am_ulb/49-GAL.usfm

295 lines
26 KiB
Plaintext

\id GAL
\ide UTF-8
\h ገላቲያ
\toc1 ገላቲያ
\toc2 ገላቲያ
\toc3 gal
\mt ገላቲያ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 በሰው በኩል ወይም ከሰው ሳይሆን በክርስቶስ ኢየሱስ ደግሞም እርሱን ከሞት ባስነሳው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ የሆንኩት ጳውሎስ
\v 2 አብረውኝ ካሉ ወንድሞች ጋር በገላትያ ለምትገኙ አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ
\s5
\v 3 ከአባታችን ከእግዚአብሔር አብ ከጌታም ከኢየሱስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ
\v 4 ይሁን፣እርሱ እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከአሁኑ ክፉ ዘመን ያድነን ዘንድ እራሱን ስለ ኃጢአታችን ሰጥቶአልና
\v 5 ለእርሱ ከዘላለም እስከዘላለም ክብር ይሁን። አሜን!
\s5
\v 6 ወደሌላ ወንጌል በዚህ ፍጥነት በመዞራችሁ እጅግ ተገርሜአለሁ። በክርስቶስ ጸጋ ከተጠራችሁ ከእርሱ ፊታችሁን ማዞራችሁ አስገርሞኛል።
\v 7 ሌላ ወንጌል የለም፣ ነገር ግን የሚያውኩዋችሁና የክርስቶስን ወንጌል ሊያጣምሙ የሚፈልጉ አንዳንድ ሰዎች አሉ።
\s5
\v 8 ነገር ግን እኛም ሆንን የሰማይ መልአክ አስቀድመን ከሰበክንላችሁ ሌላ ወንጌል ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።
\v 9 አስቀድመን እንዳልን እንደገና እላለሁ «ማንም ከተቀበላችሁት ወንጌል የተለየ ወንጌል ቢሰብክላችሁ የተረገም ይሁን»
\v 10 ለመሆኑ እኔ የምጥረው ከሰው ወይስ ከእግዚአብሔር ይሁንታን ለማግኘት ነው? ጥረቴ ሰውን ለማስደሰት ነው? እስከአሁን ድረስ ሰውን ለማስደሰት እየጣርኩ ከሆነ እውነት እኔ የክርስቶስ አገልጋይ አይደለሁም።
\s5
\v 11 ወንድሞች ሆይ የሰብኩላችሁ ወንጌል ከሰው እንዳልሆን እንድታውቁ እፈልጋለሁ።
\v 12 ከጌታ ከኢየሱስ ከተሰጠኝ መገለጥ እንጂ ከሰው አልተቀበልኩትም ከሰውም አልተማርኩትም።
\s5
\v 13 የይሁዲ እምነት ተከታይ በነበርኩበት በቀድሞው ህይወቴ ወቅት እንዴት ቤተክርስቲያንን በአመፅ አሳድድና አጠፋ እንደነበረ ስለእኔ ሰምታችኋል።
\v 14 በይሁዲነት ከአብዛኛዎቹ አብረውኝ ከነበሩ አይሁዶች እየላቅሁ ነበር። ለአባቶቼም ወግ ከመጠን ያለፈ ቀናኢ ነበርኩ።
\s5
\v 15 ነገር ግን እግዚአብሔር ገና በማህጸን ሳለሁ ሊመርጥኝ ወደደ፣
\v 16 በአረማውያን መካከል አውጀው ዘንድ ልጁን በእኔ ለመግለፅ በጸጋው ጠራኝ። በጠራኝ ጊዜ ወዲያውኑ ከስጋና ከደም ጋር አልተማከርኩም
\v 17 ፣ከእኔ አስቀድመው ሃዋሪያት የሆኑት ወደሚገኙበት ወደ ኢየሩሳሌምም አልሄድኩም። ነገር ግን ወደ አረቢያ በኋላም ደግሞ ወደ መቄዶኒያ ተመለስኩ።
\s5
\v 18 ከዚያም ከሶስት አመት በኋላ ኬፋን ለመጠየቅ ወደኢየሩሳሌም ሄጄ ከእርሱ ጋር አስራአምስት ቀናት ቆየሁ።
\v 19 ነገር ግን ከጌታ ወንድም ከያዕቆብ በስተቀር ሌሎች ሃዋሪያትን አላገኘሁም።
\v 20 በምፅፍላችሁ በእነዚህ ነገሮች በእግዚአብሔር ፊት እንዳልዋሸሁ እወቁ።
\s5
\v 21 ቀጥሎም ወደ ሶሪያና ኪልቂያ አውራጃዎች ሄድኩኝ።
\v 22 እስከዚያን ጊዜ ድረስ በይሁዳ ላሉት አብያተክርስቲያናት በአካል አልታወቅም ነበር፣
\v 23 ነገር ግን «ያ ቀድሞ ያሳድደን የነበረው ሰው አሁን ሊያጠፋው ሲጥር የነበረውን እምነት እየሰበከ ነው» የሚል ወሬ ብቻ ይሰሙ ነበር፣
\v 24 ስለ እኔም እግዚአብሔርንም ያከብሩ ነበር።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 ከአስራ አራት ዓመት በኋላ ቲቶን ይዤ ከበርናባስ ጋር እንደገና ወደ ኢየሩሳሌም ሄድኩ።
\v 2 የሄድኩበትም ምክንያት መሄድ እንዳለብኝ እግዚአብሔር ስላመለከተኝ ነበር። ሄጄም በአህዛብ መካከል እየሰበኩት ስላለው ወንጌል ነገርኳቸው፣ ነገር ግን በከንቱ እንዳልሮጥኩ ወይም እየሮጥኩ እንዳልሆን እርግጠኛ ለመሆን ይህን የተናገርኩት በሌሎቹ ዘንድ እንደ ዋና ለሚታሰቡት ብቻ ነበር።
\s5
\v 3 ግሪካዊ የሆነው ሲላስ እንኳ እንዲገረዝ አልተገደደም።
\v 4 ይህ ጉዳይ የተንሳው በክርስቶስ ያገኘነውን ነፃነት ለመሰለል ሾልከው በገቡ ውሸተኞች ወንድሞች ምክንያት ነበር።
\v 5 የህግ ባሪያዎች ሊያደርጉን ይመኙ ነበር። ነገር ግን ለእናንተ ወንጌሉ ሳይለወጥ ይቆይላችሁ ዘንድ ለአንድ ሰዓት እንኳ ለሀሳባቸው አልተገዛንም።
\s5
\v 6 ነገር ግን ሌሎች መሪዎች ናቸው ያልዋቸው ምንም አስተዋፅኦ አላደርጉልኝም። ማንም ይሁኑ ለእኔ ትርጉም አልነበረውም። ሆኖም ግን ልክ ጴጥሮስ ለተገረዙት ወንጌልን ለማድረስ አደራ እንደተሰጠው ሁሉ
\v 7 እኔም ላልተገረዙት ወንጌልን ለማድረስ አደራ እንደተቀበልኩ አዩ፥
\v 8 ምክንያቱም ለተገረዙት ሃዋሪያ ይሆን ዘንድ በጴጥሮስ የሰራ እግዚአብሔር ላልተገረዙት ሃዋሪያ እሆን ዘንድ በእኔም ስለሚስራ ነው።
\s5
\v 9 እንደመሪዎች የሚታወቁት ያዕቆብ፥ኬፋና ዮሀንስ በእኔ ላይ ያለውን ፀጋ ባዩ ጊዜ እኛ ወደ አህዛብ እነርሱ ደግሞ ወደተገረዙት ይሄዱ ዘንድ የማህበራቸውም ተካፋዮች እንድንሆን ሙሉ መብት ሰጡን።
\v 10 እኔ ለማድረግ የምናፍቀውን ድሆችን እንድናስብም አሳሰቡን።
\s5
\v 11 ከዚያም ኬፋ ወደ አንፆኪያ በመጣ ጊዜ ሥራው ትክክል ስላልነበረ ፊት ለፊት ተቃወምኩት።
\v 12 ምክንያቱም ከያዕቆብ ዘንድ ሰዎች ከመምጣታቸው በፊት ኬፋ ከአህዛብ ጋር ይበላ ነበር። ሰዎቹ በመጡ ጊዜ ግን እነኚህን የተገረዙ ሰዎች ፈርቶ ከአህዛብ ጋር መብላቱን አቆመ እንዲያውም ተለያቸው።
\s5
\v 13 በርናባስ እንኳ በግብዝነታቸው እስኪሳብ ድረስ ሌሎቹም አይሁድ በኬፋ ግብዝነት ተካፋዮች ነበሩ።
\v 14 ወንጌልን በሚፃረር መንገድ መሄዳቸውን ባየሁ ጊዜ ኬፋን በሁሉም ፊት «አንተ አይሁዳዊ ሆንህ በአህዛብ ስርአት የምትኖር ከሆነ አህዛብ በአይሁድ ስርአት እንዲኖሩ ለምን ታስገድዳቸዋልህ?» አልኩት።
\s5
\v 15 እኛ«አህዛብ ኃጢአተኞች» ያልሆንን ነገር ግን በትውልድ አይሁዳዊ የሆንን በክርስቶስ ኢየሱስ ላይ ባለ እምነት እንጂ ማንም ህግን በመፈፀም እንደምይፀድቅ እናውቃለን።
\v 16 በህግ ሥራ ማንም ሊፀድቅ ስለማይችል በህግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ ኢየሱስ ባለ እምነት እንፀድቅ ዘንድ ወደ ክርስቶስ ኢየሱስ እምነት ተጠርተናል።
\s5
\v 17 ነገር ግን እግዚአብሔር በክርስቶስ እንዲያፀድቀን እየፈለግን ሳለ ራሳችንን ኃጢአተኞች ሆነን እናገኛለን፥
\v 18 ታዲያ ክርስቶስ የኃጢአት አገልጋይ ሆነ ማለት ነው? በፍፁም አይደለም።
\v 19 ምክንያቱም አውልቄ የጣልኩትን ህግን የመፈፀም ትምክህት እንደገና ብገነባ ራሴን ህግ ተላላፊ ሆኜ አገኘዋለሁ። በህግ በኩል ለህግ ሞቼአለሁ።
\s5
\v 20 ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ። ከእንግዲህ የምኖረው እኔ አይደለሁም፥ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል። አሁን በሥጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና እራሱን ስለ እኔ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።
\v 21 የእግዚአብሔርን ፀጋ አላቃልልም፥ ህግን በመጠበቅ ፅድቅ የሚገኝ ቢሆን ኖሮ ክርስቶስ መሞቱ ከንቱ በሆነ ነበር።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 እናንተ ማስተዋል የጎደላችሁ የገላቲያ ሰዎች ማነው በክፉ ዓይኑ ያያችሁ፥ ክርስቶስ እንደተሰቀል ሆኖ በፊታችሁ ተስሎ አልነበረምን?
\v 2 ይህን ብቻ ከእናንተ ማወቅ እፈልጋለሁ። መንፈስ ቅዱስን የተቀበላችሁት በህግ ሥራ ነው ወይስ የሰማችሁትን በማመናችሁ?
\v 3 ይህን ያህል ሞኞች ናችሁ እንዴ፥ በመንፈስ ጀምራችሁ በሥጋ ትጨርሳላችሁ?
\s5
\v 4 በእርግጥ ይህ ከንቱ ከተባለ ያን ሁሉ መከራ የተቀብላችሁት በከንቱ ነውን?
\v 5 መንፈስ ቅዱስን የሰጣችሁና በመካከላችሁ ኃይለኛ ነገርን ያደረገው እርሱ ይህን ያደረገው በህግ ሥራ ነው ወይስ ከእምነት በሆነ እምነታችሁ ነው?
\s5
\v 6 ልክ አብርሀም «እንዳመነና እምነቱ እንደ ፅድቅ እንደተቆጠረለት»
\v 7 የሚያምኑ ሁሉ የአብርሀም ልጆች እንደሆኑ አስተውሉ።
\v 8 ቅዱሳት መፅሀፍት እግዚአብሔር አህዛብን እንደሚያፀድቅ አስቀድመው አመልክተዋል። ወንጌል «አህዛብ ሁሉ በአንተ ይባረካሉ» ተብሎ በመጀመሪያ ለአብርሀም ተሰብኳል።
\v 9 ስለዚህም የሚያምኑ እምነት ከነበረው ከአብርሀም ጋር የተባረኩ ናቸው።
\s5
\v 10 «ህግን ሁሉ ይፈፅም ዘንድ ለህግ የማይታዘዝ ሁሉ የተረገመ ነው» ተብሎ ተፅፎአልና በህግ ስራ የሚታመን ሁሉ በእርግማን ስር ነው።
\v 11 «ጻድቅ በእምነት ይኖራልና» እግዚአብሔር ማንንም በህግ እንደማያጸድቅ ግልጽ ነው።
\v 12 ህግ ከእምነት የመነጨ አይደለም፥ ይልቁኑም «በህግ ውስጥ ያሉትን እነዚያን ነገሮች የሚያደርግ በህግ ይኖራል»
\s5
\v 13 «በእንጨት ላይ የሚሰቀል የተረገመ ነው» ተብሎ በተጻፈው መሰረት እርሱ ስለኛ እርግማን በመሆን ከህግ እርግማን ዋጀን።
\v 14 የዚህ ተግባር ዓላማ የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ በእምነት እንቀበል ዘንድ በአብርሀም ላይ የነበረው በረከት በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል በአህዛብም ላይ እንዲሆን ነው።
\s5
\v 15 የምናገረው በሰው ቋንቋ ነው። ልክ በሰዎች መካከል እንደተደረገ ውል ማንም ከዚህ ሊቀንስ ወይም ሊጨምር አይችልም።
\v 16 እንግዲህ ተስፋዎቹ የተነገሩት ለአብርሀምና ለዘሩ ነው። ብዙ ሰዎችን እንደሚያመለክት «ለዘሮቹ» አላለም። ነገር ግን አንድ መሆኑን በሚገልጽ መልኩ«ለዘሩ» ብሎ ይናገራል። ያም ለዘሩ የተባለለት ክርስቶስ ነው።
\s5
\v 17 እንግዲህ እንዲህ ልበል። አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠው ቃል ኪዳን ተስፋ ከ430 ዓመት በኋላ በተሰጠ ህግ አልተሻረም።
\v 18 ምክንያቱም ውርሱ በህግ የመጣ ቢሆን ኖሮ በተስፋ በኩል ባልመጣ ነበር፥ ነገር ግን እግዚአብሔር ለአብርሃም በተስፋ አማካኝነት ርስትን እንዲያው ሰጠው።
\s5
\v 19 ታዲያ ህግ ለምን አስፈለገ? የአብርሃም ዘር ተስፋ ወደተሰጣቸው እስኪመጣ ድረስ በመተላለፍ ምክንያት ህግ ተሰጠ፤ ህጉ በመካከለኛ አማካኝነት በመላዕክት አማካኝነት ተግባራዊ ሆኗል።
\v 20 መካከለኛ ሲል ከአንድ ሰው በላይ እንደሆነ ያመለክታል፥ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው።
\s5
\v 21 ታዲያ ህግ የእግዚአብሔርን ተስፋ ይቃረናል ማለት ነው? በፍጹም አይደለም። ህይወትን ሊሰጥ የሚችል ህግ ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ በእርግጠኝነት ጽድቅ በህግ በኩል ይመጣ ነበር።
\v 22 ነገር ግን ይልቁኑ መጽሀፍ ሁሉን ነገር ከኃጢአት በታች እስርኛ አድርጓል። ስለዚህም እኛን በክርስቶስ ኢየሱስ ለማዳን እግዚአብሔር የሰጠው ተስፋ ለሚያምኑ ተሰጠ።
\s5
\v 23 ነገር ግን በክርስቶስ ማመን ከመምጣቱ በፊት እምነት እስከተገለጠበት ጊዜ ድረስ በህግ ታስረንና ታግደን ነበር።
\v 24 ስለዚህ በእምነት እንድንጸድቅ ህግ ወደ ክርስቶስ ዘመን የሚያደርሰን ሞግዚት ሆነ።
\v 25 አሁን እምነት ስለመጣ ከዚህ በኋላ በሞግዚት ሥር አይደለንም።
\v 26 ምክንያቱም ሁላችሁም በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ።
\s5
\v 27 በክርስቶስ ስም የተጠምቃችሁ ሁላችሁ ክርስቶስን ለብሳችሁታል።
\v 28 ሁላችሁ በክርስቶስ አንድ ስለሆናችሁ በዚህ ጉዳይ በአይሁድና በግሪክ ሰዎች፥ በባሪያና ነጻ በሆነ፥በሴትና በወንድ መካከል ልዩነት የለም።
\v 29 እንግዲህ የክርስቶስ ከሆናችሁ የአብርሀም ዘሮች እንደተስፋ ቃሉም ወራሾች ናችሁ።
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 ያን የምለው ህጻን ሳለ ምንም እንኳ ሁሉም የእርሱ ቢሆንም ወራሹ ከባሪያ አይለይም።
\v 2 ነገር ግን አባቱ የወሰነልት ቀን እስኪደርስለት ድረስ በተንከባካቢዎቹና በሞግዚቶቹ ስር ይቆያል።
\s5
\v 3 እኛም ልጆች ሳለን በዚህ ዓለም ዋና ትምህርቶች እስራት ሥር ነበርን።
\v 4 ነገር ግን በትክክለኛው ጊዜ እግዚአብሔር በህግ ሥር ያሉትን
\v 5 ነጻ እንዲያወጣና የልጅነትን መብት እንዲኖረን ከሴት የተወለደውንና በህግ ሥር የተወለደውን ልጁን ላከ።
\s5
\v 6 ልጆች ስለሆናችሁ «አባ አባት» እያለ የሚጣራውን የልጁን መንፈስ ወደ ልባችን ላከ።
\v 7 በዚህም ምክንያት ከእንግዲህ ልጆች እንጂ ባሮች አይደላችሁም፥ ልጆች ከሆናችሁ ደግሞ የእግዚአብሔር ወራሾች ናችሁ።
\s5
\v 8 ነገር ግን እግዘአብሔርን በማታውቁበት በቀድሞው ዘመን በባህሪያቸው ፈጽሞ አማልክት ላልሆኑት ተገዝታችሁ ኖራችሁ።
\v 9 አሁን ግን እግዚአብሔርን አውቃችኋል ይልቁኑም በእግዚአብሔር ታውቃችኋል፥ ታዲያ እንዴት ወደ ደካማና ዋጋ ወደሌለው የዚህ ዓለም ዋና ትምህርት ተመለሳችሁ።እንደገና ባሮች መሆን ትፈልጋላችሁ?
\s5
\v 10 ልዩ ቀናትን፥አዳዲስ ጨረቃዎችን፥ ወራትና ዓመታትን ታመልካላችሁ።
\v 11 ስለ እናንተ የደከምኩት ድካም ከንቱ ሆኖብኝ እንዳይሆን ብዬ እፈራለሁ።
\s5
\v 12 ወንድሞች ሆይ ልክ እኔ ለእናንተ እንደምሆነው እናንተም ለእኔ እንደዚያው እንድትሆኑ እለምናችኋለሁ።
\v 13 ምንም ክፉ አላደርጋችሁብኝም ነገር ግን ወንጌልን በመጀመሪያ በሰብኩላችሁ ጊዜ የሥጋ ህመም አሞኝ እንደነበረ ታውቃላችሁ።
\v 14 በሥጋዬ ላይ የነበረው ለእናንተ ከባድ ፈተና ቢሆንም አልተጸየፋችሁኝም አልጣላችሁኝምም፥ ይልቁኑ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ወይም ክርስቶስን በተቀበላችሁብት አቀባበል ተቀበላችሁኝ።
\s5
\v 15 አሁን ደስታችሁ በምንድነው? ዓይናችሁን እንኳ አውጥታችሁ ልትሰጡኝ ፈቃደኛ እንደነበራችሁ እኔ ራሴ ምስክር ነኝ።
\v 16 ታዲያ እውነትን ስለነገርኳችሁ የእናንተ ጠላት ሆንኩ ማለት ነው?
\s5
\v 17 አጥበቀው ይፈልጓችኋል ነገር ግን ለመልካም አይደለም። እነርሱን እንድትከተሉ ከእኔ ሊለዩዋችሁ ይፈልጋሉ።
\v 18 እኔ ከእናንተ ጋር ስሆን ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜ ለመልካም ነገር መትጋት ተገቢ ነው።
\s5
\v 19 ጨቅላ ልጆቼ ሆይ ክርስቶስ በውስጣችሁ እስኪቀረጽ ድረስ ስለእናንተ ምጥ ይዞኛል!
\v 20 የእናንተ ነገር ግራ ስለገባኝ በመካከላችሁ ተገኝቼ በቁጣ ልናገራችሁ እመኛለሁ።
\s5
\v 21 እስኪ እናንተ በህግ ሥር ለመሆን የምትፈልጉ ንገሩኝ ህጉ ምን እንደሚል አልሰማችሁምን?
\v 22 አብርሃም አንድ ባሪያ ከነበረች ሴት አንድ ደግሞ ነጻ ከነበረች ሴት የተወለዱ ሁለት ልጆች እንደነበሩት ተጽፏል።
\v 23 ነገር ግን ከባሪያይቱ የተወለደው በሥጋ ብቻ የተወለደ ነው፥ ከነጻይቱ የተወለደው ግን በተስፋ የተወለደ ነው።
\s5
\v 24 እነዚህ ነገሮች እንደ ምሳሌ ሊገለጹ ይችላሉ።እነኚህ ሴቶች እንደ ሁለቱ ቃል ኪዳኖች ናቸው፥ አንደኛዋ በሲና ተራራ የተሰጠውንና ባርነትን የወለደውን ታመለክታለች፥ እርሷም አጋር ናት።
\v 25 እንግዲህ አጋር በአረቢያ ምድር የሚገኘው የሲና ተራራ ስትሆን ከልጆቿ ጋር በባርነት የምትኖረውን የአሁኗን ኢየሩሳሌምን ትወክላለች።
\s5
\v 26 ነገር ግን እናታችን የሆነችው ላይኛይቱ ጽዮን ነጻ ነች።
\v 27 ምክንያቱም እንዲህ ተብሎ ተጽፏል «አንቺ ያልወለድሽና መካን የሆንሽ ሴት ሀሴት አድርጊ፥አንቺ መውለድን ያልተለማምድሽ ውጪና በደስታ ጩኺ፤ ባል ካላቱ ይልቅ የመካኗ ልጆች በዝተዋልና»።
\s5
\v 28 እንግዲህ እናንተ ወንድሞቼ እንደ ይስሀቅ የተስፋ ልጆች ናችሁ።
\v 29 ነገር ግን እንደ ሥጋ ፈቃድ የተወለደው እንደ መንፈስ ፈቃድ የተወለደውን እንዳሳደደው አሁንም እየሆነ ያለው እንደዚያው ነው።
\s5
\v 30 መጽሀፍ ስለዚህ ነገር ምን ይላል«የባሪያይቱ ልጅ ከነጻይቱ ልጅ ጋር አይወርስምና ባሪያይቱንና ልጇን አስወጣ»።
\v 31 ስለዚህ ወንድሞች ሆይ እኛ የነጻይቱ እንጂ የባሪያይቱ ልጆች አይደለንም።
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 ክርስቶስ ነጻ ያወጣን በነጻነት እንድንኖር ነው ። ስለዚህ ጸንታችሁ ቁሙ፥ እንደገና በባርነት ቀንበር አትጠመዱ።
\v 2 እኔ ጳውሎስ የምለውን ተመልከቱ ብትገረዙ ክርስቶስ በምንም ዓይነት መልኩ አይጠቅማችሁም።
\s5
\v 3 የተገረዘ ሁሉ ህግን ሁሉ የመፈጸም ግዴታ አለበት ብዬ እንደገና እመሰክራለሁ።
\v 4 በህግ ልትጸድቁ የምትደክሙ ሁላችሁ የእግዚአብሔር ጠላቶች ሆናችኋል፤ከጸጋም ርቃችኋል።
\s5
\v 5 ምክንያቱም እኛ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የጽድቅን ዋስትና ስለምንጠብቅ ነው።
\v 6 በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍቅር የሆነ እምነት እንጂ መገረዝም ሆነ አለመገረዝ ምንም ትርጉም የለውም።
\v 7 በጥሩ ሁኔታ ትሮጡ ነበር። ታዲያ ለእውነት ከመታዘዝ ያስቆማችሁ ማነው?
\v 8 ይህን እንድታደርጉ የሚያደርግ ጉትጎታ ከጠራችሁ የመጣ አይደለም።
\s5
\v 9 ትንሽ እርሾ ሊጡን በሙሉ እንዲቦካ ያደርጋል።
\v 10 በሌላ መልኩ እንደማታስቡ በጌታ እተማመንባችኋለሁ። ግራ የሚያጋባችሁ ማንም ይሁን ማን ፍርዱን ይቀበላል።
\s5
\v 11 ወንድሞች ሆይ እስከአሁን ተገረዙ እያልኩ የምሰብክ ቢሆን ለምን እሰደድ ነበር? እንግዲያውስ የመስቀሉ እንቅፋት ይደመሰሳል።
\v 12 የሚያስቷችሁ እራሳቸው ሄደው በተሰለቡ ብዬ እመኛለሁ።
\s5
\v 13 ወንድሞች ሆይ እግዚአብሔር የጠራችሁ ለነጻነት ነው። ብቻ ነጻነታችሁን ለሥጋ ፈቃድ አትጠቀሙበት፥ በዚያ ፈንታ እርስ በእርሳችሁ በፍቅር አንዳችሁ አንዳችሁን አገልግሉ።
\v 14 ምክንያቱም ህግ ሁሉ «ባልንጀራህን እንደራስህ ልትወድ ይገባል»
\v 15 በሚለው ትዕዛዝ የተጠቀለለ ነው።
\s5
\v 16 በመንፈስ ተመላለሱ የሥጋን ክፉ ምኞት አትፈጽሙ እላችኋለሁ።
\v 17 ምክንያቱም ሥጋ ከመንፈስ ተቃራኒ መንፈስም ከሥጋ ተቃራኒ ነገር ይመኛሉና ነው።
\v 18 እነዚህ እርስ በእርሳቸው ስለሚቀዋወሙ በውጤቱ እናንተ የምትፈልጉትን ለማድረግ አትችሉም።
\s5
\v 19 እንግዲህ የሥጋ ስራዎች የተገለጡ ናቸው። እነዚህም አስቀድሜ እንዳስጠነቀኩዋችሁ
\v 20 ዝሙት፣እርኩሰት፣ክፉ ምኞት፣ጣዖትን ማምለክ፣ምዋርት፣ጥል፣ክርክር፣ቅናት፣ በቁጣ መገንፈል፣አድመኛነት፣መለያየት፣
\v 21 መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ስካር፥ ዘፋኝነትና የመሳሰሉት ናቸው፥ ፥አስቀድሜ እንደነገርኳችሁ እነዚህን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።
\s5
\v 22 የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፣ ሠላም፣ ትዕግሥ፣ ቸርነት፥ መልካምነት፥ እምነት፥
\v 23 የውሃት፥ ራስን መግዛት ናቸው። ህግ እነዚህን አይቃወም።
\v 24 የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑት ሥጋን ከክፉ ስሜቱና መሻቱ ጋር ሰቅለውታል።
\s5
\v 25 በመንፈስ የምንኖር ከሆነ በመንፈስ እንመላለስ።
\v 26 አንታበይ፣ እርስ በእርሳችን ለክፉ አንነሳሳ፣ አንቀናና።
\s5
\c 6
\cl ምዕራፍ 6
\p
\v 1 ወንድሞች ሆይ አንድ ሰው ስቶ ቢገኝ መንፈሳዊያን የሆናችሁ እናንት በጨዋነት መንፈስ ልታቀኑት ይገባል።ወደ ፈተና እንዳትገቡ ለራሳችሁም ተጠንቀቁ።
\v 2 የእርስ በእርሳችሁን ሸክም በመሸካከም የክርስቶስን ህግ ፈጽሙ።
\s5
\v 3 ምክንያቱም ማንም ምንም ሳይሆን ምንም እንደሆነ ቢያስብ ራሱን ያታልላል።
\v 4 እያንዳንዱ ከሌላው ጋር ሳያነጻጽር የራሱን ሥራ ሊመዝን ይገባል፥ያን ጊዜ የሚመካበት ሊያገኝ ይችላል።
\v 5 እያንዳንዱ የየራሱን ሸክም ይሸከማልና።
\s5
\v 6 ቃሉን የሚማር ከመምህሩ ጋር ሁሉን ነገር ይካፈል ዘንድ ይገባዋል።
\v 7 አትታለሉ እግዚአብሔር አይቀለድበትም።ሰው ምንም ነገር ቢዘራ ያንኑ ደግሞ ያጭዳል።
\v 8 በሥጋው የሚዘራ ከሥጋው ውድቀትን ያጭዳል፤በመንፈስ የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘላለምን ህይወት ያጭዳል።
\s5
\v 9 በተገቢው ጊዜ ፍሬውን እናጭዳለንና መልካምን ከመስራት አንቦዝን።
\v 10 ስለዚህም ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ለሰው ሁሉ በተለይም ለእምነት ቤተሰቦች መልካምን እናድርግ።
\s5
\v 11 በገዛ እጅ ጽህፈቴ ምን ዓይነት ትልልቅ ቃላት እንደጻፍኩላችሁ ተመልከቱ።
\v 12 እነዚያ በሥጋ መልካም መስለው የሚታዩ ስለክርስቶስ መስቀል መከራ ላለመቀበል ብለው እንድትገረዙ ያስገድዱዋችኋል።የተገረዙት እራሳቸው ህጉን አይጠብቁ፣
\v 13 ነገር ግን እናንተን እንድትገረዙ በማድረጋቸው ጉራ ለመንዛት እንድትገረዙ ይፈልጋሉ።
\s5
\v 14 ዓለም ለእኔ ከተሰቀለበት እኔም ለዓለም ከተሰቀልኩበት ከክርስቶስ መስቀል በስተቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።
\v 15 አዲስ ፍጥረት መሆን እንጂ መገረዝም ሆነ አለመገረዝ ምንም አይጠቅምም።
\v 16 በዚህ ሥርዓት ለሚሄዱ ሁሉ እንዲሁም የእግዚአብሔር ለሆነችው ለእስራኤል ሠላምና ምህረት ይሁን።
\s5
\v 17 የክርስቶስን ምልክት በሥጋዬ ተሸክሜአለሁና ከእንግዲህ ማንም አይረብሸኝ።
\v 18 ወንድሞች ሆይ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከመንፈሳችሁጋር ይሁን። አሜን!