am_ulb/53-1TH.usfm

176 lines
17 KiB
Plaintext

\id 1TH
\ide UTF-8
\h 1 ተሰሎንቄ
\toc1 1 ተሰሎንቄ
\toc2 1 ተሰሎንቄ
\toc3 1th
\mt 1 ተሰሎንቄ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 ከጳውሎስ፣ ስልዋኖስና ጢሞቴዎስ በእግዚአብሔር አብና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላሉ ለተሰሎንቄ ቤተክርስቲያን፤ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን!
\s5
\v 2 በጸሎታቻን እያሳሰብን እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ስለ ሁላችሁም እናመሰግናለን።
\v 3 በእምነት ስለምትሠሩት ሥራ፣ በፍቅር ስለምትደክሙት ድካምና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ባላችሁ ተስፋ በመታመን ስለመጽናታችሁ በእግዚአብሔር በአባታችን ፊት ሳናቋርጥ እናስታውሳችኋለን።
\s5
\v 4 በእግዚአብሔር የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ! መመረጣችሁን እናውቃለን፣
\v 5 ወንጌላችን በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፥ ነገር ግን በኃይል፣ በመንፈስ ቅዱስና በብዙ መረዳትም እንጂ፥ ስለእናንተ ስንል በመካከላችሁ ደግሞ እንዴት እንደነበርን ታውቃላችሁ።
\s5
\v 6 በብዙ መከራ ውስጥ ቃሉን ከመንፈስ ቅዱስ ደስታ ጋር ስትቀበሉት እኛንና ጌታን የምትመስሉ ሆናችሁ፣
\v 7 በመቄዶንያ ሁሉና በአካይያ ላሉ ለሚያምኑት ምሳሌ ሆናችሁላቸዋል።
\s5
\v 8 የጌታ ቃል ከእናንተ ተነሥቶ በመቄዶንያና አካይያ ብቻ ሳይሆን ምንም መናገር እስከማያስፈልገን ድረስ በእግዚአብሔር ላይ ያላችሁ እምነት በሁሉ ሥፍራ ተወርቷል።
\v 9 እኛን በሚመለከት እንዴት ያለ አቀባበል እንዳደረጋችሁልን፣ ሕያውና እውነተኛ የሆነውን አምላክ ታገለግሉ ዘንድ ከጣዖታት እንዴት ወደ እግዚአብሔር ዘወር
\v 10 እንዳላችሁ፣ደግሞም ከሰማይ የሚመጣውን ልጁን፣ ያም ከሙታን ያስነሳውን፣ ሊመጣ ካለው ቁጣ የሚያድነንን ኢየሱስን እንደምትጠባበቁ እነርሱ ራሳቸው ይመሰክራሉ።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 ወንድሞች ሆይ! ወደ እናንተ መምጣታችን ፍሬቢስ እንዳልነበረ እናንተው እራሳችሁ ታውቃላችሁ፣
\v 2 ነገር ግን እንደምታውቁት ቀደም ሲል በፊልጵስዩስ መከራና እንግልት ደረሰብን። በብዙ ተቃውሞ መካከል የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ ለመንገር አምላካችን ድፍረት ሰጥቶናል።
\s5
\v 3 የምንመክራችሁ ምክር ከስሕተት ወይም ከእርኩሰት ወይም ከማታለል የመነጨ አይደለም፣
\v 4 ነገር ግን ወንጌልን በአደራ ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔር ታማኞች አድርጎ እንደቆጠረን እንዲሁ ሰውን ሳይሆን ልባችንን የሚመረምረውን እርሱን ደስ ለማሰኘት እንናገራለን።
\s5
\v 5 እናንተው እንደምታውቁት መቼም ቢሆን የሽንገላን ቃል አልተጠቀምንም፣ ገንዘባችሁን በመመኘት እንዳልሆነም እግዚአብሔር ምስክር ነው፣
\v 6 የክርስቶስ ሐዋርያት እንደመሆናችን ልንጠቀምባችሁ መብት ቢኖረንም እንኳን ከእናንተ ወይም ከሌሎች ክብርን ከማንም ሰው አልፈለግንም።
\s5
\v 7 ይልቁንም እናት የራስዋን ልጆች እንደምትንከባከብ በመካከላችሁ የዋሆች ሆንን።
\v 8 ለእናንተ ካለን ፍቅር የተነሳ የእግዚአብሔርን ወንጌል ብቻ ሳይሆን የራሳችንን ሕይወት እንኳን ጨምረን ብንካፈላችሁ ደስ ይለን ነበር፣ ምክንያቱም ለእኛ እጅግ የተወደዳችሁ ሆናችኋልና።
\v 9 ወንድሞች ሆይ! የእግዚአብሔርን ወንጌል በሰበክንላችሁ ጊዜ በማናችሁም ላይ ሸክም ላለመሆን ቀንና ሌሊት እንደሠራን ድካማችንንና ጥረታችንን ታስታውሳላችሁ።
\s5
\v 10 በእናንተ በምታምኑት መካከል እንዴት በቅድስና፣ በጽድቅና ነቀፋ በሌለበት ኑሮ ራሳችንን እንዳቀረብንላችሁ እግዚአብሔርና እናንተም ጭምር ምስክሮች ናችሁ፣
\v 11 እናንተው እንደምታውቁት አባት ለራሱ ልጆች እንደሚያደርገው እያንዳንዳችሁን መከርናችሁ፣ አበረታታናችሁና
\v 12 መሰከርንላችሁ፣ይኸውም ወደ ራሱ መንግሥትና ክብር ለጠራችሁ ለእግዚአብሔር እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ ነው።
\s5
\v 13 በዚህ ምክንያት እኛ ደግሞ ሳናቋርጥ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፣ የመልዕክቱን ቃል፣ የእግዚአብሔርን ቃል ከእኛ በሰማችሁ ጊዜ እንደ ሰው ቃል ሳይሆን፣ ነገር ግን እውነት እንደሆነ፣ በእናንተ በምታምኑት ደግሞ እንደሚሠራ እንደ እግዚአብሔር ቃል ተቀበላችሁት።
\s5
\v 14 እናንተም ወንድሞች ሆይ፣ በይሁዳ የሚኖሩ በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያምኑትን የእግዚአብሔር አብያተክርስቲያናት የምትመስሉ ሆናችኋል፣ እነርሱ ከአይሁድ መከራ እንደደረሰባቸው እናንተ ደግሞ ከገዛ ራሳችሁ ሕዝብ ያንኑ መከራ ተቀብላችኋልና፣
\v 15 አይሁድ ጌታ ኢየሱስንና ነቢያትን ገደሉ፣ እኛንም አሳደዱን፣ እነርሱ እግዚአብሔርን ደስ አያሰኙትም፥ ሰውን ሁሉ ይቃወማሉ።
\v 16 ዘወትር ኀጢአታቸውን ለማብዛትም ይድኑ ዘንድ ለአሕዛብ እንዳንናገር ይከለክሉናል። ቁጣው በላያቸው ላይ መጥቶባቸዋል።
\s5
\v 17 ወንድሞች ሆይ፣ እኛ ለጥቂት ጊዜ በልባችን ሳይሆን በአካል ተለይተናችሁ ነበር፣ በመሆኑም በነበረን ታላቅ ናፍቆት ፊታችሁን ለማየት የተቻለንን ያህል ጥረት አድርገናል፣
\v 18 ወደ እናንተ ለመምጣት ፈልገን ነበር፣ እኔ ጳውሎስም ከአንድም ሁለት ጊዜ ሞከርኩኝ፣ ነገር ግን ሰይጣን አዘገየን።
\v 19 ጌታችን ኢየሱስ በሚመጣበት ጊዜ በፊቱ ተስፋችን ወይም ደስታችን ወይም የመክበራችን አክሊል እንደሌሎቹ ሁሉ እናንተ አይደላችሁምን?
\v 20 ምክንያቱም እናንተ ክብራችንና ደስታችን ናችሁ።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 ስለዚህ ከዚያ በላይ ልንታገስ ባልተቻለን ጊዜ በአቴና ለብቻችን መቅረታችን መልካም እንደሆነ አሰብን።
\v 2 በእምነታችሁ ያጸናችሁና ያበረታችሁ ዘንድ ወንድማችንንና በክርስቶስ ወንጌል የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነውን ጢሞቴዎስን ላክንላችሁ፣
\v 3 ይህንን ያደረግነውም በእነዚህ መከራዎቻችሁ ማንም እንዳይናወጥ ነው፣ ለዚህ እንደተመረጥን ራሳችሁ ታውቃላችሁና።
\s5
\v 4 በእርግጥ ከእናንተ ጋር በነበርንበት ወቅት መከራ ልንቀበል እንዳለን አስቀድመን ነግረናችሁ ነበር፣ እንደምታውቁት የሆነውም ይኸው ነው።
\v 5 በዚህ ምክንያት ወደፊት ልታገስ ባቃተኝ ጊዜ ምናልባት ፈታኙ ፈትኗችሁ ልፋታችንም ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር ስለ እምነታችሁ አውቅ ዘንድ ላክሁት።
\s5
\v 6 ጢሞቴዎስ ከእናንተ ዘንድ ተመልሶ ስለ እምነታችሁና ፍቅራችሁ የምሥራች ባመጣልን ጊዜ ሁልጊዜ በመልካም እንደምታስታውሱንና እኛ ደግሞ ልናያችሁ እንደምንናፍቅ ሁሉ ልታዩን እንደምትናፍቁ ሲነግረን
\v 7 በዚህ ምክንያት ወንድሞች ሆይ፣ በችግራችንና በመከራችን ሁሉ በእናንተ እምነት ተጽናንተናል።
\s5
\v 8 በጌታ ጸንታችሁ ብትቆሙ እኛ ደግሞ አሁን በሕይወት እንኖራለን።
\v 9 በእናንተ ምክንያት በአምላካችን ፊት ስላገኘነው ደስታ ሁሉ ስለ እናንተ ለእግዚአብሔር እንዴት ያለ ምስጋና ማቅረብ እንችል ይሆን?
\v 10 ፊታችሁን ለማየትና በእምነታችሁ የሚጎድላችሁን ለመሙላት ሌሊትና ቀን እጅግ አጥብቀን እንጸልያለን።
\s5
\v 11 ራሱ አምላካችንና አባታችን፣ ጌታችንም ኢየሱስ ወደ እናንተ እንድንመጣ መንገዳችንን ያቅና፣
\v 12 እኛ ደግሞ እንደምናፈቅራችሁ ጌታ ለእርስ በርሳችሁና ለሰው ሁሉ የሚሆን ፍቅራችሁን ያብዛ ያትረፍርፍም።
\v 13 ጌታችን ኢየሱስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ሲመጣ በአምላካችንና በአባታችን ፊት ልባችሁን ነቀፋ በሌለበት ቅድስና ያጸና ዘንድ ይህንን ያድርግላችሁ።
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ፣ እንዴት መመላለስና እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት እንዳለባችሁ ከእኛ በተቀበላችሁት ትምህርት መሠረት አሁን እንደምትኖሩት ሁሉ ከዚህም አብልጣችሁ እንድታደርጉ በጌታ በኢየሱስ እንመክራችኋለን እናደፋፍራችሁማለን።
\v 2 በጌታ በኢየሱስ በኩል እንዴት ያለውን ትዕዛዝ እንደሰጠናችሁ ታውቃላችሁና፤
\s5
\v 3 በቅድስና መኖራችሁ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፣
\v 4 ከእናንተ እያንዳንዱ ከዝሙት በመራቅ የራሱን አካል በቅድስናና በክብር ማግኘት እንዳለበት ታውቃላችሁ፣
\v 5 እግዚአብሔርን እንደማያውቁ እንደ አሕዛብ የፍትወት ምኞት አይሁን፣
\v 6 በዚህ ጉዳይ ማንም አይተላለፍ ወንድሙንም አያታልል፣ ምክንያቱም አስቀድመን እንደነገርናችሁና እንዳስጠነቀቅናችሁ ጌታ ስለነዚህ ነገሮች ሁሉ የሚበቀል ነውና።
\s5
\v 7 እግዚአብሔር ለቅድስና እንጂ ለእርኩሰት አልጠራንም።
\v 8 ስለዚህ ይህንን የማይቀበል ሰውን ሳይሆን የማይቀበለው ቅዱስ መንፈሱን የሰጣችሁን እግዚአብሔርን ነው።
\s5
\v 9 የወንድማማች መዋደድን በተመለከተ ማንም ሊጽፍላችሁ አያስፈልጋችሁም፣ እርስ በርስ ስለመዋደድ እናንተው ራሳችሁ ከእግዚአብሔር ተምራችኋልና።
\v 10 በመቄዶንያ ላሉ ወንድሞች ሁሉ ይህንን ታደርጋላችሁ፣ ይሁን እንጂ ወንድሞች ሆይ፣ ከዚህም አብልጣችሁ እንድታደርጉት ደግሞ እንመክራችኋለን።
\v 11 ደግሞም ልክ እንዳዘዝናችሁ በጸጥታ እንድትኖሩ፣ በራሳችሁ ጉዳይ ላይ እንድታተኩሩና በገዛ እጆቻችሁ እንድትሠሩ እንመክራችኋለን።
\v 12 በማያምኑት ዘንድ በአግባብ እንድትመላለሱና በኑሮአችሁ ምንም የሚጎድላችሁ እንዳይኖር ይህንን አድርጉ።
\s5
\v 13 ወንድሞች ሆይ፣አንቀላፍተው ስላሉት ባለማወቃችሁ ስለወደፊቱ ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ሀዘናችሁ መሪር እንዲሆን አንፈልግም።
\v 14 ኢየሱስ እንደሞተና እንደተነሳ ካመንን በእርሱ አምነው ያንቀላፉትን እግዚአብሔር ከኢየሱስ ጋር ያመጣቸዋል።
\v 15 በጌታ ቃል የምንነግራችሁ ይህንን ነው፣ ጌታ በሚመጣበት ጊዜ እኛ ሕያዋን ሆነን የቀረነው አስቀድመው ያንቀላፉትን በርግጥ አንቀድምም።
\s5
\v 16 ጌታ ራሱ በታላቅ ድምፅ፣ በመላዕክት አለቃ ድምፅና በእግዚአብሔር መለከት ከሰማይ ይወርዳል፣ በክርስቶስ የሞቱትም አስቀድመው ይነሳሉ።
\v 17 ከዚያም እኛ ሕያዋን ሆነን የምንገኘው ጌታን በአየር ላይ ለመገናኘት ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፣ ሁልጊዜም ከጌታ ጋር እንሆናለን።
\v 18 ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በእነዚህ ቃላት ተጽናኑ።
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 ወንድሞች ሆይ፣ አሁን ስለ ጊዜያትና ዘመናት ሊጻፍላችሁ አያስፈልጋችሁም።
\v 2 ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ የጌታ ቀንም እንደዚያው እንደሆነ እናንተ ራሳችሁ በሚገባ ታውቃላችሁና።
\v 3 እርጉዝን ሴት የምጥ ህመም እንደሚሆንባት ሁሉ “ሁሉ ሰላምና ደህና ነው” በሚሉበት በዚያን ጊዜ ድንገተኛ ጥፋት ይመጣባቸዋል፣ እነርሱም በምንም መንገድ አያመልጡም።
\s5
\v 4 ወንድሞች ሆይ፣ እናንተ ግን ያ ቀን እንደ ሌባ ይመጣባችሁ ዘንድ በጨለማ አይደላችሁም።
\v 5 ሁላችሁም የብርሃን ልጆች የቀንም ልጆች ናችሁና። እኛ የሌሊት ወይም የጨለማ ልጆች አይደለንም።
\v 6 እንግዲያውስ ሌሎች እንደሚያደርጉት አናንቀላፋ፣ ነገር ግን እንንቃ በመጠንም እንኑር።
\v 7 የሚያንቀላፉ በሌሊት ያንቀላፋሉ፣ የሚሰክሩትም በሌሊት ይሰክራሉና።
\s5
\v 8 የብርሃን ልጆች እንደመሆናችን በመጠን እንኑር፣ የእምነትንና የፍቅርን ጥሩር፣ የድነታችንን ተስፋ እርግጠኝነትም እንደ ራስ ቁር እንልበስ።
\v 9 በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ድነትን ልንቀበል እንጂ እግዚአብሔር ለቁጣ አልመደበንም፣
\v 10 የነቃን ወይም ያንቀላፋን ብንሆን ከእርሱ ጋር እንድንኖር ስለ እኛ ሞቶአልና።
\v 11 ስለዚህ አሁን እንደምታደርጉት ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተጽናኑ፣ አንዱም ሌላውን ያንጸው።
\s5
\v 12 ወንድሞች ሆይ፣በመካከላችሁ በማገልገል የሚለፉትንና በጌታ የሚያስተዳድሯችሁን፣ የሚመክሯችሁንም እንድታከብሯቸው እንጠይቃችኋለን።
\v 13 ደግሞም በሥራቸው ምክንያት ከፍ ያለ የፍቅር አክብሮት እንድታሳዩአቸው እንጠይቃችኋለን። እርስ በርሳችሁ በሰላም ኑሩ።
\v 14 ወንድሞች ሆይ እንመክራችኋለን፣ ያለ ሥርዓት የሚመላለሱትን ገስጹአቸው፣ ድፍረት ያጡትን አበረታቱአቸው፣ ደካሞችን ደግፉአቸው፣ሰውን ሁሉ ታገሱ።
\s5
\v 15 ማንም ስለተደረገበት ክፉ ነገር ለሌላው በክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፣ ነገር ግን ለእርስ በርሳችሁና ለሰው ሁሉ መልካም የሆነውን ለማድረግ ሁልጊዜ ትጉ።
\v 16 ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፣
\v 17 ባለማቋረጥ ጸልዩ፣
\v 18 ስለ ሁሉም ነገር አመስግኑ፣ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ ነውና።
\s5
\v 19 የመንፈስ ቅዱስን ሥራ አታዳፍኑ።
\v 20 ትንቢትን አትናቁ።
\v 21 ሁሉን መርምሩ፣ መልካም የሆነውን ያዙ፣
\v 22 ማንኛውንም ዓይነት ክፋት አስወግዱ።
\s5
\v 23 የሰላም አምላክ ራሱ ፈጽሞ ይቀድሳችሁ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ መላው መንፈሳችሁ፣ ነፍሳችሁና ሥጋችሁ ያለ ነቀፋ ይጠበቅ።
\v 24 የጠራችሁ ታማኝ ነው፣ እርሱም ደግሞ ያደርገዋል።
\s5
\v 25 ወንድሞች ሆይ፣ ስለ እኛ ደግሞ ጸልዩ።
\v 26 ወንድሞችን ሁሉ በተቀደሰ አሳሳም ሰላም በሏቸው።
\v 27 ይህ መልዕክት ለወንድሞች ሁሉ እንዲነበብ በጌታ አደራ እላችኋለሁ።
\v 28 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።