am_ulb/47-1CO.usfm

849 lines
83 KiB
Plaintext

\id 1CO
\ide UTF-8
\h 1ኛ ቆሮንቶስ
\toc1 1ኛ ቆሮንቶስ
\toc2 1ኛ ቆሮንቶስ
\toc3 1co
\mt 1ኛ ቆሮንቶስ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 በእግዚአብሔር ፈቃድ ሐዋርያ ሊሆን በክርስቶስ ኢየሱስ የተጠራ ጳውሎስና ወንድማችን ሶስቴንስ በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱት።
\v 2 የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ከሚጠሩት ሁሉ ጋር ቅዱሳን ለመሆን ለተጠሩት ደግሞ እንጽፍላቸዋለን።
\v 3 ከአባታችን ከእግዚአብሔር ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
\s5
\v 4 ክርስቶስ ኢየሱስ ከሰጣችሁ ከእግዚአብሔር ጸጋ የተነሳ ሁልጊዜ ስለእናንተ አምላኬን አመሰግናለሁ።
\v 5 በነገር ሁሉ፤በንግግርና በዕውቀት ሁሉ ባለጸጋ እንድትሆኑ አድርጎአችኋልና።
\v 6 ስለክርስቶስ የተሰጠው ምስክርነት በመካከላችሁ እውነት ሆኖ እንደጸና ሁሉ ባለጸጎች አድርጎአችኋል።
\s5
\v 7 ስለዚህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ በጉጉት ስትጠባበቁ አንድም መንፈሳዊ ስጦታ አይጎድልባችሁም።
\v 8 እርሱ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ያለ ነቀፋ እንድትሆኑ እስከ ፍጻሜ ድረስ ያጸናችኋል።
\v 9 ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው።
\s5
\v 10 ስለዚህ ወንድሞችና እህቶች ሆይ፤ ሁላችሁም በአንድ አሳብ እንድትስማሙ እንጂ በመካከላችሁ መለያየት እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ድርስቶስ ስም አሳስባችኋለሁ። እንዲሁም በአንድ ልብና በአንድ ዓለማ የተባበራችሁ እንድትሆኑ አሳስባችኋለሁ።
\v 11 በመካከላችሁ መከፋፈል እንደተፈጠረ የቀሎዔ ቤተ ሰዎች አስታውቀውኛል።
\s5
\v 12 ይህን የምላችሁ፦ እያንዳንዳችሁ፦ "እኔ ከጳውሎስ ጋር ነኝ፥ ወይም ከአጵሎስ ጋር ነኝ፤ ወይም እኔ ከኬፋ ጋር ነኝ፤ ወይም እኔ ከክርቶስ ጋር ነኝ" ትላላችሁ።
\v 13 ለመሆኑ ክርስቶስ ተከፍሎአልን? ጳውሎስስ ስለ እናንተ ተሰቅሎአልን? ወይም የተጠመቃችሁት በጳውሎስስ ስም ነውን?
\s5
\v 14 ከቀርስጶስና ከጋይዮስ በቀር ማናችሁንም ስላላጠመቅሁ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
\v 15 ስለዚህ ማናችሁም በእኔ ስም እንደተጠመቃችሁ ለመናገር አትችሉም። (የእስጢፋኖስን ቤተ ሰብ ደግሞ አጥምቄአለሁ።
\v 16 ከዚህ ውጪ ሌላ ማንን አጥምቄ እንደሆነ አላውቅም።)
\s5
\v 17 ክርስቶስ ወንጌልን እንድሰብክ እንጂ እንዳጥምቅ አላከኝም። በሰው ጥበብ እንድሰብክ አልላከኝም፤ እንዲሁም የክርስቶስ መስቀል ኃይሉ ከንቱ መሆን ስለሌለበት በሰው የንግግር ጥበብ አልሰብክም ።
\s5
\v 18 ስለመስቀሉ ያለው መልእክት ለሚጠፉት ሞኝነት፤ ነገር ግን ለምንድን ለእኛ የእግዚአብሔር ኃይል ነው።
\v 19 "የጥበበኖችን ጥበብ አጠፋለሁ፤ የአስተዋዮችንም ማስተዋል ከንቱ አደርጋለሁ" ተብሎ ተጽፎአልና።
\s5
\v 20 ጥበበኛ ሰው የት አለ? ፈላስፋስ የት አለ? የዚህ ዓለም መርማሪስ የት አለ? እግዚአብሔር የዚህን ዓለም ጥበብ ሞኝነት እንዲሆን አላደረገምን?
\v 21 ዓለም በጥበብዋ እግዚአብሔርን ስላላወቀች በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖአል።
\s5
\v 22 አይሁድ ታዓምራትን ይፈልጋሉ፤ የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ።
\v 23 እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን። ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለግሪክ ሰዎችም ሞኝነት ነው።
\s5
\v 24 ነገር ግን እግዚአብሔር ለጠራቸው ለአይሁዶችም ሆነ ለግሪክ ሰዎች የእግዚአብሔር ኃይልና ጥበብ የሆነውን ክርስቶስን እንሰብካለን።
\v 25 ምክንያቱም የእግዚአብሔር ሞኝነት የሚመስለው ነገር ከሰዎች ጥበብ ይበልጣል፤ እንዲሁም የእግዚአብሔር ድካም የሚመስለው ነገር ከሰዎች ብርታት ይበልጣል።
\s5
\v 26 ወንድሞችና እህቶች ሆይ፤ በእናንተ ያለውን የእግዚአብሔርን ጥሪ ተመልከቱ። ብዙዎቻችሁ በሰው መስፈርት ጥበበኞች አልነበራችሁም። ብዙዎቻችሁ ኃያላን አልነበራችሁም፤ ብዙዎቻችሁም ከመሳፍንት አልነበራችሁም።
\v 27 ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ። ብርቱንም ነገር ለማሳፈር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ።
\s5
\v 28 ዓለም እንደ ከበረ ነገር የምትቆጥረውን ከንቱ ለማድረግ እግዚአብሔ የዓለምን ምናምንቴ ነገር መረጠ። የተናቀውንና ያልሆነውን ነገር መረጠ።
\v 29 ይህን ያደረገው ማንም ሰው በእግዚአብሔር ፊት ለመመካት ምክንያት እንዳይኖረው ነው።
\s5
\v 30 በክርስቶስ ኢየሱስ ለመሆን የበቃችሁት ከእግዚአብሔር ሥራ የተነሳ ነው፤ እርሱም ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበባችን፤ጽድቃችንና ቅድስናችን ቤዛችንም ሆኖአልና።
\v 31 እንግዲህ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ ፦"የሚመካ በጌታ ይመካ" ነው።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 ወንድሞችና እህቶች ሆይ፦ወደ እናንተ ስመጣ ስለ እግዚአብሔር የተሰወረውን የእውነት ምስጢር ሲሰብክላችሁ በሚያባብል የንግግር ችሎታ ወይም በላቅ ጥበብ አልመጣሁም።
\v 2 በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀርና፥ እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ እንዳላውቅ ወስኜ ነበርና።
\s5
\v 3 ወደ እናንተ የመጣሁት በድካምና በፍርሃት፤ እንዲሁም በብዙ መንቀጥቀጥ ነበር።
\v 4 መልእክቴና ስብከቴም የመንፈስን ኃይል በመግለጥ እንጂ በሚያባብል የጥበብ ቃል አልነበረም፤
\v 5 ይህም እምነታችሁ በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ ላይ እንዳይመሠረት ነው።
\s5
\v 6 በእምነታቸው በሰሉት ሰዎች መካከል በጥበብ እንናገራለን፤ ነገር ግን የምንናገረው የዚህን ዓለም ጥበብ ወይም ከጊዜ በኋላ የሚሻሩትን የዚህን ዓለም ገዢዎች ጥበብ አይደለም።
\v 7 ይልቁን እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን ያዘጃውን፥ ተሰውሮም የነበረውን የእግዚአብሔርን የጥበብ እውነት እንናገራለን።
\s5
\v 8 የዚህም ዓልም ገዢዎች አንዳቸውም ይህን ጥበብ አላወቁትም፤ በዚያን ጊዜ ይህን አውቀውስ ቢሆን ኖሮ የክብርን ጌታ ባልሰቀሉትም ነበር።
\v 9 ነገር ግን፦ "ዓይን ያላየውን፤ ጆሮም ያልሰማውን፤ በሰውም ልብ ያልታሰበውን፤ እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀውን ነገር" ተብሎ ተጽፎአልና።
\s5
\v 10 እግዚአብሔር በመንፈሱ አማካይነት የተሰወሩትን ነገሮች ገልጦናን ። ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራል። በሰው ውስጥ ካለው ከእርሱ መንፈስ በቀር የሰውን አሳብ የሚያውቅ ማን ነው?
\v 11 እንዲሁም ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር የሚያውቅ ማንም የለም።
\s5
\v 12 እኛ ግን ክእግዚአብሔር በነፃ የተሰጠንን እንድናውቅ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበለንም።
\v 13 የሰው ጥበብ ሊያስተምር የማይችለውን ነገር ግን የእግዚአብሔር መንፈስ የሚያስተምረውን ስለ እነዚህ ነገሮች በቃላት እንናገራለን። መንፈስ ቅዱስም መንፈሳዊውን ቃላት በመንፈሳዊ ጥበብ ይገልጥልናል።
\s5
\v 14 የእግዚአብሔር መንፈስ የሌለው ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ስለሚሆንበት አይቀበለውም ። በመንፈስም የሚመረመር ስለሆነ ሊያውቀው አይችልም።
\v 15 የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት ሰው ሁሉን ይመረምራል፤ እርሱ ግን በማንም አይመረመርም።
\v 16 "የጌታን አሳብ ማን አወቀው፤ ማንስ ሊያስተምረው ይችላል?" እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 ወንድሞችና እህቶች ሆይ፤ እንደ ሥጋውያን፤ በክርስቶስም እንደ ሕፃናት እንጂ መንፈሳውያን እንደ ሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም።
\v 2 ገና ጠንካራ ምግብ ለመብላት ስላልቻላችሁ ጠንካራ ምግብ ሳይሆን ወተት ጋትኋችሁ። እስከ አሁን ስንኳ ጠንካራ ምግብ ለመብላት ገና አልበቃችሁም።
\s5
\v 3 ምክንያቱም ገና ሥጋውያን ናችሁና። ቅናትና ክርክር ስለ ሚገኝባችሁ በሥጋ ፈቃድ እየኖራችሁ አይደላችሁምን? እንደ ሰውስ ልማድ እየተመላለሳችሁ አይደለምን?
\v 4 አንዱ፦ "እኔ ጳውሎስን እከተላለሁ" እንዲሁም ሌላውም፦ "እኔ የአጵሎስ ተከታይ ነኝ" ሲል እንደ ሰዎች ልማድ መመላለሳችሁ አይደለምን?
\v 5 ታዲያ አጵሎስ ማን ነው? ጳውሎስስ ማን ነው? በእነርሱ እጅ ያመናችሁ እንደ ተሰጣቸው አገልጋዮች ናቸው።
\s5
\v 6 እኔ ተክልሁ አጽሎስም አጠጣ፤ ግን ያሳደገው እግዚአብሔር ነው።
\v 7 እንግዲህ የሚተክል ወይም የሚያጠጣ ምንም አይደለም። ነገር ግን የሚያሳድግ እግዚአብሔር ነው።
\s5
\v 8 የሚተክልና የሚያጠጣ አንድ ናቸው። እንዲሁም እያንዳንዱ እንደ ራሱ ድካም መሠረት የራሱን ደመወዝ ይቀበላል።
\v 9 ምክንያቱም ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንሠራ ነን። የእግዚአብሔር እርሻ፤ የእግዚአብሔርም ሕንፃ ናችሁ። ።
\s5
\v 10 ከእግዚአብሔር በተሰጠኝ ጸጋ እንደ ዋና ሙያተኛ መሐንድስ መሠረትን ጠልሁ፤ ሌላውም ሰው በላዩ ያንጻል። እያንዳንዱ ሰው ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንደሚያንጽ ይጠንቀቅ።
\v 11 ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልም፤ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
\s5
\v 12 ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ቢሆን፤ በብር፤ በከበረ ድንጋይ፤ በእንጨት፤ በሣር ወይም በአገዳ ቢያንጽ፤
\v 13 የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤ የቀን ብርሃንም ይገልጠዋልና። የእያንዳንዱም ሥራ ጥራት እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል።
\s5
\v 14 አንድ ሰው ማንኛውንም ነገር ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ሽልማቱን ይቀበላል። ነገር ግን የማንም ሥራ የተቃጠለበት ከሆነ ይከስራል።
\v 15 ነገር ግን እርሱ ራሱ ከእሳት እንደሚያመልጥ ሆኖ ይድናል ።
\s5
\v 16 እናንተ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደሆናችሁ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደሚኖርባችሁ አታውቁምን?
