am_ulb/50-EPH.usfm

303 lines
27 KiB
Plaintext

\id EPH
\ide UTF-8
\h ኤፌሶን
\toc1 ኤፌሶን
\toc2 ኤፌሶን
\toc3 eph
\mt ኤፌሶን
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 በእግዚአብሔር ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፥ ለእግዚአብሔር ለተለዩት በክርስቶስ ኢየሱስ ለሚያምኑ በኤፌሶን ለሚኖሩ ቅዱሳን፤
\v 2 ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
\s5
\v 3 በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ ይባረክ።
\v 4 እግዚአብሔር በክርስቶስ የምናምነውን እኛን ዓለም ከመፈጠሩ በፊት መርጦናል። ይህም በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን እንሆን ዘንድ ነው
\s5
\v 5 እግዚአብሔር በፍቅር በኢየሱስ ክርስቶስ የራሱ ልጆች አድርጎ ሊቀበለን አስቀድሞ ወሰነን። ይህንንም የፈጸመው ሊያደርግ የፈለገውን ነገር ለማድረግ ደስ ስለተሰኘ ነበር።
\v 6 ይህ ሁሉ የተፈጸመው በሚወደው ልጁ እንዲያው በነጻ ስለ ተሰጠን ክቡር ጸጋው እግዚአብሔር ይመሰገን ዘንድ ነው።
\s5
\v 7 እንደ ጸጋው ባለጠግነት መጠን በሚወደው ልጁ ደም ቤዛነትን ይኸውም የሐጢአት ይቅርታን አገኘን።
\v 8 ይህም ጸጋ በጥበብና በማስተዋል ሁሉ ተትረፍርፎ ተሰጠን።
\s5
\v 9 በክርስቶስ በተገለጠው ፈቃዱ መሠረት እግዚአብሔር በዕቅዱ ውስጥ ያለውን የተሰወረውን እውነት እንድናውቅ አድርጎናል፤
\v 10 ዕቅዱን የሚፈጽምበት ጊዜ ሲድርስ በሰማይና በምድር ያሉትን ነገሮች ሁሉ በአንድ ላይ በክርስቶስ ስር ይጠቀልላል።
\s5
\v 11 ሁሉንም ነገር እንደ ገዛ ፈቃዱ በሚያደርገው ዕቅድ መሠረት በክርስቶስ ተመረጥን፤ አስቀድሞም ተወሰንን
\v 12 ይህም የሆነው በክርስቶስ በማመን ቀዳሚ የሆንነው እኛ ለክብሩ ምስጋና ይሆን ዘንድ እንድንኖር ነው።
\s5
\v 13 ባመናችሁበትና እንደ ተሰጠው ተስፋ በመንፈስ ቅዱስ በታተማችሁበት በክርስቶስ አማካይነት የመዳናችሁ ወንጌል የሆነውን የእውነት ቃል የሰማችሁት በክርስቶስ ነው
\v 14 ለክብሩ ምስጋና እንዲሆን ተስፋ የተደረገው ሀብት በእጅ እስገሚገባ ድረስ መንፈስ ቅዱስ የርስታችን ዋስትና የሚሆን መያዣ ነው።
\s5
\v 15 ስለዚህ በጌታ ኢየሱስ ስላላችሁ እምነትና ለእርሱም ቅዱሳን ሁሉ ስላላችሁ ፍቅር ከሰማሁበት ጊዜ አንስቶ
\v 16 ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ማመስገንና እናንተንም በጸሎቴ ማስታወስ አላቋረጥሁም ።
\s5
\v 17 የክብር አባት፥የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን ለማወቅ የሚያስችላችሁን የጥበብ እና የመገለጥ መንፈስ እንዲሰጣችሁ እጸልያለሁ፤
\v 18 የምጸልየውም የመጠራታችን አስተማማኝነት እና በእርሱ ቅዱሳን መካከል የርስቱ ክብር ባለጠግነት ምን እንደሆነ ታውቁ ዘንድ የልባችሁ ዐይኖች እንዲበሩ
\s5
