am_ulb/48-2CO.usfm

524 lines
53 KiB
Plaintext

\id 2CO
\ide UTF-8
\h 2ኛ ቆሮንቶስ
\toc1 2ኛ ቆሮንቶስ
\toc2 2ኛ ቆሮንቶስ
\toc3 2co
\mt 2ኛ ቆሮንቶስ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 በእግዚአብሔር ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ እና ወንድማችን ከሆነው ጢሞቲዎስ፥ በቆሮንቶስ ለምትገኝ የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን እንዲሁም በመላው አካይያ ላሉ አማኞች ሁሉ፡
\v 2 ከእግዚአብሔር ከአባታችን እንዲሁም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋና ሰላም ለናንተ ይሁን።
\s5
\v 3 የምህረት አባት፥ የመፅናናት አምላክ እና በመከራችን ሁሉ የሚያፅናናን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።
\v 4 እግዚአብሔር በመከራችን ሁሉ ያፅናናል፥እኛም ራሳችን በእርሱ በእግዚአብሔር በተፅናናንበት መፅናናት ልክ ሌሎችን ማፅናናት እንችላለን።
\s5
\v 5 ምክንያቱም የክርስቶስ መከራ በእኛ ላይ እንደበዛ፥ መፅናናታችንም በክርስቶስ በኩል እንዲሁ ይበዛልናል።
\v 6 ነገር ግን መከራን ብንቀበል፥ስለናንተ መፅናናት እና ድነት ነው። ወይንም ደግሞ የእኛ መፅናናት የእናንተም መፅናናት ማለት ነው፤ይህም እኛ በምንቀበለው መከራ እናንተም በተመሳሳይ መልኩ በትእግስት አብራችሁን ስለምትካፈሉ ነው።
\v 7 በናንተም ያለን መታመን ፅኑ ነው፥በመከራችን እንደምትካፈሉ ሁሉ በመፅናናታችንን ደግሞ እንደምትካፈሉ እናውቃለን።
\s5
\v 8 ወንድሞች ሆይ፥በእስያ ስለደረሰብን መከራ እንድታውቁ እንወዳለን፤ በህይወት ለመኖር ተስፋ እስክንቆርጥ ድረስ ከአቅማችን በላይ ከብዶን ነበር።
\v 9 በርግጥም ሞት ተፈርዶብን ነበር። ሆኖም ግን ያ የደረሰብን መከራ ሙታንን በሚያስነሳ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን እንዳንታመን አደረገን።
\v 10 ከብርቱ ጥፋት አዳነን እንዲሁም ያድነናል። መታመናችንን በእርሱ ላይ አድርገናል፤እርሱም ይታደገናል።
\s5
\v 11 በእናንተም የፀሎት ድጋፍ አምላካችን ስራውን ይሰራል። በመቀጠልም በብዙዎች ፀሎት አማካኝነት ለእኛ ስለተሰጠው ሞገስ በርካቶች ምስጋናን ያቀርባሉ።
\s5
\v 12 የምንመካው በህሊናችን ምስክርነት ላይ ነው። ምክንያቱም በዚህ ዓለም ስንመላለስ የነበረው በንፁህ ህሊና እና ከእግዚአብሔር በሚሰጥ ቅንነት ነበር። በተለይም ከናንተ ጋር የነበረን ግንኙነት የተመሰረተው በእግዚአብሔር ፀጋ ላይ እንጂ በምድራዊ ጥበብ ላይ አልነበረም።
\v 13 ልታነቡትና ልትረዱት የማትችሉትን አንዳችም ነገር አንዳልፃፍንላችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፤
\v 14 እናንተም በከፊል እንደተረዳችሁን በጌታችን በኢየሱስ ቀን እናንተ በእኛ እንደምትመኩ እኛም እንዲሁ በእናንተ እንመካለን።
\s5
\v 15 ስለዚህ ርግጠኛ ስለነበርሁ፥ በመጀመሪያ ወደናንተ መምጣት ፈለግሁ፤ ይህ ደግሞ በሁለቱም ጉብኝቶቼ ተጠቃሚዎች እንድትሆኑ ነው።
\v 16 ወደ መቄዶንያ ስሄድ ልጎበኛችሁ ፤ከዚያ ደግሞ ክመቄዶንያ ስመለስ ላያችሁ፤በኋላ ግን እናንተው ወደ ይሁዳ እንደምትልኩኝ አቅጄ ነበር።
\s5
\v 17 ይህንን ሳስብ ታዲያ የወላወልኩ ይመስላችኋልን? ወይስ በአንድ ጊዜ እንደ ሰው መስፈርት "አዎን፥ አዎን" እና "አይደለም፥አይደለም" በማለት አቀድኩን?
\v 18 ነገር ግን እግዚአብሔር የታመነ እንደሆነ፣ እኛም በሁለት ቃል "አዎን" እና "አይደለም" ብለን አንናገርም።
\s5
\v 19 ምክንያቱም በእናንተ መካከል በእኔ፥ በስልዋኖስ እና በጢሞቲዎስ የተሰበከው የእግዚአብሔር ልጅ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በአንድ ጊዜ "አዎን" እና "አይደለም" አልነበረም፥ይልቅስ ሁልጊዜም በእርሱ "አዎን" ነው።
\v 20 በእርሱ የእግዚአብሔር ተስፋዎች ሁሉ "አዎን" ናቸው። ስለዚህ እኛም በእርሱ በኩል ለእግዚአብሔር ክብር "አሜን" እንላለን።
\s5
\v 21 እንግዲህ እኛንም ከእናንተ ጋር በክርስቶስ የሚያፀናን እንዲሁም የሾመን እግዚአብሔር ነው።
\v 22 ለዚህም ወደፊት ለሚሰጠን ዋስትና እንዲሆነን መንፈሱን በልባችን የሰጠን ማህተሙንም ያደረገብን እርሱ ነው።
\s5
\v 23 ሆኖም ግን ወደ ቆሮንቶስ ያልመጣሁት እንዳላሳዝናችሁ አስቤ እንደሆነ እግዚአብሔር ምስክሬ ነው።
\v 24 እኛም እምነታችሁ ምን መምሰል እንዳለበት በናንተ ላይ ልናዝዝ ሳይሆን በእምነታችሁ ፀንታችሁ እንድትቆሙ ለደስታችሁ የምንሰራ ነን።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 ስለዚህም በበኩሌ እንደገና ላስከፋችሁ ተመልሼ መምጣት አልፈለግሁም።
\v 2 ባስከፋችሁ እንኳ ሊያስደስተኝ የሚችለው ያው ያስከፋሁት ሰው አይደለምን?