\v 17 ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል። የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ እንደሆነ እናንተም እናንተም ቅዱሳን ናችሁ።
\s5
\v 18 ማንም ራሱን አያታልል። ከእናንተ መካከል ማንም በዚህ ዘመን ጥበበኛ እንደሆነው ቢያስብ፤ ጥበበኛ ይሆን ዘንድ እንደ ሞኝ ራሱን ይቁጠር።
\v 19 የዚህ ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ፊት ሞኝነት ነውና። ምክንያቱም "እርሱ ጥበበኞችን በተንኮላቸው ይይዛል" ተብሎ ተጽፎአል።
\v 20 ደግሞም፦ "ጌታ የጥበበኞችን አሳብ ከንቱ እንደ ሆን ያውቃል" ተብሎ ተጽፎአል።
\s5
\v 21 ስለዚህ ማንም በሰው አይመካ። ነገር ሁሉ የእናንተ ነውና፤
\v 22 ጳውሎስ ቢሆን፥ ወይም አጵሎስ ቢሆን፥ ወይም ኬፋ ቢሆን፥ ወይም ዓለምም ቢሆን፥ወይም ሕይወት ቢሆን፥ ወይም ሞት ቢሆን፥ ወይም ያለውም ቢሆን፥ ወይም የሚመጣውም ቢሆን
\v 23 ሁሉ የእናንተ ነው፤ እናንተም የክርስቶስ ናችሁ፤ ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው።
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 እንግዲህ ማንም ሰው እኛን የክርስቶስ አገልጋዮችና የእግዚአብሔር የተሰወረው ምሥጢር መጋቢዎች እንደሆነን ሊቆጥረን ይገባል።
\v 2 በዚህ መሠረት መጋቢዎች ታማኝ ሆነው መገኘት ይገባቸዋል።
\s5
\v 3 ነገር ግን በእናንተ ወይም በየትኛውም ፍርድ ቤት መፈረድ ካለብኝ ለእኔ በጣም ትንሽ ነገር ነው።
\v 4 እኔ በራሴ እንኳ አልፈርድም። እኔ ምንም ክስ የለብኝም ግን ፍጹም ነኝ ማለቴ አይደለም። በእኔ የሚፈርድ ጌታ ነው።
\s5
\v 5 ስለዚህ ጊዜ ሳይደርስ፥ ጌታ ከመምጣቱ በፊት ስለምንም ነገር አትፍረዱ።እርሱም በጨለማ የተሰወረውን ወደ ብርሃን ያወጣል፤ የልብንም አሳብ ይገልጣል። በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ሰው የሚገባውን ምስጋና ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል።
\s5
\v 6 እንግዲህ ወንድሞችና እህቶች ሆይ፦ "ከተጻፈው አትለፍ" የሚለውን ትርጉሙ ከእኛ መማር እንድትችሉ ስለ እናንተ ስል ለራሴና ለአጵሎስ እንደ ምሳሌ ተናገርሁ። ይህ ማናችሁም አንዳችሁ በሌላኛችሁ እንዳትታበዩ ነው።
\v 7 በእናንተና በሌሎች መካከል ምን ልዩነት አለ? በነጻ ያልተቀበልከውስ ምን አለህ? በነጻ የተቀበልከው ከሆንህ እንዳልተቀበልህ የምትመካ ስለ ምንድን ነው?
\s5
\v 8 አሁን የምትፈልጉት ሁሉ አላችሁ! አሁንስ ባለ ጠጎች ሆናችኋል! ከእኛ ተለይታችሁ መንገሥ ጀምራችኋል! በርግጥ እኛ ከእናንተ ጋር መንገሥ እንድንችል እናንተ ብትነግሡ በተመኘሁ ነበር።
\v 9 እግዚአብሔር እኛን ሐዋርያቱን ሞት እንደ ተፈረደባቸው ሰዎች ከሁሉ ይልቅ የኋለኞች ያደረገን ይመስለኛል። ለዓለም፥ ለመላእክትና ለሰዎች መታያ ሆነናልና።
\s5
\v 10 እኛ ስለ ክርስቶስ ሞኞች ነን፤ እናንተ ግን በክርስቶስ ጥበበኞች ናችሁ፤ እኛ ደካሞች ነን፤ እናንተ ግን ብርቱዎች ናችሁ እናንተ የከበራችሁ ናችሁ፤እኛ ግን የተዋረድን ነን።
\v 11 እስከዚህ ሰዓት ድረስ እንራባለን፤ እንጥማለን፤ እንራቆታለን፤ ያለርኅራኄ እንደበደባለን፤ ራሳችንን የምናስጠጋበት ስለሌለን እንክራተታለን።
\s5
\v 12 በገዛ እጃችን እየሠራን እንደክማለን፤ ሲሰድቡን እንመርቃለን፤ ሲያሳድዱን እንታገሣለን።
\v 13 ክፉ ሲናገሩን እንማልዳለን፤ እስከ አሁን ድረስ የዓለም ጥራጊ የሁሉም ጉድፍ ሆነናል።
\s5
\v 14 እነዚህን ነገሮች የጻፍኩላችሁ ላሳፍራችሁ ሳይሆን እንደ ተወደዱ ልጆቼ አድርጌ እንድትታርሙ ልገስጻችሁ ነው።
\v 15 በክርስቶስ ብዙ እልፍ አዕላፋት አሳዳጊዎች ቢኖሩአችሁ እንኳ ብዙ አባቶች የሉአችሁም። እኔ ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል ልጆቼ ናችሁ።
\v 16 እንግዲህ እኔን እንድትመስሉ እለምናችኋለሁ።
\s5
\v 17 እንግዲህ የተወደደና ታማኝ የሆነውን በጌታ ልጄን ጢሞቲዎስን የላክሁላችሁ ለዚህ ነው ። እኔም በየስፍራውና በየአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንደማስተምር፤ በክርስቶስ ያሉትን መንገዶቼ እርሱ ያሳስባችኋል።
\v 18 አንዳንዶቻችሁ ግን ወደ እናንተ የማልመጣ መስሎአችሁ በትዕቢት የምትመላለሱ አላችሁ።
\s5
\v 19 ነገር ግን ጌታ ቢፈቅድ ፈጥኜ ወደ እናንተ እመጣለሁ። እነዚህ በትዕቢት የሚመላለሱት የሚናገሩትን ብቻ ሳይሆን ኃይላቸውንም ለማወቅ እሞክራለሁ።
\v 20 ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይል ነው እንጂ በቃል ብቻ አይደለምና። ምን ትፈልጋላችሁ?
\v 21 በበትር ወይስ በፍቅርና በትህትና መንፈስ እንድመጣባችሁ ትፈልጋላችሁ?
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ሰምተናል፤የዚያም ዓይነት ዝሙት በአሕዛብ መካከል እንኳ ተሰምቶ የማይታወቅ ነው። እንደሰማነው ከእናንተ አንዱ ከእንጀራ እናቱ ጋር የሚተኛ አለ።
\v 2 ስለዚህ በትዕቢት የምትመላለሱ አይደላችሁምን? በዚህም ልታዝኑ አይገባችሁምን? ይህን ያደረገ ሰው ከመካከላችሁ ሊወገድ ይገባል።
\s5
\v 3 እኔ በአካል ከእናንተ ጋር ባልሆንም በመንፈስ ከእናንተ ጋር አለሁ፤ከእናንተም ጋር እንዳለሁ ሆኜ ይህን ባደረገው ሰው ላይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሁን ፈርጄበታለሁ።
\v 4 እናንተ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በምትሰበሰቡበት ጊዜ መንፈሴም ከጌታችን ኢየሱስ ኃይል ጋር እዚያው በመካከላችሁ አለ።
\v 5 ይህ ሰው በጌታ በኢየሱስ ቀን ይድን ዘንድ፤ ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው።
\s5
\v 6 መመካታችሁ መልካም አይደለም። ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ እንደሚያቦካ አታውቁምን?
\v 7 እንግዲህ እርሾ የሌለ እንጀራ ሆናችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ ከአሮጌው እርሾ ራሳችሁን አንጹ። ምክንያቱም የፋሲካችን በግ የሆነው ክርስቶስ ታርዶአል።
\v 8 ስለዚህ በአሮጌ እርሾ በመጥፎ አስተሳሰብና በክፋት ሳይሆን በቅንነትና በእውነት በዓልን እርሾ በሌለ ቂጣ እናድርግ።
\s5
\v 9 ዝሙትን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ኅብረት እንዳታደርጉ በመልእክቴ ጽፌላችሁ ነበር።
\v 10 በምንም ነገር የዚህን ዓለም ዝሙት ከሚያደርጉትን ወይም ገንዘብን ከሚመኙትን፥ ከነጣቂዎችንም፤ወይም ጣዖትን ከሚያመልኩትን ከማያምኑት አትተባበሩ። እንዲህ ቢሆን ኖሮ ከዓለም መውጣት በተገባችሁ ነበር።
\s5
\v 11 አሁን ግን በክርስቶስ ወንድሞች ወይም እህቶች ተብለው ከሚጠሩት ከማናቸውም ዝሙትን ከሚያደርግ ወይም ገንዘብን ከሚመኝ ወይም ጣኦትን ከሚያመልክ ወይም ተሳዳቢ ወይም ሰካራም ወይም ነጣቂ ቢሆኑ ከእነርርሱ ጋር እንዳትተባበሩ እጽፍላችኋለሁ። እንደነዚህ ካሉት ጋር አብራችሁ እንኳን አትብሉ።
\v 12 ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ባሉ ሰዎች ላይ ለመፍረድ እንዴት እደፍራለሁ? በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ እናንተ አትፈርዱምን?
\v 13 ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ባሉቱ ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል። "ክፉውን ከመካከላችሁ አውጡት።"
\s5
\c 6
\cl ምዕራፍ 6
\p
\v 1 ከእናንተ አንድ ሰው ከሌላ ሰው ጋር ክርክር ቢኖረው፤ በቅዱሳን ፊት ስለጉዳዩ ከመነጋገር ይልቅ በማያምን ዳኛ ፊት ለመቆም ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድ ይደፍራልን?
\v 2 ቅዱሳን በዓለም ላይ እንደሚፈርዱ አታውቁምን? በዓለም ላይ የምትፈርዱ ከሆነ፤ በትናንሽ ጉዳዮችን መፍረድ እንዴት ይሳናችኋል?
\v 3 በመላእክት ላይ እንኳ እንደምንፈርድ አታውቁምን? እንግዲህ በዚህ ዓለም ሕይወት ጉዳዮች ላይ የበለጠ ለመፍረድ እንዴት አንችልም?
\s5
\v 4 ለዕለታዊ ጠቃሚ ጉዳዮች ላይ መፍረድ ካለባችሁ በቤተ ክርስቲያን መካከል ለሚነሱ ክርክሮች የማያምኑ ሰዎችን እንዲፈርዱ ታስቀምጣላችሁን?
