am_ulb/51-PHP.usfm

198 lines
22 KiB
Plaintext

\id PHP
\ide UTF-8
\h ፊልጵስዩስ
\toc1 ፊልጵስዩስ
\toc2 ፊልጵስዩስ
\toc3 php
\mt ፊልጵስዩስ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋዮች ከሆኑት ከጳውሎስና ከጢሞቲዎስ፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ቅዱሳን ለሆኑ በፊልጵስዩስ ከተማ ከእረኞችና ከዲያቆናት ጋር ለሚኖሩ ሁሉ።
\v 2 ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ስላም ለአናንተ ይሁን።
\s5
\v 3 ስለእናንተ በማስብበት ሁሉ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
\v 4 ስለ ሁላችሁም በምጸልይበት ጊዜ ሁሉ በደስታ እጸልያለሁ።
\v 5 ከመጀመሪያ ጀምሮ እስካሁን ወንጌል በሚሰበክበት ሥራ ስላሳያችሁት ትብብራችሁ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
\v 6 ይህን መልካም ሥራ በእናንተ ውስጥ የጀመረው ኢየሱስ ክርስቶስ እስከሚመለስ ቀን ድረስ እንደሚፈጽም እርግጠኛ ነኝ።
\s5
\v 7 እናንተ በልቤ ስላላችሁ ስለ ሁላችሁ እንዲህ ማሰብ ይኖርብኛል። በእስራቴና ስለ ወንጌል በመቆሜ ስለእርሱም በመመስከሬ ሁላችሁም በጸጋ ተባባሪዎች ሆናችኋል።
\v 8 በኢየሱስ ክርስቶስ ባለኝ ጥልቅ ፍቅር ሁላችሁንም እንድምናፍቃችሁ እግዚአብሔር ምስክሬ ነው።
\s5
\v 9 ፍቅራችሁ በዕውቀትና በሙሉ መረዳት የበለጠ እንዲበዘላችሁ እጸልያለሁ።
\v 10 ይህን የምጸልይበት ምክንያት የተሻለውን ነገሮችን መርምራችሁ እንድታውቁ እንዲሁም ክርስቶስ ተመልሶ በሚመጣበት ቀን ንጹኃንና ነውር የሌለባችሁ ሆናችሁ እንድትገኙ ነው።
\v 11 ይህ ደግሞ ከኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኘው የጽድቅ ፍሬ ተሞልታችሁ ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና እንዲሆን ነው።
\s5
\v 12 ወንድሞች ሆይ፥በእኔ ላይ የደረሰው ሁሉ ወንጌል በጣም እንዲስፋፋ እንዳደረገ እንድታውቁ እወዳለሁ።
\v 13 እኔም የታሰሁት በክርስቶስ ምክንያት መሆኑን የቤተ መንግሥት ጠበቂዎችና ሌሎችም እዚያ ያሉት ሰዎች ሁሉ እንዲያውቁ ሆኖአል።
\v 14 በእኔ መታሰር ምክንያት በጌታ ወንድሞች ከሆኑት ብዙዎቹ የበለጠ ከቀድሞ ይልቅ የእግዚአብሔርን ቃል ያለ ፍርሃት ለመናገር ድፍረት አግኝተዋል።
\s5
\v 15 በርግጥ አንዳንዶቹ የክርስቶስን ወንጌል የሚሰብኩት በቅናትና በፉክክር መንፈስ ነው፤ሌሎቹ ግን ክርስቶስን የሚሰብኩት በቅን ልቡና ነው።
\v 16 እነዚህ የእግዚአብሔርን ቃል በቅን ልቡና የሚሰብኩት ከፍቅር የተነሳ ነው፤እነርሱም እኔ ስለወንጌል ቆሜ በመከራከርይ መታሰሬን ያውቃሉ።
\v 17 እነዚያ ግን ስለ ክርስቶስ የሚሰብኩት በራስ ወዳድነትና ቅንነት በሌለበት አስተሳሰብ ነው። በእስራቴም ላይ ተጨማሪ መከራ ሊያመጡብኝ አስበው ነው።
\s5
\v 18 ታዲያ ምን ይደረግ? በርግጥ በዚህ ደስ ይለኛል፤በማስመሰል ወይም በእውነት በሁሉም መንገድ ክርስቶስ ይሰበካል።
\v 19 ምክንያቱም በእናንተ ጸሎትና በኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ርዳታ ነጻ እንደምወጣ አውቃለሁ።
\s5
\v 20 እንደማላፍርበት በሙሉ መተማመ እጠባበቃለሁ። ነገር ግን ዘወትር እንደማደርገውና በተለይም ዛሬም በሕይወት ብኖር ወይም ብሞት ክርስቶስ በሰውነቴ ይከብራል ብዬ በድፍረት እናገራለሁ።
\v 21 ስለዚህ ለእኔ ሕይወት ማለት በክርስቶስ መኖር ነው፤ ሞትም ማለት ማትፍረፍ ነው።
\s5
\v 22 ነገር ግን በሥጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢሆን የትኛውን እንደምመርጥ አላውቅም።
\v 23 ምክንያቱም በእነዚህ በሁለቱ አሳቦች መካከል ተወጥሬአለሁ። በአንድ በኩል ከክርስቶስ ጋር መሆን ከሁሉ የሚበልጥ ነገር ስለሆነ ከዚህ ሕይወት ተለይቼ ከክርስቶስ ጋር መሆንን እፈልጋለሁ።
\v 24 ሆኖም በሥጋ መኖሬ ለእናንተ የበለጠ አስፈላጊ ነው።
\s5
\v 25 እምነታችሁ እንዲያድግና ደስታን እንድታገኙ እንደምቆይና ከሁላችሁም ጋር እንደምቀጥል ስለዚህ ነገር እተማመናሉ።
\v 26 በዚህ ምክንያት እኔም እንደገና ወደ እናንተ ስመጣት ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ በእኔ ትመካላችሁ።
\v 27 እንግዲህ ከሁሉም በላይ ሕይወታችሁ ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ይሁን፤ ይህም እኔ መጥቼ ባያችሁ ወይም ከእናንተ ብርቅ በአንድ መንፈስ ጸንታችሁ መቆማችሁንና ለወንጌልም እምነት በኅብረት መጋደላችሁን እሰማ ዘንድ ነው።
\s5
\v 28 ተቃዋሚዎቻችሁንም በምንም ነገር አትፍሩአቸው፤ ይህም ለእነርሱ የመጥፋታቸው ምልክት ሲሆን፤ ለእናንተ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ የመዳናችሁ ምልክት ነው።
\v 29 ምክንያቱም ከክርስቶስ የተነሳ ይህ የተሰጣችሁ አገልግሎት በእርሱ እንድታምኑ ብቻ ሳይሆን በእርሱ ምክንያት መከራ እንድትቅበሉም ጭምር ነው።
\v 30 ስለዚህ አሁን ከእኔ ጋር የመከራ ተካፋዮች ሆናችኋል፤ ይህም መከራ ከዚህ በፊት ደርሶብኝ ያያችሁትና አሁንም እየደረሰብኝ መሆኑን የሰማችሁት ነው።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 በክርስቶስ መበረታታት ካላችሁ፤ከፍቅሩም መጽናናት ካላችሁ፤የመንፈስም ኅብረት ካላችሁ፤እርስ በእርሳችሁም ደግነትና ርኅራኄ ካላችሁ።
\v 2 ስለዚህ በአንድ አሳብ፤ በፍቅር፤ በመንፈስ አንድነት፤በአንድ ዓላማ እየተስማማችሁ ደስታዬ እንዲፈጸም አድርጉት።
\s5
\v 3 በራስ ወዳድነት ወይም በከንቱ ትምክህት ምንም አታድርጉ፤ነገር ግን በዚህ ፈንታ ሌሎች ሰዎች ከእናንተ እንደሚሻሉ በትህትና ቁጠሩ።
\v 4 እንዲሁም እያንዳንዳእሁ የራሳችሁን ጥቅም ብቻ ሳይሆን የሌላውንም ሰው ጥቅም አስቡ።
\s5
\v 5 በኢየሱስ ክርስቶስ የነበረ አሳብ በእናንተም ደግሞ ይኑር፤
\v 6 እርሱም የመለኮት ባሕር ነበረው፥ ነገር ግን ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር እኩል የሚያደርጋውን የመለኮት ባሕይ እንደ ያዘ አልቆጠረም። ክብሩን ትቶ ራሱን ባዶ አደረገ።