\v 19 እንዲሁም እንደ ኀይሉ ብርታት አሠራር በእኛ በምናምነው ውስጥ የሚሠራው የኀይሉ ታላቅነት ምን እንደሆነ እንድትረዱ ነው።
\v 20 ይህም እግዚአብሔር ከሙታን ባስነሳውና በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ እንዲቀመጥ ባደረገው ጊዜ በክርስቶስ ውስጥ የታየው ኀይል ነው።
\v 21 ክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በአብ ቀኝ የተቀመጠውም ከማንኛውም ግዛት፥ ሥልጣን፥ኀይልና ጌትነት እንዲሁም በዚህ ዘመን ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም ዘመን ቢሆን ሊሰየም ከሚችለው ስም ሁሉ በላይ ነው።
\s5
\v 22 እግዚአብሔር ሁሉም ነገር በክርስቶስ እግር ሥር እንዲገዛ አድርጓል፤ እርሱንም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሁሉም ነገር ላይ ራስ አድርጎ ሾሞታል
\v 23 ቤተ ክርስቲያንም ሁሉንም ነገር በሁሉም መንገድ የሚሞላው የእርሱ ሙላት የሆነች አካሉ ናት።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 እንግዲህ እናንተ ከበደላችሁና ከሓጢአታችሁ የተነሳ የሞታችሁ ነበራችሁ።
\v 2 በዚያን ጊዜ የዚህን ዓለም ክፉ መንገድ በመከተል፥ በአየር ላይ ባሉት ኀይላት ላይ ገዥ ለሆነው እንዲሁም በማይታዘዙት ልጆች ላይ ለሚሠራው መንፈስ እየታዘዛችሁ ትኖሩ ነበር።
\v 3 በአንድ ወቅት እኛ ሁላችን ለሥጋችን ክፉ ምኞት እየታዘዝንና ፈቃዱን እየፈጸምን፥ የአእምሮአችንንም ሐሳብ እየተከተልን በእነዚህ በማያምኑት ሰዎች መካከል እንኖር ነበር፤ በተፈጥሮአችንም እንደሌሎቹ የቁጣ ልጆች ነበርን።
\s5
\v 4 ነገር ግን እግዚአብሔር ምሕረት በማድረግ ባለጠጋ ስለሆነ፥ ከወደደን ከታላቅ ፍቅሩ የተነሳ
\v 5 በበደላችን ሙታን በነበርንበት ጊዜ እንኳ ከክርስቶስ ጋር አዲስ ሕይወት ሰጠን፤የዳናችሁትም በጸጋ ነው፤
\v 6 ከእርሱም ጋር አስነሳን፤በሰማያዊ ስፍራም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር እንድንቀመጥ አደረገን።
\v 7 ይህንንም ያደረገው፥በክርስቶስ ኢየሱስ በቸርነቱ የገለጠውን የጸጋው ባለጠግነት ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ በሚመጣው ዘመን ለእኛ ያሳይ ዘንድ ነው።
\s5
\v 8 የዳናችሁት በእምነት አማካይነት በጸጋ ነውና ፤ ይህ ከእግዚአብሔር ያገኛችሁት ስጦታ እንጂ ከእናንተ የሆነ ነገር አይደለም።
\v 9 ማንም ሰው እንዳይመካ በሥራ የተገኘ ነገር አይደለም
\v 10 ምክንያቱም እግዚአብሔር ከዘመናት በፊት እንድንፈጽመው ያዘጋጀውን መልካም ሥራ ለመሥራት በክርስቶስ ኢየሱስ የተፈጠርን የእግዚአብሔር እጅ ሥራዎች ነን።
\s5
\v 11 ስለዚህ በአንድ ወቅት በአካል ላይ በሰው እጅ የሚከናወነውን መገረዝ ስላገኙ «የተገረዙ» በሚባሉት ዘንድ «ያልተገረዙ» ተብላችሁ የምትጠሩ በትውልድ አሕዛብ የነበራችሁ እንደሆነ አስታውሱ።
\v 12 በዚያን ጊዜ ከክርስቶስ ተለይታችሁ፥ የእስራኤል ወገን ከመሆን ርቃችሁ፥ለተስፋውም ኪዳን ባዕድ ሆናችሁ ያለ ተስፋ እና ያለ እግዚአብሔር በዓለም ላይ ትኖሩ እንደነበር ልብ በሉ።
