am_ulb/31-OBA.usfm

51 lines
4.9 KiB
Plaintext

\id OBA
\ide UTF-8
\h ትንቢተ አብድዩ
\toc1 ትንቢተ አብድዩ
\toc2 ትንቢተ አብድዩ
\toc3 oba
\mt ትንቢተ አብድዩ
\s5
\c 1
\p
\v 1 የአብድዩ ራእይ። ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶም እንዲህ ይላል፦ከእግዚአብሔር ዘንድ መልእክት ሰምተናል፥ መልእክተኛውም በአሕዛብ መካከል ተልኮ፥«ተነሡ! እርሷን ለመውጋት እንነሣ» ብሎአል።
\v 2 አነሆ፥ በአሕዛብ መካከል ታናሽ አደርግሃለሁ፥እጅግ የተናቅህ ትሆናለህ።
\s5
\v 3 አንተ በዓለት ስንጣቂ ውስጥ፥በከፍታ ሥፍራ በሚገኝ ቤት የምትኖር፥ በልብህም «ማን ወደ ምድር ያወርደኛል?» የምትል ሆይ፥የልብህ ኩራት አታልሎሃል።
\v 4 እንደ ንስር እጅግ ከፍ ከፍ ብትል እንኳ፥ጎጆህም በከዋክብት መካከል ቢሆን እንኳ፥እኔ ከዚያ አወርድሃለሁ ይላል እግዚአብ ሔር።
\s5
\v 5 ሌቦች ወደ አንተ ቢመጡ፥ዘራፊዎች በሌሊት ቢመጡ (አንተ እንዴት ተቆረጥህ!) ፥የሚበቃቸውን ያህል ብቻ የሚሰርቁ አይደለምን? ወይን ለቃሚዎች ወደ አንተ ቢመጡ ቃርሚያ አያስቀሩምን?
\v 6 ዔሳው ምንኛ ተበረበረ፥የተደበቀ ሀብቱ ምንኛ ተዘረፈ?
\s5
\v 7 የተማማልሃቸው ሰዎች፥በጉዞህ ወደ ድንበር ይሰድዱሃል።ከአንተ ጋር መልካም ግንኙነት የነበራቸው ሰዎች አታለሉህ፥አሸነፉህም። እንጀራህን የበሉ ከበታችህ ወጥመድ ዘረጉብህ። በእርሱም ዘንድ ማስተዋል የለም።
\v 8 በዚያ ቀን ከኤዶም ጥበበኞችን፥ ከዔሳውም ተራራ ማስተዋልን አላጠፋምን? ይላል እግዚአብሔር።
\v 9 ቴማን ሆይ፥ ሰው ሁሉ ከዔሳው ተራራ ታርዶ ይጠፋ ዘንድ፤፡ኃያላንህ ይደነግጣሉ።
\s5
\v 10 በወንድምህ በያዕቆብ ላይ ስለ ተፈጸመ ግፍ፥እፍረት ይከድንሃል፥ለዘላለምም ትጠፋለህ።
\v 11 እንግዶች ሀብቱን በዘረፉበት፥ባዕዳንም በበሮቹ በገቡበት፥በኢየሩሳሌምም ላይ ዕጣ በተጣጣሉበት ቀን፤አንተም ገለልተኛ ሆነህ በቆምህበት ቀን፥ ከእነርሱ እንደ አንዱ ሆነሃል።
\s5
\v 12 ነገር ግን ወንድምህ በገጠመው ክፉ ቀን ሐሴት ማድረግ አይገባህም ነበር፥በጥፋታቸው ቀን በይሁዳ ሕዝብ ላይ መደሰት አይገ ባህም ነበር፤በጭንቀታቸው ቀን ትኩራራ ዘንድ አይገባህም ነበር።
\v 13 በጥፋታቸው ቀን በሕዝቤ በር ትገባ ዘንድ አይገባህም ነበር፥በጥፋታቸው ቀን በመ ከራቸው ሐሴት ማድረግ አይገባህም ነበር፤በጥፋታቸው ቀን ሀብታቸውን መዝረፍ አይገባህም ነበር።
\v 14 የሸሹትን ለመግደል በመስቀለኛ መንገድ ላይ ትቆም ዘንድ አይገባህም ነበር፤በጭንቀት ቀን የተረፉለትን አሳልፈህ መስጠት አይገባህም ነበር።
\s5
\v 15 የእግዚአብሔር ቀን በአሕዛብ ሁሉ ላይ ቀርቦአልና። እንዳደረግኽው እንዲሁ ይደረግብሃል፥ ሥራህ በገዛ ራስህ ላይ ይመለሳል።
\v 16 በቅዱስ ተራራዬ ላይ እንደጠጣችሁ፥ አሕዛብ ሁሉ ዘወትር ይጠጣሉ። ይጠጣሉ፥ ይጨልጡማል፤ ከዚህ በፊት እንዳልሆኑት ይሆናሉ።
\s5
\v 17 በጽዮን ተራራ ያመለጡ ይገኛሉ፥ እርሱም ቅዱስ ይሆናል፤ የያዕቆብም ቤት የገዛ ራሱን ርስት ይወርሳል።
\v 18 የያዕቆብ ቤት እሳት፥ የዮሴፍ ቤት ነበልባል፥ የዔሳውም ቤት ገለባ ይሆናሉ፤ያቃጥሉታል፥ይበሉታልም። ከኤሳው ቤት የሚተርፍ አይኖርም፥እግዚአብሔር ተናግሮአልና።
\s5
\v 19 የኔጌብ ሰዎች የዔሳውን ተራራ ይወርሳሉ፥የቆላውም ሰዎች፦የፍልስጥኤማውያንን ምድር፥የኤፍሬምን ምድር፥ የሰማሪያንም ምድር ይወርሳሉ፤ብንያምም ገለዓድን ይወርሳል።
\s5
\v 20 የእስራኤል ሕዝብ ሠራዊት ምርኮኞች የከንዓንን ምድር እስከ ሰራጵታ ድረስ ይወርሳሉ። በስፋራድም የሚኖሩ የእስራኤል ምርኮኞች የኔጌብን ከተሞች ይወርሳሉ።
\v 21 በዔሳው ተራራ ላይ ይፈርዱ ዘንድ ነጻ አውጪዎች ወድ ጽዮን ተራራ ይወጣሉ፤ መንግሥቱም የእግዚአብሔር ይሆናል።