\v 7 የባሪያንም መልክ ያዘ፤ በሰው አምሳል ተገለጠ፤ እንደ ሰውም ሆኖ በትህትና ራሱን ዝቅ አደረገ።
\v 8 እንዲሁም እስከ ሞት፤ያውም እስከ መስቀል ሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ።
\s5
\v 9 ስለዚህም እግዚአብሔር ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ አደረገው፤ ከስም ሁሉ በላይ የሆነ ስም ሰጠው።
\v 10 በዚህም ምክንያት ጉልበት ሁሉ በሰማይና በምድር፤ ከምድርም በታች ሁሉ በኢየሱስ እግሮች በታች እንዲንበረከኩ ነው።
\v 11 አንደበትም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር እንዲሆን፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ ነው ብሎ እንዲመሰክር ነው።
\s5
\v 12 ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ፤ እኔ ከእናንተ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ሁሉ እንደምትታዘዙ፥ይልቁንም አሁን ከእናንተ በራቅሁበት ጊዜ ይበልጥ ታዛዦች እንድትሆኑ ነው።
\v 13 በፍርሃትና በመንቀጥቅቀጥም መዳናችሁን ሥሩ። ምክንያቱም ለመልካምነቱ መፍቃዱንና ማድረግን በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነው።
\s5
\v 14 ማናቸውንም ነገር ሳታጉረምግሙና ሳትከራከሩ አድርጉ።
\v 15 ይህን በማድረግ ነውርና ነቀፋ የሌለባችሁ ታማኝ የአግዚአብሔር ልጆች ትሆናላችሁ። በዚህ በጠማናና በመጥፎ ትውልድ መካከል በዚህ ዓለም እንደ ደማቅ ብርሃን ታበራላችሁ።
\v 16 ሕይወት የሚገኝበትን ቃል አጥብቃችሁ በምትይዙበት ጊዜ በከንቱ እንዳልሮጥሁና በከንቱም እንዳልደከምሁ ክርስቶስ በሚመለስበት ቀን ለማክበር ምክንያት ሊኖረኝ ይችላል።
\s5
\v 17 ነገር ግን ለእግዚአብሔር በእምነት በምታቀርቡት መሥዋዕትና አገልግሎት ላይ የእኔም ሕይወት እንደ መሥዋዕት ሆኖ ቢቀርብ እንኳ ደስ ይለኛል። ከሁላችሁ ጋር ታላቅ ደስታ እደሰታለሁ።
\v 18 እንዲሁም በተመሳሳይ ሁኔታ እናንተም ከእኔ ጋር ደስተኞች ትሆናላችሁ።
\s5
\v 19 ነገር ግን እናንተ እንዴት እየሠራችሁ እንዳላችሁ ሰምቼ እንድጽናና ጢሞቲዎስን ወደ እናንተ ፈጥኜ እንደምልክ በጌታ በኢየሱስ ተስፋ አደርጋለሁ።
\v 20 ስለ እናንተ ሁኔታ ከልብ የሚያስብ ከጢሞቲዎስ በስተቀር ሌላ ሰው የለኝም።
\v 21 ሌሎቹ ግን የራሳቸውን ጥቅም ብቻ ስለሚፈልጉ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ግድ የላቸውም።
\s5
\v 22 ነገር ግን ጢሞቲዎስ ልጅ አባቱን እንደሚያገለግል ከእኔ ጋር ወንጌልን በማሠራጨት እንዳገለገለና ስለታማኝነቱም የተመሰከረለት መሆኑን እናንተም ታውቃላችሁ።
\v 23 ስለዚህ የእኔን ሁኔታ እንዳወቅሁ በፍጥነት ጢሞቲዎስን ወደ እናንተ እንደምልክላችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።