\s5
\v 13 ነገር ግን አሁን ከእግዚአብሔር ርቃችሁ የነበራችሁት በክርስቶስ ኢየሱስ በመሆን በክርስቶስ ደም አማካይነት ወደ እግዚአብሔር እንድትቀርቡ ተደርጋችኋል።
\v 14 አይሁድንና አሕዛብን ሁለቱን አንድ ሕዝብ ያደረገ እርሱ ሰላማችን ነውና ፤ በሥጋውም እርስ በርስ የለያየንን የጥል ግድግዳ አፈረሰ።
\v 15 ይኸውም ከሁለቱ ሕዝቦች አንድ አዲስ ሕዝብ በመፍጠር ሰላምን ያደርግ ዘንድ የትእዛዛትንና የሕግ ደንቦችን በሥጋው ሻረ።
\v 16 ይህንንም ያደረገው በመስቀሉ አማካይነት በመካከላቸው የነበረውን ጠላትነት ገድሎ ሁለቱን ሕዝቦች አንድ አካል በማድረግ ከእግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ ነው።
\s5
\v 17 ኢየሱስ መጥቶ ርቀው ለነበሩት እና ቀርበው ለነበሩት ለእነዚያ የምሥራቹን ወንጌል ሰበከ፤ ሰላሙንም አወጀ።
\v 18 በኢየሱስ አማካይነት እኛ ሁለታችንም በአንድ መንፈስ ወደ አብ መቅረብ እንችላለንና።
\s5
\v 19 ስለዚህ እናንተ አሕዛብ ከቅዱሳንና ከእግዚአብሔር ቤተ ሰብ አባላት ጋር የአንድ አገር ዜጎች ናችሁ እንጂ ከእንግዲህ መጻተኞችና እንግዶች አይደላችሁም።
\v 20 እነዚህ በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ የተመሠረቱ ናቸው፤ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ራሱ ነው።
\v 21 ቤተ ሰቡ የሆነው ሕንጻ ሁሉ በኢየሱስ ኀይል አንድ ላይ ተገጣጥሞ ለጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስ ለመሆን ያድጋል።
\v 22 እናንተም እግዚአብሔር በመንፈሱ የሚኖርበት ሕንጻ እንድትሆኑ አብራችሁ በክርስቶስ እየታነጻችሁ ነው።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 በዚህ ምክንያት አሕዛብ ስለሆናችሁት ስለ እናንተ እኔ ጳውሎስ የክርስቶስ ኢየሱስ እስረኛ ሆኛለሁ።
\v 2 ለእናንተ ጥቅም ሲባል ስለ ተሰጠኝ የእግዚእብሔር ጸጋ መጋቢነት ሰምታችኋል ብዬ አስባለሁ።
\s5
\v 3 ቀደም ሲል እንደጻፍሁላችሁ እግዚአብሔር የተሰወረውን ምስጢር በመገለጥ እንዳውቅ አድርጓል።
\v 4 ይህን በምታነቡበት ጊዜ ስለ ክርስቶስ ምስጢር እኔ ያለኝን መረዳት መገንዘብ ትችላላችሁ።
\v 5 ምስጢሩም አሁን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ለሓዋርያቱ እና ለነቢያቱ የተገለጠው ያህል ባለፉት ዘመናት ለነበሩ ሰዎች አልተገለጠም ነበር።
\s5
\v 6 ይህም ምስጢር አሕዛብ በወንጌል አማካይነት አብረው ወራሾች፥ አብረው የካሉ ብልቶች እንዲሁም በክርስቶስ በተገኘው ተስፋ አብረው ተካፋዮች መሆናቸው ነው።
\v 7 እንደ እርሱ ኀይል አሠራር በተሰጠኝ በእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ አገልጋይ ሆኛለሁ።
\s5
\v 8 ምንም እንኳ ከቅዱሳን ሁሉ ያነስሁ ብሆንም፥ የማይመረመረውን የክርስቶስ የባለጠግነት ወንጌል ለአሕዛብ እሰብክ ዘንድ ይህ ጸጋ ለእኔ ተሰጠኝ።
\v 9 እንዲሁም የሁሉን ነገር ፈጣሪ በሆነው በእግዚአብሔር ላለፉት ዘመናት ተሰውሮ ስለነበረው ምስጢር የእግዚአብሔር ዕቅድ ምን እንደሆነ ለሁሉም እገልጥ ዘንድ ተሰጠኝ።
\s5
\v 10 በዚህም ምክንያት በቤተ ክርስቲያን አማካይነት ብዙ ገጽታ ያለው የእግዚአብሔር ጥበብ በሰማያዊ ስፍራ ላሉት አለቆችና ባለ ሥልጣናት እንዲታወቅ ነው።
\v 11 ይህም የሆነው በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ በፈጸመው ዘላለማዊ ዕቅዱ መሠረት ነው።
\s5
\v 12 በክርስቶስ በማመናችን በእርሱ ሆነን በድፍረትና በልበ ሙሉነት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንችላለንና።
\v 13 ስለዚህ ክብራችሁ በሆነው ለእናንተ ስል በምቀበለው መከራ ተስፋ እንዳትቆርጡ እለምናችኋለሁ።
\s5
\v 14 በዚህም ምክንያት በአብ ፊት እንበረከካለሁ፤
\v 15 እርሱም በሰማይና በምድር ላለ ቤተ ሰብ ሁሉ ስያሜ የሰጠ እና እነርሱንም የፈጠረ ነው።
\v 16 የምጸልየውም ትጠነክሩ ዘንድ በውስጣችሁ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት እንደ ክብሩ ባለጠግነት መጠን ኀይል እንዲሰጣችሁ ነው።
\s5
\v 17 ይህም በእምነት ክርስቶስ በልባችሁ እንዲኖር፥ በፍቅሩ ሥር እንድትሰዱና እንድትታነጹ ነው፤
\v 18 ደግሞም የክርስቶስ ፍቅር ስፋቱ፥ርዝመቱ፥ከፍታውና ጥልቀቱ ምን ያህል እንደ ሆነ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር መረዳት ትችሉ ዘንድ ነው።
\v 19 እንዲሁም በእግዚአብሔር ፍጹም ሙላት ሁሉ ትሞሉ ዘንድ ፥ ከሰው ዕውቀት ሁሉ በላይ የሆነውን የክርስቶስን ታላቅ ፍቅር እንድታውቁ ነው።
\s5
\v 20 እንግዲህ በእኛ ውስጥ እንደሚሠራው ሀይሉ መጠን ሁሉንም ነገር እኛ ከምንለምነው ወይም ከምናስበው በላይ እጅግ አብልጦ ማድረግ ለሚቻለው
\v 21 በቤተ ክርስቲያንና በክርስቶስ ኢየሱስ በትውልዶች ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም ለእርሱ ክብር ይሁን፤አሜን።
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 ስለዚህ የጌታ እስረኛ እንደመሆኔ በእግዚአብሔር ለተጠራችሁለት መጠራት የሚገባውን ሕይወት ትኖሩ ዘንድ እለምናችኋለሁ።
\v 2 ይኽውም እርስ በርስ በፍቅር ተቻችላችሁ በፍጹም ትሕትና፥በገርነትና በትዕግሥት እንድትኖሩ ነው።
\v 3 በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ አስፈላጊውን ጥረት ሁሉ አድርጉ።
\s5
\v 4 በተጠራችሁ ጊዜ በአንድ ተስፋ እንደተጠራችሁ ሁሉ፥ አንድ አካል እና አንድ መንፈስ አለ፤
\v 5 አንድ ጌታ፥አንድ እምነት፥አንድ ጥምቀት አለ ፤
\v 6 ደግሞም ከሁሉ በላይ የሆነ፥በሁሉ የሚሠራ፥ በሁሉ የሚኖር ፥የሁሉም አባት የሆነ አንድ አምላክ አለ።
\s5
\v 7 ክርስቶስ ስጦታ መጠን ለእያንዳንዳችን ጸጋ ተሰጥቶናል
\v 8 ይህም የእግዚአብሔር ቃል «ወደ ላይ በወጣ ጊዜ ምርኮኞችን ማረከ፤ለሰዎችም ስጦታ ሰጠ» በማለት እንደሚናገረው ነው።
\s5
\v 9 «ወደ ላይ ወጣ» ሲል ደግሞም «ወደ ምድር ጥልቅ ወረደ» ማለት ካልሆነ በቀር ሌላ ምን ሊያመለክት ይችላል?