\v 5 አሳፍራችሁ ዘንድ ይህን እላለሁ። እንደዚህ ነውን? በወንድሞችና እህቶች መካከል ክርክሮችን ሊፈታ የሚችል አንድ አስተዋይ ሰው በእናንተ ዘንድ አይገኝምን?
\v 6 ነገር ግን አንዱ አማኝ ሌላውን አማኝ ለመክሰስ በማያምን ዳኛ ፊት ለመቆም ይሄዳልን?
\s5
\v 7 እንግዲህ በክርስቲያኖች መካከል የእርስ በርስ ማንኛውም ክርክር ቢኖርባችሁ ለእናንተ ሽንፈት ነው። ብትበደሉ አይሻልምን? ብትታለሉስ እይሻልምን?
\v 8 ነገር ግን እናንተ ወድሞቻችሁንና እህቶቻችሁን ትበድላላችሁ ታታልሉማላችሁ።
\s5
\v 9 ዓመጸኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? በሐሰት አታምኑ። ዝሙት አድራጊዎች ቢሆኑ፣ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ፥ ወይም አመዝሮች ወይም ግብረ ሶዶማውዎች ቢሆኑ፤ ወይም ሌቦች፥ ወይም ስግብግቦች፤ ወይም ሰካራሞች፣ ወይም ተዳዳቢዎች፥
\v 10 ወይም ነጣቂዎች፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።
\v 11 ከእናንተም አንዳንዶቻችሁ እንዲሁ ነበራችሁ። ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፤ ጸድቃችሁማል።
\s5
\v 12 ሁሉ ተፈቅዶልኛል፤ነገር ግን ሁሉም የሚጠቅም አይደለም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል ነገር ግን በእኔ ላይ ምንም ነገር አይሠለጥንብኝም።
\v 13 "መብል ለሆድ ነው፤ ሆድም ለመብል ነው።" እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንም ያጠፋቸዋል። ሥጋ ግን ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም። ይልቁን ሥጋችንም ለጌታ ነው፤እንዲሁም ጌታ ለሥጋ ያዘጋጃል።
\s5
\v 14 እግዚአብሔርም ደግሞ ጌታን አስነሣ እኛንም በኃይሉ ያስነሣናል።ሥጋችሁ የክርስቶስ ብልቶች እንደሆነ አታውቁምን?
\v 15 እንግዲህ የክርስቶስን ብልቶች ወስጄ የሴተኛ አዳሪ ሴት ብልቶች ላድርጋቸውን? ሊሆን አይችልም።
\s5
\v 16 ከሴተኛ አዳሪ ጋር የሚተባበር ከእርስዋ ጋር አንድ ሥጋ እንዲሆን አታውቁምን? "ሁለቱ አንድ ሥጋ ይሆናሉ" በእግዚአብሔር ቃል ተጽፎአል።
\v 17 ከጌታ ጋር የሚተባበር ግን ከእርሱ ጋር አንድ መንፈስ ነው።
\s5
\v 18 ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ሌላ ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚያደርግ ሰው ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ያድርጋል።
\s5
\v 19 ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁትና በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን?
\v 20 በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም። ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።
\s5
\c 7
\cl ምዕራፍ 7
\p
\v 1 እንግዲህ ስለጻፋችሁኝ ነገር ሰው ከሴት ጋር አለመገናኘት መልካም ነው።
\v 2 ነገር ግን ስለ ዝሙት ፈተና ምክንያት እንዳይሆን እያንዳንዱ ሰው የራሱ ሚስት ይኑረው፤ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ሴት የራስዋ ባል ይኑራት።
\s5
\v 3 ባል ለሚስቱ የሚገባትን ያድርግላት፤ እንደዚሁም ደግሞ ሚስቲቱ ለባልዋ የሚገባትን ታድርግ።
\v 4 ሚስት በገዛ ሰውነትዋ ላይ ሥልጣን ያላትም፤ ሥልጣን ለባልዋ ነው እንጂ፤ እንዲሁም ባል በገዛ ሰውነቱ ላይ ሥልጣን የላውም ሥልጣን ለሚስቱ ነው እንጂ።
\s5
\v 5 በጸሎት ለመትጋት ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልሆነ በቀር እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ። ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ ደግሞ አብራችሁ መሆን ትችላላችሁ።
\v 6 ዳሩ ግን ይህን እንደ ፈቃድ እላለሁ እንጂ እንደ ትእዛዝ አይደለም።
\v 7 ሰው ሁሉ እንደ እኔ ቢሆን እወዳለሁ። ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው ለራሱ ከእግዚአብሔር የተቀበለ አንዱ አንድ ዓይነት ሌላው ሌላ ዓይነት ስጦታ አለው።
\s5
\v 8 ላላገቡትና ባሎቻቸው ለሞተባቸው ሴቶች ግን እላለሁ፦ እንደ እኔ ሳያገቡ ቢኖሩ ለእነርሱ መልካም ነው።
\v 9 ነገር ግን ራሳቸውን መግዛት የማይችሉ ከሆነ መጋባት ይሻላል። በምኞት ከመቃጠል ይልቅ መጋባት ይሻላቸዋልና።
\s5
\v 10 ደግሞ የተጋቡትን እንዲ ብዬ አዛቸዋለሁ ይህንም እኔ ሳልሆን ጌታ ነው፦ "ሚስት ከባልዋ አትለይ፥
\v 11 ብትለይ ግን ሳታገባ ትኑር" ወይም "ከባልዋ ጋር ትታረቅ፥እንዲሁም" ባልም ሚስቱን አይፍታት።"
\s5
\v 12 ነገር ግን ሌሎችንም ጌታ ሳይሆን እኔ እላለሁ፦ ማንም ያላመነች ሚስት ያለው ወንድም፥ ከእርሱ ጋር ለመኖር ብትስማማ አይፍታት፤
\v 13 እንዲሁም ያላመነ ባል ያላት ሚስትም ብትኖር፥ ከእርስዋ ጋር ለመኖር ቢስማማ አትፍታው። ያላመነች ሚስት በአማኙ ባልዋ ተቀድሳለችል፤
\v 14 እንዲሁም ያላመነ ባል በአማኝ ሚስቱ ተቀድሶአል። አለዚያ ልጆቻቸውሁ ርኩሳን ይሆኑ ነበር፤ አሁን ግን የተቀደሱ ናቸው።
\s5
\v 15 የማያምን የትዳር ጓደኛ ግን የሚለይ ከሆነ ይለይ። እንዲህ በሚመስል ነገር ወንድም ወይም እህት በቃል ኪዳን መታሰር የለባቸውም። እግዚአብሔር ግን በሰላም እንድንኖር ጠርቶናል።
\v 16 አንቺ ሴት ባልሽን ታድኚ እንደ ሆንሽ ምን ታውቂአሽ? ወይስ አንተ ሰው ሚስትህን ታድናት እንደ ሆንህ ምን ታውቃለህ?
\s5
\v 17 እያንዳንዱ ሰው እንደተጠራው ዓለማና ጌታ በሰጠው ሕይወት ብቻ ይመላለስ። ይህ ለአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የእኔ ድንጋጌ ነው።
\v 18 ማንም ተገርዞ ወደ እምነት ተጠርቶአልን? ወደ አለመገረዝ መመለስ የለበትም። እንዲሁም ማንም ሳይገርዝ ወደ እምነት ተጠርቶአልን? መገረዝ የለበትም።
\v 19 የእግአብሔርን ትእዛዛት መጠበቅ ነው እንጂ መገረዝ ወይም አለመገረዝ የሚያመጠው ችግር የለም።
\s5
\v 20 እያንዳንዱ ሰው እግዚአብሔር ለእምነት በጠራበት ጊዜ እንደነበረ ይመላለስ።
\v 21 እግዚአብሔር ሲጠራህ ባሪያ ነበርን? ይህ ሊገድህ አይገባም። ነፃ የምትወጣ ከሆንህ ተቀበለው።
\v 22 አንድ ሰው በጌታ ባሪያ ሆኖ የተጠራ የጌታ ነፃ ሰው ነው፤ እንደዚሁም ነፃ ሆኖ ለእምነት የተጠራ የክርስቶስ ባሪያ ነው።
\v 23 በዋጋ ተገዝታችልኋልና የሰው ባሪያ አትሁኑ።
\v 24 ወድሞችና እህቶች ሆይ፤ እያንዳንዳችን በተጠራንበት እንደዚሁ ሆነን በእግዚአብሔር ዘንድ እንኑር።
\s5
\v 25 ላላገቡት የጌታ ትእዛዝ የለኝም። ነገር ግን በጌታ ምሕረት እንደ ታመነ ሰው ሆኜ የራሴን ምክር እሰጣለሁ።
\v 26 ስለዚህ ለችግር ጊዜ መፍትሔ እንዲሆን ሰው ሳያገባ መኖር ከቻለ መልካም ይመስለኛል።
\s5
\v 27 በጋብቻ ቃል ኪዳን በሚስት ታስረሃልን? እንዲህ ከሆነ ከዚህ ነፃ ለመሆን አትሻ። በበጋብቻ በሚስት አልታሰርህ ወይም ያላገባህ ነህ? ሚስትን አትሻ።
\v 28 ነገር ግን ካገባህ ኃጢአት አይሆንብህም። እንዲሁም ያላገባች ሴት ብታገባ ኃጢአት አይሆንባትም። ሆኖም ግን የሚያገቡ በኑሮአቸው ብዙ ችግር ይሆንባቸዋል፤ ከእንዲ ዓይነት ሕይወት እንድትርቁ እመኛለሁ።
\s5
\v 29 ዳሩ ግን ወንድሞ ሆይ፤ ይህን እላለሁ፤ ዘመኑ አጭር ነው። ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸ እንደሌላቸው ይኑሩ።
\v 30 የሚያላቅሱም እንደማያለቅሱ ይሁኑ፤ እንዲሁም የሚደሰቱ ደስታ እንደሌላቸው ይሁኑ፤
\v 31 ደግሞ ማንኛውንም ነገር የሚገዙ ምንም እንደሌላቸ ይሁኑ፤ በዚህች ዓለም የሚጠቀሙ በሙሉ እንደ ማይጠቀሙ ይሁኑ ምክንያቱም የዚች ዓለም አሠራር ሁሉ አላፊ ነውና።
\s5
\v 32 ነገር ግን ያለ ጭንቀት እንድትኖሩ እወዳለሁ። ያላገባው ጌታን እንዴት ደስ እንደሚያሰኘው የጌታን ነገር ያስባል።
\v 33 ያገባው ግን ሚስቱን እንዴት ደስ እንዲያሰኛት የዓለምን ነገር ያስባል፥ ልቡም ተከፍሎአልና።
\v 34 ያላገባች ሴት ወይም ድንግል በሥጋና በመንፈስ እንዴትምትቀደስ የጌታን ነገር ታስባለች። ያገባች ሴት ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንደምታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች።
\s5
\v 35 ሌላ ሸክም ሊጭንባችሁ ሳይሆን ለራሳችሁ ጥቅም ይህን እላለሁ። ያለ ምንም ጉዳት በጌታ እንድትጸኑ ስለእውነት ይህን እላለሁ።
\s5
\v 36 ዳሩ ግን ማንም ሰው ያጫትን ድንግል በአግባቡ ካልያዘ የእርስዋም ዕድሜ እየገፋ ከሄደ ሊያገባት ካሰበ ያግባት። ይህ ኃጢአት የለበትም።
\v 37 ነገር ግን አንድ ሰው ላለማግባት ቢወስንና ስሜቱንም ለመቆጣጠር ከቻለ እርስዋን ባለማግባቱ መልካም ያደርጋል።
\v 38 የእርሱንም እጮኛ የሚያገባት መልካም ያደርጋል፤እርስዋንም ለማግባት የማይመርጥ የበለጠ መልካም ያድርጋል።
\s5
\v 39 አንዲት ሴት ባልዋ በሕይወት እስካለ ድረስ ከባልዋ ጋር የታሰረች ናት። ነገር ግን ባልዋ ቢሞት በጌታ የሆነውን ብቻ ለማግባት ነጻነት አላት።
\v 40 እንደ እኔ ውሳኔ ግን ሳታገባ ብትኖር ደስተኛ ትሆናለች። እኔም የእግዚአብሔር መንፈስ ያለኝ ይመስለኛል።
\s5
\c 8
\cl ምዕራፍ 8
\p
\v 1 ለጣዖት ስለተሰዋ ሥጋ፦ "ሁላችንም ዕውቀት እንዳለን" እናውቃለን።ዕውቀት ያስታብያል፤ ፍቅር ግን ያንጻል።
\v 2 አንድ ሰው አንድ ነገር እንደሚያውቅ ቢያስብ፥ ያ ሰው ፥እንደሚገባ እንደሚያውቅ ገና አለወቀም።
\v 3 ነገር ግን ማንም ሰው እግዚአብሔርን ቢወድ እርሱም በእግዚአብሔር ዘንድ ይታወቃል።
\s5
\v 4 እንግዲህ ለጣዖት የተሠዋውን ሥጋ ስለ መብላት በተመለከተ፦ "የዚህ ዓለም ጣዖት ከንቱ ነው፤" እና "ከአንዱም ከእግዚአብሔር በቀር ሌላ አምላክ የለም" ይህንን እናውቃለን።
\v 5 ብዙ "አማልክትና ጌቶች" እንዳሉ ሁሉ፥ ምንም እንኳ በሰማይና በምድር አማልክት የተባሉ ቢኖሩ ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ
\v 6 እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ ብቻ አለን፤ እንዲሁም ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ አለን።
\s5
\v 7 ይሁን እንጂ ይህ ዕውቀት በሁሉም አይገኝም። በዚህ ፈንታ፥ አንዳንዶች ግን እስካሁን ድረስ ጣዖትን ማምለክ ስለ ለመዱ፦ ለጣዖት እንደ ተሠዋ አድርገው ይበላሉ። ሕሊናቸው ደካማ ስለ ሆነ ይረክሳሉ።
\s5
\v 8 መብል ግን ወደ እግዚአብሔር አያደርሰንም። ስላልበላምንም አንረክስም፤ ወይም ስለበላንም የተሻለን አንሆንም።
\v 9 ነገር ግን ይህ ነጻነታችሁ በእምነት ደካማ ለሆኑት ምክንያት ሆኖ መሰናከያ እንዳይሆን ተጠንቃቁ።
\v 10 አንተ ዕውቀት ያለህ በጣዖት ቤት በማዕድ ተቀምጠህ ስትበላ አንድ ሰው ቢያይህ፤ በእምነቱ ያልጠነከረ ሰው ለጣዖት የተሠዋውን ለመብላት አይደፋፈርምን?