\v 24 እንዲያውም እኔ ራሴ በቶሎ ወደ እናንተ እንደምመምጣት በጌታ እተማመናለሁ።
\s5
\v 25 ነገር ግን ኤጳፍሮዲቱስን መልሼ ወደ እናንተ መላክ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። እርሱ እኔን በሚያስፈልገኝ ሁሉ እንዲረዳኝ ልካችሁት የነበረውን ወንድሜና ከእኔ ጋር የተሰለፈ ወታደርና የሥራ ባልደረባዬ ነው።
\v 26 እርሱን ወደ እናንተ የምልከውም ሁላችሁንም ለማየት በመናፈቁና እናንተም መታመሙን በመስማታችሁ ስለ ተጨነቀ ነው። በእርግጥ በጠና ታሞ ለሞት ተቃርቦ ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ምሕረት አደረገለት።
\v 27 ከሕመሙ መዳኑ ለእርሱ ብቻ ሳይሆን ሐዘን በሐዘን ላይ እንዳይደረርብኝ ለእኔም ጭምር ነው።
\s5
\v 28 ስለዚህ እናንተ እርሱን በማየት እንድትደሰቱና የእኔም ሐዘን እንዲቃለል እርሱን ወደ እናንተ ለመላክ ከፍተኛ ፍላጎት አድሮብኛል።
\v 29 እንግዲህ ኤጳፍሮዲቱስን በሙሉ ደስታ በጌታ ተቀበሉት። እንደ እርሱ ያሉትን ሰዎች አክብሩአቸው ።
\v 30 በቅርብ ተገኝታችሁ ልታደርጉልኝ ያልቻላችሁትን በእናንተ ቦታ ሆኖ ሲያገለግለኝና የሚያስፈልገኝን ለማሟላት ስለ ክርስቶስ ሥራ በማለት ለሕይወቱ ሳይሳሳ በማድረግ ለሞት ተቃርቦ ነበር።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 በጨረሻም ወንድሞቼ ሆይ፥ በጌታ ደስ ይበላችሁ። ከዚህ በፊት የጻፍኩላችሁን ተመሳሳይ ነግሮች አሁንም ደግሜ ብጽፍላችሁ አይታክተኝም። እነዚህ ነገሮች እናንተን ከስሕተት ይጠብቃችኋል።
\v 2 ከውሾች ተጠንቀቁ። ከክፉ ሠራተኞች ተጠንቀቁ፤ከሐሰተኞች መገረዝም ተጠንቀቁ።
\v 3 እኛ በእግዚአብሔር መንፈስ የምናመልክ፤ በሥጋም የማንታመን፤ በክርስቶስ ኢየሱስ የምንታመን የተገረዝን ነን።
\s5
\v 4 በሥጋ ትምክሕት የሚያስፈልግ ቢሆን እኔ በብዙ ነገር ልመካ እችል ነበረ። ማንም በሥጋ የሚመካበት አለኝ ብሎ የሚያስብ ሰው ቢኖር እኔ ከእርሱ የበለጠ የምመካበት ብዙ አለኝ።
\v 5 እኔ በተወለድኩ በስምንተኛው ቀን ተገርዤአለሁ፤ በትውልዴም ከብንያም ነገድ የሆንኩ እስራኤላዊ ነኝ፤ ከዚህም የተነሳ ጥርት ያልኩ ዕብራዊ ነኝ። የአይሁድን ሕግ ስለ መጠበቅም ቢሆን ፈሪሳዊ ነበርኩ።
\s5
\v 6 በቅንዓት ቤተ ክርስቲያን አሳድድ ነበር። ሕግን በመጠበቅ ስለ መጽደቅም ቢሆን ያለ ነቀፋ እኖር ነበር።
\v 7 ነገር ግን ከዚህ በፊት ጠቃሚዎች ናቸው ብዬ አምንባቸው የነበሩትን ነገሮች ሁሉ ስለ ክርስቶስ ብዬ ዋጋ እንደሌላቸው እንደ ከንቱ ነገሮች አድርጌ ቆጥሬአቸዋለሁ።
\s5
\v 8 በርግጥ፥ ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ጌታዬ ዕውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቆጥራለሁ። ስለ እርሱም ሁሉን ነገር አጥቻለሁ። ክርስቶስንም ለማግኝትና በእርሱም ለመገኝት ስል ሁሉን ነገር እንደ ቤት ጥራጊ እቆጥራለሁ።
\v 9 እንግዲህ በሕግ ላይ የተመሠረተው የራሴ ጽድቅ የለኝም። በዚህ ፈንታ በክርስቶስ በኩል በሚገኝ እምነት የእግዚአብሔር ጽድቅ አለኝ።
