am_ulb/44-JHN.usfm

1674 lines
159 KiB
Plaintext
Raw Permalink Blame History

This file contains ambiguous Unicode characters

This file contains Unicode characters that might be confused with other characters. If you think that this is intentional, you can safely ignore this warning. Use the Escape button to reveal them.

\id JHN
\ide UTF-8
\h ዮሐንስ
\toc1 ዮሐንስ
\toc2 ዮሐንስ
\toc3 jhn
\mt ዮሐንስ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ፤
\v 2 ይህም ቃል ከመጀመሪያው ከእግዚአብሔር ጋር ነበር፡፡
\v 3 ሁሉም ነገር የተሠራው በእርሱ አማካይነት ነው፤ ከተሠሩት ነገሮች ሁሉ ያለ እርሱ የተሠራ አንድም ነገር አልነበረም፡፡
\s5
\v 4 በእርሱ ሕይወት ነበረ፤ያም ሕይወት የሰው ሁሉ ብርሃን ነበር፡፡
\v 5 ብርሃኑ በጨለማ ይበራል፤ ጨለማም ሊያጠፋው አልቻለም፡፡
\s5
\v 6 ከእግዚአብሔር የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበር፡፡
\v 7 ሁሉም በእርሱ እንዲያምኑ እርሱ ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ።
\v 8 ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ ዮሐንስ ራሱ ብርሃን አልነበረም፡፡
\s5
\v 9 ወደ ዓለም የሚመጣውና ለሰው ሁሉ ብርሃን ሰጭ የሆነው እውነተኛ ብርሃን እየመጣ ነበር፡፡
\s5
\v 10 እርሱ በዓለም ውስጥ ነበር፤ ዓለሙም የተሠራው በእርሱ ነው፤ ዓለም ግን አላወቀውም፤
\v 11 የራሱ ወደ ሆኑት መጣ፤ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም፡፡
\s5
\v 12 ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች የመሆንን መብት ሰጣቸው፡፡
\v 13 እነርሱም ከደምና ከሥጋ ወይም ከሰው ፈቃድ አልተወለዱም፤ ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ፡፡
\s5
\v 14 ቃል ሥጋ ሆነ፤ በመካከላችንም ዐደረ፤ እኛም ጸጋና እውነት የተሞላውን ከአብ ዘንድ ያለውን የአንድያ ልጁን ክብር አየን፡፡
\v 15 ዮሐንስ ስለ እርሱ መሰከረ፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ፣ «ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ከእኔ ይበልጣል፤ 'ከእኔ በፊት ነበርና' ያልኋችሁ ይህ ነው» ይል ነበር፡፡
\s5
\v 16 ከእርሱ ሙላት ሁላችንም በጸጋ ላይ ጸጋ ተቀበልን፤
\v 17 ሕግ በሙሴ በኩል ተሰጥቶ ነበር፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ በኩል መጣ፡፡
\v 18 በየትኛውም ጊዜ እግዚአብሔርን ያየው አንድም ሰው የለም፤ ነገር ግን በአባቱ ዕቅፍ ያለውና እርሱ ራሱ እግዚአብሔር የሆነው አንድያ ልጁ እርሱ እግዚአብሔርን እንዲታወቅ አደረገው፡፡
\s5
\v 19 አይሁድ ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን ልከው፣ «አንተ ማን ነህ?» ብለው በጠየቁት ጊዜ፣ የዮሐንስ ምስክርነት ይህ ነው፡፡
\v 20 እርሱ በግልጽ ተናገረ አልካደምም፤ ነገር ግን፣ «እኔ ክርስቶስ አይደለሁም» ብሎ መለሰላቸው።
\v 21 ስለዚህ እነርሱም፣ «ታዲያ ማን ነህ? ኤልያስ ነህን?» ብለው ጠየቁት፤ እርሱ፣ «አይደለሁም» አላቸው። እነርሱ፣ «ነቢዩ ነህን?» አሉት፤ እርሱ፣ «አይደለሁም» አለ፡፡
\s5
\v 22 ከዚያም እነርሱ፣ «ለላኩን መልስ መስጠት እንድንችል፣ አንተ ማን ነህ? ስለ ራስህስ ምን ትላለህ?» አሉት፡፡
\v 23 እርሱ፣ «ልክ ነቢዩ ኢሳይያስ እንዳለው፡- 'የጌታን መንገድ አስተካክሉ' እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ እኔ ነኝ» አላቸው፡፡
\s5
\v 24 ከፈሪሳውያን የተላኩ ሰዎችም ነበሩ።
\v 25 እነርሱ፣ «ክርስቶስ፣ ኤልያስ ወይም ነቢዩ ካልሆንህ፣ ታዲያ ለምን ታጠምቃለህ?» ብለው ጠየቁት፡፡
\s5
\v 26 ዮሐንስ፣ «እኔ በውሃ አጠምቃለሁ፤ ይሁን እንጂ እናንተ የማታውቁት በመካከላችሁ ቆሟል፤
\v 27 ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ነው፤ እኔ የጫማውን ማሰሪያ ለመፍታት እንኳ የማልበቃ ነኝ» በማለት መለሰላቸው፤
\v 28 ይህ ሁሉ የሆንው ዮሐንስ ሲያጠምቅ በነበረበት በዮርዳኖስ ማዶ በምትገኘው በቢታንያ ነበር፡፡
\s5
\v 29 በማግስቱ ዮሐንስ ኢየሱስ ወደ እርሱ ሲመጣ ተመልክቶ እንዲህ አለ፤ «እነሆ፣ የዓለምን ኀጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ይኸውና!
\v 30 'ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ በፊት ስለ ነበረ ከእኔ ይበልጣል' ብዬ ስለ እርሱ የነገርኋችሁ እርሱ ነው፡፡
\v 31 እኔ አላወቅሁትም ነበር፤ ነገር ግን እርሱ ለእስራኤል ይገለጥ ዘንድ እኔ በውሃ እያጠመቅሁ መጣሁ፡፡»
\s5
\v 32 ዮሐንስ እንዲህ ሲል መሰከረ፤ የእግዚአብሔር መንፈስ ከሰማይ እንደ ርግብ ሲወርድና በእርሱ ላይ ሲያርፍ አየሁ፡፡
\v 33 እኔ አላወቅሁትም ነበር፤ ነገር ግን በውሃ እንዳጠምቅ የላከኝ እርሱ፣ 'መንፈስ ሲወርድበትና ሲያርፍበት የምታየው፣ በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቀው እርሱ ነው' አለኝ፡፡
\v 34 እኔ ይህን አይቻለሁ፤ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነም መስክሬአለሁ፡፡»
\s5
\v 35 ደግሞም በማግስቱ፣ ዮሐንስ ከሁለት ደቀ መዛሙርቱ ጋር ቆሞ ሳለ፣
\v 36 ኢየሱስን በአጠገባቸው ሲያልፍ አዩት፤ ዮሐንስም፣ «እነሆ፣ የእግዚአብሔር በግ» አለ፡፡
\s5
\v 37 ሁለቱ ደቀ መዛሙርት፣ ዮሐንስ ይህን ሲናገር ሰምተው ኢየሱስን ተከተሉት፤
\v 38 ከዚያም ኢየሱስ መለስ ብሎ ሲከተሉት አየና፣ «ምን ትፈልጋላችሁ?» አላቸው፡፡ እነርሱ፣ «ረቢ የት ነው የምትኖረው?» አሉት። ረቢ ማለት 'መምህር' ማለት ነው።
\v 39 እርሱ፣ «ኑና እዩ» አላቸው፡፡ ከዚያም እነርሱ መጥተው የሚኖርበትን አዩ፤ በዚያም ቀን ዐብረውት ዋሉ፤ ሰዓቱም ዐሥረኛው ሰዓት ያህል ሆኖ ነበርና፡፡
\s5
\v 40 ዮሐንስ ሲናገር ሰምተው ኢየሱስን ከተከተሉት ከሁለቱ አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ ነበረ፡፡
\v 41 እርሱ በመጀመሪያ የራሱን ወንድም ጴጥሮስን አገኘውና፣ «መሲሑን አግኝተነዋል» አለው። መሲሕ 'ክርስቶስ ማለት ነው'፡፡
\v 42 ወደ ኢየሱስም አመጣው፡፡ ኢየሱስ ጴጥሮስን ተመለከተውና፣ «አንተ የዮና ልጅ ስምዖን ነህ፤ ኬፋ ትባላለህ» አለው። ኬፋ 'ጴጥሮስ ማለት ነው'፡፡
\s5
\v 43 በማግስቱ፣ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ሊሄድ በፈለገ ጊዜ፣ ፊልጶስን አግኝቶ፣ «ተከተለኝ» አለው፡፡
\v 44 ፊልጶስም ጴጥሮስና እንድርያስ ከሚኖሩበት ከተማ ከቤተ ሳይዳ ነበር፡፡
\v 45 ፊልጶስ ናትናኤልን አገኘውና፣ «ሙሴ በሕግ፣ ነቢያትም በትንቢት የጻፉለትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስ አግኝተነዋል» አለው፡፡
\s5
\v 46 ናትናኤል፣ «ከናዝሬት መልካም ነገር ይወጣልን?» አለው፡፡ ፊልጶስም መጥተህ እይ አለው፡፡
\v 47 ኢየሱስ፣ ናትናኤል ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ፣ «እነሆ፣ ተንኰል የሌለበት እውነተኛ እስራኤላዊ!» አለ።
\v 48 ናትናኤል፣ «እንዴት ታውቀኛለህ?» አለው፡፡ኢየሱስም፣ «ገና ፊልጶስ ሳይጠራህ ከበለስ ዛፍ ሥር ሳለህ አየሁህ» ብሎ መለሰለት፡፡
\s5
\v 49 ናትናኤል፣ «አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ!» ብሎ መለሰለት፡፡
\v 50 ኢየሱስ፣ «ከበለስ ዛፍ ሥር ሳለህ አየሁህ ስላልሁህ አመንህን? ገና ከዚህ የሚበልጡ ነገሮችን ታያለህ» ብሎ መለሰለት፡፡
\v 51 ኢየሱስ፣ «እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ሰማያት ሲከፈቱ መላእክትም በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ» አለ፡፡
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፤ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች።
\v 2 ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ተጠርተው ነበር፡፡
\s5
\v 3 የወይን ጠጁ ባለቀ ጊዜ፣ የኢየሱስ እናት ኢየሱስን፣ «የወይን ጠጅ እኮ ዐልቆባቸዋል» አለችው፡፡
\v 4 ኢየሱስ መልሶ፣ «አንቺ ሴት፣ ከዚህ ጋር እኔ ምን ጉዳይ አለኝ? ጊዜዬ እኮ ገና አልደረሰም» አላት፡፡
\v 5 እናቱ ለአሳላፊዎቹ፣ እርሱ «የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ» አለቻቸው፡፡
\s5
\v 6 በዚያ፣ ለአይሁድ የመንጻት ሥርዐት የሚያገለግሉ እያንዳንዳቸው ሁለት ወይም ሦስት እንስራ የሚይዙ ስድስት የድንጋይ ጋኖች ነበሩ፡፡
\v 7 ኢየሱስ፣ «ጋኖቹን ውሃ ሙሉአቸው» አላቸው፡፡ እነርሱም እስከ አፋቸው ሞሉአቸው፡፡
\v 8 ከዚያም ኢየሱስ አሳላፊዎቹን፣ «ጥቂት ቅዱና ለመስተንግዶው ኀላፊ ስጡት» አላቸው፤ እነርሱም እንዳላቸው አደረጉ፡፡
\s5
\v 9 የመስተንግዶው ኀላፊ፣ ወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ ቀመሰው፤ ከየት እንደ መጣ ግን አላወቀም፤ ውሃውን የቀዱት አሳላፊዎች ግን ያውቁ ነበር፡፡ እርሱም ሙሽራውን ጠርቶ
\v 10 «ሰው ሁሉ መልካሙን ወይን ጠጅ በመጀመሪያ ያቀርባል፤ መናኛውን ሰዎች ከሰከሩ በኋላ ነው የሚያቀርበው፤ አንተ ግን መልካሙን የወይን ጠጅ እስካሁን ድረስ አቈይተሃል» አለው፡፡
\s5
\v 11 ይህ በገሊላ ቃና የተደረገው ተአምር ኢየሱስ ካደረጋቸው ተአምራዊ ምልክቶች የመጀመሪያ ነው፤ ክብሩንም ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።
\s5
\v 12 ከዚህ በኋላ ከእናቱ፣ ከወንድሞቹና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፤ በዚያም ጥቂት ቀናት ቈዩ፡፡
\s5
\v 13 የአይሁድ ፋሲካ ቀርቦ ስለ ነበረ፣ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ፡፡
\v 14 በቤተ መቅደስ ውስጥ በሬዎችን፣ በጎችንና ርግቦችን ሲሸጡ የነበሩ ሰዎችን አገኘ፡፡ ገንዘብ ለዋጮችም ደግሞ በዚያ ተቀምጠው ነበር፡፡
\s5
\v 15 እርሱም የገመድ ጅራፍ አበጅቶ በጎችንና ከብቶችን ጭምር ሁሉንም ከቤተ መቅደስ አስወጣቸው፤ የገንዘብ ለዋጮችንም ገንዘብ በተነ፤ ጠረጴዛዎቻቸውንም ገለባበጠ።
\v 16 ርግብ ሻጮችንም፣ «እነዚህን ከዚህ አስወጧቸው፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት ማድረጋችሁን አቁሙ!» አላቸው።
\s5
\v 17 ደቀ መዛሙርቱ፣ «ለቤትህ ያለኝ ቅናት ይበላኛል» ተብሎ የተጻፈውን አስታወሱ፡፡
\v 18 ከዚያም የአይሁድ ባለ ሥልጣኖች፣ «እነዚህን ነገሮች ለማድረግ መብት እንዳለህ ምን ምልክት ታሳየናለህ?» በማለት መለሱለት፡፡
\v 19 ኢየሱስ፣ «ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፤ እኔ በሦስት ቀን አስነሣዋለሁ» ብሎ መለሰ፡፡
\s5
\v 20 ከዚያም አይሁድ፣ «ይህን ቤተ መቅደስ ለመገንባት ዐርባ ስድስት ዓመት ፈጅቶአል፤ አንተ በሦስት ቀን መልሰህ ታስነሣዋለህ?» አሉት።
\v 21 ይሁን እንጂ፣ እርሱ ቤተ መቅደስ ብሎ የተናገረው፣ ስለ ራሱ ሰውነት ነበር።
\v 22 ከሙታን ከተነሣም በኋላ፣ ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ ይህን እንደ ተናገረ አስታወሱ፤ መጻሕፍትንና ኢየሱስ የተናገረውንም ቃል አመኑ።
\s5
\v 23 በፋሲካ በዓል በኢየሩሳሌም ሳለ፣ ያደረጋቸውን ተአምራት አይተው ብዙዎች በስሙ አመኑ።
\v 24 ሆኖም፣ ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ያውቅ ስለ ነበር፣ እነርሱን አላመናቸውም፤
\v 25 ደግሞም በሰው ውስጥ ያለውን ያውቅ ስለ ነበር፣ ማንም ስለ ሰው እንዲመሰክርለት አያስፈልገውም ነበር።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 ከፈሪሳውያን ወገን የሆነ፣ ስሙ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ የአይሁድ ሸንጎ አባል ነበር ፤
\v 2 ይህ ሰው በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ፣ «መምህር ሆይ፣ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ክሆነ ሰው በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ማንም ማድረግ ስለማይችል፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣህ መምህር መሆንህን እናውቃለን» አለው።
\s5
\v 3 ኢየሱስ፣ «እውነት እልሃለሁ፣ ሰው ዳግም ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም» ብሎ መለሰለት።
\v 4 ኒቆዲሞስ፣ «ሰው ካረጀ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ወደ እናቱ ማኅፀን ዳግመኛ ገብቶ ሊወለድ ይችላልን?» አለው።
\s5
\v 5 ኢየሱስ መልሶ፣ «እውነት፣ እውነት፣ እልሃለሁ፣ ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።
\v 6 ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው።
\s5
\v 7 'ዳግም መወለድ አለባችሁ' ስላልሁህ አትደነቅ፤
\v 8 ነፋስ ወደ ፈለገው ይነፍሳል፤ ድምፁን ትሰማለህ፣ ነገር ግን ከየት እንደ መጣ፣ ወዴትም እንደሚሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስም የተወለደ ሁሉ እንደዚሁ ነው።»
\s5
\v 9 ኒቆዲሞስ፣ «ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?» በማለት መለሰ።
\v 10 ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ «አንተ የእስራኤል መምህር ሆነህ ሳለ እነዚህን ነገሮች አታውቅምን?
\v 11 እውነት፣ እውነት፣ እልሃለሁ፤ የምናውቀውን እንናገራለን፤ ያየነውንም እንመሰክራለን፤ እናንተ ግን ምስክርነታችንን አትቀበሉም።
\s5
\v 12 ስለ ምድራዊው ነገር ነግሬአችሁ ያላመናችሁ፣ ስለ ሰማያዊው ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ?
\v 13 ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር፣ ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም።
\s5
\v 14 ሙሴ እባብን በምድረ በዳ እንደ ሰቀለ፣ እንዲሁ የሰው ልጅ ሊሰቀል ይገባዋል።
\v 15 ይህም በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው ነው።
\s5
\v 16 በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና፤
\v 17 እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም የላከው በዓለም ላይ ለመፍረድ ሳይሆን፣ ዓለምን በእርሱ ለማዳን ነው።
\v 18 በእርሱ የሚያምን ሁሉ አይፈረድበትም፤ በእርሱ የማያምን ግን በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ፣ አሁኑኑ ተፈርዶበታል።
\s5
\v 19 የፍርዱ ምክንያት ይህ ነው፤ ብርሃን ወደ ዓለም መጣ፤ ሰዎች ግን ሥራቸው ክፉ ስለ ነበረ፣ ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ወደዱ፤
\v 20 ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላል፤ ድርጊቱም እንዳይገለጥበት ወደ ብርሃን አይመጣም።
\v 21 እውነትን በተግባር ላይ የሚያውል ሰው ግን ሥራው እግዚአብሔርን በመታዘዝ የተፈጸመ መሆኑ በግልጽ እንዲታይ ወደ ብርሃን ይመጣል።»
\s5
\v 22 ከዚህ በኋላ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ይሁዳ አገር ሄዱ፤ በዚያ ከእነርሱ ጋር ቆየ፤ ያጠምቅም ነበር፤
\v 23 በዚህ ጊዜ ዮሐንስም በሳሌም አቅራቢያ ሄኖን በተባለ ስፍራ ብዙ ውሃ ስለ ነበረ፣ ያጠምቅ ነበር፤ ሰዎችም ወደ እርሱ እየመጡ ይጠመቁ ነበር።
\v 24 ምክንያቱም ዮሐንስ ገና በወኅኒ አልተጣለም ነበር።
\s5
\v 25 ከዚያም በዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና በአንድ አይሁዳዊ መካከል ስለ መንጻት ሥርዐት ክርክር ተነሣ።
\v 26 ደቀ መዛሙርቱ ወደ ዮሐንስም መጥተው፣ «መምህር ሆይ፣ በዮርዳኖስ ማዶ ከአንተ ጋር የነበረው ስለ እርሱ የመሰከርክለት ሰው፣ እነሆ እያጠመቀ ነው፤ ሁሉም ወደ እርሱ እየሄዱ ነው አሉት።»
\s5
\v 27 ዮሐንስ መልሶ እንዲህ አለ፤ «ሰው ከሰማይ ካልተሰጠው በቀር ምንም ነገር ሊቀበል አይችልም።
\v 28 'እኔ ክርስቶስ አይደለሁም' ነገር ግን 'ከእርሱ በፊት ተልኬአለሁ' ማለቴን እናንተ ራሳችሁ ትመሰክራላችሁ።
\s5
\v 29 ሙሽሪት ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው፤ አጅቦት ቆሞ የሚሰማው ሚዜው በሙሽራው ድምፅ እጅግ ደስ ይለዋል። አሁን ይህ ደስታዬ ፍጹም ሆኖእል።
\v 30 እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ይገባል።
\s5
\v 31 ከላይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የሆነው የምድር ነው የምድሩንም ይናገራል። ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው።
\v 32 እርሱ ያየውንና የሰማውን ይመሰክራል፤ ነገር ግን ምስክርነቱን ማንም አይቀበልም።
\v 33 ምስክርነቱን የተቀበለ ሰው የእግዚአብሔርን እውነተኝነት አረጋግጧል።
\s5
\v 34 እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራል፤ እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥምና።
\v 35 አብ ወልድን ይወዳል ሁሉንም ነገር በእጁ ሰጥቶታል።
\v 36 በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ ለልጁ የማይታዘዝ ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በላዩ ይሆናል እንጂ ሕይወትን አያይም።»
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 ፈሪሳውያን ኢየሱስ ከዮሐንስ የበለጠ ብዙ ሰዎችን ደቀ መዛሙርት እንደሚያደርግና እንደሚያጠምቅ ሰሙ፤ ኢየሱስም ይህን ዐወቀ፤
\v 2 (ያጠምቁ የነበሩት ደቀ መዛሙርቱ እንጂ እርሱ ባይሆንም)፣ ኢየሱስ መስማታቸውን ባወቀ ጊዜ
\v 3 የይሁዳን ምድር ለቅቆ ወደ ገሊላ ሄደ።
\s5
\v 4 በሰማርያም በኩል ማለፍ ነበረበት።
\v 5 ከዚያም በሰማርያ ከተማ፣ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ቦታ አጠገብ ወደምትገኝ፣ ሲካር ወደምትባል ቦታ መጣ።
\s5
\v 6 በዚያም የያዕቆብ የውሃ ጒድጓድ ነበረ፤ ኢየሱስ ከጒዞው ብዛት ደክሞት ስለ ነበር፣ በውሃው ጒድጓድ አጠገብ ተቀመጠ፤ ጊዜውም እኩለ ቀን አካባቢ ነበር።
\v 7 አንዲት ሳምራዊት ሴት ውሃ ልትቀዳ ስትመጣ፣ ኢየሱስ፣ «እባክሽ የምጠጣው ውሃ ስጪኝ» አላት።
\v 8 ደቀ መዛሙርቱ ምግብ ለመግዛት ወደ ከተማ ሄደው ነበር።
\s5
\v 9 ሳምራዊቷም ሴት፣ «አንተ አይሁዳዊ ሆነህ፣ እኔን ሳምራዊቷን ሴት እንዴት ውሃ አጠጪኝ ትለኛለህ?» አለችው። አይሁድ ከሳምራውያን ጋር አይተባበሩም ነበርና።
\v 10 ኢየሱስ፣ «የእግዚአብሔርን ስጦታና ውሃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን እንደሆነ ዐውቀሽ ቢሆን ኖሮ ፣ አንቺው በጠየቅሽው፣ እርሱም ሕያው ውሃ በሰጠሽ ነበር» ብሎ መለሰላት።
\s5
\v 11 ሴትዮዋም እንዲህ አለችው፤ «ጌታ ሆይ፣ አንተ መቅጃ የለህም፤ ጒድጓዱም ጥልቅ ነው፤ ታዲያ ሕያዉን ውሃ ከየት ታገኛለህ?
\v 12 አንተ፣ ይህን ጒድጓድ ከሰጠን፣ ከአባታችን ከያዕቆብ ትበልጣለህን? እርሱ ራሱ፣ ልጆቹና ከብቶቹም ከዚሁ ጒድጓድ ጠጥተዋል።
\s5
\v 13 ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላት፤ «ከዚህ ውሃ የሚጠጣ ሁሉ እንደ ገና ይጠማል፤
\v 14 እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ግን ፈጽሞ ዳግመኛ አይጠማም፤ ይልቁንም፣ እኔ የምሰጠው ውሃ፣ ከውስጡ የሚፈልቅ የዘላለም ሕይወት ውሃ ምንጭ ይሆናል።»
\s5
\v 15 ሴትዮዋም፣ «ጌታዬ፤ ከእንግዲህ እንዳልጠማና ውሃ ለመቅዳት ወደዚህ እንዳልመጣ፣ ይህን ውሃ ስጠኝ» አለችው።
\v 16 ኢየሱስም፣ «ሂጂ፣ ባልሽን ጥሪና ወደዚህ ተመልሰሽ ነይ» አላት።
\s5
\v 17 ሴትዮዋ፣ «ባል የለኝም» በማለት መለሰች፤ ኢየሱስ፣ 'ባል የለኝም' በማለትሽ ልክ ነሽ፤
\v 18 አምስት ባሎች ነበሩሽና፤ አሁን ከአንቺ ጋር ያለው ሰው ባልሽ አይደለም፤ ስለዚህ እውነቱን ተናግረሻል» ብሎ መለሰ።
\s5
\v 19 ሴትዮዋ፣ «ጌታ ሆይ፣ አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ ይገባኛል፤
\v 20 አባቶቻችን በዚህ ተራራ ላይ ሰገዱ፤ እናንተ ግን ሰው መስገድ ያለበት በኢየሩሳሌም ነው ትላላችሁ» አለችው።
\s5
\v 21 ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላት፤ «አንቺ ሴት፣ በዚህ ተራራም ሆነ በኢየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ እየመጣ መሆኑን እመኚኝ።
\v 22 እናንተ ሳምራውያን ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ። እኛ ግን፣ ድነት ከአይሁድ ስለ ሆነ፣ ለምናውቀው እንሰግዳለን።
\s5
\v 23 ይሁን እንጂ፣ በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ አሁንም መጥቶአል፤ አብ እንደዚህ በእውነት የሚሰግዱለትን ሰዎች ይፈልጋልና።
\v 24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ይገባል።»
\s5
\v 25 ሴትዮዋ፣ «ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንደሚመጣ ዐውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉንም ነገር ይነግረናል» አለችው።
\v 26 ኢየሱስ፣ «አሁን እያነጋገርሁሽ ያለሁት እኔ እርሱ ነኝ» አላት።
\s5
\v 27 ልክ በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ተመልሰው መጡ፤ ኢየሱስ ከሴት ጋር በመነጋገሩ ተገረሙ፤ ይሁን እንጂ፣ ማንም፣ «ምን ትፈልጋለህ? ወይም ከእርስዋ ጋር ለምን ትነጋገራለህ?» ያለው የለም።
\s5
\v 28 ሴትዮዋ እንስራዋን ትታ ወደ ከተማ ተመለሰች፤ ለሕዝቡም፣
\v 29 «ያደረግሁትን ነገር ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ፤ እርሱ ክርስቶስ ይሆንን?» አለች፤
\v 30 ሕዝቡ ከከተማ ወጥተው እርሱ ወዳለበት መጡ።
\s5
\v 31 በዚህም መሐል ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን፣ «መምህር ሆይ፣ ምግብ ብላ» አሉት።
\v 32 እርሱ ግን፣ «እናንተ የማታውቁት፣ የምበላው ምግብ አለኝ» አላቸው።
\v 33 ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ እርስ በርስ፣ «ምግብ ያመጣለት ሰው ይኖር ይሆን?» ተባባሉ።
\s5
\v 34 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ «የእኔ ምግብ የላከኝን ፈቃድ ማድረግና ሥራውንም መፈጸም ነው።
\v 35 እናንተ 'መከር ገና አራት ወር ቀርቶታል፤ ከዚያም መከሩ ይመጣል' ትሉ የለምን? ቀና በሉና ዕርሻዎቹን ተመልከቱ፣ መከሩ ደርሷልና እያልኋችሁ ነው፤
\v 36 የሚያጭድ ደመወዙን ይቀበላል፤ ለዘላለም ሕይወት የሚሆን ፍሬም ይሰበስባል፤ ስለዚህ የሚዘራውም፣ የሚያጭደውም አብረው ይደሰታሉ።
\s5
\v 37 'አንዱ ይዘራል፣ ሌላውም ያጭዳል' የሚለው አባባል እውነት የሚሆነው በዚህ ምክንያት ነው።
\v 38 እኔ ያልደከማችሁበትን እንድታጭዱ ላክኋችሁ፤ ሌሎች በሥራ ደከሙ፤ እናንተም በእነርሱ ሥራ ገባችሁ።»
\s5
\v 39 ሴትዮዋ፣ «ያደረግሁትን ሁሉ ነገረኝ» ብላ ስለ እርሱ በሰጠችው ምስክርነት የተነሣ፣ በዚያች ከተማ ከሚኖሩ ሳምራውያን ብዙዎቹ በእርሱ አመኑ።
\v 40 ስለዚህ፣ ሳምራውያኑ ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ፣ ከእነርሱ ጋር እንዲቈይ ለመኑት፤ እዚያም ሁለት ቀን ቈየ።
\s5
\v 41 ከቃሉም የተነሣ ሌሎች ብዙ ሰዎች አመኑ።
\v 42 ሴትዮዋንም፣ «የምናምነው አንቺ ስለ ነገርሽን ቃል ብቻ አይደለም፤ እኛ ራሳችን ሰምተነዋል፤ ይህ ሰው በእውነት የዓለም አዳኝ እንደ ሆነ እናውቃለን» ይሏት ነበር።
\s5
\v 43 ከእነዚያ ሁለት ቀናት በኋላም ከዚያ ተነሥቶ ወደ ገሊላ ሄደ።
\v 44 ነቢይ በገዛ አገሩ እንደማይከበር ኢየሱስ ራሱ ተናግሮ ነበርና።
\v 45 ወደ ገሊላ በደረሰ ጊዜ፣ የገሊላ ሰዎች በደስታ ተቀበሉት፤ እነርሱ በፋሲካ በዓል ወደዚያ ሄደው ስለ ነበር፣ በኢየሩሳሌም ያደረጋቸውን ነገሮች ሁሉ አይተው ነበር። እነርሱ ደግሞ ወደ በዓሉ ሄደው ነበርና።
\s5
\v 46 ኢየሱስም ውሃውን የወይን ጠጅ ወዳደረገባት፣ በገሊላ ወደምትገኘው ወደ ቃና ከተማ ዳግመኛ መጣ፤ በቅፍርናሆምም ልጁ የታመመበት አንድ ከንጉሣዊ ቤተ ሰብ የሆነ ሹም ነበር፤
\v 47 እርሱም ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ መምጣቱን በሰማ ጊዜ፣ ወደ እርሱ ሄደና በሞት አፋፍ ላይ የሚገኘውን ልጁን መጥቶ እንዲፈውስለት ለመነው።
\s5
\v 48 ከዚያም ኢየሱስ፣ «እናንተ ሰዎች ምልክቶችንና ድንቆችን ካላያችሁ አታምኑም» አለው።
\v 49 ሹሙ፣ «ጌታ ሆይ፤ ልጄ ከመሞቱ በፊት እባክህ ውረድ» አለው።
\v 50 ኢየሱስ፣ «ሂድ፤ ልጅህ በሕይወት ይኖራል» አለው። ሰውየው ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አምኖ ሄደ።
\s5
\v 51 በመንገድ ላይ ሳለም፣ አገልጋዮቹ አገኙትና ልጁ ተሽሎት በሕይወት እንዳለ ነገሩት።
\v 52 እርሱም ልጁ የተሻለው በስንት ሰዓት ላይ እንደ ነበረ ጠየቃቸው። እነርሱም፣ «ትኵሳቱ የለቀቀው ትናንት በሰባተኛው ሰዓት ላይ ነበር» አሉት።
\s5
\v 53 አባትየውም፣ ኢየሱስ «ልጅህ በሕይወት ይኖራል» ብሎት የነበረው በዚያ ሰዓት እንደ ነበረ ተገነዘበ፤ ስለዚህ እርሱ ራሱና ቤተ ሰቡ በሙሉ በኢየሱስ አመኑ።
\v 54 ይህም ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ በመጣ ጊዜ ያደረገው ሁለተኛው ምልክት ነው።
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ የአይሁድ በዓል ነበረ፤ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።
\v 2 በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ፣ አምስት ጣሪያ ያላቸው መመላለሻዎች ነበሩ። በዚያ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የሚባል አንድ መጠመቂያ ነበረ።
\v 3 በእነዚህ መመላለሻዎች ወለል ላይ በጣም ብዙ ሕሙማን፣ ዐይነ ስውሮች፣ አንካሶች ወይም ሽባዎች ተኝተው ነበር።
\v 4
\f + \ft አንዳንድ የጥንት ጽሑፎች ይህ ጥቅስ አላቸው፣ ሌሎች ግን ዘለውታል። \f*
«ዐልፎ ዐልፎ የጌታ መልአክ መጥቶ ውሃውን በሚያናውጥበት ጊዜ፣ ቀድሞ ወደ መጠመቂያው የገባ ሰው ከሚሠቃይበት ከማንኛውም በሽታ ይፈወስ ነበር» የሚለውን ክፍል እንድትተዉት እንመክራለን።
\s5
\v 5 በዚያም ለሠላሳ ስምንት ዓመት ሽባ ሆኖ የኖረ አንድ ሰው ነበረ።
\v 6 ኢየሱስ ሰውየውን እዚያ ተኝቶ ባየው ጊዜ፣ ለረጅም ጊዜ በዚያ መቆየቱን ዐውቆ፣ «መዳን ትፈልጋለህን?» አለው።
\s5
\v 7 ሕመምተኛውም ሰው መልሶ፣ «ጌታ ሆይ፣ ውሃው በሚናወጥበት ጊዜ መጠመቂያው ውስጥ የሚያስገባኝ ሰው የለኝም፤ ለመግባትም ስሞክር ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል» አለው።
\v 8 ኢየሱስ፣ «ተነሥ! የተኛህበትን ምንጣፍ ተሸክመህ ሂድ» አለው።
\s5
\v 9 ሰውየው ወዲያውኑ ተፈወሰ፤ የተኛበትንም ምንጣፍ ተሸክሞ ሄደ። ያም ቀን ሰንበት ነበረ።
\s5
\v 10 ስለዚህ የአይሁድ መሪዎች የተፈወሰውን ሰው፣ «ሰንበት ነው፤ ምንጣፍህን ልትሸከም አልተፈቀደልህም» አሉት።
\v 11 እርሱ ግን፣ «ያ ያዳነኝ ሰው፣ 'የተኛህበትን ምንጣፍ ተሸክመህ ሂድ'» አለኝ ብሎ መለሰላቸው።
\s5
\v 12 እነርሱም፣ «የተኛህበትን ምንጣፍ ተሸክመህ ሂድ» ያለህ ሰው ማን ነው?» ብለው ጠየቁት።
\v 13 የተፈወሰው ሰው ግን ኢየሱስ ከአጠገቡ ፈቀቅ ስላለና በስፍራው ብዙ ሕዝብ ስለ ነበር፣ ማን እንደ ፈወሰው አላወቀም።
\s5
\v 14 በኋላ ኢየሱስ ያን ሰው በቤተ መቅደስ አግኝቶት፣ «እነሆ፣ ተፈውሰሃል፤ ከዚህ የባሰ ነገር እንዳይደርስብህ ከእንግዲህ ኀጢአት አትሥራ» አለው።
\v 15 ሰውየው ሄዶ የፈወሰው ኢየሱስ መሆኑን ለአይሁድ መሪዎች ነገራቸው።
\s5
\v 16 ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች በሰንበት ስላደረገ፣ የአይሁድ መሪዎች ኢየሱስን ያሳድዱት ነበር።
\v 17 ኢየሱስ፣ «አባቴ እስካሁን እየሠራ ነው፤ እኔም እሠራለሁ» አላቸው።
\v 18 በዚህ ምክንያት አይሁድ ኢየሱስ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔርን አባቴ ነው በማለት፣ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር እኩል ስላደረገ፣ ሊገድሉት አጥብቀው ይፈልጉ ነበር።
\s5
\v 19 ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አላቸው፤ «እውነት እላችኋለሁ፣ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ምንም ሊያደርግ አይችልም፤ አብ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድም ያንኑ ያደርጋልና።
\v 20 አብ ወልድን ይወዳልና፣ የሚያደርገውንም ሁሉ ያሳየዋል፤ እናንተም ትደነቁ ዘንድ ከዚህ የሚበልጥ ነገር ያሳየዋል።
\s5
\v 21 አብ ሙታንን እንደሚያስነሣና ሕይወትንም እንደሚሰጣቸው፣ ወልድም ደግሞ ለሚፈልገው ሁሉ ሕይወትን ይሰጣል።
\v 22 አብ በማንም ላይ አይፈርድም፤ ነገር ግን ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጥቶታል፤
\v 23 ይኸውም፣ ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ ነው፤ ወልድን የማያከብር፣ የላከውን አብንም አያከብርም።
\s5
\v 24 እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማ፣ በላከኝም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ ከሞት ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ አይፈረድበትም።
\s5
\v 25 እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ሙታን የእኔን፣ የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ አሁንም መጥቶአል፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ።
\s5
\v 26 አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው ሁሉ፣ ወልድም በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና፤
\v 27 ወልድ የሰው ልጅ ስለ ሆነ፣ አብ የመፍረድን ሥልጣን ለወልድ ሰጥቶታል።
\s5
\v 28 በዚህ አትደነቁ፤ በመቃብር ውስጥ ያሉ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ጊዜ ይመጣል፤
\v 29 መልካም የሠሩ ለሕይወት ትንሣኤ፣ ክፉ የሠሩም ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉ።
\s5
\v 30 እኔ ከራሴ ምንም ማድረግ አልችልም፤ የምፈርደው በሰማሁት መሠረት ነው፤ የላከኝን ፈቃድ እንጂ የራሴን ፈቃድ ስለማልሻም፣ ፍርዴ ትክክል ነው።
\v 31 እኔው ስለ ራሴ ብመሰክር፣ ምስክርነቴ እውነት አይደለም።
\v 32 ስለ እኔ የሚመሰክር ሌላ አለ፤ እርሱ ስለ እኔ የሚሰጠውም ምስክርነት እውነት እንደ ሆነ ዐውቃለሁ።
\s5
\v 33 ወደ ዮሐንስ ልካችሁ ነበር፤ እርሱም ስለ እውነት መስክሮአል፤
\v 34 ይሁን እንጂ፣ እኔ የሰው ምስክርነት የምቀበል አይደለሁም፤ ነገር ግን ይህን የምናገረው እናንተ እንድትድኑ ነው።
\v 35 ዮሐንስ እየነደደ ብርሃን የሚሰጥ መብራት ነበረ፤ እናንተም ለጥቂት ጊዜ በብርሃኑ ሐሤት ልታደርጉ ፈለጋችሁ።
\s5
\v 36 እኔ ያለኝ ምስክርነት ግን ከዮሐንስ ምስክርነት ይበልጣል፡፡ አብ እንድፈጽመው የሰጠኝ፣ እኔም እየሠራሁት ያለሁት ሥራ አብ እንደ ላከኝ ይመሰክራል።
\v 37 የላከኝ አብ እርሱ ስለ እኔ መስክሮአል፤ እናንተም ከቶ ድምፁን አልሰማችሁም፤ መልኩንም አላያችሁም፤
\v 38 እርሱ በላከው አላመናችሁምና ቃሉ በእናንተ አይኖርም።
\s5
\v 39 በእነርሱ የዘላለምን ሕይወት የምታገኙ ስለሚመስላችሁ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ ይመሰክራሉ፤
\v 40 እናንተ ወደ እኔ መጥታችሁ ሕይወት ማግኘት አትፈልጉም።
\s5
\v 41 እኔ ከሰው ክብር አልቀበልም፤
\v 42 ነገር ግን የእግዚአብሔር ፍቅር በእናንተ ውስጥ እንደሌለ ዐውቃለሁ።
\s5
\v 43 እኔ በአባቴ ስም መጥቼ አልተቀበላችሁኝም፤ ሌላው በራሱ ስም ቢመጣ ግን ትቀበሉታላችሁ።
\v 44 እናንተ አንዳችሁ ከሌላችሁ ክብር የምትቀበሉ፣ ነገር ግን ከአንዱ አምላክ የሚመጣውን ክብር የማትሹ ከሆነ፣ እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ?
\s5
\v 45 በአብ ፊት የምከሳችሁ እኔ አልምሰላችሁ፤ የሚከሳችሁ ሌላ አለ እርሱም ተስፋ ያደረጋችሁበት ሙሴ ነው።
\v 46 ሙሴን ብታምኑ ኖሮ፣ እኔን ባመናችሁ ነበር፤ ምክንያቱም እርሱም የጻፈው ስለ እኔ ነው።
\v 47 ታዲያ እርሱ የጻፈውን ካላመናችሁ፣ ቃሌን እንዴት ታምናላችሁ?»
\s5
\c 6
\cl ምዕራፍ 6
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ የጥብርያዶስ ባሕር ወደሚባለው ወደ ገሊላ ባሕር ማዶ ተሻገረ፡፡
\v 2 ብዙ ሰዎች ሕመምተኞችን በመፈወስ ያደረጋቸውን ተአምራት ስላዩ ተከተሉት፡፡
\v 3 ኢየሱስ ወደ ተራራ ወጥቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በዚያ ተቀመጠ፡፡
\s5
\v 4 የአይሁድ የፋሲካ በዓልም ተቃርቦ ነበር፡፡
\v 5 ኢየሱስ ብዙ ሕዝብ ወደ እርሱ ሲመጣ ባየ ጊዜ፣ ፊልጶስን፣ ‹‹ይህ ሁሉ ሕዝብ እንዲበላ እንጀራ ከየት እንግዛ? አለው፡፡
\v 6 ኢየሱስ ይህን ያለው ፊልጶስን ሊፈትን ነበር እንጂ፣ እርሱ ራሱ ሊያደርግ ያሰበውን ያውቅ ነበር፡፡
\s5
\v 7 ፊልጶስ፣ ‹‹ይህ ለእያንዳንዱ ሰው ቍራሽ እንዲደርሰው የሁለት መቶ ዲናር እንጀራ እንኳ ብንገዛ አይበቃም›› አለ፡፡
\v 8 ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፣ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም የሆነው እንድርያስም ኢየሱስን፣
\v 9 ‹‹አምስት የገብስ እንጀራና ሁለት ዓሣ የያዘ አንድ ልጅ እዚህ አለ፤ ነገር ግን ይህ ለዚህ ሁሉ ሕዝብ ምን ይጠቅማል? አለው፡፡
\s5
\v 10 ኢየሱስ፣ ‹‹ሕዝቡ እንዲቀመጡ አድርጉ›› አላቸው፡፡ ስፍራውም በሣር የተሸፈነ ነበር፡፡ ስለዚህ ቍጥራቸው አምስት ሺህ የሚያህል ወንዶች ተቀመጡ፡፡
\v 11 ከዚያም ኢየሱስ እንጀራውንና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ባረከና ለተቀመጡት ዐደለ፡፡ በተመሳሳይ መንገድ ከዓሣውም የሚፈልጉትን ያህል ዐደላቸው፡፡
\v 12 ሕዝቡ በጠገቡ ጊዜ፣ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፣ ‹‹አንዳችም እንዳይጣል የተረፈውን ፍርፋሪ ሰብስቡ›› አላቸው፡፡
\s5
\v 13 ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ ሕዝቡ ከበሉ በኋላ የተረፈውን ዐሥራ ሁለት መሶብ ሙሉ የገብስ እንጀራ ፍርፋሪ ሰበሰቡ፡፡
\v 14 ከዚያም ሕዝቡ ኢየሱስ ያደረገውን ይህን ምልክት ባዩ ጊዜ፣ ‹‹ይህስ በእውነት ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ ነው›› አሉ፡፡
\v 15 ኢየሱስም ሊመጡና ይዘው በግድ ሊያነግሡት እንደ ፈለጉ በተረዳ ጊዜ፣ እንደ ገና ለብቻው ወደ ተራራ ጫፍ ወጣ፡፡
\s5
\v 16 በመሸም ጊዜ፣ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ባሕሩ ወረዱ፤
\v 17 በጀልባ ተሳፍረው ወደ ቅፍርናሆም በባሕር ላይ መጓዝ ጀመሩ፡፡ ጊዜው መሽቶ ነበር፤ ኢየሱስም ገና ወደ እነርሱ አልመጣም ነበር፡፡
\v 18 በዚህ ጊዜ ባሕሩ ከኀይለኛ ነፋስ የተነሣ ይታወክ ነበር፡፡
\s5
\v 19 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ሃያ አምስት ወይም ሠላሳ ምዕራፍ ያህል እንደ ቀዘፉ፣ ኢየሱስ በባሕር ላይ እየሄደ እነርሱ ወዳሉበት ጀልባ ሲቃረብ አይተውት ፈሩ፡፡
\v 20 ይሁን እንጂ እርሱ፣ ‹‹እኔ ነኝ አትፍሩ›› አላቸው፡፡
\v 21 ከዚያም ጀልባዋ ላይ እንዲወጣ ፈቀዱለት፣ ጀልባዋም ወዲያው ወደሚሄዱበት ስፍራ ደረሰች፡፡
\s5
\v 22 በማግስቱም በማዶ ቆመው የነበሩ ሕዝብ አንድም ጀልባ በባሕሩ ላይ እንዳልነበረ አዩ፤ በዚያ የነበረው አንድ ጀልባ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ያልተሳፈረበት ብቻ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱም ብቻቸውን ከዚያ ሄደው ነበር፡፡
\v 23 ይሁን እንጂ ጌታ አመስግኖ ሰዎቹን እንጀራ ካበላበት ስፍራ አጠገብ፣ ከጥብርያዶስ የመጡ አንዳንድ ጀልባዎች እዚያ ነበሩ፡፡
\s5
\v 24 ሕዝቡም፣ ኢየሱስም ሆነ ደቀ መዛሙርቱ እዚያ እንዳልነበሩ በተረዱ ጊዜ፣ ራሳቸው በጀልባዎቹ ተሳፍረው ኢየሱስን ፍለጋ ሄዱ፡፡
\v 25 በባሕሩ ማዶ ኢየሱስን ባገኙት ጊዜ፣ ‹‹መምህር ሆይ፤ ወደዚህ የመጣኸው መቼ ነው? አሉት፡፡
\s5
\v 26 ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ ‹‹እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ እኔን የምትፈልጉኝ ምልክቶችን ስላያችሁ ሳይሆን፣ እንጀራውን በልታችሁ ስለ ጠገባችሁ ነው፡፡
\v 27 ለሚጠፋ ምግብ አትሥሩ፤ ይልቁን ወልድ ለሚሰጣችሁ ዘላለም ለሚኖር ሕይወት ሥሩ፤ እግዚአብሔር አብ ማኅተሙን በእርሱ ላይ አትሞአልና፡፡››
\s5
\v 28 ከዚያም፣ ‹‹የእግዚአብሔርን ሥራ እንድንሠራ ምን እናድርግ? አሉት፡፡
\v 29 ኢየሱስ፣ ‹‹የምትሠሩት የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ በላከው ማመን ነው›› ብሎ መለሰላቸው፡፡
\s5
\v 30 ስለዚህ እነርሱ እንዲህ አሉት፤ ‹‹አይተን እንድናምንህ ምን ተአምር ትሠራለህ? ምንስ ታደርጋለህ?
\v 31 ‹እንዲበሉ ከሰማይ እንጀራ ሰጣቸው› ተብሎ እንደ ተጻፈ፣ አባቶቻችን በምድረ በዳ መና በሉ፡፡››
\s5
\v 32 ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ ‹‹እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ መና እንድትበሉ ከሰማይ የሰጣችሁ ሙሴ አልነበረም፤ ነገር ግን ከሰማይ እውነተኛ እንጀራ የሚሰጣችሁ አባቴ ነው፤
\v 33 ከሰማይ የሚወርድና ለዓለም ሕይወትን የሚሰጥ የእግዚአብሔር እንጀራ ነውና፡፡››
\v 34 ስለዚህ፣ ‹‹ጌታ ሆይ፣ ይህን እንጀራ ዘወትር ስጠን›› አሉት፡፡
\s5
\v 35 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ ‹‹እኔ የሕይወት እንጀራ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ አይራብም፤ በእኔ የሚያምንም ከቶ አይጠማም፡፡
\v 36 ነገር ግን እኔን አይታችሁ አሁንም ገና ስላላመናችሁብኝ ይህን አልኋችሁ፡፡
\v 37 አባቴ የሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፤ እኔም አባቴ የሰጠኝን ከቶ ወደ ውጭ አላባርርም፡፡
\s5
\v 38 ከሰማይ የወረድሁት የራሴን ፈቃድ ለማድረግ ሳይሆን የላከኝን ፈቃድ ለመፈጸም ነውና፡፡
\v 39 የላከኝም ፈቃድ፣ እርሱ ከሰጠኝ ሁሉ አንድም ሳይጠፋ፣ በመጨረሻው ቀን እንዳስነሣቸው ነው፡፡
\v 40 የአባቴ ፈቃድ፣ ወልድን አይቶ በእርሱ ያመነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው ነው፡፡ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ፡፡››
\s5
\v 41 ከዚያም የአይሁድ መሪዎች፣ ‹‹እኔ ከሰማይ የወረድሁ የሕይወት እንጀራ ነኝ›› በማለቱ አጕረመረሙበት፡፡
\v 42 እነርሱ፣ ‹‹ይህ ኢየሱስ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን? አባቱንና እናቱንስ የምናውቃቸው አይደሉምን? ታዲያ፣ እንዴት ከሰማይ ወረድሁ ይለናል? ተባባሉ፡፡
\s5
\v 43 ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ ‹‹እርስ በርስ ማጕረምረማችሁን ተዉት፡፡
\v 44 አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ የሚመጣ የለም፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ፡፡
\v 45 በነቢያት፣ ‹ሁሉም ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ› ተብሎ እንደ ተጻፈ፣ ከአብ የሰማና የተማረ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፡፡
\s5
\v 46 ከእግዚአብሔር ከሆነው በቀር አብን ያየ ማንም የለም፤ እርሱ አብን አይቶታል፡፡
\v 47 እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፡፡
\s5
\v 48 እኔ የሕይወት እንጀራ ነኝ፡፡
\v 49 አባቶቻችሁ በበረሐ መና በሉ፣ ሞቱም፡፡
\s5
\v 50 ሰው በልቶት እንዳይሞት፣ ከሰማይ የወረደ እንጀራ ይህ ነው፡፡
\v 51 ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፡፡ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፡፡ ለዓለም ሕይወት እንዲሆነው የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው፡፡››
\s5
\v 52 አይሁድ በዚህ አባባሉ ተቈጥተው፣ ‹‹ይህ ሰው እንዴት እንድንበላ ሥጋውን ሊሰጠን ይችላል? በማለት እርስ በርስ ተከራከሩ፡፡
\v 53 ከዚያም ኢየሱስ፣ ‹‹እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ፣ ደሙንም ካልጠጣችሁ የራሳችሁ የሆነ ሕይወት አይኖራችሁም›› አላቸው፡፡
\s5
\v 54 ‹‹ሥጋዬን የሚበላ፣ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ፤
\v 55 ሥጋዬ እውነተኛ መብል፣ ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና፡፡
\v 56 ሥጋዬን የሚበላ፣ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል፤ እኔም በእርሱ እኖራለሁ፡፡
\s5
\v 57 ሕያው አብ እንደ ላከኝና እኔ ከአብ የተነሣ እንደምኖር፣ የሚበላኝም ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል፡፡
\v 58 አባቶቻችን በልተውት እንደ ሞቱ ዐይነት ሳይሆን፣ ይህ ከሰማይ የወረደ እንጀራ ነው፡፡ ይህን እንጀራ የበላ ለዘላለም ይኖራል፡፡››
\v 59 ኢየሱስ ይህን የተናገረው በቅፍርናሆም፣ በምኵራብ ሲያስተምር ነበር፡፡
\s5
\v 60 ከዚያም ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎቹ ይህን ሲሰሙ፣ ‹‹ይህ ጠንካራ ትምህርት ነው፤ ማን ሊቀበለው ይችላል? አሉ፡፡
\v 61 ኢየሱስ በዚህ ማጕረምረማቸውን በገዛ ራሱ ስላወቀ፣ ‹‹ይህ አሰናከላችሁ እንዴ?
\s5
\v 62 ታዲያ፣ የሰው ልጅ ቀድሞ ወደ ነበረበት ስፍራ፣ ተመልሶ ወደ ላይ ሲወጣ ብታዩ ምን ልትሉ ነው?
\v 63 ሕይወት የሚሰጠው መንፈስ ነው፤ ሥጋ ለምንም አይጠቅምም፡፡ እኔ የነገርኋችሁ ቃላት መንፈስ ናቸው፤ ሕይወትም ናቸው፡፡
\s5
\v 64 ይሁን እንጂ፣ ከእናንተ መካከል የማያምኑ አንዳንዶች አሉ›› አለ፡፡ ከመጀመሪያው በእርሱ የማያምኑ እነማን እንደ ሆኑና የሚከዳው ማን እንደ ሆነ ያውቅ ነበርና፡፡
\v 65 ደግሞም፣ ‹‹ከአብ ከተሰጠው በቀር ማንም ወደ እኔ ሊመጣ አይችልም ያልኋችሁ ለዚህ ነው›› አለ፡፡
\s5
\v 66 ከዚህ በኋላ፣ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎቹ ትተውት ወደ ኋላቸው ተመለሱ፤ አብረውትም አልተጓዙም፡፡
\v 67 ኢየሱስ ዐሥራ ሁለቱን፣ ‹‹እናንተም ትታችሁኝ ልትሄዱ ትፈልጋላችሁን? አላቸው፡፡
\v 68 ስምዖን ጴጥሮስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ ‹‹ጌታ ሆይ፣ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ፤
\v 69 እኛም አምነናል፤ አንድያ የእግዚአብሔር ቅዱስ መሆንህንም ዐወቀናል፡፡››
\s5
\v 70 ኢየሱስ፣ ‹‹እኔ ዐሥራ ሁለታችሁንም መርጫችሁ የለም ወይ? ከእናንተም መካከል አንዱ ዲያብሎስ ነው›› አላቸው፡፡
\v 71 ይህን ያለው ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ስለ ሆነውና ኋላም ኢየሱስን አሳልፎ ስለ ሰጠው፣ ስለ አስቆሮቱ ስምዖን ልጅ፣ ስለ ይሁዳ ነው፡፡
\s5
\c 7
\cl ምዕራፍ 7
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አይሁድ ሊገድሉት ይፈልጉ ስለ ነበር፣ ወደ ይሁዳ መሄድ አልፈለገም፤ ስለዚህ እዚያው በገሊላ ውስጥ ይመላለስ ነበር፡፡
\v 2 የአይሁድ የዳስ በዓል የሚከበርበትም ጊዜ ተቃርቦ ነበር፡፡
\s5
\v 3 ስለዚህ ወንድሞቹ እንዲህ አሉት፤ ‹‹ተነሥተህ ከዚህ ስፍራ ወደ ይሁዳ አውራጃ ሂድ፤ ደቀ መዛሙርትህም ደግሞ አንተ የምትሠራውን ሥራ ይዩ፡፡
\v 4 በሕዝብ ፊት መታወቅ የሚፈልግ ሰው የሚሠራውን ሥራ በድብቅ አያደርግም፡፡ እነዚህን ነገሮች የምታደርግ ከሆነ፣ ራስህን ለዓለም አሳይ፡፡››
\s5
\v 5 ምክንያቱም ወንድሞቹ እንኳ ገና አላመኑበትም ነበር፡፡
\v 6 ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ ‹‹ጊዜዬ ገና ነው፡፡ ለእናንተማ ጊዜው ሁሉ የተመቸ ነው፡፡
\v 7 ዓለም እናንተን ሊጠላችሁ አይችልም፡፡ እኔን ግን በክፉ ሥራው ስለምመሰክርበት፣ ይጠላኛል፡፡
\s5
\v 8 እናንተ ወደ በዓሉ ውጡ፤ እኔ ግን ጊዜዬ ገና ስላልደረሰ፣ ወደ በዓሉ አልሄድም፡፡››
\v 9 እርሱ ይህን ካላቸው በኋላ፣ በገሊላ ቈየ፡፡
\s5
\v 10 ነገር ግን ወንድሞቹ ወደ በዓሉ ከሄዱ በኋላ እርሱም በግልጽ ሳይሆን በስውር ወደዚያው ሄደ፡፡
\v 11 አይሁድ በበዓሉ ላይ ሊፈልጉት ሄደው፣ ‹‹እርሱ ያለው የት ነው? አሉ፡፡
\s5
\v 12 በሕዝቡም መካከል ብዙ ውይይት ተነሥቶ ነበር፡፡ አንዳንዶቹ፣ ‹‹እርሱ ጥሩ ሰው ነው›› አሉ፤ ሌሎቹም፣ ‹‹አይደለም፣ ሕዝቡን እያሳተ ነው›› አሉ፡፡
\v 13 ይሁን እንጂ፣ አይሁድን ስለ ፈሩ፣ ስለ እርሱ በግልጽ የተናገረ ማንም አልነበረም፡፡
\s5
\v 14 በበዓሉ አጋማሽ ላይ፣ ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ወጥቶ ማስተማር ጀመረ፡፡
\v 15 አይሁድም እየተደነቁ፣ ‹‹ይህ ሰው እንዴት ይህን ሁሉ ዐወቀ? ትምህርት እንኳ አልተማረም›› ይሉ ነበር፡፡
\v 16 ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ ‹‹የማስተምረው ከራሴ አይደለም፤ ነገር ግን ትምህርቴ ከላከኝ ነው›፡፡
\s5
\v 17 ማንም የእርሱን ፈቃድ ለማድረግ ቢፈልግ፣ ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር የመጣ መሆኑን ወይም ከራሴ የምናገር መሆኑን ያውቃል፡፡
\v 18 ከራሱ የሚናገር የራሱን ክብር ይፈልጋል፤ የላከውን ክብር የሚፈልግ ግን እውነተኛ ነው፤ ሐሰትም የለበትም፡፡
\s5
\v 19 ሙሴ ሕግ ሰጥቶአችሁ አልነበረምን? ነገር ግን ከእናንተ ሕጉን የሚጠብቅ አንድም ሰው የለም፡፡ ለመሆኑ፣ ልትገድሉኝ የምትፈልጉት ለምንድን ነው?
\v 20 ሕዝቡ፣ ‹‹ጋኔን አለብህ፤ አንተን ማን ሊገድል ይፈልጋል? ብለው መለሱ፡፡
\s5
\v 21 ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ ‹‹አንድን ሥራ በመሥራቴ ሁላችሁም በዚህ ትደነቃላችሁ፡፡
\v 22 ሙሴ ግዝረትን ሰጣችሁ፤ ይህም የመጣው ከአባቶች እንጂ ከሙሴ አልነበረም፤ ስለሆነም፣ በሰንበት ቀን ሰውን ትገርዛላችሁ፡፡
\s5
\v 23 ሰውን በሰንበት ቀን ስትገርዙ የሙሴ ሕግ የማይሻር ከሆነ፣ እኔ በሰንበት ቀን የሰውን መላ አካል ስላዳንሁ ለምን በእኔ ላይ ትቈጣላችሁ?
\v 24 መልክ በማየት ሳይሆን በቅንነት ፍረዱ፡፡››
\s5
\v 25 ከኢየሩሳሌም ከመጡት አንዳንዶቹ እንዲህ አሉ፤ ‹‹ሊገድሉት የሚፈልጉት ይህን ሰው አልነበረም?
\v 26 ተመልከቱ፤ እንዲህ በግልጽ እየተናገረ ምንም አይሉትም፡፡ ገዦቹ እርሱ በትክክል ክርስቶስ መሆኑን ዐውቀው ይሆን?
\v 27 እኛ ግን ይህ ሰው ከየት እንደ መጣ እናውቃለን፤ ክርስቶስ ሲመጣ ግን ማንም ከየት እንደ መጣ አያውቅም፡፡››
\s5
\v 28 ኢየሱስ በቤተ መቅደስ ሲያስተምር ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፤ ‹‹እኔን ታውቁኛላችሁ፤ ከየት እንደ መጣሁም ታውቃላችሁ፤ ሆኖም በራሴ አልመጣሁም፤ የላከኝ ግን እውነተኛ ነው፤ እርሱን ደግሞ እናንተ አታውቁትም፡፡
\v 29 እኔ ከእርሱ ዘንድ ስለ መጣሁ፣ ዐውቀዋለሁ፤ የላከኝም እርሱ ነው፡፡››
\s5
\v 30 እነርሱም በዚህ ጊዜ ሊይዙት ሞከሩ፤ ነገር ግን የነካው አንድም ሰው አልነበረም፤ ምክንያቱም የተወሰነለት ሰዓት ገና ነበር፡፡
\v 31 ይሁን እንጂ፣ በሕዝቡ መካከል ብዙዎች በእርሱ አመኑ፡፡ ያመኑትም፣ ‹‹ክርስቶስ ሲመጣ ይህ ሰው ከሠራው ተአምር የሚበልጥ ሊሠራ ይችላልን? አሉ፡፡
\v 32 ፈሪሳውያን ሕዝቡ ስለ ኢየሱስ በሹክሹክታ የሚያወሩትን ሰሙ፤ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ሊያስይዙት የጥበቃ ሰዎችን ላኩበት፡፡
\s5
\v 33 ኢየሱስ፣ ‹‹ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ ከዚያም ወደ ላከኝ እሄዳለሁ፡፡
\v 34 ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን አታገኙኝም፡፡ እናንተ ወደምሄድበት መምጣት አትችሉም›› አላቸው፡፡
\s5
\v 35 ስለዚህ አይሁድ እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፤ ‹‹ይህ ሰው እንዳናገኘው ወዴት ሊሄድ ነው? ተበትነው በግሪክ ወዳሉት ሰዎች ሄዶ እነርሱን ሊያስተምር ይሆን?
\v 36 ‹ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን አታገኙኝም፡፡ እናንተ እኔ ወደምሄድበት መምጣት አትችሉም› ያለውስ ቃል ምን ማለት ነው?
\s5
\v 37 በታላቁ የበዓሉ ቀን፣ በመጨረሻው ቀን፣ ኢየሱስ ቆሞ ድምፁን ከፍ በማድረግ፣ ‹‹የተጠማ ማንም ቢኖር፣ ወደ እኔ መጥቶ ይጠጣ፡፡
\v 38 ቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ተናገሩት፣ በእኔ የሚያምን የሕይወት ውሃ ወንዝ ከውስጡ ይፈልቃል›› አለ፡፡
\s5
\v 39 ይህን ያለው ግን በእርሱ የሚያምኑት ወደ ፊት ስለሚቀበሉት፣ መንፈስ ቅዱስ ነው፤ ኢየሱስ ገና ስላልከበረ፣ መንፈስ ቅዱስ ገና አልተሰጠም ነበር፡፡
\s5
\v 40 ከሕዝቡ አንዳንዶቹ ይህን ቃል ሲሰሙ፣ ‹‹ይህ በእርግጥ ነቢዩ ነው›› አሉ፡፡
\v 41 ሌሎቹ ደግሞ፣ ‹‹እርሱ ክርስቶስ ነው›› አሉ፡፡ አንዳንዶቹ ግን፣ ‹‹ክርስቶስ ከገሊላ እንዴት ይመጣል!
\v 42 ቅዱሳት መጻሕፍት ክርስቶስ ከዳዊት ዘር፣ የዳዊት ከተማ ከሆነችው ከቤተ ልሔም እንደሚመጣ ተናግረው የለምን? አሉ፡፡
\s5
\v 43 ስለዚህ እርሱን በተመለከተ በመካከለቸው መለያየት ተከሠተ፡፡
\v 44 ከእነርሱ አንዳንዶቹ ሊይዙት ፈልገው ነበር፤ ነገር ግን ማንም አልነካውም፡፡
\s5
\v 45 ከዚያም የጥበቃ ሰዎቹ ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ፈሪሳውያን ተመልሰው መጡ፤ የላኳቸውም፣ ‹‹ለምንድን ነው ይዛችሁ ያላመጣችሁት? አሏቸው፡፡
\v 46 የጥበቃ ሰዎቹ፣ ‹‹ከዚህ ቀደም እንደዚህ የተናገረ አልነበረም›› አሏቸው፡፡
\s5
\v 47 ፈሪሳውያንም እንዲህ አሏቸው፤ ‹‹እናንተም ሳታችሁን?
\v 48 ከገዦቹ ወይም ከፈሪሳውያን በእርሱ ያመነ አለ?
\v 49 ነገር ግን ሕጉን የማያውቅ ይህ ሕዝብ የተረገመ ነው፡፡››
\s5
\v 50 ከፈሪሳውያን አንዱ፣ ከዚህ በፊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረው ኒቆዲሞስ፣
\v 51 ‹‹መጀመሪያ ከሰውየው ሳይሰማና የሚሠራውን ሳያውቅ፣ የእኛ ሕግ በሰው ላይ ይፈርዳልን? አላቸው፡፡
\v 52 እነርሱ፣ ‹‹አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህ ወይ? ነቢይ ከገሊላ እንደማይመጣ መርምረህ ዕወቅ›› አሉት፡፡
\s5
\v 53 ከዚያም እያንዳንዱ ሰው ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ (*53 የጥንት ቅጆች በዮሐንስ 7፡53-8፡11 ላይ ያለውን ክፍል አያካትቱም፡፡)
\s5
\c 8
\cl ምዕራፍ 8
\p
\v 1 ኢየሱስ ወደ ደብረ ዘይት ሄደ።
\v 2 ጠዋት በማለዳ ተመልሶ ወደ ቤተ መቅደስ መጣ፤ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ መጡ፤ እርሱም ተቀምጦ አስተማራቸው።
\v 3 የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያንም ስታመነዝር የተያዘችን ሴት አምጥተው፤ በመካከላቸው አቆሟት።
\s5
\v 4 ከዚያም ኢየሱስን እንዲህ አሉት፤ «መምህር ሆይ፣ ይህች ሴት ስታመነዝር እጅ ከፍንጅ የተያዘች ናት፤
\v 5 ሙሴ በሕጉ እንዲህ ያሉትን በድንጋይ እንድንወግር አዞናል፤ አንተስ ስለ እርሷ ምን ትላለህ?»
\v 6 ይህን ያሉት እርሱን ወጥመድ ውስጥ ለማስገባትና ለመክሰስ ፈልገው ነው፤ ኢየሱስ ግን ጎንበስ ብሎ በጣቱ መሬት ላይ ጻፈ።
\s5
\v 7 ጥያቄ ማቅረባቸውን በቀጠሉ ጊዜም፣ ተነሥቶ ቆመና፣ “ከእናንተ መካከል ኃጢአት የሌለበት ሰው በመጀመሪያ ይውገራት” አላቸው።
\v 8 ዳግመኛም ጐንበስ ብሎ፣ በጣቱ መሬት ላይ ጻፈ።
\s5
\v 9 ይህንም በሰሙ ጊዜ፣ ከታላቅ ጀምረው አንድ ባንድ ወጥተው ሄዱ። በመጨረሻ ኢየሱስ በመካከላቸው ቆማ ከነበረችው ሴት ጋር ለብቻው ቀረ።
\v 10 ኢየሱስ ተነሥቶ በመቆም፣ “አንቺ ሴት፤ የከሰሱሽ ሰዎች የት ናቸው? አንድም የፈረደብሽ የለም?” አላት።
\v 11 እርሷም፣ “ጌታ ሆይ፣ አንድም የለም” አለች። ኢየሱስ፣ “እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁን በኋላ ግን ደግመሽ ኀጢአት አትሥሪ” አላት።
\s5
\v 12 ደግሞም ኢየሱስ ሕዝቡን፣ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ ቢኖር የሕይወት ብርሃን ያገኛል እንጂ፣ በጨለማ አይመላለስም” አላቸው።
\v 13 ፈሪሳውያንም፣ “አንተው ስለ ራስህ ስለምትመሰክር፤ ምስክርነትህ እውነት አይደለም” አሉት።
\s5
\v 14 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር እንኳ ምስክርነቴ እውነት ነው። ከየት እንደ መጣሁ፣ ወዴትም እንደምሄድ ዐውቃለሁ፤ እናንተ ግን እኔ ከየት እንደ መጣሁ ወይም ወዴት እንደምሄድ አታውቁም።
\v 15 እናንተ በሥጋዊ ዐይን ትፈርዳላችሁ፤ እኔ በማንም አልፈርድም።
\v 16 ብፈርድም እንኳ፣ ብቻዬን አይደለሁም፤ ከላከኝ አብ ጋር ስለ ሆንሁ፣ ፍርዴ እውነት ነው።
\s5
\v 17 አዎን፤ በሕጋችሁ የሁለት ሰዎች ምስክርነት እውነት እንደ ሆነ ተጽፎአል።
\v 18 እኔ ስለ ራሴ እመሰክራለሁ፤ የላከኝም አብ ስለ እኔ ይመሰክራል።”
\s5
\v 19 እነርሱም፣ “አባትህ የት ነው ያለው?” አሉት። ኢየሱስም፣ “እናንተ እኔንም ሆነ አባቴን አታውቁንም፤ እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም ባወቃችሁት ነበር” አላቸው።
\v 20 ይህንም የተናገረው በቤተ መቅደሱ ግምጃ ቤት አጠገብ ሆኖ ሲያስተምር ነበር፤ ሆኖም ሰዓቱ ገና ስላልደረሰ፣ ማንም አልያዘውም።
\s5
\v 21 ደግሞም፣ “እኔ ተለይቻችሁ እሄዳለሁ፤ እናንተም ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ። እኔ ወደምሄድበት መምጣት አትችሉም” አላቸው።
\v 22 አይሁድም፣ “ይህ 'እኔ ወደምሄድበት መምጣት አትችሉም' የሚለው ራሱን ሊገድል ዐስቦ ይሆን?” አሉ።
\s5
\v 23 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ ከታች ናችሁ፤ እኔ ግን ከላይ ነኝ። እናንተ ከዚህ ዓለም ናችሁ፤ እኔ ግን ከዚህ ዓለም አይደለሁም።
\v 24 በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ ያልኋችሁ ለዚህ ነው። ምክንያቱም እኔ ነኝ ስላችሁ ካላመናችሁ፣ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ።”
\s5
\v 25 እነርሱም፣ “ለመሆኑ፣ አንተ ማን ነህ?” አሉት። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤”ከመጀመሪያው እንደ ነገርኋችሁ ነኝ።
\v 26 ብዙ የምናገረውና ስለ እናንተም የምፈርደው አለኝ። ይሁን እንጂ የላከኝ እርሱ እውነተኛ ነው፤ እኔም ከእርሱ የሰማሁትን፣ ያንኑ ለዓለም እናገራለሁ።”
\v 27 እነርሱ ግን ስለ አብ እየነገራቸው እንደ ነበር አልተረዱም።
\s5
\v 28 ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “የሰውን ልጅ ወደ ላይ ከፍ ስታደርጉት፣ በዚያን ጊዜ እኔው እንደ ሆንሁና ከራሴ አንድም ነገር እንደማላደርግ ታውቃላችሁ። አብ እንዳስተማረኝ ይህን እናገራለሁ።
\v 29 የላከኝ እርሱ ከእኔ ጋር ነው፤ ብቻዬንም አልተወኝም፤ እኔ ሁልጊዜ እርሱን ደስ የሚያሰኘውን ነገር አደርጋለሁና።”
\v 30 ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች በተናገረ ጊዜ ብዙ ሰዎች በእርሱ አመኑ።
\s5
\v 31 ኢየሱስ በእርሱ ያመኑትን አይሁድ፣ “እናንተ በቃሌ ብትኖሩ፣ በርግጥ ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤
\v 32 እውነትን ታውቃላችሁ፤ እውነትም ነጻ ያወጣችኋል” አላቸው።
\v 33 እነርሱም፣ “እኛ የአብርሃም ዘሮች ነን፤ የማንም ባሪያ ሆነን አናውቅም፤ ታዲያ እንዴት ‘ነጻ ትወጣላችሁ’ ትለናለህ?” አሉት።
\s5
\v 34 ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ ኃጢአት የሚሠራ ሁሉ የኃጢአት ባሪያ ነው።
\v 35 ባሪያ ለዘለቄታ በቤት አይኖርም፤ ልጅ ግን ለዘለቄታ ይኖራል።
\v 36 ስለዚህ ልጁ ነጻ ካወጣችሁ፣ በርግጥ ነጻ ትወጣላችሁ።
\s5
\v 37 የአብርሃም ዘር መሆናችሁን ዐውቃለሁ፤ ቃሌን ስላልተቀበላችሁ፣ ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ።
\v 38 አባቴ ጋ ያየሁትን እናገራለሁ፤ እናንተም ደግሞ ከአባታችሁ የሰማችሁትን ታደርጋላችሁ።”
\s5
\v 39 እነርሱም መልሰው፣ “አባታችንስ አብርሃም ነው” አሉት። ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “የአብርሃም ልጆችስ ብትሆኑ ኖሮ፣ የአብርሃምን ሥራ በሠራችሁ ነበር።
\v 40 አሁን ግን ከእግዚአብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው ለመግደል ትፈልጋላችሁ። አብርሃምኮ ይህን አላደረገም።
\v 41 እናንተ ግን የአባታችሁን ሥራ ትሠራላችሁ።” እነርሱም፣ “እኛ በዝሙት የተወለድን አይደለንም፤ አንድ አባት እግዚአብሔር አለን” አሉት።
\s5
\v 42 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እግዚአብሔር አባታችሁ ቢሆን ኖሮ፣ እኔ ከእግዚአብሔር ወጥቼ ስለ መጣሁ፣ በወደዳችሁኝ ነበር፤ በራሴም ፈቃድ አልመጣሁም፤ ነገር ግን እርሱ ላከኝ።
\v 43 ቃሌን የማትረዱት ለምንድን ነው? ምክንያቱም ቃሌን መስማት ስለማትችሉ ነው።
\v 44 እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ፤ የአባታችሁንም ፍላጎት ለማድረግ ትመኛላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያውም ነፍሰ ገዳይ ነበር፤ እውነት በእርሱ ዘንድ ስለሌለም፣ በእውነት አይጸናም። ሐሰትንም ሲናገር ከራሱ አፍልቆ ይናገራል፤ ምክንያቱም እርሱ ሐሰተኛ፣ የሐሰትም አባት ነው።
\s5
\v 45 እኔ ግን እውነትን ስለምናገር አታምኑኝም።
\v 46 ከእናንተ ስለ ኃጢአት የሚወቅሰኝ ሰው ማን ነው? እውነትን የምናገር ከሆነስ፣ ታዲያ ለምን አታምኑኝም?
\v 47 ከእግዚአብሔር ስላልሆናችሁ፣ ቃሉን አትሰሙም።”
\s5
\v 48 አይሁድም፣ “እንግዲህ ጋኔን ያደረብህ ሳምራዊ ነህ በማለታችን እውነት አልተናገርንምን?” በማለት መለሱለት።
\v 49 ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ “እኔ ጋኔን የለብኝም፤ እኔ አባቴን አከብረዋለሁ እንጂ፣ እናንተ ግን ታዋርዱኛላችሁ።
\s5
\v 50 እኔ የራሴን ክብር አልሻም፤ የሚሻና የሚፈርድ አንድ አለ።
\v 51 እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚጠብቅ ማንም ቢኖር፣ እርሱ ሞትን በፍጹም አያይም።”
\s5
\v 52 አይሁድም፣ “አሁን ጋኔን እንዳለብህ ዐወቅን። አብርሃምም ነቢያትም ሞተዋል፤ አንተ ግን 'ማንም ቃሌን ቢጠብቅ ሞትን አይቀምስም' ትላለህ።
\v 53 አንተ ከሞተው ከአባታችን፣ ከአብርሃም ትበልጣለህን? ነቢያትም ሞተዋል። ለመሆኑ፣ አንተ ማን ነኝ ልትል ነው?” አሉት።
\s5
\v 54 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እኔ ራሴን ባከብር፣ ክብሬ ከንቱ ነው፤ እኔን የሚያከብረኝ እናንተ አምላካችን ነው የምትሉት አባቴ ነው።
\v 55 እናንተ እርሱን አላወቃችሁትም፤ እኔ ግን ዐውቀዋለሁ። እኔ ‘አላውቀውም’ ብል እንደ እናንተው ሐሰተኛ እሆናለሁ። ነገር ግን እኔ ዐውቀዋለሁ፤ ቃሉንም እጠብቃለሁ።
\v 56 አባታችሁ አብርሃም ቀኔን በማየቱ ደስ አለው፤ አይቶም ሐሤት አደረገ።”
\s5
\v 57 አይሁድም፣ “ገና ዐምሳ ዓመት ያልሞላህ፣ አንተ አብርሃምን አይተሃልን?” አሉት።
\v 58 ኢየሱስም፣ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ አብርሃም ከመወለዱ በፊት እኔ አለሁ” አላቸው።
\v 59 እነርሱም፣ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ራሱን ሰውሮ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ሄደ።
\s5
\c 9
\cl ምዕራፍ 9
\p
\v 1 ኢየሱስ በመንገድ ሲያልፍ ፣ ከተወለደ ጀምሮ ዐይነ ስውር የነበረ አንድ ሰው አየ።
\v 2 ደቀ መዛሙርቱ፣ “መምህር ሆይ፤ ይህ ሰው ዐይነ ስውር ሆኖ እንዲወለድ ያደረገው የራሱ ኀጢአት ነው ወይስ የወላጆቹ?” አሉት።
\s5
\v 3 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ እንዲገለጥ ነው እንጂ፣ እርሱ ወይም ወላጆቹ ኀጢአት አልሠሩም።
\v 4 የላከኝን ሥራ ቀን ሳለ መሥራት ይገባናል። ማንም ሊሠራ የማይችልበት ሌሊት እየመጣ ነው።
\v 5 በዓለም እስካለሁ፣ የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ።”
\s5
\v 6 ኢየሱስ ይህን ካለ በኋላ፣ መሬት ላይ እንትፍ ብሎ፣ በምራቁ ጭቃ ሠራ፤ በጭቃውም የሰውየውን ዐይን ቀባ።
\v 7 ሰውየውንም፣ “ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠበ” አለው፣ ‘ሰሊሆም’ የተላከ ማለት ነው። ሰውየውም ወደዚያው ሄዶ ታጠበ፤ ዐይኑም እያየለት ተመልሶ መጣ።
\s5
\v 8 የሰውየው ጐረቤቶችና ቀድሞ ለማኝ ሆኖ ያዩት ሰዎችም፣ “ይህ ሰው ተቀምጦ ሲለምን የነበረው ሰው አይደለምን?” አሉ።
\v 9 አንዳንዶቹ፣ “እርሱ ነው” አሉ፤ ሌሎችም፣ “ይመስለዋል እንጂ እርሱ አይደለም” አሉ። እርሱ ግን፣ “እኔው ነኝ” አለ።
\s5
\v 10 እነርሱም፣ “ታዲያ፣ ዐይኖችህ እንዴት ተከፈቱልህ?” አሉት።
\v 11 እርሱም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ “ኢየሱስ የሚባለው ሰው ጭቃ ሠርቶ ዐይኔን ቀባ፤ ከዚያም፣ ‘ወደ ሰሊሆም ሄደህ ታጠብ’ አለኝ። እኔም ሄጄ ታጠብሁ፤ ዐይኖቼም በሩ።”
\v 12 እነርሱም፣ “ታዲያ፣ እርሱ የት ነው?” አሉ። እርሱም፣ “እኔ አላውቅም” ብሎ መለሰላቸው።
\s5
\v 13 እነርሱም ዐይነ ስውር የነበረውን ሰው ወደ ፈሪሳውያን ወሰዱት።
\v 14 ኢየሱስ ጭቃ ሠርቶ የሰውየውን ዐይን የከፈተው በሰንበት ቀን ነበረ።
\v 15 ፈሪሳውያንም ዐይኑ እንዴት እንደ ተከፈተለት እንደ ገና ሰውየውን ጠየቁት። እርሱም፣ “ዐይኖቼን ጭቃ ቀባ፤ ታጠብሁና ማየት ቻልሁ” አላቸው።
\s5
\v 16 ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ፣ “ይህ ሰው ሰንበትን ስለማያከብር፣ ከእግዚአብሔር አይደለም” አሉ። ሌሎቹም፣ “ኀጢአተኛ የሆነ ሰው እንዴት እንደዚህ ያለ ተአምር ይሠራል?” አሉ። ስለዚህ በመካከላቸው መከፋፈል ተፈጠረ።
\v 17 እንደ ገናም ዐይነ ስውሩን ሰው፣ “ዐይንህን ስለ ከፈተው ሰው ምን ትላለህ?” አሉት። ዐይነ ስውሩም፣ “ነቢይ ነው” አለ።
\v 18 ፈሪሳውያንም ዐይነ ስውር የነበረው ሰው ዐይኖች መከፈታቸውን አሁንም ስላላመኑ፣ ዐይኑ የበራለትን ሰው ወላጆች አስጠሩ።
\s5
\v 19 ወላጆቹንም፣ “ይህ ዐይነ ስውር ሆኖ የተወለደ ነው የምትሉት ሰው ልጃችሁ ነውን? ከሆነስ፣ አሁን እንዴት ማየት ቻለ?” ብለው ጠየቋቸው።
\v 20 ወላጆቹም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤ “ይህ ልጃችን መሆኑንና ዐይነ ስውር ሆኖ መወለዱን እናውቃለን።
\v 21 አሁን እንዴት ማየት እንደ ቻለ ግን አናውቅም፤ ዐይኑን የከፈተለት ማን እንደ ሆነም አናውቅም። እርሱን ጠይቁት፤ ጕልማሳ ነው፤ ስለ ራሱ መናገር ይችላል።”
\s5
\v 22 ወላጆቹ እንዲህ ያሉት አይሁድን ስለ ፈሩ ነበር። ምክንያቱም አይሁድ፣ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው የሚል ሰው ካገኙ፣ ከምኵራብ ሊያስወግዱት ቀደም ብለው ተስማምተው ነበር።
\v 23 ወላጆቹ፣ “እርሱ ጕልማሳ ነው፤ ራሱን ጠይቁት” ያሉትም በዚህ ምክንያት ነበር።
\s5
\v 24 ዐይነ ስውር የነበረውን ሰው እንደ ገና አስጠርተው፣ “ለእግዚአብሔር ክብር ስጥ፤ እኛ ይህ ሰው ኀጢአተኛ እንደ ሆነ እናውቃለን” አሉት።
\v 25 ሰውየውም፣ “እኔ እርሱ ኀጢአተኛ መሆኑን አላውቅም። ነገር ግን አንድ ነገር ዐውቃለሁ፤ ዐይነ ስውር ነበርሁ፤ አሁን ግን እያየሁ ነው” አላቸው።
\s5
\v 26 እነርሱም፣ “ያደረገልህ ምንድን ነው? ዐይኖችህንስ የከፈተው እንዴት ነው?” አሉት።
\v 27 እርሱም፣ “አስቀድሜ ነግሬአችሁ ነበር! እናንተ ግን አትሰሙም። እንደ ገና መስማትስ ለምን ፈለጋችሁ? እናንተም የእርሱ ደቀ መዛሙርት ለመሆን ትፈልጋላችሁን?” ብሎ መለሰ።
\v 28 ሰደቡትና እንዲህ አሉ፤ “አንተ የእርሱ ደቀ መዝሙር ነህ፣ እኛ ግን የሙሴ ደቀ መዛሙርት ነን።
\v 29 እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ተናገረው እናውቃለን፤ ይህ ሰው ግን ከየት እንደ መጣ አናውቅም።”
\s5
\v 30 ሰውየውም፣ “ይህ ሰው ከየት እንደ መጣ አለማወቃችሁ የሚገርም ነው፤ ይሁን እንጂ፣ ዐይኔን የከፈተው እርሱ ነው።
\v 31 እግዚአብሔር ኀጢአተኞችን እንደማይሰማ እናውቃለን፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን የሚያመልክና ፈቃዱን የሚያደርግ ሰው ሁሉ እግዚአብሔር ይሰማዋል።
\s5
\v 32 ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ፣ ዐይነ ስውር ሆኖ የተወለደን ሰው ዐይን የከፈተ ሰው ከቶ አልተሰማም።
\v 33 ይህ ሰው ከእግዚአብሔር ባይሆን ኖሮ፣ አንድም ነገር ማድረግ ባልቻለ ነበር።”
\v 34 እነርሱም፣ መልሰው “አንተ ሁለንተናህ በኀጢአት የተወለደ፣ አሁን አንተ እኛን ታስተምረናለህን?” አሉት። ከዚያም ከምኵራብ አስወጡት።
\s5
\v 35 ኢየሱስም ሰውየውን ከምኵራብ እንዳስወጡት ሰማ። ሰውየውንም አግኝቶ፣ “በሰው ልጅ ታምናለህን?” አለው።
\v 36 እርሱም፣ “ጌታ ሆይ፣ አምንበት ዘንድ እርሱ ማን ነው?” አለው።
\v 37 ኢየሱስም፣ “አይተኸዋል፤ አሁን እንኳ ከአንተ ጋር እየተነጋገረ ያለው እርሱ ነው” አለው።
\v 38 ሰውየውም፣ “ጌታ ሆይ፣ አምናለሁ” አለ። ከዚያም ሰገደለት።
\s5
\v 39 ኢየሱስም፣ “የማያዩ እንዲያዩ፣ የሚያዩም እንዳያዩ፣ ለፍርድ ወደዚህ ዓለም መጣሁ” አለ።
\v 40 ከእነርሱም ጋር ከነበሩት አንዳንድ ፈሪሳውያን ይህን ሰምተው፣ “እኛም ደግሞ ዐይነ ስውራን ነን ወይ?” አሉት።
\v 41 ኢየሱስም ፣ “ዐይነ ስውራን ብትሆኑማ፣ ኀጢአት ባልሆነባችሁ ነበር። ነገር ግን፣ ‘እናያለን’ ስለምትሉ፣ ኀጢአታችሁ እንዳለ ይኖራል።”
\s5
\c 10
\cl ምዕራፍ 10
\p
\v 1 “እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ ወደ በጎች በረት በበር ሳይሆን፣ በሌላ መንገድ ተንጠላጥሎ የሚገባ እርሱ ሌባና ወንበዴ ነው።
\v 2 በበር የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው።
\s5
\v 3 በር ጠባቂውም ለእርሱ ይከፍትለታል። በጎቹም ድምፁን ይሰማሉ፤ እርሱም የራሱን በጎች በስማቸው ጠርቶ፣ ወደ ውጭ ይመራቸዋል።
\v 4 የራሱን ሁሉ ካወጣቸው በኋላ፣ ፊት ፊታቸው ይሄዳል፤ በጎቹም ድምፁን ስለሚያውቁ ይከተሉታል።
\s5
\v 5 ባዕድ የሆነውን አይከተሉትም፤ ይልቁንም የባዕዱን ድምፅ ስለማያውቁት ይሸሹታል።”
\v 6 ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ እነርሱ ግን የነገራቸው ስለ ምን እንደ ሆነ አልገባቸውም።
\s5
\v 7 ኢየሱስም እንደ ገና እንዲህ አላቸው፤ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ የበጎች በር እኔ ነኝ።
\v 8 ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው፤ በጎቹ ግን አላዳመጡአቸውም።
\s5
\v 9 በሩ እኔ ነኝ። ማንም በእኔ በኩል ቢገባ፣ ይድናል፤ ይገባል፣ ይወጣልም፤ መሰማሪያም ያገኛል።
\v 10 ሌባው የሚመጣው ሊሰርቅ፣ ሊገድልና ሊያጠፋ ብቻ ነው። እኔ ግን ሕይወት እንዲኖራቸውና እንዲትረፈረፍላቸው መጥቻለሁ።
\s5
\v 11 መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ለበጎቹ ሲል ነፍሱን ይሰጣል።
\v 12 እረኛ ያልሆነው ተቀጣሪ በጎቹም የእርሱ ያልሆኑት፣ ቀበሮ መምጣቱን ሲያይ በጎቹን ጥሎ ይሸሻል ። ቀበሮም ነጥቆአቸው ይሄዳል፤ ይበታትናቸውማል።
\v 13 የሚሸሸውም ተቀጣሪ ስለ ሆነና ለበጎቹ ደንታ ስለሌለው ነው።
\s5
\v 14 መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ የእኔ የሆኑትን ዐውቃቸዋለው፤ የእኔ የሆኑትም ያውቁኛል።
\v 15 አብ እንደሚያውቀኝ፤ እኔም አብን ዐውቀዋለው፤ ነፍሴንም ስለ በጎች እሰጣለሁ።
\v 16 ከዚህ በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ። እነዚያን ደግሞ ማምጣት አለብኝ፤ እነርሱ ድምፄን ይሰማሉ። አንድ መንጋ ይሆናሉ፤ እረኛቸውም አንድ ይሆናል።
\s5
\v 17 አባቴ የሚወደኝ ለዚህ ነው፤ መልሼ ልወስደው እንድችል ነፍሴን እሰጣለሁ ።
\v 18 ነፍሴን ማንም ከእኔ አይወሰድም፤ ግን እኔው ራሴ እሰጣለሁ ። ለመስጠት ሥልጣን አለኝ፤ መልሼ ለመውሰድም ሥልጣን አለኝ። ይህን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀብያለሁ።”
\s5
\v 19 ከዚህ አባባል የተነሣም በአይሁድ መካከል እንደ ገና መከፋፈል ተፈጠረ።
\v 20 ብዙዎች፣ “ጋኔን ስላለበት ዐብዶአል፤ ለምን ታዳምጡታላችሁ?” አሉ።
\v 21 ሌሎችም፣ “ንግግሩ ጋኔን ያለበት ሰው ንግግር አይደለም። ጋኔን ያለበት ሰው የዐይነ ስውርን ዐይን መክፈት ይችላልን?” አሉ።
\s5
\v 22 በኢየሩሳሌምም የቤተ መቅደስ መታደስ በዓል ደርሶ ነበር።
\v 23 ጊዜው ክረምት ነበረ፤ ኢየሱስም በቤተ መቅደስ በሰሎሞን መተላለፊያ ይመላለስ ነበር።
\v 24 ከዚያም አይሁድ ወደ እርሱ ተሰብስበው፣ «እስከ መቼ ድረስ ልባችንን ታንጠለጥላለህ? አንተ ክርስቶስ ከሆንህ፣ በግልጽ ንገረን» አሉት።
\s5
\v 25 ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “ነገርኋችሁኮ፤ እናንተ ግን አታምኑም፤ በአባቴ ስም የማደርጋቸው ሥራዎች እነዚህ ስለ እኔ ይመሰክራሉ።
\v 26 እናንተ ግን በጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም።
\s5
\v 27 በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ፤ እኔ ዐውቃቸዋለሁ፤ እነርሱም ይከተሉኛል።
\v 28 የዘላለም ሕይወት እሰጣቸዋለው፤ ፈጽሞም አይጠፉም፤ ነጥቆ ከእጄ የሚያወጣቸው ማንም የለም።
\s5
\v 29 እነርሱን ለእኔ የሰጠ አባቴ ከሌሎች ሁሉ ይበልጣል፤ ስለዚህ ከአብ እጅ ነጥቆ ሊያወጣቸው የሚችል ማንም የለም።
\v 30 እኔና አብ አንድ ነን።”
\v 31 አይሁድ ሊወግሩት እንደ ገና ድንጋይ አነሡ።
\s5
\v 32 ኢየሱስም መልሶ፣ «ከአብ የሆነ ብዙ መልካም ሥራ አሳይቻችኋለሁ፤ ከእነዚህ ሥራዎች ውስጥ በየትኛው ምክንያት ትወግሩኛላችሁ?” አላቸው።
\v 33 አይሁድም መልሰው፣ «የምንወግርህ በየትኛውም መልካም ሥራ ምክንያት አይደለም፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ በምትሰነዝረው የስድብ ቃል ምክንያት ነው፤ አንተ ሰው ሆነህ ሳለህ፣ ራስህን አምላክ እያደረግህ ስለ ሆነ ነው» አሉት።
\s5
\v 34 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ «በሕጋችሁ፣ ‘አማልክት ናችሁ አልሁ’ ተብሎ አልተጻፈምን?
\v 35 የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት ናችሁ ካላቸው፣ የመጻሕፍት ቃል አይሻርምና፣
\v 36 እኔ ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ስላልሁ፣ አብ ቀድሶ ወደ ዓለም የላከውን እንዴት የስድብ ቃል ሰነዘረ ትሉታላችሁ?
\s5
\v 37 እኔ የአባቴን ሥራዎች የማላደርግ ከሆንሁ አትመኑኝ።
\v 38 ነገር ግን የማደርጋቸው ከሆንሁ፣ በእኔ ባታምኑ እንኳ፣ አብ በእኔ እንዳለ፣ እኔም በአብ እንዳለሁ እንድታውቁና እንድትረዱ፣ በሥራዎቹ እመኑ።»
\v 39 እነርሱም ኢያሱስን እንደ ገና ለመያዝ ሞከሩ፣ እርሱ ግን ከእጃቸው አምልጦ ሄደ።
\s5
\v 40 ኢየሱስ ዮርዳኖስን ተሻግሮ፣ ዮሐንስ በመጀመሪያ ሲያጠምቅበት ወደ ነበረው ቦታ እንደ ገና ሄደ፤ በዚያም ቆየ ።
\v 41 ብዙ ሰዎች ወደ ኢየሱስ መጡ። እነርሱም፣ «በርግጥ ዮሐንስ ምንም ተአምር አልሠራም፤ ነገር ግን ዮሐንስ ስለዚህ ሰው የተናገረው ሁሉ እውነት ነው» ይሉ ነበር።
\v 42 በዚያም ብዙ ሰዎች በኢያሱስ አመኑ።
\s5
\c 11
\cl ምዕራፍ 11
\p
\v 1 አልዓዛር የተባለ አንድ ሰውም ታሞ ነበር። እርሱም ማርያምና እኅትዋ ማርታ በሚኖሩበት መንደር በቢታንያ ይኖር ነበር።
\v 2 ወንድምዋ የታመመባትም የጌታ ኢየሱስን እግር ሽቱ የቀባችውና በጠጕርዋ ያበሰችው ናት።
\s5
\v 3 ከዚያም እኅትማማቹ፣ ‹‹እነሆ፣ የምትወደው ታሞአልና በፍጥነት ድረስ›› በማለት ወደ ኢየሱስ ላኩበት።
\v 4 ኢየሱስ መልእክቱን በሰማ ጊዜ፣ ‹‹ይህ የእግዚአብሔር ልጅ እንዲከብርበት ለእግዚአብሔር ክብር የሚሆን ነው›› አለ።
\s5
\v 5 ኢየሱስ ማርታንና እኅቷን እንዲሁም አልዓዛርን ይወድ ነበር፡፡
\v 6 ስለሆነም አልዓዛር መታመሙን በሰማ ጊዜ፣ ኢየሱስ በነበረበት ቦታ ሁለት ተጨማሪ ቀናት ቆየ፡፡
\v 7 ከዚህ በኋላም ደቀ መዛሙርቱን፣ “ወደ ይሁዳ ዳግመኛ እንሂድ” አላቸው፡፡
\s5
\v 8 ደቀ መዛሙርቱ፣ “መምህር ሆይ፣ አይሁድ አሁን ሊወግሩህ ነበር፣ እንደ ገና ወደዚያ ተመልሰህ ትሄዳለህን?” አሉት፡፡
\v 9 ኢየሱስም፣ “በአንድ ቀን ውስጥ አሥራ ሁለት የብርሃን ሰዓታት አሉ አይደለምን? አንድ ሰው በቀን የሚራመድ ከሆነ የቀኑን ብርሃን ስለሚመለከት፣ አይደናቀፍም፡፡
\s5
\v 10 በሌሊት የሚራመድ ከሆነ ግን ብርሃኑ በእርሱ ውስጥ ስለሌለ፣ ይደናቀፋል፡፡”
\v 11 ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ተናገረ፣ ከእነዚህም ነገሮች በኋላ፣ “ወዳጃችን አልዓዛር አንቀላፍቷል፣ እኔ ግን ከእንቅልፉ ላነቃው እሄዳለሁ” አላቸው፡፡
\s5
\v 12 ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ፣ “ጌታ ሆይ፣ ተኝቶስ ከሆነ ይድናል” አሉት፡፡
\v 13 ኢየሱስም የተናገረው አልዓዛር ስለ መሞቱ ነበር፣ እነርሱ ግን ዕረፍት ለማድረግ ስለ መተኛቱ የተናገረ መስሎአቸው ነበር፡፡
\v 14 ከዚያም ኢየሱስ በግልጽ፣ “አልዓዛር ሞቷል
\s5
\v 15 እናንተ ታምኑ ዘንድ እኔ እዚያ ባለመኖሬ ስለ እናንተ ደስ ብሎኛል” አላቸው፡፡
\v 16 ዲዲሞስ የተባለው ቶማስ ባልደረቦቹ ደቀ መዛሙርትን፣ “ከኢየሱስ ጋር እንሞት ዘንድ እኛም ከእርሱ ጋር እንሂድ” አላቸው፡፡
\s5
\v 17 ኢየሱስ በመጣ ጊዜ፣ አልዓዛር በመቃብር ውስጥ አራት ቀን መቆየቱን ተረዳ፡፡
\v 18 ቢታንያ አሥራ አምስት ኪሎ ሜትር ብቻ የምትርቅ ለኢየሩሳሌም ቅርብ ስፍራ ነበረች፡፡
\v 19 ስለ ወንድማቸው ሞት ሊያጽናኗቸው ከአይሁድ ብዙዎቹ መጥተው ነበር፡፡
\v 20 ከዚያም ማርታ ኢየሱስ እንደ መጣ በሰማች ጊዜ፣ ልትቀበለው ወጣች፣ ማርያም ግን በቤት ተቀምጣ ነበር፡፡
\s5
\v 21 ከዚያም ማርታ ኢየሱስን፣ “ጌታ ሆይ፣ አንተ እዚህ ብትኖር ኖሮ ወንድሜ ባልሞተም ነበር፡፡
\v 22 አሁንም ቢሆን የምትለምነውን ሁሉ እግዚአብሔር እንደሚሰጥህ ዐውቃለሁ” አለችው፡፡
\v 23 ኢየሱስ፣ “ወንድምሽ ይነሣል” አላት፡፡
\s5
\v 24 ማርታ፣ “በመጨረሻው ቀን በሚሆነው በትንሣኤ ከሞት እንደሚነሣ ዐውቃለሁ” አለችው፡፡
\v 25 ኢየሱስ፣ “እኔ ትንሣኤና ሕይወት ነኝ፣ በእኔ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፡፡
\v 26 በእኔ የሚኖርና የሚያምንብኝ ሁሉ ፈጽሞ አይሞትም፤ ይህን ታምኛለሽን?” አላት፡፡
\s5
\v 27 እርሷም፣ “አዎን፣ ጌታ ሆይ፣ አንተ ወደ ዓለም ልትመጣ ያለኸው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆንህ አምናለሁ” አለችው፡፡
\v 28 ማርታ ይህን ከተናገረች በኋላ እኅቷን ማርያምን በግል ለማነጋገር ትጠራት ዘንድ ሄደችና፣ “መምህሩ እዚህ ነው፣ ሊያነጋግርሽ ይፈልጋል” አለቻት፡፡
\v 29 ማርያም ይህን እንደ ሰማች በፍጥነት ተነሥታ ወደ ኢየሱስ ሄደች፡፡
\s5
\v 30 ኢየሱስም ማርታን ባገኘበት ስፍራ ነበር እንጂ ገና ወደ መንደሩ አልገባም ነበር፡፡
\v 31 ከዚያም በቤት ውስጥ ሆነው ማርያምን ሲያጽናኗት የነበሩት አይሁድ ፈጥና ስትወጣ ባዩአት ጊዜ፣ ወደ መቃብር ሄዳ በዚያ ልታለቅስ መስሏቸው ተከተሏት፡፡
\v 32 ከዚያም ማርያም ኢየሱስ ወደ ነበረበት መጥታ ስታየው በእግሩ ሥር ወድቃ፣ “ጌታ ሆይ፣ አንተ እዚህ ብትሆን ኖሮ፣ ወንድሜ ባልሞተም ነበር” አለችው፡፡
\s5
\v 33 ኢየሱስ እርሷና ዐብረዋት የነበሩት አይሁድ ሲያለቅሱ ተመልክቶ በመንፈሱ ቃትቶና ተጨንቆ፣
\v 34 “ወዴት አኖራችሁት?” አላቸው፡፡ እነርሱም፣ “ጌታ ሆይ፣ መጥተህ እይ” አሉት፡፡
\v 35 ኢየሱስ አለቀሰ፡፡
\s5
\v 36 ከዚያም አይሁድ፣ “አልዓዛርን ምን ያህል ይወደው እንደ ነበረ ተመልከቱ!” አሉ፡፡
\v 37 ከእነርሱ አንዳንዶቹ ግን፣ “ዓይነ ስውር የነበረውን ሰውዬ ዓይን የከፈተ ይህ ሰው የሞተውን ይህን ሰው እንዳይሞት ማድረግ አይችልም ነበር?” አሉ፡፡
\s5
\v 38 ከዚያም ኢየሱስ አሁንም በውስጡ እየቃተተ ወደ መቃብሩ ሄደ፡፡ መቃብሩ ዋሻ ነበረ፣ ድንጋይም ተገጥሞበት ነበር፡፡
\v 39 ኢየሱስ፣ “ድንጋዩን አንሡት” አለ፡፡ የሟቹ የአልዓዛር እኅት ማርታም ኢየሱስን፣ “ከሞተ አራት ቀን ስለሆነው፣ በአሁኑ ጊዜ ገላው ይበሰብሳል” አለችው፡፡
\v 40 ኢየሱስ ማርታን፣ “ብታምኚስ፣ የእግዚአብሔርን ክብር እንደምታዪ አልነገርሁሽምን” አላት፡፡
\s5
\v 41 ስለዚህ ድንጋዩን አነሡት፡፡ ኢየሱስም ሽቅብ እየተመለከተ፣ “አባት ሆይ፣ ስለ ሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ፤
\v 42 ሁልጊዜም እንደምትሰማኝ ዐውቃለሁ፣ ነገር ግን ይህን ያልሁት አንተ እንደላክኸኝ ያምኑ ዘንድ እዚህ በዙሪያዬ ስለቆመው ሕዝብ ነው” አለ፡፡
\s5
\v 43 ይህን ካለ በኋላ ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “አልዓዛር ሆይ፣ ውጣ!” አለ፡፡
\v 44 የሞተው ሰው እጁና እግሩ በመገነዣ ጨርቅ እንደ ተጠቀለለ፣ ፊቱም በጨርቅ እንደ ተሸፈነ ወጣ፡፡ ኢየሱስ፣ “ፍቱትና ይሂድ” አላቸው፡፡
\s5
\v 45 ከዚያም ወደ ማርያም ከመጡትና ይህን ከተመለከቱት አይሁድ አብዛኛዎቹ በእርሱ አመኑ፤
\v 46 ነገር ግን ከእነርሱ አንዳንዶቹ ወደ ፈሪሳውያን ሄደው ኢየሱስ ያደረገውን ነገሯቸው፡፡
\s5
\v 47 ከዚያም ሊቀ ካህናቱና ፈሪሳውያን ጉባዔ ጠርተው፣ “ምን እናድርግ? ይህ ሰው ብዙ ምልክቶችን እያደረገ ነው፡፡
\v 48 እንደዚሁ የምንተወው ከሆነ፣ ሮማውያን መጥተው ስፍራችንና አገራችንንም ይወስዳሉ” አሉ፡፡
\s5
\v 49 ሆኖም በዚያ ዓመት ሊቀ ካህን የነበረ ከእነርሱ መካከል ቀያፋ የተባለው አንዱ፣ “እናንተ ምንም አታውቁም፤
\v 50 አገሪቱ በመላ ከምትጠፋ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ቢሞት የተሻለ እንደሆነ ከግምት ውስጥ አላስገባችሁም” አላቸው፡፡
\s5
\v 51 እርሱ ይህን የተናገረው ከራሱ አልነበረም፣ ይልቁንም በዚያ ዓመት ሊቀ ካህን ስለ ነበረ፣ ኢየሱስ ስለ ሕዝቡ፣
\v 52 ደግሞም ስለ ሕዝቡ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በልዩ ልዩ ስፍራ የተበታተኑትን የእግዚአብሔርን ልጆች ይሰበስብ ዘንድ መሞት እንደሚገባው ትንቢት ተናገረ፡፡
\v 53 ስለዚህ ከዚያ ቀን ጀምሮ ኢየሱስን እንዴት መግደል እንዳለባቸው ዕቅድ አወጡ፡፡
\s5
\v 54 ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ በአይሁድ መካከል በግልጽ መውጣትና መግባቱን ትቶ ኤፍሬም ወደ ተባለው በበረሐው አጠገብ ወዳለው ከተማ ሄደ፡፡ እዚያ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ቈየ፡፡
\v 55 የአይሁድ የፋሲካ በዓልም ቀርቦ ነበረና ብዙዎች ራሳቸውን ያነጹ ዘንድ ከፋሲካው በፊት ከየገጠሩ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄዱ ነበር፡፡
\s5
\v 56 ኢየሱስን እየፈለጉት፣ በቤተ መቅደስ ቆመው ሳሉ፣ “ምን ይመስላችኋል? ወደ በዓሉ አይመጣ ይሆን?” እያሉ እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ነበር፡፡
\v 57 ሊቀ ካህናቱና ፈሪሳውያኑም ኢየሱስን ይይዙት ዘንድ እርሱ የት እንዳለ ያወቀ ማንኛውም ሰው ጥቆማ እንዲያቀርብ ትእዛዝ አስተላለፉ፡፡
\s5
\c 12
\cl ምዕራፍ 12
\p
\v 1 የፋሲካ በዓል ሊከበር ስድስት ቀናት ሲቀሩት ኢየሱስ ከሞት ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ፡፡
\v 2 ስለዚህ በዚያ እራት አዘጋጁለት፣ አልዓዛር ከኢየሱስ ጋር በማዕድ ከተቀመጡት ጋር ሲሆን ማርታ ደግሞ ታገለግላቸው ነበር፡፡
\v 3 ማርያም ከንጹሕ ናርዶስ የተሠራ በጣም ውድ የሽቱ ብልቃጥ ወስዳ የኢየሱስን እግር ትቀባ፣ በፀጉሩዋም ታብስ ስለነበር፣ ቤቱ በሽቱው መዓዛ ታወደ፡፡
\s5
\v 4 ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ ኢየሱስን አሳልፎ የሚሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ፣
\v 5 “ይህ ሽቱ በሦስት መቶ ዲናር ተሸጦ ለድሆች ያልተሰጠው ለምንድን ነው?” አለ፡፡
\v 6 ይህን ያለው ለድሆች ተገዶላቸው ሳይሆን ሌባ ስለነበረ ነው፤ የገንዘብ ከረጢቱን የሚይዘው እርሱ ስለነበረ፣ ከዚያ ውስጥ ለራሱ ጥቂት ይወስድ ነበር፡፡
\s5
\v 7 ኢየሱስ፣ “የያዘችውን ለቀብሬ ቀን እንድታቆየው ፍቀዱላት፤
\v 8 ድሆች ምንጊዜም ከእናንተ ጋር ይሆናሉ፣ እኔን ግን ሁልጊዜ አታገኙኝም” አላቸው፡፡
\s5
\v 9 ብዙ የአይሁድ ሕዝብም ኢየሱስ በዚያ እንደነበረ ተረድተው ነበርና ወደዚያ መጡ፣ የመጡትም ለኢየሱስ ብቻ ብለው ሳይሆን ኢየሱስ ከሞት ያስነሣውን አልዓዛርንም ለማየት ጭምር ነበር፡፡
\v 10 የካህናት አለቆች አልዓዛርን ደግሞ ለመግደል በአንድነት የተንኮል ስምምነት አደረጉ፣
\v 11 ምክንያቱም ብዙ አይሁድ የሄዱትና በኢየሱስ ያመኑት ከእርሱ የተነሣ ነበር፡፡
\s5
\v 12 በማግስቱ ብዙ ሕዝብ ወደ በዓሉ መጡ። ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም መምጣቱን በሰሙ ጊዜ፣
\v 13 የዘንባባ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው፣ “ሆሣዕና! በጌታ ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው” እያሉ ሊቀበሉት ወጡ፡፡
\s5
\v 14 ኢየሱስ የአህያ ውርንጫ አገኘና ተቀመጠባት፣ ይህንን ያደረገው፣
\v 15 “የጽዮን ልጅ ሆይ፣ አትፍሪ፣ እነሆ፣ ንጉሥሽ በአህያ ውርንጫ ላይ ተቀምጦ ይመጣል” ተብሎ በተጻፈው መሠረት ነው፡፡
\s5
\v 16 ደቀ መዛሙርቱ በመጀመሪያ ይህን አልተረዱም ነበር፣ ኢየሱስ በከበረ ጊዜ ግን እነዚህ ነገሮች ስለ እርሱ ተጽፈው እንደነበረና እነርሱም እነዚህን ነገሮች ለእርሱ እንዳደረጉለት ተገነዘቡ፡፡
\s5
\v 17 ኢየሱስ አልዓዛርን ከመቃብር በጠራውና ከሞት ባስነሣው ጊዜ በዚያ የነበሩት ሕዝብም ለሌሎች መሰከሩላቸው፡፡
\v 18 ይህን ምልክት እንዳደረገ ሰምተው ነበርና ሊቀበሉት የወጡትም በዚህ ምክንያት ነበር፡፡
\v 19 ስለዚህ ፈሪሳውያን እርስ በርሳቸው፣ “ምንም ማድረግ እንደማትችሉ ተመልከቱ፣ ዓለሙ ተከትሎታል” ተባባሉ፡፡
\s5
\v 20 በበዓሉ ሊያመልኩ ከሄዱት መካከል አንዳንድ የግሪክ ሰዎችም ነበሩ፡፡
\v 21 እነዚህ በገሊላ ካለችው ከቤተሳይዳ ወደ ሆነው ወደ ፊልጶስ ዘንድ ሄደው፣ “ጌታ ሆይ፣ ኢየሱስን ማየት እንፈልጋለን” አሉት፡፡
\v 22 ፊልጶስ ሄዶ ለእንድርያስ ነገረው፣ እንድርያስና ፊልጶስም ዐብረው ሄዱና ለኢየሱስ ነገሩት፡፡
\s5
\v 23 ኢየሱስም፣ “የሰው ልጅ የሚከብርበት ሰዓት ደርሷል፤
\v 24 እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ የስንዴ ዘር ወደ ምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ከሞተች ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች፡፡” ብሎ መለሰላቸው፡፡
\s5
\v 25 ሕይወቱን የሚወድ ያጠፋታል፤ ነገር ግን በዚህ ዓለም እያለ ሕይወቱን የሚጠላ ለዘላለም ሕይወት እንድትጠበቅ ያደርጋታል።
\v 26 ማንም ሊያገለግለኝ የሚወድ ይከተለኝ፤ እኔ ባለሁበት አገልጋዬም በዚያ ይሆናል። ማንም ቢያገለግለኝ አብ ያከብረዋል።
\s5
\v 27 አሁን ነፍሴ ታውካለች ምን እላለሁ? 'አባት ሆይ፣ ከዚህ ሰዓት አድነኝ' ነገር ግን ስለዚህ ጉዳይ ወደዚህ ሰዓት መጥቻለሁ።
\v 28 አባት ሆይ፣ ስምህን አክብረው።» ከዚያም ከሰማይ፣ «አክብሬዋለሁ ደግሞም አከብረዋለሁ» የሚል ድምፅ መጣ።።
\v 29 ባጠገቡ ቆመው የነበሩትና ድምፁን የሰሙት ብዙ ሕዝብ ነጐድጓድ መሰላቸው። ሌሎች ደግሞ «መልአክ ተናግሮታል» አሉ።
\s5
\v 30 ኢየሱስ መልሶ፣ «ይህ ድምፅ የመጣው ስለ እኔ ሳይሆን ስለ እናንተ ነው» አለ።
\v 31 በዚህ ዓለም ላይ የሚፈረድበት ጊዜ አሁን ነው፤ አሁን የዚህ ዓለም ገዢ ወደ ውጭ ይጣላል።
\s5
\v 32 እኔ ከምድር ከፍ ከፍ በምልበት ጊዜ፣ ሰውን ሁሉ ወደ ራሴ እስባለሁ።»
\v 33 ይህን የተናገረው በምን ዓይነት ሁኔታ እንደሚሞት ለማመልከት ነበር።
\s5
\v 34 ሕዝቡ፣ «ክርስቶስ ለዘላለም እንደሚኖር ከሕጉ ሰምተናል። ታዲያ 'የሰው ልጅ ከፍ ከፍ ማለት አለበት እንዴት ትላለህ?' ይህስ የሰው ልጅ ማን ነው?» ብለው መለሱለት።
\v 35 ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ «አሁን ለጥቂት ጊዜ ብርሃን በመካከላችሁ አለ፤ ጨለማ እንዳይውጣችሁ በዚህ ብርሃን ተመላለሱ። በጨለማ የሚመላለስም ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም።
\v 36 የብርሃን ልጆች እንድትሆኑ ብርሃኑ እያለላችሁ በብርሃኑ እመኑ።» ኢየሱስ ይህን ከተናገረ በኋላ ከእነርሱ ተለየ፤ ተሰወረባቸውም።
\s5
\v 37 ምንም እንኳ ኢየሱስ በሕዝቡ ፊት ብዙ ምልክቶችን ቢያደርግም በእርሱ አላመኑም።
\v 38 ይህም ነቢዩ ኢሳይያስ፣ «ጌታ ሆይ የተናገርነውን ማን አመነ? የጌታስ ክንድ ለማን ተገለጠ?» በማለት የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው።
\s5
\v 39 በዚህም ምክንያት ማመን አልቻሉም፤ ኢሳይያስ እንደ ገና እንዲህ ብሏልና፤
\v 40 «ዐይኖቻቸውን አሳውሯል፤ ልባቸውንም አደንድኗል፤ ይህም የሆነው በዐይናቸው ዐይተው በልባቸው አስተውለውና ተመልሰው እንዳልፈውሳቸው ነው።»
\s5
\v 41 ኢሳይያስ እነዚህን ነገሮች የተናገረው የኢየሱስን ክብር ስላየና ስለ እርሱም ስለ ተናገረ ነው፤
\v 42 የሆነ ሆኖ ከገዢዎች እንኳ ብዙዎች በኢየሱስ አምነዋል፤ ነገር ግን ፈሪሳውያን ከምኵራብ እንዳያግዷቸው በመፍራት ማመናቸውን አልገለጹም።
\v 43 በእግዚአብሔር ከመመስገን ይልቅ በሰዎች ለመመስገን ወደዱ።
\s5
\v 44 ኢየሱስ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፤ «በእኔ የሚያምን በእኔ ብቻ የሚያምን ሳይሆን በላከኝም ያምናል፤
\v 45 እንደዚሁም እኔን የሚያይ የላከኝንም ያያል።
\s5
\v 46 በእኔ የሚያምን በጨለማ ውስጥ እንዳይኖር ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤
\v 47 ማንም ቃሌን ሰምቶ ባያደርገው የምፈርድበት እኔ አይደለሁም፤ ዓለምን ለማዳን እንጂ በዓለም ላይ ልፈርድ አልመጣሁምና።
\s5
\v 48 እኔን የሚቃወምና ቃሌንም የማይቀበል የሚፈርድበት አለ፤ በመጨረሻው ቀን የሚፈርድበት እኔ የተናገርሁት ቃል ነው።
\v 49 ምክንያቱም ይህ ቃል ከራሴ የተናገርሁት አይደለም፤ ይልቁን ምን እንደምልና እንደምናገር ትእዛዝ የሰጠኝ የላከኝ አብ ነው።
\v 50 ትእዛዙም የዘላለም ሕይወት እንደሚያስገኝ አውቃለሁ፤ ስለዚህ የምናገረው ቃል አብ እንደ ነገረኝ የምናገረው ነው።»
\s5
\c 13
\cl ምዕራፍ 13
\p
\v 1 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ ከፋሲካ በዓል በፊት ከዚህ ዓለም ተለይቶ ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ ስላወቀ፣ ቀድሞውኑ የሚወዳቸውን በዓለም ይኖሩ የነበሩትን የራሱን ወገኖች እስከ መጨረሻው ወደዳቸው።
\v 2 ዲያብሎስም ኢየሱስን አሳልፎ እንዲሰጥ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ ይሁዳ ልብ ክፉ ዐሳብ አስገባ።
\s5
\v 3 ኢየሱስ አብ ሁሉን ነገር በእጁ አሳልፎ እንደ ሰጠው፣ ከእግዚአብሔር እንደ መጣ ወደ እግዚአብሔርም ተመልሶ እንደሚሄድ ዐወቀ፤
\v 4 ከእራት ላይ ተነሣ፤ መጎናጸፊያውንም አስቀመጠ፤ ከዚያም ፎጣ ወስዶ ወገቡ ላይ ከታጠቀ በኋላ
\v 5 በሳሕን ውስጥ ውሃ ጨምሮ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠብና በያዘውም ፎጣ ማበስ ጀመረ።
\s5
\v 6 ወደ ስምዖን ጴጥሮስ መጣ፤ ጴጥሮስም «ጌታ ሆይ የእኔን እግር ልታጥብ ነውን?» አለው
\v 7 ኢየሱስም «የማደርገውን አሁን አይገባህም፤ወደፊት ግን ትረዳዋለህ» በማለት መለሰለት
\v 8 ጴጥሮስም «ፈጽሞ የእኔን እግር አታጥብም» አለው ኢየሱስም «እግርህን ካላጠብሁህ ከእኔ ጋር ዕድል ፈንታ አይኖርህም» ሲል መለሰለት
\v 9 ስምዖን ጴጥሮስም «ጌታ ሆይ እንግዲያስ እግሬን ብቻ ሳይሆን እጄንና ራሴንም እጠበኝ» አለው
\s5
\v 10 ኢየሱስም «ገላውን የታጠበ እግሩን ብቻ ከመታጠብ በስተቀር ሌላ ሰውነቱ ንጹህ ነው፤ እናንተ ንጹሓን ናችሁ ነገር ግን ይህን ስል ሁላችሁንም ማለቴ አይደለም»
\v 11 ኢየሱስ «ሁላችሁም ንጹህ አይደላችሁም» ያለው ኣሳልፎ የሚሰጠው ማን እንደሆነ ያውቅ ስለነበረ ነው
\s5
\v 12 ኢየሱስ እግራቸውን አጥቦ ከጨረሰ በኋላ ልብሱን ለብሶ ተቀመጠ፤ እነርሱንም፣ «ያደረግሁላችሁን ልብ ብላችኋል?
\v 13 'መምህር' እና 'ጌታ' ትሉኛላችሁ። እንደዚያም ስለሆንሁ አባባላችሁ ትክክል ነው።
\v 14 እኔ ጌታና መምህር ሆኜ እግራችሁን ካጠብሁ፣ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ልትተጣጠቡ ይገባል።
\v 15 እኔ እንዳደረግሁላችሁ እንደዚያው ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ትቼላችኋለሁ።
\s5
\v 16 እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ አገልጋይ ከጌታው አይበልጥም ወይም የተላከ ሰው ከላኪው አይበልጥም።
\v 17 እነዚህን ነገሮች ብታውቁና ብታደርጓቸው የተባረካችሁ ናችሁ።
\v 18 የምናገረው ሁላችሁን በሚመለከት አይደለም፤ የመረጥኋቸውን አውቃለሁና፣ ነገር ግን እንደዚህ የምናገረው እንጀራዬን የበላ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣ የሚለው የመጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም ነው።
\s5
\v 19 ከመሆኑ በፊት አስቀድሜ የምነግራችሁ በሚፈጸምበት ጊዜ እኔ እንደሆንሁ እንድታምኑ ነው።
\v 20 እውነት እውነት እላችኋለሁ እኔን የሚቀበል የላክሁትን ይቀበላል፤ እኔን የተቀበለ ደግሞ የላክኝን ይቀባላል»
\s5
\v 21 ኢየሱስ ይህን በሚናገርበት ጊዜ በመንፈሱ ታወከ፤ «እውነት እውነት እላችኋለሁ ከእናንተ መካከል አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል» ብሎ በግልጽ ነገራቸው
\v 22 ደቀ መዛሙርቱም ስለማን እየተናገረ እንደሆነ ስላልገባቸው እርስ በርስ ተያዩ።
\s5
\v 23 ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የሆነው ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር ወደ ደረቱ ተጠግቶ ተቀምጦ ነበር።
\v 24 ስለዚህ ስምዖን ጴጥሮስ ወደዚህ ደቀ መዝሙር ጠጋ ብሎ «ንገረን ለመሆኑ ስለ ማን ነው እየተናገረ ያለው?» በማለት ጠየቀው።
\v 25 ወደ ኢየሱስ ደረት ተጠግቶ የተቀመጠው ደቀ መዝሙርም፣ «ጌታ ሆይ፣ ይህ የምትለው ሰው ማን ነው?» ብሎ ጠየቀው።
\s5
\v 26 ከዚያም ኢየሱስ፣ «ይህን ቍራሽ እንጀራ ከወጭቱ አጥቅሼ የምሰጠው ያ ሰው እርሱ ነው» በማለት መለሰለት። ስለዚህ ቍራሹን እንጀራ አጥቅሶ ለአስቆሮቱ ይሁዳ ሰጠው።
\v 27 ቍራሹንም እንጀራ ከተቀበለ በኋላ፣ ሰይጣን ገባበት። ከዚያም ኢየሱስ፣ «ለማድረግ ያሰብኸውን ፈጥነህ አድርግ» አለው።
\s5
\v 28 ኢየሱስ ለይሁዳ እንደዚያ ለምን እንዳለው በማዕድ ላይ ከተቀመጡት ማንም ያወቀ የለም።
\v 29 አንዳንዶቹ ይሁዳ ገንዝብ ያዥ ስለ ነበር፣ ኢየሱስ «ለበዓሉ የሚያስፈልጉንን ነገሮች ግዛ» ወይም ለድኾች ገንዘብ ስጥ ብሎ ነግሮታል ብለው ዐሰቡ።
\v 30 ይሁዳ ቍራሹን እንጀራ ከተቀበለ በኋላ፣ ፈጥኖ ወጣ ምሽትም ነበረ።
\s5
\v 31 ይሁዳ በሄደ ጊዜ፣ ኢየሱስ እንዲህ በማለት ተናገረ፤ «አሁን የሰው ልጅ ከብሯል፣ እግዚአብሔርም በእርሱ ከብሯል።
\v 32 እግዚአብሔር በራሱ ያከብረዋል፣ ደግሞም ፈጥኖ ያከብረዋል።
\v 33 ልጆች ሆይ፣ ከእንግዲህ ከእናንተ ጋር የምቆየው ለጥቂት ጊዜ ነው። እናንተ ትፈልጉኛላችሁ፣ ይሁን እንጂ፣ ለአይሁድ፣ 'እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም' እንዳልኋቸው፣ ለእናንተም የምናገረው እንደዚያ ነው።
\s5
\v 34 እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ዐዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ።
\v 35 እርስ በርሳችሁም ብትዋደዱ የእኔ ደቀ መዛሙርት እንደ ሆናችሁ ሰዎች በዚህ ያውቃሉ።»
\s5
\v 36 ስምዖን ጴጥሮስ «ጌታ ሆይ፣ ወዴት ልትሄድ ነው?» ሲል ጠየቀው። ኢየሱስ፣ «ወደምሄድበት አሁን ልትከተለኝ አትችልም፣ በኋላ ግን ትከተለኛለህ» በማለት መለሰለት።
\v 37 ጴጥሮስ፣ «ጌታ ሆይ፣ አሁን ልከተልህ የማልችለው ለምንድን ነው? ስላንተ ሕይወቴን እንኳ አሳልፌ ለመስጠት ቈርጫለሁ» አለው።
\v 38 ኢየሱስ፣ «ስለ እኔ ሕይወትህን አሳልፈህ ትሰጣለህን? እውነት፣ እውነት እልሃለሁ፣ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ» ብሎ መለሰለት።
\s5
\c 14
\cl ምዕራፍ 14
\p
\v 1 «ልባችሁ አይታወክ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔ ደግሞ እመኑ።
\v 2 በአባቴ ቤት ብዙ የመኖሪያ ስፍራ አለ፤ እንደዚያ ባይሆን ኖሮ፣ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁ ብዬ አልነግራችሁም ነበር።
\v 3 ሄጄም ስፍራ ካዘጋጀሁላችሁ በኋላ፣ እኔ ባለሁበት እናንተም እንድትሆኑ ዳግመኛ እመጣለሁ፣ ወደ ራሴም እወስዳችኋለሁ።`
\s5
\v 4 ወዴት እንደምሄድ መንገዱን ታውቃላችሁ።»
\v 5 ቶማስ ኢየሱስን፣ «ጌታ ሆይ፣ ወዴት እንደምትሄድ አናውቅም፣ መንገዱን እንዴት ማወቅ እንችላለን?» በማለት ጠየቀው።
\v 6 ኢየሱስ እንዲህ አለው፤ «እኔ መንገድ፣ እውነትና ሕይወት ነኝ፤ በእኔ ካልሆነ በቀር ማንም ሰው ወደ አብ ሊመጣ አይችልም።
\v 7 እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም ባወቃችሁት ነበር። ከአሁን ጀምሮ ታውቁታላችሁ አይታችሁትማል።»
\s5
\v 8 ፊልጶስ ጌታ ኢየሱስን፣ «ጌታ ሆይ፣ አብን አሳየን ያ ለእኛ በቂያችን ነው» አለው።
\v 9 ኢየሱስ፣ «ፊልጶስ ሆይ፣ ይህን ያህል ጊዜ ከእናንተ ጋር ኖሬ ገና ኣላወቅኸኝምን? እኔን ያየ አብን አይቷል፤ 'እንዴትስ አብን አሳየን' ትላለህ?
\s5
\v 10 እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? እየነገርኋችሁ ያለው ቃል ከራሴ የምናገረው አይደለም፤ ይልቁንስ ይህን ሥራ የሚሠራው በእኔ ውስጥ የሚኖረው አብ ነው።
\v 11 እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ሌላው ቢቀር ከምሠራው ሥራ የተነሣ እመኑኝ።
\s5
\v 12 እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ በእኔ የሚያምን እኔ የምሠራውን ሥራ እርሱም ይሠራል፤ እንዲያውም እኔ ወደ አብ ስለምሄድ፣ እኔ ከሠራሁት የሚበልጥ ሥራ ይሠራል።
\v 13 አብ በልጁ ይከብር ዘንድ ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።
\v 14 ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ፣ እኔ አደርገዋለሁ።
\s5
\v 15 የምትወዱኝ ከሆነ ትእዛዜን ትጠብቃላችሁ።
\v 16 እኔም ለዘላለም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ እንዲሰጣችሁ አብን እለምናለሁ።
\v 17 እርሱም የእውነት መንፈስ ነው፤ ዓለም ስለማያየው ወይም ስለማያውቀው አይቀበለውም። ይሁን እንጂ፣ ከእናንተ ጋር ስለሚኖርና በውስጣችሁም ስለሚሆን፣ እናንተ ታውቁታላችሁ።
\s5
\v 18 ወላጅ እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፣ ዳግመኛ ወደ እናንተ እመጣለሁ።
\v 19 ከጥቂት ጊዜ በኋላ ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና እናንተም ሕያዋን ትሆናላችሁ።
\v 20 በዚያን ቀን እኔ በአብ እንዳለሁ፣ እናንተ በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ ታውቃላችሁ።
\s5
\v 21 ትእዛዜ በውስጡ ያለ የሚያደርገውም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ፤ ራሴንም እገልጥለታለሁ።
\v 22 የአስቆሮቱ ያልሆነው ይሁዳም ኢየሱስን፣ «ጌታ ሆይ፣ ለዓለም ሳይሆን ለእኛ ራስህን የምትገልጠው እንዴት ነው?» ብሎ ጠየቀው።
\s5
\v 23 ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ «ማንም ሰው ቢወደኝ ቃሌን ይጠብቃል። አባቴም ይወደዋል፣ ወደ እርሱ እንመጣለን፣ መኖሪያችንንም በእርሱ እናደርጋለን።
\v 24 የማይወደኝ ማንኛውም ሰው ቃሌን አይጠብቅም። የምትሰሙት ቃል የእኔ ሳይሆን፣ የላከኝ የአብ ቃል ነው።
\s5
\v 25 በመካከላችሁ ሳለሁ እነዚህን ነገሮች ልብ እንድትሉ ነግሬአችኋለሁ።
\v 26 የሆነ ሆኖ፣ አብ በስሜ የሚልከው አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ሁሉንም ነገር ያስተምራችኋል፤ እኔ የነገርኋችሁንም ነገር ሁሉ እንድታስታውሱ ያስችላችኋል።
\v 27 ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜንም እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጠው ሰላም ዓለም እንደሚሰጠው ዓይነት አይደለም። ልባችሁ አይጨነቅ፣ አይፍራም።
\s5
\v 28 'እሄዳለሁ፣ ዳግመኛም ወደ እናንተ እመጣለሁ' ብዬ የነገርኋችሁን ቃል ሰምታችኋል። ከወደዳችሁኝስ ወደ አብ በመሄዴ ደስ ሊላችሁ ይገባ ነበር፤ ምክንያቱም አብ ከእኔ ይበልጣል።
\v 29 ይህ ነገር በሚፈጸምበት ጊዜ ታምኑ ዘንድ አሁን ከመሆኑ በፊት አስቀድሜ ነገርኋችሁ።
\s5
\v 30 የዚህ ዓለም ገዥ እየመጣ ስለሆነ ከዚህ በላይ ከእናንተ ጋር መነጋገር አልችልም።እርሱ በእኔ ላይ ምንም ሥልጣን የለውም፡
\v 31 ነገር ግን አብን እንደምወድ ዓለም ሁሉ ያውቅ ዘንድ በሰጠኝ ትዕዛዝ መሠረት አብ ያዘዝኝን አደርጋለሁ። ተነሱ ከዚህ እንሂድ»
\s5
\c 15
\cl ምዕራፍ 15
\p
\v 1 እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ ገበሬው ደግሞ አባቴ ነው።
\v 2 እርሱም በእኔ ላይ ያለውን ፍሬ ያማያፈራውን ማንኛውንም ቅርንጫፍ ያስወግደዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውን ግን ይበልጥ ያፈራ ዘንድ ያጠራዋል።
\s5
\v 3 ከነገርኋችሁ ቃል የተነሣ እናንተ ንጹሓን ናችሁ።
\v 4 በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ላይ ካልኖረ በቀር በራሱ ፍሬ ማፍራት እንደማይችል ሁሉ፣ እናንተም በእኔ ካልኖራችሁ ፍሬ ማፍራት አትችሉም።
\s5
\v 5 እኔ የወይን ግንድ ነኝ፤ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ የምኖርበት ያ ሰው ብዙ ፍሬ ያፈራል። ያለ እኔ ምንም ነገር ልታደርጉ አትችሉም።
\v 6 ማንም ሰው በእኔ ባይኖር፣ እንደ ቅርንጫፍ ይወገዳል፣ ይደርቃልም፤ ሰዎች ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉታል፣ ይቃጠላልም።
\v 7 በእኔ ብትኖሩ፣ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ፣ የምትፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ለምኑ ይሰጣችኋል።
\s5
\v 8 ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል።
\v 9 አብ እንደ ወደደኝ እኔም ወደድኋችሁ፣ በፍቅሬ ኑሩ።
\s5
\v 10 እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደጠበቅሁና በፍቅሩ እንደምኖር ሁሉ እናንተም ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።
\v 11 ደስታዬ በውስጣችሁ እንዲሆንና ደስታችሁም ፍጹም እንዲሆን እነዚህን ነገሮች ነግሬአችኋለሁ።
\s5
\v 12 እኔ የምሰጣችሁ ትእዛዝ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው።
\v 13 ስለ ወዳጁ ሲል ሕይወቱን አሳልፎ እንዲሰጥ ግድ ከሚል የሚበልጥ ፍቅር ማንም ሰው የለውም።
\s5
\v 14 ያዘዝኋችሁን ነገር ብታደርጉ ወዳጆቼ ናችሁ።
\v 15 ከእንግዲህ አገልጋዮች ብዬ አልጠራችሁም፤ ምክንያቱም አገልጋይ ጌታው ምን እያደረገ እንዳለ አያውቅም። ከአባቴ የሰማሁትን ነገር ሁሉ እንድታውቁ ስለ ነገርኋችሁ፣ ወዳጆች ብያችኋለሁ።
\s5
\v 16 እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ነገር ግን እኔ መረጥኋችሁ፤ ሄዳችሁ ፍሬ እንድታፈሩ፣ ፍሬአችሁም ዘላቂ ሆኖ እንዲቆይ ሾምኋችሁ። ይህም አብን በስሜ የምትለምኑትን ማንኛውንም ነገር እንዲሰጣችሁ ነው።
\v 17 እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ይህን ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።
\s5
\v 18 ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ ዕወቁ።
\v 19 ከዓለም ብትሆኑ ኖሮ ዓለም የራሱ እንደሆኑት አድርጎ በወደዳችሁ ነበር። ነገር ግን ከዓለም ስላይደላችሁ ከዓለምም ስለ መረጥኋችሁ ዓለም ይጠላችኋል።
\s5
\v 20 'አገልጋይ ከጌታው አይበልጥም' በማለት የነገርኋችሁን ቃል ልብ በሉ፤ እኔን አሳድደውኝ ከሆነ፣ እናንተንም ያሳድዷችኋል፤ ቃሌን ጠብቀው ከሆነ፣ የእናንተንም ቃል ይጠብቃሉ።
\v 21 የላከኝን እርሱን ስለማያውቁ፣ በስሜ ምክንያት ይህን ሁሉ ያደርጉባችኋል።
\v 22 እኔ ባልመጣና ባልነግራቸው ኖሮ ኀጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ ነገር ግን አሁን ለኀጢአታቸው የሚሰጡት ምክንያት የለም።
\s5
\v 23 እኔን የሚጠላ አባቴንም ይጠላል።
\v 24 ማንም ያልሠራውን ሥራ በመካከላቸው ሠርቼ ባላሳያቸው ኖሮ ኀጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን ሥራዬን አይተዋል፤ እኔንና አባቴንም ጠልተዋል።
\v 25 ይህም የሆነው በሕጋቸው 'በከንቱ ጠሉኝ' ተብሎ የተጻፈው ቃል እንዲፈጸም ነው።
\s5
\v 26 ከአብ የምልክላችሁ አጽናኝ፣ እርሱም ከአብ የሚወጣው የእውነት መንፈስ በሚመጣበት ጊዜ፣ ስለ እኔ ይመሰክራል።
\v 27 ከመጀመሪያ ጀምሮ ከእኔ ጋር ስለ ነበራችሁ፣ እናንተም ትመሰክራላችሁ።
\s5
\c 16
\cl ምዕራፍ 16
\p
\v 1 «እነዚህን ነገሮች የምነግራችሁ እምነታችሁ እንዳይናወጥ ነው፡፡
\v 2 ከምኵራብ ያስወጡአችኋል፤ እናንተን የሚገድል ሁሉ ለእግዚአብሔር መልካም እንዳደረገ የሚያስብበት ጊዜ መምጣቱ አይቀርም፡፡
\s5
\v 3 እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉት አብንም ሆነ እኔን ስለማያውቁ ነው፡፡
\v 4 ይህን የምነግራችሁ እነርሱ እነዚህ ነገሮች የሚፈጸሙበት ጊዜ በደረሰ ጊዜ፣ ነገሮቹን እንድታስተውሷቸውና እንዴት እንደነገርኋችሁ እንድታስቡ ነው፡፡ አብሬችሁ ስለ ነበርሁ ስለነዚህ ነገሮች ቀደም ሲል አልነገርኋችሁም፡፡
\s5
\v 5 ነገር ግን አሁን ወደ ላከኝ እመለሳለሁ፤ ያም ሆኖ ከእናንተ ማንም 'የት ነው የምትሄደው? ˋ ብሎ የሚጠይቀኝ የለም።
\v 6 ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች ስላልኋችሁ ልባችሁ በሐዘን ተሞልቷል፡፡
\v 7 ነገር ግን እውነቱን ልንገራችሁ፤ እኔ ብሄድ ይሻላችኋል፤ እኔ ካልሄድሁ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣም፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ፡፡
\s5
\v 8 አጽናኙ በመጣ ጊዜ ስለ ኃጢአት፣ ስለ ጽድቅና ስለ ፍርድ ዓለምን ይወቅሳል፤
\v 9 ስለ ኀጢአት በእኔ ባለማመናቸው፤
\v 10 ስለ ጽድቅ እኔ ወደ አባቴ ስለምሄድና ከእንግዲህ ስለማታዩኝ፣ እንዲሁም
\v 11 ስለ ፍርድ የዚህ ዓለም ገዢ ስለ ተፈረደበት ነው፡፡
\s5
\v 12 ብዙ የምነግራችሁ ነገር አለኝ፤ ነገር ግን አሁን ልትረዱአቸው አትችሉም፡፡
\v 13 ነገር ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፣ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ ምክንያቱም እርሱ ከራሱ አይናገርም፤ ነገር ግን ከእኔ የሰማውን ሁሉ እነዚያን ይናገራል፤ ደግሞም ሊመጡ ስላሉ ነገሮች ይነግራችኋል፡፡
\v 14 የእኔ የሆኑትን ነገሮች ወስዶ ስለሚነግራችሁም ያከብረኛል፡፡
\s5
\v 15 የአባቴ የሆነው ነገር ሁሉ የእኔ ነው፤ ስለዚህ ነው መንፈስ ቅዱስ የእኔ የሆኑትን ነገሮች ወስዶ ይነግራችኋል ያልኋችሁ፡፡
\v 16 ከጥቂት ጊዜ በኋላ ፈጽሞ አታዩኝም ደግሞም እንደ ገና ከጥቂት ጊዜ በኋላ ታዩኛላችሁ።»
\s5
\v 17 ከደቀ መዛሙርቱ አንዳንዶቹ እርስ በርሳቸው ‹‹ወደ አባቴ ስለምሄድ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ፈጽሞ አታዩኝም ደግሞም እንደ ገና ከጥቂት ጊዜ በኋላ ታዩኛላችሁˋ እያለ የሚነግረን ነገር ምንድን ነው? ተባባሉ፡፡
\v 18 ከዚህም የተነሣ ‹‹ከጥቂት ጊዜ በኋላˋ ሲል ምን ማለቱ ነው። ምን እያለ እንደ ሆነ አናውቅም›› አሉ፡፡
\s5
\v 19 ኢየሱስም ሊጠይቁት በጣም እንደ ፈለጉ አይቶ፣ ‹‹ከጥቂት ጊዜ በኋላ ፈጽሞ አታዩኝም ደግሞም እንደ ገና ከጥቂት ጊዜ በኋላ ታዩኛላችሁˋ ስላልሁት ነገር እርስ በርሳችሁ ትጠያየቃላችሁን?
\v 20 እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ እናንተ ታለቅሳለችሁ ታዝናላችሁም፤ ዓለም ግን ደስ ይለዋል፤ እናንተ በሐዘን ትሞላላችሁ፣ ነገር ግን ሐዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል፡፡
\v 21 አንዲት ሴት የመውለጃዋ ወራት በደረሰ ጊዜ፣ የምጧን ሥቃይ እያሰበች ታዝናለች፤ ነገር ግን ከወለደች በኋላ ሕፃን ወደዚህ ዓለም በመምጣቱ ከሚሰማት ደስታ የተነሣ ጭንቀቷን ፈጽሞ አታስበውም፡፡
\s5
\v 22 ደግሞም አሁን ዐዝናችኋል፤ ነገር ግን ተመልሼ አያችኋለሁ፤ ልባችሁም ደስ ይለዋል፤ ደስታችሁንም ማንም ከእናንተ ሊወስድ አይችልም፡፡
\v 23 በዚያም ቀን ምንም ጥያቄ አትጠይቁኝም፤ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ከአብ ዘንድ ማንኛውንም ነገር ብትለምኑ አብ ስለስሜ ይሰጣችኋል፡፡
\v 24 እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፣ ለምኑ፣ ደስታችሁም ሙሉ ይሆን ዘንድ ትቀበላላችሁ፡፡
\s5
\v 25 እስከ አሁን በምሳሌ ስነግራችሁ ነበር፤ ነገር ግን በምሳሌ የማልናገርበትና ለእናንተ ስለ አብ በግልጽ የምናገርበት ጊዜ ይመጣል፡፡
\s5
\v 26 በዚያን ቀን በስሜ ትለምናላችሁ፤ እኔም ስለ እናንተ ወደ አብ እለምናለሁ አልላችሁም፤
\v 27 ምክንያቱም አብ ራሱ እኔን ስለወደዳችሁኝና ከአብ ዘንድ እንደ መጣሁ ስላመናችሁ ይወዳችኋልና ነው፡፡
\v 28 ከአብ ወደዚህ ዓለም መጥቻለሁ፤ እንደ ገናም ይህን ዓለም ትቼ ወደ አብ እሄዳለሁ፡፡»
\s5
\v 29 ደቀ መዛሙርቱ፣ ‹‹እነሆ፣ አሁን በግልጽ ተናገርህ፤ ምንም በምሳሌ አልተናገርህም፡፡
\v 30 አሁን ሁሉን እንደምታውቅና ማንም ጥያቄ ሊጠይቅህ እንደማያስፈልግ አውቀናል። በዚህም ምክንያት አንተ ከአብ እንደ መጣህ እናምናለን» አሉት፡፡
\v 31 ኢየሱስ፣ ‹‹አሁንስ አመናችሁ ማለት ነው?
\s5
\v 32 እነሆ፣ እያንዳንዳችሁ እኔን ብቻዬን ትታችሁ ወደየቤታችሁ የምትበታተኑበት ጊዜ እየመጣ ነው፡፡ አዎን፣ በርግጥም መጥቷል፡፡ ነገር ግን አብ ከእኔ ጋር ስላለ ብቻዬን አይደለሁም፡፡
\v 33 በስሜ ሰላም እንዲሆንላችሁ እነዚህን ነገሮች ነግሬአችኋለሁ፡፡ በዓለም ውስጥ ስትኖሩ መከራ አለባችሁ ነገር ግን አይዟችሁ፣ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ፡፡»
\s5
\c 17
\cl ምዕራፍ 17
\p
\v 1 ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ እያየ፣ ‹‹አባት ሆይ፣ ሰዓቱ ደርሷል፣ ያከብርህ ዘንድ ልጅህን አክብረው
\v 2 ይህም ከአንተ ለተቀበላቸው ሁሉ የዘላለምን ሕይወት እንዲሰጣቸው በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ በሰጠኸው ሥልጣን ልክ ነው፡፡
\s5
\v 3 ብቻህን እውነተኛ አምላክ የሆንኸውን አንተን፣ የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲያውቁ ይህ የዘላለም ሕይወት ነው፡፡
\v 4 አባት ሆይ፣ እንዳከናውነው የሰጠኸኝን ሥራ በመፈጸም በምድር ላይ አከበርሁህ፡፡
\v 5 አሁን አባት ሆይ፣ ዓለም ሳይፈጠር በፊት በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር ከአንተ ጋር አክብረኝ፡፡
\s5
\v 6 ከዓለም ለሰጠኸኝ ለእነዚህ ሰዎች ስምህን ገለጥሁላቸው። የአንተ ነበሩ፣ ለእኔም ሰጠሃቸው፣ ቃልህንም ጠብቀዋል።
\v 7 አሁን ከአንተ የተቀበልኋቸው ነገሮች ሁሉ በርግጥ ከአንተ እንደ መጡ አምነዋል፣
\v 8 የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና። እነርሱም ተቀብለውታል፤ ከአንተ እንደ መጣሁ አውቀዋል አንተ እንደላክኸኝም አምነዋል።
\s5
\v 9 እነርሱ የአንተ ናቸውና አንተ ለሰጠኸኝ ለእነርሱ እንጂ ለዓለም አልጸልይም፡፡
\v 10 የእኔ የሆነው ሁሉ የአንተ ነው፤ የአንተ የሆነውም ነገር ሁሉ የእኔ ነው፤ እኔ በእነርሱ ከብሬአለሁ፡፡
\v 11 እኔ ወደ አንተ እመጣለሁና። ከእንግዲህ በዓለም አልኖርም፤ እነርሱ ግን በዓለም ውስጥ ናቸው፡፡ ቅዱስ አባት ሆይ፣ እኔና አንተ አንድ እንደ ሆንን አንድ እንዲሆኑ በሰጠኸኝ በስምህ ጠብቃቸው፡፡
\s5
\v 12 ከእነርሱ ጋር እያለሁ በሰጠኸኝ በስምህ ጠበቅኋቸው፡፡ በቅዱሳት መጻሕፍት የተባለው እንዲፈጸም ከጥፋት ልጅ በቀር ከእነርሱ አንዱም እንዳይጠፋ ጋረድኋቸው፡፡
\v 13 አሁን ወደ አንተ እመጣለሁ፤ ይህን በዓለም ሳለሁ የምናገረው፣ ደስታዬ በእነርሱ ሙሉ እንዲሆን ነው፡፡
\v 14 ቃልህን ሰጥቻቸዋለሁ፤ እኔ ከዓለም እንዳልሆንሁ እነርሱም ከዓለም አይደሉምና ዓለም ይጠላቸዋል፡፡
\s5
\v 15 ከክፉው እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልጸልይም፡፡
\v 16 እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ እነርሱም ከዓለም አይደሉም፡፡
\v 17 በእውነት ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው፡፡
\s5
\v 18 አንተ ወደ ዓለም ላክኸኝ፣ እኔም ደግሞ እነርሱን ወደ ዓለም ልኬአቸዋለሁ፡፡
\v 19 እነርሱ በእውነት እንዲቀደሱ እኔ ራሴን ስለ እነርሱ ቀድሼአለሁ፡፡
\s5
\v 20 ከእነርሱ ምስክርነት የተነሣ በእኔ ስለሚያምኑት ሁሉ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልጸልይም፡፡
\v 21 ይህም አባት ሆይ፣ አንተ በእኔ እኔም በአንተ እንዳለሁ እነርሱም አንድ እንዲሆኑ ነው፡፡ ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ እንዲያምን እነርሱም በእኛ እንዲሆኑ እጸልያለሁ፡፡
\s5
\v 22 እኛ አንድ እንደ ሆንን እነርሱም አንድ እንዲሆኑ የሰጠኸኝን ክብር ሰጥቻቸዋለሁ፤
\v 23 ይህም እኔ በእነርሱ አንተም በእኔ ሆነህ እነርሱ በአንድነት ፍጹማን እንዲሆኑና ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ እኔን በወደድህበት ፍቅር እነርሱንም እንደ ወደድሃቸው እንዲያውቅ ነው።
\s5
\v 24 አባት ሆይ፣ የሰጠኸኝ እነዚህ ስለ ወደድኸኝ ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ የሰጠኸኝን ክብር እንዲያዩ እኔ ባለሁበት እነርሱም ከእኔ ጋር እንዲሆኑ እወዳለሁ፡፡
\s5
\v 25 ጻድቅ አባት ሆይ፣ ዓለም አላወቀህም፤ እኔ ግን አውቅሃለሁ፤ እነዚህም አንተ እንደ ላክኸኝ አውቀዋል፡፡
\v 26 አንተን እንዲያውቁ አድርጌአለሁ፤ እኔን የወደድህበት ፍቅር በእነርሱም እንዲሆንና እኔም በእነርሱ እንድሆን ስምህን አስታውቃቸዋለሁ፡፡
\s5
\c 18
\cl ምዕራፍ 18
\p
\v 1 ኢየሱስ ይህን ከተናገረ በኋላ ከቄድሮን ሸለቆ ማዶ የአትክልት ስፍራ ወደሚገኝበት ቦታ ሄደ፣ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደ አትክልት ስፍራው ገባ፡፡
\v 2 ኢየሱስ በተደጋጋሚ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደዚያ ስፍራ ይመጣ ስለ ነበር አሳልፎ ሊሰጠው ያለው ይሁዳ ቦታውን ያውቅ ነበር፡፡
\v 3 ከዚያም ይሁዳ ከካህናት አለቆችና ከፈሪሳውያን ብዙ ወታደሮችንና ጠባቂዎችን ከተቀበለ በኋላ ፋኖስ፣ ችቦና የጦር መሣሪያ ይዞ ወደ አትክልት ስፍራው መጣ፡፡
\s5
\v 4 ከዚያም እየደረሰበት ያለውን የተረዳው ኢየሱስ ወደ ፊት ወጥቶ፣ ‹‹ማንን ፈለጋችሁ? አላቸው፤
\v 5 እነርሱ፣ ‹‹የናዝሬቱ ኢየሱስን›› ብለው መለሱለት፡፡ ኢየሱስ፣ ‹‹እኔ ነኝ›› አላቸው፡፡ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳም ከወታደሮቹ ጋር ቆሞ ነበር፡፡
\s5
\v 6 ስለዚህ ‹‹እኔ ነኝ›› ባላቸው ጊዜ ወደ ኋላ አፈግፍገው በምድር ላይ ወደቁ፡፡
\v 7 እንደ ገናም፣ ‹‹ማንን ፈለጋችሁ? አላቸው። እነርሱም፣ ‹‹የናዝሬቱ ኢየሱስን›› ብለው በድጋሚ መለሱለት፡፡
\s5
\v 8 ኢየሱስ፣ ‹‹እኔ ነኝ አልኋችሁ፤ ስለዚህ እኔን የምትፈልጉ ከሆነ እነዚህን እንዲሄዱ ተዉአቸው›› አላቸው፡፡
\v 9 ይህም ‹‹ከሰጠኸኝ ከእነዚህ አንዱም አልጠፋብኝም›› ተብሎ የተነገረው ቃል እንዲፈጸም ነው፡፡
\s5
\v 10 ከዚያም ስምዖን ጴጥሮስ የታጠቀውን ሰይፍ መዞ የሊቀ ካህናቱን አገልጋይ ቀኝ ጆሮውን ቈረጠ፡፡ የአገልጋዩም ስም ማልኮስ ነበረ፡፡
\v 11 ኢየሱስ ጴጥሮስን፣ ‹‹ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልስ፡፡ አብ የሰጠኝን ጽዋ መጠጣት የለብኝም እንዴ? አለው፡፡
\s5
\v 12 ስለዚህ ወታደሮቹና አዛዣቸው እንዲሁም የአይሁድ ጠባቂዎች ኢየሱስን ይዘው አሰሩት፡፡
\v 13 በዚያን ዓመት ሊቀ ካህናት የነበረው ቀያፋ ለሐና አማቹ ስለ ነበረ፣ በመጀመሪያ ወደ ሐና ወሰዱት ፡፡
\v 14 ቀያፋ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ቢሞት ይሻላል ብሎ አይሁድን የመከረው ሰው ነው፡፡
\s5
\v 15 ጴጥሮስና አንድ ሌላ ደቀ መዝሙር ኢየሱስን ተከትለው ሄዱ፡፡ ሌላኛው ደቀ መዝሙር ከሊቀ ካህናቱ ጋር ይተዋወቅ ስለ ነበረ፣ ከኢየሱስ ጋር ወደ ሊቀ ካህናቱ አደባባይ ገባ፡፡
\v 16 ጴጥሮስ ግን በውጭ በር ላይ ቆሞ ነበር፡፡ ከሊቀ ካህናቱ ጋር የሚተዋወቀው ያ ደቀ መዝሙር በር የምትጠብቀውን አገልጋይ አናግሮ ጴጥሮስን ወደ ውስጥ አስገባው፡፡
\s5
\v 17 ከዚያም በር ትጠብቅ የነበረችው አገልጋይ ጴጥሮስን፣ ‹‹አንተ ከዚህ ሰው ደቀ መዛሙርት አንዱ አይደለህም እንዴ? አለችው፡፡ እርሱ፣ ‹‹አይደለሁም›› አለ፡፡
\v 18 ጊዜው ብርድ ስለ ነበረ፣ አገልጋዮችና ጠባቂዎች እሳት አቀጣጥለው ዙሪያውን ከበው እየሞቁ ነበር፡፡ ጴጥሮስም በዚያ ከእነርሱ ጋር ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር፡፡
\s5
\v 19 ከዚያም ሊቀ ካህናቱ ኢየሱስን ስለ ደቀ መዛሙርቱና ስለ አስተማረው ትምህርት ጠየቀው፡፡
\v 20 ኢየሱስ፣ ‹‹ለዓለም ሁሉ በግልጽ ስናገር ነበር፤ ሁልጊዜ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኵራብና በቤተ መቅደስ ሳስተምር ነበር፤ በድብቅ የተናገርሁት ምንም ነገር የለም፣
\v 21 ታዲያ ለምን ትጠይቀኛለህ? የተናገርኋቸውን ነገሮች ስለሚያውቁ ሲሰሙኝ የነበሩትን ሰዎች ስለተናገርኋቸው ነገሮች ጠይቅ›› ብሎ መለሰለት፡፡
\s5
\v 22 ኢየሱስ ይህን በተናገረ ጊዜ፣ በዚያ ከቆሙት ጠባቂዎች መካከል አንዱ በጥፊ መታውና፣ ‹‹እንደዚህ ነው ለሊቀ ካህናቱ የምትመልሰው? አለው፡፡
\v 23 ኢየሱስ፣ ‹‹አንዳች ክፉ ነገር ተናግሬ ከሆነ መስክርብኝ፤ በትክክል መልሼ ከሆነ ግን ለምን ትመታኛለህ? አለው፡፡
\v 24 ሐናም ኢየሱስን እንደ ታሰረ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ላከው፡፡
\s5
\v 25 ስምዖን ጴጥሮስም ቆሞ እሳት እየሞቀ ነበር። ሰዎቹ፣ ‹‹አንተ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ አይደለህም እንዴ? አሉት። ጴጥሮስ፣ ‹‹አይደለሁም›› ብሎ ካደ፡፡
\v 26 ጴጥሮስ ጆሮውን የቈረጠው ሰው ዘመድ የሆነ ከሊቀ ካህናቱ አገልጋዮች አንዱ፣ ጴጥሮስን፣ ‹‹አንተን በአትክልት ስፍራው ከእርሱ ጋር አላየሁህም እንዴ? አለው፡፡
\v 27 ጴጥሮስ እንደ ገና ካደ፣ ወዲያውም ዶሮ ጮኸ፡፡
\s5
\v 28 ከዚያም ኢየሱስን ከቀያፋ ወደ ገዢው ግቢ ወሰዱት። ጊዜው ማለዳ ነበረ፣ ይዘውት የመጡት አይሁድ እንዳይረክሱና ፋሲካን መብላት እንዲችሉ ወደ ገዢው ግቢ መግባት አልፈለጉም።
\v 29 ስለዚህ ጲላጦስ ወደ ውጭ ወጥቶ፣ «በዚህ ሰው ላይ ያላችሁ ክስ ምንድን ነው?» ብሎ ጠየቃቸው።
\v 30 እነርሱም፣ «ይህ ሰው ክፉ ባያደርግ ኖሮ ወደ አንተ አናመጣውም ነበር» አሉት።
\s5
\v 31 ስለዚህ ጲላጦስ፣ «እናንተ ወስዳችሁ በሕጋችሁ መሠረት ፍረዱበት» አላቸው። አይሁድ፣ «እኛ ማንንም ሰው ለመግደል አልተፈቀደልንም» ብለው መለሱለት።
\v 32 ይህንም ያሉት ኢየሱስ በእንዴት ዓይነት ሞት እንደሚሞት የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።
\s5
\v 33 ጲላጦስ ወደ ግቢው ተመልሶ ኢየሱስን ጠራውና፣ «አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?» አለው።
\v 34 ኢየሱስ፣ «ይህን የምትጠይቀኝ ከራስህ ነው ወይስ ሌሎች እንድትጠይቀኝ ስለ ነገሩህ ነው?» አለው።
\v 35 ጲላጦስ፣ «እኔ አይሁዳዊ አይደለሁም፤ ነኝ እንዴ? ለእኔ አሳልፈው የሰጡህ የገዛ አገርህ ሰዎችና የካህናት አለቆች ናቸው፣ ምን አድርገህ ነው?» አለው።
\s5
\v 36 ኢየሱስ፣ «የእኔ መንግሥት ከዚህ ዓለም አይደለም፤ የእኔ መንግሥት ከዚህ ዓለም ቢሆን ኖሮ አይሁድ እንዳይዙኝ አገልጋዮቼ ይዋጉልኝ ነበር። በመሠረቱ የእኔ መንግሥት ከምድር አይደለም» ብሎ መለሰለት።
\v 37 ጲላጦስ፣ «ታዲያ አንተ ንጉሥ ነህ?» አለው፤ ኢየሱስ፣ «እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ተናገርህ፤ የተወለድሁት ወደ ዓለምም የመጣሁት ስለ እውነት ለመመስከር ነው፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል» ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 38 ጲላጦስ፣ «እውነት ምንድን ነው?» ካለ በኋላ፣ እንደ ገና ወደ አይሁድ ወጣና፣ «በዚህ ሰው ላይ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም።
\v 39 እንደ ተለመደው በየዓመቱ በፋሲካ በዓል አንድ እስረኛ እለቅላችኋለሁ፣ ታዲያ የአይሁድን ንጉሥ ልፍታላችሁን?» አላቸው።
\v 40 ከዚያም፣ እነርሱ፣ እንደ ገና ጮኸው «ይህን ሰው አይደለም፣ በርባንን ፍታልን» አሉ። በርባን ግን ወንበዴ ነበር።
\s5
\c 19
\cl ምዕራፍ 19
\p
\v 1 ከዚያም ጲላጦስ ኢየሱስን ወስዶ አስገረፈው።
\v 2 ወታደሮቹ የእሾኽ አክሊል ጐንጕነው በኢየሱስ ራስ ላይ አደረጉ። ሐምራዊ ልብስም አለበሱት።
\v 3 ወደ እርሱ መጥተው፣ «የተከበሩ የአይሁድ ንጉሥ ሆይ!» አሉ በጥፊም መቱት።
\s5
\v 4 ከዚያም ጲላጦስ እንደ ገና ወደ ወጥቶ ሕዝቡን፣ «ምንም ጥፋት እንዳላገኘሁበት እንድታውቁ እነሆ፣ ሰውየውን ወደ ውጭ አወጣላችኋለሁ» አላቸው።
\v 5 ስለዚህ ኢየሱስ የእሾኽ አክሊል ደፍቶና ሐምራዊ ልብስ ለብሶ ወደ ውጭ ወጣ። ጲላጦስም፣ «እነሆ፣ ሰውየው!» አላቸው።
\v 6 የካህናት አለቆችና ጠባቂዎቹ ኢየሱስን ባዩ ጊዜ፣ «ስቀለው፣ ስቀለው» እያሉ ጮኹ። ጲላጦስ፣ «እናንተ ወስዳችሁ ስቀሉት፤ እኔ ምንም ወንጀል አላገኘሁበትም» አላቸው።
\s5
\v 7 አይሁድ፣ «እኛ ሕግ አለን፣ በሕጋችን መሠረትም ይህ ሰው ራሱን የእግዚአብሔር ልጅ አድርጓልና ሞት ይገባዋል» ብለው መለሱ።
\v 8 ጲላጦስ ይህን ሲሰማ የበለጠ ደነገጠ፤
\v 9 ወደ ግቢውም ተመልሶ ኢየሱስን፣ «ከየት ነው የመጣኸው?» ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስ ግን ምንም አልመለሰለትም።
\s5
\v 10 ጲላጦስም ኢየሱስን፣ «አናግረኝ እንጂ፤ ልፈታህም ሆነ ልሰቅልህ ሥልጣን እንዳለኝ አታውቅም እንዴ?» አለው።
\v 11 ኢየሱስ፣ «ከላይ ባይሰጥህ ኖሮ በእኔ ላይ ምንም ሥልጣን ባልኖረህ ነበር። ስለዚህም ለአንተ አሳልፎ የሰጠኝ ኀጢአቱ የከፋ ነው» አለው።
\s5
\v 12 ከዚህ መልሱ የተነሣ ጲላጦስ ሊፈታው ፈለገ፣ ነገር ግን አይሁድ፣ «ራሱን ንጉሥ ብሎ የሚጠራ ቄሣርን የሚቃወም ስለ ሆነ፣ ይህን ሰው ብትለቀው አንተ የቄሣር ወዳጅ አይደለህም» እያሉ ይጮኹ ነበር።
\v 13 ጲላጦስ እነዚህን ቃላት በሰማ ጊዜ ኢየሱስን ወደ ውጭ አውጥቶ የድንጋይ ንጣፍ፣ በዕብራይስጥ ግን ገበታ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ በፍርድ ወንበር ላይ ተቀመጠ።
\s5
\v 14 ቀኑ ለፋሲካ በዓል ዝግጅት የሚደረግበትና ሰዓቱም ከቀኑ ስድስት ሰዓት አካባቢ ነበር። ጲላጦስ አይሁድን፣ «እነሆ፣ ንጉሣችሁ» አላቸው።
\v 15 እነርሱም፣ «አስወግደው፣ አስወግደው፣ ስቀለው!» እያሉ ጮኹ። እርሱ፣ «ንጉሣችሁን ልስቀለውን?» አላቸው። የካህናት አለቆችም፣ «እኛ ከቄሣር በቀር ሌላ ንጉሥ አናውቅም» ብለው መለሱለት።
\v 16 ስለዚህ ጲላጦስ ኢየሱስን እንዲሰቅሉት ፈቀደላቸው።
\s5
\v 17 ከዚያም ኢየሱስን፣ የሚሰቀልበትን መስቀል አሸክመው የራስ ቅል፣ በዕብራይስጥ ደግሞ ጎልጎልታ ወደሚባል ቦታ ወሰዱት።
\v 18 በዚያም ስፍራ ሰቀሉት፤ ሁለት ሌሎች ሰዎችንም በኢየሱስ ግራና ቀኝ ሰቀሉ።
\s5
\v 19 ጲላጦስም ጽሑፍ አዘጋጅቶ በኢየሱስ መስቀል ላይ አስቀመጠ። ጽሑፉም፣ «የናዝሬቱ ኢየሱስ፣ የአይሁድ ንጉሥ» የሚል ነበር።
\v 20 ኢየሱስ የተሰቀለበት ቦታ ለከተማው ቅርብ ስለ ነበር፣ ብዙ አይሁድ ጽሑፉን ያነቡት ነበር። ጽሑፉም የተጻፈው በዕብራይስጥ፣ በላቲንና በግሪክ ቋንቋዎች ነበር።
\s5
\v 21 የአይሁድ የካህናት አለቆችም ጲላጦስን «እርሱ ራሱን 'የአይሁድ ንጉሥ ነኝ' ብሏል ብለህ ነው እንጂ፣ 'የአይሁድ ንጉሥ' ብለህ መጻፍ የለብህም» አሉት።
\v 22 ጲላጦስም፣ «አንዴ የጻፍሁትን ጽፌአለሁ» አላቸው።
\s5
\v 23 ወታደሮቹ ኢየሱስን ከሰቀሉት በኋላ ልብሱን ወስደው ለእያንዳንዳቸው እንዲዳረስ አድርገው አራት ቦታ ቈራረጡት፣ እጀ ጠባቡንም ወሰዱ።
\v 24 እጀ ጠባቡ ግን ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበረና እርስ በርሳቸው «ከምንቀደው ዕጣ እንጣጣልና የሚደርሰው ይውሰደው» ተባባሉ። ይህም የሆነው በቅዱስ መጽሐፍ፣ «ልብሴን ተከፋፈሉት በእጀ ጠባቤም ላይ ዕጣ ተጣጣሉበት» የተባለው ቃል እንዲፈጸም ነው።
\s5
\v 25 ወታደሮቹ ይህን በሚያደርጉበት ጊዜ የኢየሱስ እናት ማርያም፣ የእናቱ እኅት፣ የቀለዮጳ ሚስት ማርያምና መግደላዊት ማርያም በዚያ በኢየሱስ መስቀል አጠገብ ቆመው ነበር።
\v 26 ኢየሱስ እናቱንና ይወደው የነበረውን ደቀ መዝሙር አብረው ቆመው ባየ ጊዜ፣ እናቱን «አንቺ ሴት እነሆ፣ ከአጠገብሽ ያለው እንደ ልጅሽ ይሁንልሽ» አላት ፤
\v 27 ደቀ መዝሙሩንም፣ «እነኋት፣ በአጠገብህ ያለችው እንደ እናትህ ትሁንልህ» አለው። ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።
\s5
\v 28 ኢየሱስ ሁሉ እንደ ተፈጸመ ዐውቆ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፈው እንዲፈጸም፣ «ተጠማሁ» አለ።
\v 29 በዚያም በሆምጣጤ የተሞላ ዕቃ ተቀምጦ ነበር፤ ወዲያውም በሆምጣጤ የተሞላ ሰፍነግ በሂሶጵ ወደ አፉ አስጠጉለት።
\v 30 ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከጠጣ በኋላ «ተፈጸመ» አለ። ራሱንም አዘንብሎ ሞተ።
\s5
\v 31 ቀኑ የመዘጋጀት ቀን በመሆኑና ሰንበትም በአይሁድ ዘንድ በጣም የሚከበር ስለነበረ በሰንበት ሥጋቸው በመስቀል ላይ መቆየት ስለሌለበት የሞት ፍርድ የተፈጸመባቸው ሰዎች እግሮቻቸው እየተሰበረ ሥጋቸው ከመስቀል እንዲወርድ አይሁድ ጲላጦስን ለመኑት።
\v 32 ከዚያም ወታደሮቹ መጥተው ከኢየሱስ ጋር ከተሰቀሉት ሰዎች በመጀመሪያ የአንዱን፣ ቀጥሎም የሌላኛውን ሰው እግሮች ሰበሩ።
\v 33 ወደ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን ሞቶ ስላገኙት እግሮቹን አልሰበሩም።
\s5
\v 34 ይሁን እንጂ፣ ከወታደሮቹ አንዱ ጐኑን በጦር ወጋው፣ ወዲያውም ከጐኑ ደምና ውሃ ወጣ።
\v 35 ይህን ያየው ሰው ስለዚህ መስክሯል፣ ምስክርነቱም እውነት ነው። እናንተም እንድታምኑ የተናገረው እውነት እንደ ሆነ ያውቃል።
\s5
\v 36 እነዚህ ነገሮች የሆኑት «ከዐጥንቱ አንድም አይሰበርም» የሚለው የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው።
\v 37 ደግሞም በሌላ መጽሐፍ፣ «የወጉትን ያዩታል» ተብሎ ተጽፎአል።
\s5
\v 38 ከእነዚህ ነገሮች በኋላ አይሁድን ፈርቶ በድብቅ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረውና ከአርማትያስ ከተማ የሆነው ዮሴፍ የኢየሱስን አስከሬን ለመውሰድ ጲላጦስን ለመነ። ጲላጦስም ፈቀደለት። ዮሴፍም መጥቶ የኢየሱስን አስከሬን ወሰደ።
\v 39 በአንድ ወቅት በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረው ኒቆዲሞስም አንድ መቶ ነጥር ያህል የእሬትና የከርቤ ቅልቅል ይዞ መጣ።
\s5
\v 40 ስለዚህ የኢየሱስን አስከሬን ወስደው በአይሁድ ባህል አስከሬን ከመቀበሩ በፊት እንደሚደረገው ልማድ አስከሬኑን ሽቱ በተቀባ በበፍታ ጨርቅ ገነዙት።
\v 41 ኢየሱስ ከተቀበረበት ቦታ አጠገብ የአትክልት ስፍራ ነበረ፤ በዚያም ማንም ገና ያልተቀበረበት ዐዲስ መቃብር ይገኝ ነበረ።
\v 42 ቀኑ ለአይሁድ የመዘጋጀት ቀን በመሆኑና መቃብሩም ቅርብ ስለ ነበር፣ የኢየሱስን አስከሬን በዐዲሱ መቃብር አኖሩት።
\s5
\c 20
\cl ምዕራፍ 20
\p
\v 1 በሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ገና ጨለማ እያለ መግደላዊት ማርያም በሌሊት ወደ መቃብሩ መጣች፤ ድንጋዩ ከመቃብሩ ተንከባሎ አየች።
\v 2 ስለዚህ ወዲያው እየሮጠች ተመልሳ ወደ ጴጥሮስና ኢየሱስ ይወደው ወደ ነበረው ደቀ መዝሙር መጥታ፣ «ጌታን ከመቃብሩ አውጥተው ወስደውታል፣ የት እንዳደረጉትም አናውቅም» አለቻቸው።
\s5
\v 3 ከዚያም ጴጥሮስና ሌላኛው ደቀ መዝሙር ወደ መቃብሩ ሄዱ።
\v 4 አብረው እየሮጡ ሳለ፣ ሌላኛው ደቀ መዝሙር ጴጥሮስን ቀድሞ ወደ መቃብሩ ደረሰ።
\v 5 ጐንበስ ብሎ ወደ ውስጥ ሲመለከት፣ የበፍታ ጨርቁ ተቀምጦ አየ፣ ወደ ውስጥ ግን አልገባም።
\s5
\v 6 ከእርሱም በኋላ ጴጥሮስ ደረሰና ወደ መቃብሩ ውስጥ ገባ። የበፍታ ጨርቁ ተቀምጦ አየ፣
\v 7 በኢየሱስ ራስ ላይ የነበረውንም ጨርቅ ከበፍታ ጨርቁ ጋር ዐብሮ ሳይሆን ለብቻው እንደ ተጠቀለለ በቦታው ተቀምጦ አየ።
\s5
\v 8 ከዚያም ጴጥሮስ ቀድሞ ወደ መቃብሩ ደርሶ የነበረው ደቀ መዝሙር ወደ ውስጥ ገባና አይቶ አመነ።
\v 9 ምክንያቱም እስከዚያን ሰዓት ድረስ ኢየሱስ ከሞት እንደሚነሣ በመጻሕፍት የተነገረውን ቃል አላስተዋሉም ነበር።
\v 10 ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ ወደየቤታቸው ሄዱ።
\s5
\v 11 ነገር ግን መግደላዊት ማርያም እያለቀስች ከመቃብሩ ውጭ ቆማ ነበር፤ እያለቀሰችም ጐንበስ ብላ ወደ መቃብሩ ውስጥ ተመለከተ።
\v 12 የኢየሱስ አስከሬን ተጋድሞበት በነበረው ቦታ ላይ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት መላእክት፣ አንደኛው በራስጌ፣ ሌላው ደግሞ በእግርጌ ተቀምጠው አየች።
\v 13 እነርሱም፣ «አንቺ ሴት፣ ለምን ታለቅሻለሽ?» አሏት፤ እርሷም፣ «ጌታዬን ስለወሰዱትና ወዴትም እንዳኖሩት ስለማላውቅ ነው።» አለቻቸው።
\s5
\v 14 ይህን ብላ ዞር ስትል፣ ኢየሱስን እዚያው ቆሞ አየችው፤ እርሱ እንደ ሆነ ግን አላወቀችም ነበር።
\v 15 ኢየሱስ፣ «አንቺ ሴት ለምን ታለቅሽያለሽ፣ ማንንስ እየፈለግሽ ነው?» አላት። እርሷም የአትክልት ስፍራው ጠባቂ መስሏት፣ «ጌታዬ የወሰድኸው አንተ ከሆንህ እባክህ የት እንዳስቀመጥኸው ንገረኝና ልውሰደው።» አለችው።
\s5
\v 16 ኢየሱስም፣ «ማርያም» አላት። ዞር ብላ በአረማይክ ቋንቋ፣ «ረቡኒ» አለችው፤ ትርጓሜውም «መምህር» ማለት ነው።
\v 17 ኢየሱስም«ገና ወደ አብ አልሄድሁምና አትንኪኝ፣ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ፣ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ መሄዴ ነው ብለሽ ንገሪአቸው» አላት።
\v 18 መግደላዊት ማርያምም ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጥታ፣ «ጌታን አየሁት» ብላ ኢየሱስ የነገራትን ሁሉ ነገረቻቸው።
\s5
\v 19 በዚያው ቀን ማለትም ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ምሽት ላይ፣ ደቀ መዛሙርቱ አይሁድን ፈርተው በሮቹ ተዘግተው ሳለ ኢየሱስ በመካከላቸው ቆሞ፣ «ሰላም ለእናንተ ይሁን» አላቸው።
\v 20 ይህንም ብሎ እጁንና ጐኑን አሳያቸው። ደቀ መዛሙርቱም ጌታን ባዩት ጊዜ፣ ደስ አላቸው።
\s5
\v 21 እንደ ገናም ኢየሱስ፣ «ሰላም ለእናንተ ይሁን፣ አብ እንደ ላከኝ እኔም እልካችኋለሁ» አላቸው።
\v 22 ይህንም ብሎ እፍ አለባቸውና፣ «መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ፣
\v 23 ኀጢአቱን ይቅር ያላችሁት ማንም ይቅር ይባልለታል፣ ኀጢአቱን የያዛችሁበት ማንም ይያዝበታል» አላቸው።
\s5
\v 24 ኢየሱስ ወደ ደቀ መዛሙርቱ በመጣ ጊዜ፣ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው ሌላ ስሙ ዲዲሞስ የሚባለው ቶማስ ዐብሮአቸው አልነበረም።
\v 25 ኋላ ላይ ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት፣ «ጌታን አየነው እኮ» አሉት። እርሱም፣ «የምስማር ምልክቱን በእጆቹ ላይ ካላየሁ፣ ጣቶቼንም በምስማር ምልክቱና እጄን በጐኑ ካላስገባሁ አላምንም» አላቸው።
\s5
\v 26 ከስምንት ቀን በኋላ ደቀ መዛሙርቱ በቤት ውስጥ ነበሩ፤ ቶማስም ዐብሯቸው ነበረ። በሮቹ ተዘግተው ሳለ ኢየሱስ በመካከላቸው ቆሞ፣ «ሰላም ለእናንተ ይሁን» አላቸው።
\v 27 ቶማስንም፣ «ጣቶችህን አምጣና እጆቼን ንካ፣ እጆችህንም ወደ ጐኔ አስገባ፣ እመን እንጂ የማታምን አትሁን» አለው።
\s5
\v 28 ቶማስም፣ «ጌታዬና አምላኬ» ብሎ መለሰለት።
\v 29 ኢየሱስ «አንተ ስላየኸኝ አመንህ፣ ሳያዩ የሚያምኑ የተባረኩ ናቸው» አለው።
\s5
\v 30 ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፉ ብዙ ምልክቶችን በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ፤
\v 31 ነገር ግን ይህ የተጻፈው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ እንድታምኑና አምናችሁም በስሙ ሕይወት እንድታገኙ ነው።
\s5
\c 21
\cl ምዕራፍ 21
\p
\v 1 እነዚህ ነገሮች ከተፈጸሙ በኋላ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንደ ገና በጥብርያዶስ ባሕር አጠገብ ተገለጠላቸው፤ ሁኔታውም እንደዚህ ነበር፦
\v 2 ስምዖን ጴጥሮስ ዲዲሞስ ከተባለው ከቶማስ፣ ከገሊላ አውራጃ ከቃና መንደር ከሆነው ከናትናኤል፣ ከዘብዴዎስ ልጆችና ከሌሎች ሁለት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ጋር ዐብረው ነበሩ።
\v 3 ስምዖን ጴጥሮስ፣ «ዓሣ ለማጥመድ መሄዴ ነው» አላቸው። እነርሱም፣ «እኛም ከአንተ ጋር እንሄዳለን» አሉት። በጀልባ ተሳፍረው ሄዱ፤ ነገር ግን በዚያች ሌሊት ምንም ዐሣ አላጠመዱም።
\s5
\v 4 ቀኑ እየነጋ ሳለ ኢየሱስ መጥቶ በባሕሩ ዳር ቆመ፤ እነርሱ ግን ኢየሱስ እንደ ሆነ አላወቁም ነበር።
\v 5 ከዚያም ኢየሱስ «ልጆች ሆይ፣ የሚበላ ዐሣ አላችሁን?» አላቸው። «የለንም» ብለው መለሱለት።
\v 6 ኢየሱስ፣ «መረባችሁን ከጀልባው በቀኝ በኩል ጣሉት ታገኙማላችሁ» አላቸው። እነርሱም እንደተባሉት መረባቸውን ጣሉ፤ ነገር ግን ከዐሣው ብዛት የተነሣ መረቡን ወደ ጀልባው ውስጥ መጐተት አቃታቸው።
\s5
\v 7 ከዚያም ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር ስምዖን ጴጥሮስን፣ «ጌታ እኮ ነው» አለው። ጴጥሮስ ጌታ እኮ ነው የሚለውን ቃል በሰማ ጊዜ፣ መደረቢያውን ልብስ ታጥቆ ወደ ውሃው ውስጥ ዘሎ ገባ።
\v 8 ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት ግን ከምድር የነበራቸው ርቀት ሁለት መቶ ክንድ ያህል ብቻ ስለ ነበር ዐሣ የሞላውን መረብ እየጐተቱ በጀልባ ወደ ዳር መጡ።
\v 9 ወደ መሬትም በደረሱ ጊዜ፣ በላዩ ላይ ዐሣ የተቀመጠበት ፍምና እንጀራ ተዘጋጅቶ አዩ።
\s5
\v 10 ኢየሱስ፣ «እስኪ ካጠመዳችሁት ዐሣ ጥቂት ወደዚህ አምጡ» አላቸው።
\v 11 ስምዖን ጴጥሮስም ሄዶ 153 ዐሣ የሞላውን መረብ ወደ ምድር ጐተተ፤ ምንም እንኳ የዐሣው ብዛት ከፍተኛ ቢሆንም፣ መረቡ ግን አልተቀደደም ነበር።
\s5
\v 12 ኢየሱስ፣ «ኑ ቍርስ ብሉ» አላቸው። ኢየሱስ እንደ ሆነ አውቀው ነበርና ከደቀ መዛሙርቱ ማንም፣ «አንተ ማነህ?» ብሎ ሊጠይቀው የደፈረ አልነበረም።
\v 13 ኢየሱስ እንጀራውን አንሥቶ ሰጣቸው፤ ዐሣውንም እንደዚያው አደረገ።
\v 14 ከሞት ከተነሣ በኋላ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ሲገለጥላቸው ይህ ለሦስተኛ ጊዜ ነበር።
\s5
\v 15 ቍርስ ከበሉ በኋላ፣ ኢየሱስ ስምዖን ጴጥሮስን፣ «የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፣ ከእነዚህ የበለጠ ትወደኛለህን?» አለው። ጴጥሮስ፣ «አዎን፣ ጌታ ሆይ፣ እንደምወድህማ አንተም ታውቃለህ» አለው። ኢየሱ፣ «ጠቦቶቼን መግብ» አለው።
\v 16 እንደ ገና ለሁለተኛ ጊዜ፣ «የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ ትወደኛለህን?» አለው። ጴጥሮስ፣ «አዎን፣ ጌታ ሆይ፣ እንደምወድህማ አንተም ታውቃለህ» አለው። ኢየሱስ፣ «በጎቼን ጠብቅ» አለው።
\s5
\v 17 ለሦስተኛ ጊዜ፣ «የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፣ ትወደኛለህ?» አለው። ለሦስተኛ ጊዜ «ትወደኛለህ ወይ?» ብሎ ስለ ጠየቀው ጴጥሮስ በጣም ዐዘነ። ቀጥሎም፣ «ጌታ ሆይ፣ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንደምወድህም ታውቃለህ» አለው። ኢየሱስም «በጎቼን መግብ።
\v 18 እውነት፣ እውነት እልሃለሁ፣ ወጣት እያለህ ልብስህን ራስህ ለብሰህ ወደምትፈልገው ቦታ ትሄድ ነበር፤ ስታረጅ ግን ሌላ ሰው ልብስህን አልብሶህ ወደማትፈልገው ቦታ ይወስድሃል፣ በዚያን ጊዜ አንተ እጅህን ከመዘርጋት ውጪ ሌላ ማድረግ የምትችለው ነገር አይኖርም» አለው።
\s5
\v 19 ኢየሱስ ይህን የተናገረው ጴጥሮስ በምን ዓይነት አሟሟት እግዚአብሔርን እንደሚያከብር ለማመልከት ነው። ከዚያም ኢየሱስ ጴጥሮስን፣ «ተከተለኝ» አለው።
\s5
\v 20 ጴጥሮስም ዞር ብሎ በፋሲካ እራት ላይ እያሉ ወደ ኢየሱስ ደረት ጠጋ ብሎ፣ «አሳልፎ የሚስጥህ ማን ነው?» ብሎ የጠየቀውንና ኢየሱስ ይወደው የነበረውን ደቀ መዝሙር ሲከተላቸው አየው።
\v 21 ጴጥሮስ ኢየሱስን፣ «ጌታ ሆይ፣ ይህ ሰውስ ምን ይሆናል?» አለው።
\s5
\v 22 ኢየሱስ፣ «እኔ እስክመጣ እንዲቆይ ብፈልግስ አንተን ምን ይመለከትሃል? ዝም ብለህ ተከተለኝ» አለው።
\v 23 በዚህ ምክንያት «ያ ደቀ መዝሙር አይሞትም» የሚል ወሬ በየ ስፍራው ተሠራጨ። ኢየሱስ ግን ለጴጥሮስ፣ «እኔ እስክመጣ እንዲቆይ ብፈልግስ አንተን ምን ይመለከትሃል?» አለው እንጂ ያ ደቀ መዝሙር አይሞትም አላለውም።
\s5
\v 24 ስለ እነዚህ ነገሮች የመሰከረውና የጻፈው ይህ ደቀ መዝሙር ነው፣ ምስክርነቱም እውነት እንደ ሆነ እናውቃለን።
\v 25 ከእነዚህ ሌላ ኢየሱስ ያደረጋቸው ብዙ ነገሮች አሉ። እያንዳንዱ ነገር ቢጻፍ ኖሮ ለሚጻፉት መጻሕፍት ማስቀመጫ ዓለም እንኳ የሚበቃ አይመስለኝም።