\s5
\v 11 ስለ ጣዖት ባሕርይ በአንተ ዕውቀት የተነሣ ክርስቶስ የሞተላቸው ደካማ ወንድም ወይም እህት ይጠፋሉ።
\v 12 ስለዚህም ወንድሞችንና እህቶችን ስትበድሉና ደካማ ሕሊናቸውንም ስታቆሽሹ ክርስቶስን ትበድላላችሁ።
\v 13 ስለዚህም መብል ወንድሜንና እህቴን የሚያሰናክል ከሆን ወንድሜንና እህት እንዳላሰናክል ለዘላለ ከቶ ሥጋን አልበለም።
\s5
\c 9
\cl ምዕራፍ 9
\p
\v 1 እኔ ነፃ አይደለሁም? እኔ ሐዋርያስ አይደለሁም? ጌታችን ኢየሱስን አላየሁትም? እናንተስ በጌታ የሥዬ ፍሬዎች አይደላችሁም?
\v 2 ለሌሎች ሐዋርያ ባልሆን እንኳ ቢያንስ ለእናንተ ሐዋርያ ነኝ። በጌታ ሐዋርያ ለመሆኔ እናንተ ማረጋገጫ ናችሁና።
\s5
\v 3 ለሚጠይቁኝ መልሴ ይህ ነው።
\v 4 እኛስ ለመብላትና ለመጠጣት መብት የለንም?
\v 5 እንደ ሌሎቹ ሐዋርያት፣ እንደ ጌታ ወንድሞች፣ እና እንደ ኬፋ፣ አማኝ የሆነች ሚስት ይዞ ለመሄድ መብት የለንም?
\v 6 ወይስ የመሥራት ግዴታ ያለብን እኔና በርናባስ ብቻ ነን?
\s5
\v 7 በራሱ ወጪ በውትድርና የሚያገለግል ማን ነው? የወይን ተክል ተክሎ ከፍሬው የማይበላ ማን ነው? ወይስ ከሚጠብቀው መንጋ ወተት የማይጠጣ ማን ነው?
\v 8 እነዚህን ነገሮች የምናገረው በሰው ሥልጣን መሠረት ነው? ሕጉስ ይህን አይልም?
\s5
\v 9 በሙሴ ሕግ፦ "የሚያበራየውን በሬ፣አፉን አትሰር" ተብሎ ተጽፎአል። በእርግጥ እግዚአብሔር ስለ በሬዎች አስቦ ነው?
\v 10 እየተናገረ ያለው ስለ እኛ አይደለም? የተጸፈው ስለ እኛ ነው፣ምክንያቱም የሚያርስ በተስፋ ሊያርስ፣የሚያበራይም ከመከሩ ለመካፈል ተስፋ በማድረግ ሊያበራይ ይገባዋል።
\v 11 በመካከላችሁ መንፈሳዊ ነገር ዘርተን ከሆነ፣ከእናንተ ቁሳዊ ነገሮችን ብናጭድ ይበዛብናል?
\s5
\v 12 ሌሎች ይህን መብት ከእናንተ የሚያገኙ ከሆነ፣እኛስ የበለጠ መብት የለንም? ሆኖም ግን ይህን መብት ይገባናል አላልንም፣ይልቁንም ለክርስቶስ ወንጌል እንቅፋት እንዳንሆን ሁሉን ታገስን።
\v 13 በመቅደስ የሚያገለግሉ ምግባቸውን ከመቅደስ እንደሚያገኙ አታውቁም፣በመሠዊያው ላይ የሚያገልግሉስ መሠዊያው ላይ ከሚሠዋው እንደሚካፈሉ አታውቁም?
\v 14 እንዲሁም ደግሞ ወንጌልን የሚያውጁ ከወንጌል በሚገኝ እንዲኖሩ ጌታ አዟል።
\s5
\v 15 እኔ ግን ከእነዚህ መብቶች አንዱንም ይገባኛል አላልሁም። ይህንንም የጻፍሁት አንዳች እንዲደረግልኝ አይደለም። ይህን ትምክህቴን ማንም ከሚወስድብኝ ሞትን እመርጣለሁ።
\v 16 ይህ ግዴታዬ ስለሆነ ወንጌል ብሰብክ የምታበይበት ምክንያት የለኝም፣ ወንጌልን ባልሰብክ ግን ወዮልኝ!
\s5
\v 17 ይህን በፈቃደኝነት ባደርገው ግን ሽልማት አለኝ። በፈቃደኝነት ባላደርገው ግን በአደራ የተሰጠኝ ኃላፊነት አለብኝ።
\v 18 ታዲያ ሽልማቴ ምንድነው? በወንጌል ውስጥ ያለ ሙሉ መብቴን ትቼ ያለምንም ክፍያ ወንጌልን ስሰብክ ነው።
\s5
\v 19 ምንም እንኳ ከሁሉም ነፃ ብሆንም፣ ብዙዎችን ለመማረክ እንድችል፣የሁሉ አገልጋይ ሆንሁ።
\v 20 አይሁድን ለመማረክ እንድችል፣ እንደ አይሁዳዊ ሆንሁ። ምንም እንኳ በሕግ ስር ባልሆንም፣ በሕግ ስር ያሉትን መማረክ እንድችል፣ ከሕግ ስር እንዳለ ሰው ሆንሁ።
\s5
\v 21 ከሕግ ውጭ ያሉትን መማረክ እንድችል፣እኔ ራሴ ከእግዚአብሔር ሕግ ውጭ ሳልሆን፣ ነገር ግን ከክርስቶስ ሕግ ስር እያለሁ፣ ከሕግ ውጭ እንዳለ ሰው ሆንሁ።
\v 22 ደካማውን መማረክ እንድችል፣እንደ ደካማ ሆንሁ። አንዳንዶችን ማዳን እንድችል፣ ለሰዎች ሁሉ ብዬ ሁሉን ሆንሁ።
\v 23 ይህን ሁሉ ያደረግሁት ከወንጌል በረከት መካፈል እንድችል፣ ስለ ወንጌል ብዬ ነው።
\s5
\v 24 በሩጫ ውድድር የሚሳተፉ ሯጮች ሁሉ እንደሚሮጡ፣ ነገር ግን ሽልማት የሚቀበል አንዱ ብቻ እንደሆነ አታውቁም? ስለዚህ ሽልማት ለማግኘት ሩጡ።
\v 25 ለውድድር የሚዘጋጅ ሰው ሥልጠና ጊዜ ሁሉ ራሱን መቆጣጠር ይለማመዳል። እነርሱ የሚጠፋውን ሽልማት ለማግኘት ይሮጣሉ፣ እኛ ግን የማይጠፋውን ሽልማት ለማግኘት እንሮጣለን።
\v 26 ስለዚህም ያለ ዓላማ አልሮጥም፣ወይም ንፋስ በቦክስ አልመታም።
\v 27 ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ከውድድሩ ውጭ እንዳልሆን ሥጋዬን በመቆጣጠር አስገዛዋለሁ።
\s5
\c 10
\cl ምዕራፍ 10
\p
\v 1 ወንድሞች እና እህቶች፣ይህን እንድታውቁ እወዳለሁ፣አባቶቻችን ከዳመና በታች እና በባሕር ውስጥ አለፉ።
\v 2 ሁሉም በዳመና እና በባሕር ውስጥ በሙሴ ተጠመቁ፣
\v 3 መንፈሳዊ ምግብ ተመገቡ፣
\v 4 ሁሉም አንድ ዓይነት መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ። እነርሱም ይከተላቸው ከነበረው መንፈሳዊ ዓለት ጠጡ፣ያም ዓለት ክርስቶስ ነበር።
\s5
\v 5 ነገር ግን እግዚአብሔር በብዙዎች አልተደሰተምና ሬሳቸው ምድረ በዳ ውስጥ ወድቆ ቀረ።
\v 6 እኛም እነርሱ እንዳደረጉት ክፉ ነገር እንዳንመኝ እነዚህ ነገሮች ምሳሌ እንዲሆኑልን ተጽፈውልናል።
\s5
\v 7 "ሕዝቡ ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ፣በዝሙት ፍላጎት በመነሳሳት ሊጨፍሩ ተነሡ።" ተብሎ እንደተጻፈ፣ከእነርሱ አንዳንዶች እንዳደረጉት ጣዖት አምላኪዎች አትሁኑ።
\v 8 ከእነርሱ ብዙዎች ዝሙት በመፈጸማቸው ምክንያት ሃያ ሦስት ሺ ሰዎች በአንድ ቀን እንደሞቱ፣እኛም ዝሙት አንፈጽም።
\s5
\v 9 ከእነርሱም ብዙዎች ክርስቶስን እንደፈተኑት እና በእባብ እንደጠፉ፣እኛም ጌታን እንፈታተን።
\v 10 በማጉረምረማቸው ምክንያት የሞት መልአክ እንዳጠፋቸው፣እኛም አናጉረምርም።
\s5
\v 11 በእነርሱ ላይ የሆኑት እነኚህ ነገሮች ምሳሌ እንዲሆኑልን የተጻፈው፣ የዘመን ፍጻሜ ለደረሰብን ለእኛ ትምህርት እንዲሆንልን ነው።
\v 12 ስለዚህ ማንም ቆሜአለሁ ብሎ የሚያስብ፣ እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።
\v 13 በሰው ሁሉ ላይ ከሚደርሰው በላይ የሆነ ፈተና አልደረሰባችሁም። ነገር ግን እግዚአብሔር ታማኝ ነውና ከምትችሉት በላይ እንድትፈተኑ አያደርግም። ይልቁን ፈተናውን መወጣት እንድትችሉ ከፈተናው ጋር ማምለጫ መንገዱንም ያዘጋጅላችኋል።
\s5
\v 14 ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ፣ከጣዖት አምልኮ ሽሹ።
\v 15 ይህን የምናገራችሁ አስተዋዮች በመሆናችሁ ነው፤የምለውን አመዛዝኑ።
\v 16 የምንባርከው የበረከት ጽዋ፣የክርስቶስን ደም መካፈል አይደለም? የምንቆርሰው እንጀራ የክርስቶስን ሥጋ መካፈል አይደለም?
\v 17 እንጀራው አንድ እንደሆነ፣ብዙዎች ሆነን ሳለ አንዱን እንጀራ በመካፈል አንድ አካል ነን።
\s5
\v 18 የእስራኤልን ሕዝብ ተመልከቱ፦ ከመሥዋዕቱ የሚበሉ ከመሠዊያው ተካፋዮች አይደሉም?
\v 19 ስለዚህ ምን እያልሁ ነው? ጣዖት ምንም አይደለም እያልሁ ነው? ወይስ ለጣዖት የተሠዋ ምግብ ምንም አይደለም ማለቴ ነው?
\s5
\v 20 እያልሁ ያለሁት፣አሕዛብ የሚሠዋቸው ነገሮች፣ለአጋንንት እንጂ ለእግዚአብሔር አይደለም። ከአጋንንት ጋር ተካፋዮች እንድትሆኑ አልፈልግም! የጌታንም ጽዋ፣ የአጋንንትንም ጽዋ ልትጠጡ አትችሉም።
\v 21 በጌታም ማዕድ፣ በአጋንንትም ማዕድ ኅብረት ልታደርጉ አትችሉም።
\v 22 ይህን ብማድረግ ጌታን ለቅናት እናነሳሳዋለን? ከእርሱ የምንበረታ ነን?
\s5
\v 23 "ሁሉም ነገር ተፈቅዷል፣" ነገር ግን ሁሉም ነገር የሚጠቅም አይደልም። "ሁሉም ነገር ተፈቅዷል፣" ነገር ግን ሁሉም ነገር ሰዎችን የሚያንጽ አይደለም።
\v 24 ማንም ለራሱ መልካም የሆንውን ብቻ አያስብ። ይልቁን፣እያንዳንዱ ለሌሎች ሰዎች ሁሉ መልካም የሆነውን ይፈልግ።
\s5
\v 25 በገበያ ቦታ የሚሸጥ ማንኛውንም ነገር፣የኅሊና ጥያቄ ሳታነሱ መብላት ትችላላችሁ።
\v 26 "ምድርና በውስጧ ያለው ሁሉ የጌታ ነውና።"
\v 27 አንድ አማኝ ያልሆነ ሰው ምግብ ቢጋብዛችሁና ግብዣውን ተቀብላችሁ መሄድ ብትፈልጉ፣ በፊታችሁ የቀረበላችሁን ማንኛውንም ነገር የኅሊና ጥያቄ ሳታነሱ ብሉ።
\s5
\v 28 ነገር ግን እንድ ሰው፣"ይህ ምግብ ለጣዖት የተሠዋ ነው።" ብሎ ቢነግራችሁ አትብሉ። ይህን ማድረግ የሚገባችሁ፣ ለነገራችሁ ሰው እና ለኅሊና ስትሉ ነው።
\v 29 ይህን ስል ስለ እናንተ ኅሊና ሳይሆን ስለ ሌላው ሰው ኅሊና ነው። ስለ ሌላው ኅሊና ሲባል ለምን በነፃነቴ ላይ ይፈረዳል?
\v 30 ምግቡን በአክብሮት ከተቀበልሁ፣አመስግኜ ለበላሁት ነገር ለምን እሰደባልሁ?
\s5
\v 31 ስለዚህ፣ስትበሉ እና ስትጠጡ፣ወይም በምታደርጉት ሁሉ፣ሁሉን ለጌታ ክብር አድርጉት።
\v 32 ለአይሁዶች ወይም ለግሪኮች፣ እንዲሁም ለእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን መሰናከያ አታድርጉ።
\v 33 እኔ ሰዎችን ሁሉ በሁሉ ነገር ደስ ለማሰኘት እንደምፈልግ ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉ። የራሴን ጥቅም ሳይሆን፣ለብዙዎች ጥቅም የሚሆነውን እፈልጋለሁ። ይህን የማደርገው ወደ ድነት እንዲመጡ ብዬ ነው።
\s5
\c 11
\cl ምዕራፍ 11
\p
\v 1 እኔ ክርስቶስን እንደምመስል፣እናንተም እኔን ምሰሉ።
\v 2 አሁን የማመሰግናችሁ በሁሉ ነገር ስለምታስቡኝ ነው። ለእናንተ ያስተላለፍኳቸውን ልምዶች ልክ እንደዚያው እንዳሉ አጥብቃችሁ በመያዛችሁ አመሰግናችኋለሁ።
\v 3 ክርስቶስ የወንድ ሁሉ ራስ ፣ወንድ ደግሞ የሴት ራስ ፣ እግዚአብሔር የክርስቶስ ራስ እንደሆነ እንድትረዱ እፈልጋለሁ።
\v 4 ራሱን ሸፍኖ የሚጸልይ ወይም ትንቢት የሚናገር ወንድ የእርሱ ራስ የሆነውን ክብር ያሳጣል።
\s5
\v 5 ነገር ግን ራሷን ሳትሸፍን የምትጸልይ ወይም ትንቢት የምትናገር ሴት ራሷን ክብር ታሳጣለች። ይህን ማድረግ ልክ ጠጉሯን እንደመላጨት ነው።
\v 6 ሴት ራሷን ካልሸፈነች፣ጠጕሯን አሳጥራ መቆረጥ ይኖርባታል። ሴት ጠጕሯን አሳጥራ መቆረጧ ወይም መላጭቷ አሳፋሪ ከሆነ፣ ራሷን ትሸፍን።
\s5
\v 7 ወንድ ራሱን መሸፈን የለበትም፣ ምክንያቱም እርሱ የእግዚአብሔር መልክ እና ክብር ነውና።
\v 8 ሴት ግን የወንድ ክብር ነች። ወንድ ከሴት አልተገኘምና። ይልቁንስ፣ሴት ከወንድ ተገኝታለች።
\s5
\v 9 ወንድ ለሴት አልተፈጠረም፣ሴት ግን ለወንድ ተፈጥራለች።
\v 10 ለዚህ ነው፣ ከመላእክቱ የተነሳ፣ ሴት በራሷ ላይ የሥልጣን ምልክት ሊኖራት የሚገባው።
\s5
\v 11 የሆነ ሆኖ፣በጌታ ሴት ከወንድ፣ ወንድም ከሴት የተነጣጠሉ አይደሉም።
\v 12 ሴት የተገኘችው ከወንድ እንደሆነ ሁሉ፣ወንድም የተገኘው ከሴት ነው። ሁሉም ነገር ደግሞ የተነኘው ከእግዚአብሔር ነው።
\s5
\v 13 ራሳችሁ ፍረዱ፦ሴት ራሷን ሳትሸፈን ወደ እግዚአብሔር ብትጸልይ ተገቢ ነው?
\v 14 ወንድስ ረጅም ጠጕር ቢኖረው አሳፋሪ እንደሆነ ተፈጥሮ ራሱ አያስተምራችሁም?
\v 15 ሴት ግን ረጅም ጠጕር ቢኖራት ክብሯ እንደሆነ ተፈጥሮ ራሱ አያስተምራችሁም? ለእርሷ ጠጕር የተሰጣት እንደ መሸፈኛ ነውና።
\v 16 ነገር ግን በዚህ ማንም ክርክር ሊያስነሳ ቢፈልግ፣እኛም ሆንን የእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት ከዚህ የተለየ ልምምድ የላቸውም።
\s5
\v 17 በሚከተሉት መመሪያዎቼ ግን፣አላመሰግናችሁም። ምክንያቱም በምትሰበሰቡበት ጊዜ፣ ለተሻለ ነገር ሳይሆን እጅግ ለከፋ ነገር ትሰበሰባላችሁ።
\v 18 በመጀመሪያ፣ በቤተክርስቲያን ስትሰበሰቡ በመካከላችሁ መከፋፈል እንዳለ ሰምቼአለሁ፣ ደግሞም ይህ እንደሚሆን በመጠኑም ቢሆን አምኜበታልሁ።
\v 19 ምክንያቱም በእናንተ መካከል ተቀባይነትያላቸው እንዲለዩ የተለያዩ ቡድኖች መኖራቸው ግድ ነው።
\s5
\v 20 በአንድነት በምትሰብሰቡበት ጊዜ፣የምትበሉት የጌታን ማዕድ አይደለምና።
\v 21 በምትበሉበት ጊዜ፣ሌሎች ምግብ ከማግኘታቸው በፊት እያንዳንዱ ቀድሞ የየራሱን ምግብ ይበላል። አንዱ ተርቦ ሳለ ሌላው ይሰክራል።
\v 22 የምትበሉበትና የምትጠጡበት ቤት የላችሁም? የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን በመናቅ ምንም የሌላቸውን ታዋርዳላችሁ? ምን ልበላችሁ? ታዲያ ላመስግናችሁ? ለዚህ አላምሰግናችሁም!