\v 10 ይኸውም እርሱን የማወቅ ጽድቅ፤ የእርሱ የትንሣኤ ኃይልና የመከራው ተካፋይ የመሆንና በሞቱም ክርስቶስን ለመምሰል ነው።
\v 11 ደግሞም ከሙታን ትንሣኤን አገኝ ዘንድ ነው።
\s5
\v 12 እነዚህን ነገሮች ገና አልጨበጥኩአቸውም ፤ ፍጹም ሆኜአለሁ ማለትም አልችልም። ነገር ግን በክርስቶስ ኢየሱስ ያገኘሁትን አገኝ ዘንድ ወደ ፊት ጥረቴን እቀጥላለሁ።
\v 13 ወንድሞች ሆይ፤እኔ ራሴ ገና እንደጨበጥኩ አልቆጥርም። ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ ይኸውም በስተኋላዬ የነበረውን እየረሰሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እተጋለሉ።
\v 14 እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ጠርቶ ሽልማቴን ለማግኘት በፊት ወዳለው ግብ እሮጣለሁ።
\s5
\v 15 ስለዚህ እኛ ብዙዎቻችን በመንፈሳዊ ሕይወት እንዳደጉ ሰዎች ነገሮችን ሁሉ ማሳብ ይኖርብናል። ደግሞ በማንኛውም ነገር የተለያየ አስተሳሰብ ቢኖራችሁ እግዚአብሔር ሁሉንም ግልጥ ያደርግላችኋል።
\v 16 ይሁን እንጂ በደረሰንበት በዚያው ሁኔታ እንመላለስ።
\s5
\v 17 ወንድሞች ሆይ፥ የእኔን ምሳሌነት ተከተሉ፤ በእኛም ምሳሌነት የሚመላለሱትን ሁሉ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ።
\v 18 ከአሁን በፊት ብዙ ጊዜ እንደ ነገርኳችሁና አሁንም እንባዬን እያፈሰስኩ እንደምነግራችሁ ሁሉ ብዙዎቹ በአካሄዳቸው የክርስቶስ መስቀል ጠላቶች ሆነዋል።
\v 19 የእነርሱ አምላክ ሆዳቸው ነው፤ አሳፋሪ የሆነ ነገርም ለእነርሱ ክብራቸው ነው፤ አሳባቸውም የሚያተኩረው በምድራዊ ነገር ላይ ነው ስለዚህ የእነርሱም መጨረሻ ጥፋት ነው፤
\s5
\v 20 ነገር ግን የሚመጣውን አዳኝ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን የምንጠብቅ የሰማይ መንግሥት ዜጎች ነን።
\v 21 እርሱ ይህን የተዋረደውን ሰውነታችንን በመለወጥ የእርሱን ክቡር ሰውነት እንዲመስል ያደርገዋል። ይህንንም የሚያደርገው ሁሉን በሥልጣኑ ሥር ለማድረግ በሚያስችለው ኃይል ነው።
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 ስለዚህ ውድ ወንድሞቼ፤ ወዳጆቼም ሆይ፤ የምናፍቃችሁ፤ ደስታዬና አክሊሎቼ የሆናችሁ በዚህ መንገድ በጌታ ጸንታችሁ ቁሙ።
\v 2 ኤዎድያና ሲንጢኪ እርስ በርሳቸው በጌታ ተስማምተው እንዲኖሩ እለምናቸዋለሁ።
\v 3 በርግጥ አንተም እዚያ ያለኸው የሥራ ባልደርባዬ እነዚህን ሴቶች እንድትረዳቸው እለምንሃለሁ። እነርሱም ወንጌልን በማሰራጨት ከእኔና ከቅሌምንጦስ ጋር እንዲሁም ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት ከሌሎች የሥራ ባልደረቦቼ ጋር ብዙ ተጋድለዋል።
\s5
\v 4 ሁል ጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ደግሜም እላለሁ ደስ ይበላችሁ።
\v 5 ደግነታችሁ በሰዎች ሁሉ ዘንድ ይታወቅ።
\v 6 ስለ ሁሉም ነገር በጸሎት፤ በልመናና በምስጋና ለእግዚአብሔር አስታውቁ እንጂ ስለምንም ነገር አትጨነቁ። ጌታ ቅርብ ነውና።
