am_ulb/26-EZK.usfm

2477 lines
289 KiB
Plaintext

\id EZK
\ide UTF-8
\h ሕዝቅኤል
\toc1 ሕዝቅኤል
\toc2 ሕዝቅኤል
\toc3 ezk
\mt ሕዝቅኤል
\s5
\c 1
\p
\v 1 በሰላሳኛው ዓመት ክአመቱም በአራተኛው ወር ከወሩም በአምስተኛው ቀን በኬብሮን አጠገብ ከምርኮኞቹ ጋር አብሬ እየኖርኩኝ ሳለሁ ሰማያት ተክፍተው የእግዚአብሔርን ራዕይ አየሁ።
\v 2 ንጉስ ኢዮአኬም በተማረከበት በአምስተኛው ቀን በከለዳዊያን አገር በኬብሮን ወንዝ አጠገብ
\v 3 የእግዚአብሔር ቃል ወደ ካህኑ ወደ ኡዝ ልጅ ወደ ሕዝቅኤል በኃይል መጣ። የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ነበረች።
\s5
\v 4 እኔም በውስጡ የእሳት ነበልባል ያለበት ዙሪያውና ውስጡ የሚያበራ ታላቅ ደመና የሚመስል አውሎ ነፋስ ከሰሜን አቅጣጫ ሲመጣ አየሁ፣ በደመናው ውስጥ ያለው እሳት ቀለሙ ቢጫ ነበር።
\v 5 መካከል ላይ የአራት ህያዋን ፍጡራን ምስል ነበር። ፍጥረታቱ የሰው መልክ ነበራቸው፣
\v 6 ነገር ግን እያንዳንዳቸው አራት አራት ፊቶችና አራት አራት ክንፎች ነበሩዋቸው።
\s5
\v 7 እግሮቻቸው ቀጥ ያሉ ነበሩ፣ ነገር ግን የእግሮቻችው ኮቴ እንደ ነሀስ የሚያበራ የጥጃ ኮቴ ያለ ነበር።
\v 8 ከክንፎቻቸው ስር በአራቱም አቅጣጫ የሰው እጅ ነበራቸው።
\v 9 በክንፎቻቸው ተነካክተው ወደ ኋላ ሳይገላመጡ ቀጥ ብለው ወደፊት ይራመዱ ነበር።
\s5
\v 10 መልካቸውም በአንድ በኩል የሰው፥ በቀኝ በኩል የአንበሳ፣ በግራ በኩል የበሬና በሌላ በኩል ደግሞ የንስር ነበር።
\v 11 መልካቸው ያንን ይመስል ነበር፣ ክንፎቻቸውም ተዘርግተው ነበር፣ በሁለት ክንፎቻቸው እርስ በርሳቸው ተነካክተው ነበር፣ በሁለት ክንፎቻቸው ደግሞ ሰውነታቸውን ይሸፍኑ ነበር።
\v 12 እያንዳንዳቸው ሳይገላመጡ ወደፊት ይራመዱ ነበር፣ መንፈስ ወደመራቸው ሳይገላመጡ ይሄዱ ነበር።
\s5
\v 13 ህያዋን ፍጡራን የከሰል ፍም እሳት ወይም ችቦ ይመስሉ ነበር፣ ከህያዋን ፍጡራኑ ጋር ደማቅ እሳት ይንቀሳቀስ ነበር፣ የመብረቅ ብልጭታዎችም ነበሩ።
\v 14 ህያዋን ፍጡራኑ በዝግታ ወደ ኋላና ወደ ፊት ይንቀሳቀሱ ነበር፣ እንደ መብረቅም ነበሩ።
\s5
\v 15 ወዲያውም ወደ ህያዋን ፍጥረታቱ ተመለከትኩ፣ በምድር ላይ ከእያንዳንዱ ፍጡር አጠገብ አንዳንድ መንኮራኩር ነበረ።
\v 16 የመንኮራኩረቹ መልክ የሚከተለውን ይመስል ነበር፡ እንደ ብርሌ ያንጸባርቁ ነበር፣ አራቱም አንድ አይነት ነበሩ፣ አንዱም በአንዱ ላይ የተስካ ይመስል ነበር።
\s5
\v 17 መንኮራኩሮቹ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ፍጡራኑ ወደየትኛውም አቅጣጫ ሳይገላመጡ ይሄዱ ነበር።
\v 18 ዙሪያውን በዓይን የተሞላ ስለሆነ የመንኮራኩሮቹ ጠርዝ ርጅምና አስፈሪ ነበር።
\s5
\v 19 ህያዋን ፍጡራኑ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ መንኮራኩሮቹ አብረው ይንቀሳቀሱ ነበር፣ ህያዋን ፍጥረታቱ ወደ ላይ ከፍ ሲሉ መንኮራኩሮቹም ከፍ ይሉ ነበር።
\v 20 መንፈስ ወደሚሄድበት ሁሉ ይሄዱ ነበር፣ የህያዋን ፍጡራኑ መንፈስ ስላለባቸው መንኮራኩሮቹ አብረው ወደ ላይ ከፍ ይሉ ነበር።
\v 21 የፍጡራኑ መንፈስ ስላለባቸው ፍጡራኑ ሲሄዱ መንኮራኩሮቹም ከአጠገባቸው ይሄዱ ነበር፣ ሲቆሙ እነርሱም ይቆሙ ነበር፣ ከምድር ወደ ላይ ከፍ ሲሉ እነርሱም ከፍ ይሉ ነበር።
\s5
\v 22 ከህያዋን ፍጡራኑ ራስ በላይ ጠፈር የሚምስል ነገር ነበረ፤ ያም ጠፈር የሚመስል ነገር በህያዋን ፍጡራኑ ራስ በላይ እንደ አስፈሪ በረዶ ዙሪያቸውን ነበረ።
\v 23 ከጠፈሩ በታች የእያንዳንዱ ህያው ፍጡር ክንፍ ቀጥ ብሎ ተዘርግቶ የአንደኛው ፍጡር ክንፍ ከሌላው ፍጡር ክንፍ ጋር ተነካክቶ ነበር። እያንዳምዱ ፍጡር ሰውነቱን የሚሸፍንበት ሁለት ክንፍ ነበረው።
\s5
\v 24 ህያዋን ፍጡራኑ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ሁሉ የክንፎቻቸው ድምጽ ይሰማኝ ነበር፣ ድምጹም እንደ ውሃ ጎርፍ፣እንደ ህያው አምላክ ድምጽ፣ እንደ ሠራዊት ድምጽ፣ እንደ ዝናብ ውሽንፍር ነበረ! በሚቆሙበት ጊዜ ክንፎቻችውን ያጥፉ ነበር።
\v 25 በሚቆሙበትና ክንፎቻቸውን በሚያጥፉበት ጊዜ ከራሶቻቸው በላይ ካለው ጠፈር ድምጽ ይመጣ ነበር።
\s5
\v 26 ከራሶቻቸው በላይ ከሚገኘው ጠፈር በላይ ዕንቁ የሚመስል የዙፋን አምሳያ ነበር፣ በዙፋኑም አምሳያ ላይ ሰው የሚመስል ተቀምጦ ነበር።
\s5
\v 27 ከወገብ በላይ በእሳት የጋለ ብረት ከወገቡ በታች ደግሞ እሳት የሚመስል ምስል አየሁ።
\v 28 በዝናብ ጊዜ እንደሚታይ ቀስተ ደመና ይመስል ዙሪያውም ደማቅ ብርሀን ነበረ። ባየሁትም ጊዜ በግንባሬ ተደፋሁ፣ ወዲያውም የሚያናግረኝ ድምጽ ሰማሁ።
\s5
\c 2
\p
\v 1 "የሰው ልጅ ሆይ ተነስና ቁም ክዚያም አነጋግርሃልሁ" አለኝ።
\v 2 እየተናገረኝ ሳለ መንፈስ አንስቶ በእግሮቼ አቆመኝ የናገረኝንም ሰማሁ።
\v 3 "የሰው ልጅ ሆይ አመፀኛ ወደሆኑትና በእኔ ላይ ወዳመፁት ወደ እስራኤል ህዝብ እልክሃለሁ፦ እነርሱና የቀደሙ አባቶቻችው እስከዚች ቀን ድረስ በድለውኛል!
\s5
\v 4 ልጆቻቸው የተጨማደደ ፊትና ደንዳና ልብ አላቸው። አንተም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ትላቸዋለህ።
\v 5 አመጸኛ ቤት ስለሆኑ ወይ ይሰሙሃል አሊያም አይሰሙህም። ነገር ግን ቢያንስ ነቢይ በመካከላቸው እንዳለ ያውቃሉ።
\s5
\v 6 አንተም የሰው ልጅ ሆይ እነርሱንም ሆነ ቃላቸውን አትፍራ። በእሾሆች፣በኩርንችት እና በጊንጦች መካከል ብትቀመጥም አትፍራ። አመጸኛ ቤቶች ስለሆኑ ቃላቸውን አትፍራ ፊታቸውን አይተህ አትደንግጥ።
\s5
\v 7 እጅግ አመጸኞች ስለሆኑ ቢሰሙህም ባይሰሙህም ቃልን ትነግራቸዋለህ።
\v 8 ነገር ግን አንተ የሰው ልጅ የምነግርህን ስማ። አንተም እንደአመጸኞቹ ሰዎች አመጸኛ አትሁን። አፍህን ክፈትና የምሰጥህን ብላ።
\s5
\v 9 ጽሁፍ የተጻፈበት ጥቅል የያዝ እጅ ወደኔ ሲዘረጋ አየሁ።
\v 10 በፊቴም ዘረጋው ክፊትና ከኋላው ተጽፎበት ነበር፤ በሀዘን፣ በልቅሶና በዋይታ የተሞላ ነበር።
\s5
\c 3
\p
\v 1 የሰው ልጅ ሆይ ያገኘኽውን ብላ ይህን የመጽሀፍ ጥቅል ብላ ሄደህም ለእስራኤል ህዝብ ተናገር።
\v 2 አፌንም ከፈትኩ የመጽሀፉን ጥቅል አጎረሰኝና
\v 3 "የሰው ልጅ ሆይ በሰጠሁህ በዚህ የመጽሀፍ ጥቅል ሆድህን ሙላ" አለኝ። እኔም በላሁት እንደማርም ጣፈጠኝ።
\s5
\v 4 ከዚያም "የሰው ልጅ ሆይ ወደ እስራኤል ህዝብ ሄደህ ቃሌን ንገራቸው" አለኝ።
\v 5 ምክንያቱም የተላከው ቋንቋቸው ወደማይታወቅ ወይም አስቸጋሪ ወደሆን ህዝብ አይደለም፦
\v 6 እንግዳ ቋንቋ ወደሚናገር ታላቅ ህዝብ ወይም የቋንቋቸውን ቃላት መረዳት ወደሚያስቸግር ህዝብ አላኩህም። ወደዚህ ዓይነት ህዝብ ብልክህ ኖሮ ይሰሙህ ነበር። ነገር ግን የእስራኤል ህዝብ እኔን መስማት ስለማይፈልጉ አይሰሙህም።
\v 7 የእስራኤል ህዝብ ሁሉ ግንባረ ጠንካራና አንገተ ደንዳና ናቸው።
\s5
\v 8 እነሆ! ፊትህን እንድፊታቸው ግንባርህንም እንደግንባራቸው ጠንካራ አደርገዋለሁ።
\v 9 ግንባርህን ከባልጩት ድንጋይ ይልቅ እንደሚጠነክር እንደ አልማዝ አድርጌዋለ! ስለዚህ የእሴራኤል ህዝብ አመጸኞች ስለሆኑ አትፍራቸው ፊታቸውንም አይተህ አትደንግጥ።
\s5
\v 10 ቀጥሎሜ እንዲህ አለኝ "የሰው ልጅ ሆይ የነገርኩህን ቃል ስማ በልብህም ተቀበለው።
\v 11 ከዚያም በምርኮ ወዳሉት ህዝብህ ሂድና ቢሰሙህም ባይሰሙህም 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል' በላቸው።"
\s5
\v 12 መንፈስም ከምድር ከፍ አደረግኝ ከኋላዬም የእግዚአብሔር ክብር በማደሪያው ይባረክ የሚል እንደ ምድር መናወጥ ዓይነት ድምጽ ሰማሁ።
\v 13 ወዲያውም የህያው ፍጥርታቱ ክንፎች ሲነካካ የሚፈጠረውን ድምጽ፣ አብረዋቸው ያሉትን መንኮራኩሮች ድምጽ፥ እና የምድር መናወጥ ድምጽ ሰማሁ።
\s5
\v 14 መንፈስም አንስቶ ወሰደኝ፤ የእግዚአብሔርም እጅ በእኔ ላይ ከብዶ ስለነበር የምሄደው በምሬትና በጋለ መንፈስ ነበር።
\v 15 ከዚያም በኬብሮን ወንዝ አጠገብ ወደሚኖሩት በቴላቢብ ወደሚገኙት ምርኮኞች ሄጄ በድንጋጤና በመደነቅ ተሞልቼ በመካከላቸው ሰባት ቀን ተቀመጥኩ።
\s5
\v 16 ከስባት ቀንም በኋላ እንዲህ ሆነ፥
\v 17 "የሰው ልጅ ሆይ አንተን ለእስራኤል ህዝብ እንደጠባቂ አድርጌሀለሁ፥ ስለዚህ የአፌን ቃል ስማና የእኔን ማስጠንቀቂያ ንገራቸው!
\v 18 ኃጢአተኛውን 'በእርግጥ ትሞታለህ' ብለህ ንገረው ብዬህ አንተ ግን ባትነግረው ከክፉ መንገዱም እንዲመለስ ባታስጠነቅቀው እርሱ በኃጢአቱ ይሞታል ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።
\v 19 ነገር ግን ኃጢአተኛውን ብታስጠነቅቀው እርሱ ግን ከክፋቱና ከመጥፎ ተግባሩ ባይመለስ በኃጢአቱ ይሞታል አንተም ነፍስህን ታድናለህ።" ብሎ እግዚአብሔር ሲናገረኝ ሰማሁ።
\s5
\v 20 ደግሞም አንድ ጻድቅ ሰው ጽድቅ ማድረግን ቢተው እኔም በፊቱ መሰናክል ሳስቀምጥ እርሱ በኃጢአቱ ይሞታል። አንተ ስላላስጠነቀከው እርሱ በኃጢአቱ ይሞታል፣ ቀድሞ የሰራውንም የጽድቅ ስራ አላስብለትም፣ ነገር ግን አንተን የሞቱ ተጠያቂ አደርግሀለሁ።
\v 21 ነገር ግን አንድ ጻድቅ ሰው ኃጢአት መስራቱን እንዲያቆም ብታስጠነቅቀው ከማስጠንቀቂያው የተነሳ በእርግጥኝነት በህይወት ይኖራል፣ አንተም የራስህን ህይወት ታድናለህ።"
\s5
\v 22 ደግሞም የእግዚአብሔር እጅ በላዬ መጣ፣ እግዚአብሔርም ፣ "ተነሳ! ወደ ሜዳማው ቦታ ሂድ፣ በዚያ የምነግርህ ነገር አለ" አለኝ።
\v 23 እኔም ተነስቼ ወደ ሜዳማው ቦታ ሄድኩ፥ በዚያም በኬብሮን ወንዝ አጠገብ ያየሁት ዓይነት የእግዚአብሔር ክብር ነበረ፣ ስለዚህም በግንባሬ ተደፋሁ።
\s5
\v 24 የእግዚአብሔርም መንፈስ መጥቶ በእግሮቼ አቆመኝና እንዲህ ሲል ተናገረኝ "ወደ ቤትህ ሂድና በር ዘግተህ ተቀመጥ፣
\v 25 ምክንያቱም አሁን የሰው ልጅ ሆይ በመካከላቸው እንዳትንቀሳቀስ በገመድ ያስሩሀል።
\s5
\v 26 አመጸኛ ህዝብ ስለሆኑ እንዳትገስፃቸው እኔ ምላስህን ከላንቃህ ጋር አጣብቀዋለሁ አንተም ዲዳ ትሆናለህ።
\v 27 ነገር ግን እኔ ስናገርህ አፍህን እከፍታለሁ አንተም 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል' ትላቸዋለህ፤ አመጸኛ ህዝብ ስለሆኑ የሚሰማ ይሰማሀል የማይሰማ አይሰማህም!"
\s5
\c 4
\p
\v 1 አንተ ግን የሰው ልጅ ሆይ ሸክላ ውሰድና የኢየሩሳሌምን ካርታ ሳልበት። የጦር ከበባ አድርግባት፣
\v 2 ምሽግም ስራባት፣ ዙሪያውን በአፈር ደልድለው፣ ትልቅ ቅጥር ና የጦር ሰፈሮችን አስቀምጥ ፣ ቅጥር መደርመሻ ግንዶች ዙሪያውን አስቀምጥ።
\v 3 ክዚያም ብረት ምጣድ ለራስህ ውሰድና በአንተና በከትማይቱ መካከል በብርት አጥር ምሳሌ አቁመው። ትከበባለችና ፊትህንም ወደከትማይቱ አዙር ክበባትም! ይህም ለእስራኤል ህዝብ ምልክት ይሆናል።
\s5
\v 4 ክዚያም በግራ ጎንህ ተኛና የእስራኤልን ህዝብ ኃጢአትም ተሸከም፤ በእስራኤል ህዝብ ፊት በግራ ጎንህ በተኛህበት ቀን ቁጥር ልክ ኃጢአታቸውን ትሸከማለህ።
\v 5 አንድ ቀን የሚቀጡበትን አንድ አመት እንዲወክል እኔ ራሴ መድቤልሀለሁ፡ 390 ቀናት! በዚህ መልኩ የእስራኤልን ህዝብ ኃጢአት ትሸከማለህ።
\s5
\v 6 እነዚህን ቀናት ስትጨርስ በቀኝ ጎንህ ትተኛና የይሁዳን ህዝብ ኃጢአት ለአርባ ቀናት ትሸከማለህ። አንድ ቀን አንድ አመት እንዲወክል መድቤልሀለሁ።
\v 7 እጅህን ክልብስህ ውስጥ አውጥተህ ፊትህን ወደተከበበችው ኢየሩሳሌም ከተማ አድርገህ ትንቢት ትናገርባታለህ።
\v 8 እነሆ! የሜርኮው ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ከአንድ ጎን ወደ ሌላ ጎን እንዳትዞር ቀንበርን አድርጌብሀለሁ።
\s5
\v 9 ስንዴ፣ገብስ፣ባቄላ፥ ምስር፥ ጤፍና አጃ ወስደህ በአንድ ዕቃ ውስጥ አድርገህ በጎንህ በምትተኛባቸው ቀናት ቁጥር ልክ ዳቦ ትጋግራልህ። ለ390 ቀናት ትመገበዋለህ!
\v 10 በየቀኑ ሃያ ሃያ ሰቅል የሚመዝን ዳቦ ትበላለህ። በየጊዜውም ትመገበዋለህ።
\v 11 አንድ ስድስተኛ ኢን ውሃም ትጠጣለህ። በየጊዜውም ትጠጣዋለህ።
\s5
\v 12 እንደ ገብስ ቂጣ አድርገህ ትበላዋለህ፣ የምትጋግረው ግን በሰው ዓይነ ምድር ነው።
\v 13 እግዚአቤሔር "በበተንኳቸው አህዛብ መካከል የእስራኤል ህዝብ የሚመገቡት ዳቦ ርኩስ ይሆናል።" ይላል።
\s5
\v 14 እኔም "ወየው ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ረክሼ አላውቅም! የሞተ ወይም በአውሬ የተገደለ በልቼ አላውቅም፣ የረከሰ ሥጋም ወደ አፌ ገብቶ አያውቅም!" አልኩኝ።
\v 15 እርሱም "እነሆ በሰው ዓይነ ምድር ፋንታ የከብት ፍግ ስጥቼሀለሁ ዳቦውን በእርሱ መጋገር ትችላለህ" አለኝ።
\s5
\v 16 ደግሞም "የስው ልጅ ሆይ! ከኢየሩሳሌም የእንጀራን በትር እሰብራለሁ፣ ህዝቡም እንጀራን በጭንቅ ውሃም በስስት ይጠጣሉ።
\v 17 የምግብና የውሃ እጥረት ስለሚኖር ሰው ወንድሙን በድንጋጤ ይመለከተዋል፣ ከኃጢአታቸው የተነሳ ይመነምናሉ።" አለኝ።
\s5
\c 5
\p
\v 1 "ከዚያም የሰው ልጅ ሆይ ጎራዴን እንደጢም መላጫ ተጠቀመህ ራስህንም ጢምህንም ተላጨው፣ በመቀጠልም ሚዛን ተጠቅመህ ጠጉሩን ትከፍለዋለህ።
\v 2 የምርኮው ዘመን ሲያበቃ የጠጉሩን አንድ ሶስተኛ በከተማው መካከል በእሳት ታቃጥለዋለህ። አንድ ሶስተኛውንም ወስደህ በክተማይቱ ዙሪያ አስቀምጠህ በሰይፍ ትመታዋለህ። ከዚያም አንድ ሶስተኛውን ወደ ነፋስ ትበትነዋለህ፣ እኔም ህዝቡን አሳድድ ዘንድ ሰይፌን እመዛለሁ።
\s5
\v 3 ነገር ግን ጥቂት ጠጉሮችን ወስደህ በጋቢህ ጫፍ ላይ ትቋጥረዋለህ።
\v 4 ክዚያም በርከት ያለ ጠጉር ወስደህ ወደ እሳቱ መሀል ጥለህ በእሳቱ አቃጥለው፤ በእሳት ውስጥ ይቃጠል፤ ከዚያም ውስጥ እሳት ወደ እስራኤል ህዝብ ሁሉ ይወጣል።"
\s5
\v 5 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ይህች በሌሎች አገሮች ዙሪያዋን እንድትዋሰን ያደረኳት፣ በአህዛብ መካከል ያለች ኢየሩሳሌም ናት።
\v 6 ነግር ግን ከሌሎች አህዛብ ይልቅ ከኃጢእታቸው የተነሳ ትዕዛዛቴን አቃለዋል፣ በዙሪያቸው ካሉ አገሮች ይልቅ ህጌን ተላልፈዋል። ፍርዴን አቃለዋል በህጌም አልኖሩም!"
\s5
\v 7 ስለዚህም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "በዙሪያቹ ካሉ አገሮች ይልቅ አመጸኞች ስለሆናችሁና በህጌ ስላልኖራችሁ ተግባራችሁም እንድትዕዛዛቴ ስላልሆነ ይባስ ብሎ የምታደርጉት ሁሉ በዙሪያችሁ እንዳሉት አግሮች ትዕዛዝ ስለሆነ ።"
\v 8 ስለዚህም ይላል ጌታ እግዚአብሔር "እነሆ! እኔ እራሴ በእናንተ ላይ እነሳለሁ! አህዛብ ሁሉ ያዩ ዘንድ ፍርዴን በመካከልሽ አመጣለሁ።
\s5
\v 9 ከጸያፍ ተግሮችሽ የተነሳ አድርጌ የማላውቀውን ደግሜም የማላደርገውን ነገር በአንቺ ላይ አደርጋለሁ።
\v 10 ስለዚህም በመካከልሽ አባቶች ልጆቻችውን ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፣ ፍርድንም አመጣብሻለሁና የተርፉትን በየአቅጣጫው እበትናቸዋለሁ!
\s5
\v 11 ስለዚህም በራሴ እምላለሁ፦ ይህ የጌታ የእግዚአብሄር አዋጅ ነው- ቤተመቅደሴን በሚያስጠሉ ነግሮችና በሚያጸይፉ ተግባራት ሞልታችሁታልና ከቁጥር አጎድላችኋለሁ፤ ፊቴን አልመልስልሽም፣ አልራራልሽምም።
\v 12 አንድ ሶስተኛችው ህዝብ በመቅሰፍት ይሞታል በመካከልሽም በረሀብ ያልቃሉ፣ አንድ ሶስተኛው ደግሞ በከበቡሽ ጠላቶች ሰይፍ ይገደላሉ። ቀሪውን አንድ ሶስተኛ ደግሞ በየአቅጣጫው እበትናቸዋለሁ አሳድዳቸውም ዘንድ ሰይፌን ከሰገባው እመዛለሁ።
\s5
\v 13 ከዚያም ቁጣዬ ይፈጸማል፣ በእነርሱም ላይ የነበረኝ ንዴት ይበርዳል። በእነርሱ ላይ የነበረኝ ንዴቴ በተፈጸመ ጊዜ እኔ እግዚአብሄር በቁጣዬ እንደተናገርኳቸው ያውቃሉ።
\v 14 ዙሪያሽን በከበቡሽ አህዛብና በአላፊ አግዳሚው ሁሉ የተዋረድሽና አሳፋሪ አድርግሻለሁ።
\s5
\v 15 ስለዚህ ኢየሩሳሌም በሌሎች የምትወገዝና መቀለጃ በዙሪያዋ ላሉ አህዛብ ቁጣና ድንጋጤ ትሆናልች። ፍርዴን በንዴትና በቁጣ በጽኑ ተግሳጽም አመጣባችኋለሁ- እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
\v 16 የርሀብን አስከፊ ቀስቶች እሰድባችኋለሁ፣ ያም እናንተን የማጠፋበት መሳሪያ ይሆናል። ርሀብን አበዛለሁ የእንጀራ በትራችሁንም እሰብራለሁ።
\v 17 ልጆች አልባ እንድትሆኑ ርሀብና አደጋን እልክባችኋለሁ። መቅሰፍትና ደም በመካከላችሁ ያልፋል ሰይፍንም አመጣባችኋለሁ -- እኔ እግዚአብሄር ይህን ተናግሬአልሁ!"
\s5
\c 6
\p
\v 1 የእግዚአብሄር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ
\v 2 "የሰው ልጅ ሆይ ፊትህን ወደ እስራኤል ተራሮች አዙርና ትንቢት ተናገር።
\v 3 እንዲህም በላቸው 'የእስራኤል ተራሮች ሆይ የጌታ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ! ጌታ እግዚአብሔር ለተራሮች፣ ለኮረብቶች፣ ለሸንተረሮችና ለሸለቆዎች እንዲህ ይላል፡ እነሆ ሰይፍን አመጣባችኋለሁ ከፍታችሁን ሁሉ አጠፋለሁ።
\s5
\v 4 መሰዊያዎቻችሁ ባድማ ይሆናሉ የዕጣን መሰዊያዎቻችሁም ይደመሰሳሉ የሞቱ ሰዎቻችሁን ሬሳዎች በጣዖቶቻቸው ፊት እጥላለሁ።
\v 5 የእስራኤልን ህዝብ ሬሳዎችን በጣዖቶቻችው ፊት አጋድማለሁ፣ አጥንቶቻችሁንም በመሰዊያዎቻችሁ ዙሪያ እበትናለሁ።
\s5
\v 6 መሰዊያዎቻችሁ የተጣሉና ባድማ እንዲሆኑ የምትኖሩባቸው ከተሞች ሁሉ የተጣሉ የማምለኪያ ኮረብቶቻቸው ሁሉ ባድማ ይሆናሉ፣ እንዳልነበሩም ሆነው ይጠፋሉ፤ የዕጣን መሰዊያዎቻችሁ ይወገዳሉ ሥራቼሁ ሁሉ ተጠርጎ ይጠፋል።
\v 7 የሰዎች ሬሳ በመካከላችሁ ይወድቃል ያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ ታውቃላችሁ!
\s5
\v 8 ነገር ግን ቅሬታዎችን አስቀራለሁ፣ እናንተ በየአገሩ ስትበተኑ ከአህዛብ መካከል ከሰይፍ የሚያመልጡ ይኖራሉ።
\v 9 እነዚያ ያመለጡትም በምርኮ አገር ሆነው ከእኔ ዘወር ካለው አመንዝራ ልባቸውና ወደ ጣዖታቶቻቸው ከሚያየው አመንዝራ ዓይናቸው የተነሳ ምን ያህል እንዳዝንኩ ስለእኔ ያስባሉ። ባደረጉት ክፋትና ርኩሰት መጸጸታቸው ከፊታቸው ይነበባል።
\v 10 ስለዚህም እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ ያውቃሉ። ይህን ክፉ ነገር አመጣባቸዋለሁ ብዬ አስቀድሜ የተናገርኩት በዓላማ ነው።
\s5
\v 11 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡ ከፈጸሙት አስነዋሪ ተግባር የተነሳ የእስራኤል ህዝብ በሰይፍ፣ በረህብና በቸነፈር ይጠፋሉና በእጅህ እያጨበጭችብክ በእግርህም መሬቱን እየመታህ "ወዮ" እያልክ ጩህ!
\v 12 በሩቅ ያለው በቸነፈር በቅርብ ያለው በሰይፍ ይጠፋሉ። ከዚያ የተረፉት ደግሞ በርሀብ ያልቃሉ፤ በዚህ መንገድ ቁጣዬን በእነርሱ ላይ እፈጽማለሁ።
\s5
\v 13 በጣዖቶቻቸው መካከል፣ በመሰዊያዎቻቸው ዙሪያ፣ ከፍ ባሉ ተራሮቼ አናት ላይ፣ እንዲሁም በለመለመ ዛፍ ሁሉና በግዙፍ ዋርካ ስር- ለጣዖቶቻቸው በሚያጤኑበት ሥፍራ ሁሉ የተገደሉ ሰዎቻቸው ተጥለው ሲያዩ ያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ ያውቃሉ።
\v 14 በገዛ እጄ እመታችኋለሁ የሚኖሩብትን ስፍራ ሁሉ ከምድረ በዳ እስከ ዲብላህ ድረስ ምድሪቱን የተጣለችና ባድማ አደርጋታለሁ።"
\s5
\c 7
\p
\v 1 የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 2 "አንተ የሰው ልጅ ሆይ -- ጌታ እግዚአብሔር ለእስራኤል ምድር የሚለው እንዲህ ነው፣ 'መጨረሻ! በምድሪቱ አራቱም ማዕዘን መጨረሻ መጥቷል!
\s5
\v 3 ቁጣዬን ስለላኩባችሁ መጨረሻችሁ ቀርቧል፣ እኔም እንደመንገዳችሁ እፈርድባችኋለሁ፤ ክፉ ሥራችሁን ሁሉ በእናንተ ላይ እመልስባችኋለሁ።
\v 4 በርህራሄ አላያችሁም ምህረትም አላደርግላችሁም፤ ነገር ግን መንግዳችሁን እመልስባችኋለሁ፣ ጥፋታችሁ በመካከላችሁ ይሆናል፥ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ ታውቃላችሁ!
\s5
\v 5 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡ መዓት! በመዓት ላይ መዓት! እነሆ እየመጣ ነው!
\v 6 መጨረሻ በእርግጥ እየመጣ ነው፤ መጨረሻው ወደ እናንተ እየተራመደ ነው! እነሆ እየመጣ ነው!
\v 7 በምድሪቱ በምትኖሩት ላይ ፍርድ እየመጣ ነው። ጊዜው ደርሷል፤ የጥፋት ቀን ቀርቧል፤ ተራሮች ከእንግዲህ ለደስታ አይሆኑም።
\s5
\v 8 በቅርቡ እንደ መንገዳችሁ በምፈረድባችሁ ጊዜና ክፋታችሁን በመለስኩባችሁ ጊዜ መዓቴን አፈስባችኋለሁ ቁጣዬም በላያችሁ ይሆናል።
\v 9 ዓይኔ አይራራላችሁም ምህረትም አላደርግላችሁም። እንዳደርጋችሁብኝ አደርግባችኋለሁ፤ የምቀጣችሁ እኔ እንደሆንኩ ታውቁ ዘንድ ክፋታችሁም በመካከላችሁ ይሆናል።
\s5
\v 10 እነሆ ቀኑ እየደረሰ ነው። ጥፋት ወጥቷል። በትሩ በትዕቢት አበባ ፈክቷል።
\v 11 አመጽ ወደ ኃጢአት በትርነት አድጓል-- አንዳቸውም፣ ከህዝባቸውም ማንም፣ የትኛውም ሀብታቸው፣ የትኛው ጠቃሚ ነገራቸው አይተርፍም።
\s5
\v 12 ቀኑ እየመጣ ነው፤ ቀኑ እየቀረበ ነው። ቁጣዬ በህዝቡ ሁሉ ላይ ስለሆነ ንብረት የገዛ አይደሰት፣ የሸጠም አይዘን!
\v 13 ምክንያቱም በህይወት ዘመናቸው ሁሉ ሻጭ የሸጠውን አያስመልስም፣ ራዕዩ ለመላው ህዝብ ነው። በኃጢአቱ የሚጸና አይበረታምና አይመለሱም።
\s5
\v 14 መለከት ነፉ የሚያስፈልገውን ሁሉ አዘጋጁ ነገር ግን ቁጣዬ በህዝቡ ሁሉ ላይ ነውና ለጦርነት የከተተ አንድም የለም!
\v 15 በውጭ ሰይፍ በውስጥ ደግሞ ረሀብና ቸነፈር አለ። በእርሻ ቦታ ያሉ በስይፌ ይወድቃሉ፥ ረሀብና ቸነፈር ደግሞ በከተማ ያሉትን ይፈጃል።
\v 16 ነገር ግን ከእነርሱ ጥቂቶች ተርፈው ወደ ተራሮች ይሄዳሉ። ሁሉም ስለኃጢአታቸው እያንዳንዱም ስለስንፍናው እንደ ደሸለቆ እርግብ ያለቅሳሉ።
\s5
\v 17 እጅ ሁሉ ይቀልጣል ጉልበትም ሁሉ እንደ ውሀ ይደክማል፣
\v 18 ማቅም ይለብሳሉ ድንጋጤም ይከባቸዋል፤ ፊት ሁሉ በእፍረት ይሸፈናል ራስም ሁሉ ጠጉር አልባ ይሆናል።
\v 19 ብራቸውን በጎዳናዎቹ ላይ ይጥላሉ ወርቃቸውም እንደ ጕድፍ ይሆናል በእግዚአብሔር መዓት ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ያድናቸው ዘንድ አይችልም። እርሱ የኃጢአታቸው ዕንቅፋት ሆኖአልና ሰውነታቸውን አያጠግቡም ሆዳቸውንም አይሞሉም
\s5
\v 20 የክብሩ ጌጦችንም በማንአለብኝነት ወስደው ክፋታቸውንና የፈጸሙትን አመጻ የሚያሳዩ የምንዝርና ምስሎችን አበጁ፣ ስለዚህ እኔ እነዚህን ምስሎች ርኩስ እድርጌባቸዋለሁ።
\v 21 በባዕድም እጅ ለንጥቂያ፥ በምድር ኃጢአተኞችም እጅ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ እነርሱም ያረክሱአቸዋል።
\v 22 የተቀድሰውን ቦታዬን ባረከሱ ጊዜ ፊቴንም አዞርባቸዋለሁ፥ ወንበዴዎችም ይገቡባታል ያረክሱትማል።
\s5
\v 23 ምድሪቱ ደም ባመጣው ፍርድ፥ ከተማዪቱም በግፍ ተሞልታለችና ሰንሰለት ሥራ።
\v 24 ስለዚህም ከአሕዛብ ዘንድ ከሁሉ የሚከፉትን አመጣለሁ ቤቶቻቸውንም ይወርሳሉ፣ መቅደሶቻቸው ስለሚረክሱ የኃያላንንም ትዕቢት ወደ ፍጻሜ አመጣለሁ።
\v 25 ፍርሀት ይመጣል! ሰላምን ይሻሉ ነገር ግን ምንም ሰላም አይገኝም።
\s5
\v 26 ድንጋጤ በድንጋጤ ላይ ወሬም በወሬ ላይ ይመጣል! ከነቢዩም ዘንድ ራዕይን ይሻሉ ነገር ግን ከካህኑም ዘንድ ህግ፥ ከሽማግሌዎችም ዘንድ ምክር ይጠፋል።
\v 27 ንጉሡም ያለቅሳል፥ ልዑሉም ውርደትን ይለብሳል፥ የምድሪቱም ሕዝብ እጆቼ በፍርሀት ይንቀጥቀጣሉ። እንደ መንገዳቸውም መጠን ይህን አደርግባቸዋለሁ! እኔ እግዚአብሔር እንድሆንኩ እስኪያውቁ ድረስ በፍርዳቸውም መጠን እፈርድባቸዋለሁ ።
\s5
\c 8
\p
\v 1 በስድስተኛውም ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በአምስተኛው ቀን በቤቴ ተቀምጬ ሳለሁ የይሁዳም ሽማግሌዎች በፊቴ ተቀምጠው ሳሉ፥ በዚያ የጌታ የእግዚአብሔር እጅ እንደገና በእኔ ላይ ወደቀች።
\v 2 እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ የሰው አምሳያ ነበረ ከወገቡም በታች እሳት ይመስል ነበረ፥ ከወገቡም በላይ የቀለጠ ብረት የሚመስል የሚያብለጨልጭ ነበር።
\s5
\v 3 ከዚያም እጅ የሚመስል ነገር ዘረጋ በራስ ጠጕሬም ያዘኝ፤ መንፈስም በምድርና በሰማይ መካከል አነሣኝ፥ በእግዚአብሔርም ራእይ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ሰሜን ወደሚመለከተው ወደ ውስጠኛው አደባባይ በር መግቢያ አመጣኝ በዚያም ቅንዓት የሚያነሣሣ የቅንዓት ጣዖት ተተክሎ ነበር።
\v 4 እነሆም፥ በቈላው እንዳየሁት ራእይ አይነት የእስራኤል አምላክ ክብር በዚያ ነበረ።
\s5
\v 5 እርሱም፦ "የሰው ልጅ ሆይ፥ ዓይንህን ወደ ሰሜን አንሣ አለኝ።" ዓይኔንም ወደ ሰሜን መንገድ አነሣሁ እነሆም፥ በመሠዊያው በር በሰሜን በኩል መግቢያው ላይ የቅንዓት ጣዖት ነበረ።
\v 6 የእግዚአብሔርም መንፈስ፦ "የሰው ልጅ ሆይ፥ አየህ የሚያደርጉትን? ይህ ከመቅደሴ ያርቁኝ ዘንድ የእስራኤል ቤት በዚህ የሚያደርጉት ታላቁን ርኵሰት ነው! ግን ዞረህ ስታይ ከዚህ የበለጠ ታላቅ ርኵሰት ታያለህ አለኝ!"
\s5
\v 7 ወደ አደባባዩም መግቢያ አመጣኝ ፥ በግንቡ ውስጥ ቀዳዳ እንዳለ አየሁ።
\v 8 እርሱም፦ "የሰው ልጅ ሆይ፥ ግንቡን ንደለው አለኝ ግንቡንም በነደልሁት ጊዜ መግቢያ በር አገኘሁ።
\v 9 እርሱም፦ "ግባና የሚያደርጉትን የከፋ ርኵሰት እይ አለኝ።
\s5
\v 10 እኔም ገባሁና እነሆ፥ በግንቡ ዙሪያ ላይ የሚሳብና አስቀያሚ አውሬ ምስል አየሁ! በግንቡም ዙሪያ የእስራኤል ቤት ጣዖታት ሁሉ ተስለው አየሁ።
\v 11 ሰባ እስራኤል ቤት ሽማግሌዎች በዚያ ቆመው ነበር፥ በመካከላቸውም የሳፋን ልጅ ያእዛንያ ቆሞ ነበር፥ በምስሎቹም ፊት ቆመው ነበር ። እያንዳንዱ ሰው በእጁ ጥናውን ይዞ ነበር፥ የዕጣኑም ጢስ ሽቱ ይወጣ ነበር።
\s5
\v 12 እርሱም፦ "የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች በጨለማ የሚያደርጉትን አየህ? 'እግዚአብሔር አያየንም እግዚአብሔር ምድሪቱን ትቶአታል' ብለው ሁሉም ሰው ይህን የሚያድርገው በየራሱ ስውር ቦታ ከጣዖቱ ጋር ሆኖ ነው።
\v 13 እርሱም፦ "ደግሞ ወደኋላ ዙርና እያደረጉ ያለውን ከዚህ የበለጠውን ሌላ ታላቅ ርኵሰት እይ" አለኝ።
\s5
\v 14 ከዚያም ወደ በሰሜን አቅወጣጫ ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በር መግቢያ አመጣኝ፣ እነሆም! ሴቶች ለተሙዝ እያለቀሱ በዚያ ተቀምጠው ነበር።
\v 15 እርሱም፦ "የሰው ልጅ ሆይ፥ ይህን ታያለህ? ደግሞ ተመልሰህ ከዚህ የበለጠ ርኵሰት ታያለህ አለኝ።
\s5
\v 16 ደግሞም ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፥ እነሆም፥ በእግዚአብሔር መቅደስ መግቢያ በወለሉና በመሠዊያው መካከል ሀያ አምስት የሚያህሉ ሰዎች ጀርባቸው ወደ እግዚአብሔር መቅደስ ፊታቸውም ወደ ምሥራቅ ሆኖ ሸሚሽ ለተሰኘው ጣዖት ይሰግዱ ነበር።
\s5
\v 17 እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ይህን ታያለህ? በዚህ የሚያደርጉት ይህ ርኵሰት ለይሁዳ ቤት እንድ ቀላል ነገር ነውን? ምድሪቱን በግፍ ሞልተዋታል ያስቈጡኝም ዘንድ ተመልሰዋል፥ ቅርንጫፎችንም ወደ አፍንጫዎቻቸው አቅርበዋል።
\v 18 ስለዚህ እኔ ደግሞ በመካከላቸው እንቀሳቀሳለሁ ዓይኔ አይራራም ፣አላዝንላቸውም። ወደ ጆሮዬም በታላቅ ድምፅ ቢጮኹ አልሰማቸውም አለኝ።
\s5
\c 9
\p
\v 1 ከዚያም "ጠባቂዎች የሚያጠፋ መሣሪያን በእጃቸው ይዘው ወደ ከተማይቱ ይቅረቡ" ብሎ በታላቅ ድምፅ በጆሮዬ ጮኸ።
\v 2 እነሆም፥ እያንዳንዳቸው አጥፊውን መሣሪያ በእጃቸው ይዘው ስድስት ሰዎች በሰሜን አቅጣጫ ካለው ከላይኛው በር በኩል መጡ፣ በመካከላቸውም የበፍታ ልብስ የለበሰ የጸሐፊም ቀለም ቀንድ በወገቡ የያዘ አንድ ሰው ነበረ። እነርሱም ገብተው በናሱ መሠዊያ አጠገብ ቆሙ።
\s5
\v 3 የእስራኤልም አምላክ ክብር በበላዩ ከነበረበት ከኪሩብ ላይ ተነሥቶ ወደ ቤቱ መድረክ ሄደ። በፍታም የለበሰውን የጸሐፊውንም ቀለም ቀንድ በወገቡ የያዘውን ሰው ጠራ።
\v 4 እግዚአብሔርም "በኢየሩሳሌም ከተማ መካከል እለፍ፥ በመካከልዋም ስለ ተሠራው ርኵሰት ሁሉ በሚያለቅሱና በሚተክዙ ሰዎች ግምባር ላይ ምልክት አድርግ" አለው።
\s5
\v 5 እኔም እየሰማሁ ለሌሎቹ "እርሱን ተከትላችሁ በከተማይቱ መካከል እለፉ ግደሉም! ዓይናችሁ አይራራ አትዘኑም
\v 6 ሽማግሌውንና ጐበዙን ቈንጆይቱንም ሕፃናቶቹንና ሴቶቹን ፈጽማችሁ ግደሉ! ነገር ግን ምልክቱ ወዳለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ። ከመቅደሴም ጀምሩ!" አላቸው። በቤቱም አንጻር ባሉ ሽማግሌዎች ጀመሩ።
\s5
\v 7 እርሱም "ቀጥሉ! ቤቱን አርክሱ፥ አደባባዮቹንም በሬሳ" አላቸው። እነርሱም ወጥተው በከተማይቱ ላይ ጥቃት ፈጸሙ።
\v 8 ጥቃቱን እየፈጸሙ ሳሉ እኔ ብቻዬን እንደቀረሁ ሳይ በግምባሬ ተደፍቼ "ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ወዮ! መዓትህን በኢየሩሳሌም ላይ ስታፈስስ የእስራኤልን ቅሬታ ሁሉ ታጠፋለህን?" ብዬ ጮኽሁ።
\s5
\v 9 እርሱም፦ "'እግዚአብሔር ምድሪቱን ትቶአታል እግዚአብሔርም አያይም!' እያሉ የእስራኤልና የይሁዳ ቤት ኃጢአት እጅግ በዝቶአል ምድሪቱም ደም፥ ከተማይቱም ዓመፅን ተሞልታለች ።
\v 10 እኔም ደግሞ ዓይኔ አትራራላቸውም አላዝንምም። ይልቁኑ መንገዳቸውን በራሳቸው ላይ እመልሳለሁ" አለኝ።
\v 11 እነሆም፥ በፍታ የለበሰው የቀለም ቀንድም በወገቡ የያዘው ሰው ተመልሶ መጣና "ያዘዝኸኝን አድርጌአለሁ" የሚል ሪፖርት አቀረበ።
\s5
\c 10
\p
\v 1 ከዚያም በኪሩቤል ራስ ላይ ወደ ነበረው ጠፈር ተመለከትኩ። በላያቸው እንደ ሰንፔር ድንጋይ ያለ እንደ ዙፋን የሚመስል መልክ ተገለጠ።
\v 2 እግዚአብሔርም በፍታም የለበሰውን ሰው "በመንኰራኵሮች መካከል ከኪሩብ በታች ግባ፥ ከኪሩቤልም መካከል ካለው እሳት ፍም እጆችህን ሙላ በከተማይቱም ላይ በትነው" አለው። ሰውዬውም እያየሁት ገባ።
\s5
\v 3 ሰውዬውም ሲገባ ኪሩቤል በቤቱ ቀኝ በኩል ቆመው ነበር፥ ደመናም ውስጠኛውን አደባባይ ሞላው።
\v 4 የእግዚአብሔር ክብርም ከኪሩቤል ወጥቶ በቤቱ መድረክ ላይ ቆመ፤ ቤቱም በደመናው ተሞላ፥ አደባባዩም በእግዚአብሔር ክብር ፀዳል ተሞላ።
\v 5 ሁሉንም የሚችል አምላክ እንደሚናገረው ያለ ጽምፅ እንዲሁ የኪሩቤል ክንፎችን ድምፅ ክውጭው አደባባይ ሰማሁ።
\s5
\v 6 እግዚአብሔርም በፍታ የለበሰውን ሰው "ከመንኰራኵሮች ከኪሩቤል መካከል እሳት ውሰድ" ብሎ ባዘዘው ጊዜ ሰውዬው ገብቶ በአንደኛው መንኰራኵር አጠገብ ቆመ።
\v 7 ኪሩብም ከኪሩቤል መካከል እጁን በኪሩቤል መካከል ወዳለው እሳት ዘርግቶ ከዚያ ወሰደ፥ በፍታም በለበሰው ሰው እጅ አኖረው እርሱም ይዞ ወጣ።
\v 8 በኪሩቤልም ከክንፎቻቸው በታች የሰው እጅን መሳይ አየሁ።
\s5
\v 9 እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ በኪሩቤል አጠገብ አራት መንኰራኵሮች ነበሩ አንዱ መንኰራኵር በአንዱ ኪሩብ፥ አንዱ መንኰራኵር በአንዱ ኪሩብ አጠገብ ነበረ። የመንኰራኵሮቹም መልክ እንደ ቢረሌ ድንጋይ ነበረ።
\v 10 የአራቱም መልክ አንድ ይመስል ነበር፥ መልካቸውም በመንኰራኵር ውስጥ እንዳለ መንኰራኵር ነበረ።
\v 11 ሲንቀሳቀሱም ወደየትኛውም አቅጣጫ ይሄዱ ነበር፤ ፊት ለፊት ስለሚሄዱ ሲሄዱ አይገላመጡም ነበር። ሲሄዱም አይገላመጡም ነበር።
\s5
\v 12 ሰውነታቸው ሁሉ ማለትም ጀርባቸው፣ እጃቸውና ክንፋቸው በዓይን ተሞልቶ ነበር፣ አራቱ መንኰራኵሮችም ዙሪያቸውን በዓይኖች ተሞልተው ነበር።
\v 13 መንኰራኵሮችም እኔ እየሰማሁ "ተሽከርካሪዎች" ተብለው ተጠሩ።
\v 14 ለእያንዳንዱም አራት አራት ፊት ነበሩት አንደኛው ፊት የኪሩብ ፊት፥ ሁለተኛውም የሰው ፊት፥ ሦስተኛው የአንበሳ ፊት፥ አራተኛውም የንስር ፊት ነበረ።
\s5
\v 15 ከዚያም ኪሩቤል ማለትም በኮቦር ወንዝ ያየኋቸው ህያዋን ፍጥረታት ከፍ ከፍ አሉ
\v 16 ።ኪሩቤል በተንቀሳቀሱ ጊዜ ሁሉ መንኰራኵሮቹ በአጠገባቸው ይሄዱ ነበር፤ ኪሩቤልም ከምድር ከፍ ከፍ ይሉ ዘንድ ክንፎቻቸውን ሲዘረጉ መንኰራኵሮች ደግሞ ከአጠገባቸው ፈቀቅ አይሉም ነበር።
\v 17 የህያዋኑ ፍጥረታት መንፈስ በመንኰራኵሮች ውስጥ ስለነበረ ኪሩቤል ሲቆሙ መንኮራኩሮችመ ይቆሙ ነበር፥ ከፍ ከፍ ሲሉም መንኮራኩሮቹም ከእነርሱ ጋር ከፍ ከፍ ይሉ ነበር።
\s5
\v 18 የእግዚአብሔርም ክብር ከቤቱ መድረክ ላይ ወጥቶ በኪሩቤል ላይ ቆመ።
\v 19 ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ዘረጉ እኔም እያየሁ ከምድር ከፍ ከፍ አሉ በወጡም ጊዜ መንኰራኵሮች በአጠገባቸው እንደዚያው አደረጉ። በእግዚአብሔርም ቤት በምሥራቁ በር መግቢያ ቆሙ፥ የእስራኤልም አምላክ ክብር በላያቸው ወረደ።
\s5
\v 20 እነኚህም በኮበር ወንዝ ከእስራኤል አምላክ በታች ያየኋቸው ህያዋን ፍጥረታት ስለነበሩ ኪሩቤልም እንደ ነበሩ አውቄ ነበር።
\v 21 ለእያንዳንዱ አራት አራት ፊትና አራት አራት ክንፍ ነበሩት፥ የሰውም እጅ አምሳያ ከክንፎቻቸው በታች ነበረ።
\v 22 ፊቶቻቸውም በኮቦር ወንዝ በራዕይ ያየኋቸውን ፊቶች ይመስሉ ነበር ፣ እያንዳንዱም አቅንቶ ወደ ፊት ይሄድ ነበር።
\s5
\c 11
\p
\v 1 መንፈስም አነሣኝ ወደ ምስራቅ መውጫ ወደሚመለከት ወደ እግዚአብሔር ቤት ምሥራቅ በር አመጣኝ። እነሆም፥ በበሩ መግቢያ ሀያ አምስት ሰዎች ነበሩ፥ በመካከላቸውም የሕዝቡን አለቆች የዓዙርን ልጅ ያእዛንያንና የበናያስ ልጅ ፈላጥያን አየሁ።
\s5
\v 2 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፣ "የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ ክፋትን የሚያስቡ በዚህችም ከተማ ክፉን ምክር የሚመክሩ ሰዎች ናቸው።
\v 3 እነርሱም 'ቤቶችን የምንሠራበት ዘመን አይደለም። ይህች ከተማ ድስት እኛም ሥጋ ነን' ብለዋል።
\v 4 ስለዚህ፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገርባቸው፣ ትንቢት ተናገር።
\s5
\v 5 የእግዚአብሔርም መንፈስ በኔ ላይ ሆኖ እንዲህ አለኝ፥ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ተናገር። የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ይህን ነገር ተናግራችኋል፥ እኔም የልባችሁን አሳብ አውቃለሁ።
\v 6 በዚህች ከተማ ውስጥ ብዙ ሰዎችን ገድላችኋል ጎዳናዎችዋንም በሬሳዎቻቸው ሞልታችኋል።
\v 7 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በአየሩሳሌም ከተማ መካከልም ሬሳዎቻቸው ያኖራችኋቸው የገደላቹኋቸው ሰዎች ሥጋው ሲሆኑ፥ ይህችም ከተማ ድስቱ ናት። እናንተን ግን ከከተማዋ መካከል ተነቅላችሁ ትወጣላችሁ።
\s5
\v 8 ሰይፍን ፈርታችኋል እኔም ሰይፍን አመጣባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\v 9 ከከተማይቱ መካከል አወጣችኋለሁ፥ በእንግዶችም እጅ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፥ በላያችሁም ፍርድ አመጣባችኋለሁ።
\v 10 በሰይፍ ትወድቃላችሁ በእስራኤልም ድንበር ውስጥ እፈርድባችኋለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
\s5
\v 11 ይህች ከተማ የማብሰያ ድስት አትሆንላችሁም እናንተም በመካከልዋ ሥጋ አትሆኑም፣ እኔም በእስራኤል ድንበር ውስጥ እፈርድባችኋለሁ።
\v 12 እኔም በትዕዛዙ ያልሄዳችሁለት ፍርዱንም ያላደረግችሁለት እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። ይልቁኑ በዙሪያችሁ እንደሚኖሩት እንደ አሕዛብ ሕግ አድርጋችኋል።
\s5
\v 13 እንዲህም ሆነ ትንቢትም በተናገርሁ ጊዜ የበናያስ ልጅ ፈላጥያ ሞተ፣ እኔም በግምባሬ ተደፍቼ "ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! በውኑ የእስራኤልን ቅሬታ ፈጽመህ ታጠፋለህን?" ብዬ በታላቅ ድምፅ ጮኽሁ።
\s5
\v 14 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ
\v 15 "የሰው ልጅ ሆይ፥ ወንድሞችህ! አዎ ወንድሞችህ! ዘመዶችህ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩ ሁሉ! 'እነርሱ ከእግዚአብሔር የራቁ ናቸው! ይህች ምድር ርስት ሆና ለእኛ ተሰጥታለች' የሚሉአቸው ናቸው።
\s5
\v 16 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በላቸው፣ 'ምንም እንኳ እኔ በሩቅ ወዳሉ አሕዛብ ባርቃቸውና ወደ አገሮችም ብበትናቸውም በሄዱባቸው አገሮች ለጥቂት ጊዜ ቤተ መቅደስ ሆኜላቸዋለሁ' ።
\v 17 ስለዚህም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በላቸው 'ከአሕዛብ ዘንድ አከማቻችኋለሁ ከተበተናችሁባቸውም አገሮች እሰበስባችኋለሁ፥ የእስራኤልንም ምድር እሰጣችኋለሁ።
\v 18 ወደዚያም ይመጣሉ፥ ጸያፉንና ርኩሱንም ነገር ሁሉ ከዚያች ምድር ያስወግዳሉ።
\s5
\v 19 ወደኔ ሲቀርቡ አንድ ልብ እሰጣቸዋለሁ፥ በውስጣቸውም አዲስ መንፈስ አስቀምጣለሁ፤
\v 20 ከሥጋቸውም ውስጥ ድንጋዩን ልብ አውጥቼ የሥጋን ልብ እሰጣቸዋለሁ፣ ይህም በትእዛዜም እንዲሄዱና ፍርዴንም እንዲጠብቁና እንዲያደርጉት ነው። በዚያን ጊዜ እነርሱ ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።
\v 21 በልባቸው ወደ ጸያፍና ርኩስ ነገሮቻቸው በሚሄዱት ላይ መንገዳቸውን ወደራሳቸው እመልሳለሁ። ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው። "
\s5
\v 22 ኪሩቤልም ክንፎቻቸውንና በአጠገባቸው የነበሩትን መንኰራኵሮች ከፍ አደረጉ፣ የእስራኤልም አምላክ ክብር በላያቸው ላይ ነበረ።
\v 23 የእግዚአብሔርም ክብር ከከተማይቱ ውስጥ ተነሥቶ በከተማይቱ ምሥራቅ በኩል ባለው ተራራ ላይ ቆመ።
\s5
\v 24 መንፈስም አነሣኝ፥ ከእግዚአብሔርም ዘንድ በሆነ ራእይ ምርኮኞቹ ወዳሉበት ወደ ከላውዴዎን ምድር አመጣኝ። ያየሁትም ራእይ ከእኔ ተለየ።
\v 25 ከዚያም እግዚአብሔር ያሳየኝን ነገር ሁሉ ለምርኮኞች ነገርኳቸው።
\s5
\c 12
\p
\v 1 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 2 "የሰው ልጅ ሆይ፥ የምትኖረውዓመጸኞች ከመሆናቸው የተነሳ አይን እያላቸው በማያዩ ጆሮ እያላቸው በማይሰሙ በዓመፀኛ ሰዎች መካከል ነው!
\s5
\v 3 አንተ ግን የሰው ልጅ ሆይ፥ ለስደት ተዘጋጅ ምክንያቱም በፊታቸውም በጠራራ ፀሀይ ከስፍራህ ወደ ሌላ ስፍራ ተማርከህ እንድትሄድ አደርጋለ። ምናልባት ይህን ሲያዩ ዓመፀኛ ቤት እንደ ሆኑ ያስተውሉ ይሆናል።
\s5
\v 4 እቃዎችህን ሰብስበህ በቀን በፊታቸው ለስደት ተዘጋጅ፤ በማታም ጊዜ በፊታቸው ልክ ስደተኞች እንደሚያደርጉት ሂድ።
\v 5 እያዩህም ግንቡን ፈንቅለውና በእዚያ በኩል ውጣ።
\v 6 እያዩህም እቃዎችህን በጫንቃህ ላይ ተሸከምና በጨለማ ውጣ። ለእስራኤልም ህዝብ ምልክት አድርጌሃለሁና ምድሪቱን እንዳታይ ፊትህን ሸፍን።
\s5
\v 7 እንዳዘዘኝም አደረግሁ። በቀንም የስደት እቃዬን ወስጄ ማታ ላይ ግንቡን በእጄ ፈነቀልኩና በጨለማ አወጣቼ እያዩኝ በጫንቃዬ ላይ ተሸከምሁት።
\s5
\v 8 በነጋታውም የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
\v 9 "የሰው ልጅ ሆይ፥ ዓመፀኛው የእስራኤል ቤት 'የምታደርገው ምንድር ነው?' ብለው ጠየቁህን?
\v 10 አንተም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'ይህ ትንቢታዊ ጉዳይ በኢየሩሳሌም የሚኖረውን አለቃና በመካከላቸውም የሚኖሩትን የእስራኤል ቤትን ሁሉ የሚመለከት ነው' በላቸው።
\s5
\v 11 ደግሞም፦ እኔ ምልክታችሁ ነኝ እኔ እንዳደረግሁ እንዲሁ ይደረግባቸዋል፥ እነርሱም በስደት ወደ ምርኮ ይሄዳሉ በላቸው።
\v 12 በመካከላቸውም የሚኖረው አለቃ ንብረቱን በጫንቃው ላይ ተሸክሞ ግንቡን ፈንቅሎ በጨለማ ይወጣል። ንብረታቸውን ለማውጣት ግንቡን ይፈነቅላሉ። አለቃውም በዓይኑ ምድሪቱን እንዳያይ ፊቱን ይሸፍናል።
\v 13 መረቤንም በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ በወጥመዴም ይያዛል፥ ወደ ከለዳውያንም ምድር ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ ሆኖም አያያትም በዚያም ይሞታል።
\s5
\v 14 ሊረዱትም በዙሪያው ያሉትን ሁሉና ወታደሮቹን ሁሉ በየእቅጣጫው እበትናቸዋለሁ፣ከኋላቸውም ሰይፍ እልክባቸዋለሁ።
\v 15 በአሕዛብም መካከል በበተንኋቸው ጊዜ፥ በአገሮችም በዘራኋቸው ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
\v 16 ነገር ግን በሚሄዱባቸውም አሕዛብ መካከል ርኵሰታቸውን ሁሉ እንዲመዘግቡ ከሰይፍና ከራብ ከቸነፈርም ጥቂቶች ሰዎችን ከእነርሱ አተርፋለሁ፣ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
\s5
\v 17 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 18 "የሰው ልጅ ሆይ፥ እንጀራህን በመረበሽ ብላ ውኃህንም በመንቀጥቀጥና በኀዘን ጠጣ።
\s5
\v 19 ለምድሪቱም ሕዝብ 'ጌታ እግዚአብሔር ስለኢየሩሳሌም ነዋሪዎችና ስለ እስራኤል ምድር እንዲህ ይላል 'ክሚኖሩባት ሰዎች አመጽ የተንሳ ምድሪቱ ሞላዋ ስለምትጠፋ እንጀራቸውን በመረበሽ ወኃቸውንም በድንጋጤ ይጠጣሉ።
\v 20 ሰዎች የሚኖሩባቸው ከተሞች ባድማ ይሆናሉ ምድሪቱም ውድማ ትሆናለች እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ በላቸው።
\s5
\v 21 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ,
\v 22 "የሰው ልጅ ሆይ፥ በእስራኤል ምድር የሚነገረው'ዘመኑ ረዝሞአል ራእዩም ሁሉ ጠፍቶአል' የሚለው ምሳሌ ምንድር ነው?
\v 23 ስለዚህ እንዲህ በላቸው 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ክዚህ በኋላ የእስራኤል ህዝብ እንዳይጠቀሙበት ይህን ምሳሌ አስቀረዋለሁ ።' ከዚያም እንዲህ በላቸው "ዘመኑ ቀርቦአል እያንዳንዱ ራዕይም ይናገራል!'
\s5
\v 24 ምክንያቱም ከዚህ በኋላ በእስራኤል ቤት መካከል ከንቱ ራእይና ውሸተኛ ምዋርት አይሆንም።
\v 25 እኔ እግዚአብሔር ነኝና! እናገራለሁ የተናገርኩትንም ቃል እፈጽማለሁ። ነገሩ ከእንግዲህ አይዘገይም። እናንተ ዓመፀኛ ቤት ሆይ፥ በዘመናችሁ ቃሌን እናገራለሁ እፈጽመውማለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።"
\s5
\v 26 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል እንደገና መጣ፣
\v 27 "የሰው ልጅ ሆይ፥ እነሆ፥ የእስራኤል ቤት 'ይህ ያየው ራእይ ገና ስለወደፊቱ ነው ስለሩቅ ዘመንም ትንቢት ይናገራል' ብለዋል።
\v 28 ስለዚህ እንዲህ በላቸው 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የምናገረው ቃል ይፈጸማል እንጂ ከዚህ በኋላ አይዘገይም' ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው!"
\s5
\c 13
\p
\v 1 የእግዚአብሔርም ቃል እንደገና ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
\v 2 የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት በሚናገሩ በእስራኤል ነቢያት ላይ ትንቢት ተናገር፥ ከገዛ ልባቸውም ትንቢት የሚናገሩትን 'የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ!
\v 3 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ምንምን ሳያዩ የገዛ መንፈሳቸውን ለሚከተሉ ለሰነፎች ነቢያት ወዮላቸው!
\v 4 እስራኤል ሆይ፥ ነቢያትህ በምድረ በዳ እንደሚኖሩ ቀበሮች ናቸው።
\s5
\v 5 ፥ በእግዚአብሔርም ቀን በሰልፍ ትቆሙ ዘንድ ልትጠግኑት ወደ ፈረሰው ቅጥር አልወጣችሁም ።
\v 6 እግዚአብሔር ሳይልካቸው "እግዚአብሔር እንዲህና እንዲህ ይላል" የሚሉ ሰዎች ውሸተኛ ትንቢትንና ውሸተኛ ራዕይን አይተዋል። ያም ሆኖ ግን ቃላቸው እንደሚፈጸም ተስፋ ያደርጋሉ።
\v 7 እኔም ሳልናገር "እግዚአብሔር እንዲህ ብሎአል" የምትሉ እናንተ ከንቱ ራእይን ያያችሁ ውሸተኛንም ትንቢትን መናገራቼሁ አይደለምን?
\s5
\v 8 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ውሸተኛ ራእይንም ስላያችሁ ውሸት ስለተናገራችሁ ጌታ እግዚአብሔር በእናንተ ላይ የሚናገረው ይህ ነው፡
\v 9 እጄም ከንቱ ራእይን በሚያዩ፥ የውሸት ትንቢት በሚናገሩ ነቢያት ላይ ይሆናል። እነርሱም በሕዝቤ ጉባኤ ውስጥ አይገኙም፥ በእስራኤልም ቤት መዝገብ ላይ አይጻፉም፥ ወደ እስራኤልም ምድር አይገቡም እኔም ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ!
\s5
\v 10 በዚህም ምክንያት ሰላም ሳይኖር "ሰላም ነው!" እያሉ ሕዝቤን መረን ሰደዋል፣ ገለባ በሌለበት ጭቃ የተመረገ ቅጥር ይገነባሉ።
\v 11 ቅጥሩን ገለባ በሌለበት ጭቃ ለሚመርጉት ሰዎች እንዲህ በላቸው 'ቅጥሩ ይወድቃል፤ የሚያሰጥም ዝናብ ይዘንባል፥ ቅጥሩኔ ለማፍረስ ታላቅም የበረዶ ድንጋይ እልካለሁ፥ እንዲያደቀውም ዐውሎ ነፋስን እልካለሁ።
\v 12 እነሆ፥ ግንቡ በወደቀ ጊዜ። የመረጋችሁት ጭቃ ወዴት አለ? አይሉአችሁምን?
\s5
\v 13 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'በመዓቴ ዐውሎ ነፋስ አመጣለሁ ፥ በቍጣዬም ዶፍ ዝናብ ይዘንባል! በመዓቴም ታላቅ የበረዶ ድንጋይ ፈጽሞ ያወድመዋል።
\v 14 ገለባም በሌለበት ጭቃ የመረጋችሁትን ቅጥር አፈርሳለሁ ወደ ምድርም እጥለዋለሁ፥ መሠረቱም ይታያል። እርሱም ይናዳል እናንተም በመካከሉ ትጠፋላችሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
\s5
\v 15 በመዓቴም ግንቡንና ገለባ በሌለው ጭቃ የመረጉትን ሰዎችአጠፋለሁ። ግንቡም ሆነ መራጊዎቹ የሉም እላችኋለሁ።
\v 16 እነርሱም ስለ ኢየሩሳሌም ትንቢት የሚናገሩ የሰላምን ራእይ የሚያዩላት የእስራኤል ነቢያት ናቸው። ሰላምም የለም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር"
\s5
\v 17 አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ከገዛ ልባቸው ትንቢት በሚናገሩ በሕዝብህ ሴቶች ልጆች ላይ ፊትህን አድርግ ትንቢትም ተናገርባቸው፥
\v 18 እንዲህም በል፣ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነፍስን ለማጥመድ በመላ እጆቸው የጥንቆላ መከዳ ለሚሰፉ ለራሶቻቸውም የተለያየ መጠን ያላቸው ሽፋን ለሚሠሩ ሴቶች ወዮላቸው! የሕዝቤንም ነፍስ ብታጠምዱ በውኑ ነፍሳችሁን ታድናላችሁን?
\s5
\v 19 ውሸታችሁን ለሚሰሙት ሕዝቤ እየዋሻችሁ ለጭብጥ ገብስና ለቍራሽ እንጀራ ብላችሁ መሞት የማይገባቸውን ለመግደል በሕይወትም መኖር የማይገባቸውን በሕይወት በማኖር በሕዝቤ ፊትአርክሳችሁኛል።
\s5
\v 20 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ፦እነሆ፥ እኔ ነፍሳትን እንደ ወፍ በምታጠምዱባት በአስማት መተቶቻችሁ ላይ ነኝ፥ ከክንዳችሁም ወስጄ እቀደዋለሁ፥ እንደ ወፍም ያጠመዳችኋቸውን ህዝብ ነጻ አወጣለሁ።
\v 21 ሽፋኖቻችሁንም እቀድዳለሁ ሕዝቤንም ከእጃችሁ አድናለሁ፥ ከዚያም ወዲያ በእጃችሁ አይጠመዱም እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
\s5
\v 22 እኔም እንዲያዝን የማልፈልገውን የጻድቁን ልብ በውሸታችሁ አሳዝናችኋልና፥ በተቃራኒው ደግሞ ከክፉ መንገዱ ተመልሶ በሕይወት እንዳይኖር የኃጢአተኛውን ተግባር አበረታታችኋልና
\v 23 ሕዝቤን ከእጃችሁ ስለማድን ክእንግዲህ ከንቱን ራእይ አታዩም የውሸት ትንቢትም አትናገሩም፥ ምክንያቱም እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
\s5
\c 14
\p
\v 1 ከእስራኤልም ሽማግሌዎች መካከል የተወሰኑ ሰዎች ወደ እኔ መጥተው በፊቴ ተቀመጡ።
\v 2 ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
\v 3 የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ ሰዎች ጣዖቶቻቸውን በልባቸው አኑረዋል የበደላቸውንም መቅሠፍት በፊታቸው አቁመዋል ታዲያ እኔ ከእነርሱ ጥያቄ መቀበል አለብኝ?
\s5
\v 4 ስለዚህ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ፦ ከእስራኤል ቤት ጣዖቶቹን በልቡ የሚያኖር፥ የበደሉንም መቅሠፍት በፊቱ የሚያቆም ሰው ሁሉ ወደ ነቢዩ በመጣ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ጣዖታቱ ብዛት እመልስለታለሁ።
\v 5 ይህንንም የማደርገው ሁሉም በጣዖቶቻቸው ምክንያት ከእኔ በጣም በራቀው በልባቸው የእስራኤልን ቤት እንደገና ለመመለስ ነው!' ብለህ ንገራቸው።
\s5
\v 6 ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፣ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ንስሐ ግቡ ከጣዖቶቻችሁም ተመለሱ፥ ፊታችሁንም ከርኵሰታችሁ ሁሉ መልሱ።
\s5
\v 7 ከእስራኤልም ቤት፥ በእስራኤልም ዘንድ ከሚቀመጡ መጻተኞች ማንም፥ ከእኔ ተለይቶ ጣዖቶቹን በልቡ ያኖረ፥ የበደሉንም መቅሠፍት በፊቱ ያቆም ሰው ሁሉ፥ ጥያቄ ይዞ ወደ ነቢዩ ቢመጣ ፥ እኔ እግዚአብሔር እራሴ እመልስለታለሁ!
\v 8 ፊቴንም እዞርበታለሁ ከሕዝቤም መካከል አጠፋውና መቀጣጫና ምሳሌም አደርገዋለሁ ፣ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ!
\s5
\v 9 ነቢዩም ስቶ ሳለ መልዕክትን ቢናገር፥ እኔ እግዚአብሔር ያንን ነቢይ አስተዋለሁ፥ እጄንም በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ ከሕዝቤም ከእስራኤል መካከል አጠፋዋለሁ።
\v 10 ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ፤ የነቢዩ ኃጢአት መልዕክት ፍለጋ ወደእርሱ የሄደ ሰው ኃጢአት አንድ ይሆናል።
\v 11 በዚህም ምክንያት ከዚህ በኋላ የእስራኤል ቤት ከእኔ ርቀው አይቅበዘበዙም በኃጢአታቸውም ሁሉ አይረክሱም። እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።"
\s5
\v 12 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
\v 13 የሰው ልጅ ሆይ፥ ምድር በማመፅ በእኔ ላይ ኃጢአት ብትሠራ፥ እኔም እጄን ብዘረጋባት የእንጀራዋንም በትር ብሰብር ራብን ብሰድድባት ሰውንና እንስሳውንም ከእርስዋ ባጠፋ፥
\v 14 እነዚህም ሦስት ሰዎች፥ ኖኅ፣ ዳንኤልና ኢዮብም፥ በመካከልዋ ቢገኙ እነርሱ በጽድቃቸው ሊያዱኑ የሚችሉት የገዛ ነፍሳቸውን ብቻ ነበር፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\s5
\v 15 ክፉዎቹን አራዊት በምድር ባሳልፍ እነርሱም ልጆችዋን ቢያጠፉ ስለ አራዊትም ማንም እንዳያልፍባት ባድማ ብትሆን፥
\v 16 እነዚህም ሦስት ሰዎች ቢኖሩባት፥ እኔ ሕያው ነኝና እነርሱ ብቻቸውን ይድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም፥ ምድሪቱም ባድማ ትሆናለች፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\s5
\v 17 ወይም በዚያች ምድር ላይ ሰይፍ አምጥቼ። ሰይፍ ሆይ፥ በምድሪቱ ላይ እለፊ ብል፥ ሰውንና እንስሳውንም ከእርስዋ ባጠፋ፥
\v 18 እነዚህም ሦስት ሰዎች ቢኖሩባት፥ እኔ ሕያው ነኝና እነርሱ ብቻቸውን ይድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\s5
\v 19 ወይም በዚያች ምድር ላይ ቸነፈር ብሰድድ ሰውንና እንስሳውንም ከእርስዋ ለማጥፋት መዓቴን በደም ባፈስስባት፥
\v 20 ኖኅና ዳንኤል ኢዮብም ቢኖሩባት፥ እኔ ሕያው ነኝና በጽድቃቸው ነፍሳቸውን ብቻ ያድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\s5
\v 21 ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል። ይልቁንስ ሰውንና እንስሳን ከእርስዋ አጠፋ ዘንድ በኢየሩሳሌም ላይ አራቱን ክፉ ፍርዶቼን፥ ሰይፍንና ራብን ክፉዎችንም አውሬዎች ቸነፈርንም፥ በመስደድ ነገሮች እንዲከፉ አደርጋለሁ።
\s5
\v 22 ነገር ግን፥ እነሆ! ከወንዶችና ሴቶች ልጆች ጋር የሚያመልጡ ቅሬታዎች ይተርፉላታል። እነሆ! ወደ እናንተ ይወጣሉ እናንተም መንገዳቸውንና ሥራቸውን ታያላችሁ በኢየሩሳሌምም ላይ ስላመጣሁት ቅጣት በምድሪቱም ላይ ስላመጣሁባት ነገር ሁሉ ትጽናናላችሁ ።
\v 23 መንገዳቸውንና ሥራቸውን ባያችሁ ጊዜ ያጽናኑአችኋል ያደረግሁባትንም ሁሉ በከንቱ እንዳላደረግሁባት ታውቃላችሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\c 15
\p
\v 1 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
\v 2 "የሰው ልጅ ሆይ፥ የወይን ግንድ፥ በዱር ዛፎች መካከል ካለ ቅርንጫፎቼ ካሉት ማንኛውም ዛፍ ብልጫው ምንድር ነው?
\v 3 በውኑ ሥራ የሚሠራበትን እንጨት ከወይን ግንድ ይወስዳሉን? ወይስ ሰዎች ዕቃ የሚንጠለጠልበትን ችካል ከእርሱ ይወስዳሉን?
\v 4 እነሆ፥ ለመቃጠል በእሳት ላይ ቢጣል ፥ እሳቱም ሁለቱን ጫፎቹንና በልቶአል፥ መካከሉንም ቢያቃጥለው በውኑ ለሥራ ይጠቅማልን?
\s5
\v 5 እነሆ፥ ደህና ሳለ ለሥራ ካልጠቀመ፥ ይልቁንስ እሳት ከበላው እርሱም ከተቃጠለ በኋላ ለምንም አይጠቅምም!
\v 6 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዱር ዛፎች መካከል ካሉት ዛፎች ይልቅ የወይን ግንዱን እሳት ይበላው ዘንድ እንደ ሰጠሁት፥ እንዲሁ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን አሳልፌ እሰጣለሁ።
\s5
\v 7 ፊቴንም በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ ከእሳትም ይወጣሉ፥ እሳት ግን ይበላቸዋል ፊቴንም በእነርሱ ላይ ባደረግሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
\v 8 ዓመፅን አድርገዋልና ምድሪቱን ባድማ አደርጋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር!"
\s5
\c 16
\p
\v 1 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
\v 2 የሰው ልጅ ሆይ፥ ለኢየሩሳሌም ርኵሰትዋን አስታውቃት፥
\v 3 እንዲህም በል፣ "ጌታ እግዚአብሔር ለኢየሩሳሌም እንዲህ ይላል፡ ዘርሽና ትውልድሽ ከከነዓን ምድር ነው አባትሽ አሞራዊ ነበረ እናትሽም ኬጢያዊት ነበረች።
\s5
\v 4 በተወለድሽ ጊዜ እናትሽ እትብትሽን አልቆረጠችም ፣ በውኃ አላጠበችሽም ወይም በጨው አላሸችሽም፣ በጨርቅም አልጠቀለለችሽም።
\v 5 ከእነዚህ ነገሮች አንዱን እንኳ ሊያደርግልሽ ማንም አልራራልሽም! በተወለድሽበት ቀን በሜዳ ላይ ተጣልሽ።
\s5
\v 6 እኔ ግን በአንቺ ዘንድ ባለፍሁ ጊዜ በደምሽም ውስጥ ተለውሰሽ አየሁ፤ ስለዚህም በደምሽ እንዳለሽ "በሕይወት ኑሪ!" አልሁሽ።
\v 7 በእርሻ ላይ እንዳለ ቡቃያ አሳደግሁሽ። አንቺም አደግሽ ታላቅም ሆንሽ፥ በእጅጉም አጌጥሽ። ጡቶችሽም አጐጠጐጡ ጠጕርሽም አደገ፥ ነገር ግን ዕርቃንሽን ሆነሽ፥ ተራቍተሽም ነበር።
\s5
\v 8 እንደገና በአንቺ ዘንድ ባለፍሁና ባየሁሽ ጊዜ፥ እነሆ፥ ጊዜሽ የፍቅር ጊዜ ነበረ እኔም መጐናጸፊያዬን በላይሽ ዘርግቼ እራቁትነትሽን ሸፈንኩ።ከዚያም ማልሁልሽ ከአንቺም ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ አንቺም ለእኔ ሆንሽ።
\s5
\v 9 በውኃም አጠብሁሽ ከደምሽም አጠራሁሽ በዘይትም ቀባሁሽ።
\v 10 በወርቅ የተንቆጠቆጠ ልብስም አለበስሁሽ ከቆዳ የተሰራ ጫማ አደረግሁልሽ፤ በጥሩ በፍታ አስታጠቅሁሽ በሐርም ከደንሁሽ።
\v 11 በጌጥም አስጌጥሁሽ በእጅሽም ላይ አንባር በአንገትሽም ላይ ድሪ አደረግሁልሽ።
\v 12 በአፍንጫሽም ቀለበት በጆሮሽም ጕትቻ በራስሽም ላይ የክብር አክሊል አደረግሁ።
\s5
\v 13 በወርቅና በብር አጌጥሽ፤ ልብስሽም ጥሩ በፍታና ሐር ወርቀ ዘቦም ነበረ፤ አንቺም መልካምን ዱቄትና ማርን ዘይትንም በላሽ እጅግ በጣም ውብ ነበርሽ ከዚያም ንግሥት ሆንሽ።
\v 14 ባንቺ ላይ ካኖርኋት ከክብሬ የተነሣ ውበትሽ ፍጹም ነበረና ዝናሽ በአሕዛብ መካከል ወጣ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\s5
\v 15 ነገር ግን በውበትሽ ታምነሻል ስለ ዝናሽም አመንዝረሻል ምንዝርናሽንም ከመንገድ አላፊ ሁሉ ጋር አበዛሽ። የእነርሱም ንብረት ሆንሽ!
\v 16 ከልብስሽም ወስደሽ በኮረብቶች ላይ በዝንጕርጕር ልብስ ያስጌጥሻቸውን መስገጆች ለራስሽ ሠራሽ በዚያም ገለሞትሽ። እንዲህም ያለ ነገር ከአሁን በፊት አልነበረም፥ ከእንግዲህም ወዲያ አይሆንም።
\s5
\v 17 ከሰጠሁሽም ከወርቄና ከብሬ የተሠራውን የክብርሽን ዕቃ ወስደሽ የወንድ ምስሎች ለራስሽ አድርገሻል አመንዝረሽባቸውማል።
\v 18 ወርቀዘቦውን ልብስሽንም ወስደሽ ደረብሽላቸው፥ ዘይቴንና ዕጣኔንም በፊታቸው አኖርሽ።
\v 19 የሰጠሁሽንም እንጀራዬን ያበላሁሽንም መልካሙን ዱቄትና ዘይቱን ማሩንም ጣፋጭ ሽታ አድርገሽ በፊታቸው አኖርሽ፥ ይህ በእርግጥ ሆኖአል! ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\s5
\v 20 ለእኔም የወለድሻቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆችሽን ወስደሽ መብል ይሆኑ ዘንድ ለጣዖታቱ ሠዋሽላቸው። በውኑ የግልሙትና ተግባርሽ እንደ ቀላል የሚታይ ነገር ነውን?
\v 21 ልጆቼን አረድሽ ለእነርሱም የሚቃጠል መስዋዕት አድርገሽ አቀረብሽ
\v 22 በዚህ ሁሉ የርኵሰትና የግልሙትና ተግባርሽ ወቅት ዕርቃንሽን ተራቍተሽ በደምሽም ተለውሰሽ የነበርሽበትን የሕፃንነትሽን ወራት አላሰብሽም።
\s5
\v 23 ወዮ! ወዮልሽ! ይላል ጌታ እግዚአብሔር
\v 24 ከክፋትሽም ሁሉ በኋላ የጣዖት ማምለኪያ ስፍራ፥ በየአደባባዩም አጸዶችን ሠራሽ።
\s5
\v 25 በየመንገዱ ራስ ከፍ የማምለኪያ አጸዶችን ሠራሽ፥ ለመንገድ አላፊም ሁሉ እግርሽን በመግለጥና በርካታ የግልሙትና ተግባራት በመፈጸም ውበትሽን አረከስሽ ።
\v 26 እጅግ የሴሰኝነት ፍላጎት ካላቸው ከጐረቤቶችሽ ከግብጻውያን ጋር አመነዘርሽ፥ እኔንም ታስቈጭ ዘንድ ግልሙትናሽን አበዛሽ።
\s5
\v 27 ስለዚህ፥ በእጄ አደቅሻለሁ እህልንም ከአንቺ ዘንድ አጠፋለሁ። ለሚጠሉሽም ከክፉ ምኞትሽ የተነሣ ለውርደት ለሚዳርጉሽ ለፍልስጥኤም ሴቶች ልጆች ፈቃድ አሳልፌ ሰጥቼሻለሁ።
\v 28 አልጠግብ ብለሽ ከአሦራውያን ጋር ደግሞ ገለሞትሽ። ያም ሆኖ ግን አሁንም አልበቃሽም።
\v 29 እስከ ነጋዴዎች ምድር እስከ ከላውዴዎን ድረስ ግልሙትናሽን አበዛሽ። አሁንም ግን ገና አልጠገብሽም።
\s5
\v 30 የማታፍረውን የጋለሞታን ሥራ ሁሉ ሠርተሻልና ልብሽ ምንኛ ደካማ ነው? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\v 31 በየመንገዱ ራስ የምንዝርናሽን ስፍራ ሠርተሻል በየአደባባዩም ከፍ ያለውን ቦታሽን አድርገሻል። ዋጋዋን እንደምትንቅ እንደ ጋለሞታ አልሆንሽም።
\s5
\v 32 አንቺ ዘማዊ ሴት በባልሽ ፋንታ ሌሎች እንግዳ ሰዎች ተቀበልሽ።
\v 33 ሰዎች ለጋለሞቶች ሁሉ ዋጋ ገንዘብ ይከፍላሉ አንቺ ግን ለውሽሞችሽ ገንዘብ ትከፍያለሽ፥ ከአንቺም ጋር ለማመንዘር ከአካባቢው ሁሉ ወድ እንቺ እንዲምጡ ማባበያ ትሰጫቸዋለሽ።
\v 34 ግልሙትናሽ ከሌሎች ሴቶች ፈጽሞ የተለየ ነው፥ ምክንያቱም ማንም ከአንቺ ጋር ልትኛ ብሎ የሚጠይቅሽ የለም። ይልቁኑ አንቺ ትከፍያቸዋለሽ እንጂ የሚክፍልሽ የለም።
\s5
\v 35 ስለዚህ፥ ጋለሞታ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሚ!
\v 36 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከውሽሞችሽና ከአጽያፊ ጣዖታትሽ ጋር ባደረግሽው ግልሙትና አማካኝነት ክፉ ምኞትሽን በማፍሰስሽና ኀፍረተ ሥጋሽንም በመግለጥሽ እንዲሁም ለጣዖታትሽ በሰጠሻቸው በልጆችሽ ደም ምክንያት፥
\v 37 እነሆ፥ ከእነርሱ ጋር ደስ ያለሽን የወደድሻቸውንም ውሽሞችሽና የጠላሻቸው ሁሉ ከሁሉም አቅጣጫ በአንቺ ላይ እንዲነሱ እሰበስባቸዋለሁ። እራቁትነትሽን እንዲያዩ በፊታቸው ኀፍረተ ሥጋሽን እገልጣለሁ።
\s5
\v 38 ስለምንዝርናሽና ደም ማፍሰስሽ እቀጣሻለሁ፥ በቁጣዬና በቅንዓቴ ደም መፋሰስን አመጣብሻለሁ።
\v 39 በእጃቸውም አሳልፌ እሰጥሻለሁ፥ የምንዝርናሽንም ስፍራ ያፈርሳሉ ከፍ ያለውንም ቦታሽን ይገለብጣሉ ልብስሽንም ይገፉሻል የክብርሽንም ጌጥ ይወስዳሉ፥ ዕርቃንሽን አድርገው ዕራቁትሽን ይተዉሻል።
\s5
\v 40 ህዝብንም ያስነሱብሻል በድንጋይም ይወግሩሻል፥ በሰይፋቸውም ይሰነጥቁሻል።
\v 41 ቤቶችሽንም በእሳት ያቃጥላሉ በብዙም ሴቶች ፊት ብዙ ቅጣቶችን ይፈጽሙብሻል፥ ግልሙትናሽንም አስተውሻለሁ፥ ከእንግዲህ ለእነርሱ ዋጋ አትሰጭም!
\v 42 መዓቴንም በአንቺ ላይ እጨርሳለሁ ቅንዓቴም ከአንቺ ይርቃል፥ እኔም እረካለሁ፣ከዚያ በኋላም አልቈጣም።
\s5
\v 43 በእንዚህ ነገርች ሁሉ ስታስቆጪኝ የሕፃንነትሽን ወራት አላሰብሽምና፥ ስለዚህ፥ እነሆ፥ እኔ እራሴ ለፈጸምሽው ጥፋት ቅጣትን በአንቺ ላይ አመጣለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ ከዚህ በኋላ በአስነዋሪ መንገድሽ በክፋት አትሄጂም።
\s5
\v 44 እነሆ፥ በምሳሌ የሚናገር ሁሉ፥ "ልክ እንደ እናቲቱ ሴት ልጂቱ እንደዛው ናት" እያለ ምሳሌ ይመስልብሻል።
\v 45 አንቺ ባልዋንና ልጆችዋን የጠላች የእናትሽ ልጅ ነሽ፤ ደግሞም ባሎቻቸውንና ልጆቻቸውን የጠሉ የእኅቶችሽ እኅት ነሽ። እናታችሁ ኬጢያዊት ነበረች አባታችሁም አሞራዊ ነበረ።
\s5
\v 46 ታላቂቱም እኅትሽ ከሴቶች ልጆችዋ ጋር በስተ ሰሜን የምትኖረው ሰማርያ ናት ታናሺቱም እኅትሽ ከሴቶች ልጆችዋ ጋር በስተ ምዕራብ የምትኖረው ሰዶም ናት።
\s5
\v 47 አንቺ ግን በመንገዳቸው አልሄድሽም እንደ ርኵሰታቸውም አላደረግሽም የእነርሱ ድርጊት ለአንቺ ጥቂት ነበረና። ይልቁኑ በመንገድሽ ሁሉ ከእነርሱ የከፋሽ ሆንሽ።
\v 48 በህያውነቴ እምላለሁ አንቺና ሴቶች ልጆችሽ ያደርጋችሁትን ክፋት ያህል ሰዶምና ሴቶች ልጆችዋ አላደረጉም! ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\v 49 እነሆ፥ የእኅትሽ የሰዶም ኃጢአት ይህ ነበረ፡ በሥራ ፈትነት የበረታች፣ ስለምንም ነገር የማይሰማት ግድ የለሽት ነበረች። የችግረኛውንና የድሀውንም እጅ አላበረታችም ።
\v 50 ትዕቢተኛ ነበረች በፊቴም ርኩስ ነገርችን አደረገች፣ እንዳየሽውም አጠፋኋቸው።
\s5
\v 51 ሰማርያም የኃጢአትሽን እኵሌታ እንኳ አልሠራችም ፤ አንቺ ግን ከእኅቶችሽ ይልቅ ርኵሰትሽን አበዛሽ፥ በሠራሽውም ርኵሰት ሁሉ እህቶችሽ ካንቺ እንድሚሻሉ አሳየሽ።
\v 52 አሁንም ለእኅቶችሽ ስለ ፈረድሽ እፍረትሽን ተሸከሚ ከእነርሱ የባሰ ኃጢአት ሠርተሻልና ከአንቺ ይልቅ የተሻሉ ሆነው ታይተዋል። እህቶችሽ ካንቺ እንድሚሻሉ በማሳየትሽ እፈሪ ።
\s5
\v 53 የሰዶምና የሴቶች ልጆችዋን ምርኮ፥ የሰማርያንና የሴቶች ልጆችዋንም ምርኮ እመልሳለሁ፤ ነገር ግን የአንቺ ምርኮ በእነርሱ መካከል ይሆናል።
\v 54 በእዚህም ነገሮች ቀመር እፍረትሽን ታሳዪአለሽ ስለ አደረግሽውም ሁሉ ታፍሪያለሽ፣ በዚህም ምክንያት ለእነርሱ መጽናኛ ትሆኚያለሽ።
\v 55 እኅቶችሽም ሰዶምና ሴቶች ልጆችዋ ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው ይመለሳሉ፥ ሰማርያና ሴቶች ልጆችዋም ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው ይመለሳሉ። ከዚያም አንቺና ሴቶች ልጆችሽ ወደ ቀድሞ ሁኔታችሁ ትመለሳላችሁ።
\s5
\v 56 ኩሩ በነበርሽ ጊዜ ስለ እኅትሽ ሰዶም ተናግረሽ አታውቂም ነበር፥
\v 57 ክፋትሽ ከመገለጡ በፊትማለት ነው። አሁን ግን ለኤዶም ሴቶች ልጆችና በጎረቤቶችዋ ላሉ የፍሊስጤማውያን ልጆች ሁሉ፥ የውርደት ምሳሌ ሆነሻል። ሰው ሁሉ ይንቅሻል።
\v 58 ምንዝርነትሽንና ርኵስነትሽን ይገለጣል ፥ ይላል እግዚአብሔር፦
\s5
\v 59 ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል። ቃል ኪዳንን ለማፍረስ መሐላን በሚንቅ ሁሉ ላይ የማደርገውን በአንቺም ላይ አደርጋለሁ።
\s5
\v 60 ነገር ግን በሕፃንነትሽ ወራት ከአንቺ ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳኔን እኔ እራሴ አስባለሁ የዘላለምንም ቃል ኪዳን ከአንቺ ጋር እገባለሁ።
\v 61 እኅቶችሽንም ታላቂቱንና ታናሺቱን በተቀበልሽ ጊዜ መንገድሽን ታስቢያለሽ ታፍሪማለሽ። ለአንቺም ልጆች ይሆኑ ዘንድ እሰጣቸዋለሁ፥ ይህን የማደርገው ግን ስለ ቃል ኪዳንሽ አይደለም።
\s5
\v 62 ቃል ኪዳኔን ከአንቺ ጋር አጸናለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ!
\v 63 በዚህም ምክንያት ስላደረግሽውም ሁሉ ይቅር ባልሁሽ ጊዜ፥ ያደርግሽውን ሁሉ አስበሽ ታፍሪያለሽ ከዚያም ወዲያ ለምናገር አፍሽን አትከፍቺም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\s5
\c 17
\p
\v 1 የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 2 የሰው ልጅ ሆይ፥ በእንቈቅልሽ አጫውት እንዲህም ብለህ ለእስራኤል ቤት ምሳሌ ንገራቸው ፥
\v 3 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ታላቅ ክንፍ ረጅምም ማርገብገቢያ ያለው ላባም የተሞላ፥ መልከ ዝንጕርጕር ታላቅ ንስር ወደ ሊባኖስ መጣ፥ የዛፍ ቅርንጫፍን ጫፍ ወሰደ።
\v 4 የቅርንጫፉን ጫፍ ወደ ከነዓንም ምድር ወሰደው በነጋዶችም ከተማ ተከለው።
\s5
\v 5 ከዚያም ምድር ዘር ወሰደ በፍሬያማ እርሻም ተከለው። በብዙም ውኃ አጠገብ እንደ አኻያ ዛፍ አኖረው።
\v 6 በበቀለም ጊዜ ቁመቱ ያጠረ አረጉም ወደ እርሱ የሚመለስ ሥሩም በበታቹ የነበረ ሰፊ ወይን ሆነ።
\s5
\v 7 ታላቅ ክንፍና ብዙ ላባም ያለው ሌላ ታላቅ ንስር ነበረ። እነሆም፥ ውሀ ያጠጣው ዘንድ ይህ ወይን ሥሩን ወደ እርሱ አዘነበለ አረጉንም ከተተከለበት ከመደቡ ወደ እርሱ ሰደደ።
\v 8 አረግም ያወጣ ፍሬም ያፈራ የከበረም ወይን እንዲሆን በመልካም ላይ በብዙም ውኃ አጠገብ ተተክሎ ነበር።
\s5
\v 9 ለህዝቡም እንዲህ በል፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውኑ ይከናወንለት ይሆንን? ይደርቅስ ዘንድ፥ አዲስ የበቀለውስ ቅጠሉ ይጠወልግ ዘንድ ሥሩን አይነቅለውምን? ፍሬውንስ አይለቅመውምን? የትኛውም ጠንካራ ክንድ ወይም ብዙ ህዝብ ሥሩን ሊነቅል አይችልም።
\v 10 እነሆ፥ ከተተከል በኋላስ ይከናወንለት ይሆንን? የምሥራቅ ነፋስ ባገኘው ጊዜ ፈጽሞ አይደርቅምን? በተተከለበት መደብ ላይ ይደርቃል።
\s5
\v 11 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
\v 12 "ለዓመፀኛ ቤት፥ 'የዚህ ነገር ትርጓሜ ምን እንደ ሆነ አታውቁምን? እነሆ፥ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፥ ንጉሥዋንና መኳንንቶችዋንም ማረከ፥ ወደ እርሱም ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው።
\s5
\v 13 ከንጉሳዊያን ዘር የሆነውን ወስዶ ቃል ኪዳን ከእርሱ ጋር አደረገ አማለውም። የምድሪቱንም ኃያላን ወሰደ
\v 14 ይኸውም ቃል ኪዳኑን በመጠበቅ እንድትጸና እንጂ መንግሥቱ እንድትዋረድና ከፍ እንዳትል ነው።
\s5
\v 15 የኢየሩሳሌም ንጉስ ግን በእርሱ ላይ ሸፈተ ፈረሶችንና ብዙንም ሕዝብ ይሰጡት ዘንድ መልእክተኞችን ወደ ግብጽ ላከ። በውኑ ይከናወንለት ይሆንን? ይህንስ ያደረገ ያመልጣልን? ቃል ኪዳንንስ አፍርሶ ያመልጣልን?
\v 16 በህያውነቴ እምላለሁ! ባነገሠውና መሐላውን በናቀበቱ፥ ቃል ኪዳኑንም ባፈረሰበቱ ንጉሥ ምድር ይሞታል። በባቢሎን መካከል ይሞታል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\s5
\v 17 የባቢሎን ሠራዊት ብዙዎችን ነፍሳት ለማስወገድ አፈርን በደለደሉ ምሽግም በሠሩ ጊዜ፥ ፈርዖን ከብዙ ሠራዊቱና ከታላቁ ጉባኤው ጋር የኢየሩሳሌምን ንጉሥ በሰልፍ አይረዳውም።
\v 18 ይህም የሚሆነው መሐላውን ንቆ ቃል ኪዳኑንን በማፍረሱ ነው። ለቃል ኪዳን እጁን ዘርጋ፥ ነገር ግን እነዚህን ነገሮች አደረገ። ስለዚህ አያመልጥም።
\s5
\v 19 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በህያውነቴ እምላለሁ የናቀው መሐላዬን ያፈረሰስ ቃል ኪዳኔን አይደለምን? ስለዚህ ቅጣትን በርሱ ላይ አመጣለሁ!
\v 20 መረቤንም በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ በማጥመጃ መረቤም ይያዛል። ወደ ባቢሎንም አመጣዋለሁ በእኔም ላይ ስላደረገው ዓመፅ በዚያ በእርሱ ላይ እፈርዳለሁ።
\v 21 ጭፍሮቹም ሁሉ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ የቀሩትም ሁሉ በየአቅጣጫው ይበታተናሉ። እኔም እግዚአብሔር እንደሆንኩ ይህም እንደሚሆን እንደ ተናገርሁ ታውቃላችሁ!'
\s5
\v 22 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ 'እኔ እራሴ ከረጅሙ ዝግባ ጫፍ ላይ ቀንበጥን እወስዳለሁ ከለምለም ቅርንጫፎቹ አርቄ እተክለዋለሁ። ቀንጥቤ እኔ እራሴ በረጅምና በታላቅ ተራራ ላይ እተክለዋለሁ!
\v 23 ከፍ ባለው በእስራኤል ተራራ ላይ እተክለዋለሁ፥ ቅርንጫፎችም ያወጣል ፍሬም ያፈራል የከበረም ዝግባ ይሆናል በበታቹም በክንፍ የሚበርሩ ወፎች ሁሉ ያርፋሉ፥ በቅርንጫፎቹም ጥላ ውስጥ ጎጆአቸውን ይሰራሉ።
\s5
\v 24 በዚያን ጊዜ የዱር ዛፎች ሁሉ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ ያውቃሉ። ረጅሙን ዛፍ ዝቅ አደርጋለሁ፥ አጭሩንም ዛፍ ከፍ አድርጋለሁ! የለመለመውንም ዛፍ አደርቃለሁ፥ የደረቀውንም ዛፍ አለመልማለሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ይህ እንደሚሆን ተናግሬአለሁ እኔም አድርጌዋለሁ።
\s5
\c 18
\p
\v 1 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
\v 2 "ስለ እስራኤል ምድር፥ 'አባቶች መራራ የወይን ፍሬ በሉ፥ የልጆችም ጥርሶች ጠረሱ' ብላችሁ የምትመስሉት ምሳሌ ምንድር ነው?
\s5
\v 3 በህያውነቴ እምላለሁ እንግዲህ ወዲህ ይህን ምሳሌ በእስራኤል የምትናገሩብት ሁኔታ አይኖርም ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
\v 4 እነሆ፥ ነፍስ ሁሉ የእኔ ነው! የአባት ነፍስ የእኔ እንደ ሆነች የልጅም ነፍስ የእኔ ናት! ኃጢአት የሚሰራ ሰው ይሞታል!
\s5
\v 5 ሰውም ጻድቅ ቢሆን ፍርድንና ቅን ነገርን ቢያደርግ፥
\v 6 በተራራም ላይ ባሉ የጣዖት አምልኮ ስፍራ ባይበላ ዓይኞቹንም ወደ እስራኤል ቤት ጣዖታት ባያነሣ የባልንጀራውንም ሚስት ባያረክስ በወር አበባ ላይ ወዳለች ሴት ባይቀርብ
\s5
\v 7 ሰውንም ባያስጨንቅ ለባለ ዕዳም መያዣውን ቢመልስ የሌባ ተቀባይ ባይሆን ከእንጀራውም ለተራበ ቢሰጥ የተራቈተውንም ቢያለብስ
\s5
\v 8 በአራጣ ባያበድር፥ የማይገባ ትርፍን ባይወስድ፥ ፍትህን ቢያደርግ፥ በሰውና በሰው መካከልም መተማመንን ቢፈጥር
\v 9 በትእዛዜም ቢሄድ፥ እውነትንም ለማድረግ ፍርዴን ቢጠብቅ፥ ይህ ሰው ጻድቅ ነው፤ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል! ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\s5
\v 10 እርሱም ቀማኛና ደም አፍሳሽ ልጅ ከዚህም ሁሉ አንዳቸውን የሚያደርገውን ቢወልድ፥
\v 11 እርሱም ጻድቅ አባቱ የሠራውን ሁሉ ባይሠራ በተራራምላይ ባሉ የጣዖት አምልኮ ስፍራ ላይ ቢበላ የባልንጀራውንም ሚስት ቢያረክስ፥
\s5
\v 12 ድሀውንና ችግረኛውንም ቢያስጨንቅ ቢቀማም መያዣውንም ባይመልስ ዓይኖቹንም ወደ ጣዖታት ቢያነሣ ወይም ርኩስን ነገር ቢያደርግ፥
\v 13 በአራጣ ቢያበድር፥ የማይገባ ትርፍ ቢወስድ፥ በውኑ እርሱ በሕይወት ይኖራልን? በሕይወት አይኖርም! ይህን ርኵሰት ሁሉ አድርጎአልና ፈጽሞ ይሞታል ደሙም በላዩ ላይ ይሆናል።
\s5
\v 14 እነሆም፥ ልጅ ቢወልድ፥ እርሱም አባቱ የሠራውን ኃጢአት አይቶ ቢፈራ እንዲህም ባይሠራ፥
\v 15 በተራራ ባሉ የጣዖት አምልኮ ስፍራዎች ላይ ባይበላ ዓይኖቹንም ወደ እስራኤል ቤት ጣዖታት ባያነሣ የባልንጀራውንም ሚስት ባያረክስ፥
\s5
\v 16 ሰውንም ባያስጨንቅ መያዣውን ባይወስድ ባይቀማም ከእንጀራውም ለተራበ ቢሰጥ ለተራቈተውም ልብስን ቢያለብስ፥
\v 17 እጁንም ድሀን ከመበደል ቢመልስ፥ በአራጣ ባያበድር የማይገባ ትርፍንም ባይወስድ፤ ፍርዴንም ቢያደርግ በትእዛዜም ቢሄድ፥ እርሱ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል እንጂ በአባቱ ኃጢአት አይሞትም።
\s5
\v 18 አባቱ ግን ፈጽሞ በድሎአልና፥ ወንድሙንም ዘርፏልና፥ በሕዝቡም መካከል ክፉን ነገር አድርጎአልና እነሆ፥ እርሱ በበደሉ ይሞታል።
\s5
\v 19 እናንተ ግን፥ 'ልጅ የአባቱን ኃጢአት ስለ ምን አይሸከምም? ትላላችሁ። ልጅ ፍርድንና ቅን ነገርን ባደረገ ትእዛዜንም ሁሉ በጠበቀና ባደረገ ጊዜ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል!
\v 20 ኃጢአትን ያደረገ ሰው ይሞታል። ልጅ የአባቱን ኃጢአት አይሸከምም፥ አባትም የልጁን ኃጢአት አይሸከምም። የጻድቁ ጽድቅ በራሱ ላይ ይሆናል፥ የኃጢአተኛውም ኃጢአት በራሱ ላይ ይሆናል።
\s5
\v 21 ኃጢአተኛውም ካደረጋት ኃጢአት ሁሉ ቢመለስ ትእዛዜንም ሁሉ ቢጠብቅ ፍርድንና ቅን ነገርንም ቢያደርግ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም።
\v 22 የበደለው በደል ሁሉ አይታሰብበትም በሠራው ጽድቅ በሕይወት ይኖራል።
\s5
\v 23 በውኑ ከመንገዱስ ቢመለስና በሕይወት ቢኖር እንጂ በኃጢአተኛ ሞት እደሰታለሁን? ይላል ጌታ እግዚአብሔር
\s5
\v 24 ጻድቁ ግን ከጽድቁ ቢመለስ ኃጢአትንም ቢሠራ ኃጢአተኛውም እንደሚያደርገው ርኵሰት ሁሉ ቢያደርግ፥ በሕይወት ይኖራልን? የሠራት ጽድቅ ሁሉ አትታሰብለትም ባደረገው ዓመፅና በሠራት ኃጢአት በዚያች ይሞታል።
\s5
\v 25 እናንተ ግን፥ 'የጌታ መንገድ የቀናች አይደለችም' ትላላችሁ። የእስራኤል ቤት ሆይ፥ እንግዲህ ስሙ! በውኑ መንገዴ የቀናች አይደለችምን? ይልቅስ የእናንተ መንገድ ያልቀናች አይደለችምን?
\v 26 ጻድቁ ከጽድቁ ቢመለስ፥ ኃጢአትንም በሠራ ጊዜ፥ በዚያም ቢሞት፥ እርሱ ባደረገው በደል ይሞታል።
\s5
\v 27 ኃጢአተኛውም ከሠራው ኃጢአት ቢመለስ ፍርድንና ቅን ነገርንም ቢያደርግ ነፍሱን ያድናል።
\v 28 አስቦ ከሠራው በደል ሁሉ ተመልሶአልና ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም።
\s5
\v 29 ነገር ግን የእስራኤል ቤት፥ 'የጌታ መንገድ የቀናች አይደለችም!' ይላል። የእስራኤል ቤት ሆይ፥ መንገዴ የቀናች ያልሆነው እንዴት ነው? የእናንተ መንገድስ የቀናች የሆነችው እንዴት ነው?
\v 30 የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ስለዚህ በመካከላችሁ በእያንዳንዱ ሰው እንደ መንገዱ እፈርድበታለሁ! ይላል ጌታ እግዚአብሔር። ንስሐ ግቡ ኃጢአትም ዕንቅፋት እንዳይሆንባችሁ ከኃጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።
\s5
\v 31 የበደላችሁትን በደል ሁሉ ከእናንተ ጣሉ አዲስ ልብና አዲስ መንፈስም ለእናንተ አድርጉ። የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ስለ ምን ትሞታላችሁ?
\v 32 የምዋቹን ሞት አልፈቅድምና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ።
\s5
\c 19
\p
\v 1 አንተም በእስራኤል አለቆች ላይ ይህን ሙሾ አሙሽ፥ እንዲህም በል፥
\v 2 'እናትህ ማን ነበረች? አንበሳ ነበረች ከአንበሳ ደቦል ጋር ተጋደመች ግልገሎችዋን አሳደገች።
\v 3 ከግልገሎችዋም አንዱን ደቦል አንበሳ እንዲሆንና ጠላቶቹን የሚቆራርጥ እንዲሆን አሳደገችው። ሰዎችንም በላ።
\v 4 አሕዛብም ወሬውን ሰሙ እርሱም በወጥመዳቸው ተያዘ፥ በሰንሰለትም አድርገው ወደ ግብጽ ምድር ወሰዱት።
\s5
\v 5 እርስዋም ይመለሳል ብላ ብትጠብቅም ተስፋዋ እንደ ጠፋ ባየች ጊዜ፥ ከግልገሎችዋ ሌላን ወስዳ ደቦል አንበሳ እንዲሆን አሳደገችው።
\v 6 ደቦል አንበሳውም በአንበሶች መካከል ተመላለሰ ደቦል አንበሳም ሆነ ንጥቂያም ተማረ፥ ሰዎችንም በላ።
\v 7 መበለቶቻቸውን አስነወረ፥ ከተሞቻቸውንም አፈረሰ ከግሣቱም ድምፅ የተነሣ ምድሪቱና በሞላ ሰው አልባ ሆነች።
\s5
\v 8 አሕዛብም ከየአገሩ ሁሉ ተሰበሰቡ፤ መረባቸውንም በእርሱ ላይ ዘረጉ በወጥመዳቸውም ተያዘ።
\v 9 በሰንሰለትም አድርገው በሳጥን አድርገው ወደ ባቢሎን ንጉሥ አመጡት። ድምፁም በእስራኤል ተራሮች ላይ ከዚያ ወዲያ እንዳይሰማ ወደ አምባ አመጡት።
\s5
\v 10 እናትህ በውኃ አጠገብ በደምህ ውስጥ እንደ ተተከለች ወይን ነበረች። ከውኃም ብዛት የተነሣ ፍሬያማና በቅርንጫፍ የትሞላች ነበረች ።
\v 11 ለእርስዋም ብርቱዎች በትሮች ነበሩአት እነርሱም ለነገሥታት በትሮች ነበሩ። ቁመቷም በዛፎች ቅርንጫፎች መካከል ከፍ አለ።
\s5
\v 12 ነገር ግን በመዓት ተነቀለች ወደ መሬትም ተጣለች የምሥራቅም ነፋስም ፍሬዋን አደረቀ። ብርቱዎች ቅርንጫፎቿተሰበሩና ደረቁ፥ እሳትም በላቻው።
\v 13 አሁን በምድረ በዳ፥ በደረቅና ውሀ በሌለው መሬት ተተክላለች።
\s5
\v 14 ከቅርንጫፎቿ እሳት ወጥቶ ፍሬዋ በላ፥ ጠንካራ ቅርንጫፍ የለባትም የነገሥታትም በትር ሊሆን የሚችልም የለም።' ይህ ሙሾ ነው፥ የልቅሶ ዝማሬም ይሆናል።
\s5
\c 20
\p
\v 1 እንዲህም ሆነ በሰባተኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በአሥረኛው ቀን የእስራኤል ሽማግሌዎች እግዚአብሔርን ሊጠይቁ መጥተው በፊቴ ተቀመጡ።
\s5
\v 2 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
\v 3 "የሰው ልጅ ሆይ፥ ለእስራኤል ሽማግሌዎች ተናገር፥ እንዲህም በላቸው። 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔን ትጠይቁ ዘንድ መጥታችኋልን? በህያውነቴ እምላለሁ በእናንተ አልጠየቅም! ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\s5
\v 4 ትፈርድባቸዋለህን? የሰው ልጅ ሆይ፥ በውኑ ትፈርድባቸዋለህን? የአባቶቻቸውን ርኵሰት አስታውቃቸው!
\v 5 እንዲህም በላቸው፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እስራኤልን በመረጥሁበት ለያዕቆብም ቤት ዘር እጄን አንስቼ በማልሁበት ቀን በግብጽም ምድር በተገለጥሁላቸውና። እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ ብዬ በማልሁላቸው ጊዜ፥
\v 6 በዚያ ቀን ከግብጽ ምድር በጥንቃቄ ወደመረጥኩላቸው፥ ወተትና ማር ወደምታፈስሰው፥ የምድርም ሁሉ ጌጥ ወደምትሆን ምድር እንደማወጣቸው ማልሁላቸው!
\s5
\v 7 እኔም፥ "ከእናንተ እያንዳንዱ ርኩስ ነገርንና የግብጽን ጣዖታት ከዓይኑ ፊት ያስወግድ። ራሳችሁን አታርክሱ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።" አልኋቸው።
\s5
\v 8 እነርሱ ግን ዐመፁብኝ ሊሰሙኝም አልወደዱም። እያንዳንዱ ርኩስ ነገሮችን ከአይኑ ፊት አላስወገደም የግብጽንም ጣዖታት አልተወም በዚህም ጊዜ። በግብጽ ምድር መካከል ቍጣዬን ልፈጽምባቸው መዓቴንም ላፈስባቸው ወሰንኩ።
\v 9 ነገር ግን በመካከላቸው በሚኖሩበት ህዝብ መካከል እንዳይረክስ ስለ ስሜ ሰራሁ። ከግብጽ ምድር በማውጣት ራሴን በአይናቸው ፊት ገለጥኩላቸው።
\s5
\v 10 ከግብጽም ምድር አወጣኋቸው ወደ ምድረ በዳም አመጣኋቸው።
\v 11 ሰው ቢያደርገው በሕይወት የሚኖርበትን ሥርዓቴንም ሰጠኋቸው፥ ፍርዴንም አስታወቅኋቸው።
\v 12 ለራሴ የለየኋቸው እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቁ ዘንድ፥ በእኔና በእነርሱ መካከል ምልክት እንዲሆን ሰንበታቴን ሰጠኋቸው።
\s5
\v 13 ነገር ግን የእስራኤል ቤት በምድረ በዳ ዐመፁብኝ። በትዕዛዜም አልሄዱም፤ ይልቁኑ ሰው ቢያደርገው በሕይወት የሚኖርበትንም ፍርዴን ጣሉ። ሰንበታቴንም ፈጽመው አረከሱ፥ ስለዚህም አጠፋቸው ዘንድ ቍጣዬን በምድረ በዳ አፈስስባቸዋለሁ አልሁ።
\v 14 ነገር ግን በፊታቸው ባወጣኋቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።
\s5
\v 15 ወተትና ማርም ወደምታፈስሰው የምድር ሁሉ ጌጥ ወደምትሆን ልሰጣቸው ወዳሰብኩት ምድር አላመጣቸውም ብዬ በምድረ በዳ ማልሁባቸው።
\v 16 ይህን የማልኩት ልባቸው ጣዖቶቻቸውን ስለተከተሉ፥ ፍርዴንም ስለጣሉ ፥ በሥርዓቴም ስላልሄዱ፥ ሰንበታቴንም ስላረከሱ ነው።
\v 17 ነገር ግን ዓይኔ ራራችላቸው እኔም አላጠፋኋቸውም፥ በምድረ በዳም ፈጽሜ አልፈጀኋቸውም።
\s5
\v 18 ለወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው በምድረ በዳ እንዲህ አልኋቸው፥ "በአባቶቻችሁ ሥርዓት አትሂዱ፤ ወጋቸውንም አትጠብቁ በጣዖቶቻቸውም አትርከሱ።
\v 19 እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ! በትእዛዜ ሂዱ ፍርዴንም ጠብቁ አድርጓትም!
\v 20 በእናንተና በእኔ መካከል ምልክት እንዲሆኑና እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ እንድታውቁ ሰንበታቴን ጠብቁ።"
\s5
\v 21 ነገር ግን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው ዐመፁብኝ። በሥርዓቴም አልሄዱም ወይም ሰው ቢፈጽመው በሕይወት የሚኖርባትን ፍርዴን አልጠበቁም። ሰንበታቴንም አረከሱ ስለዚህም በምድረ በዳ መዓቴን ላፈስባቸው ቍጣዬንም ልፈጽምባቸው ወሰንክ።
\v 22 ነገር ግን እጄን መለስሁ፥ በፊታቸውም ባወጣኋቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።
\s5
\v 23 ደግሞም ወደ አሕዛብ ልበትናቸው ፥ በአገሮችም መካከልም ለነቀፋ ላደርጋቸው በምድረ በዳ እጄን አንስቼ ማልሁባቸው። ፍርዴን አላደረጉምና
\v 24 ሥርዓቴንም ጥሰዋልና ሰንበታቴንም አርክሰዋልና ዓይናቸውም የአባቶቻቸውን ጣዖታቶች ተከትለዋልና ይህን ላደርግባቸው ወሰንኩ።
\s5
\v 25 ደግሞም መልካም ያልሆነውን ሥርዓት በሕይወት የማይኖሩበትንም ህግ ሰጠኋቸው።
\v 26 እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ እንዲያውቁ አጠፋቸው ዘንድ፥ ማኅፀን የሚከፍተውን በኩር ሁሉ በእሳት ባሳለፉ ጊዜ፥ በመባቸው አረከስኋቸው።
\s5
\v 27 ስለዚህ፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ለእስራኤል ቤት ተናገር፥ እንዲህም በላቸው፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡ በዚህም ደግሞ አባቶቻችሁ ባደረጉት ዓመፅ አስቈጡኝ።
\v 28 እሰጣቸውም ዘንድ ወደ ማልሁላቸው ምድር ባገባኋቸው ጊዜ፥ በኮረብታ ላይ ያለውን የጣዖት ማምለኪያ ሁሉና ቅጠልማውንም ዛፍ ባዩ ጊዜ፥ በዚያ መሥዋዕታቸውን ሠዉ በዚያም የሚያስቈጣኝን ቍርባናቸውን አቀረቡ። በዚያም ደግሞ ጣፋጩን ሽታቸውን አደረጉ በዚያም የመጠጥ ቍርባናቸውን አፈሰሱ።
\v 29 እኔም፥ "እናንተ ወደ እርሱ የምትሄዱበት ኮረብታማ ሥፍራ ምንድር ነው?" አልኋቸው። እስከ ዛሬም ድረስ ስሙ ባማ ተብሎ ተጠርቶአል።
\s5
\v 30 ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በላቸው፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንደ አባቶቻችሁ ልማድ ለምን ትረክሳላችሁ? ለምን እንደአመንዝራ የሚያጸይፍ ተግባር ታከናውናላችሁ?
\v 31 ቍርባናችሁን ስታቀርቡ፥ ልጆቻችሁንም በእሳት ስታሳልፉ፥ እስከ ዛሬ ድረስ በጣዖቶቻችሁ ትረክሳላችሁ። ታዲያ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ከእናንተስ ዘንድ እጠየቃለሁን? በህያውነቴ እምላለሁ ከእናንተ ዘንድ አልጠየቅም-ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
\v 32 እናንተ "እንጨትና ድንጋይ እንድሚያመልኩት ወገኖች እንደ ሌሎች አሕዛብ እንሁን" ብላችሁ ያሰባችሁት ሀሳብ ይፈጸማል።
\s5
\v 33 በህያውነቴ እምላለሁ በበረታች እጅና በተዘረጋች ክንድ በእናንተ ላይ በፈሰሰችም መዓት እነግሥባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር!
\v 34 ከአሕዛብም ዘንድ አወጣችኋለሁ ከተበተናችሁባትም አገር ሁሉ በበረታች እጅና በተዘረጋች ክንድ በፈሰሰችም መዓት እሰበስባችኋለሁ።
\v 35 ወደ አሕዛብም ምድረ በዳ አመጣችኋለሁ በዚያም ፊት ለፊት ከእናንተ ጋር እፋረዳለሁ።
\s5
\v 36 በግብጽ ምድረ በዳ በአባቶቻችሁ ላይ እንደፈረድኩ እንዲሁ በእናንተ ላይ እፋረዳለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
\v 37 ከበሬም በታች አሳልፋችኋለሁ ወደ ቃል ኪዳንም እስራት አገባችኋለሁ፤
\v 38 ከእናንተም መካከል ዓመፀኞችንና የበደሉኝን እለያለሁ። በእንግድነት ከኖሩባትም ምድር አወጣቸዋለሁ፥ ወደ እስራኤል ምድር ግን አይገቡም። እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ!
\s5
\v 39 ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል። እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ እያንዳንዳችሁ ወደየጣዖቶቻችሁ ሂዱ፥ ከዚህም በኋላ እኔኔ መስማት ካልፈለጋችሁ እነርሱን አምልኩ። ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ በቍርባናችሁና በጣዖቶቻችሁ ቅዱሱን ስሜን አታረክሱም።
\s5
\v 40 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል- በቅዱሱ ተራራዬ፥ ከፍ ባለው በእስራኤል ተራራ ላይ፥ በዚያ የእስራኤል ቤት ሁሉ ሁላቸው በምድራቸው ያመልኩኛል። በዚያም ቍርባናችሁን በኵራታችሁንም የቀደሳችሁትንም ነገር ሁሉ በደስታ እቀበላለሁ።
\v 41 ከአሕዛብም ዘንድ ባወጣኋችሁ ጊዜ ከተበተናችሁባትም አገር ሁሉ በሰበሰብኋችሁ ጊዜ እንደ ጣፋጭ ሽታ እቀበላችኋለሁ፥ በአሕዛብም ፊት እቀደስባችኋለሁ።
\s5
\v 42 ለአባቶቻችሁም እሰጣት ዘንድ ወደ ማልሁላቸው ምድር ወደ እስራኤል አገር ባገባኋችሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
\v 43 በዚያም የረከሳችሁባትን መንገዳችሁንና ሥራችሁን ሁሉ ታስባላችሁ ስለ ሠራችሁትም ክፋት ሁሉ ራሳችሁን ትጸየፋላችሁ።
\v 44 ስለዚህም የእስራኤል ቤት ሆይ፥ እንደ ክፉ መንገዳችሁና እንደ ርኩስ ሥራችሁ ሳይሆን ስለ ስሜ ብዬ ይህን ባደረኩላችሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\v 45 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
\v 46 "የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ ደቡብ አቅና በደቡብ ላይ ተናገር፤ በኔጌብ ዱር ላይ ትንቢት ተናገር
\v 47 ለኔጌብም ዱር፥ 'የእግዚአብሔርን ቃል ስማ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በአንተ ውስጥ እሳት አነድዳለሁ። በውስጥህም ያለውን የለመለመውንና የደረቀውን ዛፍ ሁሉ ይበላል። የሚንበለበለው እሳትም አይጠፋም፤ ከደቡብም ጀምሮ እስከ ሰሜን ድረስ ያለው ገጽታ ሁሉ ይቃጠላል።
\s5
\v 48 እሳቱን ስለኩሰውና ሳይጠፋ በሚነድበት ጊዜ ሥጋ ለባሽ ሁሉ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ ያያል።'"
\v 49 እኔም፥ "ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! እነርሱ ስለ እኔ፥ "ይሄ ምሳሌን ብቻ ተናጋሪ አይደለም እንዴ?" ይላሉ አልሁ።
\s5
\c 21
\p
\v 1 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
\v 2 "የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ ኢየሩሳሌም አቅና በመቅደሶችም ላይ ተናገር፤ በእስራኤልም ምድር ላይ ትንቢት ተናገር።
\v 3 ለእስራኤልም ምድር እንዲህ በል፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በእናንተ ላይ ነኝ፥ ሰይፌንም ከሰገባው እመዝዘዋለሁ፥ ጻድቁንና ክፉውንም ከእናንተ ዘንድ አጠፋለሁ።
\s5
\v 4 እኔም ጻድቁንና ክፉውን ከእናንተ ዘንድ ስለማጠፋ፥ ሰይፌ ከደቡብ ጀምሮ እስከ ሰሜን ድረስ ባለ በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ ከሰገባው ይመዘዛል።
\v 5 ሥጋ ለባሹም ሁሉ እኔ እግዚአብሔር ሰይፌን ከሰገባው እንደ መዘዝሁ ያውቃል፥ ስይፌም ከእንግዲህ አይመለስም!
\s5
\v 6 ስለዚህም፥ አንተ የሰው ልጅ ሆይ፥ አልቅስ ወገብህን በማጕበጥ በፊታቸው ምርር ብለህ አልቅስ።
\v 7 እነርሱም 'ስለ ምን ታለቅሳለህ?' ብለው ይጠይቁሀል፥ አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፥ 'ስለሚምጣው ክፉ ዜና ነው፥ ምክንያቱም ልብ ሁሉ ይቀልጣል፥ እጆችም ሁሉ ይዝላሉ፥ ነፍስም ሁሉ ትደክማለች፥ ጉልበትም እንደ ውኃ ይፈስሳል። እነሆ፥ ይመጣል ይፈጸምማል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር'"
\s5
\v 8 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
\v 9 የሰው ልጅ ሆይ፥ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ትንቢት ተናገር ሰይፍ! ሰይፍ! የተሳለና የተወለወለ ሰይፍ በል።
\s5
\v 10 ለታላቅ ግድያ ተስሎአል! እንደመብረቅም እንዲያብረቀርቅ ይወለወላል! በልጄን በትረ መንግስት ደስ ሊለን ይገባልን? የሚመጣው ስይፍ የዚህ አይነቱን በትር ይጠላል።
\v 11 ሰይፉም እንዲወለወልና በእጅ እንዲያዝ ይሰጣል! ሰይፉ የትሳል ነው! ለገዳይም ሊስጥ ተወልውሎ ተዘጋጅቷል!'
\s5
\v 12 የሰው ልጅ ሆይ፥ ሰይፉ እየመጣ ያለው በሕዝቤ ላይ ነውና፥ ለሰይፉም የሚሰጡት የእስራኤል አለቆች ሁሉ ናቸውና ለእርዳታ ተጣራ፥ አልቅስ! ሕዝቤ ነበሩና ስለዚህ ጭንህን በምሬት ጽፋ!
\v 13 ፈተና ደርሶአል፥ በትረ መንግስት ቢጸና ምን ዋጋ አለው? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\s5
\v 14 ስለዚህ፥ አንተ የሰው ልጅ፥ ትንቢት ተናገር፥ እጅህን አጨብጭብ ሰይፍ ለሶስተኛ ጊዜ ጥቃት ይፈጽማልና! ለሚታረዱ የተዘጋጅ ስይፍ! ሰውነታቸውን ሁሉ ሊወጋ ለሚታረዱ ለብዙዎች ሰዎች የተመደበ ሰይፍ ነው!
\s5
\v 15 ልባቸው እንዲቀልጥ መሰናክላቸውም እንዲበዛ የሚገድለውን ሰይፍ በበሮቻቸው ሁሉ ላይ አድርጌአለሁ! ወዮ! እንድመብረቅ ሆኗል እንዲገድልም ነጻ ተለቋል።
\v 16 ሰይፍ ሆይ ተዘጋጅ! ስለትህ ወደፈቀደው ወደ ቅኝም ወደ ግራም ምታ።
\v 17 እኔ ደግሞ በእጄ አጨበጭባለሁ መዓቴንም እፈጽማለሁ! እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።"
\s5
\v 18 የእግዚአብሔርም ቃል እንደገና ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
\v 19 "አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ ይመጣ ዘንድ ሁለት መንገዶችን አድርግ። ሁለቱም መንገዶች ከአንድ ምድር ይነሳሉ፥ የመንገድ ምልክቱም አንደኛው መንገድ ወደ ከተማ እንድሚወስድ ያሳያል።
\v 20 አንዱ መንገድ የባቢሎን ጦር ወደ አሞናዊያን ከተማ ወድ ረባት እንድሚወስድ አመልክት። ሌላኛው መንገድ ወደ ይሁዳ ወደ ተመሸገች ወደ ኢየሩሳሌም እንድሚወስድ አመልክት።
\s5
\v 21 የባቢሎን ንጉሥ የጥንቆላ ምሪት ለማግኘት በመንታ መንገድ መታጠፊያ ላይ ይቆማል። ፍላጾችን ይወዘውዛል፥ ከጣዖታቱም ምሪት ይጠይቃል። ጉበትም ይመለከታል።
\v 22 የቅጥሩን ማፍረሻ ያደርግ ዘንድ፥ አፍንም በጩኸት ይከፍት ዘንድ፥ በውካታም ድምፅን ከፍ ያደርግ ዘንድ፥ የቅጥሩን ማፍረሻ በበሮች ላይ ያደርግ ዘንድ፥ አፈርን ይደለድል ዘንድ፥ ምሽግም ይሠራ ዘንድ የኢየሩሳሌም ዕጣ በቀኝ እጁ ውስጥ ነበረ።
\v 23 በኢየሩሳሌም ላሉ ለባቢሎናዊያን መሐላን ማሉ ዓይን ፊት የሐሰት ምዋርት ይመስላል፥ ነገር ግን ንጉሱ እንዲያዙ ለማድረግ ስምምነታችሁን አፍርሳችኋል ብሎ ይከሳቸዋል።
\s5
\v 24 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ኃጢአታችሁን እንዳስብ ስላደርጋችሁኝ መተላለፋችሁ ይገለጣል! ኃጢአታችሁም በሥራችሁ ሁሉ ይታያል! በዚህም ምክንያት በጠላቶቻችሁ እጅ እንደተያዛችሁ ስውን ሁሉ ታሳስባላችሁ!
\s5
\v 25 አንተም የምትቀጣበት ቀን የደረስብህ ፥ አመጻ የማድረጊያ ዘመን ያበቃብህ፥ አመጸኛና ክፉ የእስራኤል አለቃ ሆይ፥
\v 26 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መጠምጠሚያውን አውልቅ፥ ዘውዱንም ከራስህ ላይ አንሳ! ከእንግዲ ነገሮች እንደነበሩ አይቀጥሉም! የተዋረደውን ከፍ አድርግ፥ ከፍ ያለውንም አዋርድ።
\v 27 ባድማ፥ ባድማ፥ ሁሉንም ባድማ አደርጋለሁ! የሚገባው ሰው እስኪመጣና ለእርሱ እስከምሰጠው ድረስ ንግስና ከእንግዲህ አይኖርም።
\s5
\v 28 አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ 'ጌታ እግዚአብሔር ስለሚመጣባቸው ውርደት ለአሞን ልጆች እንዲህ ይላል፡ ሰይፍ፥ ሰይፍ ተመዟል! ለማጥፋትና ለመግደል ተስሏል፤ እንደመብረቅም ያብለጨልጫል!
\v 29 ነቢያት ባዶ ራዕይ እያዩልህና ምዋርት እያሟረቱልህ ሳለ ይህ ሰይፍ ሊገደሉ ባሉት የሚቀጡበት ቀን በደረሰባቸው የእመጽ ዘመናቸው ባበቃባቸው ሰዎች አንገት ላይ ያርፋል።
\s5
\v 30 ሰይፉን ወደ ሰገባውም መልሰው። በተፈጠርህበት ስፍራ በተወለድህባትም ምድር እፈርድብሃለሁ!
\v 31 ቍጣዬንም አፈስስብሃለሁ! የመዓቴም እሳት አናፋብሃለሁ፥ በማጥፋት ለተካኑ ለጨካኞች ሰዎች እጅ አሳልፌ እሰጥሃለሁ!
\s5
\v 32 ለእሳት ማገዶ ትሆናለህ! ደምህም በምድሪቱ መካከል ይፈሳል፥ መታሰቢያም አይኖርህም፥ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁና።
\s5
\c 22
\p
\v 1 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
\v 2 "አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ትፈርዳለህን? ደም በምታፈስስ ከተማ ላይ ትፈርዳለህን? ርኵሰትዋን ሁሉ አስታውቃት።
\v 3 እንዲህም ልትላት ይገባል፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡ ይህች ጊዜዋ እንዲደርስ በመካከልዋ ደምን የምታፈስ፤ እንድትረክስም ጣዖታትን የምታደርግ ከተማ ናት!
\s5
\v 4 ስላፈሰስሽው ደም በደለኛ ነሽ ፥ ባደረግሽውም ጣዖታት ረክሰሻል! ቀንሽን አቀረብሽ ዘመንሽንም አሳጠርሽ። ስለዚህ ለአሕዛብ መሰደቢያ ለአገሮችም ሁሉ መሳለቂያ አደርግሻለሁ።
\v 5 አንቺ ስምሽ የረከሰ ግራ መጋባት የሞላብሽ ሆይ፥ በቅርብም በሩቅም ያሉ ይሳለቁብሻል።
\s5
\v 6 እነሆ፥ የእስራኤል አለቆች እያንዳንዳቸው በኃይላቸው መጠን ደም ያፈስሱ ዘንድ በአንቺ ውስጥ ነበሩ።
\v 7 በውስጥሽ አባቶችንና እናቶችም አቃለሉ፥ በመካከልሽ በመጻተኛው ላይ በደልን አደረጉ። በአንቺ ውስጥ ድሀ አደጉንና መበለቲቱን አስጨነቁ።
\v 8 ቅዱሳቴንም ናቅሽ ሰንበታቴንም አረከስሽ!
\v 9 ደምን ያፈስሱ ዘንድ ቀማኞች ሰዎች በአንቺ ውስጥ ነበሩ በተራሮችም ላይ በሉ። በመካከልሽ ክፋትን አደረጉ።
\s5
\v 10 በአንቺ ውስጥ የአባቶቻቸውን ኀፍረተ ሥጋ ገለጡ በአንቺም ውስጥ በወር አበባ ላይ ያለችን ሴት አዋረዱ።
\v 11 በባልንጀራቸው ሚስቶች ጋር ርኵሰትን ያደርጉ፥ የልጆቻአውን ሚስቶች ያረከሱ፥ የገዛ አባቶቻቸውን ሴት ልጆች እህቶቻችውን ያስነወሩ፥ እንዲህ ያሉ ስዎች ሁሉ በአንቺ ውስጥ አሉ።
\v 12 በአንቺ ውስጥ ደምን ለማፍሰስ ጉቦን ይቀብላሉ። አንቺም አራጣና አላስፈላጊ ትርፍ ወስደሻል፥ ጎረቤቶችሽን በጭቆና ጎዳሻቸው ፥ እኔንም ረሳሽኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\v 13 ስለዚህ፥ እነሆ፥ ያለቅንነት የሰበሰብሽውን ሀብት በመካከልሽ ያለውን ደም ማፍስስ በእጄ እቀጣለሁ።
\v 14 በውኑ እኔ ይህን በማደርግብሽ ወራት ልብሽ ይታገሣልን? ወይስ እጅሽ ትጸናለችን? እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ አደርገውማለሁ።
\v 15 ወደ አሕዛብም እበትንሻለሁ ወደ አገሮችም እዘራሻለሁ። በዚህ መንገድ ርኵሰትሽን ከአንቺ ዘንድ አጠፋለሁ።
\v 16 በአሕዛብም ፊት አንቺ የረከሽ ትሆኚያለሽ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂአለሽ።
\s5
\v 17 ቀጥሎም የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
\v 18 የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤል ቤት ለእኔ እንደ ዝቃጭ ሆኑብኝ። እነርሱ ሁሉ በእንቺ ውስጥ የመዳብና የቆርቆሮ ፥ የብረትና የእርሳስ ተረፍ ምርት ናቸው። እነርሱ በማቅለጫ ውስጥ የብር ዝቃጭ ናቸው።
\v 19 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሁላችሁ ዝቃጭ ሆናችኋልና ስለዚህ፥ እነሆ፥ በኢየሩሳሌም ውስጥ እሰበስባችኋለሁ።
\s5
\v 20 እንዲያቀልጡት እሳት ያናፉበት ዘንድ ብርንና መዳብን ብረትንና እርሳስን ቈርቈሮንም በከውር እንደሚሰበስቡ፥ እንዲሁ አቀልጣችኋለሁ። ስለዚህ በቍጣዬና በመዓቴ እሰበስባችኋለሁ፥ በዚያም ውስጥ እጨምራችኋለሁ እሳትም አናፋባችኋለሁ አቀልጣችሁማለሁ።
\v 21 ስለዚህም አሰበስባችሁማለሁ የመዓቴንም እሳት አናፋባችኋለሁ በውስጡም ትቀልጣላችሁ።
\v 22 ብርም በማቅለጫ ውስጥ እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ በውስጧ ትቀልጣላችሁ እኔም እግዚአብሔር መዓቴን እንዳፈሰስሁባችሁ ታውቃላችሁ።
\s5
\v 23 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
\v 24 የሰው ልጅ ሆይ እንዲህ በላት 'አንቺ ያልነጻሽ ምድር ነሽ። በቍጣ ቀን ዝናብ የለም!
\v 25 በውስጥዋ ያሉ ነቢያት እንደሚጮኽና እንደሚናጠቅ አንበሳ አንድ ሆነው ተማምለው ህይወት ያጠፋሉ፥ ከፍ ያለ ብልጥግና ይወስዳሉ! በውስጥዋም መበለቶችን ያበዛሉ!
\s5
\v 26 ካህናቶችዋም ሕጌን አቃለዋል ቅድሳቴንም አርክሰዋል። ቅዱስ በሆነና ቅዱስ ባልሆነ መካከልም አይለዩም፥ በንጹሕና በርኩስ መካከል ያለውን ልዩነት አያስተምሩም። ፊታቸውንም ከሰንበታቴ መለሱ እኔም በመካከላቸው ረከስሁ።
\v 27 በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ እንደሚናጠቁ ተኵላዎች ናቸው። የስስትን ትርፍ ለማግኘት ሲሉ ደምን ያፈሳሉ ህይወትንም ያጠፋሉ።
\v 28 እግዚአብሔርም ሳይናገር ነቢያቶችዋ፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል" እያሉ ከንቱን ራእይ በማየት የሐሰትንም ምዋርት ለእነርሱ በማምዋረት ያለ ገለባ በጭቃ ይመርጓቸዋል።
\s5
\v 29 የምድሪቱም ሕዝብ በማስፈራራት ግፍ አደረጉ ዘረፋ ፈጸሙ፥ ድሆችንና ችግረኞችን አስጨነቁ፥ ያለ ፍትህ መጻተኛውንም በደሉ።
\s5
\v 30 ቅጥርን የሚጠግንን፥ ምድሪቱንም እንዳላጠፋት በፈረሰበት በኩል በፊቴ የሚቆምላትን ሰው በመካከላቸው ፈለግሁ፥ ነገር ግን አንድም ሰው አላገኘሁም።
\v 31 ስለዚህ ቍጣዬን አፈስባቸዋልሁ፥ በመዓቴም እሳት አጠፋቸዋለሁ መንገዳቸውንም በራሳቸው ላይ እመልሳለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።"
\s5
\c 23
\p
\v 1 የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
\v 2 የሰው ልጅ ሆይ፥ የአንዲት እናት ልጆች የሆኑ ሁለት ሴቶች ነበሩ።
\v 3 በግብጽ አገር በኰረዳነታቸው ዕድሜ አመነዘሩ በዚያ ገለሞቱ። በዚያ ጡቶቻቸው ምዋሸሹ በዚያም የድንግልናቸው ጡቶች ተዳበሱ።
\v 4 ስማቸውም የታላቂቱ ኦሖላ የታናሽ እኅትዋም ኦሖሊባ ነበረ። ለእኔም ሆኑ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለዱ። ኦሖላ ሰማርያ ናት ኦሖሊባ ደግሞ ኢየሩሳሌም ናት።
\s5
\v 5 ኦሖላም የእኔ ሆና እያለ ገለሞተችብኝ፤ ውሽሞችዋንም ኃያላኑን ጎረቤቶችዋን አሦራውያንን በሴሰኝነት ተከተለቻቸው።
\v 6 እነርሱም ሰማያዊ ሐር የለበሱ አለቆችና ሹማምቶች፥ መልከ መልካሞች ጐበዛዝት፥ በፈረስ ላይ የሚቀመጡ ፈረሰኞች ነበሩ።
\v 7 ስለዚህ ራሷን ለተመረጡ ለአሦር ሰዎች ሁሉ ለግልሙትና ሰጠቻቸው ፥ በሴሰኝነት በተከተለቻቸውም ጣዖቶቻቸው ሁሉ ረከሰች።
\s5
\v 8 በግብጽም የነበረውን ግልሙትናዋን አልተወችም በዚያ በኰረዳነትዋ ጊዜ ከእርስዋ ጋር ተኝተው ነበር፥ የድንግልናዋንም ጡቶች ዳብሰው ነበር፥ ግልሙትናቸውንም አፍስሰውባት ነበር።
\v 9 ስለዚህ በፍቅር በተከተለቻቸው በውሽሞችዋ በአሦራውያን እጅ አሳልፌ ሰጠኋት።
\v 10 እነርሱም ኅፍረተ ሥጋዋን ገለጡ ወንዶችና ሴቶች ልጆችዋንም ማርከው ወሰዱ፥ እርስዋንም በሰይፍ ገደሉ በሌሎች ሴቶች ዘንድ መተረቻ ሆነች ስለዚህም ፈረዱባት።
\s5
\v 11 እኅትዋም ኦሖሊባ ይህን አየች ሆኖም ከእርስዋ ይልቅ በሴሰኝነቷ በረታች፥ ግልሙትናዋም ከእኅትዋ ግልሙትና ይልቅ በዛ።
\v 12 አለቆችንና ሹማምቶችን ጎረቤቶችዋን ጌጠኛ ልብስ የለበሱትን በፈረሶች ላይ የሚቀመጡትን ፈረሰኞች፥ ሁሉም መልከ መልካሞችን ጐበዛዝት አሦራውያንን በሴሰኝነት ተከተለቻቸው።
\v 13 የረከሰችም እንደ ሆነች አየሁ። የሁለቱም አእህትማማቾች ሁኔታ አንድ ነው።
\s5
\v 14 ግልሙትናዋንም አበዛች! በቀይ ቀለምም የተሳለውን የከለዳውያንን ስዕል፥ በግድግዳ ላይ የተሳሉትን ሰዎች አየች።
\v 15 በወገባቸው ዝናር የታጠቁ ራሳቸውንም በቀለማዊ መጠምጠሚያ የጠመጠሙ ነበሩ! ሁሉም የከለዳዊያን ተወላጆችና የሠረገላ አዛዦች ይመስሉ ነበር።
\s5
\v 16 ባየቻቸውም ጊዜ ለክፉ ተመኘቻቸው፥ ወደ ከላውዴዎን ምድር ወደ እነርሱ መልእክተኞችን ላከች።
\v 17 የባቢሎንም ሰዎች ወደ እርስዋ ወደ ሴሰኝነት መኝታ መጡ በግልሙትናቸውም አረከሱአት እርስዋም ከእነርሱ ጋር ረከሰች በውርደትም ከእነርሱ ተለየች።
\s5
\v 18 ግልሙትናዋንም ገለጠች ኅፍረተ ሥጋዋንም አሳየች ነፍሴም ከእኅትዋ እንደ ተለየች እንዲሁ ነፍሴ ከእርስዋ ተለየች።
\v 19 ነገር ግን በግብጽ ምድር የገለሞተችበትን የኰረዳነትዋን ዘመን በማሰላሰል ግልሙትናዋን አበዛች።
\s5
\v 20 የወንድ ብልቶቻቸው እንደ አህዮች የወንድ ዘራቸውም እንደ ፈረሶች ዘር የሆነውን ውሽሞቿን በሴሰኝነት ተከተለቻቸው።
\v 21 ስለ ኰረዳነትሽ ምክንያት ግብጻውያን ጡቶችሽን የዳበሱበትን ጊዜ የኰረዳነትሽን ሴሰኝነት ተመኘሽ።
\s5
\v 22 ስለዚህ፥ ኦሖሊባ ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'የተለየሻቸውን ውሽሞችሽን አስነሣብሻለሁ! ከሁሉም አቅጣጫ በአንቺ ላይ አመጣቸዋለሁ!
\v 23 እነርሱም የባቢሎን ሰዎች ከለዳውያንም ሁሉ፥ ፋቁድ፥ ሱሔ፥ ቆዓ፥ ከእነርሱም ጋር አሦራውያን ሁሉ፥ መልከ መልካሞች ጐበዛዝት፥ አለቆችና ሹማምቶች ሁሉ፥ መሳፍንቶችና አማካሪዎች ሁሉ፥ በፈረስ ላይ የተቀመጡ ናቸው።
\s5
\v 24 በመሣሪያና በሰረገላ በመንኰራኵርም በብዙ ሠራዊትም ይመጡብሻል! ታላላቅና አነስተኛ ጋሻና ራስ ቍርም ይዘው በዙሪያሽ ይዘጋጁብሻል! እንዲቀጡሽ እድልን እሰጣቸዋለሁ፥ በተግባራቸውም ይቀጡሻል!
\v 25 ቅንዓቴንም በአንቺ ላይ ስለማደርግ በመዓትም ስለሚገናኙሽ አፍንጫሽንና ጆሮሽንም ከአንቺ ይቈርጣሉ፥ ከአንቺም የቀረ በሰይፍ ይወድቃል ወንዶችና ሴቶች ልጆችሽንም ማርከው ይወስዳሉ፥ ከአንቺም የቀረውን እሳት ትበላቸዋለች!
\s5
\v 26 ልብስሽንም ይገፍፉሻል ጌጣጌጥሽንም ይወስዳሉ!
\v 27 አሳፋሪ ባህሪሽን፥ ከግብጽ ምድር ያመጣሽውን ግልሙትናሽንም ከአንቺ አስወግዳለሁ። ዓይንሽንም ወደ እነርሱ በናፍቆት አታነሺም ግብጽንም ከዚያ ወዲያ አታስቢም።
\s5
\v 28 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ 'እነሆ፥ በጠላሻቸው እጅ፥ በተለየሻቸውም እጅ አሳልፌ እሰጥሻለሁ!
\v 29 እነርሱም በጥላቻ ይገናኙሻል፥ ንብረትሽን ሁሉ ይወስዳሉ፥ ዕራቁትሽንና ዕርቃንሽን ይተዉሻል። የግልሙትናሽም ነውር፥ ሴሰኝነትሽና ግልሙትናሽም ሁሉ ይገለጣል።
\s5
\v 30 ከአሕዛብ ጋር ስላመነዘርሽ በጣዖቶቻቸውም ስለ ረከስሽ ይህ ነገር ይደርስብሻል።
\v 31 በእኅትሽ መንገድ ሄደሻል ስለዚህ የቅጣት ጽዋዋን በእጅሽ እሰጥሻለሁ።
\s5
\v 32 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 'የጠለቀውንና የሰፋውን ብዙም የሚይዘውን የእኅትሽን ጽዋ ትጠጪአለሽ መሳቂያና መሳለቂያም ትሆኛለሽ!
\s5
\v 33 በእኅትሽ በሰማርያ ጽዋ፥ በድንጋጤና በጥፋት ጽዋ፥ በስካርና በውርደት ትሞያለሽ!
\v 34 ትጠጪዋለሽ ትጨልጪውማለሽ መጠጫውንም ትሰባብሪዋለሽ በስብርባሪውም ጡትሽንም ትሸነትሪዋለሽ እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር፦
\s5
\v 35 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 'ረስተሽኛልና፥ ወደ ኋላሽም ጥለሽኛልና አንቺ ደግሞ የሴሰኝነትሽንና የግልሙትናሽን ውጤት ተሸከሚ።
\s5
\v 36 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ "የሰው ልጅ ሆይ፥ በኦሖላና በኦሖሊባ ትፈርዳለህን? እንግዲያውስ አሳፋሪ ተግባራቸውን አስታውቃቸው
\v 37 አመንዝረዋልና፥ ደምም በእጃቸው አለና! ከጣዖቶቻቸውም ጋር አመንዝረዋልና፥ ለእኔም የወለዱአቸውን ልጆቻቸውን ለእሳት መቃጠል አሳልፈዋቸዋልና።
\s5
\v 38 ይህን በእኔ ላይ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል፡ በዚያ ቀን መቅደሴን አርክሰዋል ሰንበታቴንም ሽረዋል!
\v 39 ልጆቻቸውንም ለጣዖቶቻቸው በሠዉበት በዚያው ቀን ያረክሱት ዘንድ ወደ መቅደሴ ገቡ! እነሆም፥ በቤቴ ውስጥ ያደረጉት ይህ ነው።
\s5
\v 40 ደግሞ ከሩቅም ወደሚመጡ ሰዎች መልእክተኛ ልከሻቸዋል። እነርሱም መጥተዋል! እነሆም መጡ፥ አንቺም ታጠብሽና ዓይኖችሽን ትኩለሽ አጊጠሽም ጠብቅሻቸው።
\v 41 ከፊት ለፊቱ ገብታ በተዘጋጀበት በክብር አልጋ ላይ ተቀመጥሽ፥ ዕጣኔንና ዘይቴንም አኖርሽበት።
\s5
\v 42 በጭንቀት የተሞላ የህዝብ ድምፅ በአንቺ ዘንድ ነበረ፥ ሰካራሞችም ከሌሎች ምናምንቴ ሰዎች ጋር ከምድረ በዳ መጡ። በእጅሽም ላይ አንባር በራስሽም ላይ የተዋበ አክሊል አደረጉ።
\s5
\v 43 እኔም በምንዝር ስለሻገተችው ፥ 'አሁን ከእርስዋ ጋር ያመነዝራሉ እርስዋም ከእነርሱ ጋር ታመነዝራለች' አልሁ።'
\v 44 ወደ ጋለሞታም እንደሚገቡ ወደ እርስዋ ገቡ እንዲሁ ይሴስኑ ዘንድ በግልሙትና በደለኛ ወደሆኑት ወደ ኦሖላና ወደ ኦሖሊባ ገቡ።
\v 45 ሴቶቹ አመንዝሮች ናቸውና፥ በእጃቸውም ደም አለና ጻጽቃን ሰዎች ለአመንዝሮቹና ለደም አፍሳሾቹ የተመደበውን ቅጣት ያስተላልፉባቸዋል።
\s5
\v 46 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ታላቅ ጦር አመጣባቸዋለሁ፥ ለመበተንና ለመበዝበዝም አሳልፌ አሰጣቸዋለሁ።
\v 47 ሠራዊቱም በድንጋይ ይወግሩአቸዋል በሰይፋቸውም ይቈርጡአቸዋል። ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም ይገድላሉ፥ ቤቶቻቸውንም በእሳት ያቃጥላሉ።
\s5
\v 48 ከእንግዲህ ሴቶች ሁሉ የሴሰኝነት ተግባር እንዳይፈጽሙ ሴሰኝነትን ከምድሪቱ ላይ አጠፋለሁ።
\v 49 ሴሰኝነታችሁንም በላያችሁ ላይ ይመልሳሉ። እናንተም ኃጢአታችሁንና ጣዖቶቻችሁን ትሸከማላችሁ በዚህ መንገድ እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
\s5
\c 24
\p
\v 1 በዘጠነኛው ዓመት በአሥረኛው ወር ከወሩም በአሥረኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
\v 2 "የሰው ልጅ ሆይ፥ በዚህ ቀን የባቢሎን ንጉሥ ኢየሩሳሌምን ከቧልና የዚህን ቀን፥ የዛሬን ቀን ስም ጻፍ ።
\s5
\v 3 ለዓመፀኛውም ቤት ምሳሌን ተናገር እንዲህም በላቸው፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ድስቱን ጣድ! ጣደው! ውኃም ጨምርባት!
\v 4 የምግብ ፍራፍሬዎችን በውስጡ ጨምር፥ ጭኑንና ወርቹን በእርስዋ ውስጥ ሰብስብ፥ የተመረጡትንም አጥንቶች ሙላባት!
\v 5 ከመንጋው የተመረጠውን ውሰድ፥ አጥንቶቹም እንዲበስሉ እንጨት በበታችዋ ማግድ አጥንቶቹም በውስጥዋ ቀቅል።
\s5
\v 6 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዝገት ላለባት ዝገትዋም ለማይለቃት ምንቸት፥ ለደም ከተማ ወዮላት! ጥቂት ጥቂት ከውስጡ ውሰድ፥ ነገር ግን ዕጣ አታውጣላት።
\s5
\v 7 ደምዋ በውስጥዋ አለና! በተራቈተ ድንጋይ ላይ አደረገችው እንጂ በአፈር ይከደን ዘንድ በመሬት ላይ አላፈሰሰችውም
\v 8 ይህም መዓትን አመጣባት። ደምዋም እንዳይከደን በተራቈተ ድንጋይ ላይ አፈሰስኩት!
\s5
\v 9 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለደም ከተማ ወዮላት! እኔ ደግሞ የማገዶውን ክምር አሳድጋለሁ።
\v 10 እንጨቱን ጨምር! እሳቱን አንድድ! ሥጋውን ቀቅል መረቁን አጣፍጠው! አጥንቶቹም በደንብ ይቃጠሉ።
\s5
\v 11 እንድትሞቅና እንድትግል በውጧ ያለው ርኵሰትዋ በውስጥዋ ይቀልጥ ዘንድ ዝገትዋም ይጠፋ ዘንድ ባዶዋን ድስት በፍም ላይ ጣዳት።
\v 12 በከንቱ ደከመች ሆኖም ዝገትዋ በእሳት ስንኳ አልለቀቀም።
\s5
\v 13 አሳፋሪው ተግባርሽ በርኵሰትሽ ውስጥ ነው። እኔ ባነጻሽም አልነጻሽም። መዓቴን በላይሽ እስክጨርስ ድረስ ከርኵሰትሽ አትነጺም።
\s5
\v 14 እኔ እግዚአብሔር ይሆናል ብዬ ተናግሬአለሁ ፥ እኔም አደርገዋለሁ! አልመለስም፥ ፥ አልጸጸትምም። እንደ መንገድሽና እንደ ሥራሽ ይፈርዱብሻል! ይላል ጌታ እግዚአብሔር።"
\s5
\v 15 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
\v 16 "የሰው ልጅ ሆይ፥ እነሆ፥ የዓይንህን አምሮት በመቅሠፍት እወስድብሃለሁ አንተም ማዘንም ሆነ ማልቀስ የለብህም እንባህንም አታፍስስ።
\v 17 በቀስታ ተክዝ። ለምዋቾችም የቀብር ሥርዓትም አታዘጋጅ። መጠምጠሚያህን በራስህ ላይ አድርግ፥ ጫማህንም በእግርህ አጥልቅ፥ ጢምህን አትሸፍን ወይም ሚስቶቻቸው በመሞታቸው ምክንያት እያዘኑ ያሉ ሰዎችን እንጀራ አትብላ።
\s5
\v 18 እኔም በማለዳ ለሕዝቡ ተናገርሁ፥ ምሽት ላይም ሚስቴ ሞተች። በነጋውም እንደ ታዘዝሁ አደረግሁ።
\s5
\v 19 ሕዝቡም፥ "ይህ የምታደርገው ነገር ምን እንደ ሆነ አትነግረንምን?" አሉኝ።
\v 20 እኔም እንዲህ አልኋቸው፥ "የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
\v 21 ለእስራኤል ቤት ተናገር እንዲህም በል፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የኃይላችሁ ትምክሕት፥ የዓይናችሁ አምሮት፥ ክፉ ምኞታችሁ መቅደሴን አርክሰዋል! ያስቀራችኋቸውም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።
\s5
\v 22 እኔም እንዳደረግሁ እናንተ ታደርጋላችሁ ጢማችሁን አትሸፍኑም የኃዘንተኛ ሰዎችንም እንጀራ አትበሉም!
\v 23 ይልቁኑ መጠምጠሚያችሁም በራሳችሁ ጫማችሁም በእግራችሁ ይሆናል፤ አታዝኑም ወይም አታለቅሱምም በኃጢአታችሁም ትሰለስላላችሁና እያንዳንዱ ሰው ስለወንድሙ ያቃስታል።
\v 24 ይህ በሚሆንባችሁ ጊዜ ሕዝቅኤልም ምልክት ይሆናችኋል እርሱ እንዳደረገ ሁሉ እናንተ ታደርጋላችሁ። ከዚያም እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
\s5
\v 25 አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ደስታቸው፥ ትምክህታቸው የሆነውን መቅደሳቸውንና የሚያዩትና የተመኙትን በያዝኩ ጊዜ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በወሰድሁባቸው ቀን፥
\v 26 በዚያ ቀን ያመለጠ ሰው ይህን ሊነግርህ ይመጣል።
\v 27 በዚያ ቀን አፍህ አምልጦ ለመጣው ይከፈታል፥ አንተም ትናገራለህ ከዚያ ወዲያም ዝም አትልም። ምልክትም ትሆናቸዋለህ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
\s5
\c 25
\p
\v 1 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
\v 2 "የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ አሞን ልጆች አቅንተህ ትንቢት ተናገርባቸው።
\s5
\v 3 ለአሞንም ሰዎች እንዲህ በል፥ 'የጌታን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡ መቅደሴ በረከሰ ጊዜ የእስራኤልም ምድር ባድማ በሆነች ጊዜ የይሁዳም ቤት በተማረኩ ጊዜ ስለ እነርሱ "እሰይ!" ብላችኋል።
\v 4 ስለዚህ፥ እነሆ፥ ርስት አድርጌ ለምሥራቅ ሰዎች ርስት አድርጌ አሳልፌ አሰጣችኋለሁ፥ እነርሱም በእናንተ ላይ ምሽግን ይሰራሉ ፥ ድንኳኖቻቸውንም በእናንተ ዘንድ ይተክላሉ። ፍሬያችሁን ይበላሉ ወተታችሁንም ይጠጣሉ!
\v 5 የአሞንን ከተማ ለግመሎች ማሰማርያ፥ የአሞንንም ልጆች ለመንጋ መመሰጊያ አደርጋለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
\s5
\v 6 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ በእጃችሁ አጨብጭባችኋልና፥ በእግራችሁም አሸብሽባችኋልና፥ በእስራኤልም ምድር ላይ በነፍሳችሁ ንቀት ሁሉ ደስ ብሏችኋልና
\v 7 ስለዚህ፥ እነሆ፥ በእጄን እመታችኋለሁ፥ ለአሕዛብም ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፥ ከአሕዛብም ለይቼ እቈርጥሃለሁ፥ ከአገሮችም አጠፋሃለሁ እፈጅህማለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃለህ።
\s5
\v 8 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 'ሞዓብና ሴይር እነሆ፥ "የይሁዳ ቤት ያው እንደ ሌሎቹ አሕዛብ ሁሉ ነው!" ብለዋልና
\v 9 ስለዚህ፥ እነሆ፥ የሞዓብን ጫንቃ ከከተሞቹ፥ በዳርቻው ካሉት የምድሩ ትምክሕት ከሆኑት ከተሞቹ፥ ከቤትየሺሞት፥ ከበኣልሜዎን፥
\v 10 ከቂርያታይም፥ ከአሞን ልጆች ጋር ለምሥራቅ ልጆች እከፍታለሁ። የአሞን ህዝብ በአሕዛብ መካከል ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታሰቡ ርስት አድርጌ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።
\v 11 በሞዓብም ላይ ፍርድን አደርጋለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
\s5
\v 12 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 'ኤዶምያስ በይሁዳ ቤት ላይ በቀል አድርጎአል፥ ይህን በማድረጉም ስህተት ፈጽሟል።
\v 13 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እጄን በኤዶምያስ ላይ እዘረጋለሁ ከእርስዋም ዘንድ ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ። ከቴማንም ጀምሮ እስከ ድዳንም ድረስ ባድማ አደርጋታለሁ፥ በሰይፍም ይወድቃሉ።
\s5
\v 14 በሕዝቤ በእስራኤል እጅ ኤዶምያስን እበቀላለሁ እንደ ቍጣዬና እንደ መዓቴም መጠን በኤዶምያስ ያደርጋሉ በቀሌንም ያውቃሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር!'
\s5
\v 15 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'ፍልስጥኤማውያን በንቀት በቀልን አድርገዋልና፥ ይሁዳንም ከውስጣቸው ለማጥፋት ደጋግመው ሞክረዋልና
\v 16 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እጄን በፍልስጥኤማውያን ላይ እዘረጋለሁ፥ ከሊታውያንንም እቈርጣለሁ፥ የባሕሩንም ዳር ቅሬታ አጠፋለሁ።
\v 17 በመዓት መቅሠፍትም ታላቅ በቀል አደርግባቸዋለሁ በቀሌንም በላያቸው ባደረግሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
\s5
\c 26
\p
\v 1 እንዲህም ሆነ በአሥራ አንደኛው ዓመት ከወሩ በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፡
\v 2 "የሰው ልጅ ሆይ፥ ጢሮስ በኢየሩሳሌም ላይ። 'እሰይ፥ የአሕዛብ በር የነበረች ተሰብራለች ወደ እኔም ተመልሳለች እርስዋ ፈርሳለችና እኔ እሞላለሁ!' ብላለች።
\s5
\v 3 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ "ጢሮስ ሆይ፥ እነሆ፥ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ባሕርም ሞገድዋን እንደምታወጣ እንዲሁ ብዙ ህዝቦችን በአንቺ ላይ አስነሳልሁ።
\v 4 የጢሮስንም ቅጥሮች ያጠፋሉ ግንቦችዋንም ያፈርሳሉ ትቢያዋንም ከእርስዋ እጠርጋለሁ፥ የተራቈተ ድንጋይም አደርጋታለሁ።
\s5
\v 5 በባሕር ውስጥ የመረብ ማስጫ ትሆናለች እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር ለአሕዛብም ብዝበዛ ትሆናለች።
\v 6 በሜዳ ያሉትም ሴቶች ልጆችዋ በሰይፍ ይገደላሉ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
\s5
\v 7 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና። እነሆ፥ ከሰሜን የነገሥታት ንጉሥ የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን ከፈረሶችና ከሰረገሎች ከፈረሰኞችም ከብዙ ሕዝብ ጋር በጢሮስ ላይ አመጣለሁ።
\v 8 በሜዳ ያሉትን ሴቶች ልጆችሽን በሰይፍ ይገድላቸዋል፥ ምሽግም ይሠራብሻል አፈርንም ይደለድልብሻል ጋሻም ያነሣብሻል።
\s5
\v 9 ማፍረሻውን በቅጥርሽ ላይ ያደርጋል፥ መሳሪያውም ግንቦችሽንም ያፈርሳል!
\v 10 ከፈረሶቹም ብዛት የተነሣ ትቢያቸው ይከድንሻል! ሰዎችም በፈርሰ ቅጥር በኩል ወደ ከተማ እንደሚገቡ እርሱ በበሮችሽ ሲገባ፥ ከፈረሰኞችና ከመንኰራኵሮች ከሰረገሎችም ድምፅ የተነሣ ቅጥርሽ ይናወጣል።
\v 11 በፈረሶቹ ኮቴ ጎዳናዎችሽን ሁሉ ይረመርማል፤ ሕዝብሽንም በሰይፍ ይገድላል፥ የብርታትሽም ሐውልት ወደ ምድር ይወድቃል።
\s5
\v 12 በዚህ መንገድ ብልጥግናሽንም ሸቀጥሽንም ይዘርፋሉ! ቅጥርሽንም ያፈርሳሉ፥ ተድላ የምታደርጊባቸውን ቤቶችሽን ያጠፋሉ ድንጋይሽንና እንጨትሽን መሬትሽንም በባሕር ውስጥ ይጥላሉ።
\v 13 የዝማሬ ጩኸትሽን ዝም አሰኛለሁ የክራሮች ድምፅ ከዚያ ወዲያ አይሰማም!
\v 14 የተራቈተ ድንጋይ አደርግሻለሁ የመረብም ማስጫ ትሆኛለሽ። ከእንግዲህ እንደገና አትገነቢም እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር!
\s5
\v 15 ጌታ እግዚአብሔር ጢሮስን እንዲህ ይላታል፥ 'በውስጥሽ እልቂት በሆነ ጊዜ በውድቀትሽ ጩኸትና በቆሰሉ ሰዎች የሥቃይ ድምጽ የተወጉት ባንቋረሩ ጊዜ፥ ፥ ከውድቀትሽ ድምፅ የተነሣ ደሴቶች አይነዋወጡምን?
\v 16 የባሕርም አለቆች ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ መጐናጸፊያቸውን ያወጣሉ ወርቀ ዘቦ ልብሳቸውንም ያወልቃሉ መንቀጥቀጥን ለብሰው በመሬት ላይ ይቀመጣሉ፥ ሁልጊዜም ይንቀጠቀጣሉ ስለአንቺም ይፈራሉ።
\s5
\v 17 በአንቺም ላይ ሙሾ ያሞሻሉ፥ እንዲህም ይሉሻል። የመርከበኞች መኖሪያ የነበርሽ እንዴት ወደምሽ! ዝናሽ የወጣ ጠንካራ ከተማ አሁን ግን ከባህር ጠፋሽ! በአንድ ወቅት በእርሷ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ አስፍሪነታቸው በዙሪያቸው ባሉ ሁሉ ላይ ነበር።
\v 18 አሁን በውድቀትሽ ቀን የባህር ዳርቻዎችይንቀጠቀጣሉ፥ በባሕርም ውስጥ ያለ ደሴቶች ከመጥፋትሽ የተነሣ ይደነግጣሉ።
\s5
\v 19 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፡ ሰው እንደሌለባቸው ከተሞች ባድማ ከተማ ባደረግሁሽ ጊዜ፥ ቀላያትንም ባንቺ ላይ ባስነሳሁብሽ ጊዜ ብዙ ውኆችም በከደኑሽ ጊዜ፥
\v 20 ያኔ ወደ ጉድጓድ እንደወረዱ ሰዎች ወደ ጥንት ሰዎች አወርድሻለሁ፤ እንደ ጥንት ዘመን ፍርስራሾች በምድር ጥልቅ ውስጥ እንድትኖሪ አደርግሻልችሁ። ከዚህ የተነሳ ሰዎች ወደሚኖሩበት
\v 21 ጥፋትን አመጣብሻለሁ ለዘላለምም ትጠፊያለሽ፤ ይፈልጉሻል ነገር ግን ለዘላለም አያገኙሽም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\c 27
\p
\v 1 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
\v 2 "አንተ የሰው ልጅ ሆይ እንግዲህ ፥ ስለ ጢሮስ ሙሾ ጀምር ጢሮስንም እንዲ በላት
\v 3 'አንቺ በባሕር መግቢያ የምትኖሪ በብዙም ደሴቶች ላይ ከሚኖሩ ህዝቦች ጋር ንግድን የምታደርጊ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጢሮስ ሆይ፥ አንቺ። 'በውበት ፍጹም ነኝ ብለሻል!
\s5
\v 4 ዳርቻሽ በባሕር ውስጥ ነው የሰሩሽ ፍጹም ውብ አድርገውታል።
\v 5 ሳንቃዎችሽን ሁሉ ከሳኔር ጥድ ሠርተዋል፥ ደቀልንም ሊሰሩልሽ ከሊባኖስ ዝግባ ወስደዋል።
\s5
\v 6 ከባሳን ዛፍ መቅዘፊያሽን ሠርተዋል፥ በዝሆን ጥርስ ከታሸበ ከኪቲም ደሴቶች ዛፍ የመርከብ ወለሎችሽን ሠርተዋል።
\v 7 የመርከብሽ ሸራ ልክ እንደ ሰንደቅ ዓላማሽ የግብጽ ባለብዙ ቀለማት በፍታ ጨርቆች ነበሩ።
\s5
\v 8 የሲዶናና የአራድ ሰዎች ቀዛፎችሽ ነበሩ፤ የጢሮስ ጥበበኞችሽ በአንቺ ዘንድ ነበሩ የመርከቦችሽም መሪዎች ነበሩ።
\v 9 ልምድ ያላቸው ጥበበኞች መጋጠሚያዎችሽን ሞልተዋል። የባሕር መርከቦች ሁሉና መርከበኞቻቸው የንግድ እቃዎችሽን ለንግድ ያጓጉዙልሻል።
\s5
\v 10 ፋርስና ሉድ ፉጥም በሠራዊትሽ ውስጥ ነበሩ፥ ጋሻና ራስ ቍርም በአንቺ ውስጥ ያንጠለጥሉ ነበር፥ እነርሱም ውበትሽን አሳዩ።
\v 11 በሠራዊትሽ ውስጥ የነበሩት የአራድ እና የኤሌክ ሰዎች በቅጥሮችሽ በዙሪያ ነበሩ፥ ገማዳውያንም በግንቦችሽ ውስጥ ነበሩ! ጋሻቸውንም ዙሪያውን በቅጥርሽ ላይ አንጠለጠሉ! ውበትሽንም ፍጹም አደረጉት!
\s5
\v 12 በብዙ ዓይነት ማለትም በብር፥ በብረት ፥ በቈርቈሮና በእርሳስ ካለሽ ብልጥግና ብዛት የተነሣ ተርሴስ የንግድ ደንብኛሽ ነበረች። ሸቀጥሽን ይገዙና ይሸጡ ነበር።
\v 13 ያዋንና ቶቤል ሞሳሕም ባሮችንና ከናስ የተሰሩ እቃዎችን ይነግዱ ነበር። ንግድሽን የሚመሩት እነርሱ ነበሩ።
\s5
\v 14 ከቤተ ቴርጋማም መጋዣዎችን፥ የጦር ፈረሶችንና በበቅሎዎችን ወደ ንግድሽ አመጡ።
\v 15 የድዳን ሰዎች በብዙ ዳርቻዎችሽ የንግድ አጋሮችሽ ነበሩ። ንግድ በእጅሽ ነበረ፤ በሸቀጥሽ ምላሽ የዝሆን ጥርስና ዞጲ ይልኩልሽ ነበር።
\s5
\v 16 ሶርያ የብዙ ምርቶችሽ ተጠቃሚ ነበረች። በልዋጩም የከበረ ድንጋይ፥ የወይን ጠጅ፥ ባለ ብዙ ቀለም ልብሶች፥ ያማሩ ጨርቆች፥ በዛጎል እና ቀይ ዕንቍም ያቀርቡ ነበር።
\v 17 ይሁዳና የእስራኤል ምድር የንግድ አጋሮችሽ ነበሩ። የሚኒትን ስንዴ ጣፋጭም እንጐቻ፥ ማር ዘይትም በለሳንም ያቀርቡ ነበር።
\v 18 ደማስቆ የምርትሽ ሁሉ፥ ተዝቆ የማያልቅ ሀብትሽ እንዲሁም የኬልቦን የወይን ጠጅና የዘሀርን የበግ ጠጕር ይነግዱ ነበር።
\s5
\v 19 ዌንዳንና ያዋን ከአንቺ ጋር ይነግዱ ነበር። ቀልጦ የተሠራ ብረት፥ ብርጕድና ቀረፋም ያቀርቡ ነበረ። ይህም ላንቺ ንግድ ሆነልሽ
\v 20 ድዳን የግላስ ንግድ ከአንቺ ጋር ነበራት።
\v 21 ዓረብና ሌሎች የቄዳር አለቆች ሁሉ የንግድ አጋሮችሽ ነበሩ፤ ጠቦቶች፥ አውራ በጎችና ፍየሎችን ለንግድ ያቀርቡልሽ ነበር።
\s5
\v 22 የሳባና የራዕማ ነጋዴዎች ምርጥ የሆነ የቅመም ሽቱ ሁሉና ብዙ ዓይነት የከበሩ ድንጋዮች ሊሸጡልሽ ይመጡ ነበር። ወርቅም ይነግዱ ነበር።
\v 23 ካራንና ካኔ ዔድንም ከሳባ፥ ከአሦርና ከኪልማድ በመሆን የንግድ አጋሮችሽ ነበሩ።
\s5
\v 24 እነዚህ ባማረ ልብስ በሰማያዊ ካባ በወርቀ ዘቦም፥ በዝግባ በተሠራች በገመድም በታሰረች በግምጃም በተሞላች ሳጥን ይነግዱ የነበሩ ናቸው።
\v 25 የተርሴስ መርከቦች የሸቀጥሽ ማጓጓዣዎች ነበሩ። አንቺም በባህር መካከል ተሞልተሽ በጭነትም ከብደሽ ነበር።
\s5
\v 26 ቀዛፊዎችሽ ወደ ስፊ ባህሮች አመጡሽ፤ የምሥራቅ ነፋስም በባህሮቹ መካከል ሰበረሽ።
\v 27 በውድቀትሽ ቀን ብልጥግናሽ፥ ሸቀጥሽና የንግድ ዕቃዎችሽ፤ የመርከብ ነጂዎችሽ፥ መርከበኞችሽም መርከብ ሠሪዎችሽ፤ ነጋዴዎችሽ ሁሉ በአንቺም ውስጥ የነበሩ ሰዎች ሁሉ በውስጥሽ ካሉት ሠራተኞች ጋር ወደ ባሕር ጥልቅ ይወድቃሉ።
\s5
\v 28 ከመርከብ መሪዎች ጩኸት ድምፅ የተነሣ በባህር አጠገብ ያሉ ከተሞች ይንቀጠቀጣሉ።
\v 29 ቀዛፊዎችም ሁሉ መርከበኞችም መርከብ መሪዎችም ሁሉ ከመርከቦቻቸው ወርደው በመሬት ላይ ይቆማሉ።
\v 30 ከዚያም ድምፃቸውን እንድትሰሚ ያደርጉሻል ምርር ብለውም ይጮኻሉ፥ ፤ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ይነሰንሳሉ፥ በአመድም ውስጥ ይንከባለላሉ
\s5
\v 31 ስለ አንቺም የራሳቸውን ጠጕር ይላጫሉ ማቅም ይታጠቃሉ በምሬትም ስለአንቺ ያነባሉ ይጮኸሉ።
\v 32 በትካዜያቸውም ልቅሶ ያነሡልሻል፥ ስለ አንቺም ሙሾ ያሞሻሉ እንዲህም ይላሉ። በባሕር መካከል ጠፍቶ እንደ ቀረ እንደ ጢሮስ ያለ ማን ነው?
\v 33 ሸቀጥሽ ከባሕር በወጣ ጊዜ ብዙ አሕዛብን ያጠግብ ነበር በብልጥግናሽና በንግድሽ ብዛት የምድርን ነገሥታት ባለ ጠጎች አድርገሻል።
\s5
\v 34 ነገር ግን በጥልቅ ውኃ ውስጥ በባህር በተሸፈንሽ ጊዜ ንግድሽና ሠራተኞችሽ ሁሉ ሰጠሙ!
\v 35 በባህር ዳርቻ የሚኖሩ ሁሉ ተደንቀውብሻል፥ ነገሥታቶቻቸውም በፍርሀት ተንቀጥቅጠዋል። ፊታቸውም ደንግጧል።
\v 36 የአሕዛብ ነጋዴዎች አፍዋጩብሽ፤ ለድንጋጤ ሆነሻል፥ ከእንግዲህ በኋላም አትኖሪም።
\s5
\c 28
\p
\v 1 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
\v 2 የሰው ልጅ ሆይ፥ የጢሮስን ገዥ እንዲህ በለው፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልብህ ኰርቶአል፥ አንተም "እኔ አምላክ ነኝ! በባሕር መካከል በአማልክት ወንበር ላይ እቀመጣለሁ!" ብለሃል። ነገር ግን አንተ ሰው እንጂ እግዚአብሔር ባትሆንም ልብህን እንደ አምላክ ልብ አደረግህ።
\v 3 እነሆ፥ ከዳንኤል ይልቅ ጥበበኛ እንደሆንክ ምንም ሚስጢር ከአንተ እንደማይሰወር አሰብክ።
\s5
\v 4 በጥበብና በማስተዋል ራስህን አበልጽገሀል፥ ወርቅና ብርም በግምጃ ቤትህ ውስጥ ሰብስበሃል!
\v 5 በታላቅ ጥበብና በንግድህ ብልጥግናህን አብዝተሃል ከብልጥግናህም የተነሳ ልብህ ኰርቶአል!
\s5
\v 6 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልብህን እንደ አምላክ ልብ አድርገሃልና
\v 7 ስለዚህ፥ እነሆ፥ እንግዳ ሰዎችን፥ የአሕዛብን ጨካኝ ሰዎችን አመጣብሃለሁ! ሰይፋቸውንም በጥበብህ ውበት ላይ ይመዝዛሉ፥ ክብርህንም ያዋርዳሉ!
\s5
\v 8 ወደ ጕድጓድ ያወርዱሃል፥ በባህር ልብ ውስጥ የሞቱትን ሰዎች ሞት ትሞታለህ።
\v 9 በውኑ በገዳይህ ፊት፥ "እኔ አምላክ ነኝ" ትላለህን? አንተ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም፥ በሚቆራርጡህ እጅ ትወድቃለህ።
\v 10 በእንግዶች ሰዎች እጅ ያልተገረዙትን ሰዎች ሞት ትሞታለህ እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር!"
\s5
\v 11 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
\v 12 የሰው ልጅ ሆይ፥ በጢሮስ ንጉሥ ላይ ሙሾ አሞሽተህ እንዲህ በለው፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡ጥበብን የተሞላህ የፍጽምና መደምደሚያ በውበትህም ፍጹም ነበርክ!
\v 13 በእግዚአብሔር ገነት በዔድን ነበርህ! በከበረ ዕንቍስ ሁሉ፥ ሰርድዮን፥ ቶጳዝዮን፥ አልማዝ፥ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያስጲድ፥ ሰንፔር፥ በሉር፥ የሚያብረቀርቅ ዕንቍ፥ ወርቅ፥ ተሽፍነህ ነበረ። እነዚህ የከበሩ ድንጋዮች በወርቅ ዕቃ በፊትህ ተቀምጠው ነበር። አነዚህም በተፈጠርህበት ቀን እንድትለብሳቸው ተዘጋጅተው ነበር!
\s5
\v 14 የሰውን ዘር እንዲጋርድ እንደቀባሁት ኪሩብ በተቀደሰው በእግዚአብሔር ተራራ ላይ አኖርሁህ! ትመላለስባቸው በነበሩ የእሳት ድንጋዮች መካከል ነበርክ።
\v 15 ከተፈጠርህበት ቀን ጀምረህ በደል እስኪገኝብህ ድረስ በመንገድህ ፍጹም ነበርህ።
\s5
\v 16 በንግድህ ብዛት በአምጽ ተሞላህ ስለዚህም ኃጢአትን ሠራህ! ስለዚህ እንደ ርኩስ ነገር ከእግዚአብሔር ተራራ ጣልሁህ የምትጋርድ ኪሩብ ሆይ፥ ከእሳት ድንጋዮች መካከል አጠፋሁህ።
\v 17 በውበትህ ምክንያት ልብህ ኰርቶአል፤ ከክብርህ የተነሣ ጥበብህን አረከስህ! ወደ ምድርም ጣልሁህ! ያዩህም ዘንድ በነገሥታት ፊት አስቀመጥኩህ።
\s5
\v 18 በበደልህ ብዛት ቅን ባልሆነው ንግድህም ቅዱስ ስፍራህን አረከስህ! ስለዚህ እሳትን ከውስጥህ አውጥቻለሁ እርስዋም ትበላሀለች። በሚያዩህም ሁሉ ፊት በምድር ላይ አመድ አደርግሀለሁ።
\v 19 በአሕዛብም ውስጥ የሚያውቁህ ሁሉ ይደነቁብሃል፤ ይደነግጣሉ ፥ አንተም እስከ ዘላለምም አትገኝም።
\s5
\v 20 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
\v 21 "የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ ሲዶና አቅንተህ ትንቢት ተናገርባት! እንዲህም በል፥
\v 22 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሲዶና ሆይ፥ እነሆ፥ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ፍርድን በውስጥሽ በማደርግበት ጊዜ ህዝብሽ እኔ እግዚአብሔር እንድሆንኩ እንዲያውቁ በመካከልሽ ክብሬን እገልጣለሁ። ቅዱስ መሆኔም ይገለጣል።
\s5
\v 23 ቸነፈርንም በአንቺ ላይ፥ ደምንም በጎዳናሽ ላይ እሰድዳለሁ፥ በሰይፍ የታረዱ በመካከልሽ ይወድቃሉ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ!
\v 24 እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ እንዲያውቁ ከእንግዲህም ወዲያ ለእስራኤል ቤት የሚወጋ እሾህ፥ በዙሪያቸውም ካሉ ከናቋቸው ሁሉ የሚያቈስል ኵርንችት አይሆንም
\s5
\v 25 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤልን ቤት ከተበተኑባቸው አሕዛብ ዘንድ በሰበሰብሁ ጊዜ፥ በአሕዛብም ፊት በተቀደስሁባቸው ጊዜ፥ ለባሪያዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት ምድራቸው ይቀመጣሉ።
\v 26 በውስጧም ተዘልለው ይቀመጡባታል ቤቶችንም ይሠራሉ ወይኑንም ይተክላሉ በዙሪያቸውም ባሉ በሚንቋቸው ሁሉ ላይ ፍርድን ባደረግሁ ጊዜ ተዘልለው ይቀመጣሉ እኔም እግዚአብሔር አምላካቸው እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
\s5
\c 29
\p
\v 1 በአሥረኛው ዓመት በአሥረኛው ወር ከወሩም በአሥራ ሁለተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
\v 2 የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን በግብጽ ንጉሥ በፈርዖን ላይ አድርግ፥ በእርሱና በግብጽ ሁሉ ላይም ትንቢት ተናገር፥
\v 3 እንዲህም በል። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በወንዞች መካከል የምትተኛና። ወንዙ የእኔ ነው ለራሴም ሠርቼዋለሁ የምትል ታላቅ የባህር ውስጥ ፍጥረት፥ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ሆይ፥ እነሆ፥ በአንተ ላይ ነኝ።
\s5
\v 4 በመንጋጋህ መቃጥን አገባብሃለሁ፥ የወንዞችህንም ዓሦች ወደ ቅርፊትህ አጣብቃለሁ በቅርፊትህ ላይ ከተጣበቁ ዓሦች ሁሉ ጋር ከወንዞችህም መካከል አወጣሃለሁ።
\v 5 አንተንና የወንዞችህን ዓሦች ሁሉ ወደ ምድረ በዳ እጥላለሁ፥ በምድርም ፊት ላይ ትወድቃለህ እንጂ አትከማችም አትሰበሰብም። መብልም አድርጌ ለምድር አራዊትና ለሰማይ ወፎች እሰጥሀለሁ።
\s5
\v 6 ለእስራኤል ቤት የሸንበቆ በትር ሆነዋልና በግብጽም የሚኖሩ ሁሉ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
\v 7 በእጅ በያዙህ ጊዜ ተሰበርህና ተሰነጣጥቅህ ትከሻቸውን ትወጋለህ፤ በተደገፉብህም ጊዜ እግራቸውን ትሰባብራለህ ወገባቸውንም እንዲንቀጠቀጥ ታደርጋለህ።
\s5
\v 8 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሰይፍ አመጣብሃለሁ፥ ሰውንና እንስሳንም ከአንተ ዘንድ አጠፋለሁ።
\v 9 የባህር ጭራቁ "ወንዙ የእኔ ነው የሠራሁትም እኔ ነኝ" ብሏልና የግብጽ ምድር ባድማና ውድማ ትሆናለች፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ አንተ።
\v 10 ስለዚህ፥ እነሆ፥ በአንተና በወንዞችህ ላይ ነኝ፥ የግብጽንም ምድር ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሴዌኔና እስከ ኢትዮጵያ ዳርቻ ድረስ ውድማና ባድማ አደርጋታለሁ።
\s5
\v 11 የሰው እግር አያልፍባትም የእንስሳም ኮቴ አያልፍባትም፥ እስከ አርባ ዓመትም ድረስ ማንም አይኖርባትም።
\v 12 ባድማም በሆኑ ምድሮች መካከል የግብጽን ምድር ባድማ አደርጋታለሁ፥ በፈረሱትም ከተሞች መካከል ከተሞችዋ አርባ ዓመት ፈርሰው ይቀመጣሉ ግብጻውያንንም ወደ አሕዛብ እበትናቸዋለሁ በአገሮችም እዘራቸዋለሁ።
\s5
\v 13 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከአርባ ዓመት በኋላ ግብጻውያንን ከተበተኑባቸው አሕዛብ ዘንድ እሰበስባለሁ
\v 14 የግብጽንም ምርኮ እመልሳለሁ፥ ወደ ተወለዱባትም ምድር ወደ ጳትሮስ እመልሳቸዋለሁ በዚያም የተዋረደች መንግሥት ይሆናሉ።
\s5
\v 15 ከሌሎች መንግሥታት ሁሉ ይልቅ የተዋረደች ትሆናለች ከእንግዲህ ወዲያ ከአሕዛብ መካከል ከፍ አትልም።ከእንግዲህም በአሕዛብም ላይ እንዳይገዙ አሳንሳቸዋለሁ።
\v 16 ግብጻውያን ከእንግዲህ ለእስራኤል ቤት የትምክህት ምክንያት አይሆኑም። ይልቁኑ እስራኤል ለእርዳታ ፊቷን ወደ ግብጽ ባዞረች ጊዜ የፈጸመችውን በደል የሚያሳስቡ ይሆናሉ።እኔም ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
\s5
\v 17 እንዲህም ሆነ በሀያ ሰባተኛው ዓመት በመጀመሪያው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
\v 18 የሰው ልጅ ሆይ፥ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በጢሮስ ላይ ጽኑ ሥራ ለማሰራት ሠራዊቱን ሰበሰበ። ራስ ሁሉ ተላጭቶ ጫንቃም ሁሉ ተልጦ ነበር፥ ነገር ግን በላይዋ ስላገለገለው አገልግሎት እርሱና ሠራዊቱ ምንም አይነት ደመወዝ ከጢሮስ አልተቀበሉም።
\s5
\v 19 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የግብጽን ምድር ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እሰጠዋለሁ፥ ብዛትዋንም ይወስዳል ምርኮዋንም ይማርካል ብዝበዛዋንም ይበዘብዛል ይህም ለሠራዊቱ ደመወዝ ይሆናል።
\v 20 ለእኔ ለሠሩት ሥራ ደመወዝ አድርጌ የግብጽን ምድር ሰጥቼዋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\s5
\v 21 በዚያ ቀን ለእስራኤል ቤት ቀንድን አበቅላለሁ፥ በመካከላቸውም ለአንተ የተከፈተ አፍን እሰጣለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
\s5
\c 30
\p
\v 1 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
\v 2 የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር እንዲህም በል። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዋይ! በሉ፥ ለቀኑ ወዮ! ቀኑ ቅርብ ነው፥
\v 3 የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ ነው፥ የደመና ቀን፥ ለአሕዛብም ክፉ ወቅት ይሆናል።
\s5
\v 4 ሰይፍ በግብጽ ላይ ይመጣል፥ የተገደሉት ሰዎች በግብጽ ውስጥ ሲወድቁ ሀብቷን ሲወስዱ መሠረትዋም ሲፈርስ በኢትዮጵያ ውስጥ ሁከት ይሆናል!
\v 5 ኢትዮጵያ፥ ፉጥና ሉድም እንግዶችም የቃል ኪዳንም ህዝቦች ከእነርሱ ጋር በሰይፍ ይወድቃሉ።
\s5
\v 6 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ግብጽን የሚደግፉ ይወድቃሉ፥ የኃይልዋም ትምክህት ይወርዳል። ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሴዌኔ ድረስ ወታደሮቻቸው በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር!
\v 7 ባድማም በሆኑ አገሮች መካከል ይሸበራሉ፥ ከተሞቻቸውም እንደ ፈረሱት ከተሞች ይሆናሉ።
\s5
\v 8 እሳትንም በግብጽ ባነደድሁ ጊዜ ረዳቶችዋም ሁሉ በጠፉጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ!
\v 9 በዚያ ቀን መልእክተኞች ተዘልለው የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያንን ለማስፈራት ከፊቴ በመርከብ ይወጣሉ በግብጽም ጥፋት ቀን ሁከት ይሆንባቸዋል። እነሆ፥ ይመጣልና!
\s5
\v 10 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ የግብጽን ህዝብ ፍጻሜ አመጣለሁ።
\v 11 የአህዛብ ድንጋጤ የሆኑት እርሱና ሠራዊቱ ምድሪቱን ለማጥፋት ይመጣሉ፤ ሰይፋቸውንም በግብጽ ላይ ይመዝዛሉ ምድሪቱንም በሞቱ ሰዎች ይሞላሉ!
\s5
\v 12 ወንዞችን ደረቅ መሬት አደርጋለሁ ምድሪቱንም ለክፉ ሰዎች እሸጣለሁ። ምድሪቱንና ሙላዋንም በእንግዶች እጅ ባድማ አደርጋለሁ! እኔ እግዚአብሔር ተናግሬያለሁ!
\s5
\v 13 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጣዖቶችን አጠፋለሁ እርባና ቢስ የሆኑትን የሜምፎስ ጣዖታት እሽራለሁ። ከእንግዲህ ወዲያ በግብጽ ምድር አለቃ አይገኝም ፥ በግብጽም ምድር ላይ ሽብርን አደርጋለሁ!
\v 14 ጳትሮስንም አፈርሳለሁ፥ በጣኔዎስም እሳትን አነድዳለሁ፥ በኖእ ላይም ፍርድን አደርጋለሁ።
\s5
\v 15 በግብጽም ምሽግ በሲን ላይ መዓቴን አፈስሳለሁ፥ የኖእንም ህዝብ አጠፋለሁ።
\v 16 ከዚያም በግብጽ እሳትን አነድዳለሁ። ሲንም ትጨነቃለች ኖእም ትሰበራለች፥ ሜምፎስም በየቀኑ ጠላቶች ይነሱባታል!
\s5
\v 17 የሄልዮቱና የቡባስቱም ወጣቶች በሰይፍ ይወድቃሉ ከተሞቻቸውም ይማረካሉ።
\v 18 በዚያ የግብጽን ቀንበር በሰበርሁ ጊዜ በጣፍናስ ቀኑ ይጨልማል የኃይልዋም ትዕቢት ይጠፋል። ደመናም ይጋርዳታል፥ ሴቶች ልጆችዋም ይማረካሉ።
\v 19 እንዲሁ በግብጽ ላይ ፍርድን አደርጋለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
\s5
\v 20 እንዲህም ሆነ በአሥራ አንደኛው ዓመት በመጀመሪያው ወር ከወሩም በሰባተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
\v 21 የሰው ልጅ ሆይ፥ የግብጽን ንጉሥ የፈርዖንን ክንድ ሰብሬያለሁ።። እነሆም፥ እንዲድን በጨርቅ አልታሰረም በመቃም አልታሰረለትም ስለዚህም ሰይፍን ለመያዝ የሚያስችል ጥንካሬ የለውም።
\s5
\v 22 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እኔ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖን ላይ ተነስቻለሁ! ጠንካራውንም የተሰበረውንም ክንዱን እሰብራለሁ፥ ሰይፉንም ከእጁ አስጥላለሁ።
\v 23 ግብጻውያንንም ወደ አሕዛብ እበትናለሁ ወደ አገሮችም እዘራቸዋለሁ።
\v 24 የፈርዖንን ክንድ ለመስበር የባቢሎንን ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ ሰይፌንም በእጁ እሰጣለሁ። በባቢሎን ንጉሥ ፊት ለሞት እንድሚያጣጥር ሰው ያጓራል።
\s5
\v 25 የባቢሎንንም ንጉሥ ክንድ አጸናለሁ የፈርዖን ክንድ ግን ይወድቃል። ሰይፌንም በባቢሎን ንጉሥ እጅ በሰጠሁ ጊዜ እርሱም በሰጠሁት ሰይፍ የግብጽን ምድር በሚመታ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
\v 26 ግብጻውያንንም ወደ አሕዛብ እበትናለሁ ወደ አገሮችም እዘራቸዋለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
\s5
\c 31
\p
\v 1 እንዲህም ሆነ በአሥራ አንደኛው ዓመት በሦስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
\v 2 የሰው ልጅ ሆይ፥ የግብጽን ንጉሥ ፈርዖንንና በዙሪያው ያሉትን አገልጋዮቹን እንዲህ በላቸው። 'በታላቅነትህ ማንን ትመስላለህ?
\s5
\v 3 እነሆ፥ አሦር ጫፉ እንደ ተዋበ፥ ችፍግነቱ ጥላ እንደ ሰጠ፥ ቁመቱም እንደ ረዘመ፥ ራሱም በደመናዎች መካከል እንደ ነበረ እንደ ሊባኖስ ዝግባ ነበረ።
\v 4 ውኆችም አበቀሉት፥ ቀላይም ግዙፍ አደረገው። ወንዞችም በተተከለበት ዙሪያ ይጐርፉ ነበር፥ መስኖዎቻቸውን በሜዳ ወዳሉ ዛፎች ይሰዳሉ።
\s5
\v 5 ቁመቱ ከምድረ በዳ ዛፍ ሁሉ ከፍ ያለ ነበር አለ፤ ቅርንጫፎቹም ከብዙ ውኆች የተነሣ ረዘሙ።
\v 6 የሰማይ ወፎች ሁሉ ጎጆቻቸውን በቅርንጫፎቹ ላይ አደረጉ፥ የምድርም አራዊት ሁሉ ከጥላው በታች ተዋለዱ። ታላላቅ ህዝቦች ከጥላውም በታች ኖሩ።
\v 7 ሥሩም በብዙ ውኃ አጠገብ ነበረና በታላቅነቱና በቅርንጫፎቹ ርዝመት የተዋበ ነበረ።
\s5
\v 8 በእግዚአብሔር ገነት የነበሩ ዝግባዎች አልተካከሉትም! ጥዶችም ቅርንጫፎቹን አይመስሉትም አስታ የሚባለውም ዛፍ ቅርንጫፎቹን አይተካከሉም! በእግዚአብሔርም ገነት ካሉ ዛፎች በውበቱ ሊተካከለው አልቻለም!
\v 9 በቅርንጫፎቹ ብዛት ውብ አደረግሁት፤ በእግዚአብሔርም ገነት በዔድን የነበሩ ዛፎች ሁሉ ቀኑበት።
\s5
\v 10 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ቁመቱ ከፍ ከፍ ብሎአልና፥ ጫፎቹንም ከቅርንጫፎች በላይ አድርጎአልና፥
\v 11 ልቡም በቁመቱ ልክ ኰርቶአልና ከአሕዛብ ሁሉ በላይ ኃይለኛ ገዢ እጅ አሳልፌ እሰጠዋለሁ! ይህም ገዢ ይቃወመዋል እንደ ክፋቱም መጠን ያሳድደዋለሁ።
\s5
\v 12 የአህዛብ ድንጋጤ የሆኑ የሌላ አገር ሰዎች፥ አስወግዱት ፈጽሞም ጣሉት። ቅርንጫፎቹ በተራሮችና ላይና በሸለቆች ውስጥ ወደቁ፥ ቅርንጫፎቹም በምድር ፈሳሾች ሁሉ ላይ ተሰባበሩ። የምድርም አሕዛብ ሁሉ ከጥላው ወጥተው ጥለውት ሄዱ።
\s5
\v 13 የሰማይ ወፎች ሁሉ በግንዱ ላይ ይቀመጣሉ የምድርም አራዊት ሁሉ በቅርንጫፎቹ ላይ ይቀመጣሉ።
\v 14 ይህም የሆነው ወደ ጕድጓድ በሚወርዱ በሰው ልጆች መካከል ሁላቸው ለታችኛው ምድር ለሞት አልፈው ተሰጥተዋልና ውሀ ሲጠጡ ከነበሩት ዛፎች ውስጥ አንዳቸውም ረጅም ሆነው እንዳያድጉ፥ ጫፎቻቸውም ከቅጠሎች በላይ እንዳይሆኑ፥ በውኃ አጠገብ ያሉ ዛፎች ሁሉ ከእንግዲህ በቁመታቸው እንዳይረዝሙ ነው።
\s5
\v 15 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ሲኦል በወረደበት ቀን ልቅሶን ወደ ምድር አመጣሁ። በቀላያትም ሸፈንኩት፥ የውቅያኖስ ፈሳሾቹንም ከለከልሁ። ታላላቆችም ውኆች ከለከልኩ፥ ሊባኖስንም ስለ እርሱ አሳዘንሁት! የዱርም ዛፎች ሁሉ ስለ እርሱ አለቀሱ።
\s5
\v 16 ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ጋር ወደ ሲኦል በጣልሁት ጊዜ ክአውዳደቁ ድምፅ የተነሣ በአሕዛብ ላይ መንቀጥቀጥን አመጣሁ! በምድር ዝቅተኛ ቦታ የኤደን ዛፎችን ሁሉ አጽናናለሁ! እነርሱም ውኃ የሚጠጡ ፥ ምርጦችና መልካካሞች የሊባኖስ ዛፎች ናቸው።
\s5
\v 17 ክንዱም ወደ የነበሩት በአሕዛብም መካከል በጥላው ሥር የተቀመጡት፥ በሰይፍ ወደ ተገደሉት ሰዎች ወደ ሲኦል ከእርሱ ጋር ወርደዋልና።
\v 18 በክብርና በታላቅነት በዔድን ዛፎች መካከል ማን ይመስልህ ነበር? ነገር ግን ከዔድን ዛፎች ጋር ወዳልተገረዙት መካከል ወደ ታችኛው ምድር ያወርዱሃል፤ በሰይፍም ከተገደሉት ጋር ትኖራለህ! እነርሱም ፈርዖንና አገልጋዮቹ ናቸው ይላል ጌታ እግዚአብሔር!"
\s5
\c 32
\p
\v 1 እንዲህም ሆነ በአሥራ ሁለተኛው ዓመት በአሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
\v 2 የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አሙሽ፥ እንዲህም በለው፥ 'በእህዛብ መካከል እንደ አንበሳ ደቦል በባህር እንዳለ አስፈሪ ፍጥረት ነበርክ፤ ውሃውን አናወጥከው፥ ውሆችን በእግርህ በጥብጠህ አጨቀየሀቸው።
\s5
\v 3 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በብዙ አሕዛብ ጉባኤ መረቤን እዘረጋብሃለሁ፥ እነርሱም በመረቤ ይይዙሀል!
\v 4 በምድርም ላይ እተውሃለሁ፥ በምድረ በዳም ፊት እጥልሃለሁ፥ የሰማይንም ወፎች ሁሉ አሳርፍብሃለሁ፥ የተራቡ ምድርን አራዊት በአንተ አጠግባቸዋለሁ።
\s5
\v 5 ሥጋህን በተራሮች ላይ አደርጋለሁ ሸለቆቹንም በትል በተሞላ ሬሳህ እሞላለሁ!
\v 6 ደምህንም በተራሮች ላይ አፈሳለሁ መስኖችም በደምህ ይሞላሉ።
\s5
\v 7 መብራትህን ባጠፋህ ጊዜ ሰማዮችን እሸፍናለሁ፥ ከዋክብቶችንም አጨልማለሁ። ፀሐይንም በደመና እሸፍናለሁ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም!
\v 8 የሰማይን ብርሃኖች ሁሉ በላይህ አጨልማለሁ፥ በምድርህም ላይ ጨለማ አደርጋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\s5
\v 9 በአዛብ መካከል ጥፋትህን በማመጣ ጊዜ የማታውቃቸውን የብዙ ሕዝብን ልብ አስደነግጣለሁ።
\v 10 ብዙም አሕዛብን ስለዘንተ አስደንቃለሁ፤ ሰይፌንም በፊታቸው ባወዛወዝሁ ጊዜ ነገሥታቶቻቸው ስለ አንተ እጅግ አድርገው ይፈራሉ። በውድቀትህም ቀን እያንዳንዱ በአንተ ምክንያት ይንቀጠቀጣል።
\s5
\v 11 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና። የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ ይመጣብሃል።
\v 12 አገልጋዮችህ የአህዛብ ድንጋጤ በሆኑ ጦርኞች ሥይፍ እንዲወድቁ አደርጋልሁ! የግበጽንም ትዕቢት ያውርዳሉ ህዝቧንም ሁሉ ያጠፋሉ!
\s5
\v 13 እንስሶችን ከብዙ ውኃ አጠገብ አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲያ የሰው እግርም ሆነ የእንስሳት ኮቴ ውሃውን አያደፈርስም!
\v 14 በዚያን ጊዜ ውኃቸውን አረጋጋለሁ፥ እንደ ዘይትም እንዲፈስሱ አደርጋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\s5
\v 15 ሙሉ የነበረውን የግብጽን ምድር ባድማና ውድማ ባደረግሁ ጊዜ፥ የሚኖሩባትንም ሁሉ በቀሠፍሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ!
\v 16 የአሕዛብ ቈነጃጅት ያለቅሱበታል ያለቅሱባታልና ሙሾ ይሆናል፥ ነው ስለ ግብጽና ስለአገልጋዮቿ ሁሉ ያለቅሳሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\s5
\v 17 እንዲህም ሆነ በአሥራ ሁለተኛው ዓመት ከወሩም በአሥራ አምስተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
\v 18 የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ግብጽ አገልጋዮች አልቅስ፥ እርስዋንና የብርቱዎችን አሕዛብ ሴቶች ልጆች ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ጋር ወደ ታችኛው ምድር ጣላቸው።
\s5
\v 19 እንዲህ ብለህ ጥይቃቸው፥ 'ከማንም ይልቅ በውበት ትበልጣላችሁን? ውረዱና ካልተገረዙትም ጋር ተኙ!
\v 20 በሰይፍ በተገደሉት መካከል ይወድቃሉ፤ ጥላቶቿ እርሷንና አገልጋዮቿን ይይዛሉ!
\v 21 በሲኦል የኃያላን አለቆች ስለ ግብጽ ፥ "ወደዚህ ወደ ሲዖል መጥተዋል! በሰይፍ ከተገድሉ ካልተገርዙት ጋር ይተኛሉ!' ብለው ይናገራሉ።
\s5
\v 22 አሦርና ጉባኤዋ ሁሉ በዚያ አሉ መቃብሮችም ከበዋታል፤ ሁሉም በሰይፍ የተገደሉ ናቸው።
\v 23 መቃብራቸው በጕድጓዱ በውስጠኛው ክፍል የሆኑትም ከእርሷ ጉባኤ ሁሉ ጋር በዚያ አሉ! መቃብሯ በተገደሉ፥ በሰይፍ በወደቁ እንዲሁም በሕያዋን ምድር ፍርሀትን ባመጡ ተከቧል።
\s5
\v 24 ኤላምም ከአገልጋዮቿ ጋር በዚያ አለች፤ መቃብሮቿም ከበዋታል። ሁሉም የተገደሉ ናቸው። እነርሱም በሕያዋን ምድር ያስፈሩ ሁሉ ፥ ሳይገረዙም ወደ ታችኛው ምድር የወረዱ፥ በህያዋን ምድር ሽብርን ያመጡና ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱ ጋር እፍረታቸውን የተሸከሙ ናቸው።
\v 25 በተገደሉት መካከል ለኤላምና ለአገልጋዮቻ መኝታን አድርገውላታል፤ መቃብርዋ በዙሪያዋ ነው! ሁሉም ያልተገረዙና በህያዋን ምድር ሽብርን በማምጣታቸው በሰይፍ የተገደሉ ናቸው! ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱ ጋር እፍረታቸውን ተሸክመዋል። ኤላምም በተገደሉትም መካከል ነች።
\s5
\v 26 ሞሳሕና ቶቤል ብዛታቸውም ሁሉ በዚያ አሉ መቃብራቸውም በዙሪያቸው ነው ሁሉም ያልተገረዙ ሲሆኑ በሕያዋን ምድር ሽብር ያመጡ ስለነበር በሰይፍ የተገደሉ ናቸው!
\v 27 በሕያዋንም ምድር ኃያላኑን ያስፈሩ ነበርና መሣሪያቸውን ይዘው ወደ ሲኦል ከወረዱ፥ ሰይፋቸውንም ከራሳቸው በታች ካደረጉ፥ ካልተገረዙ ኃያላን ጋር አልተኙምን? በህያዋን ምድር አስፈሪ ተዋጊዎች በመሆናቸው ጋሻቸውም በአጥንታቸው ላይ ነው ።
\s5
\v 28 አንቺም ግብጽ ባልተገረዙት መካከል ትሰበሪያለሽ! በሰይፍም ከተገደሉት ጋር ትተኚያለሽ።
\v 29 ኤዶምያስ ከነገሥታቶችዋና ከአለቆችዋ ሁሉጋር በዚያ አሉ። ኃያላን ነበሩ፥ ነገር ግን አሁን በሰይፍ ከተገደሉትና ካልተገረዙት ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ጋር ይተኛሉ ።
\s5
\v 30 የሰሜን አለቆች ሁሉ ከሙታን ጋር የወረዱ ከሲዶናውያንም በዚያ አሉ! ኃያላን ነበሩ፥ አሁን ግን በዚያ በእፍረት ፥ በሰይፍ ከተገደሉት ጋር ሳይገረዙ ተኝተዋል። እፍረታቸውን ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱት ጋር ይሸከማሉ።
\s5
\v 31 ፈርዖንም ይመለከታል በሠይፍ ስለተገደሉት አገልጋዮቹ ይጽናናል ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
\v 32 መፈራቱን በሕያዋን ምድር አድርጌአለሁ፥ ነገር ግን በሰይፍ በተገደሉት ባልተገረዙት መካከል ይተኛል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር!"
\s5
\c 33
\p
\v 1 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
\v 2 "የሰው ልጅ ሆይ፥ ለሕዝብህ ልጆች ተናገር እንዲህም በላቸው፥ 'ሰይፍን በምድር ላይ ባመጣሁ ጊዜ፥ የምድር ሕዝብ ከመካከላቸው ሰውን ወስደው ለራሳቸው ጕበኛ ያድርጉ።
\v 3 ሰይፍ በመጣ ጊዜ ይመልከት ቀንደ መለከቱንም በመንፋት ህዝቡን ያስጠንቅቅ!
\v 4 ህዝቡም የመለከቱን ድምፅ ሰምተው ባይጠነቀቁ ፥ ሰይፍ መጥቶ ቢገድላቸው እያንዳንዱ ሰው ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል።
\s5
\v 5 አንድ ሰው የመለከቱን ድምፅ ሰምቶ ባይጠነቀቅ ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል፤ ነገር ግን ቢጠነቀቅ የራሱን ህይወት ያድናል።
\v 6 ጕበኛው ግን ሰይፍ ሲመጣ ቢያይ መለከቱንም ባይነፋ ሕዝቡንም ባያስጠነቅቅ ሰይፍም መጥቶ አንድን ሰው ቢገድል እሱ በኃጢአቱ ይሞታል፥ደሙን ግን ከጕበኛው እጅ እፈልጋለሁ።
\s5
\v 7 አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ለእስራኤል ቤት ጕበኛ አድርጌሃለሁ፤ ከአፌ ቃሌን ስማ እኔን ወክለህ አስጠንቅቃቸው።
\v 8 ኃጢአተኛውን "ኃጢአተኛ ሆይ፥ በእርግጥ ትሞታለህ!" ባልኩት ጊዜ፥ ኃጢአተኛውን ከመንገዱ እንዲመለስ ለማስጠንቀቅ ባትናገር ያ ኃጢአተኛ በኃጢአቱ ይሞታል፥ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።
\v 9 ነገር ግን ከመንገዱ እንዲመለስ ኃጢአተኛውን ብታስጠነቅቀው እርሱ ግን ከመንገዱ ባይመለስ በኃጢአቱ ይሞታል አንተ ግን ነፍስህን አድነሃል።
\s5
\v 10 አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤልን ቤት እንዲህ በላቸው፥ 'እናንተ በደላችንና ኃጢአታችን በላያችን አሉ እኛም ሰልስለንባቸዋል እንዴትስ በሕይወት እንኖራለን? ብላችኋል' ።
\v 11 'እኔ ሕያው ነኝና ኃጢአተኛው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት እንዲኖር እንጂ ኃጢአተኛው እንዲሞት አልፈቅድም፥ የእስራኤል ቤት ሆይ ንስሀ ግቡ! ስለ ክፉ መንገዳችሁ ንስሀ ግቡ ለምን ትሞታላችሁ ይላል ጌታ እግዚአብሔር?' በላቸው።
\s5
\v 12 አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ህዝብህን እንዲህ በላቸው፥' ጻድቅ ቢበድል ጽድቁ አያድነውም! ኃጢአተኛም ከኃጢአቱ ቢመለስ በኃጢአቱ አይጠፋም። ጻድቁም ኃጢአት ቢስራ በጽድቁ በሕይወት ሊኖር አይችልም።
\v 13 እኔ ጻድቁን፥ "በእርግጥ በሕይወት ይኖራል!" ባልሁ ጊዜ፥ እርሱ በጽድቁ ታምኖ ኃጢአት ቢሠራ በሠራው ኃጢአት ይሞታል እንጂ ጽድቁ አላስብለትም።
\s5
\v 14 እኔም ኃጢአተኛውን። በእርግጥ ትሞታለህ ባልሁ ጊዜ፥ እርሱ ከኃጢአቱ ተመልሶ ፍርድንና ቅን ነገርን ቢያደርግ፥
\v 15 ኃጢአተኛውም የብድር መያዣን ቢመልስ የነጠቀውንም ቢመልስ ሕይወት በሚሰጡ ትእዛዛት ቢራመድ ከዚያም በኋላ ኃጢአት ባይሠራ፥ በእርግጥም በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም።
\v 16 የሠራው ኃጢአት ሁሉ አይታሰብበትም። ፍርድንና ቅን ነገርን አድርጎአል በእርግጥ በሕይወት ይኖራል።
\s5
\v 17 ነገር ግን ሕዝብህ ፥ "የጌታ መንገድ የቀና አይደለም!" ይላሉ ነገር ግን ቅን ያልሆነው የእናንተ መንገድ ነው!
\v 18 ጻድቅ ከጽድቁ ተመልሶ ኃጢአትን ቢሠራ በኃጢአቱ ይሞታል!
\v 19 ኃጢአተኛውም ከኃጢአቱ ተመልሶ ፍርድንና ቅን ነገርን ቢያደርግ ባደረጋቸው ነገሮች ምክንያት በሕይወት ይኖራል።
\v 20 እናንተ ግን፥ "የጌታ መንገድ የቀና አይደለም!" ትላላችሁ። የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በእያንዳንዳችሁ ላይ እንደ መንገዳችሁ እፈርድባችኋለሁ።
\s5
\v 21 እንዲህም ሆነ በተማረክን በአሥራ ሁለተኛው ዓመት በአሥረኛው ወር ከወሩም በአምስተኛው ቀን ከኢየሩሳሌም ያመለጠ አንድ ሰው ወደ እኔ መጥቶ "ከተማይቱ ተያዘች!"አለኝ።
\v 22 ሰውዬው ከመምጣቱ በፊት ባለው ምሽት የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ነበረች፥ ሰውዬው በምሽት ወደ እኔ በመጣ ጊዜ አፌ ተከፍቶ ነበር። ስለዚህም አፌ ተከፍቶ ነበር ከዚያም በኋላ እኔ ዲዳ አልሆንሁም።
\s5
\v 23 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
\v 24 የሰው ልጅ ሆይ፥ በእስራኤል ምድር ባሉ በባድማ ስፍራዎች የተቀመጡ፥ 'አብርሃም ብቻውን ሳለ ምድሪቱን ወረሰ እኛም ብዙዎች ነን ምድሪቱም ርስት ሆና ለእኛ ተሰጥታለች' ይላሉ።
\s5
\v 25 ስለዚህ እንዲህ በላቸው፥'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከደም ጋር ትበላላችሁ፥ ዓይናችሁንም ወደ ጣዖቶቻችሁ ታነሣላችሁ፥ የስዎችንም ደም ታፈስሳላችሁ። በውኑ ምድሪቱን ትወርሳላችሁን?
\v 26 በሰይፋችሁ ተማምናችሁ፥ ርኩስ ነገርን ታደርጋላችሁ፥ የባልንጀሮቻችሁንም ሚስቶች ታስነውራላችሁ። በውኑ ምድሪቱን ትወርሳላችሁን?
\s5
\v 27 እንዲህም በላቸው፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና በባድማ ስፍራዎች ያሉ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ በምድረ በዳ ያለውን ለአራዊት መብል አድርጌ እሰጣለሁ፥ በአምባዎችና በዋሾች ያሉ በቸነፈር ይሞታሉ።
\v 28 ምድሪቱንም ባድማና ውድማ አደርጋታለሁ በኃይሏም መመካቷ ይቀራል፥ የእስራኤልም ተራሮች ማንም የማያልፍባቸው በረሀ ይሆናሉ፥ ።
\v 29 ስላደረጉትም ርኵሰት ሁሉ ምድሪቱን ባድማና ውድማ ባደርግሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
\s5
\v 30 አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ሕዝብህ በቅጥር አጠገብና በቤት ደጆች ውስጥ ስለ አንተ ይናገራሉ፥ እርስ በርሳቸውም፥ አንዱ ከአንዱ ጋር፥ 'ወደ ነቢዩ እንሂድና እግዚአብሔር ያለው ቃል ምን እንደ ሆነ እንስማ!' እያሉ ይነጋገራሉ።
\v 31 ስለዚህ ሕዝቤ ብዙ ጊዜ እንደሚያደርጉት መጥተው በፊትህ ይቀመጣና ቃልህንም ይሰማሉ ነገር ግን አያደርጉትም። ትክክለኛው ቃል በፍቸው ነው ፥ ልባቸው ግን ቅንነት የሌለበትን ትርፍ ትከተላለች።
\s5
\v 32 እነሆ፥ አንተ መልካም ድምፅ እንዳለው እንደሚወደድ መዝሙር ማለፊያም አድርጎ እንደሚጫወቱት በገና ሆነህላቸዋል ስለዚህም ቃልህን ይሰማሉ ነገር ግን አንዳቸውም አያደርጉትም።
\v 33 እነሆ፥ ይህ ይመጣል በመጣም ጊዜ እነርሱ ነቢይ በመካከላቸው እንደ ነበረ ያውቃሉ።"
\s5
\c 34
\p
\v 1 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
\v 2 "የሰው ልጅ ሆይ፥ በእስራኤል እረኞች ላይ ትንቢት ተናገር፥ እረኞችንም እንዲህ በላቸው፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ራሳቸውን ለሚያሰማሩ ለእስራኤል እረኞች ወዮላቸው! እረኞች በጎችን ያሰማሩ ዘንድ አይገባቸውምን?
\v 3 ጮማውን ትበላላችሁ ጠጕሩንም ትለብሳላችሁ! ከመንጋው መካከል የወፈሩትን ታርዳላችሁ! በጎቹን ግን ፈጽሞ አታሰማሩም።
\s5
\v 4 የደከመውን አላጸናችሁትም የታመመውንም አላከማችሁትም የተሰበረውንም አልጠገናችሁትም የባዘነውንም አልመለሳችሁትም የጠፋውንም አልፈለጋችሁትም በኃይልና በጭቈናም ገዛችኋቸው።
\v 5 ያለ እረኛም በማጣት ተበተኑ፥ ከተበተኑም በኋላ ለምድር አራዊት ሁሉ መብል ሆኑ።
\v 6 በጎቼ በተራሮች ሁሉና በረዘሙ ኮረብቶች ሁሉ ላይ ተቅበዝብዘዋል፥ በምድርም ፊት ሁሉ ላይ ተበትነዋል። የሚፈልጋቸውም የለም።
\s5
\v 7 ስለዚህ፥ እረኞች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ
\v 8 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና እረኛ ስለሌለ እረኞቼም በጎቼን ስላልፈለጉ እረኞችም ራሳቸውን እንጂ በጎቼን ስላላሰማሩ፥ በጎቼ ንጥቂያና፥ ለምድር አራዊት ሁሉ መብል ሆነዋልና
\s5
\v 9 ስለዚህ፥ እረኞች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ
\v 10 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በእረኞች ላይ ነኝ፥ በጎቼንም ከእጃቸው እፈልጋለሁ፥ በጎቼንም ከማሰማራት አስተዋቸዋለሁ። ከዚያም ወዲያ እረኞች ራሳቸውን አያሰማሩም በጎቼንም ከአፋቸው አድናለሁ፥ መብልም አይሆኑላቸውም።
\s5
\v 11 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና። እነሆ፥ እኔ ራሴ በጎቼን እሻለሁ አሰማራቸውማለሁ።
\v 12 እረኛ በተበተኑት በጎች መካከል ባለ ጊዜ መንጋውን እንደሚፈልግ፥ እንዲሁ በጎቼን እፈልጋለሁ በደመናና በጨለማ ቀን ከተበተኑት ስፍራ ሁሉ አድናቸዋለሁ።
\v 13 ከአሕዛብም መካከል አወጣቸዋለሁ ከአገሮችም እሰበስባቸዋለሁ፥ ወደ ገዛ አገራቸውም እሰበስባቸዋለሁ። በእስራኤልም ተራሮች ላይ በፈሳሾችም አጠገብ በምድርም ላይ ሰዎች በሚኖሩበት ስፍራ ሁሉ አሰማራቸዋለሁ።
\s5
\v 14 በመልካም ማሰማርያ እሰማራቸዋለሁ የእስራኤል ረጃጅም ተራሮች የግጦሽ ቦታቸው ይሆናል። በዚያ በለመለመ መስክ በመልካምም የግጦሽ ሥፍራ ያርፋሉ፥ በእስራኤልም ተራሮች ላይ ይግጣሉ።
\v 15 እኔ ራሴ በጎቼን አሰማራለሁ አስመስጋቸውማለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\v 16 የጠፋውንም እፈልጋለሁ የባዘነውንም እመልሳለሁ የተሰበረውንም እጠግናለሁ የደከመውንም አጸናለሁ የወፈረውንና የበረታውንም አጠፋለሁ! በመልካም አሰማራለሁ።
\s5
\v 17 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እናንተም መንጋዬ ሆይ፥ እነሆ፥ በበግና በበግ መካከል፥ በአውራ በግና በአውራ ፍየልም መካከል፥ እፈርዳለሁ።
\v 18 የቀረውን ማሰማርያችሁን በእግራችሁ የረገጣችሁት፥ በመልካሙ ማሰማርያ መሰማራታችሁ አልበቃ ብሏችሁ ነው? የቀረውንስ ውኃ በእግራችሁ ያደፈረሳችሁት፥ ጥሩውን ውኃ መጠጣታችሁ አልበቃ ብሏችሁ ነው?
\v 19 በጎቼም በእግራችሁ በረገጣችሁት ይሰማራሉ በእግራችሁም ያደፈረሳችሁትን ይጠጣሉ።
\s5
\v 20 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላቸዋል፥ እነሆ፥ እኔ በወፈሩት በጎችና በከሱት በጎች መካከል እፈርዳለሁ።
\v 21 ይህም እስክትበትኑአቸው ድረስ በእንቢያና በትከሻ ስለምትገፉአቸው የደከሙትንም ሁሉ በቀንዳችሁ ስለምትወጉአቸው ነው።
\s5
\v 22 ስለዚህ መንጋዬን አድናለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህም ለንጥቂያ አይሆኑም። በበግና በበግ መካከልም እፈርዳለሁ።
\v 23 በላያቸውም አንድ እረኛ አቆማለሁ እርሱም ያሰማራቸዋል፥ እርሱም ባሪያዬ ዳዊት ነው! ያሰማራቸዋል እረኛም ይሆናቸዋል።
\v 24 እኔም እግዚአብሔር አምላክ እሆናቸዋለሁ ባሪያዬም ዳዊት በመካከላቸው አለቃ ይሆናል እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።
\s5
\v 25 የሰላምን ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር እገባለሁ ክፉዎችንም አራዊት ከምድሪቱ አጠፋለሁ፥ በጎቼም ተጠብቀው በምድረ በዳ ይኖራሉ በዱርም ውስጥ ይተኛሉ።
\v 26 በእነርሱና በዙሪያ ባሉ ኮረብቶቼ በረከቴን አፈሳለሁ፥ ዝናቡንም በጊዜው እልካለሁ። ይህም የበረከት ዝናብ ይሆናል።
\v 27 የምድረ በዳም ዛፍ ፍሬውን ይሰጣል ምድርም ቡቃያዋን ትሰጣለች፥ በጎቼ በምድራቸው ተዘልለው ይኖራሉ የቀንበራቸውንም ማነቆ በሰበርሁ ጊዜ ከሚገዙአቸውም እጅ ባዳንኋቸው ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
\s5
\v 28 እንግዲህም ለአሕዛብ ንጥቂያ አይሆኑም የምድርም አራዊት አይበሉአቸውም ተዘልለውም ይቀመጣሉ የሚያስፈራቸውም የለም።
\v 29 መልካም የእርሻ ቦታ አዘግዝጅላቸዋልሁ፥ ከእንግዲህም ከራብ የተነሣ በምድሪቱ አያልቁም አሕዛብም ከእንግዲህ ወዲህ አይሰድቧቸውም።
\s5
\v 30 እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ከእነርሱ ጋር እንዳለሁ ያውቃሉ። የእስራኤል ቤት ሕዝቤ እነርሱ ህዝቤ ናቸው ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
\v 31 እናንተም በጎቼ፥ የማሰማርያዬ በጎች፥ ህዝቤ ናችሁ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር"
\s5
\c 35
\p
\v 1 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
\v 2 "የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ ሴይር ተራራ አድርግ፥ ትንቢትም ተናገርበት፥
\v 3 እንዲህም በለው 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሴይር ተራራ ሆይ፥ እነሆ፥ በአንተ ላይ ነኝ፥ በእጄ እመታሀለሁ ባድማና ድንጋጤ አደርግሃለሁ።
\s5
\v 4 ከተሞችህንም አፈራርሳቸዋለሁ፥ አንተም ባድማ ትሆናለህ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃለህ።
\v 5 ለእስራኤልን ህዝብ ሁል ጊዜ ጥላቻ ስላለህ በመከራቸውም ጊዜ በጽኑ ቅጣት በተቀጡበት ጊዜ የእስራኤልን ልጆች በሰይፍ እጅ ጥለሃቸዋልና
\v 6 ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና ለደም መፋሰስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ ደም መፋሰስም ያሳድድሃል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር ደም መፋሰስን ስላልጠላህ ደም መፋሰስ ያሳድድሃል።
\s5
\v 7 በእርሱ የሚያልፈውንም ሆነ ወደ እርሱ የሚመለስ እንዳይኖሬ በማድረግ የሴይርን ተራራ ውድማ አደርገዋለሁ ።
\v 8 ተራሮቹንም በተገደሉት ሰዎች እሞላለሁ በኮረብቶችህና በሸለቆችህ በፈሳሾችህም ሁሉ ላይ በሰይፍ የተገደሉት ሁሉ ይወድቃሉ።
\v 9 ለዘላለምም ባድማ አደርግሃለሁ ከተሞችህም ሰው የማይኖርባቸው ይሆናሉ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
\s5
\v 10 አንተ፥ "እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋሬ ቢሆንም እነዚህ ሁለቱ ሕዝቦች እነዚህም ሁለቱ አገሮች ለእኔ ይሆናሉ እኛም እንወርሳቸዋለን" ብለሃል።
\v 11 ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና እንደ ቍጣህ መጠን እነርሱንም ጠልተህ እንዳደረግኸው እንደ ቅንዓትህ መጠን እኔ አደርግብሀለሁ፥ በፈረድሁብህም ጊዜ በእነርሱ ዘንድ የታወቅሁ እሆናለሁ ይላል ጌታ እግዚአብሔር ።
\s5
\v 12 ስለዚህም እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ ታውቃለህ። በእስራኤል ተራሮች ላይ "ፈርሰዋል! መብልም ሆነው ለእኛ ተሰጥተዋል" ብለህ የተናገርኸውን ስድብ ሁሉ ሰምቻለሁ።
\v 13 በአፋህም በእኔ ላይ የተናገርከውን ትምክህት የተሞላ ንግግር ሰምቻለሁ፤ በኔ ላይ ብዙ ነገሮችን ተናገርክ።፥ እኔም ሰምቼዋለሁ።
\s5
\v 14 ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል። ምድር ሁሉ ደስ ሲላት አንተን ባድማ አደርግሃለሁ።
\v 15 የእስራኤል ቤት ርስት ባድማ ስለ ሆነ አንተ ደስ እንዳለህ፥ እንዲሁ አደርግብሃለሁ። የሴይር ተራራ ሆይ፥ አንተና ኤዶምያስ ሁሉ ሁለንተናውም ባድማ ትሆናላችሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
\s5
\c 36
\p
\v 1 አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ለእስራኤል ተራሮች ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው ፥ 'የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ!'
\v 2 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠላት በእናንተ ላይ "እሰይ! የጥንት ከፍታዎች ለእኛ ርስት ሆነዋል" ብሎአል።
\v 3 ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በል፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ባድማ በመሆናችሁና ከሁሉም አቅጣጫ ከመጣባችሁ ጥቃት የተነሳ ለሌሎች አሕዛብ ርስት ሆናችኋል፤ የተናጋሪዎች ከንፈር መተረቻና የአሕዛብ ማላገጫም ሆናችኋል።
\s5
\v 4 ስለዚህ፥ እናንተ የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ የጌታን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ ጌታ እግዚአብሔር ለተራሮችና ለኮረብቶች፥ ለፈሳሾችና ለሸለቆች ለምድረ በዳዎች ባዶ ለሆኑትም በዙሪያ ላሉት ለቀሩት አሕዛብ ምርኮና መሳቂያ ለሆኑት ከተሞች እንዲህ ይላል
\v 5 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያሳድዱአትና ይበዘብዙአት ዘንድ በልባቸው ሁሉ ደስታና በነፍሳቸው ንቀት ምድሬን ርስት አድርገው ለራሳቸው በወሰዱ በቀሩት አሕዛብና በኤዶምያስ ሁሉ ላይ በቅንዓቴ እሳት ተናግሬአለሁ
\v 6 ስለዚህ ስለ እስራኤል ምድር ትንቢት ተናገር፥ ለተራሮችና ለኮረብቶችም ለፈሳሾችና ለሸለቆችም እንዲህ በል። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የአሕዛብን ስድብ ስለ ተሸከማችሁ በቅንዓቴና በመዓቴ ተናግሬአለሁ
\s5
\v 7 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዙሪያችሁ ያሉ አሕዛብ ስድባቸውን በእርግጥ ይሸከማሉ ብዬ ምያለሁ።
\s5
\v 8 እናንተ የእስራኤል ተራሮች ግን ወደ እናንተ ተመልሰው የሚመጡበት ቀን ቀርቧልና፥ ቅርንጫፎቻችሁን ታቈጠቍጣላችሁ፥ ለሕዝቤ ለእስራኤልም ፍሬአቸሁን ትሰጣላችሁ።
\v 9 እነሆ፥ እኔ ለእናንተ ነኝና ወደ እናንተም እመለከታለሁ፥ እናንተም ትታረሳላችሁ ይዘራባችሁማል።
\s5
\v 10 ስለዚህም እናንተ ተራሮች ሆይ በእስራኤል ቤት ሁሉ ሰዎችን አበዛባችኋለሁ። ሁሉም! ከተሞች የሰዎች መኖሪያ ይሆናሉ ባድማዎቹም ስፍራዎች ይሠራሉ።
\v 11 እናንተ ተራሮች ሆይ ሰውንና እንስሳውንም አበዛባችኋለሁ፥ እነርሱም ይበዛሉ ያፈሩማል። ቀድሞ እንደነበራችሁት የሰዎች መኖሪያ አደርጋችኋለሁ፥ ከቀድሞ ይልቅ አበለጥጋችኋለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
\v 12 በእናንተ ላይ እንዲረማመዱ የሕዝቤን የእስራኤልን ሰዎችን አመጣቸዋለሁ። እነርሱም ይወርሱዋቸዋል ርስትም ትሆኑላቸዋላችሁ፥ ከእንግዲህም የልጆቻቸው ሞት ምክንያት አትሆኑም።
\s5
\v 13 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነርሱ "እናንተ ሰው በሊታ ናችሁ የሕዝባችሁም ልጆች አልቀዋል" ብለዋችኋልና
\v 14 ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲያ ሰው በሊታ አትሆኑም፥ ዳግመኛም ሕዝብችሁን በሚሞቱ ሰዎች ምንንያት እንዲያለቅሱ አታደርጉም ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
\v 15 ዳግመኛም የአሕዛብን ስድብ አላሰማብሽም፤ ዳግመኛም የአሕዛብን ስድብ አትሸከሚም፥ ዳግመኛም ሕዝብሽን አታሰናክዪም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\v 16 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
\v 17 "የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤል ቤት በምድራቸው በተቀመጡ ጊዜ በመንገዳቸውና በሥራቸው አረከሱአት፥ መንገዳቸውም በፊቴ እንደ መርገም አደፍ ነበረ።
\v 18 በምድሪቱም ላይ ስላፈሰሱት ደም በጣዖቶቻቸውም ስላረከሱአት መዓቴን አፈሰስሁባቸው።
\s5
\v 19 ወደ አሕዛብም በተንኋቸው ወደ አገሮችም ተዘሩ እንደ መንገዳቸውና እንደ ሥራቸው መጠን ፈረድሁባቸው።
\v 20 ወደ ሌሎች ሕዝቦች ሄዱ። በሄዱም ጊዜ ሰዎች ስለነርሱ 'አሁን እነዚህ ከአገራቸው የተፈናቅሉ የእግዚአብሔር ሕዝብ እነዚህ ናቸው?' በማለታቸው ቅዱስ ስሜን አረከሱ።
\v 21 እኔ ግን የእስራኤል ቤት በመጡባቸው በአሕዛብ መካከል ስላረከሱት ስለ ቅዱስ ስሜ ስል ራራሁላቸው።
\s5
\v 22 ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ይህን የማደርገው በሄዳችሁበት በአሕዛብ መካከል ሁሉ ስላረከሳችሁት ስለ ቅዱስ ስሜ ነው እንጂ ስለ እናንተ አይደለም።
\v 23 በአሕዛብም ዘንድ የረከሰውን፥ በመካከላቸው ያረከሳችሁትን ስሜን እቀድሰዋለሁ። በዓይናቸውም ዘንድ በተቀደስሁባችሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ አሕዛብ ያውቃሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\s5
\v 24 ከአሕዛብም መካከል እወስዳችኋለሁ ከየአገሩም ሁሉ እሰበስባችኋለሁ ወደ ገዛ ምድራችሁም አመጣችኋለሁ።
\v 25 ከእርኩሰታችሁ ሁሉ እንድትነጹም ጥሩ ውኃን እረጭባችኋለሁ። ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አጠራችኋለሁ።
\s5
\v 26 አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ።
\v 27 መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ በትእዛዜም መሄድ አስችላችኋለሁ ፥ ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ።
\v 28 ለአባቶቻችሁም በሰጠኋት ምድር ትኖራላችሁ ሕዝቤ ትሆናላችሁ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ።
\s5
\v 29 ከርኵሰታችሁም ሁሉ አድናችኋለሁ እህልንም እጠራዋለሁ አበዛውማለሁ ከእንግዲህም ራብን አላመጣባችሁም።
\v 30 ደግሞም የራብን ስድብ በሕዝቦች መካከል እንዳትሸከሙ የዛፍን ፍሬና የእርሻውን ቡቃያ አበዛለሁ።
\v 31 ከዚያም ክፉውን መንገዳችሁንና መልካም ያይደለውን ሥራችሁንም ታስባላችሁ፥ ስለ በደላችሁና ስለ ርኵሰታችሁም ራሳችሁን ትጸየፋላችሁ።
\s5
\v 32 ይህን ያደረኩት ስለ እናንተ ብዬ እንዳይደለ እወቁ-ይላል ጌታ እግዚአብሔር። የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ስለ መንገዳችሁ እፈሩና ተዋረዱ።
\v 33 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ክእርኩሰታችሁ ሁሉ ባነጻኋችሁበት ቀን በከተሞቻችሁ እንድትኖሩ የፈረሱትንም ሥፍራዎች እንደገና እንድትጠግኑ አደርጋችኋለሁ።
\v 34 ባድማ የነበረች ምድር በመንገደኛ ሁሉ ዓይን ባድማ ባል ድረስ ትታረሳለች።
\s5
\v 35 ሰዎችም፥ "ባድማ የነበረች ይህች ምድር እንደ ዔድን ገነት ሆናለች የፈረሱት ባድማ የሆኑት የጠፉትም ከተሞች ተመሽገዋል ሰውም የሚኖርባቸው ሆነዋል" ይላሉ።
\v 36 በዙሪያችሁም ያሉ አሕዛብ እኔ እግዚአብሔር የፈረሱትን ስፍራዎች እንደ ሠራሁ ውድማ የሆነውንም እንደገና እንደተከልሁ ያውቃሉ፥ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፥ እኔም አደርገዋለሁ።
\s5
\v 37 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለዚህ ደግሞ እንደመንጋ እንዳበዛቸው የእስራኤል ቤት ይጠይቁኛል።
\v 38 ለእግዚአብሔሬእንደ ተለዩ በጎች፥ በበዓላቶችዋ ቀን እንደሚሆኑ እንደ ኢየሩሳሌም በጎች፥ እንዲሁ የፈረሱት ከተሞች በሰዎች መንጋ ይሞላሉ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
\s5
\c 37
\p
\v 1 የእግዚአብሔርም እጅ በላዬ ነበረ እግዚአብሔርም በመንፈሱ አወጣኝ አጥንቶችም በሞሉባት ሸለቆ መካከል አኖረኝ።
\v 2 ዙሪያውን በመካከላቸው እንዳልፍ አደረገኝ፥ እነሆ በሸለቆው ውስጥ እጅግ ብዙ ነበሩ፥ እነሆም፥ እጅግ ደርቀው ነበር።
\v 3 እርሱም፥ "የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ አጥንቶች እንደገና በሕይወት ሊኖሩ ይችላሉን?" አለኝ። እኔም። ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ይህን የምታውቀው አንተ ብቻ ነህ!" አልሁ።
\s5
\v 4 እርሱም እንዲህ አለኝ፥ "በእነዚህ አጥንቶች ላይ ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው፥ 'እናንተ የደረቃችሁ አጥንቶች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ሰሙ።
\v 5 ጌታ እግዚአብሔር ለእነዚህ አጥንቶች እንዲህ ይላል። እነሆ፥ መንፈስን አገባባችኋለሁ በሕይወትም ትኖራላችሁ።
\v 6 ጅማትም እሰጣችኋለሁ ሥጋንም አወጣባችኋለሁ በእናንተም ላይ ቁርበትን እዘረጋለሁ ትንፋሽንም አገባባችኋለሁ በሕይወትም ትኖራላችሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
\s5
\v 7 እንዳዘዘኝም ትንቢት ተናገርሁ ስናገርም ፥ እነሆ የሚያናውጥ ድምፅ ሆነ፥ አጥንቶችም አጥንት ከአጥንት ጋር ተቀራረቡ።
\v 8 እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ ጅማት ነበረባቸው ሥጋም ወጣ ቁርበትም በላያቸው ተዘረጋ፥ ህይወት ግን አልነበራቸውም።
\s5
\v 9 እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፥ ለነፋስ ትንቢት ተናገር፥ ለነፋስም 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦' መንፈስ ቅዱስ! ከአራቱ ነፋሳት ዘንድ ና፥ እነዚህም የተገደሉት በሕይወት ይኖሩ ዘንድ እፍ በልባቸው" በል አለኝ።
\v 10 እንዳዘዘኝም ትንቢት ተናገርሁ፥ የእግዚአብሔርም መንፈስ ገባባቸው ሕያዋንም ሆኑ! እጅግም ታላቅ ሠራዊት ሆነው በእግራቸው ቆሙ።
\s5
\v 11 እርሱም እንዲህ አለኝ፥ "የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ አጥንቶች የእስራኤል ቤት ሁሉ ናቸው። እነሆ! አጥንቶቻችን ደርቀዋል ተስፋችንም ጠፍቶአል ፈጽመንም ተቈርጠናል ብለዋል።
\v 12 ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሕዝቤ ሆይ፥ እነሆ፥ መቃብራችሁን እከፍታለሁ ከመቃብራችሁም አወጣችኋለሁ፥ ወደ እስራኤልም ምድር እመልሳችኋለሁ!
\s5
\v 13 ሕዝቤ ሆይ፥ መቃብራችሁን በከፈትሁ ጊዜ ከመቃብራችሁም ባወጣኋችሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
\v 14 መንፈሴንም በውስጣችሁ አሳድራለሁ፥ እናንተም በሕይወት ትኖራላችሁ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ ባወቃችሁ ጊዜ በገዛ ምድራችሁም እንድታርፉ አደርጋለሁ። እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ አደርገውማለሁ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 15 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
\v 16 "አንተ፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ አንድ በትር ውሰድና። 'ለይሁዳና ለባልንጀሮቹ ለእስራኤል ልጆች'ብለህ በላዩ ጻፍ። 'ሌላም በትር ውሰድና 'ለኤፍሬም በትር ለዮሴፍና ለባልንጀሮቹ ለእስራኤል ቤት ሁሉ' ብለህ በላዩ ጻፍ።
\v 17 ከዚያም በእጅህ ውስጥ አንድ እንዲሆኑ ሁልቱንም በትሮች በአንድ ላይ ያዛቸው።
\s5
\v 18 ሕዝብህም ፥ 'ይህ የምታደርገው ነገር ምን ማለት እንደሆነ አትነግረንምን? ብለው በተናገሩህ ጊዜ፥
\v 19 አንተ። 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በኤፍሬም እጅ ያለውን የዮሴፍን በትር ባልንጀሮቹንም የእስራኤልን ነገዶች እወስዳለሁ፥ ከይሁዳ በትር ጋር አጋጥማቸዋለሁ አንድ በትርም አደርጋቸዋለሁ፥ በእጄም ውስጥ አንድ ይሆናሉ' በላቸው።
\v 20 የጻፍክባቸውንም በትሮች በዓይናቸው ፊት በእጅህ ያዛቸው።
\s5
\v 21 ከዚያም እንዲህ በላቸው፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የእስራኤልን ልጆች ከሄዱባቸው ከአሕዛብ መካከል የምወስድበት ጊዜ ደርሷል ከአካባቢው አገሮች ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ ወደ ገዛ ምድራቸውም አመጣቸዋለሁ።
\v 22 በምድሪቱም ውስጥ በእስራኤል ተራሮች ላይ አንድ ሕዝብ አደርጋቸዋለሁ፥ አንድ ንጉሥም በሁላቸው ላይ ይነግሣል ከዚያ ወዲያ ሁለት ሕዝብ አይሆኑም፥ ከዚያ ወዲያም ሁለት መንግሥቶች ሆነው አይለዩም።
\v 23 ከዚያ ወዲያም በጣዖቶቻቸውና በርኵሰታቸው በመተላለፋቸውም ሁሉ አይረክሱም፥ ኃጢአትም ከሠሩባት ዓመፅ ሁሉ አድናቸዋለሁ አነጻቸውማለሁ ሕዝብም ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።
\s5
\v 24 ባሪያዬም ዳዊት በላያቸው ይነግሳል። ለሁሉም አንድ እረኛ ይሆንላቸዋል በፍርዴም ይሄዳሉ ትእዛዜንም ይጠብቃሉ ያደርጓትማል።
\v 25 አባቶቻችሁም በኖሩበት ለባሪያዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት ምድር ይኖራሉ እነርሱና ልጆቻቸው የልጅ ልጆቻቸውም ለዘላለም ይኖሩባታል ባሪያዬም ዳዊት ለዘላለም አለቃ ይሆናቸዋል።
\s5
\v 26 ከእነርሱ ጋር የሰላምን ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፥ ከእነርሱም ጋር የዘላለምም ቃል ኪዳን ይሆናል። እኔም አጸናቸዋለሁ አበዛቸውማለሁም መቅደሴንም ለዘላለም በመካከላቸው አኖራለሁ።
\v 27 ማደሪያዬም በእነርሱ ዘንድ ይሆናል፤ ይሆናል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።
\v 28 መቅደሴም ለዘላለም በመካከላቸው በሆነ ጊዜ፥ እኔ እስራኤልን ለራሴ የለየሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ አሕዛብ ያውቃሉ።
\s5
\c 38
\p
\v 1 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
\v 2 "የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን በጎግ ላይና በማጎግ ምድር ላይ፥ በሞሳሕና በቶቤል ዋነኛ አለቃ ላይ አቅናበት፥ ትንቢትም ተናገርበት፥
\v 3 እንዲህም በል፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሞሳሕና የቶቢል ዋነኛ አለቃ ጎግ ሆይ፥ እነሆ፥ እኔ በአንተ ላይ ነኝ።
\s5
\v 4 እመልስህማለሁ በመንጋጋህም ልጓም አገባብሃለሁ፥ አንተንና ሠራዊትህንም ሁሉ፥ ፈረሶችንና ፈረሰኞችን የጦር ልብስ የለበሱትን ሁሉ፥ ጋሻና ራስ ቍርን ሰይፍንም ያያዙትን ሁሉ፥ ታላቁን ወገን አወጣለሁ!
\v 5 ጋሻና የራስ ቍርን የለበሱት ፋርስን ኢትዮጵያና ፉጥ ከእነርሱ ጋር ናቸው!
\v 6 ጋሜርንና ጭፍሮቹን ሁሉ፥ በሰሜን ዳርቻም ያለውን የቴርጋማን ቤትና ጭፍሮቹን ሁሉ፥ ብዙዎች ሕዝቦች ከእነርሱ ጋር ናቸው።
\s5
\v 7 ተዘጋጅ! አዎ፥ ራስህንና ሠራዊትህን አዘጋጅ አለቃም ሁናቸው።
\v 8 ከብዙ ቀናትም በኋላ ትጠራልህ ክተወሰኑ ዓመታት በኋላ ክሠይፍ እያገገመች ወዳለችው፥ ከብዙ ሕዝቦችም መካከል ተሰብስበው ያለማቋረጥ ባድማ በነበሩት በእስራኤል ተራሮች ላይ ዳግም ወደ ተሰበሰቡ ትሄዳለህ። የምድሪቱ ሕዝብ ግን ከሕዝቦች መካከል ወጥተው ሁሉም ሳይፈሩ ይቀመጡባታል።
\v 9 አንተም ትወጣለህ፥ እንደ ዐወሎ ነፋስም ትመጣለህ አንተና ጭፍሮችህ ሁሉ ከአንተም ጋር ብዙ ሕዝብ ምድሪቱን እንደ ደመና ትሸፍናላችሁ።
\s5
\v 10 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ቀን በልብህ ታቅዳለህ፥
\v 11 ክፉ አሳብንም ታስባለህ።' እንዲህም ትላለህ፥ 'ቅጥር ወደሌላቸው መንደሮች እወጣለሁ ተዘልለው ወደሚኖሩ፥ ሁላቸው ሳይፈሩ ያለ ቅጥርና ያለ መወርወሪያ ያለ መዝጊያም ወደሚቀመጡ እገባለሁ
\v 12 ባድማም በነበሩና በቅርቡ ሰዎች በሚኖሩባቸው ስፍራዎች ላይ፥ ከብትና ዕቃንም ይዘው ከአሕዛብም በተሰበሰቡ ሰዎች በምድርም መካከል በሚኖሩ ሕዝብ ላይ እጄን እዘረጋናምርኮን እማርካለሁ ብዝበዛንም እበዘብዛለሁ ።
\s5
\v 13 ሳባና ድዳን የተርሴስም ነጋዴዎች ከወጣት ጦረኞቻችው ሁሉ ጋር እንዲህ ይሉሀል፥ 'የመጣኸው ምርኮን ለመማረክ ነው? ጦርህን የሰበሰብከው ብዝበዛን ለመበዝበዝ ብርንና ወርቅንስ ለመውሰድ፥ ከብትንና ዕቃንስ ለመውሰድ እጅግም ብዙ ምርኮ ለመማረክ ነው?'።
\s5
\v 14 ስለዚህም የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር ጎግንም እንዲህ በለው፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ቀን ሕዝቤ እስራኤል ሳይፈራ በተቀመጠ ጊዜ አንተ ስለእነርሱ አታውቀውምን?
\v 15 አንተም፥ ከአንተም ጋር ብዙ ሕዝብ ሁላቸው በፈረሶች ላይ የተቀመጡ፥ ታላቅ ወገንና ብርቱ ሠራዊት፥ ከሰሜን ዳርቻ ከስፍራችሁ ትመጣላችሁ።
\v 16 ደመና ምድርን እንድሚሸፍን ህዝቤን ታጠቃለህ። ጎግ ሆይ እንዲህ ይሆናል በዓይናቸው ፊት በተቀደስሁብህ ጊዜ አሕዛብ ያውቁኝ ዘንድ በኋለኛው ዘመን በምድሬ ላይ አመጣሃለሁ።
\s5
\v 17 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእነርሱ ላይ እንደማመጣህ በዚያች ዘመን ብዙ ዓመት ትንቢት በተናገሩ በባሪያዎቼ በእስራኤል ነቢያቶች በቀደመው ዘመን ስለ እርሱ የተናገርሁ አንተ አይደለህምን?
\v 18 በዚያም ቀን ጎግ በእስራኤል ምድር ላይ በመጣ ጊዜ መቅሠፍቴ በመዓቴ ይመጣል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\s5
\v 19 በቁጣዬ ትኩሳትና በመዓቴ እሳት ተናግሬአለሁ፥ በእርግጥ በዚያ ቀን በእስራኤል ምድር ጽኑ የምድር መናወጥ ይሆናል።
\v 20 የባሕር ዓሣዎችና የሰማይ ወፎች የምድረ በዳም አራዊት በምድርም ላይ የሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾች ሁሉ በምድርም ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በፊቴ ይንቀጠቀጣሉ። ተራሮችም ይገለባበጣሉ ገደላገደሎችም ይወድቃሉ ቅጥርም ሁሉ ወደ ምድር ይወድቃል።
\s5
\v 21 በተራሮቼም ሁሉ በእርሱ ላይ ሰይፍን እጠራለሁ፥ የሰውም ሁሉ ሰይፍ በወንድሙ ላይ ይሆናል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\v 22 በቸነፈር፥ በደም ፥በዶፍ ዝናብና የድንጋይ እሳት እፈርድባቸዋለሁ። ድኝም በእርሱና በጭፍሮቹ ከእርሱም ጋር ባሉ በብዙ ሕዝብ ላይ አዘንባለሁ።
\v 23 ታላቅነቴንና ቅዱስ መሆኔን አሳያለሁ በብዙ አሕዛብም ዓይን የታወቅሁ እሆናለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
\s5
\c 39
\p
\v 1 አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ በጎግ ላይ ትንቢትን ተናገር እንዲህም በል፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ የሞሳሕና የቶቤል ዋነኛ አለቃ ጎግ ሆይ፥ እነሆ፥ እኔ በአንተ ላይ ነኝ
\v 2 እመልስሃለሁ፥ እነዳህማለሁ፥ ከሰሜንም ዳርቻ እጐትትሃለሁ፥ ወደ እስራኤልም ተራሮች አመጣሃለሁ።
\v 3 ከግራ እጅህም ቀስትህን አስጥልሃለሁ፥ ከቀኝ እጅህም ፍላጾችህን አስረግፍሃለሁ።
\s5
\v 4 የአንተና የጭፍሮች ሁሉ ከአንተም ጋር ያሉ ሠራዊትና ወታደሮች ሬሳ ይገኛል። ለሚናጠቁ ወፎች ሁሉና ለምድር አራዊትም መብል አድርጌ እሰጥሃለሁ።
\v 5 አንተ በምድር ፊት ላይ ትወድቃለህ እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
\v 6 በማጎግም ላይ ሳይፈሩም በደሴቶች በሚቀመጡ ላይ እሳትን እሰድዳለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
\s5
\v 7 ቅዱሱም ስሜ በሕዝቤ በእስራኤል መካከል እንዲታወቅ አደርጋለሁ፥ ቅዱሱንም ስሜን ከእንግዲህ ወዲህ እንዲረክስ አልፈቅድም፤ አሕዛብም እግዚአብሔር፥ የእስራኤል ቅዱስ፥ እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
\v 8 ያልሁት ቀን እነሆ፥ ይመጣል ይሆንማል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር ።
\s5
\v 9 በእስራኤልም ከተሞች የሚኖሩ ይወጣሉ፥ የጦር መሣሪያዎችን፥ አላባሽ ጋሻንና ጋሻን፥ ቀስትንና ፍላጻዎችን፥ ጎመድንና ጦርንም ያቃጥላሉ፥ ለሰባት ዓመት በእሳት ያቃጥሉአቸዋል።
\v 10 በጦር መሣሪያው እሳትን ያነድዳሉ እንጂ እንጨትን ከምድረ በዳ አይወስዱም ከዱርም አይቈርጡም የገፈፉአቸውንም ይገፍፋሉ የበዘበዙአቸውንም ይበዘብዛሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\s5
\v 11 በዚያም ቀን በእስራኤል ዘንድ በባሕር ምሥራቅ የሚያልፉበትን ሸለቆ የመቃብርን ስፍራ ለጎግ እሰጣለሁ፥ የሚያልፉትንም ይከለክላል በዚያም ጎግንና ብዛቱን ሁሉ ይቀብራሉ የሸለቆውንም ስም ሐሞንጎግ ብለው ይጠሩታል።
\s5
\v 12 ምድሩንም ያጸዱ ዘንድ የእስራኤል ቤት ሰዎች ሰባት ወር ይቀብሩአቸዋል፥
\v 13 የምድሪቱም ሰዎች ሁሉ ይቀብሩአቸዋል፥ እኔ የምከብርበት የማይረሳ ቀን ይሆንላችኋል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\s5
\v 14 ምድርንም ለማጽዳት በምድሩ ላይ ወድቀው የቀሩትን የሚቀብሩ፥ ዘወትር በምድሩ ላይ የሚዞሩትን ሰዎች ይመድባሉ ስራውንም ከሰባት ወርም በኋላ ይጀምራሉ።
\v 15 በምድሩ ላይ እንዲዞሩ የተመደቡት በሚያልፉብት ጊዜ የሰውን አጥንት ካዩ ፥ ቀባሪዎች መጥተው በሐሞን ጎግ ሸለቆ እስኪቀብሩት ድረስ ምልክት አድርገው ያልፋሉ።
\v 16 ስሟ ሐሞና የሚሰኝ ከተማ በዚያ ትገኛለች። በዚህ መንገድ ምድሪቱን ያጸዳሉ።
\s5
\v 17 አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለወፎች ሁሉና ለምድር አራዊት ሁሉ እንዲህ በላቸው፥ 'ኑ፥ ተከማቹ፥ ሥጋንም ትበሉ ዘንድ ደምንም ትጠጡ ዘንድ በእስራኤል ተራሮች ላይ ወደማርድላችሁ ታላቅ መሥዋዕት፥ ከየስፍራው ሁሉ ተሰብሰቡ።
\v 18 የኃያላኑን ሥጋ ትበላላችሁ የምድርንም አለቆች፥ የአውራ በጎችንና የጠቦቶችን፥ የፍየሎችንና የወይፈኖችን፥ የባሳንን ፍሪዳዎች ሁሉ፥ ደም ትጠጣላችሁ።
\s5
\v 19 እኔም ከማርድላችሁ መሥዋዕት እስክትጠግቡ ድረስ ጮማ ትበላላችሁ እስክትሰክሩም ድረስ ደም ትጠጣላችሁ።
\v 20 በሰደቃዬም ከፈረሶችና ከፈረሰኞች፥ ከኃያላንና ከሰልፈኞች ሁሉ ትጠግባላችሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\v 21 ክብሬንም በአሕዛብ መካከል አኖራለሁ አሕዛብም ሁሉ ያደርግሁትን ፍርዴን፥ በላያቸውም ያኖርኋትን እጄን ያያሉ።
\v 22 ከእንግዲህም ወዲያ የእስራኤል ቤት እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
\s5
\v 23 አሕዛብም የእስራኤል ቤት እኔን ባቃለሉበት በኃጢአታቸው ምክንያት እንደ ተማረኩ ያውቃሉ፥ ስለ በደሉኝ እኔም ፊቴን ከእነርሱ ስለ ሸሸግሁ፥ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ ሰጠኋቸው፥ እነርሱም ሁሉ በሰይፍ ወደቁ።
\v 24 እንደ ርኵሰታቸውም እንደ መተላለፋቸውም መጠን አደረግሁባቸው ፊቴንም ከእነርሱ ሸሸግሁ።
\s5
\v 25 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አሁን የያዕቆብን ምርኮ እመልሳለሁ ለእስራኤልም ቤት ሁሉ እራራለሁ፥ ስለ ቅዱስ ስሜም እቀናለሁ።
\v 26 እፍረታቸውንና እኔን የካዱበትን ክህደት ይረሳሉ። ማንም ሳያስፈራቸው በምድራቸው ተዘልለው በተቀመጡ ጊዜ እነዚህን ነገሮች ሁሉ ይረሳሉ።
\v 27 ከአሕዛብም ዘንድ በመለስኋቸው ጊዜ ከጠላቶቻቸውም ምድር በሰበሰብኋቸው ጊዜ በብዙ አሕዛብም ፊት እቀደሳለሁ።
\s5
\v 28 እኔም ወደ አሕዛብ አስማርኬአቸዋለሁና፥ ወደ ገዛ ምድራቸውም ሰብስቤአቸዋለሁና እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። ከእነርሱም አንድንም ሰው በአሕዛብ መካከል አልተውኩም።
\v 29 ፊቴንም ከእነርሱ ከእንግዲህ ወዲህ አልሸሽግም መንፈሴን በእስራኤል ቤት ላይ አፍስሻለሁና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\c 40
\p
\v 1 በተማረክን በሀያ አምስተኛው ዓመት በዓመቱ መጀመሪያ ከወሩ በአሥረኛው ቀን፥ ከተማይቱ ከተመታች በኋላ በአሥራ አራተኛው ዓመት፥ በዚያው ቀን የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ነበረ እርሱም ወደዚያ ወሰደኝ።
\v 2 በእግዚአብሔር ራእይ ወደ እስራኤል ምድር አመጣኝ እጅግም በረዘመ ተራራ ላይ አኖረኝ፥ በዚያም ላይ በደቡብ ወገን እንደ ከተማ ሆኖ የተሠራ ነገር ነበረ።
\s5
\v 3 ወደዚያም አመጣኝ፥ እነሆም፥ መልኩ እንደ ናስ መልክ የመሰለ አንድ ሰው በዚያ ነበረ፥ በእጁም የተልባ እግር ገመድና የመለኪያ ዘንግ ነበረ እርሱም በከተማይቱ በር አጠገብ ቆሞ ነበር።
\v 4 ሰውዬውም፥ "የሰው ልጅ ሆይ፥ ወደዚህ ያመጣሁህ ይህን ላሳይህ ስለሆን በዓይንህ እይ በጆሮህም ስማ በማሳይህም ሁሉ ላይ ልብ በል የምታየውንም ሁሉ ለእስራኤል ቤት ንገር አለኝ።
\s5
\v 5 እነሆም፥ በቤተመቅደሱ ዙሪያው ቅጥር ነበረ፥ በሰውዬውም እጅ ርዝመቱ ስድስት ክንድ የሆነ የመለኪያ ዘንግ ነበር። እያንዳንዱም ክንድ አንድ ክንድ ከስንዝር ነበረ። ሰውዬውም ቅጥሩን ለካ፤ የቅጥሩም ስፋት አንድ ዘንግ ቁመቱንም አንድ ዘንግ ነበረ።
\v 6 ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተውም በር ሄዶ በደረጃዎቹ ወጣ፥ የመድረኩንም ወለል ለካ፥ ወርዱን አንድ ዘንግ ነበር።
\v 7 የዘበኞቹም ጓዳ ሁሉ ርዝመቱ አንድ ዘንግ፥ ወርዱም አንድ ዘንግ ነበረ በዘበኞቹም ጓዳዎች መካከል አምስት ክንድ ርቀት ነበረ በበሩም ደጀ ሰላም በስተ ውስጥ በኩል የሚገኝ የበሩ የመድረክ ወለል አንድ ዘንግ ነበረ።
\s5
\v 8 የበሩን መተላለፊያ ደጅ ለካ ርዝመቱም አንድ ዘንግ ነበር።
\v 9 የበሩን መተላለፊያ ደጅ ለካ፥ ጥልቀቱ አንድ ዘንግ ነበረ። የግንቡንም አዕማድ ወርድ ሁለት ክንድ ነበረ። አድርጎ ለካ ።ይህም በቤተመቅደሱ ትይዩ የሚገኘው ድጅ መተላለፊያ ነበረ።
\v 10 በበሩ አጠገብ የሚገኙት የዘበኛ ጓዳዎች በበሩ በሁለቱም በኩል ሦስት ሦስት ነበሩ፥ የሁሉም መጠን እኩል ነበረ በሁሉም አቅጣጫ የሚለያቸው ግንብም እኩል መጠን ነበረው።
\s5
\v 11 ቀጥሎም ሰውዬው የበሩን መግቢያ ወርድ ለካ አሥር ክንድ ሆነ፤ የበሩንም መግቢያ ርዝመት ለካ አሥራ ሦስት ክንድ ሆነ።
\v 12 በእያንዳንዱ በዘበኛ ጓዳ ፊት ከፍታው አንድ ክንድ የሆነ መከለያ ነበረ። የዘበኛ ጓዳዎቹም በሁሉም አቅጣጫ ስድስት ክንድ ከፍታ ነበራቸው።
\v 13 ከአንዱም የዘበኛ ጓዳ ደርብ ጀምሮ እስከ ሌላው ደርብ ድረስ የበሩን ወርድ ሀያ አምስት ክንድ ለካ ይህም ከመጀምሪያው የዘበኞች ጓዳ መግቢያ እስከ ሌላኛው መግቢያ ድረስ ነው።
\s5
\v 14 ቀጥሎም በዘበኞች ጓዳ መካከል የሚያልፈውን ግንብ ለካ፤ ስድስት ክንድም ሆነ። እስከ መግቢያው መተላለፊያ ድረስ ለካ ።
\v 15 ከበሩም መግቢያ ፊት ጀምሮ እስከ ውስጠኛው የበሩ መተላለፊያ መጨረሻ ድረስ አምሳ ክንድ ነበረ።
\v 16 በዘበኛ ጓዳዎቹም በበሩ ውስጥ በዙሪያው በነበሩትም በግንቡ አዕማድ ትንንሽ መስኮቶች ነበሩዋቸው። በበሩም ደጅ መተላለፊያ እንደዚያው ነበር። ሁሉም መስኮቶች በውስጥ በኩል ነበሩ። በግንቡም አዕማድ ሁሉ ላይ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾባቸው ነበር።
\s5
\v 17 ቀጥሎም ሰውዬው ወደ ውጭውም አደባባይ አመጣኝ። እነሆም፥ በአደባባዩ ዙሪያ ክፍሎችና ወለል ነበሩ። በወለሉም ላይ ሠላሳ ክፍሎች ነበሩ።
\v 18 ወለሉም እስከ በሮቹ ይደርስ ነበር ስፋቱም እንደ በሮቹ ርዝመት መጠን ነበረ። ይህም ታችኛው ወለል ነበር።
\v 19 ከታችኛውም በር ፊት ጀምሮ እስከ ውስጠኛው በር ፊት ድረስ ያለውን ርቀት ለካ፤ በምስራቅ በኩል አንድ መቶ ክንድ በሰሜኑም በኩል ተመሳሳይ ነበረ።
\s5
\v 20 ቀጥሎም ከውጭው አደባባይ በሰሜን በኩል ያለውን በር ርዝመትና ስፋት ለካ።
\v 21 በበሩ በዚህና በዚያ የዘበኛ ጓዳዎቹም ነበሩ፥ በሩና መተላለፊያው ከዋናው በር ልኬታቸው እኩል ነበር- ርዝመቱ አምሳ ክንድ ወርዱም ሀያ አምስት ክንድ ነበረ።
\s5
\v 22 መስኮቶቹም ፥መተላለፊያዎቹና የዘንባባ ዛፎቹ ወደ ምሥራቅ እንደሚመለከተው በር ጋር ይዋሰኑ ነበር። ወደ እርሱና ወደ መተላለፊያዎቹ የሚያደርሱ ሰባት ደረጃዎች ነበሩ።
\v 23 በውስጠኛውም አደባባይ በሰሜኑና በምሥራቁ በኩል በሌላው በር አንጻር በር ነበረ፤ ሰውዬውም ከአንዱ በር እስከ በር ድረስ ለካ። ርቀቱም አንድ መቶ ክንድ ነበር።
\s5
\v 24 ቀጥሎም ሰውዬው ወደ ደቡቡ መግቢያ አመጣኝ፥ እነሆም፥ ግንቡና መተላለፊያዎቹ ከሌላኛው መውጪያው በር ጋር እኩል ልኬት ነበራቸው።
\v 25 በመግቢያውና በመተላለፊያዎቹ እንደዚያኛው በር አይነት ትንንሽ መስኮቶች ነበሩዋቸው። የድቡቡ በርና መተላልፊያው ርዝመቱ አምሳ ክንድ ወርዱም ሀያ አምስት ክንድ ነበረ።
\s5
\v 26 ወደ በሩና መተላለፊያዎቹ የሚያደርሱ ሰባት ደረጃዎች ነበሩ፥ በግንቡም አዕማድ ላይ በሁለቱም ወገን የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾባቸው ነበር።
\v 27 በደቡብ በኩል ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያስገባ መግቢያ ነበረ፥ ሰውዬውም ከዚህኛው በር እስከ ደቡቡ መግቢያ ድረስ ለካ፥ ርቀቱ መቶ ክንድ ነበረ።
\s5
\v 28 ቀጥሎም ሰውዬው ከሌላኛው በር እኩል ልኬት ባለው በደቡብ በር በኩል ወደ ውስጠኛው አደባባይ አገባኝ ።
\v 29 የዘበኛ ጓዳዎቹንና የግንቡን አዕማድና መተላለፊያዎቹ ከመጀመሪያዎቹ መግቢያዎች እኩል ነበሩ፤ በመተላለፊያዎቹ ዙሪያ መስኮቶች ነበሩ።ውስጠኛው መግቢያና መተላለፊያው ርዝመቱ አምሳ ክንድ ወርዱም ሀያ አምስት ክንድ ነበረ።
\v 30 በውስጠኛው ግንብ ዙሪያውም መተላለፊያዎች ነበሩ። ርዝመታቸውም ሀያ አምስት ክንድ ወርዳቸውም አምስት ክንድ ነበረ።
\v 31 መተላለፊያዎቹም ወደ ውጭው አደባባይ ይመለከቱ ነበር በግንቡም አዕማድ ላይ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾ ነበር ወደ እርሱም የሚያደርሱ ስምንት ደረጃዎች ነበሩ።
\s5
\v 32 ቀጥሎም ከሌሎቹ መግቢያዎች እኩል ልኬት ባለው በምስራቁ በር በኩል ወደ ውስጠኛው አደባባይ አገባኝ።
\v 33 የዘበኛ ጓዳዎቹንና የግንቡን አዕማድ መተላለፊያዎቹ ሌኬታቸው ከሌሎቹ መግቢያዎች እኩል ነበር በዙሪያም መስኮቶች ነበሩ። መግቢያውና መተላልፊያው ርዝመቱም አምሳ ክንድ ወርዱም ሀያ አምስት ክንድ ነበረ።
\v 34 መተላለፊያዎቹም በስተ ውጭ ወዳለው አደባባይ ይመለከቱ ነበር በግንቡም አዕማድ ላይ በዚህና በዚያ ወገን የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾ ነበር ወደ እርሱም የሚያደርሱ ስምንት ደረጃዎች ነበሩት።
\s5
\v 35 በሰሜንም ወዳለው በር አመጣኝ፥ በሩንም ለካው፤ ልኬቱም ከሌሎቹ በሮች እኩል ነበር።
\v 36 የዘበኛ ጓዳዎቹንና የግንቡን አዕማድ መተላለፊያዎቹ ልኬታቸው ከሌሎቹ በሮች እኩል ነበር በዙሪያውም መስኮቶች ነበሩ። ርዝመቱም አምሳ ክንድ ወርዱም ሀያ አምስት ክንድ ነበረ።
\v 37 መተላለፊያውም ወደ ውጭው አደባባይ ይመለከቱ ነበር በግንቡም አዕማድ ላይ በዚህና በዚያ ወገን የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾ ነበር ወደ እርሱም የሚያደርሱ ስምንት ደረጃዎች ነበሩት።
\s5
\v 38 በእያንዳኔዱ ውስጠኛ መግቢያ በር ያላቸው ክፍሎች ነበሩ። ይህም የሚቃጠለውን መሥዋዕት የሚያጥቡበትነበር።
\v 39 የሚቃጠለውንም መሥዋዕት የኃጢአቱንና የበደሉንም መሥዋዕት ያርዱባቸው ዘንድ፥ በበሩ መተላለፊያ በዚህ ወገን ሁለት ገበታዎች፥ በዚያም ወገን ሁለት ገበታዎች ነበሩ።
\s5
\v 40 በሰሜን በኩል ባለው በር በስተ ውጭው፥ በመወጣጫው ደረጃዎች አጠገብ፥ በአንድ ወገን ሁለት ገበታዎች ነበሩ፥ በሌላውም ወገን በበሩ መተላለፊያ በኩል ሁለት ገበታዎች ነበሩ።
\v 41 በበሩ በሁለቱም ወገን አራት ገበታዎች ነበሩ፤ በስምንቱም ገበታዎች እንስሳትን ይሰው ነበር።
\s5
\v 42 ለሚቃጠለውም መሥዋዕት ርዝመታቸው አነድ ክንድ ተኩል ወርዳቸውም አንድ ክንድ ተኩል ቁመታቸውም አንድ ክንድ የሆኑ ከተጠረበ ድንጋይ የተሠሩ አራት ገበታዎች ነበሩ። በእነርሱም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕቱን የሚያርዱበትን መሳሪያ ያኖሩባቸው ነበር።
\v 43 በዙሪያውም በመተላለፊያው አንድ ጋት የሚርዝም መስቀያዎችነበሩ፥ የመስዋዕቱም ሥጋ የሆነ ክፈፍ በገበታዎቹም ላይ ይቀመጡ ነበር።
\s5
\v 44 በውስጠኛው አደባባይ ከውስጠኛው መግቢያም አጠገብ የዘማሪያን ክፍሎች ነበሩ። ከክልሎቹ አንዱ በሰሜን በኩል ነበረ፥ ሌላውም በስተደቡብ ነበረ።
\v 45 ሰውዬውም፥ "ይህ ወደ ደቡብ የሚመለከት ቤት በመቅደሱ ውስጥ ለማገልገል ተረኛ ለሆኑለሚተጉ ካህናት ነው።
\s5
\v 46 ወደ ሰሜንም የሚመለከተው ቤት በመሠዊያው ዙሪያ ለሚያገለግሉ ካህናት ነው። እነዚህ ከሌዊ ልጆች መካከል ያገለግሉት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡ የሳዶቅ ልጆች ናቸው" አለኝ።
\v 47 ቀጥሎም አደባባዩን ለካ፥ አራት ማዕዘን ሆኖ ርዝመቱን መቶ ክንድ ወርዱንም መቶ ክንድ ነበረ መሠዊያውም በቤቱ ፊት ነበረ።
\s5
\v 48 ከዚያም ሰውዬው ወደ ቤቱ መተላለፊያ አመጣኝ፥ የግንብ አዕማዱንም ለካ፤ ወርድ በዚህ ወገን አምስት ክንድ በዚያም ወገን አምስት ክንድ ነበረ። መግቢያው ራሱ ወርዱ አሥራ አራት ክንድ ነበረ፥ በበሩም በዚህ ወገንና በዚያ ወገን የነበሩት ግንቦች ስፋት ሦስት ሦስት ክንድ ነበር።
\v 49 የቤተ መቅደሱ መተላለፊያ ርዝመት ሀያ ክንድ ወርዱም አሥራ ሁለት ክንድ ነበረ። ወደ እርሱም የሚያደርሱ ደረጃዎች በሁለቱም አቅጣጫ የቆሙ አዕማድ ነበሩ።
\s5
\c 41
\p
\v 1 ከዚያም ሰውዬው ወደ መቅደሱም ቅዱስ ስፍራ አገባኝ፥ የግንቡንም አዕማድ ወርድ በዚህ ወገን ስድስት ክንድ በዚያም ወገን ስድስት ክንድ አድርጎ ለካ።
\v 2 የመግቢያውም ወርድ አሥር ክንድ ነበረ፥ የመግቢያውም መቃኖች በዚህ ወገን አምስት ክንድ በዚያም ወገን አምስት ክንድ ነበሩ።ቀጥሎም ሰውዬው ቅዱስ ስፍራውን ርዝመቱ አርባ ክንድ ወርዱም ሀያ ክንድአድርጎ ለካ።
\s5
\v 3 ከዚያም ሰውዬው ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ገባ፥ የመግቢያውንም የግንብ አዕማድ ወርድ ሁለት ክንድ አድርጎ ለካ የመግቢያውም ወርድ ስድስት ክንድ ነበረ። የመግቢያውም ግንብ ወርድ በዚህ ወገን ሰባት ክንድ በዚያም ወገን ሰባት ክንድ ነበረ።
\v 4 የክፍሉንም ርዝመት ወደ መቅደሱ ፊት ለፊት ሀያ ክንድ ወርዱንም ሀያ ክንድ አድርጎ ለካና፥ "ይህ ቅድስተ ቅዱሳን ነው" አለኝ።
\s5
\v 5 የመቅደሱንም ግንብ ስድስት ክንድ አድርጎ። በመቅደሱም ዙሪያ ሁሉ ያሉትን የጓዳዎቹን ሁሉ ወርድ አራት ክንድ ነበረ።
\v 6 ጓዳዎቹም አንዱ ከአንዱ በላይ በሦስት ደርብ ነበሩ፥ በእያንዳንዱም ደርብ ሠላሳ ጓዳዎች ነበሩ። በመቅደሱም ግንብ ዙሪያ ድጋፍ የሆኑ መደርደሪያዎች ነበሩ፥ ምክንያቱም በመቅደሱ ግንብ ውስጥ ድጋፎች አልነበሩም።
\v 7 ላይኞቹ ጓዳዎች ከታችኞቹ ጓዳዎች ይበልጡ ነበር ከታችኛውም ደርብ ወደ መካከለኛው ከመካከለኛውም ደርብ ወደ ላይኛው የሚወጣበት ደረጃ ነበረ።
\s5
\v 8 በመቅደሱም ዙሪያ የጓዳዎቹም መሠረት የሆነ ከፍ ያለ ወለል እንዳለ አየሁ ቁመቱም ሙሉ ዘንግ የሚያህል ስድስት ክንድ ነበረ።
\v 9 የጓዳዎቹም የውጭው ግንብ ውፍረት አምስት ክንድ ነበረ። በመቅደሱም ጓዳዎች ውጭ የቀረ አንድ ባዶ ስፍራ ነበረ።
\s5
\v 10 በዚህም ባዶ ስፍራ በአንድ ወገን የካህናት በረንዳዎች ነበሩ፤ የባዶውም ስፍራ ወርድ በዙሪያ አምስት ክንድ ነበረ። ይህም ባዶ ሥፍራ በመቅደሱ ዙሪያ ወርዱ ሀያ ክንድ ነበረ።
\v 11 በዚህም በባዶው ስፍራ አንዱ በሰሜን በኩል አንዱም በደቡብ በኩል የጓዳዎች መግቢያ ነበረ። የባዶውም ስፍራ ዙሪያ ወርድ አምስት ክንድ ነበረ።
\s5
\v 12 በምዕራብም በኩል ባለው ግቢ አንጻር ያለው ህንጻ ስፋቱ ሰባ ክንድ ነበረ። በግቢውም ዙሪያ የነበረ ግንብ ውፍረቱ አምስት ክንድ ርዝመቱም ዘጠና ክንድ ነበረ።
\v 13 የመቅደሱንም ርዝመት መቶ ክንድ፥ የልዩውን ስፍራና ግቢውን ከግንቡ ጋር አንድ መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።
\v 14 ደግሞም ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት የሚገኘው ግቢ የፊት ለፊት ወርዱ አንድ መቶ ክንድ ነበር።
\s5
\v 15 ቀጥሎም ሰውዬው ከቤተ መቅደሱ በስተዋላ ያለውን ህንጻ የምዕራብ ክፍል በዚህና በዚያ ከነበሩት ፎቆች ጋር እንዲሁም ቅዱስ ስፍራውና መድረኩን አንድ መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።
\v 16 ውስጠኛዎቹ ግድግዳዎች፥ ጠባቦቹን ጨምሮ መስኮቶቹ እንዲሁም በሶስት ደረጃዎች ያሉ ፎቆች በእንጨት ተለብጠው ነበር።
\v 17 ከደጁም በላይ እስከ ውስጠኛው ክፍል ድረስ፥ በውጭም ግንቡ ሁሉ ውስጡም ውጭውም ተለብጦ ነበር።
\s5
\v 18 በኪሩቤልና በዘንባባ ዛፎች ተውቦ ነበር የዘንባባውም ዛፍ ከኪሩብና ከኪሩብ መካከል ነበረ እያንዳንዱም ኪሩብ ሁለት ፊት ነበረው።
\v 19 የሰው ፊት የሚመስለው በአንድ ወገን ወዳለው የዘንባባ ዛፍ ይመለከት ነበር፥ የአንበሳ ፊት የሚመስለው ደግሞ በሌላ ወገን ወዳለው የዘንባባ ዛፍ ይመለከት ነበር። ይህም በዙሪያ ያሉትን ቤቶች አስውቦ ነበር።
\v 20 ከመሬት አንሥቶ እስከ ደጁ አናት ድረስ እና በመቅደሱ ላይ በኪሩቤልና በዘንባባ ዛፎች ተውበው ነበር።
\s5
\v 21 የመቅደሱ መቃኖችም አራት ማዕዘን ነበሩ፥ ሁሉም ለእርስ በእርስ ትይዩ ነበሩ።
\v 22 ከቅዱሱ ሥፍራ ፊት ለፊት የሚገኘው ከእንጨት የተሰራው መስዋዕት ቁመቱ ሦስት ክንድ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ወርዱም ሁለት ክንድ ነበር። ማዕዘኖቹም እግሩም አገዳዎቹም ከእንጨት ተሠርተው ነበር። ሰውዬውም ፥ "ይህች በእግዚአብሔር ፊት ያለችው ገበታ ናት" አለኝ።
\v 23 ለተቀደሰው ስፍራና ለቅድስተ ቅዱሳኑ ሁለት መዝጊያዎች ነበሩአቸው።
\v 24 ለእያንዳንዱ መዝጊያም ሁለት ተዘዋዋሪ ሳንቃዎች ነበሩት ለአንዱ መዝጊያ ሁለት ለሌላውም መዝጊያ ሁለት ሳንቃዎች ነበሩት።
\s5
\v 25 ግንቦቹን እንዳስዋቡት ዓይነት በእነዚህ በቅዱስ ስፍራው መዝጊያዎች ላይ ኪሩቤልና የዘንባባ ዛፎች ተቀርጸው ነበር፣ በስተ ውጭም ባለው በደጀ ሰላሙ ፊት የእንጨት ጣራ ነበረ።
\v 26 በደጀ ሰላሙም በሁለቱ ወገን በዚህና በዚያ ጠባብ መስኮቶችና የተቀረጹ የዘንባባ ዛፎች ነበሩበት። እነዚህም የመቅደሱም ጓዳዎች ነበሩ ፥ እነርሱም ተንጠልጣይ ጣሪያዎችም ነበሯቸው።
\s5
\c 42
\p
\v 1 በመቀጠልም ሰውዬው በውጭ በሰሜን አቅጣጫ ወደሚገኘው አደባባይ አወጣኝ፥ በልዩውም ስፍራ አንጻርና በሰሜን በኩል ባለው ግቢ ፊት ለፊት ወዳሉ ክፍሎች አመጣኝ ።
\v 2 ክፍሎቹም በፊት ለፊት ገጽታቸው መቶ ክንድ ስፋታቸውም አምሳ ክንድ ነበረ።
\v 3 ከእነዚህ ክፍሎች አንዳንዶቹ ፊታቸው ወደ ግቢው ወስጥ ነበር ከቤተመቅደሱም ሃያ ክንድ ይርቁ ነበር። ባለ ሶስት ደርብ ክፍሎችም ነበሩ። ከላይ ያለው ክፍል ወደታችኛው ክፍሎች ይመለከትና ለእነርሱ ክፍት ነበር መላለፊያ መንገድም ነበረው። የተወሰኑት ክፍሎች ወደ ወደውጪኛው አደባባይ ይመለከቱ ነበረ።
\s5
\v 4 ከክፍሎቹም ፊት በስተ ውስጥ ወርዱ አሥር ክንድ ርዝመቱ መቶ ክንድ የሆነ መተላለፊያ ነበረ። የክፍሎቹም መዝጊያዎች ወደ ሰሜን ይመለከቱ ነበር።
\v 5 ነገር ግን መተላለፊያው ከህንጻው መካከለኛና ከታችኛው ክፍል በላይ ቦታቸውን የያዘ በመሆኑ የላይኞቹ ክፍሎች ትንንሽ ነበሩ።
\v 6 በሦስት ደርብ በመስራታቸውና በአደባባዩም እንዳሉት አዕማድ ያሉ፥ አዕማድ ስላልነበሯቸው ላይኞቹ ደርቦች ከመካከለኞቹና ከታችኞቹ ይልቅ ጠባብ ነበሩ
\s5
\v 7 የውጪው ግንብ ከክፍሎቹና ከክፍሎቹ ፊት ለፊት ከሚገኘው ክውጭው አደባባይ ትይዩ ይገኛል ፥ ርዝመቱም አምሳ ክንድ ነበረ።
\v 8 በውጪኛው አደባባይ ርዝመቱ ሃምሳ ክንድ ሲሆን በመቅደሱ ፊት የነበሩት ክፍሎች ደግሞ ርዝመታቸው መቶ ክንድ ነበረ።
\v 9 ከእነዚህም ዕቃ ቤቶች በታች በስተ ምሥራቅ በኩል፥ ከውጭው አደባባይ የሚጀምር መግቢያ ነበረ።
\s5
\v 10 በምስራቅ በኩል የውጭውን አደባባይ ተከትሎ ከቤተመቅደሱ ውስጠኛ አደባባይ ፊት ለፊት ክፍሎች ነበሩ።
\v 11 በስተ ፊታቸውም የነበረ መንገድ በርዝመቱና በወርዱ በሰሜን በኩል ከነበሩት ክፍሎች ጋር ተመሳሳይ ሲሆን መግቢያዎቻቸውም በቁጥር እኩል ነበሩ።
\v 12 በደቡብም በኩል ልክ በሰሜን በኩል እንዳለው ወደ ክፍሎቹ የሚያስገቡ መግቢያዎች አሉ። በውስጥ በኩል ያለው መተላለፊያ ከበላዩ መግቢያ ያለው ሲሆን መተላለፊያው ወደተለያዩ ክፍሎች ያመሩ ነበር። በምስራቅ በኩል ወደ መተላለፊያው አንደኛው ጫፍ የሚያመራ መግቢያ ነበር።
\s5
\v 13 ከዚያም እንዲህም አለኝ፥ "በውጭኛው አደባባይ ፊት ለፊት የሚገኙት የሰሜንና የደቡብ ክፍሎች ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡ ካህናት ከሁሉ ይልቅ የተቀደሰውን ምግብ የሚበሉባቸው የተቀደሱ ክፍሎች ናቸው። ስፍራው ቅዱስ ስለሆን በዚያ የተቀደሰውን ነገር የእህሉን ቍርባን የኃጢአቱንና የበደሉን መሥዋዕት ያስቀምጣሉ።
\v 14 ካህናቱም አንድ ጊዜ ወደዚያ ከገቡ ሲያገለግሉ የሚለብሷቸው ልብሶች ቅዱስ በመሆናቸው ሳያወልቁ ከተቀደሰው ሥፍራ ወደውጭኛው አደባባይ መውጣት የለባቸውም። ስለዚህም ወደ ሕዝቡ ከመጠጋታቸው በፊት ሌላ ልብስ መልበስ አለባቸው።
\s5
\v 15 ውስጠኛውንም ቤት ለክቶ በፈጸመ ጊዜ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከት በር አወጣኝና ዙሪያውን ሁሉ ለካ።
\s5
\v 16 የምሥራቁን ወገን በመለኪያ ዘንግ አምስት መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።
\v 17 የሰሜኑንም ወገን በመለኪያ ዘንግ አምስት መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።
\v 18 የደቡቡንም ወገን በመለኪያ ዘንግ አምስት መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።
\v 19 ዞረም፥ የምዕራቡንም ወገን በመለኪያ ዘንግ አምስት መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።
\s5
\v 20 በአራቱ ወገን ለካው። የተቀደሰውንና ያልተቀደሰውን ይለይ ዘንድ ርዝመቱ አምስት መቶ ክንድ ወርዱም አምስት መቶ ክንድ የሆነ ቅጥር በዙሪያው ነበረ።
\s5
\c 43
\p
\v 1 ወደ ምሥራቅም ወደሚመለከተው በር አመጣኝ።
\v 2 እነሆም፥ የእስራኤል አምላክ ክብር ከምሥራቅ በኩል መጣ፤ ድምፁም እንደ ብዙ ውኆች ያለ ነበር፥ ከክብሩም የተነሣ ምድር ታበራ ነበር።
\s5
\v 3 ያየሁትም ራእይ ከተማይቱን ለማጥፋት በመጣ ጊዜ እንዳየሁትና በኮበር ወንዝ እንዳየሁት አይነት ራእይ ነበረ- እኔም በግምባሬ ተደፋሁ!
\v 4 የእግዚአብሔርም ክብር ወደ ምሥራቅ በሚመለከት በር ወደ መቅደሱ ገባ።
\v 5 መንፈሱም አነሣኝ ወደ ውስጠኛውም አደባባይ አገባኝ እነሆም፥ የእግዚአብሔር ክብር መቅደሱን ሞልቶት ነበር።
\s5
\v 6 ሰውዬው በአጠገቤ ቆሞ ሳለ ከመቅደሱ ውስጥ የሚናገረኝን ሌላ ሰው ሰማሁ።
\v 7 እንዲህም አለኝ፥ "የሰው ልጅ ሆይ፥ ይህ በእስራኤል ልጆች መካከል ለዘላለም የምቀመጥበት የዙፋኔ ስፍራና የእግሬ ጫማ መረገጫ ነው፤ ዳግመኛም የእስራኤል ቤትና ነገሥታቶቻቸው በግልሙትናቸውና በጣዖት ማምለኪያ ቦታዎቻቸው ባለው በነገሥታቶቻቸው ሬሳ ቅዱስ ስሜን አያረክሱም፡፡
\v 8 ከእንግዲህ ግንብ ብቻ በመካከል በማድርግ የጣዖቶቻቸውን መድረክ በመድረኬ አጠገብ፥ የጣዖቶቻቸውን መቃኖች በመቃኔ አጠገብ በማስቀመጥ ቅዱስ ስሜን አያረክሱም። በሠሩትም ርኵሰት ቅዱስ ስሜን አረከሱ ስለዚህ በቍጣዬ አጠፋኋቸው።
\s5
\v 9 አሁንም ግልሙትናቸውንና የነገሥታቶቻቸውን ሬሳ ከፊቴ ያርቁ፥ እኔም ለዘላለም በመካከላቸው አድራለሁ!
\s5
\v 10 አንተም የሰው ልጅ፥ ከኃጢአታቸው የተነሣ ያፍሩ ዘንድ ለእስራኤል ቤት ራስህ ልትነግራቸው ይገባል። ስለዚህ የቤቱ ዝርዝር መግለጫ ማሰብ አለባቸው።
\v 11 ከሠሩትም ሥራ ሁሉ የተነሣ ቢያፍሩ፥ የቤቱን መልክና ምሳሌውን መውጫውንም መግቢያውንም ሥርዓቱንም ሕጉንም ሁሉ አስታውቃቸው። የቤቱን አሰራርና ሕጉን ሁሉ ይጠብቁ ዘንድ ያደርጉትም ዘንድ በፊታቸው ጻፈው።
\s5
\v 12 የቤቱ ሥርዓት ይህ ነው፡ ከተራራው ራስ ጅምሮ በዙሪያው ያለ ዳርቻ ሁሉ እጅግ የተቀደስ ይሆናል። አስተውል! የቤቱ ሥርዓት ይህ ነው።
\s5
\v 13 የመሠዊያውም ልክ በረጅም ክንድ ይህ ነው፥ ይህም ማለት አንድ ክንድ ከጋት ነው። በመሰዊያው ዙሪያ ያለው አሸንዳ ቁመቱ አንድ ክንድ ወርዱም አንድ ክንድ ነው። የዙሪያው ጠርዝ አንድ ስንዝር ነው። ይህም የመሰዊያው መሠረት ነው።
\v 14 በመሬቱም ላይ ካለው አሸንዳ ጀምሮ እስከ ታችኛው የመስዊያው እርከን ድረስ ሁለት ክንድ ወርዱም አንድ ክንድ ነው። ከመሰዊያው ትንሹ ጠርዝ እስከ ትልቁ ጠርዝ ድረስ አራት ክንድ፥ የሰፊው ጠርዝ ስፋትም አንድ ክንድ ነው።
\s5
\v 15 ለሚቃጠል መስዋዕት የሚያገለግለው በመሰዊያው ላይ ያለው ምድጃ አራት ክንድ ነው፥ በምድጃውም ላይ ጫፋቸው ወደላይ የቆመ ቀንዶች አሉበት።
\v 16 ምድጃውም አራት ማዕዘን ሆኖ ርዝመት አሥራ ሁለት ክንድ ወርዱም አሥራ ሁለት ክንድ ነው።
\v 17 ጠርዙም በአራቱም ማዕዘን አሥራ አራት ክንድ ወርዱም አሥራ አራት ክንድ ነው፥ በዙሪያውም ያለው ክፈፍ ግማሽ ክንድ ነው። አሽንዳውም ወደምስራቅ ከሚያመለክቱት ደረጃዎቹ ጋር ዙሪያውን አንድ ክንድ ነው።
\s5
\v 18 ቀጥሎም እንዲህ አለኝ፥ "የሰው ልጅ ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያቀርቡበት ዘንድ ደሙንም ይረጩበት ዘንድ መሰዊያውን በሚሠሩበት ቀን የመሠዊያው ሕግ ይህ ነው።
\v 19 ያገለግሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ለሚቀርቡ ከሳዶቅ ዘር ለሚሆኑ ለሌዋውያኑ ካህናት ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን ትሰጣቸዋለህ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\s5
\v 20 ከደሙም ትወስዳለህ፥ በአራቱ ቀንዶቹም በእርከኑም በአራቱ ማዕዘን ላይ በዙሪያውም ባለው ክፈፍ ላይ ትረጨዋለህ እንዲሁ ታነጻዋለህ ታስተሰርይለትማለህ።
\v 21 ለኃጢአትም መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን ትወስዳለህ፥ በመቅደሱም ውጭ በተዘጋጀለት ስፍራ ታቃጥለዋለህ።
\s5
\v 22 በሁለተኛውም ቀን ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ነውር የሌለበትን አውራ ፍየል ታቀርባለህ፤ ካህናቱም በወይፈኑ ደም እንዳነጹት እንዲሁ መሠዊያውን ያነጹበታል።
\v 23 ማንጻቱንም ከፈጸምህ በኋላ ነውር የሌለበትን ወይፈንና ከመንጋው የወጣውን ነውር የሌለበትን አውራ በግ ታቀርባለህ።
\v 24 በእግዚአብሔርም ፊት ታቀርባቸዋለህ፥ ካህናቱም ጨው ይጨምሩባቸዋል፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አድርገው ለእግዚአብሔር ያቀርቡአቸዋል።
\s5
\v 25 ለሰባት ቀንም በየዕለቱ ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን አውራ ፍየልን ታቀርባለህ፥ ካህናቱም ነውርም የሌለባቸውን አንድ ወይፈን ከመንጋውም የወጣውን አንድ አውራ በግ ያቀርባሉ።
\v 26 ሰባት ቀን ለመሠዊያው ያስተሰርያሉ ያነጹትማል፥ እንዲሁም ይቀድሱታል።
\v 27 እነዚህ ቀኖችንም መፈጸም አለባቸው፥ በስምንተኛውም ቀን ከዚያም በኋላ ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን የደኅንነትንም መሥዋዕታችሁን በመሠዊያው ላይ ያደርጋሉ እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\s5
\c 44
\p
\v 1 ወደ ምሥራቅም ወደሚመለከተው በስተ ውጭ ወዳለው ወደ መቅደሱ በር እንደገና አመጣኝ በሩም በጣም ተዘግቶ ነበር።
\v 2 እግዚአብሔርም፥ "ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ማንም አይገባበትም፥ በጥብቅ የተዘጋውም ለዚህ ነው
\v 3 የእስራኤል አለቃ በውስጡ ተቀምጦ በእግዚአብሔር ፊት እንጀራ ይበላል። በበሩ ደጀ ሰላም መንገድ ይገባል በዚያም መንገድ ይወጣል።
\s5
\v 4 ቀጥሎም ከቤቱ ፊት ለፊት በሰሜኑ በር በኩል አመጣኝ። እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ የእግዚአብሔር ክብር የእግዚአብሔርን ቤት ሞልቶት ነበር፥ እኔም በግምባሬ ተደፋሁ።
\v 5 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ "የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ እግዚአብሔርም ቤት ሥርዓትና ሕግ ሁሉ የምናገርህን ሁሉ ልብ አድርግ ሁሉ በዓይንህም ተመልከት በጆሮህም ስማ። የቤቱንም መግቢያ የመቅደሱንም መውጫ ሁሉ ልብ በል።
\s5
\v 6 ለዓመፀኛው ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፥ "ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፥
\v 7 እንጀራዬን፥ ስብንና ደምን፥ በምታቀርቡበት ጊዜ በመቅደሴ ውስጥ ይሆኑ ዘንድ ቤቴንም ያረክሱ ዘንድ በልባቸውና በሥጋቸው ያልተገረዙትን እንግዶችን ሰዎች አግብታችኋልና፥ እነርሱም በርኵሰታችሁ ሁሉ ላይ ይጨመሩ ዘንድ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋልና ርኵሰታችሁ ሁሉ ይብቃችሁ።
\s5
\v 8 የተቀደሰውን ሥፍራዬን ኃላፊነት ለሌሎች ሰጣችሁ እንጂ ስለእኔ ያለባችሁን ግዴታ አልተወጣችሁም።
\v 9 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእስራኤል ልጆች መካከል ካሉት ሁሉ በልቡና በሥጋው ያልተገረዘ እንግዳ ሁሉ ወደ መቅደሴ አይግባ።
\s5
\v 10 ከእኔ ዘንድ የራቁ፥ እስራኤልም በሳቱ ጊዜ ጣዖታቸውን ተከትለው ከእኔ ዘንድ የሳቱ ሌዋውያን ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ።
\v 11 እነርሱ የመቅደሴ በሮች ጠባቂዎች በመቅደሴም ውስጥ አገልጋዮች ናቸው። ለሕዝቡም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕቱን ያርዳሉ፥ ያገለግሉአቸውም ዘንድ በፊታቸው ይቆማሉ።
\v 12 ነገር ግን በጣዖቶቻቸውም ፊት መስዋዕት በማቅረባቸው ለእስራኤልም ቤት የኃጢአት ዕንቅፋት ሆነዋል። ስለዚህ ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ ብዬ እጄን አንስቼ ምያለሁ ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር!
\s5
\v 13 ካህናትም ይሆኑኝ ዘንድ ወደ እኔ አይቀርቡም፥ ወደ ተቀደሰውም ነገሬና ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ነገር አይቀርቡም እፍረታቸውንና የሠሩትንም ርኵሰታቸውን ይሸከማሉ።
\v 14 ነገር ግን ለአገልግሎቱ ሁሉና በእርሱ ውስጥ ለሚደረገው ሁሉ የቤቱ ሥርዓት ጠባቂዎች አደርጋቸዋለሁ።
\s5
\v 15 ነገር ግን የእስራኤል ልጆች ከእኔ በራቁ ጊዜ የመቅደሴን ሥርዓት የጠበቁ የሳዶቅ ልጆች ሌዋውያን ካህናት ያገለግሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ይቀርባሉ ስቡንና ደሙንም ወደ እኔ ያቀርቡ ዘንድ በፊቴ ይቆማሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
\v 16 ወደ መቅደሴም ይገባሉ ያገለግሉኝም ዘንድ ወደ ገበታዬ ይቀርባሉ ሥርዓቴንም ይጠብቃሉ።
\s5
\v 17 ወደ ውስጠኛውም አደባባይ በር በገቡ ጊዜ የተልባ እግር ልብስ ይልበሱ ወደ ውስጠኛውም አደባባይ በርና ወደ ቤቱ ውስጥ የሱፍ ልብስ ለብሰው መግባት የለባቸውም።
\v 18 በራሳቸው ላይ የተልባ እግር መጠምጠሚያ ይሁን፥ በወገባቸውም ላይ የተልባ እግር ሱሪ ይሁን የሚያልብ ልብስ መልበስ የለባቸውም።
\s5
\v 19 ወደ ውጭውም አደባባይ ወደ ሕዝብ ሲወጡ ሲያገለግሉ ለብሰውት የነበረውን ልብስ ማውለቅ አለባቸው፤ በተቀደሰ ልብሳቸው ነክተው ሕዝቡንም እንዳይቀድሱ አውልቀው በተቀደሰውም ክፍል ውስጥ ያስቀምጡት።
\s5
\v 20 ራሳቸውንም አይላጩ የራሳቸውንም ጠጕር ይከርከሙ እንጂ ጠጕራቸውን አያሳድጉ።
\v 21 ካህናቱም ሁሉ በውስጠኛው አደባባይ ሲገቡ የወይን ጠጅ አይጠጡ።
\v 22 መበለቲቱንና የተፈታችይቱን አያግቡ ነገር ግን ከእስራኤል ቤት ዘር ድንግሊቱን ወይም የካህን ሚስት የነበረችይቱን መበለት ብቻ ያግቡ።
\s5
\v 23 በተቀደሰውና ባልተቀደሰው መካከል ያለውን ልዩነት ለሕዝቤ ያስተምራሉ፥ ንጹሁን ንጹሕ ካልሆነው መለየት እንዲችሉ ያደርጓቸዋል።
\v 24 ክርክርም በሚያጋጥም ጊዜ በህጌ መሰረት ይፍረዱ፤ ፍትሀዊ መሆን አለባቸው። በበዓላቴ ሁሉ ሕጌንና ሥርዓቴን ይጠብቁ፥ ሰንበታቴንም ይቀድሱ።
\s5
\v 25 እንዳይረክሱም የአባት ወይም የእናት ወይም የወንድ ልጅ ወይም የሴት ልጅ ወይም የወንድም ወይም ከወንድ ጋር ያሌተኛች እኅት ካልሆን በስተቀር ወደ ሰው ሬሳ አይቅረቡ፤ ያለዚያ ይረክሳሉ።
\v 26 ካህን ከርከሰ ህዝቡ ሰባት ቀን ይቈጠርለት።
\v 27 በመቅደስም ውስጥ ያገለግል ዘንድ ወደ ውስጠኛው አደባባይ ወደ መቅደሱ ከመግባቱ በፊት፥ የኃጢአትን መሥዋዕት ለራሱ ያቅርብ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\s5
\v 28 ይህም ርስት ይሆንላቸዋል፡ እኔ ርስታቸው እሆንላቸዋለሁ! ስለዚህ በእስራኤል ዘንድ ግዛት አትሰጡአቸው እኔ ግዛታቸው ነኝ።
\v 29 የእህሉን ቍርባንና የኃጢአትን መሥዋዕት የበደልንም መሥዋዕት ይበላሉ በእስራኤልም ለእግዚአብሔር የተለየው ነገር ሁሉ ለእነርሱ ይሆናል።
\s5
\v 30 ከበኵራቱ ሁሉ የተሻለው ከየዓይነቱ ከቍርባናችሁም ሁሉ የማንሣት ቍርባን ሁሉ ለካህናት ይሆናል፥ በቤታችሁም ውስጥ በረከት ያድር ዘንድ የዱቄታችሁን በኵራት ለካህናቱ ትሰጣላችሁ።
\v 31 ካህናቱ የሞተ ወይም በአውሬ የተሰበረ ፥ ወፍ ወይም እንስሳ ቢሆን፥ አይበሉም።
\s5
\c 45
\p
\v 1 ርስትም አድርጋችሁ ምድሪቱን በዕጣ በምታካፍሉበት ጊዜ ለእግዚአብሔር መባ ታቀርባላችሁ። ይህም መባ የምድሪቱ የተቀደሰ ሥፍራ ሲሆን ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱም ሀያ ሺህ ክንድ ይሆናል በዳርቻው ሁሉ ዙሪያውን የተቀደሰ ይሆናል።
\v 2 ከእርሱም ርዝመቱ አምስት መቶ ወርዱም አምስት መቶ ክንድ አራት ማዕዘን የሆነ ቦታ ለመቅደሱ ይሆናል በዙሪያውም ባዶ ስፍራ የሚሆን አምሳ ክንድ ይሆናል።
\s5
\v 3 ከዚያ ቦታ ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱም አሥር ሺህ ክንድ የሆነ ስፍራ ትለካለህ፤ እርሱም ቅዱስ ስፍራና ቅድስተ ቅዱሳን ይሆንልሀል።
\v 4 ከምድሪቱም እግዚአብሔርን ለሚያገለግሉና ሊያገለግሉትም ወደ እግዚአብሔር ለሚቀርቡት ለካህናት የተለየ ክፍል ይሆናል። ለቤቶቻቸውም የሚሆን ስፍራ ለመቅደስም የሚሆን የተቀደሰ ስፍራ ይሆናል።
\v 5 ርዝመቱም ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም አሥር ሺህ የሆነ ስፍራ ለቤቱ አገልጋዮች ለሌዋውያን ይሆናል፥ ለሚቀመጡባቸውም ከተሞች ለራሳቸውም የርስት ይዞታ ይሆናል።
\s5
\v 6 ለከተማ የሚሆን ሥፍራም ከተቀደሰው የዕጣ ክፍል አጠገብ ወርዱ አምስት ሺህ ርዝመቱም ሀያ አምስት ሺህ የሆነውን ስፍራ ትለያላችሁ። ይህም ከተማ ለእስራኤል ቤት ሁሉ ይሆናል።
\v 7 ለአለቃ ይዞታ የሆነው የዕጣ ክፍል በተቀደሰው መባና በከተማይቱ ይዞታ አጠገብ በዚህና በዚያ ይሆናል። በምዕራብና በምሥራቅ ይሆናል። ርዝመቱም እንደ አንድ ነገድ ዕጣ ክፍል ሆኖ ከምድሩ ከምዕራቡ ዳርቻ ጀምሮ እስከ ምሥራቁ ዳርቻ ድረስ ይሆናል።
\s5
\v 8 ይህም ለእስራኤል አለቃ ይዞታ ይሆንለታል። አለቆቼም ለእስራኤል ቤት ምድሪቱን እንደ ነገዳቸው መጠን ይሰጡአቸዋል እንጂ ሕዝቤን ከእንግዲህ ወዲህ አያስጨንቋቸውም።
\s5
\v 9 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል አለቆች ሆይ፥ ይብቃችሁ ግፍንና ብዝበዛን አስወግዱ፥ ፍርድንና ጽድቅንም አድርጉ! ሕዝቤን መቀማት አቁሙ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር!
\v 10 እውነተኛ ሚዛን እውነተኛም የኢፍ መስፈሪያ እውነተኛውም የባዶስ መስፈሪያ ይሁንላችሁ።
\v 11 የኢፍና የባዶስ መስፈሪያ መጠናቸው እኩል ሆኖ የባዶስ መስፈሪያ የቆሮስ መስፈሪያ አንድ አሥረኛ ይሆናል ፥ መስፈሪያው እንደ ቆሮስ መስፈሪያ ይሁን።
\v 12 ሰቅሉም ሀያ አቦሊ ይሁን ሀያ ሰቅል፥ ሀያ አምስት ሰቅል፥ አሥራ አምስት ሰቅል፥ ምናን ይሁንላችሁ።
\s5
\v 13 የምታቀርቡት መባ ይህ ነው ከአንድ ቆሮስ መስፈሪያ ስንዴ የኢፍ መስፈሪያ አንድ ስድስተኛ፥ ከአንድም ቆሮስ መስፈሪያ ገብስ የኢፍ መስፈሪያ አንድ ስድስተኛ ትሰጣላችሁ።
\v 14 የዘይቱም ደንብ፥ ከእያንዳንዱ የቆሮስ መስፈሪያ የባዶስን አንድ አሥረኛ ወይም ለእያንዳንዱ ቆሮስ ምክንያቱም አሥር የባዶስ መስፈሪያ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ነው።
\v 15 ውኃም ካለበት ከእስራኤል አውራጃ ከመንጋው ከሁለቱ መቶ አንዱን የበግ ጠቦት ትሰጣላችሁ ይህ ያስተሰርይላችሁ ዘንድ ለእህል ቍርባንና ለሚቃጠል መሥዋዕት ለደኅንነትም መሥዋዕት ይሆናል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\s5
\v 16 የአገሩም ሕዝብ ሁሉ ይህን መባ ለእስራኤል አለቃ ይሰጣሉ።
\v 17 በየበዓላቱም በየመባቻውም በየሰንበታቱም በእስራኤልም ቤት ዓመት በዓል ሁሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን የመጠጡንም ቍርባን በየመደቡ ማዘጋጀት የአለቃው ይሆናል። እርሱ የእስራኤል ቤት ወክሎ የኃጢአቱን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቀርባል።
\s5
\v 18 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመጀመሪያው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ነውር የሌለበትን ወይፈን ውሰድ ስለ መቅደሱም የኃጢአት መስዋዕት ታቀርባላችሁ።
\v 19 ካህኑም ከኃጢአቱ መሥዋዕት ደም ወስዶ በመቅደሱ መቃኖችና በመሠዊያው እርከን በአራቱ ማዕዘን በውስጠኛውም አደባባይ በበሩ መቃኖች ላይ ይርጨው.
\v 20 ይህንንም ከወሩ በሰባተኛው ቀን ስለ ሳተውና ስላላወቀው ታደርጋለህ። በዚህ መንገድ ለቤተ መቅድሱ ታስተስርያላችሁ።
\s5
\v 21 በመጀመሪያ ወር ከወሩም በአሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካን በዓል ታደርጋላችሁ። የሰባት ቀንም በዓል ይሆናል። የቂጣ እንጀራም ትበላላችሁ።
\v 22 በዚያም ቀን አለቃው ለራሱና ለአገሩ ሕዝብ ሁሉ የኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን ያቀርባል።
\s5
\v 23 በበዓሉም በሰባቱ ቀኖች የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቅርብ፡ ሰባቱንም ቀኖች በየዕለቱ ነውር የሌለባቸውን ሰባት ወይፈንና ሰባት አውራ በጎች ያቅርብ ለኃጢአትም መሥዋዕት በየዕለቱ አንድ አውራ ፍየል ያቅርብ።
\v 24 ለአንድም ወይፈን አንድ የኢፍ መስፈሪያ ለአንድም አውራ በግ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ለአንድም የኢፍ መስፈሪያ አንድ የኢን መስፈሪያ ዘይት ለእህል ቍርባን ያቅርብ።
\s5
\v 25 አለቃው በሰባተኛውም ወር ከወሩም በአሥራ አምስተኛው ቀን በበዓሉ ሰባት ቀኖች፥ የኃጢአቱን መሥዋዕት የሚቃጠለውንም መሥዋዕት የእህሉንም ቍርባን ከዘይቱ ጋር እንዲሁ ያቅርብ።
\s5
\c 46
\p
\v 1 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውስጠኛው አደባባይ ወደ ምሥራቅ የሚመለከተው በር ሥራ በሚሠራበት በስድስቱ ቀን ተዘግቶ ይቈይ ነገር ግን በሰንበት ቀንና በመባቻ ቀን ይከፈት።
\v 2 አለቃውም በስተ ውጭ ባለው በር በደጀ ሰላሙ መንገድ ገብቶ ካህናቱም የእርሱን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት እስኪያቀርርቡ ድረስ በበሩ መቃን አጠገብ ይቁም። ከዚያም በበሩ መድረክ ላይ ሰግዶ ይውጣ ፥ በሩ ግን እስከ ማታ ድረስ አይዘጋ።
\s5
\v 3 የአገሩም ሕዝብ በዚያ በር መግቢያ በእግዚአብሔር ፊት በሰንበታትና በመባቻ ይስገዱ።
\v 4 አለቃውም በሰንበት ቀን ለእግዚአብሔር የሚያቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለባቸው ስድስት የበግ ጠቦቶች ነውርም የሌለበት አንድ አውራ በግ ይሁን
\v 5 የእህሉም ቍርባን ለአውራ በጉ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ይሁን፥ ለጠቦቶቹም የእህል ቍርባን የሚቻለውን ያህል ይሁን፥ ለአንዱም የኢፍ መስፈሪያ አንድ የኢን መስፈሪያ ዘይት ያቅርብ።
\s5
\v 6 በመባቻም ቀን ከመንጋው መካከል ነውር የሌለበትን አንድ ወይፈን፥ ነውር የሌለባቸውንም ስድስት ጠቦቶችና አንድ አውራ በግ ያቅርብ
\v 7 ለወይፈኑም አንድ የኢፍ መስፈሪያ ለአውራውም በግ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ለጠቦቶቹም እንደ ተቻለው ያህል፥ የእህል ቁርባን እንዲሁም ለአንዱም የኢፍ መስፈሪያ የእህል ቁርባን አንድ የኢን መስፈሪያ ዘይት ያቅርብ።
\v 8 አለቃውም በሚገባበት ጊዜ በበሩ ደጀ ሰላም መንገድ ይግባ በዚያውም ይውጣ።
\s5
\v 9 የአገሩ ሕዝብ ግን በየክብረ በዓሉ ቀን ወደ እግዚአብሔር ፊት በመጡ ጊዜ በሰሜን በር በኩል ሊሰግድ የሚገባው በደቡብ በር በኩል ይውጣ፥ በደቡብም በር የሚገባው በሰሜን በር በኩል ይውጣ። በፊት ለፊት ይውጣ እንጂ በገባበቱ በር አይመለስ።
\v 10 በሚገቡበት ጊዜ አለቃው በመካከላቸው ይግባ በሚወጡበትም ጊዜ ይውጣ።
\s5
\v 11 በበዓላትም የእህሉ ቍርባን ለወይፈኑ አንድ የኢፍ መስፈሪያ፥ ለአውራ በጉ አንድ የኢፍ መስፈሪያ፥ ለጠቦቶቹም እንደሚቻለው ያህል፥ ለኢፍ መስፈሪያም አንድ የኢን መስፈሪያ ዘይት ይሆናል።
\v 12 አለቃውም በፈቃዱ የሚያቀርበውን መሥዋዕት፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ ወይም በፈቃዱ ለእግዚአብሔር የሚያቀርበውን የደኅንነቱን መሥዋዕት፥ ባቀረበ ጊዜ፥ የምሥራቁን በር ይክፈት፥ በሰንበትም ቀን እንደሚያደርግ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቅርብ ከዚያም በኋላ ይውጣ፥ ከወጣም በኋላ በሩን ይዝጋ።
\s5
\v 13 በየዕለቱም ለሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለበትን የአንድ ዓመት በግ ጠቦት ለእግዚአብሔር ታቀርባላችሁ፤ ይህንንም በየማለዳው ታደርጋላችሁ።
\v 14 ከእርሱም ጋር እንደ ቋሚ ሥርዓት የእህልን ቍርባን፥ በኢን መስፈሪያ ሢሶ ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ ስድስተኛ እጅ መልካም ዱቄትን፥ በየማለዳው ታቀርባላችሁ።
\v 15 እንዲሁ ዘወትር ለሚቃጠለው መሥዋዕት ጠቦቱንና የእህሉን ቍርባን ዘይቱንም በየማለዳው ያቅርብ።
\s5
\v 16 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አለቃው ከልጆቹ ለአንዱ ከርስቱ ስጦታ ቢሰጥ የልጁ ውርስ ይሆናል። የልጆቹ ንብረት ውርስ ይሆንላቸዋል።
\v 17 ነገር ግን ከባሪያዎቹ ለአንዱ ከርስቱ ስጦታ ቢሰጥ እስከ ነጻነት ዓመት ድረሰ ለእርሱ ይሁን፥ ከዚያም በኋላ ለአለቃው ይመለስ። ርስቱ ግን ለልጆቹ ይሁን።
\v 18 አለቃውም ሕዝቡን ከይዞታቸው ያወጣቸው ዘንድ ከርስታቸው በግድ አይውሰድ ሕዝቤ ሁሉ ከይዞታቸው እንዳይነቀሉ ከገዛ ይዞታው ለልጆች ርስትን ይስጥ።
\s5
\v 19 ከዚያም ሰውዬው ወደ ሰሜን ወደሚመለከተው ለካህናት ወደሚሆን ወደ ተቀደሱ ክፍሎች እነሆም፥ በስትምዕራብ በኩል አንድ ስፍራ ነበረ።
\v 20 እርሱም፥ "ካህናቱ ሕዝቡን ለመቀደስ ወደ ውጭው አደባባይ እንዳያወጡ የበደሉን መሥዋዕትና የኃጢአቱን መሥዋዕት የሚቀቅሉበት፥ የእህሉንም ቍርባን የሚጋግሩበት ስፍራ ይህ ነው አለኝ።
\s5
\v 21 በውጭው አደባባይ አወጣኝ በአደባባይም ወዳለው በአራቱ ማዕዘን በኩል አሳለፈኝ እነሆም፥ በእያንዳንዱ የአደባባዩ ማዕዘን ሌላ አደባባይ እንዳለ አየሁ።
\v 22 በአደባባዩ በአራቱ ማዕዘን ርዝመቱ አርባ ክንድ ወርዱም ሠላሳ ክንድ የሆነ አደባባይ ነበረ። በማዕዘኑ ላሉ ለእነዚህ ለአራቱ ስፍራዎች አንድ ልኬቱ እኩል ነበረ።
\v 23 በአራቱም ዙሪያ ሁሉ ግንብ ነበረ፥ በግንቡም ሥር በዙሪያው የመቀቀያ ቦታ ነበረ።
\v 24 ሰውዬውም፥ "እነዚህ የቤቱ አገልጋዮች የሕዝቡን መሥዋዕት የሚቀቅሉባቸው ስፍራዎች ናቸው አለኝ።
\s5
\c 47
\p
\v 1 ወደ መቅደሱም መዝጊያ መለሰኝ እነሆም፥ ውኃ ከቤቱ መድረክ በታች ወደ ምሥራቅ ይወጣ ነበር፥ የቤቱ ፊት ወደ ምሥራቅ ይመለከት ነበርና ውኃውም ከመስዊውው በስተቀኝ በኩል ወደ ቤተመቅደሱ ደቡብ አቅጣጫ ይወርድ ነበር።
\v 2 በሰሜኑም በር በኩል አወጣኝ በስተ ውጭ ባለው መንገድ፥ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከት በስተ ውጭ ወዳለው በር መራኝ እነሆም፥ ውኃው ከበሩ ምዕራብ ወገን ይፈስስ ነበር።
\s5
\v 3 ሰውዬውም ገመዱን በእጁ ይዞ ወደ ምሥራቅ ወጣ አንድ ሺህም ክንድ ለካ፥ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፥ ውኃም እስከ ቍርጭምጭሚት ደረሰ።
\v 4 ደግሞ አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፥ ውኃውም እስከ ጕልበት ደረሰ። ደግሞም አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፥ ውኃውም እስከ ወገብ ደረሰ።
\v 5 ደግሞ አንድ ሺህ ለካ ልሻገረውም የማልችለው ወንዝ ሆነ ውኃውም ጥልቅ ነበረ፥ የሚዋኝበትም ውኃ ነበረ ሰው ሊሻገረው የማይችለው ወንዝ ነበረ።
\s5
\v 6 ሰውዬውም፥ "የሰው ልጅ ሆይ፥ አይተሃልን?" አለኝ። አመጣኝም፥ ወደ ወንዙም ዳር መለሰኝ።
\v 7 በተመለስሁም ጊዜ፥ እነሆ፥ በወንዙ ዳር በዚህና በዚያ እጅግ ብዙ ዛፎች ነበሩ።
\v 8 እርሱም እንዲህ አለኝ፥ "ይህ ውኃ ወደ ምሥራቅ ምድር ይወጣል ወደ ዓረባም ይወርዳል ወደ ጨው ባሕሩም ወደ መልካም ውሃነቱ ይመልሰዋል።
\s5
\v 9 ሕያው ነፍስ ያለው ተንቀሳቃሽ ሁሉ ወንዙ በመጣበት ስፍራ ሁሉ በሕይወት ይኖራል ይህም ውኃ በዚያ ስለ ደረሰ ዓሣዎች እጅግ ይበዛሉ። ጨዋማ ባህርን መልካም ያደርጋል። ወንዙም በሚመጣበት ያለው ሁሉ በሕይወት ይኖራል።
\v 10 የዓይንጋዲ አጥማጆችም በወንዙ ዳር ይቆማሉ በዓይንጋዲ መረብ መዘርጊያ ቦታ ይገኛል። በጨው ባህርም ዓሣዎች እንደ ታላቁ ባሕር ዓሣዎች በየወገናቸው እጅግ ይበዛሉ።
\s5
\v 11 ነገር ግን የጨው ባህር እረግረጉና እቋሪው ሥፍራ ጨው ለመስጠት ጨዋማ እንደ ሆነ ይኖራል እንጂ አይቀየርም።
\v 12 በወንዙም አጠገብ በዳሩ ላይ በዚህና በዚያ ፍሬው የሚበላ ዛፍ ሁሉ ይበቅላል። ቅጠሉም አይረግፍም ፍሬውም አይቋረጥም። ውኃውም ከመቅደስ የሚመጣ በመሆኑ ዛፎቹ በየወሩ ፍሬ ያፈራሉ። ፍሬውም ለመብል ቅጠሉም ለመድኃኒት ይሆናል።
\s5
\v 13 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ርስት አድርጋችሁ ለአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ምድሪቱን የምትከፍሉበት እንደዚህ ነው፡ ለዮሴፍ ሁለት እድል ፈንታ ይሰጠዋል።
\v 14 ለአባቶቻችሁ እሰጣቸው ዘንድ ምዬ ነበርና እናንተ እያንዳንዳችሁ እኩል አድርጋችሁ ትካፈላላችሁ። በዚህም መንገድ ይህች ምድር ርስት ትሆናችኋለች።
\s5
\v 15 የምድሪቱም ድንበር ይህ ነው። በሰሜኑ ወገን ከታላቁ ባሕር ጀምሮ በሔትሎን መንገድ ወደ ጽዳድ መግቢያ
\v 16 ሐማት፥ ቤሮታ፥ በደማስቆ ድንበርና በሐማት ድንበር መካከል ያለው ሲብራይም፥ በሐውራን ድንበር አጠገብ ያለው ሐጸርሃቲኮን።
\v 17 ስለዚህም ድንበሩ ከባሕሩ በደማስቆ ድንበር ላይ ያለው ሐጸርዔናን ሐማት ድንበር ይሆናል። ይህ የሰሜኑ ድንበር ነው።
\s5
\v 18 የምሥራቁም ድንበር በሐውራን በደማስቆና በገለዓድ በእስራኤልም ምድር መካከል ዮርዳኖስ ይሆናል። ይህም ድንበር እስከ ታማር ድረስ ይሄዳል።
\v 19 የደቡቡም ድንበር ከደቡብ ታማር ጀምሮ እስከ ሜርባ ቃዴስ ውኃ እስከ ግብጽ ወንዝ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ይሆናል። የደቡቡ ድንበር ይህ ነው።
\v 20 የምዕራቡም ድንበር ከታላቁ ባሕር ጀምሮ እስከ ሐማት መግቢያ አንጻር ድረስ ይሆናል። የምዕራቡ ድንበር ይህ ነው።
\s5
\v 21 እንዲሁ ይህችን ምድር እንደ እስራኤል ነገድነታችሁ ለእናንተ ትካፈላላችሁ።
\v 22 ለእናንተና በእናንተ መካከል ለሚቀመጡ በእናንተም መካከል ልጆችን ለሚወልዱ ፥ በእስራኤል ልጆች መካከል እንዳሉ እንደአገር ልጆች ላሉ መጻተኞች ርስት አድርጋችሁ በዕጣ ትካፈሉአታላችሁ ። በእስራኤልም ነገዶች መካከል ለርስት ክፍፍል ዕጣ ትጣላላችሁ።
\v 23 መጻተኛውም በማናቸውም ነገድ መካከል ቢቀመጥ በዚያ ርስቱን ትሰጡታላችሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
\s5
\c 48
\p
\v 1 የነገዶችም ስም ይህ ነው። የዳን ነገድ አንድ የዕጣ ክፍል ይወስዳል፡ ድንብሩም በሔትሎን መንገድ አጠገብ ወደ ሐማት መግቢያ በደማስቆም ድንበር ባለው በሐጸርዔናን በሐማትም አጠገብ በሰሜን በኩል ካለው ከሰሜን ድንበር ይጀምራል። ወርዳቸውም ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ይሆናል።
\v 2 ከዳንም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለአሴር አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።
\v 3 ከአሴርም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለንፍታሌም አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።
\s5
\v 4 ከንፍታሌም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለምናሴ አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።
\v 5 ከምናሴም ደቡብ ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለኤፍሬም አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።
\v 6 ከኤፍሬምም ደቡብ ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለሮቤል አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።
\v 7 ከሮቤልም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለይሁዳ አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።
\s5
\v 8 ከይሁዳም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለመባ የሆነ የዕጣ ክፍል ይሆናል ወርዱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል ርዝመቱም ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ከዕጣ ክፍሎች እንደ አንዱ ይሆናል፥ መቅደሱም በመካከሉ ይሆናል።
\v 9 ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት መሬት ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺህ ወርዱም ሃያ ሺህ ክንድ ይሆናል።
\s5
\v 10 ይዚህም ቅዱስ ስፍራ አገልግሎት ይህ ነው፡ ለካህናቱ በሰሜን በኩል ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ፥ በምዕራብም በኩል ወርዱ አሥር ሺህ፥ በምሥራቅም በኩል ወርዱ አሥር ሺህ፥ በደቡብም በኩል ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺህ ክንድ የሆነ ቦታ ይለይላቸዋል። የእግዚአብሔርም መቅደስ በመካከሉ ይሆናል።
\v 11 ይህም የእስራኤል ልጆች በሳቱ ጊዜ፥ ሌዋውያን እንደ ሳቱት ላልሳቱት ሥርዓቴንም ለጠበቁት ከሳዶቅ ልጆች ወገን ለተቀደሱት ካህናት ይሆናል።
\v 12 ለእነርሱም የሚሆነው መባ እስከ ሌዋውያን ድንበር የሚደርስ የዚህ የተቀደሰ ሥፍራ ክፍል ነው።
\s5
\v 13 የሌዋውያን መሬት በካህናቱም ድንበር አንጻር ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም አሥር ሺህ የሆነ ዕጣ ይሆናል። የእነኚህ ኩታ ገጠም መሬቶች ጠቅላላ ርዝመት ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም ሀያ ሺህ ክንድ ይሆናል።
\v 14 ለእግዚአብሔርም የተቀደሰ ነውና ከእርሱ ምንም አይሸጡም አይለውጡምም፥ የምድሩም በኵራት አይፋለስም።
\s5
\v 15 የቀረው ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ስፋትና አምስት ሺህ ክንድ ርዝመት ያለው ስፍራ ለከተማይቱ የጋራ ጉዳይ ፥ ለመኖሪያና ለማስማርያም ይሆናል ከተማይቱም በመካከሉ ትሆናለች።
\v 16 የከተማይቱም ልኬት ይህ ነው፡ በሰሜን በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ፥ በደቡብም በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ፥ በምሥራቅም በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ፥ በምዕራብም በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ይሆናል።
\s5
\v 17 ለከተማይቱም በሰሜን በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በደቡብም በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በምሥራቅም በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በምዕራብም በኩል ሁለት መቶ አምሳ ክንድ ጥልቀት ያለው ማሰማርያ ይኖራታል።
\v 18 ቀሪው የተቀደሰው በተቀደሰው የመሬት መባ ርዝመቱ ወደ ምሥራቅ አሥር ሺህ ወደ ምዕራብም አሥር ሺህ ክንድ ይሆናል። ድንበሩም በተቀደሰው የመሬት የተያያዘ ይሆናል። ፍሬውም ከተማይቱን ለሚያገለግሉ ለመብል ይሆናል።
\s5
\v 19 ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ከተማይቱን የሚያገለግሉ ምድሪቱን ያርሱታል።
\v 20 መባው ሁሉ ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል ። በዚህም መንገድ የተቀደሰውን የመሬት መባና የከተማይቱን ይዞታ ታደርጋላችሁ።
\s5
\v 21 በተቀደሰው መባና በከተማይቱ ይዞታ በዚህና በዚያ ወገን የቀረው ሥፍራ ለአለቃው ይሆናል። በምስራቅ በኩል ያለው የአለቃው ኩታ ገጠም መሬት ከተቀደሰው የመሬት መባ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወደ ምሥራቁ ድንበር፥ በምዕራብም በኩል ደግሞ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወደ ምዕራቡ ድንበር ይዘልቃል። የተቀደሰውም የመሬት መባውና የቤተ መቅደሱ የተቀደሰ ስፍራ በመካከል ይሆናል።
\v 22 የአለቃውም ይዞታው ከሌዋውያን ርስትና ክከተማይቱ ይዞታ መካከል ይሆናል፤ በይሁዳ ድንበርና በብንያም ድንበርም መካከል ይሆናል።
\s5
\v 23 ለቀሩትም ነገዶች ድርሻቸው ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ይሆናል። የብንያም ነገድ አንድ የዕጣ ክፍል ይቀበላል።
\v 24 ከብንያምም ደቡባዊ ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለስምዖን አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።
\v 25 ከስምዖንም ደቡባዊ ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለይሳኮር አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።
\v 26 ከይሳኮርም ደቡባዊ ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለዛብሎን አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።
\s5
\v 27 ከዛብሎንም ደቡባዊ ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለጋድ አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።
\v 28 ከጋድም ድንበር ቀጥሎ በደቡብ በኩል ድንበሩ ከታማር ጀምሮ እስከ ሜሪባ ቃዴስ ውኃ እስከ ግብጽ ወንዝ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ይሆናል።
\v 29 ርስት አድርጋችሁ ለእስራኤል ነገዶች በዕጣ የምታካፍሉአት ምድር ይህች ናት፥ ይህም ርስታቸው ይሆናል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\v 30 የከተማይቱም መውጫዎች እነዚህ ናቸው፡ በሰሜን ወገን ልኩ አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ነው።
\v 31 የከተማይቱ በሮች ሦስት ሲሆኑ እንደ እስራኤል ነገዶች ስም በሰሜን በኩል አንዱ የሮቤል በር አንዱም የይሁዳ በር አንዱም የሌዊ በር ይሆናሉ።
\v 32 በምሥራቁም ወገን አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ በሚረዝመው ሥፍራ፥ ሦስትም በሮች አሉ፡ አንዱ የዮሴፍ በር አንዱም የብንያም በር አንዱም የዳን በር ይሆናሉ።
\s5
\v 33 በምስራቅ ወገን አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ በሚረዝመው ሥፍራ፥ ሦስት በሮች አሉ፡ አንዱ የስምዖን ፥አንዱ የይሳኮር፥ እና አንዱም የዛብሎን በር ናቸው።
\v 34 በምዕራቡም ወገን ልኬቱ አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ሲሆን፥ በዚያ ሦስት በሮች አሉ፡ አንዱ የጋድ፥ አንዱም የአሴር፥ ሌላውም የንፍታሌም በር ናቸው።
\v 35 የከተማይቱ ዙሪያም አሥራ ስምንት ሺህ ክንድ ይሆናል፥ ከዚያም ቀን ጀምሮ የከተማይቱ ስም "እግዚአብሔር በዚያ አለ" ተብሎ ይጠራል።