am_ulb/45-ACT.usfm

1897 lines
206 KiB
Plaintext
Raw Permalink Blame History

This file contains ambiguous Unicode characters

This file contains Unicode characters that might be confused with other characters. If you think that this is intentional, you can safely ignore this warning. Use the Escape button to reveal them.

\id ACT
\ide UTF-8
\h የሐዋርያት ሥራ
\toc1 የሐዋርያት ሥራ
\toc2 የሐዋርያት ሥራ
\toc3 act
\mt የሐዋርያት ሥራ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 ቴዎፍሎስ ሆይ፣ ኢየሱስ እስካረገበት ቀን ድረስ ለማድረግና ለማስተማር የጀመረውን ሁሉ የሚናገረውን የመጀመሪያውን መጽሐፍ ጻፍሁ፤
\v 2 ይህም የሆነው ጌታ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት እርሱ የመረጣቸውን ሐዋርያትን ካዘዛቸው በኋላ ነበር፤
\v 3 ለምርጦቹ ከመከራው በኋላ ሕያው ሆኖ ተገልጦላቸዋል። አርባ ቀን እየታያቸው፣ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትም እየተናገረ ቆየ።
\s5
\v 4 ከእነርሱም ጋር ዐብሮ ሳለ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ አዘዛቸው፤ ነገር ግን "ከእኔ የሰማችሁትን አብ የሰጠውን ተስፋ ጠብቁ፤
\v 5 በእርግጥ ዮሐንስ በውሃ አጥምቆ ነበር፤ እናንተ ግን በጥቂት ቀናት ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ" አለ።
\s5
\v 6 ሐዋርያት በአንድነት ተሰብስበው ሳለ፣ “ጌታ ሆይ፣ ይህ የእስራኤልን መንግሥት የምትመልስበት ጊዜ ነውን?” ብለው ጠየቁት።
\v 7 እርሱም እንደዚህ አላቸው፤ “አብ በገዛ ሥልጣኑ የወሰነውን ጊዜ ወይም ወቅት ማወቅ እናንተን አይመለከትም።
\v 8 ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ ሲመጣ፣ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፣ በሰማርያና እስከ ምድር ዳርቻ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።”
\s5
\v 9 ጌታ ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ከተናገረ በኋላ፣ ሐዋርያቱ እያዩት ወደ ላይ ዐረገ፤ ደመናም ከዐይናቸው ሰወረው።
\v 10 ትኵር አድርገው ወደ ሰማይ እየተመለከቱ ሳለ፣ ድንገት ነጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ።
\v 11 እነርሱም፣ “እናንተ የገሊላ ሰዎች፣ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ለምን እዚህ ትቆማላችሁ? ወደ ሰማይ የወጣው ይህ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ ባያችሁበት ሁኔታ ተመልሶ ይመጣል” አሏቸው።
\s5
\v 12 ከዚያም በኋላ፣ የሰንበት ቀን ጕዞ ያህል ከሚያስሄደው፣ በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ካለው ከደብረ ዘይት ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው ሄዱ።
\v 13 ሐዋርያት እዚያ ሲደርሱ፣ ወደሚቈዩበት፣ ወደ ላይኛው ሰገነት ወጡ። እነርሱም ጴጥሮስ፣ ዮሐንስ፣ ያዕቆብ፣ እንድርያስ፣ ፊልጶስ፣ ቶማስ፣ በርተሎሜዎስ፣ ማቴዎስ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፣ ቀናተኛው ስምዖንና የያዕቆብ ልጅ ይሁዳ ነበሩ።
\v 14 ሁሉም በአንድነት ሆነው፣ ሴቶቹ፣ የኢየሱስ እናት ማርያምና ወንድሞቹም ጭምር በጸሎት ይተጉ ነበር።
\s5
\v 15 በዚያ ጊዜ ጴጥሮስ 120 ያህል በሚሆኑት ወንድሞች መካከል ቆመ፤ እንደዚህም አለ፤
\v 16 “ወንድሞች ሆይ፣ ኢየሱስን የያዙትንና መርቶ ያመጣውን ይሁዳን በሚመለከት መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት አፍ የተናገረው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ አስፈላጊ ነበር።
\s5
\v 17 ይሁዳ ከእኛ እንደ አንዱ ተቈጥሮና የዚህን አገልግሎት ድርሻም ተቀብሎ ነበርና።
\v 18 “ይሁዳም ለክፉ ሥራው በተከፈለው ዋጋ መሬት ገዛ። ከዚያም በግንባሩ ተደፋ፤ አካሉ ተሰነጠቀ፤ አንጀቱም ተዘረገፈ።
\v 19 በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሁሉ መሬቱ በቋንቋቸው አኬልዳማ [የደም መሬት] ተብሎ እንደሚጠራ ታወቀ።
\s5
\v 20 በመዝሙር መጽሐፍ፦ መኖሪያው ወና ይሁን፤ የሚኖርበት አንድ ሰውም እንኳ አይገኝ፤ ሹመቱንም ሌላ ሰው ይውሰደው፤ ተብሎ ተጽፎአልና።
\s5
\v 21 ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ በመካከላችን በገባበትና በወጣበት ጊዜ ሁሉ ዐብረውን ከቈዩ ሰዎች፣
\v 22 ይኸውም ዮሐንስ ካጠመቀው ጥምቀት ጀምሮ ኢየሱስ ከእኛ እስካረገበት ቀን ድረስ፣ ከነበሩት ከእነዚህ አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር ሊሆን ይገባል።”
\v 23 ኢዮስጦስም የሚባለውን፣ በርስያን ተብሎ የሚጠራውን ዮሴፍንና ማትያስን፣ ሁለት ሰዎችን እንዲቀርቡ አደረጉ።
\s5
\v 24 እንደዚህ ብለውም ጸለዩ፤ “ጌታ ሆይ፣ የሰዎችን ሁሉ ልብ አንተ ታውቃለህ፤ ስለዚህ ከእነዚህ ከሁለቱ የትኛውን እንደ መረጥኸው ግለጥ፤
\v 25 ይኸውም ይሁዳ ወደገዛ ስፍራው ትቶት በሄደው በዚህ አገልግሎትና ሐዋርያነት ውስጥ ስፍራ እንዲያገኝ ነው።”
\v 26 ሐዋርያት ዕጣዎችን ለእነርሱ ጣሉ፤ ዕጣውም ለማትያስ ወደቀ፤ እርሱም ከዐሥራ አንዱ ሐዋርያት ጋር አንድ ሆኖ ተቈጠረ።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 በበዓለ ኀምሳ ቀን ሁሉም በአንድነት አንድ ስፍራ ላይ ነበሩ።
\v 2 ድንገት እንደ ኀይለኛ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ከሰማይ መጣ፤ ተቀምጠውበት የነበረውን ቤትም ሞላው።
\v 3 እንደ እሳት የተከፋፈሉ ልሳናት ታዩአቸው፤ በእያንዳንዳቸው ላይም ተቀመጡባቸው።
\v 4 ሁሉም መንፈስ ቅዱስን ተሞሉ፤ መንፈስ ቅዱስ እንዲናገሩ እንደ ሰጣቸውም በሌሎች ቋንቋዎች መናገር ጀመሩ።
\s5
\v 5 በዚያን ጊዜ ከሰማይ በታች ካለው ሕዝብ ሁሉ የመጡ፣ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች፣ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ አይሁድ ነበሩ።
\v 6 ይህ ድምፅ ሲሰማ፣ ብዙ ሕዝብ በአንድነት ተሰበሰበ፣ እያንዳንዱ ሰውም በገዛ ራሱ ቋንቋ ሲናገሩ በመስማቱ ግራ ተጋባ።
\v 7 ሕዝቡ ተደነቁ፤ ተገረሙም፤ “እነዚህ የሚናገሩ ሰዎች ሁሉ በእውነት የገሊላ ሰዎች አይደሉምን? ብለውም ተናገሩ።
\s5
\v 8 እያንዳንዳቸው በተወለድንበት ቋንቋ ሲናገሩ የምንሰማቸው ለምንድን ነው?
\v 9 የጳርቴና፣ የሜድና የኢላሜጥ ሰዎች፣ በመስጴጦምያም፣ በይሁዳም፣ በቀጰዶቅያም፣ በጳንጦስም፣ በእስያም፣
\v 10 በፍርግያም፣ በጵንፍልያም፣ በግብፅም፣ በቀሬና በኩል በሚገኙት የሊቢያ ክፍሎች የምንኖርም፣ ከሮም የመጣን፣
\v 11 አይሁድና ወደ ይሁዲነት የገባን ቀርጤሳውያንና ዐረባውያን የሆንን እኛም፣ እነዚህ ሰዎች ስለ እግዚአብሔር ታላላቅ ሥራዎች በራሳችን ቋንቋዎች ሲናገሩ እንሰማቸዋለን።"
\s5
\v 12 ሁሉም ተደነቁ፣ ግራ ተጋቡም፤ እርስ በርሳቸውም፣ “ይህ ነገር ምን ይሆን?” ተባባሉ።
\v 13 ሌሎች ግን፣ “ዐዲስ ወይን ጠጅ ጠጥተው ጠግበው ነው” ብለውም በማፌዝ ተናገሩ።
\s5
\v 14 ነገር ግን ጴጥሮስ ከዐሥራ አንዱ ጋር ቆሞ፣ ድምፁን ከፍ በማድረግ እንደዚህ አላቸው፤ “የይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሁሉ፣ ይህ ለእናንተ የታወቀ ይሁን፤ የምናገረውንም አድምጡ።
\v 15 እነዚህ ሰዎች እናንተ እንደምታስቡት አልሰከሩም፤ ምክንያቱም ገና ከቀኑ ሦስተኛ ሰዓት ነው።
\s5
\v 16 ነገር ግን በነቢዩ በኢዩኤል ይህ ተነግሯል፦
\v 17 ‘በመጨረሻዎቹ ቀናት ይህ ይሆናል፣’ እግዚአብሔር እንደዚህ ይላል፤ ‘መንፈሴን ሥጋ በለበሱ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፣ ወንዶች ልጆቻችሁና ሴቶች ልጆቻችሁ ትንቢት ይናገራሉ። ወጣቶቻችሁ ራእይ ያያሉ፤ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልም ያልማሉ።
\s5
\v 18 በአገልጋዮቼና በሴት አገልጋዮቼ ላይም በእነዚያ ቀናት መንፈሴን አፈስሳለሁ፤ እነርሱም ትንቢት ይናገራሉ።
\v 19 በላይ በሰማይ ድንቆችን፣ ምልክቶችንም በታች በምድር ላይ፣ ደምን፣ እሳትንና የጢስ ደመናን አሳያለሁ።
\s5
\v 20 ታላቁና ገናናው የጌታ ቀን ከመምጣቱ በፊት፣ ፀሓይ ወደ ጨለማነት፣ ጨረቃም ወደ ደምነት ይለወጣሉ።
\v 21 የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል።'
\s5
\v 22 የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ እነዚህን ቃሎች ስሙ፦ ራሳችሁ እንደምታውቁት የናዝሬቱ ኢየሱስ፣ በመካከላችሁ እግዚአብሔር በእርሱ በኩል ባደረጋቸው ታላላቅ ተግባራት፣ በተኣምራትና በምልክቶች፣ ከእግዚአብሔር ለእናንተ መገለጡ የተረጋገጠ ሰው ነው።
\v 23 አስቀድሞ በተወሰነው የእግዚአብሔር ዕቅድና በቀዳሚ ዕውቀቱ መሠረት፣ ዐልፎ ተሰጥቶአል፤ እናንተም በዐመፀኞች እጅ ሰቀላችሁት፤ ገደላችሁትም፤
\v 24 እግዚአብሔርም የሞትን ጣር ከእርሱ አጥፍቶ አስነሣው፤ ምክንያቱም ሞት እርሱን ይይዘው ዘንድ አልቻለም።
\s5
\v 25 ዳዊት ስለ እርሱ እንዲህ ብሎ ይናገራልና፦ ‘ጌታን ሁልጊዜ በፊቴ አየሁት፤ በቀኜ ነውና አልናወጥም።
\v 26 ስለዚህ ልቤ ተደሰተ፤ አንደበቴም ሐሤት አደረገ። ሥጋዬም በተስፋ ያድራል።
\s5
\v 27 ነፍሴን በሲኦል አትተዋትም፤ ቅዱስህም መበስበስን እንዲያይ አትፈቅድም።
\v 28 የሕይወትን መንገድ ገለጥህልኝ፤ በፊትህም ደስታን ታጠግበኛለህ።’
\s5
\v 29 ወንድሞች ሆይ፣ ስለ አባቶች አለቃ ስለ ዳዊት በግልጽ ልነግራችሁ እችላለሁ፤ እርሱ ሞቶአል፤ ተቀብሮአልም፤ መቃብሩም እስከ ዛሬ ድረስ በእኛ ዘንድ ነው።
\v 30 ስለዚህ ዳዊት ነቢይ ነበረና ከዘሩ በዙፋኑ ላይ አንድን ሰው እንደሚያስቀምጥ እግዚአብሔር በመሐላ ለእርሱ ቃል ገብቶለት ነበር።
\v 31 ዳዊት ይህን አስቀድሞ አየ፤ ስለ ክርስቶስ ትንሣኤም ተናገረ፦ ክርስቶስ በሲኦል አልቀረም፤ ሥጋውም መበስበስን አላየም።
\s5
\v 32 ይህን ኢየሱስን እግዚአብሔር አስነሣው፤ ለዚህም እኛ ሁላችን ምስክሮች ነን።
\v 33 ስለዚህ ከሙታን በመነሣትና በእግዚአብሔር ቀኝ በመቀመጥ፣ ከአብ ቃል የተገባውን መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ፣ እናንተ የምታዩትንና የምትሰሙትን ይህን አፈሰሰው።
\s5
\v 34-35 ዳዊት ወደ ሰማይ አልወጣም፤ ነገር ግን እንዲህ ይላል፦ “ጌታ ለጌታዬ፣ ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስከማደርጋቸው ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው።”
\v 36 ስለዚህ፣ እናንተ የሰቀላችሁትን ይህን ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ።"
\s5
\v 37 ሕዝቡ ይህን ሲሰሙ ልባቸው ተነካና ለጴጥሮስና ለቀሩት ሐዋርያት፣ “ወንድሞች ሆይ፣ ምን እናድርግ?” አሉ።
\v 38 ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፤ “ንስሓ ግቡ፤ እያንዳንዳችሁም ለኀጢአታችሁ ይቅርታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ መንፈስ ቅዱስንም በስጦታነት ትቀበላላችሁ።
\v 39 የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ፣ ጌታ አምላካችን ለሚጠራቸው ሩቅ ላሉት ሁሉም ነውና።”
\s5
\v 40 ጴጥሮስ በሌሎች ብዙ ቃላት መሰከረ፤ “ከዚህ ክፉ ትውልድ ራሳችሁን አድኑ” በማለትም አስጠነቀቃቸው።
\v 41 ከዚያም ሕዝቡ ቃሉን ተቀብለው ተጠመቁ፤ በዚያም ቀን ሦስት ሺሕ ያህል ሰዎች ተጨመሩ።
\v 42 እነርሱም ሐዋርያት በሚያስተምሩት ትምህርትና በኅብረት፣ እንጀራውን በመቊረስና በጸሎትም ይተጉ ነበር።
\s5
\v 43 በሰው ሁሉ ላይ ፍርሀት መጣ፤ ብዙ ድንቆችና ምልክቶችም በሐዋርያት እጅ ተደረጉ።
\v 44 ያመኑት ሁሉ በአንድነት ነበሩ፤ ሁሉም ነገር የጋራ ነበር፤
\v 45 መሬታቸውንና ንብረታቸውን እየሸጡም ለሁሉም እንደሚያስፈልገው አካፈሉ።
\s5
\v 46 በየቀኑም በአንድ ዐላማ በመቅደስ እየተጉ፣ በቤት ውስጥ እንጀራ እየቈረሱም ምግብን ልባዊ በሆነ ደስታና ትሕትና ዐብረው ይመገቡ ነበር፤
\v 47 እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ በሕዝቡም ሁሉ ዘንድ ከበሬታ ነበራቸው። ጌታም የሚድኑትን በየቀኑ በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 ጴጥሮስና ዮሐንስ በጸሎት ጊዜ፣ በዘጠኝ ሰዓት ወደ ቤተ መቅደስ ይወጡ ነበር።
\v 2 ወደ ቤተ መቅደሱ ከሚገቡ ሰዎች ምጽዋት መለመን እንዲችል፣ ውብ ተብሎ በሚጠራው በቤተ መቅደሱ በር ላይ ሰዎች በየቀኑ በሸክም አምጥተው የሚያስቀምጡት፣ ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ ዐንካሳ የሆነ አንድ ሰው ነበረ።
\v 3 ጴጥሮስንና ዮሐንስን ወደ ቤተ መቅደሱ ሊገቡ ሲሉ ባያቸው ጊዜ፣ ምጽዋት ለመነ።
\s5
\v 4 ጴጥሮስ ዐይኖቹን ምጽዋት በሚለምነው ሰውዬ ላይ በማድረግ፣ ከዮሐንስ ጋር “ወደ እኛ ተመልከት” አለው።
\v 5 ዐንካሳውም፣ ከእነርሱ አንድ ነገር ለመቀበል በመጠበቅ ወደ እነርሱ ተመለከተ።
\v 6 ጴጥሮስ ግን፣ “ብርና ወርቅ የለኝም፤ ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ። በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተራመድ” አለው።
\s5
\v 7 ጴጥሮስ ቀኝ እጁን ያዘውና ወደ ላይ አነሣው፤ ወዲያውም እግሮቹና የቍርጭምጭሚቱ ዐጥንቶች ጥንካሬ አገኙ።
\v 8 ዐንካሳው ሰውዬ ወደ ላይ ዘልሎ ቆመ፤ መራመድም ጀመረ፤ ከጴጥሮስና ከዮሐንስ ጋርም እየተራመደ፣ እየዘለለና እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ።
\s5
\v 9 ሰዎች ሁሉ ዐንካሳው እየተራመደ ሲሄድና እግዚአብሔርን ሲያመሰግን አዩት።
\v 10 ምጽዋት ለመቀበል ውብ በሚባለው የቤተ መቅደሱ በር ላይ ይቀመጥ የነበረው ሰውዬ እንደ ሆነም ዐወቁ፤ በእርሱ ላይ ከሆነው የተነሣም በመደነቅና በመገረም ተሞሉ።
\s5
\v 11 ሰውየው የጴጥሮስንና የዮሐንስን እጅ ይዞ ሳለ፣ የሰሎሞን መመላለሻ በሚባለው ደጅ ሰዎች ሁሉ በኀይል እየተደነቁ በአንድነት ወደ እነርሱ ሮጡ።
\v 12 ጴጥሮስ ይህን ሲያይ ለሕዝቡ፣ “እናንተ የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ ለምን ትደነቃላችሁ? ይህን ሰው በገዛ ኀይላችን ወይም በመንፈሳዊነታችን እኛ እንዲራመድ እንዳደረግን ሁሉ፣ ለምን ዐይናችሁን አፍጥጣችሁ ትመለከታላችሁ? በማለት መልስ ሰጠ።
\s5
\v 13 የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ፣ የአባቶቻችን አምላክ አገልጋዩን ኢየሱስን አክብሮታል። እርሱ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትና ጲላጦስ ሊፈታው ወስኖ ሳለ፣ በፊቱ የካዳችሁት ነው።
\v 14 ቅዱሱንና ጻድቁን ካዳችሁት፤ በእርሱም ፈንታ ነፍሰ ገዳይ እንዲፈታላችሁ ለመናችሁ።
\s5
\v 15 እግዚአብሔር ከሙታን ያስነሣውን፣ የሕይወትን ጌታ ገደላችሁት፤ እኛም የዚህ ምስክሮች ነን።
\v 16 በእርሱ ስም ማመን አሁን የምታዩትንና የምታውቁትን ይህን ሰው ብርቱ አድርጎታል። አዎ፣ በኢየሱስ ያለው እምነቱ በሁላችሁ ፊት ይህን ፍጹም ጤንነት ሰጠው።
\s5
\v 17 አሁን ወንድሞች ሆይ፣ አለቆቻችሁም እንዳደረጉት ባለማወቅ ያደረጋችሁት እንደ ሆነ ዐውቃለሁ።
\v 18 ነገር ግን እግዚአብሔር በነቢያቱ ሁሉ አፍ የእርሱ ክርስቶስ መከራ መቀበል እንዳለበት አስቀድሞ የተናገረውን አሁን ፈጸመው።
\s5
\v 19 እንግዲህ ኀጢአታችሁ እንዲደመሰስ፣ ከጌታ ዘንድም የመታደስ ዘመን እንዲመጣ ንስሓ ግቡ፤ ተመለሱም፤
\v 20 ይኸውም ለእናንተ የመረጠውን ክርስቶስ የሆነውን ኢየሱስን እንዲልከው ነው።
\s5
\v 21 እርሱ ሰማያት ሊቀበሉትና ነገሮች ሁሉ እስከሚታደሱበት ዘመን ድረስ ጠብቀው ሊያቈዩት የሚገባ፣ ከጥንት ጀምሮ በነበሩ ቅዱሳን ነቢያቱ አፍ የተነገረለት ነው።
\v 22 ሙሴ በእርግጥ፣ ‘ጌታ እግዚአብሔር ከወንድሞቻችሁ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣል። የሚነግራችሁንም ሁሉ ስሙ’ አለ።
\v 23 ያን ነቢይ የማይሰማ ሰው ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋል።
\s5
\v 24 አዎ፣ ከሳሙኤል ጀምሮና ከእርሱም በኋላ የተናገሩ ነቢያት ሁሉ ስለ እነዚህ ቀኖች ተናግረዋል።
\v 25 እናንተ የነቢያትና ‘በዘርህ የምድር ሕዝቦች ሁሉ ይባረካሉ’ ብሎ ለአብርሃም እንደ ተናገረው፣ ከአባቶቻችሁ ጋር እግዚአብሔር ያደረገው ኪዳን ልጆች ናችሁ።
\v 26 እግዚአብሔር አገልጋዩን ካስነሣ በኋላ በመጀመሪያ ወደ እናንተ ላከው፤ ይኸውም እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ መልሶ ሊባርካችሁ ነው።
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 ጴጥሮስና ዮሐንስ ለሕዝቡ እየተናገሩ ሳሉ፣ ካህናቱና የቤተ መቅደሱ ሹም፣ ሰዱቃውያንም ወደ እነርሱ መጡ።
\v 2 እነርሱም፣ ጴጥሮስና ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ሕዝቡን ያስተምሩና ከሙታን መነሣቱንም ያውጁ ስለ ነበረ፣ እጅግ ተበሳጩ።
\v 3 ያዟቸውና በዚያ ጊዜ ምሽት ስለ ነበረ እስከሚቀጥለው ጧት ድረስ በወኅኒ አቈዩአቸው።
\v 4 ነገር ግን መልእክቱን ከሰሙት ብዙ ሰዎች አመኑ፤ ያመኑት ሰዎች ቍጥርም ዐምስት ሺሕ ያህል ነበረ።
\s5
\v 5 በሚቀጥለው ቀን እንደዚህ ሆነ፤ አለቆቻቸው፣ ሽማግሌዎቻቸውና የሕግ መምህራናቸው በኢየሩሳሌም ውስጥ በአንድነት ተሰበሰቡ።
\v 6 ሊቀ ካህናቱ ሐና እዚያ ነበረ፤ ቀያፋም፣ ዮሐንስም፣ እስክንድሮስና የሊቀ ካህናቱ ዘመዶች ሁሉ ነበሩ።
\v 7 ጴጥሮስንና ዮሐንስን በመካከላቸው አቁመውም፣ "በማን ሥልጣን ወይም በማንስ ስም ይህን አደረጋችሁ?" ብለው ጠየቋቸው።
\s5
\v 8 ከዚያም ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ የሕዝቡ አለቆች፣ ሽማግሌዎችም፣
\v 9 ለታመመ ሰው የተደረገ መልካም ነገርን በሚመለከት በዚህ ቀን እየተጠየቅን ከሆንን፣ ይህ ሰው በምን ዳነ?
\v 10 ይህ ለእናንተ ለሁላችሁ፣ ለእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን፤ ይህ ሰው በፊታችሁ እዚህ በጤንነት የቆመው እናንተ በሰቀላችሁት፣ እግዚአብሔር ከሞት ባስነሣው በናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው።
\s5
\v 11 ኢየሱስ ክርስቶስ እናንተ ግንበኞች የናቃችሁት፣ ነገር ግን የማእዘን ራስ የሆነ ድንጋይ ነው።
\v 12 በሌላ በማንም ድነት የለም፤ ልንድንበት የሚገባ በሰዎች መካከል የተሰጠ ሌላ ስም ከሰማይ በታች የለምና።”
\s5
\v 13 የጴጥሮስንና የዮሐንስን ድፍረት ሲያዩ፣ ያልተማሩና ተራ ሰዎች እንደ ሆኑ ሲያውቁም፣ ጴጥሮስና ዮሐንስ ከኢየሱስ ጋር እንደ ነበሩ በማወቅ ተደነቁ።
\v 14 የተፈወሰው ሰውዬ ዐብሯቸው ቆሞ ስላዩት፣ የአይሁድ መሪዎች በእነርሱ ላይ ምንም መናገር አልቻሉም።
\s5
\v 15 ሐዋርያቱ ከሸንጎው ወጥተው እንዲሄዱ ካዘዙ በኋላ፣ እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ።
\v 16 እንደዚህም አሉ፤ “በእነዚህ ሰዎች ላይ ምን እናድርግ? በእነርሱ አማካይነት የታወቀ ተአምር የመፈጸሙ እውነታ በኢየሩሳሌም ለሚኖር ሁሉ ታውቆአልና፤ ልንክደው አንችልም።
\v 17 ሆኖም ይህ በሕዝቡ መካከል የበለጠ እንዳይሠራጭ፣ በዚህ ስም ከእንግዲህ ለማንም እንዳይናገሩ እናስጠንቅቃቸው።”
\v 18 ጴጥሮስንና ዮሐንስን ወደ ውስጥ ጠርተው በኢየሱስ ስም ፈጽሞ እንዳይናገሩም፣ እንዳያስተምሩም አዘዟቸው።
\s5
\v 19 ነገር ግን ጴጥሮስና ዮሐንስ መልሰው እንዲህ አሏቸው፤ “ለእግዚአብሔር ከመታዘዝ ይልቅ እናንተን መታዘዝ በእግዚአብሔር ፊት ትክክል እንደ ሆነ እናንተ ፍረዱ።
\v 20 እኛ ስላየናቸውና ስለ ሰማናቸው ነገሮች ለመናገር ዝም ማለት አንችልም።”
\s5
\v 21 እንደ ገናም ጴጥሮስንና ዮሐንስን ካስጠነቀቋቸው በኋላ፣ ለቀቋቸው። እነርሱን ለመቅጣት ምንም ምክንያት ለማግኘት አልቻሉም፤ ምክንያቱም ሰዎቹ ሁሉ ለተደረገው እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር።
\v 22 ይህ በተአምር የተፈወሰው ሰውዬ ከዐርባ ዓመት በላይ ዕድሜ ነበረው።
\s5
\v 23 ከተለቀቁ በኋላ፣ ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ ራሳቸው ሰዎች መጡና የካህናት አለቆችና ሽማግሌዎች ያሏቸውን ሁሉ ነገሯቸው።
\v 24 ሰዎቹ የነገሯቸውን ሲሰሙም፣ ድምፃቸውን በአንድነት ወደ እግዚአብሔር ከፍ አድርገው እንዲህ አሉ፤ “ጌታ ሆይ፣ አንተ ሰማያትን፣ ምድርንና ባሕርን፣ በውስጣቸው የሚገኘውንም ሁሉ የፈጠርህ ነህ፤
\v 25 በመንፈስ ቅዱስም በአገልጋይህ በአባታችን በዳዊት አፍ እንዲህ ብለሃል፦ ‘አሕዛብ ለምን አጕረመረሙ፣ ሕዝቡስ ከንቱ ነገርን ለምን ዐሰቡ?
\s5
\v 26 በጌታ፣ በእርሱ መሲሕም ላይ የምድር ነገሥታት ተነሡ፣ አለቆችም በአንድነት ተሰበሰቡ።’
\s5
\v 27 በእውነት ሄሮድስና ጴንጤናዊው ጲላጦስ፣ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በቀባኸው በቅዱሱ አገልጋይህ በኢየሱስ ላይ በዚህ ከተማ ውስጥ በአንድነት ተሰብስበዋል።
\v 28 የተሰበሰቡትም እጅህና ዐሳብህ አስቀድመው የወሰኑት እንዲፈጸም ነው።
\s5
\v 29 ጌታ ሆይ፣ አሁን ወደ ዛቻዎቻቸው ተመልከት፤ ለባሪያዎችህም ቃልህን በሙሉ ድፍረት እንዲናገሩ ስጥ።
\v 30 ለመፈወስ እጅህን ስትዘረጋው፣ ምልክቶችና ድንቆች በቅዱሱ አገልጋይህ በኢየሱስ ስም ይደረጋሉ።"
\v 31 ጸሎት ሲጨርሱ፣ ተሰብስበውበት የነበረው ስፍራ ተናወጠ፤ ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ፤ የእግዚአብሔርን ቃልም በድፍረት ተናገሩ።
\s5
\v 32 ካመኑት እጅግ ብዙዎች አንድ ልብና አንድ ነፍስ ነበራቸው፤ ከእነርሱ አንድም ሰው፣ ያለው ማንኛውም ነገር የራሱ እንደ ሆነ አልተናገረም፤ ይልቁን ሁሉም ነገሮች የጋራ ነበሩ።
\v 33 ሐዋርያቱም በታላቅ ኀይል ስለ ጌታ ኢየሱስ ትንሣኤ ምስክርነታቸውን ያውጁ ነበር፤ በሁሉም ላይ ታላቅ ጸጋ ነበረባቸው።
\s5
\v 34 በመካከላቸው ችግረኛ ሰው አልነበረም፤ መሬት ወይም ቤት ያላቸው ሁሉ ሸጠው የሽያጩን ገንዘብ ያመጡትና፣
\v 35 በሐዋርያት እግር አጠገብ ያስቀምጡት ነበርና። አከፋፈሉም ይደረግ የነበረው እያንዳንዱ አማኝ በሚያስፈልገው መሠረት ነው።
\s5
\v 36 ሌዋዊ የሆነው፣ ቆጵሮሳዊው ዮሴፍ ሐዋርያት በርናባስ የሚባል ስም ያወጡለት ሰው ነበር (ትርጕሙ የመጽናናት ልጅ ማለት ነው)።
\v 37 እርሱ የነበረውን መሬት ሸጠው፤ ገንዘቡንም አምጥቶ በሐዋርያት እግር አጠገብ አስቀመጠው።
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 ሐናንያ የሚባል አንድ ሰውም ከሚስቱ ከሰጲራ ጋራ መሬት ሸጠ፤
\v 2 የሽያጩን ገንዘብ ከፊል መጠን አስቀረው (ሚስቱም ታውቅ ነበር)፤ ሌላውን የገንዘብ መጠን ግን አምጥቶ በሐዋርያት እግር አጠገብ አስቀመጠው።
\s5
\v 3 ጴጥሮስ ግን ሐናንያን እንዲህ አለው፤ “ሐናንያ ሆይ፣ ለመንፈስ ቅዱስ እንድትዋሽና የመሬቱን ዋጋ ከፊል መጠን እንድታስቀር ሰይጣን ልብህን ለምን ሞላው?
\v 4 መሬቱ ሳይሸጥ የአንተ እንደ ሆነ አይዘልቅም ነበርን? ከተሸጠ በኋላስ በአንተ ቊጥጥር ሥር አልነበረምን? በልብህ ይህን ነገር እንዴት ዐሰብህ? የዋሸኸው ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰዎች አይደለም።
\v 5 እነዚህን ቃሎች ሰምቶ፣ ሐናንያ ወደቀ፤ ሞተም። በሰሙት ሁሉ ላይም ታላቅ ፍርሀት መጣ።
\v 6 ጐበዛዝቱ ወደ ፊት መጡና ከፈኑት፤ ወደ ውጭ አውጥተውም ቀበሩት።
\s5
\v 7 ከሦስት ሰዓት ያህል በኋላ፣ ሚስቱ ምን እንደ ሆነ ሳታውቅ ወደ ውስጥ ገባች።
\v 8 ጴጥሮስ፣ “መሬቱን ይህን ለሚያህል ዋጋ ሸጣችሁት ከሆነ ንገሪኝ” አላት። እርሷም፣ "አዎ፣ ይህን ለሚያህል ነው” አለችው።
\s5
\v 9 ከዚያም ጴጥሮስ፣ “የጌታን መንፈስ ለመፈታተን እንዴት ተስማማችሁ? ተመልከቺ፣ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች እግር በር ላይ ነው፤ አንቺንም ወደ ውጭ ያወጡሻል።”
\v 10 እርሷም ወዲያው በጴጥሮስ እግር ሥር ወደቀች፤ ሞተችም፤ ጐበዛዝቱም ወደ ውስጥ ሲገቡ ሞታ አገኟት፤ ወደ ውጭ አወጧትና በባሏ አጠገብ ቀበሯት።
\v 11 በቤተ ክርስቲያን ሁሉና እነዚህን ነገሮች በሰሙት ላይ ታላቅ ፍርሀት መጣ።
\s5
\v 12 በሕዝቡ መካከል ብዙ ምልክቶችና ድንቆች በሐዋርያት እጅ ይደረጉ ነበር። ሁሉም በሰሎሞን ደጅ መመላለሻ በአንድነት ነበሩ።
\v 13 ነገር ግን አንድም ሌላ ሰው እንኳ ከእነርሱ ጋር ለመተባበር ድፍረት አልነበረውም፤ ሆኖም ከሕዝቡ ከፍተኛ አክብሮት ነበራቸው።
\s5
\v 14 አሁንም የበለጡ አማኞች፣ እጅግ ብዙ ወንዶችና ሴቶች ለጌታ ይጨመሩ ነበር፤
\v 15 በሽተኞችንም እንኳ ተሸክመው ወደ መንገድ እያመጡ በዐልጋና በቃሬዛ ላይ ያስቀምጧቸው ነበር፤ ይኸውም ጴጥሮስ ሲያልፍ በተወሰኑት ላይ ጥላው እንዲያርፍባቸውነው።
\v 16 በሽተኞችንና በርኩሳን መናፍስት የሚሠቃዩትን በማምጣት በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካሉ ከተሞች አያሌ ሰዎችም በአንድነት ተሰበሰቡ፤ በሽተኞችም ሁሉ ተፈወሱ።
\s5
\v 17 ነገር ግን ሊቀ ካህናቱና ዐብረውት የነበሩትም ሁሉ ተነሡ (የሰዱቃውያን ወገን የሆነው ማለት ነው)፤ እነርሱም በቅናት ተሞልተው ነበር፤
\v 18 እጃቸውንም በሐዋርያት ላይ ጫኑ፤ በሕዝብ ወኅኒ ውስጥም አስገብተው አሰሯቸው።
\s5
\v 19 ይሁን እንጂ፣ የጌታ መልአክ በሌሊት የወኅኒውን በሮች ከፈተ፤ ወደ ውጭ አውጥቶአቸውም እንዲህ አላቸው፤
\v 20 “ሂዱ፤ በቤተ መቅደስ ውስጥ ቁሙና የዚህን ሕይወት ቃሎች ሁሉ ለአሕዝቡ ተናገሩ።”
\v 21 ይህን ሲሰሙም፣ ንጋት ላይ ወደ ቤተ መቅደስ ገቡና አስተማሩ። ነገር ግን ሊቀ ካህናቱና ከእርሱ ጋር የነበሩት መጡ፤ ሸንጎውንም በአንድነት፣ የእስራኤል ሕዝብ ሽማግሌዎችንም ጠሩ፤ ሐዋርያቱን እንዲያመጧቸውም ወደ ወኅኒው ላኩ።
\s5
\v 22 ነገር ግን የተላኩት መኰንኖች በወኅኒው ውስጥ አላገኟቸውም፤ ተመልሰው በመሄድም እንዲህ ብለው ተናገሩ፣
\v 23 “ወኅኒው በደኅና እንደ ተቈለፈና ጠባቂዎችም በር ላይ እንደ ቆሙ አግኝተናል፤ በከፈትነው ጊዜ ግን በውስጡ ማንንም አላገኘንም።”
\s5
\v 24 የመቅደሱ ጥበቃ ሹምና ሊቃነ ካህናቱ እነዚህን ቃላት ሲሰሙ፣ እስረኞችን በሚመለከት ምን እንደሚሆን እጅግ ግራ ተጋቡ።
\v 25 ከዚያም አንድ ሰው መጣና፣ “ወኅኒ ውስጥ ያስገባችኋቸው ሰዎች ቤተ መቅደስ ውስጥ ቆመው ሕዝቡን እያስተማሩ ናቸው” ብሎ ነገራቸው።
\s5
\v 26 ስለዚህ ሹሙ ከመኰንኖች ጋር ሄደ፤ መልሶም አመጣቸው፤ ያመጧቸው ግን በኀይል አልነበረም፤ ሕዝቡ በድንጋይ ይወግሯቸዋል ብለው ፈርተው ነበርና።
\v 27 አምጥተዋቸው በነበረ ጊዜ፣ በሸንጎው ፊት አቆሟቸው። ሊቀ ካህናቱም ጠየቃቸው፤
\v 28 እንዲህም አላቸው፤ “በዚህ ስም እንዳታስተምሩ በጥብቅ አስጠንቅቀናችሁ ነበር፤ እናንተ ግን ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞልታችኋታል፤ የዚህን ሰው ደም በእኛ ላይ ለማምጣትም ትፈልጋላችሁ።”
\s5
\v 29 ጴጥሮስና ሐዋርያቱ ግን መልሰው፣ “ለሰው ከመታዘዝ ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።
\v 30 የአባቶቻችን አምላክ በዕንጨት ላይ በመስቀል የገደላችሁትን፣ ኢየሱስን አስነሣው።
\v 31 አዳኝና የሁሉ የበላይ እንዲሆን፣ ለእስራኤል ንስሓንና የኀጢአት ይቅርታን ለመስጠት እግዚአብሔር በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው።
\v 32 እኛና እግዚአብሔር ለሚታዘዙት የሰጠው መንፈስ ቅዱስ የእነዚህ ነገሮች ምስክሮች ነን።”
\s5
\v 33 የሸንጎው አባሎች ይህን ሲሰሙ፣ በጣም ተናደዱ፤ ሐዋርያቱንም ለመግደል ፈለጉ።
\v 34 ነገር ግን የሕግ መምህር የነበረና ሕዝቡም ሁሉ የሚያከብረው ገማልያል የሚባል አንድ ፈሪሳዊ ተነሥቶ፣ ሐዋርያት ለተወሰነ ጊዜ ውጭ እንዲቈዩ አዘዘ።
\s5
\v 35 ከዚያም እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ በእነዚህ ሰዎች ልታደርጉ ያሰባችሁትን በጥንቃቄ ተመልከቱት።
\v 36 ከጥቂት ጊዜ በፊት ቴዎዳስ ትልቅ ሰው ነኝ በማለት ተነሥቶ ነበርና፤ አራት መቶ ያህል ወንዶችም ተከተሉት። እርሱ ተገደለ፤ ይታዘዙለት የነበሩትም ሁሉ ተበታትነው እንዳልነበሩ ሆኑ።
\v 37 ከዚህም ሰው በኋላ፣ የገሊላው ይሁዳ በቈጠራው ቀናት ዐምፆ የተወሰኑ ሰዎችን አስከትሎ ሄደ። እርሱም ሞተ፤ እርሱን ይታዘዙት የነበሩትም ተበታተኑ።
\s5
\v 38 አሁንም እነግራችኋለሁ፤ ከእነዚህ ሰዎች ተለዩ፤ እነርሱንም ተዉአቸው፤ ይህ ዐሳብ ወይም ሥራ የሰዎች ከሆነ፣ ይጠፋል።
\v 39 የእግዚአብሔር ከሆነ ግን፣ ልታጠፏቸው አትችሉም፤ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጋጩም እንኳ እንዳትገኙ።” እነርሱም በዐሳቡ ተስማሙ።
\s5
\v 40 ከዚያም በኋላ፣ ሐዋርያቱን ወደ ውስጥ ጠርተው ገረፏቸው፤ በኢየሱስ ስም እንዳይናገሩም አዘዟቸውና ለቀቋቸው።
\v 41 እነርሱም ስለ ስሙ ይዋረዱ ዘንድ የተገባቸው ሆነው ስለ ተቈጠሩ፣ ደስ እያላቸው ከሸንጎው ወጡ።
\v 42 ከዚያ በኋላ በየቀኑ፣ በቤተ መቅደስና ከቤት ወደ ቤት፣ በተከታታይ ኢየሱስ፣ ክርስቶስ እንደ ሆነ ያስተምሩና ይሰብኩ ነበር።
\s5
\c 6
\cl ምዕራፍ 6
\p
\v 1 በእነዚህ ወራት፣ የደቀ መዛሙርት ቊጥር እየበዛ በሄደ ጊዜ፣ ከግሪክ የመጡት አይሁድ በዕብራውያን ላይ ማጕረምረም ጀመሩ፤ ምክንያቱም መበለቶቻቸው በየዕለቱ የምግብ ዕደላ ላይ ቸል ተብለውባቸው ነበር።
\s5
\v 2 ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ደቀ መዛሙርቱን ሁሉ ጠርተው እንዲህ አሏቸው፤ “የምግብ አገልግሎትን ለመስጠት ብለን የእግዚአብሔርን ቃል መተው ለእኛ ተገቢ አይደለም።
\v 3 ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፣ በዚህ ኀላፊነት ላይ ልንሾማቸው የምንችል መልካም አርአያነት ያላቸውን፣ መንፈስና ጥበብ የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ከእናንተ መካከል ምረጡ።
\v 4 እኛ ግን፣ ሁልጊዜ በጸሎትና በቃሉ አገልግሎት እንቀጥላለን።”
\s5
\v 5 ንግግራቸው ሕዝቡን ሁሉ ደስ አሰኘ። ስለዚህ እምነትና መንፈስ ቅዱስ የሞላበትን እስጢፋኖስን፣ ፊልጶስን፣ ጵሮኮሮስን፣ ኒቃሮናን፣ ጢሞናን፣ ጳርሜናንና ወደ ይሁዲነት ገብቶ የነበረውን አንጾኪያዊውን ኒቆላዎስን መረጡ።
\v 6 አማኞቹ እነዚህን ሰዎች፣ በጸለዩላቸውና ከዚያም እጃቸውን በላያቸው በጫኑት በሐዋርያት ፊት አቀረቧቸው።
\s5
\v 7 ስለዚህም የእግዚአብሔር ቃል አደገ፤ የደቀ መዛሙርት ቊጥርም በኢየሩሳሌም ውስጥ በብዛት ጨመረ፤ ከካህናትም ብዙዎቹ ለእምነት ታዛዦች ሆኑ።
\s5
\v 8 እስጢፋኖስ ጸጋንና ኀይልን ተሞልቶ፣ በሕዝቡ መካከል ታላላቅ ድንቆችንና ምልክቶችን ያደርግ ነበር።
\v 9 ነገር ግን ነጻ የወጡት ሰዎች ምኵራብ ከሚባለው ምኵራብ፣ ከቀሬናና ከእስክንድርያ፣ ከኪልቅያና ከእስያም የሆኑ ጥቂት ሰዎች ተነሡ። እነዚህ ሰዎች ከእስጢፋኖስ ጋር ይከራከሩ ነበር።
\s5
\v 10 ነገር ግን ሰዎቹ እስጢፋኖስ የተናረገረበትን ጥበብና መንፈስ መቋቋም አልቻሉም።
\v 11 ከዚያም፣ “እስጢፋኖስ በሙሴና በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ሲናገር ሰምተናል” እንዲሉ አንዳንድ ሰዎችን በምስጢር አሳመኑ።
\s5
\v 12 ሰዎቹን፣ ሽማግሌዎቹን፣ የሕግ መምህራኖቹንም አነሣሡ፤ እስጢፋኖስንም ይዘው ወደ ሸንጎው አቀረቡት።
\v 13 እንዲህ ብለው የሚናገሩ ሐሰተኛ ምስክሮችንም አመጡ፤ “ይህ ሰው ይህን ቅዱስ ስፍራና ሕጉን ተቃውሞ መናገርን አያቆምም።
\v 14 ምክንያቱም ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ ያፈርሰዋል፤ ሙሴም ያስተላለፈልንን ሥርዐትም ይለውጠዋል ሲል ሰምተነዋል።”
\v 15 በሸንጎው ውስጥ የተቀመጡት ሁሉ አተኵረው ተመለከቱት፤ ፊቱም እንደ መልአክ ፊት ሆኖ አዩት።
\s5
\c 7
\cl ምዕራፍ 7
\p
\v 1 ሊቀ ካህናቱም፣ “እነዚህ ነገሮች እውነት ናቸውን?” አለ።
\v 2 እስጢፋኖስ እንዲህ ብሎ መለሰ፦ “ወንድሞችና አባቶች ሆይ፣ አድምጡኝ፤ የክብር አምላክ ለአባታችን ለአብርሃም በካራን ከመኖሩ በፊት በመስጴጦምያ ሳለ ተገለጠለት፤
\v 3 እግዚአብሔርም፣ 'አገርህንና ዘመዶችህን ተውና እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ' አለው።
\s5
\v 4 ከዚያም በኋላ፣ ጊዜ አብርሃም ከከለዳውያን ምድር ወጥቶ በካራን ኖረ፤ ከዚያም፣ አባቱ ከሞተ በኋላ፣ እግዚአብሔር አሁን እናንተ ወደምትኖሩበት፣ ወደዚህ ምድር አመጣው።
\v 5 ከዚህ ምድር ምንም ርስት፣ የእግር ጫማ ለማሳረፍ የሚበቃ እንኳ አልሰጠውም። ነገር ግን አብርሃም ገና ልጅ ያልነበረው ቢሆንም እንኳ፣ እግዚአብሔር ምድሪቱን ርስት አድርጎ ለእርሱና ከእርሱ በኋላ ለዘሮቹ እንደሚሰጥ ቃል ገባ።
\s5
\v 6 እግዚአብሔር ለአብርሃም እንደዚህ እየተናገረው ነበር፤ ይኸውም ዘሮቹ ለተወሰነ ጊዜ በባዕድ ምድር እንደሚኖሩ፣ እዚያ ያሉ ኗሪዎችም በባርነት ውስጥ እንደሚያስገቧቸውና ለአራት መቶ ዓመታት እንደሚያስጨንቋቸው ነው።
\v 7 ‘በባርነት የሚኖሩበትን ሕዝብም እፈርድበታለሁ፤ ከዚያም በኋላ ይወጣሉ፤ በዚህም ስፍራ ያመልኩኛል’ አለ እግዚአብሔር።
\v 8 እግዚአብሔር ለአብርሃም የግዝረትን ኪዳን ሰጠው፤ አብርሃምም የይስሐቅ አባት ሆነ ይስሐቅንም በስምንተኛው ቀን ገረዘው፤ ይስሐቅ የያዕቆብ አባት ሆነ፤ ያዕቆብም የዐሥራ ሁለቱ አለቆች አባት።
\s5
\v 9 አለቆች በዮሴፍ ላይ በቅናት ተነሣሥተው ወደ ግብፅ ሸጡት፤ እግዚአብሔር ግን ከእርሱ ጋር ነበረ፤
\v 10 ከመከራውም ሁሉ አዳነው፤ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊትም ሞገስና ጥበብ ሰጠው። ፈርዖንም ዮሴፍን በግብፅና በቤቱ ባለው ሁሉ ላይ ገዥ አደረገው።
\s5
\v 11 በመላው ግብፅና በከነዓን ራብና ትልቅ ጭንቀት መጣ፤ አባቶቻችንም ምንም ምግብ አላገኙም።
\v 12 ነገር ግን ያዕቆብ እህል በግብፅ ውስጥ እንደ ነበረ ሲሰማ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ አባቶቻችንን ላካቸው።
\v 13 በሁለተኛው ጊዜ ዮሴፍ ለወንድሞቹ ራሱን ገለጠ፤ የዮሴፍ ቤተ ሰብም ከፈርዖን ጋር ተዋወቀ።
\s5
\v 14 ከዘመዶቹ ሁሉ ጋር፣ ሰባ ዐምስት ሰዎች ሆኖ ወደ ግብፅ እንዲመጣ፣ ለአባቱ ለያዕቆብ እንዲነግሩ ዮሴፍ ወንድሞቹን መልሶ ላካቸው።
\v 15 ስለዚህ ያዕቆብ ወደ ግብፅ ወረደ፤ ከጊዜ በኋላም፣ እርሱና አባቶቻችን በዚያ ሞቱ።
\v 16 ወደ ሴኬም ተወስደውም አብርሃም በሴኬም ከኤሞር ልጆች በብር ገዝቶት በነበረው መቃብር ተቀበሩ።
\s5
\v 17 እግዚአብሔር ለአብርሃም ገብቶት የነበረው የተስፋ ቃል ጊዜ ሲቃረብ፣ ሕዝቡ በግብፅ ውስጥ በቍጥር እያደጉና እየበዙ ሄዱ፤
\v 18 በግብፅ ሌላ ንጉሥ፣ ስለ ዮሴፍ ያላወቀ ንጉሥ እስከ ተነሣ ድረስ።
\v 19 ይኸው ንጉሥ ሕዝባችንን አታለለ፤ አባቶቻችንንም አስጨነቀ፤ ሕዝቡም ሕፃናታቸውን በሕይወት እንዳይኖሩ ወደ ውጭ መጣል ነበረባቸው።
\s5
\v 20 በዚያ ጊዜ ሙሴ ተወለደ፤ እርሱ በእግዚአብሔር ፊት በጣም ያማረ ነበር፤ በአባቱ ቤትም ሦስት ወር አደገ።
\v 21 ሙሴ ወንዝ ውስጥ ሲጣል፣ የፈርዖን ሴት ልጅ ወስዳ እንደ ልጇ አሳደገችው።
\s5
\v 22 ሙሴ በግብፃውያን ትምህርት ሁሉ የሠለጠነ፣ በንግግሩና በሥራውም ታላቅ ሰው ነበር።
\v 23 አርባ ዓመት ሲሆነው ግን ወንድሞቹን፣ የእስራኤልን ልጆች የመጐብኘት ዐሳብ ወደ ልቡ መጣ።
\v 24 አንድ እስራኤላዊ ሲጠቃ አይቶ፣ ሙሴ ተከላከለለት፤ ያጠቃውንም ግብፃዊ ተበቀለው፤
\v 25 ሙሴ በእርሱ እጅ እግዚአብሔር እያዳናቸው መሆኑን ወንድሞቹ ያስተውላሉ ብሎ ዐሰበ፤ እነርሱ ግን አላስተዋሉም።
\s5
\v 26 በሚቀጥለው ቀን ሙሴ እየተጣሉ ወደ ነበሩ እስራኤላውያን መጣ፤ እርስ በርስ ሊያስታርቃቸውም ሞከረ፤ ‘እናንተ ሰዎች ሆይ፣ ወንድማማቾች ናችሁ፤ እርስ በርስ ለምን ትጐዳዳላችሁ? አለ።
\v 27 ባልንጀራውን የጐዳው ግን ሙሴን ገፈተረው፤ እንደዚህም አለው፤ 'በእኛ ላይ ገዥና ዳኛ ያደረገህ ማን ነው?
\v 28 ግብፃዊውን ትናንት እንደ ገደልኸው እኔንም ልትገድለኝ ትፈልጋለህን?'
\s5
\v 29 ሙሴ ይህን ከሰማ በኋላ ሸሽቶ ሄደ፤ የሁለት ልጆች አባት በሆነበት በምድያም ምድር መጻተኛ ሆነ።
\v 30 አርባ ዓመት ሲያልፍ፣ በሲና ተራራ ምድረ በዳ፣ በቊጥቋጦ ውስጥ በእሳት ነበልባል መልአክ ታየው።
\s5
\v 31 ሙሴ እሳቱን ሲያይ፣ በሚታየው ተደነቀ፤ ሊመለከተው ሲቀርብም፣ እንዲህ የሚል የጌታ ድምፅ መጣ፤
\v 32 ‘እኔ የአባቶችህ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅም አምላክ፣ የያዕቆብም አምላክ ነኝ።’ ሙሴ ተንቀጠቀጠ፣ መመልከትም አልቻለም።
\s5
\v 33 ጌታም ለሙሴ እንዲህ አለው፤ ‘የቆምህበት ስፍራ ቅዱስ ነውና ጫማህን አውልቅ።
\v 34 በግብፅ ውስጥ ያሉትን የሕዝቤን ሥቃይ በእርግጥ አይቻለሁ፤ የሥቃይ ጩኸታቸውን ሰምቻለሁ፤ ላድናቸውም ወርጃለሁና አሁን ና፤ ወደ ግብፅ እልክሃለሁ።’
\s5
\v 35 “በእኛ ላይ ገዥና ዳኛ ያደረገህ ማን ነው?” ባሉት ጊዜ ተቀባይነትን ያሳጡት ይህ ሙሴ፦ እግዚአብሔር ገዥም ታዳጊም አድርጎ የላከው ነው። እግዚአብሔር ሙሴን በቊጥቋጦው ውስጥ በታየው መልአክ እጅ ላከው።
\v 36 በግብፅና በቀይ ባሕር፣ በአርባ ዓመታቱ ወቅትም በምድረ በዳ ተአምራትንና ምልክቶችን ካደረገ በኋላ፣ ሙሴ ሕዝቡን ከግብፅ አወጣቸው።
\v 37 ‘እግዚአብሔር ከወንድሞቻችሁ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋል’ ብሎ ለእስራኤል ሕዝብ የተናገረው ያው ሙሴ ነው።
\s5
\v 38 ይህ ሰው ሲና ተራራ ላይ ያናግረው ከነበረው መልአክ ጋር በምድረ በዳው በጉባኤ ውስጥ የነበረ ሰው ነው። ሰው ከአባቶችችን ጋር ነበረ፤ ለእኛ ሊሰጥ ሕያው ቃልን የተቀበለ ሰውም ነው።
\v 39 ይህ አባቶቻችን ለመታዘዝ እንቢ ያሉት ሰው ነው፤ እነርሱም ገፉት፤ በልባቸውም ወደ ግብፅ ተመለሱ።
\v 40 በዚያ ጊዜ አሮንን እንዲህ አሉት፤ ‘የሚመሩንን አማልክት ሥራልን። ከግብፅ ምድር መርቶ ያወጣን ይህ ሙሴ፣ ምን እንዳጋጠመው አናውቅም።'
\s5
\v 41 ስለዚህ እስራኤላውያን በእነዚያ ቀኖች ጥጃ ሠርተው ለጣዖቱ መሥዋዕት አቀረቡ፤ ከእጆቻቸው ሥራ የተነሣም ደስ አላቸው።
\v 42 እግዚአብሔር ግን ዘወር አለ፤ የሰማይ ከዋክብትን እንዲያመልኩም አሳልፎ ሰጣቸው፤ በነቢያት መጽሐፍ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ አርባ ዓመት በምድረ በዳ፣ የታረዱ እንስሳትንና መሥዋዕቶችን አቀረባችሁልኝን?
\s5
\v 43 የሞሎክን ድንኳን፣ ሬምፉም የሚባለውን አምላክ ኮከብም፣ ልታመልኳቸው የሠራችኋቸውን ምስሎችም ተቀበላችሁ፤ እኔም ከባቢሎን ወዲያ እሰድዳችኋለሁ።’
\s5
\v 44 አባቶቻችን የምስክሩ ድንኳን በምድረ በዳ ነበራቸው፤ ይኸውም ባየው ምሳሌ መሠረት መሥራት እንዳለበት እግዚአብሔር ሙሴን ሲያናግረው እንዳዘዘው ያለ ነው።
\v 45 ይህ አባቶቻችን በተራቸው ከኢያሱ ጋር ወደ ምድሪቱ ያመጡት ድንኳን ነው። እግዚአብሔር በአባቶቻችን ፊት ባስወጣቸው አሕዛብ አገር ውስጥ ሲገቡ፣ ይህ ሆነ። እስከ ዳዊት ዘመን ድረስ እንደዚህ ነበር፤
\v 46 ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አገኘ፤ ለያዕቆብ አምላክም ማደሪያ ስፍራን ለማግኘት ለመነ።
\s5
\v 47 ነገር ግን ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤት ሠራለት።
\v 48 ይሁን እንጂ፣ ልዑሉ በእጅ በተሠሩ ቤቶች ውስጥ አይኖርም፤ ይህም ነቢዩ እንዲህ ብሎ እንደሚናገረው ነው፦
\v 49 ሰማይ ዙፋኔ፣ ምድርም የእግሬ መርገጫ ነው። ምን ዐይነት ቤት ልትሠሩልኝ ትችላላችሁ? ይላል ጌታ፤ ወይስ የማርፍበት ስፍራ የት ነው?
\v 50 እጄ እነዚህን ሁሉ አልሠራችምን?
\s5
\v 51 እናንተ ዐንገተ ደንዳኖች፣ ልባችሁንና ጆሮዎቻችሁን ያልተገረዛችሁ፣ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ፤ አባቶቻችሁ እንዳደረጉትም ታደርጋላችሁ።
\v 52 ከነቢያት የእናንተ አባቶች ያላሳደዱት የትኛው ነው? እነርሱ ከጻድቁ መምጣት ቀድመው የተናገሩ ነቢያትን ገድለዋል፤ እናንተም አሁን ጻድቁን የምትክዱና የምትገድሉ ሆናችኋል፤
\v 53 መላእክት ያጸኑትን ሕግ ብትቀበሉም አልጠበቃችሁትም።”
\s5
\v 54 አሁን የሸንጎው አባላት እነዚህን ነገሮች ሲሰሙ፣ በልባቸው እጅግ ተቈጡ፣ ጥርሳቸውንም በእስጢፋኖስ ላይ አፋጩ።
\v 55 እስጢፋኖስ ግን በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ፣ ወደ ሰማይ አተኵሮ ተመለከተ፣ የእግዚአብሔርንም ክብር አየ፤ ኢየሱስንም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየው።
\v 56 እስጢፋኖስ፣ “እነሆ፣ ሰማያት ተከፍተው፣ የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየሁ” አለ።
\s5
\v 57 የሸንጎው አባላት ግን በታላቅ ድምፅ ጮኹ፤ ጆሮአቸውንም በመድፈን በአንድነት እየሮጡ ወደ እስጢፋኖስ ሄዱ፤
\v 58 ከከተማው አውጥተውም በድንጋይ ወገሩት፤ ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በሚባል አንድ ወጣት እግር አጠገብ አኖሩ።
\s5
\v 59 እስጢፋኖስን ሲወግሩት፣ ወደ እግዚአብሔር ይጣራ፣ “ጌታ ኢየሱስ ሆይ፣ ነፍሴን ተቀበል” እያለ ይናገርም ነበር።
\v 60 ተንበረከከና በታላቅ ድምፅ፣ “ጌታ ሆይ፣ ይህን ኀጢአት አትቊጠርባቸው” ብሎ ጮኸ። ይህን ተናግሮም፣ አንቀላፋ።
\s5
\c 8
\cl ምዕራፍ 8
\p
\v 1 ሳውል በእስጢፋኖስ ሞት ተስማምቶ ነበር። በዚያም ጊዜ በኢየሩሳሌም በነበረችዋ ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ተነሣ፤ አማኞችም ሁሉ ከሐዋርያት በቀር በይሁዳና በሰማርያ ተበታተኑ።
\v 2 በመንፈሳዊ ነገር የተጉ ሰዎች እስጢፋኖስን ቀበሩት፤ መሪር ልቅሶም አለቀሱለት።
\v 3 ሳውል ግን ቤተ ክርስቲያንን በጣም ጐዳ፤ ከቤት ወደ ቤት በመሄድም ክርስቲያን ወንዶችንና ሴቶችን ጐትቶ አወጣቸው፤ ወኅኒ ቤት ውስጥም አስገባቸው።
\s5
\v 4 የተበታተኑት አማኞች ግን ቃሉን እየሰበኩ በየቦታው ዞሩ።
\v 5 ፊልጶስ ወደ ሰማርያ ከተማ ወረደ፣ ለሕዝቡም ክርስቶስን ሰበከላቸው።
\s5
\v 6 እጅግ ብዙ ሰዎች ፊልጶስን ሲሰሙትና ያደረጋቸውንም ምልክቶች ሲያዩ፣ በአንድነት እርሱ ለተናገረው ትኵረት ሰጡ።
\v 7 ምክንያቱም ከብዙ ሰዎች ርኩሳን መናፍስት እየጮኹ ወጥተው፣ አያሌ ሽባዎችና ዐንካሶችም ተፈውሰው ነበር።
\v 8 ስለዚህ በዚያች ከተማ ውስጥ ብዙ ደስታ ነበር።
\s5
\v 9 ነገር ግን በዚያች ከተማ ውስጥ ቀደም ሲል የጥንቈላ ሥራ ይሠራ የነበረ ሲሞን የሚባል ሰው ነበረ፤ ተፈላጊ ሰው እንደ ሆነ እየተናገረ የሰማርያን ሰዎች ያስደንቅ ነበር።
\v 10 ሳምራውያን በሙሉ ከትንሹ እስከ ትልቁ፣ “ይህ ሰው ታላቅ የሚባለው የእግዚአብሔር ኀይል ነው” እያሉ በሚገባ ያደምጡት ነበር።
\v 11 በጥንቈላ ሥራው ለረጅም ጊዜ ያስገርማቸው ስለ ነበር አደመጡት።
\s5
\v 12 ስለ እግዚአብሔር መንግሥትና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ፊልጶስ የሰበከውን ወንጌል ሲያምኑ ግን ወንዶችም ሴቶችም ተጠመቁ።
\v 13 ሲሞንም ደግሞ አመነ፤ ከተጠመቀም በኋላ ከፊልጶስ ጋር መሆንን ቀጠለ፤ የተደረጉ ምልክቶችንና ታላላቅ ተኣምራትን ባየ ጊዜም ተደነቀ።
\s5
\v 14 በኢየሩሳሌም የነበሩ ሐዋርያት ሰማርያ የእግዚአብሔርን ቃል የተቀበለች መሆኗን ሲሰሙ፣ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ላኩላቸው።
\v 15 እነርሱም እዚያ ወርደው መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ ጸለዩላቸው።
\v 16 መንፈስ ቅዱስ እስከዚያ ጊዜ ድረስ በማንኛቸውም ላይ አልወረደም ነበርና፣ እነርሱ በጌታ ኢየሱስ ስም ብቻ ተጠምቀው ነበር።
\v 17 ከዚያም ጴጥሮስና ዮሐንስ እጃቸውን ጫኑባቸው፣ መንፈስ ቅዱስንም ተቀበሉ።
\s5
\v 18 በሐዋርያት እጅ መጫን መንፈስ ቅዱስ እንደሚሰጥ ሲያይ፣ ሲሞን ገንዘብ አቀረበላቸው።
\v 19 “እኔም እጁን የምጭንበት ሰው ሁሉ መንፈስ ቅዱስን መቀበል እንዲችል ይህን ሥልጣን ስጡኝ” አላቸው።
\s5
\v 20 ነገር ግን ጴጥሮስ እንዲህ አለው፤ “የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ ለማግኘት አስበሃልና ብርህ ከአንተ ጋር ይጥፋ።
\v 21 ልብህ ለእግዚአብሔር የቀና አይደለምና በዚህ ጉዳይ ውስጥ ዕድል ወይም ድርሻ የለህም።
\v 22 እንግዲህ ለዚህ ክፋትህ ንስሓ ግባ፤ ምናልባትም ለልብህ ዐሳብ ይቅር ይልህ እንደ ሆነ ጌታን ለምን።
\v 23 በኀጢአት እስራትና በመራርነት መርዝ ውስጥ እንዳለህ አያለሁና።”
\s5
\v 24 ሲሞንም መልሶ፣ “ከተናገራችኋቸው አንዱም በእኔ ላይ እንዳይፈጸም ወደ ጌታ ጸልዩልኝ” አላቸው።
\s5
\v 25 ጴጥሮስና ዮሐንስ ከመሰከሩና የጌታን ቃል ከተናገሩ በኋላ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ በመንገድም ለብዙ የሰማርያ መንደሮች ወንጌልን ሰበኩ።
\s5
\v 26 የጌታ መልአክ ፊልጶስን፣ “ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚወስደው መንገድ ወደ ደቡብ አቅጣጫ ተነሥና ሂድ” አለው። (ይህ መንገድ በበረሓ ውስጥ ነው።)
\v 27 እርሱም ተነሣና ሄደ። እነሆ፣ በኢትዮጵያውያን ንግሥት በሕንደኬ ሥር ትልቅ ሥልጣን የነበረው አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ነበረ። ሰውዬው በንግሥቲቱ ንብረት ሁሉ ላይ ኀላፊነት ነበረው። ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር።
\v 28 ከኢየሩሳሌም በመመለስ ላይ ሳለ፣ በሠረገላው ላይ ተቀምጦ ትንቢተ ኢሳይያስን እያነበበ ነበር።
\s5
\v 29 መንፈስ ፊልጶስን፣ “ሂድ ወደዚህ ሠረገላ ቅረብ” አለው።
\v 30 ፊልጶስ ወደ ጃንደረባው ሮጠ፣ ትንቢተ ኢሳይያስንም ሲያነብ ሰማው፤ “የምታነበውን ትረዳዋለህ?” አለው።
\v 31 ኢትዮጵያዊውም፣ “የሚመራኝ ከሌለ እንዴት ልረዳው እችላለሁ?” አለው። ወደ ሠረገላው እንዲወጣና ዐብሮት እንዲቀመጥ ፊልጶስን ለመነው።
\s5
\v 32 ኢትዮጵያዊው ያነበው የነበረ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይህ ነው፦ “እንደ በግ ለመታረድ ተነዳ፤ በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል ጠቦት፣ አፉን አልከፈተም፤
\v 33 በውርደቱ ፍርዱ ተወገደ፤ ትውልዱን ማን ይናገራል? ሕይወቱ ከምድር ተወግዶአልና።”
\s5
\v 34 ጃንደረባው ፊልጶስን፣ “እባክህ ነቢዩ ስለ ማን ነው የሚናገረው? ስለ ራሱ ወይስ ስለ ሌላ ነው?” አለው።
\v 35 ፊልጶስም መናገር ጀመረ፤ ከዚህም ከኢሳይያስ መጽሐፍ ጀምሮ ስለ ኢየሱስ ሰበከው።
\s5
\v 36 እየሄዱ ሳሉ ውሃ አለበት ዘንድ ደረሱ፤ ጃንደረባው፣ “ተመልከት፣ እዚህ ውሃ አለ፤ እንዳልጠመቅ ምን ይከለክለኛል?” አለ።
\v 37 ፊልጶስም፣ “በፍጹም ልብህ ካመንህ፣ መጠመቅ ትችላለህ” አለ። ኢትዮጵያዊውም መልሶ፣ “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ አምናለሁ” አለ።
\v 38 ኢትዮጵያዊው ሠረገላው እንዲቆም አዘዘና፣ ፊልጶስም ጃንደረባውም ወደ ውሃው ወረዱ፤ ፊልጶስም አጠመቀው።
\s5
\v 39 ከውሃው ውስጥ ሲወጡ፣ የጌታ መንፈስ ፊልጶስን ወሰደው፤ ጃንደረባውም ከዚያ ወዲያ አላየውም፤ ደስ ብሎትም ጕዞውን ቀጠለ።
\v 40 ነገር ግን ፊልጶስ በአዛጦን ታየ። በዚያ አገር ውስጥ በማለፍ ቂሣርያ እስኪደርስ ድረስ፣ ለከተሞች ሁሉ ወንጌልን ሰበከ።
\s5
\c 9
\cl ምዕራፍ 9
\p
\v 1 ሳውል ግን በጌታ ደቀ መዛሙርት ላይ ለግድያም እንኳ እየዛተ ወደ ሊቀ ካህናቱ ሄደ፤
\v 2 የጌታን መንገድ ከሚከተሉት ወንዶችም ሆነ ሴቶች ቢያገኝ፣ ወደ ኢየሩሳሌም አስሮ እንዲያመጣቸው፣ ለምኵራቦች ደብዳቤ እንዲሰጠውም ሊቀ ካህናቱን ጠየቀ።
\s5
\v 3 እየሄደ ሳለ ደማስቆ አጠገብ ሲደርስ፣ በድንገት ከሰማይ ብርሃን በዙሪያው በራበት፤
\v 4 በምድር ላይ ወደቀ፤ “ሳውል፣ ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ” የሚል ድምፅ ሰማ።
\s5
\v 5 ሳውልም፣ "ጌታ ሆይ፣ ማን ነህ?" ብሎ መለሰ፤ ጌታም፣ “አንተ የምታሳድደኝ ኢየሱስ ነኝ፤
\v 6 ነገር ግን ተነሥተህ ወደ ከተማው ግባ፤ ማድረግ ያለብህም ይነገርሃል” አለ።
\v 7 ከዚያም ከሳውል ጋር የተጓዙት ሰዎች ድምፁን እየሰሙ፣ ማንንም ግን ሳያዩና ሳይነጋገሩ ቆሙ።
\s5
\v 8 ሳውል ከወደቀበት ተነሣ፤ ዐይኑን ሲከፍትም ምንም ማየት አልቻለም፤ ስለዚህም በእጅ እየመሩ ወደ ደማስቆ አስገቡት።
\v 9 ሦስት ቀን ዕውር ሆኖ ቆየ፤ አልበላም አልጠጣምም።
\s5
\v 10 በዚያ ጊዜ ሐናንያ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር በደማስቆ ነበር፤ ጌታም ለእርሱ በራእይ፣ “ሐናንያ” አለው። እርሱም፣ “ጌታ ሆይ፣ እነሆኝ” አለ።
\v 11 ጌታም መልሶ እንዲህ አለው፤ “ተነሥና ቀጥተኛ ወደሚባለው ጎዳና ሂድ፤ በይሁዳ ቤትም ሳውል የሚባል የጠርሴስ ሰውን ፈልግ፤ እርሱ እዚያ እየጸለየ ነውና፤
\v 12 እርሱ እንዲያይ ሐናንያ የሚባል ሰው ሲገባና በእርሱ ላይ እጁን ሲጭንበት በራእይ አይቶአል።”
\s5
\v 13 ሐናንያም መልሶ እንዲህ አለ፤ “ጌታ ሆይ፣ ስለዚህ ሰው በኢየሩሳሌም ባሉት ሕዝብህ ላይ ምን ያህል ክፋት እንደ ፈጸመባቸው ከብዙዎች ሰምቻለሁ።
\v 14 ስምህን የሚጠሩትን ሁሉ ለማሰር ከሊቀ ካህናቱ ሥልጣን ተቀብሎአል።”
\v 15 ጌታ ግን መልሶ እንዲህ አለው፤ “ሂድ፤ እርሱ በአሕዛብ፣ በነገሥታትና በእስራኤል ልጆች ፊት ስሜን ለመሸከም የተመረጠ ዕቃየ ነውና፤
\v 16 ስለ ስሜ ሲል ምን ያህል መከራ መቀበል እንዳለበትም አሳየዋለሁና።
\s5
\v 17 ስለዚህ ሐናንያ ሄደ፤ ወደ ቤትም ገባ፤ እጁን በሳውል ላይ በመጫንም፣ “ወንድሜ ሳውል ሆይ፣ ስትመጣ በመንገድ ላይ የተገለጠልህ ጌታ ኢየሱስ እንድታይና መንፈስ ቅዱስን እንድትሞላ ወዳንተ ልኮኛል።”
\v 18 ወዲያው እንደ ቅርፊት ያለ ነገር ከሳውል ዐይን ወደቀ፤ ማየትም ጀመረ፤ ተነሥቶም ተጠመቀ፤
\v 19 በላ፣ በረታም። ሳውል በደማስቆ ውስጥ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ብዙ ቀን ቆየ።
\s5
\v 20 ወዲያውም ኢየሱስን የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በምኵራብ ውስጥ ዐወጀ።
\v 21 የሰሙትም ሁሉ በመደነቅ እንዲህ አሉ፤ “ይህ ሰው በኢየሩሳሌም ይህን ስም የሚጠሩትን ያጠፋው አይደለምን? የመጣውም አስሮ ወደ ሊቀ ካህናቱ ሊያቀርባቸው ነው።”
\v 22 ሳውል ግን ለመስበክ በረታ፣ በደማስቆ ይኖሩ የነበሩ አይሁድንም ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን በማረጋገጥ ግራ አጋባቸው።
\s5
\v 23 ከብዙ ቀን በኋላ፣ አይሁድ ሊገድሉት ዐሰቡ።
\v 24 ሳውል ግን ዐሳባቸውን ዐወቀባቸው። ሊገድሉት የከተማይቱን በሮች ቀንም ሌሊትም ይጠብቁ ነበር።
\v 25 ደቀ መዛሙርቱ ግን በግድግዳው በኩል በቅርጫት አወረዱት።
\s5
\v 26 ሳውል ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ በመጣ ጊዜ፣ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ለመገናኘት ሞከረ፤ ነገር ግን ደቀ መዝሙር መሆኑን በመጠራጠር ሁሉም ፈሩት።
\v 27 ይሁን እንጂ፣ በርናባስ ወስዶ ወደ ደቀ መዛሙርቱ አቀረበው። ሳውል ጌታን በመንገድ ላይ እንዴት እንዳየው፣ ጌታም እንደ ተናገረው፣ በኢየሱስ ስም ደማስቆ ውስጥ በድፍረት እንዴት እንደ ሰበከም ነገራቸው።
\s5
\v 28 ሳውል ኢየሩሳሌም ውስጥ ሲገባና ከዚያም ሲወጣ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተገናኘ። በጌታ ኢየሱስ ስም በድፍረት ተናገረ፤
\v 29 ከግሪክ አይሁድ ጋርም ተከራከረ፤ ሊገድሉት ሙከራ ማድረጋቸውን ግን አላቋረጡም።
\v 30 ወንድሞች ስለዚህ ባወቁ ጊዜ፣ ወደ ቂሣርያ አውርደው ወደ ጠርሴስ ላኩት።
\s5
\v 31 ከዚያም በኋላ የይሁዳ ሁሉ፣ የገሊላና የሰማርያ ቤተ ክርስቲያን ሰላም ነበራት፣ ታነጸችም፤ እግዚአብሔርን በመፍራትና በመንፈስ ቅዱስ መጽናናት ቤተ ክርስቲያን በቍጥር አደገች።
\v 32 ጴጥሮስም በየቦታው ሲዘዋወር፣ በልዳ ከተማ ወደሚኖሩ ቅዱሳንም ወረደ።
\s5
\v 33 እዚያም፣ ሽባ በመሆኑ ስምንት ዓመት የአልጋ ቊራኛ የነበረን ኤንያ የሚባለውን አንድ ሰው አገኘ።
\v 34 ጴጥሮስ፣ “ኤንያ ሆይ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈውስሃል፤ ተነሥና ዐልጋህን አንጥፍ” አለው። ወዲያውም ተነሣ።
\v 35 በልዳና በሰሮና የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ሰውየውን አዩትና ወደ ጌታ ተመለሱ።
\s5
\v 36 በኢዮጴም ጣቢታ የምትባል አንድ ደቀ መዝሙር ነበረች፤ የስሟ ትርጕም “ዶርቃ” ማለት ነው። ይች ሴት በመልካም ምግባርና ለድኾች በምታደርጋቸው የርኅራኄ ሥራዎች የተሞላች ነበረች።
\v 37 በዚያም ወቅት ታመመችና ሞተች፤ ዐጥበውም ሰገነት ላይ አስቀመጧት።
\s5
\v 38 ልዳ በኢዮጴ አጠገብ በመሆኑና ደቀ መዛሙርቱም የጴጥሮስን በዚያ መኖር ስለ ሰሙ፣ “ሳትዘገይ ወደ እኛ ና” ብለው በመለመን ሁለት ሰዎችን ወደ እርሱ ላኩ።
\v 39 ጴጥሮስም ተነሣና ከተላኩት ጋር ሄደ። እዚያ ሲደርስ፣ ወደ ሰገነቱ አወጡት። መበለታቱም ሁሉ ዶርቃ ከእነርሱ ጋር ሳለች ትለብሳቸው የነበሩትን ቀሚሶችና ልብሶች እያሳዩትና እያለቀሱ በአጠገቡ ቆሙ።
\s5
\v 40 ጴጥሮስ ሁሉንም ከክፍሉ አስወጣቸውና ተንበርክኮ ጸለየ፤ ከዚያም ወደ አስከሬኑ በመዞር፣ “ጣቢታ ሆይ፣ ተነሺ” አለ። ዐይኖቿን ከፈተች፤ ጴጥሮስንም ስታየው ተነሥታ ተቀመጠች።
\v 41 ጴጥሮስም እጇን ይዞ አነሣት፤ አማኞችንና መበለታቱን ጠርቶም በሕይወት እንዳለች ሰጣቸው።
\v 42 ይህ ጉዳይ በመላው ኢዮጴ የታወቀ ሆነ፤ ብዙ ሰዎችም በጌታ አመኑ።
\v 43 ጴጥሮስ በኢዮጴ ቍርበት ፋቂ ከነበረ ስምዖን ከሚባል ሰው ጋር ብዙ ቀን ቆየ።
\s5
\c 10
\cl ምዕራፍ 10
\p
\v 1 በቂሣርያ ከተማ ውስጥ የኢጣሊቄ ክፍለ ሰራዊት በሚባል የመቶ አለቃ የሆነ ቆርኔሌዎስ የሚባል ሰው ነበረ።
\v 2 እርሱም መንፈሳዊ፣ ከቤተ ሰቡ ጋር እግዚአብሔርን የሚያመልክ፣ ለአይሁድ ብዙ ገንዘብ የሚሰጥና ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር የሚጸልይ ሰው ነበረ።
\s5
\v 3 ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርሱ ሲመጣ በራእይ በግልጽ ታየው። መልአኩ፣ “ቆርኔሌዎስ!” አለው።
\v 4 ቆርኔሌዎስ መልአኩን አተኵሮ ተመለከተውና ፈርቶ እንዲህ አለ፤ “ጌታዬ ሆይ፣ ይህ ምንድን ነው?” መልአኩም መልሶ፣ “ጸሎትህና ምጽዋትህ በመታሰቢያነት ወደ እግዚአብሔር ደርሶአል።
\v 5 ጴጥሮስም ተብሎ የሚጠራውን ስምዖን የሚባለውን ሰውየ ለማስመጣት አሁን ወደ ኢዮጴ ከተማ ሁለት ሰዎችን ላክ።
\v 6 ሰውየው ቤቱ በባሕሩ አጠገብ ከሚገኝ ስምዖን ከሚባለው ከቆዳ ፋቂው ጋር አለ” አለው።
\s5
\v 7 ያነጋግረው የነበረው መልአክ እንደ ሄደ፣ ቆርኔሌዎስ ከሚያገለግሉት ወታደሮች መካከል እግዚአብሔርን ያመልክ የነበረ አንድ ወታደርንና ከቤት አሽከሮቹ ሁለቱን ጠራ።
\v 8 ቆርኔሌዎስ የሆነውን ሁሉ ነግሮአቸው ወደ ኢዮጴ ላካቸው።
\s5
\v 9 በሚቀጥለው ቀን ስድስት ሰዓት አካባቢ፣ በጕዞ ላይ ሳሉና ወደ ከተማዋ ሲቃረቡ፣ ጴጥሮስ ሊጸልይ ወደ ሰገነቱ ወጣ።
\v 10 ራበውና አንዳች ነገር ለመብላት ፈለገ፤ ነገር ግን ሰዎች ምግብ በማዘጋጀት ላይ ሳሉ፣ በተመስጦ ውስጥ ገባ፤
\v 11 ሰማይ ተከፍቶ፣ ትልቅ ሸማ የሚመስል አንድ መያዣ በአራቱ ጠርዞቹ ተይዞ ወደ ምድር ሲወርድም አየ።
\v 12 በውስጡም አራት እግር ያላቸው እንስሳት ሁሉና በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጡራን፣ የሰማይ ወፎችም ነበሩበት።
\s5
\v 13 “ጴጥሮስ ሆይ፣ ተነሥና ዐርደህ ብላ” የሚል ድምፅ ለጴጥሮስ መጣ።
\v 14 ጴጥሮስም፣ “ጌታ ሆይ፣ አይሆንም፤ ምክንያቱም እኔ ርኩስና አስጸያፊ የሆነ ምንም ነገር ፈጽሞ በልቼ አላውቅም” አለ።
\v 15 እንደገናም ድምፅ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ጴጥሮስ መጣ፤ “እግዚአብሔር ቅዱስ ያደረገውን ርኩስ ብለህ አትጥራው” የሚል ድምፅ።
\v 16 ይህም ሦስት ጊዜ ሆነ፤ ከዚያም መያዣው ወዲያው ወደ ሰማይ ተመልሶ ተወሰደ።
\s5
\v 17 ጴጥሮስ ያየው ራእይ ምን ትርጕም ሊኖረው እንደሚችል በጣም ግራ ገብቶት ሳለ፣ ወደ ቤት የሚያስሄደውን መንገድ ጠይቀው ካገኙ በኋላ እነሆ፣ ቆርኔሌዎስ የላካቸው ሰዎች በበሩ ፊት ለፊት ቆሙ።
\v 18 ድምፃቸውን ከፍ በማድረግም ጴጥሮስ የሚባለው ስምዖን በዚያ መኖሩንና አለመኖሩን ጠየቁ።
\s5
\v 19 ጴጥሮስ ስለ ራእዩ በማሰብ ላይ ሳለ፣ መንፈስ ቅዱስ ጴጥሮስን እንዲህ አለው፤ “እነሆ፣ ሦስት ሰዎች ይፈልጉሃል።
\v 20 ተነሥና ውረድ፤ ከእነርሱም ጋር ሂድ። ዐብረሃቸው ለመሄድ አትፍራ፤ ምክንያቱም የላክኋቸው እኔ ነኝ።”
\v 21 ስለዚህም ጴጥሮስ ወደ ሰዎቹ ወርዶ፣ “የምትፈልጉት ሰው እኔ ነኝ። የመጣችሁት ለምንድን ነው?” አላቸው።
\s5
\v 22 እነርሱም እንዲህ አሉት፤ "እግዚአብሔርን የሚያመልክ፣ በአይሁድ ሕዝብ ሁሉ ዘንድም የተመሰገነ ቆርኔሌዎስ የሚባል ጻድቅ ሰው፣ ወደ ቤቱ ሰው ልኮ እንዲያስመጣህ የእግዚአብሔር መልአክ ነገረው፤ እንዲህ ያደረገውም ከአንተ መልእክትን መስማት እንዲችል ነው።”
\v 23 ጴጥሮስም እንዲገቡና ከእርሱና ዐብረውት ከነበሩ ሰዎች ጋር እንዲቈዩ በእንግድነት ተቀበላቸው። በማግስቱ ጧት ጴጥሮስ ተነሣና ከእነርሱ ጋር ሄደ፤ በኢዮጴ ከነበሩት ወንድሞችም አንዳንዶቹ ዐብረውት ሄዱ።
\s5
\v 24 በሚቀጥለው ቀን ቂሣርያ ደረሱ። ቆርኔሌዎስ እየጠበቃቸው ነበር፤ ዘመዶቹንና የቅርብ ወዳጆቹንም ጠርቶ እንዲሰበሰቡ አደረገ።
\s5
\v 25 ጴጥሮስ ሲገባ፣ ቆርኔሌዎስ አግኝቶት እግሩ ላይ ወድቆ ሰገደለት።
\v 26 ነገር ግን ጴጥሮስ አነሣውና፣ “ተነሥ ቁም፤ እኔ ራሴም ሰው ነኝ” አለው።
\s5
\v 27 ጴጥሮስ ከቆርኔሌዎስ ጋር እየተነጋገረ ወደ ውስጥ ሲገባ፣ የተሰበሰቡ ብዙ ሰዎችን አገኘ።
\v 28 እንዲህም አላቸው፤ "አይሁዳዊ የሆነ ሰው ከሌላ ሕዝብ ከሆነ ጋር መገናኘት ወይም እርሱን መጎብኘት በሕግ እንደማይፈቀድለት እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። ነገር ግን እግዚአብሔር ማንንም ሰው ርኩስ ወይም አስጸያፊ ብዬ መጥራት እንደማይገባኝ ለእኔ አሳይቶኛል።
\v 29 ሲላክብኝ ሳልከራከር የመጣሁት ከዚህ የተነሣ ነው። ስለዚህ ለምን እንደ ላካችሁብኝ እጠይቃችኋለሁ።"
\s5
\v 30 ቆርኔሌዎስም እንዲህ አለ፤ “ከአራት ቀን በፊት ልክ በዚህ ሰዓት በዘጠኝ ሰዓት በቤቴ ውስጥ እጸልይ ነበር፤ እነሆም ነጭ ልብስ ለብሶ ፊት ለፊቴ ቆመና፣
\v 31 ‘ቆርኔሌዎስ ሆይ፣ ጸሎትህ በእግዚአብሔር ዘንድ ተሰምቶአል፤ ምጽዋትህም መታሰቢያ ሆኖልሃል።
\v 32 ስለዚህ ወደ ኢዮጴ ሰው ላክና ጴጥሮስም የሚባለውን ስምዖንን ወደ አንተ ጠርተህ አስመጣ። እርሱ በቆዳ ፋቂው በስምዖን ቤት በባሕር አጠገብ ተቀምጦአል’ አለኝ።
\v 33 ስለዚህ ወዲያው ላክሁብህ። አሁን መምጣትህ መልካም አደረግህ። አሁን እንግዲህ እኛ ሁላችን እግዚአብሔር እንድትናገር ያዘዘህን ሁሉ ለመስማት በእግዚአብሔር ፊት እንገኛለን።"
\s5
\v 34 ጴጥሮስም እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ “እግዚአብሔር ለማንም እንደማያዳላ በእውነት ተገንዝቤአለሁ።
\v 35 ይልቁን በማንኛውም ሕዝብ ውስጥ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ የጽድቅ ተግባራትንም የሚፈጽም ሁሉ በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት አለው።
\s5
\v 36 እግዚአብሔር በሁሉ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሰላምን የምሥራች ባወጀበት ጊዜ፣ ወደ እስራኤል ሕዝብ የላከውን መልእክት ታውቃላችሁ፦
\v 37 ዮሐንስ ካወጀው ጥምቀት በኋላ፣ በገሊላ በመጀመር በይሁዳ ሁሉ የታዩትን የተፈጸሙ ሁነቶችን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ፤
\v 38 ሁነቶቹም እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስና በኀይል እንዴት እንደ ቀባው የናዝሬቱን ኢየሱስን የሚመለከቱ ናቸው። ኢየሱስ መልካም እያደረገና ለዲያብሎስ የተገዙትን እየፈወሰ ዞረ፤ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና።
\s5
\v 39 በዕንጨት ላይ ሰቅለው የገደሉት ይህ ኢየሱስ ከአይሁድ አገርም በኢየሩሳሌምም ለፈጸማቸው ተግባራት ሁሉ እኛ ምስክሮች ነን።
\v 40 ይህን ሰው እግዚአብሔር በሦስተኛው ቀን አስነሣው፤ እንዲገለጥም አደረገው፤
\v 41 ይኸውም እግዚአብሔር አስቀድሞ መርጦአቸው ለነበሩ ምስክሮች እንጂ፣ ለሕዝቡ ሁሉ አይደለም፦ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ዐብረነው የበላንና የጠጣን እኛው ራሳችን ነን።
\s5
\v 42 ለሕዝቡ እንድንሰብክና በሕያዋንና በሙታን ላይ እንዲፈርድ፣ እግዚአብሔር የመረጠው ይህ እንደ ሆነ እንድንመሰክር አዘዘን።
\v 43 በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኀጢአትን ይቅርታ እንዲቀበል ነቢያት ሁሉ የሚመሰክሩት ስለ እርሱ ነው።”
\s5
\v 44 ጴጥሮስ እነዚህን ነገሮች ገና እየተናገረ ሳለ፣ መልእክቱን በሚሰሙት ሁሉ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው።
\v 45 ከተገረዙት ወገን የሆኑ አማኞች፦ ከጴጥሮስ ጋር የመጡትም ሁሉ ተደነቁ፤ ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ በአሕዛብም ላይ ወርዶ ነበር።
\s5
\v 46 እነዚህ አሕዛብ በሌሎች ቋንቋዎች ሲናገሩና እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ሰምተዋቸዋልና። ከዚያም በኋላ ጴጥሮስ መልሶ፣
\v 47 “እንደ እኛ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ እነዚህ ሰዎች እንዳይጠመቁ ማን ውሃ ሊከለክላቸው ይችላል?” አለ።
\v 48 በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲጠመቁም አዘዛቸው። ከዚያ በኋላ ከእነርሱ ጋር ጥቂት ቀን እንዲቈይ ጴጥሮስን ለመኑት።
\s5
\c 11
\cl ምዕራፍ 11
\p
\v 1 ሐዋርያትና በይሁዳ የነበሩት ወንድሞች አሕዛብ ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል ተቀብለው እንደ ነበር ሰሙ።
\v 2 ጴጥሮስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጥቶ በነበረ ጊዜ፣ ከመገረዝ ወገን የነበሩት ነቀፉት፤
\v 3 “ካልተገረዙ ወንዶች ጋር ተባብረሃል፣ አብረሃቸውም በልተሃል!” አሉት።
\s5
\v 4 ጴጥሮስ ግን እንዲህ ብሎ ጉዳዩን በዝርዝር ያብራራላቸው ጀመር፤
\v 5 እኔ በኢዮጴ ከተማ እጸልይ ነበር፤ በተመስጦም አራት ማዕዘን ያለው ታላቅ ሸማ የመሰለ ዕቃ መያዣ ከሰማይ ሲወርድ ራእይ ዐየሁ፤ ወደ እኔ ወረደ፣
\v 6 ትኵር ብዬ ተመለክትሁትና ስለ እርሱ ዐሰብሁ። አራት እግር ያላቸው የምድር እንስሳትን፣ አራዊትን፣ የሚሳቡ ፍጥረታትን፣ የሰማይ አዕዋፍንም ዐየሁ።
\s5
\v 7 በዚያን ጊዜ አንድ ድምፅ፣ “ጴጥሮስ ሆይ፣ ተነሣ፣ አርደህም ብላ!” ሲለኝ ሰማሁ።
\v 8 “ጌታ ሆይ፣ አይሆንም፣ ምክንያቱም ጸያፍ ወይም ርኩስ የሆነ ምንም ነገር ከቶ ወደ አፌ ገብቶ አያውቅም” አልሁ።
\v 9 ነገር ግን ድምፁ ዳግመኛ ከሰማይ፣ “እግዚአብሔር ንጹሕ ነው ያለውን አንተ ርኩስ ብለህ አትጥራው” ብሎ መለሰ።
\v 10 ይህም ሦስት ጊዜ ሆነ፤ ከዚያም ሁሉም ነገር እንደ ገና ወደ ሰማይ ተወሰደ።
\s5
\v 11 እነሆ፣ ወዲያውኑ እኛ በነበርንበት ቤት ፊት ለፊት ሦስት ሰዎች ቆመው ነበር፤ እነርሱም ከቂሣርያ ወደ እኔ የተላኩ ናቸው።
\v 12 መንፈስም ከእነርሱ ጋር እንድሄድ፣ ስለ እነርሱም ልዩነት እንዳላደርግ አዘዘኝ። እነዚህ ስድስት ወንድሞች አብረውኝ ሄዱ፤ ወደ ሰውዬውም ቤት ገባን።
\v 13 እርሱም መልአክ በቤቱ ቆሞ እንዳየና እንዲህ እንዳለውም ነገረን፤ “ወደ ኢዮጴ ሰዎችን ላክና ሌላው ስሙ ጴጥሮስ የሆነውን፣ ስምዖንን አስመጣ።
\v 14 አንተና ቤተ ሰቦችህ ሁሉ የምትድኑበትን መልእክት ይነግርሃል።”
\s5
\v 15 ለእነርሱ መናገር እንደ ጀመረና ልክ በመጀመሪያ በእኛ ላይ እንደ ሆነው፣ መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ ወረደ።
\v 16 “ዮሐንስ በእርግጥ በውሃ አጥምቆ ነበር፤ እናንተ ግን በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ” ብሎ እንደ ተናገረ፣ የጌታን ቃሎች አስታወስሁ።
\s5
\v 17 እኛ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ባመንን ጊዜ እንደ ሰጠን ያለ ስጦታ እግዚአብሔር ለእነርሱ ከሰጣቸው እንግዲያ፣ እግዚአብሔርን እቃወም ዘንድ እኔ ማን ነበርሁ?”
\v 18 እነርሱ እነዚህን ነገሮች በሰሙ ጊዜ፣ መልስ አልሰጡም፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን አመስግነው፣ “እግዚአብሔር ለአሕዛብ ለሕይወት የሚሆን ንስሓን ደግሞ ሰጥቷቸዋል” አሉ።
\s5
\v 19 ስለዚህ በእስጢፋኖስ መሞት የተጀመረው ሥቃይ ከኢየሩሳሌም የበተናቸው እነዚህ አማኞች እስከ ፊንቄ፣ ቆጵሮስና አንጾኪያ ድረስ ሄዱ። ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን መልእክት ለአይሁድ ብቻ እንጂ ለሌላ ለማንም አልተናገሩም።
\v 20 ነገር ግን ከቆጵሮስና ከቀሬና የነበሩ ሰዎች አንዳንዶቹ ወደ አንጾኪያ መጥተው ለግሪኮች ተናገሩ፤ ጌታ ኢየሱስንም ሰበኩላቸው።
\v 21 የጌታም እጅ ከእነርሱ ጋር ነበረ፤ በቍጥ ብዛት ያላቸው ሰዎች አምነው ወደ ጌታ ዘወር አሉ።
\s5
\v 22 ስለ እነርሱ ወሬ በኢየሩሳሌም ባለችው ጉባኤ ተሰማ፤ በርናባስንም እስከ አንጾኪያ ላኩት።
\v 23 እርሱም መጥቶ የእግዚአብሔርን ስጦታ ባየ ጊዜ፣ ደስ አለው። ከሙሉ ልባቸው ከጌታ ጋር እንዲኖሩ ሁላቸውንም አበረታታቸው።
\v 24 ምክንያቱም እርሱ መንፈስ ቅዱስና እምነት የሞላበት በጎ ሰው ነበር፤ ብዙ ሕዝብም ወደ ጌታ ተጨመሩ።
\s5
\v 25 ከዚያም በርናባስ ሳውልን ሊፈልግ ወደ ጠርሴስ ወጣ።
\v 26 ባገኘውም ጊዜ፣ ወደ አንጾኪያ አመጣው። እንዲህም ሆነ፣ አንድ ዓመት ሙሉ በቤተ ክርስቲያን አብረው ተሰበሰቡ፣ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ። ደቀ መዛሙርቱ በመጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ።
\s5
\v 27 በእነዚያ ቀናትም አንዳንድ ነቢያት ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ወረዱ።
\v 28 ከእነርሱ አንዱ አጋቦስ የተባለው፣ ተነሥቶ ቆመና በመላው ዓለም ላይ ታላቅ ራብ እንደሚሆን በመንፈስ አመለከተ። ይህም በቀላውዴዎስ ዘመን ሆነ።
\s5
\v 29 ስለ ሆነም፣ ደቀ መዛሙርቱ እያንዳንዳቸው እንደ ዐቅማቸው በይሁዳ ላሉት ወንድሞች እርዳታ ለመላክ ወሰኑ።
\v 30 ይህንም አደረጉ፤ በበርናባስና በሳውል እጅ ለሽማግሌዎቹ ገንዘብ ላኩ።
\s5
\c 12
\cl ምዕራፍ 12
\p
\v 1 በዚያን ጊዜ ንጉሡ ሄሮድስ ሊያሠቃያቸው ከቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን ያዛቸው።
\v 2 የዮሐንስን ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው።
\s5
\v 3 ይህ አይሁድን ደስ እንዳሰኛቸው ካየ በኋላ፣ ጴጥሮስንም ያዘው። ይህ የሆነው በቂጣ በዓል ጊዜ ነበር።
\v 4 ከያዘውም በኋላ ወደ ወኅኒ አገባው፤ እንዲጠብቁትም እያንዳንዳቸው አራት ወታደሮች ያሏቸው ቡድኖችን መደበ፤ ከፋሲካ በኋላ ወደ ሕዝቡ ሊያቀርበው ዐስቦ ነበር።
\s5
\v 5 ጴጥሮስም በወኅኒው ይጠበቅ ነበር፤ ነገር ግን ስለ እርሱ ጉባኤው ወደ እግዚአብሔር አጥብቆ ይጸልይ ነበር።
\v 6 ሄሮድስ ሊያወጣው ባሰበበት በዚያ ሌሊት፣ ጴጥሮስ በሁለት ሰንሰለቶች ታስሮ በሩን በሚጠብቁ ሁለት ወታደሮች መካከል ተኝቶ ነበር።
\s5
\v 7 እነሆም የጌታ መልአክ በድንገት በአጠገቡ ታየ፣ በክፍሉም ብርሃን በራ። መልአኩ የጴጥሮስን ጎን መትቶ ቀሰቀሰውና፣ “ፈጥነህ ተነሥ” አለው። በዚያን ጊዜ ሰንሰለቶቹ ከእጆቹ ወደቁ።
\v 8 መልአኩ ጴጥሮስን፣ “ልብስህን ልበስ ጫማህንም አድርግ” አለው። ጴጥሮስም እንዲሁ አደረገ። መልአኩ፣ “መደረቢያህን ልበስና ተከተለኝ” አለው።
\s5
\v 9 ጴጥሮስም መልአኩን ተከትሎ ወደ ውጭ ወጣ። መልአኩ ያደረገው ነገር በእውን እንደ ሆነ ጴጥሮስ አላወቀም። ራእይ ያየ መሰለው።
\v 10 የመጀመሪያውንና ሁለተኛውን ዘብ እንዳለፉ፣ ወደ ከተማይቱ ወደሚያወጣው የብረት በር ደረሱ፤ እርሱም ዐውቆ ተከፈተላቸው። እነርሱም ወጥተው በአንድ መንገድ በኩል ወረዱ፤ መልአኩም ወዲያውኑ ተለየው።
\s5
\v 11 ጴጥሮስም ራሱን ሲያውቅ፣ “ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅ፣ የአይሁድ ሕዝብም ይጠብቁት ከነበረው ሁሉ እንዳዳነኝ አሁን ዐወቅሁ” አለ።
\v 12 ጴጥሮስ ይህን ከተገነዘበ በኋላ፣ ማርቆስ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ዮሐንስ እናት ቤት መጣ፤ በዚያ ብዙ ምእመናን ተሰብስበው እየጸለዩ ነበር።
\s5
\v 13 የደጁን በር ባንኳኳ ጊዜ፣ ሮዴ የሚሏት የቤት ሠራተኛ ልትከፍትለት መጣች።
\v 14 የጴጥሮስን ድምፅ ባወቀች ጊዜ ከደስታዋ የተነሣ በሩን መክፈት አቃታት፤ ይልቁን ሮጣ ወደ ቤት ገባች፤ ጴጥሮስ ከበሩ ውጭ መቆሙን ተናገረች።
\v 15 ምእመናኑም፣ “ዐብደሻል” አሏት። እርሷ ግን እንዲሁ ነው ብላ በዐሳብዋ ጸናች። እነርሱም፣ “የእርሱ መልአክ ነው” አሉ።
\s5
\v 16 ጴጥሮስ ግን ማንኳኳቱን ቀጠለ፤ በሩን በከፈቱ ጊዜ፣ ዐይተውት ተደነቁ።
\v 17 ጴጥሮስ ዝም እንዲሉ በእጁ ምልክት ሰጣቸው፤ ጌታ ከወኅኒ እንዴት እንዳወጣውም ነገራቸው። “እነዚህን ነገሮች ለያዕቆብና ለወንድሞች ንገሩ” አላቸው። ከዚያም ቤት ወጥቶ ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ።
\s5
\v 18 በማግስቱም፣ ጴጥሮስን በሚመለከት ስለ ተከሠተው ነገር በወታደሮች መካከል መደናገጥ ሆነ።
\v 19 ሄሮድስ ጴጥሮስን ፈልጎ ሊያገኘው አልቻለም፤ ጠባቂዎችን መርምሮ እንዲገደሉ አዘዘ። ከዚያም ጴጥሮስ ከይሁዳ ወደ ቂሣርያ ወርዶ በዚያ ተቀመጠ።
\s5
\v 20 ሄሮድስም በጢሮስና በሲዶና ሰዎች ላይ እጅግ ተቈጥሮ ነበር። የጢሮስና የሲዶና ሰዎች ተሰብስበው ወደ እርሱ ሄዱ። እንዲረዳቸው የንጉሡን ረዳት ብላስጦስን እሺ አሰኙት። ከዚያም ዕርቀ ሰላም እንዲወርድ ጠየቁ፤ ምክንያቱም አገራቸው ከንጉሡ አገር ምግብ ያገኝ ነበር።
\v 21 በቀጠሮ ቀን ሄሮድስ ልብሰ መንግሥት ለብሶ በዙፋን ላይ ተቀመጠና ንግግር አደረገላቸው።
\s5
\v 22 ሕዝቡም፣ “ይህ የአምላክ ድምፅ ነው እንጂ፣ የሰው አይደለም!” ብለው ጮኹ።
\v 23 ሄሮድስ ለእግዚአብሔር ክብር ስላልሰጠ፣ ወዲያውኑ የጌታ መልአክ ቀሠፈው፤ በትል ተበልቶም ሞተ።
\s5
\v 24 የእግዚአብሔር ቃል ግን እያደገና እየሰፋ ሄደ።
\v 25 በርናባስና ሳውል ለኢየሩሳሌም የነበራቸውን ተልእኮ ከፈጸሙ በኋላ፣ ተመለሱ፤ ማርቆስ የተባለውንም ዮሐንስን ይዘው ሄዱ።
\s5
\c 13
\cl ምዕራፍ 13
\p
\v 1 በአንጾኪያም ባለችው ጉባኤ አንዳንድ ነቢያትና መምህራን ነበሩ። እነርሱም በርናባስ፣ ኔጌር የተባለው ስምዖን፣ የቀሬናው ወንድሙ ምናሔ፣ ሳውልም ነበሩ።
\v 2 ጌታን እያመለኩና እየጾሙ እያሉ፣ መንፈስ ቅዱስ፣ “ለጠራኋቸው ሥራ በርናባስንና ሳውልን ለዩልኝ” አለ።
\v 3 ጉባኤው ከጾመ፣ ከጸለየና እጅ ከጫነም በኋላ አሰናበታቸው።
\s5
\v 4 በርናባስና ሳውልም ለመንፈስ ቅዱስ ታዘዙና ወደ ሴሌውቅያ ወረዱ፤ ከዚያም በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ደሴት ሄዱ።
\v 5 በስልማና ከተማ በነበሩ ጊዜም፣ በአይሁድ ምኵራቦች የእግዚአብሔርን ቃል ሰበኩ። ማርቆስ የተባለው ዮሐንስ ሊረዳቸው አብሯቸው ነበር።
\s5
\v 6 በደሴቲቱም ሁሉ እስከ ጳፉ በሄዱ ጊዜ፣ ስሙ በርያሱስ የተባለ፣ አንድ አይሁዳዊ የሐሰት ነቢይና አስማተኛ አገኙ።
\v 7 ይህ አስማተኛ አስተዋይ ሰው ከነበረው ሰርግዮስ ጳውሎስ ከተባለው አገረ ገዥ ጋር ተባበረ። ይህ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ስለ ፈለገ፣ በርናባስናን ሳውልን ጠራ።
\v 8 ነገር ግን፣ “አስማተኛው” ኤልማስ ስሙ ሲተረጎም እንዲሁ ነውና ተቃወማቸው፤ አገረ ገዡን ከእምነቱ ለመመለስ ሞከረ።
\s5
\v 9 ደግሞ ጳውሎስ የተባለው ሳውል ግን በመንፈስ ቅዱስ ተሞላ፤ ትኵር ብሎም ተመለከተውና
\v 10 እንዲህ አለው፤ “አንተ የዲያብሎስ ልጅ፣ ክፋትና ተንኮል ሁሉ የሞላብህ ነህ። የጽድቅ ሁሉ ጠላት ነህ። የቀናችውን የጌታን መንገድ ማጣመምህን አታቆምምን?
\s5
\v 11 አሁንም ተመልከት፤ የጌታ እጅ በአንተ ላይ ነችና ትታወራለህ። ለጥቂት ጊዜ ፀሐይን አታይም።” ወዲያውኑ በኤልማስ ጨለማና ጭጋግ ወደቀበት፤ እጁንም ይዘው እንዲመሩት ሰዎችን እየጠየቀ ይዘዋወር ጀመር።
\v 12 አገረ ገዡ የሆነውን ካየ በኋላ፣ ስለ ኢየሱስ በቀረበው ትምህርት ስለ ተደነቀ፣ አመነ።
\s5
\v 13 ጳውሎስና ጓደኞቹም በመርከብ ከጳፉ ተነሥተው በጵንፍልያ ወዳለችው ወደ ጴርጌን መጡ። ዮሐንስ ግን ትቶአቸው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።
\v 14 ጳውሎስና ጓደኞቹ ከጴርጌን ተጕዘው የጲስድያ ወደ ሆነችው አንጾኪያ መጡ። በዚያ በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገብተው ተቀመጡ።
\v 15 ሕግና ነቢያት ከተነበቡ በኋላ፣ የምኵራብ አለቆች፣ “ወንድሞች ሆይ፣ እዚህ ላሉት ሕዝብ የሚሆን የሚያበረታታ መልእክት ካላችሁ፣ ተናገሩ” በማለት መልእክት ላኩላቸው።
\s5
\v 16 ጳውሎስም ቆመና በእጁ ምልክት ሰጥቶ እንዲህ አለ፤ “የእስራኤል ሰዎችና እናንተ እግዚአብሔርን የምታከብሩ፣ ስሙ።
\v 17 የዚህ የእስራኤል ሕዝብ አምላክ አባቶቻችንን መርጦ በግብፅ ይኖሩ በነበሩበት ጊዜ፣ ሕዝቡን አበዛላቸው፤ በተዘረጋችም ክንድ መርቶ ከዚያ አወጣቸው።
\v 18 ለአርባ ዓመታት ገደማ በምድረ በዳ ታገሣቸው።
\s5
\v 19 በከነዓን ምድርም ሰባት ሕዝቦችን ካጠፋ በኋላ፣ ምድራቸውን ለሕዝባችን ርስት አድርጎ ሰጠ።
\v 20 እነዚህ ሁነቶች ሁሉ በአራት መቶ ሃምሳ ዓመታት ውስጥ ተፈጸሙ። ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ በኋላ፣ እግዚአብሔር እስከ ነቢዩ ሳሙኤል ድረስ መሳፍንትን ሰጣቸው።
\s5
\v 21 ከዚህ በኋላ፣ ሕዝቡ ንጉሥ ይንገሥልን ብለው ጠየቁ፤ ስለሆነም፣ እግዚአብሔር ከብንያም ነገድ የሆነውን የቂስን ልጅ ሳኦልን ለአርባ ዓመታት ሰጣቸው።
\v 22 ከዚያም እግዚአብሔር እርሱን ከንጉሥነት ከሻረው በኋላ፣ ንጉሣቸው እንዲሆን ዳዊትን አስነሣ። እግዚአብሔር፣ ‘እንደ ልቤ የሆነውን የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ፤ እርሱ እኔ የምፈልገውን ሁሉ ያደርጋል’ በማለት ስለ ዳዊት ተናግሮ ነበር።
\s5
\v 23 ከዚህም ሰው ዘር እግዚአብሔር ተስፋ እንደ ሰጠ አዳኝ ኢየሱስን ለእስራኤል አመጣ።
\v 24 ይህ መሆን የጀመረው ኢየሱስ ከመምጣቱ በፊት፣ ዮሐንስ መጀመሪያ ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የንስሐን ጥምቀት ባወጀ ጊዜ ነው።
\v 25 ዮሐንስ ሥራውን እንደ ጨረሰ እንዲህ አለ፤ ‘ማን እንደ ሆንሁ ታስባላችሁ? እኔ እርሱ አይደለሁም። ነገር ግን ስሙ፤ የጫማውን ማሰሪያ መፍታት ከማይገባኝ ከእኔ በኋላ እርሱ ይመጣል።’
\s5
\v 26 ወንድሞች፣ የአብርሃም ዘር ልጆች፣ እግዚአብሔርንም የምታመልኩ ሆይ፣ የዚህ ድነት መልእክት የተላከው ለእኛ ነው።
\v 27 በኢየሩሳሌም የሚኖሩ፣ አለቆቻቸውም በእርግጥ ኢየሱስን አላወቁትም፤ በየሰንበቱ የሚነበበውን የነቢያትን ድምፅም በእውነት አልተረዱም፤ ስለ ሆነም በኢየሱስ ላይ ሞት በመፍረድ የነቢያትን ቃል ፈጸሙ።
\s5
\v 28 ምንም እንኳ በእርሱ ላይ ለሞት የሚያበቃ ምክንያት ባያገኙም፣ እንዲገድለው ጲላጦስን ለመኑት።
\v 29 ስለ እርሱ የተጻፈውን ሁሉ በፈጸሙ ጊዜም፣ ከዕንጨት ላይ አውርደው በመቃብር አኖሩት።
\s5
\v 30 እግዚአብሔር ግን ከሙታን አስነሣው።
\v 31 ከእርሱ ጋር ከገሊላ ወደ ኢየሩሳሌም የወጡት ብዙዎች ለአያሌ ቀናት ዐዩት። እነዚህ ሰዎች አሁን ለሕዝቡ የሚናገሩ የእርሱ ምስክሮች ናቸው።
\s5
\v 32 ስለ ሆነም እኛ ለአባቶቻችን ስለ ተሰጠው ተስፋ የሚናገር የምሥራች እናመጣላችኋለን፤
\v 33 ኢየሱስን ከሙታን በማስነሣት እግዚአብሔር እነዚህን ተስፋዎች ለእኛ ለልጆቻቸው ጠብቆአል። ይህም ደግሞ በሁለተኛው መዝሙር፦ ‘አንተ ልጄ ነህ፣ እኔ ዛሬ ወለድሁህ’ ተብሎ የተጻፈ ነው።’
\v 34 ደግሞም ሥጋው እንዳይበሰብስ ከሙታን እንዳስነሣው፦ ‘የተቀደሰውንና እውነተኛውን የዳዊት በረከት እሰጥሃለሁ’ ብሎ ተናግሯል።
\s5
\v 35 በሌላ መዝሙርም፣ ‘ቅዱስህ መበስበስን እንዲያይ አትፈቅድም’ የሚለው ስለዚህ ነው።
\v 36 ዳዊትም በዘመኑ የእግዚአብሔርን ዐሳብ አገልግሎ አንቀላፋ፤ ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ፤ መበስበስንም ዐየ።
\v 37 እግዚአብሔር ያስነሣው ኢየሱስ ግን መበስበስን አላየም።
\s5
\v 38 ስለ ሆነም ወንድሞች ሆይ፣ በዚህ ሰው በኩል የኃጢአት ይቅርታ እንደ ተሰበከላችሁ ይህ ለእናንተ የታወቀ ይሁን።
\v 39 በሙሴም ሕግ እንድትጸድቁበት ከማይቻላችሁ ሁሉ፣ በእርሱ የሚያምን ሁሉ ጸድቆአል።
\s5
\v 40 እንግዲያው ነቢያት እንዲህ ሲሉ የተናገሩለት ነገር እንዳይደርስባችሁ ተጠንቀቁ፦
\v 41 ‘እናንተ የምትንቁ፣ ተመልከቱ፤ ተደነቁ፣ ጥፉም፤ አንድ ስንኳ ቢነግራችሁ ከቶ የማታምኑትን ሥራ፣ በዘመናችሁ እሠራለሁና።’”
\s5
\v 42 ጳውሎስና በርናባስ እንደ ወጡ፣ በሚቀጥለው ሰንበት ይህንኑ ቃል ደግመው እንዲናገሩ ሕዝቡ ለመኑአቸው።
\v 43 የምኵራቡ ስብሰባ እንዳበቃም፣ ከአይሁድና ወደ ይሁዲነት ከገቡ ከሚያመልኩ ብዙዎቹ፣ በእግዚአብሔር ጸጋ እንዲጸኑ የመከሩአቸውን ጳውሎስና በርናባስን ተከተሉአቸው።
\s5
\v 44 በሚቀጥለውም ሰንበት፣ ጥቂቶች ሲቀሩ፣ መላው ከተማ የጌታን ቃል ለመስማት አንድ ላይ ተሰበሰበ።
\v 45 አይሁድ ሕዝቡን ባዩ ጊዜ፣ ቅንዓት ሞላባቸውና ጳውሎስ የተናገረውን ተቃወሙ፣ ሰደቡትም።
\s5
\v 46 ጳውሎስና በርናባስ በድፍረት ተናገሩ፤ እንዲህም አሉ፤ “የእግዚአብሔር ቃል መጀመሪያ ለእናንተ መነገሩ አስፈላጊ ነበር። ቃሉን ከራሳችሁ ስትገፉትና ለዘላለም ሕይወት የተገባችሁ እንዳልሆናችሁ ራሳችሁን ስትቈጥሩ ዐይተናችሁ፣ ወደ አሕዛብ ዘወር የምንል መሆናችንን ተመልከቱ።
\v 47 ጌታ፣ ‘እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ለድነት ትሆን ዘንድ፣ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ’” በማለት አዞናልና።
\s5
\v 48 አሕዛብ ይህን እንደ ሰሙ ደስ አላቸው። የጌታንም ቃል አከበሩ። ለዘላለም ሕይወት የተመረጡትም አመኑ።
\v 49 የጌታም ቃል በአገሩ ሁሉ ተስፋፋ።
\s5
\v 50 አይሁድ ግን የሚያመልኩትን ታዋቂ ሴቶችን፣ የከተማይቱን ታላላቅ ወንዶችንም ቀሰቀሱ። በጳውሎስና በበርናባስ ላይም ስደት አስነሥተው ከከተማቸው ዳርቻ ወዲያ አውጥተው ጣሏቸው።
\v 51 ጳውሎስና በርናባስ ግን የእግራቸውን ትቢያ አራገፉባቸው። ከዚያም ወደ ኢቆንዮን ከተማ ሄዱ።
\v 52 ደቀ መዛሙርቱም ደስታና መንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ነበር።
\s5
\c 14
\cl ምዕራፍ 14
\p
\v 1 በኢቆንዮንም እንዲህ ሆነ ፤ ጳውሎስና በርናባስ ወደ አይሁድ ምኵራብ አብረው ገብተው፣ ከአይሁድና ከግሪክ ብዙ ሰዎች እስኪያምኑ ድረስ ተናገሩ።
\v 2 ነገር ግን ማመን ያልፈለጉ አይሁድ የአሕዛብን ልብ በመቀስቀስ በወንድሞች ላይ በክፋት አነሣሡአቸው።
\s5
\v 3 ጳውሎስና በርናባስም በጌታ ኀይል በድፍረት እየተናገሩ ረዘም ላለ ጊዜ በዚያ ተቀመጡ፤ ጌታም ስለ ጸጋው የሚነገረውን መልእክት በማስረጃ ለመደገፍ ጳውሎስና በርናባስ ምልክትና ድንቅ በእጃቸው እንዲደረግ ሰጠ።
\v 4 የከተማዋ አብዛኛው ሕዝብ ግን፣ አንዳንዱ አይሁድን በመደገፍ፣ ሌላው ደግሞ ከሐዋርያት ጋር በመቆም ተከፋፈሉ።
\s5
\v 5 አሕዛብና አይሁድ ጳውሎስንና በርናባስን እንዲያንገላቷቸውና በድንጋይም እንዲወግሯቸው አለቆቻቸውን በማሳመን ጥረት ማድረጋቸውን
\v 6 በተረዱ ጊዜ፣ ወደ ሊቃኦንያ ከተሞች፣ ወደ ልስጥራና ወደ ደርቤ፣ እንዲሁም በአካባቢው ወዳለው ስፍራ ሸሹ፤
\v 7 በዚያም ወንጌልን ይሰብኩ ነበር።
\s5
\v 8 በእግሩ መቆም የማይችልና ሽባ ከእናቱም ማሕፀን ጀምሮ አንካሳ የሆነ አንድ ሰው ተቀምጦ ነበር።
\v 9 ይህ ሰው ጳውሎስ ሲናገር ሰማ። ጳውሎስም ዐይኑን ተከትሎ ይህን ሰው ሲመለከት ለመዳን የሚያስችል እምነት እንዳለው አየ።
\v 10 ስለዚህ ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “ቀጥ ብለህ በእግርህ ቁም” አለው፤ ሰውየውም ብድግ ብሎ ተነሣና ወዲያ ወዲህ ይመላለስ ጀመር።
\s5
\v 11 ሕዝቡም ጳውሎስ ያደረገውን ባዩ ጊዜ፣ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፣ በሊቃኦንኛ ቋንቋ፣ «አማልክት በሰዎች መልክ ወደ እኛ ወርደዋል» አሉ።
\v 12 ስለዚህም በርናባስን «ድያ» አሉት፤ ጳውሎስም ዋነኛ ተናጋሪ ስለ ነበር፣ «ሄርሜን» አሉት።
\v 13 ቤተ ጣዖቱ ከከተማው ውጭ የነበረው የድያ ካህን በሬዎችንና የአበባ ጕንጕን ይዞ ወደ ከተማይቱ በር መጣ፤ እርሱና ሕዝቡም ለእነ ጳውሎስ መሥዋዕት ሊያቀርቡላቸው ፈለጉ።
\s5
\v 14 ነገር ግን ሐዋርያቱ፣ ባርናባስና ጳውሎስ ይህን በሰሙ ጊዜ፣ ልብሳቸውን ቀደው በመጮኽ፣ ፈጥነው ወደ ሕዝቡ መካከል ገቡ፤
\v 15 እንዲህም አሉ፤ «እናንተ ሰዎች፣ ለምን እነዚህን ነገሮች ታደርጋላችሁ? እኛኮ እንደ እናንተው ዐይነት ስሜት ያለን ሰዎች ነን፤ ወደ እናንተም የመጣነው ከእነዚህ ከንቱ ነገሮች፦ ሰማያትን፣ ምድርንና ባሕርን፣ በውስጣቸውም የሚኖሩትን ሁሉ ወደ ፈጠረ፣ ወደ ሕያው እግዚአብሔር እንድትመለሱ የምሥራች ቃል ይዘን ነው።
\v 16 እግዚአብሔር ባለፉት ዘመናት አሕዛብን ሁሉ በገዛ መንገዳቸው እንዲሄዱ ተዋቸው።
\s5
\v 17 ይሁን እንጂ፣ ራሱን ያለ ምስክር አልተወም፤ ምክንያቱም መልካም ሥራ በመሥራት የሰማይን ዝናብና ፍሬያማ ወቅቶችን ሰጥቶአችኋል፤ ልባችሁንም በምግብና በርካታ ሞልቷል።"
\v 18 ጳውሎስና በርናባስ እንደዚህ እየተናገሩም እንኳ፣ ሕዝቡ እንዳይሠዉላቸው መከልከሉ ቀላል አልነበረም።
\s5
\v 19 ይልቁንም አንዳንድ አይሁድ ከአንጾኪያና ከኢቆንዮን መጥተው ሕዝቡን በማግባባት ጳውሎስን በድንጋይ ወገሩት፤ የሞተ ስለ መሰላቸውም በመሬት ላይ ጎትተው ከከተማው አወጡት።
\v 20 ይሁን እንጂ፣ ደቀ መዛሙርቱ አብረውት ቆመው ሳሉ፣ ተነሥቶ ወደ ከተማው ገባ። በማግስቱም ከበርናባስ ጋር ወደ ደርቤ ሄደ።
\s5
\v 21 በዚያም ከተማ ወንጌልን ሰብከው ብዙ ደቀ መዛሙርትን ካፈሩ በኋላ፣ ወደ ልስጥራ፣ ወደ ኢቆንዮንና ወደ አንጾኪያ ተመለሱ።
\v 22 የደቀ መዛሙርቱንም ልብ እያበረቱ በእምነት እንዲጸኑ መከሯቸው። ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት በብዙ መከራ ውስጥ ማለፍ እንዳለብንም ነገሯቸው።
\s5
\v 23 ጳውሎስና በርናባስ በአማኞች ጉባኤ ሁሉ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ከሾሙ በኋላ፣ ላመኑበት ጌታ በጾምና በጸሎት ዐደራ ሰጡአቸው።
\v 24 ከዚያም በጲስድያ አድርገው ወደ ጵንፍልያ መጡ።
\v 25 ቃሉን በጴርጌን ከተናገሩ በኋላም ወደ አጣሊያ ወረዱ።
\v 26 ለፈጸሙት ሥራ ከዚህ ቀደም ለእግዚአብሔር ጸጋ ወደ ተሰጡበት፣ወደ አንጾኪያ በመርከብ ሄዱ።
\s5
\v 27 አንጾኪያ ደርሰው፣ ጉባኤውን በአንድነት ከሰበሰቡ በኋላም፣ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ሆኖ የሠራውን ሁሉና ለአሕዛብም የእምነትን በር እንዴት እንደ ከፈተላቸው ተናገሩ።
\v 28 በዚያም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ረጅም ጊዜ ቆዩ።
\s5
\c 15
\cl ምዕራፍ 15
\p
\v 1 አንዳንድ ሰዎች ከአይሁድ ወደ አንጾኪያ ወርደው፣ «በሙሴ ሥርዓት መሠረት ካልተገረዛችሁ መዳን አትችሉም» በማለት ወንድሞችን አስተማሯቸው።
\v 2 ጳውሎስና በርናባስም ከእነርሱ ጋር ጥልና ክርክር በገጠሙ ጊዜ፣ ጳውሎስና በርናባስ እንዲሁም ሌሎች ሰዎች ስለዚህ ጉዳይ በኢየሩሳሌም ወደ ነበሩ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች እንዲወጡ ወንድሞች ወሰኑ።
\s5
\v 3 ስለዚህ በቤተ ክርስቲያን ተልከው፣ በፊንቄና በሰማርያ በኩል አድርገው ሲሄዱ፣ የአሕዛብን መለወጥ እያወጁ ዐለፉ፤ ይህም ወንድሞችን ሁሉ እጅግ ደስ አሰኛቸው።
\v 4 ወደ ኢየሩሳሌም በመጡ ጊዜም፣ ቤተ ክርስቲያን፣ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች በደስታ ተቀበሏቸው፤ እነ ጳውሎስም እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ሆኖ የሠራውን ሁሉ ነገሯቸው።
\s5
\v 5 ከፈሪሳውያን ወገን ያመኑ አንዳንድ ሰዎች ግን ተነሥተው፣ «እነርሱን መግረዝና የሙሴንም ሕግ እንዲጠብቁ ማዘዝ ያስፈልጋል» አሉ።
\v 6 ስለዚህ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ይህን ጉዳይ ለማየት ተሰበሰቡ።
\s5
\v 7 ከብዙ ጭቅጭቅ በኋላ ጴጥሮስ ተነሥቶ ቆመና እንዲህ አለ፦ «ወንድሞች ሆይ፣ አሕዛብ የወንጌልን ቃል ከአፌ እንዲሰሙና እንዲያምኑ፣ እግዚአብሔር ከጥቂት ጊዜያት በፊት ከእናንተ መካከል እኔን እንደ መረጠኝ ታውቃላችሁ።»
\v 8 ልብን የሚያውቅ አምላክ፣ ለእኛ እንዳደረገው ሁሉ፣ ለእነርሱም መንፈስ ቅዱስን በመስጠት መሰከረላቸው፤
\v 9 በእኛና በእነርሱ መካከልም ልባቸውን በእምነት በማንጻት ልዩነት አላደረገም።
\s5
\v 10 እንግዲህ አባቶቻችንና እኛ መሽከም ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ በመጫን ለምን እግዚአብሔርን ትፈታተናላችሁ?
\v 11 ነገር ግን እኛም በጌታ በኢየሱስ ጸጋ እንደ እነርሱ እንደምንድን እናምናለን።»
\s5
\v 12 በርናባስና ጳውሎስ እግዚአብሔር በእነርሱ አማካይነት በአሕዛብ መካከል ስለ ሠራው ምልክትና ድንቅ ሲናገሩ፣ ሕዝቡ ሁሉ በጸጥታ አደመጡ።
\s5
\v 13 ንግግራቸውንም በጨረሱ ጊዜ፣ ያዕቆብ እንዲህ ሲል መለሰ፤ «ወንድሞች ሆይ፣ አድምጡኝ።
\v 14 እግዚአብሔር ለስሙ የሚሆንን ሕዝብ ከእነርሱ መካከል ይወስዱ ዘንድ፣ አሕዛብን በመጀመሪያ በጸጋ እንደ ረዳ ስምዖን ተናግሮአል።
\s5
\v 15 የነቢያት ቃል ከዚህ ጋር ይስማማል እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፤
\v 16 ከእነዚህ ነገሮች በኋላ እመለሳለሁ፤ ፍርስራሹንም መልሼ እተክላለሁ፤ እንደገናም ዐድሳለሁ፤
\v 17 ይኸውም የተረፉት ሰዎችና በስሜ የተጠሩ አሕዛብ፣ እግዚአብሔርን እንዲፈልጉ ነው።
\v 18 እነዚህ ጥንታዊ ነገሮች እንዲታወቁ የሚያደርግ ጌታ የሚለው ይህን ነው።
\s5
\v 19 ስለዚህ የእኔ ዐሳብ ከአሕዛብ ወደ እግዚአብሔር የተመለሱትን እንዳናስጨንቃቸው ነው፤
\v 20 ነገር ግን በጣዖታት ከመርከስ፣ ከዝሙት፣ ከታነቀና ከደም እንዲርቁ እንጻፍላቸው።
\v 21 ሙሴስ ከጥንት ዘመናት ጀምሮ በከተሞች ሁሉ በየሰንበታቱ በምኵራብ የሚሰብኩና የሚያነቡ ሰዎች አሉትና።»
\s5
\v 22 ስለዚህ በርስያን የተባለው ይሁዳንና ሲላስን የቤተ ክርስቲያን መሪዎች አድርገው እንዲመርጡና፣ ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ እንዲልኳቸው ለሐዋርያትና ለሽማግሌዎች፣ ከቤተ ክርስቲያን ሁሉ ጋር መልካም መስሎ ታያቸው።
\v 23 እንዲህም ብለው ጻፉ፤ «ለሐዋርያት፣ ለሽማግሌዎችና ወንድሞች፣ እንዲሁም በአንጾኪያ፣ በሶርያና በኪልቅያ ለሚገኙ ከአሕዛብ ወገን ለሆኑ ወንድሞች፣ ሰላም ለእናንተ ይሁን።
\s5
\v 24 እኛ ያላዘዝናቸው አንዳንድ ሰዎች ከእኛ ዘንድ መጥተው ነፍሳችሁን በሚያስጨንቅ ትምህርት እንዳስቸገሩአችሁ ሰምተናል።
\v 25 ስለዚህ በአንድ ልብ ሆነን ሰዎችን መርጠን ከወዳጆቻችን ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር ወደ እናንተ መላክ ለሁላችንም መልካም መስሎ ታየን፤
\v 26 እነዚህ ሰዎች ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሲሉ ለሕይወታቸው እንኳ ያልሣሡ ናቸው።
\s5
\v 27 ይህንኑ እንዲነግሯችሁ ይሁዳንና ሲላስን ወደ እናንተ ልከናል፤
\v 28 ከእነዚህ አስፈላጊ ነገሮች በላይ ከባድ ሸክም እንዳንጭንባችሁ፣ ለመንፈስ ቅዱስና ለእኛ መልካም መስሎ ታይቶናልና፤
\v 29 ይኸውም ለጣዖት ከተሠዋ፣ ከደም፣ ከታነቀ፣ ከዝሙትም እንድትርቁ ነው። ራሳችሁን ከእነዚህ ብትጠብቁ መልካም ይሆንላችኋል፤ ደኅና ሁኑ።»
\s5
\v 30 ከዚያም ተሰናብተው ወደ አንጾኪያ ወረዱ፤ ሕዝቡንም ሰብስበው ደብዳቤውን ሰጡአቸው።
\v 31 ደብዳቤውንም አንብበው ስለ ተጽናኑ በጣም ደስ አላቸው።
\v 32 ደግሞም ይሁዳና ሲላስ ነቢያት ስለ ነበሩ፣ወንድሞችን በብዙ ቃል በመምከር አበረታቱአቸው።
\s5
\v 33 በዚያም ጥቂት ጊዜ ከተቀመጡ በኋላ፣ከወንድሞች በሰላም ተሰናብተው ወደ ላኳቸው ሄዱ።
\v 34 ሲላስ ግን እዚያው መቆየት መልካም መስሎ ታየው።
\v 35 ጳውሎስና በርናባስ ግን የጌታን ቃል ባስተማሩበትና በሰበኩበት በአንጾኪያ ከሌሎች ብዙ ሰዎች ጋር ተቀመጡ።
\s5
\v 36 ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ ጳውሎስ በርናባስን፣ «ተመልሰን የጌታን ቃል በሰበክንበት ከተማ ሁሉ ያሉትን ወንድሞች እንጐብኝ፤ በምን ሁኔታ እንዳሉም እንወቅ» አለ።
\v 37 በርናባስም ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስን ደግሞ ከእነሱ ጋር ይዞ ለመሄድ ፈለገ።
\v 38 ጳውሎስ ግን ማርቆስን ይዞ መሄድ አልፈለገም፤ ምክንያቱም ማርቆስ ከዚህ ቀደም ከእነርሱ ጋር ለሥራ በመሄድ ፈንታ፣ በጵንፍልያ ተለይቶአቸው ቀርቶ ነበር።
\s5
\v 39 በመካከላቸው ከፍተኛ አለምስማማት ስለ ተፈጠረም፣ ተለያዩ፤ በርናባስም ማርቆስን ይዞ ወደ ቆጵሮስ በመርከብ ሄደ።
\v 40 ጳውሎስ ግን ሲላስን መረጠ፤ ወንድሞች ለጌታ ጸጋ አደራ ከሰጡት በኋላ፣ ተለይቶአቸው ሄደ።
\v 41 ከዚያም አብያተ ክርስቲያናትን እያበረታታ በሶርያና በኪልቅያ ይዞር ነበር።
\s5
\c 16
\cl ምዕራፍ 16
\p
\v 1 ጳውሎስ ወደ ደርቤና ወደ ልስጥራ መጣ፤ እነሆም፣ እናቱ አይሁዳዊት አማኝ የሆነች፣ አባቱ ግን ግሪክ የሆነ ጢሞቴዎስ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር አገኘ።
\v 2 በልስጥራና በኢቆንዮን የነበሩ ወንድሞችም ስለ እርሱ ጥሩ ምስክርነት ነበራቸው።
\v 3 ጳውሎስም እርሱን ይዞ መጓዝ ፈለገ፤ በዚያ አካባቢ ስለ ነበሩ አይሁድ ሲልም ጢሞቴዎስን ገረዘው፤ አባቱ የግሪክ ሰው እንደ ሆነ ሁሉም ያውቁ ነበርና።
\s5
\v 4 በየከተሞቹ በሚዞሩበት ጊዜ፣ አብያተ ክርስቲያናት እንዲጠብቁት በኢየሩሳሌም የነበሩ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች የጻፉትን መመሪያ ሰጡአቸው።
\v 5 ስለዚህ አብያተ ክርስቲያናቱ በእምነት እየበረቱ፣ ቍጥራቸውም በየዕለቱ እየጨመረ ነበር።
\s5
\v 6 በእስያ አውራጃ ቃሉን እንዳይሰብኩ መንፈስ ቅዱስ ስለ ከለከላቸው፣ ጳውሎስና ባልደረቦቹ በፍርግያና በገላትያ አውራጃዎች አድርገው ዐለፉ።
\v 7 ወደ ሚስያ አካባቢ በደረሱ ጊዜ፣ ቢታንያ ለመግባት ሞከሩ፤ የኢየሱስ መንፈስ ግን ከለከላቸው።
\v 8 ስለዚህ ሚስያን ዐልፈው ወደ ጢሮአዳ ወረዱ።
\s5
\v 9 ጳውሎስም አንድ የመቄዶንያ ሰው ቆሞ፣ “ወደ መቄዶንያ ተሻግረህ ርዳን” እያለ ሲለምነው ሌሊት በራእይ ታየው።
\v 10 ራእዩንም ካየ በኋላ፣ ወዲያው ወደ መቄዶንያ ለመሄድ ተነሣን፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ወንጌልን ለእነርሱ እንድንሰብክ እንደ ጠራን ዐሰብን።
\s5
\v 11 ከጢሮአዳ ተነሥተንም ቀጥታ በመርከብ ወደ ሳሞትራቄ ሄድን፤ በማግስቱም ናጱሌ ደረስን፤
\v 12 ከዚያም የመቄዶንያ ከተማ ወደ ሆነችው ወደ ፊልጵስዩስ ሄድን፤ ከተማዋ የወረዳው ዋና ከተማና የሮም ቅኝ ግዛት ነበረች፤ በዚችም ከተማ ብዙ ቀን ተቀመጥን።
\v 13 በሰንበት ቀንም፣ በወንዝ አጠገብ በነበረው በር በኩል ወደ ውጭ ወጣን፤ ይህም ስፍራ የጸሎት ቦታ እንደ ሆነ ዐሰብን። በዚያም ተቀምጠን ተሰብስበው ለነበሩ ሴቶች ተናገርን።
\s5
\v 14 ከትያጥሮን ከተማ የመጣችና የሐምራዊ ሐር ሻጭ የነበረች፣ ልድያ የምትባል፣ እግዚአብሔርን የምታመልክ አንድ ሴት ትሰማን ነበር። ጳውሎስ እየተናገረ የነበረውን በሚገባ እንድታደምጥ፣ ጌታ ልብዋን ከፈተላት።
\v 15 ከቤተ ሰብዋ ጋር በተጠመቀች ጊዜም፣ “በጌታ ማመኔን ከተረዳችሁልኝ ወደ ቤቴ ግቡና ተቀመጡ” ብላ ለመነችን፤ አስገደደችንም።
\s5
\v 16 አንድ ቀን ጸሎት ቦታ ስንሄድ የጥንቈላ መንፈስ ያደረባት አንዲት ወጣት አገኘችን፤ በዚህ የጥንቈላ ሥራዋም ለአሳዳሪዎችዋ ከፍተኛ ገቢ ታስገኝ ነበር።
\v 17 ይህችው ሴት ጳውሎስንና እኛን ከኋላ እየተከተለች፣ “እነዚህ ሰዎች የልዑል እግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው፤ የመዳንን መንገድ ይነግሯችኋል” እያለች ትጮኽ ነበር።
\v 18 ይህንም ብዙ ቀን ደጋገመች። ጳውሎስ ግን በዚህ እጅግ ተበሳጨ፤ ዘወር ብሎም መንፈሱን፣ “ከእርስዋ እንድትወጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ” አለው፤ በዚያው ቅጽበትም መንፈሱ ወጣ።
\s5
\v 19 አሳዳሪዎችዋም ተስፋ የሚያደርጉበት የገቢያቸው ምንጭ እንደ ጠፋ ባዩ ጊዜ፣ ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው በምድር ላይ እየጎተቱ በገበያ ስፍራ ባለ ሥልጣኖቹ ፊት አቀረቡአቸው።
\v 20 ወደ ገዢዎችም አምጥተዋቸው፣ “እነዚህ ሰዎች አይሁድ ሆነው ሳሉ በከተማችን ውስጥ ከፍተኛ ሁከት እየፈጠሩ ነው።
\v 21 እኛ ሮማውያን ለመቀበል ያልተፈቀዱልንን ነገሮች ያስተምራሉ” አሉ።
\s5
\v 22 በዚህ ጊዜ ሕዝቡ በጳውሎስና በሲላስ ላይ በአንድነት ተነሡ፤ ገዦቹም ልብሳቸውን አስወልቀው በዱላ እንዲደበድቡአቸው አዘዙ።
\v 23 ብዙ ድብደባ ካደረሱባቸው በኋላ፣ ወደ ወኅኒ ጣሉአቸው፤ የወኅኒ ጠባቂውም በጥንቃቄ እንዲጠብቃቸው አዘዙት።
\v 24 የወኅኒ ጠባቂውም ይህን ትእዛዝ ተቀብሎ፣ ወደ ውስጠኛው እስር ቤት ጣላቸው፤ እግራቸውንም ከግንድ ጋር አጣብቆ አሰራቸው።
\s5
\v 25 እኩለ ሌሊት አካባቢም፣ ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ በዝማሬ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤ ሌሎች እስረኞችም አደመጡአቸው።
\v 26 ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስከሚናጋ ድረስ ታላቅ የምድር መናወጥ ተከሠተ፤ ወዲያውም የወኅኒው በሮች ሁሉ ተከፈቱ፤ የታሳሪዎችም ሁሉ ሰንሰለቶች ተፈቱ።
\s5
\v 27 የወኅኒ ጠባቂውም ከእንቅልፉ ነቅቶ በሮቹ እንደ ተከፈቱ አየ፤ እስረኞቹ ያመለጡ ስለ መሰለውም፣ ሰይፉን መዞ ራሱን ሊገድል ቃጣ።
\v 28 ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ፣ “ራስህን አትጉዳ! እኛ ሁላችን እዚሁ አለን” ብሎ ጮኸ።
\s5
\v 29 የወኅኒ ጠባቂውም መብራት ለምኖ ሮጦ ወደ ውስጥ ገባ፤ በፍርሀት እየተንቀጠቀጠም በጳውሎስና በሲላስ ፊት ተደፋ፤
\v 30 ወደ ውጭም አስወጥቶአቸው፣ “ጌቶች ሆይ፣ ለመዳን ምን ማድረግ አለብኝ?” አላቸው።
\v 31 እነርሱም፣ “በጌታ ኢየሱስ እመን፤ አንተም ቤተ ሰዎችህም ትድናላችሁ” አሉት።
\s5
\v 32 ጳውሎስና ሲላስ ለእርሱና አብረውት በቤት ለነበሩ ሰዎች ሁሉ የጌታን ቃል ተናገሩ።
\v 33 የወኅኒ ጠባቂውም ሌሊት፣ በዚያው ሰዓት ወስዶአቸው ቍስላቸውን አጠበላቸው። እርሱና ቤተ ሰዎቹም ሁሉ ወዲያው ተጠመቁ።
\v 34 ጳውሎስንና ሲላስንም ወደ ቤቱ ይዞአቸው ወጣ፤ ምግብም አቀረበላቸው። ሁሉም በእግዚአብሔርም በማመናችው ከቤተ ሰዎቹ ጋር እጅግ ደስ አለው።
\s5
\v 35 ሲነጋም ገዦቹ፣ “እነዚያን ሰዎች ልቀቋቸው” የሚል ትእዛዝ ለጠባቂዎቹ ላኩ።
\v 36 የወኅኒ ጠባቂውም፣ “ገዦቹ እንድትፈቱ ትእዛዝ ለእኔ ልከዋል፤ ስለዚህ ውጡና በሰላም ሂዱ” ብሎ ለጳውሎስ ነገረው።
\s5
\v 37 ጳውሎስ ግን እንዲህ አላቸው፤ “ሮማውያን የሆንነውን እኛን ያለ ፍርድ በሕዝብ ፊት ደብድበውናል፤ ወደ ወኅኒም አስገብተውናል፤ ታዲያ፣ አሁን በድብቅ ያስወጡናል? በፍጹም አይሆንም፤ እነርሱ ራሳቸው መጥተው ያስወጡን።”
\v 38 ጠባቂዎቹም ይህንኑ አባባል ለገዦቹ ነገሯቸው፤ ገዦቹም ጳውሎስና ሲላስ ሮማውያን እንደ ሆኑ በሰሙ ጊዜ ፈሩ።
\v 39 መጥተውም ተማጸኑአቸው፤ ከወኅኒም ካስወጡአቸው በኋላ፣ ከከተማው እንዲወጡ ጳውሎስንና ሲላስን ለመኑአቸው።
\s5
\v 40 ጳውሎስና ሲላስም ከወኅኒው ወጥተው ወደ ልድያ ቤት ገቡ። ወንድሞችንም ባዩአቸው ጊዜ፣ አበረታቱአቸው፤ ከዚያም ከከተማዪቱ ወጥተው ሄዱ።
\s5
\c 17
\cl ምዕራፍ 17
\p
\v 1 አንፊጶልና አጶሎንያ በተባሉ ከተሞች በኩል ካለፉ በኋላም፣ ተሰሎንቄ ወደ ተባለች ከተማ መጡ፤ በዚያም ከተማ የአይሁድ ምኵራብ ነበረ።
\v 2 ጳውሎስም እንደ ልማዱ፣ ወደ አይሁድ ሄዶ፣ ለሦስት ሰንበታት ያህል ከቅዱሳት መጻሕፍት እየጠቀሰ ከእነርሱ ጋር ይነጋገር ነበር።
\s5
\v 3 ቅዱሳት መጻሕፍትንም እየገለጠ፣ ክርስቶስ መከራን መቀበልና ከሙታን መነሣት እንደ ነበረበት እያስረዳም፣ «ይህ እኔ የምሰብክላችሁ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው» ይላቸው ነበር።
\v 4 ከአይሁድም አንዳንዶቹ መልእክቱን ተቀብለው ከጳውሎስና ከሲላስ ጋር ተባበሩ፤ በተጨማሪም ለእግዚአብሔር ያደሩ ግሪኮች፣ የከበሩ ብዙ ሴቶችና ከፍተኛ ቍጥር ያላቸው ሰዎች ከእነርሱ ጋር ሆኑ።
\s5
\v 5 ሌሎች ያላመኑ አይሁድ ግን፣ በቅንዓት በመነሣሣትና ክፉ ሰዎችን ከጎዳና ላይ በማሰባሰብ ሕዝብን አከማችተው ከተማዋን አወኩአት። የኢያሶንን ቤት በዐመፅ በመክበብም፣ ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው ለሕዝቡ ለማስረከብ ፈለጉ።
\v 6 ሊያገኙአቸው ባልቻሉ ጊዜም፣ ኢያሶንንና ሌሎች ወንድሞችን ይዘው መሬት ለመሬት እየጎተቱ ወደ ከተማዋ ባለ ሥልጣናት ፊት አወጡአቸው፤ እንዲህም እያሉ ይጮኹ ነበር፤ «እነዚህ ዓለምን የገለባበጡ ሰዎች ወደዚህ ደግሞ መጥተዋል፤
\v 7 ኢያሶን በቤቱ የተቀበላቸው እነዚህ ሰዎች የቄሣርን ሕግ የሚቃወሙ ናቸው፤ ኢየሱስ የሚባል ሌላ ንጉሥ አለ እያሉ ነው።»
\s5
\v 8 ሕዝቡና የከተማው ሹሞች እነዚህን ነገሮች ሲሰሙ፣ ታወኩ።
\v 9 ከኢያሶንና ከሌሎቹም የዋስትና ገንዘብ ተቀብለው ለቀቁአቸው።
\s5
\v 10 ወንድሞች ጳውሎስንና ሲላስን በዚያው ሌሊት ወደ ቤርያ ሰደዱአቸው። እነርሱም እዚያ በደረሱ ጊዜ፣ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገቡ።
\v 11 እዚህ የሚኖሩ ሰዎች በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ሰፊ አስተሳሰብ ስለ ነበራቸው፣ ነገሩ እንዲህ ይሆንን በማለት ቅዱሳት መጻሕፍትን በየዕለቱ እየመረመሩ፣ ልባቸው ቃሉን ለመቀበል ዝግጁ ነበር።
\v 12 ስለዚህ ከእነርሱ ብዙዎች አመኑ፤ በተጨማሪ አንዳንድ ተደማጭነት ያላቸው የግሪክ ሴቶችና ሌሎች ወንዶችም አመኑ።
\s5
\v 13 በተሰሎንቄ የነበሩ አይሁድም ጳውሎስ በቤርያም ደግሞ ቃሉን እንደ ሰበከ ባወቁ ጊዜ፣ ወደዚያ ሄደው ሕዝቡን በማነሣሣት አወኩ።
\v 14 ወንድሞችም ወዲያው ጳውሎስን ወደ ባሕሩ አካባቢ እንዲሄድ አደረጉ ፤ ሲላስና ጢሞቴዎስ ግን እዚያው ቆዩ።
\v 15 ጳውሎስን ይሸኙ የነበሩት ሰዎችም እስከ አቴና ድረስ ወሰዱት። ከዚያም ሲነሡ፣ ሲላስና ጢሞቴዎስ በተቻለው ፍጥነት ወደ እነሱ እንዲመጡ የሚል መልእክት ከጳውሎስ ተቀብለው ሄዱ።
\s5
\v 16 ጳውሎስ አቴና ተቀምጦ እየጠበቃቸው ሳለ፣ ከተማዋ በጣዖት የተሞላች መሆንዋን ሲያይ፣ መንፈሱ በውስጡ ተበሳጨበት።
\v 17 ስለዚህም ነገር በምኵራብ ከሚያገኛቸው አይሁድ፣ እግዚዘብሔርንም ከሚያመልኩ ሌሎች ሰዎችና ዘወትር በገበያ ቦታ ከሚያገኛቸው ሰዎች ጋር ይነጋገር ነበር።
\s5
\v 18 ከኤፌቆስና ከኢስጦኢኮች ወገን የሆኑ አንዳንድ ፈላስፎችም ደግሞ ጳውሎስን አገኙት። ከእነርሱም አንዳንዶች፣ «ይህ ለፍላፊ ምን እያለ ነው?» አሉ። ሌሎቹም፣ ስለ ኢየሱስና ስለ ትንሣኤው ሲሰብክ ስለ ሰሙት፣ «ስለ እንግዳ አማልክት የሚሰብክ ይመስላል» አሉ።
\s5
\v 19 ከዚያም፣ «አንተ የምትናገረውን ይህን ዐዲስ ትምህርት ማወቅ እንችላለን ወይ?
\v 20 ምክንያቱም እየሰማናቸው ያሉ ነገሮች እንግዳ ናቸው። ስለዚህ፣ የእነዚህን ነገሮች ትርጕም ማወቅ እንሻለን» አሉት።
\v 21 አቴናውያንና ሌሎች በዚያ የሚኖሩ እንግዶች ሁሉ ጊዜአቸውን የሚያሳልፉት በሌላ ጉዳይ ሳይሆን፣ ስለ ዐዳዲስ ነገሮች በማውራት ወይም በመስማት ነበር።
\s5
\v 22 ስለዚህ ጳውሎስ በአርዮስፋጎስ መካከል ቆሞ እንዲህ አለ፤ «እናንተ የአቴና ሰዎች ሆይ፣ በየትኛውም መልክ እጅግ ሃይማኖተኞች እንደ ሆናችሁ እመለከታለሁ።
\v 23 ምክንያቱም ወዲያ ወዲህ እየተመላለስሁ የምታመልኳቸውን ስመለከት፣ ላልታወቀ አምላክ የሚል ጽሑፍ የተጻፈበት አንድ መሠዊያ አይቻለሁ። እንግዲህ ይህን ሳታውቁ የምታመልኩትን አምላክ እኔ እነግራችኋለሁ።
\s5
\v 24 ዓለምንና በውስጧ የሚገኙትን ሁሉ የፈጠረ አምላክ፣ የሰማይና የምድር ጌታ በመሆኑ፣ በእጅ በተሠራ መቅደስ ውስጥ አይኖርም።
\v 25 ለሰዎች ሕይወት፣ እስትንፋስንና ሁሉንም ነገር የሚሰጠው እርሱ ራሱ ስለ ሆነ፣ እግዚአብሔር አንዳች እንደሚያስፈልገው በሰው እጅ አይገለገልም።
\s5
\v 26 በምድር ገጽ ላይ የሚኖሩትንም ሕዝቦች ሁሉ ከአንድ ሰው ፈጠረ፤ የሚኖሩባቸውንም ስፍራዎች ወሰን፣ ወቅቶችንም የወሰነላቸው እርሱ ነው።
\v 27 ስለዚህ እግዚአብሔርን ቢፈልጉ ሊያገኙት ይችላሉ፤ እንደ እውነቱ ከሆነ፣ እርሱ ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም።
\s5
\v 28 ምክንያቱም የምንኖረው፣ የምንንቀሳቀሰውና በሕይወት የቆምነው በእርሱ ነው፤ ከእናንተ ባለ ቅኔዎች አንዱ እንዳለውም፣ 'እኛ ልጆቹ ነን።'
\v 29 እንግዲህ የእግዚአብሔር ልጆች ከሆንን፣ መለኮትን በሰው ጥበብና እንደ ተቀረጸ ወርቅ ወይም ብር ወይም ድንጋይ አድርገን ማሰብ የለብንም።
\s5
\v 30 ስለዚህ እግዚአብሔር የአለማወቅ ጊዜያትን አሳልፎ፣ አሁን ግን በየትኛውም ስፍራ ያሉ ሰዎች ሁሉ ንስሐ እንዲገቡ ያዛል።
\v 31 ምክንያቱም በመረጠው ሰው አማካይነት በዓለም ላይ የሚፈርድበትን ቀን አዘጋጅቶአል። እግዚአብሔር ይህን ሰው ከሙታን በማስነሣቱ ለሁሉ ሰው ማረጋገጫ ሰጥቶአል።"
\s5
\v 32 የአቴና ሰዎች ስለ ሙታን ትንሣኤ በሰሙ ጊዜ፣ አንዳንዶቹ በጳውሎስ ላይ አፌዙ፤ሌሎች ግን፣ «ስለዚህ ጉዳይ ዳግመኛ እንሰማሃለን» አሉት።
\v 33 ከዚህ በኋላ፣ ጳውሎስ ተለይቶአቸው ሄደ፤
\v 34 አንዳንድ ወንዶች ግን ከእርሱ ጋር ተባብረው አመኑ፤ በእነዚህም ውስጥ የአርዮስፋጎስ አመራር አባል ዲዮናስዮስ፣ ደማሪስ የተባለች ሴትና ሌሎችም ይገኛሉ።
\s5
\c 18
\cl ምዕራፍ 18
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ፣ ጳውሎስ ከአቴና ወደ ቆሮንቶስ ሄደ።
\v 2 እዚያም ከጳንጦስ ወገን የሆነ አቂላ የሚባል አይሁዳዊ አገኘ። እርሱም አይሁድ ሁሉ ከሮም እንዲወጡ ቀላውዴዎብ ባዘዘው መሠረት፣ ከሚስቱ ከጵርቅላ ጋር በቅርብ ከኢጣሊያ የመጣ ሰው ነበር። ጳውሎስም ከእነርሱ ጋር ተቀራረበ።
\v 3 ሥራቸው አንድ ዓይነት ስለ ሆነም፣ በእነርሱ ዘንድ እየኖረ ዐብሮአቸው ይሠራ ነበር። ሥራቸውም ድንኳን መስፋት ነበር።
\s5
\v 4 በየሰንበቱም በምኵራብ ውስጥ በመገኘት እየተከራከረ፣ አይሁድንም ግሪኮችንም ያሳምን ነበር።
\v 5 ሲላስና ጢሞቴዎስ ከመቄዶንያ እርሱ ወዳለበት በወረዱ ጊዜ ግን፣ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ለአይሁድ እንዲመሰክር መንፈስ ቅዱስ ጳውሎስን ገፋፋው።
\v 6 አይሁድ በተቃወሙትና በተሳደቡ ጊዜ፣ ጳውሎስ ልብሱን እያራገፈባቸው፣ «ደማችሁ በራሳችሁ ላይ ይሁን፤ እኔ ንጹሕ ነኝ፤ ከአሁን ጀምሮ ወደ አሕዛብ እሄዳለሁ» አላቸው።
\s5
\v 7 ከዚያም ወጥቶ ቲቶ ኢዮስጦስ ወደሚባል፣ እግዚአብሔርን ወደሚያመልክ ሰው ቤት ሄደ። ቤቱም በምኵራብ አጠገብ ነበር።
\v 8 ቀርስጶስ የተባለም የምኵራብ አለቃ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር በጌታ አመነ። ጳውሎስ ሲናገር ከሰሙት ከቆሮንቶስ ሰዎች መካከልም ብዙዎቹ አምነው ተጠመቁ።
\s5
\v 9 ጌታም ሌሊት በራእይ ጳውሎስን እንዲህ አለው፤ "አትፍራ ተናገር፣ ዝምም አትበል።
\v 10 ምክንያቱም እኔ ከአንተ ጋር አለሁ፤ ሊጎዳህ የሚነሣብህ ማንም የለም፤ እንዲያውም በዚህ ከተማ ብዙ ሰዎች አሉኝ።"
\v 11 ጳውሎስም በመካከላቸው የእግዚአብሔርን ቃል እያስተማረ አንድ ዓመት ከስድስት ወር እዚያ ተቀመጠ።
\s5
\v 12 ነገር ግን ጋልዮስ የአካይያ አገረ ገዢ በሆነ ጊዜ፣ አይሁድ በጳውሎስ ላይ በአንድነት ተነሡ፤ ይዘውም ፍርድ ፊት አቀረቡት።
\v 13 ከዚያም፣ “ሕዝቡ እግዚአብሔርን እንዲያመልክ ይህ ሰው ከሕግ ውጪ እየቀሰቀሰ ነው” አሉ።
\s5
\v 14 ጳውሎስ ሊናገር ሲልም፣ ጋልዮስ አይሁድን፣ “አይሁድ ሆይ፣ ጉዳዩ በርግጥ የበደል ወይም የወንጀል ቢሆን ኖሮ፣ ልታገሣችሁ በተገባኝ ነበር።
\v 15 ነገር ግን ክርክሩ ስለ ቃላትና ስለ ስሞች፣ ደግሞም ስለ ገዛ ሕጋችሁ ስለ ሆነ፣ እናንተው ራሳችሁ ተነጋገሩበት። እኔ ስለ እንደዚህ ዐይነት ጉዳይ ፈራጅ መሆን አልፈልግም” አለ።
\s5
\v 16 ከዚያም ጋልዮስም ከችሎቱ አስወጣቸው።
\v 17 እነርሱ ሁሉ ግን የምኵራቡን አለቃ ሶስቴንስን በጉልበት ይዘው በፍርድ ወንበሩ ፊት ደበደቡት። ይሁን እንጂ፣ ይህ ድርጊታቸው ለጋልዮስ ደንታም አልሰጠውም።
\s5
\v 18 ጳውሎስም ብዙ ቀናት ከተቀመጠ በኋላ፣ ወንድሞችን ተሰናብቶ ከጵርስቅላና ከአቂላ ጋር በመርከብ ወደ ሶርያ ሄደ። ስእለት ስለ ነበረበትም፣ ከወደቡ ከክንክራኦስ ከመነሣቱ በፊት ራሱን ተላጨ።
\v 19 ኤፌሶን በደረሱ ጊዜ፣ ጳውሎስ ጵርስቅላንና አቂላን ትቶአቸው ወደ ምኵራብ ሄዶ ከአይሁድ ጋር ይነጋገር ነበር።
\s5
\v 20 እነርሱም ረዘም ላለ ጊዜ ዐብሮአቸው እንዲቆይ ሲለምኑት፣ ጳውሎስ እንቢ አለ።
\v 21 ከዚያም፣ “እግዚአብሔር ቢፈቅድ እንደ ገና ተመልሼ እመጣለሁ” ብሎ ተሰናበታቸው። ከኤፌሶንም ተነሥቶ በመርከብ ሄደ።
\s5
\v 22 ጳውሎስ ቂሣርያ በደረሰ ጊዜ፣ በኢየሩሳሌም ወደ ነበረችው ቤተ ክርስቲያን ወጥቶ ሰላምታ አቀረበላቸውና ወደ አንጾኪያ ወረደ።
\v 23 በዚያም ጥቂት ጊዜ ከተቀመጠ በኋላ፣ ጳውሎስ ተለያቸው፤ በገላትያና በፍርግያ አካባቢ በማለፍም ደቀ መዛሙርቱን ሁሉ አበረታታ።
\s5
\v 24 ትውልዱ እስክንድርያዊ የሆነ፣ አጵሎስ የሚባል አንድ አይሁዳዊ ወደ ኤፌሶን መጣ፤ እርሱም የንግግር ችሎታና በቂ የቅዱሳት መጻሕፍት ዕውቀት ያለው ሰው ነበር።
\v 25 አጵሎስ የጌታን ትምህርት በሚገባ የተማረ በመሆኑ፣ በመንፈሱ ተነቃቅቶ ስለ ኢየሱስ በትክክል ይናገርና ያስተምር ነበር፤ የሚያውቀው ግን ስለ ዮሐንስ ጥምቀት ብቻ ነበር።
\v 26 አጵሎስ ምኵራብ ውስጥ በድፍረት መናገር ጀመረ። ነገር ግን ጵርስቅላና አቂላ በሰሙት ጊዜ፣ ወደ እርሱ ቀርበው የእግዚአብሔር መንገድ ይበልጥ በትክክል አብራሩለት።
\s5
\v 27 እርሱም ወደ አካይያ ማለፍ በፈለገ ጊዜ፣ ወንድሞች አበረታቱት፤ በአካይያ የነበሩ ደቀ መዛሙርት እንዲቀበሉትም ጻፉላቸው። እዚያ በደረሰ ጊዜም፣ በጸጋ ያመኑትን እጅግ ረዳቸው።
\v 28 አጵሎስ ከቅዱሳት መጻሕፍት እያስደገፈ፣ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ በማሳየት በኀይሉና በችሎታው አይሁድን ተከራክሮ ረታቸው።
\s5
\c 19
\cl ምዕራፍ 19
\p
\v 1 አጵሎስ በቆሮንቶስ በነበረ ጊዜ፣ ጳውሎስ በላይኛው አገር አድርጎ ወደ ኤፌሶን ከተማ መጣ፤ በዚያም አንዳንድ ደቀ መዛሙርትን አገኘ።
\v 2 ጳውሎስም፣ “ባመናችሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀብላችኋል?” አላቸው። እነርሱም፣ “አልተቀበልንም፤ እንዲያውም መንፈስ ቅዱስ መኖሩን አልሰማንም” አሉት።
\s5
\v 3 ጳውሎስም፣ “ታዲያ፣ በምን ተጠመቃችሁ?” አላቸው። እነርሱም፣ “የተጠመቅነው በዮሐንስ ጥምቀት ነው” አሉት።
\v 4 ጳውሎስም መልሶ፣ “ዮሐንስ ያጠመቀው በንስሓ ጥምቀት ነው። ሰዎች ከእርሱ በኋላ በሚመጣው፣ በኢየሱስ ማመን እንደሚገባቸውም ነገራቸው” አለ።
\s5
\v 5 ሕዝቡ ይህን ሲሰሙ፣ በጌታ ኢየሱስ ስም ተጠመቁ።
\v 6 ጳውሎስም እጆቹን በሰዎቹ ላይ በጫነ ጊዜ፣ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው፤ እነርሱም በልዩ ቋንቋ መናገርና መተንበይ ጀመሩ።
\v 7 ቍጥራቸውም ዐሥራ ሁለት ያህል ነበረ።
\s5
\v 8 ጳውሎስ ከዚህ በኋላ ወደ ምኵራብ እየገባ ሦስት ወር ያህል በድፍረት ይናገር ነበር፤ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እየገለጠ ሰዎችን ያስረዳ ነበር።
\v 9 አንዳንድ አይሁድ ግን ልባቸውን አደንድነው በመቃወም፣ በሕዝቡ ፊት የክርስቶስን መንገድ ተሳደቡ፤ ስለዚህ ጳውሎስ ትቶአቸው ሄደ፤ ያመኑትንም ከእነርሱ አራቀ። ጢራኖስ በሚባል የትምህርት አዳራሽም በየዕለቱ ንግግር ያደርግ ጀመር።
\v 10 ይህም፣ በእስያ የሚኖሩ አይሁድና ግሪኮችም ሁሉ የጌታን ቃል እስኪሰሙ ድረስ፣ ሁለት ዓመት ቀጠለ።
\s5
\v 11 እግዚአብሔር በጳውሎስ እጅ ታላላቅ ተአምራትን ያደርግ ነበር፤
\v 12 ስለዚህ የጳውሎስ አካል የነካው ጨርቅ ወይም መሐረብ ሲወሰድ፣ የታመሙት ይፈወሱ፣ አጋንንትም ከሰዎች ይወጡ ነበር።
\s5
\v 13 አጋንንት እናስወጣለን እያሉ ከቦታ ቦታ የሚዞሩ አይሁድ ነበሩ፤ እነርሱም የኢየሱስን ስም ለገዛ ጥቅማቸው ለማዋል፣ በክፉ መናፍስት ላይ እየጠሩ፣ “እንድትወጡ ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ እናዛችኋለን” ይሉ ነበር።
\v 14 ይህን ያደረጉትም የአይሁድ የካህናት አለቃ የነበረው የአስቄዋ ሰባት ወንድ ልጆች ነበሩ።
\s5
\v 15 ክፉው መንፈስም፣ “ኢየሱስን ዐውቀዋለሁ፤ ጳውሎስንም ዐውቃለሁ፤ ለመሆኑ እናንተ እነማን ናችሁ?” ብለው መለሱላቸው።
\v 16 ክፉ መንፈስ ያለበትም ሰው ዘሎ ያዛቸው፤ አሸንፏቸውም ደበደባቸው። ከዚያም ቤት ቈስለው ዕራቁታቸውን ሸሹ።
\v 17 ይህም በኤፌሶን ይኖሩ በነበሩ አይሁድና ግሪኮችም ዘንድ ሁሉ ታወቀ። እነርሱም ሁሉ በፍርሀት ተዋጡ፤ የጌታ ኢየሱስም ስም ተከበረ።
\s5
\v 18 ደግሞም ካመኑት ብዙዎቹ መጥተው ቀደም ሲል ያደረጉትን ክፉ ነገር ሳይሸሽጉ ይናዘዙ ነበር።
\v 19 አስማተኞችም የጥንቈላ መጻሕፍታቸውን ሰብስበው እያመጡ በሰው ሁሉ ፊት አቃጠሉ፤ ዋጋቸውም ሲተመን ሃምሳ ሺህ ብር ሆነ።
\v 20 በዚህም መሠረት የጌታ ቃል በስፋትና በኀይል ተሠራጨ።
\s5
\v 21 ጳውሎስ በኤፌሶን የነበረውን አገልግሎቱን ከፈጸመ በኋላ፣ በመቄዶንያና በአካይያ አድርጎ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ በመንፈስ ቅዱስ ሆኖ ወሰነ፤ ደግሞም፣ “እዚያ ከደረስሁ በኋላም፣ ሮሜን ማየት ይገባኛል” አለ።
\v 22 ሲረዱት ከነበሩት ደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን፣ ጢሞቴዎስንና ኤርስጦንን ወደ መቄዶንያ ላካቸው። እርሱ ራሱ ግን ጥቂት ጊዜ በእስያ ቆየ።
\s5
\v 23 በዚህ ጊዜ የጌታን መንገድ በተመለከተ በኤፌሶን ትልቅ ሁከት ተነሣ።
\v 24 ድሜጥሮስ የሚባል አንድ ብር ሠሪም የዲያናን ምስል ከብር እያበጀ ለአንጥረኞች ትልቅ ገቢ ያስገኝላቸው ነበር።
\v 25 ስለዚህ በዚህ ሙያ ላይ የተሰማሩትን ብዙ ሠራተኞች አንድ ላይ ሰብስቦ፣ “ሰዎች ሆይ፤ በዚህ ሙያችን ብዙ ገንዘብ እንደምናገኝ ታውቃላችሁ።
\s5
\v 26 ይህ ጳውሎስ በኤፌሶን ብቻ ሳይሆን፣ ከብዙ በጥቂቱ በእስያ ሁሉ አብዛኛውን ሕዝብ በቃላት እያባበለ ከእኛ ማራቁን እያያችሁና እየሰማችሁ ነው። በእጅ የሚሠሩ አማልክት የሉም እያላቸው ነው።
\v 27 የእኛ ሞያዊ ጥበብ አላስፈላጊ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ የታላቅዋ አምላክ የዲያና ቤተ መቅደስም እንደ ከንቱ ነገር የመቍጠር አደጋ ያሠጋል፤ እስያ ሁሉና ዓለሙ የሚያመልካት ይህች አምላክም ዝናዋን ታጣለች።”
\s5
\v 28 ሕዝቡም ይህን በሰሙ ጊዜ፣ በቍጣ ተሞልተው፣ “የኤፌሶንዋ ዲያና ታላቅ ናት” እያሉ ጮኹ።
\v 29 ከተማው ሁሉ ድብልቅልቁ ወጣ፤ ሕዝቡም በአንድ ላይ ገንፍለው ወደ ቲያትር ማሳያው ቦታ ገቡ። ከመቄዶንያ የመጡትንም የጳውሎስን የጕዞ ባልደረቦች፣ ጋይዮስንና አርስጥሮኮስን ያዙአቸው።
\s5
\v 30 ጳውሎስ ወደ ሕዝቡ ሊደባለቅ ፈልጎ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ከለከሉት።
\v 31 ደግሞም፣ የጳውሎስ ወዳጆች የነበሩ አንዳንድ የአካባቢ ሹሞች ጳውሎስ ወደ ቲያትር ማሳያ ቦታ እንዳይገባ መልእክት ላኩበት።
\v 32 ሕዝቡ ሁሉ ግራ ተጋብቶ ነበርና፣ አንዳንዶቹ ስለ አንድ ነገር ሲጮኹ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ስለ ሌላ ነገር ይጮኹ ነበር። አብዛኛዎቹ ደግሞ ለምን ተሰብስበው እንደ ወጡ እንኳ አያውቁም ነበር።
\s5
\v 33 አይሁድም እስክንድሮስን ገፋፍተው ወደ ሕዝቡ ፊት አወጡት። እስክንድሮስ ለሕዝቡ በእጅ ምልክት እያሳየ ሊያስረዳቸው ሞከረ።
\v 34 ሕዝቡም አይሁዳዊ መሆኑን በተረዱ ጊዜ ሁሉም በአንድ ድምፅ፣ “የኤፌሶንዋ ዲያና ታላቅ ናት” እያሉ ለሁለት ሰዓት ያህል ጮኹ።
\s5
\v 35 የከተማዋ ጸሓፊ ሕዝቡን ዝም ካሰኘ በኋላ፣ እንዲህ አለ፤ “እናንተ የኤፌሶን ሰዎች ሆይ፣ የኤፌሶን ከተማ የታላቅዋ ዲያና ቤት መቅደስና ከሰማይ የወረደው ምስል ጠባቂ መሆንዋን የማያውቅ የትኛው ሰው ነው?
\v 36 እንግዲህ ይህ የማይካድ ነገር መሆኑ ከታያችሁ፣ ጸጥ ልትሉ፣ አንዳች ነገርም በችኰላ ልታደርጉ አይገባም፤
\v 37 ምክንያቱም አብያተ መቅደስን ያልሰረቁ፣ አማልክታችንንም ያልሰደቡ እነዚህን ሰዎች ወደዚህ ፍርድ ቤት አምጥታችኋል።
\s5
\v 38 ስለዚህ ድሜጥሮስና ከእርሱ ጋር ያሉ አንጥረኞች የሚከሱት ሰው ካለ፣ ፍርድ ቤቱ ክፍት ነው፤ ዳኞችም አሉ፤ እዚያ እርስ በርስ ይካሰሱ።
\v 39 ስለ ሌላ ጉዳይ የምትፈልጉት ነገር ካለ ግን፣ ችግሩ በመደበኛው ጉባኤ ይፈታል፤
\v 40 ምክንያቱም በዛሬው ቀን የነበረው ዐመፅ ሳያስጠይቀን አይቀርም። የነበረው ግርግር መንሥኢ የለውም፤ እንዲህ ነው ብለን ልንገልጸውም አንችልም።”
\v 41 ጸሓፊው ይህን ተናግሮ ጉባኤውን አሰናበተው።
\s5
\c 20
\cl ምዕራፍ 20
\p
\v 1 ሁከቱ ካበቃ በኋላ፣ ጳውሎስ ደቀ መዛሙርቱን አስጠርቶ አበረታታቸው። ከዚያም ተሰናበታቸውና ወደ መቄዶንያ ለመሄድ ተነሣ።
\v 2 በእነዚያም አካባቢዎች እያለፈ ያመኑትን እጅግ ካበረታታ በኋላ፣ ወደ ግሪክ ገባ።
\v 3 በዚያም ሦስት ወር ከቈየ በኋላ፣ ወደ ሶርያ በመርከብ ለመሄድ እያሰበ ሳለ፣ አይሁድ አሤሩበት፤ ስለዚህ በመቄዶንያ አድርጎ ለመመለስ ወሰነ።
\s5
\v 4 እስከ እስያ የሸኙትም የቤርያው ሱሲጳጥሮስ፣ ከተሰሎንቄ የመጡት አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ፣ የደርቤኑ ጋይዮስ፣ ጢሞቴዎስ፣ እንዲሁም ከእስያ የመጡት ቲኪቆስና ጥሮፊሞስ ነበሩ።
\v 5 እነዚህ ሰዎች ግን ቀድመውን በጢሮአዳ ጠበቁን።
\v 6 እኛም ከቂጣ በዓል ቀን በኋላ፣ ከፊልጵስዩስ በመርከብ ተነሥተን በዐምስት ቀን ውስጥ ጢሮአዳ ደረስንባቸው፤ እዚያም ሰባት ቀን ተቀመጥን።
\s5
\v 7 በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን እንጀራ ለመቊረስ በተሰበሰብን ጊዜ፣ ጳውሎስ ለምእመናኑ ንግግር አደረገ። በሚቀጥሉት ቀናት ለመሄድ ዐቅዶ ስለ ነበረ፣ እስከ እኩለ ሌሊት መናገሩን ቀጠለ።
\v 8 በተሰበሰብንበትም ሰገነት ላይ ብዙ መብራቶች ነበሩ።
\s5
\v 9 አውጤኪስ የሚባል ወጣትም በመስኮት ተቀምጦ ሳለ፣ እንቅልፍ ጭልጥ አድርጎ ወሰደው። ጳውሎስ ንግግሩን ባስረዘመ ጊዜ፣ ይህ ወጣት ገና ተኝቶ እንዳለ ከሦስተኛው ፎቅ ወደቀ፤ ሲያነሡትም ሞቶ ነበር።
\v 10 ጳውሎስ ግን ወርዶ በላዩ ተዘረጋበት፣ ዐቀፈውም። ከዚያም፣ “በሕይወት ስላለ ከዚህ በኋላ አትታወኩ” አለ።
\s5
\v 11 እንደ ገናም በደረጃ ወደ ላይ ወጣ፤ እንጀራ ቈርሶም በላ። እስኪነጋ ድረስም ለረዥም ጊዜ ከእነርሱ ጋር ከተነጋገረ በኋላ፣ ተለይቶአቸው ሄደ።
\v 12 ወጣቱንም በሕይወት እያለ አመጡት፤ በዚህም እጅግ ተጽናኑ።
\s5
\v 13 እኛም ራሳችን ጳውሎስን በመርከብ ለማሳፈር ወዳሰብንበት ወደ አሶን ቀድመን በመርከብ ሄድን። እርሱም ያሰበው ይህንኑ ነበር፤ በመርከብ ለመሄድ ዐቅዶ ነበርና።
\v 14 በአሶን ሲያገኘንም፣ ወዳለንበት መርከብ አስገብተነው ወደ ሚሊጢን ጕዞአችንን ቀጠልን።
\s5
\v 15 ከዚያም በመርከብ ተነሣንና በማግስቱ ኪዩ በምትባለዋ ደሴት ትይዩ ደረስን። በሚቀጥለውም ቀን ወደ ሳሞን ደሴት ጎራ ብለን፣ በማግስቱ ወደ ሚሊጢን ከተማ ገባን፤
\v 16 ጳውሎስም በእስያ ውስጥ ጊዜ ሳያባክን፣ ኤፌሶንን ዐልፎ በመርከብ ለመሄድ ወስኖ ነበርና፤ ምክንያቱም በተቻለው መጠን ሁሉ ለበዓለ ኀምሳ በኢየሩሳሌም ለመገኘት ቸኵሎ ነበር።
\s5
\v 17 ሰዎችንም ከሚሊጢን ወደ ኤፌሶን ልኮ፣ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ወደ ራሱ አስጠራቸው።
\v 18 ወደ እርሱ በመጡም ጊዜ፣ እንዲህ አላቸው፤ “ወደ እስያ ከገባሁበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ፣ ዘወትር እንዴት ከእናንተ ጋር እንደ ኖርሁ እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።
\v 19 ራሴን እጅግ ዝቅ በማድረግና በእንባ፣ ከአይሁድ ሤራ የተነሣ በገጠመኝ መከራም ውስጥ ጌታን ማገልገል አላቋረጥሁም።
\v 20 ጠቃሚ የሆነውን ነገር ሁሉ ለእናንተ ከመግለጽና በአደባባይም ሆነ ቤት ለቤት በመዞር እናንተን ከማስተማር ወደ ኋላ እንዳላልሁ ታውቃላችሁ።
\v 21 በንስሓ ወደ እግዚአብሔር ስለ መመለስና በጌታችን በኢየሱስ ስለ ማመን አይሁድንና ግሪኮችን እንዴት ሳስጠነቅቃቸው እንደ ነበር ታውቃላችሁ።
\s5
\v 22 እንግዲህ ተመልከቱ፤ እዚያ ምን እንደሚጠብቀኝ ሳላውቅ፣ በመንፈስ ቅዱስ ታስሬ ወደ ኢየሩሳሌም እሄዳለሁ፤
\v 23 ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ እስራትና መከራ እንደሚቆየኝ በየከተማው ይመሰክርልኛል።
\v 24 ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ኢየሱስ የተቀበልሁትን የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌል የመመስከር አገልግሎት እስከምጨርስ ድረስ፣ እንደ ውድ ነገር በመቍጠር፣ ለሕይወቴ አልሳሳላትም።
\s5
\v 25 እንግዲህ ተመልከቱ፤ የእግዚአብሔርን መንግሥት እየሰበክሁ በመካከላችሁ የዞርሁትን የእኔን ፊት ሁላችሁ ዳግመኛ እንደማታዩ ዐውቃለሁ።
\v 26 ስለዚህ ከማንም ሰው ደም ንጹሕ እንደ ሆንሁ ዛሬ እመሰክርላችኋለሁ፤
\v 27 ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሁሉ ለእናንተ ከመግለጽ ወደ ኋላ ብዬ አላውቅም።
\s5
\v 28 ስለዚህ በገዛ ራሱ ደም የገዛትን የጌታን ጉባኤ ትጠብቁ ዘንድ፣ ስለ ራሳችሁና መንፈስ ቅዱስ ጠባቂ አድርጎ እናንተን ለሾመበት፣ ለመንጋው ሁሉ ተጠንቀቁ።
\v 29 እኔ ከሄድሁ በኋላ፣ ለመንጋው ርኅራኄ የሌላቸው አጥፊ ተኵላዎች በመካከላችሁ እንደሚገቡ ዐውቃለሁ።
\v 30 ከእናንተ መካከልም እንኳ ደቀ መዛሙርትን የራሳቸው ተከታዮች ለማድረግ አንዳንድ ሰዎች መጥተው ጠማማ ነገሮችን እንደሚናገሩ ዐውቃለሁ።
\s5
\v 31 ስለዚህ ተጠንቀቁ። ሳላቋርጥ ቀንና ሌሊት፣ ሁላችሁንም ሦስት ዓመት በእንባ እንዳገለገልኋችሁም አስታውሱ።
\v 32 አሁንም ለእግዚአብሔርና ሊያንጻችሁ፣ እንዲሁም በቅዱሳን ሁሉ መካከል ርስትን ሊሰጣችሁ ለሚችለው ለጸጋው ቃል ዐደራ እሰጣችኋለሁ።
\s5
\v 33 የማንንም ብር፣ ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም።
\v 34 እነዚህ እጆቼ የእኔንም፣ ከእኔ ጋር የነበሩትንም ሰዎች ፍላጎት ሲያሟሉ እንደ ነበር እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።
\v 35 ደካሞችን በሥራ እንዴት እንደምትረዱ፣ “ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ የተባረከ ነው” የሚለውንም የጌታ ኢየሱስን ቃል እንዴት እንደምታስታውሱ በሁሉም ረገድ አርኣያ ሆንኋችሁ።
\s5
\v 36 ጳውሎስ ይህን ሁሉ ካለ በኋላ፣ ተንበርክኮ ከሁሉም ጋር ጸለየ።
\v 37 ሁሉም እጅግ በማልቀስ ዐንገቱ ላይ ተጠምጥመው ሳሙት።
\v 38 ፊቱን ዳግመኛ እንደማያዩ መናገሩም ከሁሉ በላይ አሳዘናቸው። ከዚያም እስከ መርከቡ ድረስ ሸኙት።
\s5
\c 21
\cl ምዕራፍ 21
\p
\v 1 ከእነርሱም ተለይተን የባሕር ላይ ጕዞአችንን በቀጠልን ጊዜ፣ ቀጥታ ወደ ቆስ ከተማ አመራን፤ በማግስቱም ወደ ሩድ ከተማ፣ ከዚያም ወደ ጳጥራ ከተማ ሄድን።
\v 2 ወደ ፊንቄ የሚሻገር መርከብ ባገኘን ጊዜም ተሳፍረን መጓዝ ጀመርን።
\s5
\v 3 የቆጵሮስን ደሴት ከሩቅ ባየን ጊዜ፣ ወደ ግራ ትተናት በባሕር ወደ ሶርያ ተጓዝን፤ መርከብዋ ጭነቷን የምታራግፈው በዚያ ስለ ነበር፣ ጢሮስ ወደብ ላይ ደረስን።
\v 4 ደቀ መዛሙርቱን ካገኘን በኋላም፣ በዚያ ሰባት ቀን ተቀመጥን። እነዚህም ደቀ መዛሙርት ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይገባ በመንፈስ ቅዱስ ተናገሩት።
\s5
\v 5 የምንቈይበት ጊዜ ሲገባደድ፣ ተነሥተን ጕዞአችንን ቀጠልን። ሁሉም፣ ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር ከከተማ እስክንወጣ ድረስ በመንገዳችን ሸኙን። ከዚያም እወደቡ ላይ ተንበርክከን ጸለይን፤ እርስ በርስም ተሰነባበትን።
\v 6 እኛ በመርከቡ ተሳፈርን፤ እነርሱም ወደ ቤታቸው ተመልሰው ሄዱ።
\s5
\v 7 ከጢሮስ የተነሣንበትን ጕዞ በጨረስን ጊዜ፣ አካ ደረስን። በዚያም ወንድሞችን አገኘንና አንድ ቀን ከእነርሱ ጋር ቈየን።
\v 8 በሚቀጥለው ቀን ከዚያ ተነሥተን ወደ ቂሣርያ ሄድን። ከዚያም ከሰባቱ አንዱ ወደ ሆነው፣ ወደ ወንጌል ሰባኪው ወደ ፊልጶስ ቤት ገብተን ከእርሱ ጋር ሰነበትን።
\v 9 ይህም ሰው ትንቢት የሚናገሩ አራት ደናግል ሴቶች ልጆች ነበሩት።
\s5
\v 10 የተወሰኑ ቀናት እንደ ተቀመጥንም፣ አጋቦስ የሚሉት ነቢይ ከይሁዳ ወደ ነበርንበት ወረደ።
\v 11 ወደ እኛም መጥቶ፣ የጳውሎስን መታጠቂያ ወሰደ፤ የገዛ ራሱን እጆችና እግሮችም አስሮ፣ “መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ይላል፤ ‘በኢየሩሳሌም ያሉ አይሁድ የዚህን መታጠቂያ ባለቤት እንደዚህ አድርገው ያስሩታል፤ አሳልፈውም ለአሕዛብ እጅ ይሰጡታል’” አለ።
\s5
\v 12 እነዚህን ነገሮች በሰማን ጊዜ፣ እኛና በዚያ ስፍራ የሚኖሩ ሰዎችም ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይወጣ ለመንነው።
\v 13 ጳውሎስም፣ “እያለቀሳችሁ ልቤን የምትሰብሩት ምን ማድረጋችሁ ነው? እኔኮ መታሰር ብቻ ሳይሆን፣ ለጌታችን ለኢየሱስ ስም በኢየሩሳሌም ለመሞት ዝግጁ ነኝ” ብሎ መለሰ።
\v 14 ጳውሎስ ምክር ለመቀበል እንዳልፈለገ በተረዳን ጊዜ፣ “የጌታ ፈቃድ ይሁን” ብለን መለመኑን አቆምን።
\s5
\v 15 ከእነዚህ ቀናት በኋላ፣ እኛም የጕዞ ዕቃዎቻችንን ይዘን ወደ ኢየሩሳሌም ወጣን።
\v 16 ደግሞም ከቂሣርያ የነበሩ አንዳንድ ደቀ መዛሙርት ከእኛ ጋራ መጡ። ምናሶን የሚባለውንም ሰው ይዘውት መጡ፤ እርሱም የቆጵሮስ ሰው፣ ወደ ፊት ከእርሱ ጋር እንድንቀመጥ የታሰበ የቀድሞ ደቀ መዝሙር ነበረ።
\s5
\v 17 ኢየሩሳሌም በደረስን ጊዜ፣ ወንድሞች በደስታ ተቀበሉን።
\v 18 በማግስቱም ጳውሎስ ከእኛ ጋር ወደ ያዕቆብ ሄደ፤ ሽማግሌዎችም ሁሉ በዚያ ነበሩ።
\v 19 ሰላምታ ካቀረበላቸው በኋላ፣ እግዚአብሔር በእርሱ አገልግሎት አማካይነት በአሕዛብ መካከል የሠራቸውን ነገሮች አንድ በአንድ ዘርዝሮ ነገራቸው።
\s5
\v 20 እነርሱም ስለ ሰሙት ነገር እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ እንዲህም አሉት፤ “ወንድም ሆይ፣ ከአይሁድ ያመኑት ስንትና ስንት ሺህ እንደ ሆኑ ታያለህ። ሁላቸውም ሕግን ለመጠበቅ የወሰኑ ናቸው።
\v 21 በአሕዛብ መካከል የሚኖሩት አይሁድ ሁሉ ሙሴን እንዲተዉ እንደምታስተምራቸው፣ ልጆቻቸውንም እንዳይገርዙ እንደምትነግራቸውና በቀድሞው ልማድ እንዳይሄዱ እንደምታደርግ፣ ስለ አንተ ተነግሮአቸዋል።
\s5
\v 22 እንግዲህ ምን እናድርግ? መምጣትህን እንደሚሰሙ ርግጠኞች ነን።
\v 23 ስለዚህ አሁን እኛ የምንልህን አድርግ፤ ስለት ያለባቸው አራት ሰዎች እዚህ አሉን።
\v 24 እነዚህን ሰዎች ይዘህ ከእነርሱ ጋር ራስህን አንጻ፤ ጠጕራቸውን ለመላጨት የሚያስፈልጋቸውንም ገንዘብ ክፈልላቸው። በዚህም ስለ አንተ የተነገራቸው ሁሉ ውሸት እንደ ሆነ ያውቃሉ፤ አንተም ልማዱን ጠብቀህ እንደምትኖር ይረዳሉ።
\s5
\v 25 ስላመኑ አሕዛብ ግን ለጣዖት ከተሠዋ፣ ከደም፣ ከታነቀ፣ እንዲሁም ከዝሙት ራሳቸውን እንዲጠብቁ ጽፈን ትእዛዝ ሰጥተናል።”
\v 26 ጳውሎስም ሰዎቹን ይዞ በሚቀጥለው ቀን ራሱን ከእነርሱ ጋር እያነጻ ወደ መቅደሱ ገባ፤ ይኸውም መሥዋዕቱ ስለ እያንዳንዳቸው እስከሚቀርብ ድረስ መንጻቱ የሚወስደውን ጊዜ በመንገር ነው።
\s5
\v 27 ሰባቱ ቀናት ወደ መገባደዱ ሲቃረቡ፣ ከእስያ የመጡ አንዳንድ አይሁድ ጳውሎስን በቤተ መቅደስ ውስጥ አዩት፤ ሕዝቡንም ሁሉ በእርሱ ላይ አነሣሡ፤ ያዙትም።
\v 28 እንዲህም እያሉ ይጮኹ ነበር፤ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ ርዱን። ሰዎችን ሁሉ ከሕዝቡ፣ ከሕጉና ከዚህ ስፍራ ጋር የማይስማሙ ነገሮችን የሚያስተምር ይህ ሰው ነው። ከዚህም በላይ የግሪክን ሰዎች ወደ ቤተ መቅደሱ በማስገባት፣ ይህን ቅዱስ ስፍራ የሚያረክሰውም እርሱ ነው።”
\v 29 ምክንያቱም ቀደም ሲል የኤፌሶኑን ሰው ጥሮፊሞስን ከእርሱ ጋር በከተማ ስላዩት፣ ጳውሎስ ወደ ቤተ መቅደስ ያስገባው መሰላቸው።
\s5
\v 30 ከተማውም ሁሉ ታወከ፤ ሕዝቡም በአንድነት ተሰባስበው ጳውሎስን ያዙት፤ ጐትተውም ከቤተ መቅደስ አስወጡት፤ በሮቹም ወዲያው ተዘጉ።
\v 31 ሊገድሉት ሲሞክሩም፣ መላዋ ኢየሩሳሌም እጅግ ታውካለች የሚል ወሬ ወደ ጭፍሮቹ አለቃ ደረሰ።
\s5
\v 32 እርሱም ወዲያው ወታደሮችንና የመቶ አለቆችን ይዞ ሕዝቡ ወዳሉበት በሩጫ ወረደ። ሰዎቹም ሻለቃውንና ወታደሮችን ሲያዩ፣ ጳውሎስን መደብደብ አቆሙ።
\v 33 ከዚያም ሻለቃው ወደ ጳውሎስ ሄዶ ያዘው፤ በሁለት ሰንሰለቶች እንዲታሰርም አዘዘ። ስለ ማንነቱና ስለ ፈጸመው ድርጊትም ጠየቀው።
\s5
\v 34 ከሕዝቡም ግማሾቹ ስለ አንድ ነገር ሲጮኹ፣ የቀሩት ደግሞ ስለ ሌላ ነገር ይንጫጩ ነበር። ሻለቃውም ከጫጫታው ሁሉ የተነሣ፣ ስለ ምን እንደሚጮኹ እንኳ መለየት አልቻለም፤ ስለዚህ ጳውሎስን ወደ ወታደሮች ምሽግ እንዲያገቡት አዘዘ።
\v 35 ጳውሎስ ወደ መወጣጫው ደረጃ በደረሰ ጊዜ፣ ከሕዝቡ ረብሻ የተነሣ፣ ወታደሮቹ ተሸክመውት ሄዱ።
\v 36 ሕዝቡ “አስወግደው!” እያሉና እየጮኹ ከኋላ ይከተሉ ነበር።
\s5
\v 37 ጳውሎስም ወደ ምሽጉ ሊገባ ጥቂት ሲቀረው፣ ሻለቃውን፣ “አንድ ነገር እንድናገርህ ትፈቅድልኛለህ?” አለው። ሻለቃውም፣ “የግሪክ ቋንቋ መናገር ትችላለህ ወይ?
\v 38 አንተ ከዚህ በፊት ዐመፅ አስነሥተህ፣ አራት ሺህ ሰዎችን በማስሸፈት፣ ወደ ምድረ በዳ የገባህ ግብፃዊ አይደለህምን?” አለው።
\s5
\v 39 ጳውሎስም፣ “እኔስ በኪልቅያ ከምትገኘው ከጠርሴስ ከተማ የመጣሁ አይሁዳዊ ነኝ፤ የታዋቂዋ ከተማ ዜጋ ነኝ። አንድ ነገር እለምንሃለሁ፤ ለሰዎቹ እንድናገር ፍቀድልኝ” አለው።
\v 40 ሻለቃው በፈቀደለት ጊዜም፣ ጳውሎስ መወጣጫ ደረጃው ላይ ቆሞ፣ በእጁ ወደ ሕዝቡ አመለከተ። ሕዝቡ ጸጥ እረጭ ሲልም፣ በዕብራይስጥ ቋንቋ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦
\s5
\c 22
\cl ምዕራፍ 22
\p
\v 1 “ወንድሞችና አባቶች ሆይ፣ አሁን ስለ ራሴ ለእናንተ የማቀርበውን መከላከያ አድምጡኝ።”
\v 2 ሕዝቡም ጳውሎስ በዕብራይስጥ ቋንቋ ሲያናግራቸው በሰሙ ጊዜ፣ ጸጥ አሉ። ጳውሎስም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤
\s5
\v 3 “እኔ በኪልቅያዋ ጠርሴስ የተወለድሁ አይሁዳዊ ነኝ፤ የተማርሁትም በዚሁ ከተማ በገማልያል እግር ሥር ተቀምጬ ነው። የአባቶቻችንንም ጥብቅ የሕግ መንገድ በሚገባ ተምሬአለሁ። ዛሬ እናንተ ሁላችሁ እንደ ሆናችሁት፣ እኔም ለእግዚአብሔር ቀናተኛ ነኝ።
\v 4 ይህን መንገድ እስከ ሞት አሳድጄዋለሁ፤ ሴቶችንና ወንዶችን አስሬ ለወኅኒ አሳልፌ ሰጠኋቸው።
\v 5 ደግሞም ከእነርሱ ደብዳቤ ተቀብዬ፣ በደማስቆ ስለሚገኙ ወንድሞች ወደዚያ ለመጓዝ እንደ ተነሣሁ፣ ሊቀ ካህናቱና ሽማግሌዎች ሁሉ መመስከር ይችላሉ። ከዚያ መንገድ የሆኑትን አስሬ ወደ ኢየሩሳሌም ለመምጣትና ለማስቀጣት ስንቀሳቀስም ነበር።
\s5
\v 6 እየተጓዝሁ ወደ ደማስቆ ስቃረብ፣ ቀትር ላይ ድንገት ታላቅ ብርሃን ከሰማይ በዙሪያዬ በራ፤
\v 7 እኔም መሬት ላይ ወደቅሁ፤ ከዚያም፣ 'ሳውል፣ ሳውል፣ ለምን ታሳድደኛለህ?' የሚለኝን ድምፅ ሰማሁ።
\v 8 እኔም፣ 'ጌታ ሆይ፣ አንተ ማን ነህ?' ብዬ መለስሁለት። እርሱም፣ 'አንተ የምታሳድደኝ፣ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ' አለኝ።
\s5
\v 9 ከእኔ ጋር የነበሩትም ብርሃኑን አዩ፤ ነገር ግን የተናገረኝን ድምፅ አልሰሙም።
\v 10 እኔም፣ ‘ጌታ ሆይ፣ ምን ላድረግ? አልሁ። ጌታም፣ ‘ተነሥና ወደ ደማስቆ ሂድ፤ ማድረግ የሚገባህን ሁሉ እዚያ ይነግሩሃል’ አለኝ።
\v 11 ከዚያ ብርሃን ድምቀት የተነሣም አንዳች ማየት አልቻልሁም፤ ስለዚህ ከእኔ ጋር በነበሩት ሰዎች እጅ እየተመራሁ ወደ ደማስቆ ገባሁ።
\s5
\v 12 ለሕጉ በትጋት የሚታዘዝና በዚያ የሚኖሩ አይሁድ ሁሉ መልካምነቱን የመሰከሩለት፣ ሐናንያ የሚባል አንድ ሰው አገኘሁ።
\v 13 እርሱም ወደ እኔ መጥቶ አጠገቤ በመቆም፣ ‘ወንድሜ ሳውል፣ ዐይንህን ገልጠህ እይ’ አለኝ። እኔም በዚያው ቅጽበት አየሁት።
\s5
\v 14 እርሱም እንዲህ አለኝ፤ ‘ቅዱሱን እንድታይና ከገዛ አፉ የሚወጣውን ድምፅ እንድትሰማ፣ የአባቶቻችን አምላክ ፈቃዱን እንድታውቅ መርጦሃል፤
\v 15 ምክንያቱም ስለ አየኸውና ስለ ሰማኸው ነገር ለሰዎች ሁሉ ምስክር ትሆንለታለህ።
\v 16 ስለዚህ አሁን ለምን ታመነታለህ? ተነሥ፤ ስሙን እየጠራህ ተጠመቅና ከኃጢአትህ ታጠብ።’
\s5
\v 17 ወደ ኢየሩሳሌም ከተመለስሁ በኋላም፣ በቤተ መቅደስ እየጸለይሁ ሳለሁ፣ ሸለብ አድርጎኝ ሰመመን ውስጥ ገባሁ።
\v 18 እርሱም፣ ‘ከኢየሩሳሌም ቶሎ ብለህ ውጣ፤ ምክንያቱም ስለ እኔ የምትናገረውን ምስክርነትህን አይቀበሉህም’ ሲለኝ አየሁ።
\s5
\v 19 እኔም እንዲህ አልሁ፤ ‘ጌታ ሆይ፣ በምኵራብ ሁሉ በአንተ ያመኑትን ሳስርና ስደበድብ እንደ ነበርሁ እነርሱ ራሳቸው ያውቃሉ።
\v 20 የሰማዕትህን የእስጢፋኖስንም ደም በሚያፈሱበት ጊዜ፣ በመስማማት እዚያው ቆሜ ነበር፤ የገዳዮቹንም ልብሶች እጠብቅ ነበር።’
\v 21 እርሱ ግን፣ ‘ተነሥተህ ሂድ፤ ምክንያቱም ወደ አሕዛብ እልክሃለሁ’ አለኝ።”
\s5
\v 22 ሕዝቡም እስከዚህ ድረስ እንዲናገር ፈቀዱለት፤ ከዚህ በኋላ ግን፣ “እንደዚህ ያለ ሰው ከምድር ይወገድ፤ በሕይወትም ይኖር ዘንድ አይገባውም” እያሉ ይጮኹ ጀመር።
\v 23 እየጮኹም ሳለ፣ ልብሳቸውን እያወለቁና አቧራም ወደ ላይ ይበትኑ ነበር፤
\v 24 ሻለቃውም ጳውሎስን ወደ ወታደራዊው ምሽግ እንዲወስዱት አዘዘ። እርሱ ራሱ ሕዝቡ ለምን እንደዚያ እንደ ጮኹበት ለማወቅ ስለ ፈለገ፣ እየገረፉ ጳውሎስን እንዲመረምሩት ትእዛዝ ሰጠ።
\s5
\v 25 ሰዎቹ በጠፍር ወጥረው ባሰሩት ጊዜ፣ ጳውሎስ በአጠገቡ የቆመውን መቶ አለቃ፣ “ሮማዊ የሆነን ሰው፣ ገና ሳይፈረድበት እንዲህ መግረፍህ ሕጋዊ ነው ወይ?” አለው።
\v 26 መቶ አለቃውም ይህን ሲሰማ፣ ወደ ሻለቃው ሄዶ፣ “ምን ማድረግህ ነው? ሰውየውኮ የሮማ ዜጋ ነው” በማለት ነገረው።
\s5
\v 27 ሻለቃውም መጥቶ፣ “አንተ የሮማ ዜጋ ነህን? እስቲ ንገረኝ” አለው። ጳውሎስም፣ “አዎ፣ ነኝ” አለ።
\v 28 ሻለቃውም፣ “እኔኮ ይህን ዜግነት ያገኘሁት በብዙ ገንዘብ ነው” ብሎ መለሰለት። ጳውሎስም፣ “እኔ ግን ከመወለዴ ጀምሮ ሮማዊ ነኝ” አለ።
\v 29 ሊመረምሩት የመጡ ሰዎችም ወዲያው ትተውት ሄዱ። ሻለቃውም ጳውሎስ የሮም ዜጋ መሆኑን ባወቀ ጊዜ ፈራ፤ ምክንያቱም ጳውሎስን አሳስሮት ነበር።
\s5
\v 30 በማግስቱም ሻለቃው፣ አይሁድ ጳውሎስን የከሰሱበትን ትክክለኛ ምክንያት ለማወቅ ፈለገ። ስለዚህ ጳውሎስን ከእስራት አስፈታውና የካህናት አለቆችና ሸንጎው በሙሉ እንዲሰበሰቡ አዘዘ። ከዚያም ጳውሎስን አስመጥቶ በመካከላቸው አቆመው።
\s5
\c 23
\cl ምዕራፍ 23
\p
\v 1 ጳውሎስም ትኵር አድርጎ ወደ ሸንጎው በመመልከት፣ “ወንድሞች ሆይ፣ እኔ እስካሁን ድረስ፣ በእግዚአብሔር ፊት በንጹሕ ኅሊና ሁሉ ኖሬአለሁ” አለ።
\v 2 ሊቀ ካህናቱ ሐናንያም ጳውሎስ አጠገብ የነበሩትን ሰዎች አፉን እንዲመቱት አዘዛቸው።
\v 3 በዚህ ጊዜ ጳውሎስ፣ “አንተ ነጭ ቀለም የተቀባህ ግድግዳ፣ እግዚአብሔር ይመታሃል። በሕጉ መሠረት ልትፈርድብኝ የተቀመጥህ፣ ሕጉን ጥሰህ እኔ እንድመታ ታዛለህን?” አለው።
\s5
\v 4 በአጠገቡ ቆመው የነበሩትም፣ “የእግዚአብሔርን ሊቀ ካህናት እንዴት ትሰድባለህ?” አሉ።
\v 5 ጳውሎስም፣ “ወንድሞች ሆይ፣ ሊቀ ካህናት መሆኑን አላወቅሁም፤ ምክንያቱም፣ በሕዝብህ አለቃ ላይ ክፉ ቃል ከአፍህ አይውጣ ተብሎ ተጽፎአል።”
\s5
\v 6 ጳውሎስም ከሸንጎው አባላት ከፊሉ ሰዱቃውያን፣ ሌሎቹም ፈሪሳውያን መሆናቸውን ሲያይ፣ በሸንጎ መካከል ሆኖ በከፍተኛ ድምፅ፣ “ወንድሞች ሆይ፣ እኔ የፈሪሳዊ ልጅ የሆንሁ፣ ፈሪሳዊ ነኝ። ፍርድ ፊት የቀረብሁትም የሙታን ትንሣኤ እንዳለ ስለማምን ነው” አላቸው።
\v 7 ይህን በተናገረ ጊዜ፣ በፈሪሳውያንና በሰዱቃውያን መካከል ክርክር ተነሣ፤ ጉባኤውም ተከፋፈለ።
\v 8 ምክንያቱም ሰዱቃውያን ትንሣኤ ሙታን የለም፤ መላእክትም የሉም፤ መናፍስትም የሉም ስለሚሉና፣ ፈሪሳውያን ግን እነዚህ ሁሉ አሉ ስለሚሉ ነው።
\s5
\v 9 በዚህ ጊዜ፣ ታላቅ ውካታ ሆነ፤ ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ አንዳንድ ጸሐፍትም ተነሥተው፣ “በዚህ ሰው ላይ አንድም ጥፋት አላገኘንም፤ መንፈስ ወይም መልአክ ተናግሮት እንደ ሆነስ ማን ያውቃል?” በማለት ተከራከሩ።
\v 10 ክርክሩም እየጋለ ሲሄድ፣ ጳውሎስን ይዘው እንዳይቦጫጭቁት ሻለቃው ፈራ፤ ስለዚህ ወታደሮቹ ወርደው ጳውሎስን በኀይል ይዘው ከሸንጎ አባላት መካከል እንዲወስዱትና ወደ ምሽጉ አምጥተው እንዲያስገቡት አዘዘ።
\s5
\v 11 በሚቀጥለውም ሌሊት ጌታ በጳውሎስ አጠገብ ቆሞ፣ “አትፍራ፤ በኢየሩሳሌም ስለ እኔ እንደ መሰከርኸው፣ በሮማም ደግሞ ልትመሰክር ይገባሃል” አለው።
\s5
\v 12 በነጋም ጊዜ፣ አንዳንድ አይሁድ ጳውሎስን ሳንገድል እኽል ውሃ አንቀምስም በማለት በመሐላ ተስማሙ።
\v 13 ይህን የዶለቱትም ሰዎች ቍጥር ከአርባ በላይ ነበር።
\s5
\v 14 ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ሽማግሌዎችም ሄደው እንዲህ አሉ፤ “ጳውሎስን እስከምንገድል ድረስ፣ እኽል እንዳንቀምስ በታላቅ ርግማን ተማምለናል።
\v 15 ስለዚህ አሁን ሻለቃው ጳውሎስን ወደ እናንተ እንዲያወርደውና እናንተ የእርሱን ጉዳይ ይበልጥ በትክክል እንደምታዩለት አስመስላችሁ፣ ሸንጎው ለሻለቃው ያመልክት። በእኛ በኩል ግን እዚህ ከመምጣቱ በፊትም ቢሆን ልንገድለው ዝግጁ ነን።”
\s5
\v 16 የጳውሎስ እኅት ወንድ ልጅም ጳውሎስን አድፍጠው እንደሚጠብቁት ዐወቀ፤ ሄዶም ወደ ምሽጉ ገብቶ ለጳውሎስ ነገረው።
\v 17 ጳውሎስም አንዱን መቶ አለቃ ጠራና፣ “ይህን ወጣት ወደ ሻለቃው ውሰደው፤ የሚናገረው ነገር አለውና” አለ።
\s5
\v 18 መቶ አለቃውም ወጣቱን ይዞ ወደ ሻለቃው አመጣውና እንዲህ አለ፤ “ጳውሎስ የተባለው እስረኛ ወደ ራሱ ጠርቶኝ፣ ይህን ወጣት ወደ አንተ እንዳቀርበው ለመነኝ፤ ወጣቱ ለአንተ የሚነግርህ ነገር አለው።”
\v 19 ሻለቃውም እጁን ይዞ ወደ አንድ ገለልተኛ ስፍራ ወስዶት፣ “ልትነግረኝ የፈለግኸው ነገር ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀው።
\s5
\v 20 ወጣቱም እንዲህ አለ፤ “አይሁድ ስለ ጉዳዩ ትክክለኛነት ይበልጥ ለመረዳት የፈለጉ አስመስለው፣ ነገ ጳውሎስን ወደ ሸንጎው እንድታወርደው አንተን ለመለመን ተስማምተዋል።
\v 21 ነገር ግን እሺ አትበላቸው፤ ምክንያቱም ከአርባ በላይ የሚሆኑ ሰዎች አድፍጠው እየጠበቁት ነው። ጳውሎስን ካልገደሉም እኽል ውሃ እንደማይቀምሱ ተማምለዋል። አሁንም እንኳ የአንተን መስማማት እየጠበቁ ነው እንጂ ዝግጁ ናቸው።”
\s5
\v 22 ስለዚህ ሻለቃው ወጣቱን ልጅ፣ “ስለ እነዚህ ነገሮች ለእኔ መግለጥህን ለማንም እንዳትናገር” ብሎ ካስጠነቀቀው በኋላ፣ አሰናበተው።
\v 23 ከመቶ አለቆቹም ሁለቱን ወደ ራሱ ጠርቶ፣ “እስከ ቄሣርያ ለመሄድ የሚችሉ ሁለት መቶ ወታደሮችን፣ ሰባ ፈረሰኞችንና ሁለት መቶ ባለ ጦሮችን አዘጋጁ፤ ከሌሊቱም በሦስተኛው ሰዓት ትንቀሳቀሳላችሁ” አላቸው።
\v 24 ጳውሎስ ወደ ሀገረ ገዡ፣ ወደ ፊልክስ የሚሄድበትንም ከብት እንዲያዘጋጁና በሰላም እንዲያደርሱት አዘዛቸው።
\s5
\v 25 ከዚያም እንዲህ የሚል ደብዳቤ ጻፈ፤
\v 26 “ከቀላውዴዎስ ሉስዮስ፣ ወደ ተከበረው ሀገረ ገዢ ፊልክስ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን።
\v 27 ይህን ሰው አይሁድ ይዘው ሊገድሉት ሲሉ፣ ከወታደሮች ጋር ደርሼባቸው አዳንሁት፤ ይህን ያደረግሁትም ሮማዊ ዜጋ መሆኑን ስለ ተረዳሁ ነው።
\s5
\v 28 ለምን እንደ ከሰሱት ለማወቅ ስለ ፈለግሁም፣ ወደ ሸንጎአቸው ይዤው ወረድሁ።
\v 29 የገዛ ራሳቸውን ሕግ በሚመለከት በተነሣ ጥያቄ ምክንያት ተከሶ እንጂ፣ ሞት ወይም እስራት የሚገባው ክስ እንደሌለበት ዐውቄአለሁ።
\v 30 በዚህ ሰው ላይ ሤራ እንደ ተካሄደበትም ደርሼበታለሁ፤ ስለዚህም ፈጥኜ ወደ አንተ ላክሁት፤ ከሳሾቹም በእርሱ ላይ ያላቸውን ክስ አንተ ባለህበት እንዲያቀርቡ መመሪያ ሰጥቻቸዋለሁ። በደኅና ሰንብት።”
\s5
\v 31 ስለዚህ ወታደሮቹ በታዘዙት መሠረት፣ ጳውሎስን ይዘው በሌሊት ወደ አንቲጳጥሪስ ወሰዱት።
\v 32 በሚቀጥለውም ቀን፣ አብዛኞቹ ወታደሮች ፈረሰኞቹን ከእርሱ ጋር እንዲሄዱ ትተው፣ ወደ ምሽግ ተመለሱ።
\v 33 ፈረሰኞቹም ቂሣርያ በደረሱና ደብዳቤውን ለሀገር ገዡ ሲሰጡ፣ ጳውሎስንም ለእርሱ አስረከቡት።
\s5
\v 34 ሀገረ ገዡም ደብዳቤውን ካነበበ በኋላ፣ ጳውሎስ ከየትኛው አውራጃ እንደ መጣ ጠየቀ፤ ከኪልቅያ እንደ መጣ ባወቀ ጊዜም፣
\v 35 “ከሳሾችህ ወደዚህ ሲመጡ፣ በሚገባ እሰማሃለሁ” አለው። ከዚያም በኋላ፣ በሄሮድስ ቅጥር ግቢ እንዲጠብቁት አዘዘ።
\s5
\c 24
\cl ምዕራፍ 24
\p
\v 1 ከዐምስት ቀናት በኋላ፣ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ፣ አንዳንድ ሽማግሌዎችና ጠርጠሉስ የተባለ አንድ የሕግ ባለ ሙያ ወደዚያ ሄዱ። እነዚህ ሰዎች ለገዡ አመልክተው ጳውሎስን ከሰሱት።
\v 2 ጳውሎስ በገዡ ፊት በቆመ ጊዜ፣ ጠርጠሉስ ይከሰው ጀመር፤ ገዡንም እንዲህ አለው፤ «ክቡር ፊልክስ ሆይ፣ በአንተ ምክንያት ብዙ ሰላም አግኝተናል፤ የአንተ ማስተዋልም ለሕዝባችን ጥሩ መሻሻልን ያመጣለታል፤
\v 3 ስለ ሆነም አንተ የምታደርገውን ሁሉ በፍጹም ምስጋና እንቀበለዋለን።
\s5
\v 4 ብዙ እንዳላቈይህ፣ በቸርነትህ በዐጭሩ እንድትሰማኝ እለምንሃለሁ።
\v 5 ይህ ሰው ቅንቅን ሆነና በመላው ዓለም ላይ ያሉትን አይሁዶች ሲያሳምፅ አግኝተነዋልና። የናዝራውያን ወገን መሪ ነው።
\v 6 ቤተ መቅደሱንም እንኳ ሊያረክስ ሞክሯል፤ ስለዚህ ያዝነው።
\s5
\v 7 ነገር ግን ወታደራዊው መኰንን ሉስዮስ መጥቶ፣ ጳውሎስን በኀይል ከእጃችን ወሰደው።
\v 8 አንተም ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ጳውሎስን በምትጠይቀው ጊዜ ለምን እንደምንከሰው ልታውቅ ትችላለህ።»
\v 9 አይሁድም አንድ ላይ ሆነው ጳውሎስን ከሰሱት፤ ነገሮቹም ሁሉ እውነት መሆናቸውን ተናገሩ።
\s5
\v 10 ገዡ ግን እንዲናገር ሲጠይቀው፣ ጳውሎስ እንዲህ ብሎ መልስ ሰጠ፤ «አንተ ለብዙ ዓመታት ለዚህ ሕዝብ ፈራጅ መሆንህን ዐውቃለሁ፤ ስለ ሆነም ደስ እያለኝ ስለ ራሴ እገልጽልሃለሁ።
\v 11 ለማምለክ ወደ ኢየሩሳሌም ከወጣሁ ከዐሥራ ሁለት ቀን እንደማይበልጥ አንተ መርምረህ ልትደርስበት ትችላለህ፤
\v 12 እነርሱ በቤተ መቅደስ ባገኙኝ ጊዜም፣ ከማንም ጋር አልተከራከርሁም፤ በምኵራቦችም ሆነ በከተማው ሕዝብን አልቀሰቀስሁም፤
\v 13 አሁን በእኔ ላይ የሚያቀርቡት ክስ እውነተኛ ለመሆኑ ማስረጃ የላቸውም።
\s5
\v 14 ነገር ግን ለአንተ ይህን እነግርሃለሁ፤ እነርሱ የእምነት ክፍል ብለው እንደሚጠሩት እኔም በዚያ ተመሳሳይ መንገድ የአባቶቻችንን አምላክ አገለግላለሁ። በሕግና በነቢያት ለተጻፈው ሁሉ የታመንሁ ነኝ።
\v 15 ልክ እነዚህ ሰዎች ደግሞ እንደሚጠብቁት፣ ስለሚመጣው የሙታን ማለትም የጻድቃንና የኀጥአን ትንሣኤ በእግዚአብሔር ላይ እምነት አለኝ።
\v 16 በዚህም በሁሉም ነገር በእግዚአብሕርና በሰዎች ፊት ነቀፋ የሌለበት ኅሊና እንዲኖረኝ እሠራለሁ።
\s5
\v 17 ከብዙ ዓመታትም በኋላ ለሕዝቤ ርዳታና የገንዘብ ስጦታ ለመስጠት መጣሁ።
\v 18 ይህንም ባደረግሁ ጊዜ ከእስያ የሆኑ አንዳንድ አይሁድ፣ ሕዝብም ጩኸትም ሳይኖር በቤተ መቅደስ የመንጻት ሥርዓት ላይ አገኙኝ።
\v 19 እነዚህ ሰዎች በእኔ ላይ አንዳች ነገር ካላቸው፣ በፊትህ መጥተው ክሱን ሊያቀርቡብኝ ይገባቸዋል።
\s5
\v 20 አለበለዚያም፣ እነዚሁ ሰዎች በአይሁድ ሸንጎ ፊት በቆምሁ ጊዜ፣ ምን እንዳጠፋሁ መናገር ነበረባቸው፤
\v 21 «ዛሬ አንተ የምትፈርድብኝ ስለ ሙታን ትንሣኤ ነው» ብዬ በመካከላቸው ቆሜ ድምፄን ከፍ በማድረግ ከተናገርሁት ከዚህ አንድ ነገር በቀር፣ ምንም የተናገርሁት የለም።
\s5
\v 22 ፊልክስ ግን ስለ መንገዱ በሚገባ ያውቅ ነበር፤ ስለ ሆነም፣ «አዛዡ ሉስዮስ ከኢየሩሳሌም በሚወርድበት ጊዜ ለክሳችሁ ውሳኔ እሰጣለሁ» ብሎ አይሁድን እንዲጠብቁ አደረጋቸው።
\v 23 ከዚያም ጳውሎስን እንዲጠብቀው፣ ነገር ግን እንዲያደላለት፣ እርሱንም ከመርዳት ወይም ከመጎብኘት ማንም ወዳጆቹን እንዳይከለክል የመቶ አለቃውን አዘዘው።
\s5
\v 24 ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ ፊልክስ ድሩሲላ ከምትባል አይሁዳዊት ሚስቱ ጋር ተመልሶ መጣ፤ ጳውሎስንም በማስጠራት በክርስቶስ ኢየሱስ ስላለው እምነት ከእርሱ ሰማ።
\v 25 ነገር ግን ጳውሎስ ስለ ጽድቅ፣ ራስን ስለ መግዛት፣ ስለሚመጣውም ፍርድ ከእርሱ ጋር በተነጋገረ ጊዜ፣ ፊልክስ ፈራ፤ «ለአሁኑ ሂድ፤ እንደ ገና ጊዜ ሲኖረኝ ግን፣ አስጠራሃለሁ» አለው።
\s5
\v 26 በዚሁ ጊዜ፣ ጳውሎስ ገንዘብ ይሰጠኛል ብሎ ፊልክስ ተስፋ ያደርግ ነበር፤ ስለዚህ ብዙ ጊዜ እያስጠራ ያነጋግረው ነበር።
\v 27 ከሁለት ዓመት በኋላ ግን፣ ከፊልክስ ቀጥሎ ጶርቅዮስ ፊስጦስ ገዢ ሆነ፤ ፊልክስ ግን አይሁድን ለማስደሰት ፈልጎ ጳውሎስን በጥበቃ ሥር እንዲቆይ አደረገ።
\s5
\c 25
\cl ምዕራፍ 25
\p
\v 1 ፊስጦስም ወደ ክፍለ ሀገሩ ገባ፤ ከሦስት ቀንም በኋላ ከቂሣርያ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።
\v 2 የካህናት አለቃውና ታዋቂ የሆኑት አይሁድ ጳውሎስን ፊስጦስ ላይ ከሰሱት፤ ለፊስጦስም በኀይል ተናገሩ።
\v 3 በመንገድም ላይ ሊገድሉት ጳውሎስን ወደ ኢየሩሳሌም እንዲያስጠራው ፊስጦስን ለመኑት።
\s5
\v 4 ፊስጦስ ግን መልሶ ጳውሎስ በቂሣርያ እስረኛ እንደ ሆነ፣ እርሱ ራሱም ወደዚያ እንደሚመለስ ተናገረ።
\v 5 “ስለዚህ፣ የሚችሉ ከእኛ ጋር ወደዚያ መሄድ አለባቸው። ሰውየው ያጠፋው ነገር ካለ፣ ክሰሱት” አለ።
\s5
\v 6 ፊስጦስም ስምንት ወይም ዐሥር ቀን ከቆየ በኋላ፣ ወደ ቂሣርያ ወረደ። በማግስቱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ጳውሎስን ወደ እርሱ እንዲያመጡት አዘዘ።
\v 7 ጳውሎስም በደረሰ ጊዜ፣ ከኢየሩሳሌም የመጡት አይሁድ በአጠገቡ ቆሙ፤ በማስረጃ ማረጋገጥ ያልቻሉትን ብዙ ከባድ ክስም አቀረቡ።
\v 8 ጳውሎስ፣ “በአይሁድ ስምም ላይ፣ በቤተ መቅደሱም ላይ፣ በቄሣርም ላይ በደል አልፈጸምሁም” ብሎ ራሱን ተከላከለ።
\s5
\v 9 ፊስጦስ ግን አይሁድን ለማስደሰት ፈለገ፤ ስለሆነም፣ “እስከ ኢየሩሳሌም መውጣትና ስለ እነዚህ ነገሮች በዚያ ፍርድ እንድሰጥህ ትፈልጋለህን?” ብሎ ጳውሎስን ጠየቀው።
\v 10 ጳውሎስም እንዲህ አለ፤ “ፍርድ ሊሰጠኝ በሚገባኝ በቄሣር የፍርድ ወንበር ፊት እቆማለሁ። አንተም ደግሞ በሚገባ እንደምታውቀው፣ አንድንም አይሁዳዊ አልበደልሁም።
\s5
\v 11 ብበድልና ሞት የሚገባውን ነገር አድርጌ ቢሆን እንኳ፣ አልሞትም አልልም። እነርሱ በእኔ ላይ የሚያቀርቡት ክስ ከንቱ ከሆነ ግን፣ ማንም ለእነርሱ አሳልፎ ሊሰጠኝ አይችልም። ለቄሣር ይግባኝ ብያለሁ።”
\v 12 ከዚያም ፊስጦስ ከሸንጎው ጋር ተነጋግሮ፣ “ለቄሣር ይግባኝ ብለሃልና ወደ ቄሣር ትሄዳለህ” ብሎ መለሰ።
\s5
\v 13 ከጥቂት ቀናትም በኋላ ንጉሥ አግሪጳና በርኒቄ ፊስጦስን ለመጐብኘት ቂሣርያ ደረሱ።
\v 14 ንጉሥ አግሪጳ በዚያ ብዙ ቀን ከተቀመጠ በኋላ፣ ፊስጦስ የጳውሎስን ጉዳይ ለንጉሡ አቀረበ፤ እንዲህም አለ፤ “ፊልክ አስሮ የተወው አንድ ሰው በዚህ አለ።
\v 15 እኔ በኢየሩሳሌም በነበርሁ ጊዜ የካህናት አለቆችና የአይሁድ ሽማግሌዎች ክስ መሥርተውበት ለእኔ አመለከቱ፤ እንድፈርድበትም ለመኑኝ።
\v 16 ለዚህም፣ የተከሰሰው ሰው በከሳሾቹ ፊት ቀርቦ ለተከሰሰበት ነገር እንዲከላከል ዕድል ሳይሰጠው አንድን ሰው አሳልፎ መስጠት የሮማውያን ልማድ አይደለም ብዬ መልስ ሰጠሁ።”
\s5
\v 17 ስለዚህ፣ እነርሱ በአንድ ላይ ወደዚህ በመጡ ጊዜ፣ አልዘገየሁም፤ ነገር ግን በማግስቱ በፍርድ ወንበር ተቀምጬ ሰውዬውን እንዲያመጡት አዘዝሁ።
\v 18 ከሳሾቹ ቆመው በከሰሱት ጊዜ፣ ካቀረቡበት ክሶች ማንኛቸውም ከባድ አይደሉም ብዬ ዐሰብሁ።
\v 19 ይልቁንም ስለ ገዛ ራሳቸው ሃይማኖትና ጳውሎስ ሕያው ነው ስለሚለው ሞቶ ስለ ነበረው ኢየሱስ ከእርሱ ጋር ይከራከሩ ነበር።
\v 20 ይህን ጉዳይ እንዴት እንደምመረምር ግራ ገብቶኝ ነበር፤ ስለ እነዚህ ነገሮችም በዚያ ለመፋረድ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ እንደ ሆነ ጳውሎስን ጠየቅሁት።
\s5
\v 21 ጳውሎስ ግን የንጉሠ ነገሥቱን ውሳኔ እስኪያገኝ፣ በዘብ እንዲጠበቅ ይግባኝ ባለ ጊዜ፣ ወደ ቄሣር እስክሰደው ድረስ በጥበቃ ሥር እንዲሆን አዘዝሁት።”
\v 22 አግሪጳ፣ “እኔ ደግሞ ይህን ሰው ልሰማው እፈልጋለሁ” ብሎ ፊስጦስን አነጋገረው። ፊስጦስም፣ “ነገ ትሰማዋለህ” አለው።
\s5
\v 23 ስለ ሆነም፣ በማግስቱ፣ አግሪጳና በርኒቄ በታላቅ ሥነ ሥርዓት ከወታደራዊ መኮንኖችና ከከተማዋ ታዋቂ ሰዎች ጋር ወደ አዳራሹ ገቡ። በፊስጦስ ትእዛዝም ጊዜ ጳውሎስን ወደ እነርሱ አመጡት።
\v 24 ፊስጦስም እንዲህ አለ፤ “ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፣ እዚህ ከእኛ ጋር ያላችሁትም ሰዎች ሁሉ፣ ይህን ሰው ተመልከቱት፤ በኢየሩሳሌምና እዚህም ያሉት የአይሁድ ሕዝብ ሁሉ ከእኔ ጋር ተማከሩ፤ ይህ ሰው ከእንግዲህ ወዲያ በሕይወት መኖር የለበትም ብለውም ጮኹብኝ።
\s5
\v 25 እኔ ግን ለሞት የሚያበቃው ምንም በደል አለመፍጸሙን ዐወቅሁ፤ ነገር ግን ወደ ንጉሠ ነገሥቱ ይግባኝ በማለቱ ልሰደው ወሰንሁ።
\v 26 ሆኖም ለንጉሠ ነገሥቱ ለመጻፍ አሳማኝ ነገር የለኝም። በዚህ ምክንያት ስለ ጉዳዩ የምጽፈው ነገር እንዲኖረኝ፣ በተለይ ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፣ ወደ አንተ አምጥቼዋለሁ።
\v 27 አንድን እስረኛ መስደድና የቀረበበትን ክስም አለመግለጽ ለእኔ ምክንያታዊ ያልሆነ ይመስለኛልና።”
\s5
\c 26
\cl ምዕራፍ 26
\p
\v 1 አግሪጳም ጳውሎስን፣ «አንተ ለራስህ ተናገር» አለው። ከዚያም በኋላ፣ ጳውሎስ እጁን ዘርግቶ መከላከያውን አቀረበ።
\v 2 «ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፣ ዛሬ በፊትህ አይሁድ ስለ ከፈቱብኝ ክስ ሁሉ መከላከያዬን ሳቀርብ ራሴን ደስተኛ አድርጌ እቈጥረዋለሁ፤
\v 3 ምክንያቱም በተለይ አንተ የአይሁድን ልማድና ጥያቄ ሁሉ ጠንቅቀህ ታውቃለህ። ስለዚህ በትግዕሥት እንድታደምጠኝ እለምንሃለሁ።
\s5
\v 4 በእውነት ከልጅነቴ ጀምሮ በሕዝቤ መካከልና በኢየሩሳሌም እንዴት እንደ ኖርሁ አይሁድ ሁሉ ያውቃሉ።
\v 5 ከመጀመሪያው አንሥቶ እኔን ያውቁኛል፤ የሃይማኖታችን በጣም ወግ አጥባቂ ክፍል ፈሪሳዊ ሆኜ እንደ ኖርሁም ሊያምኑ ይገባል።
\s5
\v 6 አሁን እዚህ ለፍርድ የቆምሁት እግዚአብሔር ለአባቶቻችን የሰጠውን ተስፋ የምፈልግ በመሆኔ ነው።
\v 7 በዚህ ምክንያት ዐሥራ ሁለቱ ነገዶቻችን ቀንና ሌሊት በቅንነት እግዚአብሔርን ያገለግላሉ፤ እኛም ወደ እርሱ ለመድረስ ተስፋ እናደርጋለን። ንጉሥ ሆይ፣ አይሁድ እኔን የሚከሱኝ ስለዚህ ተስፋ ነው!
\v 8 እግዚአብሔር ሙታንን እንደሚያስነሣ አይታመንም ብላችሁ ለምን ታስባላችሁ?
\s5
\v 9 አንድ ጊዜ እኔ የናዝሬቱ ኢየሱስን ስም በመቃወም ብዙ ነገር ማድረግ አለብኝ ብዬ ዐሰብሁ።
\v 10 በኢየሩሳሌምም ይህንኑ አደረግሁ፤ ከምእመናን ብዙዎችን ወኅኒ እንዲገቡ አደረግሁ፤ ለዚህም ከካህናት አለቆች ሥልጣን ተቀብዬ ነበር፤ በሚገደሉበት ጊዜም፣ ተስማምቻለው።
\v 11 ብዙ ጊዜም በምኵራቦች ሁሉ እንዲቀጡ አድርጌአለሁ፤ የስድብ ቃል እንዲናገሩም ጥረት አድርጌአለሁ። ምእመናኑን እጅግ እቈጣቸውና ሌሎች ከተሞች እንኳ አሳድዳቸው ነበር።
\s5
\v 12 ይህን እያደረግሁ፣ ከካህናት አለቆች ሥልጣንና ትእዛዝ ተቀብዬ ወደ ደማስቆ ሄድሁ፤
\v 13 ወደዚያ በመጓዝ ላይ እያለሁም ንጉሥ ሆይ፣ እኩለ ቀን ላይ ከፀሐይ ይልቅ የሚያበራ ብርሃን ከሰማይ አየሁ፤ በእኔና አብረውኝ ይጓዙ በነበሩት ሰዎች ዙሪያም አበራ።
\v 14 ሁላችንም በመሬት ላይ በወደቅን ጊዜ፣ በዕብራይስጥ ቋንቋ፣ «ሳውል፣ ሳውል፣ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የመውጊያውን ብረት ብትረግጥ ለአንተ ይከፋብሃል» የሚል ድምፅ ሲናገረኝ ሰማሁ።
\s5
\v 15 እኔም፣ 'ጌታ ሆይ፣ አንተ ማን ነህ?' አልሁ። ጌታም እንዲህ ብሎ መለሰልኝ፤ 'አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ።
\v 16 ተነሣና በእግርህ ቁም፤ እኔ የተገለጥሁልህ አሁን ስለ እኔ ስለምታውቃቸውና ኋላ ላይ ስለማሳይህ ነገሮች አገልጋዬና ምስክር እንድትሆን ልሾምህ ነው፤
\v 17 ወደ እነርሱ ከምልክህ ሕዝብና ከአሕዛብም አድንሃለሁ ፤
\v 18 ዐይናቸውን እንድትከፍትላቸውና ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከሰይጣን ኃይልም ወደ እግዚአብሔር እንድትመልሳቸው አደርግሃለሁ፤ ይኸውም በእኔ በማመናቸው ለራሴ የለየኋቸው እነርሱ፣ ከእግዚአብሔር የኃጢአትን ይቅርታና ርስትን እንዲቀበሉ ነው።'
\s5
\v 19 ስለዚህ፣ ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፣ ለሰማያዊው ራእይ አልታዘዝም አላልሁም፤
\v 20 ነገር ግን መጀመሪያ በደማስቆ ላሉት፣ ከዚያም በኢየሩሳሌም፣ በመላው ይሁዳ፣ ደግሞም ለአሕዛብ ንስሓ እንዲገቡ፣ ወደ እግዚአብሔር ዘወር እንዲሉና ለንስሓ የሚገባ ሥራ እንዲሠሩ ሰበክሁ።
\v 21 በዚህ ምክንያት አይሁድ በቤተ መቅደስ ያዙኝና ሊገድሉኝ ሞከሩ።
\s5
\v 22 እስካሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶኛል፤ ስለዚህ ለታናናሾችና ለታላላቆች ለመመስከር እዚህ ቆሜአለሁ፤ ምስክርነቴም ሙሴና ነቢያት ይሆናል ብለው ከተናገሩት የሚያልፍ አይደለም፤
\v 23 ይኸውም ክርስቶስ መከራ ይቀበላል፤ ከሙታን ለመነሣትና ለአይሁድ ሕዝብ፣ ለአሕዛብም ብርሃንን ለመስበክ የመጀመሪያው ይሆናል የሚል ነው።
\s5
\v 24 ጳውሎስም መከላከያውን እንደ ጨረሰ ፊስጦስ፣ «ጳውሎስ፣ አንተ ዕብድ ነህ፤ ብዙ መማርህ አሳብዶሃል» ሲል ጮኾ ተናገረ።
\v 25 ጳውሎስ ግን እንዲህ አለ፤ «እጅግ የተከበርህ ፊስጦስ ሆይ፣ እኔ ዕብድ አይደለሁም፤ ነገር ግን እውነተኛውንና ትክክለኛውን ቃል በድፍረት እናገራለሁ።
\v 26 ንጉሡ ስለ እነዚህ ነገሮች ያውቃልና እንደ ልብ እነግረዋለሁ፤ በመሆኑም ከእነዚህ ነገሮች አንዱም ከእርሱ የተሰወረ እንዳልሆነ እርግጠኛ ነኝ።
\s5
\v 27 ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፣ በነቢያት ታምናለህን? እንደምታምን ዐውቃለሁ።»
\v 28 አግሪጳም ጳውሎስን፣ «በአጭር ጊዜ ልታሳምነኝና ክርስቲያን ልታደርገኝ ትፈልጋለህን?» አለው።
\v 29 ጳውሎስም፣ «በአጭር ይሁን ወይም በረዥም ጊዜ፣ አንተ ብቻ ሳትሆን፣ ዛሬ የሚሰሙኝ ሁሉ፣ ከእነዚህ የወኅኒ ሰንሰለቶች በቀር እንደ እኔ እንድትሆኑ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ» አለ።
\s5
\v 30 ከዚያም ንጉሡ፣ ገዥውም፣ በርኒቄም ደግሞ፣ ከእነርሱ ጋር ተቀምጠው የነበሩትም ተነሡ፤
\v 31 ከአዳራሹም በወጡ ጊዜ፣ እርስ በርስ ተነጋግረው ፣«ይህ ሰው ለሞት ወይም ለእስራት የሚያበቃ ምንም አላደረገም» አሉ።
\v 32 አግሪጳ ፊስጦስን፣ «ይህ ሰው ወደ ቄሣር ይግባኝ ባይል ኖሮ በነጻ ሊለቀቅ ይችል ነበር» አለው።
\s5
\c 27
\cl ምዕራፍ 27
\p
\v 1 ወደ ኢጣሊያ በመርከብ እንድንሄድ በተወሰነ ጊዜ፣ ጳውሎስንና ሌሎችን እስረኞች የአውግስጦስ ክፍለ ጦር አባል ለሆነ ዩልዮስ ለተባለ የመቶ አለቃ አስረከቡአቸው።
\v 2 እኛም ከአድራሚጥዮን ተነሥተን በእስያ ጠረፍ ሊሄድ በተዘጋጀ መርከብ ላይ ተሳፍረን ወደ ባሕር ተጓዝን። በመቄዶንያ ካለችው ተሰሎንቄ የሆነው አርስጥሮኮስም ከእኛ ጋር ሄደ።
\s5
\v 3 በማግስቱ ወደ ሲዶን ከተማ ደርሰን፣ ከመርከብ ወረድን፤ እዚያም ዩልዮስ ለጳውሎስ ቸርነት አደረገለት፤ ወደ ወዳጆቹ እንዲሄድና እንክብካቤ እንዲያደርጉለትም ፈቀደለት።
\v 4 ከዚያም ተነሥተን ወደ ባሕር ሄድን፤ ነፋስ ይነፍስብን ስለ ነበር፣ በመርከብ ሆነን ነፋሱ በማያገኛት በቆጵሮስ ደሴት ዙሪያ ተጓዝን።
\v 5 በኪልቅያና በጵንፍልያ አጠገብ ያለውን ባሕር ከተሻገርን በኋላም፣ የሉቅያ ከተማ ወደ ሆነው ወደ ሙራ ደረስን።
\v 6 በዚያም፣ የመቶ አለቃው ከእስክንድርያ ወደ ኢጣሊያ የሚሄድ መርከብ አግኝቶ አሳፈረን።
\s5
\v 7 ብዙ ቀንም በዝግታ ተጓዝንና በመጨረሻ በችግር ወደ ቀኒዶስ ደረስን፤ ነፋሱም በዚያ መንገድ እንዳንሄድ ስለከለከለን፣ በሰልሙና አንጻር ያለችውን ቀርጤስን ተገን አድርገን ተጓዝን።
\v 8 በላሲያ ከተማ አጠገብ ወዳለው መልካም ወደብ ወደ ተባለው ስፍራ እስከምንደርስ ድረስ በችግር በጠረፉ በኩል ተጓዝን።
\s5
\v 9 ብዙ ጊዜም አሳለፍን፤ የአይሁድ የጾም ወራት ደግሞ ዐልፎ ነበር፤ ጕዞውን መቀጠልም አደጋ የሚያስከትል ነበር። ስለዚህ ጳውሎስ አስጠነቀቃቸው፤
\v 10 እንዲህም አለ፤ “እናንተ ሰዎች፣ አሁን የምናደርገው ጕዞ አደጋና ብዙ ጉዳት እንደሚኖርበት ይታየኛል፤ አደጋውም በመርከቡና በጭነቱ ብቻ ሳይሆን፣ በእኛም ሕይወት ላይ የሚደርስ ነው።”
\v 11 የመቶ አለቃው የሰማው ግን ጳውሎስ የተናገረውን ሳይሆን፣ በይበልጥ የመርከቡ አዛዥና ባለቤት ያሉትን ነው።
\s5
\v 12 ክረምቱን ለማሳለፍ ወደቡ ተስማሚ ስላልነበረ፣ አብዛኛዎቹ ተጓዦች የሚቻል ከሆነ ከዚያ ተነሥተን ፊንቄ ወደ ተባለችው ከተማ እንድንሄድና ክረምቱን እዚያ እንድናሳልፍ ምክር ሰጡን። ፊንቄ በሰሜን ምሥራቅና በደቡብ ምሥራቅ አንጻር የምትገኝ የቀርጤስ ወደብ ነች።
\v 13 የደቡቡ ነፋስ በቀስታ መንፈስ በጀመረ ጊዜ፣ መርከበኞቹ የፈለጉት እንደተከናወነላቸው ዐሰቡ። ስለዚህ ሸራውን አውርደው በባሕሩ ዳርቻ አቅራቢያ፣ በቀርጤስ በኩል አለፉ።
\s5
\v 14 ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን፣ የሰሜን ምሥራቅ ዐውሎ ነፋስ የተባለ ኃይለኛ ነፋስ ደሴቲቱን አቋርጦ በመምጣት ይነፍስብን ጀመረ፤
\v 15 መርከቡም ወደ ፊት በተገፋና ነፋሱን መቋቋም ባልቻለ ጊዜ፣ ዝም ብለነው በነፋሱ እየተነዳን ሄድን።
\v 16 ቄዳ የተባለችውን ትንሽ ደሴት ተተግነን ተጓዝን፤ በትልቅ ችግርም ሕይወት አድን ጀልባው ላይ መውጣት ቻልን።
\s5
\v 17 መርከበኞቹ ጀልባውን ወደ መርከቡ ጎትተው አወጡት፤ ገመዱንም የመርከቡን ዙሪያ ለማሰር ተጠቀሙበት። ስርቲስ በምትባል አሸዋማ ስፍራ እንዳንወድቅ ፈርተው ነበር፤ ስለዚህ የባሕር ሸራውን አውርደው እየተነዱ ሄዱ።
\v 18 ዐውሎ ነፋሱ በጣም ስላየለብን፣ በማግስቱ መርከበኞቹ የመርከቡን ጭነት ወደ ባሕር መጣል ጀመሩ።
\s5
\v 19 በሦስተኛው ቀን መርከበኞቹ በመርከቡ የሚያገለግሉ ዕቃዎችን እያነሡ ጣሉ።
\v 20 ለብዙ ቀንም ፀሐይና ከዋክብት ብርሃናቸውን ባልሰጡንና ትልቁ ማዕበልም በወረደብን ጊዜ፣ አንድንም ብለን ተስፋ ቈረጥን።
\s5
\v 21 ተጓዦቹ ምግብ ሳይበሉ ብዙ ቀን ቈይተው ነበር፤ በዚያን ጊዜ ጳውሎስ በተጓዦቹ መካከል ቆሞ እንዲህ አለ፤ “እናንተ ሰዎች፣ ይህ አደጋና ጉዳት እንዳይደርስባችሁ፣ ከቀርጤስ አትነሡ ብዬ የነገርኋችሁን መስማት ነበረባችሁ፤
\v 22 አሁንም መርከቡ ብቻ ይጎዳል እንጂ ከመካከላችሁ የሚሞት አይኖርምና አይዞአችሁ ብዬ እመክራችኋለሁ።
\s5
\v 23 ምክንያቱም ባለፈው ሌሊት የእርሱ የሆንሁትና ደግሞም የማመልከው የእግዚአብሔር መልአክ በአጠገቤ ቆሞ እንዲህ ብሏል፤
\v 24 “ጳውሎስ ሆይ፣ አትፍራ። በቄሣር ፊት ልትቆም ይገባሃል፤ ተመልከት፤ እግዚአብሔር በቸርነቱ ዐብረውህ የሚጓዙትን ሁሉ ሰጥቶሃል።
\v 25 ስለዚህ እናንተ ሰዎች፣ አይዞአችሁ፤ ልክ እንደ ተናገረኝ እንደሚሆን እግዚአብሔርን አምነዋለሁ።
\v 26 ነገር ግን ወደ አንዲት ደሴት ደርሰን ልናርፍ ይገባል።”
\s5
\v 27 በዐሥራ አራተኛውም ሌሊት፣ በአድርያቲክ ባሕር ወዲያና ወዲህ እየተንገላታን እያለን፣ እኩለ ሌሊት ገደማ፣ መርከበኞቹ ወደ መሬት የቀረቡ መሰላቸው።
\v 28 የባሕር ጥልቀት መለኪያ ገመድ ጣሉና ጥልቀቱን አርባ ሜትር ሆኖ አገኙት፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ መለኪያውን ሲጥሉም ሠላሳ ሜትር ሆኖ አገኙት።
\v 29 ከዐለቶቹ ጋር እንጋጫለን ብለውም ፈሩ፤ ስለዚህ ከኋላ አራት መልሕቆችን አውርደው ቶሎ እንዲነጋ ጸለዩ።
\s5
\v 30 መርከበኞቹ መርከቡን ትተው ለመሄድ መንገድ ይፈልጉና ሕይወት አድን ጀልባውን ወደ ባሕሩ ውስጥ ያወርዱ ነበር፤ መልሕቆቹንም ከቀስቱ የሚወረውሩ መሰሉ።
\v 31 ጳውሎስ ግን መቶ አለቃውንና ወታደሮቹን፣ “እነዚህ ሰዎች በመርከቡ ካልቆዩ በቀር፣ እናንተ መዳን አትችሉም” አላቸው።
\v 32 ከዚያም ወታደሮቹ የጀልባውን ገመዶች ቈረጡት፤ እንዲንሳፈፍም አደረጉት።
\s5
\v 33 ቀኑ ሊነጋ ሲልም፣ ምግብ እንዲበሉ ጳውሎስ ሁሉንም መከራቸው። እንዲህም አላቸው፤ “ምንም ሳትበሉ ከቈያችሁ ይህ ዐሥራ አራተኛ ቀናችሁ ነው።
\v 34 ስለዚህ በሕይወት እንድትኖሩ፣ ጥቂት ምግብ እንድትበሉ እለምናችኋለሁ፤ ከራሳችሁ ላይ አንዲቱም ጠጕር አትጠፋም።”
\v 35 ይህን ተናግሮ፣ እንጀራ አነሣና በሁሉም ፊት እግዚአብሔርን አመሰገነ። ከዚያም እንጀራውን ቈርሶ መብላት ጀመረ።
\s5
\v 36 በዚያን ጊዜ ሁሉም ተጽናንተው ምግብ በሉ።
\v 37 በመርከቡ ውስጥ 276 ሰዎች ነበርን።
\v 38 በልተው በጠገቡ ጊዜም፣ ስንዴውን ወደ ባሕሩ በመጣል የመርከቡን ጭነት አቃለሉ።
\s5
\v 39 በነጋታውም፣ የነበሩበትን ምድር አላወቁትም፤ ነገር ግን በዳርቻ ያለውን የባሕር ሰርጥ አዩ፤ መርከቡን ወደ ሰርጡ መግፋት ይችሉ እንደሆነም ተነጋገሩ።
\v 40 ስለዚህ መልሕቆቹን ቈርጠው ባሕሩ ላይ ተዉአቸው። በዚሁ ጊዜም የመቅዘፊያዎቹን ገመዶች ፈትተው ሸራውን ወደ ነፋሱ ከፍ አደረጉና ወደ ባሕሩ ዳርቻ ለመውጣት ሄዱ።
\v 41 ነገር ግን ሁለት ማዕበሎች ወደ ተገናኙበት ስፍራ መጡ፤ መርከቡም ወደ መሬት ገባ፤ የመርከቡ ቅስትም በዚያ ተተከለና የማይነቃነቅ ሆነ፤ የኋላ ክፍሉ ግን ከማዕበሉ ነውጥ የተነሣ ይሰባበር ጀመር።
\s5
\v 42 የወታደሮቹ ዕቅድ ከመካከላቸው ማንም ዋኝቶ እንዳያመልጥ እስረኞቹን ለመግደል ነበር።
\v 43 የመቶ አለቃው ግን ጳውሎስን ለማዳን ፈለገ፤ ስለዚህ ዕቅዳቸውን አልተቀበለም፤ መዋኘት የሚችሉትም በመጀመሪያ ከመርከቡ ላይ እየዘለሉ ወደ የብስ እንዲወጡ አዘዘ።
\v 44 ከዚያም የቀሩት ሰዎች በሳንቃዎችና ከመርከቡ በተገኙ ስብርባሪዎች ላይ ሆነው ተከትለው እንዲወጡ አደረገ። በዚህ ዐይነት ሁላችንም በደኅና ወደ የብስ ወጣን።
\s5
\c 28
\cl ምዕራፍ 28
\p
\v 1 ወደ መሬት በደኅና በደረስን ጊዜም፣ ደሴቲቱ ማልታ የምትባል መሆንዋን ዐወቅን።
\v 2 የዚያች ደሴት ሰዎችም የተለመደውን ደግነት እንኳ አላሳዩንም፤ ሆኖም፣ በማያቋርጠው ዝናብና ብርድ ምክንያት እሳት አንድደው ሁላችንንም ተቀበሉን።
\s5
\v 3 ነገር ግን ጳውሎስ ጭራሮ ሰብስቦ እሳቱ ላይ በጨመረው ጊዜ፣ ከሙቀቱ የተነሣ አንድ እፉኝት ወጣና በእጁ ላይ ተጣበቀ።
\v 4 የደሴቲቱ ሰዎችም እፉኝቱ ከእጁ ላይ ተንጠልጥሎ ባዩ ጊዜ፣ እርስ በርሳቸው፣ “ይህ ሰው በእርግጥ ከባሕር ያመለጠ ነፍሰ ገዳይ ስለ ሆነ፣ ፍትሕ በሕይወት እንዲኖር አልፈቀደለትም” ተባባሉ።
\s5
\v 5 ጳውሎስ ግን እፉኝቱን በእሳቱ ላይ አራገፈው፤ አልተጐዳምም።
\v 6 ሰዎቹም ሰውነቱ በትኵሳት ያብጣል ወይም በድንገት ይሞታል ብለው ይጠባበቁ ነበር። ነገር ግን ረዘም ላለ ጊዜ ተጠባብቀውት ምንም እንዳልደረሰበት ካዩ በኋላ፣ ዐሳባቸውን ለውጠው አምላክ ነው አሉ።
\s5
\v 7 በአቅራቢያው ባለ አንድ ስፍራም ፑብልዮስ የተባለ የደሴቲቱ ገዢ መሬት ነበር፤ እርሱም ተቀብሎን ሦስት ቀን በደግነት አስተናገደን።
\v 8 የፑብልዮስ አባት ትኵሳትና ተቅማጥ ይዞት ታሞ ነበር። ጳውሎስ ወደ እርሱ ሄዶ ጸለየ፤ እጆቹን ጫነበት፤ ፈወሰውም።
\v 9 ይህ ከሆነ በኋላ፣ በደሴቲቱ የሚኖሩ ታመው የነበሩ ሌሎች ደግሞ መጡና ተፈወሱ።
\v 10 ሰዎቹም እጅግ አከበሩን። ለመሄድ በምንዘጋጅበት ጊዜም፣ የሚያስፈልገንን ሰጡን።
\s5
\v 11 ከሦስት ወር በኋላ፣ አፍንጫው ላይ የመንታ ወንድማማች ዓርማ በነበረበት፣ ክረምቱን በደሴቲቱ ባሳለፈ የእስክንድርያ መርከብ ላይ ተሳፍረን ጕዞ ጀመርን።
\v 12 ወደ ሲራኩስ ከተማ ከደረስን በኋላም፣ እዚያ ሦስት ቀን ቈየን።
\s5
\v 13 ከዚያም ተጕዘን ወደ ሬጊዩም ከተማ ደረስን። ከአንድ ቀን በኋላ የደቡብ ነፋስ ተነሣ፤ በሁለት ቀንም ወደ ፑቲዮሉስ ከተማ መጣን።
\v 14 እዚያም አንዳንድ ወንድሞችን አገኘንና ከእነርሱ ጋር ሰባት ቀን እንድንቈይ ተጋበዝን። በዚህ ዐይነት ወደ ሮም መጣን።
\v 15 ከዚያም ወንድሞች ስለ እኛ ከሰሙ በኋላ፣ ሊቀበሉን አፍዩስ ገበያና ሦስቱ ማደሪያዎች ድረስ መጡ። ጳውሎስ ወንድሞችን ባየ ጊዜ፣ እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ተጽናናም።
\s5
\v 16 ወደ ሮም በገባን ጊዜ፣ ጳውሎስ ከሚጠብቀው ወታደር ጋር ብቻውን እንዲኖር ተፈቀደለት።
\v 17 ቀን በኋላ፣ ጳውሎስ በአይሁድ መካከል መሪዎች የነበሩትን ሰዎች አንድ ላይ ጠራ። በተሰበሰቡ ጊዜም፣ እንዲህ አላቸው፤ “ወንድሞች ሆይ፣ በሕዝቡ ወይም በአባቶች ሥርዓት ላይ የፈጸምሁት ስሕተት ባይኖርም እንኳ፣ ከኢየሩሳሌም በእስረኝነት ለሮማውያን እጅ ተላልፌ ተሰጠሁ።
\v 18 እነርሱ ከመረመሩኝ በኋላ ለሞት የሚያበቃኝ ምክንያት ስላልነበረብኝ፣ በነጻ ሊለቁኝ ፈልገው ነበር።
\s5
\v 19 ነገር ግን አይሁድ የሮማውያንን ፍላጎት ተቃውመው በተናገሩ ጊዜ፣ በሕዝቤ ላይ የማቀርበው ክስ ባይኖረኝም እንኳ፣ ወደ ቄሣር ይግባኝ ለማለት ተገደድሁ።
\v 20 በዚህ ምክንያት፣ ላያችሁና ላነጋግራችሁ ልመና አቅርቤአለሁ፤ ምክንያቱም እኔ በዚህ ሰንሰለት የታሰርሁት ለእስራኤል ስለ ተሰጠው እምነት ነው።”
\s5
\v 21 ከዚያም እነርሱ እንዲህ አሉት፤ “ከይሁዳ ስለ አንተ ደብዳቤ አልደረሰንም፤ ከወንድሞች መካከልም ስለ አንተ ያወራ ወይም ክፉ የተናገረ የለም።
\v 22 ነገር ግን በሁሉም ስፍራ ተቃውሞ እየተወራበት መሆኑን እኛ ስለምናውቅ፣ ስለዚህ የሃይማኖት ወገን ምን እንደምታስብ ከአንተ መስማት እንፈልጋለን።”
\s5
\v 23 ለጳውሎስ ቀን በቀጠሩለት ጊዜም፣ ብዙ ሰዎች ወደ መኖሪያ ቤቱ መጡ። እርሱም ጉዳዩን ገለጠላቸው፤ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትም መሰከረላቸው። ከጠዋት እስከ ማታም ከሙሴ ሕግና ከነቢያት እየጠቀሰ፣ ስለ ኢየሱስ ሊያሳምናቸው ጥረት አደረገ።
\v 24 አንዳንዶች የተናገረውን ቃል ሲያምኑ፣ ሌሎች ግን አላመኑም።
\s5
\v 25 እርስ በርሳቸው ሳይስማሙ ሲቀሩ፣ ጳውሎስ ይህን አንድ ቃል ከተናገረ በኋላ ሄዱ፤ “መንፈስ ቅዱስ በነቢዩ ኢሳይያስ አማካይነት ለአባቶቻችሁ በትክክል ተናገረ።
\v 26 እንዲህም አለ፤ ‘ወደዚህ ሕዝብ ሂድና እንደዚህ በላቸው፤ ‘መስማትስ ትሰማላችሁ፤ ነገር ግን አታስተውሉም፤ ማየትስ ታያላችሁ፤ ነገር ግን ልብ አታደርጉም።
\s5
\v 27 በዐይናቸው እንዳያዩ፣ በጆሮአቸው እንዳይሰሙ፣ በልባቸው እንዳያስተውሉ፣ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፣ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአል፤ ዐይናቸውም ተጨፍኖአል።’
\s5
\v 28-29 ስለዚህ፣ ይህ የእግዚአብሔር ድነት ወደ አሕዛብ እንደ ተላከ፣ እነርሱም እንደሚቀበሉት ዕወቁ።
\s5
\v 30 ጳውሎስ በተከራየው በራሱ ቤት ሁለት ዓመት ሙሉ ኖረ፤ ወደ እርሱ የሚመጡትንም ሁሉ ይቀበል ነበር።
\v 31 የእግዚአብሔርን መንግሥት ይሰብክ፣ ያስተምርም ነበር። ይህንም ሲያደርግ ማንም አልከለከለውም።