am_ulb/30-AMO.usfm

326 lines
33 KiB
Plaintext

\id AMO
\ide UTF-8
\h አሞጽ
\toc1 አሞጽ
\toc2 አሞጽ
\toc3 amo
\mt አሞጽ
\s5
\c 1
\p
\v 1 በቴቁሔ ከነበሩት እረኞች መካከል አንዱ የሆነው አሞጽ፥ ስለ እስራኤል በራዕይ የተቀበላቸው ነገሮች አነዚህ ናቸው። እነዚህንም ነገሮች በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ዘመነ መንግሥት፥በእስራኤል ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት፥የምድርም መናወጥ ከመሆኑ ከሁለት ዓ መት አስቀድሞ ተቀበለ።
\v 2 እንዲህም አለ፥«እግዚአብሔር ከጽዮን ይጮኻል፥ ከኢየሩሳሌምም ድምጹን ከፍ አድርጎ ያሰማል። የእረኞች ማሰማሪያ ዎች ያለቅሳሉ፥የቀርሜሎስም ራስ ይደርቃል።»
\s5
\v 3 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«ገልዓድን በብረት መሣሪያ አድቅቋልና፤ ስለ ደማስቆ ሦሥት ኃጢአቶች፥ይልቁንም ስለ አራቱ ፥ ቅጣቴን አልመልስም።
\v 4 በአዛሄል ቤት ላይ እሳት እልካለሁ፥ የወልደ አዴርንም ምሽጎች ትበላለች።
\s5
\v 5 የደማስቆን በር መቀርቀሪያዎች እሰብራኣለሁ፥በአዌን ሸለቆ የሚኖረውን ሰውና በቤተ ኤደንም በትረ መንግሥት የያዘውን ሰው ድል ነሳለሁ፤ የሶርያም ሕዝብ ተማርኮ ወደ ቂር ይሄዳል» ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 6 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«ለዔዶም አሳልፈው ሊሰጧቸው ሕዝቡን ሁሉ ማርከው ወስደዋልና፤ ስለ ጋዛ ሦሥት ኃጢአቶች፥ ይልቁን ም ስለ አራቱ ፥ ቅጣቴን አልመልስም።
\v 7 በጋዛ ቅጥሮች ላይ እሳት እልካልሁ፥ምሽጎቹዋንም ይበላል።
\s5
\v 8 በአሽዶድ የሚኖረውንና በአስቀሎና በትረ መንግሥት የያዘውን ሰው አጠፋለሁ። እጄን በአቃሮን ላይ እመልሳለሁ፥ የቀሩት ፍልስጤማውያንም ይጠፋሉ»ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 9 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«የሕዝብን ወገኖች ሁሉ ለኤዶም አሳልፈው ሰጥተዋልና የወንድማማችነትንም ኪዳን አፍርሰዋልና፥ ስለ ጢሮስ ሦሥት ኃጢአቶች፥ ይልቁንም ስለ አራቱ፥ ቅጣቴን አለመልስም።
\v 10 በጢሮስ ቅጥሮች ላይ እሳት እልካለሁ፥ምሽጎችዋንም ሁሉ ይበላል።»
\s5
\v 11 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ «ወንድሙን በሰይፍ አሳድዶታልና፥ ርኅራኄንም ሁሉ ጥሎአልና፥ ቁጣው ሳያቋርጥ ነዶአልና፥ ቁጣው ለዘላለም ነውና፤
\v 12 በቴማን ላይ እሳት እልካለሁ፥ የባሶራንም አብያተ መንግሥት አጠፋለሁ።»
\s5
\v 13 እግዚእብሔር እንዲህ ይላል፦«ድንበሩን ለማስፋት የገለዓድን እርጉዝ ሴቶች ቀድዶአልና፤ ስለ አሞን ሕዝብ ሦሥት ኃጢአቶች፥ ይልቁንም ስለ አራቱ፥ ቅጣቴን አልመልስም።
\s5
\v 14 በረባት ቅጥሮች ላይ እሳት አነድዳለሁ፥ በጦርነት ቀን ከጩኽት ጋር፥ በአውሎ ነፋስም ቀን ከማዕበል ጋር፤ አብያተ መንግሥትን ይበላል።
\v 15 ንጉሣቸው ከአለቆቻቸው ጋር ወደ ምርኮ ይሄዳል» ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\c 2
\p
\v 1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ «አመድ እስኪሆን ድረስ የኤዶምን ንጉሥ አጥንት አቋጥሏልና፤ ስለ ሞዓብን ሦሥት ኃጢአቶች፥ይልቁንም ስለ አራቱ፥ ቅጣቴን አልመልስም።
