am_ulb/34-NAM.usfm

111 lines
10 KiB
Plaintext

\id NAM
\ide UTF-8
\h ትንቢተ ናሆም
\toc1 ትንቢተ ናሆም
\toc2 ትንቢተ ናሆም
\toc3 nam
\mt ትንቢተ ናሆም
\s5
\c 1
\p
\v 1 ስለ ነነዌ የተነገረ ቃል፤ የአልቆሻዊው የናሆም ራእይ መጽሐፍ ይህ ነው፡፡
\s5
\v 2 ያህዌ ቀናተኛና ተበቃይ ነው፤ ያህዌ የሚበቀል በመዓትም የተሞላ አምላክ ነው፡፡ ያህዌ ባላጋራዎቹን ይበቀላል፤ በጠላቶቹም ላይ ቁጣውን ይወርዳል፡፡
\v 3 ያህዌ ለቁጣ የዘገየ፣ በኃይሉም ታላቅ ነው፤ በምንም ዐይነት ጠላቶቹን ንጹሕ ናችሁ አይልም፡፡ ያህዌ በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥ መንገድ አለው፤ ደመናም የእግሩ ትቢያ ነው፡፡
\s5
\v 4 ባሕርን ይገሥጻል፤ ያደርቀዋልም፤ እርሱ ወንዞችን ሁሉ ያደርቃል፡፡ ባሳንና ቀርሜሎስ ጠውልገዋል፤ የሊባኖስ አበቦችም ረግፈዋል፡፡
\v 5 ተራሮች በእርሱ ፊት ተናወጡ፤ ኮረብቶችም ቀለጡ፤ ምድር በፊቱ፣ ዓለምና በውስጧ የሚኖሩ ሰዎችም ሁሉ ተናወጡ፡፡
\s5
\v 6 በቁጣው ፊት ማን መቆም ይችላል? ጽኑ ቁጣውንስ ማን መቋቋም ይችላል? መዓቱ እንደ እሳት ፈስሶአል፤ ዐለቶችም በፊቱ ተሰነጣጠቁ፡፡
\s5
\v 7 ያህዌ መልካም ነው፤ በመከራ ጊዜም መሸሸጊያ ነው፤ በእርሱ ለሚታመኑበት ታማኝ ነው፡፡
\v 8 ጠላቶቹን ግን በኃይለኛ ጐርፍ ያጥለቀልቃቸዋል፤ ወደ ጨለማም ያሳድዳቸዋል፡፡
\s5
\v 9 እናንተ ሰዎች ያህዌ ላይ የምታሤሩት ምንድነው? እርሱ ፈጽሞ ያጠፋዋል፤ መከራም ዳግመኛ አይነሣም፡፡
\v 10 እንደ እሾኽ ይጠላለፋሉ፤ በወይን ጠጃቸውም ይሰክራሉ፤ እሳት እንደ ገለባ ይበላቸዋል፡፡
\v 11 ነነዌ ሆይ፣ ያህዌ ላይ የሚያሤር፣ ክፉ ምክር የሚመክር ከመካከላችሁ ወጥቷል፡፡
\s5
\v 12 ያህዌ እንዲህ ይላል፤ «ኅይለኞችና ቁጥራቸውም እጅግ የበዛ ቢሆን እንኳ ተቆርጠው ይጠፋሉ፤ ከእንግዲህም ሕዝባቸው አይኖም፡፡ ይሁዳ ሆይ፣ ከዚህ በፊት ባስጨንቅህም፣ ከእንግዲህ አላስጨንቅህም፡፡
\v 13 አሁንም ቀንበራቸውን ከአንተ ላይ እሰብራለሁ፤ ስንሰለትህንም በጥሼ እጥላለሁ፡፡
\s5
\v 14 ነነዌ ሆይ፣ ስለ አንቺ ያህዌ እንዲህ ብሎ አዝዞአል፤ «ስም የሚያስጠራ ትውልድ አይኖራችሁም፡፡ የተቀረጹ ምስሎችና ቀልጠው የተሠሩ ጣዖቶችን ከአማልክቶቻችሁ ቤት አጠፋለሁ፡፡ እጅግ ክፉ ነህና መቀበሪያህን እምስልሃለሁ፡፡
\s5
\v 15 የምሥራችን የሚያመጣና ሰላምን የሚያውጅ ሰው እግር በተራራው ላይ ናቸው! ይሁዳ ሆይ፣ በዓላትህን አክብር፤ ስእለትህንም ፈጽም፤ ከእንግዲህ ክፉዎች አይወርሩህም፤ እነርሱ ፈጽሞ ይጠፋሉ፡፡
\s5
\c 2
\p
\v 1 እስክትደቅቂ ድረስ የሚረግጥሽ እርሱ እየመጣ ነው፡፡ ስለዚህ ምሽጐችሽን አጠናክሪ መንገድሽን ጠብቂ፤ ወገብሽን ታጠቂ፤ ኃይልሽን ሁሉ አሰባስቢ፡፡
\v 2 አጥፊዎች ባድማ ቢያደርጓቸውም፣ የወይን ተክል ቦታቸውን ቢያጠፉባቸውም እንደ እስራኤል ክብር ሁሉ ያህዌ የያዕቆብንም ክብር ይመልሳል፡፡
\s5
\v 3 የወታደሮቹ ጋሻ ቀይ ነው፣ ተዋጊዎቹም ሐምራዊ ልብስ ለብሰዋል ዝግጁ በሆኑበት ቀን የሰረገሎቹ ብረት ያብረቀርቃል የጦሩ ዘንግ ይወዛወዛል፡፡
\v 4 ሰረገሎቹ በየመንገዱ ይከንፋሉ፤ ሰፋፊ በሆኑት መንገዶች በፍጥነት ወዲያ ወዲህ ይላሉ፡፡ የሚንቦገቦግ ችቦ ይመስላሉ፤ እንደ መብረቅም ይወረወራሉ፡፡
\s5
\v 5 እስክትደቂ ድረስ የሚረግጥሽ እርሱ የጦር ሹማምንቱን ይጠራል እነርሱም እየተደነቃቀፉ ወደ ፊት ይመጣሉ፣ ለማጥቃት ወደ ከተማ ቅጥር ይወጣሉ፤ የሚወረወርባቸውን ፍላጻ በትልቁ ጋሻቸው ይከላከላሉ፡፡
\s5
\v 6 በወንዙ በኩል ያሉ በሮች ወለል ብለው ይከፈታሉ ቤተ መንግሥቱም ተደመሰሰ፡፡
\v 7 ንግሥቲቱ ተማርካ ዕርቃኗን ተወሰደች ሴት አገልጋዮቿ ደረታቸውን እየደቁ እንደ ርግብ ያላዝናሉ፡፡
\s5
\v 8 ነነዌ ውሃ መያዝ እንደማይችል ኩሬ ናት፤ ሕዝቧም እንደ ፈጣን ወራጅ ውሃ ፈጥኖ ይሸሻል፡፡ ሌሎች «ቁሙ ቁሙ» ብለው ይጮኻሉ ዞር ብሎ የሚያይ ግን የለም፡፡
\v 9 የነነዌ ሀብት ስፍር ቁጥር የለውም የከበሩ ድንጋዮቿ የተትረፈረፉ ናቸው ስለዚህ ብሩን ዝረፉ፣ ወርቁንም ንጠቁ፡፡
\v 10 ነነዌ ባዶ ሆነች፣ ተራቆተች፡፡ የሰዎች ልብ ቀለጠ፤ የሰው ሁሉ ጉልበት ተብረከረከ ሁሉም ተጨንቀዋል፤ ፊታቸው ገርጥቷል፡፡
\s5
\v 11 የአንበሶች ዋሻ፣ የአንበሳ ደቦሎች የሚመገቡበት፣ ወንድ አንበሳና እንስት አንበሳ ምንም ሳይፈሩ ወዲያ ወዲህ ይሉበት የነበረ ቦታ የታል?
\v 12 አንበሳ ለግልገሎቹ የሚበቃውን ያህል ገደለ፤ ለእንስቶቹ የሚበቃውንም ያህል አድኖ ያዘ የገደለውን በዋሻው፣ የነጠቀውንም በመኖሪያ ቦታው ሞልቶአል፡፡
\s5
\v 13 የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ሰረገሎችን አቃጥላለሁ፤ ደቦል አንበሶችህን ሰይፍ ይበላቸዋል፡፡ የዘረፍኸውን ከምድርህ አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህ የመልእክተኞችህ ድምፅ አይሰማም፡፡»
\s5
\c 3
\p
\v 1 ደም ለሞላባት ከተማ ወዮላት! ሐሰትና የተዘረፈ ንብረት ሞልቶበታል፡፡
\v 2 አሁን ግን የአላንጋ ድምፅና የመንኰራኩር ኳኳታ ድምፅ፣ የፈጣን ፈረስ ኮቴ፣ የሰረገሎች መንጓጓት ይሰማል፡፡
\s5
\v 3 የሚያብረቀርቅ ሰይፍና የሚያንጸባርቅ ጦር የያዙ ፈረሰኞች ጥቃት ያደርሳሉ፤ የሞተው ብዙ ነው፤ ሬሳ በሬሳ ተከምሮአል እጅግ ከመብዛቱ የተነሣ አጥቂዎቹ በሞቱት ሰዎች ሬሳ ይሰናከላሉ፡፡
\v 4 ይህ ሁሉ የሆነው ገደብ በሌለው የአመንዝራዋ ፍትወት ምክንያት ነው፤ እርሷ በዝሙቷ መንግሥታን፣ በጥንቆላዋም ሕዝቦችን ባሪያ አድርጋለች፡፡
\s5
\v 5 የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ «እኔ በጠላትነት ተነሥቼብሻለሁ ዕርቃንሽን ለሕዝቦች፣ ኅፍረተ ሥጋሽን ለመንግሥታት አሳያለሁ፡፡
\v 6 በጣም የሚያስጸይፍ ቆሻሻ እደፋብሻለሁ፤ እንቅሻለሁ፤ ሰው ሁሉ እንዲሳለቅብሽ አደርጋለሁ፡፡
\v 7 የሚያይሽ ሁሉ ከአንቺ እየሸሸ፣ «ነነዌ ፈራርሳለች፤ ማን ያለቅስላታል? የሚያጽናናትንስ ከወዴት አገኛለሁ?» ይላል፡፡
\s5
\v 8 ነነዌ ሆይ፣ ለመሆኑ አንቺ ዐባይ ወንዝ አጠገብ ከተሠራችውና በውሃ ከተከበበችው፣ ወንዙ መከላከያ፣ ባሕሩ ራሱ ቅጥራ ከሆነለት ከቴብስ ትበልጫለሽን?
\v 9 ኢትዮጵያና ግብፅ ወሰን የለሽ ኃይሏ ነበሩ ፉጥና ሊቢያም ረዳቶቿ ነበሩ፡፡
\s5
\v 10 ያም ሆኖ፣ ቴብስ ተጋዘች፤ በምርኮም ተወሰደች ሕፃናቷ በየመንገዱ ማእዘን ላይ ተፈጠፈጡ፤ በመኳንንቷ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፤ ታላላቅ ሰዎቿ ሁሉ በሰንሰለት ታሰሩ፡፡
\v 11 አንቺ ደግሞ ትሰክሪያለሽ መደበቅ ትሞክሪያለሽ ከጠላቶችሽ መሸሸጊያም ትፈልጊያለሽ፡፡
\s5
\v 12 ምሽጐችሽ ሁሉ ቀድሞ እንደ ደረሰ፣ ሲነቀነቅ በላተኛው አፍ ውስጥ እንደሚወድቅ የበለስ ፍሬ ሆነዋል፡፡
\v 13 ወታደሮችሽ እንደ ሴት ፈሪዎች ሆነዋል የምድርሽ በሮች ወለል ብለው ለጠላቶችሽ ተከፍተዋል፡፡ መዝጊያዎቻቸውን እሳት በልቷቸዋል፡፡
\s5
\v 14 ለከበባው ውሃ ቅጂ፣ ምሽጐችሽን አጠናክሪ፤ ጭቃ ረግጠሸ የሸክላ መሥሪያ አዘጋጂ፤ ጡብም ሥሪ፡፡
\v 15 በዚያ እሳት ይበላሻል፤ ሰይፍ ያጠፋሻል፤ አንበጣ ማንኛውንም ነገር እንደሚጠፉ ያጠፋሻል፡፡ ስለዚህ እንደ አንበጣ እርቢ እንደ ኩብኩባም ተባዢ፡፡
\s5
\v 16 ነጋዴዎችሽን ከሰማይ ከዋክብት ይበልጥ አብዝተሻል፤ ይሁን እንጂ፣ ምድሪቱን እንደ አንበጣ ጋጡ፤ ከዚያም በርረው ሄዱ፡፡
\v 17 መኳንንቶችሽ የአንበጦችን ያህል ብዙ ናቸው፣ የጦር መሪዎችሽ በብርድ ቀን ቅጥር ሥር እንደሚቀመጥ የኩብኩባ መንጋ ናቸው፡፡ ፀሐይ ሲወጣ ግን በርረው ይሄዳሉ፤ የት እንደሚሄዱም አይታወቅም፡፡
\s5
\v 18 የአሦር ንጉሥ ሆይ፣ እረኞችህ አንቀላፉ መኳንንትህ ዐርፈው ተኙ፡፡ ሕዝብህ ሰብሳቢ አጥተው በየተራሮች ተበትነዋል፡፡
\v 19 ቁስልህን መፈወስ የሚችል የለም፤ ቁስልህ እጅግ ጽኑ ነው፡፡ ስለ አንተ የሚሰማ ሁሉ በውድቀትህ ደስ ብሎት ያጨበጭባል፡፡ ወሰን ከሌለው ጭካኔህ ማን ያመለጠ አለ?