\v 7 ከማስተዋል በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።
\s5
\v 8 በመጨረሻም ወንድሞችሆይ፥ እውነት የሆነውን ሁሉ፤ ክቡር የሆነውን ሁሉ፤ ትክክል የሆነውን ሁሉ፤ንጹሕ የሆነውን ሁሉ፤ ፍቅር የሆነውን ሁሉ፤ መልካም የሆነውን ሁሉ፤ በጎነት ቢሆን፤ ምስጋናም ቢሆን፤ እንደ እነዚህ ያሉትን ነገሮች ሁሉ አስቡ።
\v 9 ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን፤ የሰማችሁትንና ያያችሁትን ማናቸውንም ነገር አድርጉ። የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።
\s5
\v 10 እንደገና በመጨረሻ ጊዜ ለእኔ ማሰብ ስለ ጀመራችሁ በጌታ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል። በርግጥ ከዚህ በፊት ስለ እኔ ያሰባችሁ ቢሆንም እኔን ለመርዳት ዕድሉን አላገኝችሁም ነበር።
\v 11 ይህን የምለው ለራሴ ጥቅም አይደለም። ምክንያቱም በሁሉም ሁኔታ ባለኝ ነገር መርካትን ተምሬአለሁ።
\v 12 በማጣትም ሆነ በማግኘት እንዴት መኖር እንዳለብኝ ዐውቃለሁ። በማንኛውም መንገድ የመጥገብንና የመራብን፤ የማግኝትንና የማጣትን ምሥጢር ተምሬአለሁ።
\v 13 ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን ነገር ማድረግ እችላለሁ።
\s5
\v 14 ይሁን እንጂ፤ እናንተ የችግሬ ተካፋዮች በመሆናችሁ መልካም አድርጋችኋል።
\v 15 እናንተ የፊልጵስዩስ ሰዎች የወንጌልን ተልዕኮ በጀመርኩበት ጊዜ ከመቄዶንያ ስወጣ ከእናንተ በቀር በመስጠትም ሆን በመቀበል ከእኔ ጋር የተባበረ ሌላ ቤተ ክርስቲያን እንዳልነበረ ታውቃላችሁ።
\v 16 በተሰሎንቄ በነበርኩበት ጊዜም ቢሆን ከአንድ ጊዜ በላይ ለሚያስፈልገኝ ርዳታ ልካችሁልኛል።
\v 17 ይህንንም ስል የእናንተን ስጦታ ለማግኝት በመፈለግ ሳይሆን የልግሥናችሁ ፍሬ እንዲበዛላችሁ በመመኘት ነው።
\s5
\v 18 ሁሉንም ነገር ተቀብያለሁ፤በዝቶልኛል፤ ሞልቶልኛልም። የላካችሁልኝን ስጦታ ከኤጳፍሮዲቱስ እጅ ተቀብዬአለሁ። ይህም ስጦታ በመልካም መዓዛ እንደ ተሞላ መሥዋዕት እግዚአንሔር የሚቀበለውና ደስ የሚሰኝበት ነው።
\v 19 ደግሞም አምላኬ እንደ ክብሩ ባለጠግነቱ በክርስቶስ ኢየሱስ አማካይነት የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሰጣችኋል።
\v 20 እንግዲህ ለአባታችንና ለአምላካችን ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን፤ አሜን።
\s5
\v 21 በክርስቶስ ኢየሱስ ለሆኑት ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከእኔም ጋር ያሉት ወንድሞች ሰላምታ ያቀርቡላችሁኋል።
\v 22 እዚህ ያሉት አማኞች ሁሉ በተለይም የሮማ ቤተ መንግሥት ያሉ ሠራተኞች ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
\v 23 የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከመንፈሳችሁ ጋር ይሁን።