\s5
\v 2 በሞዓብ ላይ እሳት እልካለሁ፥ የቂርዮትንም ምሽጎች ይበላል። ሞዓብ በጩኽትና በመለከትድምጽ፥ በሁካታ ውስጥ ይሞታል።
\v 3 በውስጧ የሚገኝውን ፈራጁን አጠፋለሁ፥ መሳፍንቱን ሁሉ ከእርሱ ጋር እገድላለሁ» ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 4 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ «የእግዚአብሔርን ሕግ ጥለዋልና፥ ትእዛዙንም አለጠበቁምና ስለ ሦሥት የይሁዳ ኃጢአቶች፥ይልቁንም ስል አራቱ፥ ቅጣቴን አልመልስም። ሐሰታቸው አስቷቸዋልና፥በዚሁ መንገድ አባቶቻቸውም ሄዱ።
\v 5 እሳት በይሁዳ ላይ እልካለሁ፥ የኢየሩሳሌምንም ምሽጎች ይበላል።
\s5
\v 6 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«ንጹሑን ስለ ብር፥ ችግረኛውንም ስለ ጥንድ ጫማ ሽጠዋልና ፤ስለ እስራኤል ሦሥት ኃጥአቶች፥ ይልቁንም ስለ አራቱ፥ ቅጣቴን አልመልስም።
\s5
\v 7 ሰዎች በምድር ላይ ትቢያን እንደሚረግጡ፥ የድኾችን ራስ ይረግጣሉ፤ የተጨቆኑትን ይገፋሉ። አባትና ልጅ ከአንዲት ሴት ጋር ይተኛሉ፥ ቅዱስ ስሜንም ያረክሳሉ።
\v 8 በየመሠዊያው አጠገብ በመያዣነት በተወሰደ ልብስ ላይ ይተኛሉ፥በአምላካቸውም ቤት በመቀጫነት የተወሰደውን ወይን ጠጅ ይጠጣሉ።
\s5
\v 9 ነገር ግን ቁመታቸው እንደ ዝግባ፥ጥንካሬያቸው እንደ ባሉጥ ዛፍ የነበረውን አሞራዊያንን ከፊታችው አጠፋሁ። ከላይ ፍሬውን፥ ከታችም ሥሩን አጠፋሁ።
\v 10 የአሞራውያንን ምድር እንድትወርሱ እናንተን ከግብፅ አወጣሁ፤ በምድረ በዳ አርባ ዓመት መራሁዋችሁ።
\s5
\v 11 ነቢያትን ከወንዶች ልጆቻችሁ፥ናዝራዊያንንም ከጎልማሶቻችሁ መካከል አስነሳሁ። የእስራኤል ህዝብ ሆይ፥ይህ እንደዚህ አይደለም ን? ይላል እግዚአብሔር።
\v 12 «እናንተ ግን ናዝራዊያንን የወይን ጠጅ ይጠጡ ዘንድ አሳባቸውን አስለወጣችሁ፥ነቢያቱንም እንዳይተነብዩ አዘዛችኋቸው።
\s5
\v 13 እነሆ፥በእህል የተሞላ ሰረገላ ሰውን እንደሚያደቅቅ እንዲሁ አደቅቃችኋለሁ።
\v 14 ፈጣኑ ሰው አያመልጥም፥ብርቱው ለራሱ ብርታትን አይጨምርም፥ኃያልም ራሱን አያድንም።
\s5
\v 15 ቀስተኛው አይቆምም፥ፈጣኑ ሯጭ አያመልጥም፥ፈረሰኛውም ራሱን አያድንም።
\v 16 ጅግኖቹ ተዋጊዎች እንኳን በቀን ዕርቃናቸውን ይሸሻሉ፤ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»
\s5
\c 3
\p
\v 1 የእስራኤል ሕዝብ፥ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ ወገኖች ሁሉ፥እግዚአብሔር በእናንተ ላይ የሚናገረውን ይህን ቃል ስሙ፤
\v 2 ከምድር ወገኖች ሁሉ እናንተን ብቻ መረጥሁ። ስለዚህ ስለ ኃጢአታችሁ ሁሉ እቀጣችኋለሁ።
\s5
\v 3 ሁለቱ ካልተስማሙ በስተቀር አብረው ይሄዳሉን?
\v 4 አንበሳ የሚሰብረውን ሳያገኝ በጫካ ውስጥ ያገሳልን? የአንበሳ ደቦል ምንም ሳይዝ በዋ ሻው ውስጥ ያጉተመትማልን?
\s5
\v 5 ማታለያ ምግብ ካልተዘጋጀለት በስተቀር ወፍ በምድር ወጥመድ ዉስጥ ይገባልን? አንዳች ሳይዝ ወጥመድ ከምድር ይፈናጠራልን?
\v 6 በከተማ ውስጥ መለከት ሲነፋ ሕዝቡ አይፈራምን? በከተማ ላይ ጥፋት ከመጣ የላከው እግዚአብሔር አይደለምን?
\s5
\v 7 በእርግጥ ጌታ እግዚአብሔር ሊያደርግ ያለውን ለአልጋዮቹ ለነቢያት ካልገለጠ በስተቀር ምንም አያደርግም።
\v 8 አንበሳው አገሳ፥የማይፈራ ማነው? ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፥ትንቢት የማይናገር ማነው?
\s5
\v 9 ይህንን በአዛጦንና በግብጽ ምሽጎች አውጁ፥ እንዲህም በሉ፦«በሰማሪያ ተራሮች ላይ ተሰብሰቡ፥ በውስጧ ምን ዓይነት ታላቅ ግራ መጋባትና ጭቆና እንዳለ ተመልከቱ።
\v 10 ቅን ነገርን እንዴት እንደሚያደርጉ አያውቁምና፥ዝርፊያንና ጥፋትን በምሽጎቻቸው አከማችተዋል።» ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።
\s5
\v 11 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«ጠላት ምድሪቱን ይከብባል፤ምሽጎቻችሁን ያፈርሳል ይበዘብዛልም።
\v 12 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«እረኛ ከአንበሳ አፍ ሁለት እግር ብቻ፥ወይንም የጆሮ ቁራጭ እንደሚያድን፥ በመከዳ ጠርዝ ብቻ ወይም በትንሽ የአልጋ ልብስ በሰማሪያ የሚኖሩ የእስራኤል ሰዎች ብቻ ይድናሉ»
\s5
\v 13 ስሙ፥በያዕቆብም ቤት ላይ መስክሩ፥ ይላል የሠራዊት አምላክ ጌታ እግዚአብሔር።
\v 14 የእስራኤልን ኃጢአት በምቀጣበት ቀን የቤቴልን ም መሠዊያዎች እቀጣለሁ። የመሠዊያው ቀንዶች ይቆረጣሉ፥ወደ ምድርም ይወድቃሉ።
\s5
\v 15 የክረምቱን ቤት ከበጋው ቤት ጋር አጠፋለሁ። በዝሆን ጥርስ የተዋቡ ቤቶች ይጠፋሉ፥ታላላቅ ቤቶችም ይደመሰሳሉ፥» ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።
\s5
\c 4
\p
\v 1 እናንተ የባሳን ላሞች፥በሰማሪያ ተራራ የምትኖሩ፥ድኾችን የምትጨቁኑ፥ችግረኞችን የምታደቅቁ፥ ባሎቻችሁንም «መጠጥ አምጡልን» የምትሉ ይህን ቃል ስሙ።
\v 2 ጌታ እግዚአብሔር በቅድስናው እንዲህ ብሎ ምሎአል፦ «ተመልከቱ፥ እናንተን በመንጠቆ፥ የቀሩትንም በዓሳ መንጠቆ የ ሚወስዱበት ቀናት ይመጣል።
\s5
\v 3 በከተማው ቅጥር ፍራሽ በኩል ትወጣላችሁ፥እያንዳንዳችሁ በእርሱ በኩል ወደ ፊት ቀጥ ብላችሁ ትሄዳላችሁ፥ወደ ሬማንም ትጣላላችሁ--ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»
\s5
\v 4 ወደ ቤቴል ሂዱና ኃጢአት ሥሩ፥ወደ ጌልጌላ ሂዱና ኃጢአት አብዙ። መሥዋዕታችሁን በየማለዳው፥ አሥራታችሁንም በየሦሥተኛው ቀን አቅርቡ።
\v 5 እርሾ ያለበትን የምስጋና መሥዋዕት ሠው፤ እናንተ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፥ ይህ ደስ ያሰኛችኋልና በፈቃዳችሁ የምታቀርቡትን አው ጁ፥ ስለ እነርሱም አውሩ --- ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»
\s5
\v 6 የጥርስ ንፃትን በከተማዎቻችሁ ሁሉ፥ እንጀራንም ማጣትን በስፍራዎቻችሁ ሁሉ እሰጣችኋለሁ። እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም ---- ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»
\v 7 ለመከር ሦሥት ወር ሲቀረው ዝናብ ከለከልኋችሁ። በአንዱ ከተማ ላይ እንዲዘንብ፥ በሌላውም ከተማ ላይ እንዳይዘንብ አደረግሁ። በአንዱ ቁራጭ መሬት ላይ ዘነበበት፥ ያልዘነበበት ቁራጭ መሬት ግን ደረቀ።
\s5
\v 8 ሁለት ወይም ሦሥት ከተሞች ውኃ ለመጠጣት ወደ ሌላ ከተማ እየተንገዳገዱ ሄዱ፤ ነገር ግን አልረኩም። ነገር ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም --- ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»
\v 9 በዋግና በአረማሞ መታኋችሁ። የአትክልቶቻችሁን ብዛት፥ ወይኖቻችሁን፥ የበለስና የወይራ ዛፎቻችሁን ሁሉ አንበጦች በሉት። እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም --- ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»
\s5
\v 10 «በግብጽ ላይ እንዳደረግሁባቸው መቅሰፍት ላክሁባችሁ። ወጣቶቻችሁን በሰይፍ ገደልሁ፥ ፈረሶቻችሁንም አስማረክሁ፥ የሠፈራች ሁንም ግማት ወደ አፍንጫችሁ እንዲደርስ አደረግሁ። እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም --- ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»
\v 11 እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን እንደገለበጣቸው፥ በመካከላችሁ ከተሞችን ገለበጥሁ።እናንተም ከእሳት እንደተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፥ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»
\s5
\v 12 «ስለዚህ እስራኤል ሆይ አስደንጋጭ ነገር አደርግብሃለሁ፥ አስደንጋጭንም ነገር ስለማደርግብህ እስራኤል ሆይ አምላክህን ለመገናኘት ተዘጋጅ!
\v 13 እነሆ፥ ተራሮችን የሠራ፥ነፋስንም የፈጠረ፥ አሳቡንም ለሰው የሚገልጥ፥ ንጋትን ጨለማ የሚያደርግ፥የምድርንም ከፍታዎች የሚረግጥ» ስሙ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው።
\s5
\c 5
\p
\v 1 የእስራኤል ቤት ሆይ፥ይህን ቃል ይኽውም በእናንተ ላይ የማሰማውን የሐዘን እንጉርጉሮ ስሙ።
\v 2 ድንግሊቱ እስራኤል ወደቀች፤ ከእንግህም ወዲያ አትነሳም፥ በራሷ ምድር ላይ ተተወች፤ የሚያነሳትም ማንም የለም።
\s5
\v 3 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«ለእስራኤል ቤት ሺህ ታወጣ የነበረች ከተማ መቶ ይቀርላታል፥ መቶም ታወጣ የነበረች ከተማ አሥር ይቀርላታል።»
\s5
\v 4 ከዚህ የተነሳ እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት እንዲህ ይላል፦ «እኔን ፈልጉ፥በሕይወትም ኑሩ!
\v 5 ጌልጌላ በእርግጥ ትማረካለችና፥ በቴልም ታዝናለችና፤ ቤቴልን አትፈልጉ፥ወደ ጌልጌላ አትግቡ፥ ወደ ቤርሳቤህም አትሂዱ።
\s5
\v 6 እግዚአብሔርን ፈልጉ፥በሕይወትም ኑሩ፤ይህ ካልሆነ በዮሴፍ ቤት ላይ እንደ እሳት ይነሳል። ይበላል፥ በቤቴልም የሚያጠፋው ማንም የለም።
\v 7 እነዚያ ሰዎች ፍትህን ወደ መራራ ነገር ለውጠዋልና፥ ጽድቅንም ወደ ምድር ጥለዋልና።
\s5
\v 8 ሰባቱን ከዋክብትና ኦርዮንን የፈጠረ አምላክ፥ ጨለማን ወደ ንጋት ይለውጣል፥ ቀኑን በሌሊት ያጨልማል፥ የባሕርንም ውኃ ጠርቶ በምድር ፊት ላይ ያፈሳቸዋል። ስሙ እግዚአብሔር ነው!
\v 9 ምሽጉ እንዲፈርስ ድንገትኛ ጥፋትን ያመጣል።
\s5
\v 10 በከተማይቱ በር ላይ የሚያርማቸውን ማንንም ጠሉ፥ እውነትን የሚናገረውን ማንንም ተጸየፉ።
\v 11 ድኻውን ረግጣችኋልና፥ የስንዴውን ም ድርሻ ከእርሱ ወስዳችኋልና፤ ከተጠረበ ድንጋይ ቤቶችን ብትሠሩም አትኖሩባቸውም። ያማሩ የወይን ተክል ቦታዎች አሉአችሁ፥ የወይን ጠጃቸውን ግን አትጠጡም።
\s5
\v 12 እናንተ ጻድቁን የምታጥቁ፥ ጉቦ የምትቀበሉ፥ በከተማይቱም በር ችግረኛውን የምትገለብጡ፤ በደላችሁ እንዴት ብዙ እንደሆን፥ ኃጢአታችሁም እንዴት ታላቅ እንደሆን እኔ አውቃለሁ።
\v 13 ጊዜው ክፉ ነውና፥ አስተዋይ የሆነ ማንም በእንደዚህ ዓይነቱ ጊዜ ዝም ይላል።
\s5
\v 14 በሕይወት ትኖሩ ዘንድ መልካሙን ፈልጉ፥ ክፉውንም አይደለም። እርሱም እንደተናገራችሁት ነውና፥ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር በእርግጥ ከእናንተ ጋር ይሆናል።
\v 15 ክፉውን ጥሉ፥ መልካሙንም ውደዱ፥ በከተማይቱም በር ፍትሕን አጽኑ፤ ምናልባት የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ለዮሴፍ ቅሬታ ይራራ ይሆናል።
\s5
\v 16 ሰለዚህ ጌታ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ «በአደባባዮቹ ሁሉ ዋይታ ይሆናል፥ በየመንገዶቹ ወዮ! ወዮ! ይላሉ። ገበሬዎችን ለለቅሶ፥ አልቃሾችንም ለዋይታ ይጠራሉ።
\v 17 እኔ በመካከልህ አልፋለሁና፥ በወይን ተክል ቦታዎች ሁሉ ዋይታ ይሆናል» ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 18 የእግዚአብሔርን ቀን ለምትፈልጉ ወዮላችሁ! የእግዚአብሔርን ቀን ለምን ትፈልጋላችሁ? ጨለማ ነው እንጂ ብርሃን አይደለም።
\v 19 አንድ ሰው ከአንበሳ ሲሸሽ ድብ እንደሚያጋጥመው፥ ወደ ቤት ገብቶ እጁን ግድግዳ ላይ ሲያስደግፍ እባብ እንደሚነድፈው ነው።
\v 20 የእግዚአብሔር ቀን ብርሃን ሳይሆን ጨለማ አይደለምን? ብሩህ ሳይሆን ደብዛዛ አይደለምን?
\s5
\v 21 ዓመት በዓላችሁን ጠልቼዋለሁ፥ ተጸይፌዋለሁም፤በጉባዔዎቻችሁ ደስ አይለኝም።
\v 22 የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁንና የእህል ቁርባናችሁን ብታቀርቡልኝ እንኳን አልቀበላቸውም፤ ወይም ወደ ሰቡ እንስሶቻችሁ የኅብረት መሥዋዕት አልመለከትም።
\s5
\v 23 የመዝሙሮችህን ጩኽት ከእኔ አርቅ፤ የበገናህንም ድምጽ አልሰማም።
\v 24 በዚያ ፈንታ ፍትሕ እንደ ውኃ፥ ጽድቅም ሳያቋርጥ እንደሚመነጭ ምንጭ ይፍሰስ።
\s5
\v 25 የእስራኤል ቤት ሆይ በምድረ በዳው ለአርባ ዓመታት መሥዋዕትንና ቁርባንን አቅርባችሁልኝ ነበርን?
\v 26 ለራሳችሁ የሠራችኋቸውን ጣዖታት፥ ሞሎክን እንደ ንጉሣችሁ፥ሬፋን እንደ ኮከብ አምላካችሁ አንሥታችሁ ትሸከማችሁ።
\s5
\v 27 ስለዚህ ከደማስቆ ማዶ እስማርካችኋለሁ» ይላል፥ ስሙ የሠራዊት አምላክ የሆነው እግዚአብሔር።
\s5
\c 6
\p
\v 1 በጽዮን በምቾት፥በሰማሪያ ተራሮች ላይ ያለ ስጋት ለሚኖሩ፥የእስራኤል ቤት ለርዳታ ወደ እነርሱ ለሚመጡባችው፥ ለታላላቅ የሕዝብ አለቆች ወዮላቸው!
\v 2 መሪዎቻችሁ እንዲህ ይላሉ፦«ወደ ካልኔ ሂዱና ተመልከቱ፥ከዚያም ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ሐማት እለፉ፥ ከዚያም ወደ ፍልስጤም ጌት ውረዱ። እነርሱ ከእናንተ ሁለት መንግሥታት የተሻሉ ናቸውን? የእነርሱ ድንበር ከእናንተ ድንበር ይሰፋልን?»
\s5
\v 3 የጥፋትን ቀን ለምታርቁ፥የግፍንም መንበር ለምታቀርቡ ወዮላችሁ!
\v 4 ከዝሆን ጥርስ በተሠሩ አልጋዎች ላይ ይተኛሉ፥በመከዳዎቻቸውም ላይ ይዝናናሉ። ከበጎች መንጋ ጠቦትን፥ከበረትም ጥጃን ይበላሉ።
\s5
\v 5 በበገና ድምጽ ጣዕም የሌለው ዜማ ያዜማሉ፥ እንደ ዳዊት በተገኘው የሙዚቃ መሣሪያ መጫወት ይሻሉ።
\v 6 በዋንጫ የወይን ጠጅ ይጠጣሉ፥ ከሁሉ በተመረጠ ዘይት ይቀባሉ፥ ነገር ግን በዮሴፍ መጥፋት አያዝኑም።
\s5
\v 7 ስለዚህ ከመጀመሪያዎቹ ምርኮኞች ጋር ወደ ምርኮ ይሄዳሉ፥ የሚዝናኑቱ ድግሶችና ፈንጠዚያዎች ያከትማሉ።
\v 8 እኔ ጌታ እግዚአብሔር በራሴ ምያለሁ፥ ይህ የሠራዊት አምላክ የጌታ እግዚአብሔር አዋጅ ነው፦«የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌአለሁ፥ ምሽጎቹንም ጠልቼአለሁ። ስለዚህ ከተ ማይቱን በውስጧ ካሉት ሁሉ ጋር አሳላፌ አሰጣለሁ።»
\s5
\v 9 እንዲህም ይሆናል፤ በአንድ ቤት አሥር ሰዎች ቢቀሩ ሁሉም ይሞታሉ።
\v 10 የሰው ዘመድ አስከሬኖቹን ለመውሰድ በመጣ ጊዜ፤ አስከሬኖቹን ከቤት አውጥቶ የሚያቃጥላቸው ሰው፥ በቤት ውስጥ ያለውን ሰው፦«ከአንተ ጋር ሌላ ሰው አለን?» ሲለው፤ ሰውዬውም፦ «ማንም የለም» ብሎ በመለሰለት ጊዜ፥ እርሱም፦«ዝም በል፥ የእግዚአብሔርን ስም መጥራት አይገባንምና» ይለዋል።
\s5
\v 11 ተመልከቱ፥ እግዚአብሔር ትዕዛዝ ይሰጣል፤ ትልቁም ቤት ይሰባበራል፥ ትንሹም ቤት ይደቅቃል።
\s5
\v 12 ፈረሶች በጭንጫ ላይ ይሮጣሉን? ሰውስ በዚያ ላይ በበሬዎች ያርሳልን? እናንተ ግን ፍትሕን ወደ መርዝነት፥ የጽድቅንም ፍሬ ወደ መራርነት ለውጣችኋል።
\v 13 እናንተ ሎዶባርን በማሸነፋችሁ ደስ ያላችሁ፥ «ቃርናይምን በራሳችን ብርታት አልወሰድንምን?» የምትሉ፤
\s5
\v 14 «ነገር ግን፥ የእስራኤል ቤት ሆይ አነሆ ሕዝብን አስነሣባችኋለሁ»፥ ይህ የሠራዊት አምላክ የጌታ እግዚአብሔር አዋጅ ነው። «ከሐማት መግቢያ አንስቶ እስከ ዓረባ ወንዝ ድረስ ያስጨንቋችኋል።»
\s5
\c 7
\p
\v 1 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ። እነሆ፥የጸደይ አዝመራ መብቀል በሚጀምርበት ጊዜ የአንበጣን መንጋ ፈጠረ፥ ተመለከትሁም፥ ከንጉሥ አጨዳ በኋላ ዘግይቶ የበቀለ አዝመራ ነበር።
\v 2 የምድሪቱን ሣር በልተው ከጨረሱ በኋላ፤ «ጌታ እግዚአብሔር ሆይ እባክህ ይቅር በል፥ ያዕቆብ በዚህ ውስጥ እንዴት ይቆማል? እርሱ ታናሽ ነውና» አልሁ።
\v 3 እግዚአብሔርም ስለዚህ ነገር ተጸጸተ፤ «ይህ አይሆንም» አለ።
\s5
\v 4 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ፦እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔር በእሳት ለመፍረድ ጠራ። እርሱም በምድር ውስጥ የሚገኘውን ሰፊና ጥልቅ ውኃ አደረቀ፥ ምድሪቱንም ደግሞ በላ።
\v 5 እኔ ግን፦«ጌታ እግዚአብሔር ሆይ እባክህ ተው፥ያዕቆብ በዚህ ውስጥ እንዴት ይቆማል? እርሱ ታናሽ ነውና» አልሁ።
\v 6 እግዚአብሔርም ስለዚህ ነገር ተጸጸተ፤ «ይህም ደግሞ አይሆንም» ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\v 7 እንዲህም አሳየኝ፦ እነሆም ፥ጌታ በእጁ ቱምቢ ይዞ በቅጥሩ አጠገብ ቆሞ ነበር።
\v 8 እግዚአብሔርም፦ «አሞጽ ምን ታያለህ?» አለኝ፥ እኔም «ቱምቢ» አልሁኝ። ከዚያም ጌታ፦«ተመልከት፥በሕዝቤ በእስራኤል መካከል ቱምቢ አኖራለሁ። ከእንግዲህም ወዲያ አልምራቸውም።
\s5
\v 9 የይስሐቅ ከፍታ ቦታዎች ይጠፋሉ፥ የእስራኤል መቅደሶች ይፈርሳሉ፥ በኢዮርብዓምም ቤት ላይ በሰይፍ እነሳለሁ።»
\s5
\v 10 ከዚያም የቤቴል ካህን አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዮርብዓም እንዲህ ሲል መልእክት ላከ፦«አሞጽ በእስራኤል ቤት መካከል በአንተ ላይ እያሤረ ነው። ምድሪቱም ቃሎቹን ልትሸከም አትችልም።
\v 11 አሞጽ እንዲህ ሲል ተናግሮአል፦'ኢዮርብዓም በሰይፍ ይሞታል፥ እስራኤልም በእርግጥ ከምድሩ ተማርኮ ይሄዳል'።»
\s5
\v 12 አሜስያስም፥ አሞጽን እንዲህ አለው፦«ባለ ራዕዩ ሆይ፥ ወደ ይሁዳ ምድር ተመልሰህ ሽሽ፥ በዚያም እንጀራ ብላ ትንቢትም ተናገር።
\v 13 ነገር ግን ቤቴል የንጉሡ መቅድስና የመንግሥት መኖሪያ ነውና ከእንግዲህ ወድያ በዚህ ትንቢት አትናገር።»
\s5
\v 14 ከዚያም አሞጽ አሜስያስን እንዲህ አለው፦ «እኔ ነቢይ ወይም የነቢይ ልጅ አይደለሁም። እኔ እረኛና የዋርካ ዛፎች ጠባቂ ነኝ።
\v 15 ነገር ግን እግዚአብሔር የበግ መንጋ ከመጠበቅ ወሰደኝና እንዲህ አለኝ፦'ሂድ፥ ለሕዝቤ ለእስራኤል ትንቢት ተናገር።'
\s5
\v 16 አሁን የእግዚአብሔርን ቃል ስማ። አንተ፥ «'በእስራኤል ላይ ትንቢት አትናገር፥ በይስሐቅም ቤት ላይ አትናገር' ትላለህ።
\v 17 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦' ሚስትህ በከተማይቱ ውስጥ ሴተኛ አዳሪ ትሆናለች፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ምድርህ እየተለካ ይከፋፈላል፥ በረከሰ ምድር ትሞታለህ፥ እስራኤልም በእርግጥ ከምድሩ ተማርኮ ይጋዛል።»
\s5
\c 8
\p
\v 1 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ፤ የበጋ ፍሬ ቅርጫት ተመለከትሁ!
\v 2 እርሱም፥ «አሞጽ፥ ምን ታያለህ?» አለኝ። እኔም፥ «የበጋ ፍሬ ቅርጫት» አልሁት። ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ «በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ፍጻሜ መጥቶአል፤ ከእንግዲህ ወዲያ አልምራቸውም።
\v 3 የቤተ መቅደሱ ዝማሬ ዋይታ ይሆናል። የጌታ እግዚአብሔር አዋጅ ይህ ነው፥ በዚያን ቀን፥ «አስከሬኑ ብዙ ይሆናል፤ በሁሉ ሥፍራ በዝምታ ይጥሏቸዋል።»
\s5
\v 4 እናንተ ችግረⶉችን የምትረግጡና የምድሪቱን ድኾች የምታጠፉ ስሙ።
\v 5 እንዲህ ይላሉ፦«እህል እንሸጥ ዘንድ የወር መባቻው መቼ ያልፋል? በሐሰተኛ ሚዛን እያታለልን፥ መስፈሪያውን እያሳነስን፥ ዋጋውን ከፍ እያደረግን፥ ስንዴ ለገበያ እናቀርብ ዘንድ፥
\v 6 የስንዴውን ግርድ እንሸጥና ደኻውን በብር፥ ችግረኛውንም በጥንድ ጫማ እንገዛ ዘንድ ሰንብት መቼ ያልፋል?»
\s5
\v 7 እግዚአብሔር በያዕቆብ ክብር እንዲህ ሲል ምሎአል፦ «በእርግጥ የትኛውንም ሥራቸውን ፈጽሞ አልረሳም።»
\v 8 በዚህ ነገር፥ ምድር አትናወጥምን፥ በውስጧም የሚኖሩ ሁሉ አያለቅሱምን? ሁለመናዋ እንደ አባይ ወንዝ ይነሣል፥ እንደ ግብጽ ወንዝም ወደ ላይ ይወረወራል፥ተመልሶም ይወርዳል።
\s5
\v 9 «በዚያን ቀን እንዲህ ይሆናል» ፥የእግዚአብሔር አዋጅ እንዲህ ይላል፥ «ፀሐይ በቀን እንድትጠልቅ አደርጋለሁ፥ በቀንም ብርሃን እያለ ምድርን አጨልማታለሁ»።
\v 10 ዓመት በዓላችሁን ወደ ልቅሶ፥ መዝሙራችሁንም ሁሉ ወደ ዋይታ እለውጣለሁ። ሁላችሁም ማቅ እንድትለብሱ፥ ጸጉራችሁንም እንድትላጩ አደርጋለሁ። ለአንድያ ልጅ እንደሚለቀስ፥ እንደ መራራም ቀን አደርገዋለሁ።
\s5
\v 11 ተመልከቱ፥ቀኖቹ እየቀረቡ ናቸው» ፥የእግዚአብሔር አዋጅ እንዲህ ይላል፥ «ረሓብን በምድር ላይ እሰድዳለሁ፥ እርሱም የእግዚአብሔርን ቃል የመስማት ረሓብ እንጂ እንጀራን የመራብ ወይም ውኃን የመጠማት አይደለም።
\v 12 የእግዚአብሔርን ቃል ፍለጋ ከባሕር ወደ ባሕር ይንከ ራተታሉ፥ ከሰሜን ወደ ምሥራቅ ይሮጣሉ፤ ነገር ግን አያገኙትም።
\s5
\v 13 በዚያን ቀን ያማሩ ደናግላንና ወጣቶች ከውኃ ጥም የተነሳ ይዝላሉ።
\v 14 'ዳን ሆይ ሕያው አምላክህን' ድግሞም 'ሕያው የቤርሳቤህ አምላክ' እያሉ በሰማርያ ኃጢአት የሚምሉ ፤ይወድቃሉ፥ዳግመኛም አይነሱም።»
\s5
\c 9
\p
\v 1 ጌታን በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አየሁት፥ እንዲህም አለ፦«መሠረቶቹ እንዲናወጡ የአምዶቹን የላይኛውን ጫፍ ምታ። በራሶቻቸው ሁሉ ላይ ሰባብራቸው፥ ከእነርሱም የቀሩትን በሰይፍ እገድላለሁ። ከእነርሱ ማንም አያመልጥም፥ ማንም አይተርፍም።