\s5
\v 3 እንደፃፍኩላችሁ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ ደስ ሊያሰኙኝ የሚገባችው ሰዎች እንዳያሳዝኑኝ ነው። ስለሁላችሁም እርግጠኛ የምሆንበት በእኔ ያለ ደስታ በተመሳሳይ መልኩ በእናንተም ዘንድ ያለ መሆኑ ነው።
\v 4 የፃፍኩላችሁም በታላቅ ጭንቀት፥ በልብ መናወጥ እንዲሁም በብዙ እንባ ነበር፥ ምክንያቱ ደግሞ ለናንተ ያለኝን ጥልቅ ፍቅር እንድታውቁ እንጂ እንዳላሳዝናችሁ ነው።
\s5
\v 5 ማንም ያሳዘነ ሰው ቢኖር እኔን ብቻ ያሳዘነ ሳይሆን በተወሰነ መልኩ ሁላችሁንም ነው።
\v 6 ለዚያም ሰው በብዙዎች የደረሰበት ቅጣት ይበቃዋል።
\v 7 ግን ይህን ሰው በብዙ ሐዘን እንዳይዋጥ ከመቅጣት ይልቅ ይቅር ልትሉትና ልታፅናኑት ይገባል።
\s5
\v 8 ስለዚህም ለዚህ ሰው ፍቅራችሁን በይፋ እንድታረጋግጡለት አደፋፍራችኋለሁ።
\v 9 የፃፍኩላችሁ በሁሉ ነገር ታዛዦች መሆናችሁን እንድፈትንና እንዳውቅ ነው።
\s5
\v 10 አንድን ሰው ይቅር ብትሉት፣ እኔም ያንን ሰው ይቅር እለዋለሁ። እኔ ይቅር የምለው አንዳች ነገር ቢኖር ይቅርታ የማደርግለት በክርስቶስ ፊት ስለ እናንተ ስል ነው።
\v 11 ይህን የማደርገውም ሰይጣን እንዳያታልለን ነው። ምክንያቱም የርሱን እቅድ አንስተውምና።
\s5
\v 12 ምንም እንኳ ወደ ጥሮአዳ ስመጣ የክርስቶስን ወንጌል ለመስበክ በጌታ በር ተከፍቶልኝ ነበር። ሆኖም ወንድሜን ቲቶን በዚያ ስላላገኘሁት በአዕምሮዬ አላረፍኩም ነበር።
\v 13 ስለሆነም እነርሱን ትቼ ወደ መቄዶንያ ተመለስኩ።
\s5
\v 14 ነገር ግን ሁልጊዜ በክርስቶስ በድል ለሚመራን፥ ጣፋጭ የእውቀት ሽታ በየስፍራውም ለሚናኘው ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።
\v 15 ምክንያቱም በሚድኑትና በሚጠፉት መካከል ለእግዚአብሔር የክርስቶስ ጣፋጭ ሽታ ነን።
\s5
\v 16 ለሚጠፉት ሰዎች፥ለሞት የሚሆን የሞት ሽታ ስንሆን ለሚድኑት ደግሞ ለህይወት የሚሆን የህይወት ሽታ ነን። ለነዚህ ነገሮች የበቃ ማነው?
\v 17 የእግዚአብሔርን ቃል ለትርፋቸው እንድሚነግዱበት እንደ ብዙዎች አይደለንም። በዚያ ፈንታ በክርስቶስ ሆነን በእግዚአብሔር ፊት፥ ከእግዚአብሔር እንደተላክን በቅን ልቦና እንናገራለን።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 ራሳችንን እንደገና ልናወድስ እንጀምራለንን? አንዳንድ ሰዎች እንደሚያደርጉት ለናንተም ሆነ ከእናንተ የድጋፍ ደብዳቤ ያስፈልገን ይሆን? አያስፈልገንም።
\v 2 እናንተ ራሳችሁ በልባችን ላይ የተፃፋችሁ፥በሁሉም ሰዎች የምትታውቁ እና የምትነበቡ የድጋፍ ደብዳቤያችን ናችሁ።
\v 3 በእኛ የቀረባችሁ የክርስቶስ መልዕክት ከመሆናችሁም በላይ በህያው የእግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም ያልተፃፋችሁ፤በሰዎች የልብ ፅላት ላይ እንጂ በድንጋይ ፅላት ላይ ያልተቀረፃችሁ ናችሁ።
\s5
\v 4 እንግዲህ በክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ላይ ይህ መታመን አለን።
\v 5 ከእኛ የሆነ ብለን ልናስበው የምንችል አንዳች ችሎታ የለንም፤ነገር ግን ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው።
\v 6 እርሱም የአዲስ ኪዳን አገልጋዮች አደረገን። ይህ ኪዳን የፊደል ሳይሆን የመንፈስ ነው። ምክንያቱም ፊደል ይገድላል፣ መንፈስ ግን ህይወትን ይሰጣል።
\s5
\v 7 የእስራኤል ህዝብ ከፊቱ ክብር የተነሳ እያደር የሚደበዝዘውን የሙሴን ፊት መመልከት እስኪያቅታቸው ድረስ በፊደላት በድንጋይ ላይ የተቀረፀው የሞት አገልግሎት በክብር ከሆነ፤
\v 8 የመንፈስ አገልግሎት እጅግ በክብር አይልቅምን?
\s5
\v 9 የኩነኔ አገልግሎት ክብር ከነበረው፥የፅድቅ አገልግሎት እንደምን በክብር ይብዛ!
\v 10 በርግጥም ቀድሞ በክብር የነበረው ከሱ በሚበልጥ ክብር ተሽሯል።
\v 11 አላፊው በክብር ከሆነ ፀንቶ የሚኖረው በክብር እንዴት ይበልጥ!
\s5
\v 12 እንግዲያውስ እንዲህ ያለ ትምክህት ስላለን እጅግ በድፍረት እንናገራለን።
\v 13 እኛ የእስራኤል ህዝቦች የሚያልፈውን ክብር ትኩር ብለው መመልከት እንዳልቻሉት፤ ፊቱን በመሸፈኛ እንደ ከለለው እንደ ሙሴ አይደለንም።
\s5
\v 14 ሆኖም ግን አእምሮዋቸው ተሸፈነባቸው። እስከዛሬም አሮጌው ኪዳን ሲነበብ ያው መሸፈኛ ይኖራል፤ሊገለጥም አይችልም፤ ምክንያቱም ሊወገድ የሚችለው በክርስቶስ ነው።
\v 15 ሆኖም ግን እስከዛሬ ድረስ የሙሴ ህግ ሲነበብ በልባቸው ላይ መሸፈኛው ይኖራል።
\v 16 ሰው ግን ወደ ጌታ መለስ ሲል ፥መሸፈኛው ይነሳል።
\s5
\v 17 ጌታም መንፈስ ነው፤የጌታም መንፈስ ባለበት ነፃነት አለ።
\v 18 እኛም ሁላችን ባልተሸፈነ ፊት የጌታን ክብር እያየን እርሱን ወደሚመስል ከአንድ ክብር ደረጃ ወደ ሌላ ክብር ደረጃ እንለወጣለን፤ይህም የሚሆነው መንፈስ ከሆነው ጌታ ነው።
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 እንግዲህ፥ይህ አገልግሎት ስላለን እንዲሁም ምህረት እንደተቀበልን መጠን፥ ተስፋ አንቆርጥም።
\v 2 በዚያ ፈንታ ግን አሳፋሪ እና ድብቅ የሆኑ መንገዶችን ክደናል። የተንኮል ህይወት አንኖርም፥የእግዚአብሔርንም ቃል ያለ አግባብ አንጠቀምበትም። እውነትንም እየተናገርን ራሳችንን ለሰው ሁሉ ህሊና በእግዚአብሔር ፊት እናቀርባለን።
\s5
\v 3 ሆኖም ግን ወንጌላችን የተሸፈነ ቢሆን፥የተሸፈነው ለሚጠፉት ሰዎች ብቻ ነው።
\v 4 በእነርሱ ሁኔታ ታዲያ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምን አዕምሮዋቸውን አሳውሮታል። በዚህም የእግዚአብሔር መልክ የሆነውን የክርስቶስን የክብር ወንጌል ብርሃን እንዳያዩ አደረጋቸው።
\s5
\v 5 ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክም፥እንዲሁም ስለ ኢየሱስ ስንል የእናንተ አገልጋዮች ነን።
\v 6 ውስጥ ብርሃን ይብራ" ያለው ራሱ እግዚአብሔር ነው፤እናም በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔር ክብር የእውቀት ብርሃን እንዲሰጠን በልባችን ውስጥ አበራልን።
\s5
\v 7 ነገር ግን እጅግ ታላቅ የሆነው ሃይሉ ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳልሆነ ለማሳየት ይህ ሃብት በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን።
\v 8 በሁሉ መንገድ መከራን እንቀበላለን፥ሆኖም በዚያ አንዋጥም። እናመነታለን ነገር ግን ተስፋ በማጣት አንረበሽም።
\v 9 ቢሆንም ግን ተረስተን አንቀርም።
\v 10 የኢየሱስ ህይወት በሰውነታችን እንዲገለጥ የእርሱን ሞት ሁልጊዜ በሰውነታችን እንሸከማለን።
