am_ulb/37-HAG.usfm

82 lines
8.5 KiB
Plaintext

\id HAG
\ide UTF-8
\h ሐጌ
\toc1 ሐጌ
\toc2 ሐጌ
\toc3 hag
\mt ሐጌ
\s5
\c 1
\p
\v 1 ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር መጀመሪያ ቀን በነቢዩ በሐጌ በኩል ወደ ይሁዳ ገዢ ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤልና ወደ ሊቀ ካህኑ ኢዮሴዴቅ ልጅ ወደ ኢያሱ የያህዌ ቃል መጣ።
\v 2 የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ይህ ሕዝብ “እኛ የምንመጣበት ወይ የያህዌን ቤት የምንሠራበት ጊዜ ገና ነው” ይላል።
\s5
\v 3 የያህዌ ቃል በነቢዩ በሐጌ በኩ መጣ፤ እንዲህም አሉ፣
\v 4 “ይህ ቤት ፈራርሶ እያለ፣ እናንተ ራሳችሁ ባማሩ ቤቶቻችሁ ለመኖር ጊዜው ነውን?
\v 5 ስለዚህ የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ እስቲ፣ የሠራችሁትን ቤት አስቡ!
\v 6 ብዙ ዘራችሁ፤ ግን ጥቂት አጭዳችሁ፤ በላችሁ ግን አልጠገባችሁም፤ ጠጣችሁ ግን አልረካችሁም። ለበሳችሁ ግን አልሞቃችሁም፤ ደመወዝ ተቀበላችሁ ግን ብዙ ቀዳዶች በሞሉበት መያዣ የማስቀመጥ ያህል ሆነባችሁ!
\s5
\v 7 የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ እስቲ የሠራችሁትን አስቡ!
\v 8 ወደ ተራራ ውጡ፤ እንጨትን አምጡና ቤቴን ሥሩ፤ ያኔ እኔ በእርሱ ደስ ይለኛል፣ እከብርበታለሁ! ይላል ያህዌ።
\v 9 ብዙ ጠበቃችሁ፤ ግን እኔ እፍ ስላልሁበት ወደ ቤት ያመጣችሁት ግን ጥቂት ነው፤ እንዲህ ያደረግሁት ለምን ይመስላችኋል? የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል! ምክንያቱም የእኔ ቤት ፈርሶ እያለ፣ ሰው ሁሉ በገዛ ራሱ ቤት እጅግ ደስ በመሰኘቱ ነው።
\s5
\v 10 ከዚህ የተነሣ ሰማያት ጠል ከለከሉ፤ ምድርም ፍሬዋን ነሣች።
\v 11 እኔ በምድሪቱና በተራሮች፤ በእህሉና በአዲሱ ወይን ጠጅ፤ በዘይቱና ምድር በምትሰጠው ሁሉ ላይ፣ በሰዎችና በእንስሳት፣ በእጆቻችሁ ሥራ ሁሉ ላይ ድርቅ አመጣለሁ!
\s5
\v 12 ከዚህ በኋላ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና ሊቀ ካህኑ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ፣ ከምርኮ ከተረፉት ሕዝብ ሁሉ ጋር የአምላካቸው የያህዌን ድምጽ ሰሙ፤ አምላካቸው ያህዌ ልኮታልና ለነቢዩ ሐጌ ቃል ታዘዙ። ሕዝቡም ያህዌን ፈሩ።
\v 13 ከዚያም የያህዌ መልእክተኛ ሐጌ ለሕዝቡ የያህዌን መልእክት እንዲህ በማለት ተናገረ፤ “እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ! ይህ የያህዌ ቃል ነው!
\s5
\v 14 ስለዚህ ሄደው የአምላካቸውን የሠራዊት ጌታ የያህዌን ቤት እንዲሠሩ የይሁዳን ገዢ የሰላትያል ልጅ የዘሩባቤልን መንፈስና የኢዮሴዴቅ ልጅ የካህኑ ኢያሱን መንፈስ፣ እንዲሁም ከምርኮ የተረፉትን ሰዎች ሁሉ መንፈስ ያህዌ አነሣሣ።
\v 15 ይህ የሆነው በንጉሥ ዳርዮስ ሁለተኛ ዓመት በስድስተኛው ወር ሃያ አራተኛ ቀን ነው።
\s5
\c 2
\p
\v 1 በሰባተኛው ወር፣ ከወሩም በሃያ አንደኛው ቀን የያህዌ ቃል በነቢዩ በሐጌ በኩል መጣ እንዲህም አለ፤
\v 2 “ለይሁዳ ገዢ ለሰላትያል ልጅ ለዘሩባቤልና ለኢዮሴዴቅ ልጅ ለካህኑ ኢያሱ፣ እንዲሁም ከምርኮ ለተረፉት ሰዎች ተናገሩ እንዲህም በሏቸው
\s5
\v 3 የዚህን ቤት የቀድሞ ክብር ያየ በመካከላችሁ ማን አለ? አሁንስ እንዴት ሆኖ ይታያችኋል? በዓይኖቻችሁ ፊት እንደ ተራ ነገር ቀልሎ የለምን?
\v 4 አሁንም ዘሩባቤል ሆይ፣ በርታ! ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው አንተም የኢዮሴዴቅ ልጅ ሊቀ ካህኑ ኢያሱ በርታ፤ በምድሪቱ ያላችሁ ሰዎች ሁሉ በርቱ! - ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው፤ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና ተነሡ ሥሩ! ይህ የሠራዊት ጌታ የያህዌ ዐዋጅ ነው
\v 5 ከግብፅ በወጠችሁ ጊዜ በገባሁላችሁ ኪዳን፣ በመካከላችሁም ባለው መንፈሴ አትፍሩ!
\s5
\v 6 የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ በቅርብ ጊዜ ሰማያትንና ምድርን፣ ባሕርንና ደረቁን ምድር አናውጣለሁ!
\v 7 ሕዝቦችን ሁሉ አናውጣለሁ፤ ሕዝቦች የከበሩ ነገሮቻቸውን ወደ እኔ ያመጣሉ፤ ይህንንም ቤት በክብር እሞላዋለሁ! ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።
\s5
\v 8 ብርና ወርቁ የእኔ ነው! ይህ የሠራዊት ጌታ የያህዌ ዐዋጅ ነው።
\v 9 የወደፊቱ የዚህ ቤት ክብር ከመጀመሪያው ይበልጣል ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ፤ በዚህ ቦታ ሰላም እሰጣለሁ - ይህ የሠራዊት ጌታ የያህዌ ዐዋጅ ነው።”
\s5
\v 10 ዳርዮስ በነገሠ ሁለተኛው ዓመት፣ በዘጠነኛው ወር ሃያ አራተኛ ቀን የያህዌ ቃል በነቢዩ በሐጌ በኩል መጣ፤ እንዲህም አለ፣
\v 11 “የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ሕጉ ምን እንደሚል ካህናቱን ጠይቁ፤
\v 12 አንድ ሰው ለያህዌ የተቀደሰውን ሥጋ በልብሱ እጥፋት ቢይዝ፣ በልብሱ እጥፋት እንጀራ ወይም ወጥ፣ የወይን ጠጅ ወይም ዘይት ወይ ሌላ ምግብ ቢነካ፣ ያ ምግብ ይቀደሳልን?” ካህናቱም፣ “የለም፣ አይቀደስም” በማለት መለሱ።
\s5
\v 13 ሐጌም፣ “ሬሳ በመንካቱ የረከሰ ሰው ከእነዚህ አንዱን ቢነካ ይረክሳሉን?” አለ። ካህናቱም፣ “አዎን፣ ይረክሳሉ” በማለት መለሱ።
\v 14 ስለዚህ ሐጌ መልሶ፣ “ ይህም ሕዝብ በፊቴ እንዲሁ ነው! - ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው፤ የእጃቸው ሥራና ለእኔ የሚያቀርቡት ሁሉ የረከሰ ነው።
\s5
\v 15 እንግዲህ ከዘሬ ጀምራችሁ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ከመነባበሩ በፊት የነበረውን ሁኔታ ልብ በሉ፤
\v 16 ለምሆኑ ያኔ እንዴት ነበር? አንድ ሰው ሃያ መስፈሪያ እህል ጠብቆ ወደ ክምሩ ሲሄድ አሥር ብቻ አገኘ። አምሳ ማድጋ ወይን ጠጅ ለመቅዳት ወደ መጭመቂያው ሲሄድ ሃያ ብቻ አገኘ።
\v 17 እናንተንና የእጆቻችሁን ሥራ ሁሉ በዋግና በአረማሞ መታሁ፤ ያም ሆኖ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም - ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው።
\s5
\v 18 ከዚህ ቀን ጀምሮ ማለትም የያህዌ ቤተመቅደስ መሠረት ከተጣለበት ከዘጠነኛው ወር ሃያ አራተኛው ቀን ጀምሮ ወደፊት ቁጠሩ፤ ልብ አድርጋችሁ አስቡት!
\v 19 በጎተራው የቀረ ዘር ይኖራልን? የወይኑና የበለሱ፣ የሮማኑና የወይራው ዛፍ ፍሬ አላፈሩም! ከዚህ ቀን ጀምሮ እባርካችኋለሁ!”
\s5
\v 20 በዘጠነኛው ወር በወሩም ሃያ አራተኛ ቀን የያህዌ ቃል በድጋሚ ወደ ሐጌ መጣ፤ እንዲህም አለ፣
\v 21 “ለይሁዳ ገዥ ለዘሩባቤል እንዲህ በለው፤ “ሰማያትንና ምድርን አናውጣለሁ።
\v 22 የመንግሥታትን ዙፋን እገለብጣለሁ፤ የሕዝቦችን መንግሥት ብርታት አጠፋለሁ! ሰረገሎችንና በላያቸው ያሉትን እገለብጣለሁ፤ ፈረሶችና ጋላቢዎቻቸውን በገዛ ወንድሞቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ።
\s5
\v 23 በዚያ ቀን - የሠራዊት ጌታ የያህዌ ዐዋጅ እንዲህ የሚል ይሆናል- የሰላትያል ልጅ ባርያዬ ዘሩባቤል ሆይ፣ እኔ እወስድሃለሁ፤ ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው። እኔ መርጬሃለሁና ቀለበቴ ላይ እንደ ማህተም አደርግሃለሁ፤ ይህ የሠራዊት ጌታ የያህዌ ዐዋጅ ነው።