am_ulb/28-HOS.usfm

435 lines
42 KiB
Plaintext

\id HOS
\ide UTF-8
\h ሆሴዕ
\toc1 ሆሴዕ
\toc2 ሆሴዕ
\toc3 hos
\mt ሆሴዕ
\s5
\c 1
\p
\v 1 በይሁዳ ነገሥታት በዖዚያን፥ በኢዮአታም፥ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን፤በእስራኤልም ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን ወደ ብዔር ልጅ ወደ ሆሴዕ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።
\v 2 እግዚአብሔር በሆሴዕ አማካይነት መናገር በጀመረ ጊዜ እንዲህ አለው፦«ምድሪቱ እኔን በመተው ታላቅ ምንዝርናን እያደረገች ነውና፥ሂድ፥የምንዝርናዋ ፍሬዎች የሆኑ ልጆች ያሏትን ሴተኛ አዳሪዋን ሚስትህ አድርገህ ውሰድ።»
\s5
\v 3 ስለዚህም ሆሴዕ ሄዶ የዴቤላይምን ሴት ልጅ ጎሜርን አገባ፤እርስዋም ጸነሰች፥ ወንድ ልጅም ወለደችለት።
\v 4 እግዚአብሔርም አለው፦ «ከጥቂት ጊዜ በኋላ በኢይዝራኤል ስለነበረው ደም ማፍሰስ የኢዩን ቤት እቀጣለሁና፥ የቤተ እስራኤልንም መንግሥት እንዲያከትም አደርጋለ ሁና ስሙን ኢይዝራኤል ብለህ ጥራው።
\v 5 ይህም በኢይዝራኤል ሸለቆ ውስጥ የእስራኤልን ቀስት በምሰብርበት ቀን ይፈጸማል።»
\s5
\v 6 ጎሜር እንደገና ጸነሰች፥ ሴት ልጅም ወለደች። በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ሆሴዕን እንዲህ አለው፦ «ቅንጣት ታህል ይቅር እላቸው ዘንድ ከእንግዲህ ወዲያ የእስራኤልን ቤት አልምርምና ስሟን ሎሩሃማ ብለህ ጥራት።
\v 7 ነገር ግን የይሁዳን ቤት እምራለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር አምላካችው በራሴ አድናቸዋለሁ እንጂ በቀስት፥ በሰይፍ፥ በጦርነት፥ በፈረሶች ወይም በፈረሰኞች አላድናቸውም።»
\s5
\v 8 ጎሜር፥ ሎሩሃማን ጡት ካስጣለቻት በኋላ ጸነሰች፥ሌላ ወንድ ልጅም ወለደች።
\v 9 በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር እንዲህ አለው፦«ሕዝቤ አይደላችሁምና፥ እኔም አምላካችሁ አይደለሁምና ስሙን ሎዓሚ ብለህ ጥራው ።»
\s5
\v 10 ነገር ግን የእስራኤል ቤት ቁጥር ሊለካ ወይም ሊቆጠር እንደማይችል የባሕር አሸዋ ይሆናል። «ሕዝቤ አይደላችሁም» በተባሉበት ቦታ፥«የሕያው አምላክ ሕዝብ ናችሁ» ይባላሉ።
\v 11 የይሁዳ ሕዝብና የእስራኤል ሕዝብ በአንድነት ይሰበሰባሉ። የኢይዝራኤል ቀን ታላቅ ይሆናልና፥ ለራሳቸው አንድ መሪ ይሾማሉ፥ ከምድሪቱም ይውጣሉ።
\s5
\c 2
\p
\v 1 ወንድሞቻችሁን «ሕዝቤ!»፥ እኅቶቻችሁንም «የተራራላችሁ» በሏቸው።
\s5
\v 2 እርሷ ሚስቴ አይደለችምና እኔም ባሏ አይደለሁምና ከእናታችሁ ጋር ተምዋግቱ፥ ተምዋገቱ። ሴተኛ አዳሪነቷን ከፊቷ፥ምንዝርናዋንም ከጡቶቿ መካከል ታስወግድ።
\v 3 አለበለዚያ እርቃንዋን እስክትቀር እገፋታልሁ፥እንደ ተወለደችበትም ቀን እርቃንዋን እገልጣለሁ። እንደ ምድረ በዳ እንደ ደረቅም ምድር አደርጋታለሁ፥ተጠምታ እንድትሞት አደርጋለሁ።
\s5
\v 4 የሴተኛ አዳሪነት ልጆች ናቸውና ለልጆቿ ቅንጣት ምሕረት የለኝም።
\v 5 ምክንያቱም እናታቸው ሴተኛ አዳሪ ናትና፥ የጸንሰቻቸውም በአሳፋሪ ተግባር ነውና። እርሷም ፦«እንጀራዬንና ውኃዬን፥ሱፌንና ሐሬን፥ዘይቴንና መጠጤን ይሰጡኛልና ከውሽሞቼ ኋላ እሄዳለሁ» አለች።
\s5
\v 6 ስለዚህ መንገድዋን በእሾህ ለመዝጋት አጥር እሠራለሁ። መንገድዋንም እንዳታግኝ ቅጥር እገነባባታለሁ።
\v 7 ውሽሞችዋን ትከታተላቸዋለች ነገር ግን አትደርስባቸውም፤ትፈልጋቸዋለች ነገር ግን አታገኛቸውም። ከዚያም በኋላ ፦«አሁን ካለሁበት የበፊቱ ይሻላልና ወደ መጀመሪያው ባሌ እመለሳለሁ» ትላለች።
\s5
\v 8 እህሉን፥አዲሱን ወይን ጠጅና ዘይቱን የሰጠኋት፣ በአልን ያገለገሉበትን ብርና ወርቅ ያበዛሁላት እኔ እንደ ሆንኩ አላወቀችም።
\v 9 ስለዚህ እህሏን በመከር ጊዜ፥ አዲሱንም የወይን ጠጄን በወቅቱ መልሼ እወስዳለሁ። እርቃኗንም የምትሸፍንበትን ሱፌንና ሐሬን መልሼ እወስዳለሁ።
\s5
\v 10 ከዚያም ውሽሞችዋ እያዩ እርቃንዋን እስክትቀር ድረስ እገፋታለሁ፥ ከእጄም ማንም አያስጥላትም።