\s5
\v 11 ይህም የኢየሱስ ህይወት በሰብዓዊ ሰውነቶቻችን እንዲገለጥ እኛ ህያዋን የሆንን በየዕለቱ ስለ ኢየሱስ ምክንያት ለሞት ታልፈን እንሰጣለን።
\v 12 በዚህም ምክንያት ሞቱ በእኛ፥ ህይወቱም በእናንተ ይሰራል።
\s5
\v 13 ነገር ግን "አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ"ተብሎ እንደተፃፈ፡ ሁላችንም አንድ አይነት የእምነት መንፈስ አለን። ስለምናምንም እንናገራለን።
\v 14 ጌታ ኢየሱስን ከሞት ያስነሳው እኛንም ከእርሱ ጋር ያስነሳናል። ከእናንተም ጋር ወደ ፊቱ እንዲያመጣን እናውቃለን።
\v 15 የሚሆነው ለእናንተ ጥቅም ሲሆን ፀጋ ለብዙዎች ሲበዛ ለእግዚአብሔር ክብር የሚሆን ምስጋናም ይጨምራል።
\s5
\v 16 ስለዚህም ተስፋ አንቆርጥም። ምንም እንኳ ውጫዊው ማንነታችን እየደከም ቢመጣም ውስጣዊው ማንነታችን ዕለት በየዕለት ይታደሳል።
\v 17 ይህ ጊዜያዊ፣ ቀላል መከራችን መለኪያ ለሌለው፥ ለላቀው ዘላለማዊ ክብር የሚያዘጋጀን ነው።
\v 18 የሚታዩትን ነገሮች ሳይሆን የማይታዩትን ነገሮች እንመለከታለን። የምናያቸው ነገሮች ጊዜያዊ ሲሆኑ የማይታዩት ነገሮች ግን ዘላለማዊ ናቸው።
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 ምድራዊው መኖሪያችን ቢፈርስ እንኳ በሰማይ በሰው እጅ ያልተሰራ ዘላለማዊ ቤት በእግዚአብሔር እንደተሰራልን እናውቃለን።
\v 2 ድንኳን ውስጥ ሆነን እንቃትታለን፥ሰማያዊ መኖሪያችንንም ልንለብስ እንናፍቃለን።
\v 3 ምክንያቱም ያን ለብሰን ስንገኝ ራቁታችንን ሆነን አንገኝም ።
\s5
\v 4 በርግጥ በዚህ ድንኳን ውስጥ ሆነን ከብዶን እንቃትታለን፤ምክንያቱ ደግሞ ሟች የሆነው ሰውነት በህይወት መዋጥ ስላለበት እኛም ለብሰን እንጂ ራቁታችንን መሆን አንፈልግም።
\v 5 ወደ ፊት ሊመጣ ላለው የመንፈሱን ዋስትና የሰጠን ለዚህም ያዘጋጀን እግዚአብሔር ነው።
\s5
\v 6 እንግዲህ በሰውነታችን በዚህ ምድር በምንኖርበት ጊዜ በሰማይ ካለው ጌታ ርቀን እንዳለን ይህን እርግጠኛ ሁኑ
\v 7 ምክንያቱም በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና።
\v 8 ስለዚህ ይህ ድፍረት አለን፤ከሰውነታችን ተለይተን ከጌታ ጋር በሰማይ ቤት መሆንን እንመርጣለን።
\s5
\v 9 ስለሆነም በምድርም ብንሆን ወይም ከምድር ብንለይ ግባችን እርሱን ማስደሰት ነው።
\v 10 እያንዳንዳችን በሰውነታችን በዚህ ምድር ላይ የሰራነውን መልካምም ሆነ ክፉ እንቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት መቅረባችን ግድ ነው።
\s5
\v 11 እንግዲህ ጌታን መፍራት ምን ማለት እንደሆን ስለምናውቅ ሰዎችን ግድ እንላለን። ማንነታችን በእግዚአብሔር ፊት የተገለጠ ስለሆነ ለናንተም ህሊና ግልፅ እንደሚሆን ተስፋ አለኝ።
\v 12 ራሳችንን ደግመን እንድታወድሱን አናቀርብላችሁም፥ ሆኖም በልብ ሳይሆን በውጫዊው መልክ ለሚመኩ መልስ መስጠት እንዲቻላችሁ እኛን ምክንያት አድርጋችሁ እንድትመኩ እናስታውቃችኋለን።
\s5
\v 13 እንደ እብድ ቢያረገን፥ ለእግዚአብሔር ነው፤እንደ ባለአዕምሮ ብንሆን ደግሞ ለእናንተ ስንል ነው።
\v 14 የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል፥ በዚህ ነገር እርግጠኞች ነን፡አንዱ ሰው ስለሁሉ ሞተ፥ ስለሆነም ሁሉም ሞቱ ማለት ነው።
\v 15 በህይወት ያሉትም ስለእነርሱ ለሞተውና ለተነሳው እንጂ ለራሳቸው እንዳይኖሩ ክርስቶስ ስለሁሉ ሞተ።
\s5
\v 16 ስለዚህም ምክንያት ክርስቶስን ከዚህ ቀደም በሰዋዊ መንገድ አይተነው ቢሆን፥ካሁን ጀምሮ ማንንም በሰዋዊ መስፈርት አንፈርድም። በማንም ላይ ከዚህ በኋል በዚህ መንገድ አንፈርድም።
\v 17 ስለሆነም ማንም በክርስቶስ ውስጥ ቢሆን እርሱ አዲስ ፍጥረት ነው። አሮጌ ነገሮች አልፈዋል። ተመልከቱ፥ ሁሉ አዲስ ሆኗል።
\s5
\v 18 እነዚህ ነገሮች ሁሉ የሆኑት እኛን በክርስቶስ ከራሱ ጋር ባስታረቀንና የዕርቅ አገልግሎት በሰጠን በእግዚአብሔር ነው።
\v 19 እግዚአብሔርም በደላቸውን ሳይቆጥርባቸው ዓለሙን በክርስቶስ ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበር። እኛንም ለዚህ የዕርቅ መልዕክት ታማኝ አድርጎ ሾመን።
\s5
\v 20 ስለዚህም እግዚአብሔር በእኛ ሆኖ ልመናውን እንደሚያቀርብ፥ የክርስቶስ ተወካዮች ሆነን ተሹመናል። ከእናንተም ጋር በመሆን ስለ ክርስቶስ "ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ!" ብለን ልመና እናቀርባለን።
\v 21 እኛም በእርሱ የእግዚአብሔር ፅድቅ እንድንሆን ሃጢያት ሰርቶ የማያውቀውን ክርስቶስን እግዚአብሔር የሃጢያት መስዋዕት አደረገው።
\s5
\c 6
\cl ምዕራፍ 6
\p
\v 1 እንደዚሁም፥ አብሮ እንደሚሰራ የእግዚአብሔርን ፀጋ እንዲሁ እንዳትቀበሉ እለምናችኋለሁ።
\v 2 ምክንያቱም እግዚአብሔር እንዲህ ብሏልና "በምቹ ጊዜ ሰማሁህ በድነትም ቀን ረዳሁህ።" ልብ በሉ፥ ምቹ ጊዜም ሆነ የድነት ቀን አሁን ነው።
\v 3 አገልግሎታችን እንዳይነቀፍ በማንም ፊት ማሰናከያ አናኖርም።
\s5
\v 4 ከዚያ ይልቅ፥ በድርጊቶቻችን ሁሉ የእግዚአብሔር አገልጋዮች መሆናችንን እናረጋግጣለን። ይህም በመፅናት፥በመከራ፥ በስቃይ፥በችግር
\v 5 በመገረፍ፥ በእስራት፥ጥላቻ በተሞላ አመፅ፥ ፥በከባድ ስራ ፥እንቅልፍ በማጣት፥በርሃብ፥
\v 6 በንፅህና፥በእውቀት፥በትዕግስት፥በርህራሄ፥በመንፈስ ቅዱስ፥በእውነተኛ ፍቅር፥
\v 7 በእውነት ቃል፥ በእግዚአብሔር ሃይል ማለትም ለቀኝ እና ለግራ ለሚሆን ለፅድቅ የጦር ዕቃ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ነን።
\s5
\v 8 በክብርም ሆነ በውርደት፥ በሃሜትም ሆነ በሙገሳ ውስጥ እንሰራለን። በሃሰት ብንከሰስም እውነተኞች ሆነን ተገኝተናል።
\v 9 ያልታወቅን ሆነን ስንሰራ፥እንታወቃለን፤ የምንሞት ስንመስል ህያዋን ነን። በጥፋታችን እንደሚቅጣ ሰው ብንሆንም፥ሞት አልተፈረደብንም።
\v 10 እንደ ሃዘንተኞች ስንሰራ ሁልጊዜም ግን ደስተኞች ነን፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለፀጎች እናደርጋለን፥ ምንም የሌለን ስንሆን፥ ሁሉም አለን።
\s5
\v 11 የቆሮንቶስ ሰዎች ሆይ፥ ሁሉን ነገር በግልፅ ነግረናችኋል፥ልባችንንም ለእናንተ ከፍተንላችኋል።
\v 12 ልባችሁ በራሳችሁ መሻት እንጂ በእኛ ምክንያት አልተዘጋም።
\v 13 ተገቢ በሆነ ሁኔታ እኔም እንደ ልጆች እናገራችኋለሁ፤ልባችሁን ክፈቱልን።
\s5
\v 14 ከማያምኑ ጋር በማይሆን መንገድ በአንድ ላይ አትተሳሰሩ። ፅድቅ ከአመፀኝነት ጋር ምን መዛመድ አለው? ብርሃንስ ከጨለማ ጋር ምን ህብረት አለው?
\v 15 ክርስቶስስ ከቤልዖር ጋር ምን ስምምነት አለው? የሚያምንስ ከማያምን ጋር ምን ድርሻ አለው?
\v 16 የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስስ ከጣዖታት ጋር ምን ስምምነት አለው? እግዚአብሔር "ከእነርሱም ጋር አድራለሁ፥በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፤ አምላካቸው እሆናለሁ፥ እነርሱም ህዝብ ይሆኑኛል" ብሎ ስለተናገረ እኛ የህያው እግዚአብሔር መቅደሶች ነን።
\s5
\v 17 ስለዚህም "ከመካከላቸው ውጡ፤የተለያችሁም ሁኑ" ይላል ጌታ፥ "እርኩሱን አትንኩ፥እኔም እቀበላችኋለሁ።
\v 18 አባት እሆናችኋለሁ እናንተም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ትሆኑኛላችሁ።" ብሏል ሁሉን የሚችል ጌታ።
\s5
\c 7
\cl ምዕራፍ 7
\p
\v 1 የተወደዳችሁ ሆይ፥ እነዚህ ተስፋዎች ስላሉን በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን እየተከተልን ስጋችንን እና መንፈሳችንን ከሚያረክስ ከማናቸውም ነገር ራሳችንን እናንፃ።
\s5
\v 2 ለእኛ በልባችሁ ስፍራ ስጡን! ማንንም አልበደልንም፥ማንንም አልጎዳንም፥ ማንንም ለራሳችን ጥቅም አልበዘብዝንም።
\v 3 ይህንን የምላችሁ ልኮንናችሁ ብዬ አይደለም፤ምክንያቱም አብረን ለመሞትም ሆነ ለመኖር በልባችን ውስጥ አላችሁና ነው።
\v 4 በእናንተም ታላቅ መታመን አለኝ፣ትምክህቴም ናችሁ። በመከራዎቻችን እንኳ መፅናናት እና የተትረፈርፈ ደስታ ሞልቶኛል።
\s5
\v 5 ወደ መቄዶንያ በመጣን ጊዜ ሰውነታችን እረፍት አልነበረውም። ይልቁንስ በውጭ ግጭት እና በውስጥ ፍርሃት ስለነበረብን በሁሉ አቅጣጫ ተጨነቅን ።
\v 6 ነገር ግን ተስፋ የቆረጡትን የሚያፅናና አምላክ በቲቶ መምጣት አፅናናን።
\v 7 የእርሱ መምጣት ብቻ ሳይሆን እናንተም እርሱን ያፅናናችሁት ማፅናናት እኛን አፅናናን። ለእኔም ያላችሁን ታላቅ ፍቅር፥ርህራሄ እና ጥልቅ ሃሳብ ሲነግረን በይበልጥ ተደሰትሁ።
\s5
\v 8 ምንም እንኳ በመልዕክቴ ባሳዝናችሁም ለምን ፃፍኩ ብዬ አልፀፀትም። ነገር ግን፥የምፀፀተው መልዕክቴ ለጥቂት ጊዜም እንዳሳዘናችሁ ስለማውቅ ነው።
\v 9 አሁን የምደሰትበት ምክንያት ስላዘናችሁ ሳይሆን ሃዘናችሁ ወደ ንስሃ ስለመራችሁ ነው። እግዚአብሔር የሚወደው አይነት ሃዘን እየተለማመዳችሁ ስለሆነ በእኛ ምክንያት ያጣችሁት ነገር የለም።
\v 10 እግዚአብሔር የሚወደው ሃዘን ፀፀት የሌለበት፥ ወደ ድነት የሚመራ ንስሃን ያመጣል። ዓለማዊ ሃዘን ግን ሞትን ያመጣል።
\s5
\v 11 እግዚአብሔር የሚወደው ሃዘን ምን አይነት ታላቅ ቁርጠኝነት እንዳመጣላችሁ እዩ። ይህም ታላቅ ቁርጠኝነት ምን ያህል ንፁህ መሆናችሁን፥ ምን ያህል በሃጢያት ላይ እንድትቆጡ እንዳደረጋችሁ፥ ምን አይነት ናፍቆት እንዳሳደረባችሁ፥ ምን አይነት በጎ ቅንዓት እንደፈጠረባችሁ ፥ፍትህ እንድታደርጉም ምን አይነት ጥልቅ መሻት እንዳደረገላችሁ ተመልከቱ! በዚህ በኩል በሁሉም ንፁህ መሆናችሁን አስመስክራችኋል።
\v 12 ምንም እንኳ ብፅፍላችሁም የፃፍኩት ለክፉ አድራጊ ወይም በክፉ አድራጎቱ መከራ ለሚቀበል ሳይሆን ለእኛ ምን ያህል እንደምታስቡ በእግዚአብሔር ፊት እንዲታወቅ ነው።
\s5
\v 13 በዚህ እንበረታታለን። እኛ ከመፅናናታችን በተጨማሪ በቲቶ ደስታ ሃሴት አድርገናል፤ መንፈሱ በሁላችሁ ምክንያት አርፏልና ነው።
\v 14 ስለናንተ በመመካት ለእርሱ ተናግሬ ነበር፣እናንተም አላሳፈራችሁኝም። በሌላ አንፃር ስለናንተ የተናገርነው ሁሉ እውነት ነበር፥ለቲቶም ስለናንተ የተናገርነው ሁሉ ትክክል መሆኑ ተረጋግጧል።
\s5
\v 15 እርሱም በፍርሃት እና በመንቀጥቀጥ ያደረጋችሁለትን አቀባበል እንዲሁም የሁላችሁንም መታዘዝ በሚያስብበት ጊዜ ለእናንተ ያለው ፍቅር ታላቅ ነው።
\v 16 በናንተ ሙሉ መታመን ስላለኝ፥ሃሴት አደርጋለሁ።
\s5
\c 8
\cl ምዕራፍ 8
\p
\v 1 ወንድሞችና እህቶች ሆይ ለመቄዶንያ ለአብያተ ክርስቲያናት ስለ ተሰጠው የእግዚአብሔር ጸጋ እንድታውቁ እንፈልጋለን
\v 2 እጅግ የሚፈትናቸው መከራ በደረሰባቸው ጊዜ የደስታቸው መብዛትና የደህንነታቸው አስከፊነት የልግስናቸውን መትረፍረፍ አብዝቷል።
\s5
\v 3 የሚቻላቸውን ያህል ከሚቻላቸውም እንደ ሰጡ እኔ እመሰክርላቸዋለው። በፈቃዳቸውም ለቅዱሳን በሚሰጠው በዚህ አገልግሎት የመሳተፍ ዕድል ይኖራቸው ዘንድ
\v 4 እኛን በብዙ ልመና ለመኑን።
\v 5 ይህም የሆነው እኛ እንደጠበቅነው አይደለም ነገር ግን በመጀመሪያ ራሳቸውን በጌታ ከዚያም በእግዘአብሔር ፈቃድ ለእኛ ሰጡ።
\s5
\v 6 ስለዚህ አስቀድሞ ከእናንተ ጋር የጀመረውን ተግባር በእናንተ ዘንድ ያለውን ይህን የልግስና ስራ ከፍጻሜ እንዲደርስ ቲቶን ግድ ብለነው ነበር።
\v 7 ነገር ግን እናንተ በሁሉም ነገር በእምነት፥ በንግግር ፣በዕውቀት በትጋት ሁሉ እንዲሁም ለእኛ ባላችሁ ፍቅር እንደሚልቁ በዚህ በበጎ ስራ ደግሞ የምትልቁ ሁኑ።
\s5
\v 8 ከሌሎች ሰዎች ትጋት ጋር በማወዳደር የፍቅራችሁን ቅንነት ለማረጋገጥ እንጂ ይህንን እንደ ትዕዛዝ አልልም እናንተ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ ታውቃላችሁና።
\v 9 በእርሱ ድኽነት እናንተ ባለጠጎች ትሆኑ ዘንድ ፥ እርሱ ባለ ጠጋ ቢሆንም እንኳ ስለ እናንተ ደኸየ።
\s5
\v 10 በዚህ ጉዳይ እናንተን ስለሚጠቅማችሁ ነገር ምክር እለግሳችኋለው። ከአንድ ዓመት በፊት አንድን ነገር ለማድረግ መጀመር ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ልታደርጉት መሻት በውስጣችሁ ነበር።
\v 11 አሁን ያንኑ ማድረጋችሁን ፈጽሙ። እንግዲህ ልክ በዚያን ጊዜ ልታደርጉት ጉጉትና ጠንካራ ፍላጎት እንደ ነበራችሁ፣ወደ ፍጻሜ ልታመጡት ደግሞ ትችላላችሁ።
\v 12 ይህን ስራ ለመስራት ጉጉት ካለ፣ አንድ ሰው በሌለው ሳይሆን ባለው ነገር ላይ ተመስርቶ ሲሰራ መልካምና ተቀባይነት ያለው ነው።
\s5
\v 13 ይህ ተግባር ሚዛናዊነት እንዲኖር ነው እንጂ ሌሎች እንዲቀልላቸው እናንተም ሸክም እንዲበዛላችሁ አይደለም።
\v 14 አሁን ያለው የእናንተ መትረፍ ለእነርሱ የሚያስፈልጋቸውን ይሞላል። ይህም ደግሞ ሚዛናዊነት ይኖር ዘንድ የእነርሱ መትረፍረፍ የእናንተ ፍላጎት ደግሞ እንዲሞላ ነው።
\v 15 እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ ፦ «ብዙ ያለው ምንም አልተረፈውም ፣ጥቂት ያለው ግን ምንም አልጎደለውም።»
\s5
\v 16 ነገር ግን እኔ ለእናንተ ያለኝን ቅን ሃሳብ በቲቶ ልብ ያኖረው እግዚአብሔር ይመስገን።
\v 17 እርሱ ልመናችንን መቀበል ብቻ ሳይሆን ፣ ትጋትን በማሳየት በራሱ ፈቃድ ወደ እናንተ መጥቷልና።
\s5
\v 18 ከእርሱ ጋርም ወንጌልን በማወጅ ስራው በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የተመሰገነውን ወንድም ልከናል።
\v 19 ይህ ብቻ አይደለም ነገር ግን ለራሱ ለጌታ ክብርና እኛ ለመረዳት ያለንን ጉጉት ለመግለጥ ይህን የጸጋ ስራ እንዲያከናውን አብሮን ይጓዝ ዘንድ አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ መርጠውት ነበር።
\s5
\v 20 ስለምንሰበስበው ስለዚህ የልግስና ስጦታ ማንም ትችት ለማቅረብ ምክንያት እንዳያገኝ እንጠነቀቃለን።
\v 21 በጌታ ፊት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በሰዎች ፊት ደግሞ የከበረውን ነገር ለማድረግ እንተጋለን።
\s5
\v 22 ብዙ ጊዜ ፈትነን በበርካታ ተግባራት ተነሳሽነት ያለው ሆኖ ያገኘውን ፣አሁን ግን በእናንተ ላይ ትልቅ መታመን ምክንያት የበለጠ ትጋት የሚያሳየው ሌላ ወንድም ከእነርሱ ጋር እንልካለን።
\v 23 ቲቶን በሚመለከት ግን ስለ እናንተ ከእኔ ጋር የሚሰራ አጋሬ ነው። ወንድሞቻችንን በሚመለከት አብያተ ክርስቲያናት የላኳቸው የክርስቶስ ክብር ናቸው።
\v 24 ስለዚህ ፍቅራችንን ፣ በሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ዘንድም ስለ እናንተ ለምን እንደ ተመካን ግለጡላቸው።
\s5
\c 9
\cl ምዕራፍ 9
\p
\v 1 ለቅዱሳን ስለ ሚሆነው አግልግሎት ለእናንተ ልጽፍላችሁ አያስፈልገኝም ።
\v 2 ለመቄዶንያ ሰዎች ስለተመካሁት በውስጣችሁ ስላለው መሻት አውቃለው። በአካዶያ የሚነግሩት ካለፈው ዓመት ጀምሮ መዘጋጀትቱን ነገርኋቸው። የእናንተ ቅንዓት ብዙዎቻቸውን ለስራ አነሳስቷል።
\s5
\v 3 እንግዲህ የተዘጋጃችሁ ትሆናላችሁ እንዳልኩት የተዘጋጃችሁ ትሆኑ ዘንድ፣ ስለ እናንተ መመካታችን ከንቱ እንዳይሆን ወድሞችን ልኬአለው።
\v 4 ምናልባት አንዳቸው ከ እኔ ጋር ከሜቄዶንያ በመጡ፣ሳትዘጋጁ ቢያገኟችሁ ሁላችንም ሀፍረት ይሰማናል ነገር ግን በእናንተ ስለምተማመን ፣ ስለ እናንተ የምለው ምንም የለኝም።
\v 5 ስለዚህ ወደ እናንተ እንዲመጡና እናንተ ተስፋ ለሰጣችሁት ስጦታ በቅድሚያ ዝግጅት እንዲያደርጉ ወንድሞችን መለመን አስፈላጊ እንደሆነ አሰብሁ። ይህም እንድትሰጡ ስለ ተገደዳችሁ ሳይሆን በነጻ እንደተሰጠ ስጦታ ዝግጁ ይሆን ዘንድ ነው።
\s5
\v 6 ፍሬ ነገሩ ይህ ነው ፦ በጥቂት የሚዘራ በጥቂቱ ያጭዳል ፣ አትረፍርፎ የሚዘራ አትረፍርፎ ያጭዳል።
\v 7 እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ ስትሰጡ በሐዘን ወይም በግድ አይደለም።
\s5
\v 8 እግኢአብሔር ሁልጎዜ በነገር ሁሉ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አግኝቷችሁ በብጎ ስራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።
\v 9 እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ «ሀብቱን በተነ ፣ለድሆችም አከፋፈለ።»
\s5
\v 10 ለዘሪን ዘርን ለምግብ እንጀራን የሚሰጥ ፣የሚዘራ ዘርን ደግሞ ይሰጣል ያበዛውማል፣ ምርት ይጨምራል።
\v 11 ለጋሶች እንድትሆኑ በሁሉም ረገድ መበልጸግ ትላላችሁ፣ ይህም በእኛ በኩል ለእግኢአብሔር ምስጋና ምክንያት ይሆናል።
\s5
\v 12 ይህ የመስጠት አገልግሎት ለቅዱሳን ይሚያስፈልጋቸውን ሁሉ የሚሰጥ ብቻ አይደለምና፣ ነገር ግን ለእግዚአብሔር የሚቀርብ ብዙ ምስጋና ደግሞ ይበዛል።
\v 13 በዚህ አገልግሎት ተፈትናችሁ አልፋችኋል ደግሞም በክርስቶስ ወንጌል ምስክርነት በመታዘዛችሁ ፣እንዲሁም ለእነርሱና ለሁሉ ባደረጋችሁት የስጦታችሁ ልግስና እግዚአብሔርን ታከብራላችሁ።
\v 14 በእናንተ ላይ ካለው እጅግ ታላቅ የእግዚአብሔር ጸጋ የተነሳ ስለ እናንተ ሲጸልዩ ይናፍቁአችኋል።
\v 15 ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!
\s5
\c 10
\cl ምዕራፍ 10
\p
\v 1 እኔ ራሴ ጳውሎስ ፣ በፊታችሁ ትሁት የሆንሁ በክርስቶስ ገርነትና የዋህነት እለምናችኃለሁ።
\v 2 እንደ ስጋ ፈቃድ እንደምንኖር የሚያስቡትን በምቃወምበት ጊዜ ፣ ከእናንተ ጋር ሳለሁ መሆን እንደሚገባኝ በራስ በመተማመን የምደፍር መሆን የለብኝም ብዬ እለምናችኃለው ።
\s5
\v 3 ምንም እንኳ በስጋ የምንመላለስ ብንሆን፣ እንደ ስጋ አንዋጋም።
\v 4 የምንዋጋባቸው የጦር መሳሪያዎች ሥጋዊ አይደሉምና ይልቁንም ምሽጎችን ለመስበር መለኮታዊ ኃይል አለቸው ፥ አሳሳች የሆኑ ክርክሮችንም ያፈርሳሉ።
\s5
\v 5 ደግሞም በእግዚአብሔር ዕውቀት ላይ የሚነሳውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ፥ እንዲሁም ለክርስቶስ ለመታዘዝ ሀሳብን ሁሉ እንማርካለን።
\v 6 መታዘዛችሁም በተፈጸመ ጊዜ ፣ ይለመታዘዝን ተግባር ሁሉ ለመቅጣት እንዘጋጃለን።
\s5
\v 7 በግልጽ ከፊታችን ያለውን ተመልከቱ ፥ ማንም የክርስቶስ እንደሆነ ቢያምን ልክ እርሱ የክርስቶስ እንደሆነ እኛ ደግሞ እንዲሁ መሆናችንን ራሱ ያሰበው።
\v 8 ሊያንጻችሁ እንጂ ሊያጠፋችሁ የይደለ ጌት ኣስለ ሰለ ሰጠው ስልጣናችን ጥቂት አብዝቼ ብመካም እንኳ፥ አላፍርም።
\s5
\v 9 በመልዕክቶቼም ላስደነግጣችሁ አልፈልግም።
\v 10 አንዳንድ ሰዎች ፥«መልእቶቹ ጠንከር ያሉና ኃይለኛ ናቸው፥ ነገር ግን በአካል ደካማ ነው፥ ንግግሩም ሊሰማ የሚገባ አይደለም»ይሉናል።
\s5
\v 11 እንደነዚህ ያሉ ሰዎችን ስንርቅ በመልዕክት የምንለው፥እዚያ ስንሆን ከምናደርገው ጋር አንድ መሆኑን ይረዱ።
\v 12 ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ጋር ራሳችንን እስከ ማስተያየት ወይም እስከ ማወዳደር ድረስ አንሔድም። ነገር ግን እነርሱ ራሳቸውን ከሌላ ጋር ሲመዝኑና ራሳቸውን እርስ በእርስ ሲያወዳድሩ ፥ ማስተዋል ተላቸውም።
\s5
\v 13 ይሁን እንጂ እኛ ከልክ በላይ አንመካም፥ ነገር ግን ወደ እናንተ እንኳ እስክንደርስ እግዚአብሔር በወሰነልን ስራ እንሆናለን።
\v 14 ወድ እናንተ ስንደርስ ከመጠን አላለፍንምንና በክርስቶስ ወንጌል ወደእናንተ ለመድረስ የመጀመሪያዎች ነበርን።
\s5
\v 15 በሌሎች ድካም ከልክ ያለፈ አንመካም ፥ ነገር ግን ከእናንተ አካባቢ አልፎ እንኳ
\v 16 ወንጌልን እንሰብክ ዘንድ እምነታችሁ ሲያድግ ስራችን እጅግ እንደሚስፋፋ ተስፋ እናደርጋለን ። በሌላ ስፍራ እየተሰራ ስላለው ሥራ አንመካም።
\s5
\v 17 «ነገር ግን የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ።»
\v 18 ጌታ የሚያመሰግነው እንጂ፣ ራሱን የሚያመሰግን ተፈትኖ የሚወጣ አይደለምና።
\s5
\c 11
\cl ምዕራፍ 11
\p
\v 1 በጥቂት ሞኝነቴ ልትታገሱኝ ብትችሉ እመኝ ነበር፣ እናንተ ግን በእርግጥ ታግሳችሁኛል!
\v 2 እኔ ስለ እናንተ እቀናለሁና እንደ አንዲት ንጽሕት ድንግል ለክርስቶስ ላቀችርባችሁ ለአንድ ባል ስላጨዋችሁ በእግዚአብሔር ቅንአት እቀናላችኃለው ።
\s5
\v 3 ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳታለላት ፣ ሐሳባችሁ ለክርስቶስ ካልችሁ ቅንና ንጹህ ታማኝነት መረን እንዳትወጡ ብዬ እፈራለው።
\v 4 አንድሰው መጥቶ እኛ ከሰበክበው የተለየ ሌላ ኢየሱስ ቢያውጅላችሁ፣ ወይም ቀድሞ ከተቀበላችሁት የተለየ መንፈስ ብትቀበሉ ወይም እናንተ ከተቀበላችሁት የተለየ ወንጌል ቢደርሳችሁ ደህና ትታገሱታላችሁና።
\s5
\v 5 ከነዚያ «ገናና ሐዋርያት» በጥቂቱ እንኳ የማንስ አይደለሁም ብዬ አስባለውና።
\v 6 ነገር ግን በአነጋገር ያልሰለጠንሁ አይደለሁም። በሁሉም መንገድና በሁሉም ነገር ይህን አሳውቀናችኋል።
\s5
\v 7 የእግዚአብሔርን ወንጌል በነፃ ስለሰበኩለችሁ፥ እናንተ ከፍ እንድትሉ እኔ ራሴን በማዋረዴ ኋጢያት ሰራሁን?
