am_ulb/61-1PE.usfm

214 lines
22 KiB
Plaintext

\id 1PE
\ide UTF-8
\h 1ኛ ጴጥሮስ
\toc1 1ኛ ጴጥሮስ
\toc2 1ኛ ጴጥሮስ
\toc3 1pe
\mt 1ኛ ጴጥሮስ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነው ከጴጥሮስ፤ በጳንጦስ፣ በገላትያ፣ በቀጰዶቅያ፣ በእስያና በቢታንያ ተበትነው በመጻተኝነት ለሚኖሩ፤ ለተመረጡት፤
\v 2 እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ እንዳወቃቸው፣ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመታዘዝ በደሙ ለተረጩትና በመንፈስ ቅዱስ ለተቀደሱት፤ ጸጋ ለእናንተ ይሁን፤ ሰላማችሁም ይብዛ።
\s5
\v 3 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ ይባረክ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት በመነሣቱ ምክንያት ላገኘነው ርስት ዋስትና እንዲሆነን በታላቅ ምሕረቱ አዲስ ልደትን ሰጠን፤
\v 4 ይህም የማይጠፋ፣ የማይበላሽ እና የማያረጅ ርስት በመንግሥተ ሰማይ ተጠብቆላችኋል።
\v 5 እናንተም በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀው መዳን በእምነት አማካይነት በእግዚአብሔር ኅይል ተጠብቃችኋል።
\s5
\v 6 ምንም እንኳን አሁን በብዙ ልዩ ልዩ ዐይነት መከራ ማዘናችሁ ተገቢ ቢሆንም፣ በዚህ እጅግ ደስ ይላችኋል።
\v 7 ይኸውም፣ በእሳት ተፈትኖ ቢጠራም፣ ጠፊ ከሆነው ወርቅ ይልቅ እጅግ የከበረው እምነታችሁ እንዲፈተን ነው። ይህ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ አምነታችሁ ምስጋናን ክብርንና፣ ውዳሴን እንዲያስገኝላችሁ ነው።
\s5
\v 8 ኢየሱስ ክርስቶስን ባታዩትም እንኳ ትወዱታላችሁ፤ አሁን ባታዩትም በእርሱ ታምናላችሁ፤ ሊነገር በማይቻልና ክብር በሞላበት ሐሤት በጣም ደስ ይላችኋል፤
\v 9 አሁን የእምነታችሁን ፍጻሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ ነውና።
\v 10 እናንተ ስለምትቀበሉት ጸጋ ትንቢት የተናገሩት ነቢያት ስለዚህ መዳን ይፈልጉና በጥልቅ ይመረምሩ ነበር፤
\s5
\v 11 የሚመጣው መዳን ምን ዐይነት እንደ ሆነ ለማወቅ ይመረምሩ ነበር፤ እንዲሁም በእነርሱ ውስጥ የነበረው የክርስቶስ መንፈስ ስለ ክርስቶስ መከራና ከመከራው በኋላ ስለሚሆነው ክብር አስቀድሞ የተናገራቸው በምን ጊዜና እንዴት እንደሚፈጸም ይመረምሩ ነበር። ነቢያቱ ያገለግሉ የነበሩት እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳልነበረ ተገልጦላቸዋል፤
\v 12 ይኸውም ከሰማይ በተላከው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ወንጌልን ያበሠሩአችሁ ሰዎች የነገሩአችሁን በመግለጥ ነው፤ መላእክትም እንኳ ይህ ነገር ሲገለጥ ለማየት ይመኙ ነበር።
\s5
\v 13 ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጠቁ፤ ጠንቃቆች ሁኑ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ በምታገኙት ጸጋ ላይ ፍጹም መተማመን ይኑራችሁ።
\v 14 ታዛዦች ልጆች እንደ መሆናችሁ ባለማወቅ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ።
\s5
\v 15 ነገር ግን የጠራችሁ እርሱ ቅዱስ እንደ ሆነ፣ እናንተም በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ፤
\v 16 ምክንያቱም «እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ» ተብሎ ተጽፎአል።
\v 17 ሳያዳላ በእያንዳንዱ ሰው ላይ እንደየሥራው የሚፈርደውን «አባት» ብላችሁ የምትጠሩት ከሆነ፣ በእንግድነት ዘመናችሁ እርሱን በማክበር ኑሩ።
\s5
\v 18 ከቀድሞ አባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከማይረባ ሕይወት የተዋጃችሁት በሚጠፋ ነገር ማለትም በብር ወይም በወርቅ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ፤
\v 19 ይልቁንም የተዋጃችሁት ነውርና እንከን እንደሌለበት በግ ደም፣ በክርስቶስ ክቡር ደም ነው።
\s5
\v 20 ክርስቶስ የተመረጠው ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ነው፤ አሁን ግን በመጨረሻው ዘመን ለእናንተ ተገለጠ።
\v 21 በእርሱ አማካይነት፣ ከሞት ባስነሣውና ክብርን በሰጠው በእግዚአብሔር ታምናላችሁ። ይኸውም እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ላይ እንዲሆን ነው።
\s5
\v 22 ለእውነት በመታዘዝ ለእውነተኛ የወንድማማች መዋደድ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ እርስ በርሳችሁ ከልብ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።
\v 23 ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፤ ነገር ግን በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው።
\s5
\v 24 ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር፣ ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል፤ አበባውም ይረግፋል፤
\v 25 የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል። የተሰበከላችሁም ወንጌል መልእክቱ ይህ ነው።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 እንግዲህ ክፋትን ፣ ማታለልን ፣ ግብዝነትን፣ ቅናትንና ሐሜትን ሁሉ አስወግዱ።
\v 2 በድነታችሁ በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ንጹህ የሆነውን መንፈሳዊ ወተት ተመኙ፤
\v 3 ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ ከሆነ፣
\s5
\v 4 በሰው ዘንድ ወደ ተናቀው፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ወደ ተመረጠውና ክቡር ወደ ሆነው ወደዚህ ሕያው ድንጋይ ቅረቡ።
\v 5 ደግሞም እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕት የሚያቀርቡ ቅዱሳን ካህናት ትሆኑ ዘንድ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ትሠራላችሁ።
\s5
\v 6 በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈው «እነሆ፤ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም» ።
\s5
\v 7 እንግዲህ ለምታምኑት ለእናንተ እርሱ ክቡር ነው፤ ለማያምኑት ግን፣«ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣ እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ»
\v 8 እንደዚሁም ደግሞ «ሰዎችን የሚያሰናክልና የሚጥላቸውም ዐለት ሆነ»። የሚሰናከሉት ቃሉን ባለመታዘዛቸው ነው፤ የተመደቡት ለዚህ ነውና።
\s5
\v 9 እናንተ ግን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ እንድታውጁ፣ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉሥ ካህናት፣ ቅዱስ ሕዝብ፣ እግዚአብሔር የራሱ ያደረጋችሁ ሕዝብ ናችሁ።
\v 10 ቀድሞ የእርሱ ሕዝብ አልነበራችሁም፤ አሁን ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ ሆናችኋል፤ ቀድሞ ምሕረትን አላገኛችሁም ነበር፤ አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።
\s5
\v 11 ወዳጆች ሆይ፤ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ መጠን፣ ነፍሳችሁን ከሚዋጉ ከኅጢኣት ምኞቶች እንድትርቁ እለምናችኋለሁ።
\v 12 ክፉ እንደምትሠሩ አድርገው ቢያሟችሁም፣ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ መልካሙን ሥራችሁን አይተው እግዚአብሔርን እንዲያከብሩ፣ በአሕዛብ መካከል አኗኗራችሁ መልካም መሆን አለበት።
\s5
\v 13 ስለ ጌታ ብላችሁ ለምድራዊ ባለ ሥልጣን ሁሉ ታዘዙ፤
\v 14 የበላይ ባለ ሥልጣን ስለ ሆነ ለንጉሥ ቢሆን፣ ወይም ክፉ አድራጊዎችን ለመቅጣት፣ በጎ አድራጊዎችን ለማመስገን እርሱ ለሾማቸው ገዦች ታዘዙ፤
\v 15 ምክንያቱም፣ መልካም በማድረግ የአላዋቂዎችን ከንቱ ንግግር ዝም እንድታሰኙ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው።
\v 16 እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ሆናችሁ በነጻነት ኑሩ እንጂ ነጻነታችሁን የክፋት መሸፈኛ አታድርጉት።
\v 17 ለሰው ሁሉ ተገቢውን አክብሮት ስጡ፤ ወንድሞችን ውደዱ፤ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ንጉሥን አክብሩ።
\s5
\v 18 እናንተ አገልጋዮች ፤ ለመልካሞችና ለገሮች ጌቶቻችሁ ብቻ ሳይሆን ለክፉዎችም በፍጹም አክብሮት ታዘዙ።
\v 19 ስለ እግዚአብሔር ሲል የግፍ መከራን የሚቀበል ሰው ምስጋናን ያገኛል።
\v 20 ክፉ ሥራ ሠርታችሁ ስትቀጡ ብትታገሡ ምን ያስመሰግናችኋል? ነገር ግን መልካም ሥራ ሠርታችሁ መከራ ስትቀበሉ ብትታገሡ ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ ያስመሰግናችኋል።
\s5
\v 21 የተጠራችሁት ለዚህ ነው፤ ክርስቶስ ስለ እናንተ መከራን የተቀበለው የእርሱን ፈለግ እንድትከተሉ ምሳሌ ሊተውላችሁ ነው።
\v 22 እርሱ ኅጢአት አላደረገም፥ ተንኵልም በአፉ አልተገኘበትም፤
\v 23 ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራንም ሲቀበል አልዛተም፤ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤
\s5
\v 24 ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በመስቀል ላይ ተሸከመ፤ በእርሱ ቊስል እናንተ ተፈውሳችኋል።
\v 25 ቀድሞ ሁላችሁም እንደ ጠፉ በጎች ትቅበዘበዙ ነበር፤ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 ሚስቶች ሆይ፤ እናንተም እንደዚሁ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤ አንዳንድ ለቃሉ የማይታዘዙ ቢኖሩ እንኳ፣ ሚስቶቻቸው ቃል ሳይናገሩ በመልካም አኗኗራቸው ሊማርኳቸው ይችላሉ፤
\v 2 ይህም የሚሆነው ለእነርሱ ያላችሁን አክብሮት በንጹሕ አኗኗራችሁ ሲመለከቱ ነው።
\s5
\v 3 ውበታችሁ በውጫዊ ነገሮች በመሽሞንሞን ይኸውም ሹሩባ በመሠራት፣ በወርቅ በመንቆጥቆጥ ወይም ጌጠኛ ልብስ በመልበስ አይሁን፤
\v 4 ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት የከበረ፣ ገርና ጭምት መንፈስ ያለበት፣ ምንጊዜም የማይጠፋ የውስጥ ሰውነት ውበት ይሁን።
\s5
\v 5 የቀድሞ ቅዱሳት ሴቶች የተዋቡት በዚህ ዐይነት ነበር፤ እነርሱ በእግዚአብሔር የሚደገፉና ለባሎቻቸ የሚታዘዙ ነበሩ።
\v 6 ሣራም እንደዚሁ አብርሃምን «ጌታዬ» እያለች ትታዘዘው ነበር፣ እናንተም መከራን ሳትፈሩ መልካም ብታደርጉ፣ አሁን የእርሷ ልጆች ናችሁ።
\s5
\v 7 እንዲሁም ባሎች ሆይ፤ ሚስቶቻችሁ ደካማ አጋር መሆናቸውን ዐውቃችሁ፣ የሕይወትን ጸጋ ከእናንተ ጋር አብረው የሚካፈሉ መሆናቸውንም ተገንዝባችሁ አብራችኋቸው ኑሩ። ጸሎታችሁ እንዳይከለከል ይህን አድርጉ።
\s5
\v 8 በመጨረሻም፣ ሁላችሁ በአንድ ሐሳብ ተስማሙ፤ ተዛዘኑ፤ እንደ ወንድማማቾች ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ።
\v 9 ክፉን በክፉ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ፤ ምክንያቱም እናንተ የተጠራችሁት በረከትን ለመውረስ ነው።
\s5
\v 10 ስለዚህ «ሕይወትን የሚወድና መልካም ቀኖችን ሊያይ የሚፈልግ ምላሱን ከክፉ፣ ከንፈሮቹንም ተንኰል ከመናገር ይከልክል።
\v 11 ከክፉ ይራቅ፤ መልካምንም ያድርግ፤ ሰላምን ይፈልግ፤ ይከተላትም።
\v 12 የጌታ ዐይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉና፤ ጆሮቹም ጸሎታቸውን ለመስማት የተከፈቱ ናቸው፤ የጌታ ፊት ግን በክፉ አድራጊዎች ላይ ነው።»
\s5
\v 13 መልካም ነገር ለማድረግ ብትቀኑ የሚጐዳችሁ ማን ነው?
\v 14 ነገር ግን በጽድቅ ምክንያት መከራ ቢደርስባችሁ ቡሩካን ናችሁ፤ ዛቻቸውን አትፍሩ፤ አትታወኩም።
\s5
\v 15 ይልቁንም፣ ክርስቶስ የከበረ መሆኑን ተረድታችሁ በልባችሁ ቀድሱት። እናንተ በእግዚአብሔር ላይ ስላላችሁ መታመን ምክንያቱን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁል ጊዜ የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ ነገር ግን ይህን ሁሉ በትሕትናና በአክብሮት አድርጉት፤
\v 16 በክርስቶስ ያላችሁን መልካም አናናራችሁን የሚያክፋፉ ሰዎች በሐሜታቸው እንዲያፍሩ በጎ ኅሊና ይኑራችሁ።
\v 17 እግዚአብሔር የሚፈልገው ይህን ከሆነ፣ ክፉ ሠርቶ መከራ ከመቀበል ይልቅ መልካም አድርጎ መከራ መቀበል ይሻላል፤
\s5
\v 18 እንዲሁም ክርስቶስ አንድ ጊዜ ስለ ኀጢአታችን ሞቷል። ወደ እግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ፣ ጻድቅ የሆነው እርሱ ስለ እኛ ስለ ዐመፀኞች ሞተ፤ እርሱ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፤
\v 19 በመንፈስም ሄዶ በወህኒ ቤት ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው፤
\v 20 በወህኒ የነበሩት እነዚህ ነፍሳት ቀድሞ በኖኅ ዘመን መርከብ ሲሠራ እግዚአብሔር በትዕግሥት ይጠብቃቸው የነበሩ እምቢተኞች ናቸው፤ እግዚአብሔር ከውሃ ያዳናቸው ጥቂት ሰዎችን፣ ይኸውም ስምንት ሰዎችን ብቻ ነበር።
\s5
\v 21 ይህም ውሃ አሁን እናንተን የሚያድነው የጥምቀት ምሳሌ ነው፤ ይህ ጥምቀት የሰውነትን ዕድፍ ማስወገድ ሳይሆን ንጹሕ ኅሊናን ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ልመና ነው፤ የሚያድናችሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ አማካይነት ነው፤
\v 22 እርሱ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ አለ፤ መላእክት፣ ሥልጣናትና ኀይላትም ተገዝተውለታል።
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 ክርስቶስ በሥጋው መከራን ስለ ተቀበለ፣ እናንተም በዚሁ ዐላማ ታጥቃችሁ ተነሡ፤ በሥጋው መከራን የሚቀበል ሰው ኀጢአትን ትቶአል።
\v 2 እንዲህ ያለው ሰው ከእንግዲህ በሚቀረው ዕድሜ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ምኞት አይኖርም።
\s5
\v 3 አሕዛብ ፈልገው እንደሚያደርጉት በመዳራት፣ በሥጋ ምኞት፣ በስካር፣ ቅጥ ያጣ ፈንጠዝያ፣ በጭፈራና ርኵስ ከሆነ የጣዖት አምልኮ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።
\v 4 እነዚህን ነገሮች ለማድረግ ከአነርሱ ጋር አለመተባበራችሁ እንግዳ ሆኖባቸው ስለ እናንተ ክፉ ያወራሉ።
\v 5 ነገር ግን እነርሱ በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ ለተዘጋጀው መልስ ይሰጣሉ።
\v 6 ወንጌል ለሙታን የተሰበከው በዚህ ምክንያት ነው፤ በሥጋቸው እንደ ሰው ሁሉ ይፈረድባቸዋል፤ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በመንፈስ ይኖራሉ።
\s5
\v 7 የሁሉም ነገር መጨረሻ ተቃርቦአል፤ ስለዚህ መጸለይ እንድትችሉ ንቁ አእምሮ ይኑራችሁ፤ በአስተሳሰባችሁም ጠንቃቆች ሁኑ።
\v 8 ፍቅር ብዙ ኀጢአትን ይሸፍናልና ከሁሉ አስቀድሞ እርስ በርሳችሁ ከልብ ተዋደዱ፤
\v 9 ያለ ማጒረምረም እርስ በርሳችሁ በእንግድነት ተቀባበሉ።
\s5
\v 10 እንደ ታማኝ የእግዚአብሔር ልዩ ልዩ ጸጋ መጋቢ እያንዳንዱ ሰው በተቀበለው የጸጋ ስጦታ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤
\v 11 የሚናገር ቢኖር እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢኖር እግዚአብሔር በሚሰጠው ብርታት ያገልግል፤ ይኸውም እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት በሁሉም ነገር እንዲከብር ነው፤ ክብርና ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም ለእርሱ ይሁን፤ አሜን።
\s5
\v 12 ወዳጆች ሆይ፤ እንደ እሳት የሚፈትን ብርቱ መከራ ስትቀበሉ፣ እንግዳ ነገር እንደ ደረሰባችሁ በመቍጠር አትደነቁ፤
\v 13 ነገር ግን ክብሩ በሚገለጥበት ጊዜ ደስታችሁ ታላቅ እንዲሆን የክርስቶስ መከራ ተካፋዮች በመሆናችሁ ሐሴት አድርጉ።
\v 14 ስለ ክርስቶስ ስም ብትሰደቡ፣ የክብር መንፈስ የሆነው የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ስለሚያርፍ ቡሩካን ናችሁ።
\s5
\v 15 ከእናንተ ማንም እንደ ነፍሰ ገዳይ፣ እንደ ሌባ፣ እንደ ክፉ አድራጊ ወይም በሰው ነገር ጣልቃ እንደሚገባ ሰው ሆኖ መከራን አይቀበል፤
\v 16 ማንም ክርስቲያን በመሆኑ መከራ ቢደርስበት፣ በዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር፤
\s5
\v 17 ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት የሚጀምርበት ጊዜ ቀርቦአል። እንግዲህ ፍርድ የሚጀምረው በእኛ ከሆነ፣ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ ሰዎች መጨረሻቸው ምን ይሆን?
\v 18 እንግዲህ፣ ጻድቅ ሰው የሚድነው በጭንቅ ከሆነ፣ ዐመፀኛውና ኀጢአተኛው እንዴት ይሆን ይሆን?”
\v 19 ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራ የሚቀበሉ መልካም እያደረጉ ነፍሳቸውን ለታመነው ፈጣሪ ዐደራ ይስጡ። ።
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 እንግዲህ እኔም ከእነርሱ ጋር ሽማግሌና የክርስቶስ መከራ ምስክር የሆንሁ እንዲሁም ወደ ፊት የሚገለጠው ክብር ተካፋይ የምሆን በመካከላችሁ ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤
\v 2 ስለዚህ፣ በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ የምትጠብቋቸውም ማድረግ ስላለባችሁ በግዴታ ሳይሆን፣ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በደስታ ይሁን፤ ጥቅም ለማግኘት በመስገብገብ ሳይሆን፣ በበጎ ፈቃደኝነት ይሁን፤
\v 3 እንዲሁም በእናንተ ኀላፊነት ሥር ላለው መንጋ መልካም ምሳሌ ሁኑ እንጂ እንደ ዐለቃ በላያቸው አትሠልጥኑ።
\v 4 የእረኞች ዐለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማይጠፋውን የክብር አክሊል ትቀበላላችሁ።
\s5
\v 5 ጕልማሶች ሆይ፤ እናንተም እንዲሁ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ ምክንያቱም፣ «እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል» እንደ ተባለው፣
\v 6 እርሱ በወሰነው ጊዜ ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከእግዚአብሔር ብርቱ እጅ በታች ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤
\v 7 እርሱ ስለ እናንተ ስለሚያስብ የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።
\s5
\v 8 ጠንቃቆች ሁኑ፤ ንቁም፤ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሳ አንበሳ ወዲያ ወዲህ ይዞራል።
\v 9 በዓለም ዙሪያ ያሉ ወንድሞቻችሁ ተመሳሳይ መከራ እንደሚቀበሉ ዐውቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።
\s5
\v 10 ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ ፣ በክርስቶስ ወደ ዘለዓለማዊ ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ፍጹማን ያደርጋችኋል፤ ያጸናችኋል ፤ ያበረታችኋልም።
\v 11 የገዥነት ሥልጣን ከዘላለም እስከ ዘላለም ለእርሱ ይሁን! አሜን።
\s5
\v 12 እንደ ታማኝ ወንድም በምቈጥረው በስልዋኖስ አማካይነት ይህን ዐጭር መልእክት ጽፌላችኋለሁ፤ የጻፍሁላችሁም ልመክራችሁና ይህ እውነተኛ የእግዚአብሔር ጸጋ መሆኑን ልመሰክርላችሁ ነው። በዚህ ጸጋ ጸንታችሁ ቁሙ።
\v 13 ከእናንተ ጋር የተመረጠችው፣ በባቢሎን የምትገኘው ሰላምታ ታቀርብላችኋለች፤ እንዲሁም ልጄ ማርቆስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል።
\v 14 በፍቅር አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ። በክርስቶስ ላላችሁ ለሁላችሁም ሰላም ይሁን።