am_ulb/29-JOL.usfm

159 lines
16 KiB
Plaintext

\id JOL
\ide UTF-8
\h ትንቢተ ኢዩኤል
\toc1 ትንቢተ ኢዩኤል
\toc2 ትንቢተ ኢዩኤል
\toc3 jol
\mt ትንቢተ ኢዩኤል
\s5
\c 1
\p
\v 1 ወደ ባቱኤል ልጅ ወደ ኢዩኤል የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።
\v 2 እናንተ ሽማግሌዎች ይህን ስሙ፤በምድሪቱም የምትኖሩ ሁላችሁ አድምጡ። ይህ፥ከዚህ በፊት በእናንተ ወይም በአባቶቻችሁ ዘመን ሆኖ ያውቃልን?
\v 3 ይህንን ለልጆቻችሁ ንገሩ፥ልጆቻችሁም ለልጆቻቸው ይንገሩ፥የእነርሱም ልጆች ለሚቀጥለው ትውልድ ይንገሩ።
\s5
\v 4 ከአንበጣ መንጋ የተረፈውን ትላልቁ አንበጣ በላው፥ከትልቁ አንበጣ የተረፈውን ፌንጣ በላው፥ ከፌንጣ የተረፈውን አባ ጨጓሬ በላው።
\s5
\v 5 እናንተ ሰካራሞች ተነሡና አልቅሱ! አዲሱ የወይን ጠጅ ከአፋችሁ ተወግዶአልና እናንተ የወይን ጠጅ ጠጪዎች ዋይ በሉ።
\v 6 ቁጥር የሌለው ሕዝብ በምድሬ ላይ መጥቶአልና። ጥርሶቹ የአንበሳ ጥርሶች ናቸው፤የሴት አንበሳም ጥርሶች አሉት።
\v 7 የወይን ቦታዬን አስደንጋጭ ስፍ ራ አደረገው፤የበለስ ዛፌን መልምሎ ባዶውን አስቀረ። ቅርፊቱን ላጠው፥ጣለውም፤ቅርንጫፎቹም ነጡ።
\s5
\v 8 ለልጅነት ባሏ ሞት ማቅ እንደ ለበሰች ድንግል አልቅሱ።
\v 9 የእህሉ ቁርባንና የመጠጡ ቁርባን ከእግዚአብሔር ቤት ተወግዷል፤የእ አብሔርም አገልጋዮች ካህናቱ አለቀሱ።
\v 10 እርሻው ጠፍቷል፥ምድሪቱም አለቀሰች። እህሉ ወድሟል፥አዲሱ ወይን ደርቋል፥ዘይቱም ተበላሽቷል።
\s5
\v 11 እናንተ ገበሬዎችና የወይን አትክልተኞች ስለ ስንዴዉና ስለ ገብሱ እፈሩ። የእርሻው መከር ጠፍቷልና።
\v 12 ወይኑ ጠውልጓል፥የበለስም ዛፎች ደርቀዋል፤የሮማን፥የተምርና የእንኮይ ዛፎች፥የእርሻው ዛፎች ሁሉ ጠውልገዋል። ደስታም ከሰው ልጆች ርቋል።
\s5
\v 13 የእህሉ ቁርባንና የመጠጡ ቁርባን ከአምላካችሁ ቤት ተቋርጧልና፥እናንተ ካህናት ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ! ፥እናንተ የመሠዊያው አገልጋዮች ዋይ በሉ። እናንተ የአምላኬ አገልጋዮች ኑ ሌሊቱን በሙሉ ማቅ ላይ ተኙ።
\v 14 ቅዱስ ጾም አውጁ፥የተቀደሰም ጉባዔ ጥሩ። ሽማግሌዎችንና በምድሪቱ የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፤ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ።
\s5
\v 15 የእግዚአብሔር ቀን ደርሷልና፥ወዮ ለዚያ ቀን! ከእርሱ ጋር ጥፋት ሁሉን ከሚችል አምላክ ይመጣል።
\v 16 ምግብ ከዓይናችን ፊት፥ ደስታና ሐሴት ከአምላካችን ቤት አልተወገደምን?
\v 17 ዘሩ በምድር ውስጥ በስብሷል፤እህሉ ደርቋልና ጎተራዎቹ ባዶ ሆነዋል፥ጎታዎቹም ፈርሰዋል።
\s5
\v 18 እንስሳት ምንኛ ጮኹ! መሰማሪያ የላቸውምና የቀንድ ከብት መንጎች ተሰቃዩ። የበግ መንጎችም ተሰቃዩ።
\v 19 እሳቱ የምድረ በዳውን ማሰማሪያ በልቷልና፥ነበልባሉም የጫካውን ዛፎች ሁሉ አቃጥሎአልና፤እግዚአብሔር ሆይ ወደ አንተ እጮሃለሁ።
\v 20 ጅረቶች ሁሉ ስለደረ ቁና እሳ ት የምድረ በዳውን ማሰማሪያ ስለ በላው፥የዱር እንስሳት እንኳን ወደ አንተ አለኽልኹ።
\s5
\c 2
\p
\v 1 በጽዮን መለከት ንፉ፥ በቅዱስ ተራራዬም ላይ የማስጠንቀቂያ ድምጽ አሰሙ! የእግዚአብሔር ቀን መጥቷልና፥በእርግጥም ቅርብ ነውና፤የም ድሪቱ ነዋሪዎች ሁሉ በፍርሃት ይንቀጥቀጡ።
\v 2 እርሱም የጨለማና የጭጋግ ቀን፥የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ነው። ንጋት በተራሮች ላይ እንደሚዘረጋ፥ታላቅና ኃያል ሠራዊት እየመጣ ነው። እርሱን የመሰለ ሠራዊት ከቶ አልነበረም፥ከብዙ ትውልድ በኋላ እንኳን ዳግመኛ አይኖርም።
\s5
\v 3 በስተፊቱ እሳት ሁሉን ነገር ይበላል፥በስተኋላውም ነበልባል ይንቦገቦጋል። በስተፊቱ ምድሪቱ የዔደን ገነትን ትመስላለች፥በስተኋላው የሚገኘ ው ግን ባዶ ምድረ በዳ ነው።በእርግጥ፥ምንም ከእርሱ አያመልጥም።
\s5
\v 4 የሠራዊቱ ገጽታ እንደ ፈረስ ነው፥እንደ ፈረሰኛም ይሮጣሉ።
\v 5 በተራሮች ራስ ላይ እንደሚሄድ የሰረገላ ድምጽ፥ገለባውን እንደሚበላ የእሳት ነበለባል ድምጽ እያሰሙ፥ ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ኃያል ሠራዊት ያኮበኩባሉ።
\s5
\v 6 በፊታቸው ሰዎች ይታወካሉ፥የሁሉም ፊት ይገረጣል።
\v 7 እንደ ብርቱ ተዋጊዎች ይሮጣሉ፥እንደ ወታደሮችም በቅጥሩ ላይ ይዘላሉ፤እያን ዳንዱ እርምጃውን ጠብቆ ፥ሰልፋቸውንም ሳያፈርሱ፤ ይተማሉ።
\s5
\v 8 እያንዳንዱ መንገዱን ይሄዳል፥እርስ በእርሳቸው ሳይገፋፉ ይተማሉ፤ምሽጎችን ሰብረው ያልፋሉ፥ነገር ግን ከመስመራቸው አይወጡም።
\v 9 ከተማን በድንገት ያጠቃሉ፥በቅጥር ላይ ይሮጣሉ፥ቤቶች ላይ ይወጣሉ፥እንደ ሌቦችም በመስኮቶች ያልፋሉ።
\s5
\v 10 ምድር በፊታቸው ትንቀጠቀጣለች፥ሰማያትም ይናወጣሉ፥ ፀሐይና ጨረቃም ይጨልማሉ፥ከዋክብትም ማብራታችውን ያቆማሉ።
\v 11 ተዋጊዎቹ እጅግ ብዙ ናቸውና፥ትእዛዙን የሚፈጽሙ ኃያላን ናቸውና፤ እግዚአብሔር በሠራዊቱ ፊት ድምጽን ያሰማል። የእግዚአብሔር ቀን ታላቅና የሚያስፈራ ነውና፤ ማን ሊቆም ይችላል?
\s5
\v 12 «አሁንም እንኳን» ይላል እግዚአብሔር፥«በፍጽም ልባችሁ ወደ እኔ ተመለሱ፤ጹሙ፥አልቅሱ፥እዘኑም።»
\v 13 ልብሳችሁን ብቻ ሳይሆን ልባችሁንም ቅደዱ፤ ወደ አምላካችሁም ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ። እርሱ ቸርና መሐሪ፥ለቁጣ የዘገየ፥ፍቅሩ የተትረፈረፈ ነውና፤ስቃይ ካለብት ከዚህ ቅጣት መመለስ ይፈልጋል።
\s5
\v 14 ምናልባት ይመለስና ይራራ እንደሆነ፥ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባን የሚሆን በረከት በስተኋላው ያተርፍ እ ንደሆነ ማን ያውቃል?
\s5
\v 15 በጽዮን መለከት ንፉ፥የተቀደሰ ጾም አውጁ፥ የተቀደሰም ጉባዔ ጥሩ።
\v 16 ሕዝቡን ሰብስቡ፥የተቀደሰ ጉባዔ ጥሩ። ሽማግሌዎችን፥ልጆችን፥ የሚጠቡትንም ሕጻናት ሰብስቡ። ሙሽራው ከእልፍኛቸው፥ሙሽራይቱም ከጫጉላ ቤታቸው ይውጡ።
\s5
\v 17 የእግዚአብሔር አገልጋዮች፥ ካህናቱ፥ በቤት መቅደሱ መግቢያ ደጅና በመሠዊያው መካከል ያልቅሱ። እንዲህም ይበሉ፦«እግዚአብሔር ሆይ ለሕዝብህ ራራ፥አሕዛብ ይገዙአቸው ዘንድ ርስትህን ለእፍረት አሳልፈህ አትስጥ።በአሕዛብ መካከል አምላካቸው ወዴት ነው? ስለ ምን ይበሉ።»
\s5
\v 18 እግዚአብሔርም ስለ ምድሩ ቀና፥ለሕዝቡም ራራ።
\v 19 እግዚአብሔርም ለሕዝቡ እንዲህ ሲል መለሰ፦«እነሆ፥ እህል፥አዲስ ወይንና ዘይት እልክላችኋለሁ። እናንተም በእነርሱ ትጠግባላችሁ፥ ከእንግዲህም ወዲያ በአሕዛብ መካከል ለውርደት አላደርጋችሁም።
\s5
\v 20 የሰሜንን ጥቃት ፈጻሚዎች ከእናተ አርቃለሁ፥ ወደ ደረቅና ወደ ተተወ ምድር እሰድዳቸዋለሁ። የሠራዊቱ ፊተኛ ጦር ወደ ምሥራቅ ባሕር፥ የሠራዊቱ ኋለኛ ጦር ወደ ምዕራብ ባሕር ይሄዳል። ግማቱ ይውጣል፥ክርፋቱም ይነሳል፤ታላላቅ ነገሮችንም አደርጋለሁ።»
\s5
\v 21 እግዚአብሔር ታላላቅ ነገሮችን አድርጓልና፤ ምድር ሆይ አትፍሪ፥ ደስ ይበልሽ፥ ሐሴትም አድርጊ።
\v 22 የምድር እንስሶች ሆይ፥ የምድረ በዳ ማሰማሪያዎች ለምልመዋልና፥ ዛፎች ፍሬያቸውን አፍርተዋልና፥ የበለስ ዛፎችና ወይኖች ሙሉ ፍሬያቸውን ሰጥተዋልና፤አትፍሩ።
\v 23 የበልግን ዝናብ እንደሚገባ ይሰጣአችኋልና፥እንደ ቀድሞ ዘመን የበልግ ዝናብንና የፀደይን ዝናብ ያካፋላችኋልና፤ የጽዮን ሰዎች ሆይ፥ደስ ይበላችሁ፥ በአምላካችሁም በእግዚአብሔር ሐሴት አድርጉ።
\s5
\v 24 አውድማዎቹ በስንዴ ይሞላሉ፥መጥመቂያዎችም አዲስ ወይን ጠጅና ዘይት ያፈስሳሉ።
\v 25 በመካከላችሁ የላኩት ታላቁ ሠራዊቴ፥ የአንበጣ መንጋ፥ ትልቁ አንበጣ፥ ፌንጣና አባ ጮጋሬ የበሏቸውን የምርት ዓመታት እመልስላችኋለሁ።
\s5
\v 26 ተትረፍርፎ ትበላላችሁ፥ ትጠግባላችሁም፤ በመካከላችሁም ተዓምራት ያደረገውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ስም ታመሰግናላችሁ፤ ከእንግዲህም ወዲያ እፍረትን በሕዝቤ ላይ ከቶውኑ አላመጣም።
\v 27 እኔ በእስራኤል መካከል እንዳለሁ፥ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሆንኩ፥ ሌላም እንደሌለ፥ ከእንግዲህም ወዲይ እፍረትን በሕዝቤ ላይ ከቶውን እንደማላመጣ ታውቃላችሁ።
\s5
\v 28 ከዚያም በኋላ እንደዚህ ይሆናል፡- መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፥ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ። ሽማግሌዎቻችሁ ሕልም ያልማሉ፥ጎልማሶቻችሁም ራእይ ያያሉ።
\v 29 በእነዚያ ወራት በወንዶችና ሴቶች ባሪያዎች ላይም መንፈሴን አፈሳለሁ።
\s5
\v 30 በሰማያት ድንቆችን፥በምድርም ደም፥እሳትና የጢስ ዓምድ አሳያለሁ።
\v 31 ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ከመምጣቱ በፊት፥ ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ጨረቃም ወደ ደም ትለወጣለች።
\s5
\v 32 የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል። እግዚአብሔር እንደ ተናገርው፥ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም የሚያመልጡ ይኖራሉ፤ከትሩፋኑም መካከል እግዚአብሔር የጠራቸው ይገኛሉ።
\s5
\c 3
\p
\v 1 እነሆ፥ በዚያ ወራትና በዚያ ጊዜ፥ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ምርኮኞች በምመልስበት ጊዜ፥
\v 2 አሕዛብን ሁሉ እሰበስባለሁ፥ ወደ ኢዮሳፍጥም ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ። በአሕዛብ መካከል ከበተኑአቸው ከሕዝቤና ከርስቴ ከእስራኤል የተነሳ፥ ምድሬን ከመከፋፈላቸው የተነሳ፤ በዚያ እፈር ድባቸዋለሁ።
\v 3 በሕዝቤ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፥ ወንድ ልጅን በሴተኛ አዳሪ ለወጡ፥ ሴት ልጅንም ለወይን ጠጅ ሸጡ፥ ጠጡም።
\s5
\v 4 ጢሮስና ሲዶና የፍልስጤምም ክፍለ አገራት ሁሉ፥አሁን በእኔ ላይ መቆጣታችሁ ለምንድ ነው? ብድራትን ትመልሱልኛላችሁን? ብድራትን ብትመልሱልኝ፥ወዲያው ብድራታችሁን በራሳችሁ ላይ እመልሳለሁ።
\v 5 ብሬንና ወርቄን ወስዳችኋል፥የከበረውንም ሀብቴን ወደ ቤተ መቅ ደሳችሁ አግዛችኋል።
\v 6 ከግዛታቸው ልታርቋቸው፥ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሰዎች ለግሪኮች ሸጣችኋል።
\s5
\v 7 እነሆ እነርሱን የሸጣችሁብትን ሥፍራ እንዲለቁ አደርጋቸዋለሁ፥ ብድራታችሁንም በራሳችሁ ላይ እመልሳለሁ።
\v 8 ወንዶችና ሴቶች ልጆ ቻችሁን በይሁዳ ሰዎች እጅ እሸጣለሁ። እነርሱም በሩቅ ላለ ሕዝብ፥ለሳባ ሰዎች ይሸጡአቸዋል። እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአልና።
\s5
\v 9 ይህን በአሕዛብ መካከል አውጁ፦ ለጦርነት ተዘጋጁ፥ኃያላን ሰዎችን አነሣሡ፥ ይቅረቡ፥ ተዋጊዎችም ሁሉ ይውጡ።
\v 10 ማረሻችሁን ሰይፍ፥ ማጭዳችሁን ጦር ለማድረግ ቀጥቅጡ፤ ደካማውም «እኔ ብርቱ ነኝ» ይበል።
\s5
\v 11 እናንተ በዙሪያ ያላችሁ አሕዛብ ሁሉ፥ ፈጥናችሁ ኑ፥ በአንድነትም ተሰብሰቡ። እግዚአብሔር ሆይ ኃያላን ተዋጊዎችህን ወደዚያ አውርድ።
\s5
\v 12 በዙሪያ ባሉ አሕዛብ ሁሉ ላይ ልፈርድ በዚያ እቀመጣለሁና፤ አሕዛብ ይነሡ፥ ወደ ኢዮሳፍጥም ሸለቆ ይምጡ።
\v 13 መከሩ ደርሶአልና ማጭድ ላኩ፥ የወይኑ መጭመቂያ ሞልቶ እየፈሰሰ ነውና ኑ ወይኑን ርገጡ፥ ክፋታቸው በዝቶአልና።
\s5
\v 14 የእግዚአብሔር ቀን በፍርድ ሸለቆ ውስጥ ቀርቦአልና፤ ሁካታ፥ በፍርድ ሸለቆ ውስጥ ሁካታ አለ።
\v 15 ፀሐይና ጨረቃ ይጨልማሉ፥ ከዋክብትም ብርሃናቸውን ይከለክላሉ።
\s5
\v 16 እግዚአብሔር ከጽዮን ይጮኻል፥ከኢየሩሳሌም ድምጹን ከፍ አድርጎ ያሰማል። ሰማይና ምድር ይናወጣሉ፥ እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ መጠለያ፥ ለእስራኤልም ሕዝብ መመሸጊያ ይሆናል።
\v 17 «ስለዚህ በተቀደሰ ተራራዬ በጽዮን የምኖር እግዚአብሔር አምላካችሁ እኔ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ። ኢየሩሳሌም የተቀደሰች ትሆናለች፥ ዳግመኛም ሠራዊት አያልፍባትም።
\s5
\v 18 በዚያን ቀን እንዲህ ይሆናል፥ ተራሮች አዲስ ወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፥ ኮረብቶችም ወተት ያፈስሳሉ፥የይሁዳ ጅረቶች ሁሉ ውኃ ያጎርፋሉ፥ ከእግዚአብሔር ቤት ምንጭ ይመነጫል፥ የሰጢምንም ሸለቆ ያጠጣል።
\v 19 በይሁዳ ሕዝብ ላይ ግፍ ፈጽመዋልና፥ በምድራቸው የንጽሐንን ደም አፍስሰዋልና፤ ግብጽ ባድማ፥ ኤዶምም ምድረ በዳ ትሆናለች።
\s5
\v 20 ነገር ግን ይሁዳ ለዘላለም ይኖራል፥ኢየሩሳሌምም ከትውልድ ትውልድ ትኖራለች።
\v 21 ያልተበቀልኩትን ደማቸውን እበቀላለሁ፤» እግ ዚአብሔር በጽዮን ይኖራል።