\v 8 እናንተን ማገልገል እችል ዘንድ ከእነርሱ እርዳታ በመቀበል ሌሎችን አብያተ ክርስቲያናት«ጎዳሁ»።
\v 9 አብሬአችሁ በሆንኩና በተቸገርሁ ጊዜም በማንም ላይ ሸክም አልሆንሁም። ከመቄዶንያ የመጡት ወንድሞች የሚያስፈልገኝን ሰጥተዋልና። በሁሉም ረገድ ለእናንተ ሸክም ከመሆን ተጠንቅቄአለሁ፣ይህን ማድረጌንም እቀጥላለው ።
\s5
\v 10 የክርስቶስ እውነት በእኔ ውስጥ ያለ እንደ መሆኑ፣ ይህ የእኔ ትምህርት?
\v 11 ለምንስ እንዲህ ይሆናል? ለማልወደችሁ ነውን? እንደምወዳችሁ እግዚአብሔር ያውቃል። እንደነዚህ ያሉ ሰዎችን ራሳቸውን እንደ ክርስቶስ ሐዋርያት በማስመሰል ሐሰተኞች ሐዋርያት፣ አታላይ ሰራተኞች ናቸውና ።
\s5
\v 12 እኔን የሚነቅፉትንና እኛ የምናደርገውን እነርሱም እያደረጉ እንደ ሆነ እየተናገሩ የሚመኩበትን ምክንያት ለማሳጣት አሁን የሚደረገውን ወደ ፊትም አደርጋለሁ።
\v 13 እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች ሐሰተኛ ሐዋርያትና አታላይ ሸራተኞች ናቸው።
\s5
\v 14 ይህም የሚያስደንቅ አይደለም፣ ሰይጣን እንኳ ራሱን የብርሓን መልአክ በማስመሰሉ ርሱን ይለውጣልና።
\v 15 የእርሱ አግልጋዮች ደግሞ የጽድቅ አገልጋዮች በማስመሰል ራሳቸውን ቢለውጡ እጅግ የሚያስደንቅ አይደለም። ዕጣ ፈንታቸውም እንደ ሥራቸው ይሆናል።
\s5
\v 16 ደግሜ እላለሁ፦ እኔ ሞኝ እንደሆንሁ ማንም አያስብ ። ሞኝ እንደሆንሁ ብታስቡ ግን በጥቂቱ እመካ ዘንድ እንደ ሞኝ ተቀበሉኝ።
\v 17 እንደዚህ ታምኜ በመመካት የምናገረው፣ ጌታ የፈቀደው አይደለም፣ እኔ ግን እንደ ሞኝ እናገራለው።
\v 18 ብዙ ሰዎች በሥጋ ሰለሚመኩ፣ እኔም ደግሞ እመካለው።
\s5
\v 19 እናንተ ብልሆች ሆናችሁ ሞኞችን በደስታ ትታገሣላችሁና!
\v 20 ማንም ባሪያዎች ቢያደርጋችሁ፣ ማንም በመካከላችሁ መለያየትን ቢፈጥር፣ ማንም መጠቀሚያ ቢያደርጋችሁ፣ ማንም ቢቀማችሁ ፣ወይም ፊታችሁን በጥፊ ቢመታችሁ ትታገሱታላችሁና.
\v 21 ይህንን ስናደርግ በጣም ደካሞች እንደ ነበርን እያፈርሁ እናገራለ። ሆኖም ማንም በሚመካበት ጊዜ ሁሉ እንደ ሞኝ እላለው፣ እኔ ደግሞ እመካለሁ።
\s5
\v 22 እነርሱ ዕብራውያን ናቸውን? እኔ ደግሞ ነኝ እስራኤላውያን ናቸውን እኔ ደግሞ ነኝ። የአብርሃም ዘር ናቸውን? እኔ ደግሞ ነኝ።
\v 23 የክርስቶስ አግልጋዮች ናቸውን? እኔ ደግሞ ነኝ (እንደ እብድ እናገራለው) እኔ እበልጣለሁ፣ በከባድ ሥራ አብዝቼ በመታሰር አብዝቼ፣ በመደብደብ ከልክ በላይ፣ ብዙ የሞት አደጋዎችን በመጋፈጥ ብዙ ጊዜ ሆንሁ።
\s5
\v 24 አይሁድ «አንድ ሲጎድል አርባ ጅራፍ»አምስት ግዜ ገረፉኝ።
\v 25 ሦስት ጊዜ በበትር ተመታሁ። አንድ ግዜ በድንጋይ ተወገርሁ። ሦስት ጊዜ የተሳፈርኩበት መርከብ ተሰበረ። አንድ ሌሊትና አንድ ቀን በባህር ላይ አሳለፍሁሁሁ፣
\v 26 በተደጋጋሚ በመንገድ ተጓዝሁ። በወንዞች አደጋ፣ በወንበዴዎች አደጋ በወገኖቼ በኩል አደጋ፣ በአሕዛብ በኩል አደጋ፣ በከተማ አደጋ በምድረ በዳ አደጋ፣ በባሕር አደጋ፣ በሐሰተኞች በኩል አደጋ ነበረብኝ።
\s5
\v 27 በከባድ ስራና በችግር፣ እንቅልፍ ባጣሁባቸው ብዙ ሌሊቶች፣ በረሃብና በጥም ፣ እንዲሁም የሚበላ በማጣት፣በብርድባ በራቁትነት ነበርሁ።
\v 28 ከሌላውም ሁሉ በተለይ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ ለአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ያለኝ ጭንቀት ነው።
\v 29 ደካማ ምን ነው እኔስ አልደክምምን? ኃጢአት እንዲሠራ ሌላውን ያሰናከለ ማን ነው፣ እኔስ በውስጤ አልናደድምን?።
\s5
\v 30 መመካት ካለብኝ፣ ድካሜን ስለሚያሳየው ነገር እመካለው።
\v 31 እንደማልዋሽ፣ ለዘላለም የተመሰገነው የጌታ ኢየሱስ አምላክና አባት ያውቃል።
\s5
\v 32 በደማስቆ ከንጉስ አርስጦስዮስ በታች የሆነ ገዢ እኔን ይዞ ለማሰር ከተማዋን እየጠበቀ ነበር፣
\v 33 ነገር ግን በቅጥሩ ባለ መስኮት በቅርጫት አወረዱኝ፣ ከእጆቹም አመለጥሁ።
\s5
\c 12
\cl ምዕራፍ 12
\p
\v 1 መመካት አለብኝ፤ ነገር ግን በመመካት ጥቅም አይገኝም። ከጌታ ወዳሉት ራዕዮችና መገለጦች ግን እሄዳለው።
\v 2 በሥጋ ይሁን ወይም ከሥጋ ውጭ አላውቅም፤ እግዚአብሔር ግን ያውቃል። ከዐሥራ አራት ዓመታት በፊት በክርስቶስ የሆነ አንድ ሰው ወደ ሦስተኛ ሰማይ ተነጠቀ። እንደዚህ ያለውን ሰው ዐውቃለው።
\s5
\v 3 በሥጋ ይሁን ወይም ከሥጋ ውጭ እኔ አላውቅም፣ እግዚአብሔ ግን ያውቃል፣
\v 4 ይህ ሰው ወደ ገነት ተነጠቀ፤ ማንኛውም ሰው የማይናገራቸው እጅግ የተቀደሰ ነገሮችን ሰማ።
\v 5 እንደዚህ ስላለው ሰው እመካለው ስለራሴ ግን ከድካሜ በቀር አልመካም።
\s5
\v 6 ልመካ ከፈለግሁ፣ ሞኝ አይደለሁም፣ እውነትን እናገራለሁና፤ ነገር ግን ማንም በእኔ ከታየው ወይም ከእኔ ከተሰማው ፣
\v 7 ወይም በመገልጦቹ ልዩ ባሕርይ ምክንያት የምበልጥ አድርጎ እንዳያስብ አልመካም።ስለዚህ እንዳልታበይ፣ እጅግ እንዳልኩራራ የሥጋ መውጊያ፣የሚነዘንዘኝ የሰይጣን መልዕክተኛ ተሰጠኝ።
\s5
\v 8 መውጊያውን ከእኔ እንዲያነሣው ሦስት ጊዜ ጌታን ለመንሁ።
\v 9 እርሱም፣ «ጸጋዬ ይበቃሃል ኃይል በድካም ይፈጸማልና» አለኝ። ስለሆነም የክርስቶስ ኃይል ያርፍብኝ ዘንድ አብዝቼ ስለ ድካሜ እመካለው።
\v 10 ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም፣ በስድብ፣ በችግር፣ በስደት ፣ በጭንቀትም እርካታ ይሰማኛል በምደክምበት ጊዜ ሁሉ ብርቱ ነኝና።
\s5
\v 11 ሞኝ ሆኜአለሁ! እንዲህ እንድሆን ያስገደዳችሁኝ እናንተ ናችሁ፣እናንተ እኔን ልታመሰግኑኝ ይገባችሁ ነበር፥ምክንያቱም እኔ ምንም ባልሆን እንኳ ከ«ገናና ሐዋርያት» የማንስ አልነበርሁም።
\v 12 የአንድ ሐዋርያ እውነተኛ ምልክቶች በሁሉ ትዕግሥት፦ በምልክቶችና በድንቆች በብርቱ ተግባራትም በእናንተ መካከል ተደረጉ።
\v 13 እኔ ሸክም ካልሆንሁባችሁ በቀር ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት የምታንሱት እንዴት ነበር? ይህን ስሕትቴን ይቅር በሉኝ!
