am_ulb/54-2TH.usfm

100 lines
9.1 KiB
Plaintext

\id 2TH
\ide UTF-8
\h 2ኛ ተሰሎንቄ
\toc1 2ኛ ተሰሎንቄ
\toc2 2ኛ ተሰሎንቄ
\toc3 2th
\mt 2ኛ ተሰሎንቄ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 ከጳውሎስ፣ ስልዋኖስና ጢሞቴዎስ በእግዚአብሔር በአባታችን በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ላሉ ለተሰሎንቄ ሰዎች ቤተክርስቲያን።
\v 2 ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
\s5
\v 3 ወንድሞች ሆይ፣ ስለ እናንተ ሁልጊዜ ለእግዚአብሔር ምስጋና ማቅረብ አለብን፣ ይህ ተገቢ ነውና፣ ምክንያቱም እምነታችሁ እጅግ እያደገ ነውና፣ የእያንዳንዳችሁ ፍቅርም ለሌሎች የሚተርፍ ሆኗል።
\v 4 በመሆኑም በስደቶቻችሁና በመከራዎቻችሁ ሁሉ ስለ መጽናታችሁ ስለ ትዕግስታችሁና እምነታችሁ እኛ ራሳችን በእግዚአብሔር አብያተክርስቲያናት መካከል በልበ ሙሉነት እንመሰክራለን።
\v 5 እናንተ ደግሞ መከራን ለምትቀበሉለት ለእግዚአብሔር መንግሥት ብቁ ሆናችሁ ትቆጠሩ ዘንድ ይህ የእግዚአብሔር ፍርድ ጻድቅ የመሆኑ ግልጽ ምልክት ነው።
\s5
\v 6 መከራን ለሚያመጡባችሁ መከራን ይመልስላቸው ዘንድ ይህ በእግዚብሔር ፊት ቅን ፍርድ ነው፣
\v 7 ጌታችን ኢየሱስ ከኀይሉ መላዕክት ጋር ከሰማይ በሚገለጥበት ጊዜ ከእኛ ጋር መከራን ለተቀበላችሁት ደግሞ እረፍትን ይሰጣችኋል።
\v 8 እግዚአብሔርን የማያውቁትንና ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ግን በሚነድ እሳት ይበቀላቸዋል።
\s5
\v 9 ከጌታ ሀልዎትና ከኀይሉ ክብር ርቀው በዘላለም ጥፋት እየተቀጡ ይሰቃያሉ፣
\v 10 እርሱ በቅዱሳኑ ሊከበር በሚመጣበት በዚያን ቀን፣ ምስክርነታችንን አምናችኋልና በሚያምኑት ሁሉ ይገረምባቸዋል።
\s5
\v 11 በዚህ ምክንያት እኛ ደግሞ አምላካችን ለጥሪአችሁ የተገባችሁ አድርጎ ይቆጥራችሁና መልካሙን ምኞታችሁንና ማናቸውንም የእምነት ሥራ በኀይል ይፈጽምላችሁ ዘንድ ባለማቋረጥ እንጸልይላችኋለን።
\v 12 ይህም በአምላካችንና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ምክንያት የጌታችን የኢየሱስ ስም በእናንተ እንዲከበርና እናንተም በእርሱ ትከብሩ ዘንድ ነው።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 ወንድሞች ሆይ፣ አሁን የምንለምናችሁ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣትና ወደ እርሱ ስለመሰብሰባችን ነው፣
\v 2 ከእኛ የሆነ በሚመስል በመንፈስ፣ በቃል ወይም በደብዳቤ እነሆ የጌታ ቀን ሆኗል ብላችሁ በማመን በቀላሉ በአዕምሮአችሁ እንዳትናወጡ ወይም እንዳትደነግጡ እንለምናችኋለን።
\s5
\v 3 በየትኛውም መንገድ ማንም አያስታችሁ። የመጨረሻው ክህደት ሳይመጣና የአመጽ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ ያ ቀን አይመጣምና።
\v 4 የሚቃወመውና አምላክ ከተባለው ወይም ከሚመለከው ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ የሚያደርገው እርሱ ነው፣ በእግዚአብሔር ቤተመቅደስ እስኪቀመጥም ድረስ ራሱን እንደ አምላክ ያስተዋውቃል።
\s5
\v 5 ከእናንተ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ስለእነዚህ ነገሮች እንደነገርኳችሁ ትዝ አይላችሁምን?
\v 6 በትክክለኛው ጊዜ ብቻ ይገለጥ ዘንድ አሁን የሚከለክለው ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ።
\v 7 የአመጽ ምስጢር በሥራ ላይ ነው፣ ከመንገድ እስኪወገድ ድረስ አሁን የሚከለክለው አንድ ብቻ አለ።
\s5
\v 8 ከዚያም ጌታ ኢየሱስ በአፉ እስትንፋስ የሚገድለውና በመምጣቱ መገለጥ የሚያጠፋው የአመጽ ሰው ይገለጣል።
\v 9 የአመጽ ሰው አመጣጥ እንደ ሰይጣን አሰራር በኀይል ሁሉ፣ በምልክቶችና በሐሰተኛ ድንቆች፣
\v 10 ይድኑ ዘንድ የእውነትን ፍቅር ስላልተቀበሉ ለሚጠፉት በአመጽ ማታለል ሁሉ ነው።
\s5
\v 11 በዚህ ምክንያት ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል፣
\v 12 ይኸውም እነዚያ እውነትን ያላመኑ ነገር ግን በአመጻ የተደሰቱ ሁሉ ይፈረድባቸው ዘንድ ነው።
\s5
\v 13 ነገር ግን ስለ እናንተ በጌታ ስለተወደዳችሁት ወንድሞች ለእግዚአብሔር ሁልጊዜ ምስጋና ልናቀርብ ይገባናል፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ መቀደስና እውነትን በማመን ለድነት እንደ በኩራት መርጧችኋልና፣
\v 14 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር እንድትካፈሉ በወንጌላችን ጠራችሁ።
\v 15 እንግዲያውስ ወንድሞች ሆይ፣ ጸንታችሁ ቁሙ፣ በቃልም ሆነ ወይም በደብዳቤአችን የተማራችኋቸውን ልማዶች አጥብቃችሁ ያዙ።
\s5
\v 16 አሁን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱና የወደደን፣ የዘላለምን መጽናናትና በጸጋው ተስፋ የምናደርግበትን መልካሙን መታመን የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን፣
\v 17 በቃልና በመልካም ሥራ ሁሉ ልባችሁን ያጽናኑት፣ ያበርቷችሁም።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 በቀረውስ ወንድሞች ሆይ፣ በእናንተ ዘንድ ደግሞ እንደሚሆነው የጌታ ቃል በፍጥነት እንዲዳረስና እንዲከበር ስለ እኛ ጸልዩ፣
\v 2 ሁሉ እምነት ያላቸው አይደሉምና ከአመጸኞችና ከክፉዎች ሰዎች እንድንድን ጸልዩልን።
\v 3 ነገር ግን የሚያጸናችሁና ከክፉው የሚጠብቃችሁ ጌታ የታመነ ነው።
\s5
\v 4 ያዘዝናችሁን ነገሮች እንደጠበቃችሁና ወደፊትም እንደምትጠብቁ ስለ እናንተ በጌታ ታምነናል።
\v 5 ጌታ ልባችሁን ወደ እግዚአብሔር ፍቅርና ወደ ክርስቶስ ጽናት ይምራው።
\s5
\v 6 ወንድሞች ሆይ፣ ከእኛ እንደተቀበላችሁት ልማድ ሳይሆን ሥራ በመፍታት ከሚኖር ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።
\v 7 እንዴት ምሳሌነታችንን መከተል እንደሚኖርባችሁ እናንተው ታውቃላችሁ። በመካከላችሁ በስንፍና አልተመላለስንም፣
\v 8 ወይም ገንዘብ ሳንከፍል የማንንም ምግብ አልበላንም። ከዚያ ይልቅ ከእናንተ በማንም ላይ ሸክም ላለመሆን በድካምና በጥረት ሌሊትና ቀን ሠራን።
\v 9 ይህንን ያደረግነው እኛን ትመስሉ ዘንድ ምሳሌ ልንሆንላችሁ ብለን እንጂ ሥልጣን ስላልነበረን አይደለም።
\s5
\v 10 ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ “ሊሠራ የማይወድ ማንም ቢኖር እርሱ መብላት የለበትም” ብለን አዝዘናችሁ ነበር።
\v 11 በመካከላችሁ ሥራ ፈት ሆነው የሚመላለሱ አንዳንዶች መኖራቸውን ሰምተናልና፤ ሥራ አይሠሩም ነገር ግን በሰው ጉዳይ ጣልቃ ይገባሉ።
\v 12 እንደነዚህ ያሉትን በጸጥታ እንዲሠሩና የራሳቸውን ምግብ እንዲበሉ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናዛቸዋለን እንመክራቸዋለንም።
\s5
\v 13 እናንተ ግን ወንድሞች ሆይ፣ ትክክል የሆነውን ከማድረግ አትታክቱ፡፡
\v 14 በዚህ ደብዳቤ ውስጥ ያለውን ቃላችንን የማይታዘዝ ማንም ቢኖር ይህንን ሰው ልብ በሉት፣ ያፍርም ዘንድ ከእርሱ ጋር ኅብረት አታድርጉ፡፡
\v 15 እንደ ወንድም ገስጹት እንጂ እንደ ጠላት አትቁጠሩት፡፡
\s5
\v 16 የሰላም ጌታ ራሱ ሁልጊዜ በሁሉ መንገድ ሰላምን ይስጣችሁ። ጌታ ከሁላችሁም ጋር ይሁን።
\v 17 እኔ ጳውሎስ፣ ሰላምታዬ እንዲህ ነው፣ በራሴ እጅ በምጽፋቸው ደብዳቤዎች ሁሉ ላይ ምልክቴ ይህ ነው።
\v 18 የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።