am_ulb/58-PHM.usfm

52 lines
3.9 KiB
Plaintext

\id PHM
\ide UTF-8
\h ፊልሞና
\toc1 ፊልሞና
\toc2 ፊልሞና
\toc3 phm
\mt ፊልሞና
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 ስለክርስቶስ ኢየሱስ እስረኛ የሆነው ጳውሎስ ከወንድማችን ከጢሞቴዎስ ጋር ለተወደደው ወንድማችንና የሥራ አጋራችን ለሆነው ለፊሊሞና፣
\v 2 ለእህታችን ለአፒፊያ፣አብሮን ወታደር ለሆነው ለአክሪፋ እንዲሁም በቤትህ ላለችው ቤተክርስቲያን፡
\v 3 ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሠላም ለእናንተ ይሁን።
\s5
\v 4 በጸሎቴ ሁሉ ስላንተ እያነሳሁ ሁልጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
\v 5 ምክንያቱም በጌታ በኢየሱስ ስላለህ እምነት ለቅዱሳንም ሁሉ ስላለህ ፍቅር ሰምቻለሁ።
\v 6 በክርስቶስ በኩል የመልካም ነገር ሁሉ እውቀት በእኛ ውስጥ ስላለ በእምነት ያለህ ተካፋይነት ውጤታማ እንዲሆን እጸልያለሁ።
\v 7 ወንድሜ ሆይ፣ ለዚህም ምክንያቱ የቅዱሳን ሁሉ ልብ በአንተ በማረፉ ምክንያት በፍቅርህ በጣም ደስ ስላለኝና ስለተጽናናሁ ነው።
\s5
\v 8 ስለዚህም ምንም እንኳ ምን ማድረግ እንዳለብህ በክርስቶስ ለማዘዝ ድፍረት ቢኖረኝም
\v 9 በዚህ ፈንታ እንደ ሽማግሌው አሁን ደግሞ ስለ ክርስቶስ እስረኛ እንደሆነው ጳውሎስ በፍቅር እለምንሀለሁ።
\s5
\v 10 ልመናዬ በእስርቤት አባት ስለሆንኩት ስለ ልጄ ኦኖሲሞስ ነው።
\v 11 ምክንያቱም ቀድሞ ለአንተ የማይጠቅም አሁን ግን ለአንተም ለእኔም ጠቃሚ በመሆኑ ነው።
\v 12 የልቤ የሆነውን እርሱን ወደ አንተ ልኬዋለሁ።
\v 13 በእኔ በኩልስ አንተን ወክሎ ስለ ወንጌል በእስር ቤት ያለሁትን ያገለግለኝ ዘንድ እኔ ጋ ቢቀር እወድ ነበር።
\s5
\v 14 ነገር ግን መልካም ሥራህ በግድ ሳይሆን በፈቃድህ ይሆን ዘንድ ያለ አንተ ፈቃድ ምንም ማድረግ አልፈለግሁም።
\v 15 ለጥቂት ጊዜ ከአንተ ተለይቶ የነበረው ምናልባት ለዘላለም የአንተ ይሆን ዘንድ ነው ።
\v 16 ነገር ግን ከዚህ በኋላ ከባሪያ የተሻለ እንደተወደደ ወንድም እንጂ እንደባሪያ አይደለም፥ በተለይ ለእኔ የተወደደ ከሆነ ለአንተማ በሥጋም በጌታም የበለጠ ይሆናል።
\s5
\v 17 እንግዲህ እንደ አጋርህ ከቆጠርከኝ እንደኔ አድርገህ ተቀበለው።
\v 18 ነገር ግን በምንም መልኩ አሳዝኖህ ቢሆን ወይም ዕዳ ቢኖርበት በእኔ ላይ ቁጠረው።
\v 19 እኔ ጳውሎስ እኔ እከፍላለሁ ብዬ በገዛ እጄ ጽፌአለሁ።የገዛ ህይወትህ እንኳ የኔ ነው ብዬህ አላውቅም።
\v 20 አዎ ወንድሜ ሆይ እስኪ በጌታ ደስ ይበለኝ፥ ልቤም በክርስቶስ ይጽናና።
\s5
\v 21 እንደምትታዘዘኝ በመተማመን ካልኩህም በላይ እንደምታደርግ ስለማውቅ ጽፌልሀለሁ።
\v 22 በነገራችን ላይ ከጸሎታችሁ የተነሳ ወደ እናንተ እንደምመጣ ተስፋ ስለማደርግ አንድ የእንግዳ ክፍል አዘጋጅልኝ።
\s5
\v 23 ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አብሮኝ የታሰረው ኤጳፍራ
\v 24 እንዲሁም የሥራ አጋሮቼ ማርቆስ፣አርስጥሮኮስ፣ዴማስና ሉቃስ ሠላምታ ያቀርቡልሀል።
\v 25 የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከመንፈሳችሁ ጋር ይሁን። አሜን!