\s5
\v 14 አስተውሉ! ለሦስተኛ ጊዜ ወደ እናንተ ለመምጣት ተዘጋጅቻለው፤ ሸክም አልሆንባችሁም፤ እናንተን እንጂ፣ የእናንተ የሆነውን አልፈልግም። ወላጆች ለልጆች እንጂ ልጆች ለወላጆች ገንዘብ አያስቀምጡምና።
\v 15 እኔ እጅግ በጣምታልቅ በሆነ ደስታ ስለ ነፍሳችሁ እከፍላለው። እናንተን የበለጠ ብወዳችሁ፣ እኔ ከዚህ ያነሰ መወደድ አለብኝን?
\s5
\v 16 ልክ እንደዚህ፣ እኔ አልከበድሁባችሁም፤ነገር ግን በጣም በተንኮልና በጥበብ ያታለልኃችሁ መሰላችሁ።
\v 17 ወደ እናንተ በላክሁት በማንም ተጠቀምሁባችሁን?
\v 18 ወደ እናንተ እንዲመጣ ቲቶን የግድ አልኩት ፤ ከእርሱ ጋርም ሌላውን ወንድም ላክሁት። ቲቶስ ተጠቀመባችሁን? በአንድ መንገድ አልተጓዝንምን? በአንድ ፈለግስ አልተራመድንምን?
\s5
\v 19 በዚህ ጊዜ ሁሉ ለእናንተ ራሳችንን የምንከላከል ይመስላችኃልን? በእግዚአብሔር ፊት ስለእናንተ ድፍረት በክርስቶስ ብዙ ነገር እየተናገርን ነበር።
\s5
\v 20 ስመጣ እንደምፈልገው ሆናችሁ አላገኛችሁምብዬ እፈራለው። እናንተም እንደምትፈልጉት ሆኜ አታግኙኝም ብዬ እፈራለው ምናልባት ክርክር፣ ቅንዓት፣ የቁጣ መግንፈል፣ራስ ወዳድነት ያለበት ምⶉት፣ ሐሜት፣ ኩራትና ሁከት ይሆናሉ።
\v 21 ተመልሼ ስመጣ፣ አምላኬ በፊታችሁ ዝቅ እንዳያደርገኝ ብዬ እፈራለው ፣ከዚህ በፊትም ኃጢያ ስለሠሩት፣ እንዲሁም ስለ ፈጸሙት ርኩሰትና ዝሙት መዳራትም ስለ ብዙዎቻቸው አዝናለው ብዬ እፈራለው።
\s5
\c 13
\cl ምዕራፍ 13
\p
\v 1 ወደ እናንተ ስመጣ ይህ ሦስተኛዬ ነው። «ክስ ሁሉ በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች መጽናት አለበት።»
\v 2 ሁለተኛ ስመጣ በፊት ኃጢያት ለሰሩትና ለሌሎች ሁሉ ተናግሬአለው፥ አሁንም ደግሞ እላለው ተመልሼ ስመጣ እንዲሁ አላልፋቸውም።
\s5
\v 3 ክርስቶስ በእኔ በኩል እየተናገረ ስለ መሆኑ ማስረጃ ስለምትሹ ይህን እነግራችሏለው። ክርስቶስ ስለ እናንተ አይደክምም፥ ይልቁንም እርሱ በእናንተ ኃይለኛ ነው።
\v 4 እርሱ በድካም ተሰቅሏልና፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ኃይል ሕያው ነው። እኛ ደግሞ በእርሱ ደካሞች ነንና፤ ነገር ግን በመካከላችሁ ብለው የእግዚአብሔር ኀይል ሕያዋን ነን።
\s5
\v 5 በእምነት መሆናችሁን ለማየት ራሳችሁን መርምሩ። ራሳችሁን ፈትኑ። ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ እንደሚኖር አትገነዘቡምን? ተፈትናችሁ ካላለፋችሁ በቀር፣ እርሱ በእናንተ ይኖራል።
\v 6 እኛ ግን ተፈትነን ያለፍን መሆናችንን እንደምታውቁ እተማመናለው።
\s5
\v 7 እንግዲህ እናንተ ክፉ እንዳታደርጉ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፥ ይህንም የምናደርገው ፈተናውን ያለፍን መሰለን ለመታየት አይደለም፥ ነገር ግን ፈተናውን ያላለፍን ብንመስልም እንኳ፣ እናንተ ትክክል የሆነውን ታደርጉ ዘንድ እጸልያለው።
\v 8 ስለ እውነት እንጂ የእውነት ተቃራኒ የሆነ ነገር መሥራት አንችልምና።
\s5
\v 9 እኛ ደካሞች ሆነን እናንተ ብርቱዎች ስትሆኑ ደስ ይለናልና። እናንተ ፍጹማን እንድትሆኑ እንኛ ደግሞ እንጸልያለን።
\v 10 ከእናንተ ርቄ እያለው እነዚህን ነገሮች ጻፍሁላችሁ፤ ከእናንተ ጋር ሳለው እናንተ ለማነጽ እንጂ ለማፍረስ ያይደለ ጌታ የሰጠኝ ሥልጣንን በመጠቀም እንዳላመናጭቃችሁ ንችው።
\s5
\v 11 በመጨረሻ፣ ወንድሞችና እኅቶች፣ ደስ ይበላችሁ! ለተሐድሶ ሥሩ፤ተበረታቱ፤እርስ በርሳችሁ ተስማሙ፤በሰላም ኑሩ፤ የፍቅርና የሰላም አምልክም ከእናንተ ጋር ይሆናል።
\v 12 በተቀደሰ አሳሳም ሰላም ተባባሉ።
\s5
\v 13 ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
\v 14 የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ፍቅር፣የመንፈስ ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን።