2024 lines
188 KiB
Plaintext
2024 lines
188 KiB
Plaintext
\id MAT
|
||
\ide UTF-8
|
||
\h የማቴዎስ
|
||
\toc1 የማቴዎስ
|
||
\toc2 የማቴዎስ
|
||
\toc3 mat
|
||
\mt የማቴዎስ
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 1
|
||
\cl ምዕራፍ 1
|
||
\p
|
||
\v 1 የዳዊት ልጅ፣ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ መጽሐፍ፡፡
|
||
\v 2 አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና የይሁዳን ወንድሞች ወለደ፤
|
||
\v 3 ይሁዳም ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ ፋሬስም ኤስሮምን ወለደ፤ ኤስሮምም አራምን ወለደ፤
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 4 አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤
|
||
\v 5 ሰልሞንም ከረዐብ ቦዔዝን ወለደ፤ ቦዔዝም ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤ እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ፡፡
|
||
\v 6 ንጉሥ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ፤
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 7 ሰሎሞንም ሮበዓምን ወለደ፤ ሮብዓምም አብያን ወለደ፤ አብያም አሳፍን ወለደ፤
|
||
\v 8 አሳፍም ኢዮሣፍጥን ወለደ፤ ኢዮሣፍጥም ኢዮራምን ወለደ፤ ኢዮራምም ዖዝያንን ወለደ፤
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 9 ዖዝያንም ኢዮአታምን ወለደ፤ ኢዮአታምም አካዝን ወለደ፤ አካዝም ሕዝቅያስን ወለደ፤
|
||
\v 10 ሕዝቅያስም ምናሴን ወለደ፤ ምናሴም አሞጽን ወለደ፤ አሞጽም ኢዮስያስን ወለደ፤
|
||
\v 11 ኢዮስያስም በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ኢኮንያንንና ወንድሞቹን ወለደ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 12 ከባቢሎን ምርኮ በኋላም፣ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፤ ሰላትያልም ዘሩባቤልን ወለደ፤
|
||
\v 13 ዘሩባቤልም አብዩድን ወለደ፤ አብዩድም ኤልያቄምን ወለደ፤ ኤልያቄምም አዛርን ወለደ፤
|
||
\v 14 አዛርም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም አኪምን ወለደ፤ አኪምም ኤልዩድን ወለደ፤
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 15 ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛርም ማታንን ወለደ፤ ማታንም ያዕቆብን ወለደ፤
|
||
\v 16 ያዕቆብም ክርስቶስ ተብሎ የሚጠራውን ኢየሱስን የወለደችውን፣ የማርያምን ባል ዮሴፍን ወለደ፡፡
|
||
\v 17 ከአብርሃም እስከ ዳዊት፣ የነበሩት ትውልዶች ሁሉ ዐሥራ አራት፤ ከዳዊት እስከ ባቢሎን ምርኮ ድረስም እንደዚሁ ዐሥራ አራት፤ ከባቢሎን ምርኮ እስከ ክርስቶስ ድረስ የነበሩትም ዐሥራ አራት ትውልዶች ናቸው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 18 የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በሚከተለው መንገድ ተፈጸመ፡- እናቱ ማርያም ዮሴፍን ልታገባው ታጭታ ነበር፤ ነገር ግን ሳይጋቡ በመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች፡፡
|
||
\v 19 ዮሴፍ ጻድቅ ነበረ፤ በመሆኑም እርሷን በሕዝብ ፊት ሊያዋርዳት አልፈለገም፡፡ ስለዚህ ከእርሷ ጋር የነበረውን የዕጮኛነቱን ግንኙነት በምስጢር ለማቋረጥ ወሰነ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 20 ዮሴፍ ስለ እነዚህ ነገሮች እያሰበ ሳለ፣ የጌታ መልአክ፣ "የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፣ ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ፤ ምክንያቱም እርሷ የፀነሰችው በመንፈስ ቅዱስ ነው።
|
||
\v 21 እርሷ ወንድ ልጅ ትወልዳለች፣ ሕዝቡንም ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ብለህ ትጠራዋለህ" በማለት ተገለጠለት።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 22-23 ይህ ሁሉ የሆነው፣ "እነሆ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም ዐማኑኤል ብለው ይጠሩታል፤ ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ማለት ነው" ብሎ ጌታ በነቢይ የተናገረው እንዲፈጸም ነው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 24 ዮሴፍ ከእንቅልፉ ነቃ፣ የጌታ መልአክ አዝዞት እንደ ነበረውም አደረገ፡- ማርያምን እን ደሚስቱ ወሰዳት፡፡
|
||
\v 25 (ይሁን እንጂ፣ ልጅ እስከምትወልድ ድረስ ከእርሷ ጋር ግንኙነት አላደረገም፡፡) የሕፃኑንም ስም ኢየሱስ አለው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 2
|
||
\cl ምዕራፍ 2
|
||
\p
|
||
\v 1 በንጉሥ ሄሮድስ ዘመን ኢየሱስ በቤተ ልሔም ይሁዳ ከተወለደ በኋላ፣ ጠቢባን ሰዎች ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፡፡ እንደዚህም በማለት ጠየቁ፤
|
||
\v 2 ‹‹የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ የት ነው? የእርሱን ኮከብ በምሥራቅ አየን፣ ልንሰግድለትም መጥተናል፡፡››
|
||
\v 3 ንጉሡ ሄሮድስ ይህን ሲሰማ ተረበሸ፤ መላው ኢየሩሳሌምም ከእርሱ ጋር ታወከ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 4 ሄሮድስ የካህናቱን አለቆችና የሕዝቡን የሕግ መምህራን ሰብስቦ፣ ‹‹ክርስቶስ የሚወለደው የት ነው?›› በማለት ጠየቀ፡፡
|
||
\v 5 ‹‹በቤተ ልሔም ይሁዳ›› አሉት፤ በነቢዩ የተጻፈው ይህ ነውና፡
|
||
\v 6 በይሁዳ ምድር የምትገኚ አንቺ ቤተ ልሔም፣ ከይሁዳ ገዦች በምንም አታንሺም፣ ሕዝቡን እስራኤልን የሚጠብቅ ገዥ፣ ከአንቺ ይወጣልና፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 7 ከዚያም በኋላ ሄሮድስ ኮከቡ በትክክል በምን ሰዓት ታይቶ እንደ ነበር ሊጠይቃቸው ጠቢባኑን በምስጢር ጠራቸው፡፡
|
||
\v 8 ወደ ቤተ ልሔምም ላካቸው፤ ‹‹ሂዱና ሕፃኑን በጥንቃቄ ፈልጉ፡፡ ስታገኙት እኔም ደግሞ እንድመጣና እንድሰግድለት ንገሩኝ›› አላቸው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 9 ንጉሡ የተናገረውን ከሰሙ በኋላ ሄዱ፤ በምሥራቅ አይተውት የነበረውም ኮከብ ሕፃኑ በነበረበት ላይ እስኪደርስና እስኪቆም ድረስ በፊታቸው ይሄድ ነበር፡፡
|
||
\v 10 ጠቢባኑ ኮከቡን ባዩት ጊዜ፣ እጅግ በጣም ተደሰቱ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 11 ወደ ቤት ገብተው ሕፃኑንም ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፤ ተንበርክከውም ሰገዱለት፡፡ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው የወርቅ፣ የዕጣንና የከርቤ ስጦታ አቀረቡለት፡፡
|
||
\v 12 እግዚአብሔር ጠቢባኑን ወደ ሄሮድስ ተመልሰው እንዳይሄዱ በሕልም አስጠነቀቃቸው፤ ስለዚህም በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ሄዱ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 13 ጠበባኑ ከሄዱ በኋላ፣ የጌታ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገለጠለትና፣ "ተነሥ፣ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፡፡ እኔ እስክነግርም ድረስ እዚያ ቈይ፤ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልጋልና" አለው፡፡
|
||
\v 14 በዚያ ሌሊት ዮሴፍ ተነሣ፣ ሕፃኑንና እናቱንም ይዞ ወደ ግብፅ ሄደ፡፡
|
||
\v 15 ሄሮድስ እስኪሞት ድረስ እዚያው ቈየ፡፡ በዚህም ጌታ፣ ‹‹ልጄን ከግብፅ ጠራሁት›› ብሎ በነቢዩ የተናገረው ቃል ተፈጸመ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 16 ከዚያም ሄሮድስ ጠቢባኑ እንደ ተሣለቁበት ሲገነዘብ በጣም ተናደደ፡፡ በቤተ ልሔምና በዚያ አውራጃ የነበሩ ወንድ ሕፃናትን፣ እንደዚሁም ሁለት ዓመትና ከዚያም በታች የሆኑትን ሁሉ ከጠቢባኑ በትክክል በተረዳው ጊዜ መሠረት ልኮ አስፈጀ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 17 በዚያም በነቢዩ ኤርምያስ ተነግሮ የነበረው፡-
|
||
\v 18 ‹‹ድምፅ በራማ ተሰማ፣ ልቅሶና መሪር ዋይታ፣ ራሔል ስለ ልጆቿ በማልቀስ፣ ለመጽናናትም እምቢ አለች፣ በሕይወት የተረፈ የለምና›› የሚለው ተፈጸመ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 19 ሄሮድስ ሲሞት፣ እነሆ፣ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ተገለጠለትና፣
|
||
\v 20 ‹‹ሕፃኑን ሊገድሉት የፈለጉት ስለ ሞቱ፣ ተነሣ፤ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ›› አለው፡፡
|
||
\v 21 ዮሴፍ ተነሣ፣ ሕፃኑንና እናቱን ይዞ ወደ እስራኤል አገር ሄደ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 22 አርኬላዎስ በአባቱ በሄሮድስ ስፍራ ተተክቶ ይሁዳን ይገዛ እንደ ነበረ ሲሰማ ግን ወደዚያ ለመሄድ ፈራ፡፡ እግዚአብሔር በሕልም ካስጠነቀቀው በኋላ፣ ወደ ገሊላ አውራጃ ሄደ፤
|
||
\v 23 ናዝሬት በምትባል ከተማ ውስጥም ኖረ፡፡ ይህ በነቢዩ ተነግሮ የነበረውን፣ ናዝራዊ ተብሎ ይጠራል የሚለውን እንዲፈጸም አደረገ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 3
|
||
\cl ምዕራፍ 3
|
||
\p
|
||
\v 1 በእነዚያ ቀኖች መጥምቁ ዮሐንስ በይሁዳ ምድረ በዳ ፤
|
||
\v 2 "መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ" እያለ እየሰበከ መጣ።
|
||
\v 3 በነቢዩ ኢሳይያስ፦ "ምድረ በዳ ውስጥ የሚጮኽ ሰው ድምፅ፣ የጌታን መንገድ አዘጋጁ፣ ጎዳናዎቹንም አስተካክሉ" ተብሎ የተነገረለት ይህ ነውና።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 4 ዮሐንስ ይለብስ የነበረው የግመል ጠጕር፣ በወገቡ የሚታጠቀውም የቆዳ ጠፍር ነው፤ ምግቡም አንበጣና የዱር ማር ነበረ።
|
||
\v 5 በዚያ ጊዜ ኢየሩሳሌም፣ መላው ይሁዳና በዮርዳኖስ ወንዝ ዙሪያ ያለ አገር ሁሉ ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።
|
||
\v 6 ሕዝቡ ኀጢአታቸውን እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ በእርሱ እጅ ተጠመቁ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 7 ነገር ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ለመጠመቅ ወደ እርሱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፣ "እናንተ የመርዛማ እባቦች ልጆች ከሚመጣው ቊጣ ለማምለጥ ማን አስጠነቀቃችሁ?
|
||
\v 8 ለንስሐ የሚጠቅም ፍሬ ይኑራችሁ።
|
||
\v 9 ለራሳችሁም አብርሃም አባታችን አለን" ብላችሁ አታስቡ። እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች እንኳ ለአብርሃም ልጆችን ማስነሣት እንደሚችል እነግራችኋለሁና።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 10 አሁን መጥረቢያው በዛፎቹ ሥር ተቀምጦአል። ስለዚህ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል በእሳት ውስጥም ይጣላል።
|
||
\v 11 እኔ ለንስሐ የማጠምቃችሁ በውሃ ነው፤ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቃል፤ ጫማውን መሸከምም እንኳ አይገባኝም። እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል።
|
||
\v 12 ዐውድማውን ፈጽሞ ለማጥራትና ስንዴውን በጎተራ ውስጥ ለመክተት መንሹ በእጁ ነው። ገለባውን ግን ፈጽሞ በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 13 ከዚያም ኢየሱስ በዮሐንስ እጅ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መጣ።
|
||
\v 14 ነገር ግን "እኔ አንተ እንድታጠምቀኝ ሲገባ፣ አንተ እንዴት ወደ እኔ ትመጣለህ?" በማለት ሊያስቆመው ሞከረ።
|
||
\v 15 ኢየሱስም መልሶ፣ "አሁን ይህን ፍቀድ፤ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ለእኛ ተገቢ ነውና" አለው። ከዚያም በኋላ ዮሐንስ ፈቀደለት።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 16 ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ፣ ወዲያውኑ ከውሃ ውስጥ ወጣ፤ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ። የእግዚአብሔር መንፈስ በርግብ መልክ ሲወርድና በእርሱ ላይ ሲቀመጥ አየ።
|
||
\v 17 እነሆ፣ የምወደው ልጄ ይህ ነው። "በእርሱ እጅግ ደስ ይለኛል" የሚል ድምፅ ከሰማያት መጣ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 4
|
||
\cl ምዕራፍ 4
|
||
\p
|
||
\v 1 ከዚያም በኋላ በዲያብሎስ ሊፈተን መንፈስ ኢየሱስን ወደ ምድረ በዳ መራው፡፡
|
||
\v 2 ኢየሱስ ዐርባ ቀንና ዐርባ ሌሊት ከጾመ በኋላ ተራበ፡፡
|
||
\v 3 ፈታኙ ወደ እርሱ መጣና፣ ‹‹የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፣ እንጀራ እንዲሆኑ እነዚህን ድንጋዮች እዘዛቸው›› አለው፡፡
|
||
\v 4 ኢየሱስ ግን መለሰና፣ ‹‹ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል" አለው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 5 ከዚያም ዲያብሎስ ወደ ቅድስቲቱ ከተማ ወሰደው፤ በቤተ መቅደስ ሕንጻ ዐናት ላይም አቁሞ፣
|
||
\v 6 የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፣ ራስህን ወደ ታች ወርውር፤ ‹እንዲጠብቁህ መላእክቱን ይልካል፣› እና ‹‹እግርህ ድንጋይ እንዳይመታው፣ በእጆቻቸው ያነሡሃል›› ተብሎ ተጽፎአል አለው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 7 ኢየሱስም፣ ‹‹‹ጌታ አምላክህን አትፈታተን› ተብሎም ተጽፎአል›› አለው፡፡
|
||
\v 8 እንደ ገናም ዲያብሎስ ወደ አንድ ተራራ ወሰደውና የዓለምን መንግሥታት ሁሉ ከሙሉ ክብራቸው ጋር አሳየው፡፡
|
||
\v 9 ‹‹ብትወድቅና ብትሰግድልኝ፣ እነዚህን ሁሉ እሰጥሃለሁ›› አለው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 10 ከዚያም ኢየሱስ፣ አንተ ሰይጣን ከዚህ ሂድ! ‹ለጌታ ለአምላክህ ስገድ፣ እርሱንም ብቻ አምልክ››› ተብሎ ተጽፎአልና አለው፡፡
|
||
\v 11 ከዚያ በኋላ ዲያብሎስ ተወው፤ እነሆም፣ መላእክት መጡና ኢየሱስን አገለገሉት፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 12 ኢየሱስ የዮሐንስን መያዝ ሲሰማ፣ ወደ ገሊላ ሄደ፡፡
|
||
\v 13 ናዝሬትን ትቶ በመሄድ በዛብሎንና በንፍታሌም አገር በገሊላ ባሕር አጠገብ ባለው በቅፍርናሆም ኖረ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 14 ይህ የሆነው፣ በነቢዩ ኢሳይያስ ተነግሮ የነበረው እንዲፈጸም ነው፤ ይኸውም፡-
|
||
\v 15 ‹‹የዛብሎን ምድርና የንፍታሌም ምድር፣ በባሕሩ አቅጣጫ፣ ከዮርዳኖስ ማዶ፣ የአሕዛብ ገሊላ!
|
||
\v 16 በጨለማ ውስጥ የኖረ ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፣ በሞት ጥላና ምድር ውስጥ ለሚኖሩትም፣ ብርሃን ወጣላቸው›› የሚለው ነው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 17 ኢየሱስ ከዚያ ጊዜ አንሥቶ፣ ‹‹መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ›› እያለ መስበክ ጀመረ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 18 ኢየሱስ በገሊላ ባሕር አጠገብ እየሄደ ሳለ፣ ሁለት ወንድማማቾችን አየ፤ ጴጥሮስ ተብሎ የሚጠራው ስምዖንና ወንድሙ እንድርያስ ዓሣ አጥማጆች ስለ ነበሩ፣ ወደ ባሕሩ መረብ እየጣሉ ነበር፡፡
|
||
\v 19 ኢየሱስ፣ ‹‹ኑ፣ ተከተሉኝ፤ ሰዎችን የምታጠምዱ አደርጋችኋለሁ›› አላቸው፡፡
|
||
\v 20 እነርሱም ወዲያውኑ መረባቸውን ትተው ተከተሉት፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 21 ኢየሱስ ከዚያ ዐለፍ እንዳለም ሁለት ሌሎች ወንድማማቾችን፣ የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብንና ወንድሙን ዮሐንስን አየ፤ ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በጀልባ ውስጥ መረቦቻቸውን ያበጃጁ ነበር፡፡ ኢየሱስም ጠራቸው፡፡
|
||
\v 22 ወዲያውኑ ጀልባዋንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 23 ኢየሱስ በምኵራቦቻቸው ውስጥ እያስተማረ፣ የመንግሥትን ወንጌልም እየሰበከና በሕዝቡ መካከል ያሉ በሁሉም የደዌና የበሽታ ዐይነት የሚሠቃዩትን እየፈወሰ በመላው ገሊላ ተዘዋወረ፡፡
|
||
\v 24 ስለ እርሱ በሶርያ ምድር ሁሉ ተወራ፤ ሕዝቡም የታመሙትን ሁሉ፣ በልዩ ልዩ ደዌና ሕመም የሚሠቃዩትን፣ በአጋንንት የተያዙትንና የሚጥል በሽታ ያለባቸውን፣ ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው፡፡
|
||
\v 25 ከገሊላ፣ ከዐሥሩ ከተሞች፣ ከኢየሩሳሌም፣ ከይሁዳና ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ እጅግ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 5
|
||
\cl ምዕራፍ 5
|
||
\p
|
||
\v 1 ኢየሱስ ሕዝቡን ሲያይ፣ ወደ ተራራ ወጣ፤ እዚያም ሲቀመጥ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ መጡ።
|
||
\v 2 እንደዚህ እያለም አስተማራቸው፤
|
||
\v 3 በመንፈስ የደኸዩ የተባረኩ ናቸው፤ መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ናትና።
|
||
\v 4 የሚያዝኑ የተባረኩ ናቸው፤ ይጽናናሉና።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 5 የዋሆች የተባረኩ ናቸው፤ ምድርን ይወርሳሉና።
|
||
\v 6 ለጽድቅ የሚራቡና የሚጠሙ የተባረኩ ናቸው፤ ይጠግባሉና።
|
||
\v 7 የሚምሩ የተባረኩ ናቸው፤ ይማራሉና።
|
||
\v 8 ልበ ንጹሖች የተባረኩ ናቸው እግዚአብሔርን ያዩታልና።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 9 የሚያስታርቁ የተባረኩ ናቸው፤ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።
|
||
\v 10 ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ የተባረኩ ናቸው፤ መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ናትና።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 11 ሰዎች ሲሰድቧችሁና ሲያሳድዷችሁ፣ ወይም በእኔ የተነሣ ክፉውን ሁሉ በእናንተ ላይ በሐሰት ሲናገሩ ብፁዓን ናችሁ።
|
||
\v 12 በሰማይ ዋጋችሁ ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፣ ሐሤትም አድርጉ። ሰዎች ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያት በዚህ መንገድ አሳድደዋቸዋልና።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 13 እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው ጣዕሙን ካጣ፣ እንደ ገና ጨው እንዴት መሆን ይችላል? ወደ ውጭ ተጥሎ በእግር ከመረገጥ በቀር ፈጽሞ ለምንም አይጠቅምም።
|
||
\v 14 እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ የተመሠረተች ከተማ ልትሰወር አትችልም።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 15 ሰዎች መብራት አብርተው ቤት ውስጥ ላሉት ሁሉ እንዲበራ በመቅረዝ ላይ ያስቀምጡታል እንጂ በቅርጫት ሥር አያስቀምጡትም።
|
||
\v 16 መልካሙን ሥራችሁን እንዲያዩና በሰማይ ያለ አባታችሁን እንዲያከብሩት መብራታችሁ እንዲሁ በሰዎች ፊት ይብራ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 17 ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ የመጣሁት ልሽራቸው ሳይሆን ልፈጽማቸው ነው።
|
||
\v 18 ምክንያቱም፣ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ፣ ሁሉ እስኪፈጸምም ድረስ፣ ከሕግ እንዷ ፊደል ወይም ቅንጣት ከቶ አታልፍም ብዬ በእውነት እነግራችኋለሁ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 19 እንግዲህ ከእነዚህ ትእዛዞች ትንሿን የሚሽርና ለሌሎችም እንዲሁ እንዲያደርጉ የሚያስተምር፣ በመንግሥተ ሰማይ ታናሽ ይባላል። የሚጠብቃቸውና የሚያስተምራቸው ግን በመንግሥተ ሰማይ ታላቅ ይባላል።
|
||
\v 20 ምክንያቱም፣ ጽድቃችሁ ከሕግ መምህራንና ከፈሪሳውያን ጽድቅ ልቆ ካልተገኘ መንግሥተ ሰማይ ከቶ አትገቡም እላችኋለሁ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 21 ለቀደሙት፣ 'አትግደል፣ የገደለ ይፈረድበታል' እንደ ተባለ ሰምታችኋል።
|
||
\v 22 እኔ ግን፣ 'ወንድሙን የሚቆጣ ሁሉ ይፈረድበታል፣ ወንድሙን፣ 'አንተ የማትረባ!' የሚለው የሸንጎ ፍርድ፣ 'ቂል' የሚለውም የገሃነመ እሳት ፍርድ ይፈረድበታል።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 23 እንግዲህ መባህን በመሠዊያው ላይ ልታቀርብ ከሆነና ወንድምህ አንዳች ነገር በአንተ ላይ እንዳለው ካስታወስህ፣
|
||
\v 24 መባህን በመሠዊያው ፊት ትተህ ሂድ፣ በቅድሚያ ከወንድምህ ጋር ታረቅ፣ ከዚያም ተመልሰህ መጥተህ መባህን አቅርብ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 25 ባላጋራህ ለዳኛው፣ ዳኛውም ለአሳሪው አሳልፎ እንዳይሰጥህና በወህኒ ውስጥ እንዳትጣል፣ ወደ ፍርድ ቤት ዐብረኸው እየሄድህ ሳለ ከሚከስስህ ባላጋራህ ጋር በፍጥነት ተስማማ።
|
||
\v 26 እውነት እነግርሃለሁ፣ የመጨረሻዋን ሳንቲም እስክትከፍል ድረስ ከዚያ ፈጽሞ አትወጣም።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 27 "አታመንዝር" እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤
|
||
\v 28 እኔ ግን፣ ሴትን ተመኝቷት የሚመለከት ሁሉ በልቡ አመንዝሯል እላችኋለሁ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 29 የቀኝ ዐይንህ ቢያሰናክህል አውጥተህ ጣለው፤ መላ ሰውነትህ በገሃነም ከሚቃጠል፣ ከሰውነትህ ክፍሎች አንዱ ቢጠፋ ይሻልሃልና።
|
||
\v 30 የቀኝ እጅህም ቢያሰናክልህ ቆርጠህ ጣለው፤ መላ ሰውነትህ ገሃነም ውስጥ ከሚገባ ከሰውነትህ ክፍሎች አንዱ ቢጠፋ ይሻልሃል።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 31 'ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ የፍቺ ማረጋገጫ ይስጣት' ተብሎአል።
|
||
\v 32 እኔ ግን፣ 'በዝሙት ምክንያት ካልሆነ በቀር ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ፣ እንድታመንዝር ያደርጋታል፤ ከተፈታች በኋላ የሚያገባትም ምንዝርና ይፈጽማል።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 33 ደግሞም ለቀደሙት፣ በሐሰት አትማል፣ መሐላዎችህንም ለጌታ ስጥ እንደ ተባለ ሰምታችኋል።
|
||
\v 34 እኔ ግን ከቶ አትማሉ፤ በሰማይም፣ የእግዚአብሔር ዙፋን ነውና፤
|
||
\v 35 በምድርም፣ እግሩ የሚያርፍባት ናትና፤ በኢየሩሳሌምም፣ የታላቁ ንጉሥ ከተማ ናትና።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 36 በራሳችሁም አትማሉ፤ አንዷን ጠጕር ነጭ ወይም ጥቍር ማድረግ አትችሉምና።
|
||
\v 37 ነገር ግን ንግግራችሁ 'አዎ፣ አዎ'፣ ወይም 'አይደለም፣ አይደለም' ይሁን። ከዚህ የወጣ ሁሉ ከክፉው ነው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 38 ዐይን ስለ ዐይን፣ ጥርስ ስለ ጥርስ እንደ ተባለ ሰምታችኋል፣
|
||
\v 39 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ 'ክፉውን ሰው አትቃወሙት፣ ይልቁን የቀኝ ጕንጭህን ለሚመታህ ሌላውንም አዙርለት።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 40 ማንም ሰው ሊከስስህና ኮትህን ሊወስድ ቢመኝ፣ ካባህንም ይውሰድ።
|
||
\v 41 አንድ ምዕራፍ እንድትሄድ ማንም ሰው ቢያስገድድህ፣ ዐብረኸው ሁለት ምዕራፍ ሂድ።
|
||
\v 42 ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፣ ከአንተ መበደር ከሚፈልገውም ፊትህን አታዙር።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 43 ባልንጀራህን ውደድ፣ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል።
|
||
\v 44 እኔ ግን ጠላቶችህን ውደድ ለሚያሳድዷችሁም ጸልዩ ብዬ እነግራችኋለሁ።
|
||
\v 45 ይኸውም በሰማያት ያለ አባታችሁ ልጆች እንድትሆኑ ነው። እርሱ ፀሐይን በክፉዎችና በደጎች ላይ ያወጣል፤ ዝናብም በጻድቃንና በኅጥኣን ላይ ያዘንባል።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 46 የሚወድዷችሁን ብትወዱ፣ ምን ዋጋ ታገኛላችሁ? ቀራጮች እንኳ እንደዚህ ያደርጉ የለምን?
|
||
\v 47 ለወንድሞቻችሁ ብቻ ሰላምታ ብታቀርቡ፣ ከሌሎች የበለጠ የምታደርጉት ምንድን ነው? አሕዛብስ እንኳ ይህንኑ ያደርጉ የለምን?
|
||
\v 48 እንግዲህ የሰማይ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 6
|
||
\cl ምዕራፍ 6
|
||
\p
|
||
\v 1 ሰዎች እንዲያዩአችሁ የጽድቅ ተግባሮቻችሁን በፊታቸው ከማከናወን ተጠንቀቁ፤ አለበለዚያ ከሰማይ አባታችሁ ዋጋ አታገኙም፡፡
|
||
\v 2 ስለዚህ አንተ ምጽዋት ስትሰጥ ግብዞች የሰዎችን ከበሬታ ለማግኘት በምኵራቦችና በጐዳና ላይ እንደሚያደርጉት፣ በፊትህ ጥሩንባ አታስነፋ፡፡ በእውነት እነግራችኋለሁ፣ ዋጋቸውን ተቀብለዋል፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 3 አንተ ግን ምጽዋት ስትሰጥ፣ የቀኝ እጅህ የሚያደርገውን የግራ እጅህ እንዲያውቅ አታድርግ፤
|
||
\v 4 ይኸውም ምጽዋትህ በስውር የሚሰጥ እንዲሆንና ከዚያም በስውር የሚያይ አባትህ ዋጋህን እንዲከፍልህ ነው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 5 ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ግብዞች ሕዝብ እንዲያያቸው በምኵራቦችና በጐዳና ማእዘኖች ላይ ቆመው መጸለይ ይወዳሉና፡፡ በእውነት እነግራችኋለሁ፤ ዋጋቸውን ተቀብለዋል፡፡
|
||
\v 6 አንተ ግን ስትጸልይ ወደ ጓዳህ ገብተህ በር ዝጋና በስውር ወዳለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል፡፡
|
||
\v 7 ስትጸልይም አሕዛብ እንደሚያደርጉት ረብ የለሽ ድግግሞሽ አታድርግ፤ አሕዛብ በንግግራቸው ብዛት ምክንያት የሚሰሙ ይመስላቸዋልና፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 8 ስለዚህ እንደ እነርሱ አትሁኑ፤ እናንተ ከመለመናችሁ በፊት ምን እንደሚያስፈልጋችሁ አባታችሁ ያውቃልና፡፡
|
||
\v 9 እንግዲህ እንደዚህ ጸልዩ፡- ‹በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ፡
|
||
\v 10 መንግሥትህ ትምጣ፡፡ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች፣ እንዲሁ በምድር ትሁን፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 11 የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፡፡
|
||
\v 12 በደላችንን ይቅር በለን፣ እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል፡፡
|
||
\v 13 ወደ ፈተና አታግባን፣ ከክፉው አድነን እንጂ፡፡› [መንግሥት፣ ኀይል፣ ክብርም የአንተ ነውና፣ ለዘላለም፣ አሜን፡፡]
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 14 የሰዎችን ኀጢአት ይቅር ብትሉ፣ የሰማይ አባታችሁ እናንተንም ይቅር ይላችኋል፡፡
|
||
\v 15 የሰዎችን ኀጢአት ይቅር ካላላችሁ ግን፣ የሰማይ አባታችሁ የእናንተን ኀጢአት ይቅር አይልም፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 16 ስትጾሙም ግብዞች እንደሚያደርጉት ፊታችሁን አታጠውልጉ፤ እንደ ጾመኛ ለመታየት ግብዞች ፊታቸውን ያጠወልጋሉና፡፡ በእውነት እነግራችኋለሁ፣ዋጋቸውን ተቀብለዋል፡፡
|
||
\v 17 አንተ ግን ስትጾም ራስህን ተቀባ፣ ፊትሀንም ታጠብ፣
|
||
\v 18 ይኸውም፣ በስውር ላለው የሰማይ አባትህ ብቻ እንጂ ለሰዎች ጾመኛ መስለህ እንዳትታይ ነው፡፡ በስውር የሚያይ የሰማይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 19 ብልና ዝገት በሚበላውና ሌቦችም ሰብረው በሚሰርቁበት በምድር ላይ ሀብትን ለራሳችሁ አታከማቹ፡፡
|
||
\v 20 ይልቁን ብልም ሆነ ዝገት በማያጠፋበት፣ ሌቦችም ሰብረው በማይሰርቁበት በሰማይ ሀብትን ለራሳችሁ አከማቹ፡፡
|
||
\v 21 ሀብታችሁ ባለበት ልባችሁም ይገኛልና፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 22 ዐይን የሰውነት መብራት ነው፡፡ ስለሆነም ዐይንህ ጤናማ ከሆነ፣ መላ ሰውነትህ በብርሃን ይሞላል፡፡
|
||
\v 23 ዐይንህ ጤናማ ካልሆነ ግን፣ መላ ሰውነትህ ጨለማ ይሆናል፡፡ እንግዲህ በውስጥህ ያለው መብራት በእውነት ጨለማ ከሆነ፣ ጨለማው እንዴት ከባድ ይሆን
|
||
\v 24 ! ሁለት ጌቶችን ማገልገል የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ይጠላል ሌላውንም ይወዳል፣ ወይም ለአንዱ ይታዘዛል ሌላውን ደግሞ ይንቃል፡፡ እግዚአብሔርንና ሀብትን ማገልገል አትችሉም፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 25 ስለዚህ ስለ ሕይወታችሁ ምን እንደምትበሉ ወይም ምን እንደምትጠጡ፡- ወይም ስለ ሰውነታችሁ ምን እንደምትለብሱ አትጨነቁ፤ ሕይወት ከምግብ፣ ሰውነትስ ከልብስ አይበልጥምን?
|
||
\v 26 አየር ላይ የሚበርሩ ወፎችን ተመልከቱ! እነርሱ እህል አይዘሩም ወይም አያጭዱም፣ በጐተራም አያከማቹም፤ ይሁን እንጂ፣ የሰማይ አባታችሁ ይመግባቸዋል፡፡ ከወፎች ይልቅ እናንተ እጅግ የሚበልጥ ዋጋ ያላችሁ አይደላችሁምን?
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 27 ከእናንተ መካከል ተጨንቆ በዕድሜው ላይ አንድ ቀን መጨመር የሚችል ይገኛልን?
|
||
\v 28 ስለ ልብስስ የምትጨነቁት ለምንድን ነው?
|
||
\v 29 ነገር ግን እነግራችኋለሁ፤ ሰሎሞን እንኳ በዚያ ክብሩ ሁሉ ከእነዚህ አበቦች እንደ አንዱ አልለበሰም፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 30 እግዚአብሔር ዛሬ የሚታየውንና ነገ እሳት ውስጥ የሚጣለውን የሜዳ ሣር እንደዚህ ካለበሰ፣ እናንት እምነት የጐደላችሁ! እናንተንማ እንዴት እጅግ የበለጠ አያለብሳችሁም?
|
||
\v 31 እንግዲህ ‹ምን እንበላለን?› ወይም ‹ምን እንጠጣለን?› ወይም ‹ምን እንለብሳለን?› ብላችሁ አትጨነቁ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 32 አሕዛብ እነዚህን ሁሉ ይፈልጋሉና፤ የሰማይ አባታችሁ እነዚህ ሁሉ እንደሚያስፈልጓችሁ ያውቃል፡፡
|
||
\v 33 ነገር ግን በመጀመሪያ መንግሥቱንና ጽድቁን ፈልጉ፤ ከዚያም እነዚህ ሁሉ ይጨመሩላችኋል፡፡
|
||
\v 34 ስለዚህ ለነገ አትጨነቁ፤ ነገ ለራሱ ይጨነቃልና፡፡ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 7
|
||
\cl ምዕራፍ 7
|
||
\p
|
||
\v 1 አትፍረዱ፥ እናንተም አይፈረድባችሁም።
|
||
\v 2 በምትፈርዱበት ፍርድ፥ ይፈረድባችኋል፤በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ፥ ለእናንተም ይሰፈርላችኋል።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 3 በራስህ ዐይን ውስጥ ያለውን ግንድ ሳታስተውል፥ በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ የምታየው ለምንድን ነው?
|
||
\v 4 በአንተ ዐይንህ ውስጥ ግንድ እያለ፣ በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ላውጣልህ ማለት እንዴት ትችላለህ?
|
||
\v 5 አንተ ግብዝ! በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ በደንብ አይተህ ለማውጣት፣ በመጀመሪያ በራስህ ዐይን ውስጥ ያለውን ግንድ አስወግድ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 6 በእግራቸው እንዳይረግጡትና እናንተንም እንዳይቦጫጭቁዋችሁ፤ ቅዱስ የሆነውን ለውሾች አትስጡ፥ እንቁዎቻችሁንም ለዐሳማዎች አትጣሉ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 7 ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፥ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣ ይከፈትላችኋል።
|
||
\v 8 የሚለምን ሰው ሁሉ ይቀበላልና፣ የሚፈልግ ሰውም ያገኛል፥ ለሚያንኳኳም ሰው ይከፈትለታል።
|
||
\v 9 ከእናንተ መካከል ልጁ እንጀራ ሲለምነው፣ ድንጋይ የሚሰጠው፣
|
||
\v 10 ዐሣ ሲለምነው፣ እባብ የሚሰጠው? ምን ዐይነት ሰው ነው?
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 11 እንግዲህ፥ እናንተ ክፉዎች የሆናችሁ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ፥ በሰማይ የሚኖር አባታችሁ ለሚለምኑት አብዝቶ መልካም ስጦታን እንዴት አይስጣቸውም?
|
||
\v 12 ስለዚህ፣ ማንኛውንም ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ሁሉ፣ እናንተም ልታደርጉላቸው ይገባል፤ ምክንያቱም ሕጉም ነቢያቱም የሚያስተምሩት ይህንኑ ነው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 13 በጠባቡ በር ግቡ፣ ምክንያቱም ወደ ጥፋት የሚወስደው መንገድ ሰፊ፣ የሚሄዱበትም ብዙዎች ናቸው፡፡
|
||
\v 14 በሩ ጠባብ፣ ወደ ሕይወት የሚወስደውም መንገድ ቀጭን ስለ ሆነ፣ የሚያገኙት ጥቂቶች ናቸው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 15 የበግ ቆዳ ለብሰው ከሚመጡባችሁ፣ በትክክል ግን ነጣቂ ተኩላዎች ከሆኑ፣ ከሃሰተኛ ነቢያት ተጠንቀቁ።
|
||
\v 16 በሚያፈሩት ፍሬ ታውቋቸዋላችሁ፡፡ሰው ከእሾኽ የወይን ፍሬ፣ ወይም ከኩርንችት በለስ ሊሰበስብ ይችላልን?
|
||
\v 17 እንደዚያው፥ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያፈራል፣ መጥፎ ዛፍ መጥፎ ፍሬ ያፈራል።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 18 መልካም ዛፍ ሆኖ መጥፎ ፍሬ የሚያፈራ፣ ወይም መጥፎ ዛፍ ሆኖ መልካም ፍሬ የሚያፈራ ዛፍ የለም።
|
||
\v 19 ማንኛውም መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል፣ ወደ እሳትም ይጣላል።
|
||
\v 20 እንግዲህ በሚያፈሩት ፍሬ ታውቋቸዋላችሁ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 21 በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ እንጂ፣" ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ፣" እያለ የሚጠራኝ ሁሉ፣ ወደ መንግሥተ ሰማይ የሚገባ አይደለም፡፡
|
||
\v 22 በዚያ ቀን ብዙዎች፣ "ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ፣ በስምህ ትንቢት ተናግረን አልነበረም እንዴ፣ በስምህ አጋንንት አስወጥተን አልነበረም እንዴ፣ በስምህስ ብዙ ታላላቅ ነገሮችን አድርገን አልነበረም እንዴ?" ይሉኛል፡፡
|
||
\v 23 እኔም፣ “እናንት ክፉ አድራጊዎች፣ የት ዐውቃችሁና ነው? ከእኔ ራቁ ብዬ በግልጽ እነግራቸዋለሁ”
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 24 ስለዚህ፣ ቃሎቼን የሚሰማና የሚታዘዛቸው ልክ ቤቱን በድንጋይ ላይ የመሠረተ አስተዋይ ሰውን ይመስላል፡፡
|
||
\v 25 ዝናብ ዘነበ፣ ጎርፍም ጎረፈ፣ ነፋስም ነፈሰ ያንን ቤት መታው፤ ይሁን እንጂ ቤቱ በዐለት ላይ ስለ ተመሠረተ፣ አልወደቀም፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 26 ሆኖም ቃሌን ሰምቶ የማይታዘዝ፣ ቤቱን በአሸዋ ላይ የመሠረተ ሞኝ ሰውን ይመስላል፡፡
|
||
\v 27 ዝናብ ዘነበ፣ ጎርፍ ጎረፈ፣ ነፋስም ነፈሰ፣ ያንንም ቤት መታው፤ ቤቱም ወደቀ፤ አወዳደቁም ከባድ ሆነ ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 28 ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ተናግሮ ሲጨርስ፣ ሕዝቡ በትምህርቱ ተገረሙ፡፡
|
||
\v 29 ያስተማረውም እንደ ባለስሥልጣን እንጂ ፣እንደ ጽሐፍት አልነበረም።
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 8
|
||
\cl ምዕራፍ 8
|
||
\p
|
||
\v 1 ኢየሱስ ከተራራው በወረደ ጊዜ፣ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት።
|
||
\v 2 እነሆ፣ አንድ ለምጻም ወደ እርሱ መጣ፣ “ጌታ ሆይ፣ ፈቃደኛ ከሆንህ፣ ልታነጻኝ ትችላለህ” በማለት በፊቱ ሰገደለት።
|
||
\v 3 ኢየሱስም፣ “ፈቃደኛ ነኝ ንጻ” በማለት እፉን ዘርግቶ ዳሰሰው። ወዲያውኑ ከለምጹ ነጻ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 4 ኢየሱስ፣ “ተጠንቀቅ! ለማንም አትናገር። ዝም ብለህ ሂድና ራስህን ለካህን አሳይ፣ምስክር እንዲሆናቸውም ሙሴ ያዘዘውን ስጦታ አቅርብ”አለው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 5 ኢየሱስ ወደቅፍርናሆም በገባ ጊዜ፣ አንድ የመቶ አለቃ ወደ እርሱ መጥቶ፣
|
||
\v 6 ጌታ ሆይ፣ "አገልጋዬ በከባድ ሕመም ሽባ ሆኖ ቤቴ ተኝቷል" በማለት ለመነው።
|
||
\v 7 ኢየሱስ፣ "መጥቼ እፈውሰዋለሁ” አለው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 8 የመቶ አለቃውም መልሶ፣“ጌታ ሆይ፣ አንተ ወደ ቤቴ ጣራ በታች ልትገባ አይገባኝም፣ ነገር ግን ቃል ብቻ ተናገር አገልጋዬም ይፈወሳል” አለው፡፡
|
||
\v 9 እኔ ደግሞ ከሌላው ሥልጣን ሥር ያለሁና በእኔም ሥልጣን ሥር ወታደሮች ያሉኝ ሰው ነኝ። አንዱን “ሂድ” ብለው ይሄዳል፤ ሌላውንም “ና” ብለው ይመጣል፣ አገልጋዬንም 'ይህን አድርግ' ብለው ያደርጋል"፡፡
|
||
\v 10 ኢየሱስም ይህን በሰማ ጊዜ በጣም ተደነቀ፣ ይከተሉት ለነበሩት ሰዎችም “እውነት ነው የምነግራችሁ፣ በእስራኤል እንኳ እንደዚህ ያለ ትልቅ እምነት አላገኘሁም” አላቸው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 11 እነግራችኋለሁ ብዙዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ ይመጣሉ፣ በእግዚአብሔር መንግሥትም ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር በማዕድ ይቀመጣሉ።
|
||
\v 12 የመንግሥት ልጆች ግን ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ወደ ውጪው ጨለማ ይጣላሉ፡፡
|
||
\v 13 ኢየሱስም የመቶ አለቃውን፣ “ሂድ! እንደ እምነትህ ይሁንልህ" አለው። አገልጋዩም በዚያው ሰዓት ተፈወሰ ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 14 ኢየሱስ ወደ ጴጥሮስ ቤት በገባ ጊዜ የጴጥሮስን አማት በትኩሳት ታማ ተኝታ አገኛት።
|
||
\v 15 ኢየሱስ እጅዋን ነካት፣ ትኩሳቱም ለቀቃት፣ ተነሥታም ታገለግለው ጀመር።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 16 በመሸ ጊዜ፣ ሕዝቡ አጋንንት የያዙአቸውን ብዙዎችን ወደ ኢየሱስ አመጡ፣ እርሱም በቃሉ፣ መናፍስቱን አስወጣቸው፤ ታመው የነበሩትንም ሁሉ ፈወሳቸው።
|
||
\v 17 በዚህ ዐይነት፣ በነቢዩ ኢሳይያስ፣ “እርሱ ሕመማችንን ተቀበለ ደዌዎቻችንን ተሸከመ” ተብሎ የተነገረው ተፈጸመ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 18 ኢየሱስም በዙሪያው ያሉትን ሕዝብ ባየ ጊዜ፣ ወደ ገሊላ ባሕር ማዶ እንዲሻገሩ አዘዘ።
|
||
\v 19 ከዚያም አንድ ጸሐፊ ወደ እርሱ ቀርቦ፣ “መምህር ሆይ፣ ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ” አለው።
|
||
\v 20 ኢየሱስም "ቀበሮዎች ጉድጓድ የሰማይ ወፎችም ጎጆዎች አሏቸው። የሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያሳርፍበት ምንም ስፍራ የለውም"አለው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 21 ከደቀመዛሙርቱም ሌላው፣ "ጌታ ሆይ፣ በመጀመሪያ እንድሄድና አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ አለው።"
|
||
\v 22 ኢየሱስ ግን፣ “ተከተለኝ፣ ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው” አለው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 23 ኢየሱስ ወደ ጀልባ በገባ ጊዜ፣ ደቀ መዛሙርቱም ተከትለውት ገቡ።
|
||
\v 24 እነሆም፣ በባሕሩ ላይ ታላቅ ማዕበል ተነሥቶ ጀልባዋ በማዕበል ተሸፈነች። ኢየሱስ ግን ተኝቶ ነበር።
|
||
\v 25 ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ መጥተው፣ "ጌታ ሆ፣ እድነን ልንጠፋ ነው" በማለት ቀሰቀሱት።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 26 ኢየሱስ፣ "እናንተ እምነት የጐደላችሁ ስለምን ፈራችሁ?”አላቸው። ከዚያም ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠፀ፣ ከዚያ በኋላ ታላቅ ጸጥታ ሆነ።
|
||
\v 27 ሰዎቹም ተገርመው፣ "ይህ ምን ዓይነት ሰው ነው? ነፋሳትና ባሕሩም እንኳ ይታዘዙለታል" አሉ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 28 ኢየሱስም ወደ ማዶ ወደ ጌርጌሴኖን አገር በመጣ ጊዜ፣ አጋንንት የተቆጣጠራቸው ሁለት ሰዎች ተገናኙት። የመጡትም ከመቃብር ነበርና በዚያ ማንም ማለፍ እስከማይችል ድረስ በጣም ኅይለኞች ነበሩ።
|
||
\v 29 እነሆም፣ እየጮኹ፣ "አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ፣ እኛ ከአንተ ምን ጉዳይ አለን? ጊዜው ሳይደርስ ልታሠቃየን ወደዚህ መጣህን?" አሉ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 30 ከዚያ አካባቢ ብዙ ሳይርቅ በግጦሽ ላይ ያሉ ብዙ ዐሳማዎች ነበሩ።
|
||
\v 31 አጋንንቱም ኢየሱስን፣ "የምታወጣን ከሆነ ወደዚያ የዐሳማዎች መንጋ ስደደን" ብለው መለመናቸውን ቀጠሉ።
|
||
\v 32 ኢየሱስም፣ "ሂዱ!"አላቸው። አጋንንቱም ወጥተው ዐሳማዎቹ ውስጥ ገቡ፤ እነሆም፣ የዐሳማዎቹ መንጋ ሁሉ ወደ ታች ቁልቁለቱን እየተጣደፉ ወደ ባሕሩ ወርደው ውሃው ውስጥ ገብተው ጠፉ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 33 እነዚያም ዐሳማዎቹን ይጠብቁ የነበሩት ሰዎች ሸሽተው ወደ ከተማ ሄደው የሆነውን ሁሉ ፣ በአጋንንት ተይዘው ስለ ነበሩት ሰለ ሁሉቱ ሰዎችም አወሩ።
|
||
\v 34 የከተማውም ሕዝብ ሁሉ ኢየሱስን ለማየት መጡ። ባዩትም ጊዜ አካባቢያቸውን ለቆ አንዲሄድ ለመኑት።
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 9
|
||
\cl ምዕራፍ 9
|
||
\p
|
||
\v 1 ኢየሱስ ወደ ጀልባ ገባ፤ ባሕሩንም አቋርጦ ወደ ገዛ ከተማው መጣ።
|
||
\v 2 እነሆ፣ በምንጣፍ የተኛ አንድ ሽባ ሰው ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን በማየት ሽባውን፣ “አንተ ልጅ፣ አይዞህ፤ ኅጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል” አለው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 3 አንዳንድ ጸሐፍት ግን እርስ በርሳቸው፣ "ይህ ሰው እኮ እየተሳደበ ነው" ተባባሉ ።
|
||
\v 4 ኢየሱስም ዐሳባቸውን ዐውቆ፣ “ስለ ምን በልባችሁ ክፉ ታስባላችሁ?”
|
||
\v 5 ለመሆኑ የሚቀለው፣'ኃጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል' ነው፣ ወይስ 'ተነሣና ሂድ ማለት ነው?'
|
||
\v 6 ነገር ግን የሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ይቅር የማለት ሥልጣን እንዳለው ዕወቁ" አለ፡፡ ሽባውንም፣ "ተነሣና፣ምንጣፍህን ይዘህ ወደ ቤት ሂድ" አለው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 7 ከዚያም ሰውየው ተነሥቶ ወደ ቤቱ ሄደ።
|
||
\v 8 ሕዝቡም ይህን ባዩ ጊዜ ተገርመው፣ ለሰው እንዲህ ያለ ሥልጣን የሰጠውን እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
|
||
\v 9 ኢየሱስም ከዚያ አለፍ እንዳለ፣ ማቴዎስ የሚባለውን ሰው በቀረጥ መሰብሰቢያ ቦታ ላይ ተቀምጦ አየውና "ተከተለኝ" አለው።እርሱም ተነሥቶ ተከተለው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 10 ኢየሱስም በቤቱ ውስጥ ለመመገብ በተቀመጠ ጊዜ፣ ቀረጥ የሚሰበስቡ ብዙ ሰዎችና ኃጢአተኞች መጥተው፣ ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርት ጋር አብረው ተመገቡ።
|
||
\v 11 ፈሪሳውያንም ይህን ሲያዩ፣ደቀ መዛሙርቱን "ለምንድን ነው መምህራችሁ፣ ከግብር ሰብሳቢዎችና ከኃጢአተኞች ጋር የሚበላው?" አሏቸው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 12 ኢየሱስም ይህንን ሲሰማ ፣"ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች ሐኪም አያስፈልጋቸውም፡፡
|
||
\v 13 'ሂዱና' ምሕረት እንጂ መሥዋዕትን አልፈልግም' የሚለውን ተማሩ፣ እኔ የመጣሁት ጻድቃንን ሳይሆን ኅጥአንን ወደ ንስሓ ለመጥራት" ነው አለ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 14 ከዚያም የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት መጥተው፣" እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ እንጾማለን ፣የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን የማይጾሙት ለምንድን ነው?" አሉት።
|
||
\v 15 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ “ሰርገኞች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር እያለ እንዴት ሊያዝኑ ይችላሉ? ሆኖም ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፣በእነዚያ ቀናት ይጾማሉ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 16 ማንም ሰው በአሮጌ ልብስ ላይ ዐዲስ ቊራጭ ጨርቅ አይለጥፍም፤ ምክንያቱም አሮጌውን ልብስ ይቦጭቀዋል፣ ልብሱም የባሰ ይጐዳል።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 17 ሰዎች ዐዲስ የወይን ጠጅ በአሮጌ አቁማዳ ውስጥ አያስቀምጡም፤ እንደዚያ ካደረጉ አቁማዳው ይፈነዳል፣ የወይን ጠጁ ይፈሳል፣ አቁማዳውም ይቀደዳል። ይልቁንም ዐዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ውስጥ ያስቀምጡታል፣ ሁለቱም ይጠበቃሉ፡፡"
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 18 ኢየሱስ ይህን እየተናገራቸው እያለ፣ አንድ ሹም እየሰገደ ወደ እርሱ መጣ። “ልጄ አሁን ገና ሞተች፣ ነገር ግን ና ና እጅህን ጫንባት በሕይወትም ትኖራለች አለው”።
|
||
\v 19 ኢየሱስም ተነሥቶ ተከትሎት ሄደ፤ ደቀ ዛሙርቱም ደግሞ አብረውት ሄዱ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 20 አንዲት ለዐሥራ ሁለት ዓመት ከባድ የደም መፍሰስ የነበረባት ሴት፣ ከኢየሱስ ኋላ መጥታ የልብሱን ጠርዝ ነካች፤
|
||
\v 21 "የልብሱን ጫፍ ብቻ ብነካ ደኅና እሆናለሁ" ብላ ነበርና።
|
||
\v 22 ኢየሱስም ዞር ብሎ አያትና፣ “ልጄ ሆይ፣ አይዞሽ እምነትሽ አድኖሻል” አላት። ሴቲቱም ወዲያውኑ ደኅና ሆነች።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 23 ኢየሱስም ወደ ሹሙ ቤት በገባ ጊዜ፣ዋሽንት የሚነፉትንና የሚንጫጩትን አይቶ፣
|
||
\v 24 "ወደዚያ ዞር በሉ፣ ልጅቷ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም"አላቸው። እነርሱ ግን በማፌዝ ሳቁበት።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 25 ሕዝቡን ወደ ውጭ ባስወጡ ጊዜ፥ ኢየሱስ ወደ ክፍሉ ገብቶ እጅዋን ያዘ፤ልጅቱም ተነሣች።
|
||
\v 26 ወሬውም በዚያ አካባቢ ሁሉ ተዳረሰ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 27 ኢየሱስም በዚያ ሲያልፍ፣ ሁለት ዐይነ ስውሮች ተከተሉት፣ ያለ ማቋረጥም፣ "የዳዊት ልጅ ማረን!" እያሉ ይጮኹ ነበር።
|
||
\v 28 ኢየሱስም ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ፣ ዐይነ ስውሮቹ ወደ እርሱ መጡ። ኢየሱስም፣ "ይህን ለማድረግ እንደምችል ታምናላችሁ?" አላቸው። እነርሱም "አዎን፣ ጌታ ሆይ" አሉት፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 29 ከዚያም ኢየሱስ ዐይኖቻቸውን ዳስሶ፣ "እንደ እምነታችሁ ይሁንላችሁ" አላቸው።
|
||
\v 30 ዐይኖቻቸውም ተከፈቱ። ከዚያም ኢየሱስ፣"ይህንን ማንም እንዳያውቅ" ብሎ በጥብቅ አዘዛቸው።
|
||
\v 31 ሁለቱ ሰዎች ግን ሄደው ወሬውን በየቦታው አዳረሱት።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 32 ሁለቱ ሰዎች እየሄዱ እያሉ እነሆ፣ በጋኔን የተያዘ ዲዳ ወደ ኢየሱስ አመጡ።
|
||
\v 33 ጋኔኑም ከወጣ በኋላ ዲዳው ተናገረ። ሕዝቡም ተገርመው፣ "እንዲህ ያለ ከዚህ በፊት በእስራኤል አልታየም" አሉ።
|
||
\v 34 ፈሪሳውያን ግን "አጋንንትን የሚያወጣው በአጋንንት አለቃ ነው" ይሉ ነበር።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 35 ኢየሱስ ወደ ከተሞችና መንደሮች ሁሉ ሄደ፣ በየምኩኲራቦቻቸውም ማስተማሩን፣ የመንግሥትን ወንጌል መስበኩንና፣ ማንኛውንም ዐይነት በሽታና ደዌ መፈወሱን ቀጠለ።
|
||
\v 36 ሕዝቡንም ሲያይ፣ ጠባቂ እንደሌላቸው በጎች ተጨንቀውና ግራ ተጋብተው ነበርና ራራላቸው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 37 ለደቀ መዛሙርቱም፣ "መከሩ ብዙ ነው ሠራተኞች ግን ጥቂት ናቸው።
|
||
\v 38 ስለዚህ፣ ሠራተኞችን ወደ መከሩ እንዲልክ፣ ወደ መከሩ ጌታ አጥብቃችሁ ጸልዩ" አላቸው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 10
|
||
\cl ምዕራፍ 10
|
||
\p
|
||
\v 1 ሁለቱን ደቀ መዛሙርት በአንድ ላይ ጠርቶ፣ ርኩሳን መናፍስትን እንዲያወጡ፣ ሁሉንም ዐይነት በሽታና ደዌ እንዲፈውሱ ሥልጣንን ሰጣቸው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 2 የዐስራ ሁለቱም ሐዋርያት ስም ይህ ነው፤ የመጀመሪያው ጴጥሮስ የተባለው ስምዖንና ወንድሙ እንድርያስ፣ የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብና ወንድሙ ዮሐንስ፣
|
||
\v 3 ፊልጶስና በርተሎሜዎስ፣ ቶማስና ቀረጥ ሰብሳቢው ማቴዎስ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብና ታዴዎስ፣
|
||
\v 4 ቀነናዊው ስምዖን፣አሳልፎ የሚሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 5 ኢየሱስ እነዚህን ዐሥራ ሁለቱን "አሕዛብ ወደሚኖሩበት የትኛውም ቦታ አትሂዱ፤ ወደ የትኛውም የሳምራውያን ከተማ አትግቡ።
|
||
\v 6 ከዚያ ይልቅ ወደ ጠፉት የእስራኤል ቤት በጐች ሂዱ።
|
||
\v 7 መንግሥተ ሰማይ ቀርባለች፣ ብላችሁ ስበኩ" ብሎ አስተምሮ ላካቸው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 8 ሕሙማንን ፈውሱ፣ ሙታንን አስነሡ፣ ለምጻሞችን አንጹ፣ አጋንንትንም አስወጡ፣ በነጻ ተቀብላችኋል በነጻ ስጡ።
|
||
\v 9 በቦርሳችሁ ወርቅ ብር ወይም ናስ አትያዙ፤
|
||
\v 10 ለሠራተኛ ቀለቡ የሚገባው ስለ ሆነ፣ ለመንገዳችሁ ሻንጣ ወይም ትርፍ ልብስ፣ ወይም ጫማ፣ ወይም በትር አትያዙ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 11 ወደ የትኛውም ከተማ ወይም መንደር ስትገቡ፣ በዚያ ተገቢ የሆነው ሰው ማን እንደሆን እወቁ፤ ለቃችሁ እስከምትሄዱ ድረስ በዚያው ቆዩ።
|
||
\v 12 ወደ ቤት ስትገቡ፣ ሰላምታ ስጡ።
|
||
\v 13 ቤቱ የሚገባው ከሆነ ሰላማችሁ ይደርሰዋል፤ የማይገባው ከሆነ ግን ሰላማችሁ ይመለስላችኋል።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 14 እናንተን የማይቀበላችሁን፣ ወይም ቃላችሁን የማይሰማውን በተመለከተ ግን፣ ከዚያ ቤት ወይም ከተማ ስትወጡ የእግራችሁን አቧራ አራግፉ።
|
||
\v 15 እውነት እላችኋለሁ፣ በፍርድ ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ ይቀልላቸዋል።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 16 ተመልከቱ፣ እንደ በጎች በተኲላዎች መካከል እልካችኋለሁ። ስለዚህ፣ እንደ እባብ ብልኆች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።
|
||
\v 17 ከሰዎች ተጠበቁ፣ ወደ ፍርድ ሸንጎ ያቅርቧችኋል፣ በምኲራባቸውም ይገርፏችኋል።
|
||
\v 18 ለእነርሱና ለአሕዛብ ምስክር እንዲሆን፣ በእኔም ምክንያት ወደ ገዥዎችና ነገሥታት ፊት ትቀርባላችሁ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 19 ለፍርድም ሲያቀርቧችሁ፣ በዚያች ሰዓት የምትናገሩት ስለሚሰጣችሁ፣ ምን ወይም እንዴት እንደምትናገሩ አትጨነቁ።
|
||
\v 20 በእናንተ ውስጥ የሚናገረው የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ የምትናገሩት እናንተ አይደላችሁም።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 21 ወንድም ወንድሙን፣ አባትም ልጁን፣ ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፤ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ተነሥተው ያስገድሏቸዋል።
|
||
\v 22 ከስሜ የተነሣ በሰው ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ ነገር ግን ማንም እስከ መጨረሻ የሚጸና እርሱ ይድናል።
|
||
\v 23 በዚህች ከተማ በሚያሳድዷችሁ ጊዜ ወደሚቀጥለው ከተማ ሽሹ። እውነት እላችኋለሁ፣ የሰው ልጅ ከመምጣቱ በፊት፣ የእስራኤልን ከተሞች አታዳርሱም።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 24 ደቀ መዝሙር ከመምህሩ አይበልጥም፤ ወይም አገልጋይ ከጌታው በላይ አይደለም።
|
||
\v 25 ለደቀ መዝሙር ልክ እንደ መምህሩ፣ ለአገልጋይም ልክ እንደ ጌታው መሆን ይበቃዋል።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 26 እንግዲህ አትፍሯቸው፤ የማይገለጥ የተሰወረ፣ የማይታወቅ የተደበቀ ምንም የለም።
|
||
\v 27 በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን፣ በሹክሹክታ የምትሰሙትንም በአደባባይ ተናገሩት፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 28 ሥጋን እንጂ ነፍስን መግደል የማይችሉትን አትፍሩ፤ ከዚያ ይልቅ ነፍስንም፣ ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚችለውን ፍሩ፡፡
|
||
\v 29 ሁለት ድንቢጦች በትንሽ ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ሆኖም አንዷም ብትሆን አባታችሁ ሳያውቅ በመሬት ላይ አትወድቅም፡፡
|
||
\v 30 የእናንተ ግን የራሳችሁ ጠጉር እንኳን ሳይቀር የተቈጠረ ነው፡፡
|
||
\v 31 አትፍሩ፤ ከብዙ ድንቢጦች የበለጠ ዋጋ አላችሁ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 32 ስለዚህ በሰዎች ፊት ለሚመሰክርልኝ፣ እኔም በሰማይ ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፡፡
|
||
\v 33 በሰው ፊት የሚክደኝን ግን፣ እኔም ደግሞ በሰማይ ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 34 በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ፣ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም፡፡
|
||
\v 35 ሰውን በአባቱ ላይ፣ ሴት ልጅን በእናቷ ላይ፣ ምራትን በአማቷ ላይ ለማነሣሣት መጥቻለሁ፡፡
|
||
\v 36 የሰውም ጠላቶቹ የገዛ ቤተ ሰቦቹ ይሆናሉ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 37 አባትን ወይም እናትን ከእኔ የበለጠ የሚወድ ለእኔ የተገባ አይደለም፤ እንዲሁም ወንድ ልጅን፣ ወይም ሴት ልጅን ከእኔ የበለጠ የሚወድ ለእኔ የተገባ አይደለም።
|
||
\v 38 መስቀሉን ተሸክሞ፣ ከኋላዬ የማይከተለኝ የእኔ ሊሆን አይገባውም፡፡
|
||
\v 39 ሕይወቱን የሚያገኛት ያጣታል፤ ስለ እኔ ብሎ ሕይወቱን የሚያጣት ግን ያገኛታል፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 40 እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል፡፡
|
||
\v 41 ነቢይ ስለ ሆነ ነቢይን የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ያገኛል፤ ጻድቅ ስለ ሆነ ጻድቅን የሚቀበል የጻድቅን ዋጋ ያገኛል፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 42 እውነት እላችኋለሁ፣ ከእነዚህ ታናናሾች ለአንዱ፣ ደቀ መዝሙሬ ስለ ሆነ፣ አንድ ብርጭቆ ቀዝቃዛ ውሃ እንኳ የሚሰጥ ማንም፣ በምንም ዐይነት ዋጋውን አያጣም፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 11
|
||
\cl ምዕራፍ 11
|
||
\p
|
||
\v 1 እንዲህም ሆነ፣ ኢየሱስ አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት አዝዞ ከጨረሰ በኋላ፣ በከተሞቻቸው ሊያስተምርና ሊሰብክ ከዚያ ሄደ፡፡
|
||
\v 2 ዮሐንስ በወህኒ ቤት ሆኖ የክርስቶስን ሥራዎች በሰማ ጊዜ፣ በደቀ መዛሙርቱ መልእክት ላከበት፡፡
|
||
\v 3 እንዲህም አለው፣ "የሚመጣው አንተ ነህ፣ ወይስ መጠበቅ ያለብን ሌላ ሰው አለ?"
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 4 ኢየሱስም መለሰ እንዲህም አላቸው፤ “ሂዱና፣ ለዮሐንስ የምታዩትንና የምትሰሙትን እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፤
|
||
\v 5 ዕውሮች ብርሃናቸውን እያገኙ፣ አንካሶች እየተራመዱ፣ ለምጻሞች እየነጹ፣ መስማት የተሳናቸው እየሰሙ፣ ሙታን እየተነሡ፣ ድኾችም የምሥራች እየሰሙ ነው፡፡
|
||
\v 6 በማንኛውም ሁኔታ በእኔ የማይሰናከል ሁሉ የተባረከ ነው" ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 7 እነዚህ ሰዎች እንደ ሄዱ፣ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ መናገር ጀመረ፣ እንዲህም አለ፣ "ምን ልታዩ ወደ በረሓ ወጣችሁ? ነፋስ የሚያወዛውዘውን ሸምበቆን?
|
||
\v 8 ግን ምን ልታዩ ወጣችሁ? የሚያምር ልብስ የለበሰውን? በርግጥ፣ ጥሩ ልብስ የሚለብሱ የሚኖሩት በቤተ መንግሥት ነው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 9 ግን ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን ነውን? አዎ፣ እላችኋለሁ፣ ከነቢይም የሚበልጠውን ነው፡፡
|
||
\v 10 እንዲህ ተብሎ የተጻፈው ስለ እርሱ ነው፦ 'መንገድህን የሚያዘጋጅ መልእከተኛዬን በፊትህ እልካለሁ፡፡'
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 11 እውነት እላችኋለሁ፣ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም። በመንግሥተ ሰማይ ግን፣ ታናሹ ሰው ከእርሱ ይበልጣል፡፡
|
||
\v 12 ከመጥምቁ ዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት በዐመፅ ትቸገራለች፣ ዐመጸፀኞች ግን በኅይል ይወስዷታል፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 13 እስከ ዮሐንስ ዘመን ድረስ ሕጉም፣ ነቢያቱም ሁሉ ትንቢት ሲናገሩ ነበርና፡፡
|
||
\v 14 እንግዲህ ልትቀበሉት ፈቃደኞች ከሆናችሁ፣ የሚመጣው ኤልያስ እርሱ ነው፡፡
|
||
\v 15 የሚሰማ ጆሮ ያለው፣ ይስማ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 16 ይህን ትውልድ ከምን ጋር ላነጻጽረው? በገበያ ተቀምጠው፣ እየተቀባበሉ እንደሚዘፍኑ ልጆች ነው፡፡
|
||
\v 17 'ዋሽንት ነፋንላችሁ፣ አልጨፈራችሁም፤ ሙሾ አወጣንላችሁ እናንተም አላለቀሳችሁም' ይላሉ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 18 ዮሐንስ እንጀራ ሳይበላና የወይን ጠጅ ሳይጠጣ በመምጣቱ፣'ጋኔን አለበት' አሉት።
|
||
\v 19 የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ በመምጣቱ፣ 'ተመልከቱ ይህ ሰው በላተኛና ጠጪ፣ የቀረጥ ሰብሳቢዎችና፣ የኃጢአተኞች ወዳጅ ነው!' አሉት ነገር ግን ጥበብ በሥራዋ ትክክል ሆነች፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 20 ኢየሱስም ብዙ ታላላቅ ሥራዎች ያደረገባቸውን ከተማዎች፣ ንስሓ ባለመግባታቸው ይገሥጻቸው ጀመር፡፡
|
||
\v 21 ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተሳይዳ! በእናንተ የተደረጉት ታላላቅ ሥራዎች በጢሮስና በሲዶና ተደርገው ቢሆን ኖሮ፣ ማቅ ለብሰውና፥ ዐመድ ነስንሰው ድሮ ንስሓ በገቡ ነበር፡፡
|
||
\v 22 ነገር ግን በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ፣ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 23 አንቺ ቅፍርናሆም፣ እስከ ሰማይ የወጣሽ ይመስልሻልን? በፍጹም፤ ወደ ሲኦል ትወርጂያለሽ፡፡ ለአንቺ እንደተደረጉት ትልልቅ ነገሮች በሰዶም ተደርገው ቢሆን ፣ እስከ አሁን በኖረች ነበር፡፡
|
||
\v 24 ነገር ግን እላችኋለሁ፣ በፍርድ ቀን፣ ከእናንተ ይልቅ ለሰዶም ይቀልላታል፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 25 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አለ፤ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፣ ይህን ከዐዋቂዎችና ከአስተዋዮች ሰውረህ እንደ ሕፃናት ላልተማሩት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ።”
|
||
\v 26 አዎ፣ አባት ሆይ፣ በፊትህ እጅግ ደስ የሚያሰኝህ ይህ ሆኖአልና፡፡
|
||
\v 27 ከአባቴ ሁሉ ተሰጥቶኛል፣ ከአባት በቀር ማንም ልጅን የሚያውቀው የለም፤ ከልጅም በቀር፣ ልጁም ሊገልጥለት ከሚፈልገው በቀር፣ አባትን የሚያውቅ ማንም የለም፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 28 እናንተ ደካሞች፣ ሸክም የከበዳችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፣ እኔም ዕረፍት እሰጣችኋላሁ፡፡
|
||
\v 29 ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ፣ ከእኔም ተማሩ፣ እኔ የዋህና በልቤ ትሁት ነኝ፣ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፡፡
|
||
\v 30 ቀንበሬ ቀላል፣ ሸክሜም የማይከብድ ነው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 12
|
||
\cl ምዕራፍ 12
|
||
\p
|
||
\v 1 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በሰንበት በእርሻ መካከል ሄደ። ደቀ መዛሙርቱም ተርበው ስለ ነበር፣ እሸቱን እየቀጠፉ ይበሉ ጀመር፡፡
|
||
\v 2 ፈሪሳውያንም ያንን ባዩ ጊዜ፣ “ኢየሱስን፣ ደቀ መዛሙርትህ በሰንበት የሚያደርጉትን የማይገባ ነገር ተመልከት” አሉት፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 3 ኢየሱስ ግን፣ "ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች በተራቡ ጊዜ ያደረገውን ከቶ አላነበባችሁምን?
|
||
\v 4 ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ፣ ለካህናት ብቻ እንጂ ለእርሱና ከእርሱ ጋር ለነበሩት ያልተፈቀደውን የተቀደሰ እንጀራ እንዴት እንደበላ?" አላቸው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 5 በሰንበት ካህናት በቤተ በመቀደስ ሥራ እንድሚሠሩና፣ ሰንበትን እንደሚያረክሱ፣ በደልም እንደማይሆንባቸው ከሕጉ አላነበባችሁምን?
|
||
\v 6 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ ከቤተ መቅደስ የሚበልጠው እዚህ አለ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 7 “መሥዋዕትን ሳይሆን ምሕረትን እፈልጋለሁ” የሚለውን ብታውቁ ኖሮ፣ በደል የሌለባቸውን አትፈርዱባቸውም ነበር፡፡
|
||
\v 8 የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነውና።"
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 9 ከዚያም ኢየሱስ ከዚያ ተነስቶ፣ ወደ ምኲራባቸው ገባ።
|
||
\v 10 እነሆ፣ እጁ ሽባ የሆነ አንድ ሰው ነበረ፡፡ ፈሪሳውያንም ኢየሱስን በኅጢአት ለመክሰስ፣ "ሕጉ በሰንበት መፈወስን ይፈቅዳልን?" ብለው ጠየቁት፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 11 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “ከእናንተ መካከል አንድ በግ ብቻ ብትኖረውና፣ ያቺም በግ ጉድጓድ ውስጥ ብትገባበት፣ በሰንበት የማያወጣት ማን ነው?
|
||
\v 12 ታዲያ ሰውማ ፣ ከበግ ይልቅ ምን ያህል ዋጋ ይኖረዋል! ስለዚህ በሰንበት መልካም መሥራት ተፈቅዷል ፡፡"
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 13 ከዚያም ኢየሱስ፣ ሰውየውን፣ “እጅህን ዘርጋ” አለው፡፡ እጁንም ዘረጋ፣ እንደ ሌላውም እጅ ጤነኛ ሆነ፡፡
|
||
\v 14 ነገር ግን ፈሪሳውያን ሄደው አሤሩበት፣ እርሱን የሚገድሉበትን መንገድ ይፈልጉ ነበር፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 15 ኢየሱስ ይህን እንዳወቀ፣ ከዚያ ፈቀቅ አለ። ብዙ ሰዎች ተከተሉት፤ እርሱም ሁሉንም ፈወሳቸው፡፡
|
||
\v 16 ሰዎቹን ስለ እርሱ ለሌሎች እንዳይገልጹ አዘዛቸው፣
|
||
\v 17 ይህም የሆነው በነቢዩ በኢሳይያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው እንዲፈጸም ነው፤
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 18 እነሆ፣ እኔ የመረጥኩት አገልጋዬ፤ የምወደው ነፍሴም ደስ የተሰኘችበት። መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፤ እርሱም ፍትሕን ለአሕዛብ ያውጃል።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 19 አይጨቃጨቅም ወይም አይጮህም፤ ወይም ማንም ድምፁን በጐዳናዎች ላይ አይሰማም።
|
||
\v 20 ፍርድን ለድል እስኪያበቃ ድረስ፤ የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም፣ የሚጤሰውንም የጧፍ ክር አያጠፋም፣
|
||
\v 21 አሕዛብም በስሙ ይታመናሉ።"
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 22 ከዚያም በአጋንንት የተያዘን ዐይነ ስውርና ዲዳ ሰው ወደ ኢየሱስ አመጡ፤ እርሱም ፈወሰው፤ ዲዳውም ተናገረ፣ አየም።
|
||
\v 23 ሕዝቡም በመገረም፣ "ይህ ሰው የዳዊት ልጅ ይሆን እንዴ?" አሉ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 24 ነገር ግን ፈሪሳውያን ይህን ተአምር በሰሙ ጊዜ “ይህ ሰው በአጋንንት አለቃ በብዔልዜቡል ካልሆነ በቀር አጋንንቱን አያወጣም ነበር" አሉ፡፡
|
||
\v 25 ኢየሱስም ዐሳባቸውን ዐውቆ ፣“እርስ በርሱ የሚከፋፈል መንግሥት ይወድቃል፤ እርስ በርሱ የሚለያይ ከተማ ወይም ቤት ሁሉ አይጸናም፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 26 ሰይጣን ሰይጣንን የሚያወጣ ከሆነ፣ እርስ በርሱ ተከፋፍሏል፣ መንግሥቱስ እንዴት ይቆማል?
|
||
\v 27 እኔ አጋንንትን የማወጣው በብዔልዜቡል ከሆነ፣ ተከታዮቻችሁ በማን ሊያወጡ ነው? ከዚህ የተነሣ እነርሱው ይፈርዱባችኋል፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 28 ነገር ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆነ፣ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ መጥታለች፡፡
|
||
\v 29 ማንም ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ቤቱ ገብቶ ንብረቱን እንዴት መዝረፍ ይችላል?፡፡ ካሰረው በኋላ ግን፣ ንብረቱን ይዘርፋል።
|
||
\v 30 ከእኔ ጋር ያልሆነ ተቃዋሚዬ ነው፣ ከእኔም ጋር የማይሰበስብ ይበትናል፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 31 ስለዚህ እላችኋለሁ፣ ማንኛውም ኅጢአትና ስድብ ለሰዎች ይቅር ይባልላቸዋል ፤መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ግን ይቅር አይባልም፡፡
|
||
\v 32 በሰው ልጅ ላይ ማንኛውንም ቃል የሚናገር ይቅር ይባልለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚናገር ግን፣ በዚህ ዓለምም ሆነ በሚመጣው ይቅር አይባልም።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 33 እንግዲህ ዛፍ የሚታወቀው በፍሬው ስለ ሆነ ዛፉን መልካም አድርጉ፤ ፍሬውም መልካም ይሆናል፣ ወይም ዛፉን መጥፎ አድርጉ ፍሬውም መጥፎ ይሆናል፡፡
|
||
\v 34 እናንተ የእባብ ልጆች ክፉዎች ስለ ሆናችሁ፣ እንዴት መልካም ልትናገሩ ትችላላችሁ? ምክንያቱም በልብ ውስጥ የሞላውን አፍ ይናገረዋል፡፡
|
||
\v 35 . መልካም ሰው በልቡ ውስጥ ካለው መልካም መዝገብ፣ መልካሙን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም ልቡ ውስጥ ካለው ክፉ መዝገብ ክፉውን ይወጣል።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 36 ለእናንተም እላችኋለሁ፣ በፍርድ ቀን ሰዎች ስለ ተናገሯቸው ከንቱ ንግግሮች መልስ ይሰጣሉ፡፡
|
||
\v 37 ምትናገሩት ትጸድቃላችሁ፣ በምትናገሩትም ይፈረድባችኋልና፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 38 አንዳንድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን መልሰው ኢየሱስን፣ “መምህር ሆይ፣ ምልክት እንድታሳየን እንፈልጋለን" አሉት።
|
||
\v 39 ኢየሱስ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው፣ ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይፈልጋል፤ ነገር ግን ከነቢዩ ከዮናስ ምልክት በቀር ምንም አይሰጠውም፡፡
|
||
\v 40 ዮናስ በትልቅ ዐሣ ሆድ ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፣ የሰው ልጅም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በምድር ልብ ውስጥ ይሆናል፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 41 የነነዌ ሰዎች በዮናስ ስብከት ንስሓ በመግባታቸው፣ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ሰዎች ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፡፡ ደግሞም ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 42 የደቡብ ንግሥት፣ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳርቻዎች መጥታለችና፣ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፡፡ደግሞም ከሰሎሞን የሚበልጥ እዚህ አለ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 43 ርኩስ መንፈስ ከሰው በወጣ ጊዜ፣ ዕረፍት ፍለጋ ውሃ በሌለባቸው ቦታዎች ያልፋል፣ ነገር ግን አያገኝም።
|
||
\v 44 ከዚያም፣ 'ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ' ይላል። ሲመለስም ቤቱ ጸድቶ ተዘጋጅቶ ያገኘዋል፡፡
|
||
\v 45 ከዚያም ይሄድና ከእርሱ ይልቅ የከፉትን ሰባት ሌሎች መናፍስትን ይዞ ይመጣል፣ ሁሉም በዚያ ለመኖር ይመጣሉ፡፡ የዚያም ሰው የመጨረሻው ሁኔታ ከመጀመሪያው የከፋ ይሆናል፡፡ በዚህ ክፉ ትውልድ ላይ የሚሆነውም እንደዚሁ ነው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 46 ኢየሱስም ለሕዝቡ እየተናገረ እያለ፣ እናቱና ወንድሞቹ ሊያናግሩት ፈልገው፣ በውጭ ቆመው ነበር።
|
||
\v 47 አንድ ሰውም፣ "እነሆ፣ እናትህና ወንድሞችህ ሊያነጋግሩህ በውጭ ቆመዋል" አለው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 48 ኢየሱስም መልሶ ለነገረው ሰው፣ "እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው?" አለው።
|
||
\v 49 ከዚያም እጁን ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዘርግቶ፣ "እናቴና ወንድሞቼ እነዚህ ናቸው!
|
||
\v 50 በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፣ ወንድሜ፣ እኅቴ እናቴም ነውና" አለ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 13
|
||
\cl ምዕራፍ 13
|
||
\p
|
||
\v 1 በዚያ ቀን ኢየሱስ ከቤት ወጥቶ በባሕር ዳርቻ ተቀመጠ።
|
||
\v 2 በጣም ብዙ ሕዝብ በዙሪያው ተሰበሰቡ፣ ስለዚህ ጀልባ ውስጥ ገብቶ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም ሁሉ በባሕሩ ዳርቻ ቆመው ነበር።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 3 ከዚያም ኢየሱስ በምሳሌ ብዙ ነገር ነገራቸው። እንዲህም አለ፤ "ዘሪ ለመዘራት ወጣ።
|
||
\v 4 ሲዘራም፣ አንዳንዱ ዘር በመንገድ አጠገብ ወድቆ፣ ወፎች መጥተው በሉት።
|
||
\v 5 ሌላውም ዘር በቂ አፈር በሌለበት በዐለታማ መሬት ላይ ወደቀ። አፈሩም ጥልቀት ስላልነበረው ወዲያው በቀለ።
|
||
\v 6 ፀሐይ ሲወጣ ግን፣ሥር ስላልነበረው ጠውልጎ ደረቀ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 7 ሌላው ዘር ደግሞ በእሾኽማ ቊጥቋጦ መካከል ወደቀ፣ እሾኹም አድጎ አነቀው።
|
||
\v 8 ሌላው ዘር በመልካም መሬት ላይ ወድቆ ፍሬ አፈራ፤ አንዳንዱ መቶ፣ አንዳንዱ ሥልሳ፣ አንዳንዱም ሠላሳ ፍሬ አፈራ።
|
||
\v 9 ጆሮ ያለው ይሰማ።"
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 10 ደቀ መዛሙርቱም መጡና ኢየሱስን፣ “ለምንድን ነው ለሕዝቡ በምሳሌ የምትናገረው?" አሉት።
|
||
\v 11 ኢየሱስም መልሶ፣ "ለእናንተ የመንግሥተ ሰማይን ምስጢር ማወቅ ተሰጥቷችኋል፣ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም" አላቸው።
|
||
\v 12 ምክንያቱም ላለው ሁሉ የበለጠ ይሰጠዋል፤ ይበዛለትማል። የሌለው ግን ያለው እንኳ ይወሰድበታል።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 13 ስለዚህ ለእነርሱ በምሳሌ እነግራቸዋለሁ፤ ምክንያቱም ቢያዩ እንኳ እያዩ አይደለም፣ ቢሰሙም እየሰሙ አይደለም፣ ወይም አያስተውሉም።
|
||
\v 14 በእነርሱ ላይ እንዲህ የሚለው የኢሳይያስ ትንቢት ተፈጸመ ፦ መስማትን ትሰማላችሁ፣ ነገር ግን በምንም መንገድ አታስተውሉም፣ ማየትን ታያላችሁ፣ ግን ምንም አትገነዘቡትም።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 15 በዐይናቸውም እንዳይመለከቱ፣ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፣ በልባቸውም እንዳያስተውሉ ጆሯቸው ለመስማት ተደፍኗል፣ ዐይናቸውም ተጨፍኗል። እንዳይመለሱና እኔም እንዳልፈውሳቸው የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኗል።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 16 የእናንተ ዐይኖች ግን ስለሚያዩ፣ ጆሮቻችሁም ስለሚሰሙ የተባረኩ ናቸው።
|
||
\v 17 እውነት እላችኋለሁ፣ ብዙ ነቢያትና ጻድቃን የምታዩትን ለማየት ተመኝተው አላዩም፤ የምትሰሙትን ለመስማት ተመኝተው አልሰሙም።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 18 እንግዲህ የዘሪውን ምሳሌ ስሙ።
|
||
\v 19 ማንም የመንግሥትን ቃል ሰምቶ ባያስተውል፣ ክፉው ይመጣል በልቡም የተዘራውን ይነጥቃል። ይህም በመንገድ ዳር የተዘራውን ይመስላል።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 20 በዐለት ላይ የተዘራው ፣ቃሉን የሚሰማና ወዲያውኑ በደሰታ የሚቀበለው ነው፤
|
||
\v 21 ሆኖም በራሱ ሥር ስለሌለው፣ የሚቆየው ለአጭር ጊዜ ነው። በቃሉ ምክንያት መከራ ወይም ስደት በሚነሣበት ጊዜ፣ ወዲያውኑ ይሰናከላል።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 22 በእሾኽ ተክሎች መካከል የተዘራው፣ ቃሉን የሚሰማ ሆኖ የዓለም ዐሳብ፣ የብልጥግናም አሳሳችነት ቃሉን ያንቁታል፣ ፍሬ ቢስም ይሆናል።
|
||
\v 23 በመልካም መሬት ላይ የተዘራው፣ ቃሉን የሚሰማና የሚረዳ ነው፤ በርግጥ የሚያድገውና ፍሬ የሚሰጠውም ይህኛው ነው፤ አንዱ መቶ፣ አንዱም ሥልሳ፣ አንዱም ሠላሣ እጥፍ ያፈራል።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 24 ኢየሱስ ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፤ እንዲህ አለ፤ “መንግሥተ ሰማይ በዕርሻው ላይ መልካም ዘር የዘራ ሰው ትመስላለች።
|
||
\v 25 ሰዎቹ በተኙ ጊዜ ግን፣ ጠላቱ መጥቶ በስንዴው መካከል እንክርዳድ ዘርቶ ሄደ።
|
||
\v 26 ቅጠሉም በለመለመና ፍሬ ማፍራት በጀመረ ጊዜ፣ እንክርዳዱ ደግሞ አለ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 27 የዕርሻው ባለቤት አገልጋዮች መጥተው፣ "ጌታ ሆይ፣ በዕርሻው ላይ መልካም ዘር ዘርተህ አልነበረምን? ታዲያ እንክርዳድ የበቀለው እንዴት ነው?"አሉት።
|
||
\v 28 እርሱም፣ “ጠላት ይህን አደረገ" አላቸው። አገልጋዮቹም መልሰው፣"ስለዚህ ሄደን እንድንነቅለው ትፈልጋለህን?" አሉት።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 29 የዕርሻውም ባለቤት፣ 'አይሆንም፣ እንክርዳዱን በምትነቅሉበት ጊዜ ስንዴውንም አብራችሁ ልትነቅሉት ትችላላችሁ 'አላቸው።
|
||
\v 30 እስከ መከር ድረስ አብረው ይደጉ። በመከሩ ጊዜ ለኣጫጆቹ፣ "መጀመሪያ እንክርዳዱን ነቅላችሁ እንዲቃጠል አንድ ላይ ሰብስቡ። ስንዴውን ግን ሰብስባችሁ ወደ ጎተራዬ አስገቡት እላቸዋለሁ" አላቸው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 31 ኢየሱስም ሌላ ምሳሌ ነገራቸው። እንዲህም አለ፤ “መንግሥተ ሰማይ ሰው ወስዶ በዕርሻው ላይ የዘራትን የሰናፍጭ ዘር ትመስላለች።
|
||
\v 32 በርግጥ ይህች ዘር ከሌሎች ዘሮች ሁሉ ታንሳለች። በምታድግበት ጊዜ ግን የሰማይ ወፎች በቅርንጫፎቿ እስኪሰፍሩባት ድረስ፣ ከሌሎች ዛፎች ትበልጣለች፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 33 ከዚያም ኢየሱስ ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፤ “መንግሥተ ሰማይ ሴት ወስዳ ኩፍ እስኪል ድረስ ከሦስት እጅ ዱቄት ጋር የደባለቀችውን እርሾ ትመስላለች።”
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 34 ኢየሱስም ለሕዝቡ እነዚህን ነገሮች ሁሉ በምሳሌ ተናገረ፣ ያለ ምሳሌም ምንም አልነገራቸውም።
|
||
\v 35 ይህም ፦ "አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፣ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ የተሰወረውን እገልጣለሁ" ተብሎ በነቢዩ የተነገረው እንዲፈጸም ነው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 36 ኢየሱስ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ። ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ መጥተው "በዕርሻው የነበረውን የእንክርዳዱን ምሳሌ አስረዳን" አሉት።
|
||
\v 37 ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አለ፤ “መልካሙን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው።
|
||
\v 38 ዕርሻው ይህ ዓለም ነው፣ መልካሙ ዘር የመንግሥቱ ልጆች ናቸው። እንክርዳዱ የክፉው ልጆች ናቸው፤
|
||
\v 39 ዘሩን የዘራው ጠላት ዲያብሎስ ነው። መከሩ የዓለም መጨረሻ ሲሆን፣ አጫጆቹም መላእክት ናቸው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 40 ስለዚህ እንክርዳዱ ተሰብስቦ በእሳት እንደሚቃጠል፣ በዓለም መጨረሻም እንዲሁ ይሆናል።
|
||
\v 41 የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፣ ከመንግሥቱ ለኅጢአት ምክንያት የሆኑ ነገሮችን ሁሉና፣ ክፉ አድራጊዎችን ይሰበስቧቸዋል፣
|
||
\v 42 ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት፣ ወደ እቶን እሳትም ይጥሏቸዋል።
|
||
\v 43 ከዚያም ፃድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ያበራሉ። ጆሮ ያለው ይስማ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 44 መንግሥተ ሰማይ በዕርሻ ውስጥ የተደበቀ ሀብት ትመስላለች፣ አንድ ሰውም አግኝቶ ደበቃት፤ ከደስታውም የተነሳ ያለውን ንብረት ሁሉ ሸጦ ያንን ዕርሻ ገዛው።
|
||
\v 45 ደግሞም፣ መንግሥተ ሰማይ የከበሩ ዕንቈች የሚፈልግ ነጋዴን ትመስላለች።
|
||
\v 46 በጣም ትልቅ ዋጋ ያለው ዕንቊ ባገኘ ጊዜ፣ ሄዶ ያለውን ንበረት ሁሉ ሸጠና ገዛው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 47 እንዲሁም፣መንግሥተ ሰማይ ወደ ባሕር የተጣለችና ሁሉም ዓይነት ፍጥረታት የሰበሰበች መረብን ትመስላለች።
|
||
\v 48 መረቡዋ ስትሞላ፣ ዓሣ አጥማጆቹ ወደ ዳር አወጡት። ተቀምጠውም መልካም መልካሙን ሰብስበው በዕቃ አደረጉ፣ የማይጠቅመውን ግን አውጥተው ጣሉት።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 49 በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል፣ መላእክት መጥተው ከጻድቃን መካከል ክፉዎችን ይለያሉ።
|
||
\v 50 ከዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት፣ ወደሚነደው እቶን እሳት ይጥሏቸዋል።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 51 ይህን ሁሉ ተረድታችኋል?" አላቸው። ደቀ መዛሙርቱም፣ “አዎን” አሉት።
|
||
\v 52 ከዚያም ኢየሱስ፣ “ ስለዚህ የመንግሥተ ሰማይ ደቀ መዝሙር የሆነ ጸሐፊ ሁሉ፣ ከሀብቱ መካከል አሮጌውንና ዐዲሱን ያወጣ የቤት ጌታን ይመስላል አላቸው"።
|
||
\v 53 ከዚያም ኢየሱስ እነዚህን ምሳሌዎች በጨረሰ ጊዜ፣ ከዚያ ስፍራ ሄደ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 54 ኢየሱስ ወደ ራሱ አገር መጥቶ፣ በምኲራቦቻቸው ሕዝቡን አስተማረ፣ ከዚህም የተነሣ ተገርመው፣ "ይህ ሰው ይህን ጥበቡንና እነዚህን ተአምራት ከየት አገኘ?
|
||
\v 55 ይህ ሰው የአናጢው ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም አይደለችም ወይ? ያዕቆብ፣ ዮሴፍ፣ ስምዖንና ይሁዳስ ወንድሞቹ አይደሉም ወይ?
|
||
\v 56 እኅቶቹስ ከእኛው ጋር አይደሉም ወይ? ታዲያ ይህ ሰው እነዚህን ነገሮች ሁሉ ከየት አገኛቸው?" አሉ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 57 በእርሱም ተሰናከሉበት። ኢየሱስ ግን፣ "ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ቤተ ሰቡ በቀር መከበሩ አይቀርም" አላቸው።
|
||
\v 58 በአለማናቸውም ምክንያት ፣በዚያ ብዙ ተአምራት አላደረገም።
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 14
|
||
\cl ምዕራፍ 14
|
||
\p
|
||
\v 1 በዚያን ጊዜ፣ የአራተኛው ክፍል ገዢ የነበረው ሄሮድስ ስለ ኢየሱስ ሰማ።
|
||
\v 2 አገልጋዮቹንም፣ "ይህ መጥምቁ ዮሐንስ ነው። ስለዚህ ይህ ሁሉ ኅይል በእርሱ የሚሠራው ከሞት ስለ ተነሣ ነው" አላቸው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 3 ሄሮድስ፣ በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት፣ ይዞ አሳስሮት ነበርና፡፡
|
||
\v 4 ምክንያቱም ዮሐንስ፣ "እርሷን ማግባትህ ተገቢ አይደለም" ይለው ነበር።
|
||
\v 5 ሄሮድስ ሊያስገድለው ፈልጎ፣ ሕዝቡን ፈራ፣ ምክንያቱም ሕዝቡ ዮሐንስን እንደ ነቢይ ያዩት ነበር።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 6 ነገር ግን በሄሮድስ የልደት ቀን፣ የሄሮድያዳ ልጅ በመካከል ስትጨፍር፣ ሄሮድስን ደስ አሰኘችው።
|
||
\v 7 በዚህም ምክንያት፣ የምትጠይቀውን ሁሉ እንደሚሰጣት በመሓላ ቃል ገባላት።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 8 በእናቷም ተመክራ፣ “የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ እዚሁ፣ በሳሕን አድርገህ ስጠኝ” አለችው።
|
||
\v 9 ንጉሡ በጥያቄዋ በጣም ዐዘነ፣ ነገር ግን በመሓላውና ከእርሱ ጋር እራት ላይ በነበሩት ምክንያት፣ የተናገረው እንዲፈጸም አዘዘ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 10 ሰው ልኮ፣ በወህኒ ቤት የዮሐንስን ራስ አስቈረጠ።
|
||
\v 11 ከዚያም ራሱ በሳሕን ተደርጎ ለልጅቱ ተሰጣት፣ እርሷም ለእናቷ ወስዳ ሰጠች።
|
||
\v 12 ከዚያም የእርሱ ደቀ መዛሙርት መጥተው፣ በድኑን ወስደው ቀበሩት። ከዚህ በኋላ ሄደው ለኢየሱስ ነገሩት።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 13 ኢየሱስም ይህን በሰማ ጊዜ፣ በጀልባ ገለል ወዳለ ቦታ ሄደ። ሕዝቡም ይህን በሰሙ ጊዜ ፣ ከየከተሞቹ በእግር ተከተሉት።
|
||
\v 14 ከዚያም ኢየሱስ ቀድሞአቸው መጥቶ ብዙ ሕዝብ አየና ራራላቸው፣ ሕመምተኞቻቸውንም ፈወሰ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 15 በመሸም ጊዜ፣ ደቀ መዛሙርቱ መጡና፣ “ቀኑ መሽቷል ይህም ስፍራ ምድረ በዳ ነው ። ሕዝቡን ወደ መንደሮች እንዲሄዱና፣ ለራሳቸው ምግብ እንዲገዙ አሰናብት" አሉት።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 16 ኢየሱስ ግን፣ "መሄድ አያስፈልጋቸውም፤ እናንተው የሚበሉትን ስጧቸው" አላቸው።
|
||
\v 17 እነርሱም፣ “ እኛ ያለን አምስት እንጀራና ሁለት ዐሣ ብቻ ነው" አሉት።
|
||
\v 18 ኢየሱስም፣ "እነርሱኑ ወደ እኔ አምጡአቸው" አለ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 19 ከዚያም ኢየሱስ ሣሩ ላይ እንዲቀምጡ ሕዝቡን አዘዘ። ዐምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዐሣ ወሰደ፣ ወደ ሰማይ አሻቅቦ እያየ፣ አመሰገነ፤ እንጀራውንም ቈርሶ፣ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ ሰጡ።
|
||
\v 20 ሁሉም በልተው ጠገቡ፡፡ ከዚያም የተረፈውን ዐሥራ ሁለት መሶብ ሙሉ ቊርስራሽ ሰበሰቡ።
|
||
\v 21 የበሉትም፣ ከሴቶችና ከልጆች ሌላ፣ ዐምስት ሺ ያህል ወንዶች ነበሩ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 22 እርሱም ሕዝቡን እያሰናበተ እያለ፣ ደቀ መዛሙርቱን ወዲያው ወደ ጀልባ ገብተው፣ ከእርሱ በፊት ወደ ማዶ እንዲሄዱ አዘዛቸው።
|
||
\v 23 ሕዝቡን ካሰናበተ በኋላ፣ ብቻውን ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ። በመሸ ጊዜ፣ በዚያ እርሱ ብቻውን ነበር።
|
||
\v 24 ጀልባዋ በባሕሩ መካከል እያለች፤ ከተቃራኒ አቅጣጫ ይነፍስ ስለ ነበር፣ በማዕበሉ ክፉኛ ትንገላታ ነበር።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 25 ከምሽቱ በአራተኛው ክፍል፣ ኢየሱስ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ወደ እነርሱ እየመጣ ነበር።
|
||
\v 26 ደቀ መዛሙርቱም በባሕር ላይ እየተራመደ ሲያዩት፣ እጅግ ደንግጠው፣ “መንፈስ ነው”ብለው በፍርሀት ጮኹ።
|
||
\v 27 ኢየሱስ ግን ወዲያውኑ፣ “አይዟችሁ! እኔ ነኝ! አትፍሩ” ብሎ ተናገራቸው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 28 ጴጥሮስም መልሶ፣ “ጌታ ሆይ፣ አንተስ ከሆንህ፣ በውሃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ" አለው።
|
||
\v 29 ኢየሱስም፣ “ና" አለው። ስለዚህ ጴጥሮስ ከጀልባው ወጥቶ ወደ ኢየሱስ ለመሄድ፣ በውሃው ላይ ተራመደ።
|
||
\v 30 ነገር ግን ጴጥሮስ ነፋሱን አይቶ በመፍራት፣ መስጠም በጀመረ ጊዜ ፣ “ጌታ ሆይ፣ አድነኝ” ብሎ ጮኸ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 31 ኢየሱስም ያኔውኑ እጁን ዘርግቶ ጴጥሮስን ያዘውና፣ “አንተ እምነት የጎደለህ፣ ለምን ትጠራጠራለህ?” አለው።
|
||
\v 32 ከዚያም ኢየሱስና ጴጥሮስ ወደ ጀልባው በገቡ ጊዜ፣ ነፋሱ መንፈሱን አቆመ።
|
||
\v 33 በጀልባው ውስጥ የነበሩት ደቀ መዛሙርትም ኢየሱስን፣ “አንተ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብለው ሰገዱለት።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 34 ከተሻገሩም በኋላ፣ ጌንሳሬጥ ወደ ተባለ አገር መጡ።
|
||
\v 35 በዚያም ስፍራ የነበሩ ሰዎች ኢየሱስ መሆኑን ባወቁ ጊዜ፣ በአካባቢው ወዳለ ስፍራ ሁሉ መልእክት ላኩና፣ የታመመውን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ።
|
||
\v 36 የልብሱን ጫፍ ብቻ ለመንካት ለመኑት፣ የነኩትም ሁሉ ተፈወሱ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 15
|
||
\cl ምዕራፍ 15
|
||
\p
|
||
\v 1 ከዚያም አንዳንድ ፈሪሳውያንና የአይሁድ የሕግ መምህራን ከኢየሩሳሌም ኢየሱስን ለማነጋገር መጥተው እንዲህ አሉ፤
|
||
\v 2 "ደቀ መዛሙርትህ የሽማግሌዎችን ወግ የሚጥሱት ለምንድነው? ምግብ ከመብላታቸው በፊት እንደ ወጉ እጃቸውን አይታጠቡምና።"
|
||
\v 3 ኢየሱስም መለሰና፣ "እናንተስ ስለ ወጋችሁ ስትሉ ለምን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትተላለፋላችሁ?" አላቸው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 4 እግዚአብሔር፣ ‹አባትህንና እናትህን አክብር፣› ‹ስለ አባቱ ወይም ስለ እናቱ ክፉ የሚናገር በርግጥ ይሞታል› ብሏልና፡፡
|
||
\v 5 እናንተ ግን፣ "አባቱን ወይም እናቱን፣ 'ከእኔ የተቀበላችሁት ማንኛውም እርዳታ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ስጦታ ነው ትላላችሁ፡፡'
|
||
\v 6 ያ ሰው አባቱን ማክበር አያስፈልገውም። ስለ ወጋችሁ ስትሉ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 7 እናንተ ግብዞች፣ ኢሳይያስ ስለ እናንተ፣
|
||
\v 8 'ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤
|
||
\v 9 የሰዎችን ትእዛዝ እንደ ሕግ በመቊጠር የራሳቸውን ትምህርት ስለሚያስተምሩ፣ እኔን በከንቱ ያመልኩኛል›› ብሎ ትንቢት በመናገሩ መልካም አድርጓል።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 10 ከዚያ ሕዝቡን ወደ ራሱ ጠርቶ፣ "አድምጡ አስተውሉም፡-
|
||
\v 11 ወደ አፍ የሚገባ ሰውን ምንም አያረክስም፡፡ ይልቁንም ከአፍ የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ነው" አላቸው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 12 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ መጥተው ኢየሱስን፣ ‹‹ፈሪሳውያን ይህን ቃል ሲሰሙ እንደ ተሰናከሉ ዐወቀሃል?›› አሉት፡፡
|
||
\v 13 ኢየሱስም መለሰና፣ ‹‹አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል፤
|
||
\v 14 እነርሱን ተዉአቸው፤ ዐይነ ስውር መሪዎች ናቸው፡፡ አንድ ዐይነ ስውር ሌላውን ዐይነ ስውር ቢመራው ሁለቱም ተያይዘው ጕድጓድ ውስጥ ይወድቃሉ፡፡››
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 15 ጴጥሮስ መልሶ ኢየሱስን፣ ‹‹ይህን ምሳሌ አብራራልን›› አለው፡፡
|
||
\v 16 ኢየሱስ፣ ‹‹እናንተ ደግሞ አሁንም አታስተውሉምን?
|
||
\v 17 ወደ አፍ የሚገባው ሁሉ ወደ ሆድ እንደሚሄድና ከዚያም ዐይነ ምድር ሆኖ ወደ ውጭ እንደሚጣል አታስተውሉምን?
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 18 ዳሩ ግን ከአፍ የሚወጣ ከልብ ይወጣል፡፡ እነዚህ ነገሮች ሰውን ያረክሳሉ፡፡
|
||
\v 19 ከልብ ክፉ ዐሳብ፣ ነፍስ መግደል፣ ምንዝርና፣ ዝሙት፣ ስርቆት፣ የሐሰት ምስክርነትና ስድብ ይወጣሉ፤
|
||
\v 20 ሰውን የሚያረክሱት እነዚህ ናቸው፡፡ ነገር ግን ባልታጠበ እጅ መብላት ሰውን አያረክስም፡፡"
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 21 ቀጥሎም ኢየሱስ ከዚያ ወደ ጢሮስና ወደ ሲዶና ከተሞች አካባቢ ሄደ፡፡
|
||
\v 22 እነሆም፣ አንዲት ከነዓናዊት ሴት ከዚያ አካባቢ ወጣችና ጮኽ ብላ እንዲህ አለች፣ ‹‹የዳዊት ልጅ፣ ጌታ ሆይ፣ ማረኝ፡፡ ልጄ በጋኔን ተይዛ በጣም እየተሠቃየች ነው፡፡››
|
||
\v 23 ኢየሱስ ግን አንድም ቃል አልመለሰላትም፡፡ ደቀ መዛሙርቱ መጥተው፣ ‹‹ይህች ሴት ትጮኽብናለችና ሸኛት›› ብለው ለመኑት፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 24 ነገር ግን ኢየሱስ መልሶ፣ ‹‹እንደ በግ ወደ ጠፉት የእስራኤል ቤት ሰዎች ካልሆነ በቀር ወደ ማንም አልተላክሁም›› አለ፡፡
|
||
\v 25 ነገር ግን ሴቲቱ "ጌታ ሆይ፣ እርዳኝ" በማለት መጥታ በፊቱ ሰገደች፡፡
|
||
\v 26 ኢየሱስ መልሶ፣ "የልጆችን እንጀራ ወስዶ ለቡችሎች መጣል ትክክል አይደለም" አለ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 27 ሴቲቱ፣ "አዎን፣ ጌታ ሆይ፣ ቡችሎችም እኮ ከጌቶቻቸው ማዕድ ከሚወድቀው የተወሰነውን ትርፍራፊ ይበላሉ" አለች፡፡
|
||
\v 28 ከዚያም ኢየሱስ መልሶ፣ "አንቺ ሴት እምነትሽ ታላቅ ነው፤ ልክ እንደ ተመኘሽው ይሁንልሽ" አላት፡፡ ልጇም በዚያች ሰዓት ተፈወሰች፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 29 ኢየሱስ ከዚያ ቦታ ወደ ገሊላ ባሕር አቅራቢያ ሄደ፡፡ ከዚያም ወደ አንድ ኮረብታ ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ፡፡
|
||
\v 30 ብዙ ሕዝብም ወደ እርሱ መጡ፤ አንካሶችን፣ ዐይነ ስውሮችን፣ ዲዳዎችንና ጕንድሾችን፣ እንዲሁም ሌሎች ታመው የነበሩ ብዙዎችን ይዘው መጡ፡፡ በኢየሱስ እግር አጠገብም አስቀመጧቸው፤ እርሱም ፈወሳቸው፡፡
|
||
\v 31 ስለዚህ ሕዝቡ ዲዳዎች ሲናገሩ፣ ጕንድሾች ሲፈወሱ፣ አንካሶች ሲራመዱ፣ ዐይነ ስውሮችም ሲያዩ አይተው ተደነቁ፡፡ የእስራኤልንም አምላክ አመሰገኑ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 32 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ራሱ ጠርቶ፣ "ለሕዝቡ አዝንላቸዋለሁ፤ ምክንያቱም ከእኔ ጋር ሦስት ቀን ቈይተዋል፣ የሚበሉትም የላቸውም፡፡ በመንገድ ላይ ዝለው እንዳይወድቁ ሳይበሉ ዝም ብዬ አላሰናብታቸውም" አለ፡፡
|
||
\v 33 ደቀ መዛሙርቱ፣ "በዚህ በረሓ ይህን የሚያህል ብዙ ሕዝብ የሚያጠግብ እንጀራ ከየት እናገኛለን?" አሉት፡፡
|
||
\v 34 ኢየሱስ፣ "ስንት እንጀራ አላችሁ?" አላቸው፡፡ "ሰባት እንጀራና ጥቂት ትናንሽ ዐሣ አለ" አሉት፡፡
|
||
\v 35 ከዚያም ኢየሱስ ሕዝቡን መሬት ላይ እንዲቀመጡ አዘዛቸው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 36 ኢየሱስ ሰባቱን እንጀራና ዐሣዎቹን ይዞ ካመሰገነ በኋላ እንጀራውን ቈርሶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ ሰጧቸው፡፡
|
||
\v 37 ሕዝቡ ሁሉ በሉና ጠገቡ፡፡ ትርፍራፊውንም ሰበሰቡ፤ ትርፍራፊውም ሰባት ቅርጫት ሙሉ ነበር፡፡
|
||
\v 38 የበሉትም ከሴቶችና ከልጆች በቀር አራት ሺህ ወንዶች ነበሩ፡፡
|
||
\v 39 ከዚያም ኢየሱስ ሕዝቡን አሰናበተና በጀልባም ገብቶ መጌዶን ወደ ተባለ ክፍለ አገር ሄደ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 16
|
||
\cl ምዕራፍ 16
|
||
\p
|
||
\v 1 ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያንም መጥተው ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው በመጠየቅ ኢየሱስን ፈተኑት፡፡
|
||
\v 2 ነገር ግን ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አላቸው፣ "በመሸ ጊዜ ሰማዩ ቀልቷልና ዝናብ አይኖርም ትላላችሁ
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 3 በነጋ ጊዜም፣ ‹ዛሬ ሰማዩ ስለ ጠቈረ ይዘንባል› ትላላችሁ፤ የዘመኑን ምልክት ግን መለየት አትችሉም፡፡
|
||
\v 4 ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፤ ነገር ግን ከነቢዩ ከዮናስ ምልክት በቀር ሌላ ምልክት አይሰጠውም፡፡" ከዚያም ኢየሱስ ትቶአቸው ሄደ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 5 ደቀ መዛሙርቱ ወደ ማዶ ተሻገሩ፤ እንጀራ መያዝን ግን ረሱ፡፡
|
||
\v 6 ኢየሱስ፣ "ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁ፣ ተጠበቁም" አላቸው፡፡
|
||
\v 7 ደቀ መዛሙርቱ፣ "እንጀራ ስላልያዝን ነው" ብለው እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ፡፡
|
||
\v 8 ኢየሱስ ይህን ዐውቆ፣ "እናንተ እምነተ ጎደሎዎች፣ እንጀራ ስላልያዝን ነው ብላችሁ ስለ ምን እርስ በርሳችሁ ትነጋገራላችሁ?"
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 9 ዐምስት እንጀራ ለዐምስቱ ሺህ እንደ በቃና ስንት ቅርጫት እንደ ሰበሰባችሁ አሁንም አታስተውሉም ወይም አታስታውሱም?
|
||
\v 10 ወይም ደግሞ ሰባቱ እንጀራ ለአራቱ ሺህ እንደ በቃና ስንት ቅርጫት እንዳነሣችሁስ አታስታውሱምን?
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 11 እኔ የነገርኋችሁ ስለ እንጀራ እንዳልነበረ እንዴት ነው የማታስተውሉት? ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያ እርሾ ተጠንቀቁ፣ ተጠበቁም፡፡"
|
||
\v 12 ከዚያም እርሱ ሲነግራቸው የነበረው ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ትምህርት እንዲጠበቁ እንጂ፣ ስለ እንጀራ እርሾ እንዳልነበረ ተረዱ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 13 ኢየሱስም ወደ ቂሣርያ ፊልጶስ ክልል በመጣ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፣ "ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ነው ይላሉ?" በማለት ጠየቃቸው፡፡
|
||
\v 14 እነርሱ፣ እንዲህ አሉ፤ "አንዳንዶች መጥምቁ ዮሐንስ፣ ሌሎች ኤልያስ፣ የቀሩትም ኤርምያስ፣ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ፡፡"
|
||
\v 15 "እናንተስ እኔን ማን ትሉኛላችሁ?" አላቸው፡፡
|
||
\v 16 ስምዖን ጴጥሮስ፣ "አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ" በማለት መልስ ሰጠ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 17 ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለው፣ "የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፣ አንተ የተባረክህ ነህ፤ ይህን የገለጠልህ የሰማዩ አባቴ ነው እንጂ፣ ሥጋና ደም አይደለም፡፡
|
||
\v 18 ደግሞም አንተ ጴጥሮስ ነህም እላለሁ፤ በዚህም አለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆችም አያሸንፏትም፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 19 እኔ የመንግሥተ ሰማያትን መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፡፡ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የምትፈታውም ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል፡፡››
|
||
\v 20 ከዚያም ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ መሆኑን ለማንም እንዳይናገሩ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 21 ከዚያን ጊዜ አንሥቶ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም መሄድ፣ በሽማግሌዎችና በካህናት አለቆች፣ በፈሪሳውያንና በሕግ መምህራንም እጅ ብዙ መከራ መቀበልና መገደል፣ በሦስተኛውም ቀን መነሣት እንዳለበት ለደቀ መዛሙርቱ ይነግራቸው ጀመር፡፡
|
||
\v 22 ከዚያም ጴጥሮስ ኢየሱስን ለብቻው ገለል አድርጎ፣ "ጌታ ሆይ፣ ይህ ከአንተ ይራቅ፤ ይህም ከቶ አይሁንብህ" በማለት ገሠጸው፡፡
|
||
\v 23 ኢየሱስ ግን ዞር ብሎ ጴጥሮስን፣ "ከፊቴ ዞር በል፣ ሰይጣን! ስለ ሰው እንጂ ስለ እግዚአብሔር ነገር ደንታ የለህምና አንተ ለእኔ እንቅፋት ነህ" አለው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 24 ከዚያም በኋላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ "ሊከተለኝ የሚፈልግ ማንም ቢኖር፣ ራሱን መካድ፣ የራሱን መስቀል መሸከምና እኔን መከተል አለበት፡፡
|
||
\v 25 ሕይወቱን ለማዳን የሚፈልግ ሁሉ ያጣዋል፤ ስለ እኔ ሕይወቱን የሚያጣ ግን ያገኘዋል፡፡
|
||
\v 26 ሰው ሙሉውን ዓለም የራሱ ቢያደርግ ሕይወቱን ግን ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ሰው በሕይወቱ ፈንታ ምን መስጠት ይችላል?
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 27 የሰው ልጅ በአባቱ ክብር ከመላእክቱ ጋር ይመጣልና፡፡ ከዚያም ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው ይከፍለዋል፡፡
|
||
\v 28 እውነት እላችኋለሁ፤ እዚህ ከቆማችሁት መካከል የሰው ልጅ በመንግሥቱ ሲመጣ እስኪያዩ ድረስ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንዶች አሉ፡፡"
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 17
|
||
\cl ምዕራፍ 17
|
||
\p
|
||
\v 1 ከስድስት ቀን በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስን፣ ዮሐንስን፣ ያዕቆብንና ወንድሙን ይዞ ብቻቸውን ወደ ረጅም ተራራ አወጣቸው፡፡
|
||
\v 2 በፊታቸውም መልኩ ተለወጠ፤ ፊቱ እንደ ፀሐይ አበራ፤ ልብሱም እንደ ብርሃን አንጸባረቀ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 3 እነሆ፣ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው፡፡
|
||
\v 4 ጴጥሮስ መልሶ ኢየሱስን፣ "ጌታ ሆይ፣ እዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፡፡ ብትፈልግ እኔ እዚህ ሦስት ዳሶችን፡- አንድ ለአንተ፣ አንድ ለሙሴ፣ አንድ ለኤልያስ እሠራለሁ" አለው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 5 እርሱ ገና እየተናገረ እያለ፣ እነሆ፣ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፡፡ ከደመናውም፣ "በእርሱ እጅግ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት" የሚል ድምፅ ነበረ፡፡
|
||
\v 6 ደቀ መዛሙርቱ ድምፁን በሰሙ ጊዜ ፈሩ፣ በግንባራቸውም ወደቁ፡፡
|
||
\v 7 ከዚያም ኢየሱስ መጥቶ ዳሰሳቸውና፣ ‹‹ተነሡ አትፍሩ›› አላቸው፡፡
|
||
\v 8 ከዚያም እነርሱ ቀና ብለው ተመለከቱ፣ ነገር ግን ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 9 ከተራራ ሲወርዱም ኢየሱስ፣ "የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ይህን ያያችሁትን ለማንም አትንገሩ" ብሎ አዘዛቸው፡፡
|
||
\v 10 ደቀ መዛሙርቱ፣ "እንግዲያው የአይሁድ ሕግ መምህራን መጀመሪያ ኤልያስ መምጣት አለበት ለምን ይላሉ?" በማለት ጠየቁት፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 11 ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ፤ "ኤልያስ በርግጥ ይመጣል፣ ሁሉንም ነገር ያስተካክላል፡፡
|
||
\v 12 ነገር ግን እላችኋለሁ፤ ኤልያስ አስቀድሞ መጥቷል፤ ነገር ግን አላወቁትም፡፡ በዚህ ፈንታ የፈለጉትን ነገር ሁሉ አደረጉበት፡፡ በተመሳሳይ መንገድ የሰው ልጅ በእነርሱ እጅ መከራ ይቀበላል፡፡››
|
||
\v 13 በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ የተናገራቸው ስለ መጥምቁ ዮሐንስ እንደ ነበረ ተረዱ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 14 ወደ ሕዝቡ በመጡ ጊዜ አንድ ሰው መጥቶ በፊቱ ተንበረከከ፤ እንዲህም አለው፤
|
||
\v 15 "ጌታ ሆይ፣ ልጄን ማረው፣ የሚጥል በሽታ ይዞት በኀይል ይሠቃያል፤ ብዙ ጊዜ በእሳት ወይም በውሃ ውስጥ ይጥለዋልና፡፡
|
||
\v 16 ወደ ደቀ መዛሙርትህ አመጣሁት፤ ነገር ግን እነርሱ ሊፈውሱት አልቻሉም፡፡›
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 17 ኢየሱስ መልሶ፣ "የማታምኑና ምግባረ ብልሹ ትውልድ፣ እስከ መቼ ድረስ ከእናንተ ጋር እቆያለሁ? እስከ መቼስ እናንተን መታገሥ አለብኝ? እስቲ ወደ እኔ አምጡት" አለ፡፡
|
||
\v 18 ኢየሱስ ገሠጸው፤ ጋኔኑም ከእርሱ ወጣ፤ ልጁም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ተፈወሰ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 19 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ ኢየሱስ መጥተው፣ "እኛ ልናወጣው ያልቻልነው ለምንድን ነው?" አሉ፡፡
|
||
\v 20 ኢየሱስ፣ ‹‹በእምነታችሁ ማነስ ምክንያት፤ እውነት እላችኋለሁና፣ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት እንኳ ቢኖራችሁ ይህን ተራራ ከዚህ ተነሥተህ ወደ ማዶ ሂድ ብትሉት ይሄዳል፡፡ ማድረግ የሚሳናችሁ ምንም ነገር አይኖርም፡፡
|
||
\v 21 \f + \ft አንዳንድ የጥንት ቅጂዎች ቊጥር 21ን ያስቀሩታል፡፡ ነገር ግን የዚህ ዓይነቱ ጋኔን በጾምና በጸሎት ካልሆነ በቀር አይወጣም፡፡ \f*
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 22 በገሊላ እያሉ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፣ "የሰው ልጅ በሰዎች እጅ ተላልፎ ይሰጣል፤
|
||
\v 23 እነርሱም ይገድሉታል፤ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል" አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱ በጣም ዐዘኑ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 24 ወደ ቅፍርናሆም በመጡ ጊዜ ግማሽ ሰቅል ቀረጥ የሰበሰቡ ሰዎች ወደ ጴጥሮስ መጥተው፣ "መምህራችሁ ግማሽ ሰቅሉን ቀረጥ አይከፍልምን?" አሉ፡፡
|
||
\v 25 እርሱ፣ "አዎ" አለ፡፡ ጴጥሮስ ወደ ቤት በገባ ጊዜ ግን ኢየሱስ መጀመሪያ እርሱን ተናገረው፤ "ስምዖን ሆይ፣ ምን ይመስልሃል? የምድር ነገሥታት ቀረጥ ወይም ግብር የሚሰበስቡት ከማን ነው? ከዜጎቻቸው ወይስ ከውጭ አገር ሰዎች?" አለው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 26 ጴጥሮስ፣ "ከውጭ አገር ሰዎች" ባለ ጊዜ፣ ኢየሱስ እንዲህ አለው፤ "እንግዲያስ ዜጎቹ ከክፍያ ነጻ ናቸው፡፡
|
||
\v 27 ነገር ግን ቀረጥ ሰብሳቢዎቹን ኃጢአት እንዲሠሩ እንዳናደርጋቸው ወደ ባሕር ሄደህ መንጠቆ ጣል፤ በመጀመሪያ የምታጠምደውን ዐሣ አፍ ስትከፍት አንድ ሰቅል ታገኛለህ፤ ያንን ወስደህ ስለ እኔና ስለ አንተ ክፈል፡፡››
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 18
|
||
\cl ምዕራፍ 18
|
||
\p
|
||
\v 1 በዚያው ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ መጥተው፣ "በእግዚአብሔር መንግሥት ከሁሉ የሚበልጥ ማን ነው?" አሉ
|
||
\v 2 ኢየሱስ አንድ ትንሽ ልጅ ጠርቶ በመካከላቸው አቆመው፤
|
||
\v 3 እንዲህም አለ፡- "እውነት እላችኋለሁ፤ ንስሐ ካልገባችሁና እንደ ልጆች ካልሆናችሁ በምንም መንገድ ወደ መንግሥተ ሰማያት አትገቡም፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 4 ስለዚህ እንደዚህ ልጅ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሰው ሁሉ፣ እንዲሁ በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ይበልጣል፡፡
|
||
\v 5 እንደዚህ ያለውን ልጅ በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፡፡
|
||
\v 6 ነገር ግን በእኔ ከሚያምነው ከእነዚህ ልጆች አንዱን ኀጢአት እንዲሠራ የሚያደርግ ማንም፣ ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቁ ባሕር ቢሰጥም ይሻለዋል፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 7 የመሰናክል ምክንያት በመሆኗ ለዓለም ወዮላት! መሰናክል መምጣቱ ግድ ነው፤ ነገር ግን መሰናክሉን ለሚያመጣ ሰው ወዮለት!
|
||
\v 8 እጅህ ወይም እግርህ ቢያሰናክልህ፣ ቈርጠህ ከአንተ ጣለው፡፡ ሁለት እጆች ወይም እግሮች ኖረውህ ወደ ዘላለም እሳት ከምትጣል የአካል ጉዳተኛ ወይም አንካሳ ሆነህ ወደ ሕይወት ብትገባ ይሻልሃል፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 9 ዐይንህ እንድትሰናከል ቢያደርግህ፣ አውጥተህ ከአንተ ጣለው፡፡ ሁለት ዐይኖች ኖረውህ ወደ ዘላለም እሳት ከምትጣል፣ አንድ ዐይን ኖሮህ ወደ ሕይወት ብትገባ ይሻላል፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 10 ከእነዚህ ከታናናሾች ማንኛውንም እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፡፡ በሰማይ ያሉ መላእክታቸው በሰማይ ያለውን የአባቴን ፊት ሁልጊዜ ያያሉና፡፡ 11 (2) ብዙ ምንጮች፣ አንዳንድ የጥንት የሆኑ ቊ. 11ን ያስገባሉ፡፡
|
||
\v 11 \f + \ft አንዳንዶቹ ጥንታዊ የሆኑ፣ ብዙ ቅጂዎች ቊ11ን የሰው ልጅ የጠፋውን ለማዳን መጥቷልና፡፡ \f*
|
||
\s5
|
||
\v 12 ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው መቶ በጎች ቢኖሩት፣ ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ፣ ዘጠና ዘጠኙን በኮረብታው ጥግ ትቶ የጠፋውን ሊፈልግ አይሄድምን?
|
||
\v 13 በሚያገኘውም ጊዜ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ካልጠፉት ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ በእርሱ ደስ ይለዋል፡፡
|
||
\v 14 በተመሳሳይ መንገድ ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱ እንዲጠፋ የሰማዩ አባታችሁ ፈቃድ አይደለም፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 15 ወንድምህ ቢበድልህ፣ ሂድና አንተና እርሱ ብቻ ሆናችሁም ጥፋቱን አሳየው፡፡ ቢሰማህ፣ ወንድምህን የራስህ ታደርገዋለህ፡፡
|
||
\v 16 ባይሰማህ ግን፣ ቃል ሁሉ በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች ይጸናልና፣ ከአንተ ጋር አንድ ወይም ሁለት ተጨማሪ ወንድሞችን ይዘህ ሂድ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 17 እነርሱንም አልሰማም ቢል፣ ጉዳዩን ለቤተ ክርስቲያን ንገር፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ደግሞ አልሰማም ቢል፣ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ቊጠረው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 18 እውነት እላችኋለሁ፣ በምድር የምታስሩት ነገር ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የምትፈቱትም ነገር ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል፡፡
|
||
\v 19 በተጨማሪም እላችኋለሁ፣ ከእናንተ ሁለቱ በምድር ስለሚለምኑት ስለ ማንኛውም ነገር ቢስማሙ፣ በሰማይ ያለው አባቴ ያደርግላቸዋል፡፡
|
||
\v 20 ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት ቦታ እዚያ በመካከላቸው እገኛለሁና፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 21 ከዚያም ጴጥሮስ መጥቶ ኢየሱስን፣ ‹‹ጌታ ሆይ፣ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ይቅር ልበለው? እስከ ሰባት ጊዜ ነውን?›› አለው፡፡
|
||
\v 22 ኢየሱስም፣ ‹‹ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ፣ ሰባት ጊዜ አልልህም›› አለው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 23 ስለዚህ መንግሥተ ሰማያት ከአገልጋዮቹ ጋር ሒሳብ ሊተሳሰብ የፈለገ ንጉሥን ትመስላለች፡፡
|
||
\v 24 መተሳሰቡን እንደ ጀመረ፣ የዐሥር ሺህ መክሊት ዕዳ ያለበትን አገልጋይ ወደ እርሱ አመጡ፡፡
|
||
\v 25 ነገር ግን የሚከፍልበት መንገድ ስላልነበረው፣ ጌታው ከሚስቱና ከልጆቹ ጋር ያለውም ሁሉ ተሸጦ ክፍያው እንዲፈጸም አዘዘው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 26 ስለዚህ አገልጋዩ ወድቆ በፊቱ ተንበረከከ እንዲህም አለ፤ ‹ጌታዬ ሆይ፣ ታገሠኝ፣ ሁሉንም እከፍልሃለሁ፡፡›
|
||
\v 27 ስለዚህ የዚያ አገልጋይ ጌታ ስለ ራራለት፣ ተወው፤ ዕዳውንም ሠረዘለት፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 28 ነገር ግን ያ አገልጋይ ወጥቶ አብረውት ከሚሠሩት አገልጋዮች መቶ ዲናር ያበደረውን አንዱን አገልጋይ አግኝቶ ያዘው፤ ጕሮሮውን አነቀውና፣ ‹‹ያለብህን ዕዳ ክፈለኝ›› አለው፡፡
|
||
\v 29 ነገር ግን የሥራ ባልደረባው፣ ‹‹ታገሠኝ፣ እከፍልሃለሁ›› በማለት ወድቆ ለመነው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 30 የመጀመሪያው አገልጋይ ግን አሻፈረኝ አለ፤ በዚህ ፈንታ ያለበትን ዕዳ እስኪከፍለው ድረስ በእስር ቤት ጣለው፡፡
|
||
\v 31 የሥራ ጓደኞቹ የሆኑት አገልጋዮች የሆነውን ነገር ባዩ ጊዜ፣ በጣም ተበሳጩ፤ መጥተውም ለጌታቸው የሆነውን ሁሉ ነገሩት፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 32 ከዚያም የዚያ አገልጋይ ጌታ ጠራው፣ እንዲህም አለው፤ 'አንተ ክፉ አገልጋይ፣ ስለ ለመንኸኝ ያን ሁሉ ዕዳ ተውሁልህ፡፡
|
||
\v 33 እኔ አንተን እንደማርሁህ፣ የሥራ ባልደረባህ የሆነውን አገልጋይ ልትምረው አይገባህም ነበርን?'
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 34 ጌታው ተቈጥቶ ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍል ድረስ ለሚያሠቃዩት አሳልፎ ሰጠው፡፡
|
||
\v 35 ስለዚህም ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልብ ይቅር ባይል የሰማዩ አባቴ እንዲሁ ያደርግበታል፡፡"
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 19
|
||
\cl ምዕራፍ 19
|
||
\p
|
||
\v 1 እንዲህም ሆነ፤ ኢየሱስ ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ገሊላን ትቶ፣ በዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ወዳለው ወደ ይሁዳ ጠረፍ መጣ፡፡
|
||
\v 2 ብዙ ሕዝብ ተከተሉት፤ እዚያም ፈወሳቸው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 3 ፈሪሳውያን እንዲህ በማለት ሊፈትኑት ወደ እርሱ መጡ፤ "በማንኛውም ምክንያት ሰው ሚስቱን ቢፈታ ሕጋዊ ነውን?"
|
||
\v 4 ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ፣ "ከመጀመሪያው የፈጠራቸው እግዚአብሔር ወንድና ሴት አድርጎ እንደ ፈጠራቸውና
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 5 ደግሞም፣ 'በዚህ ምክንያት ሰው አባቱንና እናቱን ትቶ ከሚስቱ ጋር ይጣመራል፤ አንድ ሥጋም ይሆናሉ' የተባለውን አላነበባችሁምን?
|
||
\v 6 ስለዚህ እነርሱ ከእንግዲህ አንድ ሥጋ እንጂ ሁለት አይደሉም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር አንድ ላይ ያጣመረውን፣ ማንም አይለየው፡፡››
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 7 እነርሱ፣ "ታዲያ የፍቺ የምስክር ወረቀት ሰጥተን ከዚያ በኋላ እንድናባርራት ሙሴ ለምን አዘዘን?" አሉት፡፡
|
||
\v 8 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ "ከልባችሁ ድንዳኔ የተነሣ ሚስቶቻችሁን እንድትፈቱ ሙሴ ፈቀደላችሁ፤ ነገር ግን ከመጀመሪያው እንደዚያ አልነበረም፡፡
|
||
\v 9 እኔ እላችኋለሁ፣ ከዝሙት በቀር ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ፣ ሌላይቱንም የሚያገባ ያመነዝራል፤ የተፈታችውንም የሚያገባ ያመነዝራል፡፡"
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 10 ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን፣ "የባልና የሚስት ጉዳይ እንዲህ ከሆነ ማግባት ጥሩ አይደለም" አሉት፡፡
|
||
\v 11 ኢየሱስ ግን እንዲህ አላቸው፤ "እንዲቀበሉት የተፈቀደላቸው እንጂ፣ ሁሉም ሰው ይህን ትምህርት አይቀበለውም፡፡
|
||
\v 12 በተፈጥሮ ከእናታቸው ማኅፀን ስልብ ሆነው የተወለዱ አሉና፡፡ ሰዎች የሰለቧቸውም ይገኛሉ፡፡ ስለ መንግሥተ ሰማያት ሲሉም ራሳቸውን ስልብ ያደረጉ አሉ፡፡ ይህን ትምህርት መቀበል የሚችል፣ ይቀበለው፡፡››
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 13 በዚያን ጊዜ እጁን ጭኖ እንዲጸልይላቸው ሰዎች ልጆችን ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ገሠጿቸው፡፡
|
||
\v 14 ኢየሱስ ግን፣ "ልጆቹን ተዉአቸው፤ ወደ እኔም እንዲመጡ አትከልክሏቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉት ናትና" አለ፡፡
|
||
\v 15 15 እጁንም በልጆቹ ላይ ጫነባቸው፤ ከዚያም ያን ቦታ ትቶ ሄደ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 16 እነሆ፣ አንድ ሰው ወደ ኢየሱስ መጥቶ፣ ‹‹መምህር ሆይ፣ የዘላለም ሕይወት እንዳገኝ ምን መልካም ነገር ማድረግ አለብኝ?›› አለ፡፡
|
||
\v 17 ኢየሱስ፣ ‹‹ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም አንድ ብቻ ነው፤ ነገር ግን ወደ ሕይወት ለመግባት ብትፈልግ ትእዛዛትን ጠብቅ›› አለው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 18 ሰውዬው፣ ‹‹የትኞቹን ትእዛዛት? አለ፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አለው፤ "አትግደል፤" "አታመንዝር" "አትስረቅ፤" "በሐሰት አትመስክር፤"
|
||
\v 19 "አባትህንና እናትህን አክብር፤" እንዲሁም፣ "ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፡፡"
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 20 ወጣቱ፣ "እነዚህን ነገሮች ሁሉ ፈጽሜአለሁ፣ ሌላስ ምን ያስፈልገኛል?" አለው፡፡
|
||
\v 21 ኢየሱስ እንዲህ አለው፤ "ፍጹም ለመሆን ብትፈልግ፣ ሂድና ያለህን ሽጠህ ለድኾችም ስጠው፤ በሰማይም ሀብት ይኖርሃል፡፡ ከዚያም መጥተህ ተከተለኝ፡፡››
|
||
\v 22 ነገር ግን ወጣቱ ኢየሱስ የተናገረውን በሰማ ጊዜ፣ ብዙ ንብረት ነበረውና ዐዝኖ ሄደ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 23 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ "እውነት እላችኋለሁ፤ ለባለ ጠጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት ከባድ ነው፡፡
|
||
\v 24 ደግሜ እላችኋለሁ፤ ለባለ ጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከመግባት፣ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል፡፡"
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 25 ደቀ መዛሙርቱ ይህን በሰሙ ጊዜ በጣም ተደነቁና፣ "ታዲያ ማን ሊድን ይችላል?" አሉ፡፡
|
||
\v 26 ኢየሱስ ወደ እነርሱ ተመልክቶ፣ "ይህ ለሰዎች የማይቻል ነው፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል" አለ፡፡
|
||
\v 27 ከዚያም ጴጥሮስ መልሶ፣ "ተመልከት፣ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ፤ ታዲያ ምን እናገኛለን?" አለ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 28 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ "እውነት እላችኋለሁ፣ እናንተ እኔን የተከተላችሁኝ፣ በዐዲሱ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን ላይ በሚቀመጥበት ጊዜ፣ እናንተም በዐሥራ ሁለት ዙፋኖች ላይ ትቀመጣላችሁ፤ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶችም ላይ ትፈርዳላችሁ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 29 ስለ ስሜ ቤቶችን፣ ወንድሞችን፣ እኅቶችን፣ አባትን፣ እናትን፣ ልጆችን፣ ወይም ርስትን የተወ ሁሉ፣ መቶ እጥፍ ይቀበላል፣ የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል፡፡
|
||
\v 30 ነገር ግን አሁን ፊተኞች የሆኑ ብዙዎች ኋለኞች ይሆናሉ፤ ኋለኞች የሆኑ ብዙዎችም ፊተኞች ይሆናሉ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 20
|
||
\cl ምዕራፍ 20
|
||
\p
|
||
\v 1 መንግሥተ ሰማይ ለወይኑ አትክልት ሠራተኞችን ሊቀጥር ማልዶ የወጣ ባለቤትን ትመስላለች።
|
||
\v 2 በቀን አንዳንድ ዲናር ሊከፍላቸው ከሠራተኞቹ ጋር ከተስማማ በኋላ፣ ወደ ወይኑ አትክልት ስፍራ ላካቸው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 3 ደግሞም በሦስት ሰዓት ገደማ ወጥቶ በገበያ ቦታ ሥራ ፈትተው የቆሙ ሌሎች ሠራተኞችን አየና፣
|
||
\v 4 'እናንተ ደግሞ ወደ ወይኑ አትክልት ስፍራ ሂዱ፤ የሚገባችሁንም እከፍላችኋለሁ' አላቸው። ስለዚህ እነርሱም ሊሠሩ ሄዱ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 5 ደግሞ በስድስት ሰዓትና በዘጠኝ ሰዓት ገደማ ወጥቶ እንደዚሁ አደረገ።
|
||
\v 6 አሁንም በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ገደማ ወጥቶ ሥራ ፈትተው የቆሙ ሌሎችን አገኘ። እነርሱንም፣ 'ቀኑን ሙሉ ሥራ ፈትታችሁ እዚህ ለምን ቆማችኋል?' አላቸው።
|
||
\v 7 'ማንም ስላልቀጠረን ነው' አሉት። 'እናንተም ደግሞ ወደ ወይኑ አትክልት ስፍራ ሂዱ' አላቸው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 8 ቀኑ በመሸ ጊዜ፣ የወይኑ አትክልት ባለቤት ሥራ አስኪያጁን፣ 'ሠራተኞቹን ጥራ ከኋለኞቹ አንሥተህ እስከ ፊተኞቹ የሠሩበትን ገንዘብ ክፈላቸው' አለው።
|
||
\v 9 በዐሥራ አንደኛው ሰዓት የተቀጠሩት ሠራተኞች በመጡ ጊዜ፣ እያንዳንዳቸው አንዳንድ ዲናር ተቀበሉ።
|
||
\v 10 ፊተኞቹ ሠራተኞች በመጡ ጊዜ፣ የበለጠ የሚቀበሉ መሰላቸው፤ ነገር ግን እነርሱም ደግም እያንዳንዳቸው አንዳንድ ዲናር ተቀበሉ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 11 ገንዘባቸውን በተቀበሉ ጊዜ፣ በወይኑ አትክልት ባለቤት ላይ አጕረመረሙ።
|
||
\v 12 እንዲህም አሉ፤ 'እነዚህ በመጨረሻ የመጡ ሠራተኞች በሥራ ላይ አንድ ሰዓት ብቻ አሳልፈዋል፤ ነገር ግን አንተ የዕለቱን ሸክምና የሚለበልበውን ሙቀት ከተሸከምነው ከእኛ ጋር እኩል አድርገሃቸዋል።'
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 13 ባለቤቱ ግን መልሶ ከእነርሱ አንዱን እንዲህ አለው፤ "ወዳጄ ሆይ፣ አልበደልኩህም። ከእኔ ጋር በአንድ ዲናር አልተስማማህምን?
|
||
\v 14 የሚገባህን ተቀብለህ መንገድህን ሂድ፤ ለእነዚህ በመጨረሻ ለተቀጠሩት ሠራተኞች ልክ እንደ አንተው ልሰጣቸው ደስ ይለኛል።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 15 በገዛ ንብረቴ የፈለግሁትን ማድረግ አይገባኝምን? ወይስ እኔ ደግ ስለ ሆንሁ ትመቀኛለህን?
|
||
\v 16 ስለዚህ ኋለኞች ፊተኞች፣ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ።"
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 17 ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይወጣ ስለ ነበር፣ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ለብቻቸው ወሰደ፤ በመንገድ ላይም እንዲህ አላቸው፦
|
||
\v 18 እነሆ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፤ የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለሕግ መምህራን ተላልፎ ይሰጣል። ሞትም ይፈርዱበታል፤
|
||
\v 19 እንዲዘብቱበት፣ እንዲገርፉት፣ እንዲሰቅሉትም ለአሕዛብ ይሰጡታል። ነገር ግን በሦስተኛው ቀን ይነሣል።"
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 20 በዚያን ጊዜ የዘብዴዎስ ልጆች እናት ከልጆቿ ጋር ወደ ኢየሱስ መጣች፤ በፊቱ ተንበርክካም ከእርሱ አንድ ነገር ለመነች።
|
||
\v 21 ኢየሱስ፣ "ምን ትፈልጊያለሽ?" አላት። እርሷም፣ "በመንግሥትህ እነዚህ ሁለት ልጆቼ አንዱ በቀኝህ፣ አንዱም በግራህ እንዲቀመጡ እዘዝ" አለችው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 22 ኢየሱስ ግን መልሶ፣ "የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ የምጠጣውን ጽዋ መጠጣት ትችላላችሁን?" አለ። እነርሱ፣ "እንችላለን" አሉት።
|
||
\v 23 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ "በርግጥ ጽዋዬን ትጠጣላችሁ። በቀኜና በግራዬ መቀመጥን የምሰጥ ግን እኔ አይደለሁም፤ ነገር ግን በአባቴ ለተዘጋጀላቸው ለእነርሱ ነው።"
|
||
\v 24 ሌሎቹ ዐሥሩ ደቀ መዛሙርት ይህን በሰሙ ጊዜ፣ በሁለቱ ወንድማማች ላይ ተቈጡ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 25 ነገር ግን ኢየሱስ ወደ ራሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፣ "የአሕዛብ አለቆች ሕዝባቸውን ጨቊነው ይገዛሉ፤ የበላዮቻቸውም ይሠለጥኑባቸዋል።
|
||
\v 26 በእናንተ መካከል ግን እንዲህ መደረግ የለበትም። ይልቁንም፣ ከእናንተ መካከል ታላቅ ሊሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋያችሁ ይሁን፤
|
||
\v 27 ከእናንተም ፊተኛ ሊሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋያችሁ ይሁን።
|
||
\v 28 የሰው ልጅ ሊያገለግል፣ ሕይወቱንም ለብዙዎች ቤዛ አድርጎ ሊሰጥ እንጂ፣ እንዲያገለግሉት አልመጣም።"
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 29 ከኢያሪኮ እንደ ወጡ፣ ብዙ ሕዝብ ኢየሱስን ተከተሉት።
|
||
\v 30 እነሆ፣ ሁለት ዐይነ ስውሮች በመንገድ ዳር ተቀምጠው ነበር፤ ኢየሱስ ሲያልፍ በሰሙ ጊዜ ጮኽ ብለው፣ "ጌታ ሆይ፣ የዳዊት ልጅ፣ ማረን" አሉ።
|
||
\v 31 ሕዝቡ ግን ዝም እንዲሉ በመንገር ገሠጿቸው። ይሁን እንጂ፣ እነርሱ አብዝተው በመጮኽ፣ "ጌታ ሆይ፣ የዳዊት ልጅ ማረን" አሉ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 32 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ቆም ብሎ ጠራቸውና፣ "ምን እንዳደርግላችሁ ትፈልጋላችሁ?" አለ።
|
||
\v 33 እነርሱም፣ "ጌታ ሆይ፣ ዐይኖቻችን እንዲከፈቱ ነው" አሉት።
|
||
\v 34 ከዚያም ኢየሱስ ራርቶ፣ ዐይኖቻቸውን ዳሰሰ። እነርሱም ወዲያውኑ አይተው ተከተሉት።
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 21
|
||
\cl ምዕራፍ 21
|
||
\p
|
||
\v 1 ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሩሳሌም እንደቀረቡ፣ በደብረ ዘይት ወዳለው ወደ ቤተ ፋጌ መጡ፤
|
||
\v 2 ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ በማለት ሁለት ደቀ መዛሙርት ላከ፤ “ወደሚቀጥለው መንደር ሂዱ፤ አህያም ከነውርንጫዋ ታስራ ታገኛላችሁ። ፈትታችሁ ወደ እኔ አምጧቸው፤
|
||
\v 3 ማንም ስለዚያ አንዳች ቢናገራችሁ፣ እርሱም ከእናንተ ጋር ፈጥኖ ይሰዳቸዋል።”
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 4-5 ይህ የሆነው፣ “እነሆ፣ ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ በአህያና በውርንጫዋ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል ብላችሁ ለጽዮን ልጅ ንገሯት” ተብሎ በነቢዩ የተተነበየው ይፈጸም ዘንድ ነው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 6 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ሄደው ልክ ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ።
|
||
\v 7 አህያይቱንና ውርንጫዋን አመጡ፤ ልብሳቸውንም አደረጉባቸውና ኢየሱስ ተቀመጠባቸው።
|
||
\v 8 ከሕዝቡ አብዛኞቹ ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፣ ሌሎችም የዘንባባ ዝንጣፊ እየቈረጡ በመንገድ ላይ አደረጉ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 9 ከኢየሱስ ፊት ይሄዱ የነበሩትና የተከተሉትም ሕዝብ፣ “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ እርሱ የተባረከ ነው። ሆሣዕና በአርያም ይሁን!” በማለት ጮኹ።
|
||
\v 10 ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ ከተማይቱ በሞላ ታወከችና፣ “ይህ ማን ነው?” አለች።
|
||
\v 11 ሕዝቡ፣ “ይህ ከገሊላ ናዝሬት የሆነው ነቢዩ ኢየሱስ ነው” ብለው መለሱ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 12 ከዚያም ኢየሱስ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሄደ። በቤተ መቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን አስወጣ። የገንዘብ ለዋጮችን ጠረጴዛዎችና ወንበሮች ገለበጠ።
|
||
\v 13 እንዲህም አላቸው፤ ‘ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል’ ተብሎ ተጽፏል። እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት።"
|
||
\v 14 ከዚያም ዐይነ ስውሮችና ሽባዎች ወደ እርሱ ወደ ቤተ መቅደስ መጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 15 ነገር ግን የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን እርሱ ያደረጋቸውን ድንቅ ነገሮች ባዩና በቤተ መቅደስ ልጆች፣ “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ” በማለት ሲጮኹ በሰሙ ጊዜ፣ ተቈጡ።
|
||
\v 16 “ሕዝቡ የሚሉትን ትሰማለህን?” አሉት። ኢየሱስ፣ “አዎ! ነገር ግን ‘ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ’ የሚለውን ከቶ አላነበባችሁምን?” አላቸው።
|
||
\v 17 ከዚያም ኢየሱስ ትቷቸው ከከተማው ወጣና ወደ ቢታንያ ሄዶ በዚያ ዐደረ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 18 ኢየሱስ ጠዋት ወደ ከተማው እንደተመለሰ፣ ተራበ።
|
||
\v 19 በመንገድ ዳር አንዲት የበለስስ ተክል አየና ወደ እርሷ ሄደ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም። “ሁለተኛ ከቶ ፍሬ አይገኝብሽ” አላት። የበለስ ተክሊቱም ወዲያውኑ ደረቀች።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 20 ደቀ መዛሙርቱ ባዩአት ጊዜ ተደንቀው፣ “የበለስ ተክሊቱ እንዴት ወዲያውኑ ደረቀች?” አሉ።
|
||
\v 21 ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አላቸው፤ "እውነት እላችኋለሁ፣ እምነት ቢኖራችሁና ባትጠራጠሩ፣ በዚች የበለስ ተክል የሆነባትን ብቻ ሳይሆን፣ ይህን ኮረብታ ከዚህ ተነሥተህ ወደ ባሕር ተወርወር ብትሉት እንኳ ይሆናል።
|
||
\v 22 አምናችሁ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ።”
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 23 ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ሲያስተምር የካህናት አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሌዎች ወደ እርሱ መጥተው፣ “በምን ሥልጣን እነዚህን ነገሮች ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ?” አሉ።
|
||
\v 24 ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “እኔ ደግሞ አንድ ጥያቄ እጠይቃችኋለሁ። ያንን ከነገራችሁኝ እኔ ደግሞ በማን ሥልጣን እነዚህን ነገሮች እንደማደርግ እነግራችኋለሁ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 25 የዮሐንስ ጥምቀት ከየት መጣ ከሰማይ ነውን ወይስ ከሰዎች?” እርስ በርሳቸው እንዲህ በማለት ተነጋገሩ፤ “ከሰማይ ነው ብንለው፣ ‘ለምን አታምኑትም?’ ይለናል።
|
||
\v 26 ነገር ግን ‘ከሰው ነው ብንል፣ ዮሐንስን እንደ ነቢይ ስለሚያዩት ሕዝቡን እንፈራለን።”
|
||
\v 27 ከዚያም መልሰው ኢየሱስን፣ “አናውቅም” አሉት። እርሱ ደግሞ፣ “እኔም በምን ሥልጣን እነዚህን ነገሮች እንደማደርግ አልነግራችሁም” አላቸው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 28 ነገር ግን ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት፣ ወደ መጀመሪያው ሄዶ፣ ልጄ ሆይ፣ ዛሬ ወደ ወይኑ አትክልት ስፍራ ሄደህ ሥራ’ አለው።
|
||
\v 29 ልጁ መልሶ፣ ‘አልሄድም’ አለ፤ በኋላ ግን ዐሳቡን ለውጦ ሄደ።
|
||
\v 30 ሰውዬውም ወደ ሁለተኛው ልጅ ሄዶ ይህንኑ ነገረው። ይህኛው ልጅ መልሶ፣ ‘እሄዳለሁ፣ አባዬ’ አለ። ነገር ግን አልሄደም።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 31 ከሁለቱ ልጆች የአባቱን ትእዛዝ የፈጸመው የትኛው ነው? እነርሱ፣ "የመጀመሪያው” አሉ። ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና አመንዝራዎች ቀድመዋችሁ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ይገባሉ።
|
||
\v 32 ዮሐንስ በጽድቅ መንገድ ወደ እናንተ መጥቶ ነበርና፤ እናንተ ግን አላመናችሁትም፤ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና አመንዝራዎች ግን አመኑት። እናንተም ይህ ሲሆን አይታችሁ ታምኑት ዘንድ በኋላ እንኳ ንሰሐ አልገባችሁም።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 33 ሌላም ምሳሌ ስሙ። ሰፊ መሬት ያለው አንድ ሰው ነበር። የወይን አትክልት ተከለ፤ ዐጥር አጠረለት፤ የወይን መጥመቂያ ማሰለት፤ መጠበቂያ ማማ ሠራለት፤ ለወይን ገበሬዎችም አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ።
|
||
\v 34 የወይን ፍሬ የሚሰበሰብበት ጊዜ እንደ ደረሰ፣ ፍሬውን እንዲቀበሉ ጥቂት አገልጋዮችን ላከ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 35 የወይኑ ገበሬዎች ግን አገልጋዮቹን ያዙ፤ አንዱን ደበደቡት፣ ሌላውን ገደሉት፤ ሌላውንም በድንጋይ ወገሩት።
|
||
\v 36 ባለቤቱ እንደ ገና ከፊተኞቹ የበዙ ሌሎች አገልጋዮችን ላከ፤ ነገር ግን የወይን ገበሬዎቹ ያንኑ አደረጉባቸው።
|
||
\v 37 ከዚያ በኋላ ባለቤቱ፣ ‘ልጄንስ ያከብሩታል’ በማለት የገዛ ልጁን ላከ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 38 የወይን ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩ ጊዜ፣ እርስ በርሳቸው፣ 'ይህ ወራሹ ነው፤ ኑ፣ እንግደለውና ርስቱን እንውረስ’ ተባባሉ።
|
||
\v 39 ስለዚህ ያዙትና ከወይኑ አትክልት ስፍራ ወደ ውጭ ጣሉት፤ ገደሉትም።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 40 እንግዲህ የወይኑ አትክልት ባለቤት በሚመጣበት ጊዜ እነዚያን የወይን ገበሬዎች ምን ያደርጋቸዋል?”
|
||
\v 41 ሕዝቡ እንዲህ አሉት፤ “እነዚያን ክፉ ሰዎች እጅግ በጣም አሰቃቂ በሆነ መንገድ ያጠፋቸዋል፤ ከዚያም የወይኑን አትክልት ስፍራ ወይኑ በሚያፈራበት ጊዜ ገንዘቡን ለሚከፍሉ ለሌሎች የወይን ገበሬዎች ያከራየዋል።”
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 42 ኢየሱስ እነርሱን፣ “ 'ግንበኞች የናቁት ድንጋይ የማዕዘን ራስ ሆነ። ይህ ከጌታ ዘንድ ሆነ፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው ተብሎ የተጻፈውን ፈጽሞ አላነበባችሁም?’
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 43 ስለዚህ እላችኋለሁ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ትወሰድና ፍሬዋን ለሚያፈራ ሕዝብ ትሰጣለች።
|
||
\v 44 በዚህ ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ሁሉ ይሰባበራል። ድንጋዩ የሚወድቅበትን ሁሉ ግን ይፈጨዋል።”
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 45 የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ምሳሌዎቹን በሰሙ ጊዜ፣ የተናገረው ስለ እነርሱ እንደ ሆነ ተረዱ።
|
||
\v 46 ነገር ግን ሊይዙት በፈለጉ ጊዜ ሁሉ፣ ሰዎቹ እንደ ነቢይ ይቈጥሩት ስለ ነበር ሕዝቡን ፈሩ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 22
|
||
\cl ምዕራፍ 22
|
||
\p
|
||
\v 1 ኢየሱስም ደግሞ እንዲህ በማለት በምሳሌ መለሰላቸው፤
|
||
\v 2 "መንግሥተ ሰማይ ለልጁ የሰርግ ድግስ የደገሰ ንጉሥን ትመስላለች፡፡
|
||
\v 3 ወደ ሰርጉ እንዲመጡ ወደ ጋበዛቸው ሰዎች አገልጋዮቹን ላከ፤ እነርሱ ግን መምጣት አልፈለጉም፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 4 እንደ ገና ንጉሡ ሌሎች አገልጋዮችን እንዲህ በማለት ላከ፤ "እነሆ፣ እራት አዘጋጅቻለሁ፤ በሬዎቼንና የሰቡ ወይፈኖቼን አርጃለሁ፤ ሁሉም ተዘጋጅቶአልና ወደ ሰርግ ግብዣው ኑ በሏቸው፡፡' "
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 5 ሰዎቹ ግን ግብዣውን ከልብ አልተቀበሉትም፡፡ አንዳንዶቹ ወደ እርሻዎቻቸው፣ ሌሎች ደግሞ ወደ ሥራ ቦታቸው ሄዱ፡፡
|
||
\v 6 አንዳንዶቹ የንጉሡን አገልጋዮች ደበደቡአቸው፤ አዋረዱአቸው፤ ገደሉአቸው፡፡
|
||
\v 7 ንጉሡ ግን ተቈጣ፤ ወታደሮቹን ላከ፤ እነዚያን ነፍሰ ገዳዮች ገደለ፤ ከተማቸውንም አቃጠለ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 8 ከዚያም ለአገልጋዮቹ እንዲህ አለ፤ 'ሰርጉ ተዘጋጅቶአል፤ ጥሪ የተደረገላቸው ሰዎች ግን የሚገባቸው ሆነው አልተገኙም፡፡
|
||
\v 9 ስለዚህ ወደ ዐውራ መንገድ ማቋረጫ ሄዳችሁ የምታገኙአቸውን ያህል ሰዎች ወደ ሰርጉ ግብዣ ጥሩ፡፡
|
||
\v 10 ሰዎቹም ወደ ዐውራው መንገድ ሄደው መልካምም ሆኑ መጥፎዎች ያገኙአቸውን ሁሉ አንድ ላይ ሰበሰቡ፡፡ ስለዚህ የግብዣው አዳራሽ በተጋባዦች ተሞላ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 11 ንጉሡ ተጋባዦቹን ለማየት ሲመጣ ግን፣ የሰርግ ልብስ ያልለበሰ ሰው አየ፡፡
|
||
\v 12 ንጉሡ እንዲህ አለው፤ ‹ወዳጄ፣' የሰርግ ልብስ ሳትለብስ እንዴት ወደዚህ ገባህ?› ሰውየውም ዝም አለ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 13 ከዚያም ንጉሡ ለአገልጋዮቹ እንዲህ አላቸው፤ እጅና እግሩን አስራችሁ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጥታችሁ ጣሉት፡፡'
|
||
\v 14 የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸው፡፡"
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 15 ከዚያም ፈሪሳውያን ሄደው ኢየሱስን እንዴት በንግግሩ ማጥመድ እንደሚችሉ ዕቅድ አወጡ፡፡
|
||
\v 16 ከዚያም ከሄሮድስ ሰዎች ጋር ደቀ መዛሙርታቸውን ወደ እርሱ ላኩ፡፡ ኢየሱስንም እንዲህ አሉት፤ "መምህር ሆይ፣ አንተ በእውነት የእግዚአብሔርን መንገድ የምታስተምር እውነተኛ ሰው መሆንህን እናውቃለን፤ ሰውን በመፍራት ዐሳብህን አትለውጥም፤ በሰዎች መካከል አድልዎ አታደርግም፡፡
|
||
\v 17 እስቲ ንገረን ምን ይመስልሃል? ለቄሳር ግብር መስጠት ተገቢ ነው ወይስ አይደለም?"
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 18 ኢየሱስ ግን ተንኰላቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፤ "እናንት ግብዞች የምትፈትኑኝ ለምንድን ነው?
|
||
\v 19 እስቲ የግብሩን ገንዘብ አሳዩኝ" አላቸው፡፡ እነርሱም ዲናሩን አመጡለት፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 20 ኢየሱስም፣ "ይህ የማን መልክና ስም ነው?›› አላቸው፡፡
|
||
\v 21 እነርሱም፣ "የቄሣር፣" አሉት፡፡ ከዚያም ኢየሱስ፣ "እንግዲያስ የቄሣር የሆነውን ለቄሣር ስጡ፤ የእግዚአብሔር የሆነውን ለእግዚአብሔር ስጡ" አላቸው፡፡
|
||
\v 22 ያንን ሲሰሙ ተገረሙ፡፡ ትተውትም ሄዱ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 23 በዚያው ቀን ትንሣኤ ሙታን የለም የሚሉ ጥቂት ሰዱቃውያን ወደ እርሱ መጡ፡፡
|
||
\v 24 "መምህር ሆይ፣ ‹አንድ ሰው ልጅ ሳይወልድ ከሞተ ሚስቱን ወንድሙ እንዲያገባና ለወንድሙ ልጅ እንዲወልድለት ሙሴ ተናግሮአል›
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 25 ሰባት ወንድማማች ነበሩ፡፡ የመጀመሪያው አግብቶ ልጅ ሳይወልድ ሞተ፡፡ ሚስቱ የወንድምየው ሆነች፡፡
|
||
\v 26 ሁለተኛውና ሦስተኛውም እስከ ሰባተኛው ድረስ ያንኑ አደረጉ፡፡
|
||
\v 27 ከሁሉም በኋላ ደግሞ ሴትየዋ ሞተች፡፡
|
||
\v 28 እንግዲህ ሰባቱም ወንድማማች አግብተዋት ነበርና በትንሣኤ ቀን የማንኛው ሚስት ልትሆን ነው?" በማለት ጠየቁት፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 29 ኢየሱስ ግን እንዲህ በማለት መለሰላቸው፤ "መጻሕፍትንም ሆነ የእግዚአብሔርን ኀይል ስለማታወቁ ተሳስታችኋል፡፡
|
||
\v 30 ምክንያቱም በትንሣኤ ቀን እንደ ሰማይ መላእክት ይሆናሉ እንጂ፣ አያገቡም፣ ደግሞም አይጋቡም፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 31 ትንሣኤ ሙታንን በተመለከተ፣ እግዚአብሔር
|
||
\v 32 "እኔ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብም አምላክ ነኝ" በማለት ለእናንተ የተናገረውን አላነበባችሁምን? እግዚአብሔር የሕያዋን አምላክ እንጂ፣ የሙታን አምላክ አይደለም፡፡"
|
||
\v 33 ሕዝቡ ይህን ሲሰሙ በትምህርቱ ተገረሙ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 34 ኢየሱስ ሰዱቃውያንን ዝም እንዳሰኛቸው ፈሪሳውያን ሲሰሙ፣ በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡
|
||
\v 35 ከእነርሱ መካከል ሕግ ዐዋቂ የሆነ አንዱ እርሱን ለመፈተን፣
|
||
\v 36 "መምህር ሆይ፣ ከሕጉ ሁሉ የሚበልጠው ትእዛዝ የትኛው ነው" ብሎ ጠየቀው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 37 ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ "እግዚአብሔር አምላክህን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህና በሙሉ ዐሳብህ ውደድ፡፡"
|
||
\v 38 ከሁሉም የሚበልጠው የመጀመሪያው ትእዛዝ ይህ ነው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 39 ሁለተኛውም ትእዛዝ ያንኑ ይመስላል፤ 'ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፡፡'
|
||
\v 40 ሕግና ነቢያት ሁሉ የትመሠረቱት በእነዚህ ሁለት ትእዛዛት ላይ ነው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 41 ፈሪሳውያን በአንድነት ተሰብስበው እያለ ኢየሱስ አንድ ጥያቄ አቀረበላቸው፡፡
|
||
\v 42 "ስለ ክርስቶስ ምን ታስባላችሁ? ለመሆኑ የማን ልጅ ነው?" አላቸው፡፡ "የዳዊት ልጅ ነው" አሉት፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 43 ኢየሱስም፣ "ታዲያ፣ ዳዊት፣ በመንፈስ፣
|
||
\v 44 ጌታ ጌታዬን ‹ጠላቶችህን በእግርህ ሥር እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ' በማለት እንዴት ጌታ ብሎ ይጠራዋል?
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 45 ዳዊት ክርስቶስን 'ጌታ' በማለት ከጠራው እንዴት የዳዊት ልጅ ሊሆን ይችላል?"
|
||
\v 46 ማንም አንዲት ቃል ሊመልስለት አልቻለም፤ ከዚያ ቀን ጀምሮ ጥያቄ ሊያቀርብለት የደፈረ አልነበረም፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 23
|
||
\cl ምዕራፍ 23
|
||
\p
|
||
\v 1 ከዚያም ኢየሱስ ለሕዝቡና ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ሲል ተናገረ፤
|
||
\v 2 "የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል፡፡
|
||
\v 3 ስለዚህ የሚያዝዙአችሁን ሁሉ አድርጉ፤ አክብሩትም፡፡ እነርሱ የሚያደርጉትን ግን አታደርጉ፤ ምክንያቱም እነርሱ ራሳቸው የሚናገሩትን አያደርጉትም፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 4 ለመሸከም የሚያስቸግር ከባድ ሸክም አንሥተው በሰዎች ትከሻ ላይ ይጭናሉ፡፡ እነርሱ ራሳቸው ግን መሸከም ቀርቶ በጣታቸው ሊያነሡት እንኳ አይፈልጉም፡፡
|
||
\v 5 ሥራቸውን ሁሉ የሚያደርጉት በሰዎች ለመታየት ነው፤ አሸንክታባቸውን ያሰፋሉ፤ የልብሳቸውንም ዘርፍ ያስረዝማሉ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 6 ግብዣ ላይ የከበሬታ ቦታዎችንና በምኵራብ ውስጥ የተለየ መቀመጫ እንዲሰጣቸው ይፈልጋሉ፤
|
||
\v 7 በገበያ ቦታ ሰዎች የተለየ ክብር እንዲሰጧቸውና፣ 'መምህር ሆይ› በማለት እንዲጠሩአቸው ይፈልጋሉ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 8 እናንተ ግን ያላችሁ አንድ መምህር ብቻ ስለሆነና ሁላችሁም ወንድማማች ስለሆናችሁ ‹መምህር› ተብላችሁ አትጠሩ፡፡
|
||
\v 9 በምድር ላይ ማንንም አባት ብላችሁ አትጥሩ፤ ምክንያቱም በሰማይ የሚኖር አንድ አባት ብቻ አላችሁ፡፡
|
||
\v 10 ‹ሊቅም› ተብላችሁ አትጠሩ፤ ምክንያቱም ያላችሁ አንድ ሊቅ ብቻ ነው፤ እርሱም ክርስቶስ ነው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 11 ከእናንተ መካከል ታላቅ የሆነው አገልጋያችሁ ይሁን፡፡
|
||
\v 12 ራሱን ከፍ የሚያደርግ ዝቅ ይላል፤ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ከፍ ይላል፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 13 እናንተ፣ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ግን ወዮላችሁ! በሰዎች ፊት መንግሥተ ሰማይን ትዘጋላችሁ፡፡ እናንተ ራሳችሁ አትገቡበትም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ፡፡
|
||
\v 14 \f + \ft በጣም የታወቁ የጥንት ቅጂዎች ቊጥር 14 የላቸውም፡፡ (አንዳንድ ቅጂዎች ይህን እዚህና ከቊጥር 12 በኋላ አስገብተውታል)፡፡ \f*
|
||
እናንተ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ለታይታ ረጅም ጸሎታችሁን በማድረግ የመበለቶችን ቤት ስለምትበሉ ወዮላችሁ! ስለዚህ የበለጠውን ፍርድ ትቀበላላችሁ፡፡ እናንተ ግብዞች የአይሁድ ሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ!
|
||
|
||
\v 15 አንድን ሰው ተከታያችሁ ለማድረግ በባሕርና በምድር ትሄዳላችሁ፤ ተከታያችሁ ካደረጋችሁት በኋላ፣ ከእናንተ እጥፍ የሚከፋ የገሃነም ልጅ ታደርጉታላችሁ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 16 እናንተ ዐይነ ስውራን መሪዎች ወዮላችሁ፤ አንድ ሰው 'በቤተ መቅደሱ ቢምል ምንም ማለት አይደለም፤ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ባለው ወርቅ ቢምል ግን፣ በመሐላው ይጠመዳል' ትላላችሁ፡፡
|
||
\v 17 እናንተ የታወራችሁ ሞኞች፣ ለመሆኑ የትኛው ይበልጣል ወርቁ ወይስ ወርቁን የሚቀድሰው ቤተ መቅደሱ?
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 18 አንድ ሰው በመሠዊያው ቢምል ምንም ማለት አይደለም፤ መሠዊያው ላይ ባለው ስጦታ ቢምል ግን በመሐላው ይጠመዳል ትላላችሁ፡፡
|
||
\v 19 እናንተ ዕውሮች፤ ለመሆኑ የትኛው ይበልጣል ስጦታው ወይስ ስጦታውን የሚቀድሰው መሠዊያ?
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 20 ስለዚህ በመሠዊያው የሚምል በመሠዊያውና እርሱ ላይ ባሉ ነገሮች ሁሉ ይምላል፡፡
|
||
\v 21 በቤተ መቅደሱ የሚምል በቤተ መቅደስና እርሱ ውስጥ በሚኖረው ይምላል፡፡
|
||
\v 22 በሰማይ የሚምል በእግዚአብሔር ዙፋንና በእርሱ ላይ በተቀመጠው ይምላል፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 23 እናንተ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ፣ ከአዝሙድ፣ ከእንስላልና ከከሙን ዐሥራት ብታወጡም፣ የሕጉን ዋና ዋና ነገሮች ማለትም ፍትሕን፣ ምሕረትንና እምነትን ሥራ ላይ አታውሉም፡፡ ሌላውን ችላ ሳትሉ እነዚህን መፈጸም ነበረባችሁ፡፡
|
||
\v 24 እናንተ ዐይነ ስውራን መሪዎች፣ ትንኝን አውጥታችሁ ትጥላላችሁ፤ ግመልን ግን ትውጣላችሁ!
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 25 እናንተ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! የጽዋውንና የሳሕኑን ውጫዊ ክፍል ታጠራላችህ፤ ውስጡ ግን ቅሚያና ስስት ሞልቶበታል፡፡
|
||
\v 26 አንተ ዕውር ፈሪሳዊ፣ ውጫዊ አካሉም ንጹሕ እንዲሆን በመጀመሪያ የጽዋውንና የሳሕኑን ውስጥ አጽዳ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 27 እናንተ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ከውጭ ሲያዩት እንደሚያምር፣ ውስጡ ግን የሞቱ ሰዎች አጥንትና ርኵሰት እንደ ሞላበት መቃብር ናችሁ፡፡
|
||
\v 28 በተመሳሳይ መንገድ እናንተም ከውጭ ለሰዎች ጻድቃን ትመስላላችሁ፤ ውስጣችሁ ግን ግብዝነትና ርኲሰት ሞልቶበታል፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 29 እናንተ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! የነቢያትን መቃብር ስለምትሠሩ፣ የጻድቃንን መቃብር ስለምታስጌጡ፣
|
||
\v 30 በአባቶቻችን ዘመን ኖረን ቢሆን ኖሮ፣ የነቢያትን ደም በማፍሰስ አንተባበራቸውም ነበር ትላላችሁ፡፡
|
||
\v 31 ስለሆነም የነቢያት ገዳይ ልጆች መሆናችሁን እናንተ ራሳችሁ ትመሰክራላችሁ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 32 እናንተ ራሳችሁም አባቶቻችሁ የጀመሩትን ኃጢአት ትፈጽማላችሁ፡፡
|
||
\v 33 እናንተ እባቦች፣ እናንተ የእፉኝት ልጆች፣ ከገሃነም ፍርድ እንዴት ታመልጣላችሁ?
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 34 ስለዚህ ነቢያትን፣ አስተዋይ ሰዎችንና የአይሁድ ሕግ መምህራንን ወደ እናንተ እልካለሁ፡፡ አንዳንዶቹን ትገድላላችሁ፣ ትሰቅላላችሁ፤ ሌሎቹን በምኵራቦቻችሁ ትገርፋላችሁ፣ ከከተማ ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፡፡
|
||
\v 35 ከጻድቁ ከአቤል አንሥቶ በቤተ መቅደሱና በመሠዊያው መካካል እስከ ገደላችሁት የበራክዩ ልጅ ዘካርያስ ደም ድረስ፣ በምድር ላይ በፈሰሰው ጻድቃን ደም ሁሉ ትጠየቃላችሁ፡፡
|
||
\v 36 እውነት እላችኋለሁ፤ እነዚህ ነገሮች ሁሉ በዚህ ትውልድ ላይ ይሆናሉ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 37 ኢየሩሳሌም፣ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ አንቺ ነቢያትን የምትገድዪ ወደ አንቺ የተላኩትን በድንጋይ የምትወግሪ! ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎቿ ሥር እንደምትሰበስብ እኔም ልጆችሽን መሰብሰበ ብዙ ጊዜ ፈልጌ ነበር፤ እናንተ ግን አልፈለጋችሁም!
|
||
\v 38 ስለሆነም ቤታችሁ ወና ሆኖ ይቀራል፡፡
|
||
\v 39 'በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው' እስክትሉ ድረስ ከአሁን ጀምሮ አታዩኝም እላችኋለሁ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 24
|
||
\cl ምዕራፍ 24
|
||
\p
|
||
\v 1 ኢየሱስ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ እየሄደ ሳለ፤ ደቀ መዛሙርቱ የቤተ መቅደሱን ሕንጻ ሊያሳዩት ወደ እርሱ መጡ፡፡
|
||
\v 2 እርሱ ግን፣ "እነዚህን ሁሉ ነገሮች ታያላችሁ? እውነት እላችኋለሁ፣ ይፈርሳል እንጂ፣ አንድ ድንጋይ እንኳ በሌላ ድንጋይ ላይ እንደ ተነባበረ አይቀርም" በማለት መለሰላቸው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 3 በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ እያለ፣ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ መጥተው፣ "እስቲ ንገረን፤ ይህ ሁሉ የሚሆነው መቼ ነው? የአንተ መምጣትና የዓለም መጨረሻስ ምልክቱ ምንድን ነው?" አሉት፡፡
|
||
\v 4 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፣ "ማንም እንዳያሳስታችሁ ተጠንቀቁ፡፡
|
||
\v 5 ምክንያቱም ብዙዎች በስሜ ይመጣሉ፤ 'እኔ ክርስቶስ ነኝ' እያሉ ብዙዎችን ያሳስታሉ
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 6 ጦርነትንና የጦርነትን ዜና ትሰማላችሁ፤ በፍጹም እንዳትታወኩ፤ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች እንዲሆኑ ግድ ነው፤ ቢሆንም፣ መጨረሻው ገና ነው፡፡
|
||
\v 7 ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሣል፡፡ በተለያየ ቦታ ራብና የምድር መናወጥ ይሆናል፡፡
|
||
\v 8 እነዚሀ ሁሉ ግን የምጥ ጣር መጀመሪያ ብቻ ናቸው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 9 ከዚያም ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል ይገድሏችኋልም፡፡ ስለ ስሜ ሕዝቦች ሁሉ ይጠሏችኋል፡፡
|
||
\v 10 ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ እርስ በርስ ይካካዳሉ፤ እርስ በርስ ይጠላላሉ፡፡
|
||
\v 11 ብዙ ሐሰተኛ ነቢያት ተነሥተው፣ ብዙዎችን ያሳስታሉ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 12 ዐመፅ ስለሚበዛ የብዙዎች ፍቅር ይቀዘቅዛል፡፡
|
||
\v 13 እስከ መጨረሻ የሚታገሥ ግን ይድናል፡፡
|
||
\v 14 ለሕዝቦች ሁሉ ምስክር እንዲሆን የመንግሥቱ ወንጌል ለመላው ዓለም ይሰበካል፤ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 15 ስለዚህ በነቢዩ ዳንኤል የተነገረለት የጥፋት ርኲሰት በተቀደሰው ቦታ ቆሞ ስታዩ፣ (ያኔ አንባቢው ያስተውል)
|
||
\v 16 በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፣
|
||
\v 17 ጣራ ላይ ያለ ሰው በቤቱ ያለውን ምንም ነገር ከቤቱ ለመውሰድ አይመለስ፣
|
||
\v 18 በእርሻ ያለ ልብሱን ለመውሰድ አይመለስ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 19 ልጆች ላሉአቸውና ለሚያጠቡ እናቶች ግን ወዮላቸው!
|
||
\v 20 ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ፡፡
|
||
\v 21 ምክንያቱም ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስና ከዚያም በኋላ ፈጽሞ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናል፡፡
|
||
\v 22 እነዚያ ቀኖች ባያጥሩ ኖሮ፣ ማንም ሥጋ ለባሽ አይድንም ነበር፤ ለተመረጡት ሲባል ግን እነዚያ ቀኖች ያጥራሉ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 23 ስለዚህ ማንም "እነሆ ክርስቶስ፣ እዚህ ነው" ወይም፣ 'ክርስቶስ እዚያ ነው' ቢላችሁ አትመኑ፡፡
|
||
\v 24 ምክንያቱም ብዙዎችን ለማሳሳት ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት መጥተው ታላላቅ ምልክቶችንና ድንቆችን ያደርጋሉ፤ ከተቻለም የተመረጡትን እንኳ ያሳስታሉ፡፡
|
||
\v 25 ይህ ከመሆኑ በፊት አስቀድሜ ነግሬአችኋለሁ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 26 ስለዚህ፣ ‹ክርስቶስ በምድረ በዳ ነው› ቢሏችሁ ወደ ምድረ በዳ አትሂዱ ወይም ቤት ውስጥ ነው ቢሏችሁ አትመኑ፡፡
|
||
\v 27 መብረቅ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ በአንዴ እንደሚታይ የሰው ልጅ ሲመጣ እንደዚያው ይሆናል፡፡
|
||
\v 28 የሞተ እንስሳ ባለበት ሁሉ፣ በዚያ አሞሮች ይሰበሰባሉ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 29 ከእነዚህ የመከራ ቀኖች በኋላ ወዲያውኑ ፀሐይ ትጨልማለች፣ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም፤ ከዋክብት ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኅይላት ይናወጣሉ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 30 ከዚያም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፤ የምድር ነገዶች ሁሉ አምርረው ያለቅሳሉ፡፡ የሰው ልጅንም በኀይልና በታላቅ ክብር ሲመጣ ያዩታል፡፡
|
||
\v 31 መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፤ እነርሱም፣ ከአንድ የሰማይ ጫፍ እስከ ሌላው ጫፍ ድረስ ከአራቱም ነፋሳት ምርጦቹን ይሰበስቧቸዋል፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 32 ከበለስ ዛፍ ተማሩ፡፡ ቅርንጫፎቿ ሲለመልሙና ቅጠሎች ብቅ ብቅ ሲሉ በጋ መቅረቡን ታውቃላችሁ፡፡
|
||
\v 33 እናንተም እነዚህን ሁሉ ስታዩ እርሱ መቅረቡን፣ እንዲያውም በደጅ መሆኑን ዕወቁ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 34 እውነት እላችኋለሁ፣ እነዚህ ሁሉ እስኪፈጸሙ ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም፡፡
|
||
\v 35 ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን ፈጽሞ አያልፍም፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 36 ስለዚያች ቀንና ሰዓት ግን ማንም አያውቅም፤ የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ አያወቁም፤ አብ ብቻ እንጂ ወልድ እንኳ ቢሆን አያውቅም፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 37 በኖኅ ዘመን እንደ ነበረው፣ የሰው ልጅ መምጣትም እንዲሁ ይሆናል፡፡
|
||
\v 38 ከጥፋት ውሃ በፊት እንደ ነበረው ዘመን፣ ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባ ድረስ ይበሉና ይጠጡ፣ ያገቡና ይጋቡ ነበር።
|
||
\v 39 ጐርፉ መጥቶ እስኪያጠፋቸው ድረስ ምንም አላወቁም፣ የሰው ልጅ ሲመጣም እንዲሁ ይሆናል፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 40 በዚያን ጊዜ ሁለት ሰዎች በዕርሻ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል ሌላው ይቀራል፡፡
|
||
\v 41 ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዷ ትወሰዳለች ሌላዋ ትቀራለች፡፡
|
||
\v 42 ስለዚህ ጌታችሁ በምን ቀን እንደሚመጣ አታውቁምና ተጠንቀቁ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 43 ይህን ግን ዕወቁ፤ ሌባው በየትኛው ሰዓት እንደሚመጣ የቤቱ ባለቤት ቢያውቅ ኖሮ ይጠነቀቅ ነበር፤ ቤቱ አይዘረፍም ነበር፡፡
|
||
\v 44 የሰው ልጅ ባልጠበቃችሁት ሰዓት ስለሚመጣ እናንተም ብትሆኑ ተዘጋጅታችሁ መጠበቅ አለባችሁ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 45 በተገቢው ጊዜ ለቤተ ሰቦቹ ምግባቸውን ለመስጠት ጌታው በቤቱ ላይ ኀላፊነት የሰጠው ታማኝና አስተዋይ አገልጋይ ማን ነው?
|
||
\v 46 ጌታው ሲመጣ ያንን እያደረገ የሚያገኘው አገልጋይ የተባረከ ነው፡፡
|
||
\v 47 እውነት እላችኋለሁ የምላችሁ፣ ጌታው ባለው ነገር ሁሉ ላይ ኀላፊ አድርጎ ይሾመዋል፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 48 ይሁን እንጂ፣ አንድ ክፉ አገልጋይ በልቡ፣ ‹‹ጌታዬ ከመምጣት ዘግይቶአል ብሎ ቢያስብ፣
|
||
\v 49 አገልጋይ ጓደኞቹን መደብደብና ከሰካራሞች ጋር መብላት መጠጣት ቢጀምር
|
||
\v 50 የዚያ አገልጋይ ጌታ አገልጋዩ ባልጠበቀው ቀንና በማያውቀው ሰዓት ይመጣበታል፡፡
|
||
\v 51 ጌታው ለሁለት ይሰነጥቀዋል፤ ዕጣ ፈንታውን ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፣ በዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 25
|
||
\cl ምዕራፍ 25
|
||
\p
|
||
\v 1 መንግሥተ ሰማይ መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ለመቀበል የወጡ ዐሥር ድንግሎችን ትመስላለች።
|
||
\v 2 ዐምስቱ ሞኞች፣ ዐምስቱ ልባሞች ነበሩ።
|
||
\v 3 ሞኞቹ ድንግሎች መብራታቸውን ይዘው ሲሄዱ ምንም ዘይት አልያዙም ነበር።
|
||
\v 4 ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር ዘይትም ይዘው ነበር።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 5 ሙሽራው በዘገየ ጊዜ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ሁሉም ተኙ።
|
||
\v 6 ዕኩለ ሌሊት ላይ ግን፣ “ሙሽራው መጥቶአልና ወጥታችሁ ተቀበሉት!” የሚል ሁካታ ሆነ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 7 ያኔ እነዚያ ድንግሎች ሁሉ ተነሥተው መብራታቸውን አዘጋጁ።
|
||
\v 8 ሞኞቹም ልባሞቹን፣ “መብራታችን እየጠፋ ስለ ሆነ፣ ከዘይታችሁ ጥቂት ስጡን” አሏቸው።
|
||
\v 9 ልባሞቹ ግን፣ “ለእኛና ለእናንተ የሚበቃ ስለሌለን፣ ወደ ሻጮች ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ” በማለት መለሱአቸው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 10 ለመግዛት ሲሄዱ፣ ሙሽራው መጣ፤ ተዘጋጅተው የነበሩት ግብዣው ላይ ለመገኘት ከእርሱ ጋር ሄዱ፤ በሩም ተዘጋ።
|
||
\v 11 በኋላ ሌሎቹ ድንግሎች መጥተው፣ “ጌታው፣ በሩን ክፈትልን” አሉ።
|
||
\v 12 እርሱ ግን መልሶ፣ “እውነት እላችኋለሁ፣ አላውቃችሁም” አላቸው።
|
||
\v 13 ስለዚህ ቀኑን ወይም ሰዓቱን አታውቁምና ነቅታችሁ ጠብቁ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 14 ነገሩ ወደ ሌላ አገር ለመሄድ ያሰበ ሰውን ይመስላልና፤ አገልጋዮቹን ጠርቶ በሀብት በንብረቱ ሁሉ ላይ ኀላፊነት ሰጣቸው።
|
||
\v 15 እንደ ዐቅማቸው መጠን ለአንዱ ዐምስት መክሊት፣ ለሌላው ሁለት፣ ለሌላው ደግሞ አንድ መክሊት ሰጣቸውና ሄደ።
|
||
\v 16 ዐምስት መክሊት የተቀበለው ወዲያውኑ ሄዶ ነገደበት፤ ሌላ ዐምስት አተረፈ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 17 ሁለት መክሊት የተቀበለውም እንደዚያው ሌላ ሁለት መክሊት አተረፈ።
|
||
\v 18 አንድ መክሊት የተቀበለው አገልጋይ ግን ሄዶ ጉድጓድ ቈፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 19 ከብዙ ጊዜ በኋላ የእነዚያ አገልጋዮች ጌታ ተመልሶ መጣና ተሳሰባቸው።
|
||
\v 20 ዐምስት መክሊት የተቀበለው አገልጋይ ሌላ ዐምስት መክሊት ጨምሮ አመጣና፣ “ጌታ ሆይ፣ ዐምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እኔ ግን ሌላ ዐምስት መክሊት አተረፍሁ” አለ።
|
||
\v 21 ጌታውም፣ 'አንተ መልካምና ታማኝ አገልጋይ ደግ አደረግህ! በጥቂት ነገሮች ታምነሃል፤ በብዙ ነገሮች ላይ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ።' አለው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 22 ሁለት መክሊት ተቀብሎ የነበረው አገልጋይም መጥቶ፣ ‘ጌታ ሆይ፣ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር። ሌላ ሁለት መክሊት አትርፌአለሁ’ አለ።
|
||
\v 23 ጌታውም፣ 'አንተ መልካምና ታማኝ አገልጋይ ደግ አደረግህ! በጥቂት ነገሮች ታምነሃል፤ በብዙ ነገሮች ላይ እሾምሃለሁ። ወደ ጌታህ ደስታ ግባ’ አለው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 24 ከዚያም አንድ መክሊት የተቀበለው አገልጋይ መጥቶ፣ 'ጌታ ሆይ፣ ካልዘራህበት የምታጭድ፣ ካልበተንህበት የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ።
|
||
\v 25 ስለዚህ ፈራሁ፤ መክሊትህን መሬት ውስጥ ቀበርሁት። መክሊትህ ይኸውልህ' አለው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 26 ጌታው ግን መልሶ፣ 'አንተ ዐመፀኛና ሰነፍ አገልጋይ፤ ካልዘራሁበት የማጭድ፣ ካልበተንሁበት የምሰበስብ መሆኔን ታውቃለህ።
|
||
\v 27 ስለዚህ ገንዘቤን በባንክ ማስቀመጥ ይገባህ ነበር፤ እኔ ስመጣ ከነወለዱ እወስደው ነበር' አለው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 28 ስለዚህ መክሊቱን ከእርሱ ወስዳችሁ ዐሥር መክሊት ላለው ስጡት።
|
||
\v 29 ላለው የበለጠ እንዲያውም የተትረፈረፈ ይሰጠዋል። ምንም ከሌለው ግን፣ ያው ያለው ነገር እንኳ ይወሰድበታል።
|
||
\v 30 ይህን የማይረባ አገልጋይ አውጡና ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት በውጭ ወዳለው ጨለማ ጣሉት” አለ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 31 የሰው ልጅ በክብሩ ከመላእክቱ ሁሉ ጋር ሲመጣ፣ በክብር ዙፋኑ ላይ ይቀመጣል።
|
||
\v 32 አሕዛብ ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛ በጎችን ከፍየሎች እንደሚለይ ሕዝቡን ይለያቸዋል።
|
||
\v 33 በጎቹን በቀኙ፣ ፍየሎቹን በግራው ያደርጋቸዋል።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 34 ከዚያም ንጉሡ በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፤ 'እናንተ አባቴ የባረካችሁ ኑ፤ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።
|
||
\v 35 ተርቤ ነበር ምግብ ሰጣችሁኝ፤ ተጠምቼ ነበር የምጠጣው ሰጣችሁኝ፤ እንግዳ ሆኜ ነበር አስተናገዳችሁኝ፤
|
||
\v 36 ተራቊቼ ነበር አለበሳችሁኝ፤ ታምሜ ነበር ተንከባከባችሁኝ፤ ታስሬ ነበር ጠየቃችሁኝ' ይላቸዋል።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 37 ከዚያም ጻድቃን እንዲህ ብለው ይመልሱለታል፣ ‘ጌታ ሆይ፣ ተርበህ ያገኘንህና ያበላንህ ወይስ ተጠምተህ ያጠጣንህ መቼ ነው?
|
||
\v 38 38 እንግዳ ሆነህ ያየንህና ያስተናገድንህ መቼ ነው? ወይም ተራቊተህ ያለበስንህ መቼ ነው?
|
||
\v 39 ታምመህ የተንከባከብንህ ወይስ ታስረህ የጠየቅንህ መቼ ነው?’
|
||
\v 40 ንጉሡም መልሶ እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ለእነዚህ ታናናሽ ወንድሞቼ ያደረጋችሁትን ለእኔ አድርጋችሁታል።’
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 41 ከዚያም በግራው ያሉትን፣ ‘እናንተ ርጉማን ከእኔ ራቁ፤ ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው ገሃነም እሳት ሂዱ።
|
||
\v 42 ምክንያቱም ‘ተርቤ ነበር አላበላችሁኝም፤ ተጠምቼ ነበር አላጠጣችሁኝም፤
|
||
\v 43 እንግዳ ሆኜ ነበር አልተቀበላችሁኝም፤ ተራቊቼ ነበር አላለበሳችሁኝም፤ ታምሜ፣ ታስሬ ነበር፣ እናንተ ግን አልተንከባከባችሁኝም’ ይላቸዋል።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 44 እነርሱም መልሰው እንዲህ ይሉታል፤ ‘ጌታ ሆይ፣ ተርበህ ወይም ተጠምተህ ወይም እንግዳ ሆነህ ወይም ተራቊተህ ወይም ታምመህ ወይም ታስረህ ያላገለገልንህ መቼ ነው?’
|
||
\v 45 እርሱም መልሶ፣ ‘እውነት እላችኋለሁ፣ ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ አለማድረጋችሁ ለእኔ አለማድረጋችሁ ነው’ ይላቸዋል።
|
||
\v 46 እነዚህ ወደ ዘላለም ቅጣት፣ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።"
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 26
|
||
\cl ምዕራፍ 26
|
||
\p
|
||
\v 1 ኢየሱስ እነዚህን ቃሎች ተናግሮ በጨረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤
|
||
\v 2 "ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካ እንደሚሆን ታውቃላችሁ፣ የሰው ልጅም ተሰቅሎ እንዲገደል ተላልፎ ይሰጣል፡፡"
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 3 ከዚያ የካህናት አለቆቹና የሕዝቡ ሽማግሌዎች ቀያፋ በሚሉት ሊቀ ካህናት ግቢ ውስጥ ተሰበሰቡ፤
|
||
\v 4 ኢየሱስን በረቀቀ ዘዴ ለማሰርና ለመግደል ተማከሩ፡፡
|
||
\v 5 ምክንያቱም፣ በሕዝቡ መሓል ረብሻ እንዳይነሣ በበዓሉ ሰሞን መሆን የለበትም እያሉ ነበር፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 6 ኢየሱስ በቢታንያ በለምጻሙ ስምዖን ቤት
|
||
\v 7 ማዕድ ላይ ተቀምጦ እያለ፣ አንዲት ሴት ዋጋው ውድ የሆነ ሽቱ ያለበት የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣችና ራሱ ላይ አፈሰሰች፡፡
|
||
\v 8 ደቀ መዛሙርቱ ይህን ሲያዩ በጣም ተቈጥተው፣ "ይህ ብክነት ምንድን ነው?
|
||
\v 9 ይህ እኮ ከፍ ባለ ዋጋ ተሸጦ ገንዘቡን ለድኾች መስጠት ይቻል ነበር" አሉ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 10 ኢየሱስም ይህን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፣ "ይህችን ሴት ለምን ታስቸግሯታላችሁ? ለእኔ መልካም ነገር አድርጋለች፡፡
|
||
\v 11 ድኾች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ናቸው፤ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልሆንም፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 12 ይህን ሽቱ እኔ ላይ ባፈሰሰች ጊዜ ለቀብሬ አድርጋዋለች፡፡
|
||
\v 13 እውነት እላችኋለሁ፣ ይህ ወንጌል በመላው ዓለም ሲሰበክ ለእርሷ መታሰቢያ እንዲሆን ይህች ሴት ያደረገችውም ይነገርላታል።"
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 14 ከዚያም የአስቆሮቱ ይሁዳ የሚባለው ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ወደ ካህናት አለቆቹ ሄዶ፣
|
||
\v 15 "እርሱን አሳልፌ ብሰጣችሁ ለእኔ ምን ትሰጡኛላችሁ?" አላቸው፡፡ እነርሱም ሠላሣ ጥሬ ብር ተመኑለት፡፡
|
||
\v 16 ከዚያ ጊዜ ወዲህ እርሱን አሳልፎ የሚሰጥበትን ምቹ ጊዜ ይጠባበቅ ጀመር፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 17 በቂጣ በዓል በመጀመሪያው ግን ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ መጥተው፣ "የፋሲካን እራት እንድትበላ የት እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?" አሉት፡፡
|
||
\v 18 እርሱም፣ "ከተማው ውስጥ ወዳለ አንድ ሰው ሂዱና፣ 'መምህሩ "ጊዜዬ ደርሷል፤ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን በአንተ ቤት ማክበር እፈልጋለሁ' ይልሃል በሉት'" አላቸው፡፡
|
||
\v 19 ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ እንደ ነገራቸው አደረጉ፤ የፋሲካንም እራት አዘጋጁለት፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 20 ምሽት ላይ ከዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ጋር ለመብላት ተቀመጠ፡፡
|
||
\v 21 በመብላት ላይ እያሉ፣ "እውነት እላችኋለሁ፣ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል" አላቸው፡፡
|
||
\v 22 እነርሱ በጣም ዐዘኑ፤ እያንዳንዱም፣ "እኔ እሆንን?" በማለት ይጠያየቁ ጀመር፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 23 እርሱም፣ "አሳልፎ የሚሰጠኝ ከእኔ ጋር እጁን ወደ ሳሕኑ የሚሰደው ነው፡፡
|
||
\v 24 የሰው ልጅ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈው ይሄዳል፤ የሰውን ልጅ አሳልፎ ለሚሰጠው ግን ወዮለት! ያ ሰው ባይወለድ ይሻለው ነበር" በማለት መለሰላቸው፡፡
|
||
\v 25 አሳልፎ የሚሰጠው ይሁዳ፣ "መምህር ሆይ፣ እኔ ነኝ እንዴ?" አለው፤ እርሱም፣ "አንተው ራስህ ብለኸዋል" አለው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 26 በመብላት ላይ እያሉ፣ ኢየሱስ እንጀራ አንሥቶ ባርኮ ቈረሰ፡፡ "እንካችሁ ውሰዱ፣ ብሉት፤ ይህ ሥጋዬ ነው" ብሎ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 27 ጽዋውንም አንሥቶ አመሰገነና ሰጣቸው፤ እንዲህም አላቸው፤ "ሁላችሁም ጠጡት
|
||
\v 28 ይህ ለብዙዎች ኀጢአት ይቅርታ የሚፈስ የኪዳኑ ደሜ ነው፡፡
|
||
\v 29 እንደ ገና በአባቴ መንግሥት ከእናንተ ጋር እስክጠጣው ድረስ ከእንግዲህ ከዚህ ወይን ፍሬ እንደማልጠጣ ግን እነግራችኋለሁ፡፡"
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 30 መዝሙር ከዘመሩ በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ወጡ፡፡
|
||
\v 31 ያኔ ኢየሱስ፣ "በዚህ ሌሊት ሁላችሁም በእኔ ምክንያት ትሰናከላላችሁ፤ ምክንያቱም፣ 'እረኛውን እመታለሁ በጎቹም ይበተናሉ' ተብሎ ተጽፎአል፡፡
|
||
\v 32 ከተነሣሁ በኋላ ግን ቀድሜአችሁ ወደ ገሊላ እሄዳለሁ" አላቸው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 33 ጴጥሮስ ግን፣ "ሁሉም በአንተ ቢሰናከሉ እንኳ እኔ አልሰናከልም" አለው፡፡
|
||
\v 34 ኢየሱስም፣ "እውነት እልሃለሁ ፣ በዚህች ሌሊት ዶሮ ከመጮኹ በፊት ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ" አለው፡፡
|
||
\v 35 ጴጥሮስም፣ "ከአንተ ጋር መሞት ቢኖርብኝ እንኳ አልክድህም" አለ፡፡ ሌሎችም ደቀ መዛሙርት ሁሉ እንደዚያው አሉ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 36 ከዚያም ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ጌቴሴማኒ ወደሚሉት ቦታ ሄደ፤ ደቀ መዛሙርቱንም፣ "ወደዚያ ሄጄ እስክጸልይ ድረስ እዚህ ሁኑ" አላቸው፡፡
|
||
\v 37 ጴጥሮስንና ሁለቱን የዘብዴዎስ ልጆች ይዞ ሄደ፤ ያዝንና ይጨነቅም ጀመር፡፡ ከዚያም፣
|
||
\v 38 "ነፍሴ፣ እስከ ሞት ድረስ በጣም ዐዝናለች፡፡ እዚህ ሆናችሁ ከእኔ ጋር ትጉ" አላቸው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 39 ጥቂት ራቅ ብሎ በመሄድ በግንባሩ ወድቆ ጸለየ፤ "አባት ሆይ፣ የሚቻል ከሆነ ይህ ጽዋ ከእኔ ይለፍ፤ ይሁን እንጂ፣ የእኔ ፈቃድ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይሁን" አለ፡፡
|
||
\v 40 ወደ ደቀ መዛሙርቱ ሲመጣ ተኝተው አገኛቸው፤ ጴጥሮስንም፣ "ከእኔ ጋር አንድ ሰዓት ያህል እንኳ መትጋት አልቻላችሁምን?
|
||
\v 41 ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፡፡ መንፈስ በእርግጥ ፈቃደኛ ነው፤ ሥጋ ግን ደካማ ነው" አለው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 42 ለሁለተኛ ጊዜ ጥቂት ፈቀቅ ብሎ ጸለየ፤ "አባት ሆይ፣ እኔ ካልጠጣሁት በቀር ይህ የማያልፍ ከሆነ፣ ፈቃድህ ይሁን" አለ፡፡
|
||
\v 43 እንደ ገና ሲመጣ ዐይኖቻቸው ከብደው ነበርና ተኝተው አገኛቸው፡፡
|
||
\v 44 እንደ ገና ትቶአቸው ሄዶ ለሦስተኛ ጊዜ ያንኑ ቃል ጸለየ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 45 ከዚያም ኢየሱስ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጥቶ፣ "አሁንም ዐርፋችሁ ተኝታችኋል? ጊዜው ደርሷል፤ የሰው ልጅ በኀጢአተኞች እጅ ተላልፎ ይሰጣል፡፡
|
||
\v 46 እንግዲህ ተነሡ እንሂድ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቧል" አላቸው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 47 ገና እየተናገረ እያለ፣ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው ይሁዳ መጣ፣ ከእርሱም ጋር ከካህናት አለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሌዎች የመጡ ሰይፍና ዱላ የያዙ ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡
|
||
\v 48 በዚህ ጊዜ አሳልፎ የሚሰጠው፣ "እኔ የምስመው እርሱ ነው፤ ያዙት" የሚል ምልክት ሰጣቸው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 49 ወዲያውኑ ወደ ኢየሱስ መጥቶ፣ "መምህር ሆይ፣ ሰላም ለአንተ ይሁን!" ብሎ ሳመው፡፡
|
||
\v 50 ኢየሱስም፣ "ወዳጄ፣ የመጣህበትን ጉዳይ ፈጽም" አለው፡፡ ከዚያም መጡ ኢየሱስ ላይ እጃቸውን ጫኑ፣ ያዙትም።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 51 ከኢየሱስ ጋር ከነበሩት አንዱ እጁን ዘርግቶ ሰይፍ አወጣ፤ የሊቀ ካህናቱን አገልጋይ ጆሮ መትቶ ቈረጠ፡፡
|
||
\v 52 ያኔ ኢየሱስ፣ "ሰይፍህን ወደ ቦታው መልስ፤ ሰይፍ የሚያነሡ በሰይፍ ይጠፋሉ፡፡
|
||
\v 53 አባቴን ብጠይቅ በብዙ ሺህ የሚቈጠሩ መላእክት የማይልክልኝ ይመስልሃል?
|
||
\v 54 እንደዚያ ከሆነ ይህ እንደሚሆን የሚናገረው መጽሐፉ ቃል እንዴት ይፈጸማል?" አለው፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 55 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለሕዝቡ፣ "ወንበዴን እንደምትይዙ ሰይፍና ዱላ ይዛችሁ መጣችሁ? በየቀኑ በቤተ መቅደስ ተቀምጬ እያስተማርሁ ነበርሁ፡፡ እናንተም አልያዛችሁኝም ነበር፡፡
|
||
\v 56 የነቢያት መጽሐፍ እንዲፈጸም ይህ ሆኗል" አላቸው፡፡ ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ትተውት ሸሹ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 57 ኢየሱስን የያዙ ሰዎች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ሽማግሌዎቹ ተሰብስበው ወደ ነበሩበት ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ቤት ወሰዱት፡፡
|
||
\v 58 ጴጥሮስ ግን ከሩቅ ሆኖ እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ድረስ ተከተለው፤ ወደ ውስጥ ገብቶም የሚሆነውን ለማየት ከጠባቂዎቹ ጋር ተቀመጠ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 59 እርሱን ለማስገደል የካህናት አለቆቹና ሸንጎው ሁሉ በኢየሱስ ላይ በሐሰት የሚመሰክሩበትን ሰዎች እየፈለጉ ነበር፡፡
|
||
\v 60 ምንም እንኳ ብዙ የሐሰት ምስክሮች ቢመጡም፤ በቂ ማስረጃ አላገኙም፡፡ በኋላ ግን ሁለት ሰዎች ወደ ፊት መጥተው፣
|
||
\v 61 "ይህ ሰው፣ 'የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ አፍርሼ በሦስት ቀን ውስጥ እንደ ገና ልሠራው እችላለሁ' ብሏል" አሉ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 62 ሊቀ ካህናቱ ተነሥቶ፣ "መልስ የለህም? በአንተ ላይ እየመሰከሩብህ ያለው ምንድን ነው?" አለው፡፡
|
||
\v 63 ኢየሱስ ግን ዝም አለ፡፡ ሊቀ ካህናቱም፣ "በሕያው እግዚአብሔር አዝሃለሁ፤ አንተ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆን አለመሆንህን ንገረን" አለው፡፡
|
||
\v 64 ኢየሱስም፣ "አንተው ራስህ አልህ፤ ግን ልንገርህ፣ ከአሁን ጀምሮ የሰው ልጅ በኀይል ቀኝ በሰማይ ደመና ሲመጣ ታያለህ" በማለት መለሰለት፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 65 ከዚያም ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀደደና፣ "እግዚአብሔርን ተሳድቧል፤ ታዲያ፣ ምስክር የምንፈልገው ለምንድን ነው? አሁን ስድቡን ሰምታችኋል
|
||
\v 66 ለመሆኑ፣ ምን ታስባላችሁ?" አለ፡፡ እነርሱም መልሰው፣ "ሞት ይገባዋል" አሉ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 67 ከዚያም ፊቱ ላይ ተፉበት፣ በጡጫና በጥፊ መቱት፤
|
||
\v 68 "አንተ ክርስቶስ እስቲ ትንቢት ተናገር፡፡ ለመሆኑ፣ በጥፊ የመታህ ማን ነው?" አሉት፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 69 በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ እደጅ ግቢው ውስጥ ተቀምጦ ነበር፤ አንዲት አገልጋይ ልጅ ወደ እርሱ መጥታ፣ "አንተም ደግሞ ከገሊላው ኢየሱስ ጋር ነበርህ" አለችው፡፡
|
||
\v 70 እርሱ ግን፣ "ምን እየተናገርሽ እንደ ሆነ አላውቅም" በማለት በሁሉም ፊት ካደ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 71 ከግቢው ወደሚያስወጣው በር እየሄደ እያለ፣ ሌላ አገልጋይ ልጅ አየችውና እዚያ ለነበሩት፣ "ይህኛውም ሰውየ ከናዝሬቱ ኢየሱስ ጋር ነበረ" አለች፡፡
|
||
\v 72 እርሱም፣ "ሰውየውን አላውቀወም" በማለት በመሐላ ጭምር በድጋሚ ካደ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 73 ጥቂት ቆየት ብሎ እዚያ ቆመው የነበሩት መጥተው ጴጥሮስን፣ "በርግጥ አንተም ብትሆን ከእነርሱ አንዱ ነህ፤ አነጋገርህ ራሱ ያጋልጥሃል" አሉት፡፡
|
||
\v 74 ከዚያም፣ "ሰውየውን ጨርሶ አላውቀውም" በማለት ይራገምና ይምል ጀመር፤ ወዲያውኑ ዶሮ ጮኸ፡፡
|
||
\v 75 ጴጥሮስ "ዶሮ ሳይጮኽ ሦስቴ ትክደኛለህ" በማለት ኢየሱስ የተናገረውን አስታወሰ፡፡ ከዚያ ወደ ውጭ ወጥቶ ምርር ብሎ አለቀሰ፡፡
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 27
|
||
\cl ምዕራፍ 27
|
||
\p
|
||
\v 1 ጠዋት በማለዳ የካህናት አለቆቹና የሕዝቡ ሽማግሌዎች ሁሉ ኢየሱስን ለመግደል ተማከሩ።
|
||
\v 2 አስረው ወሰዱትና ለአገሩ ገዢው ለጲላጦስ አስረከቡት።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 3 አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ ኢየሱስ እንደ ተፈረደበት ባየ ጊዜ ተጸጸተ፣ ሠላሣውን ጥሬ ብር ለካህናት አለቆቹና ለሽማግሌዎቹ መልሶ፣
|
||
\v 4 "ንጹሕ ሰው አሳልፌ በመስጠት በድያለሁ" አለ። እነርሱ ግን፣ “ታዲያ፣ እኛን ምን አገባን? የራስህ ጉዳይ ነው” አሉት።
|
||
\v 5 ከዚያም ጥሬ ብሩን በቤተ መቅደሱ ውስጥ ወረወረና ወጥቶ ራሱን ሰቀለ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 6 የካህናት አለቆቹ ጥሬ ብሩን ወስደው፣ “ይህ የደም ዋጋ ስለ ሆነ፣ ከቤተ መቅደሱ ገንዘብ ጋር መቀላቀል ተገቢ አይደለም” አሉ።
|
||
\v 7 እርስ በርሳቸው ተነጋግረው የእንግዶች መቀበሪያ እንዲሆን የሸክላ ሠሪውን መሬት ገዙበት።
|
||
\v 8 ከዚህ የተነሣ ያ መሬት እስከዚህ ጊዜ ድረስ፣ “የደም መሬት” ተባለ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 9 በነቢዩ ኤርምያስ፣ “የእርሱ ዋጋ እንዲሆን የእስራኤል ልጆች የተመኑለትን ሠላሣ ጥሬ ብር ወሰዱ፣
|
||
\v 10 እግዚአብሔር እንደ አዘዘኝ ለሸክላ ሠሪው መሬት ከፈሉት” ተብሎ የተነገረው ተፈጸመ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 11 ኢየሱስ በአገረ ገዢው ፊት ቆመ፤ አገረ ገዢውም፣ “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህ እንዴ?” በማለት ጠየቀው። ኢየሱስም፣ “አንተ እንዳልኸው ነው” በማለት መለሰለት።
|
||
\v 12 የካህናት አለቆችና፣ ሽማግሌዎቹ፣ ሲከሱት ምንም አልመለሰም።
|
||
\v 13 በዚህ ጊዜ ጲላጦስ፣ “በአንተ ላይ የሚያቀርቡትን ክስ ሁሉ አትሰማምን?” አለው።
|
||
\v 14 እርሱ ግን አንድ ቃል እንኳ ስላልመለሰለት አገረ ገዡ በጣም ተደነቀ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 15 በዓል ሲመጣ አገረ ገዢው ሕዝቡ የሚፈልጉትን አንድ እስረኛ የመፍታት ልማድ ነበረው።
|
||
\v 16 በዚያን ጊዜ በርባን የሚሉት ከባድ ወንጀለኛ በእስር ቤት ውስጥ ነበር።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 17 ተሰብስበው እያለ ጲላጦስ፣ “ማንን እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁ፣ በርባንን ወይስ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን?” አላቸው።
|
||
\v 18 ምክንያቱም አሳልፈው የሰጡት በቅናት መሆኑን ያውቅ ነበር።
|
||
\v 19 በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ እያለ ሚስቱ፣ “በዚያ ንጹሕ ሰው ላይ ምንም እንዳታደርግ፤ እርሱን በተመለከተ በዚህ ሌሊት በሕልሜ ብዙ መከራ ተቀብያለሁ” የሚል ቃል ላከችበት።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 20 የካህናት አለቆቹና ሽማግሌዎቹ በርባን እንዲፈታና ኢየሱስ እንዲገደል እንዲጠይቁ ሕዝቡን ቀሰቀሱ።
|
||
\v 21 አገረ ገዢው፣ “ከሁለቱ የትኛውን እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁ?” በማለት ጠየቃቸው። እነርሱም፣”በርባንን” አሉ።
|
||
\v 22 ጲላጦስም፣ “ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስንስ ምን ላድርገው?” አላቸው። ሁሉም፣ “ስቀለው” በማለት መለሱ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 23 እርሱም፣ “ለምን፣ የሠራው ወንጀል ምንድንነው?” አላቸው። እነርሱ ግን፣ “ስቀለው” እያሉ የበለጠ ጮኹ።
|
||
\v 24 ስለዚህ ምንም ማድረግ እንዳልቻለና እንዲያውም ዐመፅ እየተነሣ መሆኑን ጲላጦስ ባየ ጊዜ፣ በሕዝቡ ፊት እጁን በውሃ ታጥቦ፣ “እኔ ከዚህ ንጹሕ ሰው ደም ነጻ ነኝ፤ ከእንግዲህ ኀላፊነቱ የእናንተው ነው” አለ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 25 ሕዝቡ ሁሉ፣ “ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን” አሉ።
|
||
\v 26 ከዚያም በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን ገርፎ እንዲሰቅሉት ሰጣቸው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 27 የአገረ ገዢው ወታደሮች ኢየሱስን ወደ ገዢው ግቢ ወሰዱትና ወታደሮቹን ሁሉ ሰበሰቡ።
|
||
\v 28 ልብሱን ገፍፈው ቀይ ልብስ አለበሱት።
|
||
\v 29 ከዚያም የእሾኽ አክሊል ሠርተው በራሱ ላይ ደፉ፣ በቀኝ እጁ በትር አስያዙት፤ በፊቱ ተንበርክከውም፣ “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፣ ሰላም ለአንተ ይሁን!” እያሉ አሾፉበት።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 30 ፊቱ ላይም ተፉበት፤ በትሩን ወስደው ራሱን መቱት።
|
||
\v 31 ካፌዙበትም በኋላ ልብሱን አውልቀው የራሱን ልብስ አለበሱትና እንዲሰቀል ወሰዱት።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 32 እንደወጡ ስምዖን የሚሉት የቀሬና ሰው አገኙ፤ መስቀሉን እንዲሸከም አስገደዱት።
|
||
\v 33 ጎልጎታ ወደሚባል ቦታ መጡ፤ ትርጕሙም “የራስ ቅል” ማለት ነው።
|
||
\v 34 ከሐሞት ጋር የተቀላቀለ የወይን ጠጅ ሰጡት፤ እርሱ ግን ቀምሶ ሊጠጣው አልፈለገም።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 35 በሰቀሉት ጊዜ ዕጣ በመጣጣል ልብሶቹን ተከፋፈሉ፤
|
||
\v 36 ተቀምጠው ይጠብቁትም ጀመር።
|
||
\v 37 ከራሱ በላይ፣ “ይህ የአይሁድ ንጉሥ ኢየሱስ ነው” የሚል የክስ ጽሕፈት አኖሩ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 38 ሁለት ወንበዴዎች አንዱ በቀኙ ሌላው በግራው በኩል ከእርሱ ጋር ተሰቅለው ነበር።
|
||
\v 39 የሚያልፉ ሰዎችም ሰደቡት፤ ራሳቸውን እየነቀነቁም
|
||
\v 40 “ቤተ መቅደሱን የምታፈርስና በሦስት ቀን የምትሠራ ራስህን አድን። የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ ከመስቀል ውረድ” ይሉት ነበር።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 41 በተመሳሳይ መንገድ የካህናት አለቆች፣ ከአይሁድ የሕግ መምህራንና ከሽማግሌዎቹ ጋር አብረው፣
|
||
\v 42 “ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ግን ማዳን አልቻለም። እርሱ የእስራኤል ንጉሥ ነው፣ ከመስቀል ይውረድ፣ ከዚያም እኛ እናምንበታለን።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 43 በእግዚአብሔር ተማምኖአል፤ እርሱ ከወደደ ያድነው፤ ምክንያቱም፣ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ብሏል" እያሉ ያፌዙበት ነበር።
|
||
\v 44 ከእርሱ ጋር የተሰቀሉት ወንበዴዎችም እንዲሁ ይሰድቡት ነበር።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 45 ከስድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ምድሩን ሁሉ የሚሸፍን ጨለማ ሆነ።
|
||
\v 46 በዘጠኝ ሰዓት ኢየሱስ፣ “ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰባቅታኒ” በማለት በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ትርጒሙም፣ “አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ” ማለት ነው።
|
||
\v 47 እዚያ ቆመው ከነበሩት አንዳንዶቹ ይህን ሲሰሙ፣ “ኤልያስን እየተጣራ ነው” አሉ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 48 ወዲያውኑ ከእነርሱ አንዱ ሮጦ ሄደና ስፖንጁን የኮመጠጠ ወይን ጠጅ ውስጥ ነክሮ በሸንበቆ በትር አድርጎ እንዲጠጣ ሰጠው።
|
||
\v 49 የተቀሩትም፣ "እስቲ ተዉት፤ ኤልያስ መጥቶ ሲያድነው እናያለን” አሉ።
|
||
\v 50 ከዚያም ኢየሱስ በድጋሚ በታላቅ ድምፅ ጮኾ መንፈሱን ሰጠ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 51 የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ተከፈለ፤ ምድር ተናወጠ፤ ዐለቶችም ተሰነጠቁ፤
|
||
\v 52 መቃብሮች ተከፈቱ፤ አንቀላፍተው የነበሩ ብዙ ቅዱሳን ተነሡ።
|
||
\v 53 ከትንሣኤው በኋላ ከመቃብር ወጡ፤ ወደ ቅድስት ከተማ ገብተው ለብዙዎች ታዩ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 54 የመቶ አለቃውና ኢየሱስን ይጠብቁ የነበሩ ሰዎች የምድር መናወጡንና የሆኑትን ነገሮች ሲያዩ በጣም ፈርተው፣ "በእውነት ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ነው" አሉ።
|
||
\v 55 እርሱን ለመርዳት ከገሊላ ጀምሮ ኢየሱስን ተከትለው የነበሩ ብዙ ሴቶች በሩቅ ሆነው ይመለከቱ ነበር።
|
||
\v 56 ማርያም መግደላዊት፣ የያዕቆብና የዮሴፍ እናት ማርያም፣ እንዲሁም የዘብዲዎስ ልጆች እናት ከእነርሱ ጋር ነበሩ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 57 ምሽት ላይ ዮሴፍ የሚሉት አንድ ሀብታም ሰው ከአርማትያስ መጣ፤ እርሱ ራሱ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነበር።
|
||
\v 58 ወደ ጲላጦስ መጥቶ የኢየሱስን አስከሬን እንዲሰጠው ጠየቀ። ጲላጦስም እንዲሰጠው አዘዘ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 59 ዮሴፍ አስከሬኑን ወስዶ፤ በንጹሕ ናይለን ጨርቅ ጠቀለለውና
|
||
\v 60 ለራሱ ከዐለት በሠራው መቃብር ውስጥ አኖረው። ከዚያም ትልቅ ድንጋይ አንከባልሎ መቃብሩ ደጃፍ ላይ አድርጎ ሄደ።
|
||
\v 61 ማርያም መግደላዊትና ሌላዋ ማርያም መቃብሩ ፊት ለፊት ተቀምጠው በዚያ ነበሩ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 62 በሚቀጥለው ቀን ከዝግጅት በኋላ የካህናት አለቆቹና ፈሪሳውያን በአንድነት ከጲላጦስ ጋር ተሰበሰቡ።
|
||
\v 63 እንዲህም አሉ፣ "ጌታ ሆይ፣ ያ አሳሳች በሕይወት በነበረ ጊዜ፣ 'ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ' ብሎ እንደ ነበር ትዝ አለን።
|
||
\v 64 ስለሆነም፣ እስከ ሦስተኛው ቀን ድረስ መቃብሩ በጥንቃቄ እንዲጠበቅ እዘዝ፤ አለበለዚያ ግን፣ ደቀ መዛሙርቱ መጥተው ሥጋውን ይሰርቁና ለሕዝቡ፣ ‘ከሞት ተነሣ’ ይላሉ፤ የኋላው ስሕተት ከመጀመሪያው የከፋ ይሆናል” አሉት።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 65 ጲላጦስም፣ “ጠባቂ ወስዳችሁ፣ የሚቻላችሁን ያህል በጥንቃቄ እንዲጠበቅ አድርጉ” አላቸው።
|
||
\v 66 ስለዚህ ሄደው መቃብሩ በጥንቃቄ እንዲጠበቅ አደረጉ፤ ድንጋዩን አተሙ፤ ጠባቂ አኖሩ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\c 28
|
||
\cl ምዕራፍ 28
|
||
\p
|
||
\v 1 ሰንበት እንዳለፈ፣ በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ማለዳ፣ ማርያም መግደላዊትና ሌላዋ ማርያም ወደ መቃብሩ መጡ።
|
||
\v 2 የጌታ መልአክ ከሰማይ ወርዶ ነበርና ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ መጥቶም ድንጋዩን አንከባልሎ በላዩ ተቀመጠ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 3 መልኩ እንደ መብረቅ፣ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበር።
|
||
\v 4 ጠባቂዎቹ በፍርሃት ተንቀጠቀጡ፤ እንደ ሞተ ሰውም ሆኑ።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 5 መልአኩም እንዲህ በማለት ተናገረ፤ "አትፍሩ፤ ተሰቅሎ የነበረውን ክርስቶስን እንደምትፈልጉ አውቃለሁ።
|
||
\v 6 እንደ ተናገረ ተነሥቷል እንጂ፣ እዚህ የለም፤ ኑና የነበረበትን ቦታ እዩ።
|
||
\v 7 በፍጥነት ሄዳችሁ፣ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ በማለት ንገሩ፤ 'እርሱ ከሞት ተነሥቷል፤ ቀድሟችሁ ወደ ገሊላ ይሄዳል። እዚያ ታዩታላችሁ።' እንግዲህ ነግሬአችኋለሁ።”
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 8 ሴቶቹ ፈጥነው በፍርሃትና በታላቅ ደስታ ለደቀ መዛሙርቱ ለመንገር ከመቃብሩ እየሮጡ ሄዱ።
|
||
\v 9 እነሆ ኢየሱስ አገኛቸውና፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው። ሴቶቹም እግሮቹን ይዘው ሰገዱለት።
|
||
\v 10 ከዚያም ኢየሱስ፣ "አትፍሩ፤ ሄዳችሁ ወደ ገሊላ እንዲሄዱ ለወንድሞቼ ንገሩ፤ እዚያ ያዩኛል" አላቸው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 11 ሴቶቹ እየሄዱ እያሉ፣ ከጠባቂዎች ጥቂቱ ወደ ከተማ ሄደው የሆነውን ሁሉ ለካህናት አለቆቹ ነገሩ።
|
||
\v 12 ካህናቱ ከሽማግሌዎቹ ጋር ተገናኝተው የሆነውን ሁሉ ሲናገሩ፣ ለወታደሮቹ ብዙ ገንዘብ በመስጠት፣
|
||
\v 13 “እኛ ተኝተን እያለ ፣ ሌሊት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መጥተው አስክሬኑን ሰረቁ” ብለው እንዲናገሩ ነገሩዋቸው።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 14 ይህ ወሬ ወደ አገረ ገዢው ከደረሰ፤ እኛ እናሳምነዋለን፣ እናንተም ከሥጋት ነጻ ትሆናላችሁ" አሏቸው።
|
||
\v 15 ወታደሮቹ ገንዘቡን ተቀብለው ፣ እንደ ተነገራቸው አደረጉ። ይህ ወሬ እስከ ዛሬ ድረስ በአይሁድ መሐል በሰፊው ተሰራጭቷል።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 16 ዐሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት ግን ወደ ገሊላ ኢየሱስ ወደ ነገራቸው ተራራ ሄዱ።
|
||
\v 17 ባዩት ጊዜ ሰገዱለት፤ አንዳንዶቹ ግን ተጠራጥረው ነበር።
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 18 ኢየሱስ ወደ እነርሱ መጥቶ፣ “በሰማይና በምድር ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠኝ።
|
||
\v 19 ስለዚህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ፣ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስም ስም እያጠመቃችኋቸው፤
|
||
|
||
\s5
|
||
\v 20 እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ እንዲያደርጉ እያስተማራችኋቸው፤ ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው። እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”
|