am_ulb/36-ZEP.usfm

115 lines
12 KiB
Plaintext

\id ZEP
\ide UTF-8
\h ሶፎንያስ
\toc1 ሶፎንያስ
\toc2 ሶፎንያስ
\toc3 zep
\mt ሶፎንያስ
\s5
\c 1
\p
\v 1 ይህ በይሁዳ ንጉሥ በአሞን ልጅ በኢዮስያስ ዘመን፣ ወደ ሕዝቅያስ ልጅ፣ ወደ አማርያ ልጅ፣ ወደ ጐዶልያስ ልጅ፣ ወደ ኩሲ ልጅ፣ ወደ ሶፎንያስ የመጣ የያህዌ ቃል ነው፡፡
\v 2 «ማንኛውንም ነገር ከምድር ገጽ ፈጽሜ አጠፋለሁ! ይላል ያህዌ
\v 3 ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤ የሰማይን ወፎችና የባሕር ዓሦች አጠፋለሁ፡፡ ሰውን ከምድር ገጽ በማስወግድበት ጊዜ ክፉዎች የፍርስራሽ ክምር ይሆናሉ ይላል ያህዌ፡፡
\s5
\v 4 እጄን በይሁዳና በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ሁሉ ላይ እዘረጋለሁ፡፡ የበአልን አምልኮ ርዝራዥ፣ የጣዖቶቹንና የአመንዝራ ካህናቱን ስም ከዚህ ቦታ አጠፋለሁ ስም ሁሉ ከዚህ ቦታ አጠፋለሁ፤
\v 5 በየቤቶቹ ጣራ የሰማይን ሰራዊት የሚያመልኩትን፣ በያህዌ ስም እየማሉ ደግሞም በሜልኮም የሚምሉትን ሕዝብ አጠፋለሁ፡፡
\v 6 ያህዌን ከመከተል ወደ ኃላ የሚሉትን፣ ያህዌን የማይፈልጉትንም ሆነ ከእርሱ ምሪት የማይፈልጉትን አጠፋለሁ፡፡»
\s5
\v 7 የያህዌ ቀን እየቀረበ ነውና በጌታ ያህዌ ፊት ጸጥ በሉ፤ ያህዌ መሥዋዕት አዘጋጅቷል፤ የጠራቸውንም እንግዶች ቀድሷል፡፡
\v 8 በያህዌ የመሥዋዕት ቀን መኳንንቱንና የንጉሡን ልጆች፣ እንግዳ ልብስ የሚለብሱትንም ሁሉ እቀጣለሁ፡፡
\v 9 በዚያን ቀን፣ በመድረኩ ላይ የሚዘልሉትን ሁሉ፣ የጌቶቻቸውን ቤት በዐመፅና በማጭበርበር የሚሞሉትንም ሁሉ እቀጣለሁ፡፡
\s5
\v 10 በዚያን ቀን ይላል ያህዌ፣ ከዓሣው በር ጩኸት፣ ከሁለተኛው አደባባይ ዋይታ፣ ከኮረብቶችም ታላቅ የጥፋት ድምፅ ይሰማል፡፡
\v 11 እናንት በገበያው ቦታ የምትኖሩ ዋይ በሉ፤ ነጋዴዎች ሁሉ ይደመሰሳሉ፤ በብር የሚነግዱትም ሁሉ ይጠፋሉ፡፡›
\s5
\v 12 በዚያ ዘመን፣ ኢየሩሳሌምን በመብራት እፈትሻለሁ፤ ወይን ጠጅ የሚያዘወትሩንና በልባቸው፣ «ክፉም ሆነ መልካም ያህዌ ምንም አያደርግም» የሚሉትን ሰዎች እቀጣለሁ፡፡»
\v 13 ሀብታቸው ይዘረፋል፤ ቤቶቻቸውም ይፈርሳሉ፤ ቤት ይሠራሉ፤ ሆኖም፣ አይኖሩበትም፤ ወይን ይተክላሉ የወይን ጠጁን ግን አይጠጡም፡፡
\s5
\v 14 ታላቁ የያህዌ ቀን ቀርቧል፤ እጅግ እየፈጠነ ነው፤ የያህዌ ቀን ድምፅ ጦረኞች አምርረው የሚያለቅሱበት ይሆናል፤
\v 15 ያ ቀን የቁጣ፣ የመከራና የጭንቀት፣ የጥፋትና የመፍረስ፣ የጨለማና የጭጋግ፣ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ይሆናል፡፡
\v 16 በዚያ ቀን በተመሸጉት ከተሞችና በረጃጅም ግንቦች ላይ የጦር መለከትና የማስጠንቀቂያ ድምፅ ይሰማል፡፡
\s5
\v 17 እንደ ዕውሮች እስኪደናበሩ ድረስ በሰዎች ላይ ታላቅ ጭንቀት አመጣለሁ፤ ያህዌ ላይ ኃጢአት አድርገዋልና ደማቸው እንደ ውሃ ይፈስሳል፤ ሬሳቸውም እንደ ጉድፍ የትም ይጣላል፡፡
\v 18 ብራቸውም ሆነ ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ ያህዌ ቁጣውን በሚገልጥበት ቀን የቁጣው እሳት ምድርን ሁሉ ይበላል፤ ይህም የሆነው በምድር በሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ላይ በድንገት ጥፋት ስለሚመጣ ነው፡፡»
\s5
\c 2
\p
\v 1 እናንት ዕፍረት የሌላችሁ ሕዝብ ሆይ፣ በአንድነት ተሰብሰቡ ተከማቹም፤
\v 2 የወሰነው ጊዜ ሳይደርስ፣ ቀኑ እንደ ገለባ ሳይጠራርጋችሁ፣ የያህዌ ቁጣ በእናንተ ላይ ሳይመጣና የያህዌ መዓት ቀን ሳይደርስባችሁ ተሰብሰቡ፡፡
\v 3 እናንተ ትእዛዙን የምትፈጽሙ በምድር ያላችሁ ትሑታን ሁሉ ያህዌን ፈልጉ፤ ጽድቅንና ትሕትናንም ፈልጉ፤ በያህዌ ቀን ምናልባት ጥበቃ ታገኙ ይሆናል፡፡
\s5
\v 4 ጋዛ ባድማ ትሆናለች፤ አስቀሎናም ትፈራርሳለች፤ አሸዶድ በቀትር ባዶ ትሆናለች፤ አቃሮንም ትነቀላለች፡፡
\v 5 እናንተ በባሕር ዳርቻ የምትኖሩ የከሌታውያን ሰዎች ሆይ፣ የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ፣ ያህዌ እናንተ ላይ ተናግሯልና ወዮላችሁ፤ ከእናንተ ማንም እስከማይተርፍ ድረስ አጠፋችኃለሁ፡፡
\s5
\v 6 የባሕሩ ዳርቻ የእረኞች መሰማርያና የበጐች በረት ይሆናል፡፡
\v 7 የባሕሩ ዳርቻ ከይሁዳ ቤት ለተረፉት ይሆናል፤ እነርሱም በዚያ መንጐቻቸውን ያሰማሩበታል፡፡ በአስቀሎና ቤቶች ውስጥ በምሽት ይተኛሉ፤ አምላካቸው ያህዌ ይጠብቃቸዋል፤ ሀብታቸውንም ይመልሳል፡፡
\s5
\v 8 በሕዝቤ ላይ የደረሰውን የሞዓብን ሕዝብ ፌዝና የአሞናውያንን ንቀት ሰምቻለሁ፤ ሕዝቤን ሰድበዋል፤ ርስታቸውን ለመውሰድም ዝተዋል፡፡
\v 9 ስለዚህ ይላል የሰራዊት ጌታ፣ የእስራኤል አምላክ ያህዌ፣ የሞዓብ ሕዝብ እንደ ሰዶም፣ አሞናውያንም እንደ ገሞራ ዐረም እንደ ዋጠው ቦታና እንደ ጨው ጉድጓድ ለዘላለም ጠፍ እንደሚሆኑ በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ከሕዝቤ የተረፉት ይዘርፏቸዋል፤ ከወገኔ የተረፉትም ምድራቸውን ይወርሳሉ፡፡
\s5
\v 10 ከትዕቢታቸው የተነሣ፣ የሰራዊት ጌታ ያህዌ ሕዝብ ላይ በማፌዛቸውና እነርሱንም በመስደባቸው የሞዓብና የአሞን ሕዝብ ላይ ይህ ይሆናል፡፡
\v 11 እርሱ የምድሪቱን አማልክት በሚያጠፋበት ጊዜ፣ ያህዌ በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፡፡ በባሕሩ ጠረፍና በየምድራቸው የሚኖሩ ሁሉ በያሉበት ያመልኩታል፡፡
\s5
\v 12 እናንተ ኢትዮጵያውያንም በሰይፌ ትገደላላችሁ፣
\v 13 የእግዚአብሔር እጅ ሰሜንን ይመታል፤ አሦርንም ያጠፋል፤ ነነዌን ባድማ ያደርጋል፤ እንደ ምድረ በዳም ትደርቃለች፡፡
\v 14 የአራዊት መንጋዎች፣ የአሕዛብ እንስሶች ሁሉ አሦር ውስጥ ያርፋሉ፤ ወፎችና ልዩ ልዩ ዐይነት ጉጉቶች በጉልላትዋ ላይ ይሰፍራሉ፡፡ ጩኸታቸው በየመስኮቱ ያስተጋባል፤ ከዝግባ የተሠሩ ተሸካሚዎች ተገልጠዋልና ቁራዎች በየደጃፎቻቸው ይጮኻሉ፡፡
\s5
\v 15 ይህች በልቧ «እኔ ብቻ ነኝ፤ ከእኔ በቀር ማንም የለም» ያለች ያለ አንዳች ፍርሃት ተደላድላ ትኖር የነበረች ከተማ ነች፡፡ ታዲያ፣ እንዴት የዱር አራዊት የሚኖሩባት ባድማ ሆና ቀረች? በአጠገቧ የሚያልፉ ሁሉ ያፌዙባታል፤ እጃቸውንም በንቀት ያወዛውዙባታል!
\s5
\c 3
\p
\v 1 ለዐመፀኛዋ፣ ለጨቋኛና ለረከሰች ከተማ ወዮላት፡፡
\v 2 እርሷ የእግዚአብሔርን ድምፅ አልሰማችም፤ የያህዌንም ተግሣጽ አልተቀበለችም፤ በያህዌ አትታመንም፤ ወደ አምላኳም አትቀርብም፡፡
\s5
\v 3 መሪዎቿ እንደሚያገሡ አንበሶች፣ ዳኞችዋም ለነገ ሳያስተርፉ ያገኙት ሁሉ በልተው እንደሚጨርሱ እንደ ተራቡ የማታ ተኩላዎች ናቸው፡፡
\v 4 ነቢያቶችዋ ትዕቢተኞችና ተንኰለኞች ናቸው፡፡ ካህናትዋ የተቀደሰውን አርክሰዋል፤ ሕጉንም ተላልፈዋል፡፡
\s5
\v 5 ጻድቁ ያህዌ በእርሷ ውስጥ አለ፤ እርሱ ፈጽሞ አይሳሳትም፤ በየማለዳው ፍርዱን ይሰጣል፤ በየቀኑም ይህን ከማድረግ አይቆጠብም፤ ዐመፀኞች ግን ዕፍረት አያውቁም፡፡
\s5
\v 6 ሕዝቦችን አጥፍቻለሁ፤ ምሽጐቻቸውንም ደምስሻለሁ፡፡ ማንም እንዳያልፍባቸው መንገዶቻቸውን አፈራርሻለሁ፡፡ ከተሞቻቸው ስለ ተደመሰሱ ከእንግዲህ የሚኖርባቸው አይኖርም፡፡
\v 7 እኔም፣ «በእርግጥ ትፈሪኛለሽ፣ እርምትም ተቀበዪ፤ ላደርግብሽ እንዳሰብኩት ከመኖሪያሽ አትነቀዪ አልኩ፡፡ እነርሱ ግን በሚያደርጉት ሁሉ ክፋትን እያበዙ ሄዱ፡፡
\s5
\v 8 ስለዚህ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ «እስከምፈርድበት ቀን ድረስ ጠብቁኝ፤ ምድሪቱ ሁሉ በቁጣዬ እሳት እንድትጠፋ አሕዛብን ለመሰብሰብ፣ መንግሥታትን ለማከማቸት፤ ቁጣዬንና ጽኑ መዓቴን እነርሱ ላይ ለማፍሰስ ወስኛለሁ፡፡
\s5
\v 9 በዚያ ጊዜ ሰዎች የያህዌን ስም እንዲጠሩ፣ አንድ ልብ ሆነውም እንዲያገለግሉት ንጹሑን አንደበት እሰጣቸዋለሁ፡፡›
\v 10 ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ ያሉት እኔን የሚያመልኩ የተበተኑ ሕዝቤ ለእኔ የሚገባውን ቁርባን ያመጡልኛል፡፡
\v 11 በዚያ ቀን በእኔ ላይ ከፈጸማችሁት በደል ሁሉ የተነሣ አታፍሩም፤ በትዕቢታቸው የሚደሰቱትን ከመካከላችሁ ስለማስወግድ ከእንግዲህ ወዲያ በቅዱሱ ተራራዬ ላይ አትታበዩብኝም፡፡
\s5
\v 12 ሆኖም፣ የዋሃንንና ትሑታንን አስቀራለሁ፤ እናንተም በያህዌ ስም ትተማመናላችሁ፡፡
\v 13 የእስራኤል ትሩፋን ከእንግዲህ ፍርድ አያጐድሉም፤ ሐሰትንም አይናገሩም፤ በአንደበታቸው ሐሰት አይገኝም፡፡ ይበላሉ፤ በሰላምም ያርፋሉ፤ የሚያስፈራቸውም አይኖርም፡፡»
\s5
\v 14 የጽዮን ልጅ ሆይ፣ ዘምሪ፤ እስራኤል ሆይ፣ እልል በዪ፤ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፣ በፍጹም ልብሽ ደስ ይበልሽ ደስ ይበልሽ፤ ሐሤትም አድርጊ፡፡
\v 15 ያህዌ ቅጣትሽን አስወግዷል፤ ጠላቶችንም አስወጥቷል፤ የእስራኤል ንጉሥ ያህዌ በመካከልሽ ነው፡፡ ከእንግዲህ ክፉን አትፈሪም፡፡
\v 16 በዚያ ቀን ኢየሩሳሌምን እንዲህ ይሏታል፤ «ጽዮን ሆይ አትፍሪ፤ እጆችሽም አይዛሉ፡፡
\s5
\v 17 አንቺን ለማዳን ብርቱ የሆነው አምላክሽ ያህዌ በመካከልሽ ነው፡፡ በአንቺ እጅግ ደስ ይለዋል፤ በፍቅሩም ያሳርፍሻል፡፡ በዝማሬ በአንቺ ደስ ይለዋል፡፡
\v 18 ለታወቁ ክብረ በዓላት ሐዘንን ከአንቺ አርቃለሁ፤ በመካከልሽ ሸክምና ዕፍረት ሆነውብሻል፡፡
\s5
\v 19 በዚያ ቀን የበደሉሽን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ያነከሱትን እታደጋለሁ፤ የተጣሉትንም እሰበስባለሁ፡፡ ዕፍረታቸውን አስወግጄ በምድር ሁሉ ላይ ለምስጋናና ለክብር አደርጋቸዋለሁ፡፡
\v 20 በዚያ ቀን እመራችኃለሁ፤ በዚያ ቀን በአንድነት እሰበስባችኃለሁ፡፡ እኔ እንደ ሰበሰብኃችሁ፣ ምርኮአችንም እንደ ሰበሰብሁ ስታዩ የምድር ሕዝቦች ሁሉ ያመሰግኗችኃል፤ ያከብራችኃል ይላል ያህዌ፡፡