am_ulb/56-2TI.usfm

163 lines
15 KiB
Plaintext

\id 2TI
\ide UTF-8
\h 2 ጢሞቴዎስ
\toc1 2 ጢሞቴዎስ
\toc2 2 ጢሞቴዎስ
\toc3 2ti
\mt 2 ጢሞቴዎስ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 በእግዚአብሔር ፈቃድ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ለሆነው የሕይወት ተስፋ፣ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ የሆነው፣ጳውሎስ
\v 2 ለተወደደው ልጄ፣ ለጢሞቴዎስ፣ ጸጋና ምሕረት ሰላምም በእግዚአብሔር አባታችን፣ ቤታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ለአንተ ይሁን፡፡
\s5
\v 3 ሌትና ቀን በጸሎቴ ስለማስብህ፣ እንደ አባቶቼ አድርጌ በንጹህ ኅሊና የማገለግለወን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፣
\v 4 እምባህን እያሰብኩ በደስታ እሞላ ዘንድ ላይህ እናፍቃለሁ፤
\v 5 ያለህንም እውነተኛ እምነት አስባለሁ፣ ይህም እምነት አስቀድሞ በአያትህ በሎይድ በእናትህም በኤውንቄ ነበረባቸው፣ በአንተም እንዳለ ተረድቼአለሁ፡፡
\s5
\v 6 እግዚአብሔር የሰጠህን በአንተ ያለውን ስጦታ እንድታነሣሣ ስእጆቼን በመጫኔ አሳስብሃለሁ፡፡
\v 7 እግዚአብሔር የኃይል እና የፍቅር ራስንም የመግዛት እንጂ፣ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንም፡፡
\s5
\v 8 በጌታ እና የእርሱ እስረኛ በሆንኩት በእኔም ምሥክርነት አትፈር፣ እንደ እግዚአብሔር ኃይል መጠን ስለ ወንጌል መከራን ተቀበል፡፡
\v 9 ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ያዳነን፣ በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነው፤ ይህም የሆነው በራሱ እቅድና በጸጋወ ነው እጂ በእኛ ሥራ አይደለም፡፡
\v 10 አሁን ግን የእግዚአብሔር ማዳን፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ እና፣ ሞትን በማጥፋቱ እና የዘላለምን ሕይወት ወደ ብርሃን በማውጣቱ በወንጌሉ ተገልጦአል፣
\v 11 ይህንንም ወንጌል ለማብሰር እኔ ሐዋርያ እና አስተማሪ ሆኜ ተሹሜአለሁ፡፡
\s5
\v 12 ስለዚህ ምክንያት እኔ መከራ እቀበላለሁ፣ ነገር ግን አላፍርበትም፣ ያመንኩትን አውቃለሁና፤ የሰጠሁትን አደራ እስከዚያች ቀን ድረስ እንደሚጠብቅ ተረድቼአለሁ፡፡
\v 13 ከእኔ የሰማኸውን ጤናማ ቃል፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለ እምነትና ፍቅር በምሳሌነት ጠብቅ፡፡
\v 14 በእኛ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ አድርገህ በእግዚአበሔር የተሰጠህንም አደራ ጠብቅ፡፡
\s5
\v 15 በእስያ ያሉት ሁሉ ከእኔ ፈቀቅ እንዳሉ ታውቃለህ፣ ከእነዚህም ጊሊጎስ እና ሄርዋጌኔስ ይገኙባቸዋል፡፡
\v 16 ጌታ ለሄኔሲፎሩ ቤተ ሰብ ምሕረትን ይስጣቸው፣ ብዙ ጊዜ አሳርፎኛልና፣ በሰንሰለቴም አላፈረበትም፡፡
\v 17 ነገር ግን በሮም በነበረ ጊዜ፣ በብርቱ ፈልጎ አገኘኝ፣
\v 18 ጌታ በዚያች ቀን ምሕረትን እንዲያገኝ ይስጠው፣ በኤፌሶን ምንያህል እንደረዳኝ አንተ በደኅና ታውቃለህ፡፡
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 እንግዲህ ልጄ ሆይ በኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ጽጋ በርታ፡፡
\v 2 ከብዙ ምስክሮች ጋር ከእኔ የሰማኸውን፣ ሌሎችን ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ፡፡
\s5
\v 3 እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ መልካም ወታደር ሆነህ አብረኸኝ መከራ ተቀበል፡፡
\v 4 አለቃውን ማስደሰት የሚፈልግ ወታደር በምድራዊው ነገር ራሱን አያጠላልፍም፡፡
\v 5 ማንም በስፖርታዊ ውድድር የሚሳተፍ፣ በደንቡ መሠረት ካልተወዳደረ የድሉን አክሊል ሊያገኝ አይችልም፡፡
\s5
\v 6 በርትቶ የሚሠራው ገበሬ ምርቱን ከሚበሉት የመጀመሪያው ሊሆን ይገባል፡፡
\v 7 የምለወን ተመልከት ጌታም በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጥህ፡፡
\s5
\v 8 በወንጌል መልእክቴ የገለጽኩትን፣ ከሙታን የተነሣውንና ከዳዊት ዘር የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ፡፡
\v 9 በዚህም ምክንያት እንደ ወንጀለኛ በመታሰር መከራ እቀበላለሁ፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል አይታሰርም፡፡
\v 10 ስለዚህ ስለተመረጡት ስል በሁሉ እጸናለሁ፣ እነርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ የሆነውን መዳን ከዘላለማዊ ክብር ጋር ያገኙ ዘንድ፡፡
\s5
\v 11 እንዲህ የሚለው ቃል የታመነ ነው ‹‹ከእርሱ ጋር ከሞትን፣ ከእርሱ ጋር እንኖራለን፡፡
\v 12 ብንጸና ከእርሱ ጋር እንነግሣለን፡፡ ብንከዳው እርሱ ደግሞ ይክደናል፡፡
\v 13 ባናምነው እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፣ ራሱን ሊክድ አይችልምና፡፡
\s5
\v 14 እነዚህን ነገሮች አስታውሳቸው፡፡ በቃል እንዳይጣሉ በእግዚአብሔርም ዘንድ አስጠንቅቃቸው፣ይህ ምንም ጥቅም የሌለው የሚሰሙትንም የሚጎዳ ነው፡፡
\v 15 የእውነትን ቃል በትክክል የሚይዝ፣ የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነሀ ራስህን በእግዚአብሔር ፊት ለማቅረብ ትጋ፡፡
\s5
\v 16 እግዚአብሔርን ከመምሰል የሚያርቅህን አለማዊ ተረቶቸን አስወግድ፡፡
\v 17 ቃላቸው እንደ ቆላ ቁስል ነው፣ ከእነርሱም ሄሜኔዎስና ፊሊጦስ ይገኙባቸዋል፣
\v 18 እነዚህም ሰዎች ከእውነት ርቀው ትንሣኤ ሙታነ ካሁን ቀደም ሆናል ይላሉ፣ በዚህም የአንዳንዶችን እምነት ይገለብጣሉ፡፡
\s5
\v 19 ሆኖም፣ ‹‹ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል›› ደግሞም ‹‹የጌታን ስም የሚጠራ ከዓመፃ ይራቅ›› የሚለው ማኅተም ያለበት የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል፡፡
\v 20 በሀብታም ቤት ውስጥ የሚገኙት የወርቅ እና የብር ዕቃዎች ብቻ አይደሉም ነገር ግን የእንጨት እና የሸክላ ዕቃዎችም ይገኛሉ፣ አንዳንዶቹ ለክብር ሌሎቹም ክብር ለማይሰጣቸው ሥራዎች ይውላሉ፡፡
\v 21 ማንም ከማያስከብር ሥራ ራሱን ቢያነጻ፣ የተከበረ ዕቃ፣ የተቀደሰ፣ ለጌታውም የሚጠቅም፣ ለማንኛውም መልካም ሥራ የተዘጋጀ ይሆናል፡፡
\s5
\v 22 ከወጣትነት ምኞት ራቅ፣ በንጹህ ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን፣ እምነትን፣ ፍቅርን፣ ሰላምን ተከታተል፡፡