\v 10 ታች የወረደው ሁሉንም ይሞላ ዘንድ ከሰማያት ሁሉ በላይ የወጣው ያው እርሱ ራሱ ነው።
\s5
\v 11 ወንጌል ሰባኪዎችን፥እረኞችን እና አስተማሪዎችን ስጦታ አድርጎ የሰጠ ክርስቶስ ራሱ ነው።
\v 12 ያደረገው የክርስቶስን አካል ለማነጽና ለአገልግሎት ሥራ ቅዱሳንን ለማስታጠቅ ነው።
\v 13 የሚሆነው ሁላችንም የእግዚአብሔርን ልጅ በማመን እና በማወቅ ወደ ሚገኘው አንድነት እንዲሁም ወደ ክርስቶስ ሙላት ልክ እንዳደጉት ሰዎች ሙሉ ሰው ወደ መሆን ደረጃ እስከምንደርስ ድረስ ነው።
\s5
\v 14 በሰዎች ረቂቅ ተንኮል እና ማታለል በተዘጋጀ የትምህርት ነፋስ ወዲያና ወዲህ የምንነዳ ሕጻናት መሆን አይገባንም
\v 15 ይልቁንም እውነትን በፍቅር የምንናገር እና ራስ ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ በሁሉም መንገድ የምናድግ ሰዎች መሆን ይጠበቅብናል።
\v 16 የአማኞችን አካል ሁሉ በሚያገናኘው ጅማት እየተያያዘና እየተጋጠመ፥እያንዳንዱም ክፍል የራሱን ተግባር እያከናወነ በፍቅር ያድጋል።
\s5
\v 17 እየለመንኋችሁ ይህን የምናገረው፥ ከእንግዲህ በአእምሮአቸው ከንቱነት እንደሚመላለሱት እንደ አሕዛብ እንዳትኖሩ ነው።
\v 18 እነርሱም አእምሮአቸው ጨልሞአል፤ካለማወቃቸውና ከልባቸው ደንዳናነት የተነሳ ከእግዚአብሔር ሕይወት ርቀዋል፤
\v 19 ስግብግብነት ሁሉ ለሞላበት ቅጥ ላጣ ብልግና ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል።
\s5
\v 20 ግን ስለ ክርስቶስ የተማራችሁት እንደዚህ አይደለም።
\v 21 እርሱ የሰማችሁ እና የተማራችሁ ከሆነም በርግጥ የተማራችሁት ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን እውነት ነው።
\v 22 ክፉ ምኞት የጎደፈውን አስቀድሞ ትኖሩበት የነበረውን አሮጌውን ሰው ልታስወግዱ ይገባል።
\s5
\v 23 በአእምሮአችሁ መንፈስ እንድትታደሱ
\v 24 እውነተኛ በሆነው ጽድቅና ቅድስና በእግዚአብሔር የተፈጠረውን አዲሱን ሰው እንድትለብሱ ነው።
\s5
\v 25 ውሸትን አስወግዱ፤ ሁላችንም የአንድ አካል ብልቶች ስለሆንን «እያንዳንዱ ከባልንጀራው ጋር እውነትን ይነጋገር»።
\v 26 «ተቆጡ፤ ነገር ግን ኀጢአት አትሥሩ» በቁጣችሁ ጸሓይ እስከሚገባ ድረስ አትቆዩ፤
\v 27 ዕድል አትስጡት።
\s5
\v 28 የነበረ ከእንግዲህ አይስረቅ፤ይልቁንም ለተቸገሩ ሰዎች ማካፈል ይችል ዘንድ በራሱ እጅ በተገቢው ሁኔታ እየሠራ ለማግኘት ጥረት ማድረግ ይገባዋል።
\v 29 ለማነጽ የሚያስፈልግ፥ ለሚሰሙትም ጸጋን የሚሰጥ ጠቃሚ ቃል እንጂ የማይረባ ቃል ከቶ ከአፋችሁ አይውጣ።
\v 30 ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝኑ።
\s5
\v 31 ሁሉ፥ቁጣንና ንዴትን፥ጭቅጭቅንና ስድብን ከማንኛውም ዓይነት ክፋት ጋር ከእናንተ ዘንድ አስወግዱ።
\v 32 በርሳችሁ ቸሮች፥ ርኅሩሆች ሁኑ፤ ደግሞም እግዚአብሔር በክርስቶስ እንዲሁ ይቅር እንዳላችሁ እርስ በርሳችሁ ይቅር ተባባሉ።
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 እንግዲህ እንደ ተወደዱ የእርሱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትመስሉ ሁኑ፤
\v 2 እንደ ወደደን፥ ራሱንም ስለ እኛ መልካም መዓዛ ያለው መባና መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር እንዳቀረበ ሁሉ እናንተም በፍቅር ኑሩ።
\s5
\v 3 የሚገባ ባለመሆኑ ዝሙት፥ማንኛውም ርኩሰትና ስስት በእናንተ ዘንድ ሊኖር አይገባም፤
\v 4 ጸያፍ ንግግር፥ዋዛ ወይም ውርደትን የሚያስከትል ቀልድ ለእናንተ ስለማይገባ ከመካከላችሁ አስወግዱ፤ከዚህ ይልቅ የምታመሰግኑ ሁኑ።
\s5
\v 5 አመንዝራ፥ርኩስ፥ ስግብግብ የሆነ ይኽውም ጣዖት አምላኪ ሰው በክርስቶስና በእግዚአብሔር መንግሥት ርስት እንደማይኖረው ርግጠኛ ልትሆኑ ይገባል።
\v 6 ከንቱ በሆነ ንግግር ማንም አያታላችሁ፤በእነዚህ ነገሮች ምክንያት የእግዚአብሔር ቁጣ በማይታዘዙት ልጆች ላይ ይመጣል
\v 7 ስለዚህ የእነርሱ ተባባሪዎች አትሁኑ።
\s5
\v 8 ወቅት ጨለማ ነበራችሁና፤ አሁን ግን በክርስቶስ ብርሃን ናችሁ። ስለዚህ እንደ ብርሃን ልጆች ኑሩ።
\v 9 ምክንያቱም ከብርሃኑ የሚገኘው ፍሬ መልካም ነገር ሁሉ፥ ጽድቅና እውነት ነው
\v 10 እንዲሁም ጌታን ደስ የሚያሰኝ ነገር ለማድረግ አስቡ፤
\v 11 ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፤ይልቁን ልትገልጡት ይገባል።
\v 12 በስውር ያደረጉትን ነገር ለመግለጽ እንኳ አሳፋሪ ነውና።
\s5
\v 13 በሚኖርበት ጊዜ ማንኛውም ነገር በግልጽ ይታያል።
\v 14 ብርሃኑ በላዩ ላይ ስለሚያበራ ነው። ስለዚህ፥ «አንተ የምትተኛ ንቃ፤ከሙታን ተነሳ፤ክርስቶስም ያበራልሃል» ተብሎ ተነግሯል።
\s5
\v 15 ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን፥እንደ ጥበብኞች እንዴት እንደምትኖሩ ተጠንቀቁ።
\v 16 ክፉዎች ስለሆኑ ዘመኑን ዋጁ።
\v 17 ፈቃድ ምን እንደሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ።
\s5
\v 18 ሕይወታችሁን ለጥፋት ስለሚዳርግ፥በወይን ጠጅ አትስከሩ፤ይልቁንስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ።
\v 19 እርስ በርሳችሁ በመዝሙር፥በቅኔና በመንፈሳዊ ዝማሬ ተነጋገሩ፤ ጌታንም በልባችሁ አመስግኑ፤ለእርሱም ተቀኙ።
