am_ulb/32-JON.usfm

108 lines
9.7 KiB
Plaintext

\id JON
\ide UTF-8
\h ዮናስ
\toc1 ዮናስ
\toc2 ዮናስ
\toc3 jon
\mt ዮናስ
\s5
\c 1
\p
\v 1 የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲል መጣ፤
\v 2 «ተነሣና ወደ ታላቋ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ ክፏቷ ወደ ፊቴ ወጥቶአልና በእርሷ ላይ ስበክ፡፡»
\v 3 ዮናስ ግን ከያህዌ ፊት ኮበለለ፤ ወደ ተርሴስ ለመሄድም ተነሣ፡፡ ወደ ኢዮጴ ወረደ፡፡ ወደ ተርሴስ በምትሄድ መርከብ ተሳፈረ፡፡
\s5
\v 4 ያህዌ ግን በባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስ ላከ፤ ከባድ ማዕበልም ተነሥቶ መርከቧን አናወጠ፤ ወዲያውኑ የምትሰበር መስሎ ታየ፡፡
\v 5 መርከበኞቹ በጣም ፈሩ፤ እያንዳንዱ ሰው ወደ አምላኩ ጮኸ ፡፡ የመርከቧ ክብደት እንዲቀልል በውስጧ የነበረው ሸክም ወደ ባሕሩ ተጣለ፡፡ ዮናስ ግን ወደ መርከቧ ታችኛ ክፍል ሄዶ ተኛ፤ ከባድ እንቅልፍ ላይም ነበር፡፡
\s5
\v 6 የመርከቧ አዛዥ ወደ እርሱ መጥቶ፣ «እንዴት ትተኛለህ? ተነሥና አምላክህን ጥራ! ምናልባትም አምላክህ ያስበንና ከጥፋት ያድነን ይሆናል፡፡ አለው፡፡
\v 7 እርስ በርሳቸውም፣ ይህ ክፉ ነገር የደረሰብን በማን ኃጢአት መሆኑን እንድናውቅ ኑ፣ ዕጣ እንጣጣል» ተባባሉ፡፡ ዕጣ ተጣጣሉ፤ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ፡፡
\s5
\v 8 ከዚያም ዮናስን፣ «ይህ ክፉ ነገር የደረሰብን በማን ምክንያት እንደ ሆነ እባክህ ንገረን፡፡ ሥራህ ምንድነው? ከወዴትስ መጣህ? አገርህ የት ነው? ከየትኛውስ ሕዝብ ነህ?» አሉት፡፡
\v 9 ዮናስም፣ «እኔ ዕብራዊ ነኝ፤ ባሕሩንና ደረቁን ምድር የፈጠረውን የሰማይን አምላክ ያህዌን አመልካለሁ» አላቸው፡፡
\v 10 እርሱ ራሱ ነግሮአቸው ስለ ነበር ከያህዌ ፊት እየኮበለለ እንደ ነበር አወቁ፤ ስለዚህ የበለጠ ፈርተው፣ «ለመሆኑ፣ ምን እያደረግህ ነው?» አሉ፡፡
\s5
\v 11 ባሕሩ ይበልጥ እየተናወጠ በመሄዱ፣ ሰዎቹ ዮናስን፣ «ባሕሩ ጸጥ እንዲልልን አንተ ላይ ምን ብናደርግ ይሻላል?» አሉት፡፡
\v 12 ዮናስም፣ «አንሥታችሁ ወደ ባሕሩ ጣሉኝ፤ ያኔ ባሕሩ ጸጥ ይልላችኃል፤ ይህ ታላቅ ማዕበል የመጣባችሁ በእኔ ምክንያት እንደ ሆነ አውቃለሁ» አላቸው፡፡
\v 13 ሰዎቹ ግን ወደ መሬት ለመመለስ የሚቻላቸውን ያህል ቀዘፉ፤ ይሁን እንጂ ባሕሩ የባሰ ይናወጥ ጀመረ፡፡
\s5
\v 14 ስለዚህም፣ «ያህዌ ሆይ፣ በዚህ ሰው ነፍስ ምክንያት እንዳታጠፋን እንለምንሃለን፤ የዚህ ሰው ሞት እኛ ላይ አይሁንብን፤ ምክንያቱም አንተ ያህዌ የወደድኸውን አድርገሃል» በማለት ወደ ያህዌ ጮኹ፡፡
\v 15 ዮናስንም አንሥተው ወደ ባሕሩ ጣሉት፤ ባሕሩም መናወጡ ቆመ፡፡
\v 16 ሰዎቹም ያህዌን እጅግ ፈሩ፡፡ ለያህዌ መሥዋዕት አቀረቡ፤ ለእርሱም ስእለትን ተሳሉ፡፡
\s5
\v 17 እግዚአብሔር ግን ዮናስን የሚውጥ ትልቅ ዓሣ አዘጋጀ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ዓሣው ሆድ ውስጥ ኖረ፡፡
\s5
\c 2
\p
\v 1 ከዚያም ዮናስ ዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ ያህዌ ጸለየ፡፡
\v 2 እንዲህ አለ፤ «ተጨንቄ ሳለሁ ወደ ያህዌ ተጣራሁ፤ እርሱም መለሰልኝ፤ እርሱ እንዲረዳኝ ከጥልቁ መቃብር ጮኽኩ አንተም ጩኸቴን ሰማህ፡፡
\s5
\v 3 ጥልቅ ወደ ሆነው ወደ ባሕሩ መሠረት ጣልኸኝ፤ ፈሳሾች ዙሪያዬን ከበቡኝ፣ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላየ አለፈ፡፡
\v 4 እኔም፣ ከፊትህ ጠፋሁ፤ ሆኖም፣ እንደ ገና ወደ ቅዱስ መቅደስህ እመለከታለሁ» አልሁ፡፡
\s5
\v 5 ሕይወቴን ለማጥፋት ውሆች ሸፈኑኝ፤ ጥልቁም በዙሪያዬ ነበረ፤ የባሕር ዐረም ራሴ ላይ ተጠመጠመ፡፡
\v 6 ወደ ተራሮች መሠረት ሰመጥሁ የምድርም በር ለዘላለም ተዘጋብኝ፤ ያህዌ አምላኬ ሆይ፣ አንተ ሕይወቴን ከጥልቁ አወጣህ!
\s5
\v 7 ነፍሴ በዛለች ጊዜ ያህዌን አሰብሁት፤ ጸሎቴ ወደ አንተ ወደ ቅዱስ መቅደስህ መጣ፤፤
\v 8 ልባቸውን ከንቱ አማልከት ላይ የሚያደርጉ ለእነርሱ ያለህን ጸጋ ያጣሉ፡፡
\s5
\v 9 እኔ ግን፣ በምስጋና መዝሙር መሥዋዕት አቀርብልሃለሁ፤ የተሳልሁትንም እፈጽማለሁ፡፡ ድነት ከያህዌ ዘንድ ነው፡፡
\v 10 ከዚም ያህዌ ዓሣውን አዘዘ ዮናስንም ደረቁ ምድር ላይ ተፋው፡፡
\s5
\c 3
\p
\v 1 የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ዮናስ መጣ፤
\v 2 «ተነሥተህ ወደ ታላቋ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ እኔ የምነግርህንም መልእክት ስበክላት፡፡»
\v 3 ስለዚህም ዮናስ ለያህዌ ቃል በመታዘዝ ወደ ነነዌ ሄደ፡፡ ነነዌ ታላቅ ከተማ ነበረች፤ እርሷን ዳር እስከ ዳር ለማዳረስ ሦስት ቀን ይወስድ ነበር፡፡
\s5
\v 4 ዮናስ ወደ ከተማዋ ገባ፤ ከአንድ ቀን ጉዞ በኃላ፣ «ነነዌ በአርባ ቀን ውስጥ ትገለበጣለች» ብሎ ዐወጀ፡፡
\v 5 የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ጾምንም ዐወጁ፡፡ ከታላቁ እስከ ታናሹ ድረስ ሁሉም ማቅ ለበሱ፡፡
\s5
\v 6 ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ በደረሰ ጊዜ፣ ከዙፋኑ ወረደ፤ ልብሱን አወለቀ፣ ማቅም ለብሶ ዐመድ ላይ ተቀመጠ፡፡
\v 7 ከዚያም እንዲህ የሚል ዐዋጅ በነነዌ አስነገረ፤ «በንጉሡና በመኳንንቱ» ሥልጣን ከነነዌ የወጣ ዐዋጅ፤ ሰውም ሆነ እንስሳ፣ የከብት መንጋም ሆነ የበግ ምጋ ምንም ነገር አይቅመስ አይብላ ውሃም አይጣጣ፡፡
\s5
\v 8 ሰውም ሆነ እንስሳ ማቅ ይልበስ፤ አጥብቆ ወደ እግዚአብሔር ይጮኽ፡፡ ሰው ሁሉ ከክፉ መንገዱ ይመለስ፤ ግፍ መሥራቱንም ይተው፡፡
\v 9 እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ራርቶ ከጽኑ ቁጣው ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?»
\s5
\v 10 እግዚአብሔርም ያደረጉትን፣ ከክፉ መንገዳቸው መመለሳቸውንም አየ፡፡ በእነርሱ ላይ ሊያመጣ ያሰበውንም ጥፋት አላመጣም፡፡
\s5
\c 4
\p
\v 1 ይህ ግን ዮናስን ደስ ስላላሰኘው በጣም ተቆጣ፡፡
\v 2 እንዲህ በማለትም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ «ያህዌ ሆይ፣ ገና በአገሬ ሳለሁ ያልሁት ይህንኑ አልነበረምን? አንተ ቸርና ርኅሩኅ አምላክ፣ ለቁጣ የዘገየህ ምህረትህም የበዛ፣ ጥፋትን ከማምጣት የምትመለስ አምላክ መሆንህን ስለማውቅ ወደ ተርሴስ ለመኮብለል የሞከርኩት በዚሁ ምክንያት ነበር፡፡
\v 3 አሁንም ያህዌ ሆይ፣ ሕይወቴን እንድትወስድ እለምንሃለሁ፣ በሕይወት ከመኖር መሞት ይሻለኛል» አለ፡፡
\s5
\v 4 ያህዌ ግን፣ «መቆጣትህ ተገቢ ነውን?» አለው፡፡
\v 5 ከዚያም ዮናስ ከከተማዋ ወጥቶ በስተ ምሥራቅ በኩል ተቀመጠ፡፡ በዚያም ለራሱ ዳስ ሠርቶ በከተማዋ የሚደርሰውን ለማየት ከጥላው ሥር ተቀመጠ፡፡
\s5
\v 6 ያህዌ አምላክም አንድ ተክል አብቅሎ፣ የዮናስ ራስ ጥላ እንዲሆንና ትኩሳቱም እንዳያስጨንቀው ከበላዩ እንዲያድግ አደረገ፤ ዮናስም ስለ ተክሉ በጣም ደስ አለው፡፡
\v 7 ነገር ግን በሚቀጥለው ጠዋት ፀሐይ ስትወጣ አንድ ትል አዘጋጅቶ ያንን ተክል እንዲያጠቃ አደረገ፤ ተክሉም ጠወለገ፡፡
\s5
\v 8 ፀሐይ ስትወጣ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ አመጣ፡፡ ፀሐዩ የዮናስንም ራስ አቃጠለ እርሱም ተዝለፈለፈ፡፡ ያኔ ዮናስ መሞት ፈልጐ፣ «ከመኖር መሞት ይሻለኛል» አለ፡፡
\v 9 እግዚአብሔርም ዮናስን፣ «ስለ ተክሉ መቆጣትህ ተገቢ ነውን?» አለው፡፡ ዮናስም፣ «አዎን፣ እንዲያውም እስከ ሞት ድረስ መቆጣት ይገባኛል» አለ፡፡
\s5
\v 10 ያህዌ እንዲህ አለ፣ «አንተ እንዲበቅል ወይም እንዲያድግ ላልደከምህበት ተክል ይህን ያህል አዝነሃል፤ በአንድ ሌሊት በቀለ፤ በአንድ ሌሊትም ደረቀ፡፡
\v 11 ታዲያ፣ እኔ ቀኝና ግራቸውን ለይተው መናገር የማይችሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺህ በላይ ሰዎችና እንስሶች ለሚኖሩባት ለታላቋ ከተማ ለነነዌ ማዘን የለብኝምን? ፡፡»