\v 23 ነገር ግን ጠብን እንደሚያመጣ አውቀህ ከሰነፎችና ካልተማሩ ምርመራ ራቅ፡፡
\s5
\v 24 የጌታ አገልጋይ ሊጣላ አይገባውም፣ ከዚሀ ይልቅ ለሁሉ የሚጠነቀቅ፣ ለማስተማርም የሚበቃ በትእግስትም የሚጸና፣
\v 25 በትህትናም ለሚቃወሙት ትምህርት የሚሰጥ ሊሆን ይገባዋል፡፡ እውነትን በማወቃቸው እግዚአብሔር ምናልባት ንስሐን ይሰጣቸው ይሆናልና፣
\v 26 እንዲሁም ለዲያብሎስ እና ለፈቃዱ ከተያዙበት ወጥመድ ተላቀው ወደ ኅሊናቸው ሊመለሱ ይችሉ ይሆናል፡፡
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 ነገር ግን ይህን እወቅ፣ በመጨረሻዎቹ ቀናት አደገኛ ዘመን ይመጣል፡፡
\v 2 ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉ፣ ገንዘብን የሚወዱ፣ ትእቢተኞች፣ ትምክህተኞቸ፣ በእግዚአብሔር ላይ የስድብን ቃል የሚናገሩ፣ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ ቅድስና የሌላቸው፣
\v 3 ተፈጥሮአዊ ፍቅር የሌላቸው፣ ሰላምን የማይፈጥሩ፣ ሐሜተኞች፣ ራሳቸውን የማይገዙ፣ አመጸኞች፣ መልካም የሆነውን የማይወዱ፣
\v 4 ከዳተኞች፣ ምክርን የማይሰሙ፣ በትእቢት የተነፉ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 5 እግዚአብሔርን የመምሰል መልክ አላቸው ነገር ግን ኃይሉን ይክዳሉ፣ ከእነዚህ ሰዎች ራቅ፡፡
\v 6 ከእነዚህም አንዳንዶች በቤተ ሰብ ውስጥ ሾልከው እየገቡ በኃጢአት የሚገረሙትንና በልዩ ልዩ ምኞትም የሚነዱትን ሞኞችን ሴቶች ይማርካሉ፡፡
\v 7 እነዚህ ሴቶች ሁል ጊዜ አዳዲስ ነገሮችን ለመማር ይሞክራሉ፣ ነገር ግን ፈጽሞ ወደ እውነት እውቀት ሊደርሱ አይችሉም፡፡
\s5
\v 8 ኢያኔስ እና ኢያንበሬስ ሙሴን እንደተቃወሙት፣ እነዚህ የስህተት አስተማሪዎች እውነትን ይቃወማሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች አዕምሮአቸው የተበላሸባቸው፣ የእምነታቸውም እውነተኝነት ያልተረጋገጠ ነው፡፡
\v 9 ዳሩ ግን የእነዚያ የሁለቱ ሰዎች ሞኝነት እንደተጋለጠ፣ እነዚህም ሞኝነታቸው ይገለጣልና አይሳካላቸውም፡፡
\s5
\v 10 አንተ ግን ትምህርቴን፣ አካሄዴን፣ ዓላማዬን፣ እምነቴን፣ መጽናቴን፣ ፍቅሬን፣ ትእግስቴን፣
\v 11 ስደቴን፣ መከራዬን፣ በአንጾኪያ፣ በኢቆንዮን እና በልስጥራን የደረሰብኝን ሁሉ ተከትለሃል፡፡ ይህን ሁሉ ስደት በጽናት አልፌዋለሁ፣ ጌታም ከሁሉ አዳነኝ፡፡
\v 12 በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔር እንደሚወደው ሊኖሩ የሚፈልጉ ሁሉ ይሰደዳሉ፡፡
\v 13 ከፉ ሰዎች እና አታላዮች በክፋት እየባሱ ሌሎችንም እያሳቱና ራሳቸውም ችየሳቱ ይሄዳሉ፡፡
\s5
\v 14 አንተ ግን በተማርህበትና በምታምንበት ነገር ጸንተህ ኑር፣ ከማን እንደተማርከው ታውቃለህና፡፡
\v 15 ከሕፃንነትህ ጀምሮ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ስለሚገኘው መዳን ጥበብ ሊሰጡህ ስለሚችሉት ቅዱሳት መጻሕፍት አውቀሃል፡፡
\s5
\v 16 በእግዚአብሔር የተገለጡ ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ ለመሠረተ እምነት፣ በእምነትም ለመጽናት፣ በጽድቅም ላለው ምክር ይጠቅማሉ፣