\v 20 በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለ ሁሉም ነገር ሁልጊዜ እግዚአብሔር አብን አመስግኑ
\v 21 ክርስቶስን ለማክበር ስትሉ አንዳችሁ ለሌላችሁ ተገዙ።
\s5
\v 22 ሚስቶች ሆይ! ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ።
\v 23 ክርስቶስ አካሉ ለሆነችውና አዳኟ ለሆናት ቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ ሁሉ ባልም የሚስቱ ራስ ነውና።
\v 24 ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ ሁሉ ሚስቶችም በማንኛውም ነገር ለባሎቻቸው ሊገዙ ይገባል።
\s5
\v 25 ባሎች ሆይ፤ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ስለ እርስዋም ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ፥ እናንተም ሚስቶቻችሁን ውደዱ።
\v 26 ይህንንም ያደረገው በቃሉ አማካይነት በውሃ አጥቦ በማንጻት እንድትቀደስ፥
\v 27 ጉድፍ ወይም የፊት መጨማደድ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ ነገር ሳይታይባት ቅድስት የሆነችና ነውር የሌለባት ክብርት ቤተ ክርስቲያን አድርጎ ለራሱ ሊያቀርባት ነው።
\s5
\v 28 ባሎች የገዛ ሥጋቸውን እንደሚወዱ ሚስቶቻቸውን መውደድ ይገባቸዋል። ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል።
\v 29 የራሱን ሥጋ የሚጠላ ማንም የለም፤ ይልቁን ይመግበዋል፤ ይንከባከበዋልም። ይህም ክርስቶስ ልክ ቤተ ክርስቲያንን እንደሚወድ ነው።
\v 30 እኛ የእርሱ ብልቶች ነን።
\s5
\v 31 ምክንያት ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ከሚስቱም ጋር አንድ ይሆናል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።
\v 32 ታላቅ ምስጢር ነው፤ እኔም ይህን የምናገረው ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያኑ ነው።
\v 33 ግን ከእናንተ እያንዳንዱ ደግሞ ሚስቱን እንደ ራሱ አድርጎ መውደድ ይገባዋል፤ ሚስትም ባልዋን ታክብር።
\s5
\c 6
\cl ምዕራፍ 6
\p
\v 1 ልጆች ሆይ፤ በጌታ ለወላጆቻችሁ ታዘዙ፤ ይህ ተገቢ ነውና።
\v 2 «አባትህንና እናትህን አክብር» በሚለው የመጀመሪያ ትእዛዝ ውስጥ ያለው ተስፋ
\v 3 እንዲሆንልህ፥ ዕድሜህም በምድር ላይ እንዲረዝም» የሚል ነው።
\s5
\v 4 እናንተም አባቶች ሆይ፤ ልጆቻችሁን አታስቆጡአቸው፤ ይልቁንስ በጌታ ሥርዓትና ምክር አሳድጓቸው።
\s5
\v 5 ባሮች ሆይ፤ ለክርስቶስ እንደምትታዘዙት ለምድራዊ ጌቶቻችሁም በታላቅ አክብሮት፥ በመንቀጥቀጥና በልባችሁ ቅንነት ታዘዙ፤