\v 2 ቆፍረው ወደ ሲዖል ቢወርዱም፥ እጄ ከዚያ ታወጣቸዋለች። ወደ ሰማይ ቢወጡም፥ ከዚያ አወርዳቸዋለሁ።
\s5
\v 3 በቀርሜሎስ ራስ ላይ ቢሸሸጉም፥ በርብሬ ከዚያ እወስዳቸዋለሁ። በባሕሩ ሥር ከዓይኔ ቢደበቁም፥ በዚያ እባቡን አዝዛለሁ፥ እርሱም ይነድፋቸዋል።
\v 4 በጠላቶቻቸው ፊት እየተነዱ ወደ ምርኮ ይጋዛሉ፤ በዚያም ሰይፍን አዝዛለሁ፥ እርሱም ይገድላቸዋል። ዓይኔን ለክፉ በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ፥ ለመልካምም አይደለም።»
\s5
\v 5 ጌታ፥ የሠራዊቱ እግዚአብሔር ምድርን ይዳስሳል፥ እርስዋም ትቀልጣለች፥ በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሁሉ፤ ሁለመናዋ እንደ ወንዝ ወደ ላይ ይወረወራል፥ እንደ ግብጽም ወንዝ ተመልሶ ይሰምጣል።
\v 6 አዳራሹን በሰማይ የሠራ፥ ግምጃ ቤቱን በምድር የመሠረተ እርሱ ነው። የባሕርን ዉኆች ይጠራቸዋል፥ በምድርም ፊት ላይ ያፈስሳቸዋል፥ ስሙም እግዚአብሔር ነው።
\s5
\v 7 የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር። እስራኤልን ከግብጽ፥ፍልስጤማያንን ከከፍቶር፥ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን?
\v 8 እነሆ፥ የጌታ እግዚአብሔር ዓይኖች በኃጢአተኛ መንግሥት ላይ ናቸው፥ ከምድርም ገጽ አጠፋዋለሁ፣ የያቆብን ቤት ግን ፈጽሜ አላጠፋም፤ ይላል እግዚአብሔር።»
\s5
\v 9 እነሆ፥አዝዛለሁ፥ ሰው በወንፊት እህል እንደሚነፋ፥ የእስራኤልን ቤት በአሕዛብ ሁሉ መካከል እነፋለሁ፤ ነገር ግን አንዲትም ቅንጣት በምድር ላይ አትወድቅም።
\v 10 «ጥፋት አይደርስብንም ወይም አያገኘንም» የሚሉ፤ የሕዝቤ ኃጢአተኞች ሁሉ በሰይፍ ይሞታሉ።
\s5
\v 11 «በዚያን ቀን የወደቀችውን የዳዊትን ድንኳን አነሳለሁ፥ ሽንቁሩንም እዘጋለሁ። ፍራሽዋንም አነሳለሁ፥ በቀድሞ ዘመን እንደነበረች እን ደገና እሠራታለሁ፤
\v 12 ይኼውም የኤዶምን ቅሬታ፥ በስሜም የተጠሩትን አሕዛብ ሁሉ ይወርሱ ዘንድ ነው፥ ይላል ይህን የሚያደርግ እግዚአብሔር።»
\s5
\v 13 እነሆ፥ አራሹ አጫጁ ላይ፥ ወይን ጠማቂው ዘሪው ላይ የሚደርስበት ጊዜ ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር። ተራሮቹ ጣፋጩን ወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፥ ኮረብቶችም ሁሉ ይፈስባቸዋል።
\s5
\v 14 ሕዝቤን እስራኤልን ከተማረከበት እመልሰዋለሁ። የፈረሱትን ከተሞች ሠርተው ይኖሩባቸዋል፥ ወይንንም ተከለው የወይን ጠጃቸውን ይጠጣሉ፥አትክልትም ተክለው ፍርውን ይበላሉ።
\v 15 በምድራቸው ላይ እተክላቸዋለሁ፥ ከሰጠኋቸውም ምድር ከቶውን ዳግመኛ አይነቀሉም» ይላል አምላካችሁ እግዚአብሔር።