\s5
\v 23 ከጌታ የተቀበልሁትን ለእናንተ አሳልፌ ሰጥቼአለሁ፣ ጌታ ኢየሱስ ታልፎ በተሰጠበት ምሽት፣እንጀራ አንሳ።
\v 24 ካመሰገነ በኋላ ቆረሰውና፣"ለእናንተ የሆነ ሥጋዬ ይህ ነው፣ይህን እኔን ለማስታወስ አድርጉት፣" አለ።
\s5
\v 25 እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋን አንስቶ፣"ይህ በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው።ይህን በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ እኔን ለማስታወስ አድርጉት።"
\v 26 ይህን እንጀራ በበላችሁ እና ይህን ጽዋ በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ፣ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ታውጃላችሁ።
\s5
\v 27 ስለዚህ ማንም፣ተገቢ ባልሆነ ሁኔታ የጌታን እንጀራ ቢበላ ወይም የጌታን ጽዋ ቢጠጣ፣ለጌታ ሥጋ እና ለጌታ ደም ተጠያቂ ይሆናል።
\v 28 አንድ ሰው ራሱን ከመረመረ በኋላ እንጀራውን ይብላ ጽዋዉንም ይጠጣ።
\v 29 የጌታ ሥጋ መሆኑን ሳይረዳ የሚበላ እና የሚጠጣ፣በራሱ ላይ ፍርድን ይበላል ይጠጣልም።
\v 30 በመካከላችሁ ብዙዎች የታመሙ እና በሽተኞች የሆኑት ስለዚህ ነው፣ አንዳንዶችም ደግሞ ሞተዋል።
\s5
\v 31 ነገር ግን ራሳችንን ብንመረምር አይፈረድብንም።
\v 32 በጌታ ስንፈረድ ግን፣ከዓለም ጋር እንዳንኮነን እንገሠጻለን።
\s5
\v 33 ስለዚህ፣ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ለመብላት ስትሰበሰቡ፣እርስ በርሳችሁ ተጠባበቁ።
\v 34 ማንም የተራበ ቢኖር፣እቤቱ ይብላ፣እንዲያ ሲሆን ስትሰበሰቡ ለፍርድ አይሆንባችሁም። ስለ ጻፋችሁልኝ ሌሎች ነገሮች፣ስመጣ መመሪያዎችን እሰጣለሁ።
\s5
\c 12
\cl ምዕራፍ 12
\p
\v 1 ወንድሞች እና እህቶች መንፈሳዊ ስጦታዎችን በተመለከተ፣የማታውቁት ነገር እንዲኖር አልፈልግም።
\v 2 አረማውያን በነበራችሁበት ወቅት፣መናገር እንኳ በማይችሉ ጣዖታት ወደማታውቁት መንገድ ተመርታችሁ እንደነበር ታውቃላችሁ።
\v 3 ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ፣"ኢየሱስ የተረገመ ነው፣" የሚል እንደሌለ ሁሉ፤ እንዲሁም በእግዚአብሔር መንፈስ ካልሆነ በቀር፣"ኢየሱስ ጌታ ነው፣" ሊል የሚችል እንደሌለ እወቁ።
\s5
\v 4 ልዩ ልዩ ስጦታዎች አሉ፣መንፈስ ቅዱስ ግን አንድ ነው።
\v 5 አገልግሎቶች ልዩ ልዩ ናቸው፣ጌታ ግን አንድ ነው።
\v 6 ልዩ ልዩ ሥራዎች አሉ፣ነገር ግን ለእያንዳንዱ ሰው ችሎታን የሚሰጥ አንዱ እግዚአብሔር ነው።
\s5
\v 7 ደግሞም ለእያንዳንዱ መንፍስ ቅዱስን መግለጥ የተሰጠው ለሁሉም ጥቅም ሲባል ነው።
\v 8 ለአንዱ የጥበብ ቃል በመንፈስ ቅዱስ ይሰጣል፣ለሌላው ደግሞ የእውቀት ቃል በዚያው መንፈስ ይሰጣል።
\s5
\v 9 ለሌላው በዚያው መንፈስ እምነት ይሰጠዋል፣ለሌላው ደግሞ በዚያው መንፈስ የፈውስ ስጦታ ይሰጠዋል።
\v 10 ለሌላው ደግሞ የኃይል ሥራዎች፣ለሌላው ትንቢት መናገር። ለሌላው ደግሞ መናፍስትን መለየት፣ለሌላው በልዩ ልዩ ልሳኖች መናገር፣እና ለሌላው ልሳኖችን የመተርጎም ስጦታ ይሰጠዋል።
\v 11 ነገር ግን፣ለእያንዳንዳቸው እንደወደደ ልዩ ልዩ ስጦታዎችን በመስጠት በእነዚህ ሁሉ የሚሠራው ያው አንዱ መንፈስ ቅዱስ ነው።
\s5
\v 12 አካል አንድ ሆኖ ሳለ ብዙ ብልቶች እንዳሉት ሁሉ፣ ሁሉም ብልቶች የእንዱ አካል ክፍል እንደሆኑ፣በክርስቶስም እንዲሁ ነው።
\v 13 በአንድ መንፈስ በአንድ አካል እንደተጠመቅን፣አይሁድ ይሁኑ ግሪኮች፣ባሪያ ይሁን ነጻ፣ሁሉ ከአንዱ መንፈስ ጠጥተዋል።
\s5
\v 14 አካል አንድ ብልት ብቻ ሳይሆን ብዙ ብልቶች አሉት።
\v 15 እግር፣"እኔ እጅ አይደለሁም፣ስለዚህ የአካሉ ክፍል አይደለሁም፣" ቢል የአካሉ ክፍል መሆኑ አይቀርም።
\v 16 ጆሮም ተነስቶ፣"ዓይን ስላይደለሁ፣የአካሉ ክፍል አይደለሁም፣" ቢል የአካሉ ክፍል ከመሆን አይቀነስም። አካል ሁሉ ዓይን ቢሆን፣ መስማት ወዴት ይሆናል?
\v 17 አካል ሁሉ ጆሮ ቢሆን፣ማሽተት ወዴት ይሆናል?
\s5
\v 18 እግዚአብሔር ግን እያንዳንዱን የአካል ክፍል እንደወደደ ሠርቶታል።
\v 19 ሁሉም አንድ ብልት ቢሆኑ ኑሮ፣አካል ወዴት በሆነ ነበር?
\v 20 አሁን ግን ብዙ ብልቶች ያሉት፣ አንድ አካል ነው።
\s5
\v 21 ዓይን እጅን፣"አንተ አታስፈልገኝም፣" ሊል አይችልም። ራስም እግርን፣"አታስፈልገኝም፣" ሊል አይችልም።
\v 22 ነገር ግን ዝቅተኛ ግምት የሚሰጣቸው ብልቶች አስፈላጊ ናቸው፣
\v 23 ዝቅተኛ ግምት የምንሰጣቸውን የሰውነት ክፍሎች ትልቅ ክብር እንሰጣቸዋለን፣እምናፍርባቸውን ብልቶች ደግሞ በአክብሮት እንይዛለን።
\v 24 የማናፍርባቸውን ብልቶች ደግሞ በአክብሮት መያዝ አያስፈልገንም ምክንያቱም ቀድሞዉኑ ክብር አግኝተዋል። እግዚአብሔር ግን ብልቶችን ሁሉ በአንድነት በማያያዝ ክብር ላልተሰጣቸው የበለጠ ክብርን ሰጥቷል።
\s5
\v 25 እግዚአብሔር እንዲህ ያደረገው በአካል ውስጥ መከፋፈል እንዳይኖርና ይልቁን ብልቶች በበለጠ ፍቅር እርስ በርሳቸው አንዳቸው ሌላቸውን እንዲከባከቡ ነው።
\v 26 እናም አንዱ ብልት ሲሰቃይ ሁሉም ብልቶች አብረው ይሰቃያሉ። አንዱ ብልት ሲከብር፣ሁሉም ብልቶች አብረው ሐሴት ያደርጋሉ።
\v 27 እንግዲህ እናንተ የክርስቶስ አካል ስትሆኑ እያንዳንዳችሁ የአካሉ ብልቶች ናችሁ።
\s5
\v 28 እግዚአብሔርም በቤተክርስቲያን በመጀመሪያ ሐዋርያትን፣ሁለተኛ ነቢያትን፣ሦስተኛ አስተማሪዎችን፣ከዚያም ተአምራት ማድረግን፣በመቀጠል የፈውስ ስጦታዎችን፣እርዳታ የሚያደርጉትን፣ የአስተዳደር ሥራ የሚሠሩትን፣ እና ልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችን የሚናገሩትን ሰጥቷል።
\v 29 ታዲያ ሁላችን ሐዋርያት ነን? ሁላችንስ ነቢያት ነን? ወይስ ሁላችን አስተማሪዎች ነን? ሁላችን ተአምራቶችን እናደርጋለን?
\s5
\v 30 ሁላችን የፈውስ ስጦታዎች አሉን? ሁላችን በልሳኖች እንናገራለን? ሁላችን ልሳኖችን እንተረጉማለን?
\v 31 የሚበልጡትን ስጦታዎች በከፍተኛ ጉጉት ፈልጉ። እጅግ የሚበልጠውንም መንገድ አሳያችኋልሁ።
\s5
\c 13
\cl ምዕራፍ 13
\p
\v 1 በሰዎች እና በመላእክት ልሳኖች ብናገር፣ግን ፍቅር ከሌለኝ፣የሚንጫጫ ቃጭል ወይም የሚጮህ ታንቡር ነኝ።
\v 2 የትንቢት ስጦታ ቢኖረኝ፣ የተሰወሩ እውነቶችን እና እውቀት ሁሉ ቢኖረኝ፣ተራሮችን ከስፍራቸው የሚያስወግድ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ፣ ፍቅር ከሌለኝ ግን ምንም የማይጠቅም ነኝ።
\v 3 ድሆችን ለመመገብ ያለኝን ሁሉ ብሰጥ፣ ሰውነቴንም እንዲቃጠል ብሰጥ፣ፍቅር ከሌለኝ ግን ምንም አይጠቅመኝም።
\s5
\v 4 ፍቅር ታጋሽና ደግ ነው። ፍቅር አይመቀኝም ደግሞም አይመካም። አይታበይም
\v 5 ወይም ትህትና የጎደለው አይደለም። ራስ ወዳድ አይደለም። በቀላሉ አይበሳጭም፤ወይም በደልን አይቆጥርም።
\v 6 ፍቅር በአመጽ ደስ አይሰኝም፣በእውነት ግን ደስ ይለዋል።
\v 7 ፍቅር ሁሉን ይታገሳል፤ሁሉን ያምናል፤በሁሉም ድፍረት አለው በሁሉ ይጸናል።
\s5
\v 8 ፍቅር ፍጻሜ የለውም። ትንቢቶች ያልፋሉ፤ልሳኖችም ቢሆኑ ያበቃሉ፤ዕውቀትም ቢሆን ጊዜ ያልፍበታል።
\v 9 ከዕውቀት የተወሰነውን እናውቃልን፣ትንቢትም በከፊል እንተነቢያለን።
\v 10 ነገር ግን ፍጹም የሆነው ሲመጣ፣ፍጹም ያልሆነው ወደ ፍጻሜ ይደርሳል።
\s5
\v 11 ልጅ በነበርሁበት ጊዜ፣እንደ ልጅ እናገር ነበር፣እንደ ልጅም አስብ ነበር፣የመረዳት ችሎታዬም እንደ ልጅ ነበር። ጎልማሳ ስሆን ግን የልጅነት ነገሮችን አስወገድሁ።
\v 12 አሁን በጨለማ ውስጥ ያለን ምስል በመስታዋት እንደሚያይ እንመለከታለን፣የዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን። አሁን ዕውቀትን በከፊል አውቃለሁ፣የዚያን ጊዜ ግን ልክ እኔ ሙሉ በሙሉ እንደምታወቀው ሙሉ በሙሉ አውቃለሁ።
\v 13 ነገር ግን እምነት፣ ተስፋ፣ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ግን ጸንተው ይኖራሉ። ከእነዚህ የሚበልጠው ፍቅር ነው።
\s5
\c 14
\cl ምዕራፍ 14
\p
\v 1 ፍቅርን ተከታተሉ ለመንፈሳዊ ስጦታዎችም ከፍተኛ ጉጉት ይኑራችሁ፣
\v 2 በተለይም ደግሞ ትንቢት የመናገር ስጦታን በብርቱ ፈልጉ። በልሳን የሚናገር ለሰው ሳይሆን ለእግዚአብሔር ይናገራል፣በመንፈስ የተሰወሩ ነገሮችን ይናገራልና ማንም አይረዳውም።
\v 3 ትንቢት የሚናገር ግን ሰዎችን ለማነጽ፣ለማበረታታትና፣ ለማጽናናት፣ ይናገራል።
\v 4 በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፣ትንቢት የሚናገር ግን ቤተክርስቲያንን ያንጻል።
\s5
\v 5 እንግዲህ ሁላችሁም በልሳኖች ብትናገሩ ምኞቴ ነበር። ከዚያ ይበልጥ ትንቢት ብትናገሩ እወዳለሁ። በልሳን የተነገረውን የሚተረጉም ከሌለ፣ ቤተክርስቲያን እንድትታነጽ ልሳን ከሚናገር ይልቅ ትንቢት የሚናገር ይበልጣል።
\v 6 ወንድሞች እና እህቶች፣ልሳን እየተናገርሁ ወደ እናንተ ብመጣ ምን እጠቅማችኋለሁ? በመገለጥ፣ወይም በእውቀት፣ወይም በትንቢት፣ወይም በማስተማር ካልሆነ ልጠቅማችሁ አልችልም።
\s5
\v 7 ሕይወት የሌላቸው እንደ ዋሽንት ወይም ክራር ያሉ የሙዚቃ መሣሪያዎች መለየት የሚቻሉ ድምፆችን ካላወጡ፣አንድ ሰው የትኛው የሙዚቃ መሣሪያ እንደተጫወተ እንዴት ማወቅ ይችላል?
\v 8 መለከት ሊለይ በማይቻል ድምፅ ቢነፋ፣አንድ ሰው ለጦርነት ለመዘጋጀት ጊዜው እንደሆነ እንዴት ሊያውቅ ይችላል?
\v 9 እናንተንም በተመለከተ እንዲሁ ነው። ሊታወቅ የማይችል ንግግር ብትናገሩ አንድ ሰው ምን እንደተናገራችሁ እንዴት ሊያውቅ ይችላል? እናንተ ትናገራላችሁ ነገር ግን ማንም አይረዳችሁም።
\s5
\v 10 በዓለም ውስጥ ብዙ ልዩ ልዩ ቋንቋዎች እንዳሉ ጥርጥር የለውም፣
\v 11 አንዳቸውም ግን ትርጉም የሌላቸው አይደሉም። የአንድን ቋንቋ ትርጉም የማላውቅ ከሆን ለሚናገረው ሰው እንግዳ እሆንበታለሁ፣ተናጋሪውም እንግዳ ይሆንብኛል።
\s5
\v 12 ለእናንተም እንዲሁ ነው። ለመንፈስ ቅዱስ መገለጦች ከፍተኛ ፍላጎት ስላላችሁ፣ቤተክርስቲያንን ለማነጽ ጉጉት ይኑራችሁ።
\v 13 ስለዚህ በልሳን የሚናገር መተርጎም እንዲችል ይጸልይ።
\v 14 በልሳን በምጸልይበት ጊዜ መንፈሴ ይጸልያል፣አእምሮዬ ግን ያለ ፍሬ ነው።
\s5
\v 15 ታዲያ ምን ላድርግ? በመንፈሴም እጸልያልሁ፣በአእምሮዬም እጸልያለሁ። በመንፈሴ እዘምራለሁ፣በአእምሮዬም እዘምራለሁ።
\v 16 እንደዚያ ካልሆነ ግን እግዚአብሔርን በመንፈሳችሁ ብታመሰግኑና ሌላው ሰው በምታመሰግኑበት ሰዓት ምን እያላችሁ እንደሆነ ካላወቀ እንዴት "አሜን" ይላል?
\s5
\v 17 በእርግጠኝነት በሚገባ እያመሰገናችሁ ነው፣ሌላው ሰው ግን እየታነጸበት አይደለም።
\v 18 ከሁላችሁም የበለጠ በልሳን ስለምናገር እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
\v 19 በቤተክርስቲያን ውስጥ ግን ሰዎችን ማስተማር እንድችል፥ በልሳን አሥር ሺ ቃላትን ከምናገር፣ በአእምሮዬ አምስት ቃላትን መናገር እመርጣለሁ።
\s5
\v 20 ወንድሞች እና እህቶች፣በአስተሳሰባችሁ ልጆች አትሁኑ። ይልቁን ክፋትን በተመለከተ እንደ ሕፃናት ሁኑ። ነገር ግን በአስተሳሰባችሁ ይበልጥ የበሰላችሁ ሁኑ።
\v 21 በሕጉ እንደተጻፈው፣"የማያውቁት ቋንቋ ባላቸው ሰዎችና እንግዳ በሆነ ንግግር ለዚህ ሕዝብ እናገራለሁ። እንደዚያም ሆኖ አይሰሙኝም፣" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 22 ስለዚህ ልሳኖች ለአማኞች ሳይሆን አማኝ ላልሆኑ ሰዎች ምልክት ናቸው። ትንቢት መናገር ግን ለማያምኑ ሰዎች ሳይሆን ለአማኞች ምልክት ነው።
\v 23 ስለዚህ፣ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለ ሰው ሁሉ ቢሰበሰብ እና በልሳኖች በመናገር ላይ እያሉ ከውጭ ያሉና የማያምኑ ሰዎች ቢገቡ አብደዋል አይሉምን?
\s5
\v 24 ነገር ግን ሁላችሁም ትንቢት እየተናገራችሁ ባለበት ሰዓት አማኝ ያልሆነ ወይም የውጭ ሰው ቢገባ በሚሰማው ነገር ሁሉ ኃጢአተኝነቱ ይሰማዋል። በሚነገረው ነገር ሁሉ ይፈረድበታል።
\v 25 የልቡም ምስጢር ሁሉ ይገልጣል። ከዚህም የተነሳ፣ በግንባሩ ተደፍቶ እግዚአብሔርን ያመልካል። እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው! ብሎ ያውጃል።
\s5
\v 26 ታዲያ ምን ይሁን፣ወንድሞች እና እህቶች? በአንድነት በምትሰበሰቡበት ጊዜ፣እያንዳንዳችሁ መዝሙር፣ትምህርት፣መገለጥ፣ልሳን፣ወይም ልሳን መተርጎም አላችሁ። የምታደርጉትን ሁሉ ቤተክርስቲያንን ለማንጽ አድርጉት።
\v 27 ማንም በልሳን ቢናገር ሁለትም ሦስትም ብትሆኑ ተራ በተራ አድርጉት። ሌላው ሰው ደግሞ በልሳን የተነገረውን ይተርጉም።
\v 28 የሚተረጉም ከሌለ ግን፣ሁሉም ሰው ድምፁን ሳያሰማ ለራሱ እና ለእግዚአብሔር ብቻ ይናገር።
\s5
\v 29 ሁለት ወይም ሦስት ነቢያቶች በሚናገሩበት ጊዜ ሌሎች የሚነገረውን በመመርመር ያዳምጡ።
\v 30 ነገር ግን በስብሰባው ውስጥ አንድ ሰው መረዳት ከመጣለት በመናገር ላይ ያለው ዝም ይበል።
\s5
\v 31 ትንቢት ስትናገሩ ሁሉም ሰው እንዲበረታታ እያንዳንዳችሁ ተራ በተራ መናገር ትችላላችሁ።
\v 32 የነቢያቶች መንፈስ ለነቢያት ይገዛል።
\v 33 እግዚአብሔር የሰላም አምላክ እንጂ ግራ የመጋባት አምላክ አይደለም። በሁሉም የአማኞች አብያተክርስቲያናት ውስጥ፦
\s5
\v 34 ሴቶች በቤተክርስቲያን ውስጥ ዝም ይበሉ። እንዲናገሩ አይፈቀድላቸውም። ሕጉ ይህን ይላልና ይልቁንስ ይገዙ ።
\v 35 ሊያውቁ የሚፈልጉት ነገር ቢኖር፣ባሎቻቸውን በቤት ውስጥ ይጠይቁ። ሴት በቤተክርስቲያን ውስጥ መናገሯ አሳፋሪ ነውና።
\v 36 የእግዚአብሔር ቃል የመጣው ከእናንተ ነውን? ወይስ ወደ እናንተ ብቻ ደርሷልን?
\s5
\v 37 ማንም ሰው ራሱን ነቢይ እንደሆነ ወይም መንፈሳዊ እንደሆነ ቢያስብ፣የጻፍሁላችሁ ነገሮች የጌታ ትዕዛዛት እንደሆኑ ሊያውቅ ይገባዋል።
\v 38 ነገር ግን ማንም ይህን ባያውቅ እርሱም ዕውቅና አያግኝ።
\s5
\v 39 እንግዲህ ወንድሞች እና እህቶች፣ትንቢትን መናገር በቅንነት ፈልጉ፣ ማንንም ልሳኖችን እንዳይናገር አትከልክሉ።
\v 40 ነገር ግን ማንኛውም ነገር በመልካም ምግባር እና በሥርዓት ይደረግ።
\s5
\c 15
\cl ምዕራፍ 15
\p
\v 1 ወንድሞች እና እህቶች፣ ስላወጅሁላችሁ እና እናንተም ጸንታችሁ ስለቆማችሁበት ወንጌል አሳስብባችኋለሁ።
\v 2 የሰበክሁላችሁን ቃል አጥብቃችሁ ብትይዙ፣በዚህ ወንጌል መዳን ይሆንላችኋል፣አለዚያ ግን ማመናችሁ ምንም ጥቅም የለውም።
\s5
\v 3 ለእናንተ ያስተላለፉሁት በቀዳሚነት አስፈላጊ የሆነውን እና እኔም የተቀበልሁትን ነው፤ መጽሐፍት እንደሚሉት ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፣
\v 4 ተቀበረ፣ በሦስተኛውም ቀን ተነሳ፣መጽሐፍትም ይህን ያረጋግጣሉ።
\s5
\v 5 ለኬፋ ታየ፣ከዚያም ለእሥራ ሁለቱ።
\v 6 እንደገና ከአምስት መቶ ለሚበልጡ ወንድሞች እና እህቶች በእንድ ጊዜ ታየ። አብዛኛዎቹ እስካሁን ድረስ በሕይወት አሉ፣የተወሰኑት ደግሞ አንቀላፍተዋል።
\v 7 ከዚያም ለያዕቆብ፣ደግሞም ለሐዋርያቱ ሁሉ ታየ።
\s5
\v 8 ከሁሉም በኋላ፣ያለ ጊዜው እንደተወለደ ልጅ ለሆንሁት ለእኔ ታየ።
\v 9 ከሐዋርያት ሁሉ የማንስ ነኝና። የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን አሳድጃለሁና ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም።
\s5
\v 10 ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ የሆንሁትን ሆኜአለሁ፣በእኔ ውስጥ የነበረው ጸጋም በከንቱ አልነበረም። ይልቁን ከሁሉም በላይ ጠንክሬ ሠራሁ። ሆኖም ይህ የሆነው ከእኔ ሳይሆን ከእኔ ጋር ካለው የእግዚአብሔር ጸጋ የተነሳ ነው።
\v 11 ስለዚህ እኔም ሆንሁ እነርሱ ስንሰብክላችሁ አመናችሁ።
\s5
\v 12 አሁን ክርስቶስ ከሞት እንደተነሳ ከተሰበከ፣ከእናንተ አንዳንዶች ታዲያ እንዴት የሙታን ትንሣኤ የለም ይላሉ?
\v 13 ሙታን ትንሣኤ ከሌለ እንግዲያው ክርስቶስም ከሙታን አልተነሳማ።
\v 14 ክርስቶስም ካልተነሳ ስብከታችንም፣የእናንተም እምነት ዋጋ የሌለው ሆኗላ።
\s5
\v 15 እንግዲህ እኛም ስለ እግዚአብሔር የሐሰት ምስክሮች ሆነን ተገኝተናል፣ ምክንያቱም እርሱ ክርስቶስን ሳያስነሳ እኛ አስነስቶታል በማለታችን በእግዚአብሔር ላይ በሐሰት መስክረንበታል።
\v 16 ሙታን ካልተነሱ፣ክርስቶስም አልተነሳም ማለት ነው።
\v 17 ክርስቶስ ካልተነሳ ደግሞ፣ እምነታችሁ ምንም ዋጋ የለውምናም አሁንም በኃጢአታችሁ አላችሁ።
\s5
\v 18 ስለዚህ በክርስቶስ ሆነው የሞቱ ደግሞ ጠፍተዋል ማለት ነው።
\v 19 ክርስቶስ ተስፋ ያደረግነው ለዚህ ሕይወት ብቻ ከሆነ፣ከሰዎች ሁሉ ይልቅ የምናሳዝን ነን።
\s5
\v 20 አሁን ግን ክርስቶስ ከሙታን ሁሉ በኩር ሆኖ ተነስቷል።
\v 21 ሞት በአንድ ሰው በኩል እንደመጣ፣ የሙታን ትንሣኤም በአንድ ሰው በኩል መጥቷል።
\s5
\v 22 በአዳም ሁሉም እንደሞቱ፣ሁሉም ደግሞ በክርስቶስ ሕያው ይሆናሉ።
\v 23 ግን እያንዳንዱ በቅደም ተከተሉ መሠረት፦ ክርስቶስ በኩር፣ ቀጥሎ የክርስቶስ የሆኑት እርሱ ተመልሶ ሲመጣ ሕያዋን ይሆናሉ።
\s5
\v 24 ከዚያም ክርስቶስ መንግሥቱን ለእግዚአብሔር አብ ሲያስረክብ ፍጻሜ ይሆናል። ይህም የሚሆነው ግዛትን ሁሉ፣ ሥልጣንን ሁሉ፣ እና ኃይልን ሁሉ ሲደመስስ ነው።
\v 25 ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሮቹ ስር እስኪያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋል።
\v 26 ሊደመሰስ የሚገባው የመጨረሻው ጠላት ሞት ነው።
\s5
\v 27 "ሁሉን ከእግሮቹ በታች አደረገ።" ነገር ግን፣"ሁሉን አደረገ፣" ሲል፣ሁሉን እንዲገዛለት ያደረገውን እንደማይጨምር ግልጽ ነው።
\v 28 ሁሉም ሲገዛለት፣ ልጁ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ለእርሱ ይገዛል። ይህ የሚሆነው እግዚአብሔር አብ ሁሉ በሁሉ እንዲሆን ነው።
\s5
\v 29 አለበዚያ ግን ፤ ስለ ሙታን የሚጠመቁ ሰዎች ለምን ያደርጉታል? ሙታን ፈጽሞ የማይነሱ ከሆነ፣ስለምን ያጠምቁላቸዋል?
\v 30 ስለምንስ በየሰዓቱ አደጋ ውስጥ እንወድቃለን?
\s5
\v 31 ወንድሞች እና እህቶች፣ ስለ እናንተ በክርስቶስ ባለኝ ትምክህት ይህን እናገራለሁ፦ በየቀኑ እሞታለሁ ።
\v 32 በሰው ዓይን ሲታይ፣ በኤፌሶን ከአውሬዎች ጋር መጋደሌ፣ ሙታን የማይነሱ ከሆነ ምን ይጠቅመኛል? "ነገ መሞታችን ስለማይቀር፣እንብላ፣ እንጠጣ።"
\s5
\v 33 አትታለሁ፦ "መልካም ያልሆነ ግንኙነት መልካሙን ጠባይ ያበላሻል።"
\v 34 ራሳችሁን ተቆጣጠሩ! የጽድቅ ሕይወት ኑሩ! ኃጢአት ማድረግን አትቅጠጥሉ። አንዳንዶቻችሁ ስለ እግዚአብሔር ዕውቀት የላችሁም። ይህን የምላችሁ ላሳፍራችሁ ነው።
\s5
\v 35 አንዳንዶች ግን እንዲህ ይላሉ፣"ሙታን የሚነሱት እንዴት ነው? በምን ዓይነት አካል ይመጣሉ?"
\v 36 ዕውቀት የጎደላችሁ ናችሁ! የዘራችሁት ዘር ካልሞተ አይበቅልም።
\s5
\v 37 የዘራችሁት አካል ተምልሶ አይበቅልም፣ይልቁን ዘር ነው እንጂ። ስንዴ ወይም የተዘራውን ሌላ ዓይነት ዘር ሆኖ ይበቅላል።
\v 38 እግዚአብሔር እንደወደደ አካልን ይሰጠዋል፣ለእያንዳንዱም ዘር የራሱን አካል ይሰጠዋል።
\v 39 ሥጋ ሁሉ አንድ ዓይነት አይደለም። ይልቁን፣ የሰው ሥጋ አለ፣ እንዲሁም የእንሰሳት ሥጋ አለ፣ የአእዋፍት ሥጋም እንዲሁ፣ ዓሣም ደግሞ ሌላ ዓይነት ሥጋ አለው።
\s5
\v 40 እንዲሁም ደግሞ ሰማያዊ አካልና ምድራዊ አካል አለ። ነገር ግን የሰማያዊ አካል ክብር አለ የምድራዊ አካል ክብር ደግሞ ሌላ ነው።
\v 41 የፀሐይ ክብር አለ፣ የጨረቃ ክብር ደግሞ ሌላ ነው፣ ከዋክብት ደግሞ ሌላ ክብር አላቸው። የአንዱ ኮከብ ክብር ከሌላው ኮከብ ይለያል።
\s5
\v 42 የሙታን ትንሣኤም ልክ እንደዚሁ ነው። የተዘራው የሚጠፋ ነው፣ የሚነሳው ደግሞ የማይጠፋ ነው።
\v 43 ሲዘራ በውርደት ሲነሳ ግን በክብር ነው። ሲዘራ በድካም፣ሲነሳ ግን በኃይል ነው።
\v 44 የተዘራው ፍጥረታዊ አካል፣የሚነሳው ግን መንፈሳዊ አካል ነው። ፍጥረታዊ አካል እንዳለ ሁሉ መንፈሳዊ አካልም አለ።
\s5
\v 45 እንዲህም ተብሎ ተጽፎአል፣ "የመጀመሪያው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ።" የመጨረሻው አዳም ግን ሕይወት ሰጭ መንፈስ ሆነ።
\v 46 መጀመሪያ የመጣው መንፈሳዊው ሳይሆን ፍጥረታዊው ነው፣ከዚያም መንፈሳዊው ተከተለ።
\s5
\v 47 የመጀመሪያው ሰው ከምድር ሲሆን የተሠራውም ከአፈር ነው። ሁለተኛው ሰው ከሰማይ ነው።
\v 48 አንዱ ከአፈር እንደተሠራ፣ከአፈር የተሠሩ ሁሉ እንዲሁ ናችው። እንዲሁም ከሰማይ እንደሆነው ሰው፣ ከሰማይ የሆኑትም እንዲሁ ናቸው።
\v 49 ልክ እኛ ከአፈር የተሠራውን ሰው እንደምንመስል፣ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩን ሰው መልክ እንይዛለን።
\s5
\v 50 ወንድሞች እና እህቶች፣ አሁን እንዲህ እላለሁ፣ሥጋ እና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርስ አይችልም። እንዲሁም የሚጠፋው የማይጠፋውን ሊወርስ አይችልም።
\v 51 ምስጢር የሆነ እውነት እነግራችኋለሁ፦ ሁላችን አንሞትም፣ግን ሁላችን እንለወጣለን።
\s5
\v 52 የመጨረሻው መለከት ሲነፋ፣ዐይን ተጨፍኖ እስኪገለጥ ባለ ፍጥነት ድንገት እንለወጣለን። መለከቱ ሲነፋ፣ ሙታን የማይጠፋውን አካል ለብሰው ይነሳሉ፣ እኛም እንለወጣለን።
\v 53 ይህ የሚጠፋው የማይጠፋውን ይለብሳል፣ ሟቹ ደግሞ የማይሞተውን ይለብሳል።
\s5
\v 54 የሚጠፋው የማይጠፋውን ሲለብስ፣እና ይህ ሟች የሆነው የማይሞተውን ሲለብስ፣ እንዲህ ተብሎ የተጻፈው ይፈጸማል፣"ሞት በድል ተዋጠ።"
\v 55 ሞት ሆይ ድል ማድረግህ የት አለ? ሞት ሆይ መንደፊያህ የት አለ?"
\s5
\v 56 የሞት መንደፊያ ኃጢአት ነው፣ የኃጢአት ኃይል ደግሞ ሕጉ ነው።
\v 57 ነገር ግን በጌታ በክርስቶስ ኢየሱስ ድል የሚሰጠን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!
\s5
\v 58 ስለዚህ ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ የጸናችሁ እና የማትነቃነቁ ሁኑ። ሁልጊዜም የእግዚአብሔር ሥራ ይብዛላችሁ፣ምክንያቱም በጌታ የምትደክሙት ድካም በከንቱ አይደለም።
\s5
\c 16
\cl ምዕራፍ 16
\p
\v 1 አሁን ደግሞ ለአማኞች የሚሰበሰበውን ገንዘብ በተመለከተ፣የገላትያ አብያተክርስቲያናትን እንዳዘዝሁት ሁሉ፣እናንተም እንደዚሁ አድርጉ።
\v 2 እኔ ስመጣ ገንዘብ ከመሰብሰብ፣ በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን፣እያንዳንዳችሁ እንደቻላችሁት መጠን የተወሰነ ገንዘብ አጠራቅሙ።
\s5
\v 3 ወደ እናንተ በደረስሁ ጊዜ በመረጣችሁት ሰው በኩል ከደብዳቤ ጋር መባችሁን ወደ እየሩሳሌም እልከዋለሁ።
\v 4 የእኔም መሄድ አስፈላጊ ከሆነ ከእኔ ጋር ይሄዳሉ።
\s5
\v 5 ነገር ግን ወደ መቄዶንያ መሄዴ ስለማይቀር፣ በመቄዶንያ በኩል ሳልፍ ወደ እናንተ እመጣለሁ። በምሄድበት ሁሉ ለጉዞዬ እንድትረዱኝ፣
\v 6 ምናልባትም ከእናንተ ጋር ልቆይና ክረምቱንም ከእናንተ ጋር ላሳልፍ እችላልሁ።
\s5
\v 7 አሁን ግን ጊዜው ስለሚያጥር ላያችሁ አላስብም። ጌታ ቢፈቅድና ብመጣ ግን ከእናንተ ጋር ረዘም ላለ ጊዜ ለመቆየት ተስፋ አደርጋልሁ።
\v 8 ግን በኤፌሶን እስከ በዓለ ኅምሳ ቀን ድረስ እቆያልሁ፣
\v 9 ሰፊ በር የተከፈተልኝ ቢሆንም ብዙ ተቃዋሚዎች አሉብኝ።
\s5
\v 10 ጢሞቴዎስ ልክ እንደ እኔ የጌታን ሥራ የሚሠራ ነውና ወደ እናንተ ሲመጣ፣ያለ አንዳች ስጋት ከእናንተ ጋር እንዲቀመጥ አድርጉ።
\v 11 ማንም አይናቀው። ወደ አኔ ሲመጣ በሰላም እንዲሄድም እርዱት። ምክንያቱም ከሌሎች ወንድሞች ጋር እንዲመጣ እጠብቃለሁ።
\v 12 አጵሎስን በተመለከተ፣ከወንድሞች ጋር በመሆን እንዲጎበኛችሁ አበረታትቼው ነበር። አሁን ለመምጣት አልወሰነም፣ይሁን እንጂ ዕድሉን ሲያገኝ ይመጣል።
\s5
\v 13 ተጠንቀቁ፣በእምነትም ጸንታችሁ ቁሙ፣ቆራጦች ሁኑ፣በርቱ።
\v 14 የምታደርጉት ሁሉ በፍቅር ይሁን።
\s5
\v 15 የእስጢፋኖስን ቤተሰቦች ታውቃላችሁ። እነርሱ በአካይያ የመጀመሪያ አማኞች እንደሆኑና አማኞችን ለማገልገል ራሳችውን እንደሰጡ ታውቃላችሁ። ወንድሞች እና እህቶች
\v 16 እንደዚህ ላሉ ሰዎች፣ በሥራ እየረዱንና አብረውን እየደከሙ ላሉ ሰዎች ሁሉ እንድትገዙ አሳስባችኋለሁ።
\s5
\v 17 በእስጢፋኖስ፣በፈርዶናጥስ፣ እና በአካይቆስ መምጣት ተደስቼአልሁ። የእናንተን በዚህ ያለመኖር ጉድለት ሞልተውልኛል።
\v 18 የእኔን እና የእናንተን መንፈስ አድሰዋል። እንዲህ ላሉ ሰዎችን እውቅና ስጧቸው።
\s5
\v 19 በእስያ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። አቂላና ጵርስቅላ፣ እንዲሁም በቤታቸው ያለችው ቤተክርስቲያን በጌታ ስም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
\v 20 ወንድሞች እና እህቶች ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተለዋወጡ።
\s5
\v 21 እኔ ጳውሎስ፣ ይህን በእጄ ጽፌአለሁ።
\v 22 ማንም ጌታን የማይወድ ቢኖር፣ የተረገመ ይሁን። ጌታ ሆይ ና!
\v 23 የጌታ የኢየሱስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።
\v 24 በክርስቶስ ኢየሱስ ፍቅሬ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።