am_ulb/33-MIC.usfm

229 lines
23 KiB
Plaintext

\id MIC
\ide UTF-8
\h ትንቢተ ሚክያስ
\toc1 ትንቢተ ሚክያስ
\toc2 ትንቢተ ሚክያስ
\toc3 mic
\mt ትንቢተ ሚክያስ
\s5
\c 1
\p
\v 1 በይሁዳ ንጉሦች በአዮአታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ወደ ሞሬታዊው ወደ ሚክያስ የመጣው የያህዌ ቃል፣ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ራእይ ይህ ነው፡፡
\s5
\v 2 እናንት ሕዝቦች ስሙ ምድርና በውስጧ የምትኖሩ ሁሉ አድምጡ፡፡ ጌታ ከቅዱስ መቅደሱ፣ ጌታ ያህዌም ይመሰክርባችኃል፡፡
\v 3 ተመልከቱ፤ ያህዌ ከመኖሪያው ስፍራ ይመጣል፤ ‹ወርዶም፣ በምድር ከፍታዎች ላይ ይራመዳል፡፡
\v 4 ተራሮች ከሥሩ ይቀልጣሉ ሸለቆዎች ይሰነጠቃሉ እሳት ፊት እንዳለም ሰም በገደል ላይ እንደሚወርድ ውሆች ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 5 ይህ ሁሉ የሚሆነው ከያዕቆብ ዐመፅ ከእስራኤልም ቤት ኃጢአት የተነሣ ነው፡፡ የያዕቆብ ዐመፅ ምክንያት ምን ነበር? ሰማርያ አይደለችምን? የይሁዳስ ኮረብታ መስገጃ ምንድው? ኢየሩሳሌም አይደለችምን?
\s5
\v 6 ስለዚህ ሰማርያን ሜዳ ላይ እንዳለ ፍርስራሽ ክምር፣ ወይን እንደሚተከልባትም ቦታ አደርጋታለሁ፡፡ የከተማዋን ፍርስራሽ ድንጋይ ወደ ሸለቆው አወርዳለሁ፤ መሠረቶችዋንም እገልጣለሁ፡፡
\v 7 ምስሎቿ ሁሉ ይሰባበራሉ፤ ለእርሷ የተሰጡ ስጦታዎችም ይቃጠላሉ፡፡ ጣዎቶችዋም ሁሉ ለጥፋት ይሆናሉ፡፡ እነዚህን የሰበሰበችው ለዝሙት ሥራዋ ካገኘችው ገጸ በረከት እንደ ነበር ሁሉ አሁንም ገጸ በረከትዋ የዝሙት አዳሪነት ዋጋ መቀበያ ይሆናል፡፡
\s5
\v 8 በዚህ ምክንያት ዋይ ዋይ እያልሁ አለቅሳለሁ፤ ባዶ እግሬንና ዕርቃኔን እሄዳለሁ፤ እንደ ቀበሮ አላዝናለሁ እንደ ጉጉትም አለቅሳለሁ፡፡
\v 9 ቁስሏ የማይፈወስ ነውና ለይሁም ተርፏል፡፡ ወደ ሕዝቤ ደጅ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ደርሷል
\v 10 በጌት አታውሩ፣ ከቶም አታልቅሱ በቤትዓፍራ ትቢያ ላይ እንከባለላለሁ
\s5
\v 11 እናንት በሻፊር የምትሮሩ ዕርቃናችሁን ሆናችሁ እለፉ፡፡ በጸዓናን የሚኖሩ ከዚያ አይወጡም፡፡ ቤትዔጼል ሐዘን ላይ ስለሆነች መጠጊያ ልትሆን አትችልም፡፡
\v 12 የማሮት ነዋሪዎች መልካም ዜና ለመስማት እጅግ ጓጉተዋል፤ ምክንያቱም ከያህዌ ዘንድ ጥፋት እስከ ኢየሩሌም ደጆች መጥቷል፡፡
\s5
\v 13 እናንት በለኪሶ የምትኖሩ የሰረገሎችን ፈረሶች ለጉሙ፣ ለጽዮን ሴት ልጅ ኃጢአት መጀመሪያ እናንተ ነበራችሁ፡፡ የእስራኤልም በደል አንተ ዘንድ ተገኝቷል፡፡
\v 14 ስለዚህ እናንተ ለሞሬሴት ጌት የመሰነባበቻ ስጦታ ትሰጣላችሁ፤ የአክዚብም ከተሞች የእስራኤልን ንጉሦች ያታልላሉ፡፡
\s5
\v 15 እናንት በመሪሳ የምትኖሩ ወራሪ አመጣባችኃለሁ፡፡ የተከበሩ የእስራኤል መሪዎች በዓዶላም ዋሻ ይሸሸጋሉ፡፡
\v 16 ደስ ትሰኙባቸው ለነበሩ ልጆቻችሁ በማዘን ራሳችሁን ተላጩ ጡራችሁን ተቆረጡ ራሳችሁን እንደ ንስር ራስ ተመለጡት ምክንያቱም ልጆቻችሁ በምርኮ ከእናንተ ይወሰዳሉና፡፡
\s5
\c 2
\p
\v 1 ክፉ ነገር ለማድረግ ለሚያቅዱ መኝታቸው ላይ ሆነው ተንኰል ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው፡፡ ያን ለማድረግ ሥልጣን ስላላቸው ሌሊቱ ሲነጋ ዕቅዳቸውን ሥራ ላይ ያውሉታል፡፡
\v 2 የዕርሻ ቦታ ሲፈልጉ፣ ቀምተው ይወስዳሉ ቤት ሲፈልጉ ነጥቀው ይወስዳሉ፡፡ የሰው መብት ረግጠው ሀብቱን ይዘርፋሉ
\s5
\v 3 ስለዚህ ያህዌ እንዲህ ይላል በዚያ ሕዝብ ላይ ጥፋት አመጣለሁ ከዚህም ልታመልጡ አትችሉም፡፡ ያ የመከራ ጊዜ ስለሚሆን ከእንግዲህ በእብሪት አትኖሩም፡፡
\v 4 በዚያ ቀን ጠላቶቻችሁ ይሳለቁባችኃል በሐዘን እንጉርጉሮ እንዲህ እያሉ ያፌዙባችኃል እኛ እስራኤላውያን ፈጽሞ ጠፍተናል ያህዌ የሕዝቤን ንብረት ወስዶ ርስታችንንም ለከሐሂዲዎች አከፋፈለ
\v 5 ስለዚህ እናንተ ባለጸጐች በያህዊ ጉባኤ ውስጥ ርስት በዕጣ የሚከፋፈሉ ልጆች አይኖሯችሁም፡፡
\s5
\v 6 «ትንቢት አትናገር» ምንም ውርደት አይደርስብንም፤ ስለ እነዚህ ነገሮች ትንቢት አትናገር ይላሉ፡፡
\v 7 የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ እንደህ መባል ነበረበትን? የያህዌ ትዕግሥት አልቋልን? እነዚህስ የእርሱ ድርጊቶች ናቸውን? አካሄዳቸው ቀና ለሆነ ሰዎች ቃሎቼ መልካም አያደርጉምን?
\v 8 በመጨረሻ በሕዝቤ ላይ በጠላትነት ተነሥታችኃል ከጦርነት በኃላ ሰላም ነው ብለው ወደሚያስቡት እንደሚመለሱ ወታደሮች ምንም ሳይጠራጠሩ የሚያልፉ ሰዎችን ልብስ ገፋችኃል፡፡
\s5
\v 9 የወገኔን ሴቶች ከሚወዱት ቤታቸው አባረራችሁ በረከቴን ለዘላለም ከልጆቻቸው ወሰዳችሁ፡፡
\v 10 በርኩሰት ምክንያት ከባድ ጥፋት ስለሚመጣ እዚህ ቦታ መቆየት አትችሉም፤ ስለዚህ ተነሥታችሁ ሂዱ፡፡
\v 11 አንድ ሰው በሐሰት መንፈስ ተነሣሥቶ «ስለ ወይን ጠጅና ጠንካራ መጠጥ ትንቢት እናገራለሁ» ቢል፤ በእነዚህ ሰዎች ዘንድ እንደ ነቢይ ይቆጠራል፡፡
\s5
\v 12 ያዕቆብ ሆ በእርግጥ ሁላችሁንም እሰበስባለሁ፤ የእስራኤልን ትሩፍ ጉረኖ ውስጥ እንዳለ በጐች በመሰማሪያ ላይ እንዳለ መንጋ አመጣቸዋለሁ፡፡ ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ታላቅ ጩኸት ይሆናል፡፡
\v 13 መንገዳቸውን የሚከፍትላቸው መሪ ከእነርሱ ፊት ፊት ይሄዳል እነርሱም ተግተልትለው በበሩ ይወጣሉ ንጉሣቸው ፊት ፊታቸው ይሄዳል፤ ያህዌ መሪያቸው ይሆናል፡፡
\s5
\c 3
\p
\v 1 ከዚያም እኔ እንዲህ አልሁ፤ «እናንተ የያዕቆብ መሪዎች የእስራኤልም ቤት ገዦች አድምጡ፤ ፍትሕን ማወቅ ይገባችሁ አልነበረምን?
\v 2 እናንተ ግን መልካሙን ጠላችሁ ክፉን ወደዳችሁ ቆዳቸውን ገፈፋችሁ ሥጋቸውን ከአጥንታቸው ጋጣችሁ የሕዝቤን ሥጋ በላችሁ ቆዳቸውን ገፈፋችሁ ዐጥንቶቻቸውን ሰባበራችሁ፤ በመጥበሻ እንደሚጠበስ በድስት እንደሚቀቀል ሥጋ ቆራረጣችኃቸው፡፡
\v 3 እናንተ መሪዎች ወደ ያህዌ ትጮኻላችሁ እርሱ ግን አይሰማችሁም፡፡ ከክፉ ሥራችሁ የተነሣ በዚያ ጊዜ ፊቱን ከእናንተ ይሰውራል፡፡
\s5
\v 4 ሕዝቤን ስለሚያስቱ ነቢያት ያህዌ እንዲህ ይላል፤
\s5
\v 5 «ጥቅም የሚያገኙበት ሲሆን፣ «ብልጽግና ይሆናል» ይላሉ፤ ጥቅም በማያገኙበት ጊዜ ግን፣ ‹ጦርነት ይመጣባችኃል› እያሉ በማወጅ ሕዝቡን ያስታሉ፡፡
\v 6 ስለዚህ ራእይ የማታዩበት ሌሊት ይሆንባችኃል ሌሊት ስለሚሆንባችሁ ንግርት አታደርጉም፡፡ በነቢያት ላይ ፀሐይ ትጠልቅባቸዋለች ቀኑ እነርሱ ላይ ይጨልማል፡፡
\v 7 ባለ ራእዮች ያፍራሉ ንግርተኞችም ይዋረዳሉ ከእኔ ዘንድ መልስ የለምና ሁሉም ፊታቸውን ይሸፍናሉ፡፡
\s5
\v 8 እኔ ግን፣ ለያዕቆብ በደሉን ለእስራኤል ኃጢአቱን እንድናገር በያህዌ መንፈስ ኃይል ተሞልቻለሁ ፍትሕና ብርታትንም ተሞልቻለሁ፡፡
\s5
\v 9 እናንት የያዕቆብ ቤት መሪዎች ፍትሕ የምትጠሉ፣ ቀና የሆነውን የምታጣምሙ የእስራኤል ቤት ገዦች ይህን ስሙ፡፡
\v 10 ጽዮንን ደም በማፍሰስ ኢየሩሳሌምን በርኩሰት የምትገነቡ ስሙ
\v 11 መሪዎቻችሁ በጉቦ ይፈርዳሉ ካህናቶቻችሁ በዋጋ ያስተምራሉ ነቢያቶቻችሁ በገንዘብ ንግርት ይናገራሉ፡፡ ያም ሆኖ በያህዌ በመተማመን፣ «ያህዌ ከእኛ ጋር ስለሆነ ክፉ ነገር አይደርስብንም» ይላሉ፡፡
\s5
\v 12 ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ጽዮን እንደ ማሳ ትታረሳለች፤ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች የቤተ መቅደሱ ኮረብታ ጥቅጥቅ ያለ ደን ይሆናል፡፡
\s5
\c 4
\p
\v 1 በመጨረሻው ዘመን የያህዌ ቤት ተራራ ሌሎች ተራቶች ላይ ይመሠረታል ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ይላል ሕዝቦችም ወደ እርሱ ይጐርፋሉ፡፡ ብዙ ሕዝቦች መጥተው እንዲህ ይላሉ
\s5
\v 2 «ኑ ወደ ያህዌ ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንሂድ እርሱ መንገዱን ያስተምረናል እኛም በመንገዱ እንሄዳለን፡፡ ሕግ ከጽዮን፣ የያህዌም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣል፡፡
\v 3 እርሱ በብዙ ሕዝብ መካከል ይፈርዳል በሩቅ ባሉ ሕዝቦችም ላይ ይበይናል፡፡ ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ያደርጉታል፡፡ መንግሥት በመንግሥት ላይ ሰይፍ አያነሣም፤ ከእንግዲህ የጦር ትምህርት አይማሩም፡፡
\s5
\v 4 ይልቁን፣ እያንዳንዱ ሰው ከገዛ ወይኑ ሥር ከገዛ በለሱም ሥር ይቀመጣል፡፡ የሰራዊት አምላክ ያህዌ ተናግሮአልና የሚያስፈራቸው አይኖርም፡፡
\v 5 ሕዝቦች ሁሉ በአምላኮቻቸው ስም ይሄዳሉ፡፡ እኛ ግን በአምላካችን በያህዌ ስም ለዘላለም እንሄዳለን
\s5
\v 6 በዚያ ቀን ይላል ያህዌ፣ አንካሳውን እሰበስባለሁ ስደተኞችና ሐዘንተኞች ያደረግኃቸውን እሰበስባለሁ፡፡
\v 7 አንካሳውን ወደ ተረፉት ወገኖች የተገፉትንም ወደ ብርቱ ሕዝብ እመልሳለሁ፤ እኔ ያህዌ በጽዮን ተራራ ከዘላለም እስከ ዘላለም እነግሣለሁ፡፡
\v 8 አንተ የመጠበቂያው ማማ፣ የጽዮን ሴት ልጅ አምባ የቀድሞው ግዛትህ፣ የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ መንግሥት ይመለስልሃል፡፡
\s5
\v 9 አሁንስ እንደዚህ የምትጮኺው ለምንድነው? በመካከልሽ ንጉሥ የለምን? ምጥ እንደ ያዛት ሴት የምትጨነቂው መካሪሽ ስለጠፋ ነውን?
\v 10 የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ ምጥ እንደያዛት ሴት ተጨነቂ፤ አሁን ከከተማ ወጥተሸ ሜዳ ላይ ስፈሪ ወደ ባቢሎንም ትሄጃለሽ፡፡ በዚያም ከጠላት እጅ ትድኛለሽ በዚያም እግዚአብሔር ከጠላቶችሽ ይታደግሻል፡፡
\s5
\v 11 አሁን ግን፣ ብዙ ሕዝቦች አንቺ ላይ ተሰብስበዋል እነርሱም፣ «የረከሰች ትሁን፤ እኛም መፈራረስዋን እንይ» ብለዋል፡፡
\v 12 ነቢዩ እንዲህ ይላል፤ «የያህዌን ሐሳብ አያወቁም የእርሱንም ዕቅድ አያስተውሉም፤ እርሱ ዐውድማ ላይ እንደ ነዶ ይሰበስባቸዋል፡፡»
\s5
\v 13 ያህዌ እንዲህ ይላል፤ «ቀንድሽን እንደ ብረት፣ ሰኮናሽን እንደ ናስ አደርጋለሁ ብዙ ሕዝቦችን ታደቂያለሽ የጽዮን ልጅ ሆይ፣ ተነሥተሸ አበራዪ፡፡ በግፍ የሰበሰቡትን ሀብት ለራሴ ሀብታቸውንም ለምድር ሁሉ ጌታ አቀርባለሁ፡፡»
\s5
\c 5
\p
\v 1 አንቺ የወታደር ከተማ ሰራዊትሽን አሰልፊ ከበባ ተደርጐብናልና የእስራኤልን ገዥ ጉንጩን በበትር ይመቱታል፡፡
\s5
\v 2 አንቺ ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፣ ከይሁዳ ነገዶች መካከል ትንሿ ብትሆኚም፣ ጅማሬው ከጥንት ከዘላለም ዘመናት የሆነ የእስራኤል ገዥ ከአንቺ ይወጣልኛል፡፡
\v 3 ስለዚህ ያማጠችው ልጅ እስክትወልድ ድረስ እግዚአብሔር ሕዝቡን ይተዋቸዋል የተቀሩት ወንድሞቹም ወደ እስራኤል ሕዝብ ይመለሳሉ፡፡
\s5
\v 4 በያህዌ ብርታት፣ በአምላኩ በያህዌ ስም ክብር ጸንቶ ይቆማል፤ መንጋውንም ይጠብቃል፡፡ በዚያ ጊዜ ታላቅነቱ እስከ ምድር ዳርቻ ስለሚደርስ ተደላድለው ይኖራሉ፡፡
\v 5 እርሱ ሰላማችን ይሆናል፡፡ አሦራውያን ወደ ምድራችን ሲመጡ ወደ ምሽጐቻችንም ሲገሠግሡ ሰባት እረኞችን፣ እንዲሁም ስምንት መሪዎችን እናስነሣባቸዋልን፡፡
\s5
\v 6 እነዚህ ሰዎች የአሦርን ምድር በሰይፍ፣ የናምሩዱንም ምድር እጃቸው ላይ ባለው ሰይፍ ይገዛሉ፡፡ ወደ ምድራችን ሲመጡ ወደ ድንበራችንም ሲገሠግሡ እርሱ ከአሦራውያን ይድነናል፡፡
\v 7 የያዕቆብ ትሩፍ በብዙ ሕዝብ መካከል ከያህዌ ዘንድ እንደሚወርድ ጠል፣ ሣር ላይ እንደሚጥል ካፊያ ሰውን እንደማይጠብቅ፣ በሰው ልጆችም እንደማይተማመን ሰው ይሆናል፡፡
\s5
\v 8 የያዕቆብ ትሩፍ በሕዝቦች መካከል፣ በብዙ ሕዝቦች መካከል ይሆናል፤ በዱር አራዊት መካከል እንዳለ አንበሳ፣ በበጐች መካከል እንዳለ አንበሳ ደቦል ይሆናል፡፡ በእግሩ እየረጋገጠ ይቦጫጭቃቸዋል፤ የሚያድናቸውም አይኖርም፡፡
\v 9 እጅህ በጠላቶችህ ላይ ከፍ ከፍ በማለት ያጠፋቸዋል፡፡
\s5
\v 10 በዚያ ቀን ይላል ያህዌ «ፈረሶቻችሁን ከመካከላችሁ አጠፋለሁ ሠረገሎቻችሁንም እደመስሳለሁ፡፡
\v 11 የምድራችሁን ከተሞች አጠፋለሁ ምሽጐቻችሁንም ሁሉ አፈርሳለሁ፡፡
\s5
\v 12 በምድራችሁ ያለውን ጥንቆላ አጠፋለሁ ከእንግዲህ አታሟርቱም፡፡
\v 13 የተቀረጹ ምስሎቻችሁንና የድንጋይ ዐምዶቻችሁን ከመካከላችሁ አጠፋለሁ፡፡ ከእንግዲህ የእጆቻችሁን ሥራ አታመልኩም፡፡
\v 14 የአሼራ ምሰሶዋችሁን ከምድራችሁ እነቅላለሁ ከተሞቻችሁንም አጠፋለሁ፡፡
\v 15 ያልታዘዙኝን ሕዝቦች በቀጣዬና በመዓቴ እበቀላሁ፡፡»
\s5
\c 6
\p
\v 1 እንግዲህ ያህዌ የሚናገረውን አድምጡ፤ «ተነሡ፤ ያላችሁንም ቅርታ በተራሮች ፊት አቅርቡ ኮረብቶችም የምትሉትን ይስሙ፡፡
\v 2 እናንተ ተራሮች እናንተ ጸንታችሁ የቆማችሁ የምድር መሠረቶች ያህዌ የሚያቀርበውን ክስ አድምጡ፤ እርሱ ከእስራኤል ጋር ይፋረዳል፡፡»
\s5
\v 3 «ሕዝቤ ሆይ፣ ምን አደረግሁህ? ያታከትሁህስ በምንድነው? እስቲ መስክርብኝ!
\v 4 እኔ ከግብፅ ምድር አወጣሁህ ከባርነት ቤትም ታደግሁህ፡፡ ሙሴን፣ አሮንንና ማርያምን ወደ አንተ ላክሁ፡፡
\v 5 ሕዝቤ ሆይ፣ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ ያቀደብህን የቢዖር ልጅ በለዓም የመለሰለትን፣ ከሺጡም ተነሥተህ ወደ ጌልጌላ ስትሄድ፣ እኔ፣ ያህዌ ያደረግሁትን የጽድቅ ሥራ ታውቅ ዘንድ አስታወስ፡፡
\s5
\v 6 ለልዑል አምላክ ለመስገድ በምመጣበት ጊዜ፣ ለያህዌ ምን ይዤ ልምጣ? የሚቃጠል መሥዋዕት እንዲሆኑ የአንድ ዓመት ጥጃ ይዤ ልምጣን?
\v 7 በሺህ የሚቆጠሩ ዐውራ በጐችን ወይስ የአሥር ሺህ ወንዞች የሚያህል ዘይት ባቀርብለት ያህዌ ይደሰት ይሆን? ስለ መተላለፌ የበኩር ልጄን፣ ስለ ኃጢአቴስ የአካሌን ፍሬ ልስጥን?
\v 8 ሰው ሆይ፣ መልካሙን፣ ያህዌ ከአንተ የሚፈልገውን ነግሮሃል ፍትሕ አድርግ፤ ደግነትን ውደድ፤ ከአምላክህ ጋር በትሕትና ተመላለስ፡፡
\s5
\v 9 የያህዌ ድምፅ ከተማዋን ይጣራል አሁን እንኳ ጥበብ ስምህን ትገነዘባለች በትሩን አስታውስ፤ በቦታው ያደረገው ማን እንደ ሆነ አስታውስ፡፡
\v 10 ክፉው ቤት ውስጥ በግፍ የተገኘ ሀብት አስጸያፊ የሆነ ሐሰተኛ መስፈሪያ አለ፡፡
\s5
\v 11 ዐባይ ሚዛን የሚጠቀመውን ሰው፣ ሐሰተኛ መመዘኛ በከረጢት የቋጠረውን ሰው ንጹሕ ላድርገውን?
\v 12 ባለ ጠጐች በግፍ ተሞልተዋል በዚያ የሚኖሩ ሐሰት ተናግረዋል ምላሳቸው አታላይ ናት፡፡
\s5
\v 13 ስለዚህ በጽኑ ቁስል መታሁህ ከኃጢአትህ የተነሣም አፈረስሁህ፡፡
\v 14 ትበላለህ ግን አትጠግብም ሁሌም ባዶነት ውስጥህ ይኖራል፡፡ ታከማቻለህ ግን አይጠራቀምልህም ያጠራቀምኸውን ለሰይፍ እዳርጋለሁ፡፡
\v 15 ትዘራለህ ግን አታጭድም የወይራ ፍሬ ትጨምቃለህ፤ ግን ዘይት አትቀባም፤ ወይን ትጨምቃህ ግን ጠጅ አትጠጣም፡፡
\s5
\v 16 የዖምሪን ሥርዐት የአክዓብን ቤት ተግባርም አጥብቀህ ይዘሃል በምክራቸው መሠረት ኖረሃል፡፡ ስለዚህ አንተንና ከተማህን ለውድመት ሕዝብህንም ለመዘባበቻ አሳልፌ እሰጣለሁ በሕዝቤ ላይ የተሰነዘረውን ነቀፋ ትሸከማለህ፡፡
\s5
\c 7
\p
\v 1 ለእኔ ወዮልኝ! የመከር ጊዜ ፍሬ ተሰብስቦ የወይኑም ቃርሚያ ካበቃ በኃላ እርሻ ውስጥ እንደ ቀረው ፍሬ ሆኛለሁ ከዚያ የሚበላ ወይን ፍሬ አይገኝም የምጓጓለትና ቶሎ ቀድሞ የሚደርሰው በለስ አይኖርም፡፡
\v 2 ከምድሩ ታማኝ ሰዎች ጠፍተዋል በሰው ልጆች መካከልም ቅን ሰው የለም፡፡ ሁሉም ደም ለማፍሰስ ያደባል እያንዳንዱም የገዛ ወንድሙን በመረብ ያጠምዳል፡፡
\s5
\v 3 እጆቻቸው ሌሎችን ለመጉዳት ሠልጠነዋል፤ ገዦቻቸው ገንዘብ ይፈልጋሉ ፈራጁ ጉቦ ይጠብቃል፤ ኃይለኞች ያሻቸውን ያስፈጽማሉ ሁሉም አንድ ላይ ያሤራሉ፡፡
\v 4 ከእነርሱ ይሻላል የተባለው እንደ አሜኬላ እጅግ ቀና የተባለውም እንደ ኩርንችት ነው፡፡ ነቢያቶቻችሁ አስቀድመው የተናገሩለት ቀን እናንተ የምትቀጡበት ቀን ነው፡፡ የሚሸበሩበት ቀን ደርሶአል፡፡
\s5
\v 5 ጐረቤትህን አትመን፣ ወዳጅህም ላይ አትተማመን፡፡ በዕቅፍህ ከምትተኛዋ እንኳ ለምትናገረው ተጠንቀቅ፡፡
\v 6 ወንድ ልጅ አባቱን ያዋርዳል ሴት ልጅ በእናትዋ ላይ ምራት በአማቷ ላይ ትነሣለች፡፡ የሰው ጠላቶች የገዛ ቤተ ሰቦቹ ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 7 እኔ ግን ያህዌን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ የመድኃኒቴን አምላክ እጠብቃለሁ አምላኬም ይሰማኛል፡፡
\v 8 ጠላቴ፣ ሆይ ብወድቅ እንኳ በእኔ ደስ አይበልሽ፤ ከወደቅሁበት እነሣለሁ በጨለማ ብቀመጥ እንኳ ያህዌ ብርሃን ይሆንልኛል፡፡
\s5
\v 9 ያህዌን ስለ በደልሁ እርሱ እስኪፈርድልኝ ድረስ ቁጣውን እታገሣለሁ፡፡ እርሱ ወደ ብርሃን ያወጣኛል በጽድቁ ሲያድነኝም አያለሁ
\s5
\v 10 ጠላቴም ታያለች፣ «አምላክህ ያህዌ የታል?» ያለች ጠላቴ ታፍራለች፡፡ እኔም የጠላቴን ውድቀት አያለሁ፤ መንገድ ላይ እንዳለ ጭቃ ትረገጣለች፡፡
\s5
\v 11 ቅጥሮቻችሁን የምትሠሩበት ቀን ይመጣል በዚያን ቀን ድንበራችሁ ይሰፋል!
\v 12 በዚያ ቀን ሕዝባችሁ ወደ እናንተ ይመለሳል፤ ከአሦርና ከግብፅ ከተሞች ከግብፅ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ከባሕር እስከ ባህር፣ ከተራራ እስከ ተራራ ድረስ ሕዝባችሁ ወደ እናንተ ይመለሳል፡፡
\v 13 ከሚኖሩበት ሰዎች ክፋት የተነሣ ምድሪቱ ወና ትሆናለች፡፡
\s5
\v 14 በለመለመ መስክ መካከል ብቻቸውን ዱር ውስጥ ያሉትን የርስትህ መንጋ የሆኑት ሕዝብህን በበትርህ ጠብቅ፡፡ እንደ ቀድሞው ዘመን በባሰንና በገለዓድ አሰማራቸው፡፡
\v 15 ከግብፅ እንደ ወጣችሁበት ዘመን ድንቆችን አሳያቸዋለሁ፡፡
\s5
\v 16 ኃይል ያላቸው ቢሆኑም አሕዛብ ይህን አይተው ያፍራሉ፤ እጃቸውን አፋቸው ላይ ያደርጋሉ ጆሮዋቸውም ይደነቁራል፡፡
\v 17 እንደ እባብ፣ ምድር ላይ እንደሚርመሰመሱም ፍጥረቶች ትቢያ ይልሳሉ፡፡ እየተንቀጠቀጡ ከዋሻዎቻቸው ይወጣሉ አምላካችን ያህዌ ሆይ በፍርሃት ወደ አንተ ይመጣሉ ከአንተ የተነሣ ይሸበራሉ፡፡
\s5
\v 18 ኃጢአትን ይቅር የሚል የርስቱንም ትሩፍ መተላለፍ የሚምር እንደ አንተ ያለ አምላክ ማነው? የኪዳን ታማኝነትህን ለእኛ ማሳየት ደስ ስለሚልህ አንተ ለዘላለም አትቆጣም፡፡
\s5
\v 19 እንደ ገና ትራራልናለህ፤ ርኩሰታችንን በእግሮችህ ትረግጣለህ፡፡ ኃጢአታችንን ሁሉ ወደ ባሕሩ ጥልቅ ትጥላለህ፡፡
\v 20 በቀድሞ ዘመን ለአባቶቻችን በመሐላ እንደ ገባኸው ቃል ለያዕቆብ ታማኝነትን፣ ለአብርሃምም የኪዳን ታማኝነትን ትሰጣለህ፡፡