am_ulb/52-COL.usfm

185 lines
19 KiB
Plaintext

\id COL
\ide UTF-8
\h ቆላስይስ
\toc1 ቆላስይስ
\toc2 ቆላስይስ
\toc3 col
\mt ቆላስይስ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 በእግዚአብሔር ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስና ከወንድማችን ከጢሞቲዎስ፤
\v 2 በቆላስይስ ለሚኖሩ ለእግዚአብሔር ለተለዩና በክርስቶስ ታማኝ ለሆኑ አማኞች፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ጸጋና ሰላም ይሁንላችሁ።
\v 3 ለእናንተ በምንጸልይበት ጊዜ ሁሉ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔርን እናመሰግናለንን።
\s5
\v 4 በክርስቶስ ኢየሱስ ስላላችሁ እምነትና ለእግዚአብሔር ለተለዩት ሁሉ ስላላችሁ ፍቅር ሰምተናል።
\v 5 በሰማይ ከተጠበቀላችሁ ከመታመነ ተስፋ የተነሣ ይህ እምነትና ፍቅር አላችሁ። ስለዚህም ተስፋ በወንጌል የእውነት ቃል አስቀድማችሁ ሰማችሁ፤ ይህም ወደ እናንት ደርሶአል።
\v 6 ይህንም ወንጌል ከሰማችሁበትና የእግዚአብሔርን ጸጋ በእውነት ከተረዳችሁበት ቀን ጀምሮ በእናንተም ዘንድ እየሠራ እንዳለ ሁሉ በዓለም ዙሪያ ሁሉ ፍሬ እያፈራና እያደገ ነው።
\s5
\v 7 በእኛ ምትክ ለእናንተ የክርስቶስ ታማኝ አገልጋይ የሆነውና ከእኛም ጋር አብሮን ከሚያገለግል ከተወዳጁ ከኤጳፍራ ይህን ተምራችኋል።
\v 8 ደግሞም በእግዚአብሔር መንፈስ ያላችሁን ፍቅር ነግሮናል።
\s5
\v 9 ከዚህም ፍቅር የተነሣ ስለ እናንተ ከሰማንበት ቀን ጀምሮ ለእናንተ ከመጸለይ አላቋረጥንም። በፈቃዱ ዕውቀት፣ በጥበብ ሁሉና በመንፈሳዊ ማስተዋል እንድትሞሉ እንጸልይላችኋለን።
\v 10 ጌታን ደስ በሚያሰኝ መንገድ በሁሉም እንደሚገባ እንድትመላለሱ፤ በማናቸውንም መልካም ሥራ ፍሬ እንድታፈሩና በእግዚአብሔርም ዕውቀት እንድታድጉ እንጸልያለን።
\s5
\v 11 በሁሉም ነገር እንድትጽኑና ትእግሥት እንዲኖራችሁ ፣ከኅይሉ ክብር የተነሣም በሁሉ ብርታትና ጥንካሬ እንዲኖራችሁ እንጸልያለን።
\v 12 በብርሃን ከሚኖሩት አማኞች ጋር የርስቱ ተካፋይ እንድንሆን ላበቃን ለእግዚአብሔር በደስታ ምስጋና ማቅረብ እንድትችሉ እንጸልያለን።
\s5
\v 13 ከጨለማ ኅይል አዳነን፤ ወደ ተወደደውም ወደ ልጁ መንግሥት አሸጋገረን።
\v 14 በልጁም የኅጢአታችንን ይቅርታ፣ ድነትን አገኘን።
\s5
\v 15 ልጁ የማይታየው አምላክ ምሳሌ ነው። እርሱ የፍጥረት ሁሉ በኩር ነው።
\v 16 ምክንያቱም በሰማያትና በምድር፤ የሚታዩትና የማይታዩት ነገሮች ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋል። ዙፋናትም ሆኑ ኅይላት ወይም ግዛቶችች ወይም ሥልጣናት፤ሁሉም ነገር በእርሱና ለእርሱ ተፈጥረዋል።
\v 17 እርሱ ከሁሉ በፊት ነበረ፤ሁሉም ነገር የተያያዘው በእርሱ ነው።
\s5
\v 18 እርሱ አካሉ ለሆነችው ቤተ ክርስቲያን ራስ ነው። እርሱ የሁሉም መገኛና የሁሉም የመጀመሪያ፣ከሙታንም በኩር ነው።
\v 19 በመሆኑም በሁሉም ነገሮች መካከል የመጀመሪያ ነው። በእርሱ የእግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ እንዲኖርና እግዚአብሔር በልጁ በኩል ሁሉን ነገር
\v 20 ከራሱ ጋር ያስታርቅ ዘንድ ስለ ወደደ ነው። እግዚአብሔር ልጁ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደም በሰማያትም ሆነ በምድር ያሉትን ነገሮች ሁሉ አስታረቀ።
\s5
\v 21 እናንተም ቀድሞ ከእግዚአብሔር ርቃችሁ ነበር፤ በአሳባችሁና በክፉ ሥራችሁም ምክንያት ጠላቶች ነበራችሁ።
\v 22 አሁን ግን ቅዱሳንና ንጹሓን፤ ነቀፋም የሌለባችሁ አድርጎ በፊቱ ሊያቀርባችሁ በልጁ ሞት እግዚአብሔር ከራሱ ጋር አስታረቃችሁ። ይህም በእርሱ ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ በወንጌሉ ከተገኘው ተስፋ ሳትናወጡ
\v 23 በእምነት ጸንታችሁ እንድትኖሩ ነው። ይህም ወንጌል እናንተ የሰማችሁትና ከሰማይ በታች ላለ ፍጥረት ሁሉ ተሰብኮአል። እኔም ጳውሎስ አገልጋይ የሆንኩት ለዚህ ወንጌል ነው።
\s5
\v 24 አሁን ስለ እናንተ በምቀበለው መከራ ደስ ይለኛል። አካሉ ስለ ሆነችው ስለ ቤተ ክርስቲያንም ከክርስቶስ መከራ ከመካፈል የጎደለውን በሥጋዬ አሟላለሁ።
\v 25 የእግዚአብሔርን ቃል በሙሉ ለእናንተ እንድገልጥ ከእግዚአብሔር በተሰጠኝ ኅላፊነት ቃሉን ለመፈጸም የማገለግለው ይህችን ቤተ ክርስቲያን ነው።
\v 26 ይህም ባለፉት ዘመናትና ትውልዶች ከሰው ልጆች ተሰውሮ የቆየውና አሁን ግን እግዚአብሔር ለሚያምኑት ሁሉ የገለጠው ምስጢር ነው።
\v 27 እግዚአብሔርም በእናንተ መካከል ለአሕዛብ ሊገልጥላቸው የፈለገው የዚህ ምስጢር የክብር ብልጽግና ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ ነው። ይህም ምሥጢር በተስፋ የምንጠባበቀው ክብር የሚገኝበት ክርስቶስ በእናንተ መካከል መሆኑ ነው።
\s5
\v 28 የምንሰብከው እርሱን ነው። እያንዳንዱን ሰው በክርስቶስ ፍጹም አድርገን ለማቅረብ ጥበብን ሁሉ በማስተማርና በመምክር ሰውን ሁሉ እንገስጻለን።
\v 29 በውስጤ በኅይል በሚሠራው መሠረት በብርቱ እየታገልኩ እደክማለሁ።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 ስለ እናንተና በሎዶቅያ ስላሉት ሰዎች እንዲሁም ፊቴን በሥጋ አይተውት ስለማያውቁ ስለ ብዙዎች ምን ያህል ብርቱ ትግል እንዳደረግሁ እንድታውቁ እወዳለሁ።
\v 2 ልባቸው ተጽናንቶና በፍቅር ተሳሰረው ፍጹም የሆነ የመረዳት ብልጽግና እንዲኖራቸውና የእግዚአብሔርን ምስጢር የሆነውን እውነት ክርስቶስን እንዲያውቁ እታገላለሁ።
\v 3 የጥበብና የዕውቀት ሀብት ሁሉ የተሰወረው በእርሱ ነው።
\s5
\v 4 ይህን የምላችሁ ማንም በሚያታልል ንግግር እንዳያስታችሁ ነው።
\v 5 በሥጋ ከእናንተ ጋር ባልሆን እንኳ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ። የእናንተን መልካም ሥርዐትና በክርስቶስ ያላችሁን ጽኑ እምነት እያየሁ ደስ ይለኛል።
\s5
\v 6 ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ።
\v 7 በእርሱም ተመሥርታችሁና ታንጻችሁ፤ እንደ ተማራችሁትም በእምነት ተደላድላችሁ ኑሩ፤ ምስጋናም ይብዛላችሁ።
\s5
\v 8 በክርስቶስ ላይ ባልተመሠረተ በሰው ሠራሽ ልማድና በዓለማዊ ነገሮች፥ በፍልስፍናና በከንቱ ሽንገላ ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠንቀቁ።
\v 9 የእግዚአብሔር ፍጹም ሙላት በእርሱ ይኖራልና።
\s5
\v 10 በእርሱም ተሞልታችኋል። እርሱ የአለቅነትና የሥልጣን ሁሉ ራስ ነው።
\v 11 በእርሱም ተገርዛችኋል፤ ይህም መገረዛችሁ የሥጋዊ አካል በማስወገድ በሰው እጅ የተደረገ ሳይሆን በክርስቶስ የተደረገ ነው።
\v 12 በተጠመቃችሁ ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ተቀበራችሁ፤በእርሱም ክርስቶስን ከሞት ባስነሣው በእግዚአብሔር ኅይል በእምነት ተነሥታችኋል።
\s5
\v 13 እናንተም በበደላችሁና በሥጋችሁ ባለመገረዝ ሙታን ሳላችሁ፤ እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ሕያዋን አድርጎ መተላለፋችንንም ሁሉ ይቅር ብሎአል።
\v 14 እርሱ ይከሰን የነበረውን የዕዳ ጽሑፍ ደመሰሰው። ሁሉንም በመስቀል ላይ ቸንክሮ ከእኛ አስወገደው።
\v 15 ኅይላትንና ባለሥልጣናትን በመስቀሉ ድል አድርጎ በይፋ እንዲጋለጡ አደረጋቸው።
\s5
\v 16 እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም የበዓላትን ቀናት ወይም የወር መባቻን፤ ወይም ሰንበትን በማክበር ምክንያት ማንም አይፍረድባችሁ።
\v 17 እነዚሁ ሁሉ ወደ ፊት ሊመጡ ላሉት ነገሮች እንደ ጥላ ናቸው፤ እውነተኛው አካል ግን በክርስቶስ ነው።
\s5
\v 18 አስመሳይ በሆነ ትሕትና የመላእክትን አምልኮ በመፈለግ ማንም ዋጋ እንዳያሳጣችሁ። እንዲህ ያለው ሰው ስለሚያየው ነገር በሥጋዊ አስተሳሰቡ ይታበያል።
\v 19 እርሱም ራስ ከሆነ ከክርስቶስ ጋር አልተያያዘም። በእግዚአብሔር በተሰጠው እድገት በመገጣጠሚያና በጅማት አካልን በሙሉ አያይዞ የሚመግበውና ለአካል ሙሉ ዕድገት የሚሰጠው ራስ ነው።
\s5
\v 20 ከክርስቶስ ጋር ከሞታችሁ፣ ለዓለማዊ ነገሮች እየታዘዛችሁ ስለ ምን ትኖራላችሁ? ትእዛዞቹም፦
\v 21 «አትያዝ፤አትቅመስ፤ አትንካ!» የሚሉ ናቸው።
\v 22 እነዚህ ሁሉ የሰው ትእዛዛትና ትምህርቶች ሥራ ላይ ከዋሉ በኋላ የሚጠፉ ናቸው።
\v 23 እነዚህ ትእዛዞች ሰው ሰራሽ «ጥበብ» አምልኮና የሐሰት ትሕትና ሰውነትንም በማጎሳቆል ላይ የሚያተኩሩ፤ ነገር ግን ሥጋዊ ስሜትን በመቆጣጠር ረገድ ዋጋ ቢሶች ናቸው።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ከሞት ካስነሣችሁ፤ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያሉትን ነገሮች እሹ።
\v 2 በላይ ስላሉት ነገሮች እንጂ በምድር ስላሉት ነገሮች አታስቡ።
\v 3 ምክንያቱም ሞታችኋል፤ ሕይወታችሁንም እግዚአብሔር በክርስቶስ ውስጥ ሰውሮታልና።
\v 4 ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እናንተም ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ።
\s5
\v 5 ስለዚህ ምድራዊ ምኞቶቻችሁን ግደሉ፦ እነርሱም፦ ዝሙት፣ ርኩሰት፣ ፍትወት፣ ክፉ ምኞት፣ ስግብግብነትና ጣዖትን ማምለክ ናቸው።
\v 6 በእነዚህም ነገሮች ምክንያት በማይታዘዙ ልጆች ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ይመጣባቸዋል።
\v 7 እናንተም ራሳችሁ ከዚህ በፊት በማይታዘዙ ሰዎች መካከል ሳላችሁ እነዚህን ነገሮች እያደረጋችሁ ትመላለሱ ነበር።
\v 8 አሁን ግን ቁጣን፤ ንዴትን፤ ተንኮልን፤ ስም ማጥፋትን ከእናንተ አስወግዱ፤ የሚያሳፍር ንግግርም ከአፋችሁ አይውጣ።
\s5
\v 9 አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋር አውልቃችሁ ስለ ጣላችሁ፣ አንዳችሁ በሌላው ላይ አትዋሹ።
\v 10 የፈጠረውንም ምሳሌ እንዲመስል ዕውቀትን ለማግኘት የሚታደሰውን አዲሱን ሰው ለብሳችሁታል።
\v 11 በዚህ ዕውቀት በግሪካዊና በአይሁዳዊ፣ በተገረዘና ባልተገረዘ፣ በሠለጠነና ባልሠለጠነ፣ በባሪያና በነጻ ሰው መካከል ልዩነት የለም፤ ክርስቶስ ግን ሁሉ ነው፤ በሁሉም ነው።
\s5
\v 12 ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳንና የተወደዳችሁ ሆናችሁ ርኅራኄን፣ ቸርነትን፣ ትሕትናን፣ ገርነትን፣ ትዕግሥትን ልበሱ።
\v 13 እርስ በርሳችሁ ታገሱ፤ እርስ በርሳችሁም ቸሮች ሆኑ። ከእናንተ አንዱ በሌላው ላይ ቅርታ ቢኖረው፣ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።
\v 14 በዚህ ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነው ፍቅር ይኑራችሁ።
\s5
\v 15 የአንድ አካል ክፍሎች ሆናችሁ የተጠራችሁት ለዚህ ሰላም ስለ ሆነ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይንገሥ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ።
\v 16 የክርስቶስ ቃል በሙላት ይኑርባችሁ። በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤በመዝሙርና በውዳሴ፤ በመንፈሳዊ ዜማም እግዚአብሔርን ከልብ እያመሰገናችሁ ዘምሩ።
\v 17 በእርሱ እግዚአብሔር አብን እያመሰገናችሁ በቃልም ሆነ በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።
\s5
\v 18 ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደሚገባ ለባሎቻችሁ ታዘዙ።
\v 19 ባሎች ሆይ፥ ሚስቶቻችሁን ውደዱ መራራም አትሁኑባቸው።
\v 20 ልጆች ሆይ፥ ይህ ጌታን ደስ የሚያሰኝ በመሆኑ ለወላጆቻችሁ በሁሉ ነገር ታዘዙ።
\v 21 አባቶች ሆይ፥ልጆቻችሁ ተስፋ እንዳይቆርጡ አታስመርሩአቸው።
\s5
\v 22 አገልጋዮች ሆይ፥ ሰውን ለማስደሰትና ለታይታ ሳይሆን በቅን ልብ ጌታን በመፍራት ለምድራዊ ጌቶቻችሁ በሁሉ ነገር ታዘዙ።
\v 23 የምታደርጉትን ሁሉ ለሰው እንደምታደርጉ ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ በሙሉ ልባችሁ አድርጉት።
\v 24 ከጌታ ዘንድ እንደ ዋጋ የምትቀበሉት ርስት እንዳለ ታውቃላችሁና።
\v 25 በዚህም የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስን ነው። በእግዚአብሔር ዘንድ አድልዎ ስለሌለ ክፉ የሚሠራ ማንም ስለ ክፉ ሥራው ቅጣቱን ይቀበላል።
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 ጌቶች ሆይ፥ እናንተም በሰማይ ጌታ እንዳላችሁ ዐውቃችሁ ለአገልጋዮቻችሁ በትክክልና የሚገባቸውን ስጡአቸው።
\s5
\v 2 በንቃት እግዚአብሔርን እያመሰገናችሁ ሳታቋርጡ ጸልዩ።
\v 3 የክርስቶስ ምሥጢር የሆነውን የቃሉን እውነት መናገር እንድንችል እግዚአብሔር በር እንዲከፍትልን ለእኛም ደግሞ በአንድ ልብ ጸልዩልን፤ ምክንያቱም እስር የሆንኩት ስለእርሱ ነውና።
\v 4 እኔም እንደሚገባ ቃሉን መግለጥና መናገር እንድችል ጸልዩልኝ።
\s5
\v 5 በውጪ ካሉት ጋር በጥበብ ተመላለሱ፤ ዘመኑንም ዋጁ።
\v 6 ለእያንዳንዱ ሰው እንዴት መመለስ እንዳለባችሁ እንድታውቁ ንግግራችሁ ሁልጊዜ በጨው እንደ ተቀመመ በጸጋ ይሁን።
\s5
\v 7 ቲኪቆስ መጥቶ እኔ ስላለሁበት ሁኔታ ሁሉንም ነገር ይነግራችኋል። እርሱም ተወዳጅ ወንድም፤ ታማኝ አገልጋይና በጌታ ሥራም የአገልግሎት ባልደረባዬ ነው።
\v 8 እርሱንም ወደ እናንተ የላክሁበት ምክንያት ስለ እኛ ሁኔታ ትክክል የሆነውን እንዲነግራችሁና ልባችሁንም እንዲያጽናና ነው።
\v 9 ከእርሱም ጋር የእናንተ ወገን የሆነውን የታመነውንና የተወደደውን ወንድም አናሲሞስን ወደ እናንተ ልኬዋለሁ። እነርሱ በዚህ ስፍራ የተደረገውን ነገር ሁሉ ይነግሩአችኋል።
\s5
\v 10 ከእኔም ጋር የታሰረው አርስጥሮኮስም ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ አንድ ጊዜ፥ «ወደ እናንተ በሚመጣበት ጊዜ ተቀበሉት» ብዬ አሳስቤአችሁ የነበረው የበርናባስ የአጎት ልጅ ማርቆስም ሰላምታ ያቀርብላችኋል።
\v 11 ኢዮስጦስ ተብሎ የሚጠራው ኢያሱም ሰላምታ ያቀርብላችኋል። ከተገረዙ ወገኖች መካከል ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ከእኔ ጋር አብረው የሚሠሩት ሰዎች እነዚህ ብቻ ናቸው፤ ለእኔም መጽናናት ሆነውኛል።
\s5
\v 12 የእናንተ ወገን የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ኤጳፍራም ሰላምታ ያቀርብላችኋል። እርሱም ፍጹም ጠንክራችሁና ሙሉ በሙሉ ተማምናችሁ በእግዚአብሔር ፈቃድ በሁሉ ጸንታችሁ እንድትቆሙ ዘወትር ስለ እናንተ በጸሎት እየተጋ ነው።
\v 13 ስለ እናንተ በሎዶቅያና በሂራፖሊስ ስላሉትም ሰዎች ተግቶ እንደሚሠራ እኔ ራሴ እመሰክርለታለሁ።
\v 14 የተወደደው ሐኪም ሉቃስና ዴማስም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
\s5
\v 15 በሎዶቅያ ላሉት ወንድሞች ለንምፉና በቤትዋም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ ።
\v 16 ይህን መልእክት እናንተ ካነበባችሁ በኋላ በሎዶቅያ ሰዎች ዘንድ ባለችው ቤተ ክርስቲያን እንዲነበብ አድርጉ፤እናንተም ከሎዶቅያ የሚላክላችሁን መልእክት አንብቡ።
\v 17 ለአርኪጳስም፥ «በጌታ አገልግሎት የተሰጠህን ሥራ በጥንቃቄ ፈጽም» ብላችሁ ንገሩልኝ።
\s5
\v 18 ይህን ሰላምታ በገዛ እጄ የጻፍኩት እኔ ጳውሎስ ነኝ፤ በሰንሰለት ታስሬ እንዳለሁ አስታውሱና ጸልዩልኝ። የእግዚአብሔር ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።