\v 11 ሁሉንም ክብረ በዓላቷን፦ የደስታ በዓላቷን፥የአዲስ ጨረቃ ክብረ በዓላቷን፥ ሰንበታቷንና ዓመታዊ በዓላቷን አስቀራለሁ።
\s5
\v 12 «ውሽሞቼ የሰጡኝ ክፍያዎቼ ናቸው» የምትላቸውን ወይንዋንና የበለስ ዛፎችዋን አጠፋለሁ። ጫካ አደርጋቸዋለሁ፥ የዱር አራዊትም ይበሉዋቸዋል።
\v 13 ለበአል አማልክት ዕጣን ስላጠነችባቸው፥ በቀለበቶችዋና በጌጣ ጌጦቿ ራስዋን ስላስዋበችባቸው እና እኔን ረስታ ከውሽሞቿ ኋላ ስልሄደችባችው የደስታ በዓላት እቀጣታለሁ።» ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።
\s5
\v 14 ስለዚህ አመልሳታለሁ፥ ወደ ምድረ በዳ እወስዳታለሁ፥ በፍቅርም አነጋግራታለሁ።
\v 15 የወይን ተክሏን፥ የተስፋ በርም እንዲሆናት የአኮርን ሸለቆ መልሼ እሰጣታለሁ። በዚያም በወጣትነቷ ቀናት፥ ከግብጽ ምድር በወጣችባቸው ቀናት እንዳደረገችው ትመልስልኛለች።
\s5
\v 16 የእግዚአብሔር አዋጅ ይህ ነው፦«በዚያን ቀን እንዲህ ይሆናል፥ ባሌ ብለሽ ትጠሪኛለሽ፤ ከእንግዲህ ወዲያም በአሌ ብለሽ አትጠሪኝም።
\v 17 የበአልን አማልክት ስም ከአንደበቷ አስወግዳለሁና ስሞቻቸው ከእንግዲህ ወዲያ አይታሰቡም።
\s5
\v 18 በዚያን ቀን ከዱር አራዊት፥ ከሰማይ አእዋፍና በምድር ከሚንቀሳቀሱት ነገሮች ጋር ቃል ኪዳን አደርግላቸዋለሁ። ቀስትን፥ ሰይፍንና ጦርነትን ክምድሪቱ አስወግዳለሁ፥ በሰላምም እንድትጋደሙ አደርጋችኋለሁ።
\s5
\v 19 ለዘላለም ባልሽ ልሆን ቃል እገባልሻለሁ። በጽድቅ፥ በፍትሕ፥ በኪዳን ታማኝነትና በምሕረት ባልሽ ልሆን ቃል እገባልሻለሁ።
\v 20 በታማኝነት ባልሽ ልሆን ቃል እገባልሻለሁ። አንቺም እኔን እግዚአብሔርን ታውቂያለሽ።
\s5
\v 21 የእግዚአብሔር አዋጅ ይህ ነው፦ በዚያን ቀን እመልሳልሁ። «ለሰማያት እመልሳለሁ፥ እነርሱም ለምድር ይመልሳሉ።
\v 22 ምድርም ለእህሉ፥ ለአዲሱ ወይን ጠጅና ለዘይቱ ትመልሳለች፥ እነርሱም ለኢይዝራኤል ይመልሳሉ።
\s5
\v 23 ስለ ራሴ ስል በምድሪቱ ላይ እተክላታልሁ፥ ሎሩሃማንም እምራታለሁ። ሎዓሚንንም፦ አንተ ዓሚ አታህ ነህ እለዋለሁ፤ እነርሱም አንተ አምላካችን ነህ ይሉኛል።»
\s5
\c 3
\p
\v 1 እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦«እንደገና ሂድ፥ ባልዋ የሚወዳትን ነገር ግን አመንዝራ የሆነችውን ሴት ውደድ። ወድ ሌሎች አማል ክት ዘወር ቢሉና የዘቢብ እንጎቻ ቢወዱም እንኳን፥ እኔ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ እንደምወድ ውደዳት።»
\v 2 ስለዚህ በአሥራ አምስት የብር ሳንቲሞችና በአንድ ቆሮስ ተኩል ገብስ ገዛኋት።
\v 3 እኔም፦ «ከእኔ ጋር ብዙ ቀናት ኑሪ፥ ሴተኛ አዳሪ ወይም የሌላ የማንም ሰው አትሁኚ፥እኔም እንዲዚሁ ከአንቺ ጋር እሆናለሁ» አልኳት።
\s5
\v 4 የእስራኤል ሕዝብ ያለ ንጉሥ፥ ያለ መስፍን፥ ያለ መሥዋዕት፥ ያለ ድንጋይ ዓምድ፥ ያለ ኤፉድ ወይም ያለ ቤተሰብ ጣዖት ለብዙ ቀናት ይኖራሉ።
\v 5 ከዚያም በኋላ የእስራኤል ሰዎች ይመለሳሉ፥ እግዚአብሔር አምላካቸውንና ንጉሣቸውን ዳዊትንም ይፈልጋሉ። በመጨረሻዎቹም ቀናት በእግዚአብሔርና በበረከቱ ፊት እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ።
\s5
\c 4
\p
\v 1 የእስራኤል ሕዝብ ሆይ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። እውነተኛነት፥ ለኪዳን ታማኝነት፥ እግዚአብሔርን ማወቅ በምድሪቱ የለምና እግዚ አብሔር በምድሪቱ ከሚኖሩ ጋር ሙግት አለው።
\v 2 መርገም፥ መዋሽት፥ መግደል፥ መስረቅና ማመንዘር በዚያ አለ። ሕዝቡ ስምምነቶችን ሁሉ ያፈርሳሉ፥ ሳያቋርጡ ደም ይፋሰሳሉ።
\s5
\v 3 ስለዚህ ምድሪቱ ደረቀች፥ በእርሷ የሚኖሩ ሁሉ መነመኑ፥ የዱር አራዊትና የሰማይ አእዋፍ፥ የባሕርም ዓሦች እንኳን አለቁ።
\s5
\v 4 ነገር ግን ማንም ሙግቱን አያቅርብ፥ማንም ሌላውን ማንንም አይክሰስ። ምክንያቱም እኔ የምከስው እናንተን ካህናቱን ነውና።
\v 5 እናንተ ካህናት በቀን ትሰናከላላችሁ፥ ነቢያቶቹም ከእናንተ ጋር በሌሊት ይሰናከላሉ፥ እናታችሁንም አጠፋታለሁ።
\s5
\v 6 ሕዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል። እናንተ ካህናት ዕውቀትን ጥላችኋልና እኔም እጥላችኋለሁ። እኔ አምላካችሁ ብሆንም ሕጌን ረስታችኋል፥ እኔም ልጆቻችሁን እረሳለሁ።
\v 7 ካህናቱ በበዙ መጠን የሚሠሩብኝ ኃጢአት በዝቶአል። ክብራቸውን ወደ ውርድት እለውጠዋለሁ።
\s5
\v 8 የሕዝቤን ኃጢአት ይመገባሉ፥ ክፋታቸውም እንዲበዛ ይቋምጣሉ።
\v 9 በካህናቱ ላይ እንደሚሆን እንዲሁ በሕዝቡም ላይ ይሆናል፦ ስለ ልማዶቻቸው እቀጣቸዋለሁ፤ እንደ ሥራቸውም አከፍላቸዋለሁ።
\s5
\v 10 ከእኔ ከእግዚአብሔር ርቀው ሄደዋልና ትተውኛልምና፤ይበላሉ ግን አይጠግቡም፥ ያመነዝራሉ ግን አይበዙም።
\s5
\v 11 ሴሰኝነት፥ የወይን ጠጅና አዲስ የወይን ጠጅ ማስተዋላቸውን ወስዶታል።
\v 12 የእንጨት ጣዖቶቻችውን ያማክራሉ፥ በትሮቻቸውም ይተነብዩላቸዋል። የሴሰኝነት መንፈስ አስቶአቸዋል፥ እኔን አምላካቸውንም ትተውኛል።
\s5
\v 13 በተራሮች ጫፍ ላይ ይሠዋሉ፥ ጥላው መልካም ነውና ከባሉጥ፥ ከኮምቦልና ከአሆማ ዛፍ በታች በኮረብቶች ላይ ያጥናሉ። ስለዚህ ሴቶች ልጆቻችሁ የዝሙት ርኩሰት ይፈጽማሉ፥ የልጆቻችሁ ሚስቶች ያመነዝራሉ።
\v 14 ሴቶች ልጆቻችሁ የዝሙት ርኩሰትን በወደዱ ጊዜ፥ ወይም የልጆቻችሁ ሚስቶች ባመነዘሩ ጊዜ አልቀጣቸውም። ምክንያቱም ወንዶቹ ራሳቸውን ለሴተኛ አዳሪዎች ሰጥተዋልና፥ እንዲሁም ከቤተ ጣዖት ሴተኛ አዳሪዎች ጋር ርኩሰትን ለመፈጸም መሥዋዕት ይሰዋሉና። ስለዚህ ይህ የማያስተውል ሕዝብ ይጠፋል።
\s5
\v 15 እስራኤል ሆይ አንቺ ብታመነዝሪም፥ ይሁዳ በደለኛ አይሁን። እናንተ ሰዎች፥ ወደ ጌልጌላ አትሂዱ፥ ወደ ቤትአዌንም አትውጡ። ሕያው እግዚአብሔርን ብላችሁም አትማሉ።
\v 16 እስራኤል እንደ እልኽኛ ጊደር በእልኽኝነት ሄዳለችና፤ እንዴት እግዚአብሔር በለመለመ መስክ እንዳ ሉ ጠቦቶች ያሰማራታል?
\s5
\v 17 ኤፍሬም ራሱን ከጣዖታት ጋር አጣምሮአል፤ብቻውን ተውት።
\v 18 አስካሪ መጠጣቸው ባላቀ ጊዜ እንኳን ማመንዘራቸውን አያቆ ሙም፤ገዢዎቿም ነውራቸውን እጅግ ይወዳሉ።
\v 19 ነፋሱ በክንፎቹ ይጠቀልላታል፥ ከመሥዋዕቶቻቸውም የተነሳ ይፍራሉ።
\s5
\c 5
\p
\v 1 በእናንተ በሁላችሁ ላይ ፍርድ እየመጣ ነውና፤ ካህናት ሆይ ይህን ስሙ! የእስራኤል ቤት ሆይ ልብ በሉ! የንጉሡ ቤት ሆይ ስሙ! እናንተ፥ በምጽጳ ላይ ወጥመድ፥ በታቦርም ላይ የተዘረጋ መረብ ሆናችኋል።
\v 2 ዓመጸኞች በማረድ እጅግ በርትተዋል፥ ሁሉንም እገራቸዋለሁ።
\s5
\v 3 ኤፍሬምን አውቀዋለሁ፥ እስራኤልም ከእኔ አልተሰወረችም። ኤፍሬም፥ አንተ አሁን እንደ ሴተኛ አዳሪ ሆነሃል፤ እስራኤልም ረክሳልች።
\v 4 ሥራቸው ወደ እኔ ወደ አምላካቸው እንዲመለሱ አይፈቅድላቸውም፥ የአመንዝራነት መንፈስ በውስጣቸው አለ፥ እኔን እግዚአብሔርን አላወቁኝም።
\s5
\v 5 የእስራኤል ትዕቢት ይመሰክርባታል፤ ስለዚህ እስራኤልና ኤፍሬም በበደላቸው ይሰናከላሉ፤ ይሁዳም ከእነርሱ ጋር ትሰናከላለች።
\v 6 በጎቻቸውንና ከብቶቸውን ይዘው እግዚአብሔርን ፍልጋ ይሄዳሉ፥ ነገር ግን ከእነርሱ ተለይቶ ተመልሷልና አያገኙትም።
\v 7 ዲቃሎች ልጆችን ወልደዋልና ለእግዚአብሔር ታማኞች አልሆኑም። አሁንም የወር መባቻ በዓላቱ እነርሱን ከእርሻቸው ጋር ይበሉአቸዋል።
\s5
\v 8 በጊብዓ መለከትን፥በራማም እንቢልታን ንፉ። «ቢንያም ሆይ እንከተልሃለን!» እያላችሁ የጦርነት ድምጽ አሰሙ።
\v 9 በቁጣው ቀን ኤፍሬም የፈረሰ ይሆናል። በእስራኤል ነገዶች መካከል በእርግጥ ሊሆን ያለውን አውጄአለሁ።
\s5
\v 10 የይሁዳ መሪዎች የድምበር ድንጋይ እንደሚነቅሉት ናቸው። ቁጣዬን በላያቸው እንደ ውኃ አፈስሳለሁ።
\v 11 ለጣዖታት ሊሰግድ ወስኖአልና ኤፍሬም ደቀቀ፥ በፍርድ ደቀቀ።
\s5
\v 12 እኔ ለኤፍሬም እንደ ብል፥ለይሁዳም ቤት እንደ ነቀዝ እሆናለሁ።
\v 13 ኤፍሬም በሽታውን ባየ ጊዜ፥ ይሁዳም ቁስሉን ባየ ጊዜ፤ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፥ ይሁዳም ወደ ታላቁ ንጉሥ መልእክተኞችን ላከ። ነገር ግን እርሱ ሊያድናችሁ፥ ቁስላችሁንም ሊፈውስ አልቻለም።
\s5
\v 14 ስለዚህ በኤፍሬም ላይ እንደ አንበሳ፥ በይሁዳም ላይ እንደ አንበሳ ደቦል እሆናለሁ። እኔ፥ አዎ እኔ፥ እገነጣጥላለሁ፥ እሄዳለሁ፥ እወስዳቸዋለሁ፥ የሚያድናቸውም ማንም የለም።
\v 15 በደላቸውን እስኪያውቁና ፊቴን እስኪፈልጉ ድርስ፥ በመከራቸው አጥብቀው እስኪፈልጉኝ ድረስ፥ እሄዳለሁ፥ ወድ ስፍራዬም እመለሳለሁ።
\s5
\c 6
\p
\v 1 ኑ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ። እርሱ ገነጣጥሎናል፥ ነገር ግን እርሱ ይፈውሰናል፤ እርሱ አቁስሎናል፥ ነገር ግን እርሱ ቁስላችንን አስሮ ይጠግናል።
\v 2 ከሁለት ቀን በኋላ ያበረታናል፥ በሦሥተኛው ቀን ያሥነሣናል፥ እኛም በፊቱ እንኖራለን።
\v 3 አወጣጡ እንደ ንጋት የታመነ ነው፤ እንደ ካፊያ፥ ምድሪቱን እንደሚያጠጣ እንደ ጸደይ ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።
\s5
\v 4 ኤፍሬም ሆይ ምን ላድርግልህ? ይሁዳ ሆይ ምን ላድርግልህ? ታማኝነታችሁ እንደ ማለዳ ደመና፥ በጠዋት እንደሚጠፋ ጤዛ ነው።
\v 5 ስለዚህ በነቢያቱ ቆራረጥኋቸው፥ በአፌም ቃል ገደልኋቸው። ፍርዶችህ እንደሚያንጸባርቅ ብርሃን ናቸው።
\s5
\v 6 ታማኝነትን እሻለሁና፥መሥዋዕትንም አይደለም፥ከሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ይልቅ እኔን እግዚአብሔርን ማወቅን እሻለሁ።
\v 7 እንደ አዳም ኪዳኑን አፍርሰዋል፤ ለእኔ ያልታመኑ ነበሩ።
\s5
\v 8 ገልዓድ የክፉ አድራጊዎች ከተማ ነው፥ በደም ዱካ ተሞልቷል።
\v 9 የቀማኞች ቡድን የሚዘርፉትን አድብተው እንደሚጠባበቁ፥ ካህናቱም በሴኬም መንገድ ላይ ሰው ለመግደል በቡድን ተደራጅተዋል፤ አሳፋሪም ወንጀል ይፈጽማሉ።
\s5
\v 10 በእስራኤል ቤት የሚያሰቅቅ ነገር አይቻለሁ፤ በዚያ የኤፍሬም ምንዝርና አለ፥ እስራኤልም ተበክሏል።
\v 11 የሕዝቤን ምርኮ በምመልስበት ጊዜ፥ ይሁዳ ሆይ ለአንተም መከር ተቀጥሮልሃል።
\s5
\c 7
\p
\v 1 ማታለልን ይለማመዳሉና እስራኤልን ለመፈወስ በፈለግሁ ጊዜ ሁሉ የኤፍሬም ኃጢአት፥ የሰማሪያም ክፋት ይገለጣል፤ ሌባ ወደ ውስጥ ይገባል፥ የቀማኞች ቡድን በመንገድ ላይ አደጋ ያደርሳል።
\v 2 ክፋታቸውን ሁሉ እንደማስታውስ በልባቸው አይገነዘቡም። ሥራቸው ከቦአቸዋል፥ በፊቴም ናቸው።
\s5
\v 3 በክፋታቸው ንጉሡን፥ በሐሰታቸውም አለቆቹን ደስ ያሰኛሉ።
\v 4 የተቦካው ሊጥ ኩፍ እስኪል ድረስ እሳቱን መቆስቆስ እንድሚያቆም፥ ጋጋሪ እንደሚያነድበት ምድጃ፥ ሁሉም አመንዝራ ናቸው።
\v 5 በንጉሣችን ቀን አለቆች በወይን ጠጅ ትኩሳት ታመሙ። እርሱም ለፌዘኞች እጁን ዘረጋ።
\s5
\v 6 እንደ ምድጃ በሆነ ልባቸው፥ አታላይ እቅዶቻችውን ይወጥናሉ። ቁጣቸው ሌሊቱን ሁሉ ይጤሳል፥ በማለዳም እንደሚንቀለቀል እሳት እጅጉን ይነድዳል።
\v 7 ሁሉም እንደ ምድጃ የጋሉ ናቸው፥ ግዢዎቻቸውንም ይበላሉ። ነገሥታቶቻቸው ሁሉ ወደቁ፥ ከመካከላቸውም ማንም ወደ እኔ አልተጣራም።
\s5
\v 8 ኤፍሬም ከአሕዛብ ጋር ተደባለቅ፥ ኤፍሬም ያልተገለበጠ ቂጣ ነው።
\v 9 እንግዶች ጉልበቱን በሉት፥ እርሱ ግን አላወቀም። ሽበትም ወጣበት፥ እርሱ ግን አላወቀም።
\s5
\v 10 የእስራኤል ትዕቢት ይመሰክርበታል፤ ነገር ግን ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር አልተመለሱም፥ በዚህም ሁሉ አልፈለጉትም።
\v 11 ኤፍሬም ማስተዋል እንደሌላትና ተላላ እንደ ሆነች ርግብ ነው፤ ወደ ግብጽ ይጣራል፥ ወደ አሦርም ይበራል።
\s5
\v 12 ሲሄዱ መሬቤን እዘረጋባቸዋለሁ፥ እንደ ሰማይ አዕዋፍ አወርዳቸዋለሁ። እንደ መንጋ በሚተምሙብት እቀጣቸዋለሁ።
\v 13 ወዮ ለእነርሱ! ከእኔ ርቀው ሄደዋልና። ጥፋት ይመጣባቸዋል! በእኔ ላይ አምፀዋል! ላድናቸው ወደድሁ፥ እነርሱ ግን ሐሰትን ተናገሩብኝ።
\s5
\v 14 ከልባቸው ወደ እኔ አይጮኹም፥ ነገር ግን በአልጋዎቻችው ላይ ያለቅሳሉ። እህልና አዲስ ወይን ጠጅ ለማግኘት ራሳቸውን ለይተዋል፥ ከእኔም ዘወር ብለዋል።
\v 15 እኔ ባሠለጠናቸውም፥ ክንዶቻችውንም ባበረታ፤ እነርሱ ግን ክፉ ነገርን አሴሩብኝ።
\s5
\v 16 ተመልሰዋል፥ ነገር ግን ወደ እኔ ወደ ልዑሉ አልተመለሱም። ዒላማውን እንደ ሳተ ቀስት ናቸው። ከምላሳቸው ነውረኛነት የተነሳ አለቆቻችው በሰይፍ ይወድቃሉ። ይህም በግብጽ ምድር ለመሳለቂያ ይሆንባቸዋል።
\s5
\c 8
\p
\v 1 «መለከትን በከንፈሮችህ ላይ አድርግ። በእኔ በእግዚአብሔር ቤት ላይ ንስር እየመጣ ነው። ሕዝቡ ኪዳኔን አፍርሰዋልና በሕጌም ላይ አምጸዋልና ይህ ይሆናል።
\v 2 'አምላኬ፥ በእስራኤል ያለን እኛ እናውቅሃለን' እያሉ ወደ እኔ ይጮሃሉ።
\v 3 ነገር ግን እስራኤል በጎ የሆነውን ነገር ጥሎአል፥ ጠላትም ያሳድደዋል።
\s5
\v 4 ነገሥታትን አነገሡ፥ በእኔ ግን አይደለም። እኔም ሳላውቅ መሳፍንቶችን አደረጉ። በብራቸውና በወርቃቸው ለራሳቸው ጣዖታትን ሠሩ፥ ነገር ግን ለጥፋታቸው ብቻ ነበር።»
\v 5 ነቢዩ፦«ሰማርያ ሆይ ጥጃህን ወዲያ ጥሎታል» አለ። እግዚአብሔር፦«ቁጣዬ በዚህ ህዝብ ላይ ነድዶአል። ሳይነጹ እስከ መቼ ይኖራሉ? አለ።
\s5
\v 6 ይህ ጣዖት ከእስራኤል የመጣ ነው፤ ባለሙያ ሠራው፥ እርሱ አምላክ አይደለም! የሰማርያ ጥጃ ይደቅቃል።
\v 7 ሕዝቡ ነፋስን ዘርተዋል፥ ዐውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ። ያልተሰበሰበው እህል ዛላ የለውም፤ ዱቄትም አይገኝበትም። ለማፍራት ቢደርስም እንኳን እንግዶች ይበሉታል።
\s5
\v 8 እስራኤል ተውጦአል፤ በአሕዛብም መካከል እንደማይጠቅም ነገር ወድቀዋል።
\v 9 ሁሌ ብቻውን እንደሚሆን የዱር አህያ፥ወደ አሦር ሄደዋልና። ኤፍሬም ለራሷ ወዳጆችን ገዛች።
\v 10 በአሕዛብ መካከል ወዳጆችን ቢገዙም፥ እኔ እሁን አንድ ላይ እሰበስባቸዋለሁ። ከመሳፍንቱ ንጉሥ ጭ ቆና የተነሳም ሊመነምኑ ይጅምራሉ።
\s5
\v 11 ኤፍሬም ለኃጢአት ማስተሰሪያ መሠዊያ ቢያበዛም፥በዚያ ፈንታ ግን የኃጢአት መሥሪያ መሠዊያዎች ሆኑ።
\v 12 ሕጌን አሥር ሺህ ጊዜ ያህል ፃፍሁላቸው፥ እነርሱ ግን እንግዳ እንደ ሆነ ነገር ተመለከቱት።
\s5
\v 13 መሥዋዕቴን ይሠዋሉ፤ ሥጋ ይሠዋሉ፥ ይበሉታልም፤ እኔ እግዚአብሔር ግን አልተቀበልኳቸውም። አሁን ክፋታቸውን አስባለሁ፥ ኃጢአታቸውንም እቀጣለሁ። ወደ ግብጽ ይመለሳሉ።
\v 14 እስራኤል፥ እኔን ሠሪውን ረሳ፥ አብያተ መንግሥትንም ገነባ። ይሁዳ ብዙ ከተሞችን አጸና፥ እኔ ግን በከተሞቹ ላይ እሳት እሰድዳለሁ፤ ምሽጎቹንም ታጠፋለች።
\s5
\c 9
\p
\v 1 እስራኤል ሆይ፥ አንተ የታመንክ አይደለህምና፥ አምላክህንም ትተሃልና፤ ሌሎች ሕዝቦች ደስ እንደሚላቸው፥ ደስ አይበልህ። በአውድዎች ሁሉ ላይ ሴተኛ አዳሪ የምትጠይቀውን ዋጋ ለመክፈል ወድደሃል።
\v 2 ነገር ግን አውድማውና የወይን መጭመቂያው አይመግባቸውም፥ አዲሱ የወይን ጠጅም ይጥላታል።
\s5
\v 3 በእግዚአብሔር ምድር ላይ አይኖሩም፤ ኤፍሬም ወደ ግብጽ ይመለሳል፥ ደግሞም አንድ ቀን በአሦር የረከሰ ምግብ ይበላሉ።
\v 4 ለእግዚአብሔር የወይን ጠጅ ቁርባን አያፈሱም፤ ደስም አያሰኙትም። መስዋዕታቸው እንደ ሐዘንተኞች ምግብ ይሆንባቸዋል፦ የሚበሉት ሁሉ ይረክሳሉ። ምግባቸው ለእነርሱ ብቻ የሚሆን ነውና ወደ እግዚአብሔር ቤት ሊመጣ አይችልም።
\s5
\v 5 በእግዚአብሔር በዓል ቀን፥ በዓመት በዓል ቀን ምን ታድርጋላችሁ?
\v 6 ተመልከቱ፥ ከጥፋት ቢያመልጡ እንኳን ግብጽ ትሰበስባቸዋለች፥ ሜፎስም ትቀብራቸዋለች። የብር ክምችታቸውን ሳማ ይውጠዋል፥ድንኳኖቻቸውንም እሾህ ይሞላዋል።
\s5
\v 7 የቅጣት ቀን እየመጣ ነው፥የበቀል ቀን እየመጣ ነው። እስራኤል ሁሉ ይህን ይወቅ። ከክፋትህና ከጠላትነትህ የተነሳ፤ ነቢዩ ሞኝ፥ በመንፈስ የሚነዳውም ሰው እብድ ሆኖእል።
\s5
\v 8 ከአምላኬ ጋር የሆነው ነቢይ የኤፍሬም ጠባቂ ነው፤ ነገር ግን የወፍ ወጥመድ በመንገዱ ሁሉ ነው፥በአምላኩም ቤት ጠላትነት አለበት።
\v 9 በጊብዓ ዘመን እንደነበረው ራሳቸውን እጅግ አርክሰዋል። እግዚአብሔር ክፋታቸውን ያስባል፥ ኃጢአታቸውንም ይቀጣል።
\s5
\v 10 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥«እስራኤልን ያገኘሁበት ጊዜ፥ በምድረ በዳ ወይን እንደማግኘት ነበረ። እንደ በለስ ዛፍ የፍሬ ጊዜ የመጀመሪያ እሸት አባቶቻችሁን አገኘሁ።ነገር ግን ወደ ብዔልፌጎር ሄዱ፥ራሳቸውንም ለዚያ አሳፋሪ ጣዖት ሰጡ።እንደወደዱት ጣዖት እነርሱም የተጠሉ ሆኑ።
\s5
\v 11 የኤፍሬም ክብር እንደ ወፍ በሮ ይሄዳል።መውለድ፥ ማርገዝና መፀነስ የለም።
\v 12 ልጆችን ቢያሳድጉ እንኳን፥ አንዳቸውም እሰከማይቀሩላቸው ድረስ እወስድባቸዋለሁ። ከእነርሱ ዘወር ባልሁ ጊዜ፥ ወዮ ለእነርሱ!
\s5
\v 13 ኤፍሬም እንደ ጢሮስ በለምለም ስፍራ ተተክሎ አየሁት፥ ነገር ግን ኤፍሬም ልጆቹን ለሚያርዳቸው አሳልፎ ይሰጣል።
\v 14 እግዚአብሔር ሆይ ስጣቸው፤ ምን ትሰጣቸዋለህ? የሚጨነግፍ ማኅፀንና ወተት የማይሰጡ ጡቶች ስጣቸው።
\s5
\v 15 በጌልጌላ ካደረጉት ክፋታቸው ሁሉ የተነሳ፥ በዚያ እነርሱን መጥላት ጀመርኩ። ከክፉ ሥራቸው የተነሣ፥ ከቤቴ አስወጣቸዋለሁ። ከእንግዲህ ወዲያ አልወዳቸውም፤ አለቆቻቸው ሁሉ ዓመጸኞች ናቸው።
\s5
\v 16 ኤፍሬም በበሽታ ተመታ፤ሥራቸውም ደረቀ፥ ፍሬም አይሰጡም። ልጆች ቢወልዱም እንኳን፥ የተወደዱ ልጆቻቸውን እገድላለሁ።»
\v 17 አልታዘዙትምና አምላኬ ይጥላቸዋል። በሕዝቦች መካከል ተንከራታች ይሆናሉ።
\s5
\c 10
\p
\v 1 እስራኤል ፍሬውን የሚሰጥ ያማረ ወይን ነው። ፍሬው በበዛ መጠን፥ መሠዊያ አብዝቶ ሠራ። ምድሩ አብዝቶ ባፈራ መጠን፥የተቀደሱ አ ምዶቹን አሳመረ።
\v 2 ልባቸው አታላይ ነው፥ አሁን በደላቸውን ሊሸከሙ ይገባል። እግዚአብሔር መሠዊያዎቻቸውን ያፈርሳል፤ የተቀደሱ አምዶቻቸውን ያጠፋል።
\s5
\v 3 አሁንም እነርሱ፦ «እግዚአብሔርን ስላልፈራን፥ ንጉሥ የለንም፤ ንጉሥሥ ምን ሊያደርግልን ይችል ነበር?» ይላሉ።
\v 4 ባዶ ቃላትን ይናገራሉ፥ በሐሠት መሃላም ኪዳን ያደርጋሉ። ስለዚህ ፍትሕ፥ በእርሻ ትልም ላይ እንደሚወጣ መርዛማ አረም ይወጣል።
\s5
\v 5 የሰማሪያ ነዋሪዎች ከቤትአዌን ጥጃዎች የተነሳ ይፈራሉ። በእነርሱና በውብታቸው ደስ ይሰኙ የነበሩ እነዚያ ጣዖት አምላኪ ካህናት እንደሚያልቅሱላቸው፣ ሕዝቡም ያለቅሱላቸዋል፤ ከእንግዲህ ወዲያ በዚያ የሉምና።
\v 6 ለታላቁ ንጉሥ እጅ መንሻ ወደ አሦር ይወሰዳሉ። ኤፍሬም ይዋረዳል፥ እስራኤልም የጣዖታትን ምክር በመከተሉ ያፍራል።
\s5
\v 7 የሰማርያ ንጉሥ፥ በውኃ ላይ እንዳለ የእንጨት ፍቅፋቂ ይጠፋል።
\v 8 የእስራኤል ኃጢአት የሆኑት፥ የክፋት ቅዱስ ቦታዎች ይጠፋሉ። እሾህና አሜክላ በመሠዊያዎቻቸው ላይ ይበቅላሉ። ሕዝቡ ተራሮችን፥ «ሸፍኑን!»፥ ኮረብታዎችንም፥ «ውደቁብን!» ይላሉ።
\s5
\v 9 እስራኤል ሆይ ከጊብዓ ዘመን አንስቶ ኃጢአት ሠራችሁ፥ በዚያም ጸንታችኋል። በጊብዓ ክፉ አድራጊዎች ላይ ጦርነት በድንገት አልደረሰባቸውምን?
\s5
\v 10 በወደድሁ ጊዜ እገሥጻቸዋለሁ። ሕዝቦች በአንድነት ይሰበሰቡባቸዋል፥ ስለ ድርብ ኃጢአታቸውም ያስሯቸዋል።
\v 11 ኤፍሬም እህል ማበራየት የምትወድ የተገራ ጊደር ነች፥ ስለዚህ በሚያምር ጫንቃዋ ላይ ቀንበር አኖራለሁ። በኤፍሬም ላይ ቀንበር አኖራለሁ፥ ይሁዳ ያርሳል፥ ያዕቆብም ብቻውን መከስከሻውን ይጎትታል።
\s5
\v 12 ጽድቅን ለራሳችሁ ዝሩ፥ የኪዳኑን ታማኝንት ፍሬም እጨዱ። እስኪመጣ፥ ጽድቅንም እስኪያዝንብባችሁ ድረስ እግዚአብሔርን የምትፈልጉበት ጊዜ ነውና፤ ያልታረሰ መሬታችሁን አለስልሱ።
\v 13 ክፋትን አረሳችሁ፥ግፍንም አጨዳችሁ። በስልታችሁና በወታደሮቻችሁ ብዛት ታምናችኋልና፥ የመታለልን ፍሬ በላችሁ።
\s5
\v 14 ስለዚህ በሕዝብህ መካከል የጦርነት ሽብር ይነሣል፥ የተመሸጉ ከተሞችህም ሁሉ ይጠፋሉ። እናቶች ከልጆቻችው ጋር እንደተከሰከሱበት፥ ስልማን በሰልፍ ቀን ቤትአርብኤልን እንዳጠፋበት ጊዜ ይሆናል።
\v 15 ስለዚህ ቤቴል ሆይ፥ ከታላቅ ክፋትሽ የተነሣ በአንቺም ላይ እንዲሁ ይሆናል። ንጋት ላይ የእስራኤል ንጉሥ ፈጽሞ ይጠፋል።»
\s5
\c 11
\p
\v 1 እስራኤል ወጣት በነበረበት ጊዜ ወደድኩት፥ ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት።
\v 2 አብዝቶ በተጠሩ መጠን፥ አብዝተው ራቁ። ለበአል አማልክት ሠው፥ ለጣዖታትም አጠኑ።
\s5
\v 3 ሆኖም ግን ኤፍሬምን መራመድ ያስተማርኩት እኔ ነበርኩ። ክንዶቻቸውን ይዤ ያነሳኋቸው እኔ ነበርኩ፥ እነርሱ ግን የተጠነቀቅሁላቸው እኔ እንደሆንሁ አላወቁም።
\v 4 በሰው ገመድ፥ በፍቅርም ማሰሪያ መራኋቸው። የመንጋጋዎቻቸውን ማሰሪያ እንደሚያላላ ሆንኩላቸው፥ ዝቅ ብዬም መገብኳቸው።
\s5
\v 5 ወደ ግብጽ ምድር አይመለሱምን? ወደ እኔ መመለስን እምቢ በማለታቸው አሦር አይገዛቸውምን?
\v 6 ሰይፍ በከተሞቻቸው ላይ ይወድቃል፥ የበሮቻቸውንም መቀርቀሪያ ያጠፋል፤ከገዛ ራሳቸው ዕቅድ የተነሳ ያጠፋቸዋል።
\v 7 ሕዝቤ ከእኔ ዘወር ለማለት ቆርጦአል። በከፍታ ወደ አለሁት ወደ እኔ ቢጣሩ እንኳ፥ማንም አይረዳቸውም።
\s5
\v 8 ኤፍሬም ሆይ እንዴት እተውሃለሁ? እስራኤል ሆይ እንዴት አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴት እንደ አዳማ አደርግሃለሁ? እንዴትስ እንደ ሲባዮ አደርግሃለሁ? ልቤ በውስጤ ተለውጦአል፤ መላው ርኅራኄዬ ተነሣሥቷል።
\v 9 ጽኑ ቁጣዬን አላመጣም፤ ኤፍሬምን ዳግመኛ አላጠፋም። እኔ አምላ ክ እንጂ ሰው አይደለሁምና፥በመካከልህ ቅዱሱ ነኝና፥በቁጣ አልመጣም።
\s5
\v 10 እነርሱም ከእኔ ከእግዚአብሔር በኋላ ይመጣሉ። እንደ እንበሳ አገሳለሁ። በእርግጥ አገሳለሁ፥ ሕዝቡም ከምዕራብ እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ።
\v 11 ከግብጽ እንደ ወፍ፥ ከአሦርም ምድር እንደ ርግብ እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ። በየቤቶቻቸውም አኖራቸዋለሁ።» ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።
\s5
\v 12 «ኤፍሬም በሐሰት፥ የእስራኤልም ቤት በማታለል ከበበኝ። ይሁዳ ግን እስካሁን ከእኔ ከአምላኩ ጋር ጸንቷል፥ ለእኔም ለቅዱሱ የታመነ ነ ው።»
\s5
\c 12
\p
\v 1 ኤፍሬም ነፋስ ይመገባል፥ የምሥራቅንም ነፋስ ይከተላል። ሐሰትንና ዓመፅን ያለማቋረጥ ያበዛል። ከአሦር ጋር ኪዳን ያደርጋሉ፥ የወይራ ዘይትም ወደ ግብጽ ይወስዳሉ።
\v 2 እግዚአብሔር ከይሁዳ ጋር ሙግት አለው፥ ያዕቆብንም ስላደረገው ይቀጣዋል፥ እንደ ሥራውም ይከፍለዋል።
\s5
\v 3 ያዕቆብ በማሕፀን ውስጥ የወንድሙን ተረከዝ ያዘ፥ በጎልማስነቱም ከአምላክ ጋር ታገለ።ከመልአኩም ጋር ታግሎ አሸነፈ።
\v 4 አልቅሶም በፊቱ ተቀባይነት እንዲያገኝ ለመነው። በቤቴል ከአምላክ ተገናኘ፥ በዚያም አምላክ ከእርሱ ጋር ተነጋገረ።
\s5
\v 5 እርሱም የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው፤የሚጠራበት ስሙም «እግዚአብሔር» ነው።
\v 6 ስለዚህ ወደ አምላካችሁ ተመለሱ። ለኪዳኑ ታማኝነትን፥እንዲሁም ፍትሕን ጠብቁ፤ሁል ጊዜም አምላካችሁን ተስፋ አድርጉ።
\s5
\v 7 ነጋዴዎቹ ሐሰተኛ ሚዛኖችን በእጆቻቸው ይዘዋል፤ ማጭበርበርን ይወዳሉ።
\v 8 ኤፍሬምም፦ «በእርግጥ እጅግ ባለጠጋ ሆኜአለሁ፥ ሀብትንም አግኝቼአለሁ። በሥራዬ ሁሉ ኃጢአት የሚሆን ምንም ዓይነት በደል አያገኙብኝም» ይላል።
\s5
\v 9 ከግብጽ ምድር አንስቶ ከአናንተ ጋር የሆንኩ አምላካችሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። እንደ ዓመት በዓላት ቀናት ዳግመኛ በድንኳኖች እንድትኖሩ አደርጋችኋለሁ።
\v 10 ለነቢያቶቹም ተናገርሁ፥ ስለ እናንተም ብዙ ራዕዮችን ሰጠኋቸው። በነቢይቶቹም አማካይነት ምሳሌዎችን ሰጠኋችሁ።»
\s5
\v 11 በገለዓድ ኃጢአት ካለ፥ በእርግጥ ሕዝቡ ከንቱ ነው። በጌልጌላ ወይፈኖችን ይሰዋሉ፥ መሠዊያዎቻቸው በታረሰ መሬት ላይ እንዳለ የድ ንጋይ ክምር ይሆናሉ።
\v 12 ያዕቆብ ወደ ሶሪያ ምድር ሸሸ፤ እስራኤልም ሚስት ለማግኝት አገለገለ፥ ሚስትም ለማግኘት የበጎችን መንጋ ይጠብቅ ነበረ።
\s5
\v 13 እግዚአብሔር በነቢይ አማካይነት እስራኤልን ከግብጽ አወጣ፥ በነቢይም አማካይነት ተጠነቀቀለት።
\v 14 ነገር ግን እግዚአብሔር ይቆጣ ዘነድ ኤፍሬም ክፉኛ አነሳሳው። ስለዚህ ጌታው የደሙን በደል በእርሱ ላይ ይደርጋል፥ አሳፋሪም ስለ ሆነው ሥራው የሚገባውን ይከፍለዋል።
\s5
\c 13
\p
\v 1 «ኤፍሬም በተናገረ ጊዜ መንቀጥቀጥ ነበረ። በእስራኤል መካከል ራሱን ከፍ ከፍ አደረገ፥ ነገር ግን በአልን በማምለኩ በደለኛ ሆነ፥ ሞተም።
\v 2 አሁንም አብዝተው ኃጢአት ሠሩ። ከብራቸው የተቀረጸ ምስል ሠሩ፥ ጣዖታት በሚቻለው መጠን በጥበብ ተሠርተዋል፥ ሁሉም የባለ ሙያ ሥራ ናቸው። ሕዝቡ ስለ እነርሱ እንዲህ ይላሉ፦ 'እነዚህ የሚሠው ሰዎች ጥጃዎችን ይስማሉ።'
\s5
\v 3 ስለዚህ እንደ ማለዳ ደመና፥በጠዋት እንደሚጠፋ ጤዛ፥ከአውድማ ላይ በነፋስ እንደሚወሰድ እብቅ፣ከጪስ ማውጫ እንደሚወጣ ጢስ ናቸ ው።
\s5
\v 4 ነገር ግን ከግብጽ ምድር ያወጣሁህ አምላክህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። ከእኔ በቀር አምላክ አታውቅም፥ ከእኔም በቀር ሌላ አዳኝ አታውቅም።
\v 5 በምድረ በዳ፥ በታላቅም የድርቀት ምድር አውቅሁህ።
\v 6 መሰማሪያ ባገኘህ ጊዜ ጠገብህ፥ በጠገብህም ጊዜ ልብህ ታበየ፤ከዚህም የተነሳ ረሳኽኝ።
\s5
\v 7 እንደ አንበሳ ሆንኩባቸው፥እንደ ነብርም በመንገዳቸው አደባለሁ።
\v 8 ግልገሎቿን እንደ ተነጠቀች ድብ አጠቃቸዋለሁ። ደረታቸውን ቀድጄ ከፍታለሁ፥በዚያም እንደ አንበሳ እበላቸዋለሁ፥ እንደ ዱር አራዊትም እገነጣጥላቸዋለሁ።
\s5
\v 9 እስራኤል ሆይ በረዳትህ በእኔ ላይ ዓምፀሃልና ጥፋትህ እየመጣ ነው።
\v 10 በከተማዎችህ ሁሉ ያድንህ ዘንድ ንጉሥህ አሁን ወዴት ነው? ስለ እነርሱ፥ 'ንጉሥና መሳፍንቶች ስጠኝ' ብለህ የተናገርክላቸው፥ ገዢዎችህ ወዴት ናቸው?
\v 11 በቁጣዬ ንጉሥ ሰጠሁህ፥ በመዓቴም አስወገድኩት።
\s5
\v 12 የኤፍሬም ክፋት ተደብሮአል፥በደሉም ተደብሮአል።
\v 13 የምጥ ሕመም ይመጣበታል፥ እርሱ ግን ጥበብ የጎደለው ልጅ ነው፤ ምክንያቱም የሚወለድበት ጊዜ ቢደርስም ከማኅጸን አይወጣም።
\s5
\v 14 በእርግጥ ከሲዖል ኃይል አድናቸዋለሁን? በእርግጥ ከሞትስ አድናቸዋለሁን? ሞት ሆይ መቅሰፍቶችህ ወዴት አሉ? ወደዚህ አምጣቸው። ሲዖል ሆይ ማጥፋትህ ወዴት አለ? ወደዚህ አምጣው። ርህራኄ ከዓይኖቼ ተሰወረ።
\s5
\v 15 ኤፍሬም በወንድሞቹ መካከል ባለጸጋ ቢሆንም እንኳን፥ የምሥራቅ ነፋስ ይመጣል፤ የእግዚአብሔር ነፋስ ከምድረ በዳ ይነፍሳል። የኤፍሬም ምንጭ ይደርቃል፥ ጉድጓዱም ውኃ አይኖረውም። ጠላቱ የተከበሩ ዕቃዎች ሁሉ ያሉበትን ግምጃ ቤቱን ይበዘብዛል።
\s5
\v 16 በአምላኳ ላይ ዐምፃለችና ሰማሪያ በደለኛ ትሆናለች። በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ብላቴኖቻቸውም ይከሰከሳሉ፥ እርጉዝ ሴቶቻቸውም ይቀደዳሉ።
\s5
\c 14
\p
\v 1 እስራኤል ሆይ ከክፋትህ የተነሳ ወድቀሃልና ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ።
\v 2 የኑዛዜ ቃላት ያዝና ወደ እግዚአብሔር ተመለስ። እንዲህም በሉት፦«የከንፈሮቻችንን ፍሬ ምስጋናችንን እንሰዋልህ ዘንድ፤ክፋታችንን አስወግድ፥በቸርነትም ተቀበለን።
\s5
\v 3 አሦር አያድነንም፤ ለጦርነትም ፈረሶችን አንጋልብም። ወይም ከእንግዲህ የእጆቻችንን ሥራዎች 'እናንተ አምላኮቻችን ናችሁ' አንላቸውም፤ አባት አልባው እንኳ በአንተ ዘንድ ርኅራኄን ያገኛልና።
\s5
\v 4 ከተውኝም በኋላ ወደ እኔ በተመለሱ ጊዜ እፈውሳቸዋለሁ፤ እንዲያው እወዳቸዋለሁ፥ ቁጣዬ ከእርሱ ተመልሶአልና።
\v 5 እኔ ለእስራኤል እንደ ጠል እሆናለሁ፤ እንደ አበባ ያብባል፥ እንደ ሊባኖስም ዝግባ ሥር ይሰዳል።
\v 6 ቅርንጫፎቹ ይዘረጋሉ፤ ውበቱ እንደ ወይራ ዛፎች፥ ሽታውም እንደ ሊባኖስ ዝግባዎች ይሆናል።
\s5
\v 7 ከጥላው በታች ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ይመለሳሉ፤እንደ እህል ይለመልማሉ፥ እንደ ወይንም ያብባሉ።ዝናውም እንደ ሊባኖስ ወይን ጠጅ ይሆናል።
\v 8 ኤፍሬም፦ 'ከእንግዲህ ከጣዖታት ጋር ምን አለኝ?' ይላል። እኔ እመልስለታለሁ፥እጠነቀቅለታለሁም። እኔ ቅጠሎቹ ሁል ጊዜ ለመለም እን ደሆኑ እንደ ጥድ ነኝ፤ ፍሬህም ከእኔ ይመጣል።»
\s5
\v 9 እነዚህን ነገሮች ያስተውል ዘንድ ጠቢብ የሆነ ማን ነው? ያውቃቸው ዘንድ እነዚህን ነገሮች የሚያስተውል ማን ነው? የእግዚአብሔር መንገዶች ትክክል ናቸው፥ ጻድቃንም ይሄዱባቸዋል፥ ዓመፀኞች ግን ይሰናከሉባቸዋል።