\v 17 በመሆኑም የእግዚአብሔር ሰው ለመልካም ሥራ የተዘጋጀ እና የታጠቀ እንዲሆን ያደርጉታል፡፡
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 በእግዚአብሔር ፊት፣ በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ ባለው በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት፣ በመገለጡና በመንግስቱ፣ አዝዝሃለሁ፣
\v 2 ቃሉን ስበክ ሲመችህም ሳይመችህም የተዘጋጀህ ሁን፡፡ እየታገስክና እያስተማርክ ዝለፍ፣ ገስጽ፣ ምከርም፡፡
\s5
\v 3 ሰዎች እውነተኛውን ትምህርት የማይታገሱበት ዘመን ይመጣል፣ ይልቁን፣ ለፍላጎታቸው የሚስማማቸውን የሚሰብኩአቸውን አስተማሪዎችን በዙሪያቸው ይሰበስባሉ፡፡ ይህም ጆሮቻቸውን የሚያሳክክላቸው ይሆናል፡፡
\v 4 ጆሮቻቸውን እውነትን ከመስማት ይመልሳሉ፣ ወደ ስህተትም ያዘነብላሉ፡፡
\v 5 አንተ ግን፣ በነገር ሁሉ የነቃህ ሁን፣ መከራን ተቀበል፣ የወንጌላዊነትን ሥራ አድርግ፣ አገልግሎትህንም ፈጽም፡፡
\s5
\v 6 እኔ እንደ መስዋዕት ልሰዋ ነው፡፡ የምሄድበትም ጊዜ ደርሶአል፡፡
\v 7 መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፣ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፣ እምነቱንም ጠብቄአለሁ፡፡
\v 8 የጽድቅም አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፣ ይህንንም ጻድቅ ፈራጅ፣ የሆነው ጌታ፣ በዚያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፣ ለእኔ ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን መገለጡን ለሚወዱ ሁሉ ነው፡፡
\s5
\v 9 ወደ እኔ በቶሎ ልትመጣ ትጋ፣
\v 10 ዴማስ ትቶኛልና፣ ይህንንም ዓለም ወድዶ ወደ ተሰሎንቄ ሄዶአል፡፡ ቄርቂስ ወደ ገላትያ፣ ቲቶም ወደ ድልማጥያ ሄደዋል፡፡
\s5
\v 11 ሉቃስ ብቻ ከእኔ ጋር አለ፡፡ ማርቆስን ይዘኸው ና እርሱ በሥራው እጅግ ይጠቅመኛል፡፡
\v 12 ቲኪቆስን ወደ ኤፌሶን ልኬዋለሁ፡፡
\v 13 ስትመጣ በጢሮአዳ የተውኩትን ልብሴን፣ ይልቁንም በብራና የተጻፉትን መጻሕፍት ይዘህልኝ ና፡፡
\s5
\v 14 መዳብ አንጥረኛው አሌክሳንደር እጅግ ከፋብኝ፡፡ ጌታ ስለ ክፉ ሥራው ዋጋውን ይከፍለዋል፡፡
\v 15 አንተም ደግሞ ከእርሱ ተጠበቅ፣ ቃላችንን እጅግ ተቃውሞአልና፡፡
\v 16 በፊተኛው የፍርድ ቤት ክርክሬ ከአኔ ጋር ማንም አልቆመም፣ ነገር ግን ሁሉም ተዉኝ፡፡ ይህንንም አይቁጠርባቸው፡፡
\s5
\v 17 ነገር ግን፣ አሕዛብ ሁሉ እንዲሰሙት፣ የወንጌሉ ስብከት በእኔ እንዲፈጸም፣ ጌታ በአጠገቤ ቆሞ አበረታኝ፣ ከአንበሳም አፍ ዳንኩኝ፡፡
\v 18 ጌታ ከክፉ ሥራዎች ሁሉ አውጥቶኛል፣ ለሰማያዊውም መንግሥቱ ይጠብቀኛል፡፡ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፡፡ አሜን፡፡
\s5
\v 19 ለጵርስቅላና ለአቂላ ለሄኔሲፎሩ በተ ሰብ ሰላምታ አቅርብልኝ፡፡
\v 20 ኤርስጦስ በቆሮንቶስ ቀረ፣ ነገር ግን ጥሮፊሞስ ስለታመመ በሚሊጢን ተውኩት፡፡
\v 21 ከክረምት በፊት ልትመጣ ትጋ፡፡ ኤውግሎስና ጱዴስ፣ ሊኖስና ቅላውዲያም ወንድሞች ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡልሃል፡፡
\v 22 ጌታ ከመንፈስህ ጋር ይሁን፡፡ ጸጋ ከአንተ ጋር ይሁን፡፡ አሜን፡፡