\v 6 ለታይታ እነርሱን ደስ ለማሰኘት ብላችሁ ሳይሆን፥ እንደ ክርስቶስ አገልጋዮች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ከልብ በመፈጸም ታዘዙአቸው።
\v 7 ሰውን ሳይሆን ጌታን እንደምታገለግሉ እያሰባችሁ በደስታ አገልግሉ።
\v 8 ባሪያም ይሁን ነጻ ሰው እያንዳንዱ ሰው ለሚያደርገው መልካም ነገር ከጌታ ሽልማት እንደሚቀበል ልብ በሉ።
\s5
\v 9 እናንተም ጌቶች ሆይ፤ ለባሮቻችሁ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ የእነርሱና የእናንተም ጌታ የሆነው እርሱ በሰማይ እንዳለና ለሰው ፊትም እንደማያዳላ ተረድታችሁ አታስፈራሯቸው።
\s5
\v 10 በጌታና ብርቱ በሆነው ኀይሉ የበረታችሁ ሁኑ።
\v 11 የዲያብሎስን ተንኮል አዘል ዕቅድ መቋቋም ትችሉ ዘንድ የእግዚአብሔርን የጦር ዕቃ ሁሉ ልበሱ።
\s5
\v 12 ውጊያችን ከሥጋና ከደም ጋር ሳይሆን ከአለቆች፥ ከሥልጣናት፥ ከዚህ ከጨለማ ዓለም ገዦችና በሰማያዊ ስፍራ ካሉ ርኩሳን መናፍስት ጋር ነው።
\v 13 በክፉ ቀን ክፉውን በመቃወም ጸንታችሁ ትቆሙ ዘንድ የእግዚአብሔርን የጦር ዕቃ ሁሉ ልበሱ፤ ጸንታችሁ ለመቆምም ማድረግ የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ።
\s5
\v 14 ወገባችሁን በእውነት ቀበቶ ታጥቃችሁ፥የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ ጸንታችሁ ቁሙ፤
\v 15 የሰላምን ወንጌል ለማወጅ እግሮቻችሁ በዚያ ተጫምተው ዝግጁ ይሁኑ
\v 16 የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ማጥፋት ትችሉ ዘንድ ሁል ጊዜ የእምነትን ጋሻ አንሱ።
\s5
\v 17 የመዳንን ራስ ቁር አድርጉ፤የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ፤ይህም የእግዚአብሔር ቃል ነው።
\v 18 ዓይነት ጸሎትና ልመና ሁልጊዜ በመንፈስ በመጸለይና መልሱን ከእርሱ በመጠበቅ፥ ለቅዱሳንም ልመና በማቅረብ ትጉ።
\s5
\v 19 ምስጢር በድፍረት ለመናገር አፌን በምከፍትበት ጊዜ ሁሉ ቃል ይሰጠኝ ዘንድ ለእኔም ጸልዩልኝ።
\v 20 መናገር እንደሚገባኝ በድፍረት እናገር ዘንድ በሰንሰለት የታሰረ መልእክተኛ የሆንሁት ለዚሁ ነውና።
\s5
\v 21 ሁኔታ እንዳለሁና ምን እያደረግሁ እንደምገኝ፥ የተወደደ ወንድምና በጌታ ታማኝ አገልጋይ የሆነው ቲኪቆስ ሁሉንም ነገር ይነግራችኋል።
\v 22 ያለንበትን ሁኔታ እንድታውቁና እናንተንም እንዲያበረታታ በማለት ወደ እናንተ ልኬዋለሁ።
\s5
\v 23 ከአብ፥ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና ፍቅር ከእምነት ጋር ለወንድሞች ይሁን።
\v 24 ኢየሱስ ክርስቶስን በማይጠፋ ፍቅር ከሚወዱ ጋር ሁሉ ጸጋ ይሁን።