጆች ሆይ፤ ይህን አስቀድማችሁ ስላወቃችሁ፣ በዐመፀኞች ስሕተት ተስባችሁ ጽኑ መሠረታችሁን እንዳትለቅቁ ተጠንቀቁ።
\v 18 ነገር ግን በጌታችንና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ዕውቀት እደጉ፤ ለእርሱ አሁንም፣ ለዘላለምም ክብር ይሁን፤ አሜን!