am_ulb/43-LUK.usfm

2213 lines
215 KiB
Plaintext
Raw Permalink Blame History

This file contains ambiguous Unicode characters

This file contains Unicode characters that might be confused with other characters. If you think that this is intentional, you can safely ignore this warning. Use the Escape button to reveal them.

\id LUK
\ide UTF-8
\h ሉቃስ
\toc1 ሉቃስ
\toc2 ሉቃስ
\toc3 luk
\mt ሉቃስ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 ብዙዎች በእኛ ዘንድ ስለተፈጸሙት ጉዳዮች ታሪኩን በቅደም ተከተል ለማስቀመጥ ሞክረዋል፣
\v 2 ይህም የዓይን ምስክሮችና የቃሉ አገልጋዮች የሆኑት በመጀመሪያ ለእኛ ባስተላለፉልን መሠረት ነበር፡፡
\v 3 ስለሆነም፣ እጅግ የተከበርክ ቴዎፍሎስ ሆይ፣ እኔም የእነዚህን ነገሮች ሂደት ከመጀመሪያው በትክክል ከመረመርኩ በኋላ፣ በቅደም ተከተላቸው መጻፍ መልካም መስሎ ታየኝ፡፡
\v 4 ይህንንም ያደረግሁት ስለ ተማርኸው ነገር እውነቱን ታውቅ ዘንድ ነው፡፡
\s5
\v 5 በይሁዳ ገዢ፣ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፡፡ ሚስቱም ከአሮን ልጆች የነበረችና ስሟም ኤልሳቤጥ የሚባል ነበር፡፡
\v 6 ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ፣ የእግዚአብሔርን ሕግጋትና ትእዛዛት ሁሉ ያለ ነቀፋ እየጠበቁ ይኖሩ ነበር፡፡
\v 7 ነገር ግን ኤልሳቤጥ መካን ስለነበረች ልጅ አልነበራቸውም፣ በዚህ ጊዜ ደግሞ ሁለቱም አርጅተው ነበር፡፡
\s5
\v 8 በዚህን ጊዜ፣ ዘካርያስ በክፍሉ ተራ የክህነት አገልግሎቱን እየፈጸመ በእግዚአብሔር ፊት የሚሆንበት ጊዜ ደረሰ፡፡
\v 9 የትኛው ካህን እንደሚያገለግል ለመምረጥ በሚፈጸመው ልምድ መሠረት፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ገብቶ ዕጣን ዕጣ ደረሰው፡፡
\v 10 እርሱ ዕጣን በሚያጥንበት ወቅት፣ ሕዝቡ ሁሉ በውጭ ይጸልይ ነበር፡፡
\s5
\v 11 በዚህን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና በዕጣኑ መሠዊያ በስተቀኝ ቆመ፡፡
\v 12 ዘካርያስ በተመለከተው ጊዜ ደነገጠ፣ ፍርሃትም በእርሱ ላይ ወደቀ፡፡
\v 13 ነገር ግን መልአኩ፣ “ጸሎትህ ተሰምቶአልና ዘካርያስ ሆይ፣ አትፍራ፡፡ ሚስትህ ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ፡፡
\s5
\v 14 ሐሴትና ደስታ ይሆንልሃል፣ ብዙዎችም በእርሱ መወለድ ሐሴት ያደርጋሉ፡፡
\v 15 በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ይሆናልና፣ ወይን ጠጅ ወይም የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮም በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ይሆናል፡፡
\s5
\v 16 ከእስራኤል ሕዝብም ብዙዎቹ ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመለሳሉ፡፡
\v 17 በእግዚአብሔርም ፊት በኤልያስ መንፈስና ኃይል ይመላለሳል፡፡ ይህንንም የሚያደርገው የማይታዘዙት በጻድቃን ጥበብ ይሄዱ ዘንድ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች ለመመለስና የተዘጋጁትን ሕዝብ ለእግዚአብሔር ያዘጋጅ ዘንድ ነው” አለው፡፡
\s5
\v 18 ዘካርያስም፣ “እኔ ያረጀሁ በመሆኔና ሚስቴም ዕድሜዋ የገፋ በመሆኑ፣ ይህንን እንዴት ማወቅ እችላለሁ?” አለ፤
\v 19 መልአኩም፣ “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ ይህንን የምሥራች እነግርህ ዘንድ ተልኬያለሁ፡፡
\v 20 እነሆ፣ እነዚህ ነገሮች እስኪፈጸሙ ድረስ ጸጥ ትላለህ፣ መናገርም አትችልም፡፡ ይህም የሚሆነው በትክክለኛው ጊዜ የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንክ ነው፡፡”
\s5
\v 21 በዚህን ጊዜ ሕዝቡ ዘካርያስን እየተጠባበቁ ነበር፣ ለረጅም ጊዜ በቤተ መቅደስ በመቆየቱም ተደነቁ፡፡
\v 22 በወጣ ጊዜ ግን ሊያነጋግራቸው አልቻለም፤ እነርሱም በቤተ መቅደስ በነበረበት ጊዜ ራእይ እንደ ተገለጠለት ተገነዘቡ፡፡ ለእነርሱ ምልክት ብቻ እየሰጣቸው ጸጥ ብሎ ቆየ፡፡
\v 23 የአገልግሎቱም ወቅት እንዳበቃ ወደ ቤቱ ለመመለስ ተነሣ፡፡
\s5
\v 24 ከዚህም ወቅት በኋላ ሚስቱ ኤልሳቤጥ ፀነሰች፤ ለአምስት ወራትም ራሷን ሰወረች፣ እንደዚህም አለች፣
\v 25 “በሕዝብ ዘንድ የነበረብኝን ነቀፌታ ለማስወገድ ብሎ በሞገስ ተመልክቶኝ እግዚአብሔር ለእኔ ያደረገልኝ ይህንን ነው፡፡”
\s5
\v 26 ስድስት ወሯ በነበረ ጊዜ መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደተባለች የገሊላ ከተማ ተላከ፡፡
\v 27 የተላከውም ዮሴፍ ለተባለ ከዳዊት ነገድ ለሆነ ሰው ወደ ታጨች አንዲት ድንግል ነበር፡፡ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበር፡፡
\v 28 ወደ እርሷም መጣና እንደዚህ አላት፣ “እጅግ የተከበርሽ ሆይ፣ ሰላም ለአንቺ ይሁን! እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው፡፡”
\v 29 እርሷ ግን በንግግሩ በጣም ግራ ተጋባች፣ ምን ዓይነት ሰላምታ ሊሆን እንደሚችልም በማሰብ ተደነቀች፡፡
\s5
\v 30 መልአኩም፣ “ማርያም ሆይ፤ አትፍሪ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ አግኝተሻል፤
\v 31 እነሆ፣ ፅንስ በማሕፀንሽ ውስጥ ይፀነሳል፣ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፡፡ ስሙንም ‘ኢየሱስ’ ትይዋለሽ፡፡
\v 32 እርሱም ታላቅ ይሆናል፣ የልዑልም ልጅ ይባላል፡፡ እግዚአብሔር አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፡፡
\v 33 በያዕቆብም ቤት ላይ ለዘላለም ይነግሣል፣ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም፡፡"
\s5
\v 34 ማርያምም ለመልአኩ፣ “ከማንም ወንድ ጋር ተኝቼ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል?” አለችው፡፡
\v 35 መልአኩም እንደዚህ በማለት መለሰላት፣ “መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፣ የልዑል ኃይልም በአንቺ ላይ ያርፋል፤ ከዚህ የተነሣም የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል፡፡
\s5
\v 36 እነሆ፣ ዘመድሽም ኤልሳቤጥ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፤ መካን ትባል ለነበረችው ለእርሷ ይህ ስድስተኛ ወሯ ነው፡፡
\v 37 ለእግዚአብሔር የሚሳነው ምንም ነገር የለምና፡፡”
\v 38 ማርያምም፣ “እነሆ፣ የእግዚአብሔር ባሪያው ነኝ፤ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ፡፡” ከዚያ በኋላም መልአኩ ትቷት ሄደ፡፡
\s5
\v 39 ከዚያ በኋላ፣ ማርያም ተነሥታ በእነዚያ ቀናት በኮረብታማው አገር በይሁዳ ወዳለች ወደ አንዲት ከተማ በፍጥነት ሄደች፡፡
\v 40 ወደ ዘካርያስም ቤት ሄደችና ለኤልሳቤጥ ሰላምታ አቀረበችላት፡፡
\v 41 ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ፣ እንደዚህ ሆነ፣ በማሕፀኗ ያለው ፅንስ ዘለለ፣ ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተሞላች፡፡
\s5
\v 42 ድምፅዋን ከፍ በማድረግ ጮክ ብላ፣ “ከሴቶች መካከል አንቺ የተባረክሽ ነሽ፣ የማሕፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው፡፡
\v 43 የጌታዬ እናት ወደ እኔ እንድትመጣ ይህ ለምን ሆነ?
\v 44 እነሆ፣ የሰላምታሽ ድምፅ ወደ ጆሮዬ በመጣ ጊዜ በማሕፀኔ ውስጥ ያለው ሕፃን በደስታ ዘለለ፡፡
\v 45 ከጌታ የተነገሩላት ነገሮች እንደሚፈጸሙ የምታምን እነሆ እርሷ የተባረከች ናት፡፡”
\s5
\v 46 ከጌታ የተነገሩላት ነገሮች እንደሚፈጸሙ የምታምን እነሆ እርሷ የተባረከች ናት፡፡” 46. ማርያምም፣ “ነፍሴ እግዚአብሔርን ታመሰግናለች፣
\v 47 መንፈሴም በመድኃኒቴ በእግዚአብሔር ሐሴት ታደርጋለች፡፡
\s5
\v 48 የሴት ባሪያውን ውርደት ተመልክቶአልና፡፡ እነሆ፣ ከዚህ በኋላ ትውልድ ሁሉ የተባረከች ይሉኛል፡፡
\v 49 ብርቱ የሆነ እርሱ ለእኔ ታላቅ ነገር አድርጎልኛልና፣ ስሙም ቅዱስ ነው፡፡
\s5
\v 50 ለሚያከብሩት ምሕረቱ ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው፡፡
\v 51 በክንዱ ብርታትን ገልጾአል፣ ስለ ልባቸው ሐሳብ የሚታበዩትን በትኖአቸዋል፡፡
\s5
\v 52 ገዢዎችን ከዙፋናቸው አውርዷቸዋል፣ ዝቅ ያሉትንም ከፍ አድርጓቸዋል፡፡
\v 53 የተራቡትን በመልካም ነገር አጥግቧቸዋል፣ ባለጠጎችን ግን ባዶአቸውን ሰድዷቸዋል፡፡
\s5
\v 54 ምሕረት ማድረጉን ያስታውስ ዘንድ ለባሪያው ለእስራኤል ረድኤቱን ልኮለታል፣
\v 55 ይህንንም ያደረገው (ለአባቶቻችን እንደተናገረው) ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘላለም፡፡”
\s5
\v 56 ማርያም ከኤልሳቤጥ ጋር ሦስት ወራት ያህል ተቀመጠች፣ ከዚያ በኋላም ወደ ቤቷ ተመለሰች፡፡
\v 57 በዚያን ጊዜ ኤልሳቤጥ የምትወልድበት ወቅት ደረሰ፣ ወንድ ልጅም ወለደች፡፡
\v 58 ጎረቤቶቿና ዘመዶቿ እግዚአብሔር ምሕረቱን እንዳበዛላት ሰሙ፣ ከእርሷም ጋር ደስ አላቸው፡፡
\s5
\v 59 ልጁን የሚገርዙበት ስምንተኛው ቀን በመጣ ጊዜ፣ በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ሊሰይሙት ፈልገው ነበር፡፡
\v 60 እናትዬዋ ግን መልስ ሰጠቻቸው፣ “አይሆንም፣ ስሙ ዮሐንስ ይሆናል” አለች፡፡
\v 61 እነርሱም ለእርሷ፣ “ከዘመዶችሽ መካከል በዚህ ስም የተጠራ የለም” አሏት፡፡
\s5
\v 62 በምን ስም እንዲጠራ እንደሚፈልግ አባቱን በምልክት ጠየቁት፡፡
\v 63 አባቱም ሰሌዳ እንዲያቀርቡለት ጠየቀና፣ “ስሙ ዮሐንስ ነው” ብሎ ጻፈ፡፡ በዚህም ሁሉም ተደነቁ፡
\s5
\v 64 ወዲያውኑም አንደበቱ ተከፈተ፣ ምላሱም ተፈትቶ ተናገረ፣ እግዚአብሔርንም አመሰገነ፡፡
\v 65 በዙሪያቸውም በሚኖሩት ሰዎች ዘንድ ፍርሃት መጣባቸው፣ የእነዚህም ነገሮች ዜና በኮረብታማው በይሁዳ አገር ሁሉ ተሠራጨ፡፡
\v 66 ዜናውን የሰሙትም ሁሉ፣ የእግዚአብሔር እጅ ከእርሱ ጋር ነበርና “እንግዲህ ይህ ልጅ ምን ሊሆን ይሆን?” እያሉ ነገሩን በልባቸው ጠበቁት፡፡
\s5
\v 67 አባቱም ዘካርያስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ፣
\v 68 “የእስራኤል አምላክ፣ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፣ የመቤዠት ሥራ በመሥራት ሕዝቡን ረድቶታልና፡፡
\s5
\v 69 ከባሪያው ከዳዊት ዝርያዎች መካከል ለባሪያው ለዳዊት ቤት የድነት ቀንድ አስነሥቶልናል፡፡
\v 70 ይህም በጥንት ዘመን በነበሩት በቅዱሳን ነቢያቱ እንደ ተናገረው ነው፡፡
\v 71 ከጠላቶቻችንና ከሚጠሉን ሁሉ ያድነናል፡፡
\s5
\v 72 ይህንን የሚያደርገው ለአባቶቻችን ምሕረቱን ለማሳየትና ቅዱስ ኪዳኑን፣
\v 73 ማለትም ለአባታችን ለአብርሃም የማለውን መሐላ ለማስታወስ ነው፡፡
\v 74 መሐላውን የማለውም እኛ ከጠላቶቻችን ድነን በዘመኖቻችን ሁሉ በእርሱ ፊት በመሆን ያለ ፍርሃት፣
\v 75 በቅድስናና በጽድቅ እርሱን እንድናገለግለው ነው፡፡
\s5
\v 76 አዎን፣ አንተም ሕፃን የእርሱን መንገድን ለማዘጋጀት በጌታ ፊት ስለምትሄድና ሕዝብንም ለመምጣቱ ስለምታሰናዳ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፡፡
\v 77 ለኃጢአቶቻቸው ይቅርታ የሚያገኙትን የድነት ዕውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ፡፡
\s5
\v 78 ይህም ከእግዚአብሔር አምላካችን መልካም ምሕረት የተነሣ ከእርሱ የተነሣ የፀሐይ ብርሃን በእኛ ላይ እንዲያርፍብንና
\v 79 በጨለማና በሞት ጥላ ላሉት እናበራላቸው ዘንድ ነው፡፡ ይህንንም እግሮቻችንን በሰላም መንገድ ይመራው ዘንድ ያደርገዋል፡፡”
\s5
\v 80 ልጁም አደገ፣ በመንፈሱም ጠነከረ፣ ለእስራኤልም እስኪገለጥ ድረስ በምድረ በዳ ኖረ፡፡
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 በዚያን ጊዜ አውግስጦስ ቄሣር በዓለም የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ይቆጠሩ ዘንድ ዐዋጅ አወጣ፡፡
\v 2 ይህም ቄሬኔዎስ የሶርያ ገዥ በነበረበት ጊዜ የተደረገ የመጀመሪያው የሕዝብ ቆጠራ ነበር፡፡
\v 3 ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ለሕዝብ ቆጠራው ወደየራሱ ከተማ ሄደ፡፡
\s5
\v 4 ዮሴፍም የዳዊት ቤተሰብ ዝርያ ስለነበረ በገሊላ ከነበረችው ከናዝሬት ተነሥቶ የዳዊት ከተማ ወደምትባለው የይሁዳ ከተማ ወደ ነበረችው ወደ ቤተ ልሔም ተጓዘ፡፡
\v 5 ይመዘገብ ዘንድ ለእርሱ ታጭታ ከነበረችውና የመውለጃዋን ቀን እየተጠባበቀች ከነበረችው ከማርያም ጋር ወደዚያ ስፍራ ሄደ፡፡
\s5
\v 6 እዚያም በነበሩበት ጊዜ የምትወልድበት ወቅት ደረሰ፡፡
\v 7 የበኩር ልጅዋ የሆነውን ወንድ ልጅ ወለደች፣ በመታቀፊያ ጨርቅም በሚገባ ጠቀለለችው፡፡ በእንግዳ መቀበያውም ስፍራ ስላልነበረ በእንስሳት መመገቢያ ግርግም ውስጥ አስተኛቸው፡፡
\s5
\v 8 በዚያው አካባቢ በሌሊት የበግ መንጎቻቸውን እየጠበቁ በመስክ የነበሩ እረኞች ነበሩ፡፡
\v 9 በድንገትም የእግዚአብሔር መልአክ ለእነርሱ ተገለጠላቸው፣ የእግዚአብሔርም ክብር በእነርሱ ዙሪያ አበራላቸው፤ እነርሱም በጣም ፈሩ፡፡
\s5
\v 10 ከዚያ በኋላ መልአኩ፣ “ለሕዝብ ሁሉ ታላቅ ደስታ የሚሆን የምሥራች ይዤላችሁ መጥቻለሁና አትፍሩ፡፡
\v 11 ዛሬ በዳዊት ከተማ፣ አዳኝ ተወልዶላችኋል፤ እርሱም ክርስቶስ ጌታ ነው፡፡
\v 12 ለእናንተም ይህ ምልክት ይሰጣችኋል፣ ሕፃን በመታቀፊያ ጨርቅ ተጠቅልሎ፣ በግርግም ተኝቶ ታገኛላችሁ፡፡”
\s5
\v 13 በድንገትም ከመልአኩ ጋር ብዙ የሰማይ ሠራዊት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ፣
\v 14 “ከፍ ባለ ስፍራ ለሚኖረው ለእግዚአብሔር ክብር፣ በምድርም እርሱ ደስ በሚሰኝባቸው ሕዝቦች መካከል ሰላም ይሁን፡፡” ይሉ ነበር፡፡
\s5
\v 15 መላእክቱም ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ በሄዱ ጊዜ፣ እረኞቹ እርስ በርሳቸው፣ “ወደ ቤተልሔም እንሂድና፣ እግዚአብሔር ለእኛ የገለጠልንን ይህንን የሆነውን ነገር እንመልከት፡፡” ተባባሉ፡፡
\v 16 በችኮላ ወደዚያ ሄደው ማርያምንና ዮሴፍን አገኝዋቸው፣ ሕፃኑንም በግርግም ተኝቶ ተመለከቱት፡፡
\s5
\v 17 ይህንን ከተመለከቱ በኋላ ስለዚህ ልጅ የተባለውን ለሕዝቡ አስታወቁ፡፡
\v 18 ያዳመጡአቸውም ከእረኞቹ በተነገራቸው ነገር ተደነቁ፡፡
\v 19 ስለሰማችው ነገር ሁሉ ማርያም እያሰላሰለች በልብዋ ትጠብቀው ነበር፡፡
\v 20 ልክ እንደ ተነገራቸው ስለ ሰሙትና ስላዩት ስለ ማንኛውም ነገር እረኞቹ እግዚአብሔርን እያከበሩና እያመሰገኑ ተመለሱ፡፡
\s5
\v 21 ሕፃኑ የሚገረዝበት ስምንተኛው ቀን በደረሰ ጊዜ በማሕፀን ከመፀነሱ በፊት በመልአኩ በተሰጠው ስም ኢየሱስ ብለው ጠሩት፡፡
\s5
\v 22 በሙሴ ሕግ መሠረት የመንጻታቸው ወራት በተፈጸመ ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርቡት ዘንድ በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ ቤተ መቅደሱ
\v 23 ይህም፣ “ማሕፀንን የሚከፍት ማንኛውም ወንድ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል” ተብሎ በሕጉ እንደ ተጻፈው ነው፡፡
\v 24 በእግዚአብሔር ሕግም በተነገረው መሠረት መሥዋዕት ማለትም ‘ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች’ ያቀርቡ ዘንድ መጡ፡፡
\s5
\v 25 በኢየሩሳሌምም የሚኖር ስሙ ስምዖን የተባለ ሰው ነበር፡፡ ይህ ሰው ጻድቅና የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ የሚያከብር ነበር፤ ለእስራኤል መጽናኛም የሚሆነውን ይጠባበቅ ነበር፣ መንፈስ ቅዱስም በእርሱ ላይ ነበር፡፡
\v 26 እግዚአብሔር የቀባውን ሳያይ እንደማይሞት በመንፈስ ቅዱስ ተገልጦለት ነበር፡፡
\s5
\v 27 የሕጉ ሥርዓት የሚጠይቀውን ሊያደርጉለት ወላጆቹ ሕፃኑ ኢየሱስን ይዘው በመጡበት ቀን በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ወደ ቤተ መቅደስ መጣ፡፡
\v 28 ከዚያም ስምዖን በእጆቹ አቅፎት፣ እግዚአብሔርን እያመሰገነ፣
\v 29 “ጌታ ሆይ፣ እንግዲህ፣ ባሪያህን እንደ ቃልህ በሰላም አሰናብተው፣
\s5
\v 30 ዓይኖቼ ማዳንህን አይተዋልና
\v 31 ይህም ድነት አንተ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸው ነው፡፡
\v 32 እርሱም ለአሕዛብ መገለጥ ብርሃን፣ ለሕዝብህም ለእስራኤል ክብር ነው፡፡”
\s5
\v 33 የልጁም አባትና እናት ስለ እርሱ እየተነገረ ባለው ነገር ተደነቁ፡፡
\v 34 ከዚያ በኋላ ስምዖን ባረካቸውና እናቱን ማርያምን፣ “በጥንቃቄ አድምጪ! ይህ ልጅ በእስራኤል ለብዙዎች ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው ምክንያት፣ ክፉም ለተናገሩበት ምልክት የሚሆን ነው፡፡
\v 35 የብዙዎች የልባቸው ሐሳብ ይገለጥ ዘንድ የአንቺም የራስሽ ልብ በሰይፍ የሚወጋ ይሆናል፡፡”
\s5
\v 36 ሐና የተባለች ነቢይትም በዚያ ነበረች፤ እርሷም ከአሴር ነገድ የሆነ የፋኑኤል ልጅ ነበረች፡፡ ዕድሜዋ እጅግ የገፋ ሲሆን ከጋብቻዋ በኋላ ከባልዋ ጋር ለሰባት ዓመታት ቆይታለች፡፡
\v 37 ከዚያ በኋላ ለሰማንያ አራት ዓመታት መበለት ሆና ኖራለች፡፡ ከቤተ መቅደስ በፍጹም ሳትለይ ቀንና ሌሊት በጾምና በጸሎት እግዚአብሔርን ታመልክ ነበር፡፡
\v 38 ልክ በዚያን ሰዓት ወደ እነርሱ መጥታ እግዚአብሔርን ማመስገን ጀመረች፡፡ የኢየሩሳሌምን መቤዠት ለሚጠባበቁ ለማንኛዎቹም ሰዎች ስለ ልጁ ትናገር ነበር፡፡
\s5
\v 39 እንደ እግዚአብሔር ሕግ እንዲያደርጉ የሚፈለግባቸውን ማንኛውንም ነገር ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ገሊላ ወደ ራሳቸው ከተማ ወደ ናዝሬት ተመለሱ፡፡
\v 40 ልጁ አደገ፣ ጠነከረ፣ በጥበብም ጨመረ፤ የእግዚአብሔር ጸጋም በ እርሱ ላይ ነበረ፡፡
\s5
\v 41 ወላጆቹም ለፋሲካ በዓል በየዓመቱ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄዱ ነበር፡፡
\v 42 አሥራ ሁለት ዓመት በሆነው ጊዜ በተለመደው ጊዜ እንደገና በዓሉን ለማክበር ሄዱ፡፡
\v 43 ለበዓሉ መቆየት ያለባቸውን ሁሉንም ቀናት ከቆዩ በኋላ ወደ ቤታቸው መመለስ ጀመሩ፡፡ ልጁ ኢየሱስ ግን በኢየሩሳሌም ቀረ፣ ወላጆቹም ይህንን አላወቁም ነበር፡፡
\v 44 ከእነርሱ ጋር ይጓዙ ከነበሩት መንገደኞች ጋር የነበረ መስሏቸው ስለነበረ የአንድ ቀን መንገድ ተጓዙ፡፡ ከዚያ በኋላም በዘመዶቻቸውና በወዳጆቻቸው ዘንድ ፈለጉት፡፡
\s5
\v 45 ባላገኙትም ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው በዚያ ሊፈልጉት ጀመሩ፡፡
\v 46 ከሦስት ቀን በኋላ እያዳመጣቸውና ጥያቄዎችን እየጠየቃቸው በመምህራን መካከል ተቀምጦ በቤተ መቅደስ ውስጥ አገኙት፡፡
\v 47 ያዳመጡት ሁሉ በማስተዋሉና በሚሰጣቸው መልሶች ተገረሙ፡፡
\s5
\v 48 ባዩትም ጊዜ ተደነቁ፡፡ እናቱም እርሱን፣ “ልጄ ሆይ፣ ለምን እንደዚህ አደረግኸን? አድምጠኝ፣ እኔና አባትህ ተጨንቀን አንተን ስንፈልግህ ነበርን” አለችው።
\v 49 እርሱም፣ “ለምን ነበር የፈለጋችሁኝ? በአባቴ ቤት እሆን ዘንድ እንደሚገባኝ አታውቁምን?”
\v 50 ነገር ግን እንደዚያ ሲል ምን ማለቱ እንደነበረ አልገባቸውም፡፡
\s5
\v 51 ከዚያ በኋላ ከእነርሱ ጋር ወደ ናዝሬት ተመለሰ፣ ይታዘዝላቸውም ነበር፡፡ እናቱም ይህንን ሁሉ ነገር በልቧ ትጠብቀው ነበር፡፡
\v 52 ኢየሱስ ግን በጥበብና በሰውነት ቁመና ማደጉን ቀጠለ፣ በእግዚአብሔርና በሰዎችም ፊት ያለው ሞገስ እየጨመረ ሄደ፡፡
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 ጢባርዮስ ቄሣር በነገሠ በአሥራ አምስተኛው ዓመት፣ ጴንጤናዊው ጲላጦስ የይሁዳ ገዥ፣ ሄሮድስ የገሊላ አራተኛው ክፍል ገዥ፣ ወንድሙ ፊልጶስ የኢጡርያስና የጥራኮኒዶስ የአራተኛው ክፍል ገዥ፣ ሊሳኒዮስም የሳቢላኒስ አራተኛው ክፈል ገዥ
\v 2 እንደዚሁም ሐናና ቀያፋ ሊቃነ ካህናት በነበሩበት ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ለዘካርያስ ልጅ ለዮሐንስ በምድረ-በዳ መጣ፡፡
\s5
\v 3 ለኃጢአት ይቅርታ የንስሓን ጥምቀት እየሰበከ በዮርዳኖስ ወንዝ አውራጃ ሁሉ ተመላለሰ፡፡
\s5
\v 4 ይህም በነቢዩ በኢሳይያስ መጽሐፍ፣ “በምድረ-በዳ የሚጣራ ሰው ድምፅ፣ ‘የእግዚአብሔርን መንገድ አዘጋጁ፣ ጎዳናውንም አቅኑ፡፡
\s5
\v 5 ሸለቆ ሁሉ ይሞላል፣ ተራራውና ኮረብታው ደልዳላ ይሆናል፣ ጠማማው መንገድ ቀና ይሆናል፣ ሸካራውም መንገድ የተመቸ ይሆናል፡፡
\v 6 ሰዎችም ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ያያሉ፡፡’”
\s5
\v 7 ስለዚህ በእርሱ ለመጠመቅ ይመጣ ለነበረው ከፍተኛ ቁጥር ላለው ሕዝብ ዮሐንስ እንደዚህ አላቸው፣ “እናንተ የመርዘኛ እባብ ልጆች፣ ሊመጣ ካለው ቁጣ እንድትሸሹ ማን አስጠነቀቃችሁ?
\s5
\v 8 ለንስሓ የሚሆን ፍሬ አፍሩ፣ እርስ በርሳችሁም፣ ‘አባታችን አብርሃም አለን’ አትበሉ፣ ምክንያቱም ከእነዚህ ድንጋዮች እንኳን እግዚአብሔር ለአብርሃም ልጆችን ሊያስነሣለት ይችላል፡፡
\s5
\v 9 መጥረቢያ በዛፎች ግንድ ሥር ተቀምጦአል፤ ስለዚህ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ተቆርጦ ወደ እሳት ውስጥ ያጣላል፡፡”
\s5
\v 10 ከዚያ በኋላ ተሰብስበው የነበሩት ሰዎች እንደዚህ ብለው ጠየቁት፣ “እንግዲህ ምን እናድርግ?”
\v 11 እርሱም እንደዚህ ብሎ መለሰላቸው፣ “አንድ ሰው ሁለት ልብስ ካለው ምንም ለሌለው ለሌላ ሰው ይስጠው፤ ትርፍ ምግብ ያለውም እንደዚሁ ያድርግ፡፡”
\s5
\v 12 ከዚያ በኋላም አንዳንድ ቀረጥ ሰብሳቢዎች ለመጠመቅ መጡና እንደዚህ አሉት፣ “መምህር ሆይ፣ እኛስ ምን ማድረግ ይገባናል?”
\v 13 እርሱም እንደዚህ አላቸው፣ “መሰብሰብ ከሚገባችሁ ገንዘብ በላይ አትሰብስቡ፡፡”
\s5
\v 14 አንዳንድ ወታደሮችም እንደዚህ ብለው ጠየቁት፣ “እኛስ፣ ምን ማድረግ ይገባናል?” እርሱም እንደዚህ አላቸው፣ “ከማንም ላይ አስገድዳችሁ ገንዘብ አትውሰዱ፣ ማንንም በሐሰት አትክሰሱ፡፡ የምታገኙትም ደመወዝ ይብቃችሁ፡፡”
\s5
\v 15 ሕዝቡ የክርስቶስን መምጣት እየተጠባበቁ ሳሉ፣ ሰዎች ሁሉ በልባቸው እርሱ ክርስቶስ ይሆን እያሉ ስለ ዮሐንስ ይደነቁ ነበር፡፡
\v 16 እንደዚህ በማለት ዮሐንስ ለሁሉም መልስ ሰጣቸው፣ “እኔ በበኩሌ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፣ የጫማውን ማሠሪያ መፍታት እንኳን የማይገባኝ ከእኔ ይልቅ ብርቱ የሆነ ይመጣል፡፡ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፡፡
\s5
\v 17 አውድማውን ፈጽሞ ያጠራውና ስንዴውን ወደ ጎተራ ያስገባ ዘንድ የሚያበራይበት መንሽ በእጁ ነው፡፡ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል፡፡”
\s5
\v 18 ሌሎች ብዙ ምክሮችንም በመምከር፣ የምሥራቹን ቃል ለሕዝቡ ሰበከላቸው፡፡
\v 19 የወንድሙን ሚስት ሄሮዳይዳን ስላገባና ስላደረጋቸውም ሌሎች ክፉ ሥራዎች የአራተኛው ክፍል ገዥ የነበረውን ሄሮድስንም ገሰጸው፡፡
\v 20 ሄሮድስ ግን ከዚህም የባሰ ክፉ ሥራ ሠራ፣ ዮሐንስን ወህኒ ቤት አስገብቶ ቆለፈበት፡፡
\s5
\v 21 ሰዎች ሁሉ በዮሐንስ እየተጠመቁ ሳሉ፣ ኢየሱስም ደግሞ ተጠመቀ፡፡ እየጸለየም ሳለ ሰማያት ተከፈቱ፡፡
\v 22 መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል በአካል በእርሱ ላይ አረፈ፣ በዚህም ጊዜ ከሰማይ፣ “አንተ፣ ውድ ልጄ ነህ፤ በአንተ እጅግ ደስ ይለኛል፡፡” የሚል ድምፅ መጣ፡፡
\s5
\v 23 በዚህን ጊዜ ኢየሱስ ራሱ ማስተማር ሲጀምር ዕድሜው ሰላሳ ዓመት ገደማ ነበር፡፡ (ይገመት እንደነበረው) እርሱ የኤሊ ልጅ የነበረው የዮሴፍ ልጅ
\v 24 ኤሊም የማቲ ልጅ፣ የሌዊ ልጅ፣ የሚልኪ ልጅ፣ የዮና ልጅ፣ የዮሴፍ ልጅ፣
\s5
\v 25 የማታትዩ ልጅ፣ የአሞጽ ልጅ፣ የናሆም ልጅ፣ የኤሲሊም ልጅ፣ የናጌ ልጅ፣
\v 26 የማኦት ልጅ፣ የማታትዩ ልጅ፣ የሰሜይ ልጅ፣ የዮሴፍ ልጅ፣ የዮዳ ልጅ፣
\s5
\v 27 የዮናን ልጅ፣ የሬስ ልጅ፣ የዘሩባቤል ልጅ፣ የሰላትያል ልጅ፣ የኔር ልጅ፣
\v 28 የሚልኪ ልጅ፣ የሐዲ ልጅ፣ የዮሳስ ልጅ፣ የቆሳም ልጅ፣ የኤልሞዳም ልጅ፣ የኤር ልጅ፣
\v 29 የዮሴዕ ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ፣ የዮራም ልጅ፣ የማጣት ልጅ፣ የሌዊ ልጅ፣
\s5
\v 30 የስምዖን ልጅ፣ የይሁዳ ልጅ፣ የዮሴፍ ልጅ፣ የዮናም ልጅ፣ የኤልያቄም ልጅ፣
\v 31 የሜልያ ልጅ፣ የማይናን ልጅ፣ የማጣት ልጅ፣ የናታን ልጅ፣ የዳዊት ልጅ፣
\v 32 የእሴይ ልጅ፣ የኢዮቤድ ልጅ፣ የቦዔዝ ልጅ፣ የሰልሞን ልጅ፣ የነአሶን ልጅ፣
\s5
\v 33 የአሚናዳብ ልጅ፣ የአራም ልጅ፣ የአሮኒ ልጅ፣ የኤስሮም ልጅ፣ የፋሬስ ልጅ፣ የይሁዳ ልጅ፣
\v 34 የያዕቆብ ልጅ፣ የይስሐቅ ልጅ፣ የአብርሃም ልጅ፣ የታራ ልጅ፣ የናኮር ልጅ፣
\v 35 የሴሮህ ልጅ፣ የራጋው ልጅ፣ የፋሌቅ ልጅ፣ የአቤር ልጅ፣ የሳላ ልጅ፣
\s5
\v 36 የቃይንም ልጅ፣ የአርፋክስድ ልጅ፣ የሴም ልጅ፣ የኖኅ ልጅ፣ የላሜህ ልጅ፣
\v 37 የማቱሳላ ልጅ፣ የሄኖክ ልጅ፣ የያሬድ ልጅ፣ የመላልኤል ልጅ፣ የቃይናን ልጅ፣
\v 38 የሄኖስ ልጅ፣ የሴት ልጅ፣ የአዳም ልጅ፣ የእግዚአብሔር ልጅ፡፡
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 ከዚያ በኋላ፣ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ከዮርዳኖስ ወንዝ ተመለሰ፤ መንፈስም ወደ ምድረ-በዳ መራው፡፡
\v 2 በዚያም ለአርባ ቀናት በዲያብሎስ ተፈተነ፡፡ በእነዚያም ቀናት ምንም አልበላም፣ ያም ወቅት በተጠናቀቀ ጊዜ ተራበ፡፡
\s5
\v 3 ዲያብሎስም፣ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ ይህ ድንጋይ እንጀራ እንዲሆን እዘዝ” አለው፡፡
\v 4 ኢየሱስም፣ “’ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም’ ተብሎ ተጽፎአል፡፡” ብሎ መለሰለት፡፡
\s5
\v 5 ከዚያ በኋላም ዲያብሎስ ከፍ ወዳለ ስፍራ ወሰደውና፣ በቅጽበት የዓለም መንግሥታትን ሁሉ አሳየው፡፡
\v 6 ዲያብሎስም ለእርሱ፣ “እነዚህን ሁሉ መንግሥታት ከክብራቸው ሁሉ ጋር እንድትገዛ እኔ ሥልጣን እሰጥሃለሁ፤ ይህንን ማድረግ የምችለው እገዛቸው ዘንድ ለእኔ ስለተሰጡኝ ነው፣ እኔም ለምፈልገው ለማንኛውም ሰው ልሰጣቸው እችላለሁ፡፡
\v 7 ስለዚህ በፊቴ ብትሰግድልኝና ብታመልከኝ፣ ይሄ ሁሉ የአንተ ይሆናል አለው።
\s5
\v 8 ኢየሱስ ግን እንደዚህ ብሎ መለሰለት፣ “’እግዚአብሔር አምላክህን አምልክ፣ እርሱንም ብቻ አገልግል’ ተብሎ ተጽፎአል፡፡”
\s5
\v 9 ከዚህ በኋላ ዲያብሎስ ወደ ኢየሩሳሌም ወስዶ በቤተ መቅደሱ ሕንፃ እጅግ ከፍተኛ ስፍራ አቆመውና፣
\v 10 “’ይጠብቁህና ይንከባከቡህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዛቸዋል’
\v 11 ደግሞም፣ ‘እግርህም ከድንጋይ ጋር እንዳይጋጭ በእጆቻቸው ወደ ላይ ይይዙሃል’ ተብሎ ተጽፎአልና፣ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ ራስህን ከዚህ ላይ ወርውር፡፡” አለው፡፡
\s5
\v 12 ኢየሱስም፣ “’እግዚአብሔር አምላክህን መፈታተን የለብህም’ ተብሎአል፡፡” ብሎ መለሰለት፡፡
\v 13 ዲያብሎስም ኢየሱስን መፈተኑን ባበቃ ጊዜ፣ እስከ ሌላ ጊዜ ድረስ ትቶት ሄደ፡፡
\s5
\v 14 ከዚያ በኋላ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተሞልቶ ወደ ገሊላ ተመለሰ፤ በዚያ አካባቢ በነበሩት ስፍራዎች ሁሉ የእርሱ ዝና ተሰራጨ፡፡
\v 15 በምኩራቦቻቸው አስተማረ፣ ሰዎችም ሁሉ ያመሰግኑት ነበር፡፡
\s5
\v 16 አንድ ቀንም ወዳደገበት ከተማ ወደ ናዝሬት መጣ፡፡ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኩራብ ገባ፣ የእግዚአብሔርንም ቃል ያነብ ዘንድ ቆመ፡፡
\v 17 የነቢዩ የኢሳይያስ የመጽሐፍ ጥቅልል ተሰጥቶት ስለነበረ፣ ጥቅልሉን ሲከፍተው፣
\s5
\v 18 “ለድሆች የምሥራቹን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለምርኮኞች ነፃነትን፣ ለዕውሮች ብርሃናቸው እንደሚመለስላቸው ፣ የተጨቆኑትም መፈታትን እንደሚያገኙ
\v 19 የእግዚአብሔርን የሞገስ ዓመት ዐውጅ ዘንድ ልኮኛል፡፡” የሚለውን ስፍራ አገኘ፡፡
\s5
\v 20 ከዚያ በኋላ የመጽሐፉን ጥቅልል ዘጋና ለምኩራቡ አገልጋይ ሰጥቶ ተቀመጠ፡፡
\v 21 “እናንተ እየሰማችሁ ይህ የእግዚአብሔር ቃል ተፈጸመ፡፡” እያለ ሊነግራቸው ጀመረ፡፡
\v 22 በዚያ የነበሩ ሰዎች ሁሉ የተናገረውን አስተዋሉ፣ ከአንደበቱም በሚወጣው የጸጋ ቃል ሁሉም ተገረሙ፡፡ እነርሱም፣ “ይህ የዮሴፍ ልጅ ነው፣ አይደለም እንዴ?” ይሉ ነበር፡
\s5
\v 23 ኢየሱስም፣ “በእርግጥ ‘ሐኪም ሆይ፣ ራስህን አድን፤ በቅፍርናሆም እንደምታደርግ የሰማነውን በዚህም በትውልድ ከተማህ አድርግ’ የሚለውን ይህንን ምሳሌ ትመስሉብኛላችሁ፡፡”
\v 24 ደግሞም እንደዚህ አላቸው፣ “እውነት እላችኋለሁ፣ ማንኛውም ነቢይ በገዛ አገሩ ተቀባይነት የለውም፡፡
\s5
\v 25 ነገር ግን እኔ እውነት እላችኋለሁ፣ ለሦስት ዓመታት ተኩል ሰማይ ተዘግቶ ዝናብ ባልነበረበትና በምድሪቱም ሁሉ ረሃብ በነበረበት በኤልያስ ዘመን በእስራኤል ብዙ መበለቶች ነበሩ፡፡
\v 26 ነገር ግን ኤልያስ በሲዶና አጠገብ በሰራፕታ ትኖር ወደነበረችው መበለት ብቻ እንጂ ከእነርሱ ወደ አንዲቱም አልተላከም፡፡
\v 27 በነቢዩ በኤልሳዕ ዘመንም በእስራኤል ብዙ ለምጻሞች ነበሩ፣ ነገር ግን ከሶርያዊው ከንዕማን በቀር ከእነርሱ አንዳቸውም አልተፈወሱም፡፡”
\s5
\v 28 በምኩራብ የነበሩት ሰዎች ሁሉ እነዚህን ነገሮች በሰሙ ጊዜ በቁጣ ተሞሉ፡፡
\v 29 ተነሥተው ከከተማይቱ እንዲወጣ አስገደዱት፣ ከገደል ጫፍም ገፍትረው ይጥሉት ዘንድ ከተማይቱ ወደ ተመሠረተችበት ወደ ኮረብታው ጫፍ ገፍተው ወሰዱት።
\v 30 ነገር ግን በመካከላቸው አልፎ ጉዞውን ቀጠለ፡፡
\s5
\v 31 ከዚያ በኋላም በገሊላ ወደምትገኝ ወደ ቅፍርናሆም ከተማ ሄደ፡፡
\v 32 በሥልጣን ይናገር ስለነበረ፣ በትምህርቱ ተገረሙ፡፡
\s5
\v 33 በዚያን ቀን በምኩራብ ውስጥ ርኩስ መንፈስ የነበረበት ሰው ነበረ፤ እርሱም በታላቅ ድምፅ ጮኸ፡፡
\v 34 “የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፣ ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደሆንክ አውቄሃለሁ፣ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱስ ነህ፡፡”
\s5
\v 35 ኢየሱስም ጋኔኑን፣ “ፀጥ ብለህ ከእርሱ ውጣ!” ብሎ ገሠጸው፡፡ ጋኔኑ በሰዎቹ መካከል በጣለው ጊዜ፣ ምንም ጉዳት ሳያደርስበት ከእርሱ ወጣ፡፡
\v 36 ሰዎች ሁሉ በጣም ተደነቁ፣ እርስ በርሳቸውም ስለሆነው ነገር መነጋገር ቀጠሉ፡፡ እነርሱም፣ “እነዚህ እንዴት ያሉ ቃላት ናቸው? ርኩሳን መናፍስትን በሥልጣንና በኃይል ያዛቸዋል፣ እነርሱም ይወጣሉ፡፡”
\v 37 የእርሱም ዝና በአካባቢው ባሉት አውራጃዎች በማንኛውም ስፍራ ወጣ፡፡
\s5
\v 38 ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ከምኩራብ ወጥቶ ወደ ስምዖን ቤት ገባ፡፡ በዚያን ጊዜ የስምዖን አማት በከፍተኛ ትኩሳት ታማ ነበር፣ እነርሱም ስለ እርሷ ተማፀኑት፡፡
\v 39 ስለዚህ በአጠገብዋ ቆሞ ትኩሳቱን ገሠጸው፣ ትኩሳቱም ቆመ፡፡ ወዲያውኑም ተነሥታ ልታገለግላቸው ጀመረች፡፡
\s5
\v 40 ፀሐይም በጠለቀች ጊዜ ሰዎች በተለያዩ ደዌዎች የተያዙትን በሽተኞች ወደ እርሱ አመጡ፡፡ እርሱም እጆቹን በእያንዳንዳቸው ላይ ጭኖ ፈወሳቸው፡፡
\v 41 አጋንንትም፣ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ” እያሉ በመጮኽ ከብዙዎች ወጡ፡፡ ኢየሱስ አጋንንትን ገሠጻቸው፣ እንዲናገሩም አልፈቀደላቸውም፣ ምክንያቱም እርሱ ክርስቶስ መሆኑን አውቀው ነበርና፡፡
\s5
\v 42 ንጋትም በሆነ ጊዜ ወደ ገለልተኛ ስፍራ ሄደ፡፡ ብዙ የሕዝብ አጀብ እየፈለጉት ነበርና፣ እርሱ ወደነበረበት ስፍራ መጡ፡፡ እነርሱንም ትቷቸው እንዳይሄድ ሊያስቀሩት ሞከሩ፡፡
\v 43 እርሱ ግን እንደዚህ አላቸው፣ “የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች ለብዙ ከተሞች መስበክ ይገባኛል፣ ምክንያቱም ወደዚህ የተላክሁት ለዚህ ነው፡፡”
\v 44 ከዚያ በኋላ በመላው ይሁዳ ባሉት ምኩራቦች መስበኩን ቀጠለ፡፡
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 ሕዝቡ ከበውት የእግዚአብሔርን ቃል እያዳመጡ ሳሉ፣ ኢየሱስ በጌንሳሬጥ ሐይቅ ዳር ቆሞ ነበር፡፡
\v 2 ሁለት ጀልባዎች በሐይቁ ጥግ በኩል ሲጎተቱ ተመለከተ፡፡ ዓሣ አጥማጆቹ ከጀልባዎቹ ወርደው መረቦቻቸውን እያጠቡ ነበር፡፡
\v 3 ኢየሱስ የስምዖን ወደ ነበረችው ከጀልባዎቹ ወደ አንዲቱ ገባና ከምድር ጥቂት ፈቀቅ አድርጎ ወደ ውሃ ውስጥ እንዲያስገባት ጠየቀው፡፡ ከዚያ በኋላም በጀልባዋ ውስጥ ተቀምጦ ሕዝቡን ማስተማር ጀመረ፡፡
\s5
\v 4 ንግግሩንም በጨረሰ ጊዜ ለስምዖን፣ “ጀልባይቱን ወደ ጥልቁ ውሃ ፈቀቅ አድርጋትና ዓሣ ለማጥመድ መረቦቻችሁን ጣሉ፡፡” አለው፡፡
\v 5 ስምዖንም፣ “ጌታ ሆይ፣ ሌሊቱን ሁሉ ስንሠራ አደርን ምንም አላጠመድንም፣ ነገር ግን በቃልህ መረቡን እጥላለሁ፡፡” ብሎ መለሰለት፡፡
\v 6 ይህንን ባደረጉ ጊዜ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ፣ መረቦቻቸውም ሊቀደዱ ደረሱ፡፡
\v 7 ስለዚህ እንዲመጡና እንዲረዷቸው በሌላ ጀልባ የነበሩትን ጓደኞቻቸውን በጥቅሻ ጠሩ፡፡ እነርሱም መጥተው ሁለቱንም ጀልባዎች እስኪሰጥሙ ድረስ ሞሉአቸው፡፡
\s5
\v 8 ስምዖን ጴጥሮስ ግን ይህንን በተመለከተ ጊዜ በኢየሱስ ጉልበት ሥር ዝቅ ብሎ በመንበርከክ፣ “ጌታ ሆይ፣ እኔ ኃጢአተኛ ሰው ነኝና ከእኔ ተለይ” አለው፡፡
\v 9 እንደዚህም ያለው ስላጠመዷቸው ዓሣዎች እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሁሉ ተደንቀው ስለነበረ ነው፡፡
\v 10 በዚያም ከነበሩት መካከል የዘብዴዎስ ልጆች ዮሐንስና ያዕቆብ አብረውት ነበሩ፡፡ ኢየሱስም ለስምዖን፣ “ከእንግዲህ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህና፣ አትፍራ፡፡” አለው፡፡
\v 11 ጀልባቸውን ወደ ምድር ባመጧት ጊዜ ሁሉንም ትተው ተከተሉት፡፡
\s5
\v 12 ከከተማዎቹ በአንዲቱ በነበረ ጊዜ፣ መላ ሰውነቱ በለምጽ የተመታ ሰው በዚያ ነበረ፡፡ ኢየሱስንም ባየ ጊዜ በፊቱ ወድቆ፣ “ብትፈቅድስ፣ ልታነጻኝ ትችላለህ፡፡” ብሎ ለመነው፡፡
\v 13 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና፣ “እፈቅዳለሁ፣ ንጻ” አለው፡፡ ወዲያውኑም ለምጹ ከእርሱ ተወገደ፡፡
\s5
\v 14 ለማንም እንዳይነግር አስጠነቀቀው፣ ነገር ግን፣ “ሂድና ራስህን ለካህን አሳይ፣ ሙሴ ባዘዘውም መሠረት ለእነርሱ ምስክር ይሆን ዘንድ ለመንጻትህ መሥዋዕት አቅርብ፡፡” አለው፡
\s5
\v 15 ነገር ግን ስለ እርሱ ያለው ዝና ከዚያም ርቆ ወጣ፤ ብዙም የሕዝብ አጀብ ሲያስተምር ለመስማትና ከሕመሞቻቸው ለመፈወስ በአንድነት ወደ እርሱ መጡ፡፡
\v 16 እርሱ ግን ወደ ገለልተኛ ስፍራዎች ሄዶ በዚያ ይጸልይ ነበር፡፡
\s5
\v 17 ያስተምር ከነበረባቸውም ከእነዚያ በአንዱ ቀን ከገሊላና ከይሁዳ መንደሮችና አውራጃዎች እንዲሁም ከኢየሩሳሌም ከተማ መጥተው በዚያ የተቀመጡ ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራን ነበሩ፡፡ ይፈውስም ዘንድ የእግዚአብሔር ኃይል በእርሱ ላይ ነበረ፡፡
\s5
\v 18 በዚያን ጊዜ ጥቂት ሰዎች ሰውነቱ የደነዘዘ ሰው በቃሬዛ ይዘው መጡ፤ በኢየሱስ ፊትም ያደርጉት ዘንድ ወደ ውስጥ የሚያስገቡበትን መንገድ ይፈልጉ ነበር፡፡
\v 19 ከሕዝቡም ብዛት የተነሣ ሊያስገቡ የሚችሉበትን መንገድ አላገኙም፤ ስለዚህ ወደ ቤቱ ጣሪያ ላይ ወጥተው፣ ሰውዬውን በቃሬዛው ላይ እንዳለ በጣሪያው አሳልፈው በሰዎቹ መካከል ከኢየሱስ ፊት አወረዱት፡፡
\s5
\v 20 ኢየሱስ እምነታቸውን ተመልክቶ፣ “አንተ ሰው፣ ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል” አለው፡፡
\v 21 ፈሪሳውያንና ጸሐፍት፣ “የስድብ ቃል የሚናገር ይህ ማን ነው? እግዚአብሔር ብቻ ካልሆነ በስተቀር፣ ኃጢአትን ይቅር ማለት የሚችል ማን ነው?” በማለት መጠየቅ ጀመሩ፡፡
\s5
\v 22 ነገር ግን ኢየሱስ ምን እንዳሰቡ አውቆ፣ “በልባችሁ ይህንን ለምን ትጠይቃላችሁ?
\v 23 የትኛውን ማለት ይቀላል፡- ‘ኃጢአትህ ተሰረየችልህ’ ማለት ወይስ ‘ተነሣና ሂድ’ ማለት?
\v 24 ነገር ግን ለሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ይቅር ለማለት ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፣ ለአንተ፣ ‘ተነሣና ቃሬዛህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ’ ብዬ እናገራለሁ፡፡"
\s5
\v 25 ከዚያ በኋላ በእነርሱ ፊት ተነሣ፣ ተኝቶበት የነበረውንም ቃሬዛ ተሸክሞ እግዚአብሔርን እያከበረ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡
\v 26 ሰዎች ሁሉ ተገረሙ፣ እግዚአብሔርንም አከበሩ፡፡ “በዛሬው ዕለት ያልተለመደ ነገር አየን” እያሉ በፍርሃት ተሞሉ፡፡
\s5
\v 27 እነዚህ ነገሮች ከሆኑ በኋላ፣ ኢየሱስ ከዚያ ወጥቶ በቀረጥ መሰብሰቢያው ስፍራ ተቀምጦ የነበረውን ሌዊ የተባለውን ቀረጥ ሰብሳቢ ተመለከተ፡፡ እርሱንም፣ “ተከተለኝ” አለው፡፡
\v 28 ስለዚህ ሌዊ ሁሉንም ትቶ ተነሥቶ ተከተለው፡፡
\s5
\v 29 ከዚያ በኋላ፣ ሌዊ በቤቱ ለኢየሱስ ታላቅ ግብዣ አደረገለት፣ በዚያም ብዙ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና በማዕድ ቀርበው ከእነርሱ ጋር የሚመገቡ ሌሎች ሰዎችም ነበሩ፡፡
\v 30 ነገር ግን ፈሪሳውያንና ጻሐፍት በደቀመዛሙርቱ ላይ፣ “ከቀረጥ ሰብሳቢዎችና ከሌሎች ኃጢአተኛ ሰዎች ጋር ለምን ትበላላችሁ ትጠጣላችሁም?” እያሉ ያጉረመርሙባቸው ነበር፡፡
\v 31 ኢየሱስም እንደዚህ በማለት መለሰላቸው፣ “በመልካም ጤንነት ላይ ያሉ ሐኪም አያስፈልጋቸውም፣ ሐኪም የሚያስፈልጋቸው የታመሙ ብቻ ናቸው፡፡
\v 32 እኔ የመጣሁት ጻድቃንን ለንስሐ ለመጥራት ሳይሆን ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ ለመጥራት ነው፡፡”
\s5
\v 33 እነርሱም ፣ “የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ይጾማሉ ይጸልያሉም፣ የፈሪሳውያን ደቀመዛሙርትም እንደዚሁ ያደርጋሉ፡፡ የአንተ ደቀመዛሙርት ግን ይበላሉ፣ ይጠጣሉም፡፡” አሉት፡፡
\v 34 ኢየሱስም ፣ “ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሚዜዎቹን እንዲጾሙ ሊያደርጋቸው የሚችል አለን?
\v 35 ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወቅት ይመጣል በእነዚያ ቀናት ይጾማሉ፡፡”
\s5
\v 36 ከዚያ በኋላ ኢየሱስ በምሳሌ ተናገራቸው፣ “ማንም ሰው ከአዲስ ልብስ ላይ እራፊ ቀዶ አሮጌ ልብስ አይጥፍም፡፡ እንደዚህ የሚያደርግ ከሆነ፣ ከአዲሱ ልብስ ላይ እራፊ ይቀዳል፣ ነገር ግን ከአዲሱ ልብስ ላይ የተቀደደው እራፊ ከአሮጌው ልብስ ጋር አብሮ አይሄድም፡፡
\s5
\v 37 እንደዚሁም፣ ማንም ሰው በአሮጌው አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ አያስቀምጥም፡፡ እንደዚህ ቢያደርግ፣ አዲሱ ወይን ጠጅ አቁማዳውን ያፈነዳዋል፣ ወይን ጠጁም ይፈሳል፣ አቁማዳውም ይበላሻል፡፡
\v 38 ነገር ግን አዲስ ወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ይቀመጣል፡፡
\v 39 ማንም ሰው አሮጌውን ወይን ጠጅ ከጠጣ በኋላ አዲሱን የወይን ጠጅ አይፈልግም፣ ‘አሮጌው ይሻላል’ ይላልና፡፡”
\s5
\c 6
\cl ምዕራፍ 6
\p
\v 1 በሰንበት ቀን በእህል እርሻ መካከል በሚያልፍበት ጊዜ ደቀመዛሙርቱ እሸት እየቀጠፉና በእጆቻቸው እያሹ እህሉን ይቅሙ ነበር፡፡
\v 2 ገር ግን ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ፣ “በሰንበት ቀን ማድረግ ያልተፈቀደውን የምታደርጉት ለምንድን ነው?” አሏቸው፡፡
\s5
\v 3 ኢየሱስም ለእነርሱ፣ “ዳዊት በተራበ ጊዜ እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ያደረጉትን እንኳ አላነበባችሁምን?
\v 4 ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ ከተቀደሰው ኅብስት ጥቂት ወሰደ፤ ካህናትም ብቻ ይበሉ ዘንድ የተፈቀደላቸውን ለራሱ በላ። አብረውት ከነበሩትም ለአንዳንዶቸ ይበሉ ዘንድ ሰጣቸው” አላቸው፡፡
\v 5 ከዚያ በኋላም፣ “የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነው” አላቸው፡፡
\s5
\v 6 በሌላም ሰንበት ቀን ወደ ምኩራብ ገብቶ በዚያ የነበሩትን ሰዎች አስተማራቸው፡፡ በዚያም የቀኝ እጁ የሰለለች አንድ ሰው ነበረ፡፡
\v 7 አንድ የተሳሳተ ነገር ሲያደርግ ተመልክተው ለመክሰስ ምክንያት ያገኙ ዘንድ በሰንበት ቀን አንድን ሰው ይፈውስ እንደሆነ ፈሪሳውያንና ጸሐፍት በትኩረት ይመለከቱት ነበር፡፡
\v 8 እርሱ ግን ምን እንደሚያስቡ አውቆ፣ እጁ የሰለለችበትን ሰውዬ፣ “ተነሣና በሰዎች ሁሉ መካከል ቁም” አለው፡፡ ስለዚህም ሰውዬው ተነሣና በዚያ ስፍራ ቆመ፡፡
\s5
\v 9 ኢየሱስም፣ “ እኔም እናንተን እጠይቃችኋለሁ፡- በሰንበት ሕጋዊ የሚሆነው መልካም ማድረግ ነው ክፉ፣ ሕይወት ማድን ነው ወይስ ማጥፋት?”
\v 10 ከዚያም ዞር ብሎ ሁሉንም ተመለከታቸውና ለሰውዬው፣ “እጅህን ዘርጋ” አለው፤ ዘረጋውም፣ እጁም ዳነለት፡፡
\v 11 ከዚያ በኋላም በቁጣ ተሞልተው፣ በኢየሱስ ላይ ምን እንደሚያደርጉበት እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ፡፡
\s5
\v 12 በዚያም ወቅት ኢየሱስ ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ፣ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር መጸለዩን ቀጠለ፡፡
\v 13 በነጋም ጊዜ ደቀመዛሙርቱን ወደ እርሱ ጠራ፣ ከእነርሱም ‘ሐዋርያት’ ብሎ የሰየማቸውን አሥራ ሁለቱን መረጠ፡፡
\s5
\v 14 የሐዋርያቱም ስም፣ ስምዖን (ጴጥሮስ ብሎ የሰየመው) ወንድሙ እንድርያስ፣ ያዕቆብ፣ ዮሐንስ፣ ፊልጶስ፣ በርተሎሚዎስ፣
\v 15 ማቴዎስ፣ ቶማስ፣ ያዕቆብ የእልፍዮስ ልጅ፣ ቀናተኛ የተባለው ስምዖን፣
\v 16 የያዕቆብ ልጅ ይሁዳና ከዳተኛ የሆነው ይሁዳ አስቆሮቱ ናቸው፡፡
\s5
\v 17 ከዚያ በኋላም ኢየሱስ ከተራራው ወረደና በደልዳላ ቦታ ላይ ቆመ፡፡ ከደቀመዛሙርቱ በርከት ያሉት፣ ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም እንዲሁም ከጢሮስና ከሲዶና ባሕር ዳርቻ ብዙ ሰዎች በዚያ ነበሩ፡፡
\v 18 ወደዚያ የመጡት እርሱን ሊያዳምጡትና ከበሽታዎቻቸው ሊፈወሱ ነበር፡፡ በርኩሳን መናፍስት ሲጨነቁ የነበሩም ሰዎች ተፈወሱ፡፡
\v 19 የሚፈውስ ኃይል ከእርሱ ይወጣ ስለነበረ፣ በሕዝቡ መካከል ያለ እያንዳንዱ ሰው እርሱን ለመንካት ጥረት ያደርግ ነበር፤ እርሱም ሁሉንም ፈወሳቸ.
\s5
\v 20 ከዚያ በኋላም ወደ ደቀመዛሙርቱ ተመለከተና፣ እንደዚህ አላቸው፣ “የእግዚአብሔር መንግሥት ለእናንተ ናትና፣ እናንተ ድሆች የተባረካችሁ ናችሁ፡፡
\v 21 አሁን የምትራቡ የተባረካችሁ ናችሁ፣ ትጠግባላችሁና፡፡ አሁን የምታለቅሱ የተባረካችሁ ናችሁ፣ ትስቃላችሁና፡፡
\s5
\v 22 ሰዎች በሚጠሏችሁና በሚያገሏችሁ ጊዜ እንደዚሁም በሰው ልጅ ምክንያት ስማችሁን በክፉ ሲያነሱ የተባረካችሁ ናችሁ፡፡
\v 23 አባቶቻቸው ነቢያትን እንደዚሁ አድርገውባቸው ነበርና ፣ በዚያን ቀን ሐሴት አድርጉ፣ በደስታም ዝለሉ፣ ምክንያቱም በሰማይ በእርግጥ ታላቅ ብድራት ይኖራችኋል፡፡
\s5
\v 24 እናንተ አሁኑኑ መጽናናትን ተቀብላችኋልና፣ ነገር ግን እናንተ ባለጠጎች ወዮላችሁ!
\v 25 በኋላ ትራባላችሁና፣ እናንተ አሁን የጠገባችሁ ወዮላችሁ! በኋላ ስለምታለቅሱና ዋይ፣ ዋይ ስለምትሉ፣ እናንተ አሁን የምትስቁ ወዮላችሁ!
\s5
\v 26 ሰዎች ሁሉ ስለ እናንተ መልካም በሚናገሩላችሁ ጊዜ ወዮላችሁ! ምክንያቱም አባቶቻቸው ለሐሰተኛ ነቢያት እንደዚያ ያደርጉላቸው ነበርና፡፡
\s5
\v 27 ለእናንተ ለምታደምጡ ግን እላችኋለሁ፣ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፣ ለሚጠሏችሁም መልካም አድርጉላቸው፡፡
\v 28 የሚረግሟችሁን መርቁ፣ ለሚያንገላቷችሁም ጸልዩላቸው።
\s5
\v 29 አንድ ጉንጭህን ለሚመታህ ሌላውንም ጉንጭህን አዙርለት፡፡ አንድ ሰው ነጠላህን የሚወስድብህ ከሆነ፣ እጀ ጠባብህን አትከልክለው፡፡
\v 30 ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፣ አንድ ሰው የአንተ የሆነውን የሚወስድብህ ከሆነ፣ እንዲመልስልህ አትጠይቀው፡፡
\s5
\v 31 ሰዎች እንዲያደርጉልህ የምትፈልገውን ሁሉ አንተም ለእነርሱ ልታደርግላቸው ይገባሃል፡፡
\v 32 ኃጢአተኞችም እንኳን የሚወዷቸውን ይወዳሉና የሚወዷችሁን የምትወዱ ከሆነ፣ ምን ምስጋና ትቀበላላችሁ?
\v 33 ኃጢአተኞችም እንደዚያው ያደርጋሉና መልካም ለሚያደርጉላችሁ ብቻ መልካም የምታደርጉ ከሆናችሁ፣ ምን ምስጋና ትቀበላላችሁ?
\v 34 እንደሚመልሱላችሁ ለምትጠብቋቸው ብቻ የምታበድሩ ከሆናችሁ፣ ምን ምስጋና አላችሁ? የሰጡትን ያንኑ ያህል ለመቀበል ተስፋ አድርገው፣ ኃጢአተኞችም እንኳን ለኃጢአተኞች ያበድራሉ፡፡
\s5
\v 35 ነገር ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፣ መልካምም አድርጉላቸው፤ ምንም ነገር ስለመቀበል ሳትጨነቁ አበድሯቸው፣ ዋጋችሁም ታላቅ ይሆናል፡፡ እርሱ ራሱ ለማያመሰግኑና ለክፉ ሰዎች ቸር ነውና፣ እናንተም የልዑል ልጆች ትባላላችሁ፡፡
\v 36 አባታችሁ መሐሪ እንደሆነ ሁሉ እናንተም መሐሪዎች ሁኑ፡፡
\s5
\v 37 አትፍረዱ አይፈርድባችሁም፤ አትኮንኑ አትኮነኑምም፤ ሌሎችን ይቅር በሉ፣ እናንተም ይቅር ትባላላችሁ፡፡
\s5
\v 38 ለሌሎች ስጡ፣ ለእናንተም የተጠቀጠቀ፣ የተነቀነቀ፣ በእቅፎቻችሁም ተርፎ የሚፈስ መልካም መስፈሪያ ተሰፍሮ ይሰጣችኋል፡፡ ለሌሎች ለመስፈር በምትጠቀሙበት በዚያው መስፈሪያ ለእናንተም ይሰፈርላችኋል፡፡"
\s5
\v 39 ከዚያም ይህን ምሳሌ ነገራቸው፣ በኋላም፣ “አንድ ዕውር ሌላውን ዕውር ሊመራው ይችላልን? እንደዚያ ቢያደርግ፣ ሁለቱም ጉድጓድ ውስጥ ይገቡ የለምን?
\v 40 ደቀመዝሙር ከመምህሩ አይበልጥም፤ ነገር ግን አንድ ሰው ፈጽሞ ከተማረ እንደ መምህሩ ይሆናል፡፡
\s5
\v 41 በወንድምህ ዓይን ያለውን ትንሽ ጉድፍ ለምን ትመለከታለህ? ለምንስ በራስህ ዓይን ያለውን ግንድ አትመለከትም? በራስህ ዓይን ውስጥ ያለውን ግንድ ሳትመለከት፣
\v 42 ለወንድምህ፣ ‘ወንድሜ ሆይ፣ ዓይንህ ውስጥ ያለውን ጉድፍ ላውጣልህ’ እንዴት ትለዋለህ? አንተ ግብዝ! በመጀመሪያ በዓይንህ ውስጥ ያለውን ግንድ አውጣ፣ ከዘያም በወንድምህ ዓይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ለማውጣት አጥርተህ ታያለህ፡፡
\s5
\v 43 የተበላሸ ፍሬ የሚያፈራ መልካም ዛፍ የለምና፣ መልካም ፍሬም የሚያፈራ የተበላሸ ዛፍ የለም፡፡
\v 44 እያንዳንዱ ዛፍ የሚታወቀው በሚያፈራው ፍሬ ነውና፤ ከእሾህ የበለስ ፍሬ አይለቀምም፣ ከቀጋ ቁጥቋጦም የወይን ፍሬ አይቆረጥም፡፡
\s5
\v 45 መልካሙ ሰው በልቡ ካከማቸው መልካም ሀብት መልካም የሆነውን ነገር ያወጣል፤ ክፉም ሰው በልቡ ካከማቸው ክፉ ክምችት ክፉ የሆነውን ያወጣል፡፡ በልቡ ሞልቶ ከተረፈው በአፉ ይናገራልና፡፡
\s5
\v 46 ለምንስ ‘ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ’ ትሉኛላችሁ? ለምናገራቸውስ ነገሮች ለምን አትታዘዙም?
\v 47 ወደ እኔ የሚመጣና ለቃሌ የሚታዘዝ ምን እንደሚመስል እነግራችኋለሁ እነግራችኋለሁ፣
\v 48 መሬቱን በጥልቁ ከቆፈረ በኋላ መሠረቱን በዓለት ላይ በማድረግ ቤቱን እንደሚገነባ ሰው ነው፡፡ ጎርፍ በመጣ ጊዜ የውሃው ሙላት ያን ቤት ገፋው፣ ሆኖም በሚገባ ተገንብቶ ነበርና አልነቀነቀውም፡፡
\s5
\v 49 ነገር ግን ቃሌን ሰምቶ የማይታዘዘው ሰው ቤቱን ያለ መሠረት በመሬቱ አፈር ላይ እንደ ሠራው ሰው ነው፤ ጎርፉ በመጣ ጊዜ ቤቱን መታው፣ ወዲያውኑም ፈረሰ፣ ውድም ብሎም ጠፋ፡፡”
\s5
\c 7
\cl ምዕራፍ 7
\p
\v 1 ኢየሱስ ለሕዝቡ የሚናገረውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ፣ ወደ ቅፍርናሆም ገባ።
\s5
\v 2 እጅግ የሚወደውና ሞት አፋፍ ላይ የደረሰ አገልጋይ የነበረው አንድ የመቶ አለቃ ነበረ።
\v 3 ስለ ኢየሱስ በሰማ ጊዜ መጥቶ አገልጋዩን ከመሞት እንዲያድንለት እንዲለምኑት የአይሁድ ሽማግሌዎችን ወደ እርሱ ላካቸው።
\v 4 እነርሱ ወደ ኢየሱስ በቀረቡ ጊዜ፣ "ለእርሱ ይህን ልታደርግለት የተገባ ነው፣
\v 5 ምክንያቱም ሕዝባችንን ይወዳል፣ ምኩራብ የሠራልንም እርሱ ነው" በማለት አጥብቀው ለመኑት።
\s5
\v 6 ስለዚህ ኢየሱስ ዐብሮአቸው መንገዱን ቀጠለ። ነገር ግን ወደ ቤቱ ለመድረስ ጥቂት በቀረው ጊዜ፣ የመቶ አለቃው፣ እንዲህ ብለው እንዲነግሩት ወዳጆቹን ወደ ኢየሱስ ላካቸው፤ “ጌታ ሆይ፣ አትድከም፣ ምክንያቱም አንተ ወደ ቤቴ ልትገባ የተገባሁ አይደለሁም፤
\v 7 ከዚህ የተነሣ እኔም ራሴ ወደ አንተ ለመምጣት የምገባ አድርጌ እንኳ ራሴን አልቈጥረውም። ነገር ግን ቃል ብቻ ተናገር አገልጋዬ ይፈወሳል፤
\v 8 እኔም ደግሞ ባለ ሥልጣን ነኝና፤ በእኔ ሥር ወታደሮች አሉኝ፤ አንዱን 'ሂድ' ስለው ይሄዳል፤ ሌላውን 'ና' ስለው ይመጣል።
\s5
\v 9 ኢየሱስ ይህን በሰማ ጊዜ፣ በመቶ አለቃው ተደንቀ፣ ይከተሉት ወደነበሩት ሰዎችም ዞር ብሎ፣ “በእስራኤልም እንኳ እንዲህ ያለ እምነት ያለው ሰው አላገኘሁም” አላቸው።
\v 10 ከዚያም የተላኩት ሰዎች ወደ መቶ አለቃው ቤት ተመልሰው፣ አገልጋዩን ጤናማ ሆኖ አገኙት።
\s5
\v 11 ከጥቂት ጊዜ በኋላ ኢየሱስ ናይን ወደ ምትባል ከተማ እየተጓዘ ነበር። ከእርሱም ጋር ደቀ መዛሙርቱና ብዙ ሕዝብ ዐብረውት ይሄዱ ነበር።
\v 12 ወደ ከተማይቱም በቀረበ ጊዜ፣ እነሆ፣ ለእናቱ ብቸኛ ልጅ የነበረ ሰው ሞቶ አስከሬኑን ሰዎች ተሸክመው እየሄዱ ነበር። የልጁ እናት መበለት ነበረች፤ በርከት ያሉ ለቀስተኞችም ተከትለዋት ነበር።
\v 13 ጌታም ተመልክቷት እጅግ ዐዘነላትና፣ “አታልቅሺ” አላት።
\v 14 ከዚያም ወደ ቃሬዛው ተጠግቶ ነካው ቃሬዛውን የተሸከሙትም ቆሙ። ኢየሱስ፣ “አንተ ወጣት ተነሥ እልሃለሁ” አለ።
\v 15 ወጣቱም ተነሥቶ መናገር ጀመረ፤ ከዚያም ኢየሱስ ልጁን ለእናትዮዋ ሰጣት።
\s5
\v 16 ከዚያም ሁሉንም ፍርሀት ያዛቸው። “ታላቅ ነቢይ በመካከላችን ተነሥቶአል" "ደግሞ እግዚአብሔር ሕዝቡን ጎበኝቶአል” በማለት እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
\v 17 ይህ የኢየሱስ ዝና በመላው ይሁዳና በዙሪያው ባለው አገር ሁሉ ተሰማ።
\s5
\v 18 የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ አወሩለት።
\v 19 ከዚያም ዮሐንስ፣ “የምትመጣው አንተ ነህን ወይስ ሌላ እንጠብቅ?” ብለው እንዲጠይቁት ከእነርሱ ሁለቱን ወደ ኢየሱስ ላካቸው።
\v 20 ሰዎቹም ወደ ኢየሱስ ቀርበው፣ "'የምትመጣው አንተ ነህን ወይስ ሌ እንጠብቅ?' ብለን እንድንጠይቅህ መጥምቁ ዮሐንስ ልኮናል" አሉ።
\s5
\v 21 በዚያኑ ሰዓት ኢየሱስ ብዙ ሰዎችን ከተለያየ ደዌና በሽታ ፈወሰ። በአጋንንት የተያዙትን ነጻ አወጣ፣ ዐይነ ስውራንም ማየት እንዲችሉ አደረገ።
\v 22 ኢየሱስ መልእክተኞቹን፣ “ወደ ዮሐንስ ተመልሳችሁ ሂዱና ያያችሁትንና የሰማችሁትን እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፣ ዐይነ ስውራን ያያሉ፣ ሽባዎች ይራመዳሉ፣ ለምጻሞች ይነጻሉ፣ መስማት የተሳናቸው ይሰማሉ፣ ሙታን ይነሣሉ፣ ለድኾችም ወንጌል እየተሰበከ ነው።
\v 23 በማደርጋቸው ነገሮች በእኔ ሳይሰናከል በእምነቱ የሚጸና ሰው የተመሰገነ ነው” አላቸው።
\s5
\v 24 የዮሐንስ መልእክተኞች ከሄዱ በኋላ ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ ለሕዝቡ እንዲህ ይላቸው ጀመር፣ “ምን ልታዩ ወደ በረሐ ወጣችሁ በነፋስ የሚወዛወዘውን ሸንበቆ ለማየት ነውን?
\v 25 ወይስ የወጣችሁት የሚያማምሩ ልብሶች የለበሱትን ለማየት ነውን? እነሆ፣ የሚያማምሩ ልብሶችን ለብሰው በድሎት የሚኖሩ ሰዎች የሚገኙት በአብያተ መንግሥታት ነው።
\v 26 ልታዩ የወጣችሁት ግን ነቢይን ከሆነ፣ እንግዲያውስ ያያችሁት ነቢይን ብቻ ሳይሆን ከነቢያትም የበለጠውን ነው።
\s5
\v 27 ስለ እርሱ፣ ‘እነሆ፣ በፊታችሁ መንገድን የሚጠርግ መልእክተኛዬን እልካለሁ’ ተብሎ ተጽፏል።
\v 28 እላችኋለሁ፣ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም፤ ቢሆንም በእግዚአብሔር መንግሥት ከሁሉም የሚያንሰው ይበልጠዋል።
\s5
\v 29 ይህን በሰሙ ጊዜ ቀራጮች እንኳ ሳይቀሩ ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔር ጻድቅ እንደ ሆነ ተናገሩ፤ ምክንያቱም እነርሱን ያጠመቃቸው ዮሐንስ ነበር።
\v 30 በዮሐንስ ያልተጠመቁት ፈሪሳውያንና የአይሁድ የሕግ ዐዋቂዎች ግን በራሳቸው ፈቃድ የእግዚአብሔርን ጥበብ ተቃወሙ።
\s5
\v 31 እንግዲያውስ የዚህን ትውልድ ሰዎች ከምን ጋር አመሳስላቸዋለሁ? ምንስ ይመስላሉ?
\v 32 እርስ በርሳቸው በገበያ እየተጠራሩ፥ ‘እንቢልታ ነፋንላችሁ እናንተም አልዘፈናችሁም፣ ሙሾ አወጣንላችሁ እናንተም አላለቀሳችሁም’ እንደሚባባሉ ልጆች ናቸው።
\s5
\v 33 መጥምቁ ዮሐንስ እንጀራ ሳይበላና ወይን ጠጅ ሳይጠጣ ቢመጣ፣ ‘ጋኔን አለበት’ አላችሁት፣
\v 34 የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ ቢመጣ፦ ‘በላተኛና ጠጪ፣ የቀራጮችና የኃጢአተኞች ወዳጅ! አላችሁት።
\v 35 ጥበብ ግን በልጆቿ ሁሉ ትክክል እንደ ሆነች ታወቀች።
\s5
\v 36 አንድ ፈሪሳዊም በቤቱ ዐብሮት እንዲመገብ ኢየሱስን ጋበዘው ኢየሱስ ግብዣውን ተቀብሎ ወደ ማዕዱ ቀረበ።
\v 37 እነሆ፣ በዚያ ከተማ በመጥፎ ምግባሯ የታወቀች እንዲት ሴት ኢየሱስ በፈሪሳዊው ቤት ተጋብዞ በማዕድ እንደ ተቀመጠ ተረድታ የአልባስጥሮስ ሽቱ ብልቃጥ ይዛ ወደ ቤቱ ገባችና
\v 38 ከኢየሱስ በስተኋላ ከእግሩ አጠገብ ቆማ ማልቀስ ጀመረች። ከዚያም በእንባዋ እግሩን ማራስና በፀጉሯም ማበስ ቀጠለች፣ እግሩንም ትስመው በሽቱም ትቀባው ነበር።
\s5
\v 39 ኢየሱስን የጋበዘው ፈሪሳዊ ይህንን ባየ ጊዜ፣ "ይህ ሰው በእርግጥ ነቢይ ቢሆን ኖሮ እየነካችው ያለችው ሴት ምን ዓይነት ሴት እንደ ሆነች ባወቀም ነበር" ብሎ በልቡ ዐሰበ።
\v 40 ኢየሱስም መልሶ ፈሪሳዊውን፣ “አንድ የምነግርህ ነገር አለኝ” አለው። ፈሪሳዊውም፣ “መምህር ሆይ፣ ተናገር” አለው።
\s5
\v 41 ኢየሱስ፣ “ከአንድ አበዳሪ ገንዘብ የተበደሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፣ አንደኛው የአምስት መቶ ዲናር ሌላኛው ደግሞ የሃምሳ ዲናር ዕዳ ነበረባቸው፤
\v 42 የሚከፍሉት ስላልነበራቸው ሁለቱንም ዕዳቸውን ማራቸው። ስለዚህ ዕዳቸው ከተማረላቸው ከእነዚህ ከሁለቱ ማንኛቸው አብዳሪውን የበለጠ የሚወደው ይመስልሃል? አለው።
\v 43 ስምዖንም መልሶ፣ “ብዙ የተተወለቱ ይመስለኛል” አለው። ኢየሱስ፣ “በትክክል መልሰሃል” አለው።
\s5
\v 44 ኢየሱስም ወደ ሴትዮይቱ ዞር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፣ “ይህችን ሴት ትመለከታታለህ? እኔ ወደ ቤትህ ገብቼ ለእግሬ ውሃ እንኳን አላቀረብህልኝም፣ እርሷ ግን በእንባዋ እግሬን አራሰች፣ በፀጉሯም አበሰችው፤
\v 45 አንተ አልሳምኸኝም፣ እርሷ ግን ከመጣሁበት ጊዜ ጀምሮ እግሬን ከመሳም አላቋረጠችም።
\s5
\v 46 አንተ ራሴን ዘይት አልቀባኸኝም፣ እርሷ ግን እግሬን ሽቱ ቀባች፣
\v 47 ስለዚህ ለበዛው ኃጢአቷ ብዙ ምሕረትን አግኝታለችና አብዝታ ወዳለች። ጥቂት ኃጢአቱ ይቅር የተባለለት ግን ጥቂት ይወዳል” አለው።
\s5
\v 48 ከዚያም ወደ ሴቱቱ ዞር ብሎ፣ “ኃጢአትሽ ተሰርዮልሻል” አላት።
\v 49 በዚያም ተቀምጠው የነበሩት እርስ በርሳቸው፣ “ኃጢአትን ይቅር የሚል ይህ ማን ነው?” አሉ።
\v 50 ከዚያም ኢየሱስ ሴቲቱን፣ “እምነትሽ አድኖሻል። በስላም ሂጂ” አላት።
\s5
\c 8
\cl ምዕራፍ 8
\p
\v 1 ከዚያ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች ወንጌል እየሰበከና እያወጀ ወደ ልዩ ልዩ ከተሞችና መደሮች መጓዝ ጀመረ። በጒዞውም ወቅት ዐሥራ ሁለቱ፣
\v 2 እንዲሁም ከርኩሳን መናፍስትና ከሕመማቸው የተፈወሱ አንዳንድ ሴቶች ዐብረውት ሄዱ፤ እነርሱም ሰባት አጋንንት የወጡላት መግደላዊት ማርያም፣
\v 3 እንደ የሄሮድስ ቤተ መንግሥት አዛዥ የነበረው የኩዛ ሚስት የነበረችው ዮሐና፣ ሶስና ሌሎችም ብዙ ሴቶች ነበሩ፤ እነዚህ ኢየሱስንና ደቀ መዛሙርቱን በገንዘባቸው ያገለግሉ ነበር።
\s5
\v 4 ከብዙ የተለያዩ ከተሞች የመጡትን ጨምሮ ብዙ ሕዝብ በተሰበሰቡ ጊዜ፣ በምሳሌ ተጠቅሞ እንዲህ ብሎ ነገራቸው፤
\v 5 “አንድ ዘሪ ዘሩን ሊዘራ ወጣ።እንደ ዘራም አንዳንዱ ዘር በመንገድ ዳር ወደቀና ተረገጠ፣ የሰማይ ወፎችም መጥተው በሉት።
\v 6 ሌላው ዘርም በጭንጫ መሬት ላይ ወደቀ፤ በበቀለም ጊዜ እርጥብ አፈር ስላልነበረው ወዲያው ደረቀ።
\s5
\v 7 ሌላውም ዘር በእሾህ መካከል ወደቀ እሾሁም ከዘሩ ጋር ዐብሮት አደገና አነቀው።
\v 8 ከዘሩ አንዳንዱ ግን በመልካም ዐፈር ላይ ወደቀ መቶ እጥፍ ፍሬም አፈራ።" ኢየሱስ ይህንን ከተናገረ በኋላ ጮኽ ብሎ፣ "ጆሮ ያለው ይስማ” አለ።
\s5
\v 9 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ይህ ምሳሌ ምን ማለት እንደ ሆነ ጠየቁት፤
\v 10 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ "ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር የማወቅ ዕድል ተሰጥቷችኋል፣ ለተቀሩት ሕዝብ ግን 'እያዩ ስለማያዩ፣ እየሰሙም ስለማያስተውሉ' የሚማሩት በምሳሌ ነው።
\s5
\v 11 ትርጕም እንደዚህ ነው፣ ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው።
\v 12 በመንገድ ዳር የወደቁት ሰምተው እንዳይድኑ ዲያብሎስ መጥቶ የሰሙትን ቃል ከልባቸው የሚወሰድባቸው ናቸው።
\v 13 በድንጋይ መካከል የወደቁትም ቃሉን በሰሙ ጊዜ በደስታ የሚቀበሉትና መስማት እንጂ፣ በቃሉ ሥር ስላልሰደዱ ለጊዜው አምነው ፈተና በመጣባቸው ጊዜ፣ እምነታቸውን የሚክዱ ናቸው።
\s5
\v 14 በእሾኽ መካከል የወደቀው ዘር ቃሉን የሰሙ ሰዎች ሲሆኑ፣ በኑሮ ሂደታቸው ወቅት በምድራዊ ሕይወት ዐሳብና በባለጠግነት ምቾት የሚታነቁ በመሆናቸው ፍሬ ወደ ማፍራት የማይመጡ ናቸው።
\v 15 ነገር ግን በመልካሙ ዐፈር ላይ የወደቁት በመልካምና በቅን ልብ ካደመጡ በኋላ ቃሉን አጥብቀው የሚይዙ በመጽናት ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።
\s5
\v 16 እንግዲህ፣ አንድ ሰው መብራት ካበራ በኋላ ጎድጓዳ ነገር ውስጥ ወይም ከአልጋ ሥር አያደርገውም። ከዚያ ይልቅ ሁሉም ሰው ብርሃኑን ማየት ይችል ዘንድ ከፍ ባለ ስፍራ ላይ ያስቀምጠዋል።
\v 17 ምክንያቱም የሚታወቅ እንጂ የሚደበቅ፣ ታውቆ ወደ ብርሃን የሚወጣ እንጂ ምሥጢር የሚሆን ነገር የለም።
\v 18 ስለዚህ እንዴት እንደምትሰሙ ተጠንቀቁ፣ ምክንያቱም ላለው ሁሉ የበለጠ ይሰጠዋል፣ ከሌለው ደግሞ እንዳለው የሚመስለው እንኳ ይወሰድበታል።"
\s5
\v 19 ከዚያም የኢየሱስ እናትና ወንድሞቹ ወደ እርሱ መጡ፣ ነገር ግን ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ወደ እርሱ መቅረብ አልቻሉም።
\v 20 ስለሆነም፣ ‘እናትህና ወንድሞችህ ሊያነጋግሩህ ፈልገው እየጠበቁህ ናቸው’ የሚል መልእክት አመጡለት።
\v 21 ነገር ግን ኢየሱስ መልሶ፣ “እናቴና ወንድሞቼ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚያደርጉት ናቸው” አላቸው።
\s5
\v 22 ከዕለታት አንድ ቀን ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ በጀልባ ሲሳፈሩ ኢየሱስ፣ "ሐይቁ ማዶ እንሻገር" አላቸው። ከዚያም እነርሱ መቅዘፍ ጀመሩ።
\v 23 ነገር ግን እየቀዘፉ ሳሉ ኢየሱስ እንቅልፍ ወሰደውና በታላቅ ነፋስ የታጀበ ማዕበል በሐይቁ ላይ ስለተነሣ ጀልባቸው ውስጥ ውሃ መግባት ጀመረ'፤ታላቅ አደጋም በፊታቸው ተደቀነ።
\s5
\v 24 ከዚያም የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ መጥተው፣ "መምህር ሆይ፣ መምህር ሆይ፣ መሞታችን ነው" በማለት ቀሰቀሱት። እርሱም ከእንቅልፉ ነቅቶ ነፋሱንና የሚናወጠውን ማዕበል ገሰጸ ጸጥ አደረጋቸው።
\v 25 ከዚያም ኢየሱስ፣ “እምነታችሁ የት አለ?” አላቸው። ፍርሃት ይዟቸውና በጣም ተደንቀው እርስ በርሳቸው፣ “ነፋሳትንና ባሕርን የሚያዝ እነርሱም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው?" ተባባሉ።
\s5
\v 26 ከገሊላ ባሕር በስተ ማዶ በሌላው አንጻር ወደ ነበረው ወደ ጌርጌሴኖን ክልል ደረሱ።
\v 27 ኢየሱስ ከጀልባው ወርዶ ወደ ምድር በተሻገረ ጊዜ፣ አጋንንት የነበሩበት አንድ ሰው አገኘው። ይህ ሰው ለረጅም ጊዜ ልብስ ለብሶ አያውቅም፤ በመቃብር ስፍራ እንጂ፣ በቤትም ውስጥ አልኖረም።
\s5
\v 28 ኢየሱስን ባየው ጊዜ ጮኾ በፊቱ ተደፋ፤ በታላቅም ድምፅ፣ “የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ! እኔ ከአንተ ምን ጉዳይ አለኝ? እንዳታሠቃየኝ እለምንሃለሁ” አለው።
\v 29 እንደዚህም ያለበት ምክንያት ብዙ ጊዜ ይይዘውና ያሠቃየው የነበረውን ርኩስ መንፈስ ከእርሱ እንዲወጣ ኢየሱስ አዞት ስለነበር ነው። ምንም እንኳ በብረት ሰንሰለት የታሰረና በቁጥጥር ስር እንዲውል የተደረገ ቢሆንም፣ እስራቱን ይበጥስ፣ በአጋንንቱም ግፊት ወደ በረሐ እየሄደ ይንከራተት ነበር።
\s5
\v 30 ከዚያም ጊዜም ኢየሱስ፣ “ስምህ ማን ነው?” ብሎ ጠየቀው፤ እርሱም ብዙ አጋንንት ገብተውበት ነበርና ስሜ፣ "ጭፍራ" ነው ብሎ መለሰ።
\v 31 በውስጡ የነበሩት አጋንንት ወደ ጥልቁ እንዲሄዱ እንዳያዛቸው መለመናቸውን ቀጠሉ።
\s5
\v 32 በዚያም ብዙ ዐሳማዎች በኮረብታው ላይ ለግጦሽ ተሰማርተው ነበር፤ አጋንንቱም ወደ ዐሳማዎቹ ይገቡ ዘንድ እንዲፈቅድላቸው ለመኑት። ኢየሱስ የለመኑትን እንዲያደርጉ ፈቀደላቸው።
\v 33 ስለዚህ አጋንንቱ ከሰውዬው ወጥተው ዐሳማዎቹ ውስጥ ገቡ። ዐሣማዎቹን ከኮረብታው ተጣድፈው ቁልቁል ወረዱ፣ ወደ ሐይቁም ውስጥ ገብተው ሰጠሙ።
\s5
\v 34 ዐሳማዎቹን ሲያሰማሩ የነበሩት ሰዎች ይህን በተመለከቱ ጊዜ ወደ ከተማውና ወደ ገጠሮች ሁሉ ሸሽተው በመሄድ ዜናውን አሠራጩ።
\v 35 ስለዚህ ይህንን የሰሙት ሰዎች የሆነውን ለማየት ወጡ፤ ወደ ኢየሱስም በመጡ ጊዜ አጋንንት የወጡለትን ሰው አገኙት። ሰውዬውም ልብስ ለብሶ ወደ አእምሮውም ተመልሶ በኢየሱስ እግር ሥር ተቀምጦ ሲያዩት፣ ፍርሃት ያዛቸው።
\s5
\v 36 ከዚያም የሆነውን ነገር ያዩ ሰዎች በአጋንንት ቁጥጥር ሥር የነበረው ሰው እንዴት እንደ ዳነ ለሌሎች ተናገሩ።
\v 37 የጌርጌሴኖን ክልልና የዚያ አካባቢ ሰዎች ሁሉ ታላቅ ፍርሃት ይዟቸው ስለ ነበረ፣ ኢየሱስ ከእነርሱ እንዲሄድ ለመኑት፤ እርሱም ከዚያ ስፍራ ወደ መጣበት ለመመለስ ወደ ጀልባይቱ ገባ።
\s5
\v 38 አጋንንት የወጡለት ሰው ዐብሮት ለመሄድ ኢየሱስን ለመነው።
\v 39 ኢየሱስ ግን፣ “ወደ ቤተ ሰብህ ተመልሰህ እግዚአብሔር ያደረገልህን ታላላቅ ነገሮች ሁሉ ተርክላቸው” ብሎ አሰናበተው። ሰውየውም ኢየሱስ ያደረገለትን ታላላቅ ነገሮች በከተማው ሁሉ እየመሰከረ ጒዞውን ቀጠለ።
\s5
\v 40 ሁሉም ይጠብቁት ነበርና ኢየሱስ ሲመለስ ሕዝቡ ተቀበሉት።
\v 41 እነሆም ከምኲራብ መሪዎች አንዱ ኢያኢሮስ የተባለ ሰው መጣ፤ እርሱም በኢየሱስ እግር ላይ ወድቆ ወደ ቤቱ ይመጣ ዘንድ ለመነው።
\v 42 ወደ ቤቱ እንዲመጣ የፈለገው ዐሥራ ሁለት ዓመት የሆናት እንድያ ልጁ በሞት አፋፍ ላይ ስለነበርች ነው። ነገር ግን ወደዚያ እየሄደ በነበረበት ጊዜ፣ ብዙ ሕዝብ በመጨናነቅ ይጋፉት ነበር።
\s5
\v 43 በዚያም ለዐሥራ ሁለት ዓመት ደም ሲፈሳት የነበረች፣ ገንዘቧን ሁሉ ለሐኪሞች ብትከፍልም አንዳቸውም ያልፈወሷት አንዲት ሴት ነበረች።
\v 44 እርሷ ከኢየሱስ በስተኋላ መጥታ የልብሱን ጫፍ ነካች፤ የፈሳት የነበረው ደምም ወዲያው ቆመ።
\s5
\v 45 ኢየሱስ፣ “የነካኝ ማን ነው?” አለ። ሁሉም አልነካንህም ብለው በተናገሩ ጊዜ፣ ጴጥሮስ፣ “ጌታ ሆይ፣ ሕዝቡ እኮ እየገፋፉህና እያጨናነቁህ ነው” አለው።
\v 46 ኢየሱስ ግን፣ “ከእኔ ኅይል እንደ ወጣ ዐውቄአለሁና አንድ ሰው ነክቶኛል” አለ።
\s5
\v 47 ሴቲቱ ያደረገችውን መደበቅ እንዳልቻለች ባስተዋለች ጊዜ፣ ሴቲቱ እየተንቀጠቀጠች መጣችና በኢየሱስ እግር ሥር ወድቃ በሰዎች ሁሉ ፊት እርሱን ለምን እንደነካችውና እንዴት ወዲያው እንደ ተፈወሰች ተናገረች። ከዚያም ኢየሱስ ሴቲቱን፥
\v 48 “ልጄ ሆይ እምነትሽ አድኖሻል በሰላም ሂጂ” አላት።
\s5
\v 49 እርሱም ገና እየተናገረ ሳለ ከምኲራብ አለቃው ቤት አንድ ሰው መጥቶ፣ “ልጅህ ሞታለች። መምህሩን አታድክመው” አለ።
\v 50 ኢየሱስ ግን ይህን በሰማ ጊዜ፣ “እመን ብቻ እንጂ አትፍራ፣ እርሷም ትድናለች” አለው።
\s5
\v 51 ከዚያም እርሱ ወደዚያ ቤት በመጣ ጊዜ፣ ከጴጥሮስ፣ ከዮሐንስ፣ ከያዕቆብ እንዲሁም ከልጅቱ አባትና ከእናትዋ በስተቀር ማንም ዐብሮት እንዲገባ አልፈቀደም።
\v 52 በዚያ ስፍራ የነበሩት ሰዎች ሁሉ ያለቅሱ ዋይ ዋይም ይሉ ነበር። እርሱ ግን፣ “አታልቅሱ ልጅትዋ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አለ።
\v 53 እነርሱ ግን መሞቷን ዐውቀው ስለ ነበር፣ በንቀት ሳቁበት።
\s5
\v 54 እርሱ ግን የልጅቱን እጅ ይዞ፣ “አንቺ ልጅ ተነሽ” አላት።
\v 55 ነፍስዋም ተመለሰች፣ ወዲያውኑም ብድግ አለች። እርሱም የምትበላው እንዲሰጧት አዘዘ።
\v 56 ወላጆቿም ተደነቁ፤ እርሱ ግን ስለሆነው ነገር ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው።
\s5
\c 9
\cl ምዕራፍ 9
\p
\v 1 ኢየሱስም ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ጠርቶ በአጋንንት ሁሉ ላይና በሽታዎችን የመፈወስ ሥልጣን ሰጣቸው።
\v 2 የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዲሰብኩና በሽተኞችን እንዲፈውሱ ላካቸው።
\s5
\v 3 እንዲህም አላቸው፤ “ለጒዞአችሁ በትርም ቢሆን፣ የገንዘብም ቦርሳ ቢሆን፣ ስንቅም ቢሆን፣ ገንዘብ ወይም ቅያሬ ልብስ፣ ምንም ነገር አትያዙ።
\v 4 ከዚያ ስፍራ እስከምትወጡ በገባችሁበት ቤት በዚያ ቆዩ።
\s5
\v 5 “የማይቀበሏችሁ ቢኖሩ ከዚያ ከተማ ስትወጡ ምስክር እንዲሆንባቸው ከእግሮቻችሁ ጫማ ላይ አቧራውን አራግፉ።”
\v 6 ከዚያም እነርሱ ከዚያ ተነሥተው የምሥራቹን ወንጌል እየሰበኩ፣ በሄዱባቸውም ስፍራዎች ሁሉ በሽተኞችን እየፈወሱ ያልፉ ነበር።
\s5
\v 7 የአራተኛው ክፍል ገዢ ሄሮድስ እየተደረገ የነበረውን ሁሉ በሰማ ጊዜ፣ በጣም ተሸበረ፣ ምክንያቱም ‘አንዳንዶቹ መጥምቁ ዮሐንስ ከሞት ተነሥቷል፤
\v 8 በሌሎች ዘንድ ደግሞ ኤልያስ ተገልጧል፤ እንደ ገና ሌሎች ከጥንት ነቢያት አንዱ ሕያው ሆኖ ተነሥቷል’ ይሉ ነበር።
\v 9 ሄሮድስም “የዮሐንስን ራስ እኔ አስቈርጬዋለሁ፣ እንዲህ ያለ ነገር የምሰማበት ይህ ማን ነው?” አለ። ሄሮድስም ኢየሱስን ለማየት ጥረት ያደርግ ነበር።
\s5
\v 10 የተላኩት በተመለሱ ጊዜ፣ ያደረጉትን ሁሉ ነገሩት። ኢየሱስ ራሱ ሐዋርያቱን አስከትሎ ቤተ ሳይዳ ወደምትባል ከተማ ሄደ።
\v 11 ነገር ግን፣ ሕዝቡ ስለዚህ ጉዳይ ሰሙና ተከተሉት፣ እርሱም ተቀብሏቸው ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ነገራቸው፣ መፈወሰ የሚያስፈልጋቸውንም ፈወሳቸው።
\s5
\v 12 ቀኑ ወደ መገባደድ ተቃረበ፣ ዐሥራ ሁለቱም ወደ እርሱ መጡና “ያለንበት ቦታ ምንም የሌለበት ምድረ በዳ በመሆኑ ሕዝቡ በአካባቢው ወዳሉት መንደሮችና ገጠሮች ሄደው ማረፊያ ቦታና ምግብ እንዲያገኙ አሰናብታቸው” አሉት።
\v 13 እርሱ ግን፣ “የሚበሉትን እናንተ ስጧቸው” አላቸው። እነርሱም፣ “ወጣ ብለን ለዚህ ሁሉ ሕዝብ ምግብ ካልገዛን በስተቀር አሁን ያለን ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዐሣ የበለጠ አይደለም” አሉት።
\v 14 በዚያ አምስት ሺህ ያህል ሰዎች ነበሩ። እርሱም ደቀ መዛሙርቱን፣ “ሃምሳ ሃምሳ ሆነው በቡድን እንዲቀመጡ አድርጓቸው” አላቸው።
\s5
\v 15 ስለዚህ እርሱ እንዳላቸው አደረጉ፣ ሕዝቡም ሁሉ ተቀመጡ።
\v 16 እርሱም አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዐሣ ይዞ ወደ ሰማይ አሻቅቦ ከተመለከተ በኋላ ባርኮ፣ ቈርሶም ለሕዝቡ እንዲያቀርቡላቸው ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው።
\v 17 ሁሉም በልተው ጠገቡ፣ የተራረፈውም የምግብ ፍርፋሪ ተሰበሰበና ዐሥራ ሁለት ቅርጫት ሙሉ ሆነ።
\s5
\v 18 ኢየሱስ ብቻውን ይጸልይ በነበረበት አንድ ወቅት ደቀ መዛሙርቱ ከእርሱ ጋር ነበሩና፣ “ሕዝቡ እኔ ማን እንደሆንሁ ነው የሚናገሩት?” ብሎ ጠየቃቸው።
\v 19 እነርሱም፣ “አጥማቂው ዮሐንስ ፣ ሌሎች ደግሞ ኤልያስ፣ እንደ ገና ሌሎች ጥንት ከነበሩት ነቢያት አንዱ ከሙታን ተነሥቶ ነው ይላሉ” አሉት።
\s5
\v 20 “እናንተ ግን እኔን ማን ትሉኛላችሁ?” አላቸው። ጴጥሮስ፣ “አንተ ከእግዚአብሔር የመጣህ ክርስቶስ ነህ” ብሎ መለሰ።
\v 21 ነገር ግን ኢየሱስ ይህን ለማንም እንዳይነግሩ በማስጠንቀቅ አዘዛቸው።
\v 22 በተጨማሪም የሰው ልጅ ብዙ መከራ መቀበል እንደሚገባው በሽማግሌዎች፣ በካህናት አለቆችና በሕግ መምሕራን ተቀባይነት እንደማያገኝ፣ እንደሚሞትና በሦስተኛው ቀን ከሙታን እንደሚነሣ በቅድሚያ አስታወቃቸው።
\s5
\v 23 ለሁሉም እንዲህ አላቸው፤ "እኔን መከተል የሚፈልግ ራሱን ይካድ ዕለት ዕለትም መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ።
\v 24 ሕይወቱን ሊያድን ጥረት የሚያደርግ ሰው ካለ ያጠፋታል፣ ስለ እኔ ብሎ ሕይወቱን የሚጥል ደግሞ ያድናታል።
\v 25 አንድ ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ የራሱን ሕይወት ግን ቢያጣ ምን ይጠቅመዋል?
\s5
\v 26 በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ የሰው ልጅ በራሱ፣ በአባቱ፣ እንዲሁም በቅዱሳን መላእክቱ ክብር በሚመጣበት ጊዜ ያፍርበታል።
\v 27 እኔ ግን በእውነት እላችኋለሁ፣ እዚህ ከቆማችሁት መካከል አንዳንዶቻችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት እስከምታዩ ድረስ ሞትን አትቀምሱም።
\s5
\v 28 ኢየሱስ ይህን ከተናገረ ከስምንት ቀን ገደማ በኋላ ጴጥሮስን፣ ዮሐንስን፣ እንዲሁም ያዕቆብን ይዞ ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ።
\v 29 እየጸለየም ሳለ የፊቱ መልክ ተለወጠ ልብሱም በጣም ከመንጣቱ የተነሣ አንፀባረቀ።
\s5
\v 30 እነሆ፣ ሁለት ሰዎች ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር!
\v 31 እነርሱም በክብር የተገለጡት ሙሴና ኤልያስ ነበሩ። በኢየሩሳሌም ሊፈጽም ስላለው ከዚህ ሕይወት ስለ መለየቱ ይነጋገሩ ነበር።
\s5
\v 32 ጴጥሮስና ዐብረውት የነበሩት እንቅልፍ ከብዶባቸው ነበር። ሙሉ በሙሉ በነቁ ጊዜ ግን የኢየሱስን ክብርና ዐብረውት የነበሩትን ሁለቱን ሰዎች አዩ።
\v 33 እነርሱ ከኢየሱስ ተለይተው ሲሄዱ፣ ጴጥሮስ፣ “ጌታ ሆይ፣ ለእኛ በዚህ መሆን መልካም ነው፣ አንድ ለአንተ፣ አንድ ለሙሴ፣ አንድ ደግሞ ለኤልያስ ሦስት ዳሶችን ልንሠራ ይገባናል” አለው። ስለ ምን እየተናገረ እንደ ነበረ አላስተዋለም።
\s5
\v 34 ከዚያም እርሱ ይህን እየተናገረ ሳለ ደመና መጥቶ ጋረዳቸው፤ በዙሪያቸው ከነበረው ደመና የተነሣ ፈሩ።
\v 35 ከደመናው ውስጥ፣ “የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፣ እርሱን ስሙት” የሚል ድምፅ መጣ።
\v 36 የድምፁ መሰማት ባበቃ ጊዜ፣ ኢየሱስ ብቻውን ነበረ። እነርሱም ዝም አሉ፤ በነዚያ ቀናት ስላዩአቸው ስለ እነዚያ ነገሮች ምንም ነገር ለማንም አልተናገሩም።
\s5
\v 37 ከተራራው በወረዱ ማግስት ብዙ ሕዝብ ተሰብስበው ወደ እርሱ መጡ።
\v 38 እነሆም፣ ከሕዝቡ መካከል አንድ ሰው፣ “መምህር ሆይ፣ ብቸኛ የሆነውን አንድ ልጄን ትመለከትልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ።
\v 39 ክፉ መንፈስ በላዩ ሲመጣበት በድንገት ይጮኻል፣ እየጣለ ያንፈራግጠዋል፤ አረፋም በአፉ ይደፍቃል። በጭንቅ ለቅቆት ይሄዳል፣ በሚሄድበት ጊዜ ክፉኛ ያቈስለዋል።
\v 40 ክፉውን መንፈስ እንዲያወጡለት ደቀ መዛሙርትህን ለመንኋቸው፣ እነርሱ ግን አልቻሉም” በማለት ጮኸ።
\s5
\v 41 ኢየሱስ እንደዚህ በማለት መልስ ሰጠ፣ “ክፉና ጠማማ ትውልድ፣ ከእናንተ ጋር የምኖረውና የምታገሣችሁ እስክ መቼ ነው? ልጅህን ወደዚህ አምጣው።”
\v 42 ልጁ እየመጣ ሳለ ጋኔኑ ጣለው፣ እጅግም አንፈራገጠው። ኢየሱስ ግን ርኩሱን መንፈስ ገሠጸውና ልጁን ፈወሰው፣ ለአባቱም መልሶ ሰጠው።
\s5
\v 43 ሁሉም በእግዚአብሔር ታላቅነት ተደነቁ። ነገር ግን ሁሉም እርሱ ባደረጋቸው ነገሮች ሁሉ እየተደነቁ ሳሉ፣ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፣
\v 44 "የነገርኋችሁን እነዚህን ነገሮች በጥልቀት አስተውሉ፤ ምክንያቱም የሰውን ልጅ በሰዎች እጅ አሳልፈው ይሰጡታል" አላቸው።
\v 45 ነገር ግን ተሰውሮባቸው ስለ ነበረ፣ ይህ አባባሉ ምን እንደ ሆነ ስላልተረዱት ሊገባቸው አልቻለም። ስለዚያ አባባል እርሱን መጠየቅ ፈሩ።
\s5
\v 46 ከዚያም ከእነርሱ መካከል ከሁሉም እጅግ ታላቅ የሆነው ማን ነው የሚለውን ጥያቄ በሚመለከት ክርክር ተነሣ።
\v 47 ኢየሱስ ግን በልባቸው ምን እያሰላሰሉ እንደ ነበሩ ባወቀ ጊዜ፣ አንድ ትንሽ ልጅ ይዞ በአጠገቡ አቆመው፣ እንዲህም አላቸው፤
\v 48 "እንደዚህ ያለውን ሕፃን በስሜ የሚቀበል፣ እኔን ይቀበላል። እኔን የሚቀበል ከሆነ ደግሞ የላከኝን ይቀበላል። ስለሆነም፣ በመካከላችሁ ከሁላችሁም የሚያንስ እርሱ ታላቅ ነውና።”
\s5
\v 49 ዮሐንስ መልሶ እንዲህ አለ፤ “ጌታ ሆይ፣ አንድ ሰው በስምህ አጋንንት ሲያወጣ አየነው፣ ከእኛ ጋር ስላልሆነ ከለከልነው።"
\v 50 ኢየሱስ ግን፣ “አትከልክሉት፣ ምክንያቱም የማይቃወማችሁ ከእናንተ ጋር ነው” አላቸው።
\s5
\v 51 ወደ ሰማይ የሚሄድበት ጊዜ እየተቃረበ ሲመጣ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ቈርጦ ተነሣ።
\v 52 ከእርሱ ቀደም ብለው እንዲሄዱ መልእክተኞች ላከ፤ እነርሱም ሊያዘጋጁለት ዘንድ ወደ ሳምራውያን መንደር ገቡ።
\v 53 ነገር ግን ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ፊቱን አንቅቶ ስለ ነበር፣ በዚያ የነበሩት ሕዝብ አልተቀበሉትም።
\s5
\v 54 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ያዕቆብና ዮሐንስ ይህን ባዩ ጊዜ፣ “ጌታ ሆይ፣ እሳት ከሰማይ ወርዶ እንዲያጠፋቸው እንድናዝ ትወዳለህን?” አሉት።
\v 55 እርሱ ግን ዘወር ብሎ ገሰጻቸው።
\v 56 ከዚያም ወደ ሌላ መንደር ሄዱ።
\s5
\v 57 እየሄዱ ሳሉም አንድ ሰው፣ “ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ” አለው።
\v 58 ኢየሱስ፣ “ቀበሮዎች ጒድጓድ አላቸው፣ የሰማይ ወፎችም ጎጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት መጠለያ የለውም” አለው።
\s5
\v 59 ከዚያም ለሌላውን ሰው፣ “ተከተለኝ” አለው። ሰውዬው ግን፣ “ጌታ ሆይ፣ በቅድሚያ እንድሄድና አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ” አለው።
\v 60 እርሱ ግን፣ ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፣ አንተ ግን በየስፍራው ሁሉ ሄደህ የእግዚአብሔርን መንግሥት አውጅ” አለው።
\s5
\v 61 ሌላ ሰው ደግሞ፣ “ጌታ ሆይ፣ እከተልሃለሁ ነገር ግን በቅድሚያ የቤተ ሰቤን አባላት እንድሰናበት ፍቀድልኝ” አለው።
\v 62 ኢየሱስ ግን፣ “ዕርፍ በእጁ ይዞ ወደ ኋላ የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም” አለው።
\s5
\c 10
\cl ምዕራፍ 10
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ ጌታ፣ ሌሎች ሰባ ሰዎችን ሾመ፤ እርሱ ራሱ ሊሄድባቸው ወዳሰባቸው ከተማዎችና ስፍራዎች ሁሉ ቀድመውት እንዲሄዱ ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው፤
\v 2 እንዲህም አላቸው፣ "መከሩ ብዙ ነው፣ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፡፡ ስለዚህ ወደ መከሩ ሠራተኞችን እንዲክ የመከሩን ጌታ በአስቸኳይ ለምኑት።
\s5
\v 3 እንግዲህ ሂዱ፣ እነሆ፣ በተኲላዎች መካከል እንደ በጎች እልካችኋለሁ፡፡
\v 4 ለመንገዳችሁ ምንም አትያዙ፤ የገንዘብ ቦርሳም ቢሆን የመንገደኛ ሻንጣም ቢሆን፣ ጫማም ቢሆን አትያዙ፣ በመንገድም ላይ ለማንም ሰላምታ አትስጡ፡፡
\s5
\v 5 ወደ ማንኛውም ሰው ቤት ስትገቡ፣ በቅድሚያ 'ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን' በሉ፡፡
\v 6 በዚያ ቤት ያለው ሰው የሰላም ሰው ከሆነ ሰላማችሁ ያርፍበታል፣ የሰላም ሰው ካልሆነ ደግሞ ሰላማችሁ ይመለስላችኋል፡፡
\v 7 ያቀረቡላችሁን እየበላችሁና እየጠጣችሁ በገባችሁበት በዚያው ቤት ቆዩ፣ ምክንያቱም ሠራተኛ ደመወዙን ማግኘት ይገባዋል፡፡ ከቤት ወደ ቤት ግን አትዘዋወሩ፡፡
\s5
\v 8 ወደ ማንኛውም ከተማ ስትገቡና እነርሱም ሲቀበሏችሁ፣ ያቀረቡላችሁን ብሉ፡፡
\v 9 በዚያም ያሉትን ሕመምተኞች ፈውሱ፣ 'የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ቀርባለች' ብላችሁም ንገሩአቸው፡፡
\s5
\v 10 ነገር ግን ወደ ማንኛውም ከተማ ስትገቡ እነርሱ ባይቀበሏችሁ፣ ወደ ጐዳናዎቻቸው ውጡና፣
\v 11 'በጫማችን ላይ የተጣበቀውን የከተማችሁን አቧራ እንኳ በእናንተ ላይ ምስክር ይሆንባችሁ ዘንድ እናራግፈዋለን! የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ እንደ ቀረበ ግን ይህንን እወቁ' በሏቸው፡፡
\v 12 እላችኋለሁ፣ በፍርድ ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ ይቀልላቸዋል፡፡
\s5
\v 13 ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ! በእናንተ ዘንድ የተደረጉት ታላላቅ ታምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርገው ቢሆን ኖሮ፣ የሐዘን ልብስ ለብሰውና ራሳቸውን አዋርደው ከረጅም ጊዜ በፊት ንስሐ በገቡ ነበር፡፡
\v 14 ነገር ግን በፍርድ ወቅት ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል።
\v 15 አንቺስ ቅፍርናሆም፣ እስከ ሰማይ ከፍ እንዳልሽ ታስቢ ይሆን? እንደዚያ አታስቢ፣ እስከ ሲዖል ድረስ ትወርጃለሽ።
\s5
\v 16 እናንተን የሚሰማችሁ እኔን ይሰማኛል፣ እናንተንም የማይቀበል እኔን አይቀበለኝም፣ እኔን የማይቀበል ደግሞ የላከኝን አይቀበልም፡፡
\s5
\v 17 ሰባዎቹም ደስ እያላቸው ተመለሱና፣ ጌታ ሆይ፣ አጋንንት እንኳ በስምህ ታዘዙልን" አሉት፡፡
\v 18 ኢየሱስ፣ "ሰይጣን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ
\v 19 እነሆ፣ እባቦችንና ጊንጦችን እንድትረግጡ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፣ በምንም ዓይነት መንገድ ምንም አይጐዳችሁም፡፡
\v 20 የሆነ ሆኖ መናፍስት ስለተገዙላችሁ በዚህ ብቻ ደስ አይበላችሁ፤ ነገር ግን ስማችሁ በሰማይ ስለ ተጻፈ የላቀ ደስታ ይሰማችሁ።"
\s5
\v 21 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ እጅግ ሐሤት አደረገና፣ "የሰማይና የምድር ጌታ፣ አባት ሆይ፣ እነዚህን ነገሮች ከጥበበኞችና ከሚያስተወሉ ሰውረህ እንደ ሕፃናት ለሆኑት ላልተማሩት ለእነዚህ ስለ ገለጽህላቸው አመሰግንሃለሁ፡፡ አዎ፣ አባት ሆይ፣ ይህ በፊትህ ዘንድ መልካም ሆኖአልና።
\s5
\v 22 ሁሉም ነገር ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፣ ከአባትም በቀር ልጁ ማን እንደ ሆነ የሚያውቅ የለም፣ አባትም ማን እንደ ሆነ ከልጁ ወይም ልጁ ሊገልጥለት ከፈለገው ሰው በቀር ማንም የሚያውቅ የለም።"
\s5
\v 23 ኢየሱስ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መለስ ብሎ፣ ለእነርሱ ብቻ፣ "እናንተ የምታዩትን የሚያዩ የተባረኩ ናቸው፡፡
\v 24 ብዙ ነቢያትና ነገሥታት እናንተ ያያችሁትን ለማየት ፈልገው ሳያዩ፣ እናንተም የሰማችሁትን ሊሰሙ ፈልገው ሳይሰሙ ቀርተዋል" አለ።
\s5
\v 25 እነሆ፣ አንድ የአይሁድ የሕግ መምህር ሊፈትነው ፈልጎ ብድግ አለና፣ "መምህር ሆይ፣ የዘላለምን ሕይወት ለመውረስ ምን ማድረግ ይገባኛል?" በማለት ጠየቀው፡፡
\v 26 ኢየሱስ፣ "በሕጉ የተጻፈው ምንድን ነው? የተረዳኸው እንዴት ነው?" አለው።
\v 27 እርሱም፣ "ጌታ አምላክህን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህ፣ በሙሉ ኃይልህ፣ በሙሉ ዐሳብህም ውደድ፤ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ" ብሎ መለሰ፡፡
\v 28 ኢየሱስም፣ "በትክክል መልሰሃል፡፡ ይህን አድርግ በሕይወትም ትኖራለህ" አለው።
\s5
\v 29 መምህሩ ግን ራሱን ሊያጸድቅ ወዶ፣ ኢየሱስን፣ "ባልንጀራዬ ማን ነው?" ብሎ ጠየቀው፡፡
\v 30 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፤ "አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ እየሄደ ሳለ ወንበዴዎች አግኝተውት ንብረቱን ዘረፉት፣ ደበደቡት፣ በሞት አፋፍ ላይ እያለም ጥለውት ሄዱ።
\s5
\v 31 እንደ አጋጣሚ አንድ ካህን በዚያ መንገድ ሲሄድ ሰውዬውን ተመለከተውና በሌላ በኩል አድርጎ አልፎት ሄደ።
\v 32 በተመሳሳይ ሁኔታ አንድ ሌዋዊም ወደዚያ ስፍራ መጥቶ በሌላ በኩል አድርጎ አልፎ ሄደ።
\s5
\v 33 አንድ ሳምራዊ ግን እየተጓዘ ሳለ ሰውዬው ወደነበረበት መጣ። ባየውም ጊዜ በርኅራኄ ልቡ ተነካ።
\v 34 ወደ እርሱም ጠጋ ብሎ መድኃኒት ካደረገለት በኋላ ቊስሉን በጨርቅ አሰረለት። እርሱ ይጓጓዝበት በነበረበትም አህያ ላይ አስቀምጦት ወደ አንድ የእንግዶች ማረፊያ አመጣው፣ እንክብካቤም አደረገለት።
\v 35 በማግስቱ ሁለት ዲናር ከኪሱ አውጥቶ ለእንግዳ ማረፊያው ኅላፊ ሰጠውና፣ "ተንከባከበው፣ ከዚህ በላይ ወጪ የሚያስወጣህ ከሆነ በምመለስበት ጊዜ ያወጣኸውን ትርፍ ወጪ እመልስልሃለሁ" አለው።
\s5
\v 36 "ከእነዚህ ከሦስቱ በወንበዴዎች እጅ ለወደቀው ባልንጀራ የሆነለት የትኛው ይመስልሃል?" አለው።
\v 37 መምህሩም፣ "የራራለቱ ነው" አለ። ኢየሱስም፣ "አንተም ሂድና ይህንኑ አድርግ" አለው።
\s5
\v 38 እየተጓዙ ሳሉም ወደ አንድ መንደር ገባ፤ ማርታ የምትባልም አንዲት ሴት በቤትዋ ተቀበለችው"
\v 39 እርሷም ማርያም የተባለች በኢየሱስ እግር ሥር ተቀምጣ ቃሉን የምትሰማ እኅት ነበረቻት"
\s5
\v 40 ማርታ ግን ምግብ ለማዘጋጀት ባደረገችው ጥረት በጣም ውጥረት በዛባት። ወደ ኢየሱስም ዘንድ መጥታ፣ "ጌታ ሆይ፣ እኔ ብቻዬን ሥራ ስሠራ፣ እኅቴ እኔን ሳትረዳኝና ስትተወኝ አንተ ዝም ትላለህን? እንግዲያውስ እንድታግዘኝ ንገራት" አለችው።
\v 41 ጌታ ግን፣ "ማርታ፣ ማርታ ስለ ብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ፣
\v 42 የሚያስፈልገው ግን አንድ ነገር ነው፡፡ ማርያም በጣም ትክክል የሆነውን ምርጫ መርጣለች፣ ይህም ደግሞ ከእርሷ አይወሰድባትም›› ብሎ መለሰላት፡፡
\s5
\c 11
\cl ምዕራፍ 11
\p
\v 1 ኢየሱስ በአንድ ስፍራ መጸለዩን በፈጸመ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ እንዲህ አለው፣ “ጌታ ሆይ፣ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ እኛን መጸለይ አስተምረን” አለ።
\s5
\v 2 ኢየሱስም፣ “በምትጸልዩበት ጊዜ፣ 'በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ መንግሥትህ ትምጣ
\s5
\v 3 የዕለት እንጀራችን በየዕለቱ ስጠን።
\v 4 እኛን የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን። ወደ ፈተናም አታግባን በሉ'" አላቸው።
\s5
\v 5 ኢየሱስም፣ “ከእናንተ ወዳጅ ያለው በእኩለ ሌሊት ውድ ወዳጁ ዘንድ በመሄድ
\v 6 ‘አንድ ወዳጄ ከሌላ ስፍራ ወደ እኔ መጥቶ የማስተናግድበት ምንም ስለሌለኝ፣ ሦስት እንጀራ አበድረኝ የማይለው ማነው’?
\v 7 በቤት ውስጥ ያለው ወዳጁ ‘አታስቸግረኝ፤ በሩ ተዘግቶአል ልጆቼም ከእኔ ጋር በአልጋ ላይ ተኝተዋል። ለመነሣትና ለአንተ እንጀራ ለመስጠት አልችልም’ ይለዋልን?
\v 8 ምንም እንኳን ወዳጁ ስለሆናችሁ ተነሥቶ እንጀራ ባይሰጣችሁም ያለ ዕረፍት ስለነዘነዛችሁት ብቻ ተነስቶ የምትፈልጉትን ያህል እንጀራ ይሰጣችኋል፤
\s5
\v 9 ለምኑ ይሰጣችኋል፣ ፈልጉ ታገኛላችሁ፣ አንኳኩ ይከፈትላችኋል፤
\v 10 የሚለምን ሰው ሁሉ ይቀበላልና የሚፈልግም ሰው ያገኛል፣ ለሚያንኳኳም ይከፈትለታል።
\s5
\v 11 አባት ከሆናችሁት ከእናንተ ዓሣ ሲለምነው በዓሣ ፈንታ እባብ ወይም
\v 12 ዕንቁላል ሲለምነው በዕንቁላሉ ፈንታ ጊንጥ የሚሰጠው ማን ነው?
\v 13 ስለዚህ፣ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ፣ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን የምታውቁ ከሆነ፣ በሰማይ የሚኖረው አባታችሁማ ለሚለምኑት መንፈስ ቅዱስን እንዴት አብልጦ አይሰጣቸውም?”
\s5
\v 14 በኋላ ኢየሱስ ጋኔን እያወጣ ነበር፤ እርሱም ድዳ ነበር። ጋኔኑም በወጣ ጊዜ ድዳው ሰውዬ ተናገረ፤ ሕዝቡም ተደነቁ።
\v 15 ነገር ግን ከሕዝቡ አንዳንዶቹ፣ “አጋንንትን የሚያወጣው የአጋንንት አለቃ በሆነው በብዔል ዜቡል ነው” አሉ።
\s5
\v 16 ሌሎች ሊፈትኑት ፈልገው ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ጠየቁት።
\v 17 ኢየሱስ ግን ዐሳባቸውን አውቆ፣ “እርስ በርሱ የሚከፋፈል መንግሥት ይፈርሳል፤ እርስ በርሱ የሚለያይ ቤተ ሰብም ይወድቃል።
\s5
\v 18 ሰይጣን ራሱን በራሱ የሚቃረን ከሆነ መንግሥቱ እንዴት ይጸናል? እናንተ ግን እኔን አጋንንትን የሚያወጣው በብዔል ዜቡል ነው ትሉኛላችሁ።
\v 19 እኔ በቡዔል ዜቡል አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ የእናንተ ተከታዮች የሚያወጧቸው በማን ነው? ከዚህም የተነሣ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል።
\v 20 እኔ ግን በእግዚአብሔር ኃይል አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፣ እንግዲያውስ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ መጥቷል።
\s5
\v 21 21 በሚገባ የታጠቀ ብርቱ ሰው ቤቱን በሚጠብቅበት ጊዜ የቤቱ ንብረት ያለ ስጋት ይሆናል፤
\v 22 ከእርሱ የበረታ ሰው ሲያሸንፈው ግን ያ ከእርሱ የበረታው ሰው መሣሪያውን ይቀማዋል፣ የቤቱንም ሀብት ይበዘብዛል።
\v 23 ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፣ ከእኔ ጋርም የማይሰበስብ ይበትናል።
\s5
\v 24 ርኩስ መንፈስ ከሰው በሚወጣበት ጊዜ ውሃ በሌለባቸው ስፍራዎች እየተዘዋወረ ማረፊያ ይፈልጋል። ምንም ማረፊያ ሲያጣ ‘ወደ ወጣሁበት ቤት እመለሳለሁ’ ይላል።
\v 25 በሚመለስበት ጊዜ ያንን ቤት ተጠርጎና ጸድቶ ያገኘዋል።
\v 26 ከዚያም ከእርሱ ይልቅ የከፉ ሰባት ሌሎችን ከእርሱ ጋር ይዞ ይሄድና ሁሉም በዚያ ሰው ውስጥ ገብተው ይኖራሉ። ከዚያም ያ ሰው በመጨረሻ የሚገጥመው ሁኔታ ከመጀመሪያው ይልቅ የከፋ ይሆናል።
\s5
\v 27 ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች በሚናገርበት ጊዜ፣ ከሕዝቡ መካከል አንዲት ሴት ድምጿን ከፍ አድርጋ፣ “አንተን የተሸከመችህ ማኅፀንና የጠባሃቸው ጡቶች የተባረኩ ናቸው” አለችው።
\v 28 እርሱ ግን፣ “የተባረኩትስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው” አለ።
\s5
\v 29 የሕዝቡም ቊጥር እየጨመረ ሲሄድ፣ እንዲህ ማለት ጀመረ፣ “ይህ ትውልድ ክፉ ትውልድ ነው። ምልክት ይፈልጋል፤ ሆኖም ከዮናስ ምልክት በቀር ሌላ ምልክት አይሰጠውም።
\v 30 ልክ ዮናስ ለነነዌ ሰዎች ምልክት እንደ ሆነላቸው፣ የሰው ልጅም ለዚህ ትውልድ ምልክት ይሆናልና።
\s5
\v 31 የደቡብ ንግሥት በፍርድ ወቅት ከዚህ ትውልድ ጋር ትነሣና ትፈርድበታለች፣ ምክንያቱም የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳርቻ መጥታለችና፤ እነሆም ከሰሎሞን የሚበልጥ በዚህ አለ።
\s5
\v 32 32 የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ይነሡና ይፈርዱበታል፣ ምክንያቱም በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋል፤ እነሆም ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ።
\s5
\v 33 አንድ ሰው መብራት ካበራ በኋላ ብርሃኑ በማይታይበት ሰዋራ ስፍራ አያስቀምጠውም ወይም እንቅብ በላዩ ላይ አይደፋበትም። ነገር ግን ወደዚያ ቤት የሚገቡ እንዲታያቸው ከፍ ባለ ስፍራ ላይ ያስቀምጠዋል።
\v 34 ዓይን የሰውነት መብራት ነው። ዓይንህ ጤናማ ከሆነ፣ መላ ሰውነትህ በብርሃን የተሞላ ይሆናል። ዓይንህ ሕመምተኛ ከሆነ ግን መላ ሰውነትህ ጨለማ ይሆናል።
\v 35 ስለዚህ በአንተ ውስጥ ያለው ብርሃን ጨለማ እንዳይሆን ተጠንቀቅ።
\v 36 እንግዲህ መላ ሰውነትህ ምንም ጨለማ የሌለበትና በብርሃን የተሞላ ከሆነ፣ በዚያን ጊዜ በሙሉ ብርሃኑ መብራት በአንተ ላይ እንደሚያበራ ያህል ይሆናል።
\s5
\v 37 ንግግሩንም ሲያበቃ አንድ ፈሪሳዊ በቤቱ ምግብ ይመገብ ዘንድ ጋበዘው፤ ኢየሱስም ከፈሪሳዊው ቤት ሄዶ ለማዕድ ቀረበ።
\v 38 ኢየሱስ ወደ ማዕድ ከመቅረቡ በፊት እጁን ባለመታጠቡ ፈሪሳዊው ተደነቀ።
\s5
\v 39 ጌታ ግን እንዲህ አለው፤ “እንግዲህ፣ እናንተ ፈሪሳውያን የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ታጸዳላችሁ፣ ውስጣችሁ ግን በስስትና በክፋት የተሞላ ነው።
\v 40 እናንተ ማስተዋል የሌላችሁ ሰዎች፣ ውጪውን የፈጠረ የውስጡንስ አልፈጠረምን?
\v 41 በውስጥ ያለውን ለድኾች ስጡ፣ ከዚያም ሁሉም ነገር ንጹሕ ይሆንላችኋል።
\s5
\v 42 ነገር ግን እናንተ ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ምክንያቱም ካመረታችሁት አዝሙድና ጤና አዳም ዐሥራት እያወጣችሁ ፍትሕንና የእግዚአብሔርን ፍቅር ንቃችሁ ትተዋላችሁ። ሌላውን ነገር ማድረግ ሳትተዉ ፍትሕ ማድረግንና የእግዚአብሔርን ፍቅር መጠበቅ ያስፈልጋችኋል።
\s5
\v 43 እናንተ ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! በምኲራቦች የክብር መቀመጫዎችንና በገበያ ስፍራም የከበሬታ ሰላምታን ትወዳላችሁና።
\v 44 ሰዎች የማን እንደሆኑ ሳያውቁ የሚረማመዱባቸው መቃብሮችን ትመስላላችሁና ወዮላችሁ!"
\s5
\v 45 የአይሁድ የሕግ መምህር የነበረ አንድ ሰው፣ “መምህር ሆይ፣ በምትናገረው ነገር እኛንም እየሰደብኸን ነው” ብሎ መለሰለት።
\v 46 ኢየሱስም እንዲህ አለ፣ “እናንተም የሕግ መምህራን፣ ለመሸከም የሚከብድ ሸክም በሰዎች ላይ ትጭናላችሁና፣ እናንተ ግን እነዚያን ሸክሞች በአንድ ጣታችሁ እንኳ አትነኳቸውምና ወዮላችሁ!
\s5
\v 47 የገደሏቸው የእናንተ አባቶች ሆነው ሳለ እናንተ ግን የቀደሙ ነቢያትን መቃብር የምታንጹ ናችሁና ወዮላችሁ!።
\v 48 ከዚህም የተነሣ አባቶቻችሁ በሠሩት ሥራ ምስክሮችና ከእነርሱም ጋር የምትስማሙ ናችሁና፣ ምክንያቱም እናንተ የመታሰቢያ መቃብራቸውን የምታንጹላቸው ነቢያት በእርግጥም በአባቶቻችሁ የተገደሉ ነበር።
\s5
\v 49 በዚህ ምክንያት በእግዚአብሔር ጥበብ እንዲህ ተብሏል፣ ‘ነቢያትንና ሐዋርያትን ወደ እነርሱ እልካለሁ፣ እነርሱም አንዳንዶችን ያሳድዳሉ ይገድሉማል።
\v 50 ስለሆነም ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ለፈሰሰው የነቢያት ሁሉ ደም ይህ ትውልድ ተጠያቂ ነው’።
\v 51 ተጠያቂ የሚሆነውም ከአቤል ጀምሮ በመሠዊያውና በቤተ መቅደሱ መካከል እስከ ተገደለው እስከ ዘካርያስ ድረስ ለፈሰሰው የነቢያት ደም ነው። አዎን፣ ይህ ትውልድ ተጠያቂ ነው እላችኋለሁ።
\s5
\v 52 52 እናንተ የአይሁድ የሕግ መምህራንም የዕውቀትን ቊልፍ ጨብጣችሁ ሳላችሁ እናንተ ራሳችሁ የማትገቡ፣ ሊገቡ ያሉትን እንዳይገቡ የምትከለክሉ ናችሁና ወዮላችሁ!
\s5
\v 53 ኢየሱስ ከዚያ ለመሄድ እንደተነሣ፣ የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ተቃወሙት፣ ብዙ ጉዳዮችን አስመልክተው ከእርሱ ጋር ተከራረኩ።
\v 54 ይህንም ያደረጉት ራሱ በተናገረው ቃል ሊያጠምዱት ፈልገው ስለነበረ ነው።
\s5
\c 12
\cl ምዕራፍ 12
\p
\v 1 ይህ እየሆነ ሳለ እርስ በርሳቸው እስኪረጋገጡ ድረስ በብዙ ሺህ የሚቈጠሩ ሰዎች ተሰብስበው ባሉበት ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ይላቸው ጀመር። "ግብዝነት ከሆነው የፈሪሳውያን እርሾ ተጠንቀቁ።"
\s5
\v 2 ነገር ግን የሚገለጥ እንጂ ምንም የተሰወረ፣ የሚታወቅ እንጂ ምንም የተደበቀ ነገር የለም፡፡
\v 3 በጨለማ የተናገራችሁት ማንኛውም ነገር በብርሃን የሚሰማ፣ በጓዳ በጆሮ የተናገራችሁትም በከፍተኛ መድረኮች ላይ የሚታወጅ ይሆናል፡፡
\s5
\v 4 ለእናንተ ለወዳጆቼ፣ እንዲህ እላችኋለሁ፤ ሥጋን የሚገድሉትን ከዚያ በኋላ ግን ምንም ማድረግ የማይችሉትን አትፍሩ።
\v 5 ማንን መፍራት እንደሚገባችሁ እኔ እነግራችኋለሁ። ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም እሳት የመጣል ሥልጣን ያለውን እርሱን ፍሩት። አዎን፣ እርሱን ፍሩት ብዬ እላችኋለሁ።
\s5
\v 6 ሁለት ድንቢጦች ዝቅተኛ ዋጋ ባላቸው ሳንቲሞች ይሸጡ የለምን? ሆኖም ከእነርሱ አንዷም እንኳ በእግዚአብሔር ፊት የተዘነጋች አይደለችም።
\v 7 ነገር ግን የእናንተ የራሳችሁ ፀጉሮች እንኳ የተቈጠሩ ናቸው። አትፍሩ፣ እናንተ ከብዙ ድንቢጦች የላቀ ዋጋ አላችሁ።
\s5
\v 8 በሰዎች ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ይመሰክርለታል፤
\v 9 በሰዎች ፊት የሚክደኝ ግን በእግዚአብሔር መላእክት ፊት የሚካድ ይሆናል ብዬ እነግራችኋለሁ፡፡
\v 10 በሰው ልጅ ላይ የተቃውሞ ንግግር የተናገረ ማንኛውም ሰው ይቅርታ ያገኛል፣ በመንፈስ ቅዱስ ላይ የስድብ ቃል የሚናገር ግን ይቅርታ አያገኝም፡፡
\s5
\v 11 በምኲራቦች፣ በገዢዎችና በባለ ሥልጣኖች ፊት በሚያቀርቧችሁ ጊዜ ለቀረበባችሁ ክስ እንዴት መልስ መስጠት እንደሚገባችሁ ወይም ምን ማለት እንዳለባችሁ አትጨነቁ፤
\v 12 መንፈስ ቅዱስ በዚያ ወቅት ምን መናገር እንደሚገባችሁ ይነግራችኋልና"
\s5
\v 13 ከሕዝቡም መካከል አንድ ሰው፣ "መምህር ሆይ፣ ወንድሜ ርስት እንዲያካፍለኝ ንገረው" አለ።
\v 14 ኢየሱስም፣ "አንተ ሰው፣ በእናንተ ላይ ዳኛ ወይም አደራዳሪ አድርጎ የሾመኝ ማን ነው?" አለው።
\v 15 ለእነርሱም እንዲህ አላቸው፣ "ስግብግብነት ከሞላባቸው ምኞቶች ራሳችሁን ጠብቁ፣ ምክንያቱም የአንድ ሰው ሕይወት በሀብቱ ብዛት ላይ የተመሠረተ አይደለም"
\s5
\v 16 ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ በማለት ምሳሌ ነገራቸው፤ "የአንድ ሰው ዕርሻ ከፍተኛ ምርት አስገኘለት፤
\v 17 እርሱም፣ 'የተመረተውን እህል የማከማችበት የለኝምና ምን ማድረግ ይገባኛል?' ብሎ በልቡ ዐሰበ።
\v 18 እንዲህም አለ፤ 'እንግዲያውስ እንደዚህ አደርጋለሁ፣ ጐተራዎቼን አፍርሼ በምትኩ ትልልቅ ጐተራዎችን እሠራለሁ፣ የተመረተውን እህልና ሌሎች ንብረቶቼንም ሁሉ አከማችባቸዋለሁ።
\v 19 ነፍሴንም፣ "ነፍሴ ሆይ፣ ለብዙ ዘመን የሚበቃ ብዙ ሀብት ተከማችቶልሻልና አትጨነቂ ብዪ፣ ጠጪ ደስም ይበልሽ እላታለሁ'" አለ።
\s5
\v 20 እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለው፤ "አንተ ሞኝ ሰው፣ ዛሬ ማታ ከአንተ ልትወሰድ ነፍስህ ትፈለጋለች፣ ያዘጋጀሃቸው ነገሮች ታዲያ ለማን ይሆናሉ?"
\v 21 በእግዚአብሔር ፊት ባለ ጠጋ ያልሆነ ለራሱ ግን ሀብትን የሚያከማች ሰው ይህን ይመስላል።
\s5
\v 22 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ "ስለዚህ እላችኋለሁ፣ ምን እንበላለን ብላችሁ ስለ ሕይወታችሁ ወይም ምን እንለብሳለን ብላችሁ ስለ ሰውነታችሁ አትጨነቁ፡፡
\v 23 ምክንያቱም ሕይወት ከምግብ ሰውነትም ከልብስ ይበልጣልና፡፡
\s5
\v 24 የማይዘሩትን ወይም የማያጭዱትን ቁራዎችን ተመልከቱ። መጋዘን ወይም ጐተራ የላቸውም፤ እግዚአብሔር ግን ይመግባቸዋል። ከወፎች ይልቅ እናንተ ምን ያህል የላቀ ግምት ያላችሁ ናችሁ?
\v 25 ከእናንተስ ተጨንቆ በዕድሜው ላይ አንዲት ቀን መጨመር የሚችል ማን ነው?
\v 26 ታዲያ፣ ታናሽ የሆነውን ነገር እንኳ ማድረግ የማትችሉ ከሆነ ስለ ሌላው ጉዳይ ለምን ትጨነቃላችሁ?
\s5
\v 27 እንዴት እንደሚያድጉ አበቦችን ተመልከቱ፡፡ አይሠሩም ወይም አይፈትሉም። ሆኖም፣ ሰሎሞን እንኳ በዚያ ሁሉ ክብሩ ከእነዚህ እንደ አንዱ እንዳልለበሰ እኔ እነግራችኋለሁ።
\v 28 ዛሬ ታይቶ ነገ ወደ ቆሻሻ ማከማቻ እንደሚጣለው ሣር በሜዳ ላይ ያለውን እግዚአብሔር እንደዚህ የሚያለብሰው ከሆነ፣ እምነታችሁ ትንሽ የሆነውን እናንተንማ ምን ያህል የበለጠ አያለብሳችሁም?
\s5
\v 29 የምትበሉትንና የምትጠጡትን በመፈለግ አትጨነቁ።
\v 30 በዓለም ውስጥ ባሉት አገሮች የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ እነዚህን ይፈልጋሉና፣ እናንተም እነዚህን እንደምትፈልጉ አባታችሁ ያውቃል።
\s5
\v 31 ነገር ግን የእርሱን መንግሥት ፈልጉ፣ እነዚህም ነገሮች ይጨመሩላችኋል።
\v 32 አንተ ታናሽ መንጋ፣ መንግሥትን ሊሰጥህ አባትህ እጅግ ደስ ይለዋልና አትፍራ።
\s5
\v 33 ንብረቶቻችሁን ሽጡና ለድኾች ስጡ። በማያረጅ ከረጢት ሌቦች ሊቀርቡትና ብል ሊያጠፋው የማይቻለውን የማያልቀውን ሀብት በሰማይ አከማቹ።
\v 34 ንብረታችሁ ባለበት ልባችሁም በዚያ ይሆናልና።
\s5
\v 35 የሥራ ልብሳችሁን በአጭር ታጥቃችሁ በተጠንቀቅ ቁሙ፣ መብራታችሁም የበራ ይሁን፤
\v 36 በሚመጣበትና በሩን በሚያንኳኳበት ጊዜ ፈጥነው በሩን እንደሚከፍቱለት ጌታቸው ከሠርግ ሲመለስ እንደሚጠባበቁ ሰዎች ሁኑ።
\s5
\v 37 በሚመጣበት ጊዜ ነቅተው ሲጠብቁ ጌታቸው የሚያገኛቸው እነዚያ አገልጋዮች የተመሰገኑ ናቸው። በእርግጥ እላችኋለሁ፣ እርሱም የሥራ ልብሱን ለብሶ ምግብ ለመመገብ እንዲቀመጡ ያደርጋቸውና ወደ እነርሱ መጥቶ ያገለግላቸዋል።
\v 38 ከሌሊቱ በስድስት ሰዓት ወይም በዘጠኝ ሰዓትም እንኳ ቢሆን ሲመጣ ተዘጋጅተው የሚያገኛቸው እነዚያ አገልጋዮች የተመሰገኑ ናቸው።
\s5
\v 39 በተጨማሪ ይህን እወቁ፤ የአንድ ቤት ጌታ ሌባ የሚመጣበትን ሰዓት የሚያውቅ ቢሆን ኖሮ የቤቱ በር እንዲሰበር ባልፈቀደም ነበር፡፡
\v 40 እናንተም እንደዚሁ ዝግጁ ሁኑ፣ ምክንያቱም የሰው ልጅ የሚመጣበትን ሰዓት አታውቁም።"
\s5
\v 41 ጴጥሮስ፣ "ጌታ ሆይ፣ ይህንን ምሳሌ የተናገርኸው ለእኛ ብቻ ነው ወይስ ለሌሎችም ሰዎች ሁሉ ነው?" አለ።
\v 42 ጌታም እንዲህ አለ፣ "ታዲያ ለሌሎቹ አገልጋዮቹ የተመደበላቸውን ምግብ በትክክለኛው ጊዜ ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው የሾመው ታማኝና ብልህ አስተዳዳሪ ማን ነው?
\v 43 ጌታው በሚመጣበት ጊዜ ይህን ሲያደርግ የሚያገኘው ያ አገልጋይ የተመሰገነ ነው"
\v 44 እውነት እላችኋለሁ፣ ባለው ንብረት ሁሉ ላይ ይሾመዋል።
\s5
\v 45 ያ አገልጋይ ግን በልቡ፣ 'የጌታዬ የመመለሻ ወቅት ይዘገያል' ቢልና ወንድና ሴት አገልጋዮችን መደብደብ፣ መብላትና መጠጣት እንዲሁም መስከር ቢጀምር፣
\v 46 የዚያ አገልጋይ ጌታ ባልጠበቀው ቀንና ባላወቀው ሰዓት ይመጣል፣ ይቆራርጠዋል፣ ካልታመኑት ጋርም ይደባልቀዋል።
\s5
\v 47 የጌታውን ፈቃድ ያወቀውና እንደ ፈቃዱ ሆኖ ለመገኘት ያልተዘጋጀውና ፈቃዱን ያልፈጸመው ያ አገልጋይ ከፍተኛ ቅጣት ይቀጣል።
\v 48 ነገር ግን ያላወቀና ቅጣት የሚያስከትልበትን ተግባር የፈጸመ ጥቂት ይቀጣል። ብዙ ከተሰጠው ከማንኛውም ሰው ብዙ ይጠበቅበታል፣ ከፍ ያለ አደራ ከተሰጠውም፣ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል።
\s5
\v 49 የመጣሁት በምድር ላይ እሳት ለመለኰስ ነው፣ ሆኖም አሁኑኑ ተቀጣጥሎ ባገኘው ደስ ባለኝ ነበር።
\v 50 ነገር ግን የምጠመቀው ጥምቀት አለኝ፣ ያንንም ጥምቀት እስከምፈጽመው ምን ያህል በጭንቀት እጠባበቀዋለሁ!
\s5
\v 51 በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት እንደ መጣሁ ታስባላችሁን? እንደዚያ አታስቡ፣ እነግራችኋለሁ፣ የመጣሁት ይልቁኑ መለያየትን ላመጣ ነው፡፡
\v 52 ከእንግዲህ ወዲህ በአንድ ቤት ውስጥ አምስት ሰዎች ቢኖሩ ሦስቱ በሁለቱ ላይ፣ ሁለቱም በሦስቱ ላይ የሚነሡና የሚለያዩ ይሆናሉ፡፡
\v 53 አባት በልጅ ላይ ልጅም በአባት ላይ፤ አማት በምራት ላይ፣ ምራትም በአማት ላይ ይነሡና ይለያያሉ፡፡
\s5
\v 54 ደግሞም ኢየሱስ ለሕዝቡ እንዲህ አላቸው፤ "በምዕራብ በኩል ደመና ሲያንጃብብ በምትመለከቱበት ጊዜ ወዲያውኑ፣ 'ሊያካፋ ነው' ትላላችሁ፣ እንዳላችሁትም ይሆናል።
\v 55 የደቡብ ነፋስም ሲነፍስ፣ 'የሚያቃጥል ሙቀት ሊመጣ ነው' ትላላችሁ፣ እንዳላችሁትም ይሆናል።
\v 56 እናንተ ግብዞች፣ የምድርንና የሰማይን መልክ እንዴት እንደምትተረጒሙ ታውቃላችሁ፣ ታዲያ የአሁኑን ወቅት እንዴት እንደምትተረጒሙ እንዴት አታውቁም?
\s5
\v 57 እናንተ ራሳችሁ ትክክል የሆነውን ለምን አትፈርዱም?
\v 58 ከባላጋራህ ጋር ወደ ከተማው አስተዳዳሪ በምትሄድበት ጊዜ፣ በመንገድ ላይ ቅራኔህን ለመፍታት ጥረት ማድረግ አለብህና፣ ይህን ባታደርግ ዳኛው ለዕለቱ ተረኛ መኰንን አሳልፎ ይሰጥሃል፣ ተረኛው መኰንንም ወደ ወንጀለኛ ማረፊያ ክፍል ያስገባሃል።
\v 59 ዕዳህን ሙሉ በሙሉ እስካልከፈልህ ድረስ ከዚያ በፍጹም እንደማትወጣ እኔ እነግርሃለሁ።"
\s5
\c 13
\cl ምዕራፍ 13
\p
\v 1 በዚያን ጊዜ አንዳንድ ሰዎች ወደ ኢየሱስ መጥተው፣ የገሊላ ሰዎች ለእግዚአብሔር መሥዋዕት በሚያቀርቡበት ጊዜ፣ ጲላጦስ ስለ ገደላቸውና ደማቸውንም ከመሥዋዕታቸው ጋር ስላደባለቀባቸው ሰዎች ነገሩት፡፡
\v 2 ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ "እነዚያ የገሊላ ሰዎች ይህ ሁሉ የደረሰባቸው በዙሪያቸው ካሉት ከሌሎች የገሊላ ሰዎች ይልቅ ኅጢአተኞች ስለ ነበሩ ነውን?
\v 3 አይደለም፤ እናንተም ንስሓ ካልገባችሁ እንዲሁ ትጠፋላችሁ ።
\s5
\v 4 ወይም በሰሊሆም ግንብ ተደርምሶባቸው የሞቱ ዐሥራ ስምንት ሰዎች በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካሉ ሰዎች ይልቅ ኃጢአተኞች ስለ ነበሩ ነውን?
\v 5 አይደለም፤ ሁላችሁም ንስሓ ባትገቡ ትጠፋላችሁ።"
\s5
\v 6 ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ተናገረ፤ "አንድ ሰው በወይን አትክልት ቦታው የበለስ ዛፍ ተከለ፤ ፍሬዋንም ፈልጎ ወደ በለሲቱ መጣ፤ ነገር ግን ምንም ፍሬ አላገኘባትም።
\v 7 እርሱም ለአትክልተኛው እንዲህ አለው፤ "ተመልከት! ሦስት ዓመት ሙሉ ፍሬ ፈልጌ ወደ በለሲቱ መጣሁ፤ ግን ምንም ፍሬ አላገኘሁባትም፡፡ ቊረጣት ስለምን መሬትን ታበላሻለች።"
\s5
\v 8 አትክልተኛውም መልሰና እንዲህ አለ፣ "ለዚህ ዓመት ተዋት ዙሪያዋን ኮትኩቼ ማዳበሪያ አደርግላትና
\v 9 በሚቀጥለው ዓመት ታፈራ ይሆናል፤ ባታፈራ ግን ቊረጣት።"
\s5
\v 10 ኢየሱስም በሰንበት ቀን በአንዱ ምኲራብ እያስተማረ ነበር።
\v 11 ለዐሥራ ስምንት ዓመት ርኩስ መንፈስ ያጐበጣት አንዲት ሴት በዚያ ነበረች፡፡ እርስዋም ከመጒበጧ የተነሣ ቀና ብላ መቆም አትችልም ነበር፡፡
\s5
\v 12 ኢየሱስም ባያት ጊዜ ጠራትና፣ "ተነሺና ከበሽታሽ ተፈወሺ" አላት።
\v 13 በእጁ ዳሰሳት፣ ወዲያውኑም ቀጥ ብላ ቆመች፤ እግዚአብሔርንም
\v 14 አመሰገነች፡፡ የምኲራቡ አለቃ ግን በሰንበት በመፈወሷ ተቈጣና ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ "ከሳምንቱ ቀኖች ሥራ የሚሠራባቸው ስድስት ቀኖች አሉ፤ ሄዳችሁ በእነዚያ ቀኖች ተፈወሱ እንጂ በሰንበት ቀን አይሆንም አላቸው።"
\s5
\v 15 ጌታ እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ "እናንት ግብዞች! በሰንበት ቀን ከእናንተ መካከል በሬውን ወይም አህያውን ከታሰረበት በረት አወጥቶ ውኅ የማያጠጣው ማን ነው?
\v 16 ይህች የአብርሃም ዘር የሆነች ለዐሥራ ስምንት ዓመት በሰይጣን ታስራ የኖረች ሴት በሰንበት ቀን ከበሽታዋ መፈታት አይገባትምን?"
\s5
\v 17 ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች በተናገረ ጊዜ፣ ይቃወሙት የነበሩ ሁሉ አፈሩ፣ ሕዝቡ ግን በተደረገው ድንቅ ነገር ሁሉ ደስ አላቸው።
\s5
\v 18 ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ "የእግዚአብሔር መንግሥት በምን ትመሰላለች? ከምንስ ጋር አነጸጽራታለሁ?
\v 19 አንድ ሰው የሰናፍጭ ዘር በአትክልት ቦታው እንደተከላት ዛፍዋም አድጋ፣ ወፎች በቅርንጫፎችዋ ላይ ጎጆአቸውን ሠርተው ማረፊያ ያደረጉባት ዛፍ ትመሰላለች።"
\s5
\v 20 እንደ ገናም እንዲህ አለ፤ "የእግዚአብሔርን መንግሥት በምን ላነጻጽራት እችላለሁ?
\v 21 የእግዚአብሔር መንግሥት አንዲት ሴት ሊጡን ሁሉ እስኪያቦካ ድረስ በሶሦስት መስፈሪያ ዱቄት ውስጥ የሰወረችውን እርሾ ትመስላለች።"
\s5
\v 22 ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ ሳለ በየከተማውና በየገጠሩ እያስተማረ ያልፍ ነበር፡፡
\v 23 አንድ ሰው፣ "ጌታ ሆይ፤ የሚድኑት ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸውን?" ብሎ ጠየቀው፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤
\v 24 "በጠባብዋ በር ለመግባት ታገሉ፣ ብዙዎች በዚህች በር ሊገቡ ይሞክራሉ ነገር ግን ሊገቡባት አይችሉም።
\s5
\v 25 የቤቱ ጌታ በሩን ይዘጋል፤ እናንተም በደጅ ቆማችሁ፤ አንኳኩታችሁ፣ 'ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤ እንድንገባ ክፈትልን' ትላላችሁ፡፡ እርሱ መልሶ 'ከየት ነው የመጣችሁት? እኔ አላውቃችሁም' ይላችኋል፡፡
\v 26 ከዚያም እናንተ፣ 'ጌታ ሆይ፣ ከአንተ ጋር አብረን በልተናል፤ አብረንም ጠጥተናል፤ በአደባባዮቻችንም አስተምረሃል' ትላላችሁ፡፡
\v 27 እርሱ ግን እንዲህ ይመልሳል፤ 'ከየት እንደ መጣችሁ አላውቅም ፤ እናንተ ዐመፀኞች ከእኔ ራቁ እላችኋለሁ፡፡'
\s5
\v 28 በእግዚአብሔር መንግሥት አብርሃምን፤ይስሐቅን፤ ያዕቆብን፤ ነቢያትንም በምታዩበት ጊዜ፤ እናንተ ግን በውጪ ትጣላላችሁ ከዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል፡፡
\v 29 ብዙ ሰዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ፤ ከሰሜንና ከደቡብ መጥተው በእግዚአብሔር መንግሥት በማዕድ ተቀምጠው ይደሰታሉ፡፡
\v 30 ይህንም እወቁ ኋለኞች ፊተኞች፤ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፡፡"
\s5
\v 31 ከዚያ በኋላ፣ አንዳንድ ፈሪሳውያን ወደ እርሱ ቀርበው፣ "ሄሮድስ ሊገድልህ ይፈልጋልና ከዚህ ወጥተህ ወደ ሌላ ስፍራ ሂድ" አሉት፡፡
\v 32 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ "ሂዱና ለዚያ ቀበሮ፣ 'ዛሬና ነገ አጋንንትን አወጣለሁ፤ በሽታኞችን እፈውሳለሁ፤ በሦስተኛም ቀን ሥራዬን እፈጽማለሁ' ይላል በሉት"
\v 33 ይሁን እንጂ ዛሬና ነገ ከዚያም በኋላ ነቢይ ከኢየሩሳሌም በቀር በሌላ ስፍራ መሞት ስለሌበት ወደ ኢየሩሳሌም መንገዴን መቀጠል አለብኝ" አለ።
\s5
\v 34 አንቺ ኢየሩሳሌም! ኢየሩሳሌም ሆይ! ነቢያትን የምትገድዪ፤ መልእክተኞችሽንም የምትወግሪ ነሽ፡፡ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ ሥር እንደምትሰበስብ እኔም ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ፡፡ እናንተ ግን አልፈለጋችሁም፡፡
\v 35 እነሆ፣ ቤታችሁ ባዶ ሆኖ ቀርቶአል፡፡ እላችኋለሁ፣ እናንተ 'በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነው' እስከምትሉ ድረስ አታዩኝም፡፡"
\s5
\c 14
\cl ምዕራፍ 14
\p
\v 1 በሰንበት ቀን ኢየሱስ ከፈሪሳዊያን አለቆች ወደ እንዱ ቤት እንጀራ ሊበላ በገባ ጊዜ፣ የሚያደርገውን ለማየት በቅርበት ይጠባበቁት ነበር፡፡
\v 2 በዚያም በእጅና በእግር ዕብጠት የሚሠቃይ አንድ ሰው በኢየሱስ ፊት ነበር።
\v 3 ኢየሱስ የአይሁድ ሕግ ዐዋቂዎችንና ፈሪሳውያንን፣ "በሰንበት ቀን መፈወስ በሕግ ይፈቀዳል ወይስ አይፈቀድም? "ብሎ ጠየቃቸው፡፡
\s5
\v 4 እነርሱ ግን ዝም አሉ፡፡ ኢየሱስ የታመመውን ሰው ይዞ ፈወሰውና አሰናበተው፡፡
\v 5 ቀጥሎም ኢየሱስ፣ "ከእናንተ ልጅ ወይም በሬ በሰንበት ቀን በጒድጓድ ውስጥ ቢወድቁ ወዲያውኑ የማያወጣቸው ማን ነው?" አላቸው።
\v 6 እነርሱ ለእነዚህ ነገሮች መልስ መስጠት አልቻሉም፡፡
\s5
\v 7 ኢየሱስ በግብዣ ቦታ የከበሬታ ወንበር ለመያዝ ሲሽቀዳደሙ በተመለከት ጊዜ እንዲህ በማለት አንድ ምሳሌ
\v 8 ነገራቸው፤ "አንድ ሰው ወደ ሰርግ ግብዣ ቢጠራህ በመጀመሪያ በከበሬታ ቦታ አትቀመጥ፣ ምናልባት በዚያ ቦታ የሚቀመጥ ከአንተ ይልቅ ክብር የሚሰጠው ሰው ተጋብዞ ይሆናል፡፡
\v 9 ሁለታችሁንም የጋበዛችሁ ሰው መጥቶ፣ 'ይህን ቦታ ለሌላ ሰው ልቀቅለት' ይልሃል፣ ከዚያም አንተ በሃፍረት ወደ ዝቅተኛ ቦታ ትሄዳለህ፡፡
\s5
\v 10 ነገር ግን ወደ ግብዣ ስትጠራ በዝቅተኛ ቦታ ተቀመጥ፤ አንተን የጋበዘህ ሰው መጥቶ፤ ወዳጄ ሆይ፣ 'ወደ ከፍተኛ ስፍራ መጥተህ ተቀመጥ' ይልሃል፡፡ ከዚያም በተጋባዦቹ ፊት ሁሉ የተከበርህ ትሆናለህ፡፡
\v 11 ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ዝቅ ዝቅ ይላል፡፡ ራሱንም ዝቅ ዝቅ የሚያደርግ ደግሞ ከፍ ከፍ ይላል፡፡
\s5
\v 12 ኢየሱስ ደግሞ ጋባዡን ሰው ደግሞ እንዲህ አለው፤ "የምሳ ወይም የራት ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ መልሰው ይጋብዙኛል በማለት ብድራትን በመፈለግ ወዳጆችህን ወይም ወንድሞችህን ወይም ዘመዶችህን ወይም ሀብታም ጎረቤቶችህን አትጋብዝ፡፡
\s5
\v 13 ነገር ግን ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ድሆችን፣ የአካል ጒዳተኞችን፣ ሽባዎችንና ዐይነ ስውራንን ጥራ፡፡
\v 14 ይህን በማድረግህ እነርሱ መልሰው ሊከፍሉህ ስለማይችሉ፣ የተባረክህ ትሆናለህ፡፡ በጻድቃን ትንሣኤ ቀንም እግዚአብሔር ብድራትህን ይከፍልሃል፡፡
\s5
\v 15 በማዕድ ተቀምጠው ከነበሩት አንዱ ኢየሱስ የተናገራውን ሰምቶ፣ "በእግዚአብሔር መንግሥት ማዕድ ተቀምጦ እንጀራ የሚበላ ሰው የተባረከ ነው" አለው፡፡
\v 16 ኢየሱስ ግን እንዲህ አለው፤ "አንድ ሰው ትልቅ የእራት ግብዣ አዘጋጅቶ ብዙ ሰዎችን ጋበዘ፡፡
\v 17 የግበዣውም ዝግጅት በተጠናቀቀ ጊዜ ወደ እራት ግብዣው ወደ ተጋበዙት ሰዎች፣ 'ሁሉ ተዘጋጅቶአልና ወደ ግብዣው ኑ' ብሎ መልእክተኞችን ላከ፡፡
\s5
\v 18 ነገር ግን እያንዳንዱ ተጋባዥ ከግብዣው ለመቅረት ምክንያት መደርደር ጀመረ፡፡ የመጀመሪያው፤ "መሬት ስለ ገዛሁ ሄጄ ማየት አለብኝባ ይቅርታ አድርግልኝ አለው፡፡
\v 19 ሌላው፣ 'አምስት ጥማድ በሬዎችን ገዝቻለሁ፣ እነርሱን ልፈትናቸው ስለምሄድ፤ ይቅርታ አድርግልኝ' አለው፡፡
\v 20 ሌላኛውም ሰው፣ 'ሚስት አግብቼ ሙሽራ ስልሆንሁ፣ ልመጣ አልችልም' አለ፡፡"
\s5
\v 21 አገልጋዩ ለጌታው እነዚህን ነገሮች ነገረው። ከዚያም የቤቱ ጌታ ተቈጥቶ አገልጋዩን 'ቶሎ ሄደህ በከተማው አውራ ጐዳናዎች ስላች መንገዶች ሁሉ ያሉ ድኾችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ ዐይነ ስውራንን፣ ሽባዎችን ሁሉ ወደዚህ እንዲገቡ ጥራቸው' አለው።
\v 22 አገልጋዩም አለው፤ 'ጌታ ሆይ፤ ያዘዝኸኝን ሁሉ አድርጌአለሁ፤ አሁንም ትርፍ ቦታ አለ።'
\s5
\v 23 ጌታውም አገልጋዩን፣ 'ወደ ጎዳናዎችና ወደ ገጠር መንገዶች ውጣ፤ ቤቴም እንዲሞላ ያገኘሃቸውን ሁሉ እንዲገቡ ግድ በላቸው።
\v 24 "እላችኋለሁ፣ በመጀመሪያ ከተጋበዙት ከእነዚያ ሰዎች መካከል አንድ ሰው እንኳ ከእራቴ አይቀምስም' አለው።
\s5
\v 25 ሕዝብም ከኢየሱስ ጋር አብረው እየሄዱ ሳለ፣ እርሱ ዞር ብሎ እንዲህ አላቸው፤
\v 26 "ማንም ወደ እኔ ሊመጣ የሚወድ አባቱንና እናቱን፣ ሚስቱንና ልጆቹን፣ ወንድሞቹንና እኅቶቹን፣ እንዲያውም የራሱንም ሕይወት ስንኳ ስለ እኔ ብሎ ካልተወ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም፡፡
\v 27 የራሱንም መስቀል ተሸክሞ የማይከተለኝ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም፡፡"
\s5
\v 28 ከእናንተ አንድ ሰው ሕንጻ መሥራት ቢፈልግ ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገውን ገንዘብ በመጀመሪያ ተቀምጦ የማይተምን ማን ነው?
\v 29 መሠረቱን ሠርቶ መደመደም ቢያቅተው በዚያ የሚያልፉት ሁሉ ፣
\v 30 'ይህ ሰው መገንባት ጀምሮ መደምደም አቃተው እያሉ ይዘብቱበታል' ፡፡
\s5
\v 31 ወይም አንድ ንጉሥ ከሌላ ንጉሥ ጋር ሊዋጋ በሚነሣበት ጊዜ ሃያ ሺህ ሰራዊት አስከትቶ የሚመጣበትን በአሥር ሺህ ሰራዊት ለመመከት ተቀምጦ የማይመክር ማን አለ?
\v 32 መመከት የማይችል ከሆነ የሌላው ሰራዊት ገና ከሩቅ ሳለ መልእክተኛ ልኮ ዕርቅ ይጠይቃል፡፡
\v 33 እንዲሁም ከእናንተ ማንም ያለውን ሁሉ የማይተው ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም፡፡
\s5
\v 34 ጨው መልካም ነው፤ ነገር ግን ጨው ጣዕም ካጣ እንዴት ተመልሶ እንደ ገና የጨውነት ጣዕም ሊኖረው ይችላል?
\v 35 ለመሬትም ሆነ ለማዳበሪያነት የማይጠቅም በመሆኑ ወደ ውጪ ይጣላል፡፡ የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ!"
\s5
\c 15
\cl ምዕራፍ 15
\p
\v 1 አንድ ቀንም ቀረጥ ሰብሳቢዎችና ሌሎች ኅጢአተኞች ሁሉ ኢየሱስን ለመስማት መጡ።
\v 2 ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራን፣ "ይህ ሰው ኅጢአተኞችን ይቀበላል፤ ከእነርሱም ጋር ይበላል" በማለት እርስ በርሳቸው አጒረመረሙ።
\s5
\v 3 ኢየሱስ እንዲህ በማለት ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤
\v 4 "ከእናንተ መካከል መቶ በጎች ያሉት ከዚያም ከእነርሱ አንዱ ቢጠፋበት ዘጠና ዘጠኙን በዱር ትቶ የጠፋበትን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልግ የማይሄድ ማንነው?
\v 5 ባገኘውም ጊዜ ከመደሰቱ የተነሣ በጫንቃው ይሸከመዋል።
\s5
\v 6 ወደ ቤቱም ሲመለስ ወዳጆቹንና ጎረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ፣ 'የጠፋብኝን በጌን አግኝቻለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ' ይላቸዋል።
\v 7 እንዲሁም ንስሓ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሓ በሚገባ በአንድ ኅጢአተኛ በሰማይ ታላቅ ደስታ እንደሚሆን እነግራችኋለሁ።
\s5
\v 8 ወይስ ዐሥር የብር ሳንቲሞች ያላት ሴት ከዐሥሩ አንዱ ቢጠፋበት፣ እስከምታገኛው ድረስ መብራት አብርታ፣ ቤቷንም ሁሉ ጠርጋ በትጋት የማትፈልግ ሴት ማን ናት?
\v 9 ባገኘችም ጊዜ ወዳጆቿንና ጎረቤቶቿን ሁሉ በአንድነት ጠርታ፣ 'የጠፋብኝን የብር ሳንቲሜን አግኝቻለሁና ኑ ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ' ትላቸዋለች።
\v 10 "እንደዚሁም ንስሓ በሚገባ በአንድ ኅጢአተኛ በእግዚአብሔር መላአክት ፊት ታላቅ ደስታ እንደሚሆን እነግራችኋለሁ።"
\s5
\v 11 ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ "አንድ ሰው ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤
\v 12 ታናሹ ልጅም አባቱን፣ 'አባቴ ሆይ፣ በኋላ ከሀብትህ ከሚደርሰኝ ድርሻዬን ስጠኝ' አለው። አባቱም ሀብቱን ለሁለቱም ልጆቹ አካፈላቸው።
\s5
\v 13 ከጥቂት ቀናትም በኋላ ታናሹ ልጅ ድርሻውን ይዞ ወደ ሩቅ አገር ሄደ። እዚያም ገንዘቡን ሁሉ አላግባብ እየጨፈረ አባከነ።
\v 14 እርሱም ያለውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ በዚያ አገር ጽኑ ራብ ሆነ። ከዚህም የተነሳ ችግር ላይ ወደቀ።
\s5
\v 15 በዚያም አገር ዐሳማ ያረባ ወደ ነበረ ወደ አንዱ ሰው ዘንድ ሄዶ ተቀጠረ። ሰውዬው ዐሳማዎችን እንዲጠብቅለት አሰማራው።
\v 16 እርሱም የሚበላውን ምግብ የሚሰጠው ስላልነበረ፣ ዐሳማዎቹ ከሚመገቡት መኖ ለመብላት ይፈልግ ነበር።
\s5
\v 17 እርሱም አንድ ቀን ወደ ልቡ ተመልሶ እንዲህ አለ፤ 'ምግብ የሚተርፋቸው የአባቴ ቤት ሠራተኞች ስንት ናቸው?
\v 18 እኔ ግን እዚህ የምበላውን አጥቼ በራብ እሞታለሁ! ተነሥቼ ወደ አባቴ ቤት ልሂድና እንዲህ ልበለው፤ "አባቴ ሆይ፣ በእግዚአብሔርና በአንተ ፊት ኅጢአት አድርጌአለሁ።
\v 19 ከእንግዲህ ልጅህ ተብዬ መጠራት አይገባኝም፤ ከአገልጋዮችህ እንደ አንዱ ቊጠረኝ።"
\s5
\v 20 ስለዚህ ታናሹ ልጅ ተነሥቶ ወደ አባቱ መጣ። ልጁ ገና ከሩቅ እየመጣ ሳለ፤ አባቱ አይቶ በርኅራኄ ሮጦ ተቀበለውና ዐቅፎ ሳመው።
\v 21 ልጁ፣ 'አባቴ ሆይ፣ በእግዚአብሔርና በአንተ ፊት ኅጢአት አድርጌአለሁ። ከእንግዲህ ልጅህ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም' አለ።
\s5
\v 22 አባቱም አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፤ "ፈጥናችሁ ምርጡን ልብስ አምጡና አልብሱት፣ በጣቱ ቀለበት፣ በእግሩም ጫማ አድርጉለት።
\v 23 ከዚያም የሰባውን ወይፈን አምጡና ዕረዱት። እንብላ፤ እንደሰት።
\v 24 ይህ ልጄ ሞቶ ነበረ አሁን በሕይወት አለ፤ ጠፍቶም ነበረ ተገኝቶአል።" ይደሰቱም ጀመር።
\s5
\v 25 ታላቁ ልጅ በዕርሻ ቦታ ነበረ። ወደ ቤትም በተቃረበ ጊዜ፣ ሙዚቃና ጭፈራ ሰማ።
\v 26 ከአገልጋዮቹ አንዱን ጠርቶ፤ ምን እየሆነ እንዳለ ጠየቀው። አገልጋዩም፣ 'ወንድምህ መጥቶአል።
\v 27 በደኅና ስለተመለሰም አባትህ የሰባውን ወይፈን አርዶለታል' አለው።
\s5
\v 28 ታላቁ ልጅ ይህን ሰምቶ ተቈጣ፤ ወደ ቤትም ሊገባ አልፈለገም። አባቱም ወጥቶ እንዲገባ ለመነው።
\v 29 እርሱ ግን አባቱን እንዲህ አለው፤ 'እነሆ፣ ይህን ሁሉ ዘመን እንደ ባሪያ አገለገልሁህ፤ ከትእዛዝህ አንዱንም ሳላጎድል ከአንተ ጋር ኖርሁ፤ ከባልንጀሮቼ ጋር እንድደሰት አንዲት የፍየል ግልገል እንኳ አልሰጠኸኝም፤
\v 30 ነገር ግን ይህ ልጅህ ገንዘብህን ሁሉ ከሴተኛ አዳሪዎች ጋር አባክኖ ሲመጣ፣ የሰባውን ወይፈን አረድህለት።'
\s5
\v 31 አባቱ እንዲህ አለው፤ “ልጄ ሆይ፣ አንተ ሁልጊዜ ከእኔ ጋር ነህ፤ ያለኝ ሁሉ የአንተ ነው።
\v 32 ነገር ግን ይህ ወንድምህ ሞቶ ነበር፤ አሁን በሕይወት አለ፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቶአል። ስለዚህ ልንበላና ልንደሰት ይገባናል።'
\s5
\c 16
\cl ምዕራፍ 16
\p
\v 1 ደግሞም ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፤ "አንድ ሀብታም ሰው ነበረ፤ እርሱም በንብረቱ ሁሉ ላይ የሾመው አስተዳዳሪ ነበረው። ይህ አስተዳዳሪ ሀብተ ያባክናል ተብሎ ለሀብታሙ ተነገረው።
\v 2 ስለዚህ ሀብታሙ ሰው አስተዳዳሪውን ጠርቶ፣ 'ይህ ስለ አንተ የምሰማው ነገር ምንድን ነው? ከዚህ በኋላ ለእኔ አስተዳዳሪ ልትሆን ስለማትችል ንብረቴን አስረክበኝ' አለው።
\s5
\v 3 አስተዳዳሪው እንዲህ ብሎ አሰበ፤ 'እንግዲህ ጌታዬ ከአስተዳደር ሥራዬ ስለሚያሰናብተኝ፣ ምን ባደርግ ይሻለኛል? ዓቅም ስለሌለኝ፣ ከእንግዲህ መሬት በመቈፈር ለመተዳደር አልችልም፤ መለመንም ያሳፍረኛል።
\v 4 ከአስተዳዳሪነት ሥራዬ ስሰናበት፣ ሰዎች በቤታቸው እንዲቀበሉኝ ካሁኑ ምን እንደማደርግ ዐውቃለሁ።'
\s5
\v 5 ከዚያም አስተዳዳሪው የጌታውን ተበዳሪዎች አንድ በአንድ ጠርቶ፣ የመጀመሪያውን ሰው 'ያለብህ ዕዳ ምን ያህል ነው?' ብሎ ጠየቀው።
\v 6 እርሱም፣ 'አንድ መቶ ማድጋ ዘይት አለብኝ' አለ። አስተዳዳሪውም፣ 'በፈረምኸው ውል ላይ ዐምሳ ማድጋ ብለህ ጻፍ' አለው።
\v 7 ሌላውንም፣ 'አንተስ ስንት ዕዳ አለብህ?' ብሎ ጠየቀው። እርሱም፣ 'መቶ ኩንታል ስንዴ አለብኝ' አለ፤ በፈረምኸው ውል ላይ ሰማንያ ኩንታል ብለህ ጻፍ' አለው።
\s5
\v 8 ጌታውም እምነት ያጎደው አስተዳዳሪ ያደረገውን ሰምቶ፤ በብልኅነቱ በመደነቅ እንዲህ አለ፤ 'በዚህ ዓለም እግዚአብሔርን የማያውቁ ሰዎች እግዚአብሔርን ከሚያውቁ ሰዎች ይልቅ በዓለማዊ ሥራቸው ብልኆች ናቸው።
\v 9 ስለዚህ እላችኋለሁ፣ በዓለም ባላችሁ ሀብት ለራሳችሁ ወዳጆችን አፍሩበት፤ ምክንያቱም ሀብታችሁ ባለቀ ጊዜ በዘላለም ቤቶች ይቀበሉአችኋል።
\s5
\v 10 በጥቂቱ የታመነ ሰው በብዙ ላይ የታመነ ይሆናል፤ በጥቂቱ የሚያምፅ በብዙም ዐመፀኛ ይሆናል።
\v 11 ስለዚህ በዚህ ዓለም ሀብት ካልታመናችሁ እውነተኛውን ሀብትማ ማን አምኖ ይሰጣችኋል?
\v 12 እንደዚሁም በሌላ ሰው ሀብት ካልታመናችሁ የራሳችሁን ማን ይሰጣችኋል?
\s5
\v 13 ሁለት ጌቶችን ማገልገል የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ይተዋል፤ ሌላውን ይወዳል፤ አለበለዚያም ለአንዱ ራሱን የሰጠ ይሆናል፤ሌላውን ደግሞ ይንቃል። ስለሆነም ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።
\s5
\v 14 ገንዘብን የሚወዱ ፈሪሳውያን ይህን ሁሉ ሰምተው፣ በኢየሱስ ላይ አፌዙበት።
\v 15 እርሱም እንዲህ አላቸው፤ "እናንተ በሰው ፊት ራሳችሁን እንደ ጻድቃን ትቈጥራላችሁ፣ እግዚአብሔር ግን ልባችሁን ያውቃል። በሰዎች ፊት የከበረ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው።"
\s5
\v 16 ሕግና ነቢያት እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ ሲሠራባቸው ኖረዋል። ከዚያ በኋላ ግን የእግዚአብሔር መንግሥት ወንጌል ተሰብኳል። ሰው ሁሉ ወደዚህ ለመግባት ይጋፋል።
\v 17 ነገር ግን ከሕግ አንድ ነጥብ ዋጋ ከሚያጣ ሰማይና ምድር ቢያልፍ ይቀላል።
\s5
\v 18 ማንም ሚስቱን ፈትቶ ሌላይቱን የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል፤ ከባሏ የተፋታችውንም የሚያገባ ያመነዝራል።
\s5
\v 19 ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ "ሐምራዊና ቀጭን የሐር ልብስ የለበሰ በየቀኑም በምቾትና በደስታ የሚኖር ሀብታም ሰው ነበረ።
\v 20 ሰውነቱ በቊስል የተወረረ አልዓዛር የሚባል ለማኝም በሀብታሙ ሰው ደጅ ይተኛ ነበር።
\v 21 አልዓዛርም ከሀብታሙ ማዕድ የተረፈውን ፍርፋሪ ሊመገብ ይመኝ ነበር። ውሾች እንኳ እየመጡ ቊስሉን ይልሱ ነበር።
\s5
\v 22 ከጊዜ በኋላ ለማኙ ሞተ፤መላእክትም መጥተው ወደ አብርሃም አጠገብ ወሰዱት። ሀብታሙም ሞተ፤ ተቀበረም።
\v 23 ሀብታሙ በሲኦል እየተሠቃየ ሳለ፣ ቀና ብሎ አብርሃም አልዓዛርን በዕቅፉ ይዞት አየ።
\s5
\v 24 እርሱም፣ 'አብርሃም አባት ሆይ፣ ራራልኝ በዚህ ነበልባል እየተሠቃየሁ ስለ ሆነ፣ አልዓዛር የጣቱን ጫፍ በውሃ ነክሮ ምላሴን እንዲያቀዘቅዝልኝ እባክህ አልዓዛርን' ላክልኝ ብሎ ጮኸ።
\s5
\v 25 አብርሃም ግን እንዲህ አለው፤ "ልጄ ሆይ፣ አንተ በምድር የሕይወት ዘመንህ መልካም ነገሮችን እንደተቀበልህና በደስታ እንደ ኖርህ፤ አልዓዛርም ክፉ ነገሮችን ሲቀበል እንደ ኖረ አስታውስ። አሁን ግን አልዓዛር እዚህ በምቾት ሲኖር፣ አንተ በሥቃይ ላይ ትገኛለህ።
\v 26 ከሁሉ በላይ ከዚህ ወደ እናንተ ለማለፍ የሚፈልጉ እንዳይሻገሩ እዚያ ያሉትም ወደ እኛ እንዳይመጡ በእኛና በእናንተ መካከል ትልቅ ገደል አለ።'
\s5
\v 27 ሀብታሙ ሰው እንዲህ አለ፤ 'አባት ሆይ፣ እንግዲያውስ አልዓዛርን ወደ አባቴ ቤተ ሰብ እንድትሰደው እለምንሃለሁ፤
\v 28 ምክንያቱም አምስት ወንድሞች አሉኝና እነርሱ ወደዚህ ሥቃይ ቦታ እንዳይመጡ ያስጠንቅቃቸው።'
\s5
\v 29 አብርሃም ግን፣ 'ወንድሞችህ ሙሴና ነቢያት አሏቸው፤ እነርሱንም ይስሙአቸው' ብሎ መለሰለት። ነገር ግን
\v 30 ሀብታሙ ሰው፣ 'አብርሃም አባት ሆይ፣ እንደዚህ አይደለም፤ አንድ ሰው ከሙታን ተነሥቶ ሄዶ ቢነግራቸው ንስሓ ይገባሉ' አለ።
\v 31 አብርሃም ግን ሙሴንና ነቢያትን የማይሰሙ ከሆነ፣ አንድ ሰው ከሙታን ተነሥቶ ቢነግራቸው እንኳ አያምኑም' አለው።
\s5
\c 17
\cl ምዕራፍ 17
\p
\v 1 ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፤ "ወደ ኅጢአት የሚያመሩ ነገሮች መምጣታቸው የማይቀር ነው። ነገር ግን ለኅጢአት ምክንያት ለሚሆነው ሰው ወዮለት።
\v 2 በእምነት ደካማ ከሆኑት ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ከማስናከል ይልቅ ትልቅ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይሻለዋል።
\s5
\v 3 ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ወንድምህ ቢበድልህ ገሥጸው፤ ተመልሶ ከተጸጸተ ይቅር በለው፤ በቀንም ሰባት ጊዜ እንኳ ቢበድልህና ሰባት ጊዜ ተመላልሶ፤
\v 4 'ስለ ሠራሁት ኅጢአት ተጸጸትሁ' እያለ ወደ አንተ ቢመለስ ይቅር ልትለው ይገባል።"
\s5
\v 5 ሐዋርያት ጌታን፣ "እምነት ጨምርልን" አሉት።
\v 6 ጌታም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፣ "የሰናፍጭን ዘር ያህል እምነት ቢኖራችሁ፤ ይህን የሾላ ዛፍ፣ 'ከመሬት ተነቅለህ ወደ ባሕር ተተከል' ብትሉት ይታዘዝላችኋል።
\s5
\v 7 "በዕርሻ ወይም በበጎች እረኝነት የተሰማራ አገልጋይ ካላችሁ፣ አገልጋዩ ከሥራ ደክሞ ሲመለስ፣ ወዲያውኑ "ና ተቀመጥና እራትህን ብላ የሚለው ከእናንተ ማን ነው?"
\v 8 "እራቴን አዘጋጅልኝ፤ እስክበላና እስክጠጣም ወገብህን ታጥቀህ ቆመህ አስተናግደኝ፤ ከዚያ በኋላ አንተ ደግሞ ትበላለህ ትጠጣለህም አይለውምን?"
\s5
\v 9 ታዲያ አገልጋዩ የታዘዘውን ስለ ፈጸመ ጌታው ያመሰግነዋልን?
\v 10 እንዲሁም እናንተም የታዘዛችሁትን ሁሉ ከፈጸማችሁ በኋላ የማንጠቅም አገልጋዮች ነን፤ 'የፈጸምነውም የታዘዝንውን ግዳጃችንን ብቻ ነው' ማለት አለባችሁ።"
\s5
\v 11 ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄዱ ሳለ፣ ሰማርያንና ገሊላን በሚያዋስነው መንገድ ያልፉ ነበር።
\v 12 ኢየሱስም ወደ አንዲት መንደር በገባ ጊዜ ዐሥር ለምጻሞች አገኙት። እነርሱም ከእርሱ ርቀው ቆሙና
\v 13 ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፣ "ኢየሱስ ሆይ፣ መምህር ሆይ፣ እባክህ ማረን" እያሉ ጮኹ።
\s5
\v 14 ኢየሱስ ባያቸው ጊዜ፣ "ሂዱና ራሳችሁን ለካህናት አሳዩ" አላቸው። እነርሱም እየሄዱ ሳሉ፣ ከለምጻቸው ነጹ።
\v 15 ከእነርሱ አንዱ ከለምጹ መፈወሱን ባየ ጊዜ፣ ጮክ ብሎ እግዚአብሔርን እያከበረ ተመለሰ።
\v 16 በኢየሱስ እግር ሥር በግንባሩ ተደፍቶ አመሰገነው። እርሱም የሰማርያ ሰው ነበር።
\s5
\v 17 ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ፣ "ዐሥሩም ለምጻሞች ተፈውሰው አልነበረምን? ታዲያ ዘጠኙ የት አሉ?
\v 18 ከዚህ ከባዕድ ሰው በቀር እግዚአብርሔን ለማመስገን ተመልሶ የመጣ ሌላ የለምን?"
\v 19 ኢየሱስ ሰውየውን፣ "ተነሥና ሂድ እምነትህ አድኖሃል" አለው።
\s5
\v 20 ፈሪሳውያን ኢየሱስን፣ "የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ ትመጣለች?" ብለው ለጠየቁት ጥያቄ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ "የእግዚአብሔር መንግሥት የምትታይ አይደለችም።" ወይም'እነሆ፣ እዚህ ናት'
\v 21 ወይም 'እነሆ፣እዚያ ናት' የምትባል አይደለችም። ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናት።"
\s5
\v 22 ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፤" ከሰው ልጅ ቀኖች አንዱን ለማየት የምትናፍቁበት ቀን ይመጣል። ነገር ግን አታዩትም።
\v 23 ሰዎች፣ 'እነሆ፣ ክርስቶስ እዚህ ነው! ወይም እዚያ ነው!' ይሉአችኋል። ነገር ግን እነርሱን ሰምታችሁ አትፈልጉ፤ አትከተሉአቸውም።
\v 24 መብረቅ በሰማይ ላይ ሲበርቅ ከዳር እስከ ዳር እንደሚያበራ፣ የሰው ልጅም በሚመጣበት ቀን እንዲሁ ይሆናል።
\s5
\v 25 ነገር ግን ይህ ከመሆኑ በፊት የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል ይገባል። በዚህ ዘመን ሰዎችም ሊናቅና ሊነቀፍ ግድ ነው።
\v 26 በኖኅ ዘመን እንደሆነው፣ በሰው ልጅ ዘመንም እንዲሁ ይሆናል።
\v 27 ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ ሰዎች ሲበሉና ሲጠጡ፣ ሲያገቡና ሲጋቡና ነበር። ነገር ግን በዚያን ጊዜ የጥፋት ውሃ መጥቶ ሁሉንም አጠፋቸው።
\s5
\v 28 እንደዚሁም በሎጥ ዘመን ሰዎች ይበሉ፣ ይጠጡ፣ ይሸጡ ይገዙ፣ አትክልት ይተክሉና ቤትም ይሠሩ እንደ ነበረ ይሆናል።
\v 29 ሎጥ ከሰዶም በወጣበት ቀን ግን እሳትና ዲን ከሰማይ ዘንቦ ሁሉንም አጠፋ።
\s5
\v 30 የሰው ልጅ በሚገለጥበት ቀንም እንዲሁ ይሆናል።
\v 31 በዚያ ቀን በቤቱ ጣሪያ ላይ ያለ ሰው በቤቱ ውስጥ ያለውን ዕቃ ለመውሰድ አይውረድ። በዕርሻም ቦታ ያለ ሰው ወደ ቤቱ አይመለስ።
\s5
\v 32 የሎጥን ሚስት አስታውሱአት። ሕይወቱን ሊያድን በራሱ መንገድ ለመሄድ የሚፈልግ ሁሉ ያጣታል።
\v 33 ነገር ግን ሕይወቱን ለጌታ አሳልፎ የሚሰጥ ሁሉ ያድናታል።
\s5
\v 34 ይህን እላችሏለሁ፣ "በዚያች ሌሊት ሁለት ሰዎች በአንድ ዐልጋ ላይ ይተኛሉ።
\v 35 ከእነርሱም አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላው ይቀራል። እንዲሁም ሁለት ሴቶች በአንድ ቦታ አብረው ይፈጫሉ፤
\v 36 አንድዋ ትወሰዳለች ሌላዋ ትቀራለች። ሁለት ሰዎች በአንድ ዕርሻ ቦታ ያርሳሉ፤አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላው ይቀራል።"
\s5
\v 37 ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስን፦ 'ጌታ ሆይ፤ ወዴት?' ብለው ጠየቁት። እርሱም፦ "በድን ባለበት አሞራዎች ይሰበባሉ።" ሲል መለሰላቸው።
\s5
\c 18
\cl ምዕራፍ 18
\p
\v 1 ከዚያም ኢየሱስ ሳይታክቱ ዘወትር መጸለይ እንደሚገባቸው እንዲህ ሲል አንድ ምሳሌ ነገራቸው፤
\v 2 "በአንድ ከተማ እግዚአብሔርን የማይፈራ፤ ሰውንም የማያከብር አንድ ዳኛ ነበረ።
\s5
\v 3 አንዲት ባል የሞተባት ሴትም በዚያ ከተማ ነበረች። እርስዋም ዘወትር ወደ ዳኛው እየመጣች፣ 'ከባላጋራዬ ጋር ስላለኝ ክርክር ፍረድልኝ' ትለው ነበር።
\v 4 ዳኛውም ለረጅም ጊዜ ሊረዳት ፈቃደኛ አልነበረም። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን ወደ ልቡ ተመልሶ እንዲህ ብሎ አሰበ፤
\v 5 'ምንም እንኳ እግዚአብሔርን ባልፈራ፣ ሰውንም ባላከብር፣ ይህች ባል የሞተባት ሴት አዘውትራ በመምጣት እንዳታታክተኝ እፈርድላታለሁ።' "
\s5
\v 6 ከዚያም ጌታ እንዲህ አለ፤ "ቅንነት የሌለው ዳኛ የሚናገረውን ስሙ።
\v 7 ታዲያ እግዚአብሔር ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹት ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን?
\v 8 ደግሞስ አይታገሣቸውምን? እላችኋለሁ በቶሎ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆን?"
\s5
\v 9 ከዚያም ኢየሱስ ጻድቃን እንደ ሆኑ በራሳቸው ለሚመኩና ሌሎችንም ለሚንቁ ይህን ምሳሌ ተናገረ፤
\v 10 "ሁለት ሰዎች ለመጸለይ ወደ ቤተ መቅደስ ሄዱ፤ አንዱ ፈሪሳዊ ሲሆን፣ ሌላው ቀራጭ ነበረ።
\s5
\v 11 ፈሪሳዊው ቆሞ እንዲህ በማለት ስለ ራሱ ጸለየ፤ 'እግዚአብሔር ሆይ፣ እኔ እንደ ሌሎች ሰዎች ቀማኛ፣ ዐመፀኛ፣ አመንዝራ፣ ወይም እንደዚህ ቀራጭ እንኳ ስላልሆንሁ አመሰግንሃለሁ።
\v 12 በሳምንት ሁለት ጊዜ እጾማለሁ፣ ከማገኘውም ሁሉ ዐሥራት አወጣለሁ።'
\s5
\v 13 "ቀራጩ ግን ከርቀት ቆሞ ዐይኑን ወደ ሰማይ ሳያነሣ ደረቱን እየመታ፣ 'አምላኬ ሆይ፣ እኔን ኅጢአተኛውን ማረኝ!' ይል ነበር። እላችኋለሁ፣
\v 14 "ከሌላው ይልቅ ጻድቅ ሆኖ ይህ ሰው ወደ ቤቱ ተመለሰ ፤ ምክንያቱም ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፤ ራሱን የሚያዋርድ ከፍ ከፍ ይላል።"
\s5
\v 15 እንዲዳስሳቸው ሰዎች ልጆቻቸውን ወደ እርሱ ያመጡ ነበር። ደቀ መዛሙርቱ ይህን ባዩ ጊዜ ገሠጹአቸው።
\v 16 ኢየሱስ ግን ሕፃናትን ወደ እርሱ ጠራቸውና፣ "ሕፃናት ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተውአቸው አትከልክሏቸውም። የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ እነዚህ ላሉት ናትና።
\v 17 እውነት እላችኋለሁ፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን በየዋህነት ያልተቀበላት ፈጽሞ አይገባባትም" አለው።
\s5
\v 18 ከአለቆች አንዱ ኢየሱስን፣ "ቸር መምህር ሆይ፣ የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት ምን ማድረግ ይገባኛል?" ብሎ ጠየቀው።
\v 19 ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ "ለምን ቸር ብለህ ትጠራኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በስቀር ቸር የለም።
\v 20 ትእዛዛትን ሁሉ ታውቃቸዋለህ፤ እነርሱም፣ 'አትግደል፣ አታመንዝር፣ አትስረቅ፣ በሐሰት አትመስክር፣ እናትህንና አባትህን አክብር የሚሉ ናቸው።"
\v 21 አለቃውም ፣ "እነዚህንማ ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአቸዋለሁ።"
\s5
\v 22 ኢየሱስ ይህን በሰማ ጊዜ፣ ሰውየውን፣ "እንግዲያውስ ገና አንድ ነገር ማድረግ ይቀርሃል፤ ያለህን ሁሉ ሸጠህ ገንዘቡን ለድኾች ስጣቸው፤ በመንግሥተ ሰማያት ሀብት ይኖርሃል። ከዚያም በኋላ መጥተህ ተከተለኝ" አለው።
\v 23 ሀብታሙ ሰውዬ ግን በጣም ባለጠጋ ስለ ነበረ፣ ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ።
\s5
\v 24 ከዚያም ኢየሱስ ሰውየው እንዳዘነ አይቶ፣ "ሀብታም ለሆኑ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት አስቸጋሪ ነው!
\v 25 ሀብታም ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል" አለ።
\s5
\v 26 የሰሙትም ሰዎች፣ "እንግዲያውስ ማን ሊድን ይችላል?" አሉ።
\v 27 ኢየሱስ፣ "በሰው ዘንድ የማይቻል ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል" ብሎ መለሰ።
\s5
\v 28 ጴጥሮስ፣ "እነሆ፣ እኛ ያለንን ሁሉ ትተን ተከትለንሃል" አለው።
\v 29 ከዚያም ኢየሱስ፣ "እውነት እላችኋለሁ፣ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ብሎ ቤቱን ወይም ሚስቱን፣ ወይም ወንድሞቹን፣ ወይም ወላጆቹን ወይም ልጆቹን የተወ
\v 30 በዚህ ዓለም ብዙ ዕጥፍ በሚመጣውም ዓለም የዘላለምን ሕይወት የማያገኝ ማንም የለም" አላቸው።
\s5
\v 31 ኢየሱስ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ከሰበሰበ በኋላ እንዲህ አላቸው፤ "አሁን ወደ ኢየሩሳሌም መሄዳችን ነው፤ ስለ ሰው ልጅ በነቢያት አስቀድሞ የተነገሩት ሁሉ ይፈጸማሉ።
\v 32 እርሱ ለአሕዛብ ተላልፎ ይሰጣል፤ እነርሱም ያላግጡበታል፤ ያዋርዱታል፤ ይተፉበታልም።
\v 33 ከገረፉትም በኋላ ይገድሉታል፤ በሦስተኛውም ቀን ከሞት ይነሣል።"
\s5
\v 34 ደቀ መዛሙርቱ ግን ከዚህ ሁሉ ከተናገራቸው ነገሮች አንዱንም አልተረዱም። ይህ ቃልም ተሰውሮባቸው ነበር፤ ስለተባሉትም ነገሮች ምንም አልተረዱም።
\s5
\v 35 ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ በቀረበ ጊዜ፣ አንድ ዐይነ ስውር ምጽዋት እየለመነ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን ነበር፤
\v 36 ሕዝብ ሲያልፉ ሰምቶም እየሆነ የነበረውን ነገር ጠየቀ።
\v 37 እነርሱም፣ የናዝሬቱ ኢየሱስ በዚህ በኩል እያለፈ መሆኑን ነገሩት።
\s5
\v 38 ስለዚህ ዐይነ ስውሩ፣ "የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ፣ እባክህ ማረኝ" እያለ ጮኸ።
\v 39 እፊት እፊት ይሄዱ የነበሩት፣ "ዝም በል!" ብለው ዐይነ ስውሩን ገሠጹት። እርሱ ግን ድምፁን የበለጠ ከፍ አድርጎ፣ "የዳዊት ልጅ ሆይ፣ እባክህ ማረኝ" ብሎ ጮኸ።
\s5
\v 40 ኢየሱስ ቆሞ ሰውየውን ወደ እርሱ እንዲያመጡት አዘዛቸው ። ከዚያም ዐይነ ስውሩ ወደ እርሱ በቀረበ ጊዜ፣ ኢየሱስ፣
\v 41 "ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?" ብሎ ጠየቀው። "ጌታ ሆይ፣ ማየት እፈልጋለሁ" አለ።
\s5
\v 42 ኢየሱስም፣ "እይ። እምነትህም አድኖሃል" አለው። ዐይነ ስውሩም ወዲያውኑ ማየት ቻለ።
\v 43 እግዚአብሔርን እያመሰገነ ኢየሱስን ተከተለ። ሕዝቡ ሁሉ ይህን አይተው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
\s5
\c 19
\cl ምዕራፍ 19
\p
\v 1 ኢየሱስ ኢያሪኮ ከተማ ገብቶ እያለፈ ሳለ፣
\v 2 ዘኬዎስ የሚባል አንድ የቀራጮች አለቃና ሀብታም ሰው ወዳለበት ስፍራ ደረሰ።
\s5
\v 3 ዘኬዎስ ኢየሱስ የትኛው እንደ ሆነ ለማየት ይሞክር ነበር፣
\v 4 ነገር ግን አጭር ስለ ነበረ፣ ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ አሻግሮ ማየት አልቻለም ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ በዚያ መንገድ ያልፍ ስለነበር፣ ከሕዝቡ ቀድሞ ሮጠና ሊያየው በእንድ ሾላ ዛፍ ላይ ወጣ።
\s5
\v 5 ኢየሱስ ወደ ስፍራው በደረሰ ጊዜ፣ ቀና ብሎ ተመለከተና፣ “ዘኬዎስ ሆይ፣ ዛሬ ወደ ቤትህ መሄድ እፈልጋለሁና ቶሎ ውረድ” አለው።
\v 6 ስለዚህ ዘኬዎስ በፍጥነት ወርዶ በደስታ በቤቱ ተቀበለው።
\v 7 ይህን የተመለከቱት ሰዎች ሁሉ፣ “በኃጢአተኛ ሰው ቤት ገባ” በማለት አጒረመረሙ።
\s5
\v 8 ዘኬዎስ ተነሥቶ ቆመና ጌታን፣ “ጌታ ሆይ፣ የሀብቴን ግማሽ ለድሆች እሰጣለሁ፣ ያታለልሁት ሰው ካለ፣ የወሰድሁበትን አራት ዕጥፍ እመልስለታለሁ” አለው።
\v 9 ኢየሱስ እንዲህ አለው፣ "ዛሬ ድነት ለዚህ ቤት መጥቷል። ምክንያቱም፣ እርሱ ደግሞ የአብርሃም ልጅ ነው።
\v 10 የሰው ልጅ የመጣው የጠፉትን ሰዎች ሊፈልግና ሊያድን ነውና” አለ።
\s5
\v 11 እነርሱ እነዚህን ነገሮች እንደ ሰሙ፣ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም እየተቃረበ ስለ ነበር ሕዝቡ የእግዚአብሔር መንግሥት ወዲያው የሚገለጥ መሰላቸው።
\v 12 ስለዚህ ኢየሱስ ንግግሩን በምሳሌ በመቀጠል እንዲህ አለ፣ “አንድ መኰንን የመንግሥት ሹመት ተቀብሎ ሊመጣ ወደ ሩቅ አገር ሄዶ ነበር።
\s5
\v 13 ከዚያም፣ ከአገልጋዮቹ ዐሥሩን ጠርቶ ዐሥር ምናን ሰጣቸውና፣ “እስክመጣ ድረስ ይህን ነግዱበት” አላቸው።
\v 14 ነገር ግን የአገሩ ሰዎች ይጠሉት ስለ ነበር፣ 'ይህ ሰው ተመልሶ በእኛ ላይ ገዥ እንዲሆን አንፈልግም' በማለት ተወካዮቻቸውን ከኋላው ላኩበት።
\v 15 መኰንኑም ሹመቱን ተቀብሎ ሲመለስ፣ ነግደው ያተረፉትን ትርፍ ለመተሳሰብ ገንዘቡን የሰጣቸው አገልጋዮቹ እንዲጠሩለት አዘዘ።
\s5
\v 16 የመጀመሪያው አገልጋይ ወደፊቱ ቀረበና፣ 'ጌታ ሆይ፣ ምናንህ ተጨማሪ ዐሥር ምናን አትርፎልሃል' አለው።
\v 17 ጌታውም፣ “ደግ አድርገሃል፣ አንተ ታታሪ አገልጋይ። በጥቂቱ ስለ ታመንህ፣ በዐሥር ከተሞች ላይ ገዥ ትሆናለህ' አለው።
\s5
\v 18 ሁለተኛውም ቀርቦ፣ 'ጌታ ሆይ፣ ምናንህ ዐምስት አትርፏል' አለው።
\v 19 ጌታውም፣ 'በዐምስት ከተሞች ላይ ገዥ ሁን' አለው።
\s5
\v 20 ሌላኛውም መጣና፣ 'ጌታ ሆይ፣ በደንብ አድርጌ በጨርቅ ጠቅለዬ ያስቀመጥሁት ምናንህ ይኸውልህ፣
\v 21 ይህን ያደረግሁት አንተ ጨካኝ ሰው መሆንህን ስላወቅሁ ፈርቼ ነው። አንተ ያላስቀመጥኸውን የምትጠይቅ ያልዘራኸውን የምታጭድ ነህ' አለው።
\s5
\v 22 ጌታውም፣ እንዲህ አለው፤ 'አንተ ክፉ አገልጋይ፣ በአፍህ ቃል እፈርድብሃለሁ። ካላስቀመጥሁበት የምፈልግ፣ ካልዘራሁበት የማጭድ ጨካኝ ሰው መሆኔን ያወቅህ ከሆነ፣
\v 23 ታዲያ ስመለስ ገንዘቤን ከነትርፉ እንዳገኝ ለምን በባንክ አላስቀመጥኸውም?”
\s5
\v 24 ከዚያም ጌታው በዚያ ለቆሙት ሰዎች፣ “ምናኑን ውሰዱበት፣ ዐሥር ላለውም ጨምሩለት' አላቸው፤
\v 25 እነርሱም፣ 'ጌታ ሆይ፣ አስር ምናን አለው እኮ' አሉት።
\s5
\v 26 ጌትየውም፣ 'ላለው ይጨምርለታል፣ ከሌለው ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።
\v 27 በእነርሱ ላይ ገዥ እንዳልሆን የተቃወሙትን እነዚህን ጠላቶቼን ግን አምጡና በፊቴ ግደሏቸው' አለ።
\s5
\v 28 ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ከተናገረ በኋላ፣ ፊቱን ወደ ኢየሩሳሌም በማቅናት መንገዱን ቀጠለ።
\s5
\v 29 ደብረ ዘይት በሚባለው ተራራ አጠገብ ወደሚገኝ ቤተ ፋጌና ቢታንያ በተቃረበ ጊዜ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን
\v 30 እንዲህ ብሎ ላካቸው፤ "ወደሚቀጥለው መንደር ሂዱ። ስትገቡ፣ ማንም ያልተቀመጠበትን አንድ የአህያ ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ። ፍቱትና አምጡልኝ።
\v 31 ማንም፣ 'ለምን ትፈቱታላችሁ?' ብሎ ቢጠይቃችሁ፣ 'ለጌታ ያስፈልገዋል' በሉት" አላቸው።
\s5
\v 32 የተላኩትም ወደ ስፍራው በደረሱ ጊዜ፣ ኢየሱስ እንደ ነገራቸው፣ የአህያውን ውርንጫ ታስሮ አገኙት።
\v 33 ውርንጫውን እየፈቱ እያለ ባለቤቶቹ፣ 'ውርንጫውን ለምን ትፈቱታላችሁ?' አሉ።
\v 34 እነርሱም፣ “ለጌታ ያስፈልገዋል” ብለው መለሱለት።
\v 35 ወደ ኢየሱስ አመጡትና ልብሳቸውን በውርንጫው ጀርባ ላይ አንጥፈው ኢየሱስ እንዲቀመጥበት አደረጉ።
\v 36 ኢየሱስ በሚሄድበት ጊዜ፣ ከፊቱ ባለው መንገድ ላይ ልብሶቻቸውን ያነጥፉለት ነበር።
\s5
\v 37 ከደብረ ዘይት ተራራ ቁልቁል ወደሚወስደው መንገድ በቀረበ ጊዜ፣ ቊጥራቸው ብዙ የሆነ ደቀ መዛሙርት፣ ስላዩአቸው ድንቅ ነገሮች ሁሉ ደስ እያላቸው፣ “በጌታ ስም የሚመጣ ንጉሥ የተባረከ ነው! በሰማይ ሰላም፣
\v 38 ክብርም በአርያም ይሁንለት!” እያሉ በከፍተኛ ድምፅ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
\s5
\v 39 በሕዝቡ መካከል የነበሩ አንዳንድ ፈሪሳውያን፣ “መምህር ሆይ፣ ደቀ መዛሙርትህን ገሥጻቸው” አሉ።
\v 40 ኢየሱስም፣ “ልንገራችሁ፣ እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮችም እንኳ ይጮኻሉ” አላቸው።
\s5
\v 41 ኢየሱስ ወደ ከተማይቱ በተቃረበ ጊዜ እንዲህ በማለት አለቀሰላት፤
\v 42 “ለአንቺ ሰላም የሚያመጣልሽን ነገር ምነው ዛሬ ባወቅሽ ኖሮ! አሁን ግን ከዐይንሽ ተሰውሮብሻል።
\s5
\v 43 ጠላቶችሽ ዙሪያሽን ቅጥር ሠርተው የሚከቡሽና ከሁሉም አቅጣጫ የሚያስጨንቁሽ ጊዜያት ይመጣሉ።
\v 44 አንቺንና ልጆችሽንም በምድር ላይ ይፈጠፍጣሉ። እነርሱም ድንጋይ በድንጋይ ላይ እንደተነባበረ አይተዉም፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሊያድንሽ መፈለጉን አላወቅሽምና።”
\s5
\v 45 ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገባና በዚያ ይሸጡ የነበሩትን ያባርራቸው ጀመር፣
\v 46 ከዚያም፣ “የአባቴ ቤት 'የጸሎት ቤት ይሆናል' ተብሎ ተጽፏል፣ እናንተ ግን የወንበዴዎች መሸሸጊያ አደረጋችሁት” አለ።
\s5
\v 47 ስለዚህ ኢየሱስ በየዕለቱ በቤተ መቅደስ ያስተምር ነበር። ታዲያ የካህናት አለቆች፣ የሕግ መምህራንና የሕዝቡ መሪዎች ሊገድሉት ፈለጉ።
\v 48 ነገር ግን ሕዝቡ ከልብ ያደምጡት ስለ ነበር መንገድ አላገኙም።
\s5
\c 20
\cl ምዕራፍ 20
\p
\v 1 አንድ ቀን እንዲህ ሆነ፣ ኢየሱስ ሕዝቡን በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያስተምርና ወንጌልን ይሰብክ በነበረ ጊዜ፣ የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ከሽማግሌዎች ጋር ወደ እርሱ መጡ።
\v 2 "እነዚህን ነገሮች የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? ወይም ይህን ሥልጣን የሰጠህ እርሱ ማን ነው?" አሉት።
\s5
\v 3 እርሱም እንዲህ በማለት መለሰላቸው፤ "እኔም አንድ ጥያቄ እጠይቃችኋለሁ፣ እስቲ መልሱልኝ።
\v 4 የዮሐንስ ጥምቀት ከሰማይ ነበር ወይስ ከሰዎች?"
\s5
\v 5 እርስ በርሳቸው ተመካከሩና፣ "'ከሰማይ ነው ብንል፣ 'ታዲያ ለምን አላመናችሁትም ይለናል።
\v 6 ነገር ግን 'ከሰው ነው ብንል' ሕዝቡ ዮሐንስን ነቢይ አድርገው ስለሚቆጥሩ ይወግሩናል" አሉ።
\s5
\v 7 ስለዚህ ከየት እንደ ሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት።
\v 8 ኢየሱስ፣ "እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ አልነግራችሁም" አላቸው።
\s5
\v 9 ለሕዝቡ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፣ "አንድ ሰው ያዘጋጀውን የወይን ዕርሻ ለወይን ገበሬዎች አከራይቶ ረጅም ጊዜ ሊቆይ ወደ ሌላ አገር ሄደ።
\v 10 ምርቱ የሚሰበሰብበት ጊዜ ሲደርስ ከወይኑ የሚገባውን ፍሬ ለማግኘት ወደ ገበሬዎቹ አንድ አገልጋይ ላከ። ነገር ግን የወይኑ ገበሬዎች አገልጋዩን ደብድበው ባዶ እጁን መልሰው ላኩት።
\s5
\v 11 እርሱም አሁንም ሌላ አገልጋይ ላከባቸው፣ ይህንም ደብድበውና አዋርደው ባዶ እጁን መልሰው ላኩት።
\v 12 እንደ ገና ሦስተኛ አገልጋይ ቢልክባቸው፣ እርሱንም አቈሳስለው አውጥተው ጣሉት።
\s5
\v 13 ስለዚህ የወይኑ ዕርሻ ባለቤት፣ 'ምን ላድርግ? የምወደውን ልጄን እልከዋለሁ። ምናልባት እርሱን ያከብሩት ይሆናል' አለ።
\v 14 ነገር ግን የወይኑ ገበሬዎች ባዩት ጊዜ፣ 'ወራሹ ይህ ነው። ዕርሻው የእኛ እንዲሆን እንግድለው' ብለው እርስ በርስ ተመካከሩ።
\s5
\v 15 ከዕርሻው ቦታ አወጡትና ገደሉት። እንግዲህ የዕርሻው ባለቤት ምን ያደርግባቸዋል? መጥቶ እነዚህን የወይን ገበሬዎች ይደመስሳቸዋል፣
\v 16 ዕርሻውንም ለሌሎች ይሰጣል" አላቸው። እነርሱም ይህን በሰሙ ጊዜ፣ "እግዚአብሔር እንዲህ ያለውን ነገር ያርቀው!" አሉ።
\s5
\v 17 ኢየሱስ ግን ተመለከታቸውና፣ 'ግንበኞች የናቁት ድንጋይ የማዕዘን ራስ ሆነ' "የሚለው ይህ የመጽሐፍ ቃል ምን ማለት ነው?
\v 18 በዚህ ድንጋይ የሚደናቀፍ ሁሉ ይሰባበራል። ነገር ግን ድንጋዩ የሚወድቅበት ሁሉ ይደቃል" አለ።
\s5
\v 19 ስለዚህ፣ የሕግ መምህራንና የካህናት አለቆች በዚያን ሰዓት ሊይዙት ፈለጉ፣ ምክንያቱም ይህን ምሳሌ የተናገረው በእነርሱ ላይ እንደ ሆነ አውቀዋልና።
\v 20 ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ። በዐይነ ቁራኛ እየተከታተሉት፣ ለፍርድና ለገዢው ሥልጣን የሚዳርገውን ስሕተት ከንግግሩ ሊያገኙበት ራሳቸውን ጻድቃን አስመስለው የሚቀርቡ ሰላዮችን ላኩበት።
\s5
\v 21 እነርሱ እንዲህ በማለት ጠየቁት፤ "መምህር ሆይ፣ አንተ በትክክል እንደምትናገርና እንደምታስተምር፣ ደግሞም በማንም እንደማትመራ፣ነገር ግን ስለ እግዚአብሔር መንገድ እውነቱን እንደምታስተምር እናውቃለን።
\v 22 ለቄሣር ግብር መክፈል ተፈቅዷል ወይስ አልተፈቀደም?"
\s5
\v 23 ኢየሱስ ግን ተንኰላቸውን ተረዳ፣ እንዲህም አላቸው፣
\v 24 "አንድ ዲናር አሳዩኝ። በላዩ ያለው የማን ጽሑፍና ምስል ነው?" እነርሱም፣ "የቄሣር ነው" አሉት።
\s5
\v 25 "እንግዲያውስ የቄሣር የሆኑትን ነገሮች ለቄሣር፣ የእግዚአብሔርን ነገሮች ለእግዚአብሔር ስጡ" አላቸው።
\v 26 የሕግ መምህራንና የካህናት አለቆች በሕዝቡ ፊት በንግግሩ ሊያጠምዱት አልቻሉም። ምንም እስከማይናገሩ ድረስ በመልሱ ተደነቁ።
\s5
\v 27 የሙታን ትንሣኤ የለም የሚሉ አንዳንድ ሰዱቃውያን ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ፣
\v 28 እንዲህ ብለው ጠየቁት፤ "መምህር ሆይ፣ ሙሴ አንድ ሰው ሚስት አግብቶ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት ወንድሙ የዚያን ሰው ሚስት አግብቶ ልጅ ለእርሱ እንዲወልድለት ጽፎልናል።
\s5
\v 29 ሰባት ወንድማማች ነበሩ፤ የመጀመሪያው ሚስት አገባና ልጅ ሳይወልድ ሞተ፤
\v 30 ሁለተኛውም እንደዚሁ አግብቷት ልጅ ሳይወልድ ሞተ።
\v 31 ሦስተኛውም አገባት፤ በዚህ ዓይነት ሰባቱም ሴቲቱን አግብተው ልጅ ሳይወልዱ ሞቱ።
\v 32 በመጨረሻ ሴቲቱም ሞተች።
\v 33 ታዲያ በትንሣኤ ቀን ይህች ሴት የማንኛቸው ሚስት ትሆናለች? ምክንያቱም ሰባቱም አግብተዋታልና።"
\s5
\v 34 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ "የዚህ ዓለም ሰዎች ያገባሉ፣ ይጋባሉም።
\v 35 ነገር ግን የሙታን ትንሣኤንና የዘላለም ሕይወትን ለመቀበል የተገባቸው አያገቡም፣ አይጋቡምም።
\v 36 እንደ መላእክት ስለ ሆኑ፣ ከእንግዲህ ወዲያ ሊሞቱ አይችሉም። የትንሣኤ ልጆች እንደ መሆናቸው መጠን የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው።"
\s5
\v 37 ነገር ግን ሙታን ስለ መነሣታቸው ሙሴ እንኳ በቊጥቋጦው ስፍራ፣ጌታን የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክና የያዕቆብ አምላክ ብሎ በመጥራቱ አሳይቷል።
\v 38 አሁን እርሱ የሕያዋን እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም፣ ምክንያቱም ለእርሱ ሁሉም ሕያዋን ናቸው።"
\s5
\v 39 ከሕግ መምህራን አንዳንዶች፣ "መምህር ሆይ፣ ጥሩ አድርገህ መልሰሃል" አሉት።
\v 40 ደግሞም ተጨማሪ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ ማንም አልደፈሩም።
\s5
\v 41 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ "እንግዲህ ሰዎች ክርስቶስን የዳዊት ልጅ ነው የሚሉት እንዴት ነው?
\v 42 ዳዊት ራሱ በመዝሙር መጽሐፍ፣ "ጌታ ለጌታዬ ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ
\v 43 እስከማደርግልህ ድረስ 'በቀኜ ተቀመጥ' ይላልና።
\v 44 ስለዚህ ዳዊት ክርስቶስን ጌታ ይለዋል፣ታዲያ የዳዊት ልጅ እንዴት ይሆናል?"
\s5
\v 45 ሕዝቡ ሁሉ እየሰሙ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፣
\v 46 "ረጅም ቀሚስ ለብሰው መመላለስ ከሚፈልጉ፣ በገበያ ቦታዎችም ልዩ ሰላምታ፣ በምኲራቦች ከፍተኛ ስፍራ፣ በግብዣ ቦታዎችም የከበሬታ መቀመጫ እንዲሰጣቸው ከሚወዱ የሕግ መምህራን ተጠንቀቁ።
\v 47 ደግሞም እነርሱ ረጅም የሆኑ የማስመሰል ጸሎቶችን እየጸለዩ የመበለቶችን ቤት አለአግባብ ይበዘብዛሉ። እነዚህ የባሰ ቅጣት ይቀበላሉ።"
\s5
\c 21
\cl ምዕራፍ 21
\p
\v 1 ኢየሱስ ቀና ብሎ ሲመለከት ሀብታም ሰዎች በመባ መሰብሰቢያ ሣጥን ውስጥ ገንዘብ ሲጨምሩ አየ።
\v 2 አንዲት ድኻ መበለት ደግሞ ሁለት ሳንቲሞችን ስትጨምር አየ።
\v 3 ስለዚህ እንዲህ አለ፣ "እውነት እላችኋለሁ፣ ይህች ድኻ መበለት ከሁሉም የበለጠ ሰጠች።
\v 4 እነዚህ ሁሉ የሰጡት ስጦታ ከተትረፈረፈ ሀብታቸው ነው። ይህች መበለት ግን በድኽነቷ መተዳደሪያዋን ሁሉ ሰጠች።"
\s5
\v 5 አንዳንዶች ቤተ መቅደሱ በተዋቡ ድንጋዮች እንዴት እንዳማረና እንዳጌጠ ሲናገሩ ሰምቶ እንዲህ አለ፣
\v 6 "እነዚህ የምታዩአቸው ነገሮች፣ እንዲህ እንደተነባበሩ የማይቆዩበትና የሚፈራርሱበት ጊዜ ይመጣል" አለ።
\s5
\v 7 ስለዚህ፣ "መምህር ሆይ፣ እነዚህ ነገሮች የሚሆኑት መቼ ነው? እነዚህ ነገሮች እንደሚፈጸሙ ምልክቱስ ምንድን ነው?" በማለት ጠየቁት።
\v 8 ኢየሱስ፣ "እንዳትስቱ ተጠንቀቁ። ምክንያቱም ብዙዎች 'እኔ ኢየሱስ ነኝ፣ ደግሞም 'ጊዜው አሁን ነው' እያሉ በስሜ ይመጣሉ። አትከተሏቸው።
\v 9 ስለ ጦርነቶችና ሁከቶች ስትሰሙ አትሸበሩ፣ እነዚህ ነገሮች አስቀድመው መፈጸም ይኖርባቸዋል፣ ነገር ግን መጨረሻው ወዲያው አይሆንም" ብሎ መለሰ።
\s5
\v 10 ከዚያም እንዲህ አላቸው፣ "ሕዝብ በሕዝብ ላይ ይነሣል፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣል።
\v 11 ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ይሆናል፣ ደግሞም በተለያዩ ቦታዎች ራብና ቸነፈር ይከሠታል። አስፈሪ ሁነቶችና ታላላቅ ምልክቶች ከሰማይ ይገለጣሉ።
\s5
\v 12 ነገር ግን ከእነዚህ ሁሉ ነገሮች አስቀድሞ እናንተን ይይዟችኋል፣ ያሳድዷችኋል፣ ለምኩራቦችና ለወህኒ ቤቶች አሳልፈው በመስጠት ስለ ስሜ በገዦችና በነገሥታት ፊት ያቆሟችኋል።
\v 13 ይህም ለእናንተ ለመመስከር ዕድልን ይሰጣችኋል።
\s5
\v 14 ስለዚህ፣ አስቀድማችሁ ምን መከላከያ እናቀርባለን በማለት አትናወጡ፣
\v 15 ምክንያቱም በዚያን ጊዜ ጠላቶቻችሁ ሊቋቋሙትና ሊቃወሙት የማይችሉትን ቃልና ጥበብ እሰጣችኋለሁ።
\s5
\v 16 ነገር ግን በወላጆች፣ በወንደሞች፣ በዘመዶችና በጓደኞች ተላልፋችሁ ትሰጣላችሁ፣ ከእናንተም አንዳንዶቹን ይገድላሉ።
\v 17 በስሜ ምክንያት በሰው ሁሉ ትጠላላችሁ።
\v 18 ነገር ግን ከራሳችሁ ጠጒር አንዲቱ እንኳ አትጠፋም።
\v 19 በትዕግሥታችሁም ነፍሳችሁን ታተርፋላችሁ።
\s5
\v 20 ኢየሩሳሌም በሠራዊት ተከብባ ስታዩ ጥፋቷ መቃረቡን እወቁ።
\v 21 በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፣ በከተማይቱ መካከል ያሉትም ለቀው ይሂዱ፣ በገጠር ያሉት ደግሞ ወደ ከተማይቱ አይግቡ።
\v 22 የተጻፈው እንዲፈጸም እነዚህ ጊዜያት የበቀል ጊዜያት ናቸውና።
\s5
\v 23 በእነዚያ ቀኖች ለእርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው! በምድሪቱ ላይ ታላቅ መከራ፣ በዚህ ሕዝብም ላይ ቊጣ ይወርዳል።
\v 24 በሰይፍም ስለት ይወድቃሉ፤ ወደ ተለያዩ ሕዝቦች ሁሉ ምርኮኞች ተደርገው ይወሰዳሉ፤ የአሕዛብ ዘመን እስኪፈጸም ድረስ፣ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።
\s5
\v 25 በፀሐይ፣ በጨረቃና በከዋክብት ምልክቶች ይታያሉ። በምድር ላይ ያሉ ሕዝቦች ከባሕርና ከማዕበል ድምፅ የተነሣ ተስፋ በመቊረጥ ይጨነቃሉ።
\v 26 ከፍርሃትና በዓለም ላይ ሊከሰቱ ያሉትን ነገሮች ከመሥጋት የተነሣ የሚዝሉ ሰዎችም ይኖራሉ። ምክንያቱም የሰማያት ኅይላት ይናወጣሉና።
\s5
\v 27 ከዚያም የሰው ልጅ በኅይልና በታላቅ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል።
\v 28 ነገር ግን እነዚህ ነገሮች መፈጸም ሲጀምሩ፣ መዳናችሁ ስለ ቀረበ ንቁ፣ ቀና ብላችሁ ተመልከቱ።
\s5
\v 29 ኢየሱስ አንድ ምሳሌ ነገራቸው፤ “የበለስ ዛፍና ሌሎች ዛፎችን ተመልከቱ።
\v 30 ቀንበጥ ሲያወጡ፣ በጋ እንደተቃረበ ታውቃላችሁ።
\v 31 ልክ እንደዚሁም እነዚህ ነገሮች መፈጸማቸውን ስታዩ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ።
\s5
\v 32 እውነቱን እነግራችኋለሁ፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ከመፈጸማቸው በፊት ይህ ትውልድ አያልፍም።
\v 33 ሰማይና ምድር ያልፋሉ፣ ቃሌ ግን አያልፍም።
\s5
\v 34 ልቅ በሆነ አኗኗር፣ በስካርና በጭንቀት ልባችሁ እንዳይከብድ ተጠንቀቁ። ምክንያቱም ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት ይመጣባችኋል።
\v 35 በምድር በሚኖሩት ሁሉ ላይም ይመጣባቸዋል።
\s5
\v 36 ነገር ግን ከሚከሠቱት ከአነዚህ ነገሮች ሁሉ እንድታመልጡና በሰው ልጅም ፊት ለመቆም እንድትበረቱ ሁልጊዜ ነቅታችሁ ጸልዩ።
\s5
\v 37 ስለዚህ ኢየሱስ በየቀኑ በቤተ መቅደስ ያስተምር፣ ሌሊቱን ደግሞ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ እየወጣ ያሳልፍ ነበር።
\v 38 በቤተ መቅደስም ሲያስተምር ሰዎች ሁሉ ሊሰሙት በማለዳ ይመጡ ነበር።
\s5
\c 22
\cl ምዕራፍ 22
\p
\v 1 ፋሲካ የተባለው የቂጣ በዓል ተቃርቦ ነበር።
\v 2 የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ሕዝቡን ይፈሩ ስለ ነበር፣ ኢየሱስን እንዴት አድርገው እንደሚገድሉት ተመካከሩ።
\s5
\v 3 ሰይጣን ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ በሆነው በአስቆሮቱ ይሁዳ ገባበት።
\v 4 አርሱም ኢየሱስን እንዴት አድርጎ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ከካህናት አለቆችና ከሕዝብ መሪዎች ጋር ተነጋገረ።
\s5
\v 5 እነርሱም ደስ አላቸው፣ ገንዘብም ሊሰጡት ተስማሙ።
\v 6 እርሱም ኢየሱስን ለእነርሱ አሳልፎ ለመስጠት ሕዝብ የሌሉበትን ምቹ ጊዜ ይፈልግ ነበር።
\s5
\v 7 የፋሲካ በግ መሥዋዕት የሚደረግበት የቂጣ በዓል ደረሰ።
\v 8 ኢየሱስም ጴጥሮስንና ዮሐንስን፣ “ሂዱና የፋሲካ ምግብ እንድንበላ አዘጋጁልን” ብሎ ላካቸው።
\v 9 እነርሱም፣ “የት እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?” ብለው ጠየቁት።
\s5
\v 10 እንዲህም ብሎ መለሰላቸው፣ “አድምጡ፣ ወደ ከተማው በገባችሁ ጊዜ የውሃ እንስራ ተሸክሞ የሚመጣ ሰው ያገኛችኋል። ይህን ሰው ወደሚገባበት ቤት ተከትላችሁ ግቡ።
\v 11 ከዚያም ለቤቱ ባለቤት፣ 'መምህሩ እንዲህ ይልሃል፤" የፋሲካን እራት ከደቀ መዛሙርቴ ጋር የምበላበት የእንግዳ ክፍል የት ነው?' በሉት።”
\s5
\v 12 እርሱም በፎቁ ላይ ሰፊና በሚገባ የተሰናዳ ክፍል ያሳያችኋል። ዝግጅቱንም በዚያ አድርጉ።
\v 13 ስለዚህ ወጥተው ሲሄዱ፣ ሁሉም ነገር እርሱ እንደተናገረው ሆኖ አገኙት። ከዚያም የፋሲካውን ምግብ አዘጋጁ።
\s5
\v 14 ሰዓቱ ሲደርስ፣ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ዐብሮ ተቀመጠ።
\v 15 ከዚያም እንዲህ አላቸው፤ “መከራ ከመቀበሌ በፊት ይህን የፋሲካ እራት ከእናንተ ጋር ለመብላት በእጅጉ እጓጓ ነበር።
\v 16 በእግዚአብሔር መንግሥት እስከሚፈጸም ድረስ ከዚህ ምግብ ዳግመኛ እንደማልበላ እነግራችኋለሁና።"
\s5
\v 17 ከዚያም ኢየሱስ ጽዋውን አንሥቶ አመሰገነና እንዲህ አላቸው፤ “ይህን ውሰዱና ተካፈሉት።
\v 18 እላችኋለሁ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት እስክትመጣ ድረስ ከዚህ ወይን ፍሬ ዳግመኛ አልጠጣም።”
\s5
\v 19 እንጀራውን ወሰደ፣ ካመሰገነ በኋላ እንዲህ በማለት ቈርሶ ሰጣቸው፣ “ይህ ለእናንተ የተሰጠው ሥጋዬ ነው። እኔን እያሰባችሁ ተመገቡት።”
\v 20 በተመሳሳይ ሁኔታም፣ ከእራት በኋላ ጽዋውን አነሣና እንዲህ አለ፣ “ይህ ጽዋ ስለ እናንተ የፈሰሰ በደሜ የሚሆን ዐዲስ ኪዳን ነው።
\s5
\v 21 ነገር ግን እኔን አሳልፎ የሚሰጠኝ ከእኔ ጋር በማዕድ እየበላ መሆኑን ልብ በሉ።
\v 22 የሰው ልጅስ እንደተወሰነለት ይሆናል። ነገር ግን አሳልፎ ለሚሰጠው ለዚያ ሰው ወዮለት!"
\v 23 በዚህ ጊዜ እርስ በርሳቸው ይህን ነገር የሚያደርግ ማን እንደ ሆነ ተጠያየቁ።
\s5
\v 24 ከዚያም ከሁሉም የሚበልጥ ማን ሊሆን እንደሚገባው በመካከላቸው ጠብ ተነሣ። እርሱ እንዲህ አላቸው፣
\v 25 “የአሕዛብ ነገሥታት በሕዝብ ላይ ይገዛሉ፣ በእነርሱ ላይ ሥልጣን ያላቸውንም የተከበሩ ገዦች ይሏቸዋል።
\s5
\v 26 ነገር ግን በእናንተ ዘንድ እንዲህ አይሁን። ይልቅ ከእናንተ ታላቅ የሆነ እንደ ታናሽ ይሁን። እጅግ ተፈላጊ የሆነ እንደሚያገለግል ሰው ይሁን።
\v 27 በማዕድ ከተቀመጠውና ከሚያገለግለው የትኛው ታላቅ ነው? በማዕድ የተቀመጠ አይደለምን? እኔ ግን በእናንተ መካከል እንደሚያገለግል ሰው ነኝ።
\s5
\v 28 ነገር ግን እናንተ በፈተናዬ ከእኔ ጋር ጸንታችኋል። አብ ለእኔ መንግሥትን እንደ ሰጠኝ፣
\v 29 በመንግሥቴ በእኔ ማዕድ እንድትበሉና እንድትጠጡ መንግሥትን እሰጣችኋለሁ።
\v 30 ደግሞም በዙፋን ተቀምጣችሁ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ላይ ትፈርዳላችሁ።
\s5
\v 31 ስምዖን ሆይ፣ ስምዖን ሆይ፣ ተጠንቀቅ፤ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥርህ ፈልጎ ጠይቋል።
\v 32 ነገር ግን እኔ እምነትህ እንዳይጠፋ ጸለይሁልህ። ዳግመኛ ከተመለስህ በኋላ ወንድሞችህን አበርታቸው።”
\s5
\v 33 ጴጥሮስ፣ “ጌታ ሆይ፣ ወደ እስር ቤትም ይሁን ወደ ሞት ከአንተ ጋር ለመሄድ ዝግጁ ነኝ” አለው።
\v 34 ኢየሱስ፣ “ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ አላውቀውም ብለህ ሦስት ጊዜ እንደምትክደኝ እነግርሃለሁ” ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 35 ከዚያም ኢየሱስ፣ “ያለ ገንዘብ ቦርሣ፣ ወይም ያለ ስንቅ ወይም ያለ ጫማ በላክኋችሁ ጊዜ ያጣችሁት ነገር ነበርን?” አላቸው። እነርሱ፣ “ምንም አላጣንም" ብለው መለሱለት።
\v 36 ከዚያም እንዲህ አላቸው፣ “አሁን ግን የገንዘብ ቦርሣ ያለው ቦርሣውን፣ ደግሞም ስንቁን ይያዝ። ጎራዴ የሌለው ልብሱን ሽጦ ጎራዴ ይግዛ።
\s5
\v 37 እላችኋለሁ፣ 'ከወንበዴዎች እንደ አንዱ ተቈጠረ' ተብሎ ስለ እኔ የተጻፈው መፈጸም አለበት። ይህ ስለ እኔ የተነገረው አሁን እየተፈጸመ ነው።"
\v 38 ከዚያም እነርሱ፣ “ጌታ ሆይ፣ ተመልከት፣ እዚህ ሁለት ጎራዴዎች አሉ” አሉት። እርሱም “ይበቃል” አላቸው።
\s5
\v 39 ከእራት በኋላ ኢየሱስ ብዙ ጊዜ እንደሚያደርገው ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ሄደ፣ ደቀ መዛሙርቱም ተከተሉት።
\v 40 እዚያ በደረሱ ጊዜ፣ “ወደ ፈተና እንዳትገቡ ጸልዩ” አላቸው።
\s5
\v 41 ከእነርሱ የድንጋይ ውርወራ ያህል ራቅ ብሎ ሄደና ተንበርክኮ፣
\v 42 “አባት ሆይ፣ ብትወድ ይህን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፣ ነገር ግን የአንተ ፈቃድ እንጂ የእኔ ፈቃድ አይሁን” በማለት ጸለየ።
\s5
\v 43 የሚያበረታታው መልአክም ከሰማይ መጣለት።
\v 44 በጣር ውስጥ ሆኖ በጣም እየቃተተ ጸለየ፣ ላቡም እንደ ትልልቅ የደም ጠብታዎች ወደ መሬት ይንጠባጠብ ነበር።
\s5
\v 45 ከጸሎቱ ተነሥቶ ወደ ደቀ መዛሙርቱ በመጣ ጊዜ ከሐዘን የተነሣ ተኝተው አገኛቸውና፣
\v 46 “ለምን ትተኛላችሁ? ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተነሡና ጸልዩ” አላቸው።
\s5
\v 47 ገና እየተናገረ እያለ ብዙ ሰዎች ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው ይሁዳ እየመራቸው መጡ። ይሁዳም ሊስመው ወደ ኢየሱስ ቀረበ፤
\v 48 ነገር ግን ኢየሱስ፣ “ይሁዳ ሆይ፣ የሰውን ልጅ በመሳም አሳልፈህ ትሰጣለህን?” አለው።
\s5
\v 49 በኢየሱስ ዙሪያ የነበሩት እየሆነ ያለውን ነገር ባዩ ጊዜ፣
\v 50 “በጎራዴ እንምታቸውን?” አሉ። ከዚያም ከመካከላቸው አንዱ በጎራዴ የሊቀ ካህኑን አገልጋይ ቀኝ ጆሮ መታና ቈረጠው።
\v 51 ኢየሱስ፣ “ይህ ይብቃ” አለ። የአገልጋዩንም ጆሮ ዳሰሰ፣ ፈወሰውም።
\s5
\v 52 ኢየሱስ ሊያጠቁት ለመጡ የካህናት አለቆችና የቤተ መቅደስ መሪዎች እንዲሁም ሽማግሌዎች እንዲህ አላቸው፤ “ወንበዴን እንደሚይዝ ሰው ጐራዴና ዱላ ይዛችሁ ትመጡብኛላችሁን?
\v 53 በየዕለቱ በቤተ መቅደስ ከእናንተ ጋር ሳለሁ አልያዛችሁኝም። ነገር ግን ይህ የእናንተና የጨለማው ሥልጣን ጊዜ ነው።”
\s5
\v 54 ያዙትና ወሰዱት፣ ወደ ሊቀ ካህናቱ ቤትም አመጡት። ጴጥሮስ ግን ከርቀት ተከተለው።
\v 55 በግቢው መሓል እሳት ካቀጣጠሉና ዐብረው ከተቀመጡ ጴጥሮስ መጥቶ በመካከላቸው ተቀመጠ።
\s5
\v 56 በእሳቱ ብርሃን እንደተቀመጠም አንዲት ገረድ አየችውና በቀጥታ ተመልክታው፣ “ይህ ሰው ደግሞ ከእርሱ ጋር ነበር” አለች።
\v 57 ጴጥሮስ ግን፣ “ሴትዮ፣ የምትዪውን ሰው አላውቀውም” ብሎ ካደ።
\v 58 ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ፣ ሌላ ሰው አየውና፣ “አንተም ከእነርሱ አንዱ ነህ” አለው። ነገር ግን ጴጥሮስ፣ “አንተ ሰው፣ እኔ አይደለሁም” አለ።
\s5
\v 59 ከአንድ ሰዓት ያህል ጊዜ በኋላ፣ ሌላ ሰው፣ “በእውነት ይህ ሰው ደግሞ ገሊላዊ ስለ ሆነ ከእርሱ ጋር ነበረ” በማለት በጥብቅ ተናገረ።
\v 60 ነገር ግን ጴጥሮስ፣ “አንተ ሰው የምትለውን አላውቅም” አለ። ይህን እየተናገረ እያለ ወዲያው ዶሮ ጮኸ።
\s5
\v 61 ጌታም ዞር አለና ጴጥሮስን ተመለከተው። ጴጥሮስም፣ ጌታ “ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ያለውን ቃል አስታወሰ።
\v 62 ጴጥሮስ ወደ ውጭ ወጣና መራራ ልቅሶ አለቀሰ።
\s5
\v 63 ከዚያም ኢየሱስን ይጠብቁ የነበሩት ሰዎች እያላገጡበት ደበደቡት። ዐይኖቹን ከሸፈኑ በኋላ፣
\v 64 “እስቲ ትንቢት ተናገር። አሁን የመታህ ሰው ማን ነው?” በማለት ጠየቁት።
\v 65 እየተሳደቡ፣ ሌሎች ብዙ ነገሮችን በኢየሱስ ላይ ተናገሩ።
\s5
\v 66 እንደነጋም የሕዝቡ ሽማግሌዎች፣ ከካህናት አለቆችና ከሕግ መምህራን ጋር ዐብረው ተሰበሰቡ። ከዚያም ኢየሱስን ወደ ሸንጎው ፊት አቀረቡትና፣
\v 67 “ክርስቶስ ከሆንህ ንገረን” አሉት። እርሱ ግን፣ “እኔ ብነግራችሁ አታምኑም፣
\v 68 ደግሞም ብጠይቃችሁ አትመልሱም።
\s5
\v 69 ነገር ግን ከአሁን ጀምሮ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ኅይል ቀኝ ይቀመጣል” አላቸው።
\v 70 ሁሉም በአንድነት፣ “እንግዲህ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነሃ?” አሉት። ኢየሱስም፣ “እኔ እንደ ሆንሁ እናንተ ትናገራላችሁ” አላቸው። እነርሱ፣
\v 71 “እንግዲህ ለምን ምስክር እንፈልጋለን? ሲናገር እኛ ራሳችን ከአፉ ሰምተነዋል” አሉ።
\s5
\c 23
\cl ምዕራፍ 23
\p
\v 1 ሕዝቡ በጠቅላላ ተነሥተው ቆሙ፣ ኢየሱስንም በጲላጦስ ፊት አቀረቡት።
\v 2 “ይህ ሰው ራሱን ክርስቶስ፣ ንጉሥ ነኝ ሲልና ለቄሣር ግብር እንዳይከፈል በመከልከል አገር ሲበጠብጥ አግኝተነዋል” በማለት ይከሱት ጀመር።
\s5
\v 3 ጲላጦስ፣ “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” በማለት ጠየቀው። ኢየሱስም፣ “አንተ አልህ” ብሎ መለሰለት።
\v 4 ጲላጦስ የካህናት አለቆችንና የተሰበሰቡትን ሕዝብ፣ “በዚህ ሰው ምንም ስሕተት አላገኘሁበትም” አላቸው።
\v 5 እነርሱ ግን፣ “ከገሊላ ጀምሮ በመላው ይሁዳ፣ እስከዚህ ስፍራም እንኳ እያስተማረ ሕዝቡን ያነሣሣል” በማለት አጥብቀው ተናገሩ።
\s5
\v 6 ስለዚህ ጲላጦስ ይህን በሰማ ጊዜ ሰውየው ገሊላዊ እንደ ሆነ አጠያየቀ።
\v 7 ከሄሮድስ ሥልጣን በታች እንደ ሆነ ተረድቶ በዚያው ሰሞን ኢየሱስን በኢየሩሳሌም ወደ ነበረው ሄሮድስ ላከው።
\s5
\v 8 ሄሮድስ ኢየሱስን ባየው ጊዜ በጣም ደስ አለው፣ ምክንያቱም ለረጅም ጊዜ ሊያየው ሲፈልግ ነበር። ስለ እርሱ ሰምቶ የነበረ ሲሆን፣ አንዳንድ ተአምራት ሲያደርግ ለማየትም ተስፋ ነበረው።
\v 9 ሄሮድስ ኢየሱስን በብዙ ቃሎች ቢጠይቅም፣ ኢየሱስ ግን ምንም መልስ አልሰጠውም።
\v 10 በዚህ ጊዜ የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ተነሥተው ቆሙና በኅይለ ቃል ከሰሱት።
\s5
\v 11 ሄሮድስ ከወታደሮቹ ጋር በመሆን ኢየሱስን ሰደበው፣ አላገጠበትም፤ ጥሩ ልብስ ካለበሰው በኋላ መልሶ ወደ ሄሮድስ ላከው።
\v 12 ከዚያን ቀን ጀምሮ ሄሮድስና ጲላጦስ ወዳጆች ሆኑ (ከዚያ በፊት አንዱ የአንዱ ጠበኞች ነበሩ)።
\s5
\v 13 ከዚያም ጲላጦስ የካህናት አለቆችን፣ ገዢዎችንና ሕዝቡን አንድ ላይ ጠራ፤
\v 14 እንዲህም አላቸው፤ “ ይህን ሰው ሰዎችን ለክፉ ድርጊት የሚያነሣሣ አድርጋችሁ ወደ እኔ አመጣችሁት፣ እኔም በፊታችሁ ከጠየቅሁት በኋላ ፣ እነሆ፣ እርሱን በምትከሱባቸው ነገሮች ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም።
\s5
\v 15 ሄሮድስም ቢሆን ምንም ነገር አላገኘበትም፤ ምክንያቱም መልሶ ወደ እኛ ልኮታልና፤ እነሆ፣ እርሱን ለሞት የሚያደርስ በዚህ ሰው የተፈጸመ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም።
\v 16 ስለዚህ ቀጥቼው እለቀዋለሁ።" ጲላጦስም በበዓሉ ለአይሁድ አንድ እስረኛ የመፍታት ግዴታ ነበረበት።
\v 17
\s5
\v 18 ነገር ግን እነርሱ በአንድነት፣ “ይህን ሰው አስወግደው፣ በርናባስን ለእኛ ፍታልን!" በማለት ጮኹ።
\v 19 በርናባስ በከተማይቱ ውስጥ አንድ ዐይነት ዐመፅና ግድያ በመፈጸም የታሰረ ሰው ነበር።
\s5
\v 20 ጲላጦስ ኢየሱስን ሊፈታ ፈልጎ እንደ ገና ሕዝቡን አነጋገራቸው።
\v 21 ነገር ግን ሕዝቡ፣ “ስቀለው፣ ስቀለው” እያሉ ጮኹ።
\v 22 ለሦስተኛ ጊዜም እንዲህ አላቸው፤ “ለምን? ይህ ሰው የሠራው ክፋት ምንድን ነው? ለሞት ቅጣት የሚያበቃ ነገር አላገኘሁበትም። ስለዚህ ቀጥቼው እለቀዋለሁ።”
\s5
\v 23 እነርሱ ግን ኢየሱስ እንዲሰቀል በመጠየቅ ሳያቋርጡ አብዝተው ጮኹ። ጩኸታቸውም ጲላጦስን አሳመነው።
\v 24 ስለዚህ ጲላጦስ ፍላጎታቸውን ለማሟለት ወሰነ።
\v 25 እንዲፈታላቸው የጠየቁትን፣ በዐመፅና በግድያ ምክንያት የታሰረውን ሰው ለቀቀላቸው። ኢየሱስን ግን ለፈቃዳቸው አሳልፎ ሰጠው።
\s5
\v 26 እየወሰዱት ሳሉ፣ ከገጠር ይመጣ የነበረ ስምዖን የተባለ የቀሬናን ሰው ያዙና ኢየሱስ ይሸከመው የነበረውን መስቀል አሸከሙት።
\s5
\v 27 እጅግ ብዙ ሕዝብና ለእርሱ የሚያዝኑና የሚያለቅሱ ሴቶች ይከተሉት ነበር።
\v 28 ኢየሱስም ወደ እነርሱ ዞር ብሎ፣ “የኢየሩሳሌም ሴቶች ሆይ፣ ለእኔ ሳይሆን ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ” አለ።
\s5
\v 29 እነሆ፣ 'መካን የሆኑና ያልወለዱ ማኅፀኖች እንዲሁም ያላጠቡ ጡቶች የተባረኩ ናቸው' የሚሉባቸው ቀኖች ይመጣሉና።
\v 30 ከዚያም ተራሮችን፣ 'በላያችን ውደቁ፣ ኮረብቶችንም ክደኑን ማለትይጀምራሉ።'
\v 31 ዛፉ እርጥብ እያለ ይህን ነገር ካደረጉ፣ በሚደርቅበት ጊዜ ምን ይሆናል?"
\s5
\v 32 ሌሎች ሁለት ወንጀለኞችም ከእርሱ ጋር ሊገደሉ ተወሰዱ።
\s5
\v 33 የራስ ቅል ወደሚባል ቦታ በደረሱ ጊዜ፣ እርሱን ከሌሎች ሁለት ወንጀለኞች ጋር ሰቀሉት፥ አንደኛው በቀኙ ሌላኛው በግራው ነበሩ።
\v 34 ኢየሱስ፣”አባት ሆይ፣ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” አለ። ዕጣ ተጣጥለውም ልብሱን ተከፋፈሉ።
\s5
\v 35 “ሌሎችን አዳነ፣ እርሱ በእግዚአብሔር የተመረጠ ክርስቶስ ከሆነ አስኪ ራሱን ያድን” በማለት ገዢዎቹ እየዘበቱበት ሳለ ሕዝቡ ቆመው ያዩ ነበር።
\s5
\v 36 ወታደሮቹም ወደ እርሱ ቀርበው፣
\v 37 “አንተ ንጉሥ ከሆንህ ራስህን አድን” በማለት እያሾፉበት ኮምጣጤ ሰጡት።
\v 38 “የአይሁድ ንጉሥ” የሚል ምልክትም ከበላዩ ተደርጎ ነበር።
\s5
\v 39 ከተሰቀሉት ወንጀለኞች አንዱ፣ "አንተ ክርስቶስ ነህን? ራስህንም እኛንም አድን” በማለት ሰደበው።
\v 40 ሌላኛው ግን እየገሠጸው፣ “ከፍርድ በታች ሆነህ እግዚአብሔርን አትፈራምን? እኛ በዚህ ያለነው እንደ ሥራችን ስለ ሆነ፣ ትክክል ነው፣
\v 41 ነገር ግን ይህ ሰው ምንም ጥፋት አላደረገም” ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 42 ቀጥሎም፣ “ኢየሱስ ሆይ፣ በመንግሥትህ ስትመጣ አስታውሰኝ” አለ።
\v 43 ኢየሱስ፣ “እውነት እልሃለሁ፣ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትሆናለህ” አለው።
\s5
\v 44 ጊዜው ስድስት ሰዓት ገደማ ነበር፣ የፀሐይ ብርሃን በመቋረጡ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ላይ ጨለማ ሆነ።
\v 45 ከዚያም የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከመሐል ተቀደደ።
\s5
\v 46 ኢየሱስ፣ “አባት ሆይ፣ ነፍሴን በእጅህ አኖራለሁ” በማለት በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህን ከተናገረ በኋላ ሞተ።
\v 47 መቶ አለቃው የተደረገውን ነገር ባየ ጊዜ፣ “ይህ ሰው በእውነት ጻድቅ ነበር” በማለት እግዚአብሔርን አከበረ።
\s5
\v 48 ሁኔታውን ለማየት እጅግ ብዙ ሰዎች በመጡ ጊዜ፣ የተደረጉትን ነገሮች አይተው ደረታቸውን እየደቁ ተመለሱ።
\v 49 ነገር ግን ከገሊላ ጀምሮ የተከተሉት አንዳንድ ወንዶችና ሴቶች ከርቀት ቆመው ይህን ድርጊት ይከታተሉ ነበር።
\s5
\v 50 እነሆ፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት መምጣት የሚጠባበቅ፣ ከአይሁድ ከተማ፣ ከአርማቲያ የሆነ ዮሴፍ የሚባል
\v 51 (በውሳኔያቸውና በድርጊታቸው ያልተስማማ) አንድ መልካምና ጻድቅ ሰው ነበረ።
\s5
\v 52 ይህ ሰው ወደ ጲላጦስ በመቅረብ የኢየሱስን አስከሬን እንዲሰጠው ጠየቀው።
\v 53 አስክሬኑን አውርዶ በጥሩ የተልባ እግር ጨርቅ ከፈነውና ማንም ባልተቀበረበት ከድንጋይ በተወቀረ መቃብር ውስጥ አኖረው።
\s5
\v 54 ጊዜው የዝግጅት ቀን የነበረ ሲሆን፣ ሰንበትም እየገባ ነበር።
\v 55 ከእርሱ ጋር ከገሊላ የመጡ ሴቶች ተከትለውት በመሄድ መቃብሩንና አስከሬኑ እንዴት እንዳረፈ አዩ።
\v 56 ከዚያም ተመልሰው ቅመማ ቅመምና ቅባቶችን አዘጋጁ። ሰንበት ስለ ነበር በሕጉ መሠረት ዐረፉ።
\s5
\c 24
\cl ምዕራፍ 24
\p
\v 1 በሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ሴቶች ያዘጋጁትን ሽቱ ይዘው በጣም ማልደው ወደ መቃብሩ መጡ።
\v 2 ድንጋዩ ከመቃብሩ ተንከባሎ አገኙት።
\v 3 ወደ ውስጥ ገቡ፣ ነገር ግን የጌታ ኢየሱስን ሥጋ አላገኙም።
\s5
\v 4 ስለዚህ ነገር ግራ ተጋብተው ሳሉ፣ የሚያብረቀርቅ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በድንገት ከአጠገባቸው ቆመው አገኙ።
\v 5 ሴቶቹ በፍርሃት ተሞልተውና ወደ መሬት አቀርቅረው ሳሉ፣ ሰዎቹ ፣“ስለምን ሕያውን ከሙታን መካከል ትፈልጋላችሁ?
\s5
\v 6 እርሱ በዚህ የለም፣ ተነሥቷል! ገና በገሊላ ሳለ፣
\v 7 እንዴት በኃጢአተኞች ሰዎች እጅ ተላልፎ እንደሚሰጥ፣ እንደሚሰቀልና በሦስተኛው ቀን እንደሚነሣ የነገራችሁን አስታውሱ" አሏቸው።
\s5
\v 8 ሴቶቹ ቃሎቹን አስታወሱ፣
\v 9 ከመቃብሩም ተመለሱና እነዚህን ነገሮች ሁሉ ለዐሥራ አንዱና ለተቀሩትም ነገሩ።
\v 10 መግደላዊት ማርያም፣ ዮሐናና የያዕቆብ እናት ማርያም እንዲሁም ሌሎች ሴቶች ሁኔታውን ለሐዋርያት ነገሯቸው።
\s5
\v 11 ነገር ግን ይህ ንግግር ለሐዋርያቱ ቀልድ ስለ መሰላቸው፣ ሴቶቹን አላመኗቸውም፣
\v 12 ሆኖም ግን ጴጥሮስ ተነሣና እየሮጠ ወደ መቃብሩ ሄደ፣ ከዚያም አጎንብሶ ወደ ውስጥ ሲመለከት፣ የተልባው እግር ጨርቅ ለብቻው ተቀምጦ አየ። ከዚያ በኋላ ጴጥሮስ ምን ተፈጥሮ ይሆን ብሎ እያሰበ ወደ ቤቱ ተመለሰ።
\s5
\v 13 እነሆ፣ ከእነርሱ ሁለቱ በዚያው ቀን ከኢየሩሳሌም ስድሳ ምዕራፍ ርቆ ወደሚገኝ ኤማሁስ ወደሚባል መንደር እየተጓዙ ነበር።
\v 14 ስለሆኑት ነገሮች ሁሉ በመንገዳቸው ላይ እርስ በርስ ይነጋገሩ ነበር።
\s5
\v 15 እየተነጋገሩና እየተጠያየቁ በመሄድ ላይ ሳሉ፣ ኢየሱስ ወደ እነርሱ ተጠግቶ ይሄድ ነበር።
\v 16 ነገር ግን እርሱን እንዳያውቁት ዐይኖቻቸው ተይዘው ነበር።
\s5
\v 17 ኢየሱስ፣ “እናንተ ሁለታችሁ እየተጓዛችሁ የምትነጋገሩት ስለምንድን ነው?” አላቸው። ያዘኑ መስለው ቆም አሉ።
\v 18 ስሙ ቀለዮጳ የተባለ ከሁለቱ አንዱ፣ “በኢየሩሳሌም ሰሞኑን የተደረጉትን ነገሮች የማታውቅ አንተ ብቻ ነህን?" ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 19 ኢየሱስም፣ “ነገሮቹ ምንድን ናቸው?” አላቸው።
\v 20 እነርሱም እንዲህ ብለው መለሱለት፣ “የካህናት አለቆችና ገዢዎቻችን ኢየሱስ የተባለውን ናዝራዊና ነቢይ እንዴት አድርገው እንደ ፈረዱበትና ለሞትና ለስቅላት አሳልፈው እንደ ሰጡት ነዋ።
\s5
\v 21 እስራኤልን ነጻ ያወጣል ብለን ተስፋ ያደረግነው እርሱን ነበር። አዎን፣ ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ ይህ ነገር ከሆነ አሁን ሦስተኛ ቀኑ ነው”
\s5
\v 22 ነገር ግን ጠዋት ወደ መቃብሩ የሄዱ ከእኛ ጋር የሆኑ አንዳንድ ሴቶች አስገረሙን።
\v 23 ሥጋውን ባላገኙ ጊዜ፣ በመቃብሩ ውስጥ ሥጋውን እንዳላገኙና እርሱ ሕያው ሆኗል ብለው የነገሯቸውን የመላእክት ራእይ አይተናል አሉ።
\v 24 ከእኛ ጋር ካሉት ወንዶችም አንዳንዶች ወደ መቃብሩ ሄደው ልክ ሴቶቹ እንዳሉት ሆኖ አገኙት። ነገር ግን እርሱን አላዩትም”።
\s5
\v 25 ኢየሱስም፣ “ነቢያት የተናገሩትን ሁሉ ለማመን የዘገያችሁ እናንተ ሞኞች!
\v 26 ክርስቶስ በእነዚህ ነገሮች መሠቃየቱና ወደ ክብሩ መግባቱ ግድ መሆኑን አታውቁምን?" አላቸው።
\v 27 ከዚያም ከሙሴ ጀምሮ እስከ ነቢያት መጻሕፍት፣ በመጻሕፍት ሁሉ ስለ እርሱ የተነገረውን ተረጐመላቸው።
\s5
\v 28 ወደሚሄዱበት መንደር በተቃረቡ ጊዜ፣ ኢየሱስ ቀደም ቀደም እያለ መሄድ ጀመረ።
\v 29 ነገር ግን እነርሱ፣ “ቀኑ እየመሸ ጊዜውም እያለፈ ስለ ሆነ ከእኛ ጋር እደር” ብለው ጎተጎቱት። ስለዚህ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ሊያድር ሄደ።
\s5
\v 30 ለመብላት ከእነርሱ ጋር በማዕድ በተቀመጠ ጊዜ፣ እንጀራውን ወሰደና ከባረከው በኋላ ቈርሶ ሰጣቸው።
\v 31 በዚህ ጊዜ ዐይኖቻቸው ተከፈቱና አወቁት። እርሱ ግን ከዐይናቸው ተሰወረባቸው።
\v 32 እርስ በርሳቸው፣ “በመንገድ ላይ አብረን ሳለን ሲያናግረንና መጻሕፍትን ሲከፍት ልባችን በውስጣችን ይቃጠልብን አልነበርምን?” ተባባሉ።
\s5
\v 33 በዚያው ሰዓት ተነሥተው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። ዐሥራ አንዱና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም ተሰብስበው እንዲህ እያሉ አገኟቸው፤
\v 34 “ጌታ በእርግጥ ተነሥቷል፣ ለስምዖንም ታይቷል።”
\v 35 ከዚያም በመንገድ ላይ የሆነውን ነገርና ኢየሱስ በማዕድ እንጀራን በሚቈርስበት ጊዜ እንዴት እንደ ታያቸው ተናገሩ።
\s5
\v 36 እነዚህን ነገሮች እየተናገሩ እያሉ ኢየሱስ ራሱ በመካከላቸው ቆሞ፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን" አላቸው።
\v 37 እነርሱም ስለ ተሸበሩና በፍርሃት ስለ ተዋጡ መንፈስ ያዩ መሰላቸው።
\s5
\v 38 ኢየሱስ፣ “ለምን ትጨነቃላችሁ? ለምንስ በልባችሁ ጥያቄዎች ይነሣሉ?
\v 39 እኔው ራሴ ስለ መሆኔ እጆቼንና እግሮቼን እዩ። ዳሳችሁም እዩኝ። በእኔ እንደምታዩት መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውም" አላቸው።
\v 40 ይህን ተናግሮ እጆቹንና እግሮቹን አሳያቸው።
\s5
\v 41 ከደስታ የተነሣ ማመን ተስኗቸው ግራ ተጋብተው ሳሉ፣ ኢየሱስ፣ “የሚበላ ጥቂት ነገር ይኖራችኋል?” አላቸው።
\v 42 የተጠበሰ ዐሣ ሰጡት።
\v 43 ኢየሱስም ወስዶ በፊታቸው በላው።
\s5
\v 44 እንዲህም አላቸው፤ “ከእናንተ ጋር በነበርሁ ጊዜ በሙሴ ሕግ፣ በነቢያትና በመዝሙራት የተጻፈው ሁሉ መፈጸም እንደሚገባው ነግሬአችሁ ነበር።”
\s5
\v 45 ከዚያም መጻሕፍትን ይረዱ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው።
\v 46 እንዲህ አላቸው፤ “እንግዲህ ክርስቶስ መሠቃየት፣ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን መካከል መነሣት እንደሚገባው በመጻሕፍት ተጽፏል።
\v 47 ደግሞም ንስሐና የኃጢአት ይቅርታ ከኢየሩሳሌም ጀምሮ ለአሕዛብ ሁሉ በስሙ መሰበክ አለበት።
\s5
\v 48 እናንተ የእነዚህ ነገሮች ምስክሮች ናችሁ።
\v 49 እነሆ፣ የአባቴን ተስፋ በእናንተ ላይ እልካለሁ። ኅይልን ከላይ እስከምትቀበሉ ድረስ በዚህ ከተማ ሆናችሁ ተጠባበቁ።"
\s5
\v 50 ከዚያም ኢየሱስ ወደ ቢታንያ እስከሚቃረቡ ድረስ ይዟቸው ሄደ። እጆቹንም አነሣና ባረካቸው፤
\v 51 እየባረካቸውም ሳለ ወደ ሰማይ ከፍ ከፍ አለ።
\s5
\v 52 ስለዚህ እነርሱ ሰገዱለት፣ እጅግ ደስ እያላቸውም ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
\v 53 በቤተ መቅደስም ያለ ማቋረጥ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር።