am_ulb/59-HEB.usfm

592 lines
61 KiB
Plaintext

\id HEB
\ide UTF-8
\h ዕብራዊያን
\toc1 ዕብራዊያን
\toc2 ዕብራዊያን
\toc3 heb
\mt ዕብራዊያን
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 ከረጅም ጊዜ በፊት በተለያዩ ዘመናትና በተለያዩ መንገዶች እግዚአብሔር በነቢያት በኩል ለአባቶቻችን ተናግሮ ነበር።
\v 2 አሁን ግን የሁሉም ነገር ወራሽ ባደረገው፣ ዓለምንም በፈጠረበት በልጁ ተናገረን።
\v 3 ልጁ የክብሩ ነጸብራቅ ነው፤ እርሱ በባሕርዩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም አንድ ነው፤ በሥልጣን ቃል ሁሉን ደግፎ ይዞአል። የሰዎችንም ኃጢአት ካነዳ በኃላ በሰማይ በግርማው ቀኝ ተቀምጧል።
\s5
\v 4 እርሱ የወረሰው ስም ከሰማቸው እጅግ የላቀ በመሆኑ፣ ከመላእክትም የበለጠ ሆኖአል።
\v 5 ለመሆኑ፣ ከመላክት መካከል፣ “አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ” ደግሞስ፣ “እኔ አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል” ያለው ለማን ነው?
\s5
\v 6 የበኩር ልጁን ወደ ዓለም ሲያስገባ እግዚአብሔር፣ “የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉ ይስገዱለት” ብሏል።
\v 7 ስለ መላእክቱ ግን፣"መላዕክቱን ነፋሳት፥ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል ያደርጋል" ይላል።
\s5
\v 8 ስለ ልጁ ግን፣ “አምላክ ሆይ፣ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ነው፤ የመንግሥትህም በትር የጽድቅ በትር ነው።
\v 9 ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፅንም ጠላህ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ፣ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ” ብሏል።
\s5
\v 10 እንዲሁም፣ “ጌታ ሆይ፣ በመጀመሪያ ምድርን ፈጠርህ፤ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው።
\v 11 እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ትኖራለህ። ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ።
\v 12 እንደ መጎናጸፊያ ትጠቀልላቸዋለህ፤እንደ ልብስም ይለወጣሉ።
\s5
\v 13 በየትኛውም ጊዜ ነበር እግዚአብሔር ከመላእክቱ ለአንዱ፣ “ጠላቶችህን ከእግርህ በታች እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” ያለው?
\v 14 ታድያ፣ መላእክት ሁሉ እኔን እንዲያመልኩና ድነት የሚወርሱትን ለመርዳት ተተላኩ መንፈሶች አይደሉምን?
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 ስለዚህ ከሰማነው ነገር እንዳንወሰድ፣ ስለ ሰማነው ነገር ይበልጥ መጠንቀቅ አለብን።
\s5
\v 2 በመላእክት አማካይነት የመጣው መልእክት ጽኑ ከሆነና፣ ማንኛውም መተላለፍና ዐመፅ ተገቢውን ቅጣት የሚቀበል ከሆነ።
\v 3 ታዲያ፣ይህንን ታላቅ መዳን ቸል ካልን እንዴት ማምለጥ እንችላለን?
\v 4 እግዚአብሔርም ምልክቶችን፣ ድንቆችንና የተለያዩ ተአምራትን በማድረግ፣እንደ ፈቃዱ በታደሉት በመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች አማካይነት ምስክርነታቱን አጽንቶአል።
\s5
\v 5 ይህ እየተናገርንለት ያለውን ወደ ፊት የሚመጣውን ዓለም እግዚአብሔር ለመላእክት አላስገዛም።
\v 6 እንዲያውም በቅዱሳት መጻህፍት አንድ ሰው አንድ ስፍራ ሲናገር፣
\s5
\v 7 ሰውን ከመላእክት በጥቂት አሳነስኸው የክብርና የምስጋና ዘውድ ጫንህለት።
\f + \ft አንዳንድ ቅጆች “…በእጆችህ ሥራ ሁሉ ላይ ሾምኸው” የሚል ይጨምራሉ። \f*
\v 8 ማንኛውንም ነገር ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት” ብሏል። እግዚአብሔር ከእግሩ በታች ሲያስገዛለት ምንም ያላስገዛለት ነገር የለም። ነገር ግን በእሁኑ ጊዜ ሁሉም ነገር ተገዝቶለት ገና አናይም።
\s5
\v 9 ይሁን እንጂ፣ ከመከራውና ከሞቱ የተነሣ ከመላእክቱ በጥቂቱ አንሶ የነበረውን ኢየሱስ፣ የክብርና የምስጋና ዘውድ ተጭኖለት እናያለን። በእግዚአብሔር ጸጋ እርሱ ለሰው ሁሉ ሞትን ቀምሷል።
\v 10 ሁሉም በእርሱና ለእርሱ የሚኖር ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ለማምጣት የድነታቸውን መሥራች በመከራው አማካይነት እግዚአብሔር ፍጹም ሊያደርገው ተገቢ ሆነ።
\s5
\v 11 የሚቀድሰውም ሆነ የሚቀደሱት ሁለቱም ከአንዱ ምንጭ፣ ከእግዚአብሔር ናቸው። በዚህም ምክንያት የሚቀድሳቸው እርሱን ወንድሞቼ ብሎ ሊጠራቸው አላፈረም።
\v 12 እንዲያውም፣
\s5
\v 13 እንዲሁም፣ “እኔ በእርሱ እታመናለሁ” ይላል። በተጨማሪ፣ “እነሆ እኔንና እግዚአብሔር የሰጠኝን ልጆች ተመልከቱ” ብሏል።
\v 14 ስለዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ በሥጋና ደም ስለሆኑ፣ በሞቱ አማካይነት ሞት ላይ ሥልጣን ያለውን ማለትም ዲያብሎስን ለመሻር ኢየሱስም እንደ እነርሱ ሥጋ ለብሶ።
\v 15 ይህም የሆነው ዕድሜ ልካቸውን በሞት ፍርሃት ምክንያት ዕድሜ ልካቸውን ባርነት ውስጥ የነበሩትን ሁሉ ነጻ ለማውጣት ነው።
\s5
\v 16 እርግጥም እየረዳቸው ያለው መላእክትን ሳይሆን፣ የአብርሃም ዘሮችን ነው።
\v 17 ስለሆነም የእግዚአብሔር በሆነ ነገር ሁሉ መሓሪና ታማኝ ሊቀ ካህን ለመሆንና ለሰዎችም ሁሉ የኃጢአት ይቅርታን ለማስግገኘት በሁሉም ረገድ ወንድሞችን መምሰሉ አስፈላጊ ሆነ።
\v 18 ኢየሱስ ራሱ መከራ የተቀበለና የተፈተነ በመሆኑ፣ የሚፈተኑትን ሁሉ ሊረዳቸው ይችላል።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 ስለዚህ የሰማያዊ ጥሪ ተከፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች የእምነታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት የሆነውን ኢየሱስን አስቡ።
\v 2 ሙሴ በእግዚአብሔር ቤት ሁሉ ላይ ታማኝ እንደ ነበር ሁሉ፣ እርሱም ለሾመው ለእግዚአብሔር ታማኝ ነበር።
\v 3 ቤቱን የሚሠራው ከራሱ ከቤቱ የበለጠ ክብር እንዳለው ሁሉ፣ ኢየሱስም ከሙሴ ይልቅ የበለጠ ክብር እንደሚገባው ተቆጥሯል።
\v 4 ማንኛውም ቤት ሠሪ አለው፤ ሁሉም ነገር የሠራ ግን እግዚአብሔር ነው።
\s5
\v 5 ወደ ፊት መነገር ለሚገባው ነገር ምስክር እንዲሆን፣ ሙሴም በእግዚአብሔር ቤት ሁሉ እንደ አገልጋይ ታማኝ ነበር።
\v 6 ክርስቶስ ግን በእግዚአብሔር ቤት ሥልጣን ያለው ልጅ ነው። የምንተማመንበትንና የመተማመናችንን ድፍረት አጥብቀን ብንይዝ ቤቱ ነን።
\s5
\v 7 ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ፣ዛሬ ድምጹን ብትሰሙ
\v 8 በምድረበዳ በፈተና ቀን በአመጽ እንዳደረጋችሁት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ።
\s5
\v 9 ይህ የሆነው አባቶቻችሁ እኔን በመፈታተን ሲያምፁብኝና ዐርባ ዓመት ሙሉ ሥራዎቼን ባዩበት ጊዜ ነበር።
\v 10 ስለዚህ በዚያ ትውልድ ደስ አልተሰኘሁም። እንዲህም አልኩ፤ ልባቸው ሁል ጊዜ ይስታል መንገዴንም አላወቁም።
\v 11 ስለዚህ በቁጣዬ፥ "ወደ እረፍቴ አይገቡም" ብዬ ማልሁ።
\s5
\v 12 ወንድሞች ሆይ ከእናንተ ማንም የማያምን ክፉና ከሕያው እግዚአብሔር ዘወር የሚል ልብ እንዳይኖረው ተጠንቀቁ።
\v 13 ይልቁንስ ከእናንተ ማንም በኃጢአት መታለል እልኸኛ እንዳይሆን ከዛሬ ጀምሮ በየዕለቱ እርስ በርሳችሁ ተበረታቱ።
\s5
\v 14 ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ድረስ በእርሱ ያለንን ድፍረት አጥብቀን ከያዝን ከክርስቶስ ጋር ተባባሪዎች እንሆናለን።
\v 15 ስለዚህም፣ "ዛሬ ድምጹን ብትሰሙ በአመጽ ጊዜ እንደሆነው ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ" ተብሏል።
\s5
\v 16 ለመሆኑ፣እነዚያ ድምፁን ሰምተው ያመፁት እነማን ነበሩ? ሙሴ እየመራ ከግብፅ ያወጣቸው ሁሉ አይደሉምን?
\v 17 ለአርባ ዓመት እግዚአብሔር የተቆጣባቸውስ እነማን ነበሩ? ኃጢአት ያደረጉና ሬሳቸው በበረሃ ወድቆ የቀረው አይደሉምን?
\v 18 ደግሞስ እነዚያ ያልታዘዙት ካልሆኑ በቀር ወደ ዕረፍቱ እንደማይገቡ እግዚአብሔር የማለባቸው እነማን ሊሆኑ ነው?
\v 19 ባለማመናቸው ምክንያት ወደ ዕረፍቱ ሊገቡ እንዳልቻሉ እናያለን።
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 ከእናንተ ማንም የእግዚአብሔር ዕረፍት ከሆነው ዘላቂ ተስፋ የሚጎድል እንዳይመስለው በጣም መጠንቀቅ አለብን።
\v 2 ምክኒያቱም ለእስራኤላውያን እንደ ተነገረ ሁሉ ለእኛም ስለ እግዚአብሔር ዕረፍት መልካም ዜና ተነግሮናል፤ ሆኖም፣ የሰሙትን መልእክት ሰሞዎቹ በእምነት ስላልተቀበሉት አልጠቀማቸውም።
\s5
\v 3 “ወደ ዕረፍቴ አይገቡም፣ ብዬ በቁጣዬ ማልሁ” እንዳለው ሳይሆን እኛ ያመንን ግን ወደ ዕረፍቱ እንገባለን። የእርሱ ፍጥረት ሥራ ከዓለም መፈጠር ጀምሮ የተጠናቀቀ ቢሆንም፣
\v 4 ስለ ሰባተኛ ቀን በማመልከት አንድ ቦታ “በሰባተኛው ቀን እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ ዐረፈ” ይላል።
\v 5 ደግሞም፣ “ወደ ዕረፍቴ አይገቡም” ይላል።
\s5
\v 6 ወደ እግዚአብሔር ዕረፍት ለመግባት ለአንዳንዶች አሁንም የተጠበቀባቸው በመሆኑና ፣ መልካሙን ዜና ከሰሙት እስራኤላውያን ብዙዎቹ ባለ መታዘዛቸው ምክንያት ወደ ዕረፍቱ ባለ መግባታቸው እግዚአብሔር በድጋሚ፣
\v 7 “ዛሬ” የተባለ ቀን ወስኖአል።
\s5
\v 8 ኢያሱ አሳርፎአቸው ቢሆን ኖሮ፣ እግዚአብሔር ስለ ሌላ ቀን አይናገርም ነበር።
\v 9 ስለዚህ ለእግዚአብሔር ሕዝብ አሁንም ቢሆን የሰንበት ዕረፍት ተጠብቆላቸዋል።
\v 10 ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር ዕረፍት የገባ ሰው እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ ሁሉ፣ እርሱም ከሥራው ያርፋል።
\v 11 ስለዚህ ማንም የእነዚያን ሰዎች ዐመፅ ተከትሎ እንዳይወድቅ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንናፍቅ።
\s5
\v 12 የእግዚአብሔር ቃል ሕያው፣ የሚሠራና፣ ሁለት አፍ ካለው ሰይፍ ይልቅ፣ ስለታም ነው። ነፍስንና መንፈስን፣ ጅማትንና ቅልጥምን እስኪለያይ ድረስ ይወጋል። የልብን ሐሳብና ውስጥን ይመረምራል።
\v 13 ከእግዚአብሔር ፊት የሚሰወር ምንም ፍጥረት የለም። እኛ ተጠያቂዎች በሆንንበት በእርሱ ዓይኖች ፊት ማንኛውም ነገር የተገለጠና የተራቆተ ነው።
\s5
\v 14 እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ታላቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፣ እምነታችንን አጥብቀን እንያዝ።
\v 15 ነገር ግን እርሱ ከኃጢአት በቀር በማንኛውም ነገር እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንምና።
\v 16 ስለዚህ በሚያስፈልገን ጊዜ ምሕረትንና የሚረዳንን ጸጋ እንድንቀበል ወደ ጸጋው ዙፋን በድፍረት እንቅረብ።
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 እያንዳንዱ ሊቀ ካህን ከሰዎች መካከል ይመረጣል፤ ለኃጢአት መሥዋዕትንና መባን ለማቅረብ እግዚአብሔርን በሚመለከት ጉዳይ እነርሱን በመወከል ይሾማል።
\v 2 እርሱ ራሱም በድካም ውስጥ ያለ በመሆኑ ዐላዋቂዎችንና ከመንገድ የሳቱትን ሊራራላቸው ሊቀበላቸው ይችላል።
\v 3 ከዚህም የተነሣ ለሕዝቡ ኃጢአት እንደሚያድርገው ሁሉ እርሱም ለገዛ ራሱ ኃጥአት መሥዋዕት ማቅረብ ይኖርበታል።
\s5
\v 4 እንደ አሮን በእግዚአብሔር የተጠራ ካልሆነ በቀር ማንም ይህን ክብር በራሱ አያገኘውም።
\v 5 ክርስቶስ ራሱም ቢሆን ሊቀ ካህናት የመሆንን መብት በገዛ ራሱ አልወሰደም። ይልቁንም እግዚአብሔር ለእርሱ፣
\s5
\v 6 ይህም በሌላ ቦታ፣ እግዚአብሔር፣እንደመልከጼዴቅ ሹመት አንተ ለዘላለም ካህን ነህ" ይላል።
\s5
\v 7 ኢየሱስ ሰው ሆኖ በዚህ ምድር በነበረ ዘመን ፣ ከሞት ሊያድነው ወደሚችለው አምላክ በታላቅ ጩኸትና በብዙ እንባ ጸሎትንና ልመናን አቀረበ። እግዚአብሔርን በመፍራቱም ጸሎቱ ተሰማለት።
\v 8 ምንም እንኳ እርሱ ልጅ ቢሆንም፣ ከደረሰበት መከራ የተነሣ መታዘዝን ተማረ።
\s5
\v 9 በዚህ ሁኔታ ሁሉ የዘላለም ድነት ምክንያት ሆነላቸው፤
\v 10 እግዚአብሔርም እንደ መልከጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት አድርጎ ሾመው።
\v 11 ስለ ኢየሱስ ብዙ የምንናገረው አለን፤ ሆኖም፣ ለመቀበል ዳተኞች ስለሆናችሁ፣ ለእናንተ ማስረዳት አዳጋች ነው።
\s5
\v 12 እስከ አሁን ድረስ መምህራን መሆን ሲገባችሁ፣ የእግዚአብሔርን ቃል መሠረታዊ መርሖዎች የሚያስተምራችሁ ሰው ገና ትፈልጋላችሁ። እናንተ የምትፈልጉት ወተት እንጂ፣ ጠንካራ ምግብ አይደለም።
\v 13 ወተት ብቻ ሊጋት ማንኛውም ሰው ገና ሕፃን ስለሆነ የጽድቅ ትምህርት ልምምድ የለውም።
\v 14 በሌላ በኩል ደግሞ ጠንካራ ምግብ ግን መልካምንና ክፉውን መለየት ለተማሩና ትክክል የሆነውን ካልሆነው የመለየት ልምድ ላላቸው ትልልቅ ሰዎች ነው።
\s5
\c 6
\cl ምዕራፍ 6
\p
\v 1 ስለዚህ ስለ ክርስቶስ መልእክት በመጀመሪያ የተረዳነውን ተወት በማድረግ ወደ ብስለት ልንሻገር ይገባናል እንጂ ከሞተ ሥራ ንስሐ መግባትንና በእግዚአብሔር ማመንን፣
\v 2 ወይም ጥምቀቶችን፣እጆች መጫንን፣ የሙታን ትንሳኤን እንዲሁም የዘላለም ፍርድን ወደ ሚመለከት መሠረትን የመጣል ትምህርት መመለስ አይገባንም።
\v 3 እግዚአብሔር ከፈቀደ እነዚህንም እናደርጋለን
\s5
\v 4 ይህንን የምናደርገው አንድ ጊዜ ብርሃን በርቶላቸው ሰማያዊውን ስጦታ የተቀበሉትን፣ከመንፈስ ቅዱስ ተሳታፊዎች የነበሩትን፣
\v 5 መልካሙን የእግዚአብሔር ቃልና በመጪው ዘመን ሊመጣ ያለውን ኃይል ከቀመሱ በኃላ
\v 6 የካዱትን በንስሐ እንዲታደሱ ማድረግ የማይቻል በመሆኑ ነው። እነዚህ ለሕዝብ መሳለቂያ ይሆን ዘንድ ራሱን የእግዚአብሔርን ልጅ ራሳቸው እንደገና ይሰቅሉታል።
\s5
\v 7 በእርሷ ላይ ብዙ ጊዜ የሚዘንበውን ዝናብ ተቀብላ ለደከሙባት የሚጠቅም ፍሬን የምታፈራ መሬት ከእግዚአብሔር በረከትን ትቀበላለች።
\v 8 እሾህና አሜኬላ የምታበቅል ከሆነች ግን ዋጋ ቢስና እርግማን የሚጠብቃት ትሆናለች፣ ፍጻሜዋም መቃጠል ይሆናል።
\s5
\v 9 እንደዚህ የምንናገር ብንሆንም፣ ወዳጆች ሆይ፣ እናንተንና ድነታችሁን በሚመለከት ግን የተሻለ ነገር ስለ መኖሩ እርግጠኞች ነን።
\v 10 ምክንያቱም ቅዱሳንን በማገልገላችሁና አሁንም እያገለገላችኋቸው በመሆኑ ለስሙ ያላችሁን ፍቅር በማሳየት የሠራችሁትን ሥራ ይረሳ ዘንድ እግዚአብሔር ዓመፀኛ አይደለም።
\s5
\v 11 በፍጹም የመተማመን ዋስትና እያንዳንዳችሁ ይህንኑ ትጋት እስከመጨረሻ እንድታሳዩ በእጅጉ እንናፍቃለን።
\v 12 ከእምነትና ከትዕግሥት የተነሣ የተስፋ ቃሉን የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ቸልተኞች እንድትሆኑ አንፈልግም።
\s5
\v 13 ምክንያቱም እግዚአብሔር ለአብርሃም የተስፋ ቃል በገባለት ጊዜ ከራሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ
\v 14 “በእርግጥ እባርክሃለሁ፣ ዝርያዎችህንም እጅጉን አበዛለሁ” በማለት በራሱ ምሎአልና።
\v 15 በዚህ መንገድ በትዕግሥት ከጠበቀ በኃላ ተስፋ የተገባለትን ተቀበለ።
\s5
\v 16 ሰዎች ከእነርሱ በሚበልጠው ይምላሉና፣ በመካከላቸው ለሚፈጠርውም ለማንኛውም ሙግት መሐላ የመጨረሻው ማጽኛ ነው።
\v 17 የዓለማውን የማይለወጥ ባሕርይ ለተስፋው ወራሾች ይበልጥ ግልጽ አድርጎ ለማሳየት እግዚአብሔር በወሰነ ጊዜ በመሃላ አጸናው።
\v 18 ይህንን ያደረገው እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይችልባቸው ሁለት የማይለወጡ ነገሮች በፊታችን ያለውን መተማመኛ አጥብቀን ይዘን አምባ ፍለጋ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ ድፍረት ይሆንልን ዘንድ ነው።
\s5
\v 19 ከመጋረጃው በስተጀርባ ወዳለው ቅድስት የሚገባውና እኛ የያዝነው ይህ መተማመኛ፣ ሥጋት የሌለበትና አስተማማኝ የነፍሶቻችን መልሕቅ ነው።
\v 20 በመልከ ጼዴቅ ሥርዓት ለዘላለም ሊቀ ካህናት በመሆን ኢየሱስ ወደዚህ ስፍራ ለእኛ ቀዳሚ በመሆን ገብቷል።
\s5
\c 7
\cl ምዕራፍ 7
\p
\v 1 የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን የነበረው ይህ መልኬ ጼዴቅ የባረከው አብርሃምን ነገሥታቱን ድል አድርጎ ሲመለስ ነበር።
\v 2 አብርሃምም ከማረጀው ከማንኛውም ነገር አንድ አሥረኛውን ለእርሱ ሰጠው። ‘መልኬ ጼዴቅ’ የሚለውም የስሙ ትርጉም ‘የጽድቅ ንጉሥ’ ደግሞም ‘የሳሌም ንጉ’ ማለትም ‘የሰላም ንጉሥ’ ማለት ነው።
\v 3 እርሱ አባትም ሆነ እናት፣ የትውልድ ሐረግም ሆነ የጅማሬ ወይም የፍጻሜ አመን የሌለው ነው። ይልቁንም እንደ እግዚአብሔር ልጅ ሁሉ እርሱም ካህን ሆኖ ለዘላለም ይኖራል።
\s5
\v 4 ይህ ሰው እንግዲህ ምን ያህል ታላቅ እንደነበረ አስቡ። አባታችን አብርሃም በጦርነት ካገኛቸው ምርጥ ነገሮች አንድ አሥረኛ የሚሆነውን ሰጥቶታል።
\v 5 በእርግጥ የክህነቱን አገልግሎት የተቀበሉትም የሌዊ ዝርያዎች ከአብርሃም ዝርያ የተገኙ ቢሆኑም ከሕዝቡ ማለትም ከእስራኤላውያን ወገኖቻቸው አሥራትን ይሰበስቡ ዘንድ በሕጉ ታዘዋል።
\v 6 ይሁን እንጂ የሌዊ ዝርያ ያልነበረው መልኬ ጼዴቅ የተስፋ ቃሎች ከነበሩት ከአብርሃም አሥራትን ተቀበለ፣ ባረከውም።
\s5
\v 7 ታናሹ በታላቁ እንደሚባረክ የሚካድ ነገር አይደለም።
\v 8 በአንድ በኩል ስናየው አሥራትን የሚቀበሉ ሰዎች አንድ ቀን ይሞታሉ በሌላ በኩል ስንመለከተው ግን ከአብርሃም አሥራትን የተቀበለው ሕያው ሆኖ እንደሚኖር ተገልጿል።
\v 9 በሌላ አነጋገር አሥራትን ይቀበል የነበረው ሌዊ እንኳን በአብርሃም በኩል አሥራትን ሰጥቷል።
\v 10 ምክንያቱም መልኬ ጼዴቅ አብርሃምን ባገኘው ጊዜ ሌዊ በቀደምት አባቱ በአብርሃም አብራክ ውስጥ ነበረና።
\s5
\v 11 ሕዝቡ ሕጉን የተቀበሉት በዚህ ሥርዓት በነበሩ ጊዜ ነበርና ፍፁምና በሌዊ ክህነት ማግኘት የሚቻል ቢሆን ኖሮ በአሮን ሥርዓት ሳይሆን በመልከ ጼዴቅ ሥርዓት የሚሾም ሌላ ካህን ወደፊት ይነሳ ዘንድ ምን ያስፈልግ ነበር?
\v 12 ክህነቱ የሚለውጥ ከሆነ ደግሞ ሕጉም መለወጥ ይገባዋል።
\s5
\v 13 እነዚህ ነገሮች እየተነገሩለት ያለው ከወገኖቹ ከቶ ማንም በመሠዊያው ላይ አገልግሎ የማያውቅ የሌላ ነገድ ወገን ነውና።
\v 14 እንግዲያውስ ጌታችን ካህናትን በሚመለከት ሙሴ ከቶውንም ምንም ካልተናገረለት ከይሁዳ ነገድ የመጣ መሆኑ ግልጽ ነው።
\s5
\v 15 መልከ ጼዴቅን የመሰለ ሌላ ካህን ቢነሳ የምንለው ይበልጥ ግልጽ ይሆናል።
\v 16 ይሄኛው ካህን ደግሞ ሰብዓዊ ዝርያን መሠረት በሚያደርገው ሕግ ሳይሆን የማይጠፋ የሕይወት ያይልን መሠረት ባደረገ ሕግ ካህን የሆነ ነው።
\v 17 ቅዱሳት መጻሕርትም ስለ እርሱ እንዲህ ሲሉ ይመሰክራሉ፦ “በመልከ ጼዴቅ ሥርዓት አንተ ለዘላለም ካህን ነህ”
\s5
\v 18 የቀደመው ትዕዛዝ ገለል የተደረገው ደካማና የማይጠቅም በመሆኑ ነውና።
\v 19 ሕጉ ፍጹም ያደረገው ምንም ነገር አልነበረምና። ይሁን እንጂ ከዚህ በኃላ ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት የተሻለ መተማመኛ አለ።
\s5
\v 20 ይሄኛው የተሻለው መተማመኛ ግን ያለ መሃላ እውን አልሆነም፣ ምክንያቱም እነዚህ ሌሎቹ ካህናት ምንም መሃላ አልፈጸሙም።
\v 21 “ጌታ ምሎአል ሃሳቡንም አይቀይርም፤ ‘አንተ ለዘላለም ካህን ነህ’” ተብሎ እንደተጻፈ።
\s5
\v 22 በዚህም ደግሞ ኢየሱ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል።
\v 23 በእርግጥም ሞት ካህናቱን ለዘላለም ከማገልገል ያግዳቸዋል። እብንዱ ሌላውን እየተካ፣ ካህናት የሆኑት የበዙት ከዚህ የተነሣ ነው።
\v 24 ኢየሱስ ግን ለዘላለም ስለሚኖር የእርሱ ክህነት የማይለወጥ ነው።
\s5
\v 25 ስለዚይ ስለ እነርሱ ሊማልድ ምን ጊዜም በሕይወት ስለሚኖር በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡትን ሙሉ በሙሉ ሊያድናቸው ይችላል።
\v 26 እንደዚህ ያለው ማለትም ኃጢአትና ነቀፋ የሌለበት፣ ንጡሕ፣ ከኃጢአተኞች የተለየ ከሰማያትም በላይ ከፍ ያለ ሊቀ ካህን ሊኖረን ይገባል።
\s5
\v 27 እርሱ ሊቀ ካህናቱ ሲያደርጉት እንደነበረው በመጀመሪያ ራሱ ለሠራቸው ኃጢአቶች ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ለፈፀሟቸው ኃጢአቶች በየቀኑ መሥዋዕቶችን ማቅረብ አያስፈልገውም። ራሱ አሳልፎ በሰጠ ጊዜ ይህንን ለአብዴና ለመጨረሻ ጊዜ አድርጎታል።
\v 28 ሕጉ ድካም ያለባቸውን ሰዎች ሊቀ ካህናት አድርጎ ይሾማልና፣ ከሕጉ በኃላ የመጣው የመሐላው ቃል ግን ለዘላለም ፍጹም የተደረገውን ልጁን ሾሟልና።
\s5
\c 8
\cl ምዕራፍ 8
\p
\v 1 እንግዲህ ልንናገር የፈለግነው ጉዳይ ዋና ነጥቡ ይሄ ነው፦ በሰማያት በልዑል እግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ ሊቀ ካህን አለን።
\v 2 እርሱ እግዚአብሔር በተከላት እውነተኛይቱ የማደሪያ ድንኳን፣ በተቀደሰው መቅደስ አገልጋይ የሆነ ነው እንጂ ማንኛውም ሟች ሰው አይደለም።
\s5
\v 3 ማንኛውም ሊቅቀ ካህናት የሚሾመው ስጦታዎችንና መሥዋዕቶችን ለማቅረብ በመሆኑ፣ የሚቀርብ ነገር ይዞ መገኘት አስፈላጊ ነው።
\v 4 ታዲያ ክርስቶስ አሁን በምድር ላይ የሚኖር ቢሆን በሕጉ መሠረት ስጦታዎችን የሚያቀርቡ ስላሉ እርሱ በፍጹም ካህን መሆን ባልቻለም ነበር።
\v 5 የማደሪያ ድንኳኑን ለመሥራት በተነሣ ጊዜ እግዚአብሔር ሙሴን”አስተውል፣ በተራራው ላይ ባየኸው ምሳሌ መሰረት ማንኛውንም ነገር እንድትሠራ” በማለት እንዳስጠነቀቀው ሁሉ እነርሱ የሰማያዊ ነገሮች ጥላና ግልባጭ የሆኑ ነገሮችን የሚያገለግሉ ናቸው።
\s5
\v 6 ነገር ግን በተሻለ ተስፋ ላይ የተመሠረተ የተሻለ ኪዳን መካከለኛው በመሆኑ ክርስቶስ አሁን የላቀ አገልግሎት ተቀብሏል።
\v 7 ያ የመጀመሪያው ኪዳን ነቀፋ ካልነበረው ሁለተኛ ኪዳን የሚፈለግበት ምንም ምክንያት አይኖርም ነበር።
\s5
\v 8 እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ነቀፋ ባገኘ ጊዜ እንደዚህ ብሎ ነበርና”አስተውሉ፣ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ዘመን ይመጣል” ይላል እግዚአብሔር።
\v 9 “ከግብፅ ምድር በእጆቼ መርቼ ባወጣኋቸው በዚያን ዘመን ከአባቶቻቸው ጋር እንደገባሁት እንደዚያ ቃል ኪዳን አይሆንም። በዚያ ኪዳኔ አልጸኑምና እኔም ችላ አልኳቸው” ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 10 “ከእነዚያ ዘመናት በኃላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ይህንን ኪዳን ነው፥ ‘ሕጌን በልቦናቸው አኖራለሁ፣ በልቦቻቸውም ላይ እጽፈዋለሁ። አምላካቸው እሆናለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።
\s5
\v 11 እያንዳንዱ ጎረቤቱን እያንዳንዱም ወንድሙን፥ ‘እግዚአብሔርን እወቅ እያለ አያስተምርም፣ እጅግ ታናሽ ከሆነው ጀምሮ እጅግ ታላቅ እስከሆነው ድረስ ሁሉም ያውቁኛልና።
\v 12 በዓመፅ ለፈጸሟቸው ድርጊቶች ሁሉ ምሕረት አደርጋለሁና ኃጢአቶቻቸውንም ከእንግዲህ አላስብምና”
\s5
\v 13 ‘አዲስ’ በማለቱም የመጀመሪያው ኪዳን አስረጅቷል። አሮጌ ነው ብሎ የገለጸውም ሊወገድ ተቃርቧል።
\s5
\c 9
\cl ምዕራፍ 9
\p
\v 1 የመጀመሪያው ኪዳን ቢሆን በዚህ ምድር ለሚከናወነው አምልኮም ሆነ ለአምልኮ ደንቦች ስፍራ ነበረው።
\v 2 በመገናኛው ድንኳን የተዘጋጀ ቅድስት የተባለ ውጨኛ ክፍል ነበር። በዚህ ስፍራ መቅረዙ፣ ጠረጴዛውና የመንግስቱ መገለጫ ኅብስት ነበሩበት።
\s5
\v 3 ከሁለተኛው መጋረጃም በስተጀርባ ቅድስተ ቅዱሳን የተባለ ሌላ ክፍል ነበረ።
\v 4 ዕጣን ለማጠን የሚሆን የወርቅ መሠዊያ ነበረው። ሙሉ በሙሉ በወርቅ የተለበጠ የኪዳን ታቦትም ነበረበት። በእርሱም ውስጥ መና ያለበት የወርቅ መሶብ፣ ያቆጠቆጠች የአሮን በትርና የኪዳኑ የድንጋይ ጽላቶች ነበሩት።
\v 5 በኪዳኑም ታቦት ላይ በስርየት መክደኛው ላ ያሰፈፉ የከበሩ የኩሩቤል ምስሎች ነበሩ። ይሁን እንጂ ስለ እነዚህ ሁሉ አሁን በዝርዝር መግለጽ አንችልም።
\s5
\v 6 እነዚህ ሁሉ ነገሮች ከተዘጋጁ በኃላ፣ ካህናቱ አገልግሎቶቻቸውን ለመፈጸም በመደበኛነት በማደሪያው ድንኳን ውጫዊው ክፍል በኩል ይገባሉ።
\v 7 ሊቀ ካህናቱ ግን በዓመት አንድ ጊዜ ወደ ሁለተኛው ክፍል ይገባል፣ በሚገባበትም ጊዜ ለራሱና ሕዝቡም ባለማወቅ ለፈጸሟቸው በደሎች የደም መሥዋዕት ይዞ እንጂ እንደዚሁ አይደለም።
\s5
\v 8 የመጀመሪያይቱ የመገናኛ ድንኳን በስፍራዋ ቆማ እስካለች ድረስ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የሚያመራው መንገድ ገና እንዳልተገለጠ መንፈስ ቅዱስ በምሳሌ እያሳየ ነው።
\v 9 ይህም ለአሁኑ ጊዜ ተምሳሌት ነው። አሁን እየቀረአቡ ያሉት ስጦታዎችም ይሁኑ መሥዋዕቶች የአምላኪውን ሕሊና ፍጹም ማድረግ የሚችሉ አይደሉም።
\v 10 ከተለያዩ የመንፃት ሥርዓቶች ጋር የተያያዙ ምግቦችና መጠጦች ብቻ ናቸው። እነዚህ ሁሉ አዲሱ ሥርዓት በሥራ ላይ እስኪውል ድረስ በሥጋዊ ደረጃ እንዲከበሩ የተሰጡ ሥርዓቶች ናቸው።
\s5
\v 11 ክርስቶስ በሰው እጆች በተሠራችው ሳይሆን ላቅ ባለችውና ይበልጥ ፍጹምና ቅድስት በመሆነችው፣ ከዚህም ከፍጥረታዊው ዓለም ባልሆነችው ድንኳን በኩል ለመጡት መልካም ነገሮች ሊቀ ካህናት ሆኖ መጥቷል።
\v 12 ክርስቶስ እጅግ ቅድስት ወደሆነችው ስፍራ አንድ ጊዜ ለሰዎች ሁሉ የገባውና የዘላለም ቤዛችንን ያስገኘልን በፍየሎችና በጥጃዎች ደም ሳይሆን በራሱ ደም ነው።
\s5
\v 13 የፍየሎችና የኮርማዎች ደም እንዲሁም የጊደሮች አመድ በሥርዓታዊ ደረጃ ንፁሕ ባልሆኑት ላይ መረጨቱ የሚያጠራቸውና ሰውነቶቻቸውንም ንፁሕ የሚያደርገው ከሆነ፣
\v 14 ይልቁንም ነውር ሳይኖረው በዘላለማዊ መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም ሕያው እግዚአብሔርን እናገለግል ዘንድ ሕሊናችንን ከሞተ ሥራ ምን ያህል ያነጻን ይሆን?
\v 15 ከዚህም የተነሳ ክርስቶስ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት በእግዚአብሔር የተጠሩት ስለ ዘላለም ርስት የተሰጣቸውን የስፋ ቃል ይቀበሉ አንድ በመጀመሪያው ኪዳን ሥር ከነበረባቸው የኃጢአት ቅጣት ነፃ እንዲወጡ የሞት ቅጣት ተፈጽሞ ስለነበረ ነው።
\s5
\v 16 ይህም የሆነው አንድ ሰው ኑዛዜ እንደተወ ሲገለጽ ኑዛዜ የተወውን ሰው መሞት ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው።
\v 17 ምክንያቱም ኑዛዜ የሚጸናው ሞት ተከስቶ ከሆነ ብቻ ነው፣ ተናዛዡ በሕይወት እስካለ ሊጸና አይችልምና።
\s5
\v 18 እንደዚህም በመሆኑ የመጀመሪያው ኪዳን እንኳን ያለ ደም አልጸናምና።
\v 19 በሕጉ ውስጥ ያሉትን ማንኛቸውንም ትዕዛዛት ሙሴ ለሕዝቡ ሁሉ በሰጠ ጊዜ የጥጆችንና የፍየሎችን ደም ከውሃ፣ ከቀይ የበግ ፀጉርና ከሂሶጵ ጋር ቀላቅሎ በራሱ በሕጉ መጽሐፍና በሕዝብ ሁሉ ላይ ይረጭ ነበርና።
\v 20 ይህንንም ካደረገ በኃላ “እግዚቸብሔር ለእናንተ ሕግጋቱን የሰጠበት የኪዳኑ ደም ይህ ነው” ይል ነበር።
\s5
\v 21 በዚያው ዓይነት መንገድ ደሙን በመገናኛው ድንኳንና ለክህነት አገልግሎት በሚውሉት ዕቃዎች ሁሉ ላይ ይረጭ ነበር።
\v 22 ሕጉ በሚለውም መሠረት ሁሉም ነገር የሚነጻው በደም ነበር ማለት ይቻላል። ደምም ካልፈሰሰ በስተቀር ይቅርታ የለም።
\s5
\v 23 ስለሆነም በሰማይ ያሉት ነገሮች ግልባጮችም በእነዚህ የእንስሳት መሥዋዕቶች ይነጹ ዘንድ አስፈላጊ ነበር። ይሁን እንጂ ሰማያዊ የሆኑት ነገሮች ራሳቸው እጅግ በተሻሉ መሥዋዕት መንጻት ይገባቸዋል።
\v 24 ክርስቶስ በእጅ ወደተሠራው የእውነተኛውም ግልባጭ ብቻ ወደነበረው ቅድስተ ቅዱሳን አልገባምና። ይልቁንም እርሱ የገባው እግዚአብሔር ባለበት ስለ እኛ አሁን እግዚአብሔር ፊት ወደሚቀርብበት ሰማይ በቀጥታ ገብቷል።
\s5
\v 25 ወደዚያም የገባው የሌላውን ደም ይዞ በየዓመቱ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን እንደሚገባው እንደ ሊቀ ካህናቱ በየጊዜው ራሱን ለማቅረብ አይደለም።
\v 26 እንደዚያ ቢሆን ኖሮ ከዓለም ጅማሬ አንስቶ ብዙ ጊዜ መከራ መቀበል ባስፈለገው ነበር። አሁን ግን ራሱን መሥዋዕት በማድረግ ኃጢአትን ለማስወገድ በዘመናት መጨረሻ የተገለጠው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።
\s5
\v 27 እያንዳንዱ ሰው አንድ ጊዜ መሞት ከዚያ በኃላም ወደ ፍርድ መቅረብ እንደሚገባው ሁሉ
\v 28 እንደዚሁም የብዙዎችን ኃጢአት ለማስወገድ መሥዋዕት ሆኖ የቀረበው ክርስቶስ ኃጢአትን ለማስወገድ ዓላማ ሳይሆን በትዕግሥት ለሚጠባበቁት ድነትን ያስገኝላቸው ዘንድ ዳግመኛ ይገለጣል
\s5
\c 10
\cl ምዕራፍ 10
\p
\v 1 ሕጉ ሊመጡ ላሉ መልካም ነገሮች ጥላ ብቻ እንጂ እውነተኛው አካል አይደለም። ሕጉ ካህናት ያለማቋረጥ በየዓመቱ በሚያቀርቧቸው በነዚያው መሥዋዕቶች ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡትን ከቶ ፍጹም ሊያደርጋቸው አይችልም።
\v 2 ቢችል ኖሮ እነዚያ መሥዋዕቶች መቅረባቸው ይቀር አልነበረምን? እንደዚያ ቢሆን ኖሮ የሚያመልኩት አንድ ጊዜ ከኃጢአታቸው ከነጹ በኋላ ስለ ኃጢአታቸው የሚያስታውሱት ነገር ምንም አይኖርም ነበር።
\v 3-4 ነገር ግን በእነዚያ መሥዋዕቶች ውስጥ በየዓመቱ የተፈጸሙትን ኃጢአቶች የሚያስታውስ ነገር አለ። ለዚህ ምክንያቱ የኮርማዎችና የበጎች ደም ኃጢአትን ማስወገድ ባለመቻሉ ነው።
\s5
\v 5 ክርስቶስ ወደ ዓለም ሲመጣ፣ “አንተ መሥዋዕቶችን ወይም ስጦታዎችን አልፈለግህም። ይልቅ ለእኔ ሥጋን አዘጋጀህልኝ።
\v 6 አንተ በሚቃጠል መባ ወይም በኃጢአት መሥዋዕት ደስ አልተሰኘህም።
\v 7 ቀጥሎም፣ “እግዚአብሔር ሆይ በመጽሐፍ ስለ እኔ እንደተጻፈው እነሆ ፈቃድህን ለማድረግ እዚህ አለሁ” ብሏል።
\s5
\v 8 ከላይ እንደተጠቀሰው፡“አንተ መሥዋዕቶችን፣ ስጦታዎችን ወይም ለኃጢአት የሚቃጠሉ ሙሉ መሥዋዕቶችን ማለትም በሕጉ መሠረት የሚቀርቡ መሥዋዕቶችን አልፈለግህ፣ በእነርሱም ደስ ስላልተሰኘህም” ብሏል።
\v 9 ደግሞም፣ “እነሆ ፈቃድህን ለማድረግ እዚህ አለሁ” አለ። ሁለተኛውን ሥርዓት ለመትከል የመጀመሪያውን ሥርዓት ወደ ጎን ያደርገዋል።
\v 10 በሁለተኛው ሥርዓት ለአንድ ጊዜና ለዘላለም በቀረበው በኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ አማካኝነት በእግዚአብሔር ፈቃድ ተቀድሰናል።
\s5
\v 11 በእርግጥ እያንዳንዱ ካህን ኃጢአትን ፈጽሞ ሊያስወግድ የማይችሉትን መሥዋዕቶች ለማቅረብ በየዕለቱ ለማገልገል ይቆማል።
\v 12 ነገር ግን ክርስቶስ ለኃጢአት ሁሉ ለዘላለም የሚሆን አንድ መሥዋዕት ካቀረበ በኋላ፣
\v 13 ጠላቶቹ እስኪዋረዱና የእግሩ መረገጫ እስኪሆኑ ድረስ እየተጠባበቀ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጧል።
\v 14 ይህም በአንድ መሥዋዕት የተቀደሱትን ለዘላለም ፍጹማን ስላደረጋቸው ነው።
\s5
\v 15 ደግሞም መንፈስ ቅዱስ ለእኛ ይመሰክርልናል። ምክንያቱም በመጀመሪያ፣
\v 16 “ ከእነዚያ ቀኖች በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ቃልኪዳን ይህ ነው፡ ሕጎቼን በልባቸው ውስጥ አደርጋለሁ፣ ደግሞም በአእምሮአቸው ውስጥ እጽፈዋለሁ” ስላለ ነው።
\s5
\v 17 ቀጥሎም፣ “ኃጢአታቸውንና ዓመጻቸውን ከእንግዲህ አላስበውም” አለ።
\v 18 ለእነዚህ ነገሮች ይቅርታ በተረገበት በዚያ ለኃጢአት ከእንግዲህ ወዲያ መሥዋዕት አይቀርብም።
\s5
\v 19 ስለዚህ ወንድሞች፣ በኢየሱስ ደም አማካኝነት ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የመግባት ድፍረት አለን።
\v 20 ይህም በመጋረጃው ማለትም በሥጋው አማካኝነት ለእኛ የከፈተልን አዲስና ሕያው መንገድ ነው።
\v 21 በእግዚአብሔር ቤት ታላቅ ካህን ስላለን፣
\v 22 ልባችን በመረጨት ከክፉ ኅሊና ሁሉ ነጽቶ፣ ሥጋችንም በንጹሕ ውኃ ታጥቦ ባገኘነው የእምነት ሙሉ ዋስትና በእውነተኛ ልብ እንቅረብ።
\s5
\v 23 ተስፋን የሰጠ እግዚአብሔር ታማኝ ስለሆነ፣ አምነን የምንመሰክረውን ተስፋ ያለ ማወላወል አጥብቀን እንያዝ።
\v 24 ለፍቅርና ለመልካም ሥራ እርስ በርስ እንዴት እንደምንነቃቃ እናስብ።
\v 25 አንዳንዶቹ ልማድ እንዳደረጉት በአንድነት መሰብሰባችንን አንተው። በዚህ ፈንታ ቀኑ እየቀረበ መምጣቱን ስታዩ እርስ በርሳችሁ ይበልጥ ተበረታቱ።
\s5
\v 26 የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ሆን ብለን ኃጢአት ማድረጋችንን የምንቀጥል ከሆንን፣ ከእንግዲህ ለኃጢአት የሚሆን መሥዋዕት አይኖርም።
\v 27 ይልቅ የሚጠብቀን የሚያስፈራ ፍርድና የእግዚአብሔርን ጠላቶች ሊበላ ያለ ብርቱ እሳት ብቻ ነው።
\s5
\v 28 የሙሴን ሕግ የናቀ ማናቸውም ሰው በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች ያለ ምንም ምሕረት ይሞታል።
\v 29 ታዲያ የእግዚአብሔርን ልጅ የናቀ፣ የተቀደሰበትን የቃልኪዳኑን ደም እንደ እርኩስ የቆጠረ፣ የጸጋን መንፈስ የሰደበ ሰው ምን ያህል የባሰ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል?
\s5
\v 30 “በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ዋጋን እመልሳለሁ” ያለውን እናውቃለንና። ደግሞም፣ “ጌታ በሕዝቡ ይፈርዳል።”
\v 31 በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነገር ነው!
\s5
\v 32 ነገር ግን ከበራላችሁ በኋላ በእንዴት ያለ ታላቅ ሥቃይ ውስጥ እንደታገሣችሁ እነዚያን የቀደሙ ወቅቶች አስታውሱ።
\v 33 በስድብና በስደት ለሕዝብ መሳለቂያ ተዳርጋችኋል፣ ደግሞም በዚህ ዓይነቱ ሥቃይ ውስጥ ካለፉ ሰዎችም ጋር አብራችሁ ነበራችሁ።
\v 34 ለእስረኞች ርኅራኄ አሳያችሁ፣ የተሻለና ዘላለማዊ ሀብት ለራሳችሁ እንዳላችሁ በመረዳትም የንብረታችሁን መነጠቅ በደስታ ተቀበላችሁ።
\s5
\v 35 ስለዚህ ታላቅ ዋጋ ያለውን ድፍረታችሁን አትጣሉ።
\v 36 ፈቃዱን ካደረጋችሁ በኋላ እግዚአብሔር ለእናንተ ተስፋ የገባውን ነገር ለመቀበል መታገሥ ያስፈልጋችኋል።
\v 37 “በጣም በቅርብ ጊዜ ውስጥ የሚመጣው በእርግጥ ይመጣል፣ አይዘገይምም።
\s5
\v 38 የእኔ የሆነው ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል። ወደኋላ ቢመለስ በእርሱ ደስ አይለኝም።”
\v 39 እኛ ግን ለጥፋት ወደኋላ እንደሚያፈግፍጉት አይደለንም። ይልቅ እኛ ነፍሳቸውን ለማዳን ከሚያምኑት ነን።
\s5
\c 11
\cl ምዕራፍ 11
\p
\v 1 እንግዲህ እምነት ሰው በተስፋ ለሚጠበቀው ነገር ማረጋገጫ ያልታየውም ነገርም አስረጅ ነው።
\v 2 የቀድሞ አባቶቻችንም እምነታቸው የተረጋገጠው በዚሁ ነበር።
\v 3 ፍጥርተ-ዓለሙ በእግዚአብሔር ትእዛዝ መፈጠሩን፣ የሚታየውም ከሚታዩት ነገሮች የተፈጠረ አለመሆኑን በእምነት እንረዳለን።
\s5
\v 4 አቤል ከቃየል የበለጠ ተቀባይነት ያለውን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቀረበው በእምነት ነበር። ጻድቅ እንደሆነ የተመሰከረለትም በዚህ ምክንያት ነበር። ስላቀረባቸው መሥዋዕቶች እግዚአብሔር መስክሮለታል። ቢሞትም እንኳ አሁንም ይናገራል።
\s5
\v 5 ሄኖክ ሞትን ሳያይ ወደ ላይ የተወሰደው በእምነት ነበር። “እግዚአብሔር ስለወሰደው አልተገኘም።” ከመወሰዱ በፊት እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተነግሮለታና።
\v 6 ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ምክንያቱም፣ ወደ እግዚአብሔር የሚመጣ፣ እግዚአብሔር እንዳለና እርሱን ለሚሹትም ዋጋን እንደሚሰጥ ማመን ስለሚገባው ነው።
\s5
\v 7 ኖኅ ገና ስላልታዩ ነገሮች ከእግዚአብሔር ሲያስጠነቅቀው እግዚአብሔርን በመፍራት ቤተሰቡን የሚያድንበትን መርከብ የሠራው በእምነት ነበር። ይህን በማድረግ ዓለምን ኮንኖ በእምነት የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።
\s5
\v 8 አብርሃም በተጠራ ጊዜ ርስትን ወደሚቀበልበት ቦታ ታዞ የሄደው በእምነት ነበር። የወጣው ወዴት እንደሚሄድ ሳያውቅ ነበር።
\v 9 በተስፋው ምድር እንደ ባዕድ የኖረውም በእምነት ነበር። ያን ተስፋ ከእርሱ አብረው ከሚወርሱት እንደ ይስሐቅና እንደ ያዕቆብ በድንኳን ውስጥ ኖረ።
\v 10 ይሄውም እግዚአብሔር መሠረት ያላትን፣ ያቀዳትንና ያነጻትን ከተማ ይጠባበቅ ስለነበር ነው።
\s5
\v 11 አብርሃምና ሣራ እጅግ አርጅተው ሳሉ እንደሚወልዱ በተነገራቸው ጊዜ፣ ወንድ ልጅን እንደሚሰጣቸው ተስፋ የገባላቸውን እግዚአብሔር ታማኝ አድርገው ስለቆጠሩ ሣራ ለማርገዝ ኃይል ያገኘችው በእምነት ነበር።
\v 12 በመሆኑም፣ ሊሞት ከተቃረበ ከዚህ አንድ ሰው ቁጥር ስፍር የሌላቸው ዝርያዎች ተገኙ። እነርሱም በሰማይ እንዳሉ ከዋክብትና በባሕር ጠረፍ እንዳለ አሸዋ በዙ።
\s5
\v 13 እነዚህ ሁሉ የተሰጧቸውን ተስፋዎች ሳይጨብጡ እምነታቸውን እንደጠበቁ ሞቱ። ይልቁንም እነዚህን ተስፋዎች ከሩቅ አይተው ስለተቀበሏቸው በምድር ላይ እንግዶችና መጻተኞች መሆናቸውን ተገነዘቡ።
\v 14 እንደዚህ የሚሉ ሰዎች የራሳቸው የሆነ አገር እንዲሚሹ በግልጽ ያሳያሉ።
\s5
\v 15 በእርግጥ ለቀው የመጡትን አገር ቢያሰቡ ኖሮ ለመመለስ ዕድሉ ነበራቸው።
\v 16 አሁን ግን የሚፈልጉት የተሻለውን ሰማያዊ አገር ነው። ስለዚህም፣ እግዚአብሔር ከተማን ስላዘጋጀላቸው አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ አያፍርም።
\s5
\v 17 አብርሃም በተፈተነ ጊዜ ይስሐቅን ያቀረበው በእምነት ነበር። አዎን፣
\v 18 “ዝሮችህ የሚጠሩት በይስሐቅ ነው” የተባሉለትን ተስፋዎቹን በደስታ ስለተቀበለ አንድ ልጁን ለመሥዋዕት አቀረበ።
\v 19 አብርሃም፣ እግዚአብሔር ይስሐቅን ከሞት ሊያስነሣ እንደሚችል አምኖ ነበር። ይስሐቅን ከሞት የመነሣት አምሳያ አድርጎ መልሶ ተቀበለው።
\s5
\v 20 ይስሐቅ ገና ወደፊት የሚመጡትን ነገሮች አስቦ ያዕቆብንና ኤሳውን በእምነት ባረካቸው።
\v 21 ያዕቆብ ፍጻሜው በተቃረበ ጊዜ፣ የዮሴፍን ልጆች እያንዳንዳቸውን የባረካቸውና በምርኩዙ አናት ተደግፎ የሰገደው በእምነት ነበር።
\v 22 ዮሴፍ ሊሞት ሲቃረብ የእስራኤል ልጆች ከግብጽ እንደሚወጡ የተናገረውና የእርሱን አጽሙን እንዲወስዱ ያዘዘው በእምነት ነበር።
\s5
\v 23 ሙሴ ሲወለድ ወላጆቹ መልከ መልካም ሕፃን መሆኑን አይተው የንጉሡን ትእዛዝ ሳይፈሩ ለሦስት ወራት የደበቁት በእምነት ነበር።
\v 24 ሙሴም ካደገ በኋላ የፈርዖን የልጅ ልጅ፣ እንዳይባል እምቢ ያለው በእምነት ነበር።
\v 25 ለአጭር ጊዜ በኃጢአት ደስ ከመሰኘት ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራን መካፈልን መረጠ።
\v 26 ዓይኖቹ ወደፊት የሚቀበለውን ዋጋ አተኩረው ስለተመለከቱ፣ በግብጽ ከሚገኝ ሀብት ይልቅ ክርስቶስን መከተል የሚያስከትልበትን ውርደት የላቀ ብልጽግና አድርጎ አሰበ።
\s5
\v 27 ሙሴ ግብጽን ለቆ የወጣው በእምነት ነበር። የማይታየውን እርሱን ተመልክቶ በአቋሙ ስለጸና የንጉሡን ቁጣ አልፈራም።
\v 28 ቀሳፊው የእስራኤልን የበኩር ልጆች እንዳይነካ ሙሴ የፋሲካ በዓልንና የደም ርጭት ሥርዓትን ያካሄደው በእምነት ነበር።
\s5
\v 29 እስራኤላውያን በደረቅ መሬት ላይ እንደሚሄዱ ቀይ ባሕርን የተሻገሩት በእምነት ነበር። ግብጻውያን ይህን ለማድረግ በሞከሩ ጊዜ ተዋጡ።
\v 30 የኢያሪኮ ግንብ በእምነት የወደቀው ለሰባት ቀናት ከተከበበ በኋላ ነበር።
\v 31 ሴተኛ አዳሪዋ ረዓብ ሰላዮቹን ለደህንነታቸው ተጠንቅቃ ስለተቀበለቻቸው ከማይታዘዙት ጋር ያልጠፋችው በእምነት ነበር።
\s5
\v 32-33 እንግዲህ ከዚህ የበለጠ ምን ልበል? በእምነት መንግሥታትን ድል ስላደረጉት፣ ፍትህን ስላስከበሩትና የተስፋ ቃሎችን ስለተቀበሉት ስለነጌደዎን፣ ባርቅ፣ ሳምሶን፣ ዮፍታሄ፣ ዳዊት፣ ሳሙኤልና ነቢያት እንዳልናገር ጊዜ ያጥረኛል።
\v 34 እነርሱ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፣ የእሳትን ኃይል አጠፉ፣ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፣ ከበሽታ ተፈወሱ፣ በጦርነት ኃያላን ሆኑ፥ የባዕድን ሠራዊት አባረሩ።
\s5
\v 35 ሴቶች ሙታናቸው ከሞት ተነሡላቸው። ሌሎች የተሻለውን ትንሣኤ ያገኙ ዘንድ ከእስር መፈታታቸውን ለመቀበል እምቢ በማለት ተሠቃዩ።
\v 36 የተቀሩት ደግሞ በስድብና በግርፋት፣ እንዲያውም በሰንሰለት በመታሰር ተሠቃዩ።
\v 37 በድንጋይ ተወገሩ። በመጋዝ ለሁለት ተሰነጠቁ። በሰይፍ ተገደሉ። ይህ ዓለም ስላልተገባቸው
\v 38 በምድረበዳ፣ በተራሮች፣ በዋሻዎችና በየጉድጓዱ እየተጎሳቆሉ፣ መከራ እየተቀበሉና ግፍ እየተፈጸመባቸው የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው በመንከራተት ዞሩ።
\s5
\v 39 እነዚህ ሰዎች ሁሉ ስለ እምነታቸው በእግዚአብሔር ዘንድ የተመሰከረላቸው ቢሆኑም የተሰጣቸውን ተስፋ አልተቀበሉም።
\v 40 እነርሱ ያለ እኛ ፍጹም ስለማይሆኑ እግዚአብሔር ለእኛ የተሻለውን ነገር አስቀድሞ ሰጠን።
\s5
\c 12
\cl ምዕራፍ 12
\p
\v 1 እንደነዚህ ያሉ እጅግ ብዙ ምስክሮች ስላሉን፣ የሚከብደንን ነገር ሁሉና በቀላሉ የሚጠላልፈንን ኃጢአት አሽቀንጥረን እንጣል። ከፊታችን ያለውንም ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ።
\v 2 በእምነታችን ጀማሪና ፍጹም አድራጊ ኢየሱስ ላይ ዓይኖቻችን እንትከል። እርሱ ከፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉንና መስቀሉ የሚያስከትለውን ውርደት ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል።
\v 3 እንዳትደክሙ ወይም ልባችሁ እንዳይዝል፣ ከኃጢአተኞች የተሰነዘረበትን እንዲህ ያለውን የጥላቻ ንግግር የታገሠውን እርሱን አስቡ።
\s5
\v 4 ደም እስከማፍሰስ ድረስ ኃጢአትን አልተቃወማችሁም፣ አልታገላችሁትምም።
\v 5 ደግሞም እንደ ልጆች፡ “ልጄ ሆይ የጌታን ቅጣት አታቅልል፣ በሚቀጣህም ጊዜ ልብህ አይዛል።
\v 6 ጌታ የሚወደውን ይገሥጻል፣ የሚቀበለውን ማንኛውንም ልጅ ይቀጣል" በማለት የተናገራችሁን ማበረታቻ ምክር ረስታችኋል።
\s5
\v 7 አባት በልጆቹ እንደሚደረግ እግዚአብሔርም በእናንተ ላይ ስለሚያደርግ፣ መከራን እንደ ተግሣጽ በመቁጠር ታገሡ። ለመሆኑ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው?
\v 8 ነገር ግን እኛ ሁላችን ከምንካፈለው ተግሣጽ ውጭ ከሆናችሁ፣ ዲቃሎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም።
\s5
\v 9 ከዚህም በላይ የሚቀጡን ምድራዊ አባቶች ነበሩን፤ እኛም እናከብራቸው ነበር። ይልቁንስ መንፈስ ለሆነው አባት እየታዘዝን መኖር የቱን ያህል ይገባናል?
\v 10 በእርግጥ አባቶቻችን ለእነርሱ መልካም መስሎ እንደታያቸው ለጥቂት ጊዜ ይቀጡን ነበር፣ እግዚአብሔር ግን የእርሱን የቅድስናው ተካፋዮች እንድንሆን ለጥቅማችን ያቀጣናል።
\v 11 ቅጣት በወቅቱ የሚያም እንጂ አስደሳች አይደለም። ይሁን እንጂ፣ ለለመዱት በመጨረሻ ሰላማዊ የጽድቅ ፍሬን ያፈራል።
\s5
\v 12 ስለዚህ የዛሉ እጆቻችሁን ወደ ላይ አንሡ፣ የደከሙ ጉልበቶቻችሁንም እንደገና አበርቱ፤
\v 13 የሚያነክስ ማንም ቢኖር እንዲፈወስ እንጂ እንዳይናጋ እግሮቻችሁ የሚራመዱባቸውን መንገዶች ቀና አድርጉ።
\s5
\v 14 ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ተከታተሉ፣ ቅድስናንም ተከታተሉ፣ ያለ ቅድስና ማንም ጌታን ሊያይ አይችልም።
\v 15 ማንም ከእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጎድል፣ መራራ ሥርም አድጎ እንዳያስጨንቅና ብዙዎችን እንዳይመርዝ ተጠንቀቁ።
\v 16 ለአንድ መብል ብሎ ብኩርናውን እንደሸጠ እንደ ኤሳው እግዚአብሔርን የማይፈራ፣ ወይም ሴሰኛ የሆነ ማንም እንዳይኖር ተጠንቀቁ።
\v 17 ከዚያ በኋላ በረከትን ለመውረስ እያለቀሰ በትጋት ቢፈልግም፣ ከአባቱ ዘንድ የይቅርታ እድል እንዳጣና እንደተጣለ ታውቃላችሁ።
\s5
\v 18 የሚቃጠል እሳት፣ ጨለማ፣ ጭጋግና ማዕበል ወዳለበት በእጅ ሊነካ ወደሚችል ተራራ ገና አልመጣችሁም።
\v 19 የሰሙትም ሌላ ቃል እንዳይነገራቸው እስከሚለምኑ ወዳደረሳቸው ቃልን ወደሚያሰማ ድምጽ ወይም የመለከት ጩኹት ገና አልመጣችሁም።
\v 20 ይህም፣ “እንስሳም እንኳ ቢሆን ተራራውን ከነካ በድንጋይ ይወገር” ተብሎ የተሰጠውን ትእዛዝ ሊሸከሙት አልቻሉም።
\v 21 ሙሴ፣ “እጅግ ስለፈራሁ እየተንቀጠቀጥሁ ነኝ” እስከሚል ድረስ ይህ ስፍራ አስፈሪ ነበር።
\s5
\v 22 አሁን ግን፣ የሕያው እግዚአብሔር ከተማ ወደሆነችው ወደ ጽዮን ተራራ፣ አእላፋት መላእክት በደስታ ወደሚያመልኩባት ሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም መጥታችኋል፤
\v 23 በሰማይ ወደሚገኙት የበኩራን ሁሉ ጉባኤ፣ የሁሉም ፈራጅ ወደሆነው እግዚአብሔርና ፍጹም የተደረጉ የጻድቃን መንፈሶች ወዳሉበት መጥታችኋል፤
\v 24 የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ወደሆነው ኢየሱስና ከአቤል ደም የተሻለውን ወደሚናገር ወደተረጨው ደም ደርሳችኋል።
\s5
\v 25 የሚናገራችሁን እምቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ። እነርሱ በምድር ላይ ሆኖ ያስጠነቀቃቸውን እምቢ በማለታቸው ካላመለጡ፣ በሰማይ ሆኖ ከሚያስጠነቅቀን በእርግጥ አናመልጥም።
\v 26 በዚያን ጊዜ ድምጹ ምድርን አናወጠ። ነገር ግን፣ “አንድ ጊዜ ደግሜ ምድርን ብቻ ሳይሆን ሰማያትንም አናውጣለሁ” በማለት አሁን ተስፋ ሰጥቷል።
\s5
\v 27 “አንድ ጊዜ ደግሜ” የሚል ቃል፣ ያልተናወጡ ነገሮች መጽናታቸውን፣ የተናወጡት ማለትም የተፈጠሩት ነገሮች መወገዳቸውን ያመላክታል።
\v 28 ስለዚህ፣ ሊናወጥ የማይችል መንግሥት ስለተቀብልን አምላካችንን እናመስግነው፣ ደግሞም እግዚአብሔርን ተቀባይነት ባለው በአክብሮትና በፍርሃት እናምልከው፣
\v 29 ምክንያቱም አምላካችን የሚባላ እሳት ነው።
\s5
\c 13
\cl ምዕራፍ 13
\p
\v 1 በወንድማማችነት ፍቅር መዋደዳችሁን ቀጥሉ።
\v 2 እንግዶችን መቀበል አትርሱ፣ አንዳንድ ሰዎች ይህን ሲያደርጉ ሳያውቁት መላእክትን አስተናግደዋል።
\s5
\v 3 ከእነርሱ ጋር እንደታሰረ ሆናችሁ፣ በሰውነታችሁም እንደ እነርሱ መከራን እንደሚቀበል ሆናችሁ በእስራት ያሉትን አስቡ።
\v 4 ጋብቻ በሁሉም ዘንድ የተከበረ መኝታውም ንጹሕ ይሁን፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር በሴሰኞችና በአመንዝራዎች ላይ ይፈርድባቸዋል።
\s5
\v 5 አኗኗራችሁ ከገንዘብ ፍቅር የጸዳ ይሁን። እግዚአብሔር ራሱ፣ “እኔ ፈጽሞ አልተውህም፣ ደግሞም አልጥልህም” ስላለ፣ ባላችሁ ነገር ረክታችሁ ኑሩ።
\v 6 ስለዚህ፣ “ጌታ ረዳቴ ነው፤ አልፈራም። ሰውስ ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” ብለን በድፍረት እንናገራለን።
\s5
\v 7 የእግዚአብሔርን ቃል የነገሯችሁን መሪዎቻችሁን አስቡ፣ የምግባራቸውንም ፍሬ ተመልከቱ፤ በእምነታቸውም ምሰሏቸው።
\v 8 ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንት፣ ዛሬና ለዘላለምም ያው ነው።
\s5
\v 9 በልዩ ልዩ እንግዳ ትምህርቶች አትወሰዱ፣ ለሚከተሏቸው ሰዎች ፋይዳ የሌላቸውን የአመጋገብ ሥርዓቶች በመጠበቅ ሳይሆን ልብ በጸጋ ሲጸና መልካም ነው።
\v 10 በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉት ከእርሱ እንዲበሉ ያልተፈቀደላቸው መሠዊያ አለን።
\v 11 ሊቀካህናቱ ለኃጢአት ስርየት የተሠዋውን የእንስሳት ደም ወደ ቅድስት ያመጣል፣ የእንስሳቱ ሥጋ ግን ከሰፈር ውጭ ይቃጠላል።
\s5
\v 12 ደግሞም ኢየሱስ ሰዎችን በገዛ ደሙ ለመቀደስ ከከተማይቱ ቅጥር ውጭ መከራን ተቀበለ።
\v 13 ስለዚህ እኛም እርሱ የተሸከመውን ውርደት ተሸክመን ከሰፈር ውጭ ወደርሱ እንሂድ።
\v 14 በዚህ ምድር ምንም ዓይነት ዘላቂ ከተማ የለንም። ነገር ግን የምትመጣውን ከተማ እንጠብቃለን።
\s5
\v 15 የስሙን ታላቅነት የሚናገሩ የከንፈሮቻችንን ፍሬ፣ ማለትም የምስጋና መሥዋዕቶችን ያለማቋረጥ በኢየሱስ በኩል ለእግዚአብሔር ማቅረብ ይገባናል።
\v 16 ደግሞም መልካም ማድረግንና እርስ በርስ መረዳዳትን አትርሱ፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር የሚደሰተው እንደነዚህ ባሉ መሥዋዕቶች ነው።
\v 17 ተጠያቂነት ስላለባቸው ለነፍሳችሁ እንክብካቤ ለሚያደርጉ ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ፣ ተገዙላቸውም። ለእናንተ ስለማይጠቅም በሐዘን ሳይሆን በደስታ እንዲንከባከቧችሁ ታዘዟቸው።
\s5
\v 18 በሁሉም ነገር የከበረ ሕይወት ለመኖር የሚፈልግ ንጹሕ ኅሊና ስላለን ጸልዩልን።
\v 19 ወደ እናንተ ቶሎ መመለስ እንድችል ይበልጥ ይህን እንድታደርጉ አበረታታችኋለሁ።
\s5
\v 20-21 እንግዲህ በዘላለም ኪዳን ደም የበጎች ታላቅ እረኛ የሆነውን ጌታችን ኢየሱስን፣ ከሙታን ያስነሣው የሰላም አምላክ እግዚአብሔር፣በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት በእኛ ውስጥ የሚሠራውን፣ በእርሱ ፊት ደስ የሚያሰኘውን ፈቃዱን እንድታደርጉ በማናቸውም መልካም ነገር ያስታጥቃችሁ። ከዘላለም እስከ ዘላለም ለእርሱ ክብር ይሁን። አሜን።
\s5
\v 22 ወንድሞች ሆይ፤ አሁን በዐጭሩ የጻፍሁላችሁን ማበረታቻ እንድትቀበሉ አደፋፍራችኋለሁ።
\v 23 ወንድማችን ጢሞቴዎስ እንደተፈታ ዕወቁ፣ ቶሎ ከመጣም ከእርሱ ጋር አብሬ አያችኋለሁ።
\s5
\v 24 ለመሪዎችና ለቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ። በኢጣልያ ያሉት ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
\v 25 ጸጋ ከሁላችሁም ጋር ይሁን።