am_ulb/35-HAB.usfm

128 lines
12 KiB
Plaintext

\id HAB
\ide UTF-8
\h ዕንባቆም
\toc1 ዕንባቆም
\toc2 ዕንባቆም
\toc3 hab
\mt ዕንባቆም
\s5
\c 1
\p
\v 1 ነቢዩ ዕንባቆም የተቀበለው መልእክት፤
\v 2 «ያህዌ ሆይ፣ ለርዳታ ወደ አንተ ስጮኽ የማትሰማው እስከ መቼ ነው? «ግፍ በዛ!» በማለት ወደ አንተ ጮኽሁ፤ አንተ ግን አላዳንኸኝም፡፡
\s5
\v 3 ርኩሰትና በደልን ለምን እንዳይ አደረግኸኝ? ጥፋና ዐመፅ በፊቴ ናቸው፤ ፀብና ጭቅጭቅም እየበዛ ነው!
\v 4 ስለዚህ ሕግ ላልቶአል፤ ፍትሕ ተዛብቶአል፡፡ ክፉዎች ጻድቃንን ከብበዋል ስለዚህ ፍርድ ተጣሟል፡፡» ያህዌ እንዲህ በማለት ለዕንባቆም መለሰ
\s5
\v 5 «ቢነገራችሁ እንኳ የማታምኑትን አንድ ነገር በዘመናችሁ ስለማደርግ፣ ልብ አድርጋችሁ አሕዛብን እዩ፤ ተመልከቱ፤ እጅግም ተደነቁ፡፡
\v 6 ጨካኞቹንና ችኩሎቹን ከለዳውያንን ላስነሣ ነው፤ የራሳቸው ያልሆኑ ቤቶችን ለመውሰድ በምድሪቱ ስፋትና ርዝመት ይገሠግሣሉ፡፡
\v 7 እነርሱ አስፈሪና አስደንጋጭ ናቸው፤ ፍርዳቸውና ክብራቸው ከራሳቸው ይወጣል፡፡
\s5
\v 8 ፈረሶቻቸው ከነብር ይልቅ ፈጣኖች፣ ከማታም ተኩላ ይልቅ፣ አስፈሪዎች ናቸው፡፡ ፈረሶቻቸው በፍጥነት ይጋልባሉ፤ ነጥቆ ለመብላት እንደሚቸኩል ንስር ፈረሰኞቻቸው ከሩቅ ይመጣሉ፡፡
\v 9 ሁሉም ለዐመፅ ሥራ ይመጣሉ፤ ሰራዊታቸው እንደ ምድረ በዳ ነፋስ ይገሠግሣል፤ ምርኮኞችንም እንደ አሸዋ ይሰበስባል፡፡
\s5
\v 10 ነገሥታት ላይ ይሳለቃሉ፤ ገዥዎች ላይ ያፌዛሉ፡፡ በምሽጐች ላይ በመሳቅ ዐፈር ቆልለው ይይዟቸዋል፡፡
\v 11 ከዚያም እንደ ነፋስ አልፈው ይሄዳሉ፤ ጉልበታቸውን አምላካቸው ያደረጉ እነዚያን በደለኞች ይጠራርጋቸዋል፡፡ ዕንባቆም ለያህዌ ያቀረበው ሌላው ጥያቄ
\s5
\v 12 አንተ የእኔ አምላክ፣ የእኔ ቅዱስ፣ አንተ ከዘላለም ጀምሮ ያለህ አይደለህምን? እኛ አንሞትም፡፡ እንዲፈርዱ ያህዌ ሾሟቸዋል፤ አንተ ዐለት ሆይ፣ ይቀጡ ዘንድ ሥልጣን ሰጠሃቸው፡፡
\s5
\v 13 ዐይኖችህ እጅግ የነጹ በመሆናቸው ክፉ ነገርን መመልከት አይሆንላቸውም፤ አንተም ክፉ ነገር ሲሠራ ዝም ብለህ አታይም፤ ታዲያ፣ እነዚያን ዐመፀኞች ለምን ዝም ብለህ ትመለከታለህ? ዐመፀኛው ከራሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን ሰው ሲውጠውስ ለምን ዝም ትላለህ?
\v 14 ሰዎችን ባሕር ውስጥ እንዳለ ዓሣ፣ መሪ እንደሌላቸው በደረታቸው እየተሳቡ እንደሚሄዱ ፍጥረታት የምታደርጋቸው ለምንድነው?
\s5
\v 15 ዓሣ በመንጠቆ እንደሚያዝ ሁሉንም በመንጠቆ ይይዟቸዋል፤ ሰዎችን በመረቦቻቸው ይዘው ይሰበሰቧቸዋል፡፡ ደስ የሚሰኙትና ሐሤት የሚያደርጉት ከዚህ የተነሣ ነው፡፡
\v 16 የስቡ እንስሳት ድርሻዎቻቸው፣ የጣፈጠውም ሥጋ ምግባቸው ሆናልና ስለዚህ ለመረቦቻቸው ይሠዋሉ፤ ለአሸክላዎቻቸውም ያጥናሉ፡፡
\v 17 ታዲያ፣ መረቦቻቸውን ባዶ እያደረጉ፣ ያለ አንዳች ርኅራኄ ሕዝቦችን መግደል መቀጠል አለባቸውን?»
\s5
\c 2
\p
\v 1 በጥበቃ ቦታዬ እቆማለሁ፤ በመጠበቂያው ግንብ ላይ ቦታዬን እይዛለሁ፤ ምን እንደሚለኝና ለጥያቄዬ ምን መልስ እንደሚሰጥ እጠባበቃለሁ፡፡
\s5
\v 2 ያህዌ እንዲህ በማለት መለሰልኝ፤ «ይህን ራእይ ጻፈው፤ በቀላሉ እንዲነበብ አድርገህም በጽላት ቅረጸው፡፡
\v 3 ራእዩ የሚናገረው ገና ወደ ፊት ስለሚሆነው ነው፡፡ በመጨረሻም ይፈጸማል እንጂ፣ በፍጹም አይዋሽም፡፡
\s5
\v 4 ተመልከት! ጠማማ ሐሳብ ያለው ሰው ታብዮአል፡፡ ጻድቁ ግን በእምነቱ ይኖራል፡፡
\v 5 ዐርፎ እንዳይቀመጥ ወይን ጠጅ ዕብሪተኛውን ወጣት አስቶታል ይልቁን ምኞቱን እንደ መቃብር አስፍቶአል እንደ ሞት በቃኝ ማለትን አያውቅም፡፡ ሕዝቦችን ሁሌ ወደ ራሱ ይሰበስባል ሰዎችንም ሁሉ ማርኮ ይወስዳል፡፡
\s5
\v 6 ታዲያ፣ በእንዲህ ዐይነቱ ሰው ላይ በማፌዝና በመዘባበት እንዲህ እያሉ ሁሉም አይሣለቁበትምን? ‹የተሰረቀውን ለራሱ ለሚያከማች፣ ራሱን በዐመፅ ባለጠጋ ለሚያደርግ ወዮለት! ይህ የሚቀጥለውስ እስከ መቼ ነው?
\v 7 በአንተ የተመረሩ ድንገት አይነሡብህምን፣ አንተን የማያስደነግጡስ አይነቁብህምን? በእጃቸውም ትወድቃለህ፡፡
\v 8 አንተ ብዙ ሕዝብ ስለ ዘረፍህ የተረፉት ሕዝቦች ይዘርፉሃል፡፡ የሰው ደም አፍስሰሃል አገሮች፣ ከተሞችና የሚኖሩባቸው ሰዎች ሁሉ ላይ ግፍ ሠርተሃል፡፡
\s5
\v 9 በማጭበርበር በተገኘ ሀብት ቤቱን ለሚገነባ ከክፉ ለማምለጥ ቤቱን በከፍታ ላይ ለሚሠራ ወዮለት!
\v 10 ብዙ ሰዎችን ለማጥፋት ደባ ፈጽመሃል በገዛ ቤትህ ላይ ውርደትን፣ በራስህም ላይ ኃጢአትን አድርገሃል፡፡
\v 11 ድንጋዮች በቅጥሩ ውስጥ ይጮኻሉ፣ ከዕንጨት የተሠሩ ተሸካሚዎችም እንዲህ በማለት ይመልሱላቸዋል፣
\s5
\v 12 «ደም በማፍሰስ ከተማን ለሚሠራ፣ በወንጀልም አገርን ለሚመሠርት ወዮለት!»
\v 13 ሰዎች ለእሳት ማገዶ እንዲሆን እንዲለፉ፣ ሕዝቦችም በከንቱ እንደደከሙ፣ የሰራዊት ጌታ ያህዌ ወስኖ የለምን?
\v 14 ያም ሆኖ፣ ውሃ ባሕርን እንደሚሞላ ሁሉ ምድርም የያህዌን ክብር በማወቅ ትሞላለች፡፡
\s5
\v 15 ኅፍረተ ሥጋቸውን ለማየት ባልንጀሮቹን ለሚያጠጣ፣ እስኪሰክሩም ድረስ ወይን ለሚያቀርብላቸው ወዮለት!»
\v 16 በክብር ፈንታ ውርደት ትሞላለህ፤ አሁን ተራው የአንተ ነውና ጠጣ፤ ኀፍረተ ሥጋህም ይገለጥ፤ በያህዌ ቀኝ እጅ ያለው ጽዋ በተራው ይመልስብሃል ክብርህን ውርደት ይሸፍነዋል፡፡
\s5
\v 17 ሊባኖስ ላይ ያሠራኸው ግፍ ያጥለቀልቅሃል፤ እንስሶች ላይ የፈጸምኸው ጥፋት ያስደነግጥሃል፡፡ የሰው ደም አፍስሰሃል፤ አገሮች፣ ከተሞችና የሚኖሩባቸው ሰዎች ሁሉ ላይ ግፍ ሠርተሃል፡፡
\s5
\v 18 ታዲያ፣ የቀረጽኸው ምስል ምን ይጠቅምሃል? ምስሉን የቀረጸው፣ ከቀለጠ ብረት ጣዖት የሠራ ሰው የሐሰት መምህር ነው፤ እነዚያን የማይናገሩ አማልክት ሲሠራ በገዛ እጅ ሥራው ተማምኖአልና፡፡
\v 19 ዕንጨቱን ንቃ! ሕይወት የሌለውንም ድንጋይ ተነሣ ለሚል ወዮለት ለመሆኑ፣ እነዚህ ነገሮች ማስተማር ይችላሉን? በወርቅና በብር ተለብጦአል፤ እስትንፋስ ግን የለውም፡፡
\v 20 ያህዌ ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ፤ ምድር ሁሉ በፊቱ ጸጥ ትበል!»
\s5
\c 3
\p
\v 1 የነቢዩ ዕንባቆም ጸሎት
\v 2 ያህዌ ሆይ፣ ስላደረግኸው ድንቅ ሥራ ሰዎች ፈራሁ፤ የቀድሞ ዘመን ሥራህን በዚህ ዘመንም አድርግ፤ በየዘመናቱም እንዲታወቅ አድርግ፡፡ በቁጣህ ውስጥ እንኳ ምሕረት ርኅራኄኅን አስብ፡፡
\s5
\v 3 እግዚአብሔር ከቴማን፣ ቅዱሱንም ከፋራን ተራራ መጣ! ሴላ፡፡ ክብሩ ሰማያትን ሸፈነ፤ ምድር በምስጋናው ተሞላች፡፡
\s5
\v 4 ኃይሉ ከተሰወረበት እጁ የወጡ ሁለት ጨረሮች እንደ መብረቅ ደምቀዋል፡፡
\v 5 መቅሠፍት በፊቱ ሄደ፤ ቸነፈርም እግር በእግር ተከተለው፡፡
\s5
\v 6 እርሱ ሲቆም ምድር ትናወጣለች፤ እርሱ ሲመለከት ሕዝቦች ይንቀጠቀጣሉ፡፡ የዘላለም ተራሮች እንኳ ተፈረካከሱ የጥንት ኮረብቶችም ዝቅ አሉ፡፡ መንገዱ ዘላለማዊ ነው፡፡
\s5
\v 7 የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ፣ የምድያምም መኖሪያዎች ሲታወኩ አየሁ፡፡
\v 8 ያህዌ ወንዞች ላይ ተቆጥቷልን? መዓትህስ በምንጮች ላይ ነበርን? ወይስ በፈረሶችህና በድል አድራጊ ሰረገሎችህ በጋለብህ ጊዜ ባሕር ላይ ተቆጥተህ ነበርን?
\s5
\v 9 ቀስትህን ከሰገባው አወጣህ፤ ፍላጻህንም ለመወርወር አዘጋጀህ፡፡ ሴላ፡፡ ምድርን በወንዞች ከፈልህ፡፡
\v 10 ተራሮች አዩህ፤ በፍርሃትም ተጨማደዱ የውሃ ወጀብ በላያቸው አለፈ፤ ጥልቁ ባሕር ድምፁን አሰማ ማዕበሉም ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለ፡፡
\s5
\v 11 ከሚወረወሩ ፍላጾች ብርሃን፣ ከሚያብረቀርቀው የጦርህ ነጸብራቅ የተነሣ ፀሐይና ጨረቃ በቦታቸው ቆሙ፡፡
\v 12 በቁጣህ በምድር ላይ ተመላለስህ፤ በመዓትህ ሕዝቦችን አደቀቅህ፡፡
\s5
\v 13 ሕዝብህን ለማዳን፣ የቀባኸውንም ለመታደግ ወጣህ፡፡ ዕርቃኑን ታስቀረው ዘንድ የዐመፃን ቤት ራስ ቀጠቀጥህ፡፡ ሴላ፡፡
\s5
\v 14 እንደ ዐውሎ ነፋስ ሊበታትን የመጣውን፣ ምስኪኑን በስውር ለመዋጥ የመጣውን ሰራዊት አለቃ ራስ በገዛ ፍላጻው ወጋህ፡፡
\v 15 በፈረሶችህ ባሕሩ ላይ ተራመድህ፤ ታላላቅ ውሆችን ከመርህ፡፡
\s5
\v 16 እኔ ሰማሁ ውስጤም ተናወጠ፤ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፡፡ አጥንቶቼ ይበሰብሳሉ፤ እግሮቼም ከታች ይርዳሉ ወራሪዎቻችን ላይ መከራ የሚመጣበትን ቀን በትዕግሥት እጠብቃለሁ፡፡
\s5
\v 17 ምንም እንኳ የበለስ ዛፍ ባያብብ፣ ወይን ዛፍ ላይ ፍሬ ባይገኝ፣ የወይራ ዛፍ ምንም ፍሬ ባይሰጥ፣ ከእርሻዎች ሰብል ቢጠፋ፣ የበግ መንጋዎች ሁሉ ቢያልቁ፣ በረት ውስጥ ምንም ከብት ባይገኝ፣
\s5
\v 18 ይህም ሁሉ ቢሆን፣ እኔ በያህዌ ደስ ይለኛል በመድኃኒቴም አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ፡፡
\v 19 ጌታ ያህዌ ኃይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋሊያ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎቼም ላይ ይመራኛል፡፡ - ለመዘምራን አለቃ በባለ አውታር መሣሪያዎች